▶️ ስለቤተ #መቅደስ ሁኔታ #ሙሴ ከሰራው #ከማደሪያ #ድንኳን ጀምሮ #ማደሪያ ድንኳኑ 3 #ክፍሎች <ቅድስተ ቅዱሳን>፣ <ቅድስት>፣ እና <አደባባይ> ነበሩት {ዘጸ 26፥33} #በቅድስተ #ቅዱሳኑ ውስጥ #ታቦት ብቻ ነበር። #ታቦቱም #ሳጥን የሚመስል ሲሆን በውስጡ #አስርቱ ቃላት (ትእዛዛት) የተጻፈባቸውን 2 #ጽላት፣ #መና ያለበት #የወርቅ #መሶብ #የአሮን #በትር ይዞ ነበር {ዕብ 9፤ 2-4}። #የታቦቱ ርዝመት 2 #ክንድ ተኩል ወይም 1 #ክንድ ተኩል ቁመቱ 1 ክንድ ተኩል ነበር። በውስጥና በውጭ በጥሩ #ወርቅ #የተለበጠ በእርሱም ዙሪያ #የወርቅ #አክሊል የተደረገለትና በጎንና #በጎኑ በግርጌ በኩል #የመሸከሚያ #መሎጊያ የሚገባባቸው 4 #ቀለበቶች ነበሩት {ዘጸ 25፤ 10-11}።
▶️ በማደሪያው #ድንኳኑ 2ኛ ክፍል በሆነው #በቅድስት ውስጥ ደግሞ #በስተግራ #ከወርቅ የተሰራ መቅረዝ {ዘጸ 25፥30፣ 40} #በስተቀኝ ለመገኘቱ #ህብስት {ህብስተ-ገጽ} የሚሆን #ገበታ {ዘጸ 25፤ 23-30} እንዲሁም ፊት ለፊት #በመጋረጃው ስር #የዕጣን #መሰዊያ (የወርቅ መሰዊያ) ነበር {ዘጸ 30፥1፣ 3-4}።
▶️ በ3ኛው ክፍል (በአደባባዩ) ደግሞ #የመታጠቢያ ሰን (ሳህን) እና #የናስ #መሰዊያ #ብቻ ነበር {ዘጸ 30፤ 17-18፣ ዘዳ 27፤ 1-8}።

Forwarded from እውነት አርነት ያወጣል (ቴዎድሮስ)
በሚል ሐሳቡን ያጠናክራል (4፡51-5፡03 ደቂቃ)፡፡
ዲያቆኑ የቃላት ፍቺ ሲሠራ (‹‹…በትርጕሙ ላይ እንደተረዳነው…›› ብሏልና) በየትኛው መዝገበ ቃላት መሠረት ትርጓሜውን እንደሠራ (ትርጕሙን ከየት እንዳገኘው) አለመናገሩን ላስተዋለ አድማጭ ለራስ አስተምህሮ እንዲመች በሚል የቀረበ የግል አተያይ እንጂ እውነታን መሠረት ያደረገ ትርጓሜ አለመሆኑን ለመረዳት አይቸገርም፡፡ ታቦት እና ጽላት በተመለከተ ትክክለኛ ፍቺአቸውን ስንመለከት ዲያቆኑ ምን ነካው? ማስባሉ ግልጽ ነው፡፡
ታቦት፡- ደስታ ተክለ ወልድ ያዘጋጁት ‹‹ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት›› ታቦት ለሚለው ቃል ከሰጠው ፍቺዎች መካከል በመጀመሪያ የሚገኘው የሚከተለው ነው፤ ‹‹ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶች በውስጧ ያሉባት ሣጥን በወርቅ የተለበጠች፤ ጽላቱ ከእብነ በረድ ታቦቲቱ ከማይነቅዝ እንጨት ነው የተቀረጹት፤ ሁሉም የሙሴ ሥራዎች ናቸው፡፡ #ጽላት_እንደ_መጽሐፍ_ታቦት_እንደ_ማኅደር (ኢያሱ 3÷14፡17)›› (ደስታ ተክለ ወልድ፣ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት (1962) ገጽ 1250)፡፡
ጽላት፡- አሁንም ከደስታ ተክለ ወልድ መዝገበ ቃላት ሳንወጣ ጽላት ለሚለው ቃል ፍቺ ስንፈልግ ‹‹ከእብነ በረድ የተቀረጸ በላዩ ዐሥር የግዜር ቃል (ሕግ ትእዛዝ) የተጻፈበት ታቦት በሚባል ሣጥን የሚከተት ሁለት ገበታ፤ በግእዝ አንዱ ጽሌ ሁለቱ ጽላት ይባላል፤ ትርጓሜው መጸለያ ጸሎት ማቅረቢያ ማለት ነው፡፡…›› የሚለውን እናገኛለን (ደስታ ተክለ ወልድ፣ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት (1962) ገጽ 1018-1019)፡፡
