ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ወደ #ቅድስተ #ቅዱሳኑ (ቤተ መቅደሱ) ውስጠኛ #ክፍል ለአገልግሎቱ የሚገባው #ሊቀ ካህኑ ብቻ ሆኖ #በአመት 1 ቀን እርሱም #በማስተሰርያ ቀን #ስለራሱና #ስለህዝቡ #መስዋዕትን ይዞ #በእግዚአብሄር ፊት ይቆማል {ዘጸ 28}። #የሊቀ ካህኑ ልብሰ #ተክህኖ #በ4 #ቀለማት ማለትም #ከነጭ#ከሰማያዊ#ከሐምራዊና #ከቀይ #በፍታ #በወርቅ የተለጠፈ ነበር {ዘጸ 28}። የላይኛው አላባሽ #ኤፉድ ሲባል {ዘጸ 39፥2} #በቀኝና #በግራ ትከሻው ላይ ሁለት የመረግድ #ድንጋዮች ነበሩት። በእነዚህ #ሁለት የከበሩ #ድንጋዮች በእያንዳንዱ ላይ #የ6 ነገድ #ስም በሁለቱም ላይ #የ12ቱ ነገደ #እስራኤል ስም #ተቀርጾባቸዋል {ዘጸ 28፥9 እና 12}። በእነርሱም አማካኝነት #ሊቀ ካህኑ #የህዝቡን #ስም በአጠቃላይ በትከሻው ይሸከማል። #የደረት ኪሱ #አራት ማዕዘን ያለው ሆኖ #በወርቅ ጥልፍ የተሰራ #የ12 ነገድ #ስም የተቀረጸባቸው #የሚያንጸባርቁ #የከበሩ #ድንጋዮች እንደ #ፈርጥ ሆነው የተሰሩ ናቸው {ዘጸ 28፥29}። #የደረት ኪሱ ታጥፎ የተደረበ ነው በውስጣቸው #ኡሪምና #ቱሚም ይይዛሉ {ዘጸ 28፥30}። #ቀሚሱ ሙሉ በሙሉ #ሰማያዊ ሲሆን በታችኛውም ዘርፍ ዙሪያ #በ3 #ቀለም የተሰራ #የሮማን ፍሬ #ቅርጽ #ከወርቅ #ሻኩራ ጋር ተሰባጥሮ ይደረግበታል። የሻኩራዎቹ #ድምጽ #ለቀሚሱ ውበትን ይሰጠዋል። #ጥምጥሙ ደግሞ #ካህኑ በራሱ ላይ የሚጠመጥመው ሲሆን ከጥሩ #በፍታ የተሰራ ነው <<ቅድስና ለእግዚአብሔር>> የሚል ጽሑፍ #ከወርቅ በተሰራ #ዝርግ #ጌጥ ላይ ተቀርጾ በዚህ #ጥምጥም ላይ #ይንጠለጠልበታል {ዘጸ 28፥36}።
▶️ እነዚህ #አለባበሶች ግን አሁን #በቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግሉ አድርጋ #የኢትዮጵያ ኦ.ተ.ቤተ ክርስቲያን ከመደበቻቸው #የካህናት አለባበስ #በቁጥርም#በመልክም #በዲዛይንም እጅግ #የተራራቀ ነው። በብሉይ ኪዳን የነበሩት #የሊቀ ካህናት አለባበስ አንድ በአንድ መግለጽ አጀንዳችን ስላልሆነ እኛም እንደ #ጳውሎስ <<ስለእነዚህ እንዳንተርክ አሁን አንችልም>> {ዕብ 9፥5}። ይሁን እንጂ #በቤተ መቅደሱ (ቅድስተ ቅዱሳን) ውስጥ #ሴቶች ፈጽሞው የሚገቡበት ሁኔታ አልነበረም።

ይኸው #ካህን እንኳ በተገቢ ሁኔታ አለባበሱን አስተካክሎና ስለራሱ #ኃጢአት #መስዋዕትን በቅድሚያ አቅርቦ የህዝቡን #ኃጢአት የሚያስተሰርይበትን #መስዋዕት ይዞ በብዙ #ፍርሃት #መጋረጃውን ገልጦ ቢገባ #በታቦቱ #መክደኛ ላይ በወረደው #ደመና #ዓምድ መሰረት #እግዚአብሔር ያናግረዋል። ነገር ግን #ሊቀ ካህኑ #ባይቀደስና በተገቢው ሁኔታ #አለባበሱን #ሳያስተካክል ቢቀርና የመሳሰሉት ነገሮች ባያሟላ እዚያው #ይቀሰፍና #ይሞታል። በውጭ #በአደባባይ የተሰበሰበው #ምህረት ጠባቂ ህዝብ #ካህኑ ቢዘገይባቸውም #እንደተቀሰፈና #እንደሞተ ስለሚገባቸው #በወገቡ ላይ እስከውጨኛው ድረስ በታሰረው #ሰንሰለት ጎትተው ያወጡታል እንጂ እንኳንስ #ሴቶች #ወንዶች እንኳ ገብተው በፍጹም #ሬሳውን አያወጡም።
እንግዲህ ይኸው #ስርዓት በተሟላ መልኩ #ከድንኳንነት ወደ #ህንጻ ቤት ተቀይሮ #የዳዊት ልጅ #ሰለሞን #በኢየሩሳሌም እጅግ ውብ አድርጎ ሰራው። #የሰለሞን #ቤተመቅደስ #ሴቶች #ከአደባባዩ ውጭ ባለው #ዓምድ እንደ #ሃና #ይፀልያሉ እንጂ {1ኛ ሳሙ 1፥9} በጭራሽ #በቅድስተ ቅዱሳኑ (በቤተመቅደሱ) ውስጥ #ሴቶች አይገቡም ነበር።