አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ግን ቅንጣት ታህል የማስታወስ ምልክት, በፊቱ ላይ አልነበረም ። ፊቱ በውበቷ የተሰማውን አድናቆት ብቻ ነበር የሚገልጸው ። እንዲያ ባድናቆት እንደተሞላ እጁን ሰደድ አድርጐ ፍሬድን ለማጫወት ሞከረ ።

« ታዲያስ ፤ አያ ትንሽ ነገር » አለ ቤን ውሻውን ሊያጫውት የሚሞክር እየመሰለ ። ድምጹን ስትሰማ ሁሉ ነገር ታወሳት ። እና ደርሶ መንፈሷ ተሸበረ ። ደከመች ። አልወደቀችም ። እንዲያውም ውሻውን ለመዳበስ የተሰነዘረው የቤን አቭሪ እጅ ሙቀት እየተሰማት ከተቀመጠችበት ተነሳች ። ሁኔታው ሁሉ ገረማት ። ቤን አቭሪን ስላየች ብቻ ይህ ዓይነት የስሜት ዝብርቅርቅ እንደሚሰማት ገምታ አታውቅም ነበር ። ግን ደግሞ አይፈረድባትም ። ማይክልንና እሷን በቀጥታ የሚያገናኝ ሁኔታ ሲያጋጥማት ይህ
የመጀመሪያው መሆኑ ነው ። ከዚያ ዕንባ ተናነቃት ። ቤንን ቀና ብላ ማየት አልቻለችም ። ስለዚህም ሲመለከተው የነበረውን ሻንጣ አየች ። እጅዋ ወዳንገቷ ሄደና ያኔ ለሙሽርነቷ ቤን ያዋሳትን የወርቅ ሀብል ዳበሰ ። ካንገቷ አውልቃው አታውቅም ከተሻላት ጊዜ ጀምሮ ። « የገና ስጦታ በመግዛት ላይ ነህ መሰለኝ » አለችው ። « አዎ ላንዲት ወጣት እመቤት ከጦታ ለመግዛት አስቤ የቱን እንደምገዛ መወሰን አቃተኝ »
« ምን ዓይነት ናት እመቤቲቱ ?»
« እሳት! እሳተ ነበልባል ናት።». ሜሪ በቤን መልስ ሳቀች ። ቤን ምን ጊዜም ቤን ነው። መልሱ አጭርና ቀልድ የተሞላ ነው ። አሁንስ እንዴት ነው እመቤቲቱ ቋሚ ናቸው ? ልትለው አስባ ነበር ። ግን የማይሞከር ነገር ማሰቧ ወዲያው ገባት። ጸጉሯ ቀያቴ ሲሆን ፤ ቁመቷ እንዲህ አንቺን ታህላለች አለ ቤን። .

ይህን ብሎ ሜሪን ከላይ እስከታች በተጠሙ ዓይኖቹ ጠጣት። ይህን ሲያደርግ ስሜቷ ተደበላለቀባት ። ስለተመኛት ። እና ግንኙነታቸውን ስታስብ መናደድ አማራት ። ስላላወቃትና ቤን ሴት ካየ መጎምዥት ልማዱ መሆኑን ስታስብ ልትስቅበት አማራት ። « ግን ሻንጣ ፤ ቅራቅንቦ የሚያስፈልጋት መሆኑን ርግጠኛ ነህ » አለች። « ይመስለኛል ። ወደ አንድ ቦታ እንድንሄድ አስቤአለሁ። ሳታስበው እንዲሆን ስለምፈልግ ፤ ቲኬቱን እሻንጣ ውስጥ ከትቼ ላስገርማት ብዬ ነው» አለ ። አንድ ትኬት ደብቆ ለመስጠት አምስት መቶ ዶላር መክፈል ይገባል ቤን ? ቤን አቭሪ እንዲህ ገንዘብ በታኝ ሆነ ?

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍9
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ደስ ደስ ብሏታል፡ ከእውነተኛ ሌባ ጋር መወዳጀቷን ማመን
እያቃታት ነው፡ አንድ ሰው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት አታምነውም፡ ነገር ግን
ሄሪ አንድ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ተከሶ ስላየችው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት እውነቱን መሆኑን አወቀች።

ከስርዓት ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ማለትም ወንጀለኞች ለህግና ለመንግስት የማይገዙ ሰዎች፣ ሴተኛ አዳሪዎችና በረንዳ አዳሪዎች ሁልጊዜ
ያስደንቋታል፡ እነሱ ነጻ ሰዎች ናቸው፡፡ በእርግጥ በህብረተሰቡ የተተፋ ሰው
ጥሩ ነው የሚል አመለካከት የላትም፡፡ ነገር ግን እንደ ሄሪ ያሉ ሰዎች አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ለማድረግ አይፈቅዱም፡ይህ ነጻነታቸው ነው ማርጋሬትን የሚያስቀናት፡፡ አንዳንዴ የወታደር ልብስ ለብሶ ጠመንጃውን ታጥቆ በየመንደሩ እየዞረ ህዝብ የሚዘርፍ ሽፍታ መሆን ያምራታል እንደዚህ አይነት ሰዎች ገጥመዋት አያውቁም: አንድ ጊዜ በለንደን ጎዳናዎች
ላይ ሴተኛ አዳሪ መስላቸው ሊደፍሯት የመጡትን ሰዎች ባታይ የምታውቅበት ሁኔታ አልነበረም፡፡

ሄሪ እሷ የምትመኘውን ነገር ሁሉ ያሟላ ሆኖ ነው ያገኘችው የፈለገውን ማድረግ የሚችል ሰው! ዛሬ ጧት አሜሪካ ለመሄድ ወሰነና ዛሬ ከሰዓት በኋላ አይሮፕላኑ ላይ ተገኘ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ መደነስና ቀኑን በሙሉ መጋደም ከፈለገ ያደርገዋል፡ ከልካይ የለበትም፡፡ መብላት የፈለገውን ይበላል፧ መጠጣት የፈለገውን ይጠጣል፡ ገንዘብ ከፈለገ ገንዘባቸውን መጣያ
ካጡ ባለጸጎች ይሰርቃል፡ እሱ ነጻ የሆነ ሰው ነው፡
ስለሄሪ በይበልጥ ማወቅ ፈለገች፡ ከእሱ ጋር ራት ሳትበላ ያሳለፈቻቸው
ቀናት ቁጭት ውስጥ ጣሏት፡፡

ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ከኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ቀጥሎ ተቀምጠዋል እነዚህ ሰዎች ይሁዲ ስለሆኑ ነው ገና ወደ መብል ክፍሉ እንደገቡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ክፉኛ የገላመጧቸው፡አብረዋቸው
የተቀመጡት ኦሊስ ፊልድና ፍራንክ ጎርደን ናቸው፡፡ ፍራንክ ጎርደን በዕድሜ
hሄሪ ብዙም የማይበልጥ መልከ መልካም ወጣት ነው፡፡ ኦሊስ ፊልድ ደግሞ
ኑሮ የጠመመበት የመሰለ በዕድሜ ገፋ ያለ ራሰ በራ ሰው ነው፡፡

ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ሁሉም ሰው ከአይሮፕላኑ ወጥቶ
በየፊናው ሲበታተን እነዚህ ሁለት ሰዎች አይሮፕላኑ ውስጥ በመቅረታቸው
የለው ሁሉ መነጋገሪያ ሆነው ነበር፡፡

ሶስተኛው የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ሉሉ ቤልና ሾርባው ጨው የበዛበት ነው እያሉ ሲያማርሩ የዋሉት ልዕልት ላቪኒያ ተቀምጠዋል ከነሱ ጋር ፎየንስ ላይ የተሳፈሩት ሚስተር ላቭሴይና ሚስስ ሌኔሃን ተቀምጠዋል። ወሬ መለቃቀም የሚወደው ፔርሲ እነዚህ ሰዎች ባልና ሚስት ባይሆኑም የሙሽሮቹን ክፍል እንደሚጋሩ ወሬ ለጠማቸው አውርቷል
ባልና ሚስት ያልሆኑ ሰዎች ይህን ክፍል እንዲይዙ ፓን አሜሪካን አየር
መንገድ እንዴት እንደፈቀደላቸው ማርጋሬት ገርሟታል። አየር መንገዱ ብዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ መሄድ ስለፈለጉ ህጉን መጋፋት የግድ ሆኖበታል፡

ፔርሲ ጥቁር የይሁዲዎች ኮፊያ አናቱ ላይ ደፍቷል፡ ማርጋሬት ይህን ስታይ በሳቅ ተንፈቀፈቀች፡፡ ከየት ነው ያመጣው! አባቱ ግን ‹‹ጅል!›› ብለው ተሳድበው ኮፍያውን መንጭቀው ወረወሩት፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ኤልሳቤት ተለይታቸው ከሄደች ወዲህ ለመጀመሪያ
ጊዜ ፊታቸው በመጠኑ ፈካ ብሏል፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ‹‹የራት ሰዓታችን ገና ነው›› አሉ፡፡
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ ‹‹አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል እኮ›› አሉ፡፡
‹‹ለምንድነው ታዲያ ያልጨለመው?››
‹‹እንግሊዝ አገር አሁን ጨለማ ነው፡ አሁን ግን ከአየርላንድ ባህር
ጠረፍ ሶስት መቶ ማይል ርቀት ላይ ነው የምንገኘው ጸሃይዋን እያሳደድን
ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

‹‹መቼም መጨለሙ አይቀርም››
‹‹ምናልባት ሶስት ሰዓት ላይ የሚጨልም ይመስለኛል›› አለ ፔርሲ
‹‹ጥሩ›› አሉ እናት፡፡
እንደማይጨልም
‹‹ጸሃይዋን ተከትለን በፍጥነት ብንጓዝ
እንደማይጨልም ታውቃላችሁ? አለ ፔርሲ፡፡

‹‹እንደዚህ አይነት ፍጥነት ያለው አይሮፕላን የሰው ልጅ ይሰራል ብዬ አልገምትም›› አሉ አባት ከኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል ግብዝነት፡
ቦትውድ ካናዳ ለመድረስ አስራ ስድስት ሰዓት ተኩል ይፈጃል›› አለ ፔርሲ ‹‹እዚያ በግሪንዊች ሰዓት አቆጣጠር ከጧቱ ሶስት ሰአት እንደርሳለን››
‹‹ካናዳ ስንት ሰዓት ይሆናል ማለት ነው?,,
‹‹የኒውፋንድላንድ ካናዳ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች የሰዓት አቆጣጠር ሶስት ሰዓት ወደ ኋላ ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

እናት የፔርሲን ችሎታ አጤኑና ‹‹ወንዶች የቴክኒክ እውቀት ላይ ጎበዞች ናቸው›› አሉ፡፡

ማርጋሬት በእናቷ አነጋገር ተናደደች፡፡ እናት የቴክኒክ ነገሮች ሴቶች አይገባቸውም ብለው ያምናሉ፡፡ ‹‹ወንዶች ሴቶች ጎበዝ ሲሆኑ አይወዱም››
ብለዋታል ብዙ ጊዜ፡ በዚህ ጉዳይ ማርጋሬት ከእናቷ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት ባትፈልግም እሷ ግን አታምንበትም፡ ይህን የሚቀበሉ ወንዶች ደደቦች ናቸው ብላ ነው የምትገምተው ጎበዝ ወንድ ጎበዝ ሴት ይወዳል፡

አጠገባቸው ካለው ጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጡት ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ክርክር ገጥመዋል አጠገባቸው ያሉት የጠረጴዛ ተጋሪዎች
ባይገባቸውም በጸጥታ ያዳምጣሉ: ሁለቱ ሰዎች አይሮፕላኑ ላይ ከወጡ
ጀምሮ ጥልቅ ውይይት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ በዓለም ከታወቀ ሳይንቲስት
ጋር እንደዚህ ያለውን ውይይት የምታደርጉ ከሆነ ውይይቱ ጥብቅ መሆኑ
አያስደንቅም፡፡ በክርክራቸው ውስጥ ፍልስጤምንና እስራኤልን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡ ማርጋሬት የውይይት ርዕሳቸውን ስትሰማ
‹‹አባባ ምን ይል
ይሆን?›› እያለች አስሬ ታያቸዋለች፡፡ እሳቸውም የሁለቱ ሰዎች ውይይት
አልጥም ብሏቸው አኩርፈዋል፡፡ አባቷ ነገር እንዳይጭሩ ርዕስ ለማስለወጥ
‹‹አይሮፕላኑ የሚጓዘው ኃይለኛ ነፋስ በቀላቀለ ዝናብ ውስጥ ነው›› አለች
‹‹እንዴት አወቅሽ?›› አለ ፔርሲ አነጋገሩ ቅናት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በበረራ መረጃ ከማርጋሬት ይልቅ እሱ ነው ኤክስፐርቱ።
‹‹ሄሪ ነገረኝ››
‹‹እሱ እንዴት ያውቃል?››
‹‹እሱ ዛሬ ራት የበላው ከበረራ መሃንዲሱና ከናቪጌተሩ ጋር ነው፡››
ማርጋሬት ዝናቡ ችግር ይፈጥራል ብላ አልገመተችም፡፡ በእርግጥ
በዝናብ ውስጥ መጓዝ ምቾት ቢነሳም ለክፉ አይሰጥም፡፡

ሎርድ ኦክሰንፎርድ ብርጭቋቸው ውስጥ የቀረውን ቪኖ አጋቡና ሌላ
እንዲጨመርላቸው ቆጣ ብለው ጠየቁ፡፡ ዝናቡ ችግር ያመጣል ብለው ፈሩ
እንዴ? ከተለመደው በላይ እየጠጡ መሆናቸውን ማርጋሬት ተገንዝባለች።
ፊታቸው ከመጠጥ ብዛት ፍም መስሏል: ዓይናቸው ፈጧል፡ ምናልባትም
ነርቭ ሆነዋል፡፡በኤልሳቤት መኮብለል ክፉኛ ተበሳጭተዋል
እናትም ማርጋሬትን ‹‹ሚስተር መምበሪን አጫውቺው›› አሏት፡
ማርጋሬት የእናቷ አባባል ገርሟት ‹‹ለምን?›› ስትል ጠየቀች፡ ሲያዩት
ሰው እንዲያናግረው የሚፈልግ አይመስልም፡

‹‹ምናልባትም አይናፋር ሳይሆን አይቀርም›› አሉ እናት፡፡

እማማ ከመቼ ወዲህ ነው ለአይናፋሮች መቆርቆር የጀመረችው?የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ‹‹ግን ምን ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀች ማርጋሬት።
👍13🔥1
‹‹አሜሪካ እስክንደርስ ከዚያ ቫንዴርፖስት ከተባለ ወጠጤ ተጣብቀሽ መዋልሽን አልወደድኩትም›› ሲሉ እናት የሆዳቸውን አፈረጡላት፡

‹‹ለምን እማማ?››
እሱ እኩያሽ ስለሆነ የምትሰጪው ሃሳብ አይኖርሽም››
‹‹ብዙ የምሰጠው ሃሳብ አለኝ፡፡ እሱ መልከ መልካምና ዓይናፋር ልጅ
ነው፡››

‹‹አይሆንም የኔ ማር›› አሉ እናት ፈርጠም ብለው፡፡ ‹‹ደህና ሰው እንዳልሆነ ዓይነ ውሀው ያስታውቃል፡፡ ቀልቤ አልወደደውም:››

እናት ሄሪ የደህና ቤተሰብ ልጅ አይደለም እያሉ ነው፡ ባዶ እጁን መጥቶ ከባላባት ዘር መጋባት የሚፈልግ ሰው ነው› ብለው ገምተዋል። በዚህ በኩል እናት ከእንግሊዞች የበለጠ ደሃ ይንቃሉ፡፡

ሄሪ ሀብታም አሜሪካዊ ወጣት ለመምሰል የሚያደርገው ጥረት
አልተዋጠላቸውም፡ ምኑም አይመስልም፡፡ እሳቸውን መሸወድ አይችልም፡፡
ማን ምን እንደሆነ ያውቃሉ፡

‹‹ፊላዴልፊያ የሚኖሩትን የቫንዴርፖስት ቤተሰቦችን አውቃቸዋለሁ ነው ያልሽው?››

‹‹አዎ አውቃቸዋለሁ ይህ ሰው ግን የእዚያ ቤተሰብ አባል እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ›› አሉ እናት፡፡

‹‹እማማ ይሄ ሰው መናቅ ነው››

‹‹ይሄ ንቀት አይደለም የኔ ማር፡ የዘር ጉዳይ ነው፡፡ ንቀት እኮ ብልግና
ነው:››

ማርጋሬት ከእናቷ ጋር የምታደርገውን ክርክር አቆመች፡ የእናቷ የጌታ
ዘር እምነት አባዜ እንዲህ በቀላሉ የሚናድ እንዳልሆነ ገባት፡፡ hእሳቸው ጋር ከዚህ በላይ መነታረኩ ፍሬ እንደሌለው ተገንዝባለች፡፡ ቢሆንም ያሉትን
አልተቀበለችም፡፡ ሄሪ ልቧን ገዝቶታል፡

ፔርሲም ‹‹ሚስተር መምበሪ ስራው ምን ይሆን? የለበሳትን ቀይ
ሰደርያውን ወድጄለታለሁ፡ መደበኛ የአትላንቲክ አቋራጭ ተጓዥ አይመስልም›› አለ፡

እናትም ቀበል አደረጉና ‹‹አንድ የመንግስት ኃላፊነት የተሰጠው ሰው ይመስላል›› አሉ፡፡

ማርጋሬትም ‹‹ሳይሆን አይቀርም›› አለች፡ እናታችን እንደዚህ አይነት
ነገር ዓይኗ አይስትም› ስትል አሰበች::

አባትም ‹‹ምናልባት የአየር መንገዱ ሰራተኛ ይሆናል›› አሉ።
አስተናጋጁ ዋናውን ምግብ አመጣላቸው። እናትም የመጣውን የተቀቀለ ስጋ አይተው ‹‹እኔ የተቀቀለ ነገር አልበላም›› አሉት ኒኪን ‹‹አትክልት አምጣልኝ፡፡››

በሚቀጥለው ቦታ ላይ የተቀመጡት ባሮን ጋቦን ‹‹የራሳችን የሆነ አገር
ሊኖረን ይገባል፤ ሌላ መፍትሄ የለውም›› አሉ፡

ካርል ሃርትማንም ‹‹ከሆነም ወታደራዊ መንግስት ይሁን እያልክ ነው›› አሉ።

‹‹አዎ ይህን ያልኩት ከጠብ አጫሪ ጎረቤት አገሮች የሚመጣ ጥቃትን
መከላከል እንዲቻል ነው›› አሉ ጋቦን፡፡

‹‹ለእስራኤላውያን ጥቅም ሲል በአረቦች ላይ መድልዎ የሚያደርግ
መንግስት ማለትህ እኮ ነው፡ ይሄ ደግሞ ወታደራዊ መንግስት ከዘረኝነት ጋ ከተዋሃደ ደግሞ ፋሺዝም ይሆናል፡ አሁን እየተዋጋኸው ያለኸው ደግሞ ፋሺዝምን ነው፡››

‹‹ቀስ ብለህ ተናገር ሰው ይሰማል›› አሉ ጋቦን፡፡

ሌላ ቦታ ቢሆን እንደዚህ ያለ ውይይት ማርጋሬት ይጥማታል ከዚ ቀደም ከቦይፍሬንዷ ኢያን ጋር ተወያይታለች፡፡ የሶሻሊስት ፍልስፍና አራማጆች በፍልስጤም ጉዳይ ተከፋፍለዋል፡፡ አንዳንዶቹ ፍልስጤም ለዓለም
ምሳሌ ሊሆን የሚችል መንግስት ሊሆን ይችላል ብለው የሚያስቡም አሉ።ሌሎቹ ደግሞ አንዴ አረቦች የሚኖሩበት አገር በመሆኑ ለይሁዳውያን መሰጠት የለበትም፤ ይሁዳውያን ፍልስጤም አገራቸው እንዳልሆነ ማሰብ አለባቸው ይላሉ፡፡ ታዲያ ብዙዎቹ ሶሻሊስቶች ይሁዲዎች ስለሆኑ ነገሩን
ያወሳስቡታል፡፡

