YeneTube
120K subscribers
31.2K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ምንም እንኳ አሜሪካ በኮቪድ-19 የተያዙብኝ ዜጎች 2 ሚሊዮን ተኩል ብቻ ናቸው ብትልም ምናልባት እውነተኛው ቁጥር ከዚህ በብዙ ሊልቅ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

የአሜሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከላዊ መሥሪያ ቤት (ሲዲሲ) እንዳስቀመጠው እውነተኛው ቁጥር አሁን ከሚባለው በአሥር እጥፍ ሊልቅ ይችላል፡፡ይህም ማለት በአሜሪካ በአሁን ሰዓት 20 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል እንደማለት ነው፡፡ይህ መረጃ የወጣው ከአሜሪካ ትልልቅ ግዛቶች አንዷ የሆነችው ቴክሳስ የእንቅስቃሴ ገደብ መላላቱን ለጊዜው እንዲቆይ ከወሰነች በኋላ ነው፡፡ምክንያቱ ደግሞ በቅርብ ቀናት በርካታ ሰዎች በቫይረሱ በመያዛቸው የሆስፒታል አልጋዎች እጥረት ስለገጠመ ነው፡፡

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ፓኪስታን በተጭበረበረ 'መንጃ ፈቃድ' አውሮፕላን ያበረሩ ፓይለቶቿን እያደነች ነው!

የፓኪስታን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ 150 አውሮፕላን አብራሪዎችን መንጃ ፈቃዳቸውን ሰርዞባቸዋል፡፡የፓኪስታን አቪየሽን ሚኒስትር ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ይፋ እንዳደረጉት አብዛኛዎቹ የንግድ አውሮፕላን የሚያበሩ የአውሮፕላን 'ሾፌሮች' የማብረሪያ ፈቃዳቸው የተጭበረበረ ነው፡፡ይህ የማጥራት ዘመቻን የቀሰቀሰው ባለፈው ወር በፓኪስታን 97 ሰዎችን ጭኖ ይበር የነበረ አውሮፕላን ለማረፍ ሲቃረብ በካራቺ መከስከሱን ተከትሎ ነው፡፡በዚህ አደጋ ከ2 ተሳፋሪዎች ውጭ በሙሉ አልቀዋል፡፡የመከስከሱ ምክንያት ሲፈተሸም የአብራሪው ብቃት ማነስ እንደሆነ ተደርሶበታል፡፡

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኒው ዮርክ ከመጋቢት ወዲህ ዝቅተኛ የተባለው የሞት ቁጥር ተመዘገበ!

በአሜሪካ ክፉኛ በቫይረሱ በተጠቃችው ኒው ዮርክ ግዛት ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ሕይወታቸው ማለፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያሳያል፡፡ይህም በሌሎች ግዛቶች ከተመዘገበው የሞት ቁጥር ከሁለት እጥፍ በላይ ነው፡፡ይሁን እንጅ ለወራቶች በአሳዛኝ ዜናዎች ተውጣ በነበረችው ኒው ዮርክ አሁን ላይ የቫይረሱ ሥርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መጥቷል፡፡እሁድ ዕለት የግዛቷ አስተዳዳሪ አንድሪው ኮሞ፤ 5 ሰዎች ብቻ በቫይረሱ መሞታቸውን ጠቅሰው፤ ከመጋቢት ወር ወዲህ የተመዘገበ ዝቅተኛ የሞት ቁጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን ለማቋቋም ነገ ምክክር እንደሚደረግ ተገለጸ!

