አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ስኞ ማታ ሪቻርድ ሔደና ከቦል ጋር ተግናኘ " ታሪኩን ከሥሩ ዝርዝር አድርጐ አጫወተው።

የምትለውን ሁሉ አምናለሁ .. ሚስተር ሪቻርድ ቶርንን በሚመለከት
ግን ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነው ብሎ መቀበል በጣም ያስቸግራል »

“እኔ በተናገርኩት ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም በመጠየቅ ማረጋገጥ ትችላለህ ፍቃደኝነታቸውን እጠራጠራለሁ እንጂ ኦትዌይ ቤቴልም ሊመስክር ይችላል ኧበንዘር ጄምስም ሊመሰክር ይችላል።"

አሱም በዚያን ዘመን ቶርንን ያውቀው ነበር ። ዛሬ ደግሞ ሌቪሰን ሲባል አስተውሎ አይቶታል አለው ሪቻርድ "

ደኅና ... እንግዲያው መጀመሪያ ስለ ሰውዬው ማንነት ላረጋግጥና ከዚያ
በኋላ እቀጥላለሁ በርግጥ ልቪዞን የወጣለት ወሮበላ ነው እንደ ሊቪስንነቱ እንኳ። ይህ ሲጨመርማ እስኪ ለማንኛውም ኧበንዘር ጀምስን ጠይቄ የሚለውን ልስማ

እኔ ከዚህ እያለሁ ? ኧረ እንዳያየኝ እባክህ ካየኝ አለቀልኝ ማለት ነው...
ሚስተር ቦል „

“ ሌላ የእንግዳ መቀያ ክፍል ኮ አለን ... ሪቻርድ '

ኧበንዘር ጀሞዝ መጠራቱን እንደ ሰማ ወዲያው ደረሰና “በአስቸኳይ የሚጻፍ
ነገር አለ እንዴ ? ” አለው ሚስተር ቦልን ”

“ኧረ የለም የጠራሁህ አንድ ሁለት ጥያቄዎች እንድትመልስልኝ ብዬ ነው
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪዞን በሌላ ስም ሲጠራ ታውቅ ነበር? ሚስተር ኧበንዘር

አዎን ባንድ ወቅት ቶርን ተብሎ ሲጠራ ዐውቅ ነበር

"ወቅቱ መቼ ነበር ? "

ሆሊጆን በተገደለበት ዘመን ነው " ሁላችንም በተመሳሳይ ምክንያት በዚው አካባቢ ስንመላለስ እሱም አፊ ሆሊጆንን በወዳጅነት ይዟት ስለ ነበር ማታ ማታ ከዚያ ቤት ጠፍቶ አያውቅም "

“ እኔ እሱን ዌስት ሊን መኖሩን አላስታውስም " የት ይኖር ነበር ?

የለም ዌስት ሊን ውስጥ አልተቀመጠም ጭልምልም ሲል ማለፊያ ፈረስ እየጋለበ ይመጣና ከአፊ ጋር ሲጫወት አምሽቶ አየጋለበ ይመለስ ነበር ።

ወዴት ነበር የሚመለሰው ? የሚመጣውስ ከየት ነበር ?”

“ ከስዌንስን አካባቢ ነበር ሁልጊዜ በደንብ ለብሶና ደማቅ ላባውን ከባርኔጣው ሰክቶ ይመጣ ነበር " እንግዲህ ይመጣ የነበረው ከሌቪሰን ፓርክ ሳይሆን
አይቀርም ያጎቱ ቤት በስዌንሰን በኩል ስለሆነ " ከዚያ መምጣቱ ምንም ሊያጠራጥር አይችልም።

“ጀምስ... ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን አንተ የምታውቀው ቶርን ስለ መሆኑ
የምትጠረጥርበት ነገር የለህም ?”

«ጌታዬ ... እርስዎ ሚስተር ቦል መሆንዎ ወይም እኔ ኧበንዘር ጄምስ
መሆኔ ያጠራጥራል ?
ሌቪሰንም የዚያን ጊዜው ቶርን ለመሆኑ የዚህን ያህል ነው እርግጠኝነቴ "

“ ይህን ነገር ከፍርድ ችሎት ቀርበህ በመሐላ ልታረጋግጥ ትችላለሀ ?

“ እኔ ነገም ቢሆን በማንኛውም ፍርድ ቤት ለመመስከር ዝግጁ ነኝ "

“ በል ሒድ I ስለዚህ ጉዳይ መነጋገራችንን ለማንም እንዳትናገር

ሚስተር ቦል የሪቻርድ ሔርን ቃል እየተቀበለ ሁለቱም እስከ ዕኩስ ሌሊት
ተቀመጡ “ ሚስተር ካርላይልም በነገሩ ላለመግባት የፈለገው በሌቪሰን ጉዳይ መነካካቱን ስለ ጠላው ነው። አይመስልህም..."ሚስተር ቦል?” አለው ሪቻርድ "

ጠበቃው ከንፈሩን አጣመመ “ አስቸጋሪ ነገር ነው " ሚስተር ካርልያል
ጥንቃቄውን ያበዛው የለ ? እኔ ብሆን አለቀውም ነበር " ዳሩ ምን ይሆናል " እኔና
ካርላይል የተለያየን ነን ”

በበነጋው ማክሰኞ ቀን የኧበንዘር ጄምስን ቃል መልክ አስይዞ ጽፎ እንዳበቃ ወደ አመሻሽ ላይ ሌቪሰን ፓርክ ሔዶ አንዳንድ ነገሮችን አጠናቅሮ ተመለሰ "

ሬቻርድ ሔር አድራሻውን ለእኅቱና ለአማቹ ሰጥቶ ወደ ሊቨርፑል ተመልሶ ሔደ።

ሮብ ጧት የማውንት እስቨርን ኧርል ተመልሶ መጣ " ልጁ ሎርድ ቬንም አብሮት ነበር » በዚያ ሰዓት ልጁ ወደ ትምህርት ቤቱ ወደ ኢተን መመለስ ነበረበት ነገር ግን ' የምርጫውን መጨረሻ ለማየት እንዲፈቅዱለት አባቱን አጥብቆ ለመነው"
“ከሁሉ ከሁሉ” አለው ቀስ ብሎ አባቱን “ያ ዲያብሎስ መሸነፉን ሲያውቅ እንዴት እንዶሚበሳጭና እንደሚያፍር ለማየት እፈልጋሁ።አባትየው የልጁን
ነገር በጣም ያከብር ስለ ነበር እሺ አለው ሌቱን ተጉዘው በቁርስ ሰዓት አካባቢ ደረሱ " በኋላም ከሚስተር ካርላይል ጋር ሆነው ወደ ዌስት ሊን ሔዱ