ማርጋሬት አሁን እነዚህ ሰዎች አባባ እንዳይሰማ ስለፍልስጤም
የሚያደርጉትን ክርክር ቢያቆሙ ምናለ ስትል አሰበች። እነዚህ ሰዎች ግን ይህን ርዕስ የሚተዉት አይመስልም፡፡ ከልባቸው ነው የሚወያዩት፡፡

‹‹እኔ ግን በዘረኝነት አገር ውስጥ መኖር አልሻም›› አሉ ሃርትማን
ድምጻቸውን ከፍ አድርገው:

አባትም ጮክ ብለው ‹‹ከይሁዲ መንጋ ጋር እንደምሄድ አላወቅሁም
ነበር›› አሉ፡

ማርጋሬት በአባቷ አነጋገር ክፉኛ አዘነች፡፡ አንዳንድ ጊዜ የፖለቲካ ፍልስፍናቸው ስሜት የሚሰጣት ጊዜ ነበር፡፡ በርካታ ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎች ስራ አጥተው ሲራቡ ሲያዩ ደፍረው ካፒታሊዝምም ሶሻሊዝምም የፈየዱት ነገር የለም፡ ዲሞክራሲም ለተራው ሰው ያመጣለት ነገር የለም ይላሉ፡
በኢንዱስትሪ የበለጸገች አገርን የሚመሰርት ጠንካራ አምባገነን መሪ መመኘት በራሱ አንድ ነገር ነው፡ ከዚህ ቀደም አባቷ ያራምዷቸው የነበሩት
እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦች ዛሬ ወደ ትርጉም የለሽ ግብዝነት ዘቅጠዋል።

እነዚህ ሁለት ይሁዳውያን ያባቷን አጥንት የሚሰብር ስድብ የሰሙ አይመስልም፡፡ አባቷ አባቷ ለሰዎቹ ጀርባቸውን ስለሰጧቸውና
በክርክራቸው ስለተዋጡ ምን እንዳሉ እንኳን አላወቁም፡ ማርጋሬት አባቷ
የተቆጡበትን ርዕስ ለማስለወጥ ‹‹ብስንት ሰዓት ነው የምንተኛው?›› ስትል
ጠየቀች፡፡

እኔ ቶሎ ነው የምተኛው›› አለ ፔርሲ፡ እሱ ለወትሮው በጊዜ ተኝቶ አያውቅም፡፡ ነገር ግን አይሮፕላን ላይ መተኛት ምን እንደሚመስል ለማወቅ ጓግቷል።

‹‹በተለመደው ሰዓት ነው የምተኛው›› አሉ እናት፡
‹‹በየትኛው የጊዜ ቀመር?›› ሲል ጠየቀ ፔርሲ ‹‹በግሪንዊች ወይስ
በኒውፋውንድላንድ?››

‹‹አሜሪካ ዘረኛ አገር ናት›› አሉ ባሮን ጋቦን ‹‹ፈረንሳይም፣እንግሊዝም፣ ሶቭየት ህብረትም እንዲሁ››

አባትም ይህን ሲሰሙ ‹‹እባካችሁ ስለእግዚአብሔር ብላችሁ እናንተ ሰዎች!›› አሉ።

"ያንተ ተራ ነው አባባ አለ ፔርሲ"

ፔርሲ፡አባት ዝምታ መረጡ፡፡ እነ ማርጋሬት ልጆች ሳሉ አባት ከልጆቹ ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አሁን ግን ደስታ ርቋቸዋል፡ ሆኖም ፊታቸው በመጠኑም
ፈታ ማለት ሲጀምር ማርጋሬት ጨዋታው ውስጥ ገብተው ሊቀላቀሉ
መሆኑን ገምታ ደስ ብሏት ነበር፡፡

ከዚያም በዚያው ቅጽበት ካርል ሃርትማን ‹‹ለምን ሌላ ዘረኛ መንግስት
ይቋቋማል?›› ሲሉ ተናገሩ፡፡

አሁን ነገር መጣ፡፡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ በንዴት የቀላ ፊታቸውን ወደ ሰዎቹ አዙረው ማንም ይናገራሉ ብሎ ባልጠበቀበት ጊዜ ‹‹እናንተ ቆሻሻ
ይሁዲዎች! ድምጻችሁን ብትቀንሱ ይሻላችኋል›› አሉ፡

ሃርትማንና ጋቦን የሎርዱ ንግግር ገርሟቸው አፈጠጡባቸው:
ማርጋሬት በድንጋጤ ፊቷ የበሰለ ቲማቲም መሰለ፡፡ አባቷ የተናገሩት ጮክ ብለው ስለነበር ሰዉ ጸጥ ረጭ አለ ማርጋሬት መሬቱ ተከፍቶ ቢውጣት ወደደች፡ ይህን የተናገሩት ፊት ለፊቷ የተቀመጡት ባለጌ፣ መሆናቸውን ሰው ሁሉ ስላወቀ ተሽማቀቀች።
አስተናጋጁን ኒኪን ቀና ብላ ስታየው መሳቀቋን አይቶ ለእሷ ማዘኑን ከፊቱ አነበበች፡ ይህም የበለጠ እፍረቷን አባባሰባት"...

ይቀጥላል
👍14
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ ማርጋሬት ደስ ደስ ብሏታል፡ ከእውነተኛ ሌባ ጋር መወዳጀቷን ማመን እያቃታት ነው፡ አንድ ሰው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት አታምነውም፡ ነገር ግን ሄሪ አንድ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ተከሶ ስላየችው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት እውነቱን መሆኑን አወቀች። ከስርዓት ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ማለትም ወንጀለኞች ለህግና ለመንግስት…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስተር ካርይል ምልስ ብሎ ልጁን ከደረቱ እቅፍ ሲያደርገው እንባው ፈሰሰ
አየወረደ የልጁን ፊት አራሰው “ የኔ ልጅ ... አባባ አሁን ይመለሳል " አማማን
እንድታይክ ሊያመጣት ነው


"አናም አብራ ትመጣለች ? ደስ የምትል ልጅ ናትኮ”

"አዎን ከፈለግሃት ሕፃኒቱ አናም ትመጣለች » እነሱን ካመጣኋቸው በኋላ
ካጠግብህ ንቅንቅ አልልም

“ በል እንግዲያሙስ አስተኛኝና ሒድ "

ሚስተር ካርላይል እንባው እየወረደ ልጁን ከሚመታው ልቡ አስጠግቶ
እ.... ቅ ....ፍ ካደረገው በኋላ ትራሱን አመቻችቶ አስተኛው አሁንም
እንድ ማንኪያ የንጆራ ጭማቂ ሰጥቶት እየተጣደፈ ሔዶ "

“ ደኅና ሁን .. አባባ ” አለ ልጁ በደካማው ድምፁ » እሱ ግን አልሰማውም " ሳቤላ ከተንበረከከችበት ብድግ ብላ እጇን ወደ ሰማይ ሰቅላ እንባዋ
ዝርግፍ ዝርግፍ ብሎ እየወረዶ ትንሰቀሰቅ ጀመር

"ዊልያም . . የኔ ዓለም ፡ በዚች የሞት ሰዓት እናት ልሁንልህ " ስትለው
እንደ ገና የደከሙት ዐይኖቹን ገለጠ " ነገሩ እሷ ካለችው ዐይነት አልገባውም

“ አባባ ኮ ሊያመጣት ሔዷል ”

“ እሷን አይደለም የምልህ " እኔ እኔ ” አለችና አቋረጠችው " ከአልጋው ላይ ተደፍታ ዝም ብላ ትንሰቀሰቅ ጀመር " በዚያች በመጨረሻ ስዓት እንኳን እኔ እናትህ ነኝ ' ልትለው አልደፈረችም "

ዊልሰን ተመልሳ መጣችና “ እንቅልፍ የወሰደው ይመስላል ” አለቻት "
“ አዎን ” አለች ሳቤላ “ግድየለም ሒጅ አንድ ነገር ሲያስፈልገው እጠራሻለሁ

ዊልሰን ክፉ ሰው ባትሆንም ከዚያ የጭንቀት ክፍል መቆየቱን ስላልወደደች ወጣች " ሳቤላ ብቻዋን ቀረች " እንደገና ተንበረከከችና..... ወዲያው የዱሮው ትዝታ መጣባት " የሚስተር ካርይል ሙሽራ
ሆና ኢስት ሊን ከጎባችበት ጀምሮ እስከ ዛሬ የነበረውን ታሪኳን አሰበች "
ይህ የዱሮ ታሪኳ በየመልኩ ስታስበው አንዱ እያለ ሌላው እየተተካ እስካሁኑ ሁኔታዋ ድረስ በሐሳብ እንደ ተዋጠች አንድ ስዓት ዐለፈ " ልጁም አላስቸገረም » ሚስተር ካርላይልም ኤልተመለሰም በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች ጆይስ ደረሰች ሳቤላ ከተንበረከከችበት ብድግ አለች " ጆይስ ቀጥታ መጣችና ዊልያምን
ለማየት ልብሱን ገለጥ አደረገች ዊልያም እንደሚፈልገኝ ጌቶች ነገሩኝ አለችና ስታየው ክው አለች " ማዳም ቬንም አደናገገጧን አይታ ወደ ጀይስ ጠጋብላ
እየች » ጢስ የለበሰው ለጋ ፊት ጸጥ ብሎ ተኝቷል - ያች ሁልጊዜ ዲም -ዲሞ
ስትል የኖረችው ትንሽ ልብም ሥራ አቁማለች "

ራሷን መቆጣጠር አቃታት " እንደሚሞት ተረድታ ሞቱንም በጸጋ በእርጋታ እንደምትቀበለው አምናና ዐውቃ ተቀምጣ ነበር ግን እንደዚያ ቶሎ የሚሞት እልመስላትም " ቢያንስ በጥቂቱ ሰዓት ዕድሜ እንደሚኖረው ገምታ ነበር "
አሁን ሳታስበው እንደ ደራሽ ጎርፍ ቀደማት " ጮሽች ተንሰቀሰቀች : ተጣራች
እላዩ ላይ ወደቀች ጥምጥም አድርጋ ይዛ አቀፈችው " መነጽሯንና ዐይነ ርግቧን ወረወረች » የድሮ መልኳ እንደ ነበረው ቁጭ አለ ፊቷን ከፊቱ አድርጋ አንድ ጊዜ ወደሷ ምልስ እንዲልላት ለመነችው ወደሷ ወደምትወደው ወላጅ እናት
ምልስ ብሎ ስማ እንድታስናብተው ጠራችው።

ጆይስ ከልጁ ሞት ይልቅ የሷ ሁኔታ አስደነገጣት » እንድታስብ ልብ እንድትል ያለችበትን ሁኔታ እንድትግነዘብ ለመነቻት በመጨረሻ ያለ የሌለ ጉልበቷን ተጠቅማ ካቀፈችው የልጁ ሬሳ አለያየቻት "

"ኧረ እመቤቴ ይተዉ ! ይተዉ !

'እመቤቴ ስትላት ነገሩ ልብ ራሷን መታት በዚህ አኳኋን ነበር ዱሮ ጆይስ የምትጠራት ድርቅ ብላ ደነገጠች » ስታብድ የነበረው ኩምሽሽ አለች "
ጆይስን ትክ ብላ አየቻትና የኋሊት አፈፈገች ;

“ እሜቴ . . ይበሎ እንግዲህ ወደ ክፍለዎ ልመሰድዎ " ሚስተር ካርላይል ሚስታቸውን ይዘው እየመጡ ነው " ከፊታቸው እንደዚህ ሆነው አይቆዬዋቸው እባክዎን ቶሎ ይምጡ ”

"አንቺ . . እንዴት ዐወቅሽኝ ?

“እሜቴ . . እሳት ተነሣ ተብሎ ሌሊት ተበራግገን የተነሳን ዕለት ነበር ያወቅኦ " ሕፃኑን አርኪባልድን ከዕቅፍዎ ለመቀበል ስጠጋ ሳይዎ በመንፈስ እንጂ በአካል የተገናኘን አልመሰለኝም " ፊትዎ አልተሸፈነም " በጨረቃው ብርሃን እንደ ፀሐይ ቁልጭ ብሎ ታየኝ ትንሽ ቆይቼ ድንጋጤዬ ለቀቅ ሲያደርገኝ ከእሜቴ ሳቤላ ጋር በአካል መግናኘቴን ተረዳሁ " ይበሉ አሁን እንውጣ ሚስተር ካርላይል ሊገቡ ነው " አለቻት ጆይስ

“ጆይስ . . እዘኝልኝ አታጋልጭኝ ለቅቄ እሄዳለሁ እስካለሁ ድረስ ምሥጢሬን ጠብቂልኝ አደራሽን "

“እሜቴ አይሥጉ " እስከ ዛሬ ድረስ ችዬው ኖሬአለሁ አሁንም እችለዋለዑ"
በርግጥ ወደዚህ በመምጣትዎ ተሳስተዋል " እኔም ካሁን አሁን ምን ይፈጠር ይሆን ? እያልኩ የልብ ሰላም የሌት እንቅልፍ አጥቻለሁ "

"ሰማሽ ጆይስ . . ከነዚህ ካልታደሉት ልጆቼ ተለይቼ መኖሩ አቃተኝ እኔ ግን ወደዚህ በመምጣቴ የተቀጣሁ አይመስልሽም ? እሱን ባሌን የሌላ ባል
ሆኖ ማየቱ ቀላል ነገር ነው ? ይኸ ራሱ አየገደለኝ ነው።

“ ኧረ ይምጡ እባክዎ ! ይኸው ሲመጡ ሰማኋቸው

አንደ ማባበልም እንደ
መጎተትም አድርጋ ከክፍሏ አስገባቻትና እየሮጠች
"ተመለሰች " ልክ ሚስተር ካርሳይል ከልጁ ክፍል ሲገባ አብራ ገባች ከእግር
እስከ ራሷ ተንቀጠቀጠች "

' ጆይስ ! ምን ነካሽ ? አመመሽ ? ” አላት

ጌታዬ ይዘጋጁ ! ዊልያም–– ዊልያም
ጆይስ ! ሞተ እንዳትይኝ ? ”
መቸስ ጌታዬ ምን ይደረጋል? ከዚህ የሚቀር የለም ።

ሚስተር ካርላይል ወደ ወስጥ ገብቶ መዝጊያውን በስተውስጥ ቀርቅሮ ወደ
የመነመነው የሕፃን ፊቱ ልጁ ተጠጋ " ከትራሱ ዝንጥፍ ብሎ ወድቆ አየው

" ልጄ ! ልጄ ወይ ልጄ ! ” እያለ “ጌታ ሆይ ያቺን ያልታደለች እናቱን ተቀ
ብለሃታል ብዬ እንደማምነው ሁሉ የዚህንም ሕፃን ነፍስ ታርፍ ዘንድ ተቀበላት” ብሎ ጸለየ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሎርድ ማውንት ስቨርን ከዊልያም ካርላይል ቀብር ላይ ለመግኘት ከልጁ ጋር
መጣ ዊልሰን እንዳሰበችው ዊልያም ካባቱ አባት ጎን ተቀበረ » መቃብሩ ላይ !
ዊልያም ቬን ካርላይል የኢስት ሊኑ አርኪባልድ ካርላይል የመጀመሪያ ወንድ ልጅ የሚል ዕብነበረድ አቆመበት " ዐይን ካረፈባቸው ኀዘንተኞች አንዱ
ሪቻርድ ሔር ትንሹ ነበር "

ሳቤላ በአእምሮም ሆነ በአካልም ይዞታዋ በጣም የሚያሠጋ ሆነ ነገር ግን
ሐኪም እንዲያያት ስለ አልፈለገች የሕመሟ መጠን አልታወቀላትም ይታይባት
የነበረ የበሽተኝት ምልክት ዊልያምን ያለ ዕረፍት ስታስታምም ከድካም ብዛት
የመጣ ስለመሰለ በቤተሰብ ዘንድ አሳሳቢ ሆኖ አልታየም " ከክፍሏ መውጣት
ስትተው ጆይስ ታስታምማት ጀመር " እሷ ግን የሰው ልጆች ኃይልና ጥበብ
ሊመልሰው የማይችል ሞት በመምጣት ላይ እንደ ነበር ዐውቃው ነበር ነገር
ግን ኢስት ሊን ሆና ለመሞት አልፈለገችም ሐሳቧን በሙሉ አሰባስባ ከኢስት
ሊን የምትወጣበትን መንገድ ማውጣት ማውረድ ተግባሯ አደረገችው " እንዳትታወቅ የነበራት ሥጋት እንደ ወትሮው ማስጨነቁን እየቀነሰላት ሔደ መታወቋ ሊያስከትለው ለነበረው ውጤት ማሰቡንም ተወችው " ወደ መቃብር ሲቃረቡ ማንኛቸውም ዐይነት የዚህ ዓለም ፍራቶችና ተስፋዎች ሁሉ ኃይላቸውን ያጣል
👍15
ሳቤላ ወደ ኢስት ሊን በመመለስ ከፍተኛ ድፍረት ነበር የፈጸመችው » በተግባር ባየችው ጊዜ በጉልበትም ሆነ በመንፈስ ጥንካሬ እንደማይቻል ተረዳችው ።የደረሰባት ከፍተኛ የመልክ ለውጥና የራሷም ጥንቃቄ ተዳምረው እንድትታወቅ እንደማያደርጓት የተሰማት ኤርግጠኝነት በሁሉም ገጽታ አዙሮ የማየት ግንዛቤዋን አጨለመው የፈለጉትን ይበሉ እንጂ የሰዎችን ስሜቶች ከልባቸው ጨርሶ
ማጥፋት ይቻላል ማለት ዘበት ነው አምቆ መያዝ አደንዝዞ ማቆየት ወይም
በቁጥጥር ሥር ማዋል ይቻል ይሆናል " ነቅሎ ማጥፋት ግን አይቻልም ። በዚህ ዓለም የመጨረሻውን የፍጹምነት ደረጃ ደረሰ የሚባል ትልቅ ሰው ቢኖር እንኳን ክፋትን ከሐሳቡ ስሜታዊ ፍላጐቶችን ከተፈጥሮው ላለማስቀረብ ያለማቋረጥ መታገል ያስፈልገዋል ።

ሳቤላ የሚስተር ካርላይል ሚስት በነበረችበት ጊዜ ከልቧ አትወደውም ነበር።
እሱ ለሷ የነበረው ፍቅር ያደርግላት የነበረው እንክብካቤ ይሰጣት የነበረው አክብሮት በሷ ላይ የነበረውን ከፍተኛ ግምት እያየች : እያወቀች አጸፋውን አስተካክላ መልሳለት አታውቅም " አሁን ግን ነገሩ ተለዋወጠ " ዓለም የምትዞረው በቅራኔ ሕጎች ስለሆነ እኛም አብረናት እንዞራለን " በእጃችን የገባውን እንንቃለን የማናገኘውን እንመኛለን " ወደ ኢስት ሊን ተመልሳ ከመጣችበት ማታ
ጀምሮ ለሚስተር ካርላይል ያደረባት ፍቅር ከዚያ በፊት ሆኖ በማያውቅ ኃይልና
ግለት ነደደባት
" ገልጻው የማይለቃት ' ነዶ የማይወጣላት በርዶ የማይይጠፋላት ውስጥ ውስጡን እያቃጠለ የሚፈጃት ሆነ ከድታ ስትወጣ ወዲያው ጀመራት ተመልሳ ስትግባ ጠናባት » ስለዚህም ትታው በሔደችው ባሏ ፍቅር ተብከነከነች
አሁንም አሁንም የሆነውን ነገር ሁሉ ትዘነጋውና ባሉም ባሏ ቤቱም ቤቷ ይመስላታል ከዚህ የቀን ሕልም እየሆነ ከበጠበጣት ተስፋ ቢስ ፍላጎት ለመላቀቅ ቆርጣ እርግፍ አድርጋ ለመተውና ስለሱም ላለማሰብ ትሞክርና ለቀቅ
ሲያደርጋት በገዛ ምኞቷና ሐሳቧ ኃፍረትና ጸጸት ተተክተው ያንገበግቧታል እነሱ ደግሞ ጥቂት ቆይተው ከአአምሮዋ እልም ሲሉላት ወዲያው ተመልሳ ከወጣችበት የአጉል ምኞትና የቀን ቅዠት ባሕር ትግባለች ባሏን ሚስተር ካርላይልን ከነፍቅሩ እራሷ ለባርባራ ማስረከቧን ፈጽማ ትረሳዋስች የሚስተር ካርላይል ፍቅር የባርባራ እንጂ የሷ አይደለም ሚስተር ካርላይልም የሚስቱ የባርባራ እንጂ
የሷ አይደለም ከሁሉ የከው ነገር ደግሞ የሷ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን የሌላ መሆኑ ነበር " በዚህ ጉዳይ ባርባራ ባትኖር ኖሮ እንደ ምንም ትችለው ነበር ነገር ግን ሆነና ከጸጸት ጋር ተደርቦ ከዕድሜዋ በፊት ጣላት ።

