የቁጫ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በርካታ አባላቱ ከሕግ ውጪ ታሰሩብኝ አለ!
የቁጫ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ)፣ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በሰላማዊ መንገድ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንደተፈጠረበትና በርካታ አባላቱ እንደታሰሩበት አስታወቀ፡፡የቁጫ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችው ሰላም በር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ አብርሃም ቡሄ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባል በመሆኑና የፓርቲ ሥራ በመሥራቱ የታሰረም ሆነ የተከለከለ አንድም ሰው እንደሌለ በመግለጽ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
#Reporter
@YeneTube @FikerAssefa

በጡረታ ለተሰናበቱ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች የተፈቀደው ልዩ ጥቅማ ጥቅም ቀሪ እንዲሆን ተወሰነ!
ከሁለት ዓመት በፊት በተላለፈ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጨማሪ ውሳኔ በጡረታ ለተሰናበቱ ከፍተኛ የአገርና የመንግሥት አመራሮች ሲሰጥ የነበረ ልዩ ጥቅማ ጥቅም ቀሪ እንዲሆን ተወሰነ።የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ በጡረታ ለተሰናበቱ የአገርና የመንግሥት አመራሮች ከአዋጅ ውጪ በልዩ ውሳኔ የተፈቀደላቸው ልዩ ጥቅማ ጥቅም ቀሪ እንዲሆን ወስኗል።
እነዚህም በጡረታ የተሰናበቱ የአገርና የመንግሥት አመራሮች በኃላፊነት በነበሩበት ወቅት በተሰጣቸው ቤት መኖር እንዲቀጥሉ፣ አንድ አውቶሞቢልና አንድ የመስክ ተሽከርካሪ እንዲሰጣቸው እንዲሁም በኃላፊነት በነበሩበት ወቅት ያገኙ የነበረው የሕክምና አገልግሎት ማግኘት እንዲቀጥሉ የሚፈቅዱ ናቸው።
ከሳምንት በፊት የተላለፈው አዲሱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ከላይ የተገለጹት ሦስት ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞች እንዲሻሩና በአዋጁ መሠረት ብቻ እንዲስተናገዱ የሚል ነው:: በዚህ ውሳኔ መሠረት ቤት የተሰጣቸው በጡረታ የተሰናበቱ አመራሮች እንዲኖሩበት የተሰጣቸውን ቤትና የመስክ ተሽከርካሪ እንዲመልሱ የተባለ ሲሆን፣ የገንዘብ ሚኒስቴርም ይህንን ውሳኔ እንዲፈጽም ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም.ትእዛዝ ደርሶታል።

አቶ ልደቱ አያሌው በተጠረጠሩበት ወንጀል ሐምሌ 20 ቀን ፍርድ ቤት ይቀርባሉ!
በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረውን ሁከት በማደራጀትና በገንዘብ በመርዳት ወንጀል ተጠርጥረው ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተነገራቸው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራር አቶ ልደቱ አያሌው፣ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ታወቀ፡፡ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተለይ በቢሾፍቱ ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ሳቢያ፣ አቶ ልደቱም ሁከቱን በገንዘብ በመደገፍ መጠርጠራቸውን እንደ ነገሯቸው የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ተናግረዋል፡፡
አቶ ልደቱ በቢሾፍቱ የነበረውን ሁከት በገንዘብ ከመርዳታቸው ባለፈ፣ በሁከቱ ስለተፈጸመው የወንጀል ድርጊትና ስለደረሰው የጉዳት ዓይነት እንዳልተገለጸላቸው የተናገሩት አቶ አዳነ፣ አቶ ልደቱ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉበት ሒደትም ተናግረዋል፡፡የፌዴራል ፖሊስ ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ደውሎላቸው እንደሚፈለጉ ነግሯቸው ወደ ፌዴራል ፖሊስ መሄዳቸውን እንደ ነገሯቸው አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡በቢሮአቸው የጠበቋቸው የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተጻፈ የመያዥያ ደብዳቤ እንዳሳዩዋቸው፣ ምክንያቱ ደግሞ በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን ሁከት በገንዘብ በመደገፍ ወንጀል መጠርጠራቸው መሆኑን ነግረዋቸው ወደ ቢሾፍቱ እየወሰዷቸው እንደሆነ፣ በስልክ እንደገለጹላቸው አስታውቀዋል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምርያ ከከተማው ወረዳ ፍርድ ቤት የመያዥያ ትዕዛዝ የወሰደው፣ ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. መሆኑንም አቶ አዳነ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡አቶ ልደቱ ለበርካታ ዓመታት መኖሪያቸው ከነበረው አዲስ አበባ ከተማ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ቢሾፍቱ በመቀየር፣ አዲስ በገነቡበት ቤት እየኖሩ እንደነበርም አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡ የድምፃዊ ሃጫሉ ሞትን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ሁከት ጉዳት እንዳይደርስባቸው ቤታቸውን ፖሊስ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቦ ሲጠብቅ ካደረ በኋላ፣ በማግሥቱ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ‹‹ለደኅንነትህ›› በማለት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዳመጣቸውም አስረድተዋል፡፡አቶ ልደቱ ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ አበባና በሰሜን ወሎ ላሊበላ ከተማ ልዩ መጠሪያው ‹‹መካነ ልዕልት›› በሚባለው ሥፍራ፣ ከ12 ጓደኞቻቸው ጋር እየገነቡት ያለውን የሪዞርት ፕሮጀክት ለማየት ሄደው እዚያው ቆይተው ሐምሌ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. መመለሳቸውን አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡
#Reporter
@YeneTube @FikerAssefa1

