አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
511 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳባ  እጅ  አወጣች…በስልጠናው  እየተሰጠ  ባለው  የዕለቱ  ትምህርት  በጣም ተመስጣለች…እና በውስጧ የሚጉላላ ጥያቄ ስለነበረ እሱን ለመጠየቅ ነው  እሺ ሳባ ጠይቂ

‹‹አንድ  ሴት  ከወንዱ  ጋር  ወሲብ  ስትፈፅም  እሱን  ማርካት  ላይ  ነው  ማተኮር ያለባት ወይስ ለራሷም የእርካታ ስሜት.መጨነቅ ይጠበቅባታል››
በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳሽው፡፡ የሴቶች ቆዳ ከወንዶች 10 እጥፍ በላይ ንቁ ነው፡፡ ወንዱ በወሲብ አማካይነት ከስሜቱ ይገናኛል፤በስሜቱ አማካይነት ደግሞ ወደነፍሱ ይመለሳል ሴቷ ግን በአብሮነት ውስጥ ድጋፍ እንዳገኘች ሲገባት ልቧ ውስጥ ተቀብሮ የነበረው ፍቅር ፈንቅሎ ይወጣና በዛ መንገድ መንፈሳዊ ፍላጎቶቿ ሲሟሉላት ወሲባዊ ፍላጎቶቿን ለማሟላት መዘጋጀት ትጀምራለች፡፡ ሴቷ የወሲብ እርካታ ለማግኘት ከወንዱ እጥፍ የሆነ ጊዜ ያስፈልጋታል ቢያንስ ለ20-30  ደቂቃ ያስፈልጋታል፡፡ የወንድ  ልጅ  መንፈስ ግን ለወሲብ ከተነቃቃ በኋላ መተንፈስ ካልቻለ መንፈሱ ብቻ  ሳይሆን አካሉም ምቾት ያጣል ሴቷ ግን  ባትረካም  በወሲብ  አማካይነት በሚፈጠረው ቅብ ብቻ ጥሩ ስሜት ሊሰማትና ደስተኛ ልትሆን ትችላለች፡፡
እንግዲህ ምን ማለት ነው የወንድና የሴት የወሲብ ዝግጅት ቆይታና እይታ ጭምር ይለያያል ማለት ነው፡፡ እና ወሲብ የምትፈፅሚው  ከምን  አይነት ሰው ጋር ነው እንዴት ነው ወንድዬውን ከጥድፊያ እንዲወጣና ነገሮችን በስክነትና በእርጋታ እንዲያደርግ ማድረግ ትችያለሽ.. አንቺስ ፈጥነሽ ወደ ወደሪቲሙ ለመግባት ምን ምን ዘዴዎችን መጠቀም አለብሽ እነዚህን መሰረታዊ መልስ የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው ምክንያቱም ወንዱ በፍጥነት ይግላል በፍጥነት ይበርዳል አንቺ ዝግ ብለሽ ትግያለሽ ዘግየት ብለሽ ትበርጂያለሽ፡፡ ከእሱ ቀነስ  ከአንቺ  ጨመር  አድርጋችሁ  መሀከል  ላይ ስትገናኙ ነው  እኩል  መርካት  የምትችሉት፡፡ ግን  ምንም  አደረጋችሁት ምንም ሁል ጊዜ  ሴቷ  ከወንድ  እኩል  መርካት  አትችልም ቢሆንም  ያ ችግር የለውም ምክንያቱም ሴቷ ከእርካታው በላይ ለፕሮሰሱ ትልቅ ትርጉም ትሰጣለች፡፡ ዋናው ነገር በወሲብ ጥምረታቸው ግንኙነታቸው ይበልጥ መጠንከሩና ፍቅራቸውም ይበልጥ  እየጎለበት መሄዱ ነው፤ያ  ከእርካታ እኩል ውስጣዊ ደስታን ይፈጥርላታል፡፡ ለዛሬ እዚህ ላይ እናቁምና በተከታታይ  ቀናቶች  ብዛት  ያላቸውን  በወሲብ  ላይ  የተሰሩ  ዶክመንተሪ ፊልሞችን እየተመለከትን እያንዳንዱን በጥልቀት እንፈትሸዋለን፡
‹‹ሌላ ጥየቄ ያለው አለ?›› ሌላኛዋ ሴት እጅ አነሳች
‹‹አንድ ጥያቄ ነበረኝ…ፍቅረኛዬ ሌላ ሀገር ነው የሚኖረው በሶስት ወርም ሆነ በአራት ወር ይመጣል.. እና እንደመጣ እሱ ዘሎ ወሲብ ላይ ጉብ ማለት ነው የሚፈልገው እኔ ደግሞ እንዲያወራኝ እፈልጋለሁ ከሱ ውጭ ስላሳለፍኩት ልነግረው እፈልጋለሁ..እሱም እንዲነግረኝ እፈልጋለሁ…እና  ይሄ  ሰው እኔ ናፍቄው ሳይሆን የወሲብ ስሜቱን ለማርካት ይሆን እንዴ የሚመጣው ብዬ በማሰብ ቅሬታ ውስጥ እገባለሁ…ይሄ ነገር ሊብራራ ይችላል፡››

አሰልጣኟ ‹‹ጥሩ ጥያቄ ነው…››፡፡በማለት ማብራራቷን ቀጠለች


‹‹ሁለት ጥንዶች ከቀናቶች በኋላ ተነፋፍቀው ሲገናኙ ወንዱ ተጣድፎ ወደወሲብ ጫወታ መግባትያፈልጋል፤እንደዛም ለማድረግ ይቁነጠነጣል ሴቷ  ደግሞ ተቀምጦ ማውራትና በጫወታቸው መንደርደሪያነት ናፍቆትን መወጣት ትፈልጋለች፡፡ ቶሎ ክንዷን ጨምድዶ ወደ አልጋው ይዟት ከሄደ…ልክ ከውጥረቱ ለመርገብ እንደመጠቀሚያ እየተገለገለባት እንደሆነ እንድታስበ ያደርጋታል፡፡ በተቃራኒው የእሷ ወደአልጋ ለመሄድ ዳተኛ መሆን  ለእሱ  ሌላ  ትርጉም ይሰጠዋል…ብዙም እንዳልፈለገችው…በመመለሱ ብዙም ግድ እንዳልሰጣት በመገመት የመገፋት ስሜት ያስተናግዳል፡፡ ይሄንን በወንድና በሴትነት ምክንያት ያለን የባህሪ ልዩነት መረዳት ግን ለሁለቱም በመተጋገዝ ወደመሀል እንዲመጡና እርስ በእርስ የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት በግንኙነታቸው ላይ ጥቁር ነጥብ እንዳይጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ሴት ለወሲብ ልቧን ለመክፈት ፍቅር እንደሚያስፈልጋት ሁሉ ወንዱም ወደ ፍቅር ስሜት ዘልቆ ለመግባት ወሲብ እንደሚያስፈልገው መታወቅ አለበት፡፡ ወንድም ሆነ ሴት የመንፈስ ረሀብ አለባቸው፡፡ ግን ከዚህ ረሀባቸው ለመርካት የሚመገቡት የምግብ አይነት ግን የተለያየ ነው፡፡ ሴቷ ፍቅርን በመመገብ ከመንፈስ ርሀቧ ስታገግም ወንድ ደግሞ ወሲብን ተመግቦ ነው ረሀቡን የሚያባርረው፡፡ ከዛ ሴቷ ፍቅርን ተመግባ ከመንፈስ ርሀቧ ከጠገበች በኋላ ለማወራረጃ ቆንጆ ወሲብ ስታገኝ በጣም ደስተኛና ፍፁም የረካች ሴት ትሆናለች፡፡ በሌላ ጎኑ ወንዱም ሆድን ከሚቆርጠውና አጨናንቆት ከነበረው የመንፈስ ረሀብ ወሲብን ከተመገበ በኋላ ተነፈስ ይልና ቀጥታ በውስጡ የሚንቆረቆረውን የጋለ ፍቅር ልክ እንደውሀ በላዩ ላይ መከለስ ይጀምራል…ከዛ አጅግ ደስተኛ፤ዘና ያለና አይኖቹ የሚያበሩ ይሆናል፡፡ አለችና የእለቱን ትምህርት ዘጋች፡፡ ከዛም እንዳለችው ለ10 ቀናት  ያላዩት የወሲብ ፊልም፤ ያላወሩትና ያልተወያዩበት የወሲብ አይነት አልነበረም ሙሉ በሙሉ ነበር ስለወሲብ የነበራትን እይታ የቀየረባት፡፡ ወሲብ እሷ ከምታስበው በጣም በሰፋና በጠለቀ ሁኔታ በሰው ልጅ ዘመናት ታሪክ ሂደት  ውስጥ አስኳል ድርሻ እንዳለው ተረዳች አሁን ለዚህች አለም እንደጨው. እንደሆነ. ተገነዘበች ...ወሲብ. ለፍቅር፤ ወሲብ. ለገንዘብ፤ወሲብ.ለደስታ፤ወሲብ.ለስለላ…ወሲብለአምልኮ..ወሲብ.ዘርን.ለማስቀጠል…ወሲብ.ለበቀል….ብዙ ብዙ
   በሚቀጥለውም ወደመጨረሻው የሰልጠና ርዕስ ተሸጋገሩ

ተግባቦት ማለት በሁለት አዕምሮዎች መካከል ወይም በአንድ አዕምሮ ከሌሎች ብዛት ያላቸው አዕምሮዎች ጋር የሚደረግ የመረጃ ልውውጥ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከሌላው እንስሳት የተሻለ ነው የሚባለው በመግባባት ችሎታው ራሱን በመግለፅና በማስረዳት ክህሎቱ ነው፡፡፣አብዛኛው እንስሳት እርስ በርሱ ይግባባል…ከእኛ ከሰው ልጅ የሚጠበቀው የመግባባት ችሎታ ግን እንስሳቱ ከሚያደርጉት በላይ የላቀ እና ከዚህ በላይ የመጠቀ መሆን አለበት….ለአንድ ሰው ሀሳባችሁንና ፍላጎታችሁን ስትገልፁ አፋችሁን ከፍታችሁ ከንፈራችሁን አንቀሳቅሳችሁ በቋንቋ ብቻ በመጠቀም መሆን የለበትም፡፡ ከምንናገረው ቋንቋ ጋር አብሮ የሚሄድ የፊት ገለፃ፤የእጅ አንቅስቃሴና  የመሳሳሉት  መጣመርና  ተመሳሳይ  መልዕክት ማስተላለፍ አለባቸው፡፡

በጣም የሚወዳችሁ ሰው አበባ ይዞ ያላችሁበት ድረስ መጥቶ ‹‹የእኔ ፍቅር በጣም አፈቅርሻለሁ›› ሲላችሁ ምንድነው የምታደርጉት?፡፡ አንድም አበባውን ቀና ብላችሁ ሳታዩት ሰውዬውን ባለበት ጥላችሁ ትሄዳላችሁ፡፡ ሁለተኛ  ስላፈቀርከኝም ሆነ ይሄንን አበባ በስጦታ መልክ ልታበረክትልኝ ስለመጣህ አመሰግናለሁ….ግን አዝናለው አልችልም ሌላ ፍቅረኛ አለኝ ብላችሁ በተከዘ  ፊትና በአዘነ የድምፅ ቃና ትመልሱለታላችሁ፡፡ ሌላው አማራጭ ደግሞ አበባውን ትቀበሉና ግን ፊታችሁን አጨማዳችሁ በሻከረ የድምፅ ቃና እኔም እወድሀለሁ...አመሰግናለሁ ልትሉት ትችላላችሁ፡፡ ወይ ደግሞ አበባውን ተቀብላችሁ በሚፍለቀለቅና በደስታ በሰከረ ፊት አጅባችሁ የእኔ ማር!! በጣም ደስ የሚል አበባ ነው…በእውነት ነፍሴን ነው ያስደሰትካት...እኔም ውደድድ ነው የማደርግህ ››ትሉታላችሁ ወይ ደግሞ አበባውን ትቀበሉና እጆቻችሁን እንደክንፍ ዘርግታችሁ ትከሻው ላይ  በመንጠልጠል ጉንጮቹን አገላብጣችሁ በመሳም…‹‹የእኔ ፍቅር ይህቺን ቀን ስጠብቅ ነበር
👍6110👏1
..በእውነት ከደስታዬ የተነሳ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም››ብላችሁ ትመልሳለችሁ፡፡

እንግዲህ አፍቃሪ ሆኖ አበባ በእጆቹ ይዞ የመጣው ሰው..ካፈቀራት ሴት የሚያገኛቸውን ከላይ በተጠቀሱት የተለያዩ መልሶች ምክንያት የተለያየ አይነት ሰሜት ይሰማዋል፤የተለያየ አይነት ምላሽም ይሰጣል፡፡ስለዚህ ውጤት ተኮር ተግባቦት      ለማድረግ  እያንዳንዱ  ንግግራችን፤ ድርጊታችንና፤    የስሜት    ገለፃችን የተጠና ለውጤቱ አስተዋፅኦ የሚያደርግ መሆኑን በማሰብ መሆን ይገባዋል፡፡ በዚህ  ዘመን  ዋናው  ተግባቦት    ቴክኖሎጂ  ላይ    የተጣበቀ  ነው፡፡ ሰው      በስልክ ማውራት፤በኢንተርኔት ቻት ማድረግ፤ በሶሻል ሚዲያው ላይቭ ማውራት... በዛ ተውጧል.    አብዛኛውን        ጊዜውን  የሚያሳልፈው    በእነዚህ  ጉዳዮች  ላይ      ስለሆነ እውነተኛውና  ተፈጥሮአዊው  ተግባቦት  ላይ  ከፍተኛ  ጉድለትእያሳየ  ነው፡፡ እኛ ደግሞ    በከፍተኛ ሁኔታ እስኪል (Skill) ፉል መሆን የሚገባን እና የሚጠበቅብን የአንድ ለአንድ ተፈጥሮአዊው ግንኘኙነት ላይ ነው፡፡ ደንበኞቻችን እኛ ጋር የሚመጡት መደበኛካልሆነውና  በቴክኖሎጂ ከታጠረው ግንኙነት ነው፤በዛ ተሰላችተውና በዛም ምክንያት ከተፈጠረባቸው ጭንቀት ለመተንፈስ ነው፡

ፈገግ ስትሉ …ፈገግታችሁ ፊታችሁ ያለው ሰው አይኖቹ ላይ  ብቻ  ደርሶ  ከከሰመ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ፈገግ  ስትሉ  ፈግታችሁ  ፊት  ለፊታችሁ  የተቀመጠው ሰውዬ ቢያንስ ልቡን ማሞቅ ከተቻለ ደግሞ ማቅለጥ መቻል አለበት፡፡ ፈግታችሁ የአፍ መከፈት እና የጥርስ መሸልቀቅ ብቻ ሳይሆን  ኃይል  ሊኖረው  ይገባል…ብርሀን ሊረጭ ግድ ነው፡፡

እና በቆይታችን ፈገግታችንን እንዴት ኃይል ልናላብሰውና ብርሀን ልንዘራበት እንችላለን? የሚለውን ልናስብበትና ልንካነው የግድ ነው፡፡ አንድን ሰው ስናወራው ፊት ለፊቱ  ትኩር  ብለን  በትይዩ  አይናችንን  አይኑ  ላይ  ተክለን፤ፊታችንን በፈግታ አድምቀን ከሆነ የተነጋገርናት ጥቂት ነገር.-ያለምንም ብክነት ቀጥታ ልቡ ላይ ነው ማረፍ ያለባት፡፡ የፈለግነውን  ነገር  ለመጠየቅ የፈለግነውን ነገር ለማግኘት ቀድመን የሰውየውን የአዕምሮውን ሆነ የነፍሱን ሙሉ ትኩረት ማግኘት አለብን፡፡እስኪ አሁን የተወሰነ  ልምምድ እናደርጋለን አለችና ፈንጠር  ፈንጠር  ብለው አንድ ጠረጴዛ ለየብቻቸው ይዘው የተቀመጡትን ሰልጣኞች በትኩረት ቃኘችና ንግግሯን ቀጠለች ‹አሁን ራሳችሁን ካፌ ውስጥ ወይም የሆነ ሆቴል እንዳላችሁ ቁጠሩት፤ የሆነ ከዚህ በፊት አይታችሁት የማታውቁት ወንድ  ቀጥራችሁ እየጠበቃችሁ ነው፡፡ ያንን ወንድ ለሆነ ጉዳይ ያስፈልጋችኋል..ምን አልባት ስራ የሚያስቀጥራችሁ ወንድ ሊሆን ይችላል…ብር ሊሰጣችሁ  የሚችል ወንድ ሊሆን ይችላል …የሆነ ጉዳይ እንዲያስፈፅሙላችሁ ሊሆንም ይችላል.. ምን አልባት ፍቅረኛ ልታደርጉት የምትፈልጉት ወንድ ሊሆን  ይችላል…ብቻ የሆነ ጥቅም ከእሱ ትፈልጋላችሁ..…ወይም ለጓደኝነት  ፈልጋችኋቸው.ይሆናል..ፍቅረኞቻችሁ ከዛም አልፎ ወደፊት የትዳር አጋራችሁ እንዲሆኑ ውስጣዊ ምኞት ሊኖራችሁ ይችላል፡፡ እነሱም በተመሳሳይ፡፡ እና ይሄንን በአዕምሯችሁ አሰቀምጡና ልምምዳችንን እንቀጥል… ወንዶቹ ሲመጡ  እንዴት ነው የምትቀበሏቸው….በአካል አታውቋቸውም ለመጀመሪያ ጊዜ ግንኙነታችሁ ነው፡፡ ‹‹አብረን እንይ›› አለችና ወደውጭ ምልክት ሰጠችና ወንበር ይዛ ቁጭ ብላ መታዘብ ጀመረች፡፡ ከውጭ ሶስት ወንዶች ተከታትለው ገቡና ወደሶስቱ ሰልጣኞች ተከፋፍለው ሄዱ..የሰላምታ ልውውጡና  የ5 ደቂቃ ውይይት  እና  ጭውውት  ካደረጉ በኃላ አሰልጣኟ ወደትንተናው ተመለሰች፡፡
//
እንግዲህ እስኪ እንዴት እንደነበራችሁ እንይ አለች‹‹ ኮምፒውተሩ ተከፈተ.. የተቀረፀውን ወደኋላ እየመለሰች ፊት ለፊት ፕሮጀክተር ላይ በየተራ እያሳየች አስተያየቷንና ትችቷን ትሰጥ ጀመር፡፡ከማን  እንጀምር  ‹‹ሳባ   አየሽ  የእጅሽ  ጣቶች  ማራኪና ለጋላጋ ናቸው፡፡ ባልዳስሳቸውም ለስላሳ መሆናቸው ከሩቅ ያስታውቃሉ..ግን ወዳጅሽ የዘረጋውን አጁን ጨበጥሽው ነው ነካሽው ነው ሚባባው..? እስኪ ወዳጅሽን እንጠይቀው…
‹‹ኤፍሬም እስኪ ንገረን ስትጨብጥህ ምን ተሰማህ ?››
ኤፍሬም መናገር ጀመረ‹‹የሆነ ትዕቢት እንዳለባት ወይም እንደተፀየፈችኝ ነው የተሰማኝ፡፡››
ሳባ ደነገጠች ‹‹አረ እንደዛ አይደለም….ለምን እፀየፍሀለሁ?›አለች ፡፡
‹‹አየሽ አሁን እሱን ስለተጠየቀ ነው.የተሰማውን ስሜት እውነቱን የተረዳነው…በሪል ገጠመኝሽ ግን ይህንን ዕድል አታገኚም…ቀጥታ በመጀመሪያው ግንኙነታችሁ ሰውዬው ላይ ያሳደርሽው ጨለማ ስሜት ነው...እሺ ሌላ ያልተመቸህ ነገር አለ?››ሁለተኛ ጥያቄ ጠየቀችው
ቆፍጠን ብሎ ያለምንም ይሉኝታ መመለስ ጀመረ‹‹ፊቷን ቋጥራ ስለነበረ እኔን ለማግኘት ነገሮች አስገድደዋት እንጂ ፈፅሞ ፍላጎት እንደሌላት አይነት ነው የተሰማኝ››፡፡
‹‹አመሰግናለሁ እኔም እንደዛ እንደሚሰማህ የተቀረፀውን ምስል አይቼ መገመት ችያለሁ…ሳባ ራስሽም እይው…እንዴት ይሄንን ውብ ፊትሽን ቋጥረሽ እንዳጨለምሽው››
አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ልጠይቅህ‹‹ገና በራፉን ከፍተህ ስትገባና  ወደ እሷ እየተጠጋህ ስትሄድ ምን ነበር የተሰማህ?››

መልስ ለመስጠት የማሰቢያ ጊዜም ማባከን  አልፈለገም ‹‹ዋው!! ምን  አይነት ውብና አማላይ ልጅ ነች..በተለይ አንገቷ አስገርሞኛል...እናም አይኖቿን ስትተክልብኝና ከስር እስከ ላይ ስታንከባልልብኝ የተለየ ስሜት ነበር የተሰማኝ››
እንግዲህ የሳባን ነገር እናጠቃለው…‹‹አየሽ  ኤፍሬም  እንደተናገረው  ቆንጆ  ነሽ… ገና እንቡጥ ዕድሜ ላይ የምትገኚ ማንኛውንም ወንድ መነኩሴም ሆነ ሼኪ ቢሆን እንኳን ለሰከንድም ቢሆን አይኑን እንዲያርገበግብ  የሚያስገድደው  አይነት ውበትና ግርማ ሞገስ ከልዩ የሰውነት ቅርፅ ጋር አለሽ…ግን ሲጠጉሽ ያለሽ የኮሚኒኬሽን ችሎታና ጥበብ ይሄንን የሚመጥን የሚያግዝ እና የሚያጎላ መሆን ሲገባው በተቃራኒው የሚያደበዝዝ እና የሚገፋተር  ነው.፤የዚህ  አፍላና  ትኩስ ወጣት ወንድን በውበትሽ ተማርኮ በአቀባበልሽ፤ በሰላምታ አሰጣጥሽ በፊትሽ መቋጠርና ብሎም በአቀማመጥሽ ይሄን ያህል ስሜቱን አደፍርሰሽ ካስከፋሽው ከእሱ በእድሜ ጠና ያሉ፤በብዙ የስራ ኃላፊነት የተወጣጠሩ ለሴትም ሆነ ለሰው ያላቸው እይታ በተለያየ ገጠመኛቸው የተነሳ መጥፎ የሆኑ ሰዎች ጋር ስትቀርቢ ደግሞ ይታይሽ በእነሱ  ፊት  ውበትሽና  ሴትነትሽ ብቻውን እርባን ያጣል.. ሰውዬው ጎንሽ ከመቀመጡ  የምትናገሪውን  ተናግረሽ ቶሎ ተነስቶ እስኪሄድ ነው የሚቸኩለው…ጉዳይሽን እንድትናገሪ ቢፈቅድልሽም ይሰማሻል እንጂ አያዳምጥሽም…ሰው ደግሞ ካላዳመጠሸ ችግርሽን ከቁብ ወስዶ መፍትሄ ሊሰጥሽ ወይም ሊረዳሽ አይችልም፡፡

ስለዚህ ይሄን መስታወት ፊት ቆመሽ ፈገግታሽን የአይኖችሽ እንቅስቃሴ፤ አቀማመጥሽን፤ ከአካልሽ እንቅስቃሴ ጋር ያለውን ጥምረትና ውህደት እየቀያየርሽና እየለዋወጥሽ መለማመድና የትኛው ከየትኛው እንደሚሻል መስታወቱ ውስጥ ያለችው ሴት በምን ያህል መጠን ራስሽን እንደማረከችሽ እየገመገመችሽ በጣም መለማመድና አሁን ካለሽ ብቃት ፍፁም የተለየሽ መሆን አለብሽ.. ይሄንን በራስሽ ማድረግ ካቃተሸ ደስተኛ የሆነ ሳቁን በወላጆቹና በማህበረሰቡ ያልተነጠቀ ህፃን ልጅ ፈልጊና ከእሱ ተማሪ...
👍547👏4🥰2
​​እንዴት  ነው ሰላምታው..?ሲያወራ እንዴት ነው…?ሲስቅስ? ከዛ በቃ ክርስቶስ እንደህፃናት ካልሆናችሁ ወደመንግስተ ሰማያት እትገቡም እንዳለው እኔም የሰውን  ልብ  አቅልጦ  የሚፈልጉትን  ነገር  ለማግኘት  እንደህፃን  መሆን  የግድ  ነው እላለሁ፡፡አሁን ወደ ሌሎቻችሁ.ልምጣ.አለችና የቀጣዯን  ሰልጣኝ. የተቀረፀ. ቪዲዬ ከፈተች…

ዛሬ  ላይ…አሁን
ከትዝታዋ ውስጥ ድንገት ተመንጭቃ ወጥታ ዙሪያዋን ስትቃኝ እኩለ ለሊት አልፏል…እሷም በብርድ ደንዝዛለች..ጠረጴዛው ላይ የሚታያት ባዶ የወይን ጠርሙስና ጭላጭ የቀረለት ብርጭቆ ነው፡፡ ‹‹ሙሉ  ጠርሙስ አጠናቅቄ እንዴት ራሴን አልሳትኩም?››ስትል አሰበች.እንደምንም ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደመኝታ ክፍሏ ገብታ አልጋዋ ላይ ተዘረረች…ወዲያው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍38
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ሳባ  እጅ  አወጣች…በስልጠናው  እየተሰጠ  ባለው  የዕለቱ  ትምህርት  በጣም ተመስጣለች…እና በውስጧ የሚጉላላ ጥያቄ ስለነበረ እሱን ለመጠየቅ ነው  እሺ ሳባ ጠይቂ ‹‹አንድ  ሴት  ከወንዱ  ጋር  ወሲብ  ስትፈፅም  እሱን  ማርካት  ላይ  ነው  ማተኮር ያለባት ወይስ ለራሷም የእርካታ ስሜት.መጨነቅ ይጠበቅባታል›› በጣም…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በማግስቱ ከእንቅልፏ ተነሳችና ቁርሷን በልታ አራት ሰዓት አካባቢ ከቤቷ ወጣች፡፡ የመፅሀፍን ረቂቅ ለማተሚያ ቤት አስረክባ..ቀብድ ሰጥታ ወደስራ ቦታ ሄደች፡፡ እረፍቷ ያለቀው ትናንት ነበር፡፡ዛሬ ስራ መጀመር ነበረባት፡፡ግን ፈፅሞ  ስራ የመጀመር ሞራልም ፍላጎትም የላትም፡፡
ቀጥታ ‹‹ቤርሙዳ ማሳጅ ቤት››ሄደች፡፡ትብለጥ እቤቷ  ሰለነበረች  አገኘቻት… ሳላምታ ተቀያየሩና ሳሎን ሶፋ ላይ ጎን ለጎን ተቀመጡ..

ሳባ በፊት መፅሀፉ ታትሞ አልቆ  ስራ  ቦታውንም  ሆነ  አሁን  ከጎኗ የተቀመጠችውን ሀለቃዋን እስከወዲያኛው አውድማ እስክትገላገል ድረስ እንደምንም ጨክና ለመቀጠል እቅድ  ነበራት፡፡ቢያንስ  ለሚቀጥለው  አንድ ወር…ግን አልቻለችም፡፡አስር አመት ያለማቋረጥና ያለመታከት የሰራችውን ስራ ከመናጢ ድህነት ተነስታ ሚሊዬነር የሆነችበትን ስራ፤  ለቀጣዩ  አንድ  ወር ለመስራት ገና ስታስበው ዘገነናት..
‹‹ሳቢ ግን ሰላም ነሽ?››
‹‹አዎ… ምንም  አልል…››
‹‹ህክምናው እንዴት ነው?››
‹‹ጥሩ ሀኪም አግኝቼያለሁ .መዳሀኒትም እየወሰድኩ ነው…ግን ለውጡ አዝጋሚ ነው፡፡››
‹‹ይሁን ዋናው ለውጥ መኖሩ ነው፡፡››አለቻት ትብለጥ፡፡
‹‹አዎ ግን ስራ መቀጠል የምችል መስሎ አልተሰማኝም..እንደው ስራውን ከምጎዳ ብለቅ ብዬ አስቤ ነበር› ›
‹‹ብለቅ ስተይ.?ሙሉ በሙሉ ለማለት ነው?››ከጠበቀችው በላይ ደነገጠች፡፡
ሳባ ደግሞ የትብለጥ በተጋነነ ስሜት መደንገጧን ስትመለከት በውስጧ የነበረውን ንዴት ይበልጥ እንዲቀሰቀስባት አደረጋት…
ይህቺ ሴትዬ በእሷ ትከሻ ላይ ተንጠላጥላ ብዙ  መቶ  ሚሊዬን  ብሮችን  ወደ ካዝናዋ አጭቃለች…ስራዋ ሁሉ የማፍያ ነው፡፡ብር የምታገኝበት መንገድ በጣም ይገርማታል…ለምሳሌ ማሳጅ አገልግሎት በማግኘት አንድ የመዘጋጃ ቤት ወሳኝ ባስልጣን እሷ ጋር ይመጣል…እሷ ያንን ደንበኛ አሳልፋ ለሳባ ትሰጣታለች….ሳባ
ከማሳጅ ጀምራ ነፍሱ ሩሆን እስክትስት ድረስ ፍላጎቱንና አመሉን  መሰረት በማድረግ ፈንጠዝያ ወስጥ እንዲገባና እንዲደሰት ታደርገዋለች.፡፡ከዛ ያ ባለስልጣን ላገኘው አገልግሎት ለሳባ ሀያ ወይ  ሰላሳ  ሺ  ብር  ይሰጣጥና  ለትብለጥ የአገልግሎት አራት ወይም አምስት ሺብር ከፍሎ አመስግኖ ይሄዳል…ወይዘሪት ትብለጥ ታዲያ ደንበኛዋን አሳዳ ፕሮፖዛሏን በእጇ ይዛ ሀገር አማን ነው ብሎ በተቀመጠበት ቢሮ ተከስታ ታስደምመዋለች..ከዛ በሁለት በሶስት ወር 5መቶ ካሬ መሬት ተቀብላ ካርታውን በስሟ ታሰራና መሬቷን በእጇ ካርታውን በካዝናዋ በማስቀመጥ ወጥመዷን አስተካክላ  ሌላ ታዳኝ ትጠብቃለች…ከሆነ ወር ቆይታ በኃላ ደግሞ አንድ የግሙሩክ ወሳኝ ባለስልጣን  የወሬ  ወሬ  ሰምቶ ይመጣል…ከእሱ ምን መጠቀም እንደምትችል ታጠናለች …ከዛ ተመሳሳዩን ታደርጋለች..
እና ባለፉት አስር አመት ውስጥ በእዚህች ሴትዬ ማሳጅ ቤት ወስጥ ብዙ ብዙ ስራ ሰርታ ከ30 ሚሊዬን በላይ ንብረት ብታፈራም..ሴትየዋ  ግን  በእሷ  ትከሻ ከ200 ሚሊዬን ብር በላይ ዘርፋለች….ይህንን ሳባ በደንብ ታውቃለች.ሳባ ማወቆን ግን ትብለጥ አታውቅም..
‹‹ሳቢ ከጤናሽ ሚበልጥ ነገር የለም….ታውቂያለሽ በጣም ብዙ ማሳጅ ሰራተኛች ነበሩኝ ..አሁንም አሉኝ…ባንቺ ልክ ግን የተሳካለትም እኔም የወድኩት ሰው የለም፡፡አንቺ ለእኔ ልክ እንደልጄ  ነሽ..ያለፉትን  አንድ  ወር  ከስራ  በመቅረትሽ እንኳን የደንበኞችሽን ጭቅጭቅ እረፍት ነው የነሳኝ…››

ሳባ የሆዷን በሆዶ ይዛ ቅጥል እያለች‹‹አውቃለሁ…ግን ጤና ከሌለ ሁሉም ነገር የለም…ምን ማድረግ እችላለሁ?›ስትል መለሰችላት፡፡ስራ በጀመረች በሶስተኛው አመት ማለትም የዛሬ ሰባት አመት ከዚህች ሀለቃዋ ጋር ክፉኛ ተደማምተዋል
….የጥላቸው ምክንያት አንድ ደንበኛቸው ነው፡፡ደንበኛው በወቅቱ ሳባ ጋር ከአንድ አመት በላይ የተመላለሰ በጣም ጨዋና ደግ፤ ግን ደግሞ የናጠጠ ሀብታም ሰው ነበር…. ታዲያ ያንን ሰው በቆይታ ከሳባ ጋር በጣም  እየተቀራረብ  ሲመጡ ሚስጥሩን ሁሉ ይዘረጋፍላት ነበር፡፡ከዛ እነትብለጥ ያንን መረጃ በሚስጥር ከተደበቀው ካሜራ የተቀረፀ ፊልም በማየት የሰውዬውን በአንድ ወቅት በስህተት የሰው ነፍስ በእጁ እንዳለፈ የተናዘዘላትን ወንጀል አብራቸው በምትሰራቸው ማፍያዎቾ  በኩል  በጥልቀት  ታስጠናና  መረጃዎችን  በመሰብሰብ  የደረሱበትን ሁሉ በአድራሻው እንዲደርሰው አድርገው ይደራደሩታል….ከዛ ሰውዬውም ምርጫ አጥቶ እስከ 50 ሚሊዬን የሚደርስ ብር ሊቀባበሉት ሁሉን ነገር ከጨረሱ በኃላ ይሄንን ስራ ከጀርባ ሆኖ ማን እንደሚያስኬደው   ሰገን  ከተባለች ረዳቷ ጋር ሲማከሩ ትሰማለች.. ከዛ  ደግማ  እንኳን  አላሰበችበትም….ሚስጥሩን ለሰውዬው ደውላ ትነግረዋለች ….ሰውዬውም ቀጥታ ትብለጥ ጋር ይደውላል››
‹‹50 ሚሊዬኑን ቀጥታ ለውሾችሽ ልስጣቸው ወይስ  ለአንቺ ላምጣልሽ››
‹‹የምን 50 ሚሊዬን?››
‹‹መደባበቁ ምንም አይረባንም….እጅሽ ላይ ያለውን መረጃ አሁኑኑ ሰብስበሽ ብታቃጥዬው ይሻልሻል…ስለእኔ አንድ  ነጠላ  መረጃ  ፖሊስ  እጅ  ከገባ  እኔም ያንቺን ቢዝነስ ሙሉ በሙሉ አወድመዋለው….ማሳጅ ቤትሽ የሽርሙጥና ቤት እንደሆነ…ሀሺስ እንደምትነግጂ…ግብረሰዶም ሳይቀር በቤትሽ  እንዲከወን እያደረግሽ ከፍተኛ ቢዝነስ እንደምትሰሪ…በቂ መረጃ እና  ምስክር  አለኝ፡፡››ብሎ ኩም  ያደርጋትና  ፅፎ  የፈረመውን  ቼክ  ቀዳዶ  ይልክላታል…ከዛ  ተረጋግቶ ስራውን ይቀጥላል፡፡…ለዚህ ውለታዋ ለሳባ  አንድ  ሚሊዬን  ብር  ባንክ  ደብተሯ ላይ አስገብቶ ያመሰግናታል ..ቋሚ ወዳጀዋም ይሆናል…እነ ትብለጥ ግን ለወራት የደከሙለት ስራ ካለቀ እና ፍሬ ለማፍራት ጫፍ ላይ ከደረሰ በኃላ በመጨረሻው ደቂቃ እንዴት እንደከሸፈ ምርመራ ያካሂዳሉ፣ ከብዙ ልፋት በኃላ እንደዛ የሰራችው ታማኞና ተወዳጇ ሳባ መሆኖን ይደርሱበታል፡፡ከዛ ትብልጥ ግራ ይገባታል…እንዳወቀች ልታስገድላት ነበር ያሰበችው…፡፡ግን የራሷን ገቢ እንዲነጥፍ ማድረግ መሆኑ ትዝ ሲላት ተረጋጋት ለማሰብ ሞከረች…ዝም  ብላ  አውቆ እንዳላወቀ በማስመሰል በምህረት ልታልፋት..በቀጣይ ግን እሷን በተመለከተ ጥንቃቄ ለማድረግ ወሰነች…ይሄም አላሳቻላትም ወዲያው ሰረዘችው…ውስጧ የነበረው ንዴት ያለቅጣት እንድትታለፍ ማድረግ  አላስቻላትም...ከዛ  ሙሉ ስልጣኑን ለሰገን ሰጠቻት…‹‹ሳትገድያት፤በእሷ ላይም ቀጥተኛ የአካል ጥቃት ሳታሳርፊባት..ግን ደግሞ  ለጥፋቷ ተመጣጣኝ ቅጣት እንድታገኝ አድርጊ›› የሚል ስልጣን ሰጠቻት…፡፡ሰገንም በዛን ወቅት ሳባን በተመለከተ የነበራት ቀና አመለካከት የተቀየረበት..…እንደዋና ተቀናቃኞና ጠላቶ  ማየት  የጀመረችበት  ስለነበረ የተሰጣትን እድል እስከመጨረሻው እንጥፍጣፊ አስባ፤እንደውም ከድንበሩ አልፋ ተጠቀመችበት..
እንግዲህ ያ ትብለጥ ለሰገን የሰጠችው ትዕዛዝና ትዕዙን ተከትሎ ወደተግባር የተሸጋገረው ድርጊት ለአባቷ ሞት ቀጥተኛ  ምክንያት  እንደሆነ  ሰባ በሙሉ  ልቧ ነው የምታምነው…ለዛም ነው የባለፉት ሰባት አመታት ዋና እቅዷና የህይወት አለማዋ እነዚህን ሁለት ሰዎች  ማጥፋት  ሆኖ  የኖረው፡፡››ሳባ  ከሀሳቧ  ባና ትኩረቷን ወደ ትብለጥ መለሰች፡፡
👍629👏1
​​ትብለጥ መናገር ጀመረች‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ለማለት የፈለኩት እስኪ ትንሽ  ጊዜ ወስደሽ አስቢበት ነው..የሚቀጥሉትን አንድ ወይም ሁለት  ወራት  አርፈሽ ህመምሽን አስታሚ …ከተሻለሽ ወደስራ  ትመለሻለሽ…ካልሆነ  ደግሞ  ጊዜው ሲደርስ እንነጋገርበታለን… እና ደግሞ  ፍቃደኛ  ከሆንሽ  ከሀገር  ውጭም  ወጣ ብለሽ እንድትታዪ ማድረግ እችላለሁ፡፡››
‹‹አይ ለጊዜው እዚሁ የጀመርኩትን ህክምና ልጨርስ…በይ አሁን ልሄድ በስልክ ከምነግርሽ ብዬ ነው የመጣሁት፡፡››
‹‹አመሰግናለሁ የእኔ ልጅ››መኪናዋ ድረስ ሸኘቻትና አቅፋ ስማ ተሰናበተቻት፡፡ ከዛ ቀጥታ ወደቤቷ ነው የሄደችው፡፡
///
ከዛ በሚቀጥለው ሁለት ቀን ጭራሽ  ከመኝታዋ  አልተነሳችም..  እዛው እየተገላበጠች ትናንቷን ትቆፍራለች፡፡
ትዝታ… ከ9 ዓመት በፊት
በወቅቱ ከሁለት ወር ተኩሉ ስልጠናዋን በስኬት አጠናቃ ወደ ሚቀጥለው የ15 ቀን ተግባባዊ ግምገማ ከመሸጋገራቸው በፊት የ3 ቀን እረፍት ተሰጣቸው፡፡ታዲያ በወቅቱ ሳባ ሮጣ ወደአሰላ ነበር የሄደችው፡አባቷ በጣም ናፍቆት ነበር፤ትንሹ ወንድሟ በጣም ናፍቆት ነበር ፡፡ያደገችበት ሰፈሯ እና የተወለደችበት ቤት ሳይቀር በጣም ነበር የናፈቃት፡፡ሁለቱን ቀን ከአባትዬው ጋር ስታወራና ስትጫወት ከወንድሟ ጋር ስተላፋ ከስንዱ ጋር ስትንሾካሾክ አሰለፈችና ወደአዲስ አባ ተመለሰች፡፡

አዲስአበባ እንደደረሰች ለደምሳሽ ነበር የደወለችለት፡:፡በፍጥነት ነበር ካለበት ፈጥኖ መጥቶ የተቀበላት…ትልቅ የተባለ ሆቴል ወሰዳትና እስከምሽቱ  ሁለት  ሰዓት ሲዝናኑና ሲጠጡ ካመሹ በኃላ ሁለት ሰዓት ሲሆን ወደቤቱ ይዞት ሄደ…ምንም ቅሬታ ሳታሰማና ሳትከራከር ነበር ወደቤት እንሂድ ሲላት ያለተቃውሞ የተከተለችው.፡፡ምክንያቱም እሱ ቤት ማደርና ከወራት በፊት ወደሴትነት ያሸጋገራትን ድርጊት መድገም የእሷም ምኞትና ፍላጎት ነበር፡፡

መኝታ ቤቱ ገብተው እሷ አልጋ ጠርዝ  ላይ  ተቀምጧ  እሱ  ቁምሳጥኑ  አጠገብ ቆሞ ልብሱን እያወለቀ እያወራት ነበር፡፡

‹‹ሳቢ የዛሬ ሶስት ወር አካባቢ ከነበረችው ሰባ ፍፅም የተለየሸ ሳባ መሆንሽን ታውቂያለሽ?››ሲል ነበር ጫወታውን የጀመረው፡፡

‹‹ይገርምሀል አባቴም እንዲህ ብሎኝ ነበር.ልጄ በጥቂት ወራት ውስጥ በጣም ነው ያደግሽው››አለኝ

‹‹አዎ በጣም ነው ያደግሽው….ጠቅላላ አንቺነትሽ ነው የተቀያየረው…. ንግግርሽ፤ አስተያየትሽ፤ውበትሽ ሁሉ ተለይቷል… እንቺስ አይታወቅሽም፡››

‹‹እኔማ አንድ የተለየች ፍጡር ከወስጤ በቅላ እያደገች እያደግች ስትሄድና መላ እኔነቴን ተቆጣጥራ ቀድሞ እኔነቴን ልታወድመው ስታጣጣር ይታወቀኛል፤ የሚገርመኝ ግን ይሄ ለውጥ በቀላሉ በሌሎች ሰዎች መታወቁ ነው?››

‹‹ለውጥሽ እኮ የጎላ ስለሆነ ነው፤ለእኔ ግን የበፊቷ ሳባ ትሻለኝ ነበር››

‹‹እንዴት?››

‹‹የቀድሞዋ የዋህ ነበረች…በፍቅሬ እንደምትወድቅና የወደፊት የህይወት አጋሬ ትሆናለች የሚል እምነት ነበረኝ…በጣም ተስፋ አደርግባት ነበር››

በገረሜታ‹‹እና የአሁኖስ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አይ የአሁኗ ሳባ ጥልቅ ነች…ተስፋዋ የተሰቀለ..ምኞቷ ከአድማስ  የተሸገረ… ስሜቷን የምትገዛ…በራስ የመተማመን አቅሟ በጣም የጎለበት….በአጠቃላይ በእኔ ደረጃ ሊደረስባት የማትችል ነች››


እየሳቀች ‹‹ኸረ በጣም አጋንከው››አለችው በውስጧ ግን እሱ የተናገራቸው እያንዳንዶቹ አስተያቶች  ትክክል  እንደሆኑ  እየተሰማት  ነበር..ለመጀመሪያ  ቀን እዚህ ቤት መጥታ የቤቱን ትልቅነት የእቃዎችን ጥራት፤የእሱን ወንደላጤነት ስትመለከት የሆነ የመጎምዣት ስሜት በውስጧ ሲራወጥባት ነበር..ነገሮች ተግለብልበው ከእሱ ጋር ወሲብ ከተጋራች እና  ድንግልናዋን  ካስረከበች  በኃላ ደግሞ በፍጥነት ፍቅር የያዛት መስሏት ሁሉ ነበር፡..ስልጠናውን ጀምራ 15 ቀን ካለፋት በኃላ ግን እሱ እንደሚለው ሙሉ በሙሉ ምኞቷ ከእሱ የራቀና የበለጠ እንደሆነ ተሰማት..እርግጥ ከስልጠና ስትወጣ ወደአንዳንድ ቦታ መሄድ ስትፈልግ የምትደውለው እሱ ጋር ነበር፤  ከቦታ  ቦታ  የሚያንቀሳቅሳት  የምትፈልገውን ነገርም የሚያቀርብላት እሱ ነበር፣ ግንኙነታች  የጠበቀ  ነው..ግን  ደግሞ  ከእሱ ፍቅር መውደቅ እንደሌለባት አራሷን ያሳመነችው ወዲያው ነበር፡፡ ዛሬ እንኳን እንገናኝ ስትለው ለፍቅር ሳይሆን ለጓደኝነት እናም ወሲብ ለማጋራት ብቻ ነበር ፡፡ለብሶት የዋለውን ልብስ አውልቆ ቢጃማ ቀይሮ ይመጣል ብላ ብትጠብቅም እሱ ግን መለመላውን እያንጀላጀለ ወደእሷ መጣና ፊት ለፊቷ ቆመ፡፡

‹‹ምነው አልክ..?ቢጃማ የለህም እንዴ?››

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍6910🥰4
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ በማግስቱ ከእንቅልፏ ተነሳችና ቁርሷን በልታ አራት ሰዓት አካባቢ ከቤቷ ወጣች፡፡ የመፅሀፍን ረቂቅ ለማተሚያ ቤት አስረክባ..ቀብድ ሰጥታ ወደስራ ቦታ ሄደች፡፡ እረፍቷ ያለቀው ትናንት ነበር፡፡ዛሬ ስራ መጀመር ነበረባት፡፡ግን ፈፅሞ  ስራ የመጀመር ሞራልም ፍላጎትም የላትም፡፡ ቀጥታ ‹‹ቤርሙዳ ማሳጅ ቤት››ሄደች፡፡ትብለጥ እቤቷ …»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ:
….

‹‹ምነው አልክ..?ፒጃማ የለህም እንዴ?››

‹‹አለኝ ግን በማሳጁ ምን ያህል ብቁ ሆነሻል.ስልጠናውስ እንዴት ነበር? የሚለውን ማወቅ እፈልጋለሁ…››

‹‹ተው… እርግጠኛ ነህ?››

‹‹አዎ ምነው ፈራሽ አንዴ.?ነው ወይስ በብቃትሽ አትተማመኝም? እንዳዛ ከሆነ ይቅር፡› ብሎ ፊቱን ወደቁምሳጥኑ መልሶ ሊራመድ ሲል እጁን ለቀም አደረገችውና‹‹መፍራት ያለብህማ አንተ ነህ…ትዝ ይልሀል ያን ቀን ቤትህ አታለህ አስገብተኸኝ የዋህነቴን ተጠቅመህ እዛ የማሳጅ ጠረጴዛ ላይ አስተኝተህ እንዴት እንደተጫወትክብኝ ያንን መበቀል መቻል አለብኝ፡፡›› ብላ እየጎተተች ወደ ማሳጅ ጠረጴዛው ወሰደችና በጀርባው እንዲተኛ አደረገችው፡፡

ከዛ በቅርብ ካለው ቅባት ወደተኮለኮለበት ጠረጴዛ በመሄድ አንዱን መርጣ አነሳችና ጀርባው ላይ አፈሰሰችበትና ከላይ ከጆሮ ግንዱ ጀምራ እስከታች የእግር ጣቶቹ ድረስ በወሰደችው ሰልጠና መሰረት የተለያዩ ቴክኒኮችን በመጠቀመ እያገለባበጠች ለአርባ ደቂቃ ካሸችው በኃላ እጅግ በሚገርም ሰመመንና መመሰጥ ውስጥ ገብቶ ከተዝለፈለፈ በኃላ እንደምንም ከጠረጴዛው ላይ አስነስታ ወለሉ ላይ ዘረረችው…. ከዛማ ቀሚሷን ወደላይ መዥርጣ አውልቃ ከጎኑ ተኛች…ከዛ በኋላ የነበረውን ለማሰብም ይከብዳታል…ያንን ሰፊ የመኝታ ቤት ወለል እየተንከባለሉበት አንዴ የአልጋው ጠርዝ ሲገጫቸው፤አንዴ ከጠረጴዛው እግር ጋር ሲላተሙ አንዴ ስትገለብጠው….ከዛም ሲገለብጣት ከ30 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ነበር መጀመሪያ እሱ ከዛ ከ5 ደቂቃ ያህል ዘግይታ እሷ ጡዘት ላይ የደረሱት…፡፡

ከዛ እንደምንም.ተላቀው ወዲህና ወዲያ የነበሩበት ወለል ላይ የተዘረሩት.. ከ7ደቂቃ እረፍት በኋላ እሷ እንደምንም ከተዘረረችበት ተነስታ እየተሳበች ወደሻወር ቤት ሄደች….ውሀውን በላይዋ ላይ ለቀቀች…በሁሉም ነገር በጣም ረክታለች.. የዚህ ወሲባዊ ተራክቦ መሪ እሷ ነበረች.. እርግጥ ያ በግልፅ ለእሱ እንዲሰማው አላደረገችም ቢሆንም እያንዳንዷን ቅንጣት በንቃት አጣጥማታለች፡፡ ከ10 ደቂቃ በኃላ ፎጣዋን አገልድማ ወደመኝታ ቤቱ ስትመለስ ደምሳሽ ጥላው በሄደችበት ወለል ላይ ተዘርሮ እንደተኛ እንቅልፍ ወስዶታል፡፡ እየሳቀች  ወደእሱ  ቀረበችና በእግሯ ወዘወዘችው..

‹‹ደምሳሽ…እረ ተነስ ሻወር ውሰድና እንተኛ››

‹‹እንዴ... አንቺ ምን አደረግሺኝ?›› እያለ እደምንም ተነሳና ወደ ሻወር ቤት ገባ፡፡

እሷ ሰውነቷን በሎሺን አባበሰችና  አልጋ  ላይ  ወጥታ  ከአንገቷ  ቀና  በማለት ትራስ ተደግፋ ታጥቦ እስኪመጣ በንቃት ትጠብቀው ጀመር….እሱ 5 ደቂቃ አልፈጀበትም፡፡ፎጣውን አገልድሞ ወጣ…

ቁጭ ብላ ሲያያት ‹‹እንዴ ምነው አተኚም እንዴ?››

‹‹ምነው? አንዴ አንደግምም?››አለችው እየሳቀች፡፡

ሰውነቱን የጠቀለለበትን ፎጣ ከላዩ አነሳና የረጠበ ጸገሩን እያደራረቀ‹‹ምነው በቀል ቢሉሽ እንዲህ በአንድ ቀን ሙሉ በሙሉ ማውደም ነው እንዴ.? ቀስ እያልሽ አይሻልም?››አለና እሱም እንደእሷ አልጋ ላይ ወጣ…ከውስጥ ገብቶ ተኛ፡፡
‹‹ችግር  የለም …ዋናው እጅ መስጠትህ ነው››

‹እረ እጅ ሰጥቼያለሁ…በነገራችን ላይ የማሳጅ ችሎታሽ በጣም አስገራሚ ነው የሆነብኝ….ለረጅም አመት በስራው ላይ የቆየሽ እኮ ነው የምትመስይው… በራስሽ ካላበላሸሽው በስተቀር በቀላሉ ውጤታማ እንደምትሆኚ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ››

‹‹ይሄን ያህል?››

‹‹የምሬን ነው በጣም ነው ያስደመምሺኝ.. ሶስትና  አራት  አመት  በስራው  የቆዩ እንኳን ያንቺን ያህል በጥበብ እና በእውቀት አይሰሩም….አንቺ በዚህ ላይ  ሶስት አራት ወር ልምድ ካከልሺበት በቃ ልዩ ነው የምትሆኚው፡››

‹‹ለአድናቆትህ በጣም ነው የማመሰግነው..ግን ምነው አድናቆትህ ማሳጁ   ላይ ብቻ ሆነ ..ሌላው እስከዚህም ሆነብህ ማለት ነው?፡፡››

‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል…? በወሲብ ልምዴ እንዲህ አቅሌን ስቼ ስዘረር የመጀመሪያ ገጠመኜ ነው…ብቻ  ድንቅ ተማሪ ነሽ.. የመጀመሪያ  ጊዜ ወሲብ  ስናደርግ..ትኩስ እና ሞቃት ነበርሸ ቢሆንም አብዛኛውን ነገር ለእኔ ነበር አሳልፈሽ የሰጠሸው…ዛሬ ግን እኔ ባሪያሽ ሆኜ ነበር፡፡ በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፍ ነው የተቀየርሽው….ምን አልባት ተሰጥኦሽን ይሆናል ያገኘሽው፡፡

‹አንተ እየሰደብከኝ ነው እንዴ…? የታደሉት በስዕል ችሎታቸውና በሙዚቃ ብቃታቸው የተፈጥሮ ታለንታቸውን አገኙ ይባላል…እኔን በወሲብ?፡፡›

ሁሉን ነገር በጥበብና በእውቀት ከከወንሽው አርት ነው…ተሰጥኦ ነው፡፡ እንዴ ትቀለጂያለሽ እንዴ ለአንድ ሴት አርክቶ በእኩል ሰዓት  መርካት  መቻል  እራሱ ድንቅ መሆንን ይጠይቃል፡፡ ብዙ ጊዜ አንዱ አንዱን ለማስደሰት ምን ይህል እንደሚሰቃይ አታውቂም፡፡ ወንድ ልጅ ደግሞ አንዲትን ሴት ሲቀርብ  እሷም ሴትነቷን በሚፈልገው መጠን እንዲህ እንደ አንቺ በገለጠችለትና ይበልጥ በእሷ እየተደሰተና እየረካ በሄደ መጠን ነው ቀን ከቀን ይበልጥ በእሷ እየተሳበ እና በአካሏ ብቻ ሳይሆን መላ እሷነቷን እየወደዳትና እየተቀበላት የሚሄደው፡፡

‹‹እሺ ለማንኛውም ነገ ወደ ወሳኙ ተግባራዊ ፈተና የምሰማራበት ቀን  ስለሆነ ደክሜ  መገኘት አልፈልግም፤ እንተኛ  ለዚህ  ድንቅ  ልብ  አቅልጥ  አስተያየትህ ግን አልፎ አልፎ ያው እቸገርልሀለሁ›› አለችው፡፡

ተንጠራርቶ መብራቱን እያጠፋ‹‹በነገራችን ላይ የዛሬው አዳራችን ምን አልባት የስንብት ሊሆን ይችላል?››ሲል ነበር ያረዳት፡

የእውነት ከልቧ ደንግጣ ተነስታ ቁጭ አለች‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹ከዚህ በፊት ነግሬሽ የለ…ልጄን ፍለጋ ወደአሜሪካ እንደምሄድ አሁን ፕሮሰሱ ሁሉ.አልቆልኛል...ቪዛም አግኝቼያለሁ….ከአራት ቀን በኋላ እበራለሁ››

‹‹ምን አይነት ጨካኝ ሰው ነህ ግን…? እንዴት አራት ቀን እስኪቀረው ድረስ ሳትነግረኝ?››

‹‹ከባድ ስልጠና ላይ ስለነበርሽ ልረብሽሽ አልፈለኩም ነበር…››አላት፡፡

‹‹በፈጣሪ…ግን  ቶሎ ተመልሰህ ትመጣልህ አይደል?››

‹‹ስለእሱ ምንም የማወራው ነገር የለም….ልጄን ካገኘሁ በኋላ በቀጣይ ባለው ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡››
‹‹ያ ማለት አስከወዲያኛውም ላትመጣ ትችላለህ ማለት ነው?››
       ቁዝዝ ብሎ‹‹አዎ ላልመለስ እችላለሁ››አላት፡፡
ተመልሳ ተኛች…እሱም ተኛ…ተቃቅፈው ….እሷ  ይሄን  የመሰለ  መከታ  የሆነ ወዳጅ እንዲህ በድንገት እብስ ብሎ ከእጇ ሊያመልጥ መሆኑን ስታውቅ ሆዷን ባር  ባር  አላት… በጣም  ከፋት…ሰሰተችው….ገና  ከመሄዱ   በፊት ከአሁኑ ናፈቃት... ግን እርቃኑ ከእርቃኗ ተጣብቆ እቅፉ ወስጥ  ገብታ  ትንፋሿ ሲገርፈው ዝም ብሎ መተኛት አልፈለገም … እሷም  በተመሳሳይ…  ለሁለተኛ  ዙር  ፍልሚያ ገቡ፡፡

ጠዋት 12 ሰዓት ነበር ከእንቅልፉ ነቅቶ መኝታውን በመልቀቅ ወደ ኪችን የገባው፤ጥሩ ቁርስ ሰራና አንድ ሰዓት ሲሆን ቀሰቀሳት…ሶስት ሰዓት ስልጠና የምትወስድበት ቪላ ቤት ጋር አድርሷት አንኳኩታ ወደውስጥ ስትገባ…እሱ ወደሌላ ስራው ሄደ፡፡

ስልጠና ቦታዋ ስትደርስ ማንም አልነበረም።ግራ ገባት...አብረዋት የሚሠለጥኑት ተፎካካሪዎቿን ደውላ መጠየቅ አትችልም። ስልክ ቁጥራቸው  አልነበራትም። አሰልጣኟ  ጋር  ደወለች። አይሰራም። ምን  ተፈጠረ?"ሰገን  ጋር ደወለች። ጎሽ ይጠራል "አለችና ጆሮዋ ላይ ለጠፈች። ዝም ብሎ ይጠራል አይነሳም።

ሊዘጋ ሲል። "ምነው ፈለግሺኝ እዚህ ነኝ" የሚል  ድምፅ  ከጀርባዋ  ሰማች። በፈገግታ ዞር አለች።

"ግቢው ባዶ ሲሆንብኝ ግራ ገብቶኝ ነው"
👍727👏2
​​"እኔ አለሁ ...ሻንጣሽ እኔ መኪና ላይ ተጭኗል የሚቀጥለውን 15 ቀን የመጨረሻ የተግባር ስልጠና እኛ ጋር ነው የምትወስጂው... አሸናፊ ሆነሽ  በብቃት ከተወጣሽው ያው በዛው ስራሽን ትቀጥያለሽ ማለት ነው"
"ውይ እንደዛ ነው እንዴ....እዚሁ  የምንጨርስ
መስሎኝ.." 
"ሌሎቹስ?"
"እነሱም የመጨረሻ የተግባር ስልጠና ወደሚወሰድበት ቦታ ሄዱ... "ተከትላት መኪና ውስጥ ገባችና በመገረም ወደመጨረሻው የተግባር ፈተና ወደምትወስድበት ቦታ ጉዞ ጀመሩ ፡፡ ይዛት የሄደችው ወደዋናው ቤት ነው። መኪናው ግቢ ውስጥ ገብቶ እንደቆመ ሰገን ቀድማ ወረደች፤ ሳባም ተከተለቻት....


‹‹ነይ ሻንጣሽን ሹፌሩ ያስገባልሻል፡፡››አለቻት ተስማማችና በዝምታ ተከተለቻት።

ቀጥታ ቤቱን አልፈው ወደኋለኛው ጋርደን ነበር የሄዱት። እዛው ቁርስ ቀረበላቸውና በሉ..ቡና ቀረበላቸው፡፡ እሱን እየጠጡ ወደ ንግግራቸው ገቡ። በህይወት ስኬታማ ለመሆን ከፈለግሽ...የምትፈልጊው ነገር ላይ አተኩሪ፡፡ እሱን  ለማግኘት ስሪ እንጂ በህይወትሽ የማትፈልጊውን ነገር ወደአንቺ እንዳይመጣ ለመከላከል ኃይልሽን አታባክኚ። ይህንን ስራ የምትሰሪው ለምንድነው?ሀብታም ለመሆን ነው? ወይስ ደሀ ላለመሆን? ሁለቱ አንድ ይመስላሉ  እንጂ  ፍፁም  ተቃራኒ አቀራረቦች ናቸው...። ሀብታም ለመሆን የምትሰሪ  ከሆነ  ዓላማሽ  እንቅስቃሴና ግብሽ ሀብት ተኮር ነው። አእምሮሽን የሚሞሉት ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ፤በአየር ላይ የሚበር መኪና ፤ባህሩ ላይ ተነጥፎ የሚንሳፈፍ  መርከብ  ወዘተ  ነው። ድሀ ላለመሆን የምትሰሪ ከሆነ ግን ድህነትሽን ከቤትሽ ዙሪያ ስለማባረር  ነው ሀሳብሽ.... እዚህ ላይ ድህነት አጥቂ አንቺ  ተከላካይ  ናችሁ ..በዚህ  ስታባርሪው በዚህ ሸውዶሽ ቤትሽ ይገባል… አዎ..እሱም ሲያጠቃሽ አንቺ ስትከላከይው ትኖራላችሁ። በህይወት ጉዞ  አጥቂ  እንጂ  ፈፅሞ  ተከላካይ  አትሁኚ። ሁለቱ የተለያየ ውጤት የሚያስገኙ የተለያዩ የህይወት መንገዶች ናቸው። ተከላካይ ስትሆኚ ጎል እንዳይገባብሽ ትጠብቂያለሸ፤ አጥቂ  ስትሆኚ  ደግሞ  ጎል ታገቢያለሽ።ደግሞ እወቂ ጥሩ ማጥቃት መከላከልም ጭምር ነው። ጥሩ መከላከል ግን ያው መከላከል ብቻ ነው። የጫወታ ሜዳው እንኳን ይለያያል..ተከላካይ በራሱ ክልል ታጥሮ በሰቀቀን እንዳይሸነፍ ይጫወታል። አጥቂ የተቃራኒ ክልል ሄዶ በነፃነትና በስነልቦና የበላይነት ለማሸነፍ ይጫወታል። ልልሽ የፈለኩት ገባሽ አይደል?›
‹‹አረ በደንብ ገብቶኛል››


"ጥሩ.እንግዲህ ያው የሚቀጥሉት አስር ቀናት የመጨረሻ ተግባራዊ ስልጠና የምትወስጂባቸው ቀናቶች ናቸው። እሱን ታውቂያለሽ አይደል።"

"አዎ ተነግሮኛል፤ ግን ቦታው የት ነው? የተግባር ልምምድስ ምን አይነት ነው? የሚለውን ምንሞ የማውቀው ነገር የለም።"

"እሱን አሁን እነግርሻለሁ..የስራ ቦታው እዚሁ ነው። ለእኛ ተግባራዊ የመጨረሻ ልምምድ ላይ ነሽ እንበልሽ እንጂ አንቺ ግን ለራስሽ መንገር ያለብሽ ቀጥታ ስራ እንደጀመርሽ ነው ...ፕሮፌሽናል የማሳጅ ባለሞያ እንደሆንሽ ነው   እራስሽን ማሳመን ያለብሽ"

"እሺ እንደአልሺኝ ለማድረግ እሞክራለሁ"

"ሳባ በእዚህ በእኛ ስራ ሙከራ ብሎ ነገር አይሰራም ...አይደለም   መሞከር ነገሮችን በተለመደው መንገድ ማድረግ እንኳን ዋጋ ያስከፍላል።በዚህ ስራ ውጤታማ ለመሆን የምትሰሪውን ስራ በተለየ ትኩረት ለፍፅምና በቀረበ ብቃት
፤ባልተደጋገመ ልዩ ጥበባዊ ብልሀት ነው መፈፀም ያለብሽ...ይሄንን መቼስ ባሳለፍሻው የ10 ሳምንት ስልጠና በደንብና በዝርዝር እንደተገነዘብሽ አምናለሁ።

"አዎ ትክክል ነሽ

"እንግዲያው በሚቀጥሉት 15 ቀናት  ከ  5  ደንበኞች  ጋር  ቀጠሮ  ተይዞልሻል።ሰዎቹ ካሉን በርካታ ደንበኞች መካከል የተመረጡ ናቸው።ጥሪው ‹አዲስ ልዩ የማሳጅ ባለሞያ አስመጥተናልና በቋሚነት ከመቅጠራችን በፊት አገልግሎቷን በማየት አስተያየት ይስጡን››ብለን ነው።እንግዲህ በሶስት ቀን አንድ ቀን አንድ ደንበኛ አለሽ ማለት ነው።ዛሬ ደንበኛውን አስተናግደሽ በሁለተኛው ቀን ደንበኛውን እንዴት ነው የተቀበልሽው፤?እንዴት ነው  ማሳጅ  ያደረግሽው? በምን ያህል ፍጥነትና ብቃት ልትግባቢው ቻልሽ?ምን ያህል ጊዜ ለመቆየት አስቦ ምን ያህል ቆየ ?እያንዳንዷን ከተቀረፀው ቪዲዬ እያየን እንነጋገርበታለን።በዛ ላይ ከሰውዬውንም በቀጥታ አስተያየት  እንቀበላለን።...
እንዴት ነው ገባሽ?"

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍728🤔1
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ: …. ‹‹ምነው አልክ..?ፒጃማ የለህም እንዴ?›› ‹‹አለኝ ግን በማሳጁ ምን ያህል ብቁ ሆነሻል.ስልጠናውስ እንዴት ነበር? የሚለውን ማወቅ እፈልጋለሁ…›› ‹‹ተው… እርግጠኛ ነህ?›› ‹‹አዎ ምነው ፈራሽ አንዴ.?ነው ወይስ በብቃትሽ አትተማመኝም? እንዳዛ ከሆነ ይቅር፡› ብሎ ፊቱን ወደቁምሳጥኑ መልሶ ሊራመድ ሲል እጁን ለቀም…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


"አዎ ገብቶኛል....ግን ይቀረፃል ያልሺው?"

"አዎ ይሄንን በከፍተኛ ሚስጥር ነው....ድንገት ተስቶሽ በህልምሽ እንኳን ብታወሪ ህይወትሽን ያስከፍልሻል።ምክንያቱም ደንበኞቻችን እንደሚቀረፁ ቢያውቁ እዚህች ቤት ዳግመኛ ዝር አይሉም።እኛ ግን በጣም ምስጢራዊና ማንም በቀላል ፍተሻ ማግኘት በማይችልበት ቦታዎች ካሜራዎች አሉን።ይሄ በዎናነት ሰራተኞቻችንን ከአደጋ ለመጠበቅ ነው። ማንኛውም ሰው  አጉል  እመል  ኖሮት  ጥቃት  ልፈፅም ቢል በፈጥነን እንደርሳለን፡፡ ከእንደገና ሰውዬው በሂደት ከእኛ ጋር ተቃቅሮ ድርጅታችንን ሊያጠቃ ቢንቀሳቀስ ያ ሚስጥር መከላከያ ጋሻችን ነው።

"አሁን ገባኝ"

"አዎ...ግን ላስጠንቅቅሽ...ስራ ስትጀምሪ ፈፅሞ ስለካሜራው በአእምሮሽ ማሰብ የለብሽም...ልክ አንድ የፊልም ተዋናይ ስትተውን ፊት ለፊቷ ስለተደቀነው ካሜራ ቁብ እንደማይሰጣት ሁሉ አንቺም ተመሳሳዩን ማድረግ አለብሽ፤ ይሄንንን ከመጀመሪያው ቀን ጀምረሽ መልመድ አለብሽ"

"እሺ እንዳልሺኝ አደርጋለሁ።

"እሺ አሁን ጨርሰናል...ክፍልሽን ያሳዩሻል  ግቢና  እረፊ...  ልክ  9.30   ላይ ከክፍልሽ ወደማሳጅ ቤቱ ይወስድሻል። አስር ሰዓት ላይ የመጀመሪያ ደንበኛሽ ይመጣል። ዝግጁ ሆነሽ ጠብቂው ።ከእኔ ጋር ነገ ጠዋት እንገናኛለን ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና ጉንጯን ስማት በተቀመጠችበት ጥላት ሄደች።


ሳባ በህይወቷ ዘመኗ የከፋው ፍርሀት ነው  በመላ  ሰውነቷ  ተሰራጭቶ እያንዘፈዘፍት ያለው እርግጥ ይህ ፍራቻ ገና ጠዋት  ስለፕሮግራሙ  ከተነገራት ጀምሮ ነው ሲረብሻት የዋለው ። ሰአቱ ሲቃረብ እንዲያደፋፍራት መድሀኒት ነገር ወይም መጠጥ ጠጣ ጠጣ አድርጋ ለመሄድ ፈልጋ ነበር።ግን ስልጠና ላይ እንደተነገራት ወደስራ መጠጥ ጠጥቶ አይደለም ቀምሶ እንኳን መግባት አይቻልም።ባይሆን በስራ ላይ እያለች ደንበኛው መጠጥ እንዲቀርብለት ካዘዘና ለእሷም ከጋበዛት የዛኔ ነፃ እንደሆነች ነው የተማረችው።በመጀመሪያ ቀን የሙከራ ጊዜዎ ደግሞ ስህተት በመስራት ልትጀምረው አልፈለገችም። ቢያንስ እያወቀች መሳሳት አትፈልግም"ሰገን
ሰገን ነች ማሳጅ መስጫ ክፍል ድረስ ይዛት የሄደችው። እያንዳንዱ ለማሳጅ የምትገለገልበት እቃ የት የት እንዳለ ምን ማድረግ እንዳለባት ምን አለማድረግ እንዳለባት ከ20 ደቂቃ በላይ ክፍል ውስጥ  እየተንጎራደደች  አንድን  ዕቃ እየያዘች መልሳ እያስቀመጠች አብራራችላትና መልካም እድል ተመኘችላትና ተሰናብታት ወጣች።
ጥላት ከሄደች ከ10 ደቂቃ በኃላ በራፍ ተቆረቆረ ከተቀመጠችበት በመበርገግ ቆመች...መልሳ ቁጭ አለች...የኋላ መውጫ በር ቢኖረው በራ ለመውጣት ሁሉ ተመኘች።
ደግሞ በራፍ ተቆረቆረ..እንደምንም መቀመጫዋን ለቃ ወደበሩ ተራመደች ከፈተችው…በድንጋጤ ላይ ድንጋጤ የሚጨምር ሁኔታ ተከሰተ በራፋ ላይ የገጠማት አንድ ግዙፍ አስፈሪ መልክና  ኮስታራ ፊት ያለው ሰው ፊቷ ተጋረጠ" ወይኔ በጌታ አሁን ይሄ ምኑ ይታሻል?"ስትል በቅፅበት ውስጥ አሰበች"አሽቀንጥሮ.ገፈተራትና.ወደውስጥ.ገባ።በድንጋጤ.አይኖቿን.በለጠጠች።
በየክፍሉ  እየገባ ይፈትሽ ጀመር።ቁም ሳጥኖቹን ሁሉ  እያንዳንድን  መሳቢያ  ሳይቀር  እየከፈተ እየዘጋ ማየቱን ቀጠለ
"ይሄ ምን የሚሉት ደንበኛ ነው? "ስትል በውስጧ አሰበች። በሁኔታው ተበሳጨች፤ስትበሳጭ.በመጠኑ.ፍራቻዋ.ቀነስ.አለላት።
  "ጌታዬ ምን ፈልገው ነው?"
መሀል ወለል ላይ ቆመና ዙሪያ ገባውን ኮርኒሱንም ሳይቀር በጥንቃቄ ካየ በኋላ ለእሷ  ጥያቄ   ምንም    መልስ   ሳይሰጥ    እንደ አመጣጡ    መልሶ ወጣ። ይበልጥ ግራ ተገባች፡፡ ይሄ ጠረንገሎና አስቀያሚ እዛ የማሳጅ ጠረጴዛ ላይ ተኝቶ እሺኝ ስላላላት እግዚያብሄር ይመስገን ብላ አመስግና ሳትጨርስ በራፍ ተከፈተና ያው ሰውዬ መልሶ አንገቱን አሰገገ...ሀሞቷ ፍስስ አለ...በራፉን ሙሉ በሙሉ ከፈተው ሌሎች ሰዎች ታያት።ሶስት መሆናቸውን አየች።
"በአንዴ ሶስት ሰው ማሸት ይቻላል እንዴ? እንዲህ አይነት ነገር እንዳለ አልተነገረኝም...ምን ነካቸው ቢያንስ ለተለማማጅ ሰራተኛ እንደዚህ ማድረግ ይገባል?"በውስጧ አጉረምርማ ሳትጨርስ ግራና ቀኝ የነበሩ ሁለት  ወጠምሾች መሀል ያለውን ሰውዬ ወደውስጥ አስገቡትና እነሱ  ወደኋላ  ሸሽተው  ከክፍሉ ወጡ። በራፉ ከውጭ ተዘጋ።
ግድግዳውን ተለጥፋ እንደቆመች ሰውዬው ላይ አፈጠጠችበት። ሰውዬውን ታውቀዋለች..አዎ በደንብ ታውቀዋለች። ሮጣ ሄዳ ልትጠመጠምበት ነበር።ትዝ ሲላት ለካ የምታውቀው በመገናኛ ብዙሀን ነው።ማን ነበር..አዎ አስታወሰችው። እንዴ እዚህ ምን ይሰራል?"
‹‹ጤና ይስጥልኝ ቆንጆ?››አላት በሚያምር ግን አስገምጋሚ በሆነ ድምፅ።

በፍጥነት ወደቀልቧ ለመመለስ ጥረት አደረገች። ፊቷን በፈገግታ አደመቀችና እጇን ለሰላምታ ዘረጋች….በተመሳሳይ ድምቀት ጨበጣት ...
‹‹ጌታዬ ትንሽ አረፍ ትላለህ...ወይስ?››

"ቆይ ትንሽ ትንፋሼን ልሰብስብ... ካንቺም ጋር በደንብ ልተዋወቅ።"አለና ወደሶፋው ሄደና ተቀመጠ፡፡
"ጌታዬ ቀለል እንዲልህ ኮትህን ታወልቀው?"

"አዎ ትክክል ነሽ..››ብሎ በተቀመጠበት  ሶፋ  ሆኖ  ኮቱን  አወለቀ.. በፍጥነት ተቀብላ ወደመስቀያው ሄደችና በጥንቃቄ  ሰቀለችና  ወደ  ሰውዬው ተመለሰችና ፊት ለፊቱ ተቀመጠች።
‹‹ስምሽን ማን ልበል?›› ጠየቃት፡፡
‹‹ቬሮኒካ"አለችው፡፡ ይሄ ስም ድንገት አፏ ላይ የመጣላት ስም ነው…ለዚህ ስራ ትክክለኛ ስምን መጠቀም አግባብ መስሎ ስላልተሰማት ነው እንዲህ ያደረገችው፡፡
‹‹የእኔ ክብሮም››አላት ሰውዬው፡

‹‹ጌታዬ አንተን የማያውቅ ኢትዬጴያዊ ማን አለ?››

‹‹እንደዛ ከሆነ ጥሩ...››አለና ከኪሱ ሞባይሉን አወጣና ደወለ፡፡

"የሚጠጣ አስመጣልን እስቲ"አለና ትዕዛዝ ካስተላለፈ በኃላ ሞባይሉን ዘግቶ ቦታው መለሠና።
"ከነገሩኝ በላይ ቆንጆ ነሽ"አላት
ከት ብላ ሳቀች.‹‹..እንዴ ማነው እንዲህ አይነት ጥብቅ ሚስጥር ያሾለከው?" አለችው፡፡
"የውስጥ ሰላይ አለኝ...ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ ስራው ያንቺን እንቅስቃሴ መከታተል ይሆናል››
"እንግዲህ እኛም ቀዳሚ ስራችን ውስጣችንን ከሰላዬችና ከሰርጎ ገቦች ማፅዳት ይሆናል" ስትለው በራፍ ተቆረቆረ ፡፡ መቀመጫዋን ለቃ ተንቀሳቀሰችና ከፈተች፡፡ ከጋርዶቹ አንዱ ነው። በሰርቪስ ትሪ ሙሉ ጠርሙስ ውስኪ ከሁለት ብርጭቆ ጋር ይዟል። አልፏት ወደ ውስጥ ገባና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ወጥቶ ሄደ ...ተከትላው ሄደችና በራፉን ከውስጥ በመቀርቀር ወደ ጠረጴዛው ተመለሰች። ውስኪውን ጠርሙስ ከፈተችና በአንድ ብርጭቆ በመቅዳት አቀረበችለትና   ቦታዋ  ተመልሳ ቁጭ አለች።
"እንዴ ላንቺስ?"

"እኔማ ስራ ላይ ነኝ...ሰክሬ ሰውነትህን ብቦጫጭቅህስ? "

"ነፍሴን አትቦጫጭቂያት እንጂ ለቆዳዬ ችግር የለም...በሰርጀሪ ይድናል "
"አረ ተው ...አንተን ማሳከም አይደለም ከእኔ ከድርጅቴም አቅም በላይ ነው"
"አልገባኝም...ቆዳ ቆዳ ነው?ምኑ ነው የሚከብድ››
‹‹ኸረ ጌታዬ ቆዳ ሁሉማ ቆዳ አይደለም..››
ራሱ ተነሳና ጠርሙሱን አንስቶ በባዶው ብርጭቆ ቀዳና "በይ እንደውም ጠጪና የምታደርጊኝን አድርጊኝና የሚሆነውን አብረን እናያለን....እግረ መንገዴንም የእኔ ቆዳ እንዴት የተለየ እንደሆነ እንዳውቅ ታደርጊያለሽ።

"ጌታዬ በአንድ ምስኪን ላይማ ይሄን ያህል አትጨክንባት››
👍536👏3👎1
​​እንዲህ ሲጫወቱ በሚገርም መግባባት ሲሳሰቁ 10 ሰዓት የገባው ሰውዬ ማታ አራት ሰዓት ነበር፡፡ ከእሽጉ ያልተፈታ 10 ሺብር እጇ ላይ አስቀምጦላት በቅርብ ቀን እንደሚመለስ ነግሯት የሄደው፡፡ ሰውየው ከሄደ ከ5 ደቂቃ በኋላ ከክፍሉ ስትወጣ ሰገንን ወደእሷ ስትመጣ በረንዳው ላይ ነበር ያገኘቻት፡፡ አቅፋት በአየር ላይ ነበር ያሽከረከረቻት‹‹ልዩ ነበርሽ ይሄ ሰው ከደንበኞቻችን መካከል እጅግ ብስጩ ምን እንደሚፈልግ የማይታወቅና በቀላሉ የማይደሰት ነበር..ሲመጣ ከ10-12 ሰዓት ለሁለት ሰዓት ብቻ እንደሚቆይ ነበር ያስመዘገበው..ግን ተጨማሪ 4 ሰዓት ማሳለፍ ችሏል…ለእኛም አሁን ገና ምርጥ ልጅ አመጣችሁ አለን…ብላ አቅፋ ይዛት ወደቤት ሄደች...በተመሳሳይ ሁኔታ በ15 ቀናት ውስጥ የተዘጋጀላትን ቀሪ አራት የሙከራ ስራ በብቃት አጠናቀቀች..ለብቃቷ አሪፍ ድግስ ተደግሶ እንኳን ደስ ያለሽ ፓርቲ ተዘጋጀላት፤ትብለጥም ከአሜሪካ ደውላ ከመጀመሪያው ምርጫዋ ትክክል እንደነበረና በብቃቷ እንደተደመመችባት በመናገር በቅርብ ሽልማት እንደምትልክላት ነገረቻት……፡፡እንደዛ ነበር አሽሞንሙነውና አላሳልሰው ወደማትወጣበት አዘቅት ውስጥ የነከሯት ለዚህ ደግሞ ደምሳሽ ትብለጥና ሰገን ዋነኛዎቹ ተዋናዬችና የጥቅም ተጋሪዎች ነበሩ.እርግጥ ደምሳሽ እንዳለው ወዲያው በዛን ሰሞን ወደአሜሪካ እንደሄደ አልተመለሰም….እሱ ወደአሜሪካ ከበረረ ከሁለት ወር በኃላ ደግሞ እዛ የነበረችው ትብለጥ ወደሀገር ቤት ተመልሳ በዙፋኗ ላይ መልሳ ተቀምጣለች….እናም ስራዋን ከጀመረች አንስቶ እስከ ሶስት ዓመት ድረስ ነገሮች እጅግ መልካም ይመስሉ ነበር…ሁሉ ነገር ፍርክሰስክስ ማለት የጀመረው ከዛ በኋላ ነው እንደ እህትም እንደጓደኛም የምታያትን ሰገንንና እንደእናት ታያት የነበረችውን ትብለጥን ዋና ጠላት አድርጋ በጨለማ ልቧ ላይ በጥቁር ቀለም በትልቁ የፃፈችው፡፡

ለደምሳሽ ግን አሁንም ድረስ የተለየ አይነት ስሜት ነው ያላት..አሁን ዛሬ ላይ እዛ ሰፊና ግዙፍ አልጋ ላይ ተኝታ በዛን ሰሞን የነበረችበትን የደስታ ስካር ሞልቶ ገደቡን ያለፈ ተስፋ ትዝ አላትና ሽምቅቅ  አለች፡፡…አሁን  ድረስ  የእሱ  ትዝታ በውጧ ትኩስ ነው...ዛሬም ድረስ  ይናፍቃታል፡፡ ዳሩ  ምን  ዋጋ  አለው …አሁን ሰውን መናፈቅ ለእኔ ቅንጦት ነው›ሥትል አሰበች፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍56👏1
#የጠፋ_ጥያቄ

አጀንዳችን ሁሉ ፣ አንድነት ያነሳል
አሸንዳችን ሁሉ ፣
ጠብታ አጠራቅሞ ፣ ባንድ ቦይ ያፈሳል
መቼ ተለያየን ?
ከሚለው ጥያቄ ፣
መቼ ተገናኘን ፣ የሚለው ይብሳል፡፡
ላንድ አይነት ጥያቄ...
የተለያየ መልስ ፣ እንዴት ይመለሳል?!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለሶስ ሺ ዘመን...
አብሮ የኖረን ህዝብ ፣ ልዩነት ስናስብ
መልሱን እየፈለግን ፣ ጥያቄው ጠፋብን፡፡
ጥያቄው ምን ነበር?
"""""''""""""
መቼም የኛ ነገር ፣ ይናዳል ስንክበው
ስብሰባው ሲያበቃ...
ለመበታተን ነው ፣ ምንሰበሰበው፡፡

🎴በላይ በቀለ ወያ🎴


ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍248🔥1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በማሳጅ ስም እየሰራችው ያለችው ስራ ካሰበችው በጣም ውስብስብ ፤ከግምቷ በጣም የረቀ፤ ካደገችበት ስነ-ምግባር ያፈነገጠ፤ የተለየ አይነት አለም ሚያሳይ ቢሆንም ወደ ቦርሳዋ በሚፈስላት ብር ስለሚካካስ አሜን ብለ ተቀብላው ለአመታት ሰትሰራ ነበር፡፡እንጂማ ስራ ሲያስጀምሯት ማሳጅ ቤት ብለው የሰበኳት ስብከት ፌክ መሆኑን የተረዳችው ስራ በጀመረች ሶስት ወርም ሳይሞላት በፊት ነበር፡፡ምክንያቱም ከሚሰጡት አገልግሎቶች ውስጥ ትክክለኛ ያልበተበረዘና ያልተከለሰ ማሳጅ 25 ፐርሰንትም አይሆንም...አሱ ሽፋን ነው፡፡
ወደስራው ጠልቃ ከገባች በኃላ ብዙ ብዙ ገራሚ ገጠመኞችን አስትናግዳለች… አንዳንዶቹ እስከህይወቷ ፍፃሜ የማትዘነጋቸው አይነት ናቸው፡፡
ከበርካታ ያልተለመዱ አይነት ገጠመኞቾ መካከል  አንድን ለምሳሌ ያህል ለማየት ብንችል ነገሮችን ግልፅ ያደርግልናል፡፡ስራ በጀመረች በአራተኛው አመት ነው፡፡ደምበኛ እንዳላት ተነግሯት በሰዓቷ ስራ ቦታዋ ተገኝታ እየጠበቀች ነው፡፡ እንደተባለውም በሰዓቱ በራፍ ተንኳኳ… ከፈተች፡፡በራፍ ላይ በመግባትና ተመልሶ ሮጦ አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ውዝግብ ውስጥ የገባ ስሜት ላይ ያለ ጎልማሳ  ሰው  ቆሟል..ሰውዬውን  ታውቀዋለች… በአካል አይደለም..ታዋቂ ሰው ነው..ግን ምንድነው?  ተዋናይ  ነው?  ፖለቲከኛ ነው…? ግልፅ ብሎ ሊታወሳት አልቻለም፡፡‹‹ጌታዬ እንኳን ደህና መጡ ይግቡ.›› አለችና በራፉን በሰፊው ከፈተችለት..የመዝለል ያህል ፍንጥር አለና ወደ ውስጥ ገባ…እሷም በራፉን ዘጋችና  ተከተለችው…እቤቱ  ውስጥ  ከወዲህ  ወዲያ መንጎራደድ ጀመረ‹‹…ጌታይ ችግር አለ? ››ጠየቀችው፡፡

‹‹እዚህ መምጣቴ ትክክል ነው ወይስ ስህተት አላውቅም››

‹‹ጌታዬ ስህትም  ሆነ  ትክክል  አንዴ  መጥተዋል..አረፍ  ይበሉና  ትንሽ ይረጋጉ..እዚህ መምጣቶት ስህተትም ቢሆን የሆነ ጥቅም አይጠፋውም….ደግሞ ነገሮች እንደአጠቃቀማችን ይወሰናሉ…የህይወት ጨለማ ክፍሉ ውስጥ ዳካሮ መውጣት የብርሀኗን ውበት የበለጠ እንድናጣጥም  ግንዛቤያችንን ይጨምርልናል፡፡››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡››ብሎ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ፡፡ሳባም ወደፍሪጁ ሄደችና የታሸገ ውሀ በማምጣት ከጎኑ ያለ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችለት..ከፈተና ገርገጭ.ገርገጭ አድርጎ ግማሽ ያህሉን ከጠጣለት በኃላ ከደነና መልሶ አስቀመጠው፡፡ለእኔ እዚህ ቦታ መምጣት ቀላል አይደለም…እዚህ እንድመጣ የጠቆመኝ አንድ ወዳጄ ነው….

‹‹ጥሩ ነው…ምን አይነት አገልግሎት ነው የሚፈልጉት…ሙሉ ማሳጅ ..የእግር ማሳጅ አለ…ከአንገት በላይ ማሳጅ አለን…ሌሎች አገልግሎቶቹም አሉን.መጠጥና
…››
‹‹አይ እንዳዛ አይደለም…የዘረዘርሻቸውንም ሁሉ አንዳቸውንም አልፈልግም…እኔ የምፈልገው እንድታዳምጪኝ ብቻ ነው…ቆይ አሉና እጃቸውን ወደ ኮት ኪሳቸው በመክተት አንድ መለስተኛ ጥራዝ ያለው መፅሀፍ  አወጡና  ዘረጉላት፡፡ግራ በመጋባት ተቀበለችና አነበበችው›

‹‹የኢየሱስ ተአምራዊ የማዳን ስራ››የሚል ርዕስ አለው፡፡ጀርባውን ገልብጣ አየችው ፀሀፊ-ፓስተር ጴጥሮስ ዳንሳ ይላል፡፡ ከፊት ለፊቷ ያለው ሰው ፎቶ ገጭ ብሎበታል…እንደአዲስ ደነገጠች..ሰውዬው በደንብ ታውቀዋለች..በፕሮቴሰታንቱ መንደር በጣም ታዋቂና ዝነኘ ፓስተር ነው…በዛ ላይ የራሱ ሆነ ቴሌቬዥን ጣቢያ ስላለው.በተደጋጋሚ ስብከቱን በቴሌቪዥን መስኮት አዳምጣለች፤አሷ  ጋር መምጣቱ ለምን እንደዚህ እንደከበደው ወዲያው ነበር ግልፅ  የሆነላት..ኸረ መምጣቱ ለእሷ ለራሷ በጣም ገርሟታል..››

‹‹ፓስተር.በእውነት የአርሷ እዚህ  መምጣት  ለእኔ  ትልቅ  ክብር  ነው….እና እንዳሉኝ የሚፈልጉት እንዳዳምጧት ከሆነ በሙሉ ነፍሴ  የለምንም  ፍርድና ትዝብት እንደማዳምጧት እርግጠኛ ይሁኑ››

‹‹እሺ እንደዛ ከሆነ .ማወራሽ ስለመፅሀፉ ነው፡፡በእጅሽ ስለያዝሺው መፅሀፍ ፡፡ መፅሀፉ እውነተኛ የህይወት ገጠመኜ የሰፈረበት ነው፡ይሄ ገጠመኝ ምንም ማጣፈጫ ያልተጨመረበት ንፅህ እውነት ነው ብዬ  አምን  ነበር።ላለፍት  9 ዓመታት ሰፋ ያለ ህዝብ በታደመበት አውደ ምህረት ላይ  ያለመሰልቸት ተርኬዋለሁ። ምዕመኑም አንዳንድ ሶስቴ ሌላውም 13ቴ ደጋግሞ ሰምተውታል። ግን አይ ሰልችቶኛል የሚል የለም፡፡ ከእልልታው ጥቂት ዝንጣፊ የሚቀንስ የለም።በጌታ ሰው አንደበት የሚነገር የጌታ ተአምር እንዴት ሰለቸኝ ማለት ይቻላል...?መታሰብስ።

የዛሬ 14 አመት ለአገልግሎት ደቡብ ኢትዬጰያና ሱዳን ድንበር  አካባቢ  ወደሉ ጎሳዎች እሄዳለሁ።እርግጥ ብቻዬን ሳይሆን ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ነበር።እና ጉዞችን ጥቅጥቅ ደን የምናቋርጥበት ከአውሬ ጋር ድብብቆሽ የምንጫወትበት አስደናቂና አስፈሪ ነበር..ግን ደግሞ ጌታ ከእኛ ጋር ስለነበር በዝምታ ሳይሆን በዝማሬ ነበር የተጓዝነው። መንገድ ከሚገኝበት የሁለት ቀን የእግር መንገድ ተሂዶ ነው የሚደረሰው። ጌታ ይመስገን በሰላም ደረስን።ጌታን አገለገልን በሶስት ወር ቆይታችን 10 ብቻ የነበሩትን አማኞች ወደ ሶስት መቶ አሳድገን በመንደሩና በአካባቢው  የጌታ  አገልጋዬች  አድርገን  ጉባኤ  አደራጅተን  ቤተክርስቲያን መስርተን አንደኛውን ጓደኛችንን እዛው  እንዲያገለግል  ትተን  የመልስ  ጉዞ ጀመርን።

በመሀል ደረቀ ጉሮሮውን ለማርጠብ ከጎኑ ካለው ጠረጴዛ ውሀውን አነሳና ላይ የተቀመጠለትን ሀይላደንድ ውሀ በመክፈት እየተጎነጨ በተመስጦና በስሜት ትረካውን ቀጥሏል…፡
…በሁለተኛው ቀን ከጓደኞቼ ነጥለው ጠለፍኝ።አንድ መፅሀፍ ቅድስ ብቻ ነበር በእጄ የያዝኩት፡፡ጌታ ሆይ አንተ ጠብቀኝ አልኩ።የጠለፍኝ ሰዎች ቋንቋቸው የማይገባ እጅግ ከሰው ተነጥለው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ የሚኖሩ 2መቶ የማይሞላ ቁጥር ያላቸው አባላት ያላቸው ጎሳዎች ናቸው።
ከወሰዱኝ በኃላ አንድ ጠባብ ጎጆ ውስጥ ጠርቅመውብኝ በራፍን ገንጥዬ እንዳላመልጥ ሁለት ጦር የቀሰሩ ጠባቂዎች በራፍ  ላይ  አስቀመጡ።መፅሀፍ ቁዱሴን ደረቴ ላይ ለጥፌ እኔ ፀልያለሁ...ያለማቆረጥ ከጌታ ጋር አወራለሁ።ሶስታ ቀንና ሶስት ለሊት  እዛች  ጠባብ ጎጆ  ውስጥ  አሳደሩኝ፡፡  በአራተኛው ቀን የተለየ ነገር መታየት ጀመረ፡፡ ውጭ ታላቅ  ክብረ  በዓል  ለማዘጋጀት  ትርምስ  ላይ እንደሆኑ ይታየኛል።‹‹ጌታ ሆይ  ተአምራትህን  በዚህ  ዝግጅት  ላይ  አድርግ›› እያልኩ ፀሎቴን ቀጠልኩ.. ሲጨልም ምቀምሰውን ምግብ አንድ ልጃገረድ ይዛልኝ መጣች፡፡ ጠባቂዎቹ ወደውስጥ እንድታልፍ ፈቀድላት...:: ጎምበስ ብላ ምግብን እያቀረበችልኝ
"አይዞህ"አለችኝ፡፡

‹‹ እንዴ ጌታ ስራውን መስራት ጀመረ ››አልኩ...አማርኛ ትችላለች..

"ለምንድነው የያዙኝ...?ከእኔ ምን ፈልገው ነው ?"ከእሷ ባነሰ ደካማ ድምፅ ጠየቅኳት።
"ለመስዎእትነት..ለአማልዕክቱ ሊያቀርብህ ነው" አለችኝ... ያልጠበቅኩትን መልስ ነበር ያገኘሁት…የጌታ ጥበቃ በዙሪያዬ እንዳለ ባምንም..የልጅቷ በዛን ሰዓት

ከአማርኛ  ችሎታ  ጋር  ስሬ  መከሰት  አንድ  ምልክት  እንደሆነ  ባልጠራጠርም
...ሰውነቴ በፍራቻ መራድ፤አፌም በድንጋጤ መድረቁ አልቀረም ነበር።"
👍795🥰4👏1
"እባክሽ እርጂኝ" አልኳት...ያው እግዜያብሄር ሲረዳ በምክንያት ነው ምን አልባት በእሷ አማካይነት ከዚያ እስር ሊፈታኝ ነው ብዬ ነበር ያሰብኩት …
እሷ  ግን"  አልችልም…  ሙሉ  ጨረቃ  ከወጣች  ዛሬ  ለሊት  ለመስዋእት ትቀርባለህ›› ብላ ፍርጥ ያለውን መርዶ እንደቀልድ ነገረችኝ ፡፡
"እባክሽ የልጅ አባት ነኝ...በቅርብ የተወለደ አንድ ወንድ ልጅ  አለኝ" አልኳት "አንድ ዘዴ ብቻ ነው የሚያድንህ "አለቺኝ፡፡
‹‹ምንድነው እባክሽ.እርጂኝ››ስል ተማፀንኳት

"ይሄንን እራትህን ብላ ..ወተቱንም በደንብ ጠጣ...ትንሽ ቆይቼ እመለሳለሁ ..የዛን ጊዜ ከዚህ ችግር ለመትረፍ ያለህን አንድ እድል እነግርሀለው"ብላኝ መልስ ሳትጠብቅ ሹክክ ብላ ወጥታ ሄደች።
"በዚህን አይነት ወቅት እምነትን  በጌታ ላይ  ፀንቶ መቆየት ከምታስቢው በላይ ከባድ ነበር...በዛ ላይ የሠው ልጅ የዘላለም  ጠላት የሆነው ሰይጣን ጆሮሽ ላይ ተለጥፎ መጥፎ መጥፎ ሀሳብ በአእምሮሽ እየሠነቀረ ይፈታተንሻል...እንዳለችኝ ምግቤን በልቼ ያመጣችልኝን ወተት ጠጥቼ መዝሙሬን እየዘመርኩ ፤በመፅሀፍ ቅዱሴ ሰውነቴን እየዳበስኩ፤ የእግዚያብሄር ተአምር እስኪገለጥ መጠባበቅ ጀመርኩ.. ልጅቷ መጣለሁ ብላ ከሄደች በጣም ቆየች ..በጎጆ ቤቱ ቀዳዳ አጮልቄ ሰማዪን ሳይ ጨረቃ ሙሉ ሆና ተገማሽራለች ..ሰዓቱም  ወደ  እኩለ  ለሊት እየተቃረበ ነው።ልጅቷ ከመመለሷ በፊት መጥተው  ጎትተው  ቢወስድኝስ...? አንገቴን በካራ በመበጠስ ለጣኦታቸው ቢሰውኝስ?"ጌታ ሆይ ስጋዬን እንኳን ቢያጠፍት ነፍሴን ግን ለአንተ አደራ ሰጥቼሀለሁ ..ብዬ ፀልዬ ቀና ስል የጎጆ

የጭራሮ በር ተከፈተ...በቃ ሊወስድኝ እንደመጡ እርግጠኛ ነበርኩ...ግን ተሳስቼ ነበር፡፡ ኢየሱስ መልእክተኛውን ነበር የላከልኝ። ልጅቷ ነች ሹክክ ብላ የመጣችው
"እንካ "አለችና ሁለት ነገር አቀበለችኝ ፡፡በዳበሳ ምንነቱን ለማወቅ ሞከርኩ፡፡ አንደኛው ስለት ነገር ሲሆን ሌላው በሰፊ ቅጠል የተጠቀለለ የተጨቀጨቀ ቅጠላቅጠል መሆኑን ተረዳሁ‹‹..እንዴ እኔ እኮ  የእግዚያብሄር  ነብይ  ነኝ  ከሰዎቹ ጋር እንድፋለምበት ነው እንዴ ስለቱን የሠጠችኝ?አላደርገውም።››ሥል በውስጤ አጉረመረምኩ፡በተሰባበረና ዝቅ ባለ ድምፅ"ምን ላድርገው ?››ስል ጠየቅኳት
‹‹ ...እራስህን አቁስል..በሆነ መንገድ  የሚመችህን  ቦታ  መርጠህ  አቁስል... በባህላችን መሰረት የቆሰለ ሰው ፍፅም ለመስዋዕት አይቀርብም... የጨረቃ አምላክ የቆሰለ ሰው መስዋዕትነት ፈፁም ነው የምትጠየፈው..ካዛ መትረፍህን ካረጋገጥክ በኃላ መድሀኒቱን ተጠቀም ።ቁስሉን ያደርቅልሀል።"ብላኝ እንደልማዷ ሹልክ ብላ ወጣች።
ከዛ በቃ መፅሀፍ ቁዱሴን  አውጥቼ  በጉልበቴ  ተንበርክኬ  አመሰገንኩ፡፡ አግዚያብሄር አገልጋዩን የትም ጥሎ  አይረሳም  አልኩ›..ዳንኤልን  ከተጣለበት የአንበሳ ጉድጎድ ያወጣ አምላክ እኔንን ከከበቡኝና ሊሰዉኝ ከተዘጋጁ ገዳዮች ዘንድ ሊያድነኝ መልዕክቱን በዛች የተባረከች ሴት እንደላከ ተረዳሁ…..ከዛ እንደለችኝ የእጄን ክርን በጭካኔ ወጋሁት.. ደገምኩት…..ያም ነበር.. በጣም ያም ነበር ..ግን ከመሞት ይሻላል…. ደሙ ልብሴን እያጠበ ወደታች እየተንኳለለ ወረደና ወለሉን ሞላው ..ድምፄ እንዲሰማ አጓራሁ…ወዲያው ውጭ ሲጠብቁ  የነበሩ  ሁለት ጠባቂዎቼ እየሮጡ መጡ ….ችቧቸውን አበሩና የሆነኩትን በቋንቋቸው ይጠይቁኝ ጀመረ፡፡ ከእኔ መልስ ከማግኘታቸው በፊት አይናቸው የሚንዠቀዠቀው ደም ላይ አረፈ….ሁለቱም     ልክ     ሰይጣን     ፊት     ለፊታቸው     እንደወደቀ  ነበር አደነጋገጣቸው…. የሆነ አስፈሪ የአውሬ የመሰለ ሰቅጣጭ ጩኸት እያሰሙ እኔን ጥለው ጨረቃ ሙሉ ሆና እስክትወጣ በጭፈራና በዳንስ ወደሚጠብቁት

ዘመዶቻቸው ሮጡ፡፡ ከመደንገጣቸው የተነሳ በራፉን ሁሉ መዝጋቱን እረስተውት ነበር….አጨንቁሬ ተመለከትኳቸው ወደጎሳው ሽማግሌዎች ነበር  የቀረቡት፡፡ የሆነውን ነገሯቸው መሰለኝ ከዛ ወዲያ  ሽማግሌዎቹ  የሆነ  ከበፊቱ  ጋር የሚመሳሰል ሰቅጣጭ ድምፅ አሰሙ…ከዛ እስኪገርመኝ ደረስ ሳቁና ጭፈራው ወደመረረ ሀዘን ተቀየረ…..ከዛ በላይ  ትዕይንቱን  መከታተል  አልቻልኩም  ፡፡ ጎጇውን ለቅቄ ወጣሁና ጭለማውን ተገን አድርጌ ወደጓሮ ተጠመዘዝኩ… ሊያስቆመኝ የሞከረ ምንም አይነት ጠባቂ አልገጠመኝም…ከጀርባ ያለው ጥሻ ውስጥ ዘልዬ ገባሁ፡፡ ከዛ መፅሀፍ ቅዱሴን በጀርባዬ ለጥፌ በትንሹ ለሶስት ሰዓት ያለማቋረጥ ሳንባዬን እስክተፋ ድረስ ሮጥኩ.. ከዛ ተዳከምኩና አንድ ዛፍ ስር ተዘረርኩ….
ከዛ ያው እያረፍኩ፤ እየተጓዝኩ ከአንድ ቀን ተኩል  ጉዞ  በኃላ  ሰው  የሚገኝበት ትንሽ ገጠር ከተማ ደረስኩ..ጌታ ከዛ ከተቆረጠልኝ  ሞት  እንደዛ  አዳነኝ..ለዛ ውለታው እስከአሁን በፍቅርና በፍፅም እምነት ሳገለግለው ነበር ፤እስከ ህይወት ፍፃሜ እስትንፋሴ ተቋርጣ ወደእሱ እስከምሄድ ማገልገሌን ከመቀጠል ውጭ ሌላ ምንም አይነት እቅድም ሆነ ምኞት እልነበረኝም…ከሄድኩ በኃላም አንኳን በላይ በገነት ሆኜ ለእሱ የማቀርብለትን ዝማሬና ውዳሴ አዘጋጅቼ ዘወትር ኪቦርዴ ፊት ለፊት ቁጭ ብዬ ያለምኩ እለማመድ ነበር ፡፡
ለሳዕታት በንቃትና በጉጉት ስታዳምጥ የነበረችው ሳራ መናገር ጀመረች፡፡
‹‹እኔ  ሀይማኖተኛ  አይደለሁም..በሀይማኖተኛ  ሰዎች  ግን  እቀናለሁ…ምክያቱም እኔ ሀይማኖተኛ መሆን በጣም ፈልጋለሁ..ልቤ ግን እሺ አይለኝም፡፡ልብ ከለገመ ደግሞ ለገመ ነው፡፡ዛሬ ግን በነገሩኝ ተአምር የእውነት መነካቴን ልደብቆት አልፈልግ፡፡በእውነት አግዚያብሄር ይወዶታል፡፡››ነበር ያለቻቸው፡፡
‹‹ትክክል ነሽ ፡፡ይሄንን ታሪክ በመስማት ብቻ በአስር ሺ የሚሆኑ ሰዎች ጌታን ተቀብለዋል…ይሄንን መፅሀፍም በማንበብ ብዙዎቹ መንፈሳዊ ህይወታቸውን አፅንተዋል…እኔም በዚህ ታሪክ ባለቤት መሆኔን የመመፃደቅ ያህል እኩራራበት ነበር..አሁን ግን…››
‹‹አሁን ግን ምን.?ምን ተፈጠረ? ››ጠየቀች በጉጉት፡
ፓስተሩ ትረካቸውን ቀጠሉ‹‹አሁን ምን እንደማስብ ሁሉ ግራ ገብቶኛል.እምነቴን የሚፈታተን መጥፎ የዳቢሎስ ሀሳብ በምናቤ ተሰንቅሮ ውስጤን እየበላኝ ነው… በእውነት እንደማስበው ከእግዚያበሄር ጋር ነበር የምነጋገር የነበረውን?.እውነት የማወራውንና የማምነውን ያህል እግዚያብሄር በእኔ ህይወት ተአምራቱን ገልጧልን..?.እነዚህ በጣም የሚረብሺኝ ጥያቄዎች ናቸው››
‹‹ፓስተር እንደነገርኳት ምንም አይነት ሀይማኖታዊ እውቀት ያለኝ ሰው አይደለሁም….ስለመፅሀፍ ቅዱስም ያለኝ ግንዛቤ ኢምንት ነው…ግን ለመሆኑ በህይወት ዘመኖህ ሙሉ በልቦት ከነበረው ጠንካራ እምነት የሚሸረሽር ምን ክፍ ጉዳይ ገጠሟት?፡፡››
‹‹ይሄውልሽ …እንደአልኩሽ ይሄ የነገርኩሽን ታሪክ ጽፌ  ሌላውም  መማሪያና መፅናኛ ይሆን ዘንድ አሳትሜው ነበር፡፡የዛሬ ወር አካባቢ አንድ ጎልማሳ ሰው መፅሀፉን በእጁ ይዞ ቸርች መጣና .‹‹ፓስተር መፅሀፍን በተመለከተ ላናግርህ የምፈልገው ጉዳይ አለኝ ››አለ
‹‹ምንድነው?›› አልኩት፡፡

‹‹አይ እንዲህማ አይሆን ተቀምጠን ብናወራ ይሻላል›› አለኝ.፡፡
‹‹እሺ›› ብዬ በሀሳቡ በመስማማት ቸርች ውስጥ ወደአለኝ ቢሮ ይዤው ገባሁና በል ንገረኝ አልኩት፡፡
👍506
​​‹‹መፅሀፉን አንብቤዋለሁ…በጣም ልብ የሚያነቃ አሳዛኝ ግን ደግሞ በተመሳሳይ አስደሳች መጨረሻ ያለው ታሪክ ነው ›› አለኝ፡፡
ይሄንን አይነት አስተያት ለዘመናት ስሰማው የኖርኩት አይነት  ስለሆነ‹‹  አዎ ወንድም ….ከአሳዛኝነቱ በላይ ግን የእግዚያብሄርን ድንቅ ተአምር  እንዴት ባሪያዎችን በመከራ በተጣሉበት ጊዜ እንደሚታደግ ለማስተማር ታስቦ ነው የተፃፈው›› አልኩት፡
‹‹ትክክል ነው…አዎ አሁን መፅሀፉ ባለበት ይዘት  እርሶ  እንዳሉት  በትክክልም እንዳዛ ነው..ግን ?››
‹‹ግን ምን?››

‹‹እውነተኛው ታሪክ ማለቴ ቦታው ላይ የተፈፀመው ግን ሌላ ጭብጥ ነው ያለው›› አለኝ
ግራ ገባኝ….ሰውዬውን መልሼ በትኩረት አጤንኩት..ጤንነቱ ላይ ምንም የሚያጠራጥር ነገር አላየሁበትም.‹‹ወንድሜ ከዚህ በፊት እንተዋወቃለን እንዴ?›› ስል ጠየቅኩት
‹‹ኸረ በፍፅም ››

‹‹እና ታዲያ ?››

‹‹እኔ እርሶ ታግተው በነበሩበት ጊዜ ከታገቱበት ቦታ     የአራት ወይም የአምስት ሰዓት በሚሆን ስፍራ ላይ ወታደር ሆኜ ከጓደኞቼ  ጋር  እዛ  ነበርኩ….›› አለኝ…ማመን አልቻልኩም..ለማረጋገጥ ብዙ ብዙ ነገር ስለቦታው ጠየቅኩት፡፡ እያንዳንዱን ብትንትን አደርጎ ያለስህተት ነገረኝ፡፡ አመንኩት…እና ተደሰትኩኛ፡፡
‹‹እሺ እና ልትነግረኝ የፈለከው ምንድነበር?››ስል ጠየቅኩት

… በወቅቱ ጓደኞቾት የነበሩ ሁለት ፓስተሮች ወደካምፓችን መጥተው ጓደኛቸው እንደጠፋባቸው ነገሩን ፡፡ምንም እንኳን ስራው  የፖሊስ  ቢሆንም  አካባቢው ጠረፍና በጣም ሪሞት በመሆኑ በአካባቢው የፖሊስ ሀይል ስለሌለን ሁኔታውን ለሀለቆቻችን ነገርንና  እንድንተባበራቸው  ስለተፈቀደልን….ለሶስት  ቀን  ያህል እርሷን ፈለግኖት››
አዎ ካመለጥኩ በኃላ ጓደኖቼ ይሄንን ታሪክ ነግረውኛል.እሺ ከዛስ?›

‹‹ከዛ በኃላማ ምንም ፍንጭ ሳላላገኘን ተስፋ ቆረጥንና ጎደኞቹን ሸኘናቸው…. ይሁን እንጂ ከሳምንት በኃላ ለሌላ ተልዕኮ ስንንቀሳቀስ….የሆነ መንደር   ላይ ግጭት መቀስቀሱን ሰማንና ልናጣራ ተንቀሰቀስን፡፡ ስንደርስ በህይወቴ ካየሁት ሰቅጣጭ ድርጊቶች ውስጥ አንዱን ነበር የገጠመኝ፡፡116 አባ ወራዎች ተጨፍጭፈው ግማሹ ሆዱ ተቦትርፎ ፤ግማሹ   አንገቱ   ተቀልቶ፤   መንደሩ   ኦና ሆኖ በዝንብ እና በጥንብ አንሳ አሞራ ተሞልቶ ነበር የደረስነው፡፡፡ሌላ ምንም የለም…በህይወት ተርፎ የሚንቀሳቀስ ሰው የለም….ከብት፤ዶሮም ሆነ ፍየል ብቻ ምንም አይነት የቤት እንስሳት የለም……ግራ ገባን፡፡ ከዛ አካባቢውን እንድናስስ ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡ከሰዕታት አሰሳና ልፍት በኃላ አንድ ሴት ዛፍ ላይ ተንጠልጥላ ስትቁለጨለጭ አገኘናት….በራሀብ በውሀ ጥም ከመዳከሞ የተነሳ ከዛፍ   ላይ እንኳን መውረድ አትችልም ነበር…..ከዛ አንድ ወታድር ወጥቶ አዝሎ አወረዳት….ከያዝነው ኮዳ ውሀ አጠጥተን ከኮሾሮችንን አርሰን እንድትቀምስ አድርገን እንደምንም ከበረታች በኃላ የሆነውን እንድትነግረን ጠየቅናት ፡፡ልጅቷ ማን መሰለቾት ፓስተር እርሶን እንዲያመልጡ የረዳችዎት ልጅ ነች፡፡እንደዛ ለማድረግ ያሰበችው አስተዳደጎ እራቅ ብሎ በሚገኝ ሌላ ባህል ባለው ማህበረሰብ ውስጥ ስላደገች ነው..፤ የአባቷን ማህበረሰብ የተቀላቀለችው በቅርብ ነበር ፡፡አንጂ እርሶን ማስመለጥ በወገኖቾ ላይ የሚያመጣውን መቀሰፍት አውቃ ቢሆን ኖሮ ፈፅሞ አታደርገውም ነበር፡፡

‹ግራ አጋባኸኘ አኮ ….ስለምን መቅሰፍት ነው የምታወራው…መቼም ጣኦታቸው ተቆጥቶ ቀጣቸው አተለኝም››ስል ጠየቅኩት ግራ ተጋብቼ፡፡

‹‹አይደለም…እነዚህ   ጎሳዎች   በሰባት   አመት   አንዴ   የጨረቃዋ   አምላካችን ለሚሉት ፈጣሪያቸው መስዋዕትነት የማቅረብ ከትውልድ የተላለፈ ግዳጅ አለባቸው።ግን     እነሱ     ብቻ     አልነበሩም      ።በዛው      አካባቢ      በኪሎ ሜትሮች ተራርቀው የሚኖሩ መሠረታቸው አንድ የሆነ   5   ጎሳዎች   ነበሩ። እንግዲህ   በምርመራችን   እንደተረዳነው   ያ   አምላካችን   ለሚሉት    የጨረቃ አምላክ የሰው መስዋዕትነት ማቅረብን አምስቱም በየመንደራቸው በተመሳሳይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የመከወን ግዴታ ነበረባቸው።ከመሀከላቸው አንድ ጎሳ እንኳን ግዴታውን መወጣት ካቃተው ከአምላካቸው የሚወርደው ቁጣ አምስቱንም ይበላል    ተብሎ    ይታመናል።እና    ከዛ    ቁጣ    ለማምለጥ     ያላቸው     አንድ ብቸኛ ምርጫ ሌሎቹ አንድ ላይ በማበር ግዳጅን መወጣት ያቃተውን ጎሳ አባል የሆነ ለአቅመ አዳም የደረሰ ማንኛውንም ወንድ ልጅ ያለምህረት በመግደል ሌሎች ልጆችን ፤ሴቶችንና   የጎሳውን   ንብረት   በመካፈል   የጎሳውን   ህልውና በማክሰም ነው። እና በዛን ጊዜ የሆነው እርሶ በፃፉት በዚህ መፅሀፍ ላይ አልተካተተም...እና በቀጣይ    ህትመት    ቅጥያ    ብለው     አሁን     የነገርኮትን     የታሪኩን መደምደሚያ እንደሚያካትቱበት እምነት አለኝ።››ብሎ ሌላ ነገር ሳይናገር ጥሎኝ ሄደ....
ካዛ ቀን በኃላ አፌ ለምስጋና መከፈት አልቻለም...እጆቼም ለፀሎት ሊዘረጉልኝ አልፈቀዱም.... ከልቤ ሞልቶ ይፈስ የነበረው እምነት በውስጤ ሟሾል ፤ ካንቱነት ዙሪያዬን ከቦኛል...ህመም ላይ ነኝ...የመንፈስ ህመም።ደዌ ተፀናውቶኛል።እና ምሄድበት ግራ ሲገባኝ ነው አንቺ ጋር የመጣሁት።በህይወቴ እንዲህ ደካማ ሆኜ አላውቅም...በቃ በወጥመድ  የተያዘ  አይጥ በይኝ።ምዕመናን ፊት ለፊት ወጥቼ ስለጌታ አዳኝነት መስበክ አልቻልኩም..ቴሌቬዝን ጣቢያዬን ማኔጅ ማድረግ አቅቶኛል..በአጠቃላይ ጨለማ የሆነ ድባቴ ውስጥ ገብቼያለሁ፡፡››ሲሉ ነበር ታሪካቸውን ያጠቃለሉት፡፡
"ጌታዬ በእውነት እኔም የርሶ  ስሜት  ሙሉ  በሙሉ  ተጋብቶብኛል...ማለቴ ያሉበትን ሁኔታ በደንብ ተረድቼያለሁ...እንዴት እንደማግዞት እንዴት ሸክሞትን እንደምጋራዎት ምንም አይነት መንገድ ሊመጣልኝ አልቻለም።››
ፓስተሩ  ፈገግ  አለ፣እናም  መናገር  ጀመረ‹‹...ረዳሺኝ  እኮ...ይሄንን   የውስጥ ችግሬን ከማንም ጋር እንዲህ በግልፅ ለማውራት አልችልም...ከቤተሰቦቼ ጋርም ቢሆን? ከአንቺ ጋር ግን ይሄው ዝርዝር ነጥቦችን ሳይቀር ለሳዕታት አወራሁሽ... አንቺም ቃል እንደገባሽልኝ…ያለምንም ፍርድ በጥልቅ ተመስጦ ሰማሺኝ... ከዚህ በላይ እርዳታ ከየት ይመጣል......?.  እንዲህ  በወር  አንድ  ቀን  እየመጣሁ ብታክሚኝ ምን አልባት በሂደት  የተሸረሸረው  እምነቴ  ተመልሶ  የጨለመው ተስፋዬ ታድሶ ወደቀድሞ ማንነቴ እመለስ ይሆናል›› ብሎት የእለቱን ቆይታውን አገባደደ..
.እንዳለውም ለስድስት ወር ሳባ ጋር ተመላለሰ፡፡ከዛ  ወደ  አቋሙ  ተመልሶ አገልግሎቱ ተመለሠ.. የዘጋውን የቴሌቨዠን ጣቢያ  መልሶ ከፈተ..ከዛ በኃላ ስራ ቦታዋ መቶ ባያውቅም አልፎ አልፎ እየደወለላት ይገናኙና  ያወራሉ…ልክ እንደዘመድ ይጠያየቃሉ ፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍9616🥰3
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ ፡ ፡ #ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ በማሳጅ ስም እየሰራችው ያለችው ስራ ካሰበችው በጣም ውስብስብ ፤ከግምቷ በጣም የረቀ፤ ካደገችበት ስነ-ምግባር ያፈነገጠ፤ የተለየ አይነት አለም ሚያሳይ ቢሆንም ወደ ቦርሳዋ በሚፈስላት ብር ስለሚካካስ አሜን ብለ ተቀብላው ለአመታት ሰትሰራ ነበር፡፡እንጂማ ስራ ሲያስጀምሯት ማሳጅ ቤት ብለው የሰበኳት ስብከት ፌክ መሆኑን የተረዳችው ስራ…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ እንደተገለፀው ሳባ እዚህ ስራ ውስጥ የጀመረችውም ጠልቃ ስር ድረስ የገበችውም ለአበቷ ስትል ነው…ከዛ አልፋ ሌላውን የማጥፋትና የማውደም ትግባር ላይም የተሰማራችው በአባቷ ምክንያት ነው፡፡የሚገርመው ደግሞ ያንን በወሰነችበት ጊዜ የዬኒቨርሲቲ ትምህርቷን ላለመቀጠል ወስና ነበር…. እንዴት አድርጋ ምን አይነት ስራ ሰርታ ያን የሚያህል ገንዘብ በማግኘት ልትገዛለት እንደምትች ፍፅም ፍንጭ አልነበራትም፡፡ግን ደግሞ በሙሉ እምነት ነበር ያኔ ፕላን ያደረገችው..ከዛ በአባቷና በስንዱ ጥረት ወደትምህርቷ ተመለሰች ...ተማረች  …ተመረቀች…  ስራ  ያዘች….ሶስት  አመት  በማባከን  እሷ ብዙ ጥረት አድርጋ ትምህርቷን ጨርሳ ዲግሪዋን ጭና ስራ ብትይዝም እንኳን ዘመናዊ ዊልቸር እና መኪና የምትገዛበት ገንዘብ ለማጠራቀም ይቅርና እራሷን ማኖር እራሱ እያቃታት ሲመጣና ከቤተሰቦቾ በተለይ  ሁለት  እግሮቹን  አጥቶ በአሮጌ ዊልቸር እቤት ውስጥ ከቀረ  አባቷ  የድጎማ  ብር  ሲሰጣት  ስትመለከት ተስፋ ወደመቁረጥና ከአመታት በፊት ለአባቷ ለማድረግ ወጥና የነበረው እቅድ የዕብደት ሀሳብ ወይም የልጅ እቅድ ነበር ብላ በመቀበል  ተስፋ  ለመቁረጥ በመዳደት ላይ እያለች ነበር ተአምራዊ በሆነ አጋጣሚ ከትብለጥ ጋር የተገናኘችው..ከዛ ተአምራዊ ስራ አገኘች..በስራ ሂዳቷ የፅድቅ የመሰሉ፤መቅሰፍት ላይ የሚጥሉ፤እብደት የታከለባቸው፤ወንጀል ቀመስ የሆኑ፤ከሞራል ያፈነገጡ ብቻ ውጥንቅጡ የወጣ ስራ በመሰራት በ6 መቶ ሺ ብር እጅግ ዘመና ዊልቸር ገዝታ በአባቷም ሆነ በወዳጅ ዘመድ ለአመታት ተመርቃበት ነበር....ትዝ ይላታል ተአምራዊውን የማሳጅ ስራ ከጀመረች በአንድ አመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለአባቷ ዘመናዊ ዊልቸር መግዛት የሚያስችላት ብር አግኝታ ነበረ… እርግጥ ዊልቸር ለመግዛት የሚሆናትን ብር ገና ስድስት ወር እንደሰራች ነበር  ያገኘችው  ..ግን በወቅቱ ገበያ ላይ የዋለ በኤሌክትሪክ የሚሰራ እጅግ ዘመናዊና ምቹ ሚባለውን ለመግዛት ፈለገችና ለዛ ሚሆን በቂ ብር ለማግኘት ስትል አንድ አመት መጠበቅ ግድ ሆነባት፡፡ እንደሞላለት ወዲያው ነበር ብሩን  ለካምፓኒው  ገቢ  አድርጋ መጠበቅ የጀመረችው.. .ከዛ ውጭ ባሉ  ወዳጆቾ  አማካይነት  በሁለት  ወር ኢትየጵያ ደርሶ እጇ ገባ፡፡
በህይወቷ እንደዛን ቀን በራሷ ኮርታና ፍፅም የሆነ ደስታ ተስምቷት  አያውቅም ነበር፡፡ ጨረቃ ወለል ላይ በእግሯቾ አርፋ ኮከቦቹን በእጇቸ እየዳሰሳች ምትጫወት ነበር የመሰላት፡፡
ያ ከሆነ ከሁለት አመት በኃላ በአጠቃላይ የማሳጅ ስራዋን ከጀመረች ከሶስት አመት በኃላ ደግሞ ሁለተኛዋን ህልሞን አሳካች፡፡በጣም ተደስታለች….ግን ደግሞ እየተደሰተች ያለችው በበቂ መጠን እንደሆነ እየተሰማት  አልነበረም…የገዛችው መኪና የስድስት ድፍን አመት ህልሟ እና  የሶስት አመት ተአምራዊ ጥረቷ ውጤት ነበር፡፡ይሄን  ህልም  ገና  አባቷ  ሆስፒታል  እግሮቹ  ተቆርጦ  አልጋ  ላይ ተኝቶ ስትመለከት ያሰበችው ሀሳብ ነበር‹‹ለአባቴ መልሼ እግሯቹን ልመልስለት ባልችልም ግን ደግሞ ከቦታ ቦታ  የሚንቀሳቀስበት  አንደ  ዘመናዊ  ዊልቸርና ዘመናዊ መኪና ገዛለታለሁ፡››ብላ የወሰነችው፡፡እና ከአመታት ልፋትና ትጋት በኃላ ሁለቱንም አሳካች፡፡
እጇ የገባውን ልዩና ዘመናዊ መኪና በትዕዘዝ ካስመጣች በኃላ  አዲስ  አበባ ከእንደገና ዊልቸር እንዲያስገባ  ሞዲፋይ  ተደርጎ  እስኪሰራ፤  መቀመጫው ከእንደገና ምቹና  ለማረፍ  እንዲመችም  ተደርጎ ሲስተካከል  ፤አንድ ወር ፈጀበት… ያ ሁሉ ጊዜ ዜናው ቤተሰቦቾ ጋር እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጋ ነበር፡፡
መኪናዋን ተረከበች….የደስ ደስ የሚታረድ ሁለት ሙክት በጎች ገዛችና ጫነች፡፡ ዝግጁ ሆና አደረች፡፡ከዛ እሁድ ለሊት 12 ሰዓት ላይ ነበር እራሷ እየዘወረች ወደ አሳለ ጉዞ የጀመረችው፡፡
ስትሄድ አባቷ ፊት ላይ ምታገኘውን ፈገግታ ለማየት  በመጓጓት  ነበር..ከእሱ አንደበት የሚወጣውን የምርቃት ናዳ ለመስማት ጓጉታ ነበር…አባትዬውም ብቻ ሳይሆን ስንድም በደስታ ስታለቅስና አቅፋት እየወዘወዘቻት ሰታመሰግናት እያሰበች ነበር…. ገና ሳትደርስ ልቧ ሞቆ እንባዋ እየተንጠባጠበባት ነበር ፡፡ የሰፈር
ሽማግሌዎች ሲመርቋትና የሰፈር ወላጆች የእኛስ ልጆች መቼ ነው እንዲህ እንደአንቺ የሚያስቡልን እያሉ እሷን እየመረቁ በልጆቻቸው   ቅር   ሲሰኙ… እያለመች በደስታ ስክራ ነበር፡፡ለሁለት አመት የሰራችውን   ብር አጠራቅማ ይሄው   2.5   ሚሊዬን   ብር   የገዛቻትን   ልዩ   መኪና   በህይወቷ ለሁለተኛ ጊዜ አባቷንም   ሆነ   መላውን   የትውልድ   ቀሄዋን   ኑዋሪዎች ለማስፈንጠዝ በጉዞ ላይ ነበረች፡፡

ዴራ ላይ ስትደርስ ስልኳ ጠራ..አነሳችና አየችው.ስንዱ ነች፡፡
‹ስንድ ልብን ቀጥ ለሚያደርግ ሰርፕራይዝ ተዘጋጂ፡፡ አሁን ስልኬን አንስቼ ሰርፕራይዜን አላበላሽም›› ብላ ስልኩን ሳታነሳ ነበር ወደቦታው  የመለሰችው.. ደግሞ ተደወለ….ዝም አለችው  …አስር  ደቂቃ  ቆየና  ተደገመ.አነሳችና  ሙሉ በሙሉ ዘጋችው፡፡
‹‹…ባይሆን እርቦኛል… ቁርስ ሰርተሸ ብትጠብቂኝ ደስተኛ እሆናለው›› በማለት በውስጧ አጉረመረመችና የመኪናውን ፍጥነት ጨመረች…፡፡.
አሰላ ከተማ ገብታ …ለእቤቷ ከ10 ደቂቃ በታች ነበር የቀራት… መነኸሪያውን ትንሸ አለፈ አለችና ወደሰፈሯ ወደሚወስደው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከመታጠፏ በፊት የአስፓልቱን ጠርዝ ይዛ መኪናዋን አቆመች…፡፡.
በወቅቱ ለምን እንደዛ እንዳደረገች አልገባትም ነበር….ግን  የሆነ  መግለፅ የማትችለው የተለየ ስሜት እየተሰማት ነበረ….አዎ እያፈናት ነበር…መተንፈስ አልቻለችም ነበር..ገቢናዋን ከፈተችና ወረደች….እርጥበት አዘሉን አየር ወደውስጥ በመሳብ አተነፋፈሷን ለማስተካከል ሞከረች…ወደመኪናዋ ኃላ ሄደችና ኮፈኑን ከፈተች….በጎቹ በጤና እና በንቃት ላይ እንዳሉ በማረጋገጥ መልሳ ዘጋችው፡፡

