YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ በህንጻ ግንባታ ሰራተኞች ላይ በደረሰ አደጋ ጉዳት ደረሰ!

በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 18፤ 2012 ጠዋት ላይ በደረሰ አደጋ አንድ ሰው ሲሞት በ9 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።በህንጻው ግንባታ ላይ የተሰማሩ 55 ሰራተኞችንም ጉዳት ሳይደረስባቸው በህይወት መትረፋቸውንም አስታውቋል።በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው ይህ ህንጻ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) መገንባት የጀመረ ሲሆን ግንባታው ሲገባደድ ኤጀንሲውን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማትን በውስጡ ይይዛል ተብሎ የሚጠበቅ ነው።

ዛሬ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ገደማ በህንጻው ላይ የደረሰው አደጋ መንስኤ በውጭ ግድግዳ ላይ የተለጠፉ የሴራሚክ ልባሶች መንሸራተት ያስከተለው እንደሆነ አንድ የነፍስ አድን ሰራተኛ ተናግረዋል። የሴራሚክ ልባሶቹ፤ በግንባታ ሰራተኛ መወጣጫዎች (ስካፎሊዲንግ) ላይ በማረፋቸው የመደርመስ አደጋ መከሰቱን እና ጉዳት መድረሱን አክለዋል። በመወጣጫ መደርመስ አደጋው ጽኑ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰራተኞች መካከል አንድ ግለሰብ ሆስፒታል ሲደርስ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አንድ ባለሙያ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ዘጠኝ የግንባታ ሰራተኞች በሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙም አስረድተዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር
@YeneTube @FikerAssefa1