#እኔ
በፀጉሮችሽ መሐል እልፍ ፂም ባገኝም
የት ነበረች ብዬ ሳስብ አልገኝም
#እኔ
የሺ ወንድ ጠረን ብስብም ከአንገትሽ
እከራከራለሁ አይደለም ካንጀትሽ
#እኔ
በጡቶችሽ ጫፎች እያየሁ አሻራ
እጠርግልሻለሁ ቆጥሬ እንዳቧራ
ይልቅስ የእኔ
ስጋቴ
ፍርሃቴ
ያ ሁሉ ተባዕት እንዳያስጨንቁሽ
ያ ሁሉ ተባዕት ቀምሰው እንዳይርቁሽ
የሚያብሰከሰከኝ ሲስሙ እንዳያንቁሽ
(ነበር)
#እኔ
ሁሉን ደስታ አይተሽ
እንደፀሀይ ገላ ሙቀሽ
ስትጨርሺ
እንዳላይሽ አዝነሽ
እንዳንላይሽ ደርቀሽ
(ነበር)
እንጂ
ያዘንሽ ቀንም ከአጠገብሽ አለሁ
የደስታሽን ቀብር አብሬ እውላለሁ
ያንቺን የሀዘን ቀን እንደኔ ቆጥሬ
እንጀመር እላለሁ መውደድን ከዛሬ
ከዛሬ
ከአሁን
ከቅፅበት
ህይወት ስታበቃ እኛ እንጀምረበት
እላለሁ፡፡
እላለሁ
እንዳዲስ እንጀምር እንዳልተለመደው
ይሰፋል እላለሁ የተቀዳደደው
ይፀናል እላለሁ የተንገዳገደው
እላለሁ፡፡
እንደማቱሳላ
አኑረኝ
ቀኔን ሳላሰላ
አክርመኝ፡፡
ላቧን እስክትጨርስ
በወንድ እንክትርስ
ዓይኗ እስከሚሟሟ
እስከሚደባለቅ እውንና ህልሟ
አኑረኝ እላለሁ
አክረመኝ እላለሁ
እድሜ ስጠኝ ብዬ እለማመናለሁ
ለምን
ሁሉም የጣለሽ ቀን እኔ አነሳሻለሁ፡፡
(እስከዛ ግን አለሁ)
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
በፀጉሮችሽ መሐል እልፍ ፂም ባገኝም
የት ነበረች ብዬ ሳስብ አልገኝም
#እኔ
የሺ ወንድ ጠረን ብስብም ከአንገትሽ
እከራከራለሁ አይደለም ካንጀትሽ
#እኔ
በጡቶችሽ ጫፎች እያየሁ አሻራ
እጠርግልሻለሁ ቆጥሬ እንዳቧራ
ይልቅስ የእኔ
ስጋቴ
ፍርሃቴ
ያ ሁሉ ተባዕት እንዳያስጨንቁሽ
ያ ሁሉ ተባዕት ቀምሰው እንዳይርቁሽ
የሚያብሰከሰከኝ ሲስሙ እንዳያንቁሽ
(ነበር)
#እኔ
ሁሉን ደስታ አይተሽ
እንደፀሀይ ገላ ሙቀሽ
ስትጨርሺ
እንዳላይሽ አዝነሽ
እንዳንላይሽ ደርቀሽ
(ነበር)
እንጂ
ያዘንሽ ቀንም ከአጠገብሽ አለሁ
የደስታሽን ቀብር አብሬ እውላለሁ
ያንቺን የሀዘን ቀን እንደኔ ቆጥሬ
እንጀመር እላለሁ መውደድን ከዛሬ
ከዛሬ
ከአሁን
ከቅፅበት
ህይወት ስታበቃ እኛ እንጀምረበት
እላለሁ፡፡
እላለሁ
እንዳዲስ እንጀምር እንዳልተለመደው
ይሰፋል እላለሁ የተቀዳደደው
ይፀናል እላለሁ የተንገዳገደው
እላለሁ፡፡
እንደማቱሳላ
አኑረኝ
ቀኔን ሳላሰላ
አክርመኝ፡፡
ላቧን እስክትጨርስ
በወንድ እንክትርስ
ዓይኗ እስከሚሟሟ
እስከሚደባለቅ እውንና ህልሟ
አኑረኝ እላለሁ
አክረመኝ እላለሁ
እድሜ ስጠኝ ብዬ እለማመናለሁ
ለምን
ሁሉም የጣለሽ ቀን እኔ አነሳሻለሁ፡፡
(እስከዛ ግን አለሁ)
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍32❤15🔥3
እግዜሄር የጨበጣቸው ''ሳያቅፈን'' ብለው ሲቆጡ
እግዚሄር ያቀፋቸው
እልፍኙ ገብተን ካልበላን- ብለው በኩርፊያ ሲመጡ
የግዚያብሄር እልፍኝ የገቡት
እንጀራ ሳይሰጠን ብለው-ቂም ዘግነው ይዘው ሲወጡ
ባይ ..ደነቀኝ....ባይ ገረመኝ..
ምናለ እኔን ላ'ንድዜ
ገላምጦኝ ደስታ ቢገድለኝ።
🔘red-8🔘
እግዚሄር ያቀፋቸው
እልፍኙ ገብተን ካልበላን- ብለው በኩርፊያ ሲመጡ
የግዚያብሄር እልፍኝ የገቡት
እንጀራ ሳይሰጠን ብለው-ቂም ዘግነው ይዘው ሲወጡ
ባይ ..ደነቀኝ....ባይ ገረመኝ..
ምናለ እኔን ላ'ንድዜ
ገላምጦኝ ደስታ ቢገድለኝ።
🔘red-8🔘
🥰41👍17❤13
#አምስቱ_የስሜት_ህዋሳት_ስንት_ናቸው?
.
እኔና እሷ ሳንፋቀር..
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ የምናውቀው አምስት ነገር
በአይናችን እናያለን
በእጃችን እንዳስሳለን
በምላሳችን እንቀምሳለን
በጆሯችን እንሰማለን
ባፍንጫችን እናሸታለን ፣ የሚል ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንፋቀር..
ካንደበቷ ቃል ሳይወጣ ፣ በዝምታ ስትናገር
የከንፈሯን ንቅናቄ
እያየሁኝ የምሰማት ፣ ያለችኝን አንዳች ነገር.
አይን ማለት
በዚያ ሰአት ፥ መስሚያ ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንጣላ
ስለጃችን ከተማርነው ፤ ከመዳሰስ ስሜት ሌላ
ሌላ ስሜት ተፈጥሮብኝ ፥ ያንደበቴን ቃል ሰስቼ
አነዳች ነገር ስናገራት ፤ የመሀል ጣቴን አውጥቼ
ስድብ መሆኑ ሲገባት
ምላሷን ስታወጣብኝ
ስላቅ መሆኑ ሚገባኝ
እጅ ማለት ሌላ ስሜት ፥ ምላስ ማለት ሌላ ነገር
መቅመስ መዳበስ ያልሆነ ፥ ያልተማርነው ነገር ነበር፡፡
ብቻ
ብቻ
እኔና እሷ ስንጣላ ፥ እኔና እሷ ስንፋቀር
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ ብንማርም አምስት ነገር
እኛ ኖረን ያሳለፍነው ፥ ቁጥር አልባ ስሜት ነበር፡፡
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
.
እኔና እሷ ሳንፋቀር..
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ የምናውቀው አምስት ነገር
በአይናችን እናያለን
በእጃችን እንዳስሳለን
በምላሳችን እንቀምሳለን
በጆሯችን እንሰማለን
ባፍንጫችን እናሸታለን ፣ የሚል ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንፋቀር..
ካንደበቷ ቃል ሳይወጣ ፣ በዝምታ ስትናገር
የከንፈሯን ንቅናቄ
እያየሁኝ የምሰማት ፣ ያለችኝን አንዳች ነገር.
አይን ማለት
በዚያ ሰአት ፥ መስሚያ ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንጣላ
ስለጃችን ከተማርነው ፤ ከመዳሰስ ስሜት ሌላ
ሌላ ስሜት ተፈጥሮብኝ ፥ ያንደበቴን ቃል ሰስቼ
አነዳች ነገር ስናገራት ፤ የመሀል ጣቴን አውጥቼ
ስድብ መሆኑ ሲገባት
ምላሷን ስታወጣብኝ
ስላቅ መሆኑ ሚገባኝ
እጅ ማለት ሌላ ስሜት ፥ ምላስ ማለት ሌላ ነገር
መቅመስ መዳበስ ያልሆነ ፥ ያልተማርነው ነገር ነበር፡፡
ብቻ
ብቻ
እኔና እሷ ስንጣላ ፥ እኔና እሷ ስንፋቀር
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ ብንማርም አምስት ነገር
እኛ ኖረን ያሳለፍነው ፥ ቁጥር አልባ ስሜት ነበር፡፡
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍38❤9👏2
በደለችኝ ብዬ ሲነደኝ ሲቆጨኝ
ልወግራት ፈልጌ
ጠጠር ብወረውር አለት ኾኖ ፈጨኝ
በቃጣሁት ልምጭ ጀርባዬ ታረሰ
ቱፍ ባልኩት ምራቅ ጎጆዬ ፈረሰ
አልገባኝም እንጂ ልክ ነው ነገሩስ....
ንጹህ ነኝ ለማለት የወረወሩት ክስ
ዞሮ የመጣ እለት
አያድርስ....አያድርስ....
🔘red 8🔘
ልወግራት ፈልጌ
ጠጠር ብወረውር አለት ኾኖ ፈጨኝ
በቃጣሁት ልምጭ ጀርባዬ ታረሰ
ቱፍ ባልኩት ምራቅ ጎጆዬ ፈረሰ
አልገባኝም እንጂ ልክ ነው ነገሩስ....
ንጹህ ነኝ ለማለት የወረወሩት ክስ
ዞሮ የመጣ እለት
አያድርስ....አያድርስ....
