YeneTube
120K subscribers
31.2K photos
482 videos
79 files
3.83K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሚዲያዎች መሥራት የነበረብንን ሥራ ባለማከናወናችን ችግሮች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል- ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣንና በጀስትስ ፎር ኦል ፒኤፍ ኢትዮጵያ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የሠላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሚዲያዎች ተገርተው ባለመብቀላቸውና ላለፉት ዓመታት መሥራት የነበረብንን ሥራ ባለመሥራታችን በሀገሪቱ የተለያዩ ችግሮች እንዲፈጠሩ ምክንያት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡አቅም ያልተገነባለት ሚዲያ የተለያዩ ችግሮችን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ያነሱት ሚኒስትሯ፣ ነፃ ያልወጣ ሚዲያ ሌሎችን ነፃ ሊያወጣ አይችልም ሲሉም ተናግረዋል፡፡በውይይት መድረኩ የተለያዩ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን፣ የመናገር ነፃነትና ኃላፊነት በኢትዮጵያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሚዲያና የወቅቱ ችግሮቻችን በሚል የተለያዩ ሃሳቦች ቀርቧል፡፡

#Walta
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢሰመኮ ጋዜጣዊ መግለጫ!

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ማጣራት እና ስለ ታሳሪዎች አያያዝ

(አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም) የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አሳዛኝ ግድያ ተከትሎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎችም አንዳንድ ቦታዎች የተከሰተውን መጠነ ሰፊ የጸጥታ ችግር ፣ የሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት በሚመለከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከመነሻው ጀምሮ በቅርብ መከታተሉን የቀጠለ ሲሆን፤ እስከ አሁን የተካሄዱትና በመካሄድ ላይ ያሉት ዋና ዋና ሥራዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-

1. የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በፈጣን ምርመራ ማጣራትና መዘገብ ምንም እንኳን የደረሰውን አደጋ በተመለከተ በተወሰነ መጠን በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንና ድርጅቶች እንዲሁም የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የተዘገበ ቢሆንም፤ ኢሰመኮ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የምርመራ ስልት ላይ የተመሰረተና በበቂ ማስረጃዎች የተደገፈ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አይነት በተገቢው መጠን የሚያጣራና የሚመዘግብ የባለሙያዎች ቡድን አዋቅሮ ወደ ሥራ አሰማርቷል፡፡

ሙሉ መግለጫውን ከፍተው ያንብቡ👇👇
https://telegra.ph/EHRC-07-24
በ30 ሰከንድ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ የሚችል መሣሪያ እየተሠራ ነው፡፡

አንድ የእስራኤል ኩባንያ በ30 ሴከንድ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ የሚረዳ መሣሪያ እየሠራ ስለመሆኑ አልጀዚራ እና ሲ ጂ ቲ ኤን በድረ ገጻቸው አስነብበዋል፡፡ መሣሪያው ትንፋሽ በመውሰድ ምርመራው ማድረግ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡‘ናኖሴንት’ የተባለው ተቋም ትንፋሽን በመጠቀም ምርመራ ለማድረግ የሚረዳው መሣሪያ በእራኤል ሰፊ ሙከራ እየተደረገበት እንደሆነ አስታውቋል፡፡ 85 ከመቶ ውጤታማነቱን እንዳስመሰከረም ተቋሙ ጠቁሟል፡፡

#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
የግብጽ መንግሥት ውሃ በሚያባክኑ ዜጎቹ ላይ ጠበቅ ያለ ቅጣት እንደሚጥል ማስጠንቀቁን የሀገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡ ሁሉም መኖሪያ ቤቶች ቧንቧዎች የውሃ መቆጠቢያ መሳሪያ እንዲገጥሙ ጠቅላይ ሚንስትር ሙስጠፋ ማብዶሊ አዘዋል፡፡ በጠረፍ ከተሞች ደሞ፣ የውሃ ማጣሪያ እና የቆሻሻ ውሃ ማከሚያ ፋብሪካዎች እንዲቋቋሙ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

#ዋዜማ_ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 760 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ7 ሺህ 264 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 760 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡140 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀርበዋል!

