አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልተቋጨ


#ክፍል_አንድ


#በክፍለማርያም


የእረፍት ሰአት እንደተደወለ ግቢዉ በተማሪወች ጫጫታ ተሞላ እሮጠዉ ያልጠገቡ ህፃናት ከወዲህ ወድያ ይሯሯጣሉ ትንሽ የሚሻሉት ደግሞ ጥጋቸዉን ይዘዉ ጨዋታ ይጫወታሉ
በእድሜ እና ክፍል ከፍ ያሉት ተማሪዎች ሁሉም በየራሱ ሀሳብ ተዉጦ ገሚሱ ቆሞ ገሚሱ ተቀምጦ ያስባል የሚያወራም አለ።

ትንሳኤ ከጉዋደኛው ዮናስ አጠገብ ቢቀመጥም ሀሳቡ ያለዉ ግን ህሊና ጋር ነዉ አይኖቹን በማይታየዉ አየር ላይ ተክሎ እያሰበ ቆይቶ ፊቱ ላይ የጀግንነት የድፍረት ወኔ እየታየ
"የመጣው ይምጣ ዛሬማ እነግራታለሁ"
አለ እጁን ጨምድድ እያረገ
"እስቲ እናያለን"
ጉዋደኛዉ ዮናስ ትንሳኤን በሚያሳዝን አስተያየት እያየዉ
ይሄ ለመጀመርያ ግዜ አደለማ
እንደዚህ ሲለዉ ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ትንሳኤ የወደዳትን ያፈቀራትን ህሊናን በድፍረት ዛሬ የልቤን እነግራታለሁ ብሎ እንደዛሬዉ ይፎክር እና ልክ ህሊና ከጉዋደኞቿ ጋር በእነሱ በኩል ስታልፍ ምንም እንዳልተፈጠረ አንገቱን ደፍቶ ላብ በላብ ሆኖ ያሳልፋታል መጨረሻም ጉዋደኛዉ ዮናስ
"አይ አንተ አፍቃሪ"
እያለ ሲስቅበት ይዉላል
"ዛሬ ግን የመጨረሻ ነው ወደድኩሽ እንጂ ሌላ ምንም አልላት ታየኛለህ አሁን"
አለ ትንሳኤ የህሊናን መምጣት በጉጉት እየጠበቀ
ህሊና ከጉዋደኞቿ ጋር እያወራች ወደ እነ ትንሳኤ አቅጣጫ እየመጣች ነዉ
ዮናስ የጉዋደኛዉን የትንሳኤን ድፍረት ለማየት እና መልሷን ለመስማት ከትንሳኤ ጎን ጥቂት ፈንጠር ብሎ ቆሞዋል
ህሊና ቀስ እያለች እየተራመደች በትንሳኤ አጠገብ ስታልፍ ደፍሮ እንደማያዋራት የገመተዉ ዮናስ
"አዋራት ምን ያስፈራሀል!"
ይለዋል ድፍረት ለመስጠት ይመስል የትንሳኤን ትከሻ በእጆቹ ነካ ነካ እያደረገ
"ዛሬ ይቅር ነገ ልንገራት"
አለና ትንሳኤ ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ወደ ክፍል ተመልሶ ገባ ዮናስም እየሳቀ ተከተለዉ።

ትንሳኤ 18 አመት ከሞላው ወር አይሞላዉም ከቤት ወጥቶ የማያዉቅ ልጅ ነበር የእናቱ ህይወት ካለፈ በኋላ ግን አባቱ ሌላ ፀባይ ስላመጣ እሱንም ችላ ስላለዉ ወጣ ወጣ ማለት ጀምሯል ማንም የሚቆጣጠረዉ የሚናገረዉ
ሰው የለም ቢሆንም በትምህርቱ ጎበዝ ነዉ ጭንቅላቱ ፈጣን ነገሮችን ቶሎ የመቀበል ችሎታ አላቸዉ።