🔘red 8🔘
👍47❤11
ከሆነ ጊዜ በኋላ እኮ ምንም ነን ፥
ምድር አታስታውሰንም ፤
ከብታቿ ቀብራ በተረኛ ታስረግጠናለች ። 😔
ምድር አታስታውሰንም ፤
ከብታቿ ቀብራ በተረኛ ታስረግጠናለች ። 😔
👍49😢15❤6🔥4😁4🥰2
የግርማዊ ጃንሆይ ቤተሰቦች በዓለም በቃኝ ወሕኒ ቤት ፤አሳዛኝ ቆይታ😔
ዘውዳዊ ሥርዓትን አስወግዶ ስልጣን መያዙን መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም በይፋ ያወጀው የደርግ ወታደራዊ መንግስት ፣ በዚሁ እለት ንጉሠ ነገሥቱን ከቤተመንግሥታቸው ይዞ 4ተኛ ክፍለ ጦር በተባለው የወታደር ሰፈር እንዲታሰሩ በማድረግ ፣ እስከ ጊዜ ሞታቸው ድረስ ለአንድ አመት ያህል አቆይቷቸዋል፡፡
ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ንጉሳዊ ቤተሰቡ በጃንሆይ ልጅ በልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሴ መኖሪያ ቤት ውስጥ በቁም እስር እንዲጠበቁ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል አረጋውያን ፣ ሴቶች እና ሕፃናት ይገኙበት ነበር፡፡ ደርጉ የጃንሆይ ቤተሰቦች በቁም እስር የሚጠበቁት ምክንያት “ሰፊው ሕዝብ በግብታዊነት ተነሳስቶ የበቀል እርምጃ እንዳይወስድባቸው ነው” በማለት ለውጪ ተመልካቾች ገልፆ ነበር፡፡
ሕዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም “ስልሳዎቹ” ተብለው ከሚታወቁት ከዘውድ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር የተሰውት፣ የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ጠቅላይ አዛዥና የጃንሆይ የልጅ ልጅ፣ ሪል አድሚራል እስክንድር ደስታ በደርግ የተገደሉ የመጀመሪያው የጃንሆይ ቤተሰብ አባል ናቸው፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ በነሐሴ 1967 ዓ.ም ያረፉት ግድያ ተፈፅሞባቸው ከሆነ ደግሞ ጃንሆይ በደርግ የተገደሉ ሁለተኛው የንጉሳዊ ቤተሰብ አባል ናቸው ማለት ነው፡፡
ደርግ በመስከረም ወር 1968 ዓ.ም በቁም እሥር የሚገኙትን ንጉሳዊ ቤተሰቦች በአዲስ አበባ ወህኒ ቤት ውስጥ የእድሜ ልክ ፍርደኞች ከሚታሰሩበትና ዓለም በቃኝ ከተባለው ክልል ውስጥ በማዘዋወር አያያዛቸውም በእሥረኛ ደንብ እንዲሆን መወሰኑ ታወቀ፡፡ ከእነዚህ የንጉሳዊ ቤተሰብ እሥረኞች ውስጥ የሚበዙት ሴቶች የነበሩ ሲሆን ወጣት ወንዶችም ይገኙበት ነበር፡፡
እሥረኞቹ ልዑላን የአፄ ኃይለሥላሴ የቅርብ ዘመዶች ከመሆናቸው በስተቀር በዘውድ መንግሥት ውስጥ የያዙት ሥልጣን ወይም ሹመት አልነበረም። ለአንድ ዓመት በቁም እስር ሲቆዩም በወንጀል አልተከሰሱም ወይም ፍርድ አልተፈረደባቸውም፡፡ ከአንድ አመት የቁም እስር በኋላ ደግሞ ይባስ ብሎ ለረጅም ጊዜ ወደሚቆዩበትና የእድሜ ልክ ፍርደኞች ወደሚታሰሩበት የአለም በቃኝ የወህኒ ክልል ውስጥ እንዲዘዋወሩ ተደረገ፡፡
በዓለም በቃኝ ከታሰሩት ንጉሳዊ ቤተሰቦች ውስጥ ልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሴ እና ልጆቻቸው ልዕልት ሰብለ ደስታ ፣ ልዕልት አይዳ ደስታ ፣ ልዕልት ሒሩት ደስታ ፣ ልዕልት ሶፍያ ደስታ እንዲሁም ልዕልት ሳራ ግዛውና ልጆቻቸው ልዑል ወሰንሰገድ መኮንን ፣ ልዑል ሚካኤል መኮንን ፣ ልዑል በዕደማርያም መኮንንና ልዕልት ምሕረት መኮንን በተጨማሪም የልዑል አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን የመጀመሪያ ልጅ ልዕልት እጅጋየሁ ይገኙበት ነበር፡፡
ከእስረኞቹ በእድሜ ዝቅተኛው የ 17 አመቱ ወጣት ልዑል በዕደማርያም መኮንን ሲሆን ከፍተኛ እድሜ የነበራቸው ደግሞ የ63 አመቷ ልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሴ ነበሩ፡፡ በወህኒ ቤት ደንብ መሰረት ልዑላኑ ወንዶችና ሴቶች በዓለም በቃኝ የታሰሩት ተለያይተው በልዩ ልዩ ክፍሎች ውስጥ ነበር፡፡
የወህኒ ቤቱ ክፍሎች ከድንጋይ የተሰሩ እና የሚያዡ በመሆናቸው ዘወትር ቅዝቃዜ አይለያቸውም፡፡ ከጥቂት የመመገቢያ ቁሳቁሶች በስተቀር ሌላ መገልገያ እንዳያስገቡ የተከለከሉት እሥረኞች የሚተኙትም በወለሉ ላይ ፍራሽ ብቻ በማንጠፍ ነበር፡፡
የደርግ መንግስት የልዑላኑን ቤትና ንብረት የወረሰ በመሆኑ፣ በምትኩ በየወሩ ብር 120 እየቆረጠላቸው ለጥቂት ጊዜ ሲቀበሉ የቆዩ ሲሆን በኋላ ላይ “ይበዛል” ተብሎ ወደ 50 ብር ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡ እሥረኞቹ ከዘመዶቻቸው በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ለመቀበል፣ በሳምንት አንድ ጊዜ አጭር ደብዳቤ ለመፃፍ እንዲሁም ለጥልፍ የሚያገለግሉ ቁሳቁስ ለማስገባት የሚችሉ ቢሆንም ጠያቂ ለማነጋገር የሚፈቀድላቸው ግን በአመት ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ብቻ ነበር፡፡
እሥረኞቹ ንጉሳዊ ቤተሰቦች በጣም በሚያስጨንቅ አካላዊና ሥነ ልቡናዊ ሁኔታ ላይ እንደነበሩ በጊዜው የፖለቲካ እሥረኞችን ሁናቴ እየተከታተለ መንግሥትን ይማፀን የነበረው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጊዜው ያወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡
የንጉሳዊ ቤተሰቡ ከነበሩባቸው በርካታ ችግሮች አንዱ የመሰረታዊ ሕክምና እጦት ነበር፡፡ ምንም እንኳን በወህኒ ቤቱ ውስጥ የጤና አገልግሎት የሚሰጥ ክሊኒክ የነበረ ቢሆንም ፣ የንጉሳዊ ቤተሰቡ ሕክምና ሆነ ተብሎ እንዲዘገይ ይደረግ ነበር፡፡ ስለዚህም በጊዜ ቢደረስበት መፍትሄ ያገኝ የነበረ ቀላል ሕመም እየተባባሰ እሥረኞቹን ለከፋ አደጋ ሲያጋልጣቸው ተስተውሏል፡፡
ለዚህም አይነተኛ ምሳሌ የሚሆኑት ልዕልት እጅጋየሁ አስፋ ወሰን ናቸው፡፡ እኒህ ሴት በወህኒ ቤት በተቆራኛቸው ደዌ ለረጅም ጊዜ ሲሰቃዩ አሳሪዎቻቸው ሕክምና እንዲያገኙ አልፈቀዱላቸውም ነበር፡፡ ህመማቸው ተባብሶ ከፍተኛ ደረጃ ከደረሰ በኋላ ግን በፖሊስ ሆስፒታል ተኝተው እንዲታከሙ ተወሰነ። ሐኪሞች ልዕልቷን ኦፕራሲዮን ቢያደርጉዋቸውም ያደረባቸው ደዌ ለረጅም ጊዜ መፍትሄ ሳያገኝ የቆየ በመሆኑ፣ ጥር 23 ቀን 1970 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
እሥረኞቹን ያሰቃዩዋቸው የነበሩት ሕመሞች የመነጩት ወይም ሥር ሰደው የተባባሱት ለረጅም ጊዜ ያለ ሕክምና በቆዩበት በዚህ ወህኒ ቤት ውስጥ ነበር። በከባድ ህመም ይሰቃዩ ከነበሩት መካከል ልዕልት ሒሩት ደስታ አንዷ ናቸው፡፡ እኒህ ልዕልት በእሥር ላይ እያሉ ከተከሰተባቸውና ከባድ ደረጃ የደረሰ የቆዳ ካንሰር የተነሳ ኦፕራሲዮን የተደረገላቸው ሲሆን በሕመሙ ሳቢያ የሰውነት ክብደታቸው በአደገኛ ሁኔታ አሽቆልቁሎ ነበር፡፡
ሌላዋ የእሥር ቤት ሕመም ሰለባ ደግሞ ልዕልት አይዳ ደስታ የነበሩ ሲሆን ሕመማቸው ደግሞ የማያቋርጥና ብርቱ ራስ ምታት ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሰውነታቸው አንዱ ክፍል እዚያው ወሕኒ ቤት ውስጥ ፓራላይዝድ በመሆኑ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚችሉት በከፍተኛ ችግር ነበር፡፡ የልዑል መኮንን ባለቤት የነበሩት ልዕልት ሣራ ግዛው በበኩላቸው፤ በወሕኒ ቤት በለከፋቸው የሄፒታይተስ በሽታ ክፉኛ ታመው ለረጅም ጊዜ ተሰቃይተዋል፡፡
መሰረታዊ የሕክምና እጦት፣ ከዛሬ ነገ ልንገደል እንችላለን የሚል ብርቱ ስጋት እንዲሁም በውጪ እና እዚያው እሥር ቤት ካሉ ልጆቻቸውና ዘመዶቻቸው ጋር ለመገናኘት አለመቻል፣ ተደራርቦ እሥረኞቹን ለአስከፊ ስነልቡናዊ ስቃይ ዳርጓቸዋል። የደረሰባቸውን የመንፈስ ጭንቀት ለማስታገስም ቤተሰቦቻቸው እንቅልፍ እንዲያስወስድ የሚያደርጉ እና አእምሮን የሚያረጋጉ እንክብሎች እንዲያመጡላቸው በመጠየቅ፣ ያለ ሐኪም ፈቃድ ይወስዱ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
