ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ዕብራውያን 7፤ 20-28 << እነርሱም ያለ #መሐላ #ካህናት ሆነዋልና፤ #እርሱ ግን። ጌታ። አንተ #እንደ #መልከ ጼዴቅ ሹመት #ለዘላለም #ካህን ነህ ብሎ #ማለ #አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት #ከመሐላ ጋር #ካህን ሆኖአልና ያለ #መሐላ #ካህን እንዳልሆነ መጠን፥ እንዲሁ #ኢየሱስ #ለሚሻል #ኪዳን #ዋስ ሆኖአል። #እነርሱም እንዳይኖሩ #ሞት ስለ ከለከላቸው #ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ #እርሱ…


ዕብራውያን 9፥15 እና 24

<<ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት #የዘላለምን #ርስት #የተስፋ #ቃል እንዲቀበሉ እርሱ ፨የአዲስ ኪዳን #መካከለኛ፨ ነው። . . . ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን #ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን #በእግዚአብሔር #ፊት #ስለ #እኛ #አሁን #ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ #ሰማይ ገባ።>>


#ክርስቶስ ለምንድን ነው •የዐዲስ ኪዳን መካከለኛ• የሆነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጠው ይሄኛው ክፍል <<የተጠሩት #የዘላለም #ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ>> መሆኑን ያስረዳል። <በአሮንና በልጆቹ>፣ <በአብርሃምና በሙሴ>፣ <በዳዊትና በነቢያት> የተሠሩ #የመካከለኛነት #ሥራዎች ሁሉ #የዘላለምን #ርስት #ለማውረስ የሚሆን ምንም ዐይነት #ተስፋ የሌላቸው መሆኑ፣ #የክርስቶን #የመካከለኝነት ሥራ እንዴት #የላቀ እንደ ሆነ ያሳያል። እንዲህ ያለውን #የመካከለኛነት #ሥራ ከእርሱ #በፊት የሠራው የለም ከእርሱም #ቡኋላ ሊሠራው የሚችል #አይኖርም። በመሆኑም #ሰዎች ሁሉ #ተስፋቸው #ክርስቶስ ብቻ በመሆኑ የእርሱን #የመካከለኛነት #ሥራ በሙሉ #ደስታ #መቀበል ይገባቸዋል። #ኢየሱስ #በሰው እጅ ወዳልተሰራችው #እውነተኛይቱ #ቤተ #መቅደስ የገባው መጽሐፍ እንደሚለው <<ስለ እኛ #አሁን ይታይ ዘንድ>> ማለትም #የምልጃን #ሥራ ይሰራ ዘንድ ነው።

#ሐዋርያው የዐዲስ ኪዳን #መካከለኛ በሚል ክርስቶስን ሲጠራው #በሰው እና #በእግዚአብሄር #መካከል በመግባት ስለ ሠራው #የማዳን (የዕርቅ) #ሥራ ሆኖ ሳለ ይህን #እውነት #መዋጥ የተሳናቸው ሰዎች፦
ስለ <ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከራሱና ማኅየዊ (አዳኝ) ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያስታርቀን ዘንድ የባሪያውን መልክ ይዞ (የእኛን ባሕርይ ነሥቶ) #ትምክህታችን ከምትሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው ሆነ፤ አምላክ የሆነ ሰው ሰውም የሆነ አምላክ (መካከለኛ) ሆነ፤ በተዋሕዶ አንድ ባሕርይ የሆነ ሥግው ቃል (Incarnated word)፣ አምላክ ወሰብእ (አምላክም ሰውም) (መካከለኛ) ሆነ>

በሚል መካከለኛ ሲል አምላክነቱን እና ሰውነቱን ለማመልከት ነው የሚል መልእክት ያስተላልፋሉ[1]።

#ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ እውነት ነው። ይህም በነገረ ድነታችን ላይ ወሳኝ ቦታ አለው። ነገር ግን ይህ ምንባብ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ስለ መሆኑ የሚናገር ባለ መሆኑ ይህን ምንባብ መሠረት አድርጎ ሊቀርብ የሞከረው ማብራርያ የኢየሱስን መካከለኛነት ለመሸፈን ሆን ተብሎ የቀረበ መሆኑ ግልጽ ነው። ሐዋርያው፤ ፦

