ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.82K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ስለቤተ #መቅደስ ሁኔታ #ሙሴ ከሰራው #ከማደሪያ #ድንኳን ጀምሮ #ማደሪያ ድንኳኑ 3 #ክፍሎች <ቅድስተ ቅዱሳን>፣ <ቅድስት>፣ እና <አደባባይ> ነበሩት {ዘጸ 26፥33} #በቅድስተ #ቅዱሳኑ ውስጥ #ታቦት ብቻ ነበር። #ታቦቱም #ሳጥን የሚመስል ሲሆን በውስጡ #አስርቱ ቃላት (ትእዛዛት) የተጻፈባቸውን 2 #ጽላት#መና ያለበት #የወርቅ #መሶብ #የአሮን #በትር ይዞ ነበር {ዕብ 9፤ 2-4}። #የታቦቱ ርዝመት 2 #ክንድ ተኩል ወይም 1 #ክንድ ተኩል ቁመቱ 1 ክንድ ተኩል ነበር። በውስጥና በውጭ በጥሩ #ወርቅ #የተለበጠ በእርሱም ዙሪያ #የወርቅ #አክሊል የተደረገለትና በጎንና #በጎኑ በግርጌ በኩል #የመሸከሚያ #መሎጊያ የሚገባባቸው 4 #ቀለበቶች ነበሩት {ዘጸ 25፤ 10-11}።

▶️ በማደሪያው #ድንኳኑ 2ኛ ክፍል በሆነው #በቅድስት ውስጥ ደግሞ #በስተግራ #ከወርቅ የተሰራ መቅረዝ {ዘጸ 25፥30፣ 40} #በስተቀኝ ለመገኘቱ #ህብስት {ህብስተ-ገጽ} የሚሆን #ገበታ {ዘጸ 25፤ 23-30} እንዲሁም ፊት ለፊት #በመጋረጃው ስር #የዕጣን #መሰዊያ (የወርቅ መሰዊያ) ነበር {ዘጸ 30፥1፣ 3-4}።

▶️ በ3ኛው ክፍል (በአደባባዩ) ደግሞ #የመታጠቢያ ሰን (ሳህን) እና #የናስ #መሰዊያ #ብቻ ነበር {ዘጸ 30፤ 17-18፣ ዘዳ 27፤ 1-8}።
▶️ ወደ #ቅድስተ #ቅዱሳኑ (ቤተ መቅደሱ) ውስጠኛ #ክፍል ለአገልግሎቱ የሚገባው #ሊቀ ካህኑ ብቻ ሆኖ #በአመት 1 ቀን እርሱም #በማስተሰርያ ቀን #ስለራሱና #ስለህዝቡ #መስዋዕትን ይዞ #በእግዚአብሄር ፊት ይቆማል {ዘጸ 28}። #የሊቀ ካህኑ ልብሰ #ተክህኖ #በ4 #ቀለማት ማለትም #ከነጭ#ከሰማያዊ#ከሐምራዊና #ከቀይ #በፍታ #በወርቅ የተለጠፈ ነበር {ዘጸ 28}። የላይኛው አላባሽ #ኤፉድ ሲባል {ዘጸ 39፥2} #በቀኝና #በግራ ትከሻው ላይ ሁለት የመረግድ #ድንጋዮች ነበሩት። በእነዚህ #ሁለት የከበሩ #ድንጋዮች በእያንዳንዱ ላይ #የ6 ነገድ #ስም በሁለቱም ላይ #የ12ቱ ነገደ #እስራኤል ስም #ተቀርጾባቸዋል {ዘጸ 28፥9 እና 12}። በእነርሱም አማካኝነት #ሊቀ ካህኑ #የህዝቡን #ስም በአጠቃላይ በትከሻው ይሸከማል። #የደረት ኪሱ #አራት ማዕዘን ያለው ሆኖ #በወርቅ ጥልፍ የተሰራ #የ12 ነገድ #ስም የተቀረጸባቸው #የሚያንጸባርቁ #የከበሩ #ድንጋዮች እንደ #ፈርጥ ሆነው የተሰሩ ናቸው {ዘጸ 28፥29}። #የደረት ኪሱ ታጥፎ የተደረበ ነው በውስጣቸው #ኡሪምና #ቱሚም ይይዛሉ {ዘጸ 28፥30}። #ቀሚሱ ሙሉ በሙሉ #ሰማያዊ ሲሆን በታችኛውም ዘርፍ ዙሪያ #በ3 #ቀለም የተሰራ #የሮማን ፍሬ #ቅርጽ #ከወርቅ #ሻኩራ ጋር ተሰባጥሮ ይደረግበታል። የሻኩራዎቹ #ድምጽ #ለቀሚሱ ውበትን ይሰጠዋል። #ጥምጥሙ ደግሞ #ካህኑ በራሱ ላይ የሚጠመጥመው ሲሆን ከጥሩ #በፍታ የተሰራ ነው <<ቅድስና ለእግዚአብሔር>> የሚል ጽሑፍ #ከወርቅ በተሰራ #ዝርግ #ጌጥ ላይ ተቀርጾ በዚህ #ጥምጥም ላይ #ይንጠለጠልበታል {ዘጸ 28፥36}።