የትግራይ ክልል የራሱን የምርጫ ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችለው አዋጅ እንዲሁም የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ አዘጋጅቶ ለውይይት ማቅረቡን ቢቢሲ ዘግቧል።በአገሪቱ በዚህ ዓመት ማብቂያ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ ባለው የወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ምርጫው ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዘዋወር ቢወሰንም የትግራይ ክልል ግን ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ እንደወሰነ ማሳወቁ ይታወሳል።በዚህም በክልሉ ለማካሄድ ዕቅድ ከተያዘለት ክልላዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ሁለት የሕግ ረቂቅ ሰነዶች ተዘጋጅተው ነገ ማክሰኞ በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለመወየያያት ቀጠሮ መያዙን ለማወቅ ተችሏል።ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ከሚደረግባቸው ረቂቅ ሰነዶች አንዱ የምርጫና የምርጫ ሥነምግባር ረቂቅ አዋጁ 130 አንቀጾችን የያዘ ነው ተብሏል።ሁለተኛው ሰነድ ደግሞ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምርጫ ኮሚሽን ለማቋቋም ለማደራጀት እንዲሁም ስልጣኑንና ተግባሩን ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ነው። ይህ አዋጅ 33 አንቀጾችን የያዘና 27 ገጾች ያሉት ሰነድ መሆኑን ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ተፈጥሮ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ ከታሠሩት መካከል ሁለት የአሜሪካ ዜጎች በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ!

ሬድዋን አማን እኣነ ዩሱፍ በሽር ተከስቶ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ሁለቱ የአሜሪካ ዜጎች የዋስ መብት ተፈቀደላቸው።የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ተከስቶ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች ቁጥር ከ7ሺህ በላይ መሆኑ ባለስልጣናት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ከእነዚህም መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ሦስት የአሜሪካ ዜጎች ይገኙበታል። የአሜሪካ ዜግነት ካለቸው መካከል ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡት ሬድዋን አማን እና ዩሱፍ በሽር የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሬድዋን አማን እና ዩሱፍ በሽር ነዋሪነታቸው በአሜሪካ አገር የነበረ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ነበር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት።ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሁለቱ ግለሰቦች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው በ6ሺህ ብር የዋስትና መብት ከእስር እንዲወጡ ተወስኗል ብለዋል። ጠበቃው ትናንት ለቢቢሲ ሲናገሩ ደንበኞቻቸው ዓርብ ወይም ቅዳሜ ከእስር ቤት ይወጣሉ ብለውን እንደሚጠበቁ ተናግረዋል።ሦስተኛው የአሜሪካ ዜግነት ያለው እና በእስር ላይ የሚገኘው ግለሰብ ሚሻ ጪሪ የሚባል ሲሆን፤ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ.ኤም.ኤን) ቴክኒሺያን ሆኖ ሲያገለግል ነበር።

ሚሻ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረበት ወቅት በጉዳዩ ላይ የአሜሪካን ኤምባሲን ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት እንዳልተሳካለት ለፍርድ ቤት ተናግሮ ነበር።ትናንት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ላይ ሦስቱም የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች እንቁላል ፍብሪካ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘውን ጊዜያዊ እስር ቤት እንደሚገኙ ጠቅሷል።በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ትናንት በትዊተር ገጹ ላይ “በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካዊያን ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው” ካለ በኋላ፤ አሜሪካውያን በኢትዮጵያ ታስረው ከሆነ በተቻለ ፍጥነት እንደሚጎበኙ እና አስፈላጊው ድጋፍ እና አገልግሎቶች እንደሚያቀርብ ኤምባሲው አስታወቋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የኮሮናቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ 'የመተላለፍ ዕድሉ ዝቅተኛ ነው!'

