አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
458 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የወዲያነሽ


#ክፍል_አርባ_ሶሰት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...ስደበኝ! ወይ መቆየት! አሁንሜ ብለህ ብለህ ስለ ሕጉ አስተያየት ሰጪና እርማት አቅራቢ ሆንክ! ስንት ሊቃውንት የደከሙበትንና ያረቀቁትን ሕግ አንተ ስላቃለልከው አይቀልም።
መንገርስ ልክ ልክህን እነግርህ ነበር፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል ይልቅ ወሬሀን ጠርቅ!".ብሎ የሚሆነውን እያሳጣው በቅምጡ ተቁነጠነጠ፡፡ ሕሊናው ጉዳዩን ቢረዳም
በፈቃደኛነት እንደማይረታ፣ በጨቋኝነት የተሞላ ሕሊናው በቀላሉ እጁን እንደማይሰጥ አወቅሁ፡፡ ቢሆንም የእኔ ሕሊናና ወኔ እየሞቀና እየጎለመሰ ሲሔድ
ያ በከንቱ ግብዝነት የተወጠረው የእርሱ ሕሊና ግን ቁልቁል ሲሟሽሽ ታየኝ።

በዚሀ ልጅ እናት ላይ..» በማለት እንደገና ቀጠልኩ፡፡ «በከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የመኻል ዳኛ ሆነህ አምስት ዓመት እስራት ፊርደሀባት ነበር፡፡ በሕይወቷ ውስጥ አምስት ዓመት ብቻ ሳይሆን የሕይወቷ ብዙ
ክፍል እንዲበላሽና እንዲሰናከል ተደርጓል። ወደ ዋናው ፍሬ ነገር ልመለስና በሕግና በእውነት» ስም በተቋቋሙት ፍርድ ቤቶቻችሁ ወንጀለኛ እያላችሁ ከምትፈርዱባቸው ንጹሐን ሰዎች ይልቅ በእናንተ እጅግ ጉልህ በሆነ ጥፋትና በሚጨበጥ ኃጢኣት ወንጀለኛ በሆናችሁት ሰው በላ ሰዎች የተሞላ ነው:: ወደ ልጄ ጉዳይ ልመለስና፣ ይህ ልጅ በዕጓለ ማውታ፣ እናቱ ወህኒ ቤት ውስጥ እየማቀቀች ሳይተያዩና ሳይገናኙ በጠቅላላው አምስት ዓመት ተለያይተው ቆይተዋል፡፡ እዚህ ላይ ነበር ምስጢሩ የራሱን ጉድጓድ ቆፍሮ የራሱን ሕይወት
የሸሽገው:: ያን ሁሉ ስቃይና ችግር የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ» ብዩ በልበ ሙሉነት እንደገና ተዝናናሁ፡፡

አባቴ ስቅላት እንደ ተፈረደበት ሰው ወዙ ደረቅ። እርሱ በተደፈርኩ
ባይነት፣ እናቴና እኅቴ በድንጋጤ እንደ ተጨነቁ እኔም የዓላማዬን መጨረሻ ለማሳመር ሳሰላስል በቤቱ ስጥ ጊዜያዊ ጸጥታ ሰፈነ። የአባቴን ሕሊና ለማንበርከክ፣ ሲጨቁነኝና ሲያፍነኝ የኖረውን የበላይነቱን ለመሰባበር እእምሮዬ
ሙሉ የማጥቃት ዝግጅቱን ቀጠለ።

«ልጨርስልሃ?» አልኩት የሐሳቤን ደጀን ካጠናከርኩ በኋላ፡፡
«ደግሞ ምን ቀረህ? ምን ቀረኝ ልትል ይሆን?»
«እኔ የማሳይህና የማሳውቅህ ወርቁን ብቻ ሳይሆን የወርቁንም ማዕድን ጭምር ነው::
“ይኻ ሁሉ ዝብዝብ ምን ለማለት ፈልገህ ነው?»
«ባጭሩ ላስረዳህ እችላለሁ፡ የዚህ ልጅ እናት የወዲያነሽ አሸናፊ ያን ሁሉ መከራና ሥቃይ ካሳለፈች በኋላ እንደገና ከእኔ ጋር ትገናኝተን በአሁኑ ጊዜ እጅግ የማከብራትና የምወዳት ባለቤቴ ነች!! »