በሌላ በኩልም የፍራንሲዝ ሌቪሰን ወደ ዌስት ሊን መምጣትና በከባድ ወንጀል መከሰስ መንፈሷን አወከው ናላዋን በጠበጠው ጸጸቷን አባባሰ " ትዝታዋ ሁልጊዜ በሹል ጦር እንደ ተወጋ ሁል ጊዜ ሳይታሰቡ በሚወረወሩት የነገር
መርዞች እንደ ተነደፈች በየስዓቱ በመታወቅ ሥጋት እንደ ተሸማቀቀች ወደ
ዌስት ሊን ለምን እንደ መጣች ከሕሊናዋ ጋር እንደ ተናነቀች ማብቂያ ባልነበረው ውጥረት ውስጥ ተዘፍቃ ኖረች " ዕድሜዋ ይህን ሁሎ ችሎ ቢረዝም ነበር እንጂ ቢያጥር ምንም አያስገርምም "

ሞቷ እሷ ታስበው ከነበረው በበለጠ ቢቃረብም እሷም የጉልበቷን መድከም
የስሜቶቿን መፍlዝ እየተመለከተች ብዙ እንደማትቆይ ዐውቃው ነበር " እናቷም የሞተችው በተመሳሳይ ሁኔታ ነበር " አንዳንዶቹ እንደ ዶክተር ማርቲን ያሉ በሳንባ በሽታ ነው ሲሉ ባሏ የማውንት እስቨርን ኧርል ደግሞ በኀዘን ብዛት ነው ይል ነበር " ሳቤላም በልጅቱ ይኸ ነው የሚባል በሽታ አልነበራትም " ነገር ግን ጊዜ ሞቷ እንደ ቀረበ ዐወቅችው እሷ ደግሞ ዐይኗ እያየ ለመታወቅ አልፈለገችም
እንዲያወም እስከ ጊዜ ሞቷ ድረስ ኢስት ሊን ለመቆየት ምንም ሐሳብ
አልነበራትም ።

ኢስት ሊንን ሹልክ ብላ በወግ በማዕረግ መልቀቋን እንጂ ከዚያ ወጥታ ወዴት
አንደምትሔድ የት እንደምትገባ የቅድሚያ ትኩረት አልሰጠችውም " ጆይስም ብትሆን ለራሷ ፈርታ አንድትሔድላት በየቀኑ ትወተውታት ጀመር ስለዚህ ከሁሉ በፊት የመሔዷን ነገር ለሚስዝ ካርላይል ልትነግራት ፈለገችና ዊልያም በተቀበረ በበነጋው ወደ አመቤቲቱ መልበሻ ክፍል ሰተት ብላ ገባች "

ባርባራ በሠረገላ ወጣ ብላ ስለ መጣች ድካም ተሰምቷት ከሶፋው ላይ
ጋደም ብላለች ሳቤላ ስትገባ ሚስተር ካርላይል ወጥቶ ሔደ ።

ማዳም ቬን ” አለቻት ባርባራ ለልጆች የምታደርጊው ጥንቃቄ
ከልብ ነው የተሰማን ሚስተር ካርላይል የውለታሽ ነገር ከብዶቷል አንቺን
ማጣቱ በጣም ነው
የሚያሳዝነን ።

“እኔም ከናንተ መለየቱ በጣም አስጨንቆኛል
አለች ሳቤላ እሷማ
ምትፈልገውንና የምትወደውን ሁሉ ትታ ስትሔድ እንዴት አይጨንቃትም »

"አሁንም መሔድ የለብሽም " ዊልያምን ስታስታምሚ ስለሆነ የታመምሽው
በጎ እስክትሆኝ ድረስ ዕረፍት አድርገሽ መቀመጥ አለብሽ በደንብ ካስታመምንሽ ቶሎ ትድኛለሽ"

እርስዎ ለኔ አዝነው መሆኑ ይገባኛል " ነገር ግን እምቢታዬ የዕብደት
አይምሰልብኝ እንጂ እኔ ደክሜአለሁ ጉልበቴ ከእንግዲህ ተመልሶ እንደ
ነበረው አይሆንም
“የለም እንደሱ አትበይ ሲደክመንና ሲያመን ብዙ ሐሳብ ይመጣብናል
አሁን እኔ ለአርኪባልድ ስነግረው እያነጋገረ አበረታታኝ እንጂ ድክም ብሎኝ ነበር ላንቺም ማዳም ቬን .. የምትወጂው ባልሽ በሕይወት ቢኖርልሽ ኑሮ
ባሌ እንደሚያደርግልኝ ይወድሽና ይደግፍሽ ነበር አሁን ግን ማንም እንደሌለሽ
እያወቅን እንዲህ ሆነሽ ከቤት አውጥተን አንጥልሽም " አለቻት "

“ከዚህ ያደረሰኝ ዊልያምን በማስታመሜ አይደለም መሔድ አለብኝ በነገሩ
አስቤበታለሁ ''

“ ወደ ባሕር ዳርቻ መሔድ ደስ ይልሻል ? " አለቻት ባርባራ „ “ እኔ አርኪባልድ ሔደሽ አየር ካልለወጥሽ ብሎ ስለ አስቸግረኝ ሕፃኗን ይዤ በሚመጣው ሳምንት ልሔድ ነው " ለመሔድ ከፈለግሽ ግን ልዩ ፕሮግራም ልናዘጋጅ
እንችላለን " ሊረዳሽ ይችል ይሆኖል ... ማዳም ቬን »

ማዳም ቬን ራሷን ነቀነቀች “ይብስብኛል “ እኔ የምፈልገው ጸጥታን ነው
ስለዚህ የምለምንዎ ይኸው አስቀድሜ ስለ ተናገርኩ ከጥቂት ቀኖች በኋላ እንድለቅ እንዲፈቀድልኝ ብቻ ነው ።

“ ስሚ ” አለች ባርባራ ጥቂት ካስበች በኋላ “ እኔ በሁለት ሳምንት ውስጥ
እመለሳለሁ ። እስከዚያ ድረስ መቆየት አለብሽ " እንዲያውም ሚስተር ካርላይል አብሮኝ ሊስነብት ስለማይችልና ፡ እዚያ ብቻዬን መቀመጡ ቶሎ ሊስለቸኝ ስለሚችል ከዚያ በፊትም እመለስ ይሆናል እንድታስተምሪ ወይም ሌላ ሥራ እንድትሠሪ አልፈልግም ሉሲም ዕረፍት አድርጋ ልትሰነብት ትችላለች ሚስተር ኬን ብቻ እየመጣ ሙዚቃ ያስተምራታል ዋናው ነገር ምን መሰለሽ ልጂቱ ነፍስ እያወቀች እያደገች ነው " ስለዚህ ያንቺ ቁጥጥር ይኖርበት ለቤት ሰራተኛች
ለጆይስ እንኳን ቢሆን ጥያት መሔዱ ደስ አላለኝም " አንቺ ሐሳብሽን ካልለወጥሽ እኔ ስመለስ መሔድ ትችያለሽ " ምን ይመስልሻል ? ''

“ እሺ ” አለች ቶሎ ብላ ከልጆቿ ከሎሲና ከአርኪባልድ ጋር ሌላ ሁለት
👍20
ሳምንት መሰንበቱን በታላቅ ደስታ ተቀበለችው " በርግጥ ያ ክፉ ሞት ሊወስዳት በመምጣት ላይ እንደ ነበር ብታውቅም ከሁለት ሳምንት የበለጠ ጊዜ እንደሚኖራት ታምን ነበር " እሷም ራሷ የሚስተር ካርላይል ሚስት በነበረችበት ጊዜ ወደ
ባሕር ዳርቻ እንድትሔድ መታዘዟን ባሏም መሔድ እንደሚገባትና ጤንነቷንም
ሊሻላት እንደሚችል ምን ያህል እንደ ወተወታት አስታወሰች » በዞ በሆቴል
አያያዝ ስለ ምቾቷ ምን ያህል ይጨኔቅላት እንደ ነበር ተመልሶ ሊጠይቃት በመጣ ጊዜም ምን ያህል አሰቦላትና ናፍቋት እንደ ነበረና ደኅና ተሽሏት ሰውነቷም ተመልሶም ሞልቶና ወዝቶ ባያት ጊዜ የተሰማው ደስታ የሆነላት መሆን ሁሉ ትዝ
አላት » በተለይ ደግሞ አንድ ቀን እሷን ጠይቆ ለመመለስ ከመርከብ ሊሳፈር ሲል አንተ... ከባርባራ ሔር ጋር እንዳትዳራ ያለችው አሁን ድቅን አለባት "
ዛሬ ያ ሁሉ የነበረው ፍቅር ደግነት ባርባራ ባለመብት ሁናበት ምኑም ሳይጓዶል እየተጠቀመችበት ነው "

ባርባራ ማዳም ቬንን ከኢስት ሊን ሳትወጣ እንድትቆያት አጥብቃ በለመነቻት ጊዜ በልቧ በጣም ደስ እንዳላት ባትገልጸውም ላለመቀበል አልጨከነችም "
ይህች አስተማሪ ጠባይዋ ከብዙዎቹ ብጤዎቿ ለየት ያለች ከትልቅ ቤተስብ
የተወለዶች በጨዋ ደንብ
ያደገች መሆኗን ባርባራ ጠቅላላ ሁኔታዋን በመገምግም ዐወቀቻት " ሁለተኛዉ ለሉሲ ስትል ብቻ ደሞዟን የምትፈልገውን ያህል አሳድጋላት እንድትቀመጥላት ፈለገች ነገር ግን ባርባራ ለሉሲ ስትል ብቻ እንጂ በግል ስሜቷ ማዳም ቬንን አትወዳትም ነበር በአርግጥ ሰውነቷ ቢነግራት ይሆናል እንጂ የምትጠላበት ይኸ ነው የምትለው ምክንያት አልነበራትም ".....

💫ይቀጥላል💫
👍13
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

ሃርትማንና ጋቦን የሎርዱ ንግግር ገርሟቸው አፈጠጡባቸው:
ማርጋሬት በድንጋጤ ፊቷ የበሰለ ቲማቲም መሰለ፡፡ አባቷ የተናገሩት ጮክ ብለው ስለነበር ሰዉ ጸጥ ረጭ አለ ማርጋሬት መሬቱ ተከፍቶ ቢውጣት ወደደች፡ ይህን የተናገሩት ፊት ለፊቷ የተቀመጡት ባለጌ፣ መሆናቸውን ሰው ሁሉ ስላወቀ ተሽማቀቀች።
አስተናጋጁን ኒኪን ቀና ብላ ስታየው መሳቀቋን አይቶ ለእሷ ማዘኑን ከፊቱ አነበበች፡ ይህም የበለጠ እፍረቷን አባባሰባት"

ባሮን ጋቦን ፊታቸው በድንጋጤ አመድ መስሏል ለሎርዱ መልስ ሊሰጡ አሰቡና ትተውት ፊታቸውን ወደ ሃርትማን መለሱ፡
ሆዳቸው እያረረ በፈገግታ አለፉት፡ ነገር ግን እሳቸው ከናዚ ጀርመን አምልጠው የመጡ በመሆናቸው ከዚህ በላይ ብዙ ክፉ ነገር የደረሰባቸው ስለሆነ ይህ ስድብ ለእሳቸው እንደ ምርቃት የሚቆጠር ነው።

ማርጋሬት ባሮን ጋቦንን ተመለከተች፡ ሎርዱ ያሉትን ከምንም ባለመቁጠር ማንኪያቸውን አንስተው ሾርባቸውን መጠጣታቸውን ቢቀጥሉም እጃቸው እየተንቀጠቀጠ ስላስቸገራቸው ሰደርያቸው ላይ ሾርባው ተንጠባጠበ፡፡ውስጣቸው
የሚንተከተከው ንዴት ግን
መጠጣት ስላላስቻላቸው ማንኪያቸውን አስቀመጡት።

ማርጋሬት የባሮኑ ብስጭት ልቧን ነካው። በአባቷም ስድብ በጣም ተናደደችና ‹‹ድፍን አውሮፓ የሚያከብራቸውን ሁለት ትላልቅ ሰዎች እንደዚህ መሳደብ የለብህም›› አለቻቸው በድፍረት።

‹‹ሁለት የታወቁ ይሁዲዎች በይ›› አሉ አባቷ።

‹‹ይሁዳዊያን አያቴን ረሳሃቸው አባባ?›› አለ ፔርሲ ሁሉን ነገር ቀልድ አድርጎ።

አባት ወደ ልጃቸው ዞሩና ጣታቸውን ፔርሲ ላይ እያወዛወዙ ‹‹እንዲህ
ያለውን የማይረባ ቀልድህን ተወኝ ሰማኸኝ!›› ሲሉ አፈጠጡበት

ፔርሲ ነገሩ ስላላማረው ‹‹መጸዳጃ ቤት ልሂድ አሞኛል›› አለና ትቷቸው ሄደ፡ ማርጋሬት እሷና ፔርሲ አባታቸውን መቃወም እንደሚችሉና ምንም እንደማያመጡ አውቃለች፡ ይህም አንድ እድገት ነው ስትል አሰበች፡

‹‹ከቤታችን አባረው እንድንሰደድ ያደረጉን እነዚህ ሰዎች መሆናቸውን
እንዳትረሺ›› አሏት አባት ማርጋሬትን፡፡ ‹‹ከኛ ጋር የሚሄዱ ከሆነ ስርዓት
መማር አለባቸው›› አሉ፡

‹‹ቃ!›› ሲል ተደመጠ አንድ ድምጽ

ማርጋሬት ድምጹ ወደመጣበት አቅጣጫ ዞረች፡ ይህን ያለው ፎየንስ
ላይ የተሳፈረው መርቪን ላቭሴይ ነው፡፡ መርቪን እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ
የኦክሰንፎርድን ቤተሰብ ጠረጴዛ ተደግፎ ቆሟል። አስተናጋጆቹ በድንጋጤ
ደርቀው ቆመዋል፡ ጠብ ይነሳል ብለው ፈርተዋል፡ ላቭሴይ የሰማይ ስባሪ
የሚያክል፣ ዕድሜው በአርባዎቹ ውስጥ የሚገመትና ጸጉሩ ገብስማ መልከ መልካም ሰው ነው፡፡ ሲያዩት የሚፈራው ነገር ያለ አይመስልም፡ የለበስው
ልብስ ውድ መሆኑ ያስታውቃል፡

‹‹ይህን አመለካከትህን ለራስህ ያዘው›› አላቸው በሚያስፈራ ድምጽ“

‹‹አንተን አያገባህም!›› አሉ ኦክሰንፎርድ።
‹‹ያገባኛል!››
ማርጋሬት አስተናጋጁ ውልቅ ብሎ ሲሄድ አየችው፡ የአይሮፕላኑን አስተናጋጆች ሊጠራ እንደሄደ ተገንዝባለች፡፡

‹ስለ እኚህ ሰውዬ ምንም አታውቅም፡፡ ፕሮፌሰር ሃርትማን ባንተ አፍ የሚጠሩ ሰው አይደሉም፡፡ በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ሳይንቲስት ናቸው››
አለ ከመቆርቆር በመነጨ ብርቱ ስሜት፡

‹‹የፈለገውን ቢሆን ግድ የለኝም›› አሉ ኦክሰንፎርድ፡
‹‹አንተ ግድ ባይኖርህ እኔ ግድ ይኖረኛል፡ ስለዚህ ይህን የከረፋ አስተሳሰብህን አስተካክል›› አለ ላቭሴይ፡

እኔ የፈለኩትን ማለት እችላለሁ›› አሉና ኦክሰንፎርድ ከመቀመጫቸው ተነሱ፡
ላቭሴይ በጠንካራ እጁ የኦክሰንፎርድን ትከሻ ተጫነና አስቀመጣቸው፡፡
እንዳንተ ካሉ ሰዎች ጋር ነው ጦርነት የገጠምነው›› አለ፡፡

ኦክስንፎርድም በደከመ ድምጽ ‹‹ልቀቀኝ! ልቀቀኝ!›› ሲሉ ተወራጩ።

‹‹አፍህን የምትዘጋ ከሆነ ነው የምለቅህ››

‹ካፒቴኑን እጠራለሁ›› አሉ ኦክሰንፎርድ፡

‹‹አያስፈልግም!›› አለ ሌላ ድምጽ፡ ካፒቴን ቤከር ሙሉ ዩኒፎርሙን ለብሶ ቆሟል የአዛዥነት መንፈስ ይታይበታል፡ ‹‹ሚስተር ላቭሴይ ወደ ቦታህ ብትመለስ?›› አለ፡

‹‹እኔ ወደ ቦታዬ እመለሳለሁ›› አለ ላቭሴይ ‹‹ነገር ግን በመላው
አውሮፓ ትልቅ ክብር የሚሰጣቸው ሳይንቲስት በዚህ ሰካራም ሲሰደቡ
በዝምታ ማለፍ አልችልም፡››

‹‹ሚስተር ላቭሴይ ወደ ቦታህ›› አለ ቤከር፡

ላቭሴይ ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡

ካፒቴኑም ወደ ኦክሰንፎርድ ዞር አለና ‹‹ሎርድ ኦክሰንፎርድ የተናገሩት
ነገር አስነዋሪ ነው፡ አንድ ተሳፋሪ ሌላውን ተሳፋሪ መስደብ አይችልም፡››

ማርጋሬት አባቷ የቤከርን ምክር እንዲቀበሉ ብትፈልግም እሳቸው ግን
ጠብ ጠብ እንዳላቸው ነው፡፡

‹‹አንተ ይሁዲ ብዬ ነው የጠራሁት፡፡ ይሁዲነቱን ሊክድ ነው!›› ሲሉ
አምባረቁ፡፡

‹‹አባባ ምነው ዝም ብትል›› ስትል ተቆጣች ማርጋሬት፡

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ እስካለሁ ድረስ ማንንም እንዲሳደቡ አልፈቅድም›› አለ ቤከር፡

አባት ስድባቸውን ቀጠሉ ‹‹በይሁዲነቱ ያፍራል እንዴ?›› አሉ፡

ቤከር በቁጣ ገነፈለ፡፡ ‹‹ይሄ የአሜሪካ አይሮፕላን ነው ጌታዬ እኛ ደግሞ ጥብቅ የስነ ምግባር ደንብ እንከተላለን፡፡ ሌሎች ተሳፋሪዎችን መሳደብ
ካላቆሙ አይሮፕላኑ በሚቀጥለው በሚያርፍበት ቦታ ላይ ለፖሊስ አስረክቦታለሁ፡፡ ምንም እንኳን አልፎ አልፎ የሚከሰት ቢሆንም እንዲህ
አይነት ነገር ሲገጥም አየር መንገዱ ህግ የጣሱ ሰዎችን ይከሳል›››

ሎርዱ የክስ ነገር ሲነሳ ፍርሃት ፍርሃት አላቸው፡ የሚመጣውን በመፍራትም አፋቸውን ዘጉ፡፡ ማርጋሬት በእጅጉ በሃፍረት ተሽማቀቀች አባቷን ዝም ለማሰኘት ብዙ ብትጥርም የአባቷ አድራጎት አንገት
አስደፍቷታል ቅሌት ውስጥ የገቡት አባቷ ስለሆኑ::