ከትምህርት ቤት ሲለቀቁ ትንሳኤ እና ዮናስ በጠዋቱ ጉዳይ እያወሩ ከትምህርት ቤቱ እየወጡ
ነው
"የኛ ደፋር እኔ እኮ የሚያስቀኝ አሁን ዛሬ እነግራታለሁ እያልክ የምትምለዉ ነገር ነው "
ሲል ዮናስ ትንሳኤን ገፍተር እያረገዉ እየቀለደበት
ትንሳኤ በአይምሮዉ ወደ ኋላ ሄዶ አስታወሰ የሆነ ቀንም አዋራታለሁ ብሎ ምሎ ተገዝቶ ህሊና አጠገቡ ስትደርስ አደለም መናገር መላ ሰዉነቱም የሚሰሩም አይመስሉም
በሩቁ እየሰረቀ ያያታል እንጂ አይን ካይን እንዲገጣጠሙ እራሱ አይፈልግም እንደሚፈራት አስታዉሶ
እሱም ትንሽ እንደመሳቅ አለና
"ለምን አሁን ወደ ቤት ስትወጣ አላናግራትም"
ትከሻው ላይ ያነገበዉን ቦርሳ ወደ ዮናስ እንዲይዝለት እየሰጠዉ
"የማታረገዉን አረ አታስቀኝ አርፈን ወደ ቤት እንሂድ እርቦኛል"
ዮናስ አልይዝም አለዉ ቦርሳዉን
"እንደዉም አሁን ብነግራት ጥሩ ነዉ ምክንያቱም ነገ ቅዳሚ ከነገ ወድያ እሁድ አንተያይም አላፍራትም እስዋም አስባበት መልሷን ትነግረኛለች "
ትንሳኤ ይሄን ሲል ዮናስ አዘነለት በልቡ ምን አይነት ፍቅር ቢይዘዉ ነዉ እያለ
ከትምህርት ቤቱ መዉጫ በር ፊት ለፊት ቆመዉ የህሊናን መዉጣት በአይናቸዉ እየፈለጉ ነዉ
ትንሳኤ አይኖቹን ወደ ትምህርት ቤቱ ህንፃ ሲወረዉር ህሊና በደረጃ እየወረደች ተመለከታት አይኖቹ ፈዘዉ እያያት ነዉ በድንገት እሷም አየችዉ ተያዩ አይኖቹን ሰበር አድርጎ ድጋሜ አያት አሁንም እያየችዉ ነዉ የልብ ልብ ተሰማዉ
"ትዉረድ ብቻ ማን እንደሆንኩ አሳይሀለዉ "
ፊቱን አበስ አበስ አፍንጫውን ነካ አርጎ በተጠንቀቅ ቆመ
ዮናስ ዝግ ባለድምፅ
"አሁን ካልነገርካት እኔ እነግርልሀለዉ አለው "
ትንሳኤ ደረቱን ነፋ እያደረገ
"እኔ ምን ሆኜ ነዉ አንተ የምትነግርልኝ"
አለና ደፈር ብሎ ከደረጃዉ ወርዳ ወደ መዉጫዉ በር ወደ ምትመጣዋ ህሊና መራመድ ጀመረ.....0

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ያልተቋጨ


#ክፍል_ሁለት


#በክፍለማርያም

ወደ ህሊና አመራ ትንሳኤ ከደረጃ እየወረደች ወደሱ ትይዩ እየመጣችዉ ያለችውን ህሊናን ሲያያት ፊቱ እየቀላና ድንብርብሩ እየወጣ በር ላይ እየጠበቀዉ ወዳለዉ ጉዋደኛዉ ጋር ደርሶ
"ባክህ ፈራሁዋት አፍቃሪዉ ምናምን እያልክ ደሞ እንዳትሰድበኝ"
እያለ ቦርሳዉን ከጉዋደኛዉ ተቀብሎ ወደ ቤቱ አመራ።

ቅዳሜ እና እሁድን በጠዋት እየተነሳ ለሰኞ የፍቅር ጥያቄ ለማቅረብ እና እስዋ ፊት ሲደርስ ወንዳወንድ ለመምሰል ፑሽ አፕ ፑል አፕ በተጨማሪም ቤቱ ዉስጥ በስንሚንቶ በሰራዉ ክብደት ስፖርት ሲሰራ ፍርሀቱን ለማስወገድ እንደ እብድ መስታወት ፊት ቆሞ ሲለፈልፍ ሰኞ ደረሰ።

እንደወትሮዉ የህሊና ክፍል ከትንሳኤ ክፍል ቀጥሎ ስለሆነ ባንዲራ ተሰቅሎ ተማሪ ወደየ ክፍሉ ከገባ በኋላ አይኗን ሳያይ መዋል ስለማያስችለዉ ቀስ እያለ እየተራመደ ወደሱ ክፍል ከመግባቱ በፊት የህሊናን ክፍል በር አሻግሮ በአይኑ ህሊናን መፈለግ ጀመረ።
የቀረች መስሎት ሊበሳጭ ነበር ነገር ግን ፊቷን አዙራ ወሬ እያወራች ስለነበር ነዉ።
መጥታለች በርቀት ሲመለከታት ደስ አለዉ ደስታው በምንም የማይተካ ነበር ፈገግ እያለ በልቡ ስላያት ተመስጌን መጥታለች እያለ ወደሱ ክፍል ሲገባ ጉዋደኞቹ በሳቅ ተቀበሉት
ከዮናስ ጎን የተቀመጠዉ እዮብ በትንሳኤ አፍቅሮ እንደዚህ መሆን አይስቅበትም ምን አልባት እሱም ከሌላ ፍቅር ሊኖርበት ይችላል ዮናስም ቢሆን በሀሪዉ ሆኖ የትንሳኤ ሁኔታ ስለሚገርመዉ ይስቅበታል እንጂ ጨክኖበት አልነበረም።
የህሊና ጉዋደኞች እነ ትንሳኤ ክፍል ስላሉ ሁሌ ህሊና ምሳ ለመብላት እነሱጋር ትመጣለች ትንሳኤም መጀመርያ በህሊና ፍቅር የወደቀዉ እሷ ስትመላለስ አይቷት ነዉ
ቀኑን ያስታዉሰዋል ምሳ ስዓት ላይ አሸናፊ የሚባሉ አብሮት አንድ ዴስክ ላይ የሚቀመጥ ተማሪ በስልኩ ሙዚቃ ከፍቶ ነበር
"ለምን አየኝ አለች ሳያት እሷን ብቻ
መዉደዴን ስነግራት አርጋዉ የጥላቻ.."
እያለ የሚቀጥል የመስፍን በቀለን ዘፈን ህሊና ቦርሳ አንግባ በምን እንደምትስቅ ባያዉቅም አነስአነስ ያሉ ነጭ ጥርሶቿን እያሳየች ወደነትንሳኤ ክፍል ገባች።
ወደ ክፍሉ ብቻ አደለም የገባችዉ እንደሙዚቃዉ በልቡ ግጥምና ዜማዋ ሳቋና ሁሉነገሯ ልቡ ዉስጥ ገባ።
ዛሬም ምሳ ስዓት ሲደወል ጉዋደኞቹ
"እንዉጣ"
ቢሉትም በልቡ ያሰበዉ ነገር ስለነበር
"አልወጣም የምፅፈዉ ነገር አለ"
ሲላቸዉ ጉዋደኞቹ ጥለዉት ወጡ
ትንሳኤ ጠዋት ቁርስ በልቶ ከቤቱ ስላልወጣ ሆዱ የርሀብ ጥያቄ እያሰማ ነበር
ህሊና ወደ ጉዋደኞቿ ክፍል ስትገባ ትንሳኤ ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ በረንዳ ወጥቷ በልታ እስክትጨርስ ሠንጎማለል ጀመረ።
እርቦታል ቤቱ ቅርብ ስለነበር ሄዶ መብላት ይችላል ነገር ግን ልቡ ዉስጥ ያለዉን ለመናገር ቻል አርጎ ከአሁን አሁን በልተዉ ጨረሱ እያለ በአይኑም ለማረጋገጥ እያያቸዉ ቆይቶ በልታ ጨርሳ እጇን ታጥባ እንደጨረሰች።
ለመጥራት ፈልጎ እንዴት መጥራት እንዳለበት ግራ ገብቶት ለጉዋደኞቹ እንደለመደዉ በቅርብ እርቀት ላይ ሆና አፉዋጨላት ደፋር ደፋር እያጫወተዉ ነበር።
ህሊና ዞራ እያየችዉ እኔን ነዉ ለማለት ሌባ ጣቷን ወደ ደረቷ አስጠግታ ስታሳየዉ አዎ ለማለት አንገቱን ከላይ ወደታች እየነቀነቀ በእጆቹ ጠራት
"አንዴ መጣሁ"
አለችዉና ወደ ጉዋደኞቿ ተመለሰች
ትንሳኤ ፍርሀት አይን አዉጥቶ ሂድ ሂድ ቢለዉም ቅዳሜና እሁድ የለፋበት ስፖርት ጥቂት ወኔ ሰጥቶት ደረቱን ነፍቶ ጠበቃት አጠገቡ ህሊና
"አቤት"
ብላ ስትጠጋዉ ግን ተንፍሶ ጥቂት ዝም አለና
እጁን እየዘረጋ
"ትንሳኤ"
አላት ስሙን ለመናገር እየፈለገ
"ህሊና"
ብላዉ የሚነግራትን ለመስማት አይን አይኑን አየችዉ
ትንሳኤ አይኗን እያየ በልቡ
"አቤት ሲያምር ደሞ የሆነ የሚያሳዝን ነገር አላት "
ብሎ በድንጋጤ ሊያዋራት አፉን ከፈተ
"ካየሁሽ ቀን ጀምሮ እወድሻለሁ"
የማይባል ነገር አለ
መሸወዱ አመታት አልፎ ነዉ የገባዉ እንዴት አዉርተሀት በደንብ እንኳን አይታህ የማታዉቅ ሴትን እንደዚህ ይባላል

💫ይቀጥላል 💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1👍1
#ያልተቋጨ


#ክፍል_ሶስት


#በክፍለማርያም

...እንዴት ይባላል
ህሊና ደንገጥ ብላ አየችዉ እብድም ሳይመስላይ አይቀርም ፊቷ ላይ የመደንገጥ እና የመገረም የሚመስል ድባብ ይታይባታል ቶሎ ለመራቅ አስባ አፏ ላይ የመጣላትን

"ጉዋደኛ አለኝ"

ብላዉ ጥላዉ ወደ ጉዋደኞቿ ገባች።
የዛን ለት ወድያዉ እሷ ጥላዉ ስትገባ ደብተሩን እንኳን ሳይዝ እየተበሳጨ እየተመናቀረ ከትምህርት ቤቱ ግቢ ወጣ
ግራ የተጋባ ስሜት መናገሩ የልቡን መተንፈሱ ቢቀለዉም የመለሰችለት መልስ ያሳየችዉ ፊት ግን አስከፍቶታል
አፍቃሪ የሚጠብቀዉ እንደልቡ ፍላጎት ህልሙ ተሳክቶ ማየት ነዉ
ህይወት ግን ወጥንቅጧ የበዛ ስለሆነ አንዳንዴ በአንድ ወገን ያለ ፍቅር ለብቻዉ እንደሻማ በርቶ ይቀልጣል እንጂ አይሰምርም
መንገድ ላይ እየተሪመደ አንድ መንገድ ዳር የተቀመጠ ሲጋራ የሚያጨስ ከትንሳኤ እድሜ የሚበልጥ ልጅ
"ና" ብሎ ጠራዉ
ትንሳኤ እየተወዛገበ

"አቤት" እያለ ተጠጋዉ
"ስንት ብር ይዘሀል "
እያለ ልጁ ቆመ
ትንሳኤ ለራሱ ከባድ የፍቅር ረመጥ ዉስጥ ነዉ አደለም የማንም ጉልበተኛ ነኝ ባይ
"ና ያለህን አምጣ" ብሎት
ትንሳኤ ሳያንገራግር ወደ ልጁ ቦክስ ሰደደ ልጁም ወደ ትንሳኤ የመልስ ምት ላከ ገላጋይ ባይገባ ሁለቱም ይጎዳዱ ነበር። ትንሳኤን ሲያገላግሉ የያዙት ሰወች
"ምን አይነት ልብ ነዉ ያለህ ከታላቅህ ጋር ትጣላለህ"
እያሉ ሲመክለሩት የልብ ልብ ተሰምቶት ድጋሜ ካልተጣላሁ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ቢልም ጉልቤ ለመሆን የሞከረዉ ልጅ ግረግሩ እና የትንሳኤ ፉከራ ስላልጣመዉ ከአካባቢዉ ተሰወረ።

በነጋታዉ ትንሳኤ ወደ ክፍል እንደገባ ዮናስ በፈገግታ ተቀበለዉ
"ጀግናችን ወሬ አይደበቅም ስታዋራት ሰው አይቶካል ምን ተፈጠረ ጭዌዉን እንደወረደ"
ሲለዉ ሌሎች ጉዋደኞቹም በተሰበሰቡበት ትንሳኤ የተፈጠረዉን በሙሉ ነገራቸዉ ዮናስ ተበሳጨ
"አረ አፍቃሪዉ ተበልተሀል የሆነ በሙድ አትገባላትም ነበር ዝም ብለህ እወድሻለሁ አረ አይነፌክስ"
ትንሳኤ ላይ የእዉነት ወረደበት ተናዶ
ለትንሳኤ መልካም ስለሚያስብ ነበር
ምክንያቱም ሲጨነቅ ስለሷ ሲያስብ የእዉነት እንደወደዳት አስተዉሎታል
ትንሳኤም ግልፅ ስለሚያወራ ቀንም ማታም ስለሷ ቢያወራ ስለማይጠግብ ሁሉንም ስሜቱን ሳይደብቅ ይነግራቸዉ ስለነበረ ነዉ
በተቃራኒዉ እዮብ
"ዋናዉ ማዋራትህ ነዉ አንበሳ እኔኮ ትመቺኛለሽ"
ሲል በእጁ የትንሳኤን ትከሻ ከነካ በኃላ
"በቅርቡ የሆነ ብር አገኛለሁ እጋብዝሀለዉ ጭንቀትህንም ትረሳለህ"
ሲል አከለበት
ታሪኩ እንዲህ እያለ ቀጠለ ትንሳኤ እወድሻለሁ ካላት በኋላ ህሊና ገና ከሩቁ ትንሳኤን ካየችዉ መሸሽ መንገድ መቀየር በተለይ የትንሳኤ ክፍል ካሉት ጉዋደኞቿ ጋር ትንሳኤን ላለማየት እሱ ክፍል መምጣት ተወች
በተለይ የጉዋደኞቿ አይን ትንሳኤ ላይ በረታበት በአይናቸዉ ያወራሉ ሁሌ ሲያያቸወ እያሽሟጠጡበት እየተረቡት ይመስለዋል አንዳንዴ ወንድ ቢሆኑና ብደባደባቸዉ ብሎ ያስባል
በአይናቸዉ ጥንብእርኩሱን ያወጡት ጀመር።

ህሊናም ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ተጠየፈችዉ ትሸሸዉ ጀመር
ትንሳኤ ፍቅር ብሎ የጉዋደኛዉን የዮናስን ምክር ሳይሰማ ዘባርቆ የተምታታ ስሜት ዉስጥ ገብቶ
በተቀመጠበት ስዓት እዮብ
"ፈታ ላርግህ ወንድሜ"
ብሎ ይዞት ከትምህርት ቤቱ ግቢ ምሳ ሰአት ላይ ይዞት ወጣ
በአቅራቢያቸዉ ካለ ጠላ ቤት ገብተዉ የሚጣፍጥ ድንች በሚጥሚጣ ከበሉ በኋላ ጠላ በጣሳ ይዘዉ እየጠጡ ተቀመጡ
ትንሳኤ ስለ ህሊና መለዋወጥ በልቡ እያሰበ ጠላዉን መጎንጨት ተያያዘዉ ወደ ሞቅታ ሲገባ ተነስቶ ቆሞ
የለበሰዉን የትምህርት ቤቱን ሸሚዝ አዉልቆ በቲሸርት ሆኖ ወደ ትምህርት ቤቱ በፍጥነት መራመድ ጀመረ
ሁኔታዉ ያልጣመው እዮብ ሂሳብ ከፍሎ እየሮጠ ተከተለው
ትንሳኤ ደረጃ ወጥቶ ወደ ህሊና ክፍል ሊደርስ ሲል አፍንጫዉን ነካ አርጎ አየር ከሳበ በኋላ
ወደ ህሊና ክፍል ስትት ብሎ ገባ

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
👍1
#ያልተቋጨ


#ክፍል_አራት


#በክፍለማርያም

...ስተት ብሎ ገባ ህሊና ጥግ ላይ ወሬ እያወራች ነበር ስታየዉ በትንሹ ደንገጥ ብላ አፈጠጠችበት
ትንሳኤ ፊት ለፊቷ ቆሞ እጁን ወደ ኋላ ማረጉን ሲያስተዉል አሁን የመጣሁት ልለምናት እንዳይመስላት አለና እጆቹን አፍታቶ የእስዋ ዴስክን አሰደግፏቸዉ ጎንበስ ብሎ ቆመ
ህሊና ምን ሆኖ ነዉ እያለች በመገረም ታየዋለች

"ምን ሆነሽ ነዉ ግን"
አላት ቆጣ ብሎ

"ምን ሆንኩ"

አለችዉ ለስለስ ባለ ዜማ ባለዉ አነጋገር
ትንሳኤ ለአፍታ የጎዋደኞቿ ግልምጫ የእሷ መደባበቅ የእሱ የፍቅር ጥያቄ አለመሳካት ከጠጣዉ መጠጥ ጋር ተደራርቦ
"የወደድኩሽ መስሎሽ ነዉ እንደዚህ የሚያረግሽ አልወድሽም እሺ አልወድሽም"
ጮክ ብሎ ተናገረ ጉዋደኛዉ እዮብ ደርሶ እንዳይመታት ይሄ እብድ እያለ ይዞት ሊወጣ ሲሞክር
ትንሳኤ አስቸገረ አፉ
"አልወድሽም አልወድሽም "
ይበልእንጂ አሁንም ልቡ ዉስጥ ናት
ህሊና ምን ነካዉ በሚል አስተያየት እያየችዉ ትንሳኤ በጉዋደኛዉ እየተጎተተ ወጣ።
ከዛን ቡሀላ ህሊና ጭራሽ ከአይኑም እየራቀች መጣች
ሁሌ ሲገባ ግን በእሷ ክፍል እያለፈ አንገቱን ሰገግ አርግ በአይኖቹ ሳይፈልጋት ክፍሉ አይገባም
የጉዋደኞቿም አይን አፈር ከመሬት የሚያበላ ነበር
በዛ ሁሉ መሀል ግን ጉዋደኞቹ ሲያስባት እና ሲያስታዉሳት በቀልድ እያሳቁ እያስረሱት በተለይ ጠጥቶ
"አልወድሽም አልወድሽም"
ብሎ የጮሀዉን እያነሱ እሱንም ሲያፅናኑት በአይን ብቻ ጠዋት እና ከትምህርት ቤት ሲለቀቁ ስትወጣ ተደብቆ እያያት አመቱ አልቆ ክረምት ሲገባ በልቡ ብቻ ይዞ እያሰባት ተቀመጠ
በዛን ክረምት ትንሳኤ ብዙ አይነት መፅሀፍቶችን ሲያነብ ከጉዋደኞቹም ጋር ሲያዝግ ከሴቶች ጋር መቀራረብ መነጋገር የመሳሰሉት ፍርሀቶቹ ዘበት ሆነዉ ጠፍተዉ
በሚቀጥለዉ አመት ትምህርት ሲጀምሩ ምላስ አርዝሞ ከትምህርቱ ቀንሶ ሌላ ሰዉ ሆኖ ገባ
ያልተቀየረዉ የህሊና ፍቅር ግን አሁንም ልቡ ዉስጥ ነበር ትምህርት ቤት ውስጥ መጀመርያ ከህሊና ጋር ሲተያዩ በረንዳ ላይ ቆማ ነበር
እንዳያት ደስ አለዉ ፈገግ እያለ ተጠጋትና
"እዚህ ምን ትሰርያለሽ ገብተሽ አትማሪም"
አላት ህሊና አይኖቿን ወደ ላይ አርጋ
"ምን አገባህ"
አለችዉ
"ዋ ስትፎርፊ እንዳላይሽ"
እያለ ቆመዉ ወደሚጠብቁት ጉዋደኞቹ አመራ።
የሆነቀን ምሳ ሰአት ናፍቃዉ ወደሷ ክፍል አመራ
አሁንም ቢሆን ግን ከሌላ ሴት ልጅ ጋር ሲሆን እንደሚያወራዉ ከበፊቱ ፍርሀቱ ቀንሷል እንጂ እሷ ጋር ሲደርስ ቃላት ይጠፉበታል ሲገባ ነጭ ወረቀት ላይ ስዕል እየሳለች አገኛት
"ቆይ እኔ ልሳልልሽ"
እያለ እስራሱን ከእሷ እጅ ተቀበላት ከጎኗ ያሉት ገዋደኞቿ እሷ እርሳሱን ለማስመለስ ስትሞክር እያዩ ይስቃሉ
ትንሳኤ በቆመበት ሳያስበዉ አፍንጫውን ሲነካ የደረቀ ን ጥ ከአፍንጫዉ ወድቆ ወረቀቱ ላይ አረፈ ህሊና
"እእይይይይይ"
እያለች ወረቀቱን አራገፈችዉ።
ትንሳኤ ጀርባዉን ሲያልበዉ ይታወቀዋል
ከአጠገቧ ገፋ አርጓት አይኑን በጨዉ አጥቦ ተቀመጠ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
👍1
#ያልተቋጨ

#ክፍል_አምስት (የመጨረሻ ክፍል)

#በክፍለማርያም

ህሊና
"አይይይይይይይ" እያለች ወረቀቱን አራገፈችዉ ትንሳኤ ጀርባዉን ሲያልበዉ ይታወቀዋል
ከአጠገቧ ገፋ አርጓት አይኑን በጨዉ አጥቦ ተቀመጠ
አንዳንዴ ተዋረድ ካለህ እንደዚህ ነዉ
አጠገቧ ተቀምጦ እጆቹን ወደ ሰደርያዋ ኪስ በቀስታ ሰዶ ከኪሷ ሶፍት አወጣ
አንደኛዋ ጉዋደኛዋ አይታዉ ሳቀች ህሊናም እንደወሰደባት ስታዉቅ ተናዳ አፈጠጠችበት
ትንሳኤም በሶፍቱ አፍንጫዉን እያበሰ በመዋረዱ በልቡ በጣም እያዘነ ሲወጣ በር ላይ ዮናስ ጠበቀዉ

"ባክህ ተዋረድኩልህ"

አለዉ ትንሳኤ በንዴት ከንፈሩን ነክሶ
"ምን ተፈጠረ"
ሲል ዮናስ አፋጠጠዉ
"ደረቅ መሆኑ ጠቅሞኛል ...."
እያለ ትንሳኤ የተፈጠረዉን ነገረዉ ከዛን ቀን ጀምሮ ነገሮች በህሊናና በእሱ መሀል ሴጣን እንዳለ ተገነዘበ እየወደዳት እያፈቀራትም ቢሆን ሌላ ሌላ ነገር ዉስጥ ገባ
የሆነ ቀን ሲያገረሽበት ለጉዋደኛዉ
"ጥራልኝ ላዋራት ናፈቀችኝ"
አለዉ
"ምን ጣጣ አለዉ"
ተከተለኝ አለዉና ወደ ህሊና ክፍል አምርተዉ ትንሳኤ በረንዳ ሲቆም ደፋሩ ጉዋደኛዉ ህሊናን አቀፍ አርጎ እያዋራት ይዧት ከወጣ በኋላ
"ተነጋገሩ "
ብሏቸዉ ትንሳኤን እና ህሊናን አገናኝቷቸዉ ሄደ።
"የመጀመርያ ቀን ቦርሳ በትከሻሽ ይዘሽ እየሳቅሽ ስትገቢ ነዉ ያየሁሽ
ደሞ በግራ እጅሽ ነዉ የምትፅፊዉ አደል"
ትንሳኤ ሊያዋራት የመጣዉ ሌላ ቢሆንም የልቡን በቻለዉ ቋንቋ መናገር ቀጠለ
ነገር ግን የህሊና መልስ
"ጉዋደኛ አለኝ አንደዉም አሁን እራሱ ሰዉ አይቶኝ ካንተ ጋር መቆሜን እንዳይነግሩት"
አለችዉ
ሀሳቡ ተበታተነ እኔ ነኝ እንጂ እስዋ አትወደኝም ሲል አስቦ በልቡ እሳት እየነደደ ዉስጡ በንዴት ግሎ
"እሺ ስታገኚኝ ግን አትዝጊኝ ሰላምታ እንኳን"
"እሺ"
ብላዉ ጥላዉ ገባች
ነገር ግን አንዴ ታክሲ ስትጠብቅ ከሩቅ አይቷት በደስታ ክንፍ ብሎ ሲጠጋት እየገላመጠች እራቀችዉ
ተከትሏት ጥቂት ለማዋራት እየሞከረ ተከተላት ነገር ግን እሷ ማዋራት አልፈለገችም
ትንሳኤ አመታት አልፈዉም አሁንም እንደ መጀመርያዉ ቦርሳ ይዛ እየሳቀች ስትገባ ያለዉ ምስል አይምሮዉ ዉስጥ አለ ፍቅሯ አመታት አልፎ እንደ ትላንት ይታወሰዋል መልኳ አይኗ ሰዉነቷ አወራሯ ሁሉ ነገሯ አይረሳዉም
ማፍቀር ማለት የማያገኙትን ሰዉ በተስፋ እንደመጠበቅ ነዉ ስሜቱ ያማል ያስከፋል መንገዱ ዉስጥ ግን አይረሴ ታሪኮች አሉ
አንድ ቀን አጊንቷት ያለ ፍርሀት ያለ ሰቀቀን እንደ ጉዋደኛ እንኳን ቢያዋራት ህልሙ ነዉ አንዳንዶች ለቀልድ ተዋዉቀዉ ይጋባሉ አንዳንዶች የእዉነት አፍቅረዉ ያጣሉ አለም ትገርማለች ፍቅርም ይገርማል ይሄ ታሪክ ለትንሳኤ የህይወቱ ክፍል ለህሊና ተራ ወሬ ሊሆን ይችላል
ትንሳኤ በልቡ የያዘዉ ታሪክ ነዉ ህሊና የናቀችዉ ተራ ነገር
ትንሳኤ በህሊና መፍረድ አቁሟል ምክንያቱም ሰዉ የፍላጎቱ ዉጤት ነዉ
የእሷ ምርጫና ፍላጎት የራሷ ዉሳኔ ነዉ

💫አለቀ💫

ነገ በተለመደው ሰዓት #ህመም_ያዘለ_ፍቅርን #ምእራፍ_ሁለት እንጀምራለን እሰከዛው መልካም ቆይታ🙏
👍3