<<ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፥ እንደዚህም መባና መስዋዕት ይቀርባሉ፤ እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ #የሥጋ #ሥርዓቶች #ብቻ #ናቸውና የሚያመልከውን #በህሊና #ፍጹም #ሊያደርጉት አይችሉም። ነገር ግን #ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር #ሊቀ #ካህናት #ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥ #የዘላለምን #ቤዛነት አግኝቶ #አንድ #ጊዜ #ፈጽሞ ወደ #ቅድስት #በገዛ #ደሙ #ገባ እንጂ #በፍየሎችና #በጥጆች #ደም አይደለም። የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ #ራሱን #ለእግዚአብሔር #ያቀረበ #የክርስቶስ #ደም እንዴት #ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ #ሕሊናችሁን #ያነጻ ይሆን?>> (ቁ. 9-14)

የሚለውን ካሰፈረ ቡኋላ < #ስለዚህም> በማለት 15ኛውን ቁጥር ይቀጥላል። ይህ ክፍል የሚያመለክተው ክርስቶስ በገዛ ደሙ እንጂ በፍየሎችና በበጎች ደም ዕርቅን ያመጣልን አለመሆኑን ነው። እነዚህ ስርአቶች የሥጋ ስርአቶች ብቻ ነበሩ ማለትም ኃጢአትን መሸፈን ነው እንጂ ማስወገድ አይችሉም። የሚያመልከውን በኅሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም። ለዚህም ነው <ራሱን ለእግዚአብሄር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ከሞተ ሥራ ኅሊናችሁን ያነጻ ይሆን?> በማለት የሰፈረው። ይህም ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን መካከለኛ እንዲባል ምክንያት ሆኗል። ወደ ቅድስት በእግዚአብሄር ፊት ስለእኛ አሁን ይታይ ዘንድ በገዛ ደሙ ነውና የገባው።

የዕብራውያን መልእክት አንድምታም፦

< . . . . በተጨማሪም በየዓመቱ አንድ ጊዜ ከሚገቡት ከአሮናውያን ካህናት በተለየ ሁኔታ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ሰማይ ገብቷል። ወደ ሰማይ የገባውም ቀድሞ የዘላለም ቤዛነትን ያስገኘላቸውን #በክህነት #አገልግሎቱ #ሊረዳቸው ነው[2]።>

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..
@gedlatnadersanat @teeod

"ማጣቀሻ"
____________
[1] ሮዳስ ታደሰ (መጋቤ ዐዲስ)፣ <ነገረ ክርስቶስ> _ ክፍል 1 (የካቲት 2008) ገጽ 495።

[2] GBV፣ የዕብራውያን መልእክት አንድምታ (ትርጓሜው ከነንባቡ)፣ 1998 ገጽ 74
▶️ ድሮም ፍለጋቸው እናቱ #ማርያምን ሳይሆን #የተወለደውን #የአይሁድ #ንጉስ ነው {ማቴ 2፥2፣ 11}። #ሄሮድስም #ህጻኑን #ለመግደል አቅዶ እንደተነሳና #ህጻኑን ግን እንዳላገኘው ያሳይና ወዲያውም ወደ 30 ዓመት #ዕድሜው ተምዘግዝጎ ወደ #አገልግሎቱና #ዋና ወደ ሆነው #ሰፊ #ክፍል ውስጥ ይገባል።