‹‹ምንድነው የሆንኩት…..?ለምንድነው ቤት ስደርስ እንዲህ ብርክ የያዘኝ? በቀጣይ የሚያጋጥመኝን ደስታ ለማጣጣም ለምን  ፈራሁ?…››በወቅቱ  እራሷን ብትጠይቅም መልስ ማግኘት አልቻለችም ነበር….ወደኃላ  ተመለሺ  ..ተመለሺ የሚል ስሜት ተፈታተናት…
.‹‹እንዴ እየቀወስኩ  ሳይሆን  አይቀርም…?››አለች…እንዲህ  ያስባላት  ትናንት መሽቶ እስኪነጋና ጥዋት ተነስታ ስትወጣ በማይለካ ጉጉት ነበር ስትከንፍ የነበረችው….አዲስአበባ ለቃ ስትወጣ   ምነው መኪናዋ  እንደፕሌን ክንፍ በኖራት አና በርሬ በደቂቃዎች ውስጥ መድረስ በቻልኩ›› ብላ እስከመመኘት ደርሳ ነበር… የዚህ አይነት ስሜት ይሰማት የጀመረው ከሀያ ደቂቃ በፊት  ጀምሮ ነበር ፤.ግን ደግሞ ያፍናት የጀመረችው አሰለ ከተማ ከገባች በኃላ ነበር..ድንገት መንገድ ስታ በሀሩር ንዳድ የተሸፈነ ጭው ያለ ሰው አልባ በረሀ ውስጥ የገባች መስሎ ነው የተሰማት.. እንደምንም እራሷን አጠነከረችና መኪናዋ ውስጥ ተመልሰ ገባች…. መሪውን ተደገፈችና 10 ደቂቃ በፀጥታ አሳለፈች…ከዛ አየር ወደውስጥ እየሳበች ወደውጭ መልሳ እየተነፈሰች ለሶስት ጊዜ ያህል ተመሳሳዩን ካደረገች  በኃላ መኪናዋን አንቀሰቀሰች..
👍548👎1😱1
ወደሰፈር እየቀረበች ስትመጣ ነጣላ የለበሱ ሴቶች ከእነሱ ሰፈር ሲወጡና ወደእዛ ሲሄዱ ተመለከተች …ብዙም ነገሬ ሳትለው ነበር ወደቤታቸው የተጠመዘዘችው.. መተረማመስና እሷ ጆሮ ድረስ የሰረገ ድምፅ ተሰማት…እግሯን ከፈሬኗ አነሳች… እጆቾ መሪውን ለቀቁና ግራና ቀኝ ጆሮዋን  ደፈነች  ….አሁን  ቀርባለች…ለቅሶው እነሱ ቤት ነው..ዱንኳን ቤታቸው በራፍ ላይ እየተተከለ ነው የሆነ
ጨለማ አዋጅ እንደታወጀ  ገባት...በጋባት  ቅጽበት  ደነዘዘች  መኪናዋ እየተንደረደረች ወደ ዱንኳኑ ቀረበች…
ሰው ግራ ገባው ..ይቆማል ብላው ቢጠብቁም እየቆመ አይደለም.. ሌላ መደነጋገር ተፈጠረ ..እየተጯጯሁ ከመኪናው መሸሸ ተጀመረ.. ቀጥታ መኪናዋ ድንኳኑን

ሰንጥቃ ገባችና አልፋ በማለፍ ፊት ለፊት  ካለ  የጎረቤት  ግንብ  አጥር  ጋር ተጋጨችና ቆመች፡፡
ሌላ ግር ግር ተፈጠረ…ደግነቱ እሷም ሆነች መኪናዋ ምንም  ጉዳት አልደረሰባቸውም ነበር…እንደምንም  ተረባርበው  በሩን  ከፈቱና  ጎትተው አወጧት… ከተወሰነ ማናፈስ በኃላ ወደ ነፍሷ ተመለሰች…አይኗን ከወዲህ ወዲያ አንከራተተችና የተፈጠረውን ለማወቅ  ሞከረች…እሷ  ካለችበት  ቅርብ  ርቀት ስንዱን አየቻት… ሁለት ሴቶች ግራና ቀኝ አጅበዋታል ..የአባቷን ፎቶ በደረቷ አንጠልጥላ ባዶ ዊልቸሩን  እየገፋች  በአምላክዬ….ቤተክርስቲያን  ልውሰድህ…ና ቁጭ በል፤ልጅህ መጥታለች…በአምላክዬ ምን አጠፋሁ….?በአምላክዬ ምን አስከፋሁህ?እያለች አንጀት በሚበላ እንጉርጉሮ ሙሾ ትወርድ ነበር፡፡
….በቃ ሳባ .. ከዛ በኃላ አታስታውስም…መልሳ እራሷን ሳተች፡፡አፋፍሰው ሀኪም ቤት ወሰዷት….በእሷ ምክንያት የአባቷ ቀብር በአንድ ቀን ተራዘመ…..
ከዛ ውስጧ በጣም ተጎዳ…እስከ አርባው ድረስ እንደደነዘዘች ቢሆንም እዛው አሰላ ቀየች….የአባቷን ለአንድ ቀን እንኳን ታሟል ተብሎ  ሳይነገራት  ድንገት  ሞት መባሉን ፈጽሞ ሊዋጥለት አልቻለም፡፡እሷ ብቻ ሳትሆን ስንዱን ጨምሮ ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ነበር ግራ የተጋባው፡፡
ልዩነቱ ሌሎቹ የሆነው ሁሉ በእግዜያብሄር ፍቃድ ነው ብለው አምነው ህይወታቸውን ለመቀጠል ጥረት ማድረግ ቢጀምሩም ሳባ ግን ፈፅሞ ሊዋጥላት አልቻለም፡፡አዲስአባ በመሄድ ነገሮችን መስመር አስይዛ ስራዋንም ለቃ  ሙሉ በሙሉ ጠቅልላ ወደ አሰላ በመመለስ አባቷ ጥሎላላ የሄዳቸውን ቤተሰቦቾን ለመንከባከብ እቅድ አወጣች…አዎ ስራው እረብጣ ብር የሚያስታቅፋት ቢሆንም ከአባቷ ሞት በኃላ ግን ረብጣ ብር እንደማያስፈልጋት እርግጠኛ ነበረች….የአባቷን ሞት ተከትሎ ተስፋዋ ሟሾ፤ነገዋ ደርቆ ነበር...ያንን ወስና ሻንጣዋን ሸክፋ

ለአባቷ ይዛት የመጣችውን መኪና መልሳ አዘጋጅታ   በመጨረሰ   ለመጨረሻ ስንብት አባቷ መኝታ ቤት ገባችና ከውስጥ ቆልፋ የአባቷን ዕቃዎች መፈተሻ ጀመረች…
የኮመዲኖውን መሳቢያዎች ሁሉ ከፈተች …ውስጥ ያሉትን ወረቀቶችና ሰነዶችን እያገላበጠች ነበር መፈታተሸ ጀመረች…ምን እንደምትፈልግ እራሷም አታውቅም
፤በወቅቱ እንዲያ ስታደርግ አንድ ሰው ተደብቆ ቢያያት የሆነ የውርስ ጉዳዬች አሳስቧት ሰነዶችን በመፈተሸ በጥንቃቄ ለማስቀመጥ ወይም ቀድማ ለማሸሽ ጥረት ላይ ነች ብሎ ቢያስብ  ትክክል  ነበር  ሚመስለው….ለእሷ  ግን  የንብረት ጉዳይ በአእምሮዋ አልነበረም….በእሷ አእምሮ የተጠቀጠቀው‹‹አባቴ ለምን ሞተ? አንዴት ሞተ?››የሚለው ጥያቄ ነበር፡፡.ለዛ ፍንጭ ሚሰጠ ነገር ነበር የምትፈልገው..ድንገት በካኪ ፖስታ የተጠቀለለ ነገር አገኘች…ከወረቀቶቹ መካከል መዛ አወጣችና በተነችው….መአት  ፎቶዎች  ተዘረገፉና  ወለሉን  ሞሉት  …፡፡ አይኖቾ ላይ ብዙ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ቀለማቶች ቦግ ብልጭ ይልባት ጀመር..አንዱን አነሳችው ወደአይኖቾ አስጠጋችው….ሌላውን አነሳችው… አየችው..ሁሉንም እያፈራረቀች አየቻቸው…..፡፡
ጠቅላላ የእሷ ፎቶ ነበር…..ስራ  ላይ  እያለች  የተነሳችው…..የተለያዩ  ወንዶችን ማሳጅ  ስታደርግ  …እርቃኗን  ሆና እርቃን ካለ  ሰው  ጋር ስትሳሳም….ባዶ  ወለል ላይ ከወንድ እርቃን ተቆላልፋ ስትዋሰብ…እጇን ግራና ቀኝ በሰንሰለት  ታስራ ግድግዳ ላይ ተሰትራ ስትጋረፍ…ሙሉ  የስራ  ሪፖርቷን  በፎቶ  ሲቀርብ  ማለት ነው… .ከፎቶዎቹ ውስጥ አንዱ ፎቶ ብቻ ነው የሚለየው.አዎ ሰርፕራይዝ ብላ በምስጢር ደብቃ ይዛ እየነዳች የመጣቻት ለአባቷ የገዛቻትን መኪና ፎቶ ተቃላቅሎበታል፡፡ የሁሉም ወንዶች ፎቶ ፊታቸው እንዳይታይ በቀለም እንዲጠፋ ተደርጎል፡፡ የእሷ ግን በጥራት ይታያል…የቀረ ነገር እንዳለ  ብላ  ካኪ  ፖስታውን መልሳ አነሳችውና ውስጡን ፈተሸች… አንድ ወረቀት ውስጡ አለ..አነሳችው...

በኮምፒተር የተፃፈ መልእክት አለው… በሚንቀጠቀጥ እጆቾ ይዛ በሚርገበገቡ አይኖቾ ማንበብ ጀመረች፡፡

የሳባ አባት  እንዴት  ኖት..  ማንነቴን  በግልፅ  ልነግሮት  አልችልም…ግን  ልጇት ሳባን በጣም ከሚወዷትና ከሚያስብሏት ጓደኖቾ መሀከል አንዷ ነኝ፡፡ይሄንን ማደርገው እሷን ላሳጣ ወይንም እርሶን ላሳዝኖት ፈልጌ ሳይሆን የእሷን የወደፊት ህይወት ለማስተካከል የሚችሉ እርሶ ብቻ ስለሆኑ እየሆነ ያለውን ነገር በትክክል አውቀው የልጆትን ህይወት እንዲያስተካክሉ ብዬ ነው፡፡እርግጥ ልጇት ስራዋ ሆስተስነት  እንደሆነ  እንደነገረቾት  አውቃለሁ…ግን  የልጆት  ትክክለኛ  ስራ በፎቶው ያዩት ነው፡፡ያንን ያደረገችው ግን ለእርሶ ብላ ነው..ለአመታት ይሄን ስራ ሰርታ ባጠራቀመችው ብር ይሄንን  ፎቶውን  የላኩሎትን  መኪና  ለእርሷ  ብላ ገዝታ ሰሞኑን ይዛሎት ልትመጣ እየተዘጋጀች ነው፡፡ ከዚህ  በፊትም የሚጠቀሙበትን ዊልቸር ለመግዛትም ከአመት በላይ ይሄንን ስራ ሰርታለች...ወደፊት ደግሞ እቤቷትን አፍርሶ አዲስ ቤት ለመገንባት ሁለት ሶስት አመት ለመስራት እቅድ አላት። እንግዲህ በዚህን ጊዜ እስከአሁን እድለኛ እንደሆነችው እድለኛ ሆና መቀጠል ላትችል ትችላለች። በፎቶው ላይ ከእሷ ጋር ያዬቸው ሰዎች ገንዘብ ያላቸው  ቢሆንም  እጅግ  አደገኛ  ወንጀለኞች፤  ነፍሰ ገዳዬችና ማፍያዎች ናቸው።እናም እርሶ እንደምንም ብለው ከዚህ ስራ በፍጥነት እንድትወጣ ካላደረጉ ያጧታል።ይበሉ... ይሄንን ደብዳቤም ሆነ ፎቶ እሷ ባታየው ደስ ይለኛል።እንደውም ካዩት በኃላ ለማንም ስለማይጠቅም ቢያቃጥሉት  ጥሩ ነው፡፡
ይልና ያቆማል።
ሳባ ከዛን ቅፅበት በኃላ ነበር ሌላ ሴት ከውስጧ የበቀለችው....በመጀመሪያ  እራሷን ጠላች...ከዛ በኃላ ሰው የሚባል ፍጡር ሁሉ ተጠየፈች ።አይ እንደውም እንደዛ አይደለም የሰውነት ትርጉም ነበር የተቀየረባት...ሰው ክብር ፣ቅድስና

የእግዚያብሄርን እስትንፋስ የተሸከመ ፍጡር ነው ብሎ ልጅ እያለች  አባቷ አቅፎ     ጭንቅላቷን    እያሻሸች    ይነግራት    የነበረውን    ነገር  የተሳሳተ እንደሆነ ድምዳሜ ላይ ደረሰች...ሰው አስጠሊታ፤ጭራቃዊ ነፍስ ያለው
፤በተገኘበት ተጨፍልቆ እየተገደለ ሙሉ በሙሉ ከምድረ ገፅ  መሰረዝ  ያለበት ፍጡር ነው›› ብላ አመነች።ፎቶዎቹንም ሆነ ደብዳቤውን ሰብስባ ወደ ቦታቸው መለሰች፡፡ ሌሎች ሰነዶችን ወደቦታቸው መለሰችና ከኪ ፖስታው ይዛ  ወጣች፡፡  መኪናዋ   ውስጥ የጫነችው ቦርሳዋ ውስጥ ከተተች።
👍537🔥1
​​እንዳቀደችው ወንድሟንና የእንጀራ እናቷን ስንድን ተሰናብታ አሰላ በመጣች በ43 ተኛ ቀኗ ነበር ኩንታል ሙሉ በቀል አርግዛ በእልክ ወደአዲስ አበባ የተመለሰችው
።አዎ ያንን ደብዳቤና ፎቶዎች ካየች በኃላ ስራ ለቆ ሙሉ በሙሉ ወደአሰላ መመለስ እንደሌባት ወዲያው ነበር የወሰነችው።ስራዋ ላይ መቆየት እንዳለባት ደመደመች።ያንን ፎቶና ደብዳቤ ለአባቷ ማን እንደላከና እንዲህ እንዳወደማት የምታውቀው ስራዎ ላይ ስትሆን ነው.. እንዳፈረሷትና ህይወቷን እንደቀሟት ህይወታቸውን መቀማትና መበቀል የምትችለው ስራዋ ላይ ስትቆይ ነው።አዎ ስራዎን ከመቼውም  በላይ  ያስፈልጋታል።ከቀድሞ  የተለየ  ታላቅ  ተልእኮ  እና አላማ ነበራት።  እርግጥ  ይሄንን  ያደርጋሉ  ብላ  የምትጠራጠራቸው  ሶስት የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በአእምሮዋ ነበሩ።ግን ማረጋገጥ ነበረባት...ከዛ ሰውዬውን ታወድመዋለች ከዛ ደግሞ ያንን ማሳጅ ቤትም ሙሉ በሙሉ ታከስመዎለች።አዎ እንዲህ ያደረገው ማንም ይሁን ማንም ፎቶዎችን የወሰደው ከድርጅቱ በጣም ሚስጥራዊ ከሆነው አርካኢብ ነው።ለዛ ስህተታቸው ደግም ትብለጥም ሆነች ድርጅቶ መክፈል አለባቸው።
አዲስአበባ እንደደረሰች አፓርታማ ተከራየችና ለሦስት አመት ከኖረችበት ትብለጥ ከሰጠቻት ቤት ለቀቀች።ከዛ ሀዘኗን በውስጧ ዋጥ አድርጋ ወገቧን ጠበቅ በማድረግ ወደስራዋ ተመለሰች...እከሌ ከእከሌ ሳትል ለሁሉም ከበፊቱ ያልተቀየረ ፊት

ለማሳየት ከአንጀቷ ጣረች ግን ውስጥ ለውስጥ  ማድባቷን  ቀጠለች  ...  ለአባቷ ሞት ምክንያት የሆነውና እሷንም እንድትከስም የዳረጋት ሰው ላማወቅ ለፋች።ይሄንን በእርግጠኝነት ለማወቅ አመት ፈጀባት....እንደዛ ያደረገችው ፈትና ወደስራው ያስገባቻት ሰገን መሆኗን አረጋገጠች...ምክንያቷ ቅናት ነው ከእሷ
በተሻለ ውብ አማላይና ትኩረት የምትስብ በዛ ላይ ውጤታማ እየሆነች ስትመጣ በውስጧ በበቀለባት የመበለጥ ስጋት ነው።እና እድሉን ስታገኝ ተጠቀመችበት፡፡ግን ለዛ አረንጓዴ ካርድ በማሳየት ፍቃዱን የሰጠቻት ትብለጥ መሆኗን  ተረዳች… እርግጥ እዚህ ላይ የእሷም ጥፋት እንደነበረበት እትክድም ፤50 ሚሊዬን ብር እንዲያጡ በማድረግ አበሳጭታቸዋለች..ቢሆንም ነገሩ እዛ ድረስ ሄዶ ያባቷን ህይወት ያሳጣል የሚል ግምት አልነበራትም።
ሳባ ያልተረዳችው ግን ሰገንም ያንን ደብዳቤና ፎቶችን አሰላ ድረስ ለአባትዬው ስትልክ ያሰበችው በጥቂት መስዋዕትነት   የምትፈልገውን   ውጤት   ማግኘት መሆኑን ነው።ሰገን የመሠላት   አባትዬው   ፎቶውና   ደብዳቤው   እንደደረሳቸው ትንሽ አዝነው የተወሰነ ተበሳጭተው ልጃቸውን ሙሉ   በሙሉ   ከስራዋ በማስወጣት ከአዲስአበባ እንድትለቅ አድርገው ወደአሰላ ይመልሷታል ብላ ነበር ስሌቱን የሠራችው። ግን ያላሰበችው ሆነና ሁሉ ነገር ከእጇ አመለጠ ፡፡ከሁሉ የሚያበሳጨው ደግሞ ሳባ   ጭራሽ ኮስታራ ሆና   ከበፊቱ በተለየ ትኩረት እና ትጋት ስራውን መቀጠሏ ነው።
ሳባ የተሰራባትን ግፍ በእርግጠኝነት ከተረዳች በኋላ በቀሏን ልትመልስ ዕቅድ ነደፈች...ቅደም ተከተል አወጣች…መጀመሪያ ሰገንን ለማስወገድ…ከዛ ወዳ ዋናዋ ለመሸጋገር፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍756