እስራኤል ጎንደር ከተማ ላይ የባህል ሙዚዬም የመገንባት ፍላጎት እንዳላት በምክትል አምባሳደሯ በኩል ገልፃለች።
ዛሬ ግንቦት 29/2011 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ጉብኝት ያደረጉት የእስራኤል ምክትል አምባሳደር አቶ ዳኔሊይ ከጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን አዳነ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም እስራኤል ጎንደር ላይ የባህል ሙዚዬም የመገንባት ፍላጎት እንዳላት አንስተዋል። በጎንደር ከተማ አስተዳድር በኩልም በጎ ምላሽ ተሰጥቷል። ሙዚዬም መገንባት ያስፈለገውም የባህል ትስስርን ከፍ ለማድረግ በመሆኑ ንድፉ እንደመጣ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ተቀዳሚ ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን ጠቅሰዋል።
Via:- #AMMA
@yenetube @fikerassefa

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ባንኩ ያጋጠመውን የ‹‹ሲስተም›› ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገጠመው ‹‹የሲስተም›› ችግር በሁለት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሊፈታ እንደሚችልም አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላለፉት ሁለት ቀናት የ‹‹ሲስተም›› ብልሽት አጋጥሞታል፡፡ በዚህም የተነሳ ደንበኞች ለእንግልት መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
እንደ ሀገር በየወቅቱ እየተፈጠረ ባለው የ‹‹ኔት ወርክ›› እና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ባንኩ ለችግር እየተጋለጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ የአብሥራ ከበደ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ ይህም ደንበኞቹን ለእንግልት እየዳረገበት እንደሆነም ነው አቶ የአብሥራ ያስታወቁት፡፡
ለሁለት ቀናት በባንኩ ደንበኞች ላይ የተፈጠረው መጉላላት ምክንያቱ የ‹‹ሲስተም›› ብልሽ እንደሆነ የገለጹት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ችግሩ ከተከሠተበት ጊዜ ጀምሮ በፍጥነት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡
ባንኩ በመላው ሀገሪቱ ከ 1ሺህ 450 በላይ ቅርንጫፎች አሉት ተብሏል፡፡ ደንበኞች በበዙ ቁጥር ችግሩ ስለሚኖር ይህንን የሚፈታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወደ ሥራ ለማስገባት በእቅድ እየተሠራ እንደሆነ ነው ባንኩ ለአብመድ ያስታወቀው፡፡ ችግሩ ዛሬ ወይም ነገ ሙሉ በሙሉ ሊፈታ እንደሚችልም አቶ የአብሥራ አስታውቀዋል፤ ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ደንበኞች ችግሩ እስኪፈታ #በትዕግሥት እንዲጠብቁም ባንኩ ጠይቋል፡፡
Via #AMMA
@Yenetube @Fikerassefa

የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በኤርትራ በሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ይሳተፋል፡፡
ከ15 ዓመት በታች ታዳጊ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በኤርትራ የሚደረገው የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ቀጣና ሻምፕዮና (ሴካፋ) ውድድር ሊሳተፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ቡድኑ ከ20 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በኤርትራ የሚጫወት የኢትዮጵያ ቡድን እንደሚሆን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
በምድብ ሁለት ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን በቅድሚያ ከኡጋንዳ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነገ ይጫወታል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የፕሬስ ኃላፊ ባሕሩ ጥላሁን “ይህ ለእኛ የተጠፋፋ ቤተሰብ እንደመገናኘት የሚቆጠር ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
“ኤርትራ ውስጥ በተዘጋጀው ውድድር ተደስተናል፤ ከ20 ዓመታት በላይ ተለያይተናል። ይህም ኤርትራ ውስጥ ከሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ዘላቂ ወዳጅነት የምንመሠርትበት መልካም አጋጣሚ ይሆናልም” ብለዋል።
በውድድሩ ላይ አስተናጋጇ ኤርትራ በምድብ አንድ ከሚገኙት ቡሩንዲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ጋር ትጫወታለች።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከየምድባቸው ማለፍ ከቻሉ አብረው የመጫወት ዕድል ሊኖራቸው እንደሚችልም ቢቢሲን ጠቅሶ ኢብኮ ዘግቧል፡፡
Via #AMMA
@YeneTube @FikerAssefa

የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ከተረጋገጡ 16 አሽከርካሪዎች መካከል ስድስቱ መገኘታቸውን ጤና መምሪያው አስታወቀ፡፡
የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸው ወደ ለይቶ ማከሚያ ያልገቡትን አሽከርካሪዎች እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡በሰሜን ሸዋ ዞን 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የዞኑ ጤና መምሪያ ትናንት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ ነበር 22 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው፡፡ከ79 ተመርማሪዎች 36 አሽርካሪዎች እንደነበሩና ከእነዚህ መካከል 16 የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውም ዘግበን ነበር፡፡
ቫይረሱ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል 16ቱ አሽከርካሪዎች እየተፈለጉ እንደሚገኙ የዞኑ ጤና መምሪያ ለአብመድ ገልጾ ነበር፡፡ አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ደግሞ ስድስት አሽከርካሪዎች ተገኝተዋል፤ ወደ ለይቶ ማከሚያ ማዕከልም ተወስደዋል፡፡ ሌሎችን አሽከርካሪዎች እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉንም ጤና መምሪያው አስታውቋል፡፡በአማራ ክልል ትናንት ሰኔ 8/2012 ዓ.ም ይፋ የተደረገ መረጃ እንደሚያሳየው ከ624 የላቦራቶሪ ምርመራ በ33 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡በክልሉ እስከ ትናንት ሰኔ 8/2012 ዓ.ም ድረስ ለ5 ሺህ 590 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ231 ሰዎች ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ በክልሉ አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 44 መድረሱን መዘገባችን ይታወቃል፡፡
#AMMA

የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋግጦ ሲፈለጉ ከነበሩት አሽከርካሪዎች መካከል 15 መገኘታቸውን ጤና መምሪያው አስታወቀ፡፡
የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸው ወደ ለይቶ ማከሚያ ያልገቡትን አሽከርካሪዎች እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡በሰሜን ሸዋ ዞን22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የዞኑ ጤና መምሪያ ትናንት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ ነበር 22 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው፡፡ ከ79 ተመርማሪዎች 36 አሽርካሪዎች እንደነበሩና ከእነዚህ መካከል 16 የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውም ይታወቃል፡፡ቫይረሱ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል 16ቱ አሽከርካሪዎች እየተፈለጉ እንደሚገኙ የዞኑ ጤና መምሪያ ገልጾ ነበር፡፡አሁን በደረሰ መረጃ መሠረት ደግሞ 15 አሽከርካሪዎች ተገኝተዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ አስራ ሁለቱ ወደ ደብረ ብርሃን ለይቶ ማከሚያ ማዕከል ተወስደዋል፡፡ ሦስቱ ደግሞ አዲስ አበባ ወደ ሚገኝ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እንዲገቡ ሊደረግ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ አንድ አሽከርካሪ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ጥሪ ባለመቀበሉ እስካሁን እንዳልተገኘና ፍለጋው መቀጠሉንም ጤና መምሪያው አስታውቋል፡፡