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡በከሰአት በኋላ በነበረው ችሎትም የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በቡራዩና አዲስ አበባ በተፈጠረ አመጽና ሁከት በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት የተጠረጠሩ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።በጠዋቱ ችሎት በቀዳሚነት የቀረቡት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ላይ መርማሪ ፖሊስ የሰራውን የምርመራ ስራ ይፋ አድርጓል።በዚህም የምስክር ቃል መቀበሉን፣ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራን በቴክኒክ ማስረጃ ማረጋገጡን፣ ግብረ አበሮቻቸውን በቁጠጥር ስ ርአውሎ ምርመራ እየሰራ መሆኑን፣ አርቲስት ሃጫሉ የተገደለበትን ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎች ቤት ከተቀበረበት ጓሮ ማውጣቱን እና በምርመራ ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ስልካቸውን ወደ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት መላኩን የአስከሬን ምርመራ ውጤት እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጾ ድርጊቱ የታቀደ መሆኑን በምርመራ ማረጋገጡን ተናግሯል።ከተጠርጣሪዎቹ በስተጀርባ ያለውን በጥንቃቄ እየመረመረ መሆኑን በመጥቀስም ከኢትዮ ቴሌኮም ያገኘውን በስልካቸው የተላከ ሰፊ መልዕክት እየተነተነ መሆኑን አስረድቷል። ለተጨማሪ ምርመራም 14 ቀን ጠይቋል።ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው የእስር አያያዛቸው ብርሃን የማያገኙበት መሆኑን አቤቱታ አስመዝግበዋል።ፍርድ ቤቱም አያያዛቸው እንዲስተካከል ለፖሊስ ትዛዝ በመስጠት ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለነሃሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል።

በሌላ በኩል ከሰአት በነበረ የችሎት ውሎ የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በቡራዩና አዲስ አበባ በተፈጠረ አመጽና ሁከት በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት የተጠረጠሩ በጃምባ ሁሴን መዝገብ የተካተቱ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።መርማሪ ፖሊስ ባሳለፍነው ሃምሌ 7 ቀን 2012 ዓ.ም በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ የሰራውን ምርመራ አቅርቧል።በዚህም በ5ኛና 6ኛ ተጠርጣሪዎች ላይ የወንጀል ተሳትፎ መለየቱን 10 የተከሳሽ 20 ደግሞ የምስክር ቃል መቀበሉን ገልጿል። በአዲስ አባባ ገቢዎች ቢሮ፣ መንገዶች ባለስልጣን፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ የደረሰውን አጠቃይ ከ136 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት መድረሱን ማስረጃ ሰብስቤያለሁም ብሏል።

በቡራዩ በተነሳ ሁከት 4 ሰዎች መሞታቸውን እና አራት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል ጠቁሟል።
ከተለያዩ ተቋማት ማስረጃ ለመሰብሰብ ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀ ሲሆን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃም የተጠቀሰው ምክንያት ተጨማሪ ጊዜ የሚያሰጥ አይደለም ለማሰር ብቻ ነው ሲሉ ተቃውመዋል።ተጠርጣሪዎች ከቤተሰብ ጋር እንደማይገኛኙ በድጋሚ አቤቱታ አስመዝግበዋል።ፖሊስም ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን የአቶ በቀለ ገርባ ሁለት ልጆችን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎችን ለቀናል እኛ ለማሰር ብቻ አደለም እየሰራን ያለነው ለምርመራ ነሲል ምላሽ ሰጥቷል።ፍርድ ቤቱም በድጋሚ አያያዛቸው እንዲስተካከል እና ከቤተሰብ ጋር በጥንቃቄ እንዲገናኙ ትዕዛዝ በመስጠት ለፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ሰባት ቀን ጊዜ ፈቅዷል።የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅም ለሃምሌ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ወለጋ ዉስጥ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነዉ!

