YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#አፋር

ለ27 አመታት ተዳፍኖ የቆየ በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡ህዝቡ ይጠይቃል ነገር ግን ምላሽ ሠጭ አካል የለም፡፡ ህዝቡ ለመሆን ይጥራል ነገር ግን እንዳይሆን የሚፈልግ አካል ከአናቱ ተቀምጧል፡፡ አናቱ በማይድን በሽታ ተለክፈዋል፡፡ ግን ላይዲን ግማቱ ገምተዋል፡፡ የዘመናት ጥያቄ እንዳይመለስ የበላዮቹ ተፅዕኖያቸውን የቀጠሉ ሲሆን ጠያቂዎች ግን ከመጠየቅ ሳይታክቱ የወጣቱ ክፍል እየጠየቀ ነው፡፡

አሁን በአፋር ሁለት ሐይሎች ጎራ ፈጥረው ተፋጠዋል፡፡አንዱ የ27 አመት አሮጌ ስርዓት ይዞ ለመቀጥል፡፡ ሁለተኛው ግን አዲስ ትውልድ በመሆኑ አዲስ ነገር ማየት ፈልጎ ራሱን መሆን ይፈልጋል፡፡ማንነት ደግሞ ከሁሉም ቀዳሚ ነው፡፡ አሁን በነጋዴው በለውጥ ፈላጊ መካከል ቀዝቃዛ ጦርነት ተከፍቷል፡፡ እሳቱ ላይጠፋ ተያይዞ መንዳድ ግን አልቻለም፡፡ መንስኤው ደግሞ አለቃ ተብየው እጃዙር መአቀብ በማድረግ የወጣቱን ጥያቄ ለማክሸፍ እየሞከረ በመሆኑ፡፡

ብዙዎቹ የወጣቱ ክፍል የመንግሥት ደሙዝ ጥገኛ በመሆኑን የእለት እንጄራውን ላለማጣት መብቱን ማስከበር ተስኖት አጎብዳጅ ሁኖዋል፡፡ ጥቂት ቁራጦች ግን ለመቀቡ እጅ ላይሰጡ ፡ ለርካሽ ጥቅም ላያጎበድዱ ቃል ተገባብተው የትግሉ ፊታውራሬ ሁናዋል፡፡ ለማንኛውም አሁን ሜዳው ከሁለት ጎራ ሁነዋል፡፡ አንዱ ክንፍ ምንም አይነት ለውጥ አያስፈልግም በዚህ እንቀጥል የሚለው አብዴፓ እና አይሆንም ልክ እንደጎራቤቶቻችን ለውጥ ያስፈልገናል አዲስ ፊት እንፈልጋለን ማንም ይምራን አዲስ አመራር እንፈልጋለን የሚለው ወጣቱ ዱኮሂናሌላኛው የለውጥ ናፋቂ ቡዱን ነው፡፡

ይህ ክፍል ለአገር ተስፋ፡ የነገ ጉልበት የሆነው አገር ተረካቢ የተማረ ወጣት ክፍል የያዘ ሐይል ነው፡፡ አሁን ፍጥጫው ተጧጡፏል፡፡ አብዴፓ ውድቀቱን ላለማያት ምሎ ተነስተዋል፡፡ አዲስ የካቢኔ ድልድል አድርገዋል፡፡ጥያቄው ግን አዲሱ ለውጥ በፈጣን ባቡር ላይ ያሳፍረው ይሁን ነው? ጥያቄው አብረን የምናየው ይሆናል፡፡

💗💗መልካም ቀን ይሁንላችሁ💗💗
@YeneTube @Fikerassefa
#አፋር

አፋር ክልል ቡሬ ወረዳ በኢትዮ - ኤርትራ ጦርነት ወቅት የተቀበሩ ፈንጂዎች ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ሰላም ከወረደ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ፈንጂ ፈንድቶ የአንድ የ15 ዓመት ታዳጊ ህይወት መቅጠፉን ከአፋር ክልል የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። እንዲሁም ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም ለማወቅ ችለናል።

@YeneTube @Fikerassefa
በአማራ ክልል በ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በተፈጸመ ጥቃት 27 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን #ጂሌ_ጥሙጋ ወረዳ፤ ከየካቲት 30፣ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጸመ “የተቀናጀ ጥቃት” 27 ነዋሪዎች መገደላቸውን እና ከ40 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።
ጥቃቱ በጂሌ ጥሙጋ ወረዳ በሚገኙ ከ20 በላይ ቀበሌዎች እንደተፈፀመ ተገልጿል።

“በጥቃቱ ህጻናት፣ እረጋውያን እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። በተጨማሪም መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ ንብረቶች ወድመዋል” ሲል ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

እስከ ዛሬ ቀጥሏል በተባለው ግጭት ጉዳት ከደረሰባቸው 40 ሰዎች ውስጥ 20 የሚሆኑት ወደ አዲስ አበባ መንገድ ዝግ በመሆኑ በ #አፋር ክልል አቋርጠው በ #አዳማ ከተማ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ የለን፣ዋጮ፣ነገሶ እና ሞላሌ በሚባሉ ቀበሌዎች ከብሄረሰብ ዞኑ የመጡ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ደርሷል።

ስምንት ሰዎች ሞተዋል፣ በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል። ከ300 በላይ ከብቶች ወደ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞኑ ተወስደዋል ሲሉ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

አጣዬ ዙሪም ዛሬ ተመሳሳይ ግጭት አለ ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭19👍176👏4😁1
ህወሓትን በመቃወም የትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡት ብርጋዴር ጄነራል ገብረእግዚአብሄር በየነ፤ በ #አፋር እና በ #ትግራይ ክልሎች ውስጥ “አራት ክፍለ ጦር” ያለው የራሳቸውን ሠራዊት ማደራጀታቸውን ተናገሩ።

#ከትግራይ ኃይሎች በመለየት የራሳቸውን ሠራዊት እየገነቡ መሆናቸውን የጠቀሱት ብርጋዴር ጄነራል ገብረእግዚአብሄር፤ "አዲስ ነገር ለመፍጠር" ወደ በረሃ መውደረዳቸውን እና "ከፓርቲ ነጻ የሆነ ኃይል ለመፍጠር፣... ፓርቲ የማያዝዘው ሠራዊት ለመፍጠር" እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልፀዋል።

ጄነራሉ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ከትግራይ ሠራዊት አመራሮች ጋር የተለያዩት ከጥር 15/20017 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን አስረድተዋል።

የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጥር 15 ተሰብስበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ጊዜያዊ አስተዳደር ሲያወግዙ፣ ተቃውመው ስብሰባውን ረግጠው ከወጡ አመራሮች መካከል አንዱ ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ ናቸው።

ይህንንም ተከትሎ የሠራዊቱ አመራሮች ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነን እና ሌሎች የሠራዊቱን ውሳኔ የተቃወሙትን ማገዳቸው ይታወሳል።

ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር "ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ ማህተም የሚነጥቅ፣ ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ የሚሾም እና የሚሽር ኃይል ለወጣቱ ትውልድ ትተን መሄድ አንፈልግም። ወገንተኛ ያልሆነ ፍትሃዊ ኃይል ለመፍጠር እንጂ፣ የሆነ ፓርቲ አሽከርነት የለንም፤ አናደርገውም" ብለዋል።

ለተቃውሟቸው ጠመንጃ ማንሳትን መምረጣቸው በጦርነት ውስጥ የቆየውን የትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግጭት አዙሪት አይከተውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ጄነራሉ "እኔ ኢንተርናሽናል ጄነራል ነኝ። ይህንን ሆኜ የህወሓት ሚሊሻ መሆን አልፈልግም። ህወሓት ፓርቲያችን ነው የሚሉ የእርሱን ሚሊሻ እንደሆኑ ነው የሚቆጥረው። ሚሊሻነትን ደግሞ አልቀበልም" ብለዋል።

@Yenetube
43😁15👀1