▶️ በሉቃ 1፥26፣ እስከ 2፥52 ብንመለከትም #መልአኩ #ገብርኤል #ማርያምን #ትጸንሻለሽ ብሎ ከገለጸ ቡኋላ በሚወለደው #ህጻን #ልጅ ላይ ብቻ #አትኩሮት ሰጥቶ <<ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።. . . መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።>> የሚል #በልጁ #ታላቅነት ላይ ያነጣጠረ ነበር። ወዲያው #ኢየሱስ #ክርስቶስ ከተወለደ ቡኋላ "መጽሐፍ ቅዱስ" #የማርያምን #ሁኔታ ወደ ጎን ይተወውና <<ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።. . ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።>> ብሎ ወደ #ልጁ አጠቃላይ #አገልግሎቱ ገብቶ እስከ #እርገቱ በስፋት ያትታል።
▶️ ቅዱስ ገብርኤል #ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ #ለማርያም #ለማስረዳት የተጠቀመው #ምሳሌ #መካን የነበረችውና #ያረጀችው ዘመዷ #ኤልሳቤጥ #ወንድ ልጅ እንደጸነሰች በመግለጽ ነበር። #ልጅ አለመውለድ #የወላጆችን #የግል #ደስታ የሚያሳጣ ብቻ ሳይሆን #እግዚአብሔር እንደማይወዳቸውም የሚያመለክት ነው ተብሎ #በህብረተሰቡ ዘንድ ስለሚታመን {ዘፍ 16፥2 ፣ ዘፍ 25፥21 ፣ ዘፍ 30፥23 ፣ 1ኛሳሙ 1፤ 1-18 ፣ ዘሌ 20፤ 20-21 ፣ መዝ (128)፥3 ፣ ኤር 22፥30}። <<ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ ተመለከተኝ>> ብላ #እግዚአብሔር #የመካንነትን #ህይወቷን ስለቀየረላት ምስጋና አቅርባለች {ሉቃ 1፥24}። #በደስታ#በጥሞና#በምስጋና... የነበረችውን #ኤልሳቤጥን ማርያም #ከገብርኤል መልእክት(ብስራት) ቡኋላ ወደ እሷ መጥታ #ሰላምታ ስታሰማት #ኤልሳቤጥ #በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ከማርያም አፍ ሳትሰማው ማርያም #የጌታ #እናት እንደምትሆን አወቀች። በዚህ ጊዜ #ኤልሳቤጥ አፏን የሞላው #ቃል <<አንቺ ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?>> የሚል ነበር። አንዳንዶች እንደሚሉት ሳይሆን ኤልሳቤጥ ማርያምን <<ከሴቶች #በላይ የተባረክሽ>> እንዳላለቻትና ዳሩ ግን <<ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ>> እንዳለቻት ልብ ማለት ያስፈልጋል። #ማርያም #በእግዚአብሄር #እቅድ ውስጥ ያላትን #ስፍራ ባናሳንስም(ልናሳንስም አንችልም) #እግዚአብሔር #ብቻ ሊቀበል የሚገባውን #የአምልኮት #ክብርና #ልእልና መስጠት ግን አይገባንም።

▶️ ስለማርያም ኤልሳቤጥ #ያገነነችው ነገር ቢኖር <<ያመነች ብጽኢት[1] ናት>> በሚል የማርያምን #እምነት ነበር {ሉቃ 1-45}። #ማርያም #የእግዚአብሔርን #ቃል ስላመነች የእግዚአብሔርን #ኃይልና #አንድያ #ልጅ ተቀበለች።

▶️ በኤልሳቤጥ #ጽንስ ውስጥ ያለው #ዩሀንስም በጊዜው #ደስ #ተሰኝቷል {ሉቃ 1፤ 41-44}። ዩሀንስ #በምድራዊ #አገልግሎቱ እንዳደረገው ሁሉ #ሳይወለድም በፊት #በኢየሱስ ክርስቶስ #ብቻ ደስ ተሰኝቷል {ዩሀ 3፤ 29-30}። #ካደገ ቡሀላም #መጥምቁ #ዩሀንስ ተብሎ ሲታወቅ #መሲሁን #ኢየሱስ ክርስቶስን ለአይሁድ ህዝብ የማስተዋወቅና የመግለጥ ታላቅ #እድል አግኝቷል። ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ <<ዩሀንስ በእናቱ ማህጸን ውስጥ የማርያምን ድምጽ በመስማቱ #ለማርያም #ሰገደላት>> የሚሉ #መናፍቃን አልታጡም። ይሁን እንጂ #የጽንስ #መዝለል #ሁኔታን #ጸንሰው የሚያቁ #እናቶች የሚረዱት ነገር ቢሆንም •ስግደት• ብሎ መቀየር ግን. . . •ለማርያም ሰገደ• ያሉትም #መጽሀፍ ቅዱስ ሳይሆን #ሲኖዶስ ተብለው የተጠሩ ተስብሳቢዎች እንደሆኑ #ራሱ #ኦርቶዶክስ ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን ያሳተመችው #የሉቃስ ወንጌል አንድምታው ይገልጻል።