በቄለም ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ከባለፈው እሁድ አንስቶ 12 ሰዎች መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የታሳሪ ቤተሰቦች ተናገሩ፡፡ በነቀምቴ ከተማ ከሁለት ሳምንት በፊት  የአርቲስቲ ሀጫሉ ሞትን ተከትሎ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ሀዘናቸውን በገለጹበት ወቅት በተፈጠረው አለመግባባትን  ሰዎች መታሰራቸውን ተገልጸዋል፡፡  በደምቢዶሎ ከተማም እስከ ትናንት ድረስ የታሰሩ ሰዎች  እንዳሉ የከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጅቢሪል መሐመድ እንደተናገሩት የአርቲስት ሐጫሉ ሞትን ተከትሎ በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ሁከትን ለመቀስቀስ የሞከሩ ግልሰቦችን የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባራት እያከናኑ መሆናቸውንና በምዕራብ ኦሮሚያም የተደረገው የተለየ ነገር የለውም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦች መኖራቸውን በመጥቀስ የታሰሩት ሰዎች ቁጥርም ከዚህ በላይ ሊጨምሪ ይችላል ብለዋል፡፡

በቀሌም ወለጋ ዞን የደምቢ ዶሎ ከተማ ነዋሪዎች በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በአደባባይ ወጥቶ ከገለጹ መካከል ናቸው፡፡ ከከተማው ራቅ ባሉት ስፍራዎች ከተፈጠሩት አለመግባባቶች ውጭም በዕለቱ በከተማው  የተፈጠረ ግጭት አልነበረም፡፡ነዋሪዎች ከተለያዩ አካባቢዎች ተሳባስበው በሰላማዊ መንገድ ሀዘናቸውን ገልጸው ወደ የቤታቸው በወቅቱ መለመላሳቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ ከሰሙኑ ደግሞ ግጭት ለመቀስቀስ ሞክራቹሀል የተባሉ 5 ሰዎች በከተማው መታሰራቸውን አንድ ወንድማቸው የታሰረባቸው የከተማው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡"ከዚህ በፊት የታሰሩትን ጨምሮ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በከተማው ፖሊስ ጣቢያ፣ የወረዳ ፖሊስ፣ እና ፖሊስ ካፒም ውስጥ ብዙ ሰዎች ታስረዋው ይገኛሉ፡፡ አንድ ዓመትም፣ ሰባት ወርም ታስረው የቆዩ አሉ፡፡ በዚህን ሳምንት ብቻ ደግሞ አምስት ሰዎች ታስረዋል፡፡ እስከ ትናንት ድረስ ሰዎች ታስረዋል፡፡አንድ ጣቢያ ውስጥ ከ20 እስከ 24 ሰዎችም ታስረው ይገኛሉ" ብለዋል።

በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማም በተመሳሳይ ከባለፈው እሁድ አንስቶ ሰባት ሰዎች መታሰራቸውን አንድ የከተማው ነዋሪ በስልክ ገልጸዋል፡፡ ከታሰሩት መካከከልም የአነግ የምስራቅ ወለጋ ዞን ጽ/ቤት  አስተባባሪ የነበሩ አቶ ዲማ ቢቂላ የተባሉ እንደሚገኙበት ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት በከተማው ተፈጥረው በነበረው አለመረጋጋትም በርካታ ሰዎች ታስረው እንደነበር ጠቁመዋል፡፡የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጅብሪል መሐመድ የታሰሩ ግለሰቦች ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ እና ሲያስተባብሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል፡፡በህግ የሚፈለጉ በርካታ ሰዎችም ተሰውረው እንዳሉም ተናግረዋል፡፡በቄለም እና ምስራቅ ወለጋ እንዱሁም በሌሎች ዞኖችም ታስረው ለሰባት ወራት እና ለአንድ ዓመት ያህልም ክስ ሳይቀርብባቸው ያሉ ሰዎች ስለመኖራቸው ለተነሳው ቅሬታም አቶ ጅብሪል ሲመልሱ ቅሬታው የተለመደና የውሸት ውንጀላ ነው ብለዋል፡፡በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችም ጉዳያቸው ታይቶ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ነጻ ከሆኑ በቶሎ እንደሚለቀቁ ተናግረዋል፡፡ ከፖለቲካ አመለካከቱ እና የፖለቲካ ፓርቲ አባል በመሆኑም የታሰረ ሰው አለመኖሩንም አቶ ጅብሪል አክለዋል፡፡