ግብጽ ድርድሩን አቋርጣ የምትወጣ ከሆነ ከዚህ በኋላ ለድርድር የምትቀመጥበት ምንም ዓይነት መንገድ አለመኖሩን ኢትዮጵያ አሳወቀች፡፡
ኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ሰሞኑን እየተካሄደ ያለውን የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር አስመልክተው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በመግለጫቸው እንዳመላከቱት ግብጽ ከዚህ በፊት በድርድሩ ስታሳየው የነበረውን ሙሉ የዓባይ ውኃ ይገባኛል አካሄድ አሁንም እየተከተለች ነው፡፡ በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመናት የተከተሉት ይህ አካሄድ ለአሁኑ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን በምንም መልኩ የማያስኬድና የማንቀበለው ነው ብለዋል አቶ ገዱ በመግለጫቸው፡፡
ግብጽ አሁንም ፍላጎቷ ድርድሩ እንዲቋረጥ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት በ2015 (እ.አ.አ) ከነበረው የመርህ ስምምነት ውጭ ሌላ መተሳሰሪያ የሌለን በመሆኑ ግብጽ ድርድሩን አቋርጣ የምትወጣ ከሆነ ከዚህ በኋላ ለድርድር የምንቀመጥበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም ሲሉም አስጠንቅቀዋል።እየተደራደርን ያለነው ሁሌም እኔ ብቻ ልጠቀም ከምትለው፣ እድሜ ልኳን የኢትዮጵያን ጥቅም ከምትጻረረው፣ ሀገራችን ዘላቂ ጥንካሬ እንዳይኖራት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከምትሠራው ግብጽ ጋር ነው ሲሉም አቶ ገዱ የግብጽን አቋም አስረድተዋል፡፡የግብጽ ሕዝብ መንግሥታቸው ምክንያታዊና ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ተመስርቶ እንዲደራደር ጫና እንዲያሳድሩም ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጥበብ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀምሯል፡፡
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኃላፊ የሺጌታ ገላው (ዶክተር) ለአብመድ እንዳሉት ጥበብ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀን 96 ናሙናዎችን መርመር የሚያስችል ላቦራቶሪ ሥራ ጀምሯል፡፡በሆስፒታሉ አንድ የመመርመሪያ ማሽን እንዳለና ወደፊት ተጨማሪ ለማምጣት እንቅስቃሴ እንደተጀመረም አስታውቀዋል፡፡
#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኃላፊ የሺጌታ ገላው (ዶክተር) ለአብመድ እንዳሉት ጥበብ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀን 96 ናሙናዎችን መርመር የሚያስችል ላቦራቶሪ ሥራ ጀምሯል፡፡በሆስፒታሉ አንድ የመመርመሪያ ማሽን እንዳለና ወደፊት ተጨማሪ ለማምጣት እንቅስቃሴ እንደተጀመረም አስታውቀዋል፡፡
#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮናቫይረስ ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባሉ አንዳንድ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን ገልጸዋል።በማሻሻያው መሠረት በተለያዩ ምክንያቶች ለሞት የሚዳረጉ ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በማኅበረሰቡ የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸም ተፈቅዷል።ይህም ከዚህ ቀደም የአስክሬን የላብራቶሪ ውጤት ከመምጣቱ በፊት የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸም አይቻልም የሚለውን መመሪያ መሻሻሉን ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።ይሁን እንጂ በቀብር ሥፍራ ላይ ከዚህ ቀደም የተቀመጠው 50 ሰዎች ብቻ ተገኝተው ሥርዓቱን ማከሄድ አለባቸው የሚለው መመሪያው አልተሻሻለም ብለዋል።ግለሰቦች በኮሮናቫይረስ ቢያዙ የሚያገለግሏቸው የቤተሰብ አባላትና የራሳቸው ፍላጎት ከግምት በማስገባት ተፈጻሚ የሚሆን መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የግለሰቦችን የአኗኗር ሁኔታ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት አግባብ ከሆነ በቤታቸው እንዲቆዩ እንደሚደረጉም ተገልጿል።ከውጭ የሚገቡ ሰዎች በተለይም ወደ አገር ከገቡ በኋላ ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ ከመጡበት አገር ተመርምረው ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ ይዘው ከመጡ ናሙና ተወስዶ በቤታቸወ 14 ቀናት እንዲቆዩ ይደረጋልም ተብሏል። ኢዜአ እንደዘገበው ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ሪፖርት ይዘው ለማይመጡ መንገደኞች ናሙናቸው ተወስዶ ለሰባት ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ እንደሚደረግ ዶክተር ሊያ ተናግረዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ለ14 ቀናት የነበረውን አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ወደ ለ7 ቀናት ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።

በ30 ሰከንድ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ የሚችል መሣሪያ እየተሠራ ነው፡፡
አንድ የእስራኤል ኩባንያ በ30 ሴከንድ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ የሚረዳ መሣሪያ እየሠራ ስለመሆኑ አልጀዚራ እና ሲ ጂ ቲ ኤን በድረ ገጻቸው አስነብበዋል፡፡ መሣሪያው ትንፋሽ በመውሰድ ምርመራው ማድረግ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡‘ናኖሴንት’ የተባለው ተቋም ትንፋሽን በመጠቀም ምርመራ ለማድረግ የሚረዳው መሣሪያ በእራኤል ሰፊ ሙከራ እየተደረገበት እንደሆነ አስታውቋል፡፡ 85 ከመቶ ውጤታማነቱን እንዳስመሰከረም ተቋሙ ጠቁሟል፡፡
#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1

ባለፈው በጀት ዓመት ሕግን በማስከበር በኩል አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታወቁ።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የክልሉን 2012 በጀት ዓመት ሪፖርት በምክር ቤቱ 5ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔ ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡበት ጊዜ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ ለክልሉ ሰላምና ጸጥታ ትኩረት ተሰጥቶ ተሠርቷል።
በክልሉ ሰላም እንዳይኖር በማኅበራዊ ሚዲያ ሲለቀቁ የነበሩ የሀሰት ትርክቶች አሉታዊ ሚና እንደነበራቸውም ጠቁመዋል። በጎንደር ከተማም ከመንግስት የጸጥታ መዋቅር ውጭ በብርጌድና በሻለቃ በማደራጀት ሰው በማገትና ሃብትና ንብረት ዘረፋ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ቡድኖችን ስርአት ለማስያዝ መሠራቱን አብራርተዋል። በህገ ወጥ አደረጃጀት ተደራጅተው ከነበሩት ውስጥ 215 በምኅረት፣ 405 ሰላማዊ በሆነ መንገድ እጅ እንዲሰጡ፣ ፈቃደኛ ያልነበሩ 686 ሰዎች ደግሞ በኃይል እጅ እንዲሰጡ በማድረግ ሕግና ስርአት የማስከበር ሥራ ተሠርቷል ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ።
ትህነግ በጸብ አጫሪነት ባህሪው እንደገፋበትና እንቅስቃሴውን ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚያሻም ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል የ2013 በጀት 62 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸድቋል።
24 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ከክልሉ የሚሰበሰብ፣ 38 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ከፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እና ዜሮ ነጥብ 2 ቢሊዮን ብሩ ከውጭ ዕርዳታ የሚገኝ ነው። የፌደራል መንግሥት የሰጠው በጀት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ23 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል።0.2 ቢሊዮን ብሩ ከክልል የሚሰበሰብ ነው። የ2013 በጀት ከ2012 በጀት ጋር ሲነጻጸር በ15 ነጥብ 3 ቢሊዮን (32.4 ከመቶ) ጭማሪ አለው። በጀቱ የተወሰነ ጭማሪ ቢኖረውም የኮሮናቫረስ ወረርሽኝ ከሚያስከትለው ተጽእኖ አንጻር በቂ ነው ለማለት አዳጋች መሆኑን የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን መሐሪ (ዶክተር) ተናግረዋል።

በፎገራ ወረዳ የጎርፍ አደጋው ቢቀንስም ስጋቱ እንደቀጠለ ነው ተባለ፡፡
በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ትናንት የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ በተወሰነ ደረጃ ቢቀንስም ስጋቱ ግን እንደቀጠለ ነው፡፡ በፎገራ እና ሊቦከምከም ወረዳዎች የርብ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በዘጠኝ ቀበሌዎች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷል፡፡የፎገራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አለባቸው ደጀን እንዳሉት ከሰዓት በኋላ የጎርፉ መጠን ቀንሶ ተሽከርካሪዎች ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የየአካባቢው ነዋሪዎችም ወደየቤታቸው ተመልሰው ገብተዋል፡፡ መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም በሰዎች ቀለብ ላይ ጉዳት እንዳደረሰም ምክትል አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡ ወንዙ እንደሞላ በመሆኑ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስም ሥጋት አለ፡፡ ቀደም ብሎ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል በመሠራቱ ከዚህ በላይ ይደርስ የነበረውን አደጋ ማስቀረት እንደተቻለ የተናገሩት አቶ አለባቸው በአፋጣኝ የማስተካከል ሥራ ካልተሠራ ስጋቱ ሊያሻቅብ እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

