ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
<<ድንግል ሆይ የልጅሽን በረከት በእኔ ላይ #አዝንቢ፥ የሚጻረረኝን የሚቃወመኝን ሰው አፉን #ለጉሚው አንደበቱን #ዲዳ አድርጊ፥ ጉሮሮውን #ዝጊ፣ ጆሮውን #አደንቁሪ ኃይሉንም #አዳክሚ፣ በልጅሽ መለኮታዊ ሰይፍ አንገቱን #ቆርጠሽ #ጣይ፣ ባላየ የሚያንዣብበውን የጠላት ዲያብሎስን ክንፍ #ስበሪ አሜን።>> [እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት፥ አርኬ 3]

▶️ ይህ <<እስመ ክብርት>> የሚባለው #መጽሀፍ በሙሉ #እርግማን የሚያወርድ የ"ጸሎት" አይነት ነው። አንዳንድ #ምእመናን ሁልጊዜ #ጠዋት #ጠዋት ሲነጋ ይደግሙታል። አንዳንዶችም #ለጠላት ዋነኛ #መፍትሄ አድርገው ቆጥረውት #ይመኩበታልም

▶️ በዚህ በተጠቀሰው #አርኬ ላይ #ድንግል #ማርያም #የበረከት #አዝናቢ ሆናለች። መጽሀፍ ቅዱስ ግን <<በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።>> ይላል {ያዕ 1፥17}። ስለሆነም #በጎ #ስጦታ ፍጹምም የሆነ #በረከት #ከእግዚአብሄር ዘንድ እንጂ #ከማርያም ዘንድ ወይም #በማርያም በኩል አይደለምና ይሄ ግልጽ #ስህተት ነው።

▶️ ሌላው <<የሚጻረረኝን የሚቃወመኝን ሰው>> ተብሎ አፉ #እንዲሎጎም፣ አንደበቱ #ዲዳ እንዲሆን፣ ጉሮሮው #እንዲዘጋ፣ ጆሮው #እንዲደነቁር፣ ኃይሉም #እንዲዳከም፣ አንገቱ #እንዲቆረጥ መጸለዩ የትኛው መንፈስ ሆኖልን ይሆን? የእግዚአብሄር ሰው ግን ቃሉ እንደሚል <<ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግማችሁን መርቁ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ>> በማለት #በብሉይ ሳይሆን #በአዲስ ኪዳን #ፍቅር ይመራል [ማቲ 5፤ 44-45]። ደግሞም <<ጠላትህን ግን ቢራብ አብላው ቢጠማ አጠጣው ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና ፤ ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ>> ይላል [ሮሜ 12፤ 20-21]።

ይሄው ረጋሚው <እስመ ክብርት> #መጽሀፍ ይቀጥልና <<ድንግል ሆይ ተአምራዊ ኃይልን ማድረግ የሚቻልሽ የዓለም ንግስት አንቺ ነሽና ሊያጠፋኝ የሚያሴረውን ጠላት አጣድፈሽ #ከጥፋት #ገደል #ጣይው። ተከታትሎ አድኖ ሊያጠፋኝ የሚፈልገውን ጠላት ፈጥነሽ ደርሰሽ አይኑን #አሳውሪው እጁን #ሽባ አድርጊው እግሩንም #አሳጥሪው>> [እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት አርኬ 5] ይላል። ደግሞም <<በዚህ አለም የሚጠላኝን የሚቃወመኝን ሰው #ከምድር ላይ #ነቅለሽ #ጣይልኝ>> [እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት፥ አርኬ 9] ይላል።
▶️ ዛሬ በተለይ #በከተሞች ባሉ #አድባራት ሕዝቡ #ለትምህርትና #ለጋራ ፀሎት #በአውድ ምህረት {በአደባባዩ} ሲሰባሰብ #በሰባኪው ወይም #በመጽሐፍት አንባቢ ፊት ትላልቅ ሆነው የተሰሩ <<የማርያም ስዕል [ስእለ አድህኖ]>> #በሐምራዊ #መጋረጃዎች አንዳንዴም በልዩ ልዩ #ቀለማት በሆኑ #መብራቶች የተሽቆጠቆጡ ይቀመጣሉ። ህዝቡ እንደምናየው ወደስእሉ #እየሰገደ #አምልኮቱን ይገልጻል። ይህ ሁኔታ በተለይ በሰንበት ቀን #እሁድ #ጠዋት እና ዘውትር #በሰርክ ጉባኤ {በ11 ሰዓት ማታ ላይ} እንዲሁም #የወሩና #የዓመቱ ሲሆን በግልጽ የተለመደ ክንውን ሆኖ ይታያል።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
______________
[1] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Leo_III_the_Isaurian

