YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኦሮሚያ ክልል፣ ኢሉአባቦራ ዞን የሚኖሩ የ|#ትግራይ ብሔር ተወላጆች ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ለቢቢሲ ትግርኛ ተናግረዋል።

@YeneTube #Fikerassefa
15ኛው የኢትዮጵያና የጅቡቲ የጋራ ኮሚሽን የባለሙያዎች ውይይት
ዛሬ በጅቡቲ ተጀምሯል።

ይህንንም ተከትሎ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የሚመራው 15ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ጥር 21 እና 22 ቀን እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

የጋራ ኮሚሽኑ ትኩረት በማድረግ የሚወያየው በዋነኛነት በትራንስፖርት፣ በወደብ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በጉሙሩክና በንግድ ጉዳዮች ላይ መሆኑ ተገልጿል። የጋራ ኮሚሽኑ በእነዚህ ዘርፎች የሁለቱ ሀገራት የትብብር ግንኙነት እንዲጠናከርም ይመክራል።

እንዲሁም ከዚህ ቀደም ባጋጠሙ ችግሮች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሏል። ሁለቱ ሀገራት ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፥ የጅቡቲ ወደብ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪና የገቢ ንግድ መስመር ሆኖ ማገልገሉ ግንኙነቱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የራሱን ድርሻ አበርክቷል።

ሀገራቱ በመሰረተ ልማት የተሳሰሩ ከመሆናቸውም በላይ የጋራ ኮሚሽን አቋቁመው ግንኙነታቸውን በየጊዜው እየገመገሙ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈም የጋራ ኮሚሽን በማቋቋማቸው በትብብር ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት እንዳስቻላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ:- ፋና ብሮድካስቲንግ
#ሼር_ማድረጎን_አይርሱ
@Yenetube #Fikerassefa
በስልጤ ዞን  ለመዋኘት ወራጅ ውሃ ዉስጥ  የገቡ ሁለት ህፃናት ህይወታቸው አለፈ
       
  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር  ዋሪሻ ቀበሌ ቀጠና 3 ጭቀቄ  ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከትምህርት ቤት ሲመለሱ  ለመዋኘት ወራጅ ውሃ ዉስጥ የገቡ ሁለት ህፃናት ህይወታቸዉ ማለፉን ፖሊስ ገልጿል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በትላንትናው እለት  ከቀኑ 6:00 ሰዓት ገደማ ከትምህርት ቤት  ወደ ቤት በመመለስ ላይ የነበሩ  ዕድሜያቸዉ ከ10  አመት  በታች  የሆኑ ሁለቱ ህፃናት  ለመዋኘት ወራጅ ውሃ ዉስጥ በመግባታቸዉ ህይወታቸዉ አልፏል።

የፀጥታ አካላት ከአከባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን  በተደረገ  ርብርብ የህፃናቶቹን አስክሬን ከውሃ ዉስጥ አፈላልጎ በማዉጣት ለቤተሰብ ማስረከብ መቻሉን  ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በአየር ትንበያ ሁኔታ በክልሉ ተከታታይና  ከበድ ያለ ዝናብ እንደሚጥል ያረጋገጠ  ሲሆን  በወንዞች ሙላትና ደራሽ ዉሃ፣እንዲሁም ድንገት በሚከሰት ጎርፍ በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህብረተሰቡ ተገቢዉ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል።

በክልሉ በወንዝ አጥርና ወራጅ  ዉሃ በሌለባቸዉ አካባቢዎች በቁፋሮ የሚዘጋጁ ሰዉ ሰራሽ ውሃ ማቆሪያ ጉድጓዶችና ኩሬዎች ላይ ህፃናት ለመዋኘት እንዳይገቡ ጥንቃቄና ጥበቃ ሊደረግላቸው  ይገባል ሲሉ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ዳጉ ጆርናል
@Yenetube #Fikerassefa
👍16😭7😁1
ኢትዮጵያ በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሞስኮ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አውግዟል፡፡

ሚኒስቴሩ በሽብር ጥቃቱ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሩሲያዊያን እና ለሀገሪቱ መንግሥት መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት እና ህዝብ ጎን እንደምትቆም በመግለጫው አስታውቋል።

በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በሙዚቃ ኮንሰርት አዳራሽ በተፈፀመ የጅምላ ተኩስ በመቶዎች የሚቆጠሩ መገደላቸው እና መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡

ጥቃቱ በሞስኮ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው ኮርከስ ከተማ የተፈፀመ መሆኑን እና ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች አለመታወቃቸው ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሞስኮ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት እንደሚያወግዝ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

@Yenetube #Fikerassefa
😁64👍13😭4👎32👀2