በአማራ ክልል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም አስገዳጅ እንደሚሆን የክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ኃይል አስታውቋል።
የአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መልበስ ግዴታ ሆኗል ብለዋል።የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሀገሪቱ እና በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለፁት ዶክተር ሙሉነሽ ማኅበረሰቡ በአንፃሩ በአሳሳቢ ደረጃ እየተዘናጋ መሆኑን ነው ያነሱት።በክልሉ ያለው የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ዋጋ በሚያስከፍል ሁኔታ እንደተፋዘዘም ተናግረዋል። "ከበሽታው መራቅ ሲገባን ወደ በሽታው እየቀረብን ነው" ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ መመሪያዎች እየተጣሱ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ከመልበስ ይልቅ አለመልበስ እየተበራከተ መሆኑንም አመላክተዋል። በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መልበስ አስገዳጅ መሆኑን ያስታወሱት ዶክተር ሙሉነሽ መግለጫው ከተሰጠበት ከዛሬ ሐምሌ 24/2012 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መልበስ ግዴታ መሆኑንም አስታውቀዋል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ባላደረገ ሰው ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም ተናግረዋል።የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሚያዚያ 12 ቀን 2012 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ በትኩረት መተግበር እንደሚገባም አሳስበዋል።የፀጥታ አካለትም ተግባራዊነቱን አስገዳጅ እንዲያደርጉት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በነሀሴ ወር የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ለ 200 ሺህ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ታቅዷል።
ለአንድ ወር የሚቆይ የኮሮና ቫይረስ ማኅበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።መርሀ ግብሩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶክተር) በተገኙበት ነው ይፋ የተደረገው።በዘመቻው በነሀሴ ወር የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት 200 ሺህ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል።በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ መሰራጨቱም ተገልጿል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር የመጀመሪያው 1 ሺህ ለመድረስ 79 ቀናትን እንደወሰደ፣ አሁን ላይ ግን በሁለት ቀናት ብቻ 1 ሺህ ሰዎች መያዛቸው ተገልጿል።ማኅበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻው ይፋ የተደረገውም የስርጭቱን መጠን ለማወቅና ለመቆጣጠር ታልሞ እንደሆነ ታውቋል።በቅርቡ በአዲስ አበባ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት የማስክ አጠቃቀም 76 በመቶ ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ 38 በመቶ፣ የእጅ ንጽህና አጠባበቅ 28 በመቶ መሆኑ እንደተመላከተም ነው የተገለጸው።

ዘንድሮ የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓላት እንደበፊቱ በደመቀ ሁኔታ እንደማይከበሩ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አሳወቀ፡፡
የኮሮና ተህዋሲያን (ቫይረስ) ወረርሽኝ እየተስፋፋ መምጣቱ ስነ ስርዓቱ እንዳይካሄድ አድርጓል፡፡በዘንድሮ ዓመት የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓላት እንደ በፊቱ በደመቀ ሁኔታ እንደማይከበሩ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አሳውቋል፡፡ ይህም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት እንደሆነ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኃይለየሱስ ፍላቴ ጠቁመዋል፡፡በዓሉ በፓናል ውይይት፣ በፎቶ ማሳያ (ኤግዚቢሽን)፣ በደም ልገሣና ችግኝ ተከላ ታስቦ እንደሚውል ኃላፊው አመላክተዋል፡፡ የሻደይ አሸንድዬ ባህላዊ ትውፊት በ“ዶክሜንታሪ” በብዙኃን መገናኛ አውታሮች በተለይም በቴሌቪዥንና በሬድዮ ተዘጋጅተው እንደሚቀርቡ አቶ ኃይለየሱስ ጠቅሰዋል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ከዕቅድ በላይ ደም መሰብሰቡን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ አስሩም የደም ባንክ የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም መለስተኛ ደም ባንክ አቋቁመው አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎች ተወካዮች በተገኙበት የ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ አካሂዷል፡፡ባለፈው በጀት ዓመት ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች 58 ሺህ 440 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ 59 ሺህ 271 ዩኒት ደም መሰብሰቡን ጤና ቢሮው ገልጿል። አፈጻጸሙ 101 ነጥብ 4 በመቶ መሆኑንም የቢሮው የደም ባንክ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ አንዳርጌ አጥናፉ ገልጸዋል፡፡

በአማራ ክልል ተጨማሪ 24 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 2 ሺህ 293 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 24 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።በአጠቃላይ እስከ ዛሬ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 703 መድረሱንም ጤና ቢሮው ገልጿል።በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት ውስጥ በክልሉ ሰባት ሰዎች ማገገማቸውን ጤና ቢሮው አስታውቋል። በአጠቃላይ ያገገሙትም 489 ደርሰዋል።
#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 2 ሺህ 293 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 24 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።በአጠቃላይ እስከ ዛሬ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 703 መድረሱንም ጤና ቢሮው ገልጿል።በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት ውስጥ በክልሉ ሰባት ሰዎች ማገገማቸውን ጤና ቢሮው አስታውቋል። በአጠቃላይ ያገገሙትም 489 ደርሰዋል።
#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎች በክልሉና በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በባሕር ዳር እየመከሩ ነው።መድረኩ በለውጥ ሂደቱ የተመዘገቡ ውጤቶችና ያጋጠሙ ፈተናዎችን በመለዬት የመፍትሄ እርምጃዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው ተብሏል።መድረኩ እስከ ነገ ነሐሴ 5/2012 እንደሚቀጥልም ታውቋል።
#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ባሕር ዳር ገቡ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት ባሕር ዳር ገብተዋል።ባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በባሕር ዳር በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።