መንግሥት የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች እንዳይገቡ ወሰነ!
በመካሄድ ላይ ባለው የቴሌኮም ዘርፍ የለውጥ ትግበራ፣ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች እንዳይገቡ መንግሥት እንደወሰነ ታወቀ፡፡የቴሌኮም ዘርፍን ገበያ በመክፈት የውጭ ኩባንያዎች እንዲገቡ ለመፍቀድ መንግሥት በዝግጅት ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡የቴሌኮም ዘርፍ የለውጥ ትግበራ ሁለት ክፍሎች አሉት።የመጀመርያው በገንዘብ ሚኒስቴር የሚመራው ለ126 ዓመታት በብቸኝነት የቴሌኮም አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው በአፍሪካ አንጋፋው ኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ፣ 40 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ለውጭ ኩባንያ ለመሸጥ የሚደረገው ጥረት ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ሁለት ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች ወደ አገር ውስጥ ገብተው፣ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡የለውጥ ትግበራው ቀልባቸውን ከሳበው የውጭ ኩባንያዎች መካከል፣ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ገንብተው የሚያከራዩ ኩባንያዎች ይገኙበታል፡፡እንደ ሞባይል ምሰሶዎች ያሉ መሠረት ልማቶች የሚያከራዩ ኩባንያዎች ኃላፊዎች ወደ አዲስ አበባ ሲመላለሱ ከርመዋል፡፡
ጉዳዩ ባለፉት ዓመታት በቢሊዮን ዶላሮች ወጪ በማውጣት የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች በመላ አገሪቱ ሲዘረጋ የቆየውን ኢትዮ ቴሌኮምን አስቆጥቷል፡፡‹በቂ መሠረተ ልማት ገንብተናል፣ ለሚገቡት ኩባንያዎች አከራይተን ከፍተኛ ገቢ ማስገባት እንችላለን› ያሉት የኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት አባላት ያቀረቡትን አቤቱታ መንግሥት ተቀብሎ፣ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች ላለማስገባት እንደወሰነ ታውቋል፡፡
የ2012 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ፣ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች እንዳይገቡ እንደተወሰነ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች እንዳይገቡ መንግሥት ወስኗል፣ አይገቡም፡፡ የሚገቡት ኦፕሬተሮች ወይ ከእኛ ይከራያሉ ወይም የራሳቸውን ይገነባሉ፤›› ያሉት ወ/ሪት ፍሬሕይወት፣ ኩባንያዎቹ የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ምሰሶዎችንና የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮችን መከራየት እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በሊበራላይዜሽን ሒደቱ ላይ ያሉትን ሥጋቶችና ቅሬታዎች በጽሑፍ ለኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን አስገብቶ፣ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ‹‹ባለሥልጣኑ የኢትዮ ቴሌኮምን ህልውና የሚጎዳ አካሄድ ይከተላል ብለን አናምንም፡፡ ነገር ግን ከስምምነት ላይ ያልደረስንባቸው ቀሪ ጉዳዮች አሉ፤›› ብለዋል፡፡በተያያዘ ዜና የኢትዮ ቴሌኮም የንብረት ትመና ሥራ በማከናወን ላይ የሚገኘው ኬፒኤምጂ (KPMG) የተሰኘው ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት፣ ሥራውን በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የንብረት ትመና ሥራውን አጠናቆ ሁለት ዙር ሪፖርት ለኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት እንዳቀረበ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ተናግረዋል፡፡በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ አሠራር ሥርዓት ሪፖርት እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