አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የድንግሊቷየ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_ዘሪሁን_ገመቹ
===============

ላዳዋ ይዛቸው ትንሽ እንደተጓዘች

‹‹እሺ ምን ገጠመህ?››ሲል አለማየሁ  የመጀመሪያውን ጥያቄ ጠየቀ፡

አላዛርም‹‹ሰውዬው እየሞተ ነው መሰለኝ….፡፡››ሲል በደፈናው መለሰ፡፡

ሁሉም የአላዛር መልስ አልገባቸውም‹‹የትኛዬው ሰውዬ?››ሲል ሁሴን ጠየቀ፡፡

‹‹አባት ተብዬው፡፡››

‹‹በስመአብ..?ማን ነገረህ?››ሰሎሜ በድንጋጤ ጠየቀች፡፡

‹‹አንድ ሴትዬ ነች..ሚስቱ ነኝ አለችኝ..አላውቃትም፡፡››

‹‹ጋሽ ተሰማ አግብተዋል እንዴ?››ሁሉም በመገረም ጠየቁት..፡፡

‹‹እኔም ዛሬ ነው የሰማሁት፡፡››

‹‹አይዞህ አትደንግጥ ምንም አይሆኑም››ሰሎሜ ልታፅናናው ሞከረች፡፡

በንዴት በሚርገበገብ ድምፅ ‹‹ለምንድነው የምደነግጠው…? ቢሞት እንደውም ግልግል ነው፡፡››ሲል መለሰላቸው፡፡

‹‹ባክህ አታስመስል..ባትደነግጥ በዚህ ምሽት እኛንም ቀስቅሰህ ልታያቸው  ትሄድ ነበር?፡፡››
ሰሎሜ  ነች ተናጋሪው፡፡

‹‹አንቺን  አልቀሰቀስኩም..ብቻዬን  ከምሆን አሌክስን ብቻ ነው አካሂደኝ ያልኩት..አንቺና ሁሴንን አልጠየቅኳችሁም፡፡››

‹‹እና እናንተ ጓደኞቼ አይደላችሁም እያልከን ነው?››አለው ሁሴን በንዴት፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ሁሌ ነገር ማጣመም ትወዳለህ፡፡››አላዛር ተበሳጨ፡፡

ሰሎሜ በድጋሜ‹‹ዝም ብለህ ስታስመስል ነው..ምንም ቢሆን አባትህ ናቸው፡፡››አለችው  ፡፡

‹‹ዝም በሉኝ በቃ… ሌላ ወሬ አውሩ››ተቆጣ ፀጥ አሉ…

አላዛር ሰፈሩን እንጂ ቤቱን እርግጠኛ አይደለም..ከአመት በፊት ነው አንድ ጓደኛው ጋር በዛ ሰፍር ሲያልፉ ‹‹የአባትህ ቤት ይሄ ነው›› ብሎ ያሳየው….በወቅቱ እቤቱን በጨረፋታ ተመልክቶ ከመገርም ውጭ  ለነገረው ልጅ  እንኳን መልስ አልመለሰለትም ነበር፡፡ግን እቤቱ እንደፈራው አልጠፋውም፡፡ሲደርሱ ከላዳዋ ወርደው ወደአጥሩ በራፍ እየሄዱ በተደወለለት ስልክ መልሶ ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ አላዛር››ቀጭንና ልስልስ ድምፅ፡፡

‹‹መጥተናል በራፉን ክፈቺልን፡፡ ››

‹‹ክፍትነው ግፋውና ግባ፡፡››
እንዳለችው ገፋ ሲያደርገው ተከፈተ፡፡ሶስት ጓደኞቹን አስከትሎ አልፎ ወደውስጥ ሲገባ የሳሎኑ በራፍ ሲከፈት ተመለከተ.. በፍጥነት ተጠጉ..አንድ በእሱ እድሜ ያለች ገጠር ቀመስ ግን ደግሞ ውብ  ሴት እየተንቀጠቀጠች ትታያለች፡፡የአራቱም ዓይኖች በመላ አካሎ ላይ ተንከባለሉባት፡፡