የኮሮናቫይረስ ላለባቸው እናቶች አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ከተደረገ በወሊድ ጊዜ ወደ ህጻናቱ የመተላለፍ እድሉ ዝቅተኛ ሊሆን እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።አሜሪካ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ሆስፒታሎች ኮሮናቫይረስ ካለባቸው እናቶች ከተወለዱ 120 ህጻናት ውስጥ አንዳቸውም በበሽታው አለመያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ውጤት የተገኘው ህጻናቱ ከተወለዱ በኋላ ባለው ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከተወለዱ ከሁለት ሳምንታት በኋላ አንዳንዶቹ የእናታቸውን ጡት የመጥባት እድል ካገኙና በአንድ ክፍል ውስጥ አብረው ከቆዩ በኋላም ጭምር ነው።ጥናቱን ያደረጉት ባለሙያዎች እንደሚሉት የተገኘው ውጤት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም ተጨማሪ ሰፋ ያለ ሙከራዎች ማድረግ ያስፈልጋል።

በእርግዝናና በጡት ማጥባት ወቅት የበሽታውን ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታን በተመለከተ ያለው መረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ የሚሰጠው ምክርም የተለያየ እንዲሆን አድርጎታል።የዩናይትድ ኪንግደም ሐኪሞች እናቶች ጡት ማጥባት የሚፈልጉ ከሆነ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ተደርጎላቸው ልጆቻቸውን ጡት ማጥባትም ሆነ አንድ ክፍል ውስጥ መሆን ይችላሉ ብለዋል።ባለሙያዎቹም ሆነ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚሉት በኮሮናቫይረስ የመያዝ ስጋት የበለጠ ጡት ማጥባት ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል የቫይረሱን ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ዕድልን ለመቀነስ አዲስ የተወለዱ ህጻናት ለተወሰነ ጊዜ ከእናታቸው ተለይተው እንዲቆዩ የማድረግ ሃሳብን ተግባራዊ ለማድረግ እያሰበ ነው።ኮሮናቫይረስ ያለባት እናት ከወለደችው ልጅ ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ እንድትቆይ የሚደረግና ጡት እንድታጠባ የሚፈቀድላት ከሆነ፤ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንድትጠቀምና በተደጋጋሚ እጇን መታጠብ እንደሚኖርባት በጥናቱ ተመልክቷል።ጥናቱን የመሩት ዶክተር ክርስቲን ሳልቫቶሬ እንዳሉት "ጥናታችን ወረርሽኙ ያለባቸው እመጫት እናቶች ቫይረሱን ወደ ልጃቸው የማስተላለፍ ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።ነገር ግን ሁኔታውን የበለጠ ለመረዳት አሁንም ሰፋ ያለ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል" ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ በዩናይትድ ኪንግደም የተደረገ ቅኝትን የመሩት ፕሮፌሰር ማሪያን ናይት እንደገለጹት ጥናቱ በአገሪቱ ያለውን መመሪያ የሚደግፍና የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።ጨምረውም "በዩናይትድ ኪንግደም ከአንድ ሺህ በላይ ኮቪድ-19 ያለባቸው እናቶች የወለዱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ከ1 እስከ 2 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ላይ ብቻ ነው ቫይረሱ የተገኘው። በሽታውም በህጻናቱ ላይ የከፋ ህመምን አላስከተለም።"በአሜሪካ የተደረገው አነስ ያለ ጥናትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምበል መጠቀመን የመሰሉ ቀላል የጥንቃቄ እርምጃ በመውሰድ የኮሮናቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታ እንዳይከሰት ማድረግ መቻሉን ፕሮፌሰሯ ጠቅሰዋል።የጥናቱ ውጤት የህጻናትና የአዋቂዎች ጤና ጉዳይ ላይ በሚያተኩረው የላንሴት የህክምና ሙያዊ መጽሔት ላይ ታትሟል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ-መንበር የሆኑት የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌዴሬል ፖሊስ መከበቡን የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዳ ኦልጅራ ለቢቢሲ ተናገሩ።