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
በመጪው ነሃሴ ከኬኒያ ወደኢትዮጵያ በሚገባው አንበጣ ምክንያት እስከ 1 ሚሊየን ሰው ሊራብ ይችላል- ፋኦ

የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ)ባለፈው ሳምንት ያወጣው ሪፖርት፤ ደግሞ በቀጣዩ ነሃሴ ከኬኒያ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ የበርሃ አንበጣ በቶሎ በቁጥጥር ስር ካልዋለ ከ1 ሚሊየን በላይ የሚሆን ህዝብ ሊራብ እንድሚችል አመላክቷል፡፡

#VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa1
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን በቨርችዋል እያስመረቀ ይገኛል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ከ5600 በላይ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በቨርችዋል ቴክኖሎጂ በዩኒቨርሲቲው 6 ኪሎ ግቢ ራስ መኮንን አዳራሽ እያስመረቀ ይገኛል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የወደሙ ኢንቨስትመንቶች ተመልሰው እንደሚገነቡ አስታወቀ!

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ተከትሎ በተፈጸመ 'ሴራ' የወደሙ ኢንቨስትመንቶች ተመልሰው እንደሚገነቡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዘዳንት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በአዳማ ከተማ ኦሮሚያ ሥራ አመራር አካዳሚ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ምክንያት በማድረግ በተፈጸመ ሴራ የወደሙ ኢንቨስትመንቶች መልሰው ይገነባሉ ብለዋል፡፡

'የጥፋት ሃይሎች' የኦሮሞን ህዝብ ስሜት ቀስቅሰው ክልሉን የጦርነት አውድማ ለማድረግ መሞከራቸውን የጠቀሱት ወይዘሮ ጫልቱ፣ ያደረሱት ጥፋት ቀላል ነው ባይባልም ከውጥናቸው አንፃር ሲታይ ግን ጥቂት ነው ብላዋል፡፡በተለይም ኢንቨስትመንት ለክልሉና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምን ያህል አስተዋጽኦ እያበረከተ እንዳለ የተረዱት እነዚህ ሃይሎች ሆን ብለው ባለሃብቱን ለማስበርገግና ዜጎችን ከስራ ለማፈናቀል አልመው መስራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡በክልሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ የንግድና የኢንቨስትመንት ተቋማት እንደወደሙ የገለጹት ምክትል ፕሬዘዳንቷ እነዚህን የኢንቨስትመንት ተቋማት ለመገንባት የፌደራል መንግስት ፣ የክልሉ መንግስትና ባለሃብቶች ተረባርበው ወደ ነበረቡት ይመልሷቸዋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-ኦቢኤን
@YeneTube @FikerAssefa1
ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ዳግም ወደ ኢትዮጵያ በረራ ጀመሩ!

የኮሮና በሽታ ከተከሰተ በኋላ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት በማሳየቱ ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ መብረር መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ክብረአብ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ከተከሰተ በኋላ በርካታ ሀገራት በረራቸውን አቋርጠው ቆይተዋል።በአሁኑ ወቅት ግን በአየር ትራንስፖርት የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት በማሳየቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ሰባት ደርሰዋል። በአማካይ በቀን ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገድ አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ላይ ናቸው።እንደ ኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሽመልስ ገለጻ፤ ኮሮና በሽታ በዓለም ላይ ከተስፋፋ በኋላ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መብረር ከጀመሩ አየር መንገዶች መካከል የዱባይ ፣ የቱርክ፣ የኳታር፣ የግብጽ፣ የሱዳን፣የኬንያ እና የጅቡቲ አየር መንገዶች ይገኙበታል። በአሁኑ ወቅትም በአማካይ ሁለት መደበኛ በረራ እና አምስት መደበኛ ያልሆኑ የመንገደኛ አገልግሎት የሚሰጡ አውሮፕላኖች ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እየበረሩ ይገኛሉ።

#EPA
@YeneTube @FikerAssefa1
ተፈጥሮ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ ከታሠሩት መካከል ሁለት የአሜሪካ ዜጎች በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ!

ሬድዋን አማን እኣነ ዩሱፍ በሽር ተከስቶ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ሁለቱ የአሜሪካ ዜጎች የዋስ መብት ተፈቀደላቸው።የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ተከስቶ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች ቁጥር ከ7ሺህ በላይ መሆኑ ባለስልጣናት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ከእነዚህም መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ሦስት የአሜሪካ ዜጎች ይገኙበታል። የአሜሪካ ዜግነት ካለቸው መካከል ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡት ሬድዋን አማን እና ዩሱፍ በሽር የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሬድዋን አማን እና ዩሱፍ በሽር ነዋሪነታቸው በአሜሪካ አገር የነበረ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ነበር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት።ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሁለቱ ግለሰቦች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው በ6ሺህ ብር የዋስትና መብት ከእስር እንዲወጡ ተወስኗል ብለዋል። ጠበቃው ትናንት ለቢቢሲ ሲናገሩ ደንበኞቻቸው ዓርብ ወይም ቅዳሜ ከእስር ቤት ይወጣሉ ብለውን እንደሚጠበቁ ተናግረዋል።ሦስተኛው የአሜሪካ ዜግነት ያለው እና በእስር ላይ የሚገኘው ግለሰብ ሚሻ ጪሪ የሚባል ሲሆን፤ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ.ኤም.ኤን) ቴክኒሺያን ሆኖ ሲያገለግል ነበር።

ሚሻ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረበት ወቅት በጉዳዩ ላይ የአሜሪካን ኤምባሲን ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት እንዳልተሳካለት ለፍርድ ቤት ተናግሮ ነበር።ትናንት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ላይ ሦስቱም የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች እንቁላል ፍብሪካ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘውን ጊዜያዊ እስር ቤት እንደሚገኙ ጠቅሷል።በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ትናንት በትዊተር ገጹ ላይ “በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካዊያን ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው” ካለ በኋላ፤ አሜሪካውያን በኢትዮጵያ ታስረው ከሆነ በተቻለ ፍጥነት እንደሚጎበኙ እና አስፈላጊው ድጋፍ እና አገልግሎቶች እንደሚያቀርብ ኤምባሲው አስታወቋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የሶማሊያ ፓርላማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አሊ ካይሬ የመተማመኛ ድምፅ ነፈጋቸው!

ምክር ቤቱ ታሪካዊ በተባለ 170 ለ 8 በሆነ አብላጫ ድምፅ በጠ/ሚሩ ላይ እንደማይተማመን ድምፅ የሰጠ ሲሆን የፓርላማው አፈጉባኤም ለፕሬዝዳንቱ አዲስ ጠ/ሚር እንዲሾሙ ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንት ፋርማጆም በአፋጣኝ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሾሙ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ሲ ጂ ቲ ኤን ነው።

@YeneTube @FikerAssefa1
አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ህልፈትን ተከትሎ የወደመበትን ንብረት መንግስት ሊከፍለው እንደሚገባ ገለፀ!

በሻሸመኔ እና በባቱ ከተሞች በተፈጠረው ክስተት ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ሁለት ሆቴሎቹ ላይ አደጋ የደረሰበት አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ ክስተቱ አስደንጋጭ እንደነበር እና የበርካቶች መተዳደሪያ የነበሩ ሆቴሎች መሆናቸውን ነው የገለጸው፡፡ከተሞቹ ወደ ነበሩበት ለመመለስ በርካታ ዓመታትን ሊፈጅ እንደሚችል የገለፀው ሀይሌ፣ መንግስት ከሚሰራቸው የልማት ስራዎች ጎን ለጎን ጥፋትን መከላከል በሚያስችል መልኩ ቢሰራ እና በተዋረድ ያሉ የመንግስት መዋቅሮች በተጠያቂነት ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የነበረው ክስተት በርካቶችን ያሳዘነ መሆኑን የገለፀው አትሌት ኃይሌ፤ መንግስት የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብሏል፡፡ በመሆኑም ከሳምንታት በፊት በነበረው ክስተት የወደመበትን ንብረት መንግስት መልሶ ሊከፍለው እንደሚገባም ነው የጠየቀው፡፡ከአርቲስት ሀጫሉ ህልፈተ ጋር ተያይዞ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገራት ሰልፎች ተደርገዋል፡፡ በተለይ በውጭ ሃገራት በአንዳንድ አካባቢዎች የተደረጉ ሰልፎች ኢትዮያዊነትን የማይገልፁ እንደሆነም ነው ኃይሌ የተናገረው፡፡
የተለያዩ ዓላማዎችን አንግበው በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢትዮጵያን ከድህነት ለማውጣት ጥረት እንዲያደርጉም ኃይሌ ጠይቋል፡፡

#Walta
@YeneTube @Fikerassefa1
በአዲስ አበባ በህንጻ ግንባታ ሰራተኞች ላይ በደረሰ አደጋ ጉዳት ደረሰ!

በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 18፤ 2012 ጠዋት ላይ በደረሰ አደጋ አንድ ሰው ሲሞት በ9 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።በህንጻው ግንባታ ላይ የተሰማሩ 55 ሰራተኞችንም ጉዳት ሳይደረስባቸው በህይወት መትረፋቸውንም አስታውቋል።በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው ይህ ህንጻ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) መገንባት የጀመረ ሲሆን ግንባታው ሲገባደድ ኤጀንሲውን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማትን በውስጡ ይይዛል ተብሎ የሚጠበቅ ነው።

ዛሬ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ገደማ በህንጻው ላይ የደረሰው አደጋ መንስኤ በውጭ ግድግዳ ላይ የተለጠፉ የሴራሚክ ልባሶች መንሸራተት ያስከተለው እንደሆነ አንድ የነፍስ አድን ሰራተኛ ተናግረዋል። የሴራሚክ ልባሶቹ፤ በግንባታ ሰራተኛ መወጣጫዎች (ስካፎሊዲንግ) ላይ በማረፋቸው የመደርመስ አደጋ መከሰቱን እና ጉዳት መድረሱን አክለዋል። በመወጣጫ መደርመስ አደጋው ጽኑ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰራተኞች መካከል አንድ ግለሰብ ሆስፒታል ሲደርስ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አንድ ባለሙያ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ዘጠኝ የግንባታ ሰራተኞች በሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙም አስረድተዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 555 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ8,490 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 555 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡181 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
በአሁኑ ሰዓት ከ10 ሺ በላይ ሰዎች የእኛን ሰብዓዊ ድጋፍ ይሻሉ - ያሬድ ሹመቴ

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ተከትሎ በነበረ ጥፋት እና ሁከት ሳቢያ ብዙዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው፤ ንብረታቸውንም በማጣት አስቸኳይ የሆነ የሰብዓዊ ድጋፍን ይሻሉ፡፡ጥምረት ለሰባዓዊ ድጋፍ የተሰኙ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እና በጎፍቃደኞች ስብስብ ላለፉት አምስት ዓመታት መሰል ችግሮች ሲያጋጥሙ በሃገር ፍቅር ትያትር ቤት ግቢ ውስጥ በመገኘት የቁሳቁስ ድጋፎችን ያሰባስባሉ፡፡ከዚህ ቀደም ቅስቀሳዎችን የሚያደርጉት በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በነበረው የኢንተርኔት መቋረጥ ሳቢያ እርዳታ ለማሰባሰብ እንደዘገዩ ገልጸው ከጊዜያዊ ማከማቻቸው ከነበራቸው መጠባበቂያ አንድ አይሱዙ የሚሆን የምግብ ድጋፍ በሻሸመኔ ለተጎዱ ወገኖች ልከዋል፡፡ይሁና በአሁን ሰዓት ከቀይ መስቀል በተቀበሉት መረጃ መሰረት 10,415 ሰዎች ተፈናቅለው አስቸኳይ እርዳታ እንድሚሹ የሰብዓዊ ድጋፍ ጥምረት በጎፍቃደኛ እና አስተባባሪ የሆነውን አርቲስት ያሬድ ሹመቴ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጿል፡፡ከመጪው ሰኞ ጀምሮም በትያትር ቤቱ ቅጽር ግቢ ውስጥ በመሆንን ከገንዘብ ውጪ ያሉ የዓይነት ድጋፎችን እንደሚያሰባስቡ አስታውቀዋል፡፡

#VoA
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ልደቱ አያሌው በተጠረጠሩበት ወንጀል ሐምሌ 20 ቀን ፍርድ ቤት ይቀርባሉ!

በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረውን ሁከት በማደራጀትና በገንዘብ በመርዳት ወንጀል ተጠርጥረው ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተነገራቸው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራር አቶ ልደቱ አያሌው፣ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ታወቀ፡፡ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተለይ በቢሾፍቱ ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ሳቢያ፣ አቶ ልደቱም ሁከቱን በገንዘብ በመደገፍ መጠርጠራቸውን እንደ ነገሯቸው የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ተናግረዋል፡፡

አቶ ልደቱ በቢሾፍቱ የነበረውን ሁከት በገንዘብ ከመርዳታቸው ባለፈ፣ በሁከቱ ስለተፈጸመው የወንጀል ድርጊትና ስለደረሰው የጉዳት ዓይነት እንዳልተገለጸላቸው የተናገሩት አቶ አዳነ፣ አቶ ልደቱ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉበት ሒደትም ተናግረዋል፡፡የፌዴራል ፖሊስ ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ደውሎላቸው እንደሚፈለጉ ነግሯቸው ወደ ፌዴራል ፖሊስ መሄዳቸውን እንደ ነገሯቸው አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡በቢሮአቸው የጠበቋቸው የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተጻፈ የመያዥያ ደብዳቤ እንዳሳዩዋቸው፣ ምክንያቱ ደግሞ በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን ሁከት በገንዘብ በመደገፍ ወንጀል መጠርጠራቸው መሆኑን ነግረዋቸው ወደ ቢሾፍቱ እየወሰዷቸው እንደሆነ፣ በስልክ እንደገለጹላቸው አስታውቀዋል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምርያ ከከተማው ወረዳ ፍርድ ቤት የመያዥያ ትዕዛዝ የወሰደው፣ ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. መሆኑንም አቶ አዳነ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡አቶ ልደቱ ለበርካታ ዓመታት መኖሪያቸው ከነበረው አዲስ አበባ ከተማ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ቢሾፍቱ በመቀየር፣ አዲስ በገነቡበት ቤት እየኖሩ እንደነበርም አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡ የድምፃዊ ሃጫሉ ሞትን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ሁከት ጉዳት እንዳይደርስባቸው ቤታቸውን ፖሊስ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቦ ሲጠብቅ ካደረ በኋላ፣ በማግሥቱ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ‹‹ለደኅንነትህ›› በማለት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዳመጣቸውም አስረድተዋል፡፡አቶ ልደቱ ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ አበባና በሰሜን ወሎ ላሊበላ ከተማ ልዩ መጠሪያው ‹‹መካነ ልዕልት›› በሚባለው ሥፍራ፣ ከ12 ጓደኞቻቸው ጋር እየገነቡት ያለውን የሪዞርት ፕሮጀክት ለማየት ሄደው እዚያው ቆይተው ሐምሌ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. መመለሳቸውን አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡

#Reporter
@YeneTube @FikerAssefa1
የኮሮናቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ 'የመተላለፍ ዕድሉ ዝቅተኛ ነው!'

የኮሮናቫይረስ ላለባቸው እናቶች አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ከተደረገ በወሊድ ጊዜ ወደ ህጻናቱ የመተላለፍ እድሉ ዝቅተኛ ሊሆን እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።አሜሪካ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ሆስፒታሎች ኮሮናቫይረስ ካለባቸው እናቶች ከተወለዱ 120 ህጻናት ውስጥ አንዳቸውም በበሽታው አለመያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ውጤት የተገኘው ህጻናቱ ከተወለዱ በኋላ ባለው ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከተወለዱ ከሁለት ሳምንታት በኋላ አንዳንዶቹ የእናታቸውን ጡት የመጥባት እድል ካገኙና በአንድ ክፍል ውስጥ አብረው ከቆዩ በኋላም ጭምር ነው።ጥናቱን ያደረጉት ባለሙያዎች እንደሚሉት የተገኘው ውጤት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም ተጨማሪ ሰፋ ያለ ሙከራዎች ማድረግ ያስፈልጋል።

በእርግዝናና በጡት ማጥባት ወቅት የበሽታውን ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታን በተመለከተ ያለው መረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ የሚሰጠው ምክርም የተለያየ እንዲሆን አድርጎታል።የዩናይትድ ኪንግደም ሐኪሞች እናቶች ጡት ማጥባት የሚፈልጉ ከሆነ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ተደርጎላቸው ልጆቻቸውን ጡት ማጥባትም ሆነ አንድ ክፍል ውስጥ መሆን ይችላሉ ብለዋል።ባለሙያዎቹም ሆነ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚሉት በኮሮናቫይረስ የመያዝ ስጋት የበለጠ ጡት ማጥባት ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል የቫይረሱን ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ዕድልን ለመቀነስ አዲስ የተወለዱ ህጻናት ለተወሰነ ጊዜ ከእናታቸው ተለይተው እንዲቆዩ የማድረግ ሃሳብን ተግባራዊ ለማድረግ እያሰበ ነው።ኮሮናቫይረስ ያለባት እናት ከወለደችው ልጅ ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ እንድትቆይ የሚደረግና ጡት እንድታጠባ የሚፈቀድላት ከሆነ፤ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንድትጠቀምና በተደጋጋሚ እጇን መታጠብ እንደሚኖርባት በጥናቱ ተመልክቷል።ጥናቱን የመሩት ዶክተር ክርስቲን ሳልቫቶሬ እንዳሉት "ጥናታችን ወረርሽኙ ያለባቸው እመጫት እናቶች ቫይረሱን ወደ ልጃቸው የማስተላለፍ ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።ነገር ግን ሁኔታውን የበለጠ ለመረዳት አሁንም ሰፋ ያለ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል" ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ በዩናይትድ ኪንግደም የተደረገ ቅኝትን የመሩት ፕሮፌሰር ማሪያን ናይት እንደገለጹት ጥናቱ በአገሪቱ ያለውን መመሪያ የሚደግፍና የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።ጨምረውም "በዩናይትድ ኪንግደም ከአንድ ሺህ በላይ ኮቪድ-19 ያለባቸው እናቶች የወለዱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ከ1 እስከ 2 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ላይ ብቻ ነው ቫይረሱ የተገኘው። በሽታውም በህጻናቱ ላይ የከፋ ህመምን አላስከተለም።"በአሜሪካ የተደረገው አነስ ያለ ጥናትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምበል መጠቀመን የመሰሉ ቀላል የጥንቃቄ እርምጃ በመውሰድ የኮሮናቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታ እንዳይከሰት ማድረግ መቻሉን ፕሮፌሰሯ ጠቅሰዋል።የጥናቱ ውጤት የህጻናትና የአዋቂዎች ጤና ጉዳይ ላይ በሚያተኩረው የላንሴት የህክምና ሙያዊ መጽሔት ላይ ታትሟል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1