ዌስት ሊን ተሟሟቀች ደመቅ ደመቅ አለች " ምርጫው የሚካሔደው በዚያው ሳምንት ውስጥ ነው " ሰዎች በየግላቸውም ሆነ በኅብረት ስለ ምርጫው ሽር ጉድ ማለትን ሙያ ብለው ያዙት " የሚስተር ካርሳይል ኮሚቴ በክስሔድ ላይ ተቀመጠ " ዲያና ወዲህ ያለ የሚጐርፈው ሕዝብ ከብዛቱ የተነሣ የሚረግጠውን
ድንጋይ ማጐድጐድ የሚችል ነበር " ዳኞቹም የፍርድ ሥራቸውን ትተው ሐሳባቸውን ሁሉ ወደ ምርጫው ጉዳይ መለሱ ዘ የፍርድ ሥራቸን ቸለል ብለው ወይን ጠጅና ቀይ ጥብጣቦች በተስቀሉባቸው በበክስ ሔድ መስኮቶች እየዘለቁ ለሕዝቡ
በመታየት ትኩረታቸውን ሁሉ ከምርጫው ላይ አደረጉ "

ሚስተር ካርይል ከቢሮው ገብቶ ደብዳቤዎችን እየከፈተና አስፈላጊውን
ትእዛዝ ያሰፈረባቸው ካጠናቀቀ በኋላ ሚስተር ዲልን ጠራው ደብቤዎችን
በእጅ ሰጥቶትና አንዳንድ አስቸኳይ ትአዛዞችን ነግሮት ተነሣ "

«ትቸኩላለህ እንዴ አርኪባልድ?” አለው ሚስተር ዲል »
“ሰዎች በክስ ሔድ ይጠብቁኛል ምነው ?”

“ እኔስ ትናንት አንድ አስገራሚ ነገር አጋጥሞኝ ስለ ነበር ልነግርህ ብዬ ነው! ኦትዌይ ቤቴልና ሌቪሰን ሲጨቃጨቁ ሰማኋቸው "

“ እውነትህን ነው ?” አለው ከጠረጴዛው መሳቢያ አንድ ነገር እየፈለገ "

“በል እኔ እንግዲህ እንደዚህ ያለውን ነገር ባልሰማው እመርጣለሁ " ምናልባት የሰማኸው ነገር ለሪቻርድ ይጠቅመዋል የምትል ከሆነ ጉዳዩን ሚስተር ቦል
ሊከታተለው እያሰበ ስለሆነ ለሱ..ገባህ ለሚስተር ቦል ንገረው : '

ሚስተር ዲል ለጸሐፊዎቹ አለቃ አንዳንድ ትእዛዝ ከሰጠ በኋላ ወደ ቦልና
ትፊድማን ሔዶ ከሚስተር ቦል ጋር ለአንድ ሙሉ ሰዓት ዘግተው ተነጋገሩ ።

በዚያን ዕለት ዳኞቹ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ አልተሠየሙም ለዚያውም
ቢሆን ሔርበርትና ስፒነር ብቻ ስለ ነበሩ ከመሠየም አይቈጠርም" የሆነ ሆኖም
ሰዓት ባለማከበራቸው የሕሊና ወቀሳ እንደ ተሰማቸው ከፊታቸው እየታወቀባቸው ተከታትለው ገቡ።

ያን ጊዜ ሁለት ዐበይት ጉዳዮችን ብቻ ወሰኑ" ሁለቱም ዌስት ሊን ላይ ይካ
ፈሔድ ከነበረው ምርጫ የተፈጠሩ ነበሩ ። አንደኛው ጉዳይ አንዲት የብጫና ሁለተኛይቱ የቀይ ወይን ጠጅ ደጋፊዎች የሆኑ ሁለት ሴቶች ስለ ተወዳዳሪዎቹ ጥሩነት ሲከራከሩ በብረት ድስት የተደባቡ ነበሩ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ጥቂት ልጆች የሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ምስል በገለባ ሠርተው ከተማውን ከዞሩ በኋላ ከአንድ ሣር ከነበረበት ቦታ ወስደው ሲያቃጥሉት ፡ የሌሎች ንብረት የሆነ መጠነኛ ሣርና አዝመራ ስለ አጠፉ ተከሰው ቀረቡ » የአንዳንድ ሳምንት እስራት ልጆቹን በየግላቸው እንዲገረፉ ብለው አሰናበቷቸው ።

የመጨረሻውን ጉዳይ ወስነው እንዳበቁ ሚስተር ቦል እየተንደረደረ ገባና
ዳኞቹ አንድ ጉዳይ በዝግ ስብሰባ እንዲያዩለት ለመነ ዳኞቹም የጠበቃው አቀራረብ' “ ጉዳዩ ምን ቢሆን ነው? የሚል ጕጕት ስለ አደረባቸው እርስ በርሳቸው ተያዩና ከተመካከሩ በኋላ ጥያቄውን ተቀብለው ሊያዩለት ገቡ" ጉዳዩን እስከ አሥር ሰዓት ተኩል ሲመለክቱ ቆዩ ሲወጡ" የጠበቃው ቦል ማመልከቻ ያደናገራቸውና ያስደነገጣቸው ይመስል እነዚያ የተከበሩ ዳኞች በፊታቸው ላይ ፍራትና መቀጨም ይታይባቸው ነበር "
👍13😁1
ዛሬ ከሰዓት በኋላ ኮ ነው ዶክተር ማርቲንን ካባባ ቢሮ የምንገናኘው አለ ዊልያም ካርላይል የዚያኑ ዕለት በምሳ ሰዓት " ከዚያም ቀጠል አድርጎ ለመሆኑ ማዳም ቬን ... በእግራችን ነው የምንሔደው ?” ብሎ ጠየቃት "

"አላወቅሁም ዊልያም... ሚስዝ ካርላይል ናቸው የሚወስዱህ "

" የለም እሷ አይደለችም ምትወስጂኝ አንቺ ነሽ - እማማ ዛሬ ጧት ነግራኛለች ? አላት "

የነሱ ውይይት በሚዝ ካርላይል ድንገተኛ መምጣት ተቋረጠ “ ማዳም ቬን ለዘጠኝ ሰዓት ተዘጋጁና ከዊልያም ጋር ትሔጃለሽ » እኔ እወስደዋለሁ ብዬ ነበር "
ነገር ግን ከሩቅ አገር የሚመጡ አንግዶች ስለ አሎብኝ ልቀር ነው አለቻት።ፀ

ዊልያም በአጭር ፈረስ
ተቀምጦ ፈረሱን መልሶ ለማምጣት ሲባል የተከተለው ባልደራስ እየጠበቀው ወደ ዌስት ሊን ሔዱ ሲመለስ ግን ፈረስ አያስፈልገውም
አሁንም በእግሯ ከተhተለችው ከማዳም ቬን ጋር አዝግሞ እንዲመለስ ተባለ።

ከቢሮ ሲደርሱ ሚስተር ካርላይል አልገባም " ልጁ ማዳም ቬንን ከኋላ ትቷት
ሰተት ብሎ በድፍረት ወደ ልዩ ጽሕፈት ቤት ጥልቅ አለ ሚስተር ዲልም ተከትሎ ገባ።

“ሚስተር ዊልያም ... ስለ ክስ ጕዳዮች መመሪያ ልትሰጠን መጥተህ ነው?”
አለውና እየሳቀ “ተቀመጭ እመቤቴ ” አለ ወደ ማዳም ቬን ምልስ ብሎ "

“ዶክተር ማርቲንን ለመጠበቅ ነው የመጣሁት እኔን ለማየት እዚህ ድረስ
ይመጣል እኔ የምለው ሚስተር ዲል አባባ የት ነው?

"አረ እንጃ ልጄ!" አለ ሚሰተር ዲል "ግኖ ዶክተር ማርቲን ምን ያደርግልሃል ፊትህ እንደዚህ ጽጌሬዳ መስሎ የለመለመው በጎ ስለሆንክ መሆን አለበት።

ምነው በጎ በሆንኩና ያንን አስቀያሚ ያሣ ዘይት ከመጠጣት ባረፍኩ
አለ ልጁ “ እማማ አብራኝ ልትመጣ ነበር አልመቻት አለና ቀረች »

“እናትህ ደህና ናት ዊልያም ? ”

“በጣም ደኅና ናት " በፖሊስ ጣቢያው በኩል የሚሰማው ጮኸት ምንድነው?
ፌረሴን ኮ አስደነበረብኝ »

አንድ ብጫ ነገር ሲረጋግጡ አየሁዋቸው "
“ አዬ ምርጫው እስኪያበቃ ሰላም አይኖርም ” አለ ሚስተር ዲል “ ወዲያው ቶሎ ባለቀና ሰውየው ከከተማ በወጣልን ”

“ ያንን ሌቪሰንን ማለትህ ነው ? " አለው ዊልያም ሲነገር የሰማውን ይዞ

“ አዎ ከሁሉ የሚገርመው ኮ ምን አሳብዶት እዚህ እንደ መጣ ነው” አለ ለአድማጮች ሳይሆን ለራሱ የሚናገር መስሎ።

“ መቸም ከአባባ ጋር ተወዳድሮ ለማሸነፍ ተስፋ ማድረግማ የለበትም "

“ እሱ ከማንም ጥሩ ሰው ጋር ተወዳድሮ ማሸነፍ አይችልም ” አለ ዲል "

አንድ ጸሐፊ መጥቶ አንድ እንግዳ አስገባ ጸሐፊው ሚስተር ካርላይል ያለ መስሎት ኖሯል እንግዳው ማዳም ቬንን ሲያይ ከቆየ በኋላ ሚስተር ዲል ወደራሱ ቢሮ ወሰደው የግል እንግዳ ሳይሆን ባለጉዳዩ ነበር እሷ እንደ ወትሮዋ ጥቁር ሐር ለብሳ ነበር " ቀሚሷ ከተራ እስከ ከፍተኛ ጌጠኛ ስፌት ቢለያዩም ሁሉም ከጥቁር
ሐር የተስፉ ነበሩ አረንጓዴ መነጽር ተሠርቶ መጥቶ ተደርጓል ያንግት ልብስ ተደርቧል ዐይነ ርግብ ታስሯል እንደዚ ሁና ሰውየው ሲያያት ጊዜ ከዚያ ቦታ መገኘቷን ጠላችው። አዳዲስ ሰዎች አትኩረው ሲያዩአት አትወድም ነበር።

ወዲያው ሚስተር ካርላይል መጣ " ማዳም ቬንና ዊልያምን ወደ ኮርኒሊያ ቤት ሰደዳቸው " ኮርኒሊያ አልነበረችም " እንደ ሠራተኛው አባባል እስከ ራት ስዓት
አትመለስም " ዊልያም ከአንድ ሶፋ ተመቻችቶ ተጋደመና እንቅልፍ ይዞት ሔደ።

"ቤቱ ጸጥ ማለቱ ጊዜው አለመግፋቱ ለሳቤላ ከበዳት ቢሆንም ጸጥታውን እያዳመጠች መንገደኞቹን በመጋረጃው እየተመለከተች : እንዲሁም የልጇን
የገረጣ ፊት አየት አያደረገች ስትጠብቅ ዐሥራ አንድ ሰዓት ሆነ "

ሚስተር ካርላይል መጣ " “ ዶክተር ማርቲን ዘገዩ " አሁንማ አንቺም በሽተኛውም ደከችሁ ማዳም ቬን ” አላትና ወደ ልጁ እየተመለከ' ' እንዴት ገረጣ ልጄ ! ደግሞ ብዙ ይተኛል ጥሩ ነው ?”

“ እኔ ሚስዝ ካርላይል ይዘውት የሚመጡ መስሎኝ ነበር ” አለችው ማዳም ቬን እሱ ለጠየቃት የምትመልሰው ስታጣ ጊዜ "

ሚስዝ ካርላይል እንግዶች ይመጡባታል » ያም ባይሆን በዚህ ሁለት ቀን ጤንነት ስለ አልተሰማት ልሒድ ብትለም በሕመሟ ላይ ድካም እንድትጮምር
አልፈቅድላትም ነበር " " የንግግሩ በትር ተሰማት " ጓሮ ድካም እንዳይነካት ይጨነቅላት የነበረሙ ለሷ ነበር ዛሬ የሱ መሆን አይገኝም " ልክ እንደ ዘመኑ እንደማይመለስ ሆኖ ዐልፋል "

ታዲያስ ” አለ ራስ መላጣው ደቃቃ ሐኪም ደረሰና „ “ ወጣቱ በሽተኞዬ
አሁን እንዴት ነው ? አለና ማዳም ቬንን በፈረንሳይኛ “ዶህና ዋልሽ ? አላት" እሷም አጸፋውን መለሰችለት ሰው ሁሉ በፈረንሣይኛ ሲያነጋግራት ላለመታወቅ
ለመጠርጠር እንደሚረዳት ስለምታምን ደስ ይላታል "

የዓሳ ዘይቱስ እንዴት ነው ? " አለው ዊልያምን ወደ ብርሃኑ በማቅረብI
• ከበፊቱ ዛሬ በጣም የተሻለ ነው
. . . አይደለም ?

" የለም " አለው ዊልያም “ ከምንጊዜም የከፋ ነው . .