<<. . . ከዘካርያስ ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን እንዴት ነሽ አለቻት፥ ወሶበ ስምዓት ኤልሳቤጥ ቃላ ለማርያም እንዝ ትትኣምኃ ኦንፈርዓፀ እጓል በውስተ ከርሣ እመቤታችን እንዴት ነሽ ስትላት ኤልሳቤጥ በሰማች ጊዜ በማኅፀኑዋ ያለ ብላቴና ሰገደ። ሐተታ፡ ሐዋርያት #በሲኖዶስ ሰገደ ብለውታል። #ያሬድም ሰገደ ብሎታል።[2]>>

▶️ ከዚሁ #ከማርያምና #ከኤልሳቤጥ #ውይይት በመነሳት <<ቅድስት ኤልሳቤጥ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ ነሽ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እያማለድሽ የምትሰጪ መዝገበ በረከት ነሽ>> ብላ #አመስግናታለች #ዘምራላታለች የሚሉ አሉ[3]።

▶️ እንግዲህ እንዲህ አይነት #ቃል #በመጽሀፍ ቅዱስ ፈጽሞ ሳይኖር #ኤልሳቤጥ እንዲህ አይነት #ቃል ተጠቅማለች ብሎ #መጻፍና #ማስተማር #መጽሀፍ ቅዱስ እኛ ጋር #ብቻ ይገኛል ሌላው #ማንበብ አይችልም ብሎ ከማሰብና #የመጽሐፍ ቅዱስን #የበላይነት ካለመቀበል የሚመነጭ #ከንቱነት ነው። #ኤልሳቤጥ የተናገረችው <<አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።>> {ሉቃ 1፥47} የሚል ብቻ ነው።

▶️ በአንጻሩ ደግሞ <<መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የለብሽም>> ማለት በግልጽ #መጽሀፍ ቅዱስን መካድና #ማርያም የሰው ዘር መሆኗን #መዘንጋት ነው። እንዲያውም ማርያም ራሷ ክርስቶስን <<መድኃኒቴ>> ብላዋለች። #መድኃኒት ደግሞ #ለበሽተኞች (ለኃጢአተኞች) እንጂ #ለጤነኞች (ለጻድቃን) የሚያስፈልግ እንዳልሆነ #ቃሉ #በግልጽ ይናገራል{ማቴ 9፥12}።

▶️ በመሆኑም <<መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ. . . እያማለድሽ የምትሰጪ>> እያለ #የዘመረ #አካል #በመጽሀፍ ቅዱስ ባለመኖሩ የሌለ ነገር ላይ ተንተርሶ #ዶክትሪን ማስቀመጥ በቃሉ #መልእክት ላይ የተፈጸመ ተራ #አመጽ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_______________
[1] ብፁዕ፤፦
<<በቁሙ የታመነ፣ የተመሰገነ፣ ሥራውና ልቡ የቀና፣ ... ምስጉን፣ ብሩክ...>>
📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ *ገጽ 2081። አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ 1948 ዓ.ም።

<<የተባረከ፣ ደስተኛ>>
📚፤ የኢትዮጽያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር፤ <የመጽሀፍቅዱስ መዝገበ ቃላት>፤ 6ኛ እትም፤ *ገጽ 112። ባናዊ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ 1992 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፡ ወንጌል ቅዱስ፡ የሉቃስ ወንጌል ንባቡና አንድምታው 1፤ 36-40፤ ገጽ 268። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1997 ዓ.ም።

[3] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ ቤ/ክ፤ <መርሐ ጽድቅ ባህለ ሃይማኖት>፡ ገጽ. 24-25፡ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት። አ.አ፥ 1988 ዓ.ም።

📚፤ አንዱዓለም ዳግማዊ (መምህር) <ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት> ገጽ 290። ብራና ማተሚያ ድርጅት፥ ሚያዚያ፥ 1998 ዓ.ም።


(5.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat