ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.82K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ወደ #ቅድስተ #ቅዱሳኑ (ቤተ መቅደሱ) ውስጠኛ #ክፍል ለአገልግሎቱ የሚገባው #ሊቀ ካህኑ ብቻ ሆኖ #በአመት 1 ቀን እርሱም #በማስተሰርያ ቀን #ስለራሱና #ስለህዝቡ #መስዋዕትን ይዞ #በእግዚአብሄር ፊት ይቆማል {ዘጸ 28}። #የሊቀ ካህኑ ልብሰ #ተክህኖ #በ4 #ቀለማት ማለትም #ከነጭ#ከሰማያዊ#ከሐምራዊና #ከቀይ #በፍታ #በወርቅ የተለጠፈ ነበር {ዘጸ 28}። የላይኛው አላባሽ #ኤፉድ ሲባል {ዘጸ 39፥2} #በቀኝና #በግራ ትከሻው ላይ ሁለት የመረግድ #ድንጋዮች ነበሩት። በእነዚህ #ሁለት የከበሩ #ድንጋዮች በእያንዳንዱ ላይ #የ6 ነገድ #ስም በሁለቱም ላይ #የ12ቱ ነገደ #እስራኤል ስም #ተቀርጾባቸዋል {ዘጸ 28፥9 እና 12}። በእነርሱም አማካኝነት #ሊቀ ካህኑ #የህዝቡን #ስም በአጠቃላይ በትከሻው ይሸከማል። #የደረት ኪሱ #አራት ማዕዘን ያለው ሆኖ #በወርቅ ጥልፍ የተሰራ #የ12 ነገድ #ስም የተቀረጸባቸው #የሚያንጸባርቁ #የከበሩ #ድንጋዮች እንደ #ፈርጥ ሆነው የተሰሩ ናቸው {ዘጸ 28፥29}። #የደረት ኪሱ ታጥፎ የተደረበ ነው በውስጣቸው #ኡሪምና #ቱሚም ይይዛሉ {ዘጸ 28፥30}። #ቀሚሱ ሙሉ በሙሉ #ሰማያዊ ሲሆን በታችኛውም ዘርፍ ዙሪያ #በ3 #ቀለም የተሰራ #የሮማን ፍሬ #ቅርጽ #ከወርቅ #ሻኩራ ጋር ተሰባጥሮ ይደረግበታል። የሻኩራዎቹ #ድምጽ #ለቀሚሱ ውበትን ይሰጠዋል። #ጥምጥሙ ደግሞ #ካህኑ በራሱ ላይ የሚጠመጥመው ሲሆን ከጥሩ #በፍታ የተሰራ ነው <<ቅድስና ለእግዚአብሔር>> የሚል ጽሑፍ #ከወርቅ በተሰራ #ዝርግ #ጌጥ ላይ ተቀርጾ በዚህ #ጥምጥም ላይ #ይንጠለጠልበታል {ዘጸ 28፥36}።
▶️ በቤተክርስቲያኗ ባሉ #ድርሳናት#ገድላት#በተአምራትና #በመልክዕ እንዲሁም በ" #ጸሎት መጻሕፍት" ውስጥ ብዙ የማይታወቁ #ቋንቋዎችና ውስብስብ #የእባብና #የዘንዶ፣ የማይታወቁ #የእንስሳትና #የሐረጋት #ስእሎች ታጭቆባቸዋል። እነዚህ #ቋንቋዎች በአብዛኞቹ በየትኛውም #አለም #የቋንቋ #ሃረጋትና #መዝገበ ቃላት ውስጥ የሌሉ #ለማንበብ የሚያስቸግሩ #በቀይና #በጥቁር #ቀለማት የተጻፉ እንዲሁም #ከአውደ ነገስት፣ #ከመድፍነ ጸር፣ #ከሐተታ መናፍስት...ወ.ዘ.ተ ከሚባሉ አደገኛ #የጥንቆላ #መጻሕፍት #ቋንቋና #ስእል ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው[1]።

▶️ በ" #ነገረ ማርያም" #መጽሀፍ ውስጥ <<እመቤታችን እግዚእትነ ማርያም #ዮሳሜር#አድሜሽ#ድቸር#አዶናዊሮስ#ሰራሰቅሰሬል>> ብላ ህቡዕ አስማት (ስም) ብትደግምባቸው #መሬት ተከፍቶ ዋጣቸው። #ከነሥጋቸው #ሲኦል ወረዱ[2]።>> ይላል።
▶️ ዛሬ በተለይ #በከተሞች ባሉ #አድባራት ሕዝቡ #ለትምህርትና #ለጋራ ፀሎት #በአውድ ምህረት {በአደባባዩ} ሲሰባሰብ #በሰባኪው ወይም #በመጽሐፍት አንባቢ ፊት ትላልቅ ሆነው የተሰሩ <<የማርያም ስዕል [ስእለ አድህኖ]>> #በሐምራዊ #መጋረጃዎች አንዳንዴም በልዩ ልዩ #ቀለማት በሆኑ #መብራቶች የተሽቆጠቆጡ ይቀመጣሉ። ህዝቡ እንደምናየው ወደስእሉ #እየሰገደ #አምልኮቱን ይገልጻል። ይህ ሁኔታ በተለይ በሰንበት ቀን #እሁድ #ጠዋት እና ዘውትር #በሰርክ ጉባኤ {በ11 ሰዓት ማታ ላይ} እንዲሁም #የወሩና #የዓመቱ ሲሆን በግልጽ የተለመደ ክንውን ሆኖ ይታያል።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
______________
[1] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Leo_III_the_Isaurian

[2] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Constantine_V

[3] አንደኛው የኒቂያ ጉባኤ የሚባለው በ325 ዓ.ም 318 የሐይማኖት አባቶች በንጉስ ቆስጠንጢኖስ ዘመን አርዮስ ወልድ ፍጡር ነው በማለቱ የተወገዘበት ጉባዔ ነው።

[4] 📚፤ አባ ሊዩጂ አናታሎኒ፤ "አወያይ ነጥቦች በትምህርተ ካቶሊክ ውስጥ"፥ ገጽ 44-47፤ አ.አ፤ 1995 ዓ.ም።

📚፤ ቀሲስ ከፍ ያለው መራሒ፤ "የቤተክርስቲያን አስተዎጽኦ ለኢትዮጵያ ስልጣኔ"፤ ገጽ 47-48፥ የት.መ.ማ.ማ ድርጅት፤ አ.አ፥ የካቲት 16፥ 1986 ዓ.ም።

📚፤ ሚሊዮን በለጠ አሰፋ፤ "ቅዱሳን ሥዕላት አመጣጥና ታሪክ ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር"፥ ገጽ 88-90፤ ዓለም ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ መጋቢት፡ 1994 ዓ.ም።

📚፤ መምህር አንዱዓለም ዳግማዊ፤ "ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅንነት"፥ ገጽ 25፤ ብራና ማተሚያ ድርጅት፥ ሚያዚያ 1998 ዓ.ም።

📚፤ ብርሃኑ ጉበና፤ "ዓምደ ሃይማኖት"፡ ገጽ 141-142፤ ንግድ ማተሚያ ቤት፡ አ.አ፤ የካቲት 1985 ዓ.ም።

📚፤ ዲያቆን አሐዱ አስረስ፣ "የመናፍቃን ማንነትና መልሶቻቸው" 4ተኛ ዕትም፤ ገጽ 76-78፤ ባናዊ ማተሚያ ቤት፣ አ.አ፥ ጥቅምት 1996 ዓ.ም።

[5] 📚፤ አባ ጎርጎሪዎስ፥ የሸዋ ሊቀ ጳጳስ፤ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ"፤ 4ኛ ዕትም፤ ገጽ 96፥ ጥር 1994 ዓ.ም።

[6] 📚፤ ማህበረ ቅዱሳን፤ "ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋዜጣ፤ 9ኛ ዓመት ቁ.4፤ ቅጽ 10፤ ቁ. 65፣ ጥር 1994 ዓ.ም።

[7] 📚፤ ማህበረ ቅዱሳን፤ "ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋዜጣ፤ 9ኛ ዓመት ቁ.4፤ ቅጽ 10፤ ቁ. 65፣ ጥር 1994 ዓ.ም።

[8] 📚፤ ተአምረ ማርያም፤ 9ኛ ተዓምር፤ ገጽ 34፤ ቁ.23፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።

[9] 📚፤ ጌታቸው ኃይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ"፥ ገጽ 25፡ 1996 ዓ.ም።

[10] 📚፤ አንዱዓለም ዳግማዊ {መምህር}፤ "ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅንነት" ገጽ 24፥ 1998 ዓ.ም።

📚፤ ብርሃኑ አድማሱ {ዲያቆን}፣ "በዓላት ምን፣ ለምን? እንዴት?" ገጽ 161፤ 1999 ዓ.ም።

[11] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Society_of_Jesus

[12] 📚፤ ክርስቲያን ሻዮ፤ ትርጓሜ መልአከ ሰላም ዳኛቸው ካሳሁን፤ "የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ህይወት"፥ ገጽ 24፤ 1999 ዓ.ም።

(9.2▶️) ይቀጥላል..
@gedlatnadersanat