አቶ ገዳ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት አካባቢ የሚገኘው የጸጥታ ኃይል የሊቀመንበሩን ደኅንነት ለመጠበቅ መሰማራቱን ከፖሊስ መስማታቸውንም ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት መከበብን ለቢቢሲ ያረጋገጡት አቶ ገዳ የታጠቁ ኃይሎች በመኖሪያ ቤቱ ዙሪያ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።ኃላፊው፤ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖሪያ ቤታቸው መውጣትና መግባት እንዳልቻሉና ወደ ውጪ የሚወጡ ከሆነም በጸጥታ ኃይሎቹ በቁጥጥር ሥር ሊውሉ እንደሚችሉ ስጋተቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የግንባሩ ለቀ መንበር አቶ ዳውድ ከሦስት ቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ከአንድ ቀን በኋላ መፈታታቸውን አቶ ገዳ ገልጸዋል።"ዋና ሊቀመንበራችን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ነው ያሉት።እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው የዕለተ ዕለት ሥራቸውን ማከናወን አልቻሉም" ሲሉ አቶ ዳውድ ከቤታቸው መውጣት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።አቶ ገዳ እንደሚሉት አቶ ዳውድ ብቻ ሳይሆኑ በቤታቸው ውስጥ ያሉ የቤተሰባቸው አባላትም ከመኖሪያ ግቢው መውጣትናም ሆነ ከውጪ መግባት ተከልክለዋል።

አቶ ገዳ ካሉት የእንቅስቃሴ ገደብ በተጨማሪ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ስልክ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ እየሠራ አይደለም።የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት ለምን እንደተከበበ የሚያውቁት ነገር አለ ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ገዳ፤ ፖሊስ ይህን ያደረገው ለእሳቸው [አቶ ዳውድ] ደኅንነት ሲባል እንደሆነ ተነግሮኛል ይላሉ።ይሁን እንጂ "ሰው እንዳይገባና እንዳይወጣ እየከለከሉ ደኅንነት ለመጠበቅ አይመስልም" ይላሉ። "የአቶ ዳውድ ስልክ ስለማይሰራ ከራሳቸው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት አልቻልንም" ሲሉ ከሊቀመንበሩ ጋር መገናኘት አዳጋች እንደሆነባቸው ገልጸዋል።

ቢቢሲም ወደ አቶ ዳውድ ኢብሳ የሞባይል ስልክ ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ በተደጋጋሚ በመደወል ሊያገኛቸው ጥረት ባደረገበት ጊዜ ማግኘት እንደማይቻል እንዲሁም የኔትወርክ መጨናነቅ እንዳለ መልዕክት ብቻ ነበር የሚሰማው።ሁኔታውን ለማጣራት ቢቢሲ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጄይላን አብዲ የተየቀ ሲሆን እሳቸውም ስለጉዳዩ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው የሚታወስ ሲሆን አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባላትም በእስር ላይ ይገኛሉ።ከእነሱም መካከል የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አቶ ሚካኤል ቦረን፣ አቶ ኬነሳ አያና፣ የፓርቲው አማካሪ ዶክተር ሽጉጥ ገለታና ኮሎኔል ገመቹ አያና በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቀደም ሲል ፓርቲው አሳውቋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በኮሮናቫይረስ መያዙ የተጠረጠረው የመጀመሪያው ሰሜን ኮሪያዊ ነጻ መሆንኑን በምርመራ ማረጋገጧን ደቡብ ኮሪያ ገለፀች።

ግለሰቡ ከሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ ኮሪያ ከሦስት ዓመታት በፊት መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ግን ወደ ትውልድ አገሩ ተመልሶ ነበር።ግለሰቡ ከደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ የተሻገረው በደቡባዊ ደሴቲ አካባቢ በሚገኝ የቱቦ ማስተላለፊያ ውስጥ በመሹለከለክና በመዋኘት ነበር።ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ሰሜን ኮሪያ በኮቪድ-19 የተጠረጠረ ሰው ማግኘቷን አሳውቃ ነበር።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ትራምፕ ምርጫው እንዲዘገይ ጠየቁ!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዘንድሮው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲዘገይ ጥያቄ አቀረቡ።ፕሬዘዳንቱ ጥያቄውን ያቀረቡት በፖስታ የሚላኩ ድምጾች ላይ መጭበርበር መኖሩን የሚያሳይ መረጃ መኖሩን በማጣቀስ ቢሆንም፤ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ማስረጃ የለም።የአሜሪካ ግዛቶች በፖስታ ድምጽ እንዲሰጥ የሚፈልጉት ማኅበረሰቡን ለኮቪድ-19 ላለማጋለጥ ነው።ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው፤ በፖስታ ድምጽ ቢሰጥ “በታሪካችን እጅግ የተሳሳተ እና የተጭበረበረ ምርጫ ይሆናል” ብለዋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በቤንሻንጉል ጉሙዙ ጥቃት የተጠረጠሩ 20 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