ዶክተር ማርቴን ልጁን ተመለከተ የልቡን አመታት አየ » አተነፋፈሱንንም አዳመጠ " ቆዳን አስተመሎ “በል ቀና በልና ተቀመጥ እንቅልፍ ይበቃል” አለው "

“ እኔስ የምጠጣው ነገር ባገኘሁ በጣም ጠምቶኛል ! ልደውልና ውሃ ልጠይቅ አባባ ?

ወተት ይስጡህ ' ውሃ አይሆንም “ አለ ዶክተሩ"

ዊልያም ተነሥቶ ሔደ ሚስተር ካርላይል ከመስኮቱ አጠገብ ተደግፎ ዶክተር ማርቲን ከመስኮቱ ፊት ለፊት ክንዶቹን አጥፎ ሳቤላ ከሐኪሙ አጠገብ ሁና ቁመዋል ደማቁ ብርሃን በሁሎም ላይ ዐርፋል የሳቤላን ፊት ግን ወፍራሙ
ወይነ ርግብ ከብርኑ ከልሎታል "

“ሁኔታው እንዴት ይመስልሃል . . . ዶክተር ? ምንም ማለባበስ አያስፈልግም ገልጸህ ንገረኝ።

እውነት ኮ ሁልጊዜ ደስ አያሰኝም ... ሚስተር ካርላይል

“ እውነት ነው " ስለዚህ ግልጽ አድርጎ መንገሩ አስፈላጊ ነው " የመጨረሻውን መጥፎ ነገር ልወቀው እናቱ ትደነግጣለች እንዳይባል እንደምታውቀው
ልጁ እናት የለውም "

እኔ መቸም የመጨረሻው ጽዋ አይቀርለትም ብዬ እሠጋለሁ "

“ ሞት ?

“ አዎን " አየህ የዚህ በሽታ ዘሮች አብረውት የተፈጠሩ ሳይሆኑ አይቀሩም
በግልጽ ይታያሉ "

ሚስተር ካርላይል ስሜቱን መቆጣጠር በመቻሉ በገጽታው አልታየበትም "
የልጆቹ ነገር ጭንቁ መሆኑ ይታወቃል " ዐይኖቹን ክድን አድርጎ ጸጥ ብሎ ቆየና
ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በክፍሉ ሰፍኖ የነበረው ዝምታ አፈረሰው።

“ ይህ የሳንባ በሽታ እንዴት ሊመጣበት ቻለ ? በኔ በኰልም ሆነ በናቱ በዘሩ
የለበትም "

ይቅርታ አድርግልኝ ” አለ ዶክተሩ የናቱ እናት የማውንት እስቨርን ካውንትስ እኮ በሳንባ በሽታ ነበር የሞቱት "
“ እነሱ ታዲያ መቸ የሳንባ በሽታ ነው አሉ ? ” አለ ሚስተር ካርላይል "

“ እነሱ ያሉትን ቢሉት ግድ የለኝም " ግን የሳንባ በሽታ ነበር ቀስ አድርጎ
እያለስለስ እያዘገመ ነው ሳንባቸውን ጨርሶ የገደላቸው " በዚህ እርግጠኛ ነኝ '' አሁን ልጁ ምንም ተስፋ የለውም ?”

ዶክተር ማርቲን ቀና ብሎ ተመለከተው “ሐቁን እንድነግርህ አዝዘኸኛል ''

“ ሐቁን ብቻ " ሌላ ምንም አልፈልግም ” አለ ሚስተር ካርላይል ትእዛዝና ጭንቀት በተቀላቀለበት ድምፅ

“ እንግዲያውስ ሳንባዎቹ በጣም ተበክለዋል እንግዲህ ምንም ቢደረግ
ተስፋ የለውም "

ምን ያህል ይቆይ ይመስልሃል ?
👍9😁1
“ ይህን ለመናገር አልችልም " ብዙ ሊቆይ ወይም በቅርቡ ሊሞት ይችላል
እንግዲህ ተማር እያላችሁ አታስቸግሩት ምንም አያደርግለትም” አለና ዶክተር ወደ መምህሪቱ
ተመለከተ ትእዛዙን እሷንም
ይመለከት ስለ ነበር በቁሟ የምትወድቅ መሰለውና ደነገጠ " ፊቷ ጭው ብሎ መንጣቱን በዐይነ ርግቧ ላይ ታየው "

"አመመሽ እንዴ ማዳም በጣም አመመሽ ” አላት በእንግሊዝኛና በፈረንይኛ እየቀላቀለ "

ለመናገር ከንፈሮቿን ለመግለጥ ብትሞክር እየተንቀጠቀጡ ለመታዘዝ አቃታት ዶክተር ማርቲን እንዳይሰበርባት በመፍራት መነጽሯን ከዐይኖቿ አፈፍ
አድርጎ አነሣው " ወዲያው በአንድ እጅዋ መነጽሯን ለቀም አደረገችና አጠገቧ
ከነበሪው ወንበር በመቀመጥ በሌላው እጅዋ ፊቷን ጋረደች "

ሚስተር ካርይል የሷንና የሐኪሙን ግብግብ መግጠም እምብዛም አላስተዋለውም " ወደሷ ቀረብ ብሎ " አመመሽ ማዳም? አላት መነፅሯን በአይነ ርግቧ ውስጥ አደረገች " አሁንም ፊቷ
ንጣቱን እየጨመረ ሔደ እባካችሁ ለኔ ብላችሁ ጨወታችሁን አታቋርጡ - ሁለታችሁንም አመሰግናለሁ " አንዳንድ ጊዜ እንዴዚህ የሚያደርግ ሕመም አለብኝ" ለጊዜው በጣም የታመምኩ ያስመስለኛል"
ግን ለክፉ አይሰጥም ቶሎ ይለቃል » ለምሳሌ አሁን ለቆኛል " ደህና ሁኛለሁ

ይhተር ማርቲንና ሚስተር ካርላይል ውይይታቸውን ቀጠሉ "

“ እና ምን እናድርግለት ? አለ ሚስተር ካርላይል „

የፈለጋችሁትን ወይም ልጁ የፈለገውን ማድረግ ትችላላችሁ " ምንም ልዬነት አያመጣም " ይጫወት ይረፍ ፈረስ ይጋልብ በግሩ ይሒድ ይጠጣ

“ ዶክተር! እንዲያው የመጨረሻ ተስፋም እንዶሌለው ነው የምታየው
እንደማወቀው ነው የምናገር " ትክክለኛ አስተያየቴን እንድሰጥ አጥብቀህ ጠይቀኸኛል I ተናገርኩ "

“ እንዲያው ሞቃት አየር ምን ይመስልሃል ?”

“ ምናልባት ዕድውን በጥቂት ሳምንት ይጨምርለት ይሆናል » ለዚሁስ ቢሆን ማን ይወስደዋል ? አንተ መሔድ አትችል ! እሱ እናት የለው እኔ አልመክርህም ይቅርበት ሚስዝ ካርላይልሳ እንደምናት ?”