‹‹የደወልሽልኝ አንቺ ነሽ?››

‹‹የአባቴ ሚስት አንቺ ነሽ ?››ብሎ መጠየቅ ነበር የፈለገው…..ምክንያቱም ይሄቺን የመሰለ ትንቡክቡክ ያለች ውብ ገራገር ወጣት ያንን ያበቃለትን የሰው አውሬ ብሎ የሚያስበውን  አባቱን እንዴት ታገባለች ብሎ ይገምት?››

‹‹አዎ ግቡ ግቡ ››በማለት ይዛቸው ወደውስጥ ገባች….እቤቱ ሳሎንና አንድ መኝታ ክፍል ያለው ባለሁለት ክፍል ነው፡፡አባትዬው ሳሎን ባለ አንድ አሮጌ ሶፋ ላይ ዝርግትግት ብሎ ትኝቷል፡፡ተጠጋውና በመጠየፍ አንገቱን ይዞ አወዛወዛው.. ለበድንነት የቀረበ ሁኔታ ላይ ነው ያለው፡፡
አለማየሁ‹‹ቶሎ ብለን ሀኪም ቤት እንውሰዳቸው››ብሎ ቀድሞ ሄደና ሰቅስቆ አቀፋቸው…ሁሴን የተንንዘላዘለ እግራቸውን በመደገፍ ሊያግዘው ሞከረ፡፡ሰሎሜ ተከተለችው…፡፡አላዛር ወደኃላ ቀረና

‹‹..አንቺ እዚሁ ጠብቂን…አይዞሽ ሰውዬው በቀላሉ የሚሞት አይነት ሰው አይደለም…አትጨናነቂ››አላት፡፡

የንግግሩ ይዘት አልገባትም፡፡ግራ በመጋባት አይኖቾን አቁለጨለጨችበት፡፡ ትከሻዋን በእጆቹ ቸብ..ቸብ እያደረገ‹‹አይዞሽ አትጨነቂ አልኩሽ እኮ…ያለውን ነገር እየደወልኩ አሳውቅሻለሁ፡፡ የሚያስተኙት ከሆነ  ጥዋት መጥቼ ወደተኛበት ሆስፒታል ወስድሻለው››ሲል ቃል ገባለት፡፡

ምርጫ ስላልነበራት
‹‹እሺ..አመሰግናለሁ..እግዜር ይስጥልኝ› ›ስትል መለሰችለት፡፡

አላዛር ፊቱን አዞረና ወጥቶ ሄደ..ጓደኞቹ አባትዬውን ላዳ ውስጥ አስገብተውት ነበር የጠበቁት….፡፡
አለማሁ ቀልቡ እዛ ቤት የቀረችው ወይዞሮ ላይ ተጣብቆ ስለቀረ ዝም ብሎ ላዳዋ ውስጥ ሊገባ አልቻለም፡፡

‹‹ እሷ አትመጣም እንዴ?››ሲል አላዛርን ጠየቀው…፡፡

‹‹ምን ትሰራላች ላዳዋ ለእኛም እኮ አትበቃንም፡፡››

‹‹አይ ድንጋጤ ላይ ስላለች ብቻዋን ትፈራለች ብዬ ነው፡፡››ለእሷ ይሄን ያህል ምን እንዳሳሰበው አያውቅም፡፡ግን ድንገት በጨረፍታ እንዳያት በዛው እስከወዲያኛው ሊረሳት አልፈለገም፡፡

አላዛርም ስጋቱ ተጋባበትና‹‹ለምን ከሶስታችሁ አንዳችሁ አብራችኋት አትሆኑም?››የሚል ሀሳብ አስከተለ፡፡ ሰሎሜን፤ ሁሴንንና አሌክስ እርስ በርስ ተያዩ…‹‹አንተ አብረሀት ሁን..ሁለት ሴት አብረን ከመፍራት ውጭ ምን እረዳታለው?ሁሴንም ቢሆን ወረቀት የሌለበት ቤት ያቃዠዋል››ስትል  ሰሎሜ  የራሷን ሀሳብ አቀረበች ፡፡

አለማየሁ በቀረበው ሀሳብ በመደሰት‹‹በቃ እሺ… እኔ አብሬት ሆናለው…ግን ያለውን ነገር በስልክ አሳውቁኝ፡፡››በማለት መስማማቱን አሳወቀ፡፡

አላዛርም‹‹አመሰግናለው አሌክሶ›› አለና ገቢና ገባ ፡፡ሰሎሜ ና ሁሴን ከኃላ  አባትዬውን ከግራና ቀኝ ደግፈው  ተቀመጡ… አሌክስ መልሶ ወደ ጊቢው ሲገባ ላዳዋ ተነቀሳቀሰች፡፡

አለማየሁ ወደጊቢ ገብቶ የሳሎኑን በር ሲቆረቁር…ወዲያው ብርግድ ተደርጎ ተከፈተ..ከበራፉ ጋር.. ያልጠና የወጣትነት ልቡም ነበር አብሮ የተበረገደው፡፡እሷ በራፉን ስትከፍት አላዛርን ነበር የጠበቀችው…ጓደኛው ሆኖ ስታገኘው ግን ግራተጋብታ

‹‹ምነው…ምን እረሳችሁ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አይ ምንም አረሳንም…ብቻሽን እንዳትሆኚ አብረሀት ሁን ብለውኝ ነው››

ነበር?››አለችው ከግራ መጋባቶ ሳትላቀቅ‹‹ውይ እኔ ምን ሆናለው ?እነሱን ብትረዳቸው አይሻልም፡፡

‹‹ሶስት እኮ ናቸው..እንደውም ከባለላዳው ጋር አራት ናቸው..እሱም  የሰፈር ልጅ ስሆነ ያግዛቸዋል፡፡››

‹‹ጥሩ እሺ ግባ››ብላ በራፉን ለቀቀችለት፡፡በዝግታ እርምጃ ገባና ፊት ለፊት ያለ አሮጌ ሶፋ ላይ ተቀመጠ፡፡እሷም በራፉን ዛጋችና ከእሱ በአምስት ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ኩርሲ ላይ ጭብጥብጥ ብላ ተቀመጠች፡፡ለተወሰነ ደቂቃዎች ዝም ተባባሉ፡፡
ከገባችበት ሀሳብ እንደመባነን ብላ‹‹ወይኔ በእግዚያብሄር ዝም አልኩህ አይደል…?ሻይ ላፍላ ብና?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አረ ችግር የለውም….ከቻልሽ ውሀ ስጪኝ››አላት

‹‹ እሺ››ብላ ወደውስጥ ገባችና ውሀ በብርጭቆ አምጥታ ሰጠችው….ተመልሳ ወደ ጓዲያ ገባችና የተጣጠፈ ጋቢ እየዘራጋች መጥታ ‹‹ብርድ ነው ትከሻህ ላይ ጣል አድርገው›› አለችውና አቀበለችው… ተቀበላትና ለበሰው፡፡

‹‹የአላዛር ጓደኛው ነህ?››

‹‹አዎ ጎረቤት ነን..አብረን ነው ያደግነው..ወንድም በይኝ››

‹‹እሳቸውንም ታቃቸዋለህ ማለት ነዋ?››

‹‹ጋሽ ተሰማን…አዎ ለእኔም አባቴ በያቸው፤ግን መቼ ነው የተጋባችሁት…?›ሲል የገረመውን ጥያቄ ጠየቃት፡

‹‹ብዙም አልቆየን… አንድ ሰባት ወር ቢሆነን ነው…፡፡››

‹‹ትዳር ታዲያ እንዴት ነው?፡፡››

እንደማፈር አለችና ተሸኮረመመች‹‹ችግር የማያደርግህ ነገር የለም፡፡የምደገፍበት ቤተሰብ የማኮርፍበት ዘመድ ስላልነበረኝ እሷቸው ላግባሽ ሲሉኝ እምቢ ማለት አልቻልኩም፡፡..ምንም እንኳን በእድሜ ከአባቴ ሚበልጡ ሰውዬ እንደሆኑ ባውቅም….አምላክ ከፈቀደው ምንም አይደል እንደአባት ይንከባከቡኛል እንደባል ያስደስቱኛል ብዬ እሺኝ አልኩና ገባሁበት፡፡የተደበቀ አመላቸው አፈትልኮ ለመውጣት ግን አንድ ወር እንኳን አልፈጀበትም…፡፡በቃ ትንሽ መጠጥ ከቀመሱ ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ሳይሆን ሌላ አውሬ ነው የሚሆኑት፡፡ከዛሬ ነገ ይሻሻላሉ በማለት
👍8613😱2
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_ዘሪሁን_ገመቹ