ሐምሌ 20/2012 በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጥቃት የፈጸሙ 20 ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱላዚዝ መሃመድ በተለይ ለቢቢሲ እንደገለጹት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ትናንት ነው።እንደ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ከሆነ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ከመፈጸማቸው በፊት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል እርምጃ እየወሰደባቸው ነበር።እርምጃውን ተከትሎ ተበታትነው በመንቀሳቀስ 13 ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ጠቁመዋል።

ከጥቃቱ በኋላ በተደረገ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ 20 ሰዎች ትናንት መያዛቸውን አቶ አብዱላዚዝ አስታውቀዋል።ግለሰቦቹ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 12 መሣሪያዎችም መያዙን ነው የተናገሩት። በአሁኑ ጊዜ አካባቢው ወደ ሠላማዊ ሁኔታ መመለሱን የገለጹት አቶ አብዱላዚዝ የክልሉን የሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊን እና የክልሉን የፖሊስ ኮሚሽነር ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችም ወደ ቦታው በማቅናት ሕዝብን የማራጋጋት እና ችግር ፈጣሪዎቸን በቁጥጥር ስር እያዋሉ ነው ብለዋል።በጥቃቱ ላይ የተሳተፉ ሁሉም ተጠርጣሪዎች ስለመያዘቸው በተመለከተም፤ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ እየሠራ መሆኑን ተናግረው በውጤቱ መሠረት ተጨማሪ ሰዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ ይችላሉ ብለዋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የዚምባብዌ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው አለፈ!

የዚምባብዌ የግብርና ሚኒስትር ፔሬንስ ሺሪ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ገልፀዋል።ሚኒስትሩ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው የተረጋገጠው በምርመራ መሆኑንም የአገሪቱ መንግሥታዊ ጋዜጣ ሄራልድ ፕሬዚዳንቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።ሚኒስትሩ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት በሚያዘው በኮሮናቫይረስ ለሞቱ ሰዎች የሚደረገው የቀብር ስነ ስርዓት መመሪያ መሰረት በነገው እለት እንደሚቀበሩም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።የ65 አመቱ ሚኒስትር በመዲናዋ ሃራሬ በሚገኝ የግል ሆስፒታል ረቡዕ እለት ሕይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ በርካታ ክልሉ የልዩ ኃይል አባላትና ታጣቂ ሚሊሻዎች በዛሬው ዕለት ወታደራዊ ሰልፍ በማካሄድ ትዕይንት አድርገዋል።