“ደህና ናት እንደምታወቀው አሁን አሁን በጣም ጤንነት አይሰማትም ”

ዶክተር ማርቲን እንደ መሣቅ አለና ' “እንደዚህ ያሉ ስሜቶች ዐልፎ ዐልፎ
መሰማታቸው አይቀርም " ሚስዝ ካርላይል ሰውነተ ጠንካራ ናት " በጥንካሬ እሷ
በጣም ትበልጣለች ! ማለቴ ከ...ከ..”

' ከምን ? ” አለ ሚስተር ካርላይል ለምን እንዳመነታ እየገረመው »

“ ይቅርታ አድርግልኝ " ነገሩን አንድ ጊዜ ከጀመርኩት ልጨርሰው እንጂ አስቤው አይደለም የተናርኩት " ከእመቤት ሳቤላ እሷ ትጠነክራለች አሁን እንግዲህ ያሥራ ሁለት ሰዓቱ ባቡር ሳያመልጠኝ መሔድ አለብኝ » ”

ዊልያምን ለመጠየቅ አንዳንድ ጊዜ ወደ ኢስት ሊን ትዘልቃለህ ?”

“ ከፈለግህ እሺ " ምናልባትም እርካታ ሊሰጠው ይችል ይሆናል ደኅና ጐኚ ማዳም
”አላት በፈረንሳዊኛ
ዶክተር ማርቲን ከሚስተር ካርላይል ጋር ሲወጣ እጅ ነሣችው :

“...ይህች ፈረንዊት አስተማሪ ልጁን ምን ያህል ብትወደው ነው ?”አለው
ዶክተሩ በሹክሹክታ “ እኔማ ልብ ብዬ የተገነዘብኳት ወደ ሌንበራ ይዛው የመጣች
ዕለት ነበረ " አሁን ደግሞ እንዴት እንዳደሪጋት አይተሃታል ይህ ሁሉ ጭንቀት እኔ ልጁ እንደማይተርፍ በመናገሬ ነው " በል ደህና ሁን ”

ሚስተር ካርላይል እጁን ግጥም አድርጎ ያዘው “ ዶክተር ብታድንልኝ ምን ያህል ደስ ባለኝ ነበር ! " አለው "

“ አዬ ሚስተር ካርላይል እኛ ሥጋ ለባሾች ምስኪን ሐኪሞች ታላቁ ሐኪም ብቻ ሊፈጽመው የሚችለውን ተአምር መሥራት ብንችል ፈሊያጊያችን ምን ያህል
በበዛ ነበር ? በጥቁሩ ዳመና ውስጥም ስውር ትኩረት መኖሩን አስታውስ አትርሳ በል ደህና ሁን መንድሜ....

💫ይቀጥላል💫
👍22🥰4
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹አይሮፕላኑን ባህሩ ላይ እንድጥለው ትፈልጋለህ?››
‹‹እንደዚያማ ማድረግ አትችልምº እኔ አይሮፕላኑ ውስጥ አለሁ
ፓይለቱ እዚያ ቦታ ላይ በድንገት እንዲያርፍ የሚያስገድደው አንድ ችግር ፍጠር›› አለው በሚገባ በተከረከመ ጥፍሩ ፖስት ካርዱ ላይ ያለውን ቦታ እያመለከተው፡፡
የበረራ መሃንዲሱ ፓይለቱ በድንገት አይሮፕላኑን ለማሳረፍ የሚያስገድደው ችግር መፍጠር አያቅተውም፡፡ ነገር ግን አይሮፕላኑን የሚያሳርፍ ችግር መፍጠር ለጊዜው ኤዲ አልከሰትልህ አለው፡፡

‹‹ቀላል እንዳልሆነ ይገባኛል፤ ነገር ግን የማይሆን ነገር ግን አይደለም
እኔም ይህን ማድረግ እንደሚቻል አረጋግጫለሁ››
‹‹ማነው ይህን የነገረህ? እናንተስ እነማን ናችሁ? አለ ኤዲ ንዴቱ ተቀስቅሶ፡

‹‹ትዕዛዝ መፈጸም እንጂ መጠየቅ አትችልም›› አለው ሉተር::

ኤዲ መጀመሪያ ሉተርን ሊያስፈራራው ሞከረ፣ አሁን ግን አቅመ ቢስ ሆኗል፡ አሁን በፍርሃት መሸበብ የእሱ ተራ ሆኗል፡ ሉተር ይህን ጉዳይ በሚገባ ያቀደ የወሮበላ ቡድን አባል ነው፡፡ ኤዲን ለእኩይ ተግባራቸው
በመሳሪያነት ሊጠቀሙበት ነው የመረጡት፡ ውጥናቸውን ዳር ለማድረስ
ደግሞ ካሮል አንን እመዳፋቸው ስር አውለዋታል፡

ኤዲ ፖስት ካርዱን ኪሱ ከተተና ትተባበራለህ ወይስ አትተባበርም?›› ሲል ሉተር በጉጉት ጠየቀ፡፡

ኤዲ ዞር አለና አፈጠጠበት፡ ከዚያም መልስ ሳይሰጥ መንገዱን ቀጠለ፡

ኤዲ በጠላቶቹ ፊት ፈርጠም ያለ ባህሪ ለማሳየት ቢሞክርም እውነታው ግን እንዳንበረከኩት ነው የሚያሳየው እነዚህ ወሮበሎች ለምንድነው ይህን ማድረግ የፈለጉት? ባንድ ወቅት ጀርመኖች ቦይንግ 314 አይሮፕላንን
ሰርቀው ዲዛይኑን ኮፒ ለማድረግ ፈልገው እንደነበር ያውቃል፡ አሁን ይህን ማድረግ ቢፈልጉ አይሮፕላኑን ሜይን ስቴት ውስጥ ሳይሆን አውሮፓ
ውስጥም ሰርቀው መውሰድ የሚያግዳቸው ነገር የለም፡፡

አይሮፕላኑን በሚፈልጉበት ቦታ ላይ እንዲወርድ ለማድረግ ማሰባቸው
ቦታው ላይ የሚጠብቅ ጀልባ እንዳላቸው ይጠቁማል፡ ‹ግን ለምን?› ሉተር ሻንጣ ሙሉ ሃሺሽ፣ ባዙቃ፣ ኮሚኒስት አብዮተኛ ወይስ የናዚ ሰላይ ነው
ወደ አሜሪካ ማስገባት የፈለገው? እነ ሉተር እዚህ ችግር ውስጥ ለመግባት
የወሰኑት መቼም ሊያስገቡት ያሰቡት ሰው ወይም ነገር በጣም ጠቃሚ
ስለሆነ ነው፡፡