[2] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Constantine_V

[3] አንደኛው የኒቂያ ጉባኤ የሚባለው በ325 ዓ.ም 318 የሐይማኖት አባቶች በንጉስ ቆስጠንጢኖስ ዘመን አርዮስ ወልድ ፍጡር ነው በማለቱ የተወገዘበት ጉባዔ ነው።

[4] 📚፤ አባ ሊዩጂ አናታሎኒ፤ "አወያይ ነጥቦች በትምህርተ ካቶሊክ ውስጥ"፥ ገጽ 44-47፤ አ.አ፤ 1995 ዓ.ም።

📚፤ ቀሲስ ከፍ ያለው መራሒ፤ "የቤተክርስቲያን አስተዎጽኦ ለኢትዮጵያ ስልጣኔ"፤ ገጽ 47-48፥ የት.መ.ማ.ማ ድርጅት፤ አ.አ፥ የካቲት 16፥ 1986 ዓ.ም።

📚፤ ሚሊዮን በለጠ አሰፋ፤ "ቅዱሳን ሥዕላት አመጣጥና ታሪክ ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር"፥ ገጽ 88-90፤ ዓለም ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ መጋቢት፡ 1994 ዓ.ም።

📚፤ መምህር አንዱዓለም ዳግማዊ፤ "ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅንነት"፥ ገጽ 25፤ ብራና ማተሚያ ድርጅት፥ ሚያዚያ 1998 ዓ.ም።

📚፤ ብርሃኑ ጉበና፤ "ዓምደ ሃይማኖት"፡ ገጽ 141-142፤ ንግድ ማተሚያ ቤት፡ አ.አ፤ የካቲት 1985 ዓ.ም።

📚፤ ዲያቆን አሐዱ አስረስ፣ "የመናፍቃን ማንነትና መልሶቻቸው" 4ተኛ ዕትም፤ ገጽ 76-78፤ ባናዊ ማተሚያ ቤት፣ አ.አ፥ ጥቅምት 1996 ዓ.ም።

[5] 📚፤ አባ ጎርጎሪዎስ፥ የሸዋ ሊቀ ጳጳስ፤ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ"፤ 4ኛ ዕትም፤ ገጽ 96፥ ጥር 1994 ዓ.ም።

[6] 📚፤ ማህበረ ቅዱሳን፤ "ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋዜጣ፤ 9ኛ ዓመት ቁ.4፤ ቅጽ 10፤ ቁ. 65፣ ጥር 1994 ዓ.ም።

[7] 📚፤ ማህበረ ቅዱሳን፤ "ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋዜጣ፤ 9ኛ ዓመት ቁ.4፤ ቅጽ 10፤ ቁ. 65፣ ጥር 1994 ዓ.ም።

[8] 📚፤ ተአምረ ማርያም፤ 9ኛ ተዓምር፤ ገጽ 34፤ ቁ.23፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።

[9] 📚፤ ጌታቸው ኃይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ"፥ ገጽ 25፡ 1996 ዓ.ም።

[10] 📚፤ አንዱዓለም ዳግማዊ {መምህር}፤ "ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅንነት" ገጽ 24፥ 1998 ዓ.ም።

📚፤ ብርሃኑ አድማሱ {ዲያቆን}፣ "በዓላት ምን፣ ለምን? እንዴት?" ገጽ 161፤ 1999 ዓ.ም።

[11] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Society_of_Jesus

[12] 📚፤ ክርስቲያን ሻዮ፤ ትርጓሜ መልአከ ሰላም ዳኛቸው ካሳሁን፤ "የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ህይወት"፥ ገጽ 24፤ 1999 ዓ.ም።

(9.2▶️) ይቀጥላል..
@gedlatnadersanat