▶️ ወደ #ቅድስተ #ቅዱሳኑ (ቤተ መቅደሱ) ውስጠኛ #ክፍል ለአገልግሎቱ የሚገባው #ሊቀ ካህኑ ብቻ ሆኖ #በአመት 1 ቀን እርሱም #በማስተሰርያ ቀን #ስለራሱና #ስለህዝቡ #መስዋዕትን ይዞ #በእግዚአብሄር ፊት ይቆማል {ዘጸ 28}። #የሊቀ ካህኑ ልብሰ #ተክህኖ #በ4 #ቀለማት ማለትም #ከነጭ፣ #ከሰማያዊ፣ #ከሐምራዊና #ከቀይ #በፍታ #በወርቅ የተለጠፈ ነበር {ዘጸ 28}። የላይኛው አላባሽ #ኤፉድ ሲባል {ዘጸ 39፥2} #በቀኝና #በግራ ትከሻው ላይ ሁለት የመረግድ #ድንጋዮች ነበሩት። በእነዚህ #ሁለት የከበሩ #ድንጋዮች በእያንዳንዱ ላይ #የ6 ነገድ #ስም በሁለቱም ላይ #የ12ቱ ነገደ #እስራኤል ስም #ተቀርጾባቸዋል {ዘጸ 28፥9 እና 12}። በእነርሱም አማካኝነት #ሊቀ ካህኑ #የህዝቡን #ስም በአጠቃላይ በትከሻው ይሸከማል። #የደረት ኪሱ #አራት ማዕዘን ያለው ሆኖ #በወርቅ ጥልፍ የተሰራ #የ12 ነገድ #ስም የተቀረጸባቸው #የሚያንጸባርቁ #የከበሩ #ድንጋዮች እንደ #ፈርጥ ሆነው የተሰሩ ናቸው {ዘጸ 28፥29}። #የደረት ኪሱ ታጥፎ የተደረበ ነው በውስጣቸው #ኡሪምና #ቱሚም ይይዛሉ {ዘጸ 28፥30}። #ቀሚሱ ሙሉ በሙሉ #ሰማያዊ ሲሆን በታችኛውም ዘርፍ ዙሪያ #በ3 #ቀለም የተሰራ #የሮማን ፍሬ #ቅርጽ #ከወርቅ #ሻኩራ ጋር ተሰባጥሮ ይደረግበታል። የሻኩራዎቹ #ድምጽ #ለቀሚሱ ውበትን ይሰጠዋል። #ጥምጥሙ ደግሞ #ካህኑ በራሱ ላይ የሚጠመጥመው ሲሆን ከጥሩ #በፍታ የተሰራ ነው <<ቅድስና ለእግዚአብሔር>> የሚል ጽሑፍ #ከወርቅ በተሰራ #ዝርግ #ጌጥ ላይ ተቀርጾ በዚህ #ጥምጥም ላይ #ይንጠለጠልበታል {ዘጸ 28፥36}።