በሰልፉ ላይ የተሳፉት የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላቱ ቀላልና ከባድ የጦር መሳርያዎችን ታጥቀው መታየታቸውን የቢበሲ ዘጋቢ ከመቀለ ገልጿል።ዛሬ ረፋድ ላይ በክልሉ ዋና ከተማ በመቀለ ጎዳናዎች ላይ በሰልፍ ሲጓዙ የታዩት ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱት የልዩ ኃይሉ አባላትና ሚሊሻዎች በከተማው ወደሚገኘው ስታድየም በመጓዝ ተሰብስበው ታይተዋል።በመቀለ ከተደረገው ከዚህ ወታደራዊ የሰልፍ ትዕይንት ባሻገር በሌሎችም የክልሉ ከተሞች ጭምር መደረጉ ለማወቅ ተችሏል።ቢሆንም ይህ ዛሬ የተካሄደው ወታደራዊ ሰልፍ ዓላማው ምን እንደሆነ የትግራይ ክልል መንግሥት የገለጸው ነገር የለም።ነገር ግን የትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ ፌስቡክ ገጹ ላይ "ለሰላም ሲባል ለሚከፈል ዋጋ ሁሌም ዝግጁ ነን" የሚል መልዕክት አስፍሯል።ቢሮው አክሎም "የአንድ ሕዝብ የሰላሙ ዋስትና ውስጣዊ አቅሙ እንጂ የማንም የውጭ ኃይል ድጋፍና ጥበቃ ሆኖ አያውቅም" ሲል ገልጿል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ኢራን በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥርን ማሳነሷን አንድ ሾልኮ የወጣ መረጃ አጋለጠ!

በኢራን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር መንግሥት በይፋ ከገለጸው በሶስት እጥፋ እንደሚበልጥ የቢቢሲ ፐርሺያ ምርመራ አረጋገጠ።ለህዝብ ይፋ ያልሆነ የኢራን መንግሥት አሃዝ የሚያሳየው በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 42ሺህ የሚጠጋ ነው። ይሁን እንጂ የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር እስካሁን በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 14ሺህ 405 ነው ይላል።ይህም ብቻ ሳይሆን ከኢራን መንግሥት የተገኘው መረጃ በቫይረሱ ስለመያዛቸው በይፋ የተነገረው ቁጥር በግማሽ እንዲቀንስ መደረጉን አመልክቷል።

ጤና ሚንስቴር እስካሁን በቫይረሱ ተይዘዋል ያላቸው ሰዎች ቁጥር 278 ሺህ 827 ነው። ይሁን እንጂ የአገሪቱ መንግሥት 451ሺህ 024 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጧል። የኢራን መንግሥት በቫይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥርን ከማሳነሱም በተጨማሪ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወት ማለፍ ከጀመረ ከአንድ ወር በኋላ ነበር የአገሪቱ የጤና ሚንስቴር በቫይረሱ ሳቢያ የሰው ህይወት ማለፉን ሪፖርት ያደረገው።ይህ መረጃ እንዳረጋገጠው፤ መንግሥት የመጀመሪያውን ሟች ይፋ በሚያደርግበት ወቅት 52 ሰዎች ቀድመው በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

ማንነቱ ይፋ ያልሆነው ምንጭ ለቢቢሲ የላከው መረጃ በመላው ኢራን በየዕለቱ በኮቪድ-19 ተይዘው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎችን ዝርዝር መረጃ የያዘ ነበር።ሥም፣ እድሜ፣ ጾታ፣ ታማሚው የሚታይበት ምልክት፣ ቀን እና ተጠቂው የተጓዳኝ በሽታ ታማሚ ስለመሆኑ እና ሌሎች መረጃዎች ተካተውበታል። መረጃውን ለቢቢሲ የላከው ምንጭ “እውነቱ መታወቅ ስላለበት” እና “በወረርሽኙ የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት የሚደረገው ጥረት መቆም አለበት” በሚሉ ምክንያቶች መረጃውን ለቢቢሲ ለማጋራት መወሰኑ ተመልክቷል።ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡ የኢራን የጤና ባለሙያዎች እንዳሉት የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር በኢራን መንግሥት የደህንነት አገልግሎት ጫና ይደረግበታል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የዩኬ ዜጎች ከወትሮው በግማሽ ባነሰ ዋጋ ምግብ ሊበሉ ነው!

ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ያሉ የምግብ ቤት ተጠቃሚዎች ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ከወትሮው ዋጋ ሃምስ በመቶ ቅናሽ ይደረግላቸዋል። ግማሹን ወጭ መንግሥት የሚሸፍን ሲሆን ዓላማውም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ አቅማቸው የተዳከመ ምግብ ቤቶችን መደገፍ ነው። የመንግሥት ድጎማ ተግባራዊ የሚሆንባቸው ከ72 ሺህ በላይ ምግብ ቤቶች ሲሆኑ ድጎማው ለአንድ ወር የሚቆይ ነው።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ራማፎሳ ለኮቪድ-19 የተመደበ በጀትን የሚመዘብሩ ግለሰቦችን አስጠነቀቁ!

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለኮሮናቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር የተመደበን የሕዝብ ሃብት በሚበዘብዙና “ጅቦች” ሲሉ የጠሯቸው ግለሰቦች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠነቀቁ።ይህ የፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ ትኩረቱን ያደረገው የመንግሥት ኃብትን በሚመዘብሩ ባለስልጣናት፣ በኮሮናቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎችና፣ የእርዳታ ምግብን በድብቅ የሚያከማቹ የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ላይ ነው።“በየእለቱ የዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ካለው ቀውስ ለማትረፍ መጣር የጥንብ አንሳ ባህሪ ነው። ልክ የተጎዳውን ሰለባውን እንደሚከብ ጅብ መሆን ነው” ብለዋል ፕሬዝዳንት ራማፎሳ።“ግለሰቦች እና ድርጅቶች ያለምንም ርህራሄ በዘረፋ መሰማራታቸውን አስተውለናል” ሲሉም አክለዋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ቦይንግ 737 ማክስ በድጋሚ ለመብረር ተቃርቧል ተባለ!

የፌደራል አቪየሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ)ም እንዲሁ አውሮፕላኑ ዳግም ወደ በረራ ከመግባቱ በፊት ማሟላት ያለበትን ዝርዝር ነገሮች ማቅረቡ ተሰምቷል።737 ማክስ ሁለት አውሮፕላኖች ተከስክሰው የ346 ሰዎች ህይወት ከጠፋ በኋላ ከበረራ ከታገደ ከአንድ አመት በላይ ሆኖታል።አውሮፕላኑ ሙሉ ሙሉ ከበረራ የታገደው በጎርጎሳውያኑ መጋቢት ወር 2019 ዓ.ም ነበር።ቦይንግ 737 ማክስ እንዲያሟላ የተጠየቀውን ዝርዝር ነገሮች አሟልቶ በጎርጎሳውያኑ አዲስ አመት ዳግም ወደ በረራ ለመመለስ አቅዷል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
አልጀሪያ መስጊዶችን ልትከፍት ነው!

የአልጀሪያ ፕሬዚዳንት አብደልማድጂድ ቴቡን መስጊዶች ቀስ በቀስ የሚከፈትበቱን ሁኔታ እንዲያጠኑ ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን አዘዙ።ከፍተኛ የፀጥታ አካካላት ስብሰባ ላይ ነው ፕሬዚዳንቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብደላዚዝ ድጀራድን ከአንድ ሺህ ሰዎች በላይ ሰዎች መያዝ የሚችሉ ትልልቅ መስጊዶች ላይ እንዲያተኩሩም ነግረዋቸዋል።ፕሬዚዳንቱ ትልልቅ መስጊዶችን የመረጡበት ምክንያትም ሲያስረዱ " አስፈላጊ የሚባለውን አካላዊ ርቀት መጠበቅ ስለሚያስችሉ" ነው ብለዋል።የፊት ጭምብል ማድረግ ግዴታ ነው ተብሏል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በቼክ ሪፐብሊክ በአንድ ሕንፃ ላይ በተነሳ እሳት 11 ሰዎች ሞቱ !