ዓባይነህም በዚያው ስብከቱ ላይ ታቦትና ጽላት ሁለት የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውነ ከዚህ በታች በሚከተሉት መልኩ ተናግሮ ነበር፤ ‹‹በመጀመሪያ ታቦት የሚለው ቃል ማኅደር ማለት ሲሆን ይህም የእግዚእብሔር የጽላቱ ማደሪያ [በ]መሆኑ የተሰጠው ስያሜ ነው›› (1፡54-2፡08)፡፡ በዚህ በዲያቆን ዓባይነህ ሐሳብ መሠረት ታቦት የጽላት ማደሪያ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳብ ነው፡፡ ቀደም ሲል የቀረበው የቃላት ትርጓሜ እግዚአብሔር ተሠርቶ ማየት የፈለገው የታቦትንና የጽላትን ይዘት በሚገባ የሚያሳይ ነው፡፡ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ታቦት ነው የያዝኩት ካለ (ዓባይነህ‹‹እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የምንነጋገርበት ርዕሳችን ታቦት የሚል ይሆናል›› ማለቱን ልብ ይበሉ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ካለ እንደ ፈቃዱ ስለተሠራው ታቦት ማስተማር ነበረበት) መጽሐፍ ቅዱስ የሚያውቀው ታቦት ቀደም ሲል የቀበረውን ይዘት የያዘ ነውና እሱን ነው መያዝ ያለበት፤ እሱም በዘመነ ዐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል የሚለውን ልብን በሚያሳርፍ ሁኔታ መመለስ ከቻለ፡፡
መጽሐፍ ቅዱሳዊው ታቦትና ጽላት ሁለት የተለያዩ ነገሮች ሆነው ግን አንድ ላይ የሚያገለግሉ ከሆነ እነዓባይነህ አንዱን በአንዱ ውስጥ ማዋዋጥ ለምን ፈለጉ? መልሱ ግልጽ ነው፡፡ አንዱን መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ታቦት ለመሥራት መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ወርቅ ይጠይቃል፤ ውስጡም ውጩም በወርቅ የተለበጠ ነውና፡፡ ይህ ደግሞ አሁን እኛ ለቊጥርና ለቈጣሪ እስከሚያክት ድረስ በየመንደሩ ለደረደርነው ‹‹ታቦት›› ተብዬ ቁሳቁስ ወርቅ በቀላሉ ማግኘት እንደማንችል ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አሁን አሁን ታቦት የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ነገሮች ማንም ሰው በቀላሉ አንሥቶ ከቦታ ቦታ ሊያንቀሳቅሳቸው የሚችላቸው ሲሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊው ታቦት ግን ከቦታ ወደ ቦታ መጓጓዝ ካስፈለገው ከአንድ ሰው በላይ (ዐራት ሰዎች) ያስፈልጋሉ፡፡ ይህም ሌላው ችግር በመሆኑ መጠኑን ቀነስ መልኩንም ቀይር በማድረግ ስሙን ግን ማወራርስ አስፈልጓል፡፡ ከዚህ እንደምንረዳው ዓባይነህ ሊነግረን የፈለገው እንደ ችግኝ በየቦታው ስለፈላው ስመ ታቦትን ስለተሸከመው ቁስ እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለውን ታቦት አለመሆኑን ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡
ኢያሱ ‹‹በታቦቱ ፊት›› የተደፋው በታቦቱ ላይ አልፋና ዖሜጋ ስለተጻፈ ነው!?
ይቀጥላል…
https://tttttt.me/tewoderosdemelash/659?single

Telegram
ቴዎድሮስ ደመላሽ
በእንተ ታቦት
ክፍል 3
ከዚህ ቀደም ሲል ታቦትን በተመለከተ እንደ መግቢያ ሊሆን የሚችል ነገር መቅረቡ ይታወሳል፤ ከአሁን ጀምሮ ደግሞ ዓባይነህ ካሤ ‹‹ታቦት›› በሚል ርዕስ ያቀረበውን ስብከት (ይህን ጽሑፍ ከማንበባችሁ በፊት ስብከቱን አውርዳችሁ ብትመለከቱት ጥሩ ይሆናል፡፡ ሚዛናዊ ለመሆን ይረዳችኋልና) እንመለከታለን፡፡ ከስብከቱ ላይ ሐሳብ ሲወሰድ በተቻለ አቅም ቃል በቃል ለመውሰድ ጥረት ተደርጓል፡፡…