እነዚህ እሥረኞች ያለ ፍርድ ወደ ወህኒ የተወረወሩ በመሆኑ ለፍርድ እንዲቀርቡ ወይም እንዲለቀቁ፤ እንዲሁም አያያዛቸውም የሕግ እሥረኞች በሚጠበቁበት አግባብ ሆኖ መሰረታዊ ሕክምና ሳይዘገይ እንዲሰጣቸው፤ በማለት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ባለማቋረጥ የደርጉን መንግሥት ሲማፀን ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ ሕክምናን ማዘግየት ወይም መከልከል እንደ መደበኛ ቅጣት ተቆጥሮ፣ እሥረኞቹ እስከ 1980 ዓ.ም ድረስ መሰረታዊ ሕክምናን ተነፍገው ቆይተዋል። ንጉሳዊ ቤተሰቡ ከእሥር እንዲለቀቅ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሳያቋርጥ ለደርጉ ይቀርብ የነበረው ተማፅኖ ፍሬ ማሳየት የጀመረው እሥረኞቹ ወደ ወህኒ ከተወረወሩ ከስምንት አመታት በኋላ ነበር፡፡

❤64👏3😢3👍1🤩1
ደርግ ዘጠነኛውን የአብዮት በዓል አስመልክቶ በጳጉሜ ወር 1975 ዓ.ም ለፖለቲካ እሥረኞች ይቅርታ ሲያደርግ ወጣቷ ልዕልት ምሕረት መኮንን ከንጉሳዊ ቤተሰብ እሥረኞች መካከል ለመለቀቅ የመጀመሪያዋ ሆነች፡፡ የደርግ “አብዮታዊ ምህረት” ሁሉንም እሥረኛ ንጉሳዊ ቤተሰብ ያካተተ ባይሆንም እሥረኞቹ እንዲፈቱ ለሚማፀኑት ዓለም አቀፍ ተቋማት ግን እንደ በጐ እርምጃ ተደርጐ ተወስዷል፡፡ ተቋማቱ ምህረቱን አስመልክተው ለኢትዮጵያ መንግሥት ምስጋናቸውን በማቅረብ ቀሪዎቹ እሥረኛ ንጉሳዊ ቤተሰቦች እንዲለቀቁ የተለመደውን ልመና አቅርበዋል፡፡
ደርግ ለንጉሳዊ እሥረኞቹ ያደረገው 2ኛ ምህረት የተከናወነው ከመጀመሪያው ምህረት አምስት አመት ያህል ቆይቶ ሚያዝያ 13 ቀን 1980 ዓ.ም ነበር፡፡ ከአሥራ ሁለት አመት በኋላ ከእሥር የተለቀቁት የ75 አመቷ አዛውንት ልዕልት ተናኘ ወርቅ ኃይለሥላሴ፣ ልዕልት ሰብለ ደስታ፣ ልዕልት ሒሩት ደስታ፣ ልዕልት አይዳ ደስታ፣ ልዕልት ሶፍያ ደስታ እና ልዕልት ሳራ ግዛው ነበሩ፡፡
ደርጉ ለንጉሳዊ ቤተሰብ 2ኛውን ምህረት ከሰጠ ከአንድ አመት ከአራት ወራት በኋላ ደግሞ ሦስተኛውንና የመጨረሻውን ምህረት ጳጉሜ 2 ቀን 1981 ዓ.ም አደረገ፡፡ ከ13 አመታት በኋላ የተለቀቁት የንጉሳዊ ቤተሰብ እሥረኞች፣ ወርቃማውን የወጣትነት ጊዜያቸውን በወህኒ ቤት ያሳለፉት፡- ልዑል በዕደማርያም መኮንን ፣ ልዑል ሚካኤል መኮንን እና ልዑል ወሰንሰገድ መኮንን ነበሩ።

😢24❤16👍5
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ዘሪሁን_ገመቹ
ራሄል ከሁለት ረዳቷቾ ከሮቤልና ሎዛ ጋር ስብሰባ ላይ እያለች ነበር ስልኳ የጠራው…ንግግሯን ሳታቋርጥ ስልኩን አነሳችና አየችው፤ አባቷ አቶ ቸርነት ናቸው የደወሉላት ፡፡ስብሰባ ላይ ነኝ ብላ ልትዘጋባቸው አልፈለገችም…አባቷ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ባይሆን ኖሮ በዚህ ሰዓት አይደውሉላትም ነበር፡፡
‹‹አንዴ ይቅርታ… ይሄንን ስልክ ማንሳት አለብኝ››ብላ ከተቀመጠችበት ግዙፍ ተሸከርካሪ ወንበር ተነሳችና ቢሮውን ለቃ ወጣችና….ከዛ ስልኩን አነሳችው፡፡
‹‹ሄሎ አባዬ ..እንዴት ነህ?››
‹‹ሰላም ነኝ ልጄ››
ድምፃቸው ተጎተተባት‹‹ምነው አባዬ? ችግር አለ እንዴ?››
‹‹አይ ልጄ ሁሉ ነገር ሰላም ነው…እኔ እና እናትሽ አንድ ነገር ልናማክርሽ ነበር››
‹‹ምንድነው?››
‹‹ይሄውልሽ ልጄ ምን መሰለሽ..እኔና እናትሽ ጡረታ ወጥተን ቤት መዋል ከጀመርን በኃላ ህይወታችንን ታውቂያለሽ…ብቸኞች ነን..አንቺም አሻፈረኝ ብለሽ በራስሽ ቤት ነው የምትኖሪው…፡፡››
ራሄል በምትሰማው ነገር ፊቷን አጨማደደች….የገመተችው አብረሽን ኑሪ የሚለውን የዘወትር ጥያቄያቸውን ደግመው ሊያነሱባት ነበር የመሰላት፡፡
አባቷ ትንፋሽ ወሰዱና ንግግራቸውን ቀጠሉ‹‹እህት እንዲኖርሽ ፈልገን ነበር››
ደነገጠች‹‹እህት!!››
‹‹አዎ ቅር ማይልሽ ከሆነ እኔ እና እናትሽ እህት እንዲኖርሽ ፈልገናል…የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት ያንቺን አስተያየት ማወቅ ስለፈለግን ነው የደወልንልሽ፡፡››
‹‹ብዥ አለባት…እናቴ በሰባ አመቷ አረገዘች እንዴ?››ስትል በውስጧ እራሷ ጠየቀች፡፡‹‹አባቴ የአብረሀምን አይነት የዋህነት ስላለው እግዜር በዚህ አድሜዋ የማዬን ማህፀን ቢከፍት አይገርመኝም››ስትል በራሷ ሀሳብ ሳቀችና ትኩረቷን ወደስልኩ መለሰች፡፡
‹‹አባዬ አልገባኝም..እንዴት ነው እህት ሊኖረኝ የሚችለው?››
አንድ የሁለት አመት ቆንጅዬ ሴት ልጅ በጉዲፈቻ ልንወስድ ነው….››
‹‹በጉዲፈቻ…በጣም ደስ ይላል….ጥሩ ውሳኔ ነው የወሰናችሁት..››
ሀሳባቸውን ለመደገፍ ጥቂት ማሰብ እንኳን አላስፈለጋትም…የሁለት አመት ጣፋጭ ልጅ እዛ ግዙፍ ቪላ ቤት ውስጥ ስትሯሯጥ…አንዴ አባቷ ላይ አንዴ ደግሞ እናቷ ላይ እየተንጠለጠች ስታስቃቸውና ሰታዝናናቸው፣እነሱም ሲያሞላቅቋት…እሷን መሀላቸው አድርገው ግራና ቀኝ እጇን ይዘው ወደቤተክርስቲያን ይዘዋት ሲሄዱ .... በአይነ ህሊናዋ ታያትና በደስታ ተፍለቀለቀች፡፡
‹‹ልጄ አሁን እሷን ልናይ ሆስፒታል ነው ያለነው ..ከቻልሽ ጋንዲ ነን …ብትመጪ ደስ ይለኛል፡፡››
መልሶ መደነጋገር ውስጥ ገባች‹‹ሆስፒታል…ምን ትሰራለች?››
‹‹ትንሽ አሟታል…ከቻልሽ ነይ፡፡››ደገሙላት፡፡
‹‹በቃ መጣው››……ስልኩን ዘጋችና ወደቢሮዋ ተመልሳ ለረዳቶቾ ወደስራ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ሰጥታ ቦርሳውን አንጠልጥላ ወጣችና ቀጥታ ከፓርክ መኪናዋን በማንቀሳቀስ ስለአዲሷ እጩ እህቷ ምን እንደምትመስልና…ምኗን ታማ ሆስፒታል ልትገባ እንደቻለች እያብሰለሰለች ወደጋንዲ ሆስፒታል ነዳችው፡፡
ደርሳ ወደውስጥ ስትገባ ሰውነቷ መንቀጥቀጥ ጀመረ…ይሄ የተለመደ ስሜቷ ነው…ሆሲፒታል ሂጂ ከሚሏት ጦርነት ዝመቺ ብትባል ትመርጣለች…እንደምንም ግን ወደውስጥ ዘለቀች… አባቷን ደውላ አገኘችው…እጇን ይዞ እየመራ የተባለቸው ህፃን ወደተኛችበት ክፍል ይዟት ገባ፡፡ክፍሉ ውስጥ ከህፃኗ ጋር የገዛ እናቷ ብቻ ነች ያለችው፡፡ ከበራፉ አንድ እርምጃ ወደውስጥ ተራምዳ እንደቆመች ደንዝዛ ቀረች …ከዛ ማለፍ አልቻለችም፡፡
ፍፅም የሚባል ድንዛዜ ውስጥ ነው የገባችው…ልጅቷ ቢያንስ ከሶስት ማሽን ጋር በቱቦ ተያይዛለች…መልኳ ውብ ፀጉሯ ግንቧሯ ላይ ድፍት ያለ አጎጊ ብትሆንም ስልምልም ብላ እራሷን ስታ ተዘርራለች..እንደውም ነፍሷ ውስጧ እንዳለ እርግጠኛ መሆን አልቻለችም….
በቃ ውስጧ ግልብጥብጥ ነው ያለባት…ከአመታት በፊት ምትወደውና ልታገባው ስታልመው የነበረው እጮኛዋ ኪሩቤል እንዲህ እንደህፃኗ እራሱ ስቶና ዝርግትግት ብሎ በማሽን እገዛ ለመተንፈስ ሲያጣጥር የነበረው ትዝታ መጣባትና እራሷን ልትስት ተንገዳገደች..አጠገቧ ያለው አባቷ ፈጠን ብሎ ደገፋት…እናቷ በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ስሯ ደረሰች፡፡
‹‹ምነው ልጄ..አመመሽ እንዴ?››ሁለቱም ተቀባብለው ጠየቋት፡፡
‹‹አይ ደህና ነኝ …የመድሀኒት ሽታና የህክምና ማሽኖቹ ድምፅ ነው የረበሸኝ››
‹‹ቸሬ አንተ እኮ ነህ..እሷ ሆስፒታል እንዴት እንደምትጠላና እንደሚያማት እያወቅክ ነይ ያልካት፡፡››
‹‹እውነትሽን ነው አጥፍቻለው….በቃ ልጄ ነይ…ይሄን ያህል ካየሻት ይበቃሻል….ብለው እየጎተቱ ወደውጭ ወሰዷት…መኪናዋ ድረስ አደረሷት፡፡‹‹እርግጠኛ ነሽ ሰላም ነሽ…?መኪና መንዳት ትችያለሽ››
‹‹አታስብ አባዬ..ሰላም ነኝ..በቃ ተመለስ››
መኪና ውስጥ ገባታ ስትንቀሳቅስ አባትዬው ወደውስጥ ተመለሱ፡፡ቀጥታ ወደቤቷ ነው የሄደችው፡፡የልጅቷ ምስል ከአእምሮዋ ሊወጣ አልቻለም….ወላጆቾ ምን አስበው ያቺን በህይወት እና በሞት መካከል ባለች ቀጭን ክር ተንጠልጥላ ያለችን ልጅ በማደጎ ለመውሰድ እንዳሰቡ ሊገባት አልቻሉም…እንዴት አድርገው ሊንከባከቧት ነው…?ከለመዷትና ከወደዷት በኃላ ብትሞትባቸውስ…..?የሚወዱትን ሰው በሞት መነጠቅ እንዴት ልብን እንደሚሰብር እና ተስፋን እንደሚያከስም በራሷ ታውቀዋለች…እና በእሷ የደረሰ አይነት ሀዘን በዚህ እድሜያቸው በወላጆቾ እንዲድርስ አትፈልግም…፡፡
‹‹ግን ምን ማድረግ እችላለው?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡እንዲሁ ስትብሰለሰል አደረች…ሳምንት ሙሉ አሰበችበት..አንድ ውሳኔ ወስና ለወላጆቾ ምንም ነገር ማለት ሳትችል…ወላጆቹ ህጋዊ የአሳዳጊነት ፕሮሰሱን ጨርሰው ልጅቷን ወደቤታቸው እንደወሰዱ ሰማች፡፡በቃ ከዛ በጊዜ ሂደት የሚሆነውን ጠብቃ ለመመልከት ወሰነችና ወደወላጇቾ ቤት ሄዳ አዲሷን እህቷን አየቻት…ምንም እንኳን ከዛ ሁሉ ማሽን ነፃ ሆና ብታያትም..አሁንም ግን በጣም ደካማ እና የሰለለ ሰውነት ያለት ሆና ነው ያገኘቻት፡፡ግን ደግሞ በዛው ልክ አሳዛኝና ተወዳጅ ልጅ መሆኗን መካድ አልቻለችም፡፡