ራሄል ከሁለት ረዳቷቾ ከሮቤልና ሎዛ ጋር  ስብሰባ ላይ እያለች ነበር ስልኳ የጠራው…ንግግሯን ሳታቋርጥ ስልኩን አነሳችና አየችው፤  አባቷ አቶ ቸርነት ናቸው የደወሉላት ፡፡ስብሰባ ላይ ነኝ ብላ ልትዘጋባቸው አልፈለገችም…አባቷ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ባይሆን ኖሮ በዚህ ሰዓት አይደውሉላትም ነበር፡፡

‹‹አንዴ ይቅርታ… ይሄንን ስልክ ማንሳት አለብኝ››ብላ ከተቀመጠችበት ግዙፍ ተሸከርካሪ ወንበር ተነሳችና ቢሮውን ለቃ ወጣችና….ከዛ ስልኩን አነሳችው፡፡

‹‹ሄሎ አባዬ ..እንዴት ነህ?››

‹‹ሰላም ነኝ ልጄ››

ድምፃቸው ተጎተተባት‹‹ምነው አባዬ? ችግር አለ እንዴ?››

‹‹አይ ልጄ ሁሉ ነገር ሰላም ነው…እኔ እና እናትሽ አንድ ነገር ልናማክርሽ ነበር››

‹‹ምንድነው?››

‹‹ይሄውልሽ ልጄ ምን መሰለሽ..እኔና እናትሽ ጡረታ ወጥተን ቤት መዋል ከጀመርን በኃላ ህይወታችንን ታውቂያለሽ…ብቸኞች ነን..አንቺም አሻፈረኝ ብለሽ በራስሽ ቤት ነው የምትኖሪው…፡፡››

ራሄል በምትሰማው ነገር ፊቷን አጨማደደች….የገመተችው አብረሽን ኑሪ የሚለውን የዘወትር ጥያቄያቸውን ደግመው ሊያነሱባት ነበር የመሰላት፡፡

አባቷ ትንፋሽ ወሰዱና ንግግራቸውን ቀጠሉ‹‹እህት እንዲኖርሽ ፈልገን ነበር››

ደነገጠች‹‹እህት!!››

‹‹አዎ ቅር ማይልሽ ከሆነ እኔ እና እናትሽ እህት እንዲኖርሽ ፈልገናል…የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት ያንቺን አስተያየት ማወቅ ስለፈለግን ነው የደወልንልሽ፡፡››

‹‹ብዥ አለባት…እናቴ በሰባ አመቷ አረገዘች እንዴ?››ስትል በውስጧ እራሷ ጠየቀች፡፡‹‹አባቴ የአብረሀምን አይነት የዋህነት ስላለው  እግዜር በዚህ አድሜዋ የማዬን ማህፀን ቢከፍት አይገርመኝም››ስትል በራሷ ሀሳብ ሳቀችና ትኩረቷን ወደስልኩ መለሰች፡፡

‹‹አባዬ አልገባኝም..እንዴት ነው እህት ሊኖረኝ የሚችለው?››

አንድ የሁለት አመት  ቆንጅዬ ሴት ልጅ በጉዲፈቻ ልንወስድ ነው….››

‹‹በጉዲፈቻ…በጣም ደስ ይላል….ጥሩ ውሳኔ ነው የወሰናችሁት..››

ሀሳባቸውን ለመደገፍ ጥቂት ማሰብ እንኳን አላስፈለጋትም…የሁለት አመት ጣፋጭ ልጅ እዛ ግዙፍ ቪላ ቤት ውስጥ ስትሯሯጥ…አንዴ አባቷ ላይ አንዴ ደግሞ እናቷ ላይ እየተንጠለጠች ስታስቃቸውና ሰታዝናናቸው፣እነሱም ሲያሞላቅቋት…እሷን መሀላቸው አድርገው ግራና ቀኝ እጇን ይዘው ወደቤተክርስቲያን ይዘዋት ሲሄዱ .... በአይነ ህሊናዋ ታያትና በደስታ  ተፍለቀለቀች፡፡

‹‹ልጄ አሁን እሷን ልናይ   ሆስፒታል ነው ያለነው ..ከቻልሽ  ጋንዲ ነን  …ብትመጪ ደስ ይለኛል፡፡››

መልሶ መደነጋገር ውስጥ ገባች‹‹ሆስፒታል…ምን ትሰራለች?››

‹‹ትንሽ አሟታል…ከቻልሽ ነይ፡፡››ደገሙላት፡፡

‹‹በቃ መጣው››……ስልኩን ዘጋችና ወደቢሮዋ ተመልሳ ለረዳቶቾ ወደስራ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ሰጥታ  ቦርሳውን አንጠልጥላ ወጣችና  ቀጥታ ከፓርክ መኪናዋን  በማንቀሳቀስ ስለአዲሷ እጩ እህቷ ምን እንደምትመስልና…ምኗን ታማ ሆስፒታል ልትገባ እንደቻለች እያብሰለሰለች   ወደጋንዲ  ሆስፒታል ነዳችው፡፡

ደርሳ  ወደውስጥ ስትገባ ሰውነቷ መንቀጥቀጥ ጀመረ…ይሄ የተለመደ ስሜቷ ነው…ሆሲፒታል ሂጂ ከሚሏት ጦርነት ዝመቺ ብትባል ትመርጣለች…እንደምንም ግን ወደውስጥ ዘለቀች…  አባቷን ደውላ አገኘችው…እጇን ይዞ እየመራ የተባለቸው ህፃን ወደተኛችበት ክፍል ይዟት ገባ፡፡ክፍሉ ውስጥ ከህፃኗ ጋር የገዛ እናቷ ብቻ ነች ያለችው፡፡ ከበራፉ አንድ እርምጃ ወደውስጥ ተራምዳ እንደቆመች ደንዝዛ ቀረች …ከዛ ማለፍ አልቻለችም፡፡
ፍፅም የሚባል ድንዛዜ ውስጥ ነው የገባችው…ልጅቷ ቢያንስ ከሶስት ማሽን ጋር በቱቦ ተያይዛለች…መልኳ ውብ ፀጉሯ ግንቧሯ ላይ ድፍት ያለ አጎጊ ብትሆንም ስልምልም ብላ እራሷን ስታ ተዘርራለች..እንደውም ነፍሷ ውስጧ እንዳለ እርግጠኛ መሆን አልቻለችም….
በቃ  ውስጧ ግልብጥብጥ ነው ያለባት…ከአመታት በፊት ምትወደውና ልታገባው ስታልመው የነበረው እጮኛዋ ኪሩቤል  እንዲህ እንደህፃኗ እራሱ ስቶና ዝርግትግት ብሎ በማሽን እገዛ ለመተንፈስ ሲያጣጥር የነበረው ትዝታ መጣባትና እራሷን ልትስት ተንገዳገደች..አጠገቧ ያለው አባቷ ፈጠን ብሎ ደገፋት…እናቷ በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ስሯ ደረሰች፡፡

‹‹ምነው ልጄ..አመመሽ እንዴ?››ሁለቱም ተቀባብለው ጠየቋት፡፡

‹‹አይ ደህና ነኝ …የመድሀኒት ሽታና የህክምና ማሽኖቹ ድምፅ ነው የረበሸኝ››

‹‹ቸሬ አንተ እኮ ነህ..እሷ ሆስፒታል እንዴት እንደምትጠላና እንደሚያማት እያወቅክ ነይ ያልካት፡፡››

‹‹እውነትሽን ነው አጥፍቻለው….በቃ ልጄ ነይ…ይሄን ያህል ካየሻት ይበቃሻል….ብለው እየጎተቱ ወደውጭ ወሰዷት…መኪናዋ ድረስ አደረሷት፡፡‹‹እርግጠኛ ነሽ ሰላም ነሽ…?መኪና መንዳት ትችያለሽ››