«የወላዲተ አምላክ ያለህ! ምን? ምን አልክ አንተ!?» ብሎ እንደ ብራቅ ጮኸ፡፡ «የወዲያነሽ ሚስቴ ነች፡፡ የምንኖረውም አብረን ነው!» ብዩ በተመሳሳይ ጩኸት መለስኩለት፡፡

ከመቀመጫው ላይ በቁጣ ተነሥቶ «ውጣ! ውጣልኝ! ቅሌታም ክብረ ቢስ! ዘር አሰዳቢ! እንዴት አንተ! መድኃኒ ዓለም ያዋርድህ! ኧረ ሂድልኝ! አረ
ውጣልኝ! ክብረ ቢስ ዘር አሰዳቢ!» ካለ በኋላ ማንቁርቱን የታነቃ ያህል ድምፁ እየሰለለ «አንዳንድ ያልተባረካ ሽንት ይኸው ነው! ያህያ ሥጋ...» ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ፊቱ ፍም መስሎ ተጨማደደ፡፡ ጭንቅላቱ ላይ በመሸጎሪያ እንደ ተመታ ሰው መኻል አናቱን በቀኝ እጁ መዳፍ ጫን ብሉ አቀርቅሮ ተቀመጠ።
እውነት በዙሪያው ተጎማለለች! ከአጭር የዝምታ ቆይታ በኋላ ዐይኑ ቀይ ሽንኩርት መስሎ እንደ ሰካራም ተግተርትሮ ተነሣና «ሰበብ አትሁንብኝ! ካህያህም ከውርንጭላህም ጋር ገደል ግባ!! » ብሎ ወደፊት ራመድ አለ።
አልተነቃነቅሁም፡፡ አልተጠጋም፡፡ ነገር እንደሚያጣራ ሰው ከወደ ትከሻው ሰገግ ብሎ አንገቱን ሰብሮ ቆመ፡፡ በቁጣ የታግለበለበው ደሙ በግንባሩ ላይ አሽቆለቆለ። ፊቱ የጋለ የመቆስቆሻ ብረት መሰለ። እህቴና እናቴም ቁንጢጥ እንደ ተጠሩ
ሕፃናት ተርበተበቱ። ጋሻዬነህ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ ጨምድዶ ያዘኝ።

ልጄን በተዝናና ወኔ አቅፌ «አዎ ብትወዱም ብትጠሉም የወዲያነሽ ባለቤቴ ናት! ሕዝብ አሕዛብ እንዲሰማና እንዲያውቅ አደርጋለሁ፡፡ የሀብታምና
የከበርቴ ልጅ ብትሆን ኖሮ ይህ ሁሉ የተቃለለውና የተዋረደው አጥንቷ ልዩ ስምና ክብር ይሰጠው ነበር። እንኳን እናንተ እኔ ራሴ የገፈፍኳትንና የነጠቅኋትን
መብትና ነጻነት ታገኛለች፡፡ ይህ የውዴታ ጉዳይ አይደለም። ጤዛ የምታህለዋን ጣጣ ስትፈሩ ተራራ የሚያህል መከራ ይጠብቃችኋል። አሁንም በድጋሚ የማረጋግጥልህ የወዲያነሽ የምወዳት ባለቤቴ ናት:: የአብራኬ ክፋይ! የጋሻዬነህ
እናት ናት!» ብዩ ተጎማለልኩ።

«በሕግ! በሕግ አምላክ ውጣልኝ! ዛሬ ጉድ ይፈላል! አስወጡልኝ
ብያለሁ!» ብሎ ተመልሶ ተቀመጠ የትንሽ ትግል ፍጻሜና የአነስተኛ ፍልሚያ መደምደሚያ ሆነ፡፡
ጋሻዬነህን ይዤ ወደ ውጭ ስወጣ የወዲያነሽ ከምድር ቤቱ በር አጠገብ ከለል ብላና ዐይኗን በድንጋጤ በሰፊው ከፍታ «ምናሉህ? የእኛ ነገር እንደምን
ሆነ? ፍሬ ነገሩ አይሰማም እንጂ ስትጫጨሁ ነበር» ብላ ፍርሃት በተጠናወተው መልስ ጠባቂ ስሜት ጠየቀችኝ፡፡ ሁሉም ነገር እንዳሰብኩትና እንደ ፈለግሁት
ሆነ። ፍርሃትንና የበታችነትን እንዲሁም የሕሊና ባርነትን ተቋቁሜያቸዋለሁ፡፡
እንዲያውም እየደመሰስኳቸው ነው። አትፍሪ! እኒ ምንጊዜም ቢሆን አብሬሽ አለሁ። የሚለያየን ምንም ኃይል አይኖርም፡፡ የእኒንና የአንቺን ዘላቂ አንድነት የሚጠሉና የሚቃወሙ ሁሉ ጠላቶቻችን ናቸው። እንዳንቺ በመከራ ማጥ ውስጥ የሚሠቃዩና የተበደሉ ሁሉ አብረውን ይቆማሉ፡፡ በአባቴ ቤት ብቻ ሳይሆን በመሰሎቹ ፊት ሁሉ እየቆምን ማንነታችንን እናስመሰክራለን። ይህ ከትልቁ
ዓላማና ረጂም ግብግብ ውስጥ ቅንጣቱ ቢሆንም ከእኛ ጋር ላለችውና ወደፊት ይበልጥ እየደመቀች ለምታይለው እውነት አንድ ርምጃ ነው:: ነይ እንሒድ!
ከእንግዲህ እኔና አንቺ የምናጠቃውም ሆነ የምንከላከለው በአንድነት ነው» ብዩ ቀኝ እጅዋን ይዤ ከምድር ቤት ወጣን።

እባክህ ይቅርብህ! በዘመድና በሽማግሌ ይሁን። በዚሁ ወደ ቤታችሁ ሒዱ» ብላ የውብነሽ በተሰበረ ሕሊና ለመነችኝ፡፡
ፊቴን በቁጣ ከሰከስኩና "የመጣንበትን ጉዳይ ከፍጻሜ ሳናደርስ አንሔድም። ከእንግዲህ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አንመለስም። እንደ ዛፍ ቀጥ
እንጂ እንደ ምድር እንቧይ አፈር መሳስ የለም፡፡ ይዣት እገባለሁ። የዛሬዋን ዕለት ዕቅዴን ከፍጻሜ አድርሼ በሙሉ የሕሊና ነጻነትና ድል እንመለሳለን ዕቅዱን ነገርኳት አመዳይ እንደ መታው እህል ገረጣች።

የወዲያነሽ የንግግራችን ጠቅላላ ይዘት ስላልገባት የውብነሽ ምንድነው የምትልህ?» ብላ ትኩር ብላ አየችኝ:: አቅጣጫችሁን ለውጡ፡፡ መሬት ሳሙ፡ ጫማ ላሱ ነው የምትለን፡፡ እኔ ግን መሽቆጥቆጥ ይበቃናል፡ ለሥቃይሽና ለበታችነትሽ የማብቂያ ድንበር እንሠራለታለን፡፡ የራሣችንን መብት በትግል
ማሳወቅ እንጂ መለመንና ማጎብደድ የለብንም። የሚበድሉንና የሚጨቁኑንን
ሁሉ እውነትን ይዘን እንጋፈጣቸዋለን እላለሁ:: እኔ የአንቺን የየወዲያነሽን ያህል
ያልተበደልኩና ያልተጨቆንኩ ብሆንም በአዕላፋት የጠላት ሠራዊት መካከል አንዱን ብቻ መግደል ጠላትን ድል ”ማድረግ አይደለም። ቢሆንም » ብዬ ገና
1👍1