በቼክ ሪፐብሊክ በአንድ ሕንፃ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ሦስት ህፃናትን ጨምሮ 11 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ።ከሟቾቹ መካከል ስድስቱ በእሳቱ የሞቱ ሲሆን አምስቱ ከአደጋው ለማምለጥ ከ11ኛ ፎቅ ከዘለሉ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።ከዚህም በተጨማሪ ሁለት የእሳት አደጋ ሰራተኞችንና አንድ ፖሊስን ጨምሮ አስር ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።በሰሜን ምስራቅ ከተማ ቦሁሚን ቅዳሜ ዕለት በአንድ ሕንፃ ላይ ከነበረ ክፍል የተነሳው ይህ የእሳት አደጋ በአገሪቷ ታሪክ የተከሰተ አስከፊ አደጋ ነው ተብሏል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የሊባኖስ መንግሥት ሥልጣን ለቀቀ!

ባለፈው ማክሰኞ በዋና ከተማዋ ቤይሩት ውስጥ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የሊባኖስ መንግሥት በገዛ ፈቃዱ ሥልጣን ለቋል።ከ200 በላይ ሰዎች ለሞት የተዳረጉበት በሊባኖስ ቤይሩት በሚገኝ ወደብ ላይ የደረሰው ፍንዳታን ተከትሎ ፀረ-መንግሥት ተቃውሞዎች ተፋፍመው ነበር።ሰኞ አመሻሽ ላይ ነው ገዢው የሊባኖስ መንግሥት ሥልጣን መልቀቁን በቴሌቪዥን መስኮት ያሳወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዲያብ ናቸው።በርካታ ሊባኖሳዊያን ለፍንዳታው የገዢው ፓርቲ አመራሮችን ይወቅሳሉ፤ በሙስና ተጠምደው ረስተውናልም ይላሉ።ቤይሩትን ያናወጠው ፍንዳታ የተከሰተው 2750 ቶን የሚመዝን አሞኒዬም ናይትሬት የተባለ ንጥረ ነገር ጥንቃቄ በጎደለው መንገድ ለበርካታ ዓመታት በመከማቸቱ ነው።ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በደረሰው ፍንዳታ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 220 መድረሱንና 110 ሰዎች ደግሞ የገቡበት እንደማይታወቅ የቤይሩት ከተማ ከንቲባ ማርዋን አቡድ አል-ማርሳድ ለተሰኘው የዜና ምንጭ ተናግረዋል።

በርካታ የውጭ አገር ዜጎችና የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች የገቡበት ካልታወቁ ሰዎች መካከል ናቸው ብለዋል ከንቲባው።በፍንዳታው ሳቢያ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ቤት አልባ ሆነዋል፤ የቀሩትም በርና መስኮቶቻቸውም ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።ፍንዳታውን ተከትሎ ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ ሰልፈኞች የቤይሩትን መንገዶች አጨናንቀዋል፤ ፖሊስም ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጭስ ለመበተን ሞክሯል።ሊባኖሳዊያን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ሲያሰሙ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ፀረ-መንግሥት ተቃውሞዎች ለዓመታት የዘለቁ ናቸው።አገሪቱ በምጣኔ ሃብት ድቀት መመታቷ ሳያንስ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ኑሮ መቀዛቀዙ ለሊባኖሳዊያን ፈተና ሆኗል።ነገር ግን የዕለተ ማክሰኞው ፍንዳታ ብዙዎች ጣታቸውን መንግሥት ላይ እንዲቀስሩና ለተቃውሞ ወደ አደባባይ እንዲወጡ አድርጓቸዋል።አሁን ያለው የሊባኖስ መንግሥት ባለፈው ዓመት በአገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ሥልጣን የለቀቀውን መንግሥት ተከትሎ ወንበር የጨበጠ ነበር።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በትግራይ መራጮችን ለመመዝገብ የሞባይል መተግበሪያ ጥቅም ላይ ይውላል ተባለ!

በትግራይ መራጮችን ለመመዝገብ የሞባይል መተግበሪያ ጥቅም ላይ ይውላል ተባለ።ይህ መተግበሪያ ለመጀመርያ ጊዜ ትናንት በመቀለ ከተማ ሙከራ ተደርጎበታል ተብሏል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa