በአዳማ ሲካሄድ የቆየው የደኢህዴን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች መድረክ ተጠናቀቀ ።
በአዲስ አበባ የሚገኙ የደኢህዴን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በአዳማ ያካሄዱት መድረክ ተጠናቋል፡፡አመራሮቹ በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት አስመልክቶ ይፋ በተደረገው ጥናት ላይ ተወያይተዋል፡፡በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጠናዉ ጥናት የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ አለመሆኑም ተብራርቷል፡፡የደኢህዴንና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤ ደኢህዴን የህዝቦችን ጥያቄ በግምት ሳይሆን በእውቀት ላይ ተመስርቶ በጥናት ለመመለስ በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በመነሳት በሀገር ደረጃ አዲስ ልምድ ይዞ የመጣና አማራጭ ሃሳቦችን እያበረከተ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡የክልሉ 2011 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን፤መድረኩ ብሄራዊና ሀገራዊ ማንነትን አጣጥሞ ለመሄድ መግባባት የተፈጠረበት መሆኑ ተገልጿል፡፡ለአራት ቀናት በቆየው በዚህ መድረክ ከክልል አደረጃጀት ጥያቄ በተጨማሪ በወቅታዊ፣ አገራዊ፣ ክልላዊ እና በከተማው የፖለቲካዊና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡በምክክር መድረኩ ከ1 ሺህ በላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የድርጅቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
#Walta
@YeneTube @FikerAssefa

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያስገነባውን የኮቪድ-19 መመርመሪያ ማዕከልን በዛሬው ዕለት አሰመረቀ፡፡
በምረቃ መርኃግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ፣ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ በቀለ እንዲሁም የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሴ ቁናአ ተገኝተዋል፡፡በቀን 1 ሺህ ናሙናዎችን መመርመር እንደሚያስችለው የተገለጸው ማዕከሉ፣ ለኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል ነው የተባለው፡፡
#Walta
@YeneTube @FikerAssefa
በምረቃ መርኃግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ፣ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ በቀለ እንዲሁም የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሴ ቁናአ ተገኝተዋል፡፡በቀን 1 ሺህ ናሙናዎችን መመርመር እንደሚያስችለው የተገለጸው ማዕከሉ፣ ለኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል ነው የተባለው፡፡
#Walta
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ሶስት ወራት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል!
ባለፉት ሶስት ወራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ከኅብረተሰብ ተሳትፎ መገኘቱን የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ።ገቢው የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ከተረጋገጠበት ካለፈው መጋቢት እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።
#Walta
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ሶስት ወራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ከኅብረተሰብ ተሳትፎ መገኘቱን የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ።ገቢው የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ከተረጋገጠበት ካለፈው መጋቢት እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።
#Walta
@YeneTube @FikerAssefa
በሚዲያዎች መሥራት የነበረብንን ሥራ ባለማከናወናችን ችግሮች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል- ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣንና በጀስትስ ፎር ኦል ፒኤፍ ኢትዮጵያ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የሠላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሚዲያዎች ተገርተው ባለመብቀላቸውና ላለፉት ዓመታት መሥራት የነበረብንን ሥራ ባለመሥራታችን በሀገሪቱ የተለያዩ ችግሮች እንዲፈጠሩ ምክንያት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡አቅም ያልተገነባለት ሚዲያ የተለያዩ ችግሮችን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ያነሱት ሚኒስትሯ፣ ነፃ ያልወጣ ሚዲያ ሌሎችን ነፃ ሊያወጣ አይችልም ሲሉም ተናግረዋል፡፡በውይይት መድረኩ የተለያዩ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን፣ የመናገር ነፃነትና ኃላፊነት በኢትዮጵያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሚዲያና የወቅቱ ችግሮቻችን በሚል የተለያዩ ሃሳቦች ቀርቧል፡፡
#Walta
@YeneTube @FikerAssefa1

አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ህልፈትን ተከትሎ የወደመበትን ንብረት መንግስት ሊከፍለው እንደሚገባ ገለፀ!
በሻሸመኔ እና በባቱ ከተሞች በተፈጠረው ክስተት ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ሁለት ሆቴሎቹ ላይ አደጋ የደረሰበት አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ ክስተቱ አስደንጋጭ እንደነበር እና የበርካቶች መተዳደሪያ የነበሩ ሆቴሎች መሆናቸውን ነው የገለጸው፡፡ከተሞቹ ወደ ነበሩበት ለመመለስ በርካታ ዓመታትን ሊፈጅ እንደሚችል የገለፀው ሀይሌ፣ መንግስት ከሚሰራቸው የልማት ስራዎች ጎን ለጎን ጥፋትን መከላከል በሚያስችል መልኩ ቢሰራ እና በተዋረድ ያሉ የመንግስት መዋቅሮች በተጠያቂነት ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡
በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የነበረው ክስተት በርካቶችን ያሳዘነ መሆኑን የገለፀው አትሌት ኃይሌ፤ መንግስት የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብሏል፡፡ በመሆኑም ከሳምንታት በፊት በነበረው ክስተት የወደመበትን ንብረት መንግስት መልሶ ሊከፍለው እንደሚገባም ነው የጠየቀው፡፡ከአርቲስት ሀጫሉ ህልፈተ ጋር ተያይዞ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገራት ሰልፎች ተደርገዋል፡፡ በተለይ በውጭ ሃገራት በአንዳንድ አካባቢዎች የተደረጉ ሰልፎች ኢትዮያዊነትን የማይገልፁ እንደሆነም ነው ኃይሌ የተናገረው፡፡
የተለያዩ ዓላማዎችን አንግበው በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢትዮጵያን ከድህነት ለማውጣት ጥረት እንዲያደርጉም ኃይሌ ጠይቋል፡፡
#Walta
@YeneTube @Fikerassefa1

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ልዩ መልእክተኛ ተቀብለው አነጋገሩ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ልዩ መልእክተኛ የሆኑትን፣ ኒሃል ዴንግ ኒሃልን ዛሬ ከሰዓት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አመለከተ። ውይይታቸውም በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች፣ በተለይም ደግሞ ከኢኮኖሚያዊ ልማት፣ ሰላም እና ደህንነት አኳያ በመተባበር ላይ፣ እንዲሁም ቀጣናዊ የትስስር ጥረቶች ላይ አተኩሯል።