‹‹ወደ መቀመጫችን እንመለስ›› አሉና አባት ተነሱ ወደ ሚስታቸውም ዞር ብለው ‹‹አንሄድም የኔ ውድ?›› አሏቸው።

ሁሉም ሰው ማርጋሬት ላይ አፈጠጠባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሄሪ ከየተ መጣ ሳይባል ከመቀመጫዋ ኋላ መጥቶ ወምበሯን ያዝ አደረገላት” ሌዳ ማርጋሬት›› አለ በአክብሮት በመጠኑ አንገቱን ዝቅ አድርጎ ማርጋሬት በሄሪ አድራጎት ልቧ ተነካ፡፡

እናት ጅንን ብለው ፊታቸው ላይ ምንም የእፍረት ምልክት ሳይታይባቸው ባላቸውን አስከትለው ወጡ፡፡

ሄሪ ለማርጋሬት በጨዋ ደምብ ክንዱን ሲሰጣት ክንዷን ከክንጿ ጋ ቆላለፈች፡፡ ይሄ ትልቅ ነገር ባይሆንም ለእሷ ግን አንድ የሆነ መተማመን ፈጥሮላታል፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በእፍረት ቁንጫ አክላ የነበረችው ማርጋሬት በመጨረሻ በሄሪ እርዳታ በክብር ወደ ቦታዋ ተሸኘች፡፡ ከሄሪ ጋ ወደ መቀመጫዋ ስትመለስ ድምጹን አጥፍቶ አምባጓሮውን እንደ ትርኢት
ሲመለከት የነበረው ተሳፋሪ ከኋላ ሲንሾካሽክ ሰማች፡

‹‹አንተ ጥሩ ሰው ነህ፡፡ እንዴት እንደማመሰግንህ አላውቅም›› አለችው
ሄሪን፡፡

‹‹የተፈጠረውን አታካሮ ስመለከት ነበር፡፡ በአባትሽ አድራጎት አንገትሽን
ስትደፊ ሳይ አሳዘንሽኝ፡፡››

‹‹እንደዚህ ቀን በሃፍረት ተሸማቅቄ አላውቅም›› አለች እየተንገፈገፈች

አባቷ ግን አሁንም አደብ አልገዙም፡፡ ‹‹አንድ ቀን ይቅርታ ይጠይቁ ይሆናል እነዚህ ጅሎች!›› አሉ፡ ሚስታቸው አንድ ቃል ሳይተነፍሱ እጥግ
ተቀምጠው ባላቸውን በአግራሞት ያይዋቸዋል፡፡

‹‹ይህ ጦርነት ያበቃና! ምናለ በሉኝ›› አሉ
አባት፡፡
👍14
‹‹አባባ ከዚህ በኋላማ በቃ እባክህ›› አለች ማርጋሬት፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ አጠገባቸው ሄሪ ብቻ ነው ያለው: ሚስተር መምበሪ በቦታው የለም አባቷ የልጃቸውን ውትወታ ከምንም ባለመቁጠር ‹‹የጀርመን ጦር እንደ መአበል እንግሊዝን ያጥለቀልቃታል፡፡ ከዚያም ምን ይሆናል መሰላችሁ
ሂትለር የፋሺስት መንግስት በእንግሊዝ ይተክላል» አሉ
‹‹አባባ ምነው ቀወስክ እንዴ!›› አለች፡፡
‹‹ከዚያም የፋሺዝም አራማጅ ሰው እንዲመራ ስልጣን ይሰጠዋል!›› አሉ
አባት


‹‹ወይ አምላኬ!›› አለች ማርጋሬት አባቷ ውስጣቸው የሚንቀለቀለውን አስተሳሰብ በግልጽ ሲናገሩ ስትሰማ በእጅጉ ተስፋ ቆረጠች፡

አባቷ ሂትለር የእንግሊዝ አምባገነን መሪ ያደርገኛል ብለው ያስባሉ፡፡
እንግሊዝ በጀርመን እግር ስትወድቅ እሳቸውን ከስደት አምጥቶ እንደ አሻንጉሊት ያስቀምጣቸዋል።

‹‹አንድ የፋሺስት ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦታው ላይ ሲቀመጥ አዳሜ እሱን
ተከትላ ታሸበሽባለች!›› አሉ ኦክሰንፎርድ በድል አድራጊነት መንፈስ፤
በክርክሩ ያሸነፉ ይመስል።

ሄሪ ኦክሰንፎርድን እንደ ላንቲካ ሲመለከት ቆየና ‹‹ሂትለር ቢያሸንፍ
የፋሺስት መንግስት እንዲያቋቁሙ የሚጠራዎት ይመስሎታል?›› ሲል
ጠየቃቸው፡

‹‹ማን ያውቃል?›› አሉ ኦክሰንፎርድ ‹‹እዚህ ቦታ ላይ የሚቀመጠው
ሰው በቀድሞው መንግስት እጁ የጨቀየ መሆን የለበትም፡ እኔ አገሬን
ለማገልግል ከተጠራሁ ተመልሼ ለመምጣት አይኔን አላሽም፡፡››

ሄሪ በሰውዬው አባባል ክፉኛ ደነገጠ፡፡

ማርጋሬት በአባቷ ላይ ያላት ተስፋ ሁሉ ተሟጠጠ፡፡ ከአባቷ ተለይታ መሄድ ሊኖርባት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ለመጥፋት ሞክራ ሳይሳካላት ቀርቶ ቅሌት ውስጥ የከተታትን ሁኔታ ስታስታውስ ዘገነናት፡፡ አንድ ጊዜ ስላልተሳካላት ግን ተስፋ መቁረጥ አይኖርባትም፡፡ አንድ ሌላ የመጥፋት ሙከራ ለማድረግ ቆርጣ ተነስታለች፡

አሁን ግን በተለየ ሁኔታ ማድረግ ይኖርባታል፡ ከእህቷም መማር
አለባት፡፡ በጥንቃቄ አስባና አቅዳ መነሳት ይኖርባታል፡ ታዲያ ገንዘብ፣ ጓደኞችና የምታርፍበት ቦታ ያስፈልጋታል፡፡ በዚህ ጊዜ ውጤት ማምጣት
ይጠበቅባታል፡፡

ፔርሲ ከመጸዳጃ ቤት ሲመለስ ጠቅላላ ድራማው አምልጦታል፡ ሆኖም
እሱ የራሱን ድራማ ሲሰራ ስለቆየ ፊቱ በፈገግታ አብርቷል፡ ‹‹ምን እንዳ
የሁ ልንገራችሁ›› አለ አጠገቡ ላሉት ሰዎች ‹‹ሚስተር መምበሪ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ኮቱን አውልቆ ሲታጠብ ወገቡ ላይ የሻጠውን ሽጉጥ አየሁት፡›››.....

ይቀጥላል
👍13🥰1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...ባርባራ ማዳም ቬንን ከኢስት ሊን ሳትወጣ እንድትቆያት አጥብቃ በለመነቻት ጊዜ በልቧ በጣም ደስ እንዳላት ባትገልጸውም ላለመቀበል አልጨከነችም "
ይህች አስተማሪ ጠባይዋ ከብዙዎቹ ብጤዎቿ ለየት ያለች ከትልቅ ቤተስብ
የተወለዶች በጨዋ ደንብ
ያደገች መሆኗን ባርባራ ጠቅላላ ሁኔታዋን በመገምግም ዐወቀቻት " ሁለተኛዉ ለሉሲ ስትል ብቻ ደሞዟን የምትፈልገውን ያህል አሳድጋላት እንድትቀመጥላት ፈለገች ነገር ግን ባርባራ ለሉሲ ስትል ብቻ እንጂ በግል ስሜቷ ማዳም ቬንን አትወዳትም ነበር በአርግጥ ሰውነቷ ቢነግራት ይሆናል እንጂ የምትጠላበት ይኸ ነው የምትለው ምክንያት አልነበራትም "

ወይም መልኳ ከሳቤላ ጋር በመመሳሰሉ ሊሆን ይችላል " ባርባራ ራሷም የማዳም ቬን መልክ ከሳቤላ ጋር መመሳሰል በድምፅ ይሁን በመልክ ይሁን በጠባይ
ይሁን ግልጽ ሊሆንላት ባይችልም ብዙ ጊዜ የሚገርም መመሳሰል ሰትል ነበር
ሳቤላ ቬን ትሆናለች ብላ ግን በጭራሽ አልጠረጠረችም እንደማትወዳትም ለማንም ተናግራ አታውቅም " የሰማይ ወፎች የየብስ እንስሶችና የባሕር ዓሦች ሁሉ አንድ ነገር ከመድረሱ በፊት የማወቅ ተሰጥኦ እንዳላቸው ሁሉ ሰውም የራሱ የሆነ ተሰጥኦ አለው " ስለዚህ በዚህ ተሰጥዎው ሰውነቷ ነግሯት ይሆናል " ከላይ እንዳልነው ባርባራ ለሉሲ ስትል ብቻ ማዳም ቬን ከኢስት ሊን እንድትለቅ ባትፈልግም ሞተች ቢባል ግን አንዲት ዘለላ እንባ እንኳን እንደማታፈስላት ታውቅ ነበር ።

እነዚህ የተለያዩ አሳቦችና ትዝታዎች በሁለቱ ሴቶች ናላዎች ሲመላለሱባቸው
ቆዩና " ማዳም ቬን ለመሔድ ከወንበሯ ተነሣች
ልጄን ለአንድ ደቂቃ ያህል ትይዥልኝ .. ማዳም ቬን ? ” አለቻት ባርባራ " ማዳም ቬን ያላሰበችው ጥያቄ ሲሆንባት ጊዜ ደነገጠችና “ ይችን ሕፃኗን ! ” ስትላት ባርባራ ሣቀች

“ ይቻትልሽ ከጎኔ ተኝታለች

ማዳም ቬን ጠጋ ብላ ልጂቱን አሣቻት " ከዚያ በፈት በክንዷ ልታቅፋት
ቀርቶ ለዐይኗም በወጉ አይታት አታውቅም " አንድ ቀን ይሁን ሁለትቀን ያህል
ሚስዝ ካርላይልን ለማየት ገብታ ወንፊት በመሰለ ልብስ የተሸፈነች ትንሽ ፊት ከህፃን አልጋዋ ላይ እንደተኛች አሳይታት ነበር » ከዚያ በቀር አይታት አታውቅም።

“ አመሰግንሻለሁ አሁን መነሣት እችላለሁ " አየሽ ልጅቱ እዚሁ እንዳለች ለመነሣት ብሞክር ኖሮ ላፍናት እችል ነበር " አለቻት ባርባራ እየሣቀች "
“ እዚህ ጋደም ካልኩ ብዙ ቆይቻለሁ አሁን ድካሜ ደኅና ወጣልኝ እንደተኙ
ስለሚታፈኑት ሕፃናት ጉዳይ ከሚስተር ካርላይል ጋር አሁን ስንጫወት ነበር "
በየሳምንቱ በሚወጣው የጤና ዜና ይህን ያህል ልጆች እንደተኙ ተደርቦ ተተኛባቸው ይህን ያህል ልጆች እንደተኙ እየታፈኑ ሞቱ እየተባለ ይገጻል" በየሳምንቱ እስከ አሥር ይደርሳሉ" ሚስተር ካርላይልማ ሆነ ተብሎ ነው የሚደረገው ይላል ”

“ ኧረ ሚስዝ ካርላይል !

እሱ አንደዚህ ብሎ ሲነግረኝ እኔም እንዳንቺ ጮኩበትና እጄን ከንፈሮቹ ላይ ጣልኩበት እሱም ሥቆብኝ ሲያበቃ የዓለምን ክፋት ግማሹን አንኳን አለማወቄን ነገረኝ " አመሰግንሻለሁ " አለቻት ሚስዝ ካርላይል ልጂቱን ከማዳም ሼን እየተቀበለች ቆንጆ ልጅ አይደለችም ? አና የሚለውን ስምስ ወደድሽው ?

ቀላል ስም ነው ቀላል ስሞች ሁልጊዜም ደስ ይላሉ” አለች ሳቤላ "
አርኪባልድ ልክ እንዳንች ረጅም ስም አልወድም አለና የኔን የእኅቱንና የራሱን ስም ምሳሌ አድርጐ ነገረኝ " አሁን “ባርባራ የሚለውን ስም እወደዋለሁ ብሎ ልጂቱን ባርባራ ብሎ ስም አወጣላት » ስለዚህ አን ባርባራ ትባላለች የመጀመሪያው መጠሪያዋ ሁለተኛው ደግሞ ሙሉ ስሟ ሲመዘገብ የምትጠቀምበት
ነው ...

“ ክርስትና ገና እልተነሣችም ...አይደለም ? " አለች ማዳም ቬን "

ጥምቀት ብቻ ነው ዊልያም ባይሞት ኖሮ ቀደም ብለን እናስነሳት ነበር።
ሌላው ደግሞ የመንድሜ የሪቻርድ ጉዳይ የሊንበራው ፍርድ ቤት የሚለው እስኪ
ለይለት ስንል ነበር የቆየን " በርግጥ ለክርስትና ድግስ አናደርማፈግም ”

"ሚስተር ካርላይል ' ኮ ለክርስትና መደግስ አይወዱም ”አላች ሳቤሷ .

በምን አወቅሽ ? ” ጠየቀች ባርባራ ዐይኖን አፍጣ " ምስኪን ማዳም ቬን ፊቷ ልውጥ አለ » የኢስትሊን ባለቤትነቷ ቅዠት እንዲህ ዐልፎ ዐልፎ ልቧን ስውር ያደርገ ነበር" ለባርባራ ጥያቄ ክው ብላ ደነገጠችና " ሰዎች ሲሉ ስምቾ ነሙ ” አለች "

“እውኑት ነው አለች ባርባራ » “ ለማንኛውም ልጅ የክርስትና ድግስ አድርጎ አያሙቅም በጸሎት በሚፈጸመው ሥነ ሥርዓትኖ በአንድ ላይ ተሰባስቦ መብላት መጠጣትና ዓለማዊ ፈንጠዝያ በማድረግ ያለው ልዩነት ሊገናኝለት አልቻለም

ማዳም ቬን፡ ከባርባራ ዘንድ ወጥታ ወደ ክፍሏ ስትሔድ ወጣቱ ሎርድ ቬን
በየማእዘኑ አንገቱን እያሰገገ በመቃኘት“ ሎሲ! ሎሲ! ” እያለ የተንከለከአለ
እየተጣራ መጣ።

“ ለምን ፈለግኻት ?” አለችው ማዳም ቬን "

“እሱን ልነግርሽ አልችልም” አላት በፈረንሳይኛ „ “ የኢትን ተማሪ ስለ ነበር አጋጣሚ ሲያመቸው የፈረንሳይኛ ችሎታውን ማሳየት ደስ ይለው ነበር »

“ ሉሲ አሁን እያጠናች ስለሆነ ልትመጣ አትችልም ” አለችው " ለምን
እንደ ፈለጋት አሁንም መልሶ በፈረንሳይኛ ሲነግራት ሳትወድ ሣቅ ኤለችና “ከፈረንሳይኛ አርቲ ቡርቲ የእንግሊዝኛ ቁም ነገር? ምነው ብትናግር " አለችው

“ እንግዲያው የግድ ማወቅ ከፌለግሽ ቁም ነገሩ ሎሲን እፈልጋታለሁ እሷን ማግኘት አለብኝ " በትንሹ ሠረገላ ሽሮሽር ልወስዳት እፈልጋለሁ እሷም ተስማምታለች " ጆን ሠረገላውን እያዘጋጀ ነው ”

“ የለም አልፈቅድልሀም " አንተ ሠረገላ ላይ ከወጣች በኋላ ልታስፈራራራ
ልትረብሻት ነው የፈለግኸው ?

“ግድ የለሽም " እኔ በጣም ነው የማስብላት " ሠረገውን ዝግ አድርጌ እነዳለሁ " እሷኮ ሚስቴ ልትሆን ነው ... ታውቂያለሽ? ”

ማዳም ቬን ልጁን ክንዱን ይዛ ወደ መስኮቱ ወስዳ“ ስለ ሎሲ ካርላይል
እንደዚህ ብለህ የምትናግር እናቷ በሠራችው አጢአት እንክን እንዳለባት ረስተህው ነው?

“ እናቷ ሎሲ ማለት አይደለችም "

“ላንተ ባይመስልህም ሎርድ ማውንት እስቨርንና ወይዘሮ ማውንት እስቨርን
ቢሰሙ አይወዱልህም "

“ አባቴ ምንም አይልም !እናቴን ግን አሳምናለሁ" የእርቅ ፍልሚያ እፉለማታለሁ .... ገባሽ ጠላትን ማሳመን።

ማዳም ቬን ሰውነቷ ተረበሽ መሐረቧን አውጥታአፏ ላይ አደረግች።

ልጁም እጆቿ እንዴት እንደሚንቀጠቀ አየ "

“ሉሲን ክፉኛ ለመድኳት አብሬአት ባሳለፍኰዋቸው ጥቂት ወሮች ውስጥ
አንደ እናትና ልጅ ሆነን ነው የቆየን " ዊልያም ቬን . . እኔ በቅርቡ ምድራዊ ልዩነቶች ወደሌሉበት በደልና ኀዘን ወደማይታዩበት ዓለም እሔዳለሁ " ምናልባት እንዳሳብህ ሆኖልህ ከዘመናት በኋላ ሎሲ ካርላይል ሚስትህ ለመሆን ብትበቃ የናቷን ጥፋት እንዳታነሣባት አደራህን " ካነሳህባት ያሠቅቃታል
አለጥፋቷ ትጨነቃለች » የዚያች የዕድለ ቢስ እናቷ በደል የሷም በደል ነው » ስለዚህ የናቲቱ ኃጢአት ከናቲቱ ጋር እንደ ተቀበረ ቁጠረው » ለሎሲ ስለናቷ እንዳታነሳባት” አለችው .

"የለም ' የለም ! ሚስቴ ከሆነች በኋላ ስለናቷ ሁልጊዜ ነው የማነሣላት "
በዚህ ዓለም ከራሷ ከሉሲ በቀር እንደ መቤት ሳቤላ የምወደው ሰው እንዳልነበረ
አጫውታታለሁ " ሎሲን የምወዳት በናቷ ስለሆነ የናቷን ጥፋት የሲ መስደቢያ አላደርገውም " ይህ ቃሌ ነው ”
👍156👎1
“ በል ያባሃት እንደሆነ ውደዳት አክብራት " ይህን የምነግርህ እንደ ምሞት ሁኘ ነው " የሟቹን አደራ እንድትወጣ "

“ ግድ የለም በዚህ ቃል እገባልሻለሁ 'ግን ምን ማለትሽ ነው? ባሰብሽ
እንዴ ” አላት "

ማዳም ቬን ምንም መልስ ሳትሰጠው ሸርተት ብላ ሔደች "

ምንም እንኳን ወራቱ በጋ አየሩም ሙቀት ቢሆንም› ማታ ጊዜ የአንገት
ልብስ ደራርባም ከግራጫው ሳሎን ተቀምጣ በርዷት ስትንሰፌሰፍ በሩ ተንኳኳ“

“ ይግቡ ” አለች በግድየለሽነት ።

የገባው ሚስተር ካርላይል ነበር " ልቧ ጎኗን እየጐሸመው ከተቀመጠችበት ተነሣች » እንደዚያ ድንግርግር ብሏት እንደ ተቸገረች ወንበር አስጠጋችለት አጁን ከቀረበለት ወንበር ላይ አሳርፎ እሷንም እንድትቀመጥ አመለከታት "

“በጤንነትሽ ሁኔታ ከኛ ጋር ለመኖር ስለ አልቻልሽ ለመሔድ መፈለግሽን
ሚስዝ ካርላይል አሁን ነገረችኝ ” አላት "

“ አዎን ጌታዬ "

ምንድነው ችግርሽ ? ”

"እኔ እንደ መሰለኝ ዋናው መድከም ነው ድካም ድካም ይለኛል እያለች ተንተባተበች "

ሰዎች ዊልያምን በቅርብ ስታስታምሚ ስለ ነበር የሱ በሽታ ሳይጋባብሽ እንዳልቀረ ሲናግሩ ሰምቻለሁ " እኔ ግን አልመስለኝም ” አላት

“ ከሱ ነው የተላለፈብኝ ማለት? ” አለችና፡ “ይልቅንስ ሊመስል የሚችለው” ብላ ቀጥ አለች » ያለችበትን ሁኔታ በመዘንጋት ሊታወቅ የማትፈልገውን ነገር
እንዲታወቅ የማድረግ አባዜ አሁንም አልተዋትም ልትናገረው ጀምራው ከከንፈሯ አድርሳው የመለሰችው ቃል ከኔ ወርሶት ይሆኖል የሚል ነበር ሆኖም ቶሎ ዘወር አደረገችና የኔ መታመም ብዙ አያስገርምም » በቤተሰቤም በሽታ የተለመደ ነገር ነበር ” አለችው "

ያም ሆነ ይህ ወደ ኢስት ሊን ከመጣሽ በኋላ የኔን ልጆች ስትንከባከቢ ስለሆነ የታመምሺው ' እኛ ደግሞ ጤንነትሽን ለመመለስ የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ መፍቀድ አለብሽ " ለምንድነው ሐኪም እንዲያይሽ
የማትፈጊው።?

“ ሐኪም ምንም ፋይዳ አይሠራልኝም " "

በርግጥ በግንባር ቀርበሽ ችግርሽን ነግረሽ ካማhርሺው ምንም ሊያደርግልሽ አይችልም "

የለም ጌታዬ ... ሐኪሞች ከበሽታዬ ሊያድኑኝ ወይም ዕድሜዬን ሊቀጥሉልኝ አይችሉም " "

“ ግን ሁኔታሽ የሚያሠጋሽ ይመስልሻል ?

“ በርግጥ የቅርብ ሥጋት የለብኝም ይዞታዬን ስገምተው ግን ብዙ የምኖር አይመስለኝም "

' እና በዚህ ሁኔታ እያለሽ ሐኪም እንዲያይሽ አትፈልጊም ማዳም ቬን ?
እንደዚህ የመሰለ ነገር በቤቴ እንዲቀጥል እንደማልፈቅድ ማወቅ አለብሽ ። በአደገኛ በሽታ ተይዘሽ ሐኪም አልፊልግም ማለት ! ”

“ በሽታዬ ከአእምሮዬ ነው ። እሱም ከኀዘን ብዛት የመጣ ስለሆነ ማንም ሐኪም ሊረዳኝ አይችልም " ልትለው አልደፈረችም " ይኸን ተወችና ' “ ካስፈለገ ሚስተር ዌይንራይት ይየኝ ሌላ አያስፈልግም ይኸውም ለእርስዎ ደስ ይበል ብዬ ነው ” አለችው ።

“ ደኅና ነው እኔ እነግረውና ይመጣል " ሠራተኞች ሁሉ አንቺን እስኪሻልሽ
ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ይታዘዙሻል " ምንም ይሉኝታ እንዳይዝሽ ። የመሔድሽን ነገር ግን ሚስዝ ካርላይል እስክትመለስ ድረስ ለመቆየት መስማማትሽን ነግራኛለች የኔ ተስፋ ደግሞ እሷ እስክትመለስ ድረስ ምናልባት በጐ ትሆኝና ሐሳብሺን ለውጠሽ ከኛ ጋር ትቆዬ ይሆናል ነው በተለይ ማዳም ቬን ...ስለ ልጄ ስለ
ሉሲ ብለሽ እንደምትቀሪ አምናለሁ ” ብሎ እየተናግረ ብድግ አለና እጁን ዘረጋላት እሷም እየተጨነቀች እጅዋን ስትሰጠው ጥብቅ አድርጎ ይዞ ወደ መሬት
ያቀረቀረውን ፊቷን እያየ ' “ ውለታሺን በምን ልመልሰው ? ለዚያ ከንቱ ሆኖ ለቀረው ልጄ ለነበረሽ ፍቅርና ላደረግሽው ጥረት እንዴት አድርጌ ላመስግንሽስ?” አላት "

“ ለሱ አይዘኑ ። እሱ ዐረፈ ። ስለ አሰቡልኝ በጣም አመሰግናለሁ

”ሚስተር ካርላይል እንደገና እጅዋን ጨብጦ ወጥቶ ሔደ " እሷም የሞት መሐሪነቱ ቶሎ መምጣቱ መሆኑን እያሰበች ራሷን ከጠረጴዛ ደፍታ ተቀምጣ ቀረች።.....


💫ይቀጥላል💫
👍20🔥1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

...አይሮፕላኑ ወደ ኋላ የማይመለስበት ቦታ ላይ ሊደርስ የቀረው ትንሽ ነው፡፡ ኤዲ አዕምሮው በጭንቀት እንደተወጠረ ከምሽቱ አራት ሰዓት ወደ ስራው ተመልሶ ገብቷል፡ በዚህ ሰዓት ፀሃይ ጠልቃ ጨለማ ነግሷል፡፡
የአየር ጠባዩም ተለውጧል፡፡ዝናቡ
የአይሮፕላኑን መስታወቶች
ይጠልዛቸዋል ኃይለኛው ነፋስ አይሮፕላኑን እንደወረቀት ስለሚወዘውዘው
ተሳፋሪዎቹን ጭንቀት ውስጥ ጥሏቸዋል፡

የአየር ጠባዩ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ መጥፎ ቢሆንም ካፒቴኑ
የሚያበረው ባህሩ ጋ አስጠግቶ ነው፡፡ ከምዕራብ አቅጣጫ የሚመጣው ነፋስ
ዝቅተኛ የሆነበትን ከፍታ ለማግኘት ሲል ነፋሱን እያሳደደ ነው፡፡

የአየር ጠባዩ በትንበያው ከተገመተው በላይ እየተበላሸ በመምጣቱ
ሞተሮቹ ከተጠበቀው በላይ ነዳጅ አቃጥለዋል፡ ኤዲ ነዳጁ አነስተኛ መሆኑን በማወቁ ተጨንቋል፡፡ በነዳጅ ማጠራቀሚያው ውስጥ በቀረው ነዳጅ ምን ያህል ኪሎ ሜትር ሊሄድ እንደሚችል ለማስላት የስራ ቦታው ላይ ቁጭ አለ፡፡ የቀረው ነዳጅ ኒውፋውንድ ላንድ ካናዳ የማያደርስ ከሆነ አይሮፕላኑ ወደ ኋላ መመለስ የማይችልበት ቦታ ከመድረሱ በፊት ወደኋላ መመለስ አለበት።

ታዲያ ካሮል አን ምን ሊውጣት ነው?

ቶም ሉተር ጠንቃቃ በመሆኑ አይሮፕላኑ ሊዘገይ የሚችል መሆኑን ግምት ውስጥ አስገብቶ ከጓደኞቹ ጋር ያለውን ቀጠሮ ለማስረገጥ ወይም
ለማስለወጥ መንገድ ይፈልጋል፡፡

አይሮፕላኑ ወደ ኋላ የሚመለስ ከሆነ ካሮል አን በአፋኞቿ መዳፍ ስር ለሃያ አራት ሰዓት መቆየቷ ነው፡፡ ኤዲ ከስራ ውጭ በሆነበት ጊዜ ሁሉ አስሬ በአይሮፕላኑ መስኮት ሲመለከት አመሸ፡፡ እንቅልፍ እንደማይወስደው ስላወቀ ለመተኛት እንኳ አልሞከረም፡፡ ካሮል አን በዓይነ ህሊናው እየታየችው ጭንቅ ጥብብ ብሎታል ወይ ስታለቅስ ወይ እጅ እግሯ ታስሮ ወይ በድብደባ ቆስላ ወይ ፍርሃት ፍርሃት ብሏት ወይ ተስፋ ቆርጣ ትታየዋለች፡፡ ምንም ሊያደርግላት አለመቻሉን ሲያስበው በንዴት የአይሮፕላኑን ግድግዳ በጡጫ ይጠልዘዋል፡
አንድ ሁለት ጊዜ ደግሞ ለእሱ ተተኪ ለሆነው ሚኪ ፊን ስለአይሮፕላኑ የነዳጅ ፍጆታ ለመንገር በደመነፍስ በደረጃው እየወረደ ከራሱ ጋር እየታገለ ሳይነግረው ተመልሷል፡

ኤዲ ቶም ሉተርን በመብል ክፍሉ ውስጥ በነገር የነካካው አዕምሮው
በመረበሹ ነው፡፡ ቶም ሉተር ደግሞ ብዙም አይናገርም፡፡ እድሉ ሲጠም.ደግሞ ሁለቱ አንድ ጠረጴዛ ላይ ለመብል ተገናኙና አረፉት፡፡ ከራት በኋላ ኤዲ ምን ያህል ስርዓት የጎደለው ተግባር በተሳፋሪ ላይ ሲፈጽም እንደነበረ ጃክ ሲነግረው አመሸ፡፡ ኤዲና ቶም ሉተር የተጣሉበት ነገር እንዳለ ጃክ አውቋል፡፡ ጃክ ኤዲ ብዙም ሊነግረው እንዳልፈለገ ስለገባው ለአሁኑ ያለውን ተቀብሎታል፡፡ ኤዲ ከዚህ በኋላ መጠንቀቅ እንዳለበት አምኗል፡፡ ካፒቴን ቤከር የበረራ መሀንዲሱ የተሳፋሪዎችን ደህንነት የሚጎዳ ተግባር በግዴታ
እንዲፈጽም መታዘዙን ከጠረጠረ እንኳን አይሮፕላኑን ወደ ኋላ ከመመለስ አይቆጠብም፡፡ ይህም ኤዲ ሚስቱን ከእገታው ለማውጣት የሚያደርገውን መፍጨርጨር ያደናቅፍበታል፡፡ ስለዚህ ካፒቴኑ አንድም ነገር ማወቅ የለበትም።

በመርቪን ላቭሴይና በሎርድ ኦክሰንፎርድ መካከል የተነሳው
ጠብ ትዕይንት ኤዲ በቶም ሉተር ላይ ያሳይ የነበረውን ሁኔታ
እንዲረሳ አድርጎታል፡፡ ኤዲ ሌላ የአይሮፕላኑ ክፍል ውስጥ ሆኖ በሃሳብ ተውጦ ስለነበር አላየም፡፡ በኋላ ግን አስተናጋጆቹ የነበረውን ሁኔታ አጫወቱት።ሎርድ ጨካኝ ሰው መሆኑን በመረዳቱ ካፒቴኑ አደብ እንዲገዙ ማድረጉ ኤዲን አስደስቶታል፡ ኤዲ ታዳጊው ፔርሲ በዚህ እርጉም ሰው እጅ
ማደጉ አሳዝኖታል፡

ራት ከተበላ በኋላ ተመልሶ ጸጥታ መንገሱ አይቀርም፡፡ በእድሜ የገፉት ተሳፋሪዎች በየመኝታቸው ላይ ይሰፍራሉ፡፡ ብዙዎቹ በአይሮፕላኑ ውዝዋዜ
እንቅልፍን አጥተውት
ሲያንጎላጁ ያመሻሉ፡፡ ከዚያም አንድ በአንድ እያሉ ይተኛሉ፡፡ እንቅልፍ የማይጥላቸው ተሳፋሪዎች ደግሞ ወይ ካርታ ሲጫወቱ ወይም መጠጣቸውን ሲጨልጡ ያመሻሉ፡፡

ኤዲ የአይሮፕላኑን የነዳጅ ፍጆታ በቻርቱ ላይ ይከትባል፡ በግራፉ
የተመለከተው የአይሮፕላኑ
በቀኝ በኩል የነዳጅ ፍጆታ በእርሳስ
ከተመለከተው የእሱ ትንበያ በላይ ነው፡፡ ኤዲ የሃሰት የነዳጅ ፍጆታ ትንበያ ስላሰፈረ ይህ መሆኑ አይቀርም የአየር ጠባዩ መክፋት ደግሞ በትክክለኛው ፍጆታና በትንበያው ፍጆታ መካከል ያለውን ልዩነት እንዲጎላ አድርጎታል።

በቀሪው ነዳጅ አይሮፕላኑ ሊሄድ የሚችለውን ርቀት አስልቶ ሲጨርስ
ጭንቀቱ በረታ፡፡ የአይሮፕላኑም የነዳጅ መጠን አስተማማኝነት ደንብ እንደሚያዘው የቀረውን የነዳጅ መጠን በሶስት ሞተሮች ፍጆታ ሲያሰላው እስከ ኒውፋውንድ ላንድ እንደሚያደርሰው አወቀ።

ሌላ ጊዜ ቢሆን ይህን ሲያውቅ ለካፒቴኑ ወዲያውኑ መንገር አለበት፡ አሁን ግን አልነገረውም፡፡

የነዳጅ መጠኑ በአራት ሞተር ሲሰላ የነዳጅ እጥረቱ በጣም ስለሚያንስ
ምንም አያስጨንቅም፡፡ ከዚህም በላይ የአየር ጠባዩ ከተወሰኑ ሰዓቶች በኋላ ጸጥ ያለ ይሆን ይሆናል፡ የንፋሱ ግፊት ቀለል ያለ ከሆነ አይሮፕላኑ ከተተነበየው ያነሰ ነዳጅ ስለሚጠቀም ለቀረው ጉዞ ነዳጅ ሊተርፍ ይችላል የከፋ ነገር ከመጣ ደግሞ ርቀቱን ለማሳጠር ሲሉ የጊዜ አቅጣጫቸውን
ይለውጡና በሞገደኛው ንፋስ ውስጥ ይጓዛሉ፡፡ በዚህ አይነት ጉዞ ግን የሚሰቃዩት ተሳፋሪዎች ናቸው፡፡

ከኤዲ በስተግራ የተቀመጠው ራሰ በራው ቤን ቶምሰን በሞርስ ኮድ
የተቀበለውን የሬዲዮ መልእክት ወደ ጽሑፍ እየቀየረ ነው፡፡ ኤዲ ከፊታቸው ያለው የአየር ጠባይ የተሻለ እንዲሆን በመመኘት ከቤን ኋላ ሆኖ መልእክቱን ያነባል፡

የመጣው መልእክት ግን ማስደነቅ ብቻ ሳይሆን እንቆቅልሽ ሆኖበታል፡
መልእክቱ የተላከው ኤፍ.ቢ..አይ ኦሊስ ፊልድ ለሚባል ተሳፋሪ ሲሆን

‹ብቁጥጥር ስር ያለው እስረኛ ተባባሪ ሊሆኑ የሚችሉ ከተሳፋሪዎቹ መካhል ያሉ ስለሆነ በጥብቅ ክትትል አድርግ›› ይላል፡

ምን ማለት ነው? ከካሮል አን አፈና ጋር ግንኙነት አለው ይሆን ይህ
መልእክት?› ሲል አሰበ ኤዲ፡ ይህ ሊሆን እንደሚችል ሲያስበው ራሱን
አዞረው።

ቤን የኮድ ትርጉሙን ቀዶ
«ካፒቴን ይህን መልእክት ብታየው›› ብሎ ለአለቃው አቀበለው፡፡

ጃክ አሽፎርድ የሬዲዮ መገናኛ ባለሙያው አስቸኳይ መልእክት መኖሩን ሲናገር ሰምቶ ከሚያፈጥበት ቻርቱ ላይ ቀና አለ፡፡ ኤዲ ከቤን መልእክቱን ተቀብሎ ለጃክ አሳየውና ራቱን እየበላ ላለው ካፒቴን አሳየው።

ካፒቴኑ መልእክቱን አነበበና ‹‹እንዲህ አይነት ነገር ነው የማልወደው›› አለ፡፡ ‹‹ኦሊስ ፊልድ የኤፍ.ቢ..አይ አባል ሳይሆን አይቀርም::››

‹‹ተሳፋሪ ነው?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡፡

‹‹አዎ፡፡ ሰውየው እንግዳ ባህሪ ነው ያለው፡ ድብርታም ነው፡፡ የተሳፋሪ
ሁኔታ የለውም: ፎየንስ ላይ ቆይታ ሲደረግ ከአይሮፕላኑ ላይ አልወረደም›› አለ፡፡

ኤዲ ሰውየውን ባያስተውለውም ናቪጌተሩ ጃክ ግን አይቶታል፡
‹‹ያልከውን ሰው አውቄዋለሁ›› አለ ጃክ አገጬን እያከከ፡፡ ‹‹ራሰ በራ
ነው፡፡ አብሮት ልጅ እግር ሰው ተቀምጧል፡ ሰዎቹ ሲታዩ ምናቸውም አይጥምም::››
👍22
‹‹ወጣቱ ሰው እስረኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ስሙ ፍራንክ ጎርደን
ይመስለኛል›› አለ ካፒቴኑ።
‹‹ለዚህ ነው ፎየንስ ላይ ሁለቱ ሰዎች ከአይሮፕላኑ ያልወረዱት።
የኤፍ..ቢ.አዩ ሰው ወጣቱ ከእጁ እንዲያፈተልክ አልፈለገም›› አለ ኤዲ ካፒቴኑ ራሱን ነቀነቀና ‹‹ጎርደን ከእንግሊዝ አገር ታድኖ የመጣ እስረኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከውጭ አገር ታድነው ወደ አገራቸው የሚመለሱ እስረኞች ደግሞ አደገኛ ወንጀለኞች ናቸው፡ ይህን ሳይነግሩኝ አይሮፕላኔ
ላይ ይህን ጠብደል ወንጀለኛ ጭነዋል›› አለ ካፒቴኑ።

የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ቤን ‹‹ምን አጥፍቶ ይሆን?›› ሲል ጠየቀ።

‹‹ፍራንክ ጎርደን›› አለ ጃክ ‹‹ይሄ ስም አዲስ አይደለም እስቲ ቆዩማ
ፍራንክ ጎርዲኖ ነው ይሄ ሰውዬ››
ኤዲ ስለ ፍራንክ ጎርዲኖ ጋዜጣ ላይ ማንበቡ ትዝ አለው፡፡ በአሜሪካ
ኒው ኢንግላንድ ስቴት የማፊያ አባል ነው፡፡ የተወነጀለው አንድ ለማፊያ ቡድኑ ጉልቤዎች ገንዘብ አልከፍል ያለን የምሽት ክበብ ባለቤት ገሏል፣ውሽማውን ደፍሯል እንዲሁም የምሽት ክበቡን በእሳት አጋይቷል በሚሉ ወንጀሎች ተወንጅሏል፡ ውሽሚት ከእሳቱ ተርፋ ወንጀሉን የፈጸመው
ጎርዲኖ መሆኑን ለፖሊስ ተናግራለች፡
‹‹ወጣቱ ሰው ፍራንክ ጎርዲኖ መሆኑን እናረጋግጥ›› አለ ቤከር፡፡ ‹‹ኤዲ ሮጥ በልና ኦሊስ ፊልድን እንደምፈልገው ንገረው››

‹‹እሺ ጌታዬ›› አለና ኤዲ በደረጃው ወርዶ ወደ ተሳፋሪዎች ክፍል ገባ፡፡
ፍራንክ ጎርዲኖ ካሮል አንን ካገቷት ሰዎች ጋር የሆነ ግንኙነት ሳይኖረው
አይቀርም ሲል ገመተ፡

በአይሮፕላኑ በስተመጨረሻ ላይ አንድ እድሜው አርባ ዓመት
የሚገመት ራሰ በራ ሰው በአይሮፕላኑ መስኮት አሻግሮ ጨለማውን እያየ ሲጋራውን ያቦናል፡፡ ኤዲ ይህን ሰው ሲያየው ሽጉጡን ደግኖ ወሮበሎች
የተጠራቀሙበትን ክፍል በር በርግዶ የሚገባ ሰው አልመስልህ አለው፡ ከኦሲስ ፊልድ ፊት ለፊት ስፖርት በማቆሙ ሰውነቱ እየወፈረ የመጣ ስፖርተኛ የሚመስል ጥሩ የለበሰ ወጣት ሰው ተቀምጧል፡፡ ጎርዲኖ እሱ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ወጣቱ ሰው ሲያዩት አመለ ብልሹ ልጅ ይመስላል፡
ይህ ወጣት ሰው ጥይት ተኩሶ መግደል ይችላል?› ሲል ኤዲ ራሱን
ጠየቀ አዎ ሳይገል አይቀርም› አለ መልሶ በሆዱ፡፡

‹‹ሚስተር ፊልድ ነህ?›› አለው ትልቁን ሰው፡

‹‹አዎ›› አለ ፊልድ

ፊልድ ካፒቴኑ እንደሚፈልገው ሲነግረው ግራ ገባው: ምስጢሩ
የታወቀ መስሎት ተናደደ፡፡ ቢሆንም እሺ አለና ሲጋራውን መተርኮሻ ላይ
አጥፍቶ የመቀመጫ ቀበቶውን ፈቶ ተነሳ፡፡

‹‹ሚስተር ፊልድ ተከተለኝ›› አለ ኤዲ፡፡

ፊልድን ወደ ካፒቴኑ እየመራ ሲሄድ ከቶም ሉተር ጋር ዓይን ላይን
ግጥም ሲሉ በዚያው ቅጽበት አንድ ሃሳብ ብልጭ አለለት፡፡

የቶም ሉተር ተልዕኮ ፍራንክ ጎርዲኖ በፖሊስ እጅ እንዳይወድቅ
ማድረግ ነው፡፡

ኤዲ የገባውን ግዴታ በመተው አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል የሚል ስጋት ገብቶት ሉተር በድንጋጤ ኤዲ ላይ አፈጠጠ፡፡
አሁን ሁሉ ነገር ለኤዲ ግልጽ ሆነለት፡ ፍራንክ ጎርደን ከአሜሪካ
ሸሽቶ ቢወጣም ኤፍ.ቢ..አይ ዱካውን ተከታትሎ እንግሊዝ ውስጥ ያዘውና ወደ አሜሪካ ሊወስደው ነው፡፡ በአይሮፕላን እንደሚወሰድ መወሰኑን የማፊያ
ቡድኑ ማወቁ አልቀረም፡፡
አይሮፕላኑ አሜሪካ ከመድረሱ በፊት አንድ ቦታ
ላይ ጎርዲኖን ለማስመለጥ ይጥራሉ ማለት ነው፡፡

እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ኤዲ የተፈለገው አይሮፕላኑ በካናዳና
አሜሪካ ድንበር ሜይን ስቴት ጠረፍ አጠገብ እንዲያርፍ ይደረግና እዚያም ፈጣን ጀልባ ላይ ተጋብቶ ይዘውት ጥርግ ይላሉ፡፡ ከዚያም ካናዳ ውስጥ አንድ ቦታ ይደብቁትና በመኪና ወደ መሸሸጊያው ይወሰዳል፡፡ በዚሁ ሁኔታ
ከህግ ያመልጣል፤ ለኤዲ ምስጋና ይግባውና፡፡
ፊልድን ወደ ካፒቴኑ እየወሰደ እያለ አጠቃላይ ዕቅዳቸው ምን እንደሆ
ሲረዳ እረፍት ቢሰማውም ሚስቱን ለማዳን ሲል ነፍሰ ገዳይ እንዲያመልጥ መርዳቱ በአንጻሩ አበሳጭቶታል

‹ካፒቴን ሚስተር ፊልድ ማለት እሱ ነው›› አለ ኤዲ

ካፒቴኑ ዩኒፎርሙን ለብሶ በእጅ የሬዲዮ መልእክቱን ይዞ ቁጭ
ብሏል፡ ራት በልቶ ስለጨረሰ ገበታው ከፍ ብሏል፡በኮፍያው ስር
የሚታየው ቃጫ መሳይ ጸጉሩ የአዛዥነት ክብር አጎናጽፎታል
የሚታየው በተቀመጠበት ቀና ብሎ ፊልድን ‹‹ከኤፍ.ቢ.አይ ላንተ የተላከ መልእክት ተቀብያለሁ›› አለው

ፊልድ ወረቀቱን ከካፒቴኑ ለመቀበል እጁን ቢዘረጋም ካፒቴኑ ግን አልሰጠውም፡

‹‹የኤፍ..ቢ.አይ ነጭ ለባሽ ነህ?›› ሲል ጠየቀው::
‹‹አዎ››
‹‹አሁን በግዳጅ ላይ ነህ ያለኸው?››
‹‹አዎ››
‹‹ምንድነው ግዳጅህ ሚስተር ፊልድ?››
‹‹ማወቅ ያለብህ አይመስለኝም ለኔ የተላከ ስለሆነ ወረቀቱን ብትሰጠኝ፡››

‹‹እኔ የዚህ አይሮፕላን አዛዥ በመሆኔ ግዳጅህ ምን እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ፡ ከኔ ጋር ባትከራከር ጥሩ ነው ሚስተር ፊልድ፡››

ኤዲ ፊልድን በትኩረት አየው: ፊቱ የገረጣና ድካም የሚታይበት
ሲሆን ዓይኑ እምባ አንቆርዝዟል፡ ቁመቱ ሎጋ ሲሆን በአንድ ወቅት
ሰውነቱ በስፖርት የተገነባ እንደነበር የሚያስታውቅ ቢሆንም አሁን ቆዳው ተሸብሽቧል፡ ፊልድ ጋጠወጥ እንጂ ጎበዝ እንዳልሆነ ኤዲ አውቋል፡ ይህን ማለት ያስቻለው በካፒቴኑ የተደረገበትን ግፊት መቋቋም አቅቶት ወዲያው
እጁን በመስጠቱ ነው።

‹‹ወደ አሜሪካ ሄዶ ፍርዱን የሚቀበል አንድ እስረኛ አጅቤ እየወሰድኩ ነው ፍራንክ ጎርደን ይባላል›› አለ ፊልድ፡

‹‹ፍራንክ ጎርዲኖ ነው?››

‹‹አዎ ነው››

‹‹ሰውዬ ሳትነግረኝ አደገኛ
ወንጀለኛ በአይሮፕላኔ ውስጥ ማጓጓዝ ተገቢ አይደለም››

‹‹ትክክለኛ ስሙን ብታውቅ በምን እንደሚተዳደር ታውቅ ነበር፡፡ ከሮድ
አይላንድ ስቴት እስከ ሜይን ስቴት በዘረፋ፣ በማስፈራራት፣ በአራጣ
ማበደር፣ በህገወጥ ቁማርና ሽርሙጥና በማስፋፋት ተግባር የታወቀው የሬይ ፓትሪያርካ ተቀጣሪ ነው፡፡ ሬይ ፓትሪያርካ ቁጥር አንድ ወንጀለኛ ተብሎ በመንግስት የሚፈለግ ሰው ነው: ጎርዲኖ ደግሞ በፓትሪያርካ ትዕዛዝ
ሰዎችን ያስፈራራል፣ ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ያሰቃያል፣ ይገድላል። ላንተ አስቀድመን ያልነገርንህ ለደህንነት ጥበቃ ተብሎ ነው።››

‹‹እንዲህም ብሎ የደህንነት ጥበቃ›› ሲል ተቆናጠረ ካፒቴኑ።
ኤዲ ካፒቴኑ ተሳፋሪ ላይ ሲጮህ አይቶት አያውቅም።

‹‹የፓትሪያርካ ቡድን ሁሉን ነገር አውቆላችኋል›› አለና ወረቀቱን
ለፊልድ ሰጠው ካፒቴኑ።

ፊልድ የሬዲዮ መልእክቱን አንብቦ ሲጨርስ ፊቱ በድንጋጤ አመድ
መሰለ፡ ‹‹እንዴት ሊያውቁ ቻሉ?›› ሲል አጉተመተመ።

‹‹የትኞቹ ተሳፋሪዎች የእሱ ተባባሪዎች እንደሆኑ ማወቅ እፈልጋለሁ››አለ ካፒቴኑ። ‹‹ከተሳፋሪዎቹ መካከል የምታውቀው አለ?››

‹‹እንዴት ላውቅ እችላለሁ? አለ ፊልድ በንዴት። ባውቅ
ለኤፍ.ቢ.አይ አላሳውቅም ነበር?››

‹እነማን እንደሆኑ ቢነገረኝ አይሮፕላኑ በሚቀጥለው የሚያርፍበት ቦታ ላይ አስወርዳቸው ነበር›› አለ ካፒቴኑ፡
ኤዲ እኔ አውቄአቸዋለሁ ቶም ሉተርና እኔ ነን› አለ በሆዱ፡

ፊልድም ቀጠለና ‹‹የተሳፋሪዎቹን ስም ዝርዝር በሬዲዮ ለኤፍ.ቢ.አይ
አሳውቅና እያንዳንዱን ስም ያጣራልሃል›› አለ፡

ኤዲ ይህን ሲሰማ ፍርሃት ወረረው፡

በዚህ ማጣራት ቶም ሉተር ይጋለጥ ይሆን? እሱ ከተጋለጠ ደግሞ
ሁሉ ነገር አፈር በላው ማለት ነው። የታወቀ ወሮበላ ይሆን? ቶም ሉተርስ እውነተኛ ስሙ ነው፡ የሀሰት ስም የሚጠቀም ከሆነ የሀሰት ፓስፖርት ያስፈልገዋል፡ ከትልልቆቹ ማፍያ ቡድኖች የአንዱ አባል ከሆነ ደግሞ ይህን ማድረግ ችግር ሊሆን አይችልም። እንዲህ ያለውን ጥንቃቄ ደግሞ ማድረግ
አይቀርም፡ ሌላው ያደረገው ነገር በሙሉ በጥንቃቄ የተሰናዳ ነው።
👍13
ካፒቴን ቤከር ብልጭ አለበት።
‹‹በዚህ ምክንያት የአይሮፕላኑ
ሰራተኞች እንዲጨነቁ ማድረግ የለብንም›› አለ፡

ፊልድም ትከሻውን ነቀነቀና ‹‹እንደፈለግህ። ኤፍ ቢ.አይ የአይሮፕላኑን ሰራተኞች ስም ከፓን አሜሪካን አየር መንገድ በደቂቃ ውስጥ መውሰድ ይችላል›› አለ።

ካፒቴኑ የተሳፋሪዎቹንና የአይሮፕላኑን ሰራተኞች ስም ዝርዝር የያዘ ወረቀት ከጠረጴዛው ኪስ አውጥቶ ለሬዲዮ ኦፕሬተሩ ሰጠውና ‹‹ቤን ለኤፍ...አይ ላከው›› ሲል አዘዘው።

ቤን ቶምሰንም የስም ዝርዘሩን በኮድ መልዕክት ላከው፡

‹‹አንድ ሌላ ጉዳይ አለ›› አለው ካፒቴኑ ፊልድን፡ ‹‹መሳሪያህን ለእኛ
ታስረክባለህ››

ፊልድም ‹‹አይሆንም›› ሲል ተቃወመ::

‹‹ተሳፋሪዎች የጦር መሳሪያ እንዲይዙ አይፈቀድም፡፡ ከዚህ ክልከላ ነፄ የሚሆን ሰው የለም።
ስለዚህ ሽጉጥህን አስረክበን›› ሲል አዘዘ ካፒቴኑ፡፡

‹‹ባላስረክብስ?›› ሲል ጠየቀ ፊልድ

‹‹በሰላም ካልሰጠህ ኤዲና ጃክ በግድ እንዲነጥቁህ አደርጋለሁ፡››
ኤዲ ካፒቴኑ ባለው ቢገረምም በማስፈራራት ሁኔታ ወደ ፊልድ ጠጋ አለ፡፡ ጃክም እንዲሁ አደረገ፡፡
ካፒቴኑ ቀጠለና ‹‹ኃይል እንድጠቀም የምታስገድደኝ ከሆነ በሚቀጥለው የአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦታ ላይ አስወርድሃለሁ፡››

ፊልድ የታጠቀ ቢሆንም ካፒቴኑ
የበላይነቱን መያዙ ኤዲን
አስደንቆታል፡፡ ይሄ ደግሞ በፊልም እንደሚታየው አይደለም፡፡ ፊልም ላይ ሽጉጥ የያዘ ሰው ነው ትዕዛዝ ሰጪው፡፡

ፊልድ ምን እንደሚያደርግ ጨነቀው፡፡ ኤፍ.ቢ.አይ ሽጉጡን የማስረከቡን ጉዳይ አይቀበለውም፡፡ በአንጻሩ ካላስረከበ ከአይሮፕላኑ ሊባረር ይችላል።

ፊልድም ‹‹እኔ አደገኛ እስረኛ አጅቤ እየወሰድኩ ነው፡፡ የግድ መታጠቅ
ይኖርብኛል፡ ሽጉጤ ከኔ መለየት የለበትም›› አለ፡፡

በጥግ በኩል ያለው በር ገርበብ ብሏል፡፡ ኤዲ በአይኑ ቂጥ አንድ ነገር ውልብ ሲል ታየው፡
ካፒቴን ቤከርም ‹‹መሳሪያውን ተቀበለው ኤዲ›› ሲል አዘዘ፡፡ ኤዲ
ፊልድ ጃኬቱ ውስጥ እጁን ሰደደ፡፡ ፊልድ ከቆመበት ንቅንቅ አላለም፡ ኤዲ ፊልድ ካነገተው የሽጉጥ ማህደር ቁልፉን አላቀቀና ሽጉጡን ላጥ አድርጎ አወጣው፡ ፊልድ ይሄን ሲያይ ፊቱን አቀጨመ ኤዲ ወዲያው ወደ አይሮፕላኑ ጥግ ሄደና በሩን ከፈተው፡፡ ፔርሲ
ኦክሰንፎርድ እዚያ ቆሟል፡፡ ኤዲ ትንሽ ቀለል አለው፡፡ ምናልባትም የጎርዲኖ ጓደኞች ማሽንገን ይዞ ይሆናል ሲል አሰበ፡፡

ካፒቴን ቤከር ፔርሲን ሲያየው ‹‹ከየት ነው የመጣኸው?›› ሲል
ጠየቀው፡፡ ‹‹የሴቶች መዋቢያ ክፍል አልፎ ያለውን መሰላል ወጥቼ
የአይሮፕላኑ ጭራ ድረስ ሄድኩ››
ኤዲ የኦሊስ ፊልድን ሽጉጥ የጠረጴዛው ኪስ ውስጥ ከተተው፡፡

ካፒቴን ቤከርም ፔርሲን ‹ወደ መቀመጫህ ተመለስ ከዚህ በኋላ
ከቦታህ እንዳትነሳ›› አለው፡፡ ፔርሲ ወደ መጣበት ለመመለስ ሲል ‹‹በዚያ አይደለም›› ሲል ተቆጣ ቤከር ‹‹በደረጃው ውረድ››

ፔርሲ የቤከር ቁጣ አስደንግጦት በደረጃው ሹክክ ብሎ ወረደ፡፡
‹‹ልጁ እዚያ ቦታ ምን ያህል ቆይቷል ኤዲ?›› ሲል ጠየቀ ቤከር፡
‹‹አላወቅሁም፡፡ የተባለውን ሁሉ ሳይሰማ አይቀርም›› አለ ኤዲ፡
‹‹ተሳፋሪዎች እንደማይሰሙ ተስፋ እናደርጋለን››

ቤከር የድካም ስሜት ይታይበታል፡፡ ኤዲ ካፒቴኑ የተሸከመው ኃላፊነት ቀላል እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ ካፒቴኑ እንደገና ፈርጠም ብሎ ‹ሚስተር ፊልድ ወደ መቀመጫህ ተመለስ፡፡ ስለተባበርከን አመሰግናለሁ›› አለ፡፡ ኦሊስ ፊልድም ምንም መልስ ሳይሰጥ ወደ መቀመጫው ተመለሰ፡፡

ካፒቴኑም ‹ወደ ስራችን›› ሲል አዘዘ፡፡

ሰራተኞቹ ወደየስራ ቦታቸው ተመለሱ፡፡ ኤዲ አዕምሮው ቢታመስም ፊቱ የተደረደሩትን ሰዓቶች ቃኘ፡፡ በአይሮፕላኑ ክንፍ ላይ ያሉት የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች የያዙት ነዳጅ
እየቀነሰ ስለመጣ ከዋናው ነዳጅ
ማጠራቀሚያ ወደነዚህ ጋኖች ነዳጅ ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡ ሀሳቡ ግን ፍራንኪ ጎርዲኖጋ ነው፡፡ ጎርዲኖ አንድ ሰው በመግደል፣ የሰውየውን ሚስት በመድፈርና የምሽት ክበብ በእሳት በመለኮስ ተከሶ ፍርዱን ሊቀበል
ቢዘጋጅም ለኤዲ ምስጋና ይግባውና ከቅጣት ሊድን ነው፡፡ ከዚህ የባሰው ደግሞ ጎርዲኖ ከህግ ካመለጠ በኋላ ሌላ ሰው መግደሉ አይቀርም፡
ከመግደል ሌላ ምን ስራ አለው? አንድ ቀን ጎርዲኖ ስለሰራው ወንጀል ጋዜጣ ላይ ያነብ ይሆናል። ጎርዲኖ ያቃጥል ይሆናል፤ ወይ ደግሞ አንዷን ሴት አግተው ለሶስት ይደፍሯት ይሆናል፡ ይህንንም ያደረጉት የፓትሪያርካ
ወሮበሎች ይሆናሉ፡፡ ኤዲም ጎርዲኖ ይሆን ይህን ያደረገው?› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹ታዲያ ለዚህ ወንጀል እኔ እሆን ተጠያቂው? እነዚህ ወንጀል
የተፈፀመባቸው ሰዎች ይህን ሁሉ የሚያደርስባቸው እኔ ጎርዲኖን ከህግ እንዲያመልጥ ስለረዳሁት ነው› ብሎ ማለቱ አይቀርም፡፡

ነገር ግን ጎርዲኖ እንዲያመልጥ ከማድረግ ውጪ ምን ምርጫ አለው? ካሮል አን ፓትሪያርካ መዳፍ ስር ወድቃለች፡ ይህን ባሰበው ቁጥር ቀዝቃዛ ላብ በጆሮ ግንዱ ይወርዳል፡፡ እንድትጎዳበት አይፈልግም፡፡ እሷን ለማዳን ሲል ከቶም ሉተር ጋር መተባበር አለበት፡

ሰዓቱን ተመለከተ እኩለ ሌሊት ሆኗል፡

ጃክ አሽፎርድ አይሮፕላኑ ያለበትን ቦታ በቻርት ላይ አመላከተው፡ ቤን
ቶምሰን ደግሞ የአየር ሁኔታ ትንበያውን ሰጠው፡፡ ከፊታቸው ንፋስ የቀላቀለ ዶፍ ዝናብ ይገጥማቸዋል፡ ኤዲ የነዳጅ መጠን አመልካቹን አነበበና የሚያስ
ፈልገውን የነዳጅ መጠን ስሌት ሰራ፡፡ ያለው ነዳጅ ኒውፋውንድ ላንድ የማያደርሳቸው ከሆነ ወደኋላ ዞረው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ውጥኑ ሁሉ ውሃ በላው ማለት ነው፡፡ ግን መልሶ መላልሶ ማሰቡ ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ ኤዲ በዕድል አያምንም፡፡ አንድ ነገር ማድረግ አለበት፡፡

ካፒቴን ቤከር ‹‹እንዴት አደረግኸው የነዳጁን ነገር?›› ሲል ኤዲን
ጠየቀው::

‹‹ስሌቱን ሰርቼ አልጨረስኩም›› ሲል መለሰ፡፡

‹በደንብ ተመልከተው ወደኋላ መመለስ የማንችልበት ቦታ እየደረስን ነው››
ኤዲ በላብ የተጠመቀውን ፊቱን ጠረገ፡፡

ስሌቱን ሰርቶ ቢያጠናቅቅም ቀሪው
ነዳጅ ኒውፋውንድ ላንድ እንደማያደርሳቸው አውቋል፡

በወረቀት ላይ የሰራው ስሌት ላይ አፈጠጠ ልክ ስሌቱን ያልጨረሰ
ለመምሰል

የቀረው ነዳጅ ጉዞውን ለማጠናቀቅ አይበቃም፡፡ ካፒቴኑ እንደውም ያለውን በእሱ ፈረቃ መቀየሪያ ጊዜ ከነበረው ሁኔታ ያሁኑ የባሰ ሆኗል
ነዳጅ መጠን በአራት ሞተር ስሌት እንዲሰራ ቢያስደርግም እንደማይበቃ ታውቋል፡ መጠባበቂያ ነዳጅ የሚባል ነገር የለም፡፡ አሁን ያላቸው ምርጫ
ጉዞውን ለማሳጠር ሲሉ በአውሎ ንፋሱ ዳር ዳር ሳይሆን በአውሎ ንፋሱ ውስጥ መብረር ሊኖርባቸው ነው፡፡ በአውሎ ንፋሱ መሀል የሚበሩ ከሆነ ደግሞ ሞተር ሊቃጠል ይችላል፡

በዚህ አደገኛ ጉዞ ምክንያት ተሳፋሪዎች ሊያልቁ ይችላሉ። እሱም ቢሆን ከሞት አይድንም፡፡ ታዲያ ካሮል አንን ምን ይውጣታል?

‹‹በል እንጂ ኤዲ›› አለ ካፒቴኑ፡ ‹‹ወደ ቦትውድ (ካናዳ) ወይስ ወደ
ፎየንስ (አየርላንድ) የምንበረው?››
ኤዲ ጥርሱ በፍርሃት ተንገጫገጨ፡፡ ካሮል አን በነዚህ ጨካኝ ወንበዴዎች እጅ ስር ላንድ ቀን እንኳን እንድትቆይ አይፈልግም::ተሳፋሪዎቹን ለአደጋም አጋልጦም ቢሆን ይደርስላታል፡

‹የጉዟችንን አቅጣጫ ለውጠን በአውሎ ንፋሱ መሐል ለመሄድ ዝግጁ ነን?›› ሲል ጠየቀው ካፒቴኑን፡፡

‹‹በአውሎ ንፋሱ መሃል ግዴታ ነው?›› ሲል ጠየቀ ካፒቴኑ በድጋሚ።
‹‹ያለን ምርጫ ወይ በአውሎ ንፋሱ መሃል መሄድ አለበለዚያ መመለስ
ነው›› አለና ኤዲ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡
‹‹አትላንቲክ መሃል ደርሶ ወደኋላ መመለስ የሚፈልግ የለም፡››
ኤዲ የካፒቴኑን ውሳኔ በታላቅ ጉጉት ጠበቀ፡፡
👍161
‹‹የፈለገ ይምጣ!›› አለ ካፒቴን ቤከር ‹‹አውሎ ንፋሱን ሰንጥቀን
እንበራለን›› አለ፡፡...

ይቀጥላል
🥰4
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ...አይሮፕላኑ ወደ ኋላ የማይመለስበት ቦታ ላይ ሊደርስ የቀረው ትንሽ ነው፡፡ ኤዲ አዕምሮው በጭንቀት እንደተወጠረ ከምሽቱ አራት ሰዓት ወደ ስራው ተመልሶ ገብቷል፡ በዚህ ሰዓት ፀሃይ ጠልቃ ጨለማ ነግሷል፡፡ የአየር ጠባዩም ተለውጧል፡፡ዝናቡ የአይሮፕላኑን መስታወቶች ይጠልዛቸዋል ኃይለኛው ነፋስ አይሮፕላኑን እንደወረቀት…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ባርባራ ለዕረፍት ወደ ባሕር ዳርቻ በሔደችበት ቀን ሳቤላ ከመኝታዋ ወድቃ መጠራሞት ጀመረች።

ለመሰናበት ካሰበች በኋላ እንደገና ባርባራ እስክትመለስ ድረስ ልትቆያት የተሰማማችው ከልጆቹ ጋር መሰንበቷን ተስፋ አድርጋ ነበር " ሚስተር ካርላይልም
በሽተኛዪቱ አስተማሪ ከልጆች ጩኸትና ውካታ ተላቃ ከማንኛውም ሥራ ርቃ የተሟላ ጸጥታና ዕረፍት አንድታገኝ በማሰብ ልጆቹን ሎሲንና አርኪባልድን ወደ ሚስ ኮርኒሊያ ዘንድ ሰደደቸው " ሳቤላ ልጆቹ ከእሷ ጋር እንዲሰነብቱ ሆዷ እየፈለገ እንዳይሔዱ ብላ ለመጠየቅ ፈራች ስለዚህ ያሰበችው ነገር
ሲበላሺባት በዝምታ ተቀበለችው የሳቤላ ሁለተኛዉ ሐሳቧ ደግሞ ማንነቷ እንዳይታወቅባት የመሞቻዋ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ከኢስት ሊን ሹልክ ብላ ለመልቀቅ ነገር
እንዳይደርስባት የፈራችው ሰዓት ባላሰበችው ፍጥነት ቀደማት " ጊዜ ዐለፈ ልክ እንደ እናቷ እሷንም ሳይታሰብ አጣደፋት " ዊልሰን እመቤትን ተከትላ ስለ ሔደች የምታስታምማት ጆይስ ነበረች።

ባርባራ የሔደችበት ቦታ ከኢስት ሊን ሃምሳ ኪሎ ሜትር ያሀል ይርቃል
ሚስተር ካርላይል ቀን ቀን ከሥራው እየዋለ ማታ ማታ እዚያው ሔዶ ያድር ነበር " በዚህ ምክንያት ወደ ኢስት ሊን ከዘለቀ ዐሥር ቀን ዐለፈው " በነዚያ ጥቂት ቀኖች ውስጥ የሳቤላ ሁኔታ እየባሰ ሔዶ " ቀኑ ሮብ ነው ሚስተር ካርላይል
ከቤቱ ያድራል ተብሎ ይጠበቃል ።

ጆይስ የምታደርገው ነገር ጠፋት " በጣም ተጨነቀች ። ሳቤላ ተዳከመች
ራሷን መቈጣጠር አልችል አለች » ደብቃው የኖረችው ምስጢር ሊገለጽ ሆነ
የሚገለጽበት ጊዜ ደግሞ ጆይስ አስቀድማ ባለመናገሯ ከሳቤላ ጋር ተመሳጥራ አንደ ደበቀችው ተደርጎ እንዳይተረጐምባት ፈራች ባልና ሚስቱ ምን እንደሚሏት አስባው ተጨነቀች » ሚስተር ካርላይልን ጠርታ ሁሉን ነገር ልትገጽላት ብዙ
ጊዜ እያሰበች መልሳ ትተዋለች እሷ በዚህ ነገር ስትዋልል ሰዓቱ ገሠገሠ በተለይ ከእኩለ ቀን በላይ የነበረው ጊዜ ቶሎ መሸ የሳቤላ ሕይትም ከጀንበሪቷ
ጋር የመጥለቅ እሽቅድምድም የያዘች ይመስል ወደ ጥልቀት ገሠገሠች ጆይስ
ከአጠገቧ አልተለየችም
ቀኑን ሙሉ ዛል ብላ ውላ ወደ ማታ ትንሽ ዐለፍ ያለላት
መስለች ከመኝታዋ ላይ እንደ ሆነች በትራሶች ተደግፋ ትንሽ ቀና አለች " ከነጭ ሱፍ የተሠራ ያንን ልብስ ተደረበላት ደኅና አድርጋ አየር እንድታገኝ የሌት ቆቧ ወለቀላት » መስኮቶች ወለል ብለሙ ተከፈቱላት ።

ሞቃቱ የበጋ አየር ጸጥ ብሏል ጆሮዋ እንደነቃ አእምሮዋም እንዶ ሰላ ነበር
ጆይስ ” አለቻት "ዘ
እመት ” መለሰች ጆይስ
' ላየው ብችል ደሰ ብሎኝ እሞት ነበር "
“ ልየው ! " አለች ጆይስ በትክክል መስማቷን ጆሮዋን በመጠራጠር "
" እሜቴ ልየው አሎኝ ... ሚስተር ካርላይልን ?”

“ ምነው ምናለበት ? ያለሁ መስሎኝ ነው ? እኔ እኮ አሁን ሙት ማለት ነኝ "
እሱን ለማየት ብጠይቅ ነውር ሆነብኝ ? እኔ ላነጋግረው በልቤ ከተመኘሁ ብዙ ቀን ሆኖኛል " ይህ ፍላጎቴ ከሞት ፊት ተደንቅሮ አላሳልፍ አላሰቀርብ አለው .
ጣሬ በዛ ጆይስ እባክሺን ላግኘው? አንዴ ላነጋግረውና በሰላም ልሙት ”

ሊሆን አይችልም ... እሜቴ ” አለቻት ፍርጥ አድርጋ " የማይያገባ ነገር ነው " አይቃጣም !አይታሰብም”

ሳቤላ የጆይስን እምቢታ ስትሰማ እንባዋን ባራት ማዕዘን አወረደችው
ምነው ጆይስ ምን በደልኩሽ? በዚህ የተነሣ መሞት እኮ አልቻልኩም
ነፍሴ አልወጣ አለች ልጆቼን ከኔ ወሰድሽብኝ " እኔ እንዳልታወቅብሽ ስለፈራሽ እዚህ ግድም እንዳይመጡ ብለሽ ሰደድሻቸው " አሁን ደግሞ ባሌን እንዳላናግረው ትክለክይኝ ? ተይ .. ጆይስ ተይ ላግኘው! ግድ የለሺም ንግሪው ይምጣ።

ባሏ ! ምስኪን ዛሬም ባሌ ትለዋለች ጆይስ ከውሳኔዋ ፈቀቅ ባትልም ሁኔታዋ በጣም አሳዘናት ዐይኖቿ በእንባ ክድን አሉ ። ነገር ግን ሚስተር ካርላይልን ጠርታ ከዱሮ ሚስቱ ፊት ብታመጣው ባርባራ ላይ የክህደት ሥራ እንዶ
ፈጻመች እንዳይቆጠርባት ፈራች "

በፉ ተንኳኳ " ጆይስ “ ግቡ ” አለች ። ሁልጊዜ ወደዚያ ክፍል ይመጡ የነበሩት ሁሉት ሠራተኞች ሐናና ሣራ ነበሩ ሁለቱም ማዳም ቬንን ወይዘሮ ሳቤላ እንደ ነበረች አያውቁም ሣራ አንገቷን ብቅ አደረገችና
ስሚ ጆይስ ” አለቻት "
ጌቶች ይጠሩሻል .
ሚስ ጆይስ።

''እሺ መጣሁ።

“ ከመብል ቤት ናቸው " አሁን አርተር ካርላይልን ሰጥቻቸው መምጣቴ ነውኀ

“ ማዳም እንንዴት ሆነች . . . ጆይስ ? ” አላት አርተርን በትከሻው ተሸክሞ አገኘችውና ካርላይልን ።
ጆይስ ምን ብላ እንደምትመልስ ድንግር አላት " በሌላ በኩል'ደግሞ ከጥቂት ሰዓት በኋሳ በግድ የሚገለጸውን ነገር ሽፋፍና ልታልፈው አልፈለገችም

“ በጣም አሟታል , , ጌታዬ ” አለችው "

"በጣም ? ''

“ አዎን ' መሞቷ ነው መሰለኝ።

ሚስተር ካርላይል ያቀፈውን ልጅ በድንጋጤ አወረደው "

“ መሞቷ ነው ”
“ አዎን ዛሬ ማደሯንም እንጃ

“ ምነ ? ለሞት የሚያደርስ ምን ነገር አገኛት ? "

"ጆይስ አልመለሰችለትም " አሷም የምትለው ጠፍቷት ፊቷ ዐመድ መስሎ ነበር።

"ዶክተር ማርቲን አይቷት ነበር ? ”

" የለም ... ጌታዬ " ግን ምንም አይጠቅማትም ”

“ አይጠቅማትም ! " ደገመው ሚስተር ካርላይል ቆጣ ብሎ ሊሞቱ ለተቀረቡቃረቡ ሰዎች የምናደርግላቸው ይኸው ነው ? ማዳም ቬን አንቺ እንደምትይው ታማ ከሆነ ዶክተር ማርቲን በቴሌግራም ተጠርቶ ቶሎ መምጣት አለበት » እስኪ
እኔው ራሴ ሔጄ ልያት ” አለና ወደ መዝጊያው አመራ

ጆይስ ጀርባዋን ወደ መዝጊያው ሰጥታ ከበሩ መኻል ቆመችና እንዳይወጣ ከለከለችው
ጌታዬ . . ይቅርታዎን እለምናለሁ " ነገሩ ደግ አይደለም ።እባክዎን ወደሷ ክፍል መግባቱ ይቅርብዎ ”

“ ለምንድነው የማልገባው ?

“ ሚስዝ ካርላይልን ይከፋቸዋል ብላ ተንተባተበች "

“ የማታመጡት የለም " ሚስዝ ካርላይል ባትኖር የግድ አንድ ሰው ሊያያት
ያስፈልጋል። ከቤቴ ውስጥ ስትሞት ላልጠይቃት ነው ? አብደሻል መሰለኝ ጆይስ !
በይ ከራት በኋላ እጠይቃታለሁና በደንብ አዘጋጂያት ”

ራት ቀረበ ጆይስ ሕፃኑን አርተርን ይዛ ወደ ሣራ ሔደች "

ሚስተር ካርላይል ራት ሊበላ ሲጀምር እኅቱ ደረሰች " የመጣችው ከአንዳንድ ቤቶቿን ከተከራዩ ሰዎች ጋር ጭቅጭቅ ስለ ፈጠረች ለወንድሟ ለመንገር ነበር " የመጣችበትን ከመስማቱ በፊት ጆይስ የነገረችውን የማዳ ቬንን ሁኔታ ነገራትና ሔዳ እንድታያት ጠየቃት "

“ልትሞት ነው?” አለች ኮርኒሊያ እሷም ድንግጥ ብላ “ “ግድ የለህም ይህች
ጆይስ ዘንድሮ በጤናዋ አይደለችም " እስኪ አሁን ምን አገኛትና ነው ልትሞት
ነው ብላ የምታወራ ? ”

ኮርኒሊያ ላይኛው ቆቧንና ካባዋን አውልቃ ከወንበሩ ላይ ጣል አደረገች
መልኳን ከግድግዳው ላይ ከነበረው መስተዋት
ቆቧን ነካ ነካ አድርጋ አስተካከለችና በሽተኛዪቱ ወደ ነበረችበት ወደ ፎቅ ሔዳ በር መታች
ጆይስ " ይግቡ የሚል ምላሽ ሰጠቻት ወዲያው ጆይስ ማን መሆኑን ስታይ
ደነገጠችና ' “ ይተዉ እማማ አይግቡ ” አለችና ከበሩ ሒዳ ከፊቷ ተደቀነች

ማነው ደግሞ እኔን የሚከለክለኝ: ' አለች ነገሩ ስለገረማት ትንሽ ተግ ብላ ካሰበች በኋላ።በይ ዘወር በይ ሴትዮ ! ለመሆኑ ጭንቅላትሽ ደህና ነው?
ከዚህ በኋላ ደግሞ ምን ታመጪ ይሆን?

ጆይስ በሥልጣንም በጉልበትም ዐቅም እንዳልነበራት ታውቅ ነበር
ስለዚህ ሚስ ካርላይልን እንድትገባ አሳለፈቻትና ራሷ ወጣች "
👍20
ምንም የሚደበቅ ነገር አልነበረም " ቀረበች 1 አየቻት " ዐመድ ለብሶ
ጥውልግ ያለው ፊቷ ከመሸፈኛዎቿ ሁሉ ተላቅቆ ተገልጦ ከትራሱ ላይ ወድቋል ግራጫው መደረቢያዋ መነጽሯ ' ያንገቷና የሸንጎበቷ መሽፈኛ ያ ትልቅ ቆብ ሁሉ ከኖሩበት ወልቆ ተቀምጠዋል " በዚያ ሁሉ የመሸፈኛ ጓዝ ተሸፋፍኖ የነበረው ፊት ዛሬ በግልጽ ታየ በርግጥ በጣም ተለውጧል " ይሁን እንጂ የሷ የሳቤላ ቬን ፊት ለመሆኑ ትንሽም አያጠያይቅም ነበር " ሽበት ብርማ ቀለም የቀባው ጸጉሯ በሁለት ወግን ተከፍሎ የሐር ጥቅል መስሎ ካንጎቷ ተቆልሏል የሀዘን ጥላ ያረፈባቸው የሚያምሩት ዐይኖቾም አልተለወጡም " የድሮዎቹ የሳቤላ ቬን ዐይኖች እንደሆኑ ትንሽ እንኳን አያሳስቱም ።

ሁለቱም ተፋጠው ዝም አሉ " ሁለቱም እኩል ተጨነቁ ሚስ ካርላይልም እንደ በሽተኛይቱ ትቃትት ጀመር " በፊትም ቢሆን ማዳም ቬን እመቤት ሳቤላ ስለ መሰለቻት ተጠራጥራ እንደ ነበርና ኋላ ግን ሳቤላ ሙታ የመቀበሯ ጉዳይ ምንም እንደማያጠራጥር ሎርድ ማውንት እስቨርን ካረጋገጠላት በኋላ የሱን ቃል በማመን መጠራጠሯን እንደ ተወች ይታወሳል "

“ እንዴት ደፍረሽ ወደዚህ መምጣት ቻልሽ ? ” አለቻት በቁጣ ሳይሆን ልስልስ ባለ አነጋገር ሳቤላ የመነመኑት እጆቿን ከደረቷ ላይ በትሕትና አመሳቅላ ልጆቼን 'አለቻት በሹክሹክታ ከነሱ ተለይቼ መኖር አልቻልኩም " እዘኑልኝ ?ሚስ ካርላይል " እንዳይቆጡኝ ። በሠራሁት በደል ፡ በራሴ ላይ ባመጣሁት ኀዘንና መከራ ልጠየቅበት ወደፈጣሪ እየሔድኩ ነው ”

“ አልቆጣሽም ”

ወደ ዘለዓለም ዕረፍቴ በመሔዴ ደስ ይለኛል” አለች ዕንባዋ ችፍፍ ብሎ”
“እስኪ ስሚ ልጄ” አለቻት ኮርኒሊያ ወደ ሳቤላ ጠጋ ብላ በመደገፍ። “ላንቺ
ከኢስት ሊን መጥፋት ምክንያት የሆንኩኝ እኔ ነበርኩ እንዴ ? ”

ሳቤላ ራሷን በአሉታ ለመነቅነቅ ሞከረች ዐይኖቿን ስብር አድርጋ ድክም ባለ ድምፅ “እርስዎ አይደሉም ያስወጡኝ " እኔ እንድወጣም ያደረጉት ነገር የለም በእርግጥ በአርስዎ አልደሰትም ነበር። ነገር ግን የመሔዴ ምክንያት እርስዎ አይደሉም ይቅር ይበሉኝ ... ሚስ ካርላይል ይማሩኝ "

“ ተመስግን ጌታዬ ! ” አለች ኮርኒሊያ በሆዷ" ከዚያም ድምጿን ከፍ አድርጋ ' “ እኔም ቤትሺን ከዚያን ጊዜ የተሻለ የደስታ ቤት ላደርግልሽ ይገባኝ ነበር
አንቺ ከለቀቅሽ ጀምሮ እስከ ዛሬ ይቆረቁረኛል" በይ እኔንም ማሪኝ” አለቻት
አጅዋን ይዛ

ሳቤላ የሚስ ካርላይልን እጅ ወደሷ ሳብ አድርጋ ይዛ “ አርኪባልድን ለማየት እፈልጋለሁ ” አለቻት በሹክሹክታ “ ጆይስን እንድትጠራልኝ ብለምናት
አምቢ አለችኝ " እኔ ሙት ማለት ነኝ " ባገኘውና ባነጋግረው ምን አለበት?
አሁንም ለአንድ ደቂቃ ብቻ ልየውና ይቅርታ ሲያደርግልኝ ልስማው ከዚያ በኋላ በሰላም እሞታለሁ ”

ሚስ ካርላይል ነፍሷ ልትወጣ በጣር ላይ ሆና የለመነቻትን መንፈግ ስለ ከበዳት ይሁን ' ወይም ሌላ ምክንያት ይኑራት አይታወቅም " የሳቤላን ልመኖ ሰምታ ወደ በሩ ወጣች " ጆይስን ከኮሪዶሩ ውስጥ ግድግዳው ተጠግታ ዐይኖን በሽርጧ ሸፍና አየቻትና በጅዋ ጠቅሳ ወደሷ ጠራቻት "

“ ይኸን ነገር ካወቅሽው ስንት ጊዜ ሆነሽ ? "

“እንድ ጊዜ ለሊት እሳት ተነሣ ተብሎ ሁላችን ተደናግጠን ከየመኝታ
ቤታችን የወጣን ጊዜ ምንም ዐይነት መሸፈኛ ሳያደርጉ ፊታቸው በሙሉ ተገልጦ አየሁትና ዐወቅኋቸው » መጀመሪያ ግን መንፈሳቸው እንጂ እሳቸው በአካል የመጡ አልመሰለኝም ነበር ከዚያ ወዲህ እኔም ከፍራቴ የተነሣ የኖርኩት ኑሮ ኑሮ
አይበለው።

“ በይ እሺ አሁን ሒጅና ጌታሽን ወደኔ እንዲመጣ ንገሪው"

“ኧሪ ! እማማ ! መንገሩ ደግ ነው ? እንዲያዩዋቸው ነው ? ”

“ሒጅና ጌታሽን ወደኔ እንዲመጣ ንገሪው አለቻት መልሳ በማያወላወል ትእዛዝ። "አዛዥዋ አንቺ ነሽ ወይስ እኔ .. ጆይስ ? ”

ጆይስ ወረደችና ሚስተር ካርላይልን ራት ከሚበላበት አስነሥታ ይዛው መጣች

“ ማዳም ቬን ባሰባት እንዴ . . ኮርኒሊያ ? እኔን ፌለገችኝ ?

