የወረታ ደረቅ ወደብ በአዲሱ ዓመት ሥራ እንደሚጀምር ተገለጸ።
ግንባታው 47 በመቶ የተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የወረታ ደረቅ ወደብ መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሥራ ይጀምራል ተባለ፡፡የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት 8ኛውን የደረቅ ወደብ መዳረሻ በወረታ ከተማ ለመገንባት 20 ሄክታር መሬት ወስዶ ወደ ሥራ ገብቷል። የመጀመሪያውን ዙር የግንባታ ፕሮጀክትም በሦስት ሄክታር መሬት ላይ በ90 ሚሊዮን ብር ወጭ ለመገንባት መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ.ም በይፋ ሥራ ጀምሯል፡፡የወረታ ደረቅ ወደብ የመጀመሪያ ዙር ግንባታ 47 በመቶ ተጠናቅቋል ያሉት በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ አሸብር ኖታ ናቸው።
#EPA
@YeneTube @FikerAssefa

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ አንስቶ የተከናወኑ ሥራዎች ሲመዘኑ በ2012 ዓ.ም የላቀ ሥራ መሰራቱን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ።
የግድቡ ግንባታ በሁሉም መስክ የተሳካ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አመለከቱ ።ሥራ አስኪያጁ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፣ ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅም በሁሉም አቅጣጫ በሶስት ሽፍት እየተሰራ ነው።የግድቡ የሲቪል ኢንጅነሪንግ ሥራው 87 በመቶ ፣የብረታ ብረት ሥራዎቹ ደግሞ ከ 31 በመቶ በላይ ፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካል የተርባይንና የጀነሬተር ሥራዎች አፈጻጸምም 45 በመቶ ፤ አጠቃላይ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም ደግሞ 74 በመቶ ደርሷል።ከዚህ ቀደም ችግር የነበረባቸው የቅድመ ሀይል ማመንጫ የብረታ ብረት ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ተነስተው በአዲስ መተካታቸውን ያመለከቱት ሥራ አስኪያጁ፤ የግድቡ የግርጌ የውሃ ማስተንፈሻ (የቦተም አውትሌት) እንዲሁም ከቅድመ ሀይል ማመንጨት ጋር የተገናኙ የሁለት ጀነሬተር ተርባይን ሥራዎች ተጠናቅቆ በኮንክሪት እየተሞሉ መሆኑን አብራርተዋል።
የ 11 ቀሪ ዩኒቶች የብረታ ብረት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተው ፣ ሌሎች ለሲቪል ኮንትራክተሮች የተሰጡ ሥራዎች ደግሞ በቅርቡ እንደሚጀመሩ አስታውቀዋል። ለሁለቱ ቅድመ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የሚሆን የብረታ ብረት ሥራዎች ተከናውነው ኮንክሪት እየተሞሉ መሆኑን ጠቁመዋል። በቀጣይም የጀነሬተር ተርባይን ተከላ እንደሚጀመር ጠቁመዋል።በግድቡ በተለይም የመካከለኛው ውሃ ይፈስበት የነበረው ቦታ ርዝመቱ 525 ሜትር የነበረ ሲሆን፤ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ 560 ሜትር ለማድረስ ከፍተኛ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ ጎንና ጎኖቹም በኮንክሪት እየተሞሉ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ለዜጎች ብሄራዊ ዲጅታል መታወቂያ ለማዘጋጀት ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከተባለ የህንድ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ።
ሥምምነቱን በማስመልከት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ዛሬ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የሙከራ ትግበራ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል።በሥምምነቱ መሠረት ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ዘመናዊ የአሰራር ሲስተም ይዘረጋል።የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን ተግባራዊ ለማድረግ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በርካታ ክንውኖች ሲካሄዱ እንደቆዩም ሚኒስትሯ ግልጸዋል።የብሔራዊ መታወቂያ አገልገሎት የተሳለጠና ደህንነቱ የተረጋገጠ አገልግሎት ለማግኘት ይረዳል ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ወንጀል ከመከላከልና የፋይናንስ ዘርፉን ከማዘመን አኳያም ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።በሙከራ ትግበራው 30 ሺህ ዜጎች እንደሚሳተፉ ታውቋል። በአጠቃላይ የመግባቢያ ሥምምነቱ ቴክኖሎጂውን በራሳችን አቅምና ነባራዊ ሁኔታ ደህንነቱ የተጠበቀ ብሔራዊ መታወቂያ ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል።እንደ ኢዜአ ዘገባ የሙከራ ትግበራው ከስምንት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ዳግም ወደ ኢትዮጵያ በረራ ጀመሩ!
የኮሮና በሽታ ከተከሰተ በኋላ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት በማሳየቱ ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ መብረር መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ክብረአብ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ከተከሰተ በኋላ በርካታ ሀገራት በረራቸውን አቋርጠው ቆይተዋል።በአሁኑ ወቅት ግን በአየር ትራንስፖርት የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት በማሳየቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ሰባት ደርሰዋል። በአማካይ በቀን ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገድ አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ላይ ናቸው።እንደ ኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሽመልስ ገለጻ፤ ኮሮና በሽታ በዓለም ላይ ከተስፋፋ በኋላ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መብረር ከጀመሩ አየር መንገዶች መካከል የዱባይ ፣ የቱርክ፣ የኳታር፣ የግብጽ፣ የሱዳን፣የኬንያ እና የጅቡቲ አየር መንገዶች ይገኙበታል። በአሁኑ ወቅትም በአማካይ ሁለት መደበኛ በረራ እና አምስት መደበኛ ያልሆኑ የመንገደኛ አገልግሎት የሚሰጡ አውሮፕላኖች ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እየበረሩ ይገኛሉ።
#EPA
@YeneTube @FikerAssefa1

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2012 በጀት ዓመት ለሱዳንና ጅቡቲ ካቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ66 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ፡፡
ተቋሙ በ2012 በጀት ዓመት 56 ነጥብ 92 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ከ66 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሰብስቧል፡፡ ይህም የዕቅዱን 116 ነጥብ 5 በመቶ በማከናወን ከዕቅድ በላይ ገቢ መገኘቱ ተገልጿል፡፡በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው ገቢ 37 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ከጅቡቲ እና ቀሪው 29 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከሱዳን የተገኘ ነው ተብሏል፡፡በዚህ ዓመት ከሁለቱ ሀገራት የተገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ገቢ ከ2011 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።

የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ኢትዮጵያ አልሸባብን በመከላከል እያደረገች ባለው እና ሌሎች የጸጥታ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽእኖ እንደሚያመጣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ!
በአሜሪካ የተጣለው የቪዛ እገዳ ኢትዮጵያ በቀጣናው በምታካሂደው አልሸባብን የመከላከል እና ሌሎች የጸጥታ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽእኖ እንደሚያመጣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ እንደተናገሩት፤ ውሳኔው በቀጣናው ሽብርተኞችን በመከላከል ረገድ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው ስራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።
በአሜሪካ መንግስት የተላለፈው ውሳኔ መልሶ አሜሪካኖቹን መጉዳቱ አይቀርም ሲሉ ነው አምባሳደር ዲና ያብራሩት።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫም፤ የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ለመግባት ያለመ ከሆነና ክፍለ ዘመን የተሻገረውን ወዳጅነት ከግምት ውስጥ ያላስገባ እስከሆነ ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ መንግስት ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት መለስ ብሎ ለማጤን ይገደዳል ሲል አስታውቋል።
አምባሳደር ዲና በዛሬው መግለጫቸው፤ ሱዳንና ግብጽ የጋራ ጦር ልምምድ ማድረግ ይችላሉ፤ ኢትዮጵያውያን ግን ሉአላዊነታቸውን ለማስጠበቅ ሁሌም ዝግጁ ናቸው ብለዋል።
አምባሳደር ዲና እንደገለጹት፤ በአገሩ ሉኣላዊነት ጉዳይ የሚተኛ ህዝብም ሆነ መከላከያ ሰራዊት እንደሌለን ይታወቃል። ሱዳን እና ግብጽ በድንበር አካባቢ የጥምር ጦር ልምምድ ቢያደርጉም ሁልጊዜም እንደምንለው በኢትዮጵያ ላይ ኪሳራ የሚያመጣ መሆን የለበትም። ኪሳራ የሚያመጣ ከሆነ ግን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለመጠበቅ የሚሰራው ኃይል ምላሹን ለመስጠት ሁሌም ዝግጁ ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ደረጃ እምነት ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ አምባሳደር ዲና አብራርተዋል።
{ #በጌትነት_ተስፋማርያም #EPA }
@Yenetube @Fikerassefa