‹‹አታስብ አባዬ..ሰላም ነኝ..በቃ ተመለስ››
መኪና ውስጥ ገባታ ስትንቀሳቅስ አባትዬው ወደውስጥ ተመለሱ፡፡ቀጥታ ወደቤቷ ነው የሄደችው፡፡የልጅቷ ምስል ከአእምሮዋ ሊወጣ አልቻለም….ወላጆቾ ምን አስበው ያቺን በህይወት እና በሞት መካከል ባለች  ቀጭን ክር ተንጠልጥላ ያለችን ልጅ  በማደጎ ለመውሰድ እንዳሰቡ ሊገባት አልቻሉም…እንዴት አድርገው ሊንከባከቧት ነው…?ከለመዷትና ከወደዷት በኃላ ብትሞትባቸውስ…..?የሚወዱትን ሰው በሞት መነጠቅ እንዴት ልብን እንደሚሰብር እና ተስፋን እንደሚያከስም በራሷ ታውቀዋለች…እና በእሷ የደረሰ አይነት ሀዘን በዚህ እድሜያቸው በወላጆቾ እንዲድርስ አትፈልግም…፡፡

‹‹ግን ምን ማድረግ እችላለው?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡እንዲሁ ስትብሰለሰል አደረች…ሳምንት ሙሉ አሰበችበት..አንድ ውሳኔ ወስና ለወላጆቾ ምንም ነገር ማለት ሳትችል…ወላጆቹ ህጋዊ የአሳዳጊነት ፕሮሰሱን ጨርሰው ልጅቷን ወደቤታቸው እንደወሰዱ ሰማች፡፡በቃ ከዛ በጊዜ ሂደት የሚሆነውን ጠብቃ ለመመልከት ወሰነችና ወደወላጇቾ ቤት ሄዳ አዲሷን እህቷን አየቻት…ምንም እንኳን ከዛ ሁሉ ማሽን ነፃ ሆና ብታያትም..አሁንም ግን  በጣም ደካማ እና የሰለለ ሰውነት ያለት ሆና ነው ያገኘቻት፡፡ግን ደግሞ በዛው ልክ አሳዛኝና ተወዳጅ ልጅ መሆኗን መካድ አልቻለችም፡፡
============
ራሄል ከረዳቷ ጋር እያወራች  ነው፡፡
‹‹ሮቤል ወ.ሮ ላምሮት ልገሳዋን  ለእኛ ፋውንዴሽን  እንድታደርግ አሁን በስልክ አናግሬታለው፡፡እሷን ማሳመን ከቻልኩ እና ውሳኔዋ ለእኛ ለመለገስ ከሆነ ለፋውንዴሽናችን ትልቅ ስኬት ነው››

ራሄል  ወረቀቶቿን ወደ ቦርሳዋ አስገባች፣ አንድ አይኗ  በእንጨት በተሸፈነው የቢሮዋ ግድግዳ ላይ በተሰቀለው ሰዓት ላይ ተሰክቶ ነበር።

‹‹ ለማውራት ጊዜ የለኝም። በሃያ ደቂቃ ውስጥ በወላጆቼ መኖሪያ ቤት በተዘጋጀው የምሳ ግብዣ ላይ መገኘት አለብኝ ››አለች፡፡
ረዳቷ ማንኛውንም አይነት ቅሬታ ከማንሳቱ በፊት  አቋረጠችውና  ‹‹ እንደገና ሴትዬዋ ከደወለች  ብቻ አሳውቀኝ።››አለችው፡፡
ስልኳን ዘጋችና ሞባይሏን  ቦርሳዋ ውስጥ ለትንሿ እህቷ ጸጋ ከገዛችው ትንሽ ስጦታ ጋር  አስቀመጠችው፣ ፀጋ ወላጇቾ ሊያሳድጓት በቅርብ የተረከቧት  እህቷ ነች፡፡ ራሄል ወደ መኪና ማቆሚያ ጋራዥ በፍጥነት በምትወርድበት ጊዜ የኖብል ፋውንዴሽን ቢሮዎችና ኮሪደሮች በፀጥታ ተውጠው  ነበር።
87🔥2😱1