“ አዎን ልታነጋግርህ ትፈልጋለች ”....

💫ይቀጥላል💫
👍19🥰4
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ሰባት (27)


« ግን ሻንጣ ፤ ቅራቅንቦ የሚያስፈልጋት መሆኑን ርግጠኛ ነህ » አለች። « ይመስለኛል ። ወደ አንድ ቦታ እንድንሄድ አስቤአለሁ። ሳታስበው እንዲሆን ስለምፈልግ ፤ ቲኬቱን እሻንጣ ውስጥ ከትቼ ላስገርማት ብዬ ነው» አለ ። አንድ ትኬት ደብቆ ለመስጠት አምስት መቶ ዶላር መክፈል ይገባል ቤን ? ቤን አቭሪ እንዲህ ገንዘብ በታኝ ሆነ ? አልፎለታል ማለት ነው ። « ዕድለኛ እመቤት ናት በለኛ»
« ዕድለኛውንኳ እኔ ሳልሆን አልቀርም››
«እንዴት ? ለመጋባት አስባችኋል ማለት ነው ?»
«የለም ነገሩስ ለሥራ ነው ። የሥራ ጉብኝት አለብን»
‹‹ ያኛው ቀይ ጥብጣብ ያለው ቡናማ ከፋይ ሻንጣ ቆንጆ መሰለኝ»
«እኔም እሱ ላይ ነው ዓይኔ ያረፈው» የሜሪን ምርጫ ተቀብሎ የሱቁን ረዳት ጠራት ። ‹‹አመሰግናለሁ ሚስ…..›› አለ፡፡ ለልጅቷ ሚገዛዉን እቃ ካሳያትና እንዲጠቀለልለት ከነገራት በኋላ ሜሪን እያየ ። «አዳምሰን» ስትል ስሟን ነገረችው «ምንም ምስጋና አያስፈልግም ። ምክንያቱም እኔም ደስ ብሎኛል ። ይልቅ ትንሽ ጥያቄ ሳላበዛብህ አልቀረሁምና ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ እኔ ነኝ መሰል ። ዓመትባል ሲቃረብ ይኸው ነኝ ። የማይሆን የማይሆን ነገር አደርጋለሁ»
«እኔም ያው ነኝ ። ብቻ የዘንድሮው ዓመት ሲያልፍ ቢከፋኝም አይፈረድብኝም ። ደስ የሚል ዓመት ነበር ። ኒው ዮርክ እንኳ ሳይቀር»
«ኒው ዮርክ ነው እምትኖረው ? »
«ከመሄድ ስገላገል ፣ አዎ ። ግን ሥራዬ ቁጭ እሚያደርግ አይደለም ። ካንዱ ወዳንዱ መዞር ነው» ይህም ቢሆን ከማይክል ጋር አብረው እንደሚሠሩ ርግጡን የሚናገር ነገር አይደለም ። ብትጠይቀው ደስ ባላት ግን አትችልም ። ይህን ስታስብ በጣም ከፋት ። ኦመማት። ስለሌላ የሷ ስላልሆነ ሰው መጠየቅ ስላሰኛት አመማት ። መጠየቅና ማወቅ ስትችል ባለመቻሏም አመማት ።

«ነገሩ እንኳ የጅል ነገር እንደሆነ ይገባኛል ። ግን ከዚህ ወጣ ብለን አንዳንድ ነገር ይዘን መጠጥ ቢጤ ይዘን ብንጨዋወት ? ለነገሩ እቸኩላለሁ ። አውሮፕላን መያዝ አለብኝ ። ግን ቅዱስ ፍራንሲስ ሆቴል ጐራ ብለን »
«እኔም ቢሆን በራሪ ነኝ ። ያም ሆኖ ሐሳቡ የድርጊቱን ያህል ነው ። አመሰግናለሁ ሚስተር አቭሪ. . .» አለች ። ፊቱ ድንገት ቅጭም አለና ፤ «ስሜን እንዴት ልታውቂ ቻልሽ ?» ሲል ጠየቃት ። «ደረሰኝ ሲቆርጡልህ ስምህን ሲጠሩ ሰማሁ» አለች አመላለሷ ፈጣን ነበረና በጥርጣሬው ሊገፋ አልቻለም ይልቁንም እንዲህ ቶሎ ተገናኝተው ቶሎ በመለያየታቸው አዘነ ። በጣም ቆንጅዬ ልጅ ናት ፤ አለ በሐሳቡ ። ዌንዲን እወዳታለሁ ። ቢሆንም ከአንዲት ቆንጅዬ ልጅ ጋር አንድ ነገር መጠጣት ኃጢአት አልነበረም ። ድንገት አንድ ሀሳብ ብልጭ አለበት «ወዴት ነው የምትሔጂው ፤ ሚስ አዳምሰን?»
«ወደሳንታፌ ፤ ኒው ሜክሲኮ » ተስፋ ቆረጠ ።
«ምን ዓይነት ርጉም እጣ ነው ። እኔ ደሞ ወደ ኒውዮርክ የምትሔጂ ቢሆን ስል »
‹‹ሻንጣ የተገዛላት እመቤት አንድ ላይ ብታዬን እጅግ ደስ እንደምትሰኝ አይጠረጠርም ነበር ። »
«እጅ ሰጠሁ ። ደግ እንግዲህ አምሳክ ካለ ሌላ ጊዜ...»
«ሳንፍራንሲስኮ ትመጣለህ እንዴ ፣ ብዙ ጊዜ?»
«ከዚህ በፊትንኳ አልነበረም ። ወደፊት ግን እይቀርም እመጣለሁ ። ማለት እንመጣለን ። የምሠራበት ድርጅት አንድ ትልቅ ፕሮጀክት አለው» አለ ። « እዚሁ ሳንፍራንሲስኮ ማለቴ ነው ። ስለዚህ ወደፊት ከኒውዮርክ ይልቅ ይኸ ሳይሆን አይቀርም መኖሪያዬ »
«እንዲያ ከሆነ ምናልባት እንገናኝ ይሆናል » ይህን ያለችበት ድምፅ በመጠኑ መከፋትን የሚገልዕ ነበር ምንም አይደለም ። ከማይክል እንጂ ከቤን ጋር ቂም የለኝም ። ስለዚህ አዘውትረን ብንገናኝም ክፋት የለበትም። የሱቅ ረዳቷ እቃው መሰናዳቱን ገለጸችላቸው ። ቤን ጨበጣት ። ጠበቅ አድርጋ ጨበጠችው።
በመገረም ቀና ብሎ አያት በለሆሳስ ። « መልካም የገና በዓል » አለችና በፍጥነት ካጠገቡ ተሰወረች « ወዲያ ወዲህ ተገላምጦ ቢያይም ሊያገኛት እይችልም ።

ከቤን እንደተለያዩ ሰውነቷ ድክምክም አለ ።
ከሱቅ እንደ ወጣች ታክሲ ተሳፍራ ወደ ቤቷ ጉዞ ቀጠለች ከዚያ በፊት ግን ፍሬድን ለእንስሳት ህክምናና ጥበቃ ድርጅት በአደራ መልክ ሰጠችው። ምክንያቱም አያስፈልጋትም። ጉዞዋ አለና በዚያም ላይ በርከት ያለ ቦታ ማየትና ማዳረስ አለበባትና የፍሬድ መኖር አመቺ አልነበረም። ብቻዋን መሔድ አለባት ። ናንሲ ማክአሊስተር በሚል ስም የዱሮ ሰብእናዋ የምትኖርባቸውን የመጨረሻ ሳምንታት ከማንም ጋር መካፈል የለባትም። ምስክር መኖር የለበትም። የአንድ ሕይወት መደምደሚያ ፤የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ነውና ብቸኝነት ያስፈልጋታል። እቤቷ እንደደረሰች ተዘዋውራ ተመለከተችው በሩን ስትዘጋ አንድ ሀረግ ተናገረች ። ለቤን አቭሪ፣ ለማይክል ፤ ያውቋት ለነበሩ ፤ ይወዷት ለነበሩ ፤ ታውቃቸው ትወዳቸው ለነበሩ ሁሉ « ደህና ሁኑ » የሚል ሀረግ ተናገረች ። ደረጃውን ስትወርድ እንባ ተናነቃት ። ካሜራዋንና የዕቃ ሻንጣዋን ይዛ ነበር ።

•••••••••••••••

እረፍቷን ጨርሳ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትመለስ ፒተር እየር ማረፊያ ድረስ መጥቶ እንዳይቀበላት ቃል አስገካችው ። ምክንያቱም ያለሸኚ እንደወጣች ያለተቀባይ ልትገባ ስለፈለገች ነበር ። ጉዞውን ስትጅምር ልቧን ከብዷት መንፈሷም ተሸብሮ ነበር። ያንለት ቤን አቭሪን ማግኘቷ ወዳለፈው ሕይወቷ እየተመዘዘ በመመለስ ብዙ ነገሮችን እንድታስታውስ አስገደዳት ። በዚህም የተነሳ በመጀመሪያዎቹ እለታት ከማንም ጋር ለመነጋገር ማንንም ለማዳመጥ አልተቻላትም ። ከሀሳቧ ጋር ተፋጣ ነበር ። ያ ጉዞ ግን አብነት ስለነበረው ከጭንቀቷ ፈወሳት ። የሰላም ጊዜ አሳለፈች ። እጅግ ብዙ ነገርም ሠራች ። ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትመለስ ፤ ከሳንፍራንሲስኮ ስትነሳ የነበረው ጭንቀት አልነበረም ። አሁን ስለቤን አቭሪ ማሰብ አያስፈራትም ። ያለፈውን ሕይወቷን መለስ ብላ ለመቃኘት አትፈራም ። ይህን ያህል በመለወጥ አዲስ ሰው ሆነች ። ለመጨረሻ ጊዜ ያለፈው ሕይወቷ የሌላ የምታውቃት ሴት ሆና ታያት ።

ናንሲ ማክአሊስተር ባዕድ ሆና እሷ ሜሪ አዳምሰንን ሆነች። ሜሪ የገናንም በአል ሆነ የዘመን መለወጫን በማታውቃቸው ሰዎች መካከል ሆና አሳለፈችው ። ሰዎች በአላትን ሲያክብሩ ናንሲ እነሱን ፎቶ ግራፎች አነሳቻቸው ። በተለይ የገናን በዓል በታአሰ አካባቢ ስታከብር የበረዶ ሸርተቴ የሚጫወቱት ብዙ ነበሩና ይህን ጨዋታ ለመሞከር ልቧ እጅግ ገፋፍቷት ነበር፡፡ እንዲህ ያለውን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ጨዋታ ላለመሞከር ለፒተር ቃል ገብታለት ነበርና ለራሷም በመፍራት ፍላጎቷን መግታት ግድ ሆነባት ። ፒተር የገባውን ቃል አክብሮ ሊቀበላት እንዳልመጣ! ስትገነዘብ ደስ አላት ። እንዲሀ በማያውቅህ ሠራዊት ውስጥ ስትገባ ማንም ነህ ። ማንም ማንንም አያይም ተሰውሮ መኖርን ደግሞ ብዙ ተላምዳዋለች ። ባለፉት ሁለት ዓመታት ፊቷ በፋሻ ተደግልሎ ሥጋ ሳይሆን መልኳ ሻሽ በነበረበት ጊዜ ላለመታየት ከማድረግ ፣ ከመደበቅ በስተቀር ሌላ አማራጭ አልነበራትም ። ይምሰላት እንጂ የትም ብትሔድ ፤ የትም ብትገባ ያለመታየት ዕድል አልነበራትም ። የተዋበው መልኳ ፣ አረማመዷና አጠቃላይ እንቅስቃሴዋ አለባበስዋ ይህ ሁሉ ዓይንን በግድ ይስባሉ ። የግንባሯን ላይ ፋሻ ለመከለል ያደረገችው ኮፍያ ሳይቀር ለሷ ውበት ሆኗታል ። ይሁን እንጂ ይህን አልተገነዘበችውም ። ስለዚሀም ማንም አያውቀኝም
👍23
ማንም አያየኝም ብላ አሰበች ።

ከታክሲ ወርዳ ወደ አፓርታማው ለመግባት ደረጃዎችን ስትወጣ ርምጃዋ ፈራ ተባ ያለ ነበር ። አንድ ያልታሰበ ነገር የሚያጋጥማት ፤፡ አፓርታማው ተቀይሮ የሌላ ሰው ቤት ሆኖ የምታገኘው የመሰላት ይመስል፤ ገባች ። ፀጥ እንዳለ ምንም ነገር ሳይለወጥ አገኘችው ። ድንገተኛ ቅሬታ ተሰማት። ምን ፈልጌ ምን ጠብቄ ነበረና ቅር ተሰኘሁ ። ልክ በሩን ስከፍት የክብር ዘብ ተሰልፎ በታምቡርና በጥሩምባ እንዲቀበለኝ ፈልጌ ነበር ይሆን? ስትል አሰበች ። ሁኔታዋ አስገረማት ። አስቂኝ ሆኖ ታያት ። ወይስ ፒተር አልጋዬ ስር አድፍጦ ቆይቶ ብቅ እንዲል ምኞት ነበረኝ ? አለች ። ፒተር እንዳይቀበላት የከለከለችው ራሷ ስትሆን እንዴት ይህ ምኞት በልቧ ውስጥ ሊኖር ይችላል ? ፒተር …..

የላይ ልብሷን አውልቃ አልጋዋ ላይ ተዘረጋችና ሀሳቧን ለቀቀችው ። ፒተር . . . ፒተር የሚያደርግላት ሀክምና ወደ መፈጸሙ ተቃርቧል ። እንዲያውም ካሁን በኋላ እንደ ሀኪምና ታካሚ የሚገናኙት አንድ ቀን ብቻ ነው ። እንግዲህ ሥራዬን አከናውኜ ጨርሻለሁ ። ደህና ሁኝልኝ ቢለኝ ምን ይውጠኛል ? አይ ይህ አይሆንም ። ጅልነት ነው ። ፒተር ስለሷ ያለውን አስተሳሰብ በሚገባ ታውቀዋለች ። ሆኖም ምኑ ይታወቃል ? የለም አይሆንም ። የፎቶ ግራፎቿን ኤግዚቢሽን ያዘጋጀላት ፤ ሁሉን ነገር ያደራጀላት እሱ ሆኖ ሳለ ... በዚያም ላይ እንደታካሚ ሳይሆን እንደሰው... . ምን ያህል እንደሚወዳት እንደሚንከባከባት መች አጣችው ! ይህ ሁሉ ሀሳብ ሲተራመስባት አይዞሽ የሚላት ።፤ በኑሮ ላይ እንደጋገፋለን የሚላት ሰው ፈለገች ። አዲስ ሰው ነሽ ። ሜሪ አዳምሰን ነሽ ። ሜሪ አዳምሰን ጠንካራ ሰው ነች ። ትልቅ ደረጃ ይጠብቃታል ። ኑሮን አሳምራ ትኖራታለች የሚላት ሰው ፈለገች ። ሜሪ ጠንካራ መሆኗን አሰበች ። ነኝ አለች ። ሜረ ነኝ ጠንካራ ሰው ነኝ ። ታዲያ ምን አስፈራኝ ። አይዞሽ ባይ ለምን አስፈለገኝ… አለች በሀሳቧ ።

ከአልጋዋ ላይ ተፈናጥራ ተነስታ ምስሏን በመስታወቱ ውስጥ ተመለከተች ። በተቅበዘበዘ ሁኔታ ካሜራዋን አነሳች ። እንደለማዳ እንስሳ ዳበሰችው ። የኔ ነህ አለችው ። የሚያስፈልጋት ጓደኛ ያ ካሜራ ብቻ እንደሆነ አመነች ። ሀሳቧ ግራ አጋባት ። ምን ሆንኩ ? አለች ። ምንም ስትል ጥያቄዋን መለሰች ። ምንም አልሆንኩ ፣ ስለ ደከመኝ ነው። ሀሳቧን አቋርጣ ተኛች በማግሥቱ ጧት ወደ ፒተር መስሪያ ቤት ሄደች ። እግረመንገዷን ፍሬድን አደራ ካስቀመጠችበት የእንስሳት መጠበቂያ ሥፍራ ይዛው ሄደች ።

« አረ በስላሴ ! እንዴት አምሮብሻል እባክሽ ። ደሞ ካፖርትሽ ልክክ ብላብሻለች » አለ ፒተር እንዳያት የግንባሯን ፋሻ ለመሸሸግ የምትጠቀምበትን ኮፍያ አውልቃ በጅዋ ይዛ አይቶ በፍቅር የተነከረ ፈገግታ አሳየችው ። በደስታ ተሞላ ። ኮፍያውን አየት ካደረገች በኋላ ወደ ቢሮው የቆሻሻ መጣያ ሄደች « ከዛሬ ጀምሮ ባርኔጣ እሚሉት ነገር የማላደርግ መሆኔን በዚህ ድርጊት አስታውቃለሁ ። » ይህን ተናግራ ኮፍያውን ጭምድድ አድርጋ እቆሻሻ መጣያው ውስጥ ከተተችው ። « ፈጽሞም ባርኔጣ እንደማይነካሽ ርግጠኛ ነኝ » አለ ፒተር። « ስሜቴን ስለተረዳህልኝም ስለሌላው ሁሉ ምሥጋናዬ የላቀ ነው» አለች ሜሪ ።

የተሰማት ግን ካለችው ሁሉ የላቀ ነበር ። ፒተርን እቅፍ አድርጋ ልትስመው ፈለገች ። አላደረገችውም ። ፍላጐቷን ግን ከጠቅላላ ገፅታዋ አነበበ ። ዓይኗን ከፒተር ሳይ ሳትነቅል ተመለከተችው ። በጣም እንደናፈቃት ገባት ። ከዛሬ በኋላ ፒተር ጓደኛዋ እንጂ ሀኪሟ አይሆንም ። ከፈለገች ጓደኛዋ ፤ ከፈቀደችለት ሁሉን ነገር ይሆናል ። ፍቅረኛዬ ሁን ብትለው ደስ ይለዋል ። ባሌ ሁን ብትለውም እንደዚሁ ። ይህ ደግሞ ከንቱ አስተሳሰብ ወይም ግምት አልነበረም ። እንደሚያፈቅራት ብትፈቅድለትና ፍቅራቸውን ለመካፈል ቢችሉ ደስ እንደሚለው ደጋግሞ ገልጾላታል ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍17🎉2