============
ራሄል ከረዳቷ ጋር እያወራች ነው፡፡
‹‹ሮቤል ወ.ሮ ላምሮት ልገሳዋን ለእኛ ፋውንዴሽን እንድታደርግ አሁን በስልክ አናግሬታለው፡፡እሷን ማሳመን ከቻልኩ እና ውሳኔዋ ለእኛ ለመለገስ ከሆነ ለፋውንዴሽናችን ትልቅ ስኬት ነው››
ራሄል ወረቀቶቿን ወደ ቦርሳዋ አስገባች፣ አንድ አይኗ በእንጨት በተሸፈነው የቢሮዋ ግድግዳ ላይ በተሰቀለው ሰዓት ላይ ተሰክቶ ነበር።
‹‹ ለማውራት ጊዜ የለኝም። በሃያ ደቂቃ ውስጥ በወላጆቼ መኖሪያ ቤት በተዘጋጀው የምሳ ግብዣ ላይ መገኘት አለብኝ ››አለች፡፡
ረዳቷ ማንኛውንም አይነት ቅሬታ ከማንሳቱ በፊት አቋረጠችውና ‹‹ እንደገና ሴትዬዋ ከደወለች ብቻ አሳውቀኝ።››አለችው፡፡
ስልኳን ዘጋችና ሞባይሏን ቦርሳዋ ውስጥ ለትንሿ እህቷ ጸጋ ከገዛችው ትንሽ ስጦታ ጋር አስቀመጠችው፣ ፀጋ ወላጇቾ ሊያሳድጓት በቅርብ የተረከቧት እህቷ ነች፡፡ ራሄል ወደ መኪና ማቆሚያ ጋራዥ በፍጥነት በምትወርድበት ጊዜ የኖብል ፋውንዴሽን ቢሮዎችና ኮሪደሮች በፀጥታ ተውጠው ነበር።

❤94🔥2😱1
እናቷ ከአዲሳባ ውጭ ለገጣፎ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እንድትመጣ ነግራታለች፡፡ ይህ የግብዣና ጥሪ በየሳምንቱ የረፍት ቀኗን ጠብቆ የማይቀር ነው ፡፡ይሁን እንጂ የዛሬው የተለየ እንደሆነ ያወቀችው ፕሮቶኮሏን ጠብቃ እንድትመጣ ከሚያሳስብ ማስጠንቀቂ ጋር የተነገራት በመሆኑ ነው።ለምን ብላ እናቷን ስትጠይቅ ‹‹ወሳኝ እንግዳ ስለጋበዝኩ ዘንጠሸ እንድትገኚ ነው የምፈልገው ››ብለው ነበር በደፈናው የመለሱላት፡፡ እናቷ ሁል ጊዜ አንድትደሰትና እና ዘና እንድትል ከመምከር ተቆጥበው አያውቅም። ራሄል ግራጫ ቀለም ያለው ሙሉ ልብስ ለብሳ በላዩ ላይ የሐር ሻርፕ አንገቷ ላይ ጠምጥማ ቆንጆ ለመሆን ሞክራለች፡፡‹‹ እናቴ እኔን እንደፍላጎቴ እንድሆን መፍቀድ ነበረባት።››ስትል አጉረመረመች፡፡
ከአምስት አመት በኃላ ወላጆቿ ለገጣፎ ወደሚገኘው የእርሻ ቤታቸው ተመልሳ አብራቸው እንድትኖር ለምነዋት ነበር። ራሄል ግን ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጋ ለረጅም ጊዜ ብቻዋን መኖሯን ቀጠለች። በምትኩ መሀል ቦሌ በሚገኝ ባለሁለት መኝታ ክፍል አፓርታማ ቤት ውስጥ መኖርን መርጣለች።የእሷ ቤት በወላጇቾ ሀብት ልክ ዘመናዊ የሚባል ባይሆንም ለእሷ ግን ተስማሚ ነበር።
የተነሳችው ሰንጋ-ተራ ከሚገኘው የኖብል ፋውንዴሽን ዋና መስሪያ ቤት ነው፡፡መኪናዋን እራሷ እየሾፈረች በእጆቾ መሪውን እያሽከረከረች በአእምሮዋ ስለስራዋም ስለህይወቷም ብጥቅጣቂ ሀሳቦችን እያሰበች ፍጥነቷን ጠብቃ እየተጓዘች ሳለ…የትራፊክ መብራት አስቋማት፡፡ከኋላዋ የነበረ መኪና ከፊት ለፊቷ አልፏ ሲቀድማት በትዝብት ተመለከተችው፡፡ ከዛ ሌላ ሞተር ሳይክል በጎኗ ታኮ አጠገቧ ሲቆም ደነገጠች። የሞተሩ ጩኸት ከመኪናዋ ሲዲ ማጫወቻ የሚመጣውን የመሀመድ አህመድ ድምፅ ውጦ አስቀረው።ሞተረኛውን ተመለከተችው፡፡ የቆዳ ጃኬት፣ ጂንስ ሱሪ እና ቡትስ ጫማ አጥልቋል..ጭንቅላቱ ላይ ሄልሜት አድርጎል፡፡
ራሄል መሪውን አጥብቃ ያዘችው፡፡ ሞተር ሳይክሎችን ትጠላለች። እጮኛዋ ኪሩቤል በዚያ ምሽት መኪናውን እየነዳ ቢሆን ኖሮ-አሁን በዚህ ሰዓት ስለእሱ ሞት በማሰብ ልቧ በሀዘን አይኮመታተርም ነበር ። ይህም ሆኖ በሞተር ሳይክሉ ላይ ያለውን ሰው በጨረፍታ ለማየት ከመሞከር መቆጠብ አልቻለችም።ሄልሜቱን ወደ ኋላ ገፋ እና እያየችው እንደሆነ ሲመለከት ቀስ ብሎ ፈገግ አለላት፡፡ ረጅምና ባለፈርጣማ ጡንቻ ነው፡፡ጠይምና አይናማ ነው፡፡ለግላጋ ቁመናው በአእምሮዋ ብልጭ ድርግም እያለ ሲታያት ተናደደች ፡፡ወደ ፊት ተመለከተች።ወደ ወላጆቿ ቤት የሚያመራውን መንገድ ክፍት መሆኑን ተገነዘበች፡፡ ሞተር ሳይክሉን እየስጮኸ ቀድሟት ተፈተለከ፡፡
ሲዲውን አወጣች፣ የምትፈልገውን ሙዚቃ የሚጫወት ኤፍ ኤም ጣቢያ ፍልጋ አገኘች እና ድምጹን ከፍ አደረገች። በምቾት እየነዳች ነው ፣ ነገ ስለምትሰራው ሥራ ምን ማድረግ እንዳለባት እቅድ ማውጣት ጀመረች ።አዎ የእሷን ትኩረት በቀጥታ የሚፈልጉ በርካታ ስራዎች አሉ፤ውስጧን የሚሸረካክታትን በበፊት ህይወቷ የተከሰቱ ጨለማ ትዝታዎችን ወደኃላ መተው አለባት።በግዙፍ የዛፍ ጥላዎችና በተለያዩ አትክልቶች ወደተሞላው ግዙፉ የወላጆቾ ቤት ደረሰች፡፡ መኪናዋን በሁለት ረድፍ ተከርክመው ባማሩ የፅድ ቁጥቋጦዎች መካከል ባለው ጠባብ መንገድ እየሰነጠቀች ወደ ዋናው ቤት እየቀረበች ነው። ‹‹ምሽቱ ጥሩ ሊሆን ነው ››ስትል አሰበች ።እንደገና እራሷን መቆጣጠር እንደቻለች ተሰማት።
አራት መኪና ለማቆም ወደሚችለው ጋራዥ ስትቀርብ የልብ ምቷ ጨመረ ።መንገድ ላይ አበሰጭቷት ያለፈው ባለ ሞተር ሳይክል ሰውዬ አሁን ከጋራዡ ፊት ለፊት ባለው የጡብ ግድግዳ አጠገብ ቆሟል፣ ሄልሜቱን በሞተር ሳይክሉ መሪ ላይ አንጠልጥሏል።መኪናዋን አመቻችታ አቆመች፡፡ የዮጋ መምህሯ እንዳስተማራት ረጅም ትንፋሽ ወደውስጦ ሳበች…መልሳ አስወጣች ፣ከንደገና ሳበች …። እራሷን ያረጋጋች ሲመስላት ለፀጋ የገዛችላትን ስጦታ አንሥታ በጥንቃቄ እየተራመደች ወደ መግቢያው በር አመራች። ‹ምናልባት ባለሞተር ሳይክሉ የሽያጭ ሰራተኛ ወይንም የሆነ መልዕክት ሊያደርስ የመጣ ሰው ሊሆን ይችላል።›ስትል አሰበች …ወይም ከቤቱ አገልጋዬች የአንደኛዋ ውሽማ ሊሆን እንደሚችልም ገመተች፡፡
በሩን አልፋ ወደውስጥ ስትገባ የቤታቸው ሰራተኛ አለም ‹‹እንኳን በደህና መጣሽ!!›› ብላ በታላቅ ፈገግታ ተቀበለቻት፡፡
‹‹አመሰግናለው…አለም››
‹‹ እናትሽ ኩሽና ውስጥ ነች..››
‹‹…ለጥቆማው አመሰግናለሁ ።እማዬ ምን አይነት ምግብ እንደሰራች ልትነግሪኝ ትችያለሽ?››
አለም ሚስጥራዊ የሆነ ፈገግታ ፈገግ እያለች‹‹ ላንቺ እና ለእንግዳቸው የበለጠ ባህላዊ ነገር የሚያዘጋጁ ይመስለኛል…ከስጋ ጥብስ እና ክትፎ ሲኖር ሌላው ጠቅላላ የጎሯ ምርት የሆነ ቅጠላቅጠል ነው….››የሚል መልስ ሰጠቻት፡፡
ራሄል‹‹አይ እማዬ እና ቅጠላ ቅጠል መች ይሆን የሚለያዩት!!››አለችና ያንን አስጠሊታ ሞተር ሳይክል እያከነፈ የመጣው ሰው ማን እንደሆነ ሳትጠይቃት ወደ ቤቱ ጀርባ ሄደች። ራሄል የፊት ለፊት ክፍል ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለው መስታወት ውስጥ የራሷን ምስል ነጸብራቅ ተመለከተችና ቆም አለች፡፡ በመጠኑ የተዘበራረቀውን ፀጉሯን ለማስተካከል ትንሽ ጊዜ ወሰደባት፡፡ መላ አካሏ ንፁህ እና የተስተካከለ እንደሆነ አሰበች ። በጠባቡ ኮሪደር በኩል ወደ ኩሽና አመራች፡፡ እናቷ በዘመናዊው ኩሽና ውስጥ እንደ ደሴት የሚያገለግለው ግዙፉ መደርደሪያ ላይ ቆመው አትክልት ሲከትፉ አገኘቻቸው፡፡ ብርቱካናማ ልቅ ሽርጥ አድርጋገዋል፡፡ ወ.ሮ ትርሀስ ልጇቸውን ስያዩ ቢላዋዋን አስቀምጠው በሽርጣቸው ዙሪያ እጆቻቸውን እየጠራረጉ, ራሄልን እቅፏቸው ውስጥ አስገብተው አገላብጠው በመሳም ሞቅ ባለ ስሜት ተቀበሏት ‹‹በሰዓቱ በመምጣትሽ በጣም ደስ ብሎኛል ። ››
ራሄል እናቷን ሀዘን ባጠላባቸው አይኖቿ ተመለከተቻቸው።
‹‹ትንሽ የገረጣሽ ትመስያለሽ …ውዴ።?››
ራሄል ግልጽ ባልሆነ ምልክት እጇን አነሳችና ።‹‹ ስራ በዝቶብኝ ነበር..ሰሞኑን በቂ እንቅልፍ አላገኘውም…ለዛ ነው››
ለፀጋ ያመጣችውን ስጦታ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች። እናቷ ማስጠንቀቂያቸውን አጠንክረው ቀጠሉበት ‹‹ራስህሽን መንከባከብ አለብሽ …ሰውነታችን የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ነው …እግዚአብሔር በምድር ላይ ሥራውን ለመሥራት ጤናማ አገልጋዮች ያስፈልጉታል።››አሏት፡፡
ራሄል በእናቷ የተለመደ አይነት ንግግር ፈገግ አለች። በእግዚአብሔር ጉዳይ ላይ ከእናቷ ጋር ለመወያየት አልፈለገችም።ላለፉት ስምንት አመታት እግዚአብሔርን ከህይወቷ አስወጥታለች ወይም ለማስወጣት ሞክሯለች። የዚህም ምክንያት ‹‹ከእግዚአብሔር ፀሎቴን ቀብሮታል.. ህልሜን አክስሞታል…››ብላ ስለምታስብ ነው።እናቷ እጇቸውን በራሔል ትከሻ ላይ አድርገው ወደ ባንኮኒው ወሰዷት።
‹‹እኔና አባትሽ አንድ ደስ የሚል አስገራሚ ነገር አለን።የፀጋ ሐኪም መጥቶ እንዲጎበኘን ጋብዘነዋል።››
‹‹አሁን እዚህ አለ?››
እናትዬው በአውንታ ግንባራቸውን ነቀነቁ
‹‹ማለት ሞተር ሳይክ እየነዳ ቀድሞኝ የገባው ሰውዬ እንዳይሆን?››
‹‹አዎ››እናትዬው አረጋገጡላት፡፡‹‹አንቺም እሱን ለማግኘት ትፈልጊ ይሆናል ብዬ አሰብኩ››በማለት አከሉበት፡፡
እናትዬው በዘዴ ከዶ/ሩ ጋር ፊት ለፊት ከመጋፈጧ በፊት ስለሰውዬው የተወሰነ ግንዛቤ ሊያስጨብጧት እየሞከሩ እንደሆነ ገብቷታል፡፡
‹‹በሞተር ሳይክል ላይ ሳየው ግን ሞኝ መስሎ ነው የሚታየው›› ስትል ተናገረች፡፡

❤68👍6
‹‹ራሄል እንደዚህ አይነት ቃላትን መጠቀም የለብሽም።በተለይ እንደ ኤሊያስ ላለ ድንቅ ሰው።››
ራሄል እናቷ የሁለት ዓመቷን ፀጋን በማደጎ ልጅነት ወደቤታቸው ስትመጣ ለልጅ ልጆች ያላቸውን ሥር የሰደደ ፍላጎት እንደምታረካላቸው ተስፋ አድርጋ ነበር።እናም እሷን አግቢ ..ውለጂና የልጅ ልጅ አሳይን ብለው በየእለቱ የሚጨቀጭቋትን ጭቅጭቅ እንደሚያቆሙላት ትጠብቅ ነበር፡፡ አሁን እንደምታው ግን ያ ሽንቁር አሁንም እንዳለ መሆኑን ነው የገባት፡፡
‹‹አዝናለሁ እማዬ፣ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ማንም ሞተር ሳይክል የሚነዳ ሰው ኃላፊነት የሚሰማውና የሚተማመኑበት ሰው ይሆናል ብዬ አላምንም።ለዛውም የሕፃናት ሐኪም ሆኖ…ሞተር ሳይክል መንዳት።››ራሄል በጠረጴዛው ላይ ከተቀመጠው ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ አንድ አነስ ያለ ካሮት ወሰደች እና ገመጠች።
እናትዬው ልጇቸው ስለሞተር ሳይክል አንስታ ስታወራ ምን ለማለት እደፈለገች ስለገባቸው ምንም ሊመልሱላት አልፈለጉም፡፡
ራሄል ‹‹አባዬ የት ነው ያለው?››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹እሱ እና ዶ/ር ዔሊያስ ከፀጋ ጋር ሆነው ወደ አትክልት ስፍራ ወጥተዋል።እስከአሁን ተመልሰው እየመጡ እንደሆነ አምናለሁ።››
ራሄል ግቢውን ለማየት ወደ መስኮቱ ዞረች፣የመጨረሻውን የካሮት ቁርጭ አፏ ውስጥ ከታ እየኮረሸመች መመልከቷን ቀጠለች፡፡ በበር ኤሊያስ ከአባቷ ጋር ብቅ አለ፣ እጁን ዘርግቶ የፀጋን ፀጉር ከፊቷ ላይ ገልጦ ወደኃላ እያስተኛላት በለስላሳው ፈገግ አለ።ፀጋ በሩቅ ስታያት ሳቀችላት እና ወደ አባቷ ተጠጋች።ራሄል ከፊትለፊቷ ከአባቷ ጎን ያለውን ሰውዬ የእህቷ ዶክተር ይሆናል ብላ በአእምሮዋ ከቀረፀችው ፎቶ ጋር ምስሉን ማጣመር አልቻለችም።
‹‹ሞተር ሳይክሉን እየነዳ የነበረው ሰውዬ ማን ነበር?።››ራሷን ጠየቀችና ከመስኮቱ ዞር ብላ ወደእነሱ ተጠጋች፡፡
ራሄል አባቷ ወደ ክፍል ሲገባ ተመለከተች። ወደ ፊት ተንቀሳቀሰችና አባቷ እቅፍ ውስጥ ገባች …ትንሹን ሴት ልጁን በሌላኛው ክንድ ላይ አስተካክሎ አቀፋት..።‹‹ሰላም አባዬ››።
‹‹የእኔ ውድ ስላየሁሽ ደስ ብሎኛል››ፀጋን በጨረፍታ ተመለከተቻት፣ ወደ እሷ በመመልከት ሣቅች፣ የተጠማዘዘ ቡናማ ፀጉሯ እና የልብ ቅርጽ ያለው ፊቷን አስተዋለች፡፡ ሮዝ ቲሸርት እና ሰማያዊ ጂንስ ቱታ ለብሳለች። የእናቷን የልብስ ጣዕም ግምት ውስጥ በማስገባት የተለመደ አለባበስ ነው ስትል አሰበች.፡፡እሷም ልጅ እያለች ተመሳሳይ አይነት አለባበስ ታዘወትር ነበር፡፡
ራሄል በፈጣን ፈገግታ የእህቷን ትከሻ እየዳበሰች‹‹ሄይ፣ እህቴ››አለች ።ፀጋ ሚዛናዊ ሆና እጆቿን ወደ ራሄል ዘረጋች። ራሄል ወደ አባቷ እቅፍ መለሰቻት እና አንድ እርምጃ ከእነርሱ ርቃ ቆመች። ፀጋ ቆንጆ እና አፍቃሪ ሴት ነበረች። ራሄል ግን ለእሷ ያላትን በጎ ስሜት አሳይታት ስለማታውቅ ትንሽ ትጨነቃለች።ራሄል የወላጆቿን ልብ የማረከችውን ትንሽ መልአክ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ስታያት መተንፈሻ መሳሪያ ተገጥሟላት ፣ ከ IV እና ከሌሎች ማሽኖች ጋር ተሳስራና እራሷን ስታ ነበር ። ፀጋ ሴሬብራል ፓልሲ የሚባል በሽታ ነበረባት፡፡በዚህ የተነሳ እንቅስቃሴ ማድረግ በጣም የምትቸገር..አጥንቶቾ ያልጠነከሩና የተልፈሰፈሰች..ከዛም በላይ ብዙ ተያያዥ ችግሮች ያሉባት ህፃን ነበረች፡፡እና በወቅቱ የወላጆቾን ውሳኔ ደፍራ ለመቃወም ባትደፍርም በጣም ያሳሰባትና ያስጨነቃት ነበር፡፡አሁን ግን በብዙ የህክምና ክትትልና የመድሀኒት እገዛ ቀስ በቀስ ከበሽታዋ እያገገመች ነው።ከብዙ ጊዜ በፊት ወላጆቿ ልጅ ተቀብለው ለማሳደግ ለማደጎ ተቋም አመልክተው ነበር ፀጋን ሲያዬት ግን እሷን ለማሳደግ እንደሚፈልጉ በመናገር የራሔልን አስተያየት ጠየቋት። በሰዓቱ ራሄል ጋንዲ ሆስፒታል ተኝታ የነበረችውን ፀጋን ልታያት ስትሄድ ለሆስፒታሎች ያላትን ጥላቻ ማሸነፍ እንደምትችል አስባ ነበር፣ ነገር ግን ከአምስት ደቂቃ በላይ ከጸጋ አልጋ አጠገብ መቆም አልቻለችም ነበር ። የመተንፈሻ አካሉ ጩኸት እና በአየሩ ላይ የተንሰራፋው የጸረ-ተባይ ጠረን በውስጦ የተዳፈነውን ቀፋፊ ትዝታ ነበር የቀሰቀሰባት፡፡ከዛም አልፎ በማቅለሽለሽ ማዕበል ተመታች።ለወላጆቿ መልካም ምኞቷን በመግለፅ ሆስፒታሉን ለቃ ወጣች…ከዛ ፀጋ የተወሰነ የጤና መሻሻል አሳይታ ወደቤት ከመጣች በኃላ ነው ያየቻት፡፡ ።ይሁን እንጂ አሁን ድረስ ልጅቷን ስታያት አቅመቢስነት እና ጣር የታከለበት ህመም እና ቀፋፊ የሆስፒታል ምስል ነው የሚታያት ።በዛ ምክንያት ረዘም ላለ ጊዜ ከአጠገቧ ለመቆየት ምቾት አይሰማትም።
ራሔል‹‹ ታንሿ እህቴ እነሆ ስጦታ አመጣሁልሽ።›› በማለት ለፀጋ የተጠቀለለውን እሽግ ሰጠቻት።
‹‹ምን ትያለሽ ማር?››አባቷ ቸርነት ፀጋን ስለስጦታው ምን እንደተሰማት ጠየቋት።
በኮላታፈ እና በሚጎተት አንደበቷ ‹‹አመሰግ…ና..ለው›› አለች፡፡
✨ይቀጥላል✨

❤77👍8
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ፀጋ አባቷ እቅፍ ላይ እንዳለች ፈገግ በማለት የራሄልን ትኩረት ለመያዝ ሞከረች፣ በዚህ ጊዜ እናቷ ጣልቃ ገብታ መናገር ጀመሩ ፡፡
‹‹ራሄል፣ ከዶክተር ኤሊያስን ጋር እንድትተዋወቂ እፈልጋለሁ። እሱ የፀጋ ሐኪም ነው…ዔሊ ይህች ልጃችን ራሄል ናት።››
ዶ/ሩ በስሱ ፈገግ በማለት ‹‹ሰለአንቺ ብዙ ሰምቼያለው ..አንድ ቀን እንደምንገናኝ አምን ነበር›› በማለት እጁን ወደ እሷ ዘረጋ
ጨዋነት ያልጎደለው ፈገግታ ፈገግ አለችለት እና የዘረጋውን እጅን ጨበጠች፡፡ወላጆቿ ከእሱ ጋር አማች ለመሆን እያሴሩ እና እሱንም እያደፋፈሩት እንደሆነ ታውቃለች…ቢሆንም የሱ ጥፋት አልነበረም።
‹‹የሞተር ሳይክሉ ሰው ነህ አይደል?››
‹‹አዎ… ነኝ›› አላት፡፡
እጁ ሞቃታማ፣ ጣቶቹ ረዣዥም ነበሩ፣ እና ሲነካት ለረጅም ጊዜ በእንቅልፍ የመወሰድ አይነት የግንዛቤ ብልጭታ በአእምሯዋ ተንፀባረቆ ነበር….ስሜቱን አልወደደችውም። ‹‹በዛ ፍጥነት ስታበር ገርሞኝ ነበር››አለችው፣ትንፋሽ ወሰደችና ‹‹ደግሞ ዶክተር መሆን እና …..››
‹‹እና ምን?›› ከአንደበቷ ቀልቦ ጠየቃት።
‹‹ከተሸከምከው ሃላፊነት አንፃር ሞተር ማሽከርከር….አንድ ነገር ቢደርስብህስ?››
‹‹ለጊዜው አቅሜ የሚፈቅደው ርካሹ እና ፈጣኑ መጓጓዣ ሞተር ነው. እና ደግሞ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አደርጋለሁ.››ሲል መለሰላት፡፡
ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ‹‹ሁሉም የሚያቀነቅናቸው ታዋቂ የመጨረሻ ቃላቶች ናቸው…ጥንቃቄ አደርጋለው..››አለች በንዴት፡፡
በመጠኑ ደፍረስ ባሉት አይኖቹ በትኩረት ተመለከታት…ከመተዋወቃቸው እየሰጠችው ያለው ጠንከር ያለ አስተያየት ግራ አጋብቷታል…
እናትዬው ፀጋን ከአቶ ቸርነት እቅፍ ወሰድና፡፡‹‹በሉ ወደምግብ ጠረጴዛው እንሄድ….ምሳ ዝግጁ ነው››ሲሉ አወጁ፡፡
ሁሉም ወደምግብ ጠረጴዛው ተከታትለው ሄዱ፡፡ራሄል፣ የተለመደውን ቦታዋ ላይ ተቀምጣለች፣ ዔሊያስ ከእሷ ፊት ለፊት ተቀምጠ።››
አቶ ቸርነት በቀኝ እጇቸው የሴት ልጇቸውን እጅ ግራ እጇቸው ደግሞ በዔሊያስ ትከሻ ላይ ዘረጉና። ‹‹ብዙውን ጊዜ ከምግብ በፊት እንፀልያለን››ሲሉ ለዔሊያስ ገለጹለት።
‹‹እኔ ደስተኛ ነኝ. በቤተሰቦቼ ቤትም ስርዓቱ እንዲሁ ነው.››ሲል መለሰ፡፡አባቷ እጇን ጨምቀው ነበር፣መጸለይ ሲጀምሩ አንገቷን ዝቅ አደረገች።አባቷ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገሩ ማዳመጥ ብትጀምርም ከጸሎቱ ጋር በልቧ መቀላቀል አልቻለችም። እሷ በሀይማኖት ስርዓት ውስጥ ተወልዳ ያደገች ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ከመስመር ወጥታለች። አምላክ በህይወቷ ጣልቃ እንዲገባ አትፈልግም ወይም ደግሞም እሱ ራሱም ለእሷ ደንታ እንደሌለው ታምናለች።ስለዚህ ለምን ትጨቀጭቀዋለች፡፡ ወላጆቿ በዚህ መሳኔዋ ደስተኛ እንዳልሆኑ በደንብ ታውቃለች ቢሆንም ግን ርቀታቸውን በመጠበቃቸው ታመሰግናቸዋለች። እና ምናልባት ወደቀልቧ እንድትመለስ ዘወትር ለእሷ በድብቅ ይፀልዩላት ይሆናል፡፡
ፀሎቱ ተገባዶ በ‹‹አሜን›› እንደተዘጋ እናትዬው ‹‹በሉ እራሳችሁን አስተናግዱ ››አለቻቸው፡፡ሁሉም ፊት ለፊቱ ባለው ሳህን ላይ ፊለፊታቸው ከተደረደሩት በርካታ የምግብ ዓይነቶች የሚፈልጉትን መጠን መውሰድ ጀመሩ፡፡ተ
‹‹ከቻልክ ክትፎውን አቀብለኝ››ስትል ራሄል ወደኤልያስ እያየች አጉተመተመች፣
እናትዬው የራሄልን አስተያየት ውድቅ በማድረግ እጆቿን እያወዛወዘ ‹‹እስኪ እንደአንበሳ ስጋ ማሳደድሽን አቁሚ።››በማለት ገሰፃት፡፡ ቀጠል አደረጉና ‹‹ለሚያገባሽ ሰው አዝንለታለው።››ሲሉ አከሉበት፡፡
‹‹ደህና፣ ደስ ሚለው ነገር ፍቅረኛ የለኝም ››አለች ራሄል፡፡
‹‹እነዚህማ የተለመዱ ቃላቷችሽ ናቸው››
እናቷ በራሄል ንግግር ተከፍተው ‹‹አንድ ቀን ያንን በብቸኝነት የቀዘቀዘ አፓርታማሽን እርግፍ አድርገሽ ጥለሽ እንደ ዶ/ር ኤሊያስ ቤት አይነት ግቢ ወዳለው ቤት ትቀይሪ ይሆናል።››ሲሉ ምኞታቸውን ተናገሩ፡፡
እናትዬው ወደ ዶ/ሩ ዘወር አሉን‹‹ቤትህን በማስተካከል ላይ እንዳለህ ሰምቼያለው?››
‹‹በእውነቱ ወንድሜ ቢንያም ነው እየተከታተለው ያለው። እሱ አናጺ ነው። ስለ ኩሽና አሰራር አንዳንድ ውሳኔዎችን እንድወስን እየጨቀጨቀኝ ነበር, ነገር ግን ዘመናዊ ይሁን ወይም ባህላዊ ጭብጥ ይኑረው የሚለውን ለመወሰን እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም››
አቶ ቸርነት‹‹ራሄልን ይዘሀት ብትሄድ ልትረዳህ ትችል ይሆናል››የሚል ሀሳብ አቀረቡለት። ዔሊያስ የራሔልን መኮሳተር ችላ በማለት እንደ ተወደደ ልጅ ፊቱ እያበራ ነው።
አንቷም ‹‹አዎ የእኔ ልጅ …በኢንቴርዬር ዲዛይን ላይ በጣም ጎበዝ ነች።››ሲሉ የአባትዬውን ሀሳብ ደገፉ፡፡
ራሄል ስለእሷ የተሰጠ ያለው አስተያየት ከየት እንደመጣ አታውቅም። ወላጆቿ አፓርታማዋን በሚጎበኙበት ጊዜ በዕቃዎቾ፤በምንጣፎች እና በመኝታ ቤቷ ቀለም ..ብዙ ብዙ ኔጌቲቨ የሆነ አስተያየት ሲሰጧት እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ እንደውም እናቷ ‹ጥቂት እንኳን ለስሜቷ ሳይጨነቁ ቤቷን መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚየም እንዳስመሰለችው ነግረዋት ነበር፡፡
‹‹የምፈልገውን በትክክል አውቃለሁ። ትልቁ ችግሬ ግን ውሳኔዎችን ለመወሰን ጊዜ ማግኘት አለመቻሌ ነው ›› ሲል ኤሊያስ መለሰ።
ራሄል የሆነውን ነገር የተረዳች መስላ‹‹እንድትጨርሰው የምትገፋፋህ ሴት የለችም?››ስትል ጠየቀችው፡፡
አባቷ ራሄልን በግንባራቸው ገፆት ፡፡
ዶ/ሩ ‹‹ለጊዜው አቋሜ ልክ እንደአንቺው ነው….ለሴት ዝግጁ አይደለሁም››ሲል መለሰ።
ራሄል ውይይቱ ወደ መሃል ከተማ የትራፊክ ፍሰት፣ የኑሮው ውድነትና ፣ እና የፖለቲካ ውዥንብር.እና የሰላም እጦት የመሳሰሉት ጉዳዬች ላይ ሲያተኩር እፎይ አለች፡፡
በመሀል ወደ ዶ/ሩ አትኩራ እየተመለከተች ‹‹በቅርቡ የኖብል ፋውንዴሽን አመታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አለ።በዝግጅቱ ላይ መገኘትህን ማረጋገጥ አለብህ››አለችው፡፡
‹አረ ችግር የለውም..አታስቢ እገኛለው››ሲል ቃል ገባላት፡፡
እናትዬው‹‹ቀኑ ደረሰ እንዴ..?እንግዲህ በስራ ጫና ድራሽሽ ሊጠፋ ነው››ሲሉ ስጋታቸውን ገለፁላት፡፡
ራሄል ‹‹እማዬ ደግሞ ….እኔ ብቻዬን የማደርገውን አስመሰልሺው ። አብዛኛውን ስራ የሚሰሩልኝ ትላልቅ ሰራተኞች አሉኝ እኮ››
‹‹ነገር ግን ለሰራተኞችሽ በቂ ውክልና አትሰጪም።ቅድስትን ለመተካት እነዚያን ሁለቱን ረዳቶች መቅጠርሽን ስሰማ ብዙ የስራ ጫናሽን ያቃልሉልሻል ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን አሁን እንደማየው ከሆነ የበለጠ ስራ ነው ያበዛብሽ፡፡››
‹‹ሰራተኞቹ በጣም አዲስ ናቸው ። ፋይሎቹን ብቻ ሰጥቻቸው ሁሉንም ነገር በራሳቸው እንዲቋቋሙት መጠበቅ አልችልም።››
‹‹ዬኒቨርሲቲ ዲግሪ ያላቸውና …በደንብ የሰለጠኑ ናቸው እኮ።››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ግን የፋውንዴሽኑን ስራ በተመለከተ ትንሽ ተጨማሪ ልምድ ያስፈልጋቸዋል፣ሁሉም ሰው ወደሆነ አዲስ ስራ ሲሄድ ለተወሰነ ጊዜ ከአሰራሩ ጋር እስኪለማመድ አዲስ ሆኖ መገኘት አይቀርም››ለእናቷ ሌላ የማስጠንቀቂያ እይታ ሰጠቻት። ይህን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በማያውቁት ሰው ፊት መወያየታቸውን አልወደደችውም ።
‹‹ውዴ እወድሻለሁ፣ ግን ደግሞ አውቅሻለሁ።››ሲሉ እናትዬው በአቋማቸው መፅናታቸውን አረጋገጡላት፡፡
የራሄልን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት ‹‹እና ሁሉንም ነገር መቆጣጠር እንደምትችይ ማሰብ ማቆም አለብሽ። አንዳንድ ነገሮችን ለእግዚአብሔርን መልቀቅ አለብሽ።››ሲሉ ንግግራቸውን ደመደሙ፡፡

❤53👍5
‹‹እኔም ለእሱ ውክልና መስጠት አልፈልግም››ስትል ራሄል በመኮሳተር መለሰች።
የእናትና ልጅን ንግግር መክረርን የታዘቡት አባት ‹‹ርዕሱን መለወጥ እንችላለን?››ሲሉ ጣልቃ ገቡ፡፡
እናትዬው የፀጋን ፀጉር እየዳበሱ ‹እህትሽ መያዝ ትፈልጊያለሽ?››ብለው ጠየቋት።ራሄል በእናቷ እቅፍ ውስጥ ተመችቷት የተኛችውን ታዳጊ ተመለከተች። ይሄኛውም የሚመቻት የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ አልነበረም።እሺ ብላ ተቀብላ መያዝ እንዳለባት ታውቃለች፣ነገር ግን ስህተት እንዳትሰራ ፈራች።
ዔሊያስም ፍርሃቷን እንደተረዳ በሚያሳብቅ የድምፅ ቅላፄ‹‹አይዞሽ ..ታደርጊዋለሽ›› ሲል አበረታታት፡፡ማበረታቻውን ግን እንደለበጣ ነው የቆጠረችው፡፡ፀጋን በጎሪጥ ተመለከተች… ዓይኖቾ እየተቁለጨለጩ እሷን ሲመለከቱ አየች። እጆቾ ተዘርግተዋል …እግሮቿ ግትርትር እንዳሉ ነው…. ፀጋ በድንገት አሳዛኝ ለቅሶ አሰማች ።
‹‹ ልጄ፣አይዞሽ….›› ወ.ሮ ትራሀስ ለራሄል ሊያስታቅፏት ሞከሩ… ፀጋ ግን ፍቃደኛ አልሆነችም። ራሄል ወደ ፊት ተወረወረች እና የፀጋን የተወጣጠረ ሰውነት በማየቷ ልቧ ደረቷ ውስጥ ዘሎ የተሰነቀረ መሰላት።ዶ/ር ኤሊያስም መቀመጫውን ለቆ ፈጠን ብሎ ስሯ ተቀመጠና የፀጋን ሰውነት እያገለባበጠ ተመለከታት ‹‹ የጡንቻ መወጠር ይመስላል እግሮቿን መታሸት አለባቸው››አለ ፡፡ ወ.ሮ ትርሀስ እንደተናገረው የፀጋን እግሮች ማሻሸት ጀመሩ… እናም ሰውነቷ ቀስ እያለ ሲዝናና ራሄል በእፎይታ ተነፈሰች።
‹‹አየሽ? መጥፎ አይደለም››
‹‹አይ. ቢሆንም ትንሽ ፈርቼ ነበር››አለች ራሄል፡፡
ወ.ሮ ትርሀስ ወደ ራሄል ተመለከቱና እና ‹‹አሁንስ እሷን መያዝ ትችያለሽ?››ሲሉ ድጋሚ ጠየቋት፡፡
ራሄል መልስ ከመስጠቷ በፊት ኪሷ ውስጥ ያለው ስልክ ጮኸ ፡፡ አውጥታ ስታየው የደወለላትን ሮቤል ነበር፡፡ልክ እንደአዳኟ መልአክ ነበር የቆጠረችው።
‹‹ይቅርታ እማዬ ይህን ጥሪ ማንሳት አለብኝ››በማለት ይቅርታ ጠይቃና ለተፈጠረው ችግር አመሰግናለሁ፣ ኮሪደሩን ተጠቅማ ወደ ጓሮ በመሄድ ስልኩን አነሳችው፡፡
‹‹ሮቤል እንዴት ነህ?››አለችው።
‹‹ደህና ነኝ …ሴትዬዋ እንደገና ሀሳቧን ቀይራለች››አእምሮዋ በዚህ አዲስ ችግር ዙሪያ ተወጣጠረ፡፡ ራሄል ሁል ጊዜ ስትጨናነቅ እንደምታደርገው ጥፍሯን በጥርሶቿ ቀረጠፈች።‹‹ዛሬ ልታገኘን እንደምትፈልግ ተናግራለች›› ሮቤል ቀጠለ። ‹‹በእርግጥም ከአርባ አምስት ደቂቃ በፊት እዚያ መሆን ነበረብሽ.. ነገር ግን በወላጆችሽ ቤት እንደሆንሽ ስለሰማው ተውኩት።››አላት፡፡
የእህቷ ረዳት አልባ ለቅሶ ድምፅ ስታስታውስ ትንሽ ደነገጠች። ይህቺን በህመም የምትሰቃይ እና ከፍተኛ እንክብካቤ የምትፈልግ ህፃን ልጅ ለማሳደግ ወስነው በመውሰዳቸው ወላጆቿን በጣም አደነቀቻቸው። እሷ በእንሱ ቦታ ብትሆን ፈፅሞ ማድረግ እንደማትችል ታውቃለች።
‹‹ይቅርታ አድርግልኝ?››
‹‹ግድ የለም አሁን ችግሩ ምንድን ነው?››
‹‹ወ/ሮ ላምሮት የፋውንዴሽኑን የሩብ አመት ሪፖርት ማየት ትፈልጋለች። በእድገት ላይ እንደሆነ ማረጋገጥ ትፈልጋለች።››
ዔሊያስን በበሩ ላይ በዛ ቁመቱ ተጋርጦ ቆሞ ተመለከተችው።
‹‹እናትሽ በበረንዳው ላይ ኬክ እና ቡና እየቀረበ እንደሆነ እንድነግርሽ ጠይቃውኝ ነው›› አላት፡፡
‹‹አመሰግናለሁ… ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሁላችሁንም እቀላቀላችኋለው››በማለት ጠንከር ያለ ፈገግታ ሰጠችው፣
እሱ ግን ምንም አይነት የስሜት ለውጥ ሳያሳይ ፊቱን አዙሮ ሄደ። ከእሱ ጋር በመተዋወቋ ግልፅ ያልሆነ ምቾት እንደተሰማት መካድ አትችልም።የፀጋ ማራኪ ሐኪም ስለ እሷ ምን እንደሚያስብ ለማወቅ ለምን እንደምትጨነቅ አሰበች..እንደምንም እራሷን አረጋግታ ትኩረቷን ወደ ሮቤል መለሰች።
‹‹በሰዓቱ እንደምገኝ ለወይዘሮ ላምሮት ንገርልኝ››በመስኮቱ አሻግራ በአባቷ ጥናት ክፍል ግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የአያቷን ሰዓት ተመለከተች። ‹‹አንድ ሰዓት ያህል አላት››
‹‹ራሄል አንቺን ማጨናነቅ አልፈልግም ነበር….ግን ቶሎ ልታደርጊው ትችያለሽ?››
‹‹አዎ እችላለው፣ሴትዬዋ የምትኖረው በቸርቸል ጎዳና አካባቢ ነው...በ50 ደቂቃ እዚያ ለመድረስ ብዙም የምቸገር አይመስለኝም… ወላጆቼን ብቻ ተሰናብቼ አሁኑኑ ወጣለው ። ››
‹‹እሺ እንግዲህ፣ ስትደርሺ እዛው ቀድሜ እጠብቅሻለው::›› ራሄል ከንፈሯን ነክሳ የስልኩን ቁልፉ ተጫነችና ዘጋችው።አሁን ልሄድ ነው በማለቷ ወላጇቾ ደስተኛ አይሆኑም, ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ምንም ማድረግ አትችልም. ወ.ሮ ላምሮት ለፋውንዴሽኑ በጣም አስፈላጊ ሴት ነች። ዝግጅቶች በምታዘጋጅበት ጊዜ የታዋቂ እንግዶች ዝርዝር ለማውጣት በሚያስፈልግበት ጊዜ እሷ ከዋናዎቹ የዘወትር ለጋሾች ውስጥ ዋነኛዋ ነች።ወ.ሮ ላምሮት ባሏ ሲሞት ብዙ ገንዘብ በውርስ አግኝታለች፤በዛ ላይ በሀገሪቱ በብዙ ካምፓኒዎችን ታስተዳድራለች….እናም በባሏ ኑዛዜ መሰረት ከአመታዊ ትርፏ 25 ፐርሰንት ለበጎ አድራጎት ድርጅት መስጠት አለባት…እንግዲህ የእሷን ፋውንዴሽን ጨምሮ ሁሉም በሀገሪቱ በበጎአድራጎት ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች በጠቅላላ የእሷን ገንዘብ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ…. ። ራሄል ይህቺን ሴት በትክክል ካልያዘች፣በቀላሉ የእሷ ካምፑ በመልቀቅ ለተቀናቃኞ ፋውንዴሽን ገንዘቧን ለመስጠት ልትወስን ትችላለች። ህጋዊ የሚመስሉ ነገር ግን እስከ ሰማንያ በመቶ የሚሆነውን የለጋሾቻቸውን ገንዘብ “የአስተዳደር ክፍያ” ስም ለግል ጥቅማቸው ስለሚያውሉ ድርጅቶችን በሰማች ቁጥር የራሄል ደም እንዲፈላ ነው የሚያደርጋት፡፡እና የሴትዬዋን ልገሳ የማይሆኑ ድርጅቶች እጅ ገብቶ የግለሰቦች ኑሮ መዶጎሚያ እንዳይሆን መከላከልም አንደኛው አላማዋ ነው፡፡በእሷ ድርጅት የአስተዳደር ወጪ ከ25 በርሰንት መብለጥ እንደሌለበት ጥብቅ የሆነ መመሪያ አለ፡፡ለዛም ነው በዋናው ቢሮ ከሁለት ረዳቷቾ ጋር ሆና የአስር ሰው ስራ የምትሰራው፡፡
ወደውስጥ ስትገባ ወላጆቿ ቀደም ብለው በረንዳ ላይ ተቀምጠው ነበር ፣ የቀዘቀዘ ሻይ የያዘ ረጅም ኩባያ ከፊት ለፊታቸው ባለው የመስታወት ጠረጴዛ ላይ ይታያል።
ራሄል ስትደርስ ፀጋ በእግሮቾ ላይ ትልቅ ብርድ ልብስ ለብሳ እየተጫወተች ነበር፣ ለራሄል ፈገግ አለችላት፣ ቀላል ቡናማ አይኖቿ በምሽት መጀመሪያ ላይ ሲያበሩ ስትመለከት ደስ አላት። ራሄል ቆንጆ መሆኗን በውስጧ አሰበች፡፡
‹‹ እማዬ፣ አባዬ፣ ይቅርታ ዶ/ር …››ዓይኖቿ ዔሊያስ ላይ ተተከሉ ፣ ‹ አዝናለሁ ግን ሮቤል አሁን ደወሎኝ ነበር። ከለጋሾቻችን ከአንዷ ጋር ድንገተኛ ችግር ገጥሞናል ።ሄጄ ማስተካከል አለብኝ››
‹‹ኧረ ማር፣ ለምን እሱ ራሱ እንዲያስተካክለው አትተይለትም?››እናትዬው ተቃወሟት ፡፡
ወ.ሮ ትርሀስ ወደ ባላቸው ዞረው። ‹‹ቸርነት ፣ አናግራት እንጂ ።››አቶ ቸርነት ዝም ብለው ትከሻቸውን ከፍ በማድረግ ለልጃቸው ፈገግ አሉ።
‹‹ብትቆዪ ምኞቴ ነው ውዴ። ብዙ ጊዜ አናገኝሽም። ትንሿ እህትሽ እንኳን በደንብ አታውቅሽም…ከዚህ በተጨማሪ፣ እናትሽ ለአንቺ ብቻ ያዘጋጀችው የቸኮሌት ኬክ አለ›› አላት፡፡
ወ.ሮ ትርሀስም ‹‹አባትሽን ታውቂዋለሽ እና እኔም እንደዚህ አይነት ነገር አልበላም.››
‹‹በጣም አዝናለሁ እናቴ፣ ግን ኬኩን ብወስደው ደስ ይለኛል -››
‹‹እንግዲህ አልቆይም ካልሽ ምን አደርጋለው…አዘጋጅልሻለሁ።››ወ.ሮ ትርሀስ ከወንበራቸው ተነስተው ቆሙ‹‹በፍጥነት እመለሳለሁ››ብለው ወደውስጥ ገቡ፡፡

❤43👍5🥰2
ራሄል ሰዓቷን ለማየት በድብቅ የሸሚዟን እጅጌ ወደላይ ሰብሰብ አደረገችና ተመለከተች። ለመሰናበት ካሰበችው ጊዜ በላይ እየወሰደባት ነው፡፡በቀራት ደቂቃ ቀጠሮው ቦታ ለመድረስ የመኪናዋን ፍጥነት ከተገቢው በላይ ለመልቅ ልትገደድ እንደምትችል አሰበች፡፡የተጨናነቀ ትራፊክ እንዳያጋጥማት እየተመኘች ሸሚዞን ወደ ቦታው መለሰች፡፡ድንገት ዶ/ሩ በግማሽ ፈገግታ በትኩረት ሲመለከታት ያዘችው። ራሄል ይህን አልለመደችም። አብዛኞቹ ወንዶች ከእሷ ጋር እንዲህ አይነት የዓይን ጫወታ መጫወት አይደፍሩም፡፡
አባቷ ፀጋን በእቅፋቸው ይዘው እያጫወታት ነው‹‹አይዞሽ ልጄ ..ትደርሺያለሽ. .አትጨናነቂ…ሁሉነገር እግዚያብሄር ከፈቀደ ይሆናል…ካልፈቀደ ደግሞ ምንም ብትለፊ የቱንም ያህል ብትጥሪ አይሆንም››የሚል ምክር አከሉበት፡፡
የአባቷን ስብከት ውጦ ለመቀበል ትዕግሥት አጣች፡፡ ወዲያው ደግሞ እሳቸው እንደሚያምኑት ማመን ባለመቻሏ እፍረት ተሰማት። አባቷ በእምነታቸው ቅን ሰው ናቸው። እሳቸው በዚያ መጠን በእግዚያብሄር እያመኑ መቀጠላቸው እሷን ሊያበሳጫት አይገባም ነበር፡፡ እንዲያውም እሷም እንደእሳቸው በአምላክ ላይ ያላትን እምነት ለመጋራት የምትመኝበት ጊዜ አልፎ አልፎ ነበር። ግን ማድረግ አልቻለችም፡፡
ለአባቷ መልስ መስጠቱን ተወችውና እይታዋን ወደ ዶ/ሩ አዞረች፡፡እጆቹን ቁልቁል እያየ ነበር፣ የአንዱን እጁን ጣቶች ወደ ደረቱ ወሰደ ፤ከዛ በኋላ ነበር ከክርኑ አንጓ እስከ አውራ ጣት ግርጌ ድረስ የሚሄድ ረዣዥም የተሰነጠቀ ጠባሳ እንዳለበት ያስተዋለችው። በደንብ ያልተሰፋ ይመስል ነጭ እና የተቦጫጨቀ ሆኖ ይታይ ነበር። ሞተር ሳይክሉን ሲያበር ያገኘው አደጋ ይሆናል ስትል አሰበች ፡፡በዚያን ጊዜ ቀና ብሎ አያት።
‹‹ኬክሽ ይኸውልሽ ውዴ።››ወ.ሮ ትርሀስ አንድ መለስተኛ የታሸገ ካርቶን በሰማያዊ ፔስታል ውስጥ አድርገው አቀበሏት፡፡ ራሄል ፔስታሉን ተቀበለችና በእጇ እየመዘነች ‹‹ይህ ግማሹ ነው››አለች ።
‹‹ቀሪውን ደግሞ እኔና አባትሽ አንበላዋለን - ››
‹‹ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ምግቦቼ የቸኮሌት ኬክ እንደሆነ በምናቤ ሳስብ ደስታ ተሰማኝ ።››
‹‹ማር, እንዳታደርጊው››ወ.ሮ ትርሀስ ፊታቸውን በማኮሳተር ኬኩን መልሰው ሊወስድባት ሞከሩ፡፡
‹‹አይ, አታደርጊውም››ራሄል እናቷ እቃውን እንዳይነጥቋት እየተከላከለች ‹አትጨነቂ እኔ እየቀለድኩ ነው. ዛሬ ማታ አንድ ቁራጭ ከላዩ ላይ በላለትና የቀረውን ወደ ሥራ ቦታ እወስደዋለው፡፡እርግጠኛ ነኝ ሮቤል እና ሎዛ በዚህ ኬክ ላይ ይጣሉበታል.››
‹‹አዎ እንደዛ ነው ማድረግ ያለብሽ››
‹‹አሁን ሳሙኝ እና ብሄድ ይሻላል።››
ራሄል እናቷን በፍጥነት አቅፋ ሳመች እና ከአባቷ እና ከፀጋ ጋር ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ ጎንበስ ብላ ሳመቻቸው።ከመሄዷ በፊት በዔሊያስ ላይ ዓይኗን ጣለች። እሱ በሁለት ሜትር ርቀት ላይ ነበር፣ ነገር ግን በዚያ ርቀት ላይ ቢሆንም ሰውነቷን የዳሰሳት አይነት ስሜት ነው የተሰማት።ወደ መኪናዋ ስትሄድ ስሜቷን ተናወጠ።
ስትመለስ ለወላጆቿ ሁሉን ነገር ግልጽ የምታደርግላቸው መስሏት ነበር። አስፈላጊው የእናት እና የሴት ልጅ ውይይት ጊዜ እንደደረሰ አውቃለች። በተቃራኒው ራሄል በአጀንዳው ላይ የሚቀጥለውን ንጥል ፋይል ስትከፍት ማዛጋት ጀመረች።

❤39👍7
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ከወ.ሮ ላምሮት ጋር የተደረገው ስብሰባ በጣም ረጅም ጊዜ ወስዶ ነበር እና ውጤቱ በጣም ጥቂት የሚባል ነበር፡፡
ራሄል በጣም የደክማት ቢሆንም ቢሮዋ ገብታም ስራዋን ቀጥላለች፡፡
‹‹ጥሩ ነው…በብሮሹሮች ላይ ስህተቶችን አግኝቻለሁ.››
ሎዛ ወረቀቶቹን በመካከላቸው ባለው የእንጨት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠች። ራሄል በተቀመጠችበት የቆዳ ሶፋ ላይ ወደ ኋላ ተደግፋ ከፊቷ ያለውን ብሮሹር ቃኘች። ‹‹ይህ ሰማያዊ ቀለም በጣም ደማቅ ነው….እና ይህ ቢጫው ደግሞ እንዲጠናከር እፈልጋለሁ። የቀረውን ደግሞ ደውዬ አሳውቃቸዋለሁ››
‹‹ለምን ያን እኔ ራሴ እንድከታተል አትፈቅጂልኝም?›› አለች ሎዛ
‹‹አመሰግናለሁ ሎዛ.. ግን ማየት የምፈልገውን በትክክል አውቃለሁ።››
ሎዛ ራሷን በይሁንታ ነቀነቀች፣ ራሄል ግን በእሷ ውሳኔ ደስተኛ እንዳልነበረች አይታለች።
‹‹ለአሁን እንዳደርግ የምትፈልጊው ሌላ ነገር አለ?››ሎዛ ጠየቀች።
‹‹ አይ ምንም የለም… በቃ እጅሽ ላይ ያሉ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጊ።››የሚል ትእዛዝ ሰጠቻት፡፡
ራሄል ወረቀቶቹን በጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጠች እና ሎዛ ቢሮዋን ስትለቅ ወደ ሮቤል ዞረች።
‹‹ሮቤል አንተ የሆነ ነገር አንድታደርግልኝ እፈልጋለው››አለችው፡፡
ሮቤል ጎንበስ ብሎ ከቆዳው ቦርሳ ውስጥ አንድ ወረቀት አወጣና‹‹ጥቂት ስልክ ደዋውዬ ከምንጩ ያገኘሁት መረጃ ነው።›› በማለት ተጨማሪ ወረቀቶችን አቀበላት።
‹‹ከስብሰባው ጥቂት ቀደም ብሎ ከድርጅቱ ኃላፊ ጋር በግል ተወያይቼ ነበር።››
‹‹ጉልበቱን ከየት አመጣው?››ስትል አሞገሰችው፡፡ ራሄል ከወ.ሮ ላምሮት ጋር ከተገናኘ በኋላ ስላከናወናቸው ውይይቶችና ስለተለዋወጦቸው ቃላቶች በማሰብ ደክሞት ነበር።‹‹ይህ በጣም ጥሩ ነው፣ቀጣዩ እርምጃችን የበጎ አድራጎት ልገሳ ሁኔታቸውን ማረጋገጥ እና ከቻልን በእነሱ ላይ አንዳንድ ጥልቅ የጀርባ ስራዎችን መስራት ነው።››
‹‹እንደተፈጸመ ቁጠሪው.››ሲል ሮቤል ፈገግ አለ። በዚህ ጊዜ ስልኳ ጠራ…እናቷ መስመር ላይ ነበረች።‹‹እንደገና አመሰግናለሁ ሮቤል።በቅርብ ጊዜ ፋውንዴሽኑን እንደተቀላቀለ ሰው ምርጥ ስራ ሰርተሃል.›› ብላ ስልኩን አነሳች፡፡
ራሱን ነቀነቀና ዞር ብሎ ከቢሮ ወጣ።ራሄል ከኋላው ባለው ትልቅ የቆዳ ወንበር ላይ ለመቀመጥ በጠረጴዟ ዙሪያ ዞራ ሄደች።
‹‹ጤና ይስጥልኝ እናቴ››
‹‹ደህና ነኝ የእኔ ልጅ››
‹‹ እየሮጥኩ ያለሁት ባንቺ ጉዳይ እንደሆነ ከግምት ውስጥ በማስገባት ልትደሰቺ ይገባሻል።››ስትል ራሄል ወንበሯ ላይ በመቀመጥ ተሸከረከረች፡፡
‹‹ውዴ፣ ሁሌም በአንቺ ደስተኛ ነኝ ፡ ታውቃያለሽ?››
‹‹እማዬ አውቃለው…የቸኮሌት ኬኩ በጣም ጥሩ ነበር. ሮቤል እና ሎዛ አመስግኚልኝ ብለዋል.››
‹‹እንደተካፈላችሁት በማወቄ ደስተኛ ነኝ። ግን አንቺን አንድ ውለታ ልጠይቅሽ ነው። አያቶችሽ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ አድዋ ሄደን እንደንጠይቃቸው ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ፀጋን ይዘን ለመሄድ መድፈር አልቻልንም ።እስክንመለሰ እሷን ለመጠበቅ ፈቃደኛ ነሸ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡ራሄል በድንጋጤ ስልኩ ሊያመልጣት ነበር..በመከራ ነው አጥብቃ የያዘችው።
‹‹ፈቃደኛ? ምናልባት…ቆይ እስኪ ፕሮግራሜን ልመልከት››አለችና የቀጠሮ ደብተሯን ለማየት ማስታወሻ ደብተሯን ከፈተች። በዛን ወቅት የማይሰረዝ ፕሮግራም ኖሯት ያንን እንደምክንያት ማቅረብ እንድትችል በውስጧ ፀለየች፡፡
የወሩ የመጨረሻ ቅዳሜና እሁድ…..ቢንጎ …የበጎ አድራጎት ፈንድ የመሰብሰብ ፕሮግራም አለባት። ‹‹ይቅርታ እማዬ ባልሻቸው ቀናት መሰረዝ የማልችላቸው ፕሮግራሞች አሉብኝ…በነዛ ቀናት አመታዊ የፋውንዴሽኑ ፈንድ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አለብኝ ።››
‹‹ኦህ ውዴ፣ አያትሽ ቤት የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው።›› በለሆሳስ ተነፈሰች። እና ፀጋን ከማንም ጋር ልተዋት እችላለው? ….እንደምታውቂው እስካሁን በጣም ደካማ ነች።››
‹‹ለምን ስለችግርሽ ከዶክተር ዔሊያስ ጋር አታወሪበትም››ስትል ሀሳብ አቀረበች።
‹‹በእርግጥ ትክክል ብለሻል .. እሱ የግል ነርሲንግ ኤጀንሲን ወይም ተመሳሳይ ነገርን ሊመክረኝ ይችላል?››
ራሄል አሰበች፤ የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማት አይገባም። ወላጆቿ ይችን ልጅ ለማሳደግ መወሰናቸው የሷ ሀሳብ አልነበረም። እና ፀጋ ብቃት እንደሌላት እና አቅመ ቢስነት እንዲሰማት ያደረጋት የሷ ስህተት አልነበረም።
‹‹እሷን መንከባከብ ካልቻልሽ ችግር የለውም…›› እናቷ ቀጠለች‹‹እርግጠኛ ነኝ ዔሊ ፀጋን የት ልንወስደት እንደምንችል ያውቃል።››
‹‹እንደሚያውቅ እርግጠኛ ነኝ››ስትል ራሄል ተስማማች፣ እፎይታም ተሰማት።
‹እና ስለ ዶክተር ዔሊያስ ምን አሰብሽ? ››እናትዬው እንደቀልድ ሌላ ርዕስ ከፈተች፡፡
‹‹እሱ በጣም ደስ የሚል ሰው ነው…. ከፀጋ ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት አለው ››
ከእሷ ጋር ሊጣመር የሚችልበት ምንም እድል እንደማይኖር ለእናቷ ግልፅ ለማድረግ ጊዜው አሁን እንደሆነ ተሰማት ‹‹ግን እሱ የእኔ ምርጫ አይደለም ።››ስትል መለሰችላት፡፡
‹‹ምን አልሽ?››
‹‹እማዬ… እባክሽ አሁን ለማንም ቢሆን ጊዜ የለኝም… ታውቂያለሽ››
‹‹ባለፉት ስምንት አመታት ውስጥ ለማንም ጊዜ አልነበራሽም። ብዙ ማህበራዊ ህይወት የለሽም። የምታደርጊው አንድ ነገር ቢኖር ስራ መስራት ብቻ ነው።››
ራሄል ወንበሯን ትንሽ እያወዛወዘች ፊቷን ከሰከሰች። ‹‹ይህን ስራ እፈልገዋለሁ እናቴ…ለህይወቴ ትርጉም የሰጠኝ ስራዬ ነው››
‹‹ከጌታ ጋር ያለሽ ግንኙነትስ? ያ እንዴት አድርጎ ነው ስራሽን የሚጋፋው?››ወደ ማትፈልገው ሌላ ርዕስ ከተተቻት፡፡
‹‹‹እናቴ ሆይ፣ የእኔ ስራ የተቸገሩ ህፃናትንና አቅመ ደካሞችን መርዳት ነው። ኢየሱስ በዚህ ምድር እንድናደርግ የሚፈልገውን ተግባር ነው እያደረኩ ያለሁት።››ራሄል እናቷን የሚያስደስት ትክክለኛ ቃላቶችን ታውቃለች እና ያለ እፍረት ተጠቀመችባቸው፡፡
‹‹ያለ እምነት ሥራ የሞተ ነው ውዴ።›› እናቷ ወደ እምነቷ ሲመጣ…ጥልቅ የማሰብ ችሎታ ስላላት ሁሉንም የልጇን የማጭበርበሪያ ስልቶች ታውቃለች።
ራሄል በመጨረሻ ‹‹እኔ ማድረግ የምችለው ይህን ብቻ ነው እናቴ››አለች. ቀጠለችናም ‹‹ለወንድ ጓደኛ ጊዜ የለኝም እና ለአንድም ሰው ፍላጎት የለኝም። ስለዚህ እባካችሁ ከአሁን በኋላ የማልፈልገውን አይነት አስጨናቂ እራት ለማዘጋጀት አትሞክሩ።››ስትል ንግግሯን በመኮሳተር ደመደመች፡፡
የእናቷ ዝምታ እጅ የመስጠት ምልክት እንደሆነ ተስፋ አድርጋ ነበር።‹‹ደስተኛ ነኝ እማማ›› እናቷ ብርሃኑን እንድታይ ለማድረግ ቆርጣ ገፋችበት። ‹‹ዓላማ እና ትርጉም ያለው ንቁ ህይወት ነው እየኖርኩ ያለሁት ። ጓደኞች አሉኝ እናም በማህበረሰብ ውስጥ አስፈላጊ የሚባል ስራ አለኝ። እና አንቺ እና አባዬ እና ፀጋም አለችሁልኝ። ተጨማሪ አያስፈልገኝም።››
‹‹እሺ፣ ይቅርታ፣ አንቺና ዔሊ ትመጣጠናላችሁ ብዬ ስላሰብኩ ነው። እሱ ጥሩ እና ደግ ሰው ነው..ለዛ ነው ከእሱ መዛመድ የፈለኩት ።››
ራሄል ፊቱ ላይ ስለተመለከተችው ፈገግታ አሰበች‹ደህና፣ ለአንድ ሌላ ሴት ግሩም ባል እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ግን ያቺ ሴት እኔ አይደለሁም፣ እማማ።››
ወ.ሮ ትርሀስ ቃተቱ። ‹‹ካስከፋሁሽ ይቅርታ።››
‹‹አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጠርሺብኝ እንጂ አላስከፋሺኝም።››

❤62👍6
‹‹ደህና፣ በቃ ቻው፣ ከአንድ ፊዚዬቴራፒስት ጋር ቀጠሮ አለኝ እና ከዚያ በኋላ ዶ/ር ኤሊያስን አገኘዋለው። ሰላም እንዳልሽው ልንገረው?››እናቷ የማይበገሩ ነበሩ።
‹‹እናቴ የፈለግሽውን አድርጊ…. እወድሻለሁ።››
የእናቷ ድርጊት አንዳንድ ጊዜ እብድ ሲያደርጋት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንድታፍር ያደርጋታል… እንደዛም ሆኖ ራሄል ወላጆቿን በጣም ትወዳለች።‹‹አንቺንም እወድሃሸለው ውዴ።››
ራሄል ስልኩን ዘግታ በሀሳብ ተዋጠች። ራሄል እናቷ ፀጋን በማደጎ ወደቤቷ ስያመጣት ውስጣዊ ስሜቷን እንደምታረካላቸው እና እሷ ላይ የሚያደርጉትን ትኩረት ይቀንሳሉ ብላ ገምታ ነበር ግን አሁን እንደምታየው ምንም የተቀየረ ነገር የለም፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronoseቀ

👍32❤13