ኤዲ ከሌሎቹ የስራ ባልደረቦቹ ይልቅ እሱን የመረጡበት ምክንያት
አሁን ገብቶታል፡አይሮፕላኑን አንድ ቦታ በድንገት እንዲያርፍ ከተፈለገ
ይህን ማድረግ የሚችለው የበረራ መሀንዲሱ ነው፡፡ ናቪጌተሩ ምንም ማድረግ አይችልም የሬዲዮ ኦፕሬተሩም እንዲሁ፤ ፓይለቱ ደግሞ የረዳት
ፓይለቱ ድጋፍ ያስፈልገዋል፡ የበረራ መሀንዲሱ ግን ብቻውን
የአይሮፕላኑን ሞተር ቀጥ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ሉተር የፓን አሜሪካንን አየር መንገድ መሀንዲሶች ስም ዝርዝር ሳያገኝ አልቀረም፡ ስም ዝርዝሩንም ማግኘት ከባድ አይደለም:፡ የአየር መንገዱን መረጃ ለማየት አንድ ምሽት ላይ አንዱ የሉተር ጓደኛ የአየር መንገዱን ቢሮ ሰብሮም ቢሆን ሊያገኘው ይችላል ወይም አንዷን ጸሐፊ በጉቦ መደለል ነው፡፡ ለምን ግን ኤዲን መረጡ? ሉተር በዚህ ቀን የሚበረው የበረራ
መሃንዲስ ስም እጁ ገብቷል ከዚያም ኤዲ ለዚህ ሰይጣናዊ ተግባር
እንዲሆን ለማድረግ ሲያስብ አንድ መላ ያገኛል፤ ሚስቱን ማገት፡፡
እነዚህን ወንበዴዎች መርዳት ለኤዲ ልብ የሚሰብር ጉዳይ ሆኖበታል፡
ወንበዴዎች እጣ ክፍሎቹ አይደሉም፡ ሰርተው ከማግኘት ይልቅ ሌት ተቀን
ከሚለፉ ሰዎች አፍ እየነጠቁና እያጭበረበሩ ተንደላቀው ይኖራሉ፡ ህግ
አክባሪ ሰዎች የዕለት እንጀራ ለማግኘት ጀርባቸው ሲጎብጥ ይውላል፡ እነዚህ
ማፊያዎች ግን ለፍቶ አዳሪዎች ላይ ሽጉጥ እየደገኑ፣ ለፍተው ያገኙትን
ተሽከርካሪዎች ያሽከረክራሉ፡፡ እነዚህን ወንጀለኞች በኤሌክትሪክ ወንበር ላይ ጠፍሮ በኮረንቲ እያንጨረጨሩ መግደል ነው የሚያዋጣው፡፡

ቶም ሉተርን ማሞኘት ቀላል አይደለም፡፡ ሚስቱን ካሮል አንን አግቷታል። ሉተር ያቀደውን ትልም ኤዲ ለማደናቀፍ ሞከረ ማለት በሚስቱ አንገት ላይ የታሰረውን ገመድ ሸምቀቆ አጠበቀ ማለት ነው፡፡ ሊያታልላቸው
ወይም ሊታገላቸው አይችልም፤ ያሉትን ከመፈጸም ውጭ፡

ሆዱን እንደጨነቀው ከወደቡ ወጥቶ በመንደሩ ያለችውን ብቸኛ መንገድ አቋርጦ ወደ አንድ ሆቴል ሄደ፡ ሆቴሉ እንዳለ የተያዘው በፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኞች ነው ማለት ይቻላል፡፡ እዚያም ካፒቴን ቤከርና ረዳቱ ጆኒ ዶት ከፓን አሜሪካ የፎየንስ ጣቢያ ኃላፊ ጋር የራዲዮ
መልእክቶችን እየገመገሙ የአትላንቲክ አቋራጭን በረራ ስለማድረግና አለማድረግ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ጉባኤ በተቀመጡበት ክፍል ኤዲ ገብቶ ተሰየመ፡

በአይሮፕላን በረራ ሳይንስ ቁልፍ ጉዳይ የነፋሱ ጥንካሬ ነው፡፡ ወደ ምዕራብ ሲጓዙ ከጠንካራው ነፋስ ጋር እየታገሉ ነው በረራው የሚካሄደው፡ ከፊት ለፊት የሚመጣውን የንፋስ ግፊት ለመሸሽ ሲሉ ፓይለቶች
በተደጋጋሚ ከፍታቸውን ለመለዋወጥ ይገደዳሉ፡ ይህም ቴክኒክ በበረራው
ሳይንስ ‹ነፋሱን ማሳደድ›› ይባላል፡ ዝቅተኛ ቦታ ላይ ያለ ነፋስ ግፊቱ ያነሰ
ቢሆንም አይሮፕላኑ ዝቅ እያለ በበረረ ቁጥር ከመርከብ ወይም ባህር ላይ ከሚዋልል የበረዶ ቋጥኝ ጋር ሊላተም ይችላል፡፡ ከፊት ለፊት የሚመጣን ንፋስ ግፊት ለመቋቋም በርካታ ነዳጅ ማቃጠል ይጠይቃል፡ ኃይለኛ የንፋስ ግፊት ካለ ከአይርላንድ እስከ ኒውፋውንድ ላንድ (ካናዳ) ከሁለት ሺህ ማይል
በላይ ለመብረር የሚበቃ ነዳጅ አይሮፕላኑ መያዝ ስለማይችል የነዳጅ
እጥረት ሊያጋጥም ይችላል፡ በዚህም ምክንያት በረራው ለሌላ ቀን ሊተላለፍ
ስለሚችል የአየሩ ጠባይ እስከሚሻሻል ተጓዦች በሆቴል ሊቆዩ የሚችሉበት
አጋጣሚ ይፈጠራል፡

የዚህ ዓይነት የአየር መዛባት ቢከሰት ካሮል አንን ምን ይውጣት ይሆን?

የአየር ጠባይ ሪፖርቱ ነፋሱ ከባድ መሆኑን፣ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ደግሞ ከባድ ማዕበል እንዳለ ያመለክታል፡፡ አይሮፕላኑ ሙሉ ሰው ጭኗል፡
ስለዚህ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ሁሉ ነገር በጥንቃቄ መሰላት አለበት፡፡ የአየሩ
ጠባይ መጥፎ መሆን የኤዲን ጭንቀት አባባሰው፡፡ ሚስቱ ካሮል አን በወዲያኛው የውቅያኖስ ጥግ በጨካኝ ወንበዴዎች እጅ ወድቃ እሱ እዚህ አየርላንድ ውስጥ ተጣብቆ መቅረቱን
ሊቋቋመው የሚችለው ነገር
አይደለም፡፡ ለመሆኑ ምግብ ይሰጧት ይሆን? የምትተኛበት ቦታስ አላት
ይሆን? ብርድስ ይመታት ይሆን?› እያለ ያስባል።

የአትላንቲክ ውቅያኖስን አካባቢ የሚያሳየው ማፕ ጋ ሄደና ቶም ሉተር የሰጠውን አይሮፕላኑ እንዲያርፍበት የሚፈለግበትን ቦታ ተመለከተ፡፡ ቦታው
ተጠንቶ የተመረጠ ነው ከካናዳ ጠረፍ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቆ ቤይ አፍ
ፈንዲ› የሚባል በጠረፉና በአንድ ትንሽ ደሴት መካከል የሚገኝ ቦታ ነው:
ምንም እንኳን ባህር ላይ ለሚያርፉ አይሮፕላኖች ማረፊያነቱ ብዙም
ተመራጭ ባይሆንም ከገላጣው የባህር ክፍል የተሻለ ነው፡፡ ይህን ሲያውቅ ኤዲ ተስፋው ለመለመ፡ ቢያንስ የማረፉ ነገር ብዙ ችግር የለውም፡፡ ሉተር ሚስቱን በእጁ እንዲያስገባለትና እቅዱ እንዲሳካ አቅሙን በሙሉ አሟጧዐየተጣለበትን ግዴታ መወጣት አለበት፡

አሁንም ግን አይሮፕላኑን እዚያ ቦታ እንዴት ሊያሳርፍ እንደሚችልዐመጨነቁ አልቀረም፡ በዚህ ቦታ እንዲያርፍ ያደረኩት አንዱ የአይሮፕላኑ ሞተር ስለተበላሽ ነው ቢል በሶስት ሞተር ሊሄድ እንደሚችል ረዳት የበረራ መሀንዲሱ ሚኪ ፊን ስለሚያውቅ ይህ ምክንያት ብዙም አያስኬድም የአዕምሮውን ጓዳ ቢያስስም ተጨባጭ መፍትሄ አልመጣለት አለ፡፡
👍16
በካፒቴን ቤከርና በሌሎቹ የስራ ባልደረቦቹ ላይ የሚያሴረው ነገር
እምነት አጉዳይ ስለሚያደርገው ሰላም ነስቶታል፡ በእሱ ላይ እምነት ጥለው አገር ሰላም ነው ብለው በተሳፈሩት ሰዎችም ላይ ክህደት ሊፈጽም ነው፡
ምን ምርጫ አለው?

ድንገት አዕምሮው ላይ የመጣው ሃሳብ ደግሞ ሌላ ፍርሃት ጫረበት።
‹ቶም ሉተር ቃሉን ባይፈጽምስ?› ለምንስ ይፈጽማል? እሱ እንደሆነ ወሮበላ ነው፡፡ ኤዲ እንደምንም ብሎ አይሮፕላኑን አሳርፎም እኮ ካሮል አንን ላይለቁለት ይችላሉ፡

የአይሮፕላኑን አቅጣጫ የሚቆጣጠረው ባለሙያ (ናቪጌተሪ) ጃክ ተጨማሪ የአየር ሁኔታ ሪፖርቶች አመጣለትና ኤዲን ‹ምን ነካው› በሚል አስተያየት አየት አድርጎት ሄደ፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ከገባ ጀምሮ ምንም እንዳላናገረው ኤዲ ተረዳ፡፡ ሁሉም አልፈውት ይሄዳሉ፤ ‹አዕምሮው በሆነ
ነገር የውጥር መያዙን አውቀውበት ይሆን?› ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ
ሁሉ ከሌላው ጊዜ ያልተለየ የስራ ባህሪ ማሳየት ይኖርበታል፡፡

‹‹ይህ ጉዞ የሰመረ እንዲሆን የተቻለህን ጥረት አድርግ ጃክ›› አለ ኤዲ
የዘወትር አባባሉን በመድገም፡፡ እሱ እንደሆን ማስመስል አይሆንለትም፡
በግድ ነው ይህን ካፉ አውጥቶ የተናገረው፡ ሆኖም ባለው ነገር ተሳስቀው ተለያዩ፡፡

ካፒቴን ቤከር አሁን የደረሱትን የአየር ጠባይ ሁኔታ መረጃዎች ተመለከተና ‹‹የነፋሱ ግፊት እየከፋ ነው›› አለ፡፡

ጃክ በመስማማት ራሱን ነቀነቀ፡

ቤከርም ‹‹ንፋሱን ለመሸሽ በውስጡ ሳይሆን በንፋሱ ዳር ዳር ነው የምንሄደው›› አለ፡፡

ካፒቴን ቤከርም ረዳቱ ጆኒ ዶት ቦትውድ ኒውፋውንድ ላንድ የሚያደርሳቸውን የበረራ ዕቅድ አዘጋጁ፡ በዚህም የበረራ ዕቅድ ፊት ለፊት የሚመጣውን ንፋስ ትተው ዳር ዳሩን ይበራሉ፡ ኤዲም የቀረበለትን የአየር
ሁኔታ መረጃ ይዞ የጉዞ ስሌቱን መቀመር ጀመረ፡ በተለያዩ ጫማ ከፍታዎች ላይ ሊኖር የሚችለውን የንፋስ አቅጣጫና የአየር ግፊት ኃይል ይገምታል፤ የአይሮፕላኑንና የአየር ላይ በረራና የነፋሱን የግፊት ኃይል ካወቀ ደግሞ በምድር ላይ ሊኖር የሚችለውን የንፋስ ፍጥነት ማስላት ይችላል፡ በዚህ ስሌት መሰረትም በእያንዳንዱ የበረራ መደብና የከፍታ
መጠን ላይ አይሮፕላኑ የሚወስድበትን የበረራ ጊዜ ያሳውቀዋል፡፡ በስሌቱም
ላይ በመመስረት አይሮፕላኑ የሚያስፈልገውን የነዳጅ መጠን ማወቅ
ይችላል በየደረጃው ላይ የሚያስፈልገውን የነዳጅ መጠንም በግራፍ ላይ
ያስፍርና ጠቅላላ ድምሩን ከሠራ በኋላ የተወሰነ መጠባበቂያ ይይዛል፡

የነዳጅ ፍላጎቱ እጥረት ብዙም ችግር የሚፈጥር አይደለም፤ ነገር ግን
ባለው ነዳጅና በሚፈለገው ነዳጅ መጠን ያለው ልዩነት በጣም ትንሽ ነው፡፡
ታዲያ ካፒቴን ቤከርን መዋሸት ሊኖርበት ነው፡፡

አይሮፕላኑ ምንጊዜም መጠባበቂያ ነዳጅ ይይዛል፡፡ የነዳጅ እጥረት
ከመጣም አይሮፕላኑ በአውሎ ንፋሱ ዳርቻ ሳይሆን አውሎ ንፋሱን ሰንጥቆ መብረር የሚገደድበት ሁኔታም አለ፡፡
በደህና ጊዜ ቢሆን የአይሮፕላኑን አዛዥ ማታለል የሚቀበለው ነገር
አይደለም፡፡ ኤዲ የሚሰጠው ውሳኔ የሚለወጥ አይደለም፡፡ በበረራ ላይ እያሉ
በየሰዓቱ በግራፍ ላይ የተቀመጠው የነዳጅ ፍላጎት ትንበያ በትክክል
አይሮፕላኑ ከተጠቀመው የነዳጅ መጠን ጋር መነጻጸር ይኖርበታል፡ የተደረሰበት ስሌት ጥቅም ላይ የዋለው ነዳጅ ከትንበያው መብለጡን የሚያመለክት ከሆነ አይሮፕላኑ ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ወደ ኋላ እንዲመለስ ይደረጋል፡፡

ምናልባትም አሳስቶ ያሰላው ስሌት ከታወቀበት ከስራ መባረሩ አይቀርም፤ ነገር ግን የሚወዳት ነፍሰ ጡር ሚስቱና በሆዷ የተሸከመችው ጽንስ አደጋ ላይ ወድቀው ምን ምርጫ ይኖረዋል?

ከዚያም ስሌቱን እንደገና ሲሰራ ሆን ብሎ ስህተት በመፍጠር የሚያስፈልገውን የነዳጅ መጠን ለወጠው፡፡ ነገር ግን በሰራው ስራ ጥርጣሬ ገባው፡፡ ጥሎበት መዋሸት አይሆንለትም፡፡
በመጨረሻም ካፒቴን ቤከር የስሌቱን ውጤት መጠበቅ ሰለቸውና ‹‹ነዳጁ ይበቃል አይበቃም? መብረር እንችላለን አንችልም?›› አለና ጠየቀው፡፡

ኤዲም አለቃውን በቀጥታ ማየት ፈርቶ እንዳቀረቀረ ውጤቱን ወረቀት ላይ ጽፎ አሳየውና በሙሉ ልብ ‹‹መብረር እንችላለን›› አለው:
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ከፎየንስ አየርላንድ እስከ መሀል አትላንቲክ

ዳያና ላቭሴይ በውሳኔዋ መለወጥ ብታዝንም አሁን ተረጋግታለች፡ ወደ
አሜሪካ አልሄድም ብላ ወስናለች፡፡ ማርክ አልደርንም አታገባም፡፡

ብቻቸውን ሲሆኑ ልትነግረው ወስናለች፡፡ አብራው እንደማትሄድ
ስትነግረው ልቡ እንደሚሰበር ስታስብ ልቧ ተነካ፡፡ ማርክ በጣም ይወዳታል፡ነገር ግን ይህን ማሰብ ከዚህ በኋላ አይረባትም፡፡

ሁሉም ተሳፋሪዎች ከአይሮፕላኑ ሲወርዱ ከዳያና አጠገብ የተቀመጡት መልከ መልካሙ ፍራንክ ጎርደንና ራስ በራው ኦሊስ ፊልድ ብቻ ከወንበራቸው ጋር ተጣብቀው ቀሩ፡፡ ሉሉ ቤልና ማርክ አልደር የባጥ
የቆጡን መቀበጣጠራቸውን አላቆሙም፡፡ ዳያና ሉሉ ቤልን ፊት ነስታታለች፡
በሉሉም መብሸቁን ትታዋለች፡፡ በሰው ፍቅር ጣልቃ ገብታ የምትበጠብጥ
መሆኗን አውቃለች፡፡

ከአይሮፕላኑ ወርደው፣ ወደቡን አቋርጠው አንድ መንገድ ብቻ ወዳለው
መንደር ዘለቁ፡ ዳያና እግሮቿ ሰውነቷን መሸከም ስላቃታቸው ይንቀጠቀጣሉ መንገዳቸው ላይ የከብት መንጋ ገጠማቸውና እነሱን
ለማሳለፍ ቆም አሉ፡፡

ልዕልት ላቪኒያ ‹‹ለምንድነው እዚህ ባላገር ያመጡኝ›› ብለው ሲማረሩ
ዳያና ሰማች፡፡

የአይሮፕላኑ አስተናጋጅ ዴቪ ‹‹ወደ አይሮፕላን መናኸሪያው እኔ
እወስድዎታለሁ፤ የአይሪሽ ውስኪ የሚሸጥበት ቡና ቤት አለ›› አላቸው፡፡

ከብቶቹ ካለፉ በኋላ ዴቭ ተሳፋሪዎቹን ወደ ቡና ቤቱ ወሰዳቸው፡፡ ዳያናም ‹‹መንደሩ ውስጥ ቆይታ እናድርግ›› ስትለው ማርክ እሺ አላት፡፡

በመንደሩ አንድ የባቡር ጣቢያ፣ ፖስታ ቤትና ቤተክርስቲያን አለ፡፡
በመንገዱ ግራና ቀኝ ጣራቸው በሸክላ የተሰራ የድንጋይ ቤቶች የሚታዩ
ሲሆን አንዳንዶቹ ቤቶች ሱቅ አላቸው፡ ሱቆቹ ፊት ለፊት በበቀሎ የሚሳቡ
ጋሪዎችና አንድ የጭነት መኪና ቆመዋል፡ የመንደሩ ነዋሪዎች የለበሱት
ቤት ውስጥ የተዘጋጁ ልብሶች ነው፡ ፎየንስ ከመላው ዓለም የመጡ
ሀብታሞችን አስተናግዳ ስለማታውቅ ነዋሪዎቹ እንግዶቹን እንደ ትንግርት
አፍጥጠው ያይዋቸዋል፡፡

ዳያና ሰዎቹ እንዲበታተኑ ብትፈልግም ሰዎቹ ግን እንዳይጠፉ የሰጉ አገር አሳሾች ይመስል እየተጓተቱ ይሄዳሉ፡፡ ዳያና ወጥመድ ውስጥ የገባች መሰላት፡ ጊዜ እየሄደባት ነው፡፡ ወደ ሌላ ቡና ቤት ሄዱና ‹‹እዚህ እንግባ አለችው ማርክን፡፡ ሉሉ በዚህ ጊዜ ከአፉ ነጥቃ ‹‹ጥሩ ሃሳብ ነው፤ ፎየንስ ውስጥ የሚታይ ነገር የለም›› አለች፡

ዳያና የሉሉ ነገር አንገቷ ደርሷል፡፡ ‹‹ማርክን የማናግረው ነገር ስላለ
ብቻችንን ብትተይን›› አለቻት ሉሉን፡፡

ማርክ በዳያና አባባል አፈረ፡፡ ‹‹ምነው የኔ ማር እንደዚህ መናገርሽ?››

‹‹ግዴለም›› አለች ሉሉ ‹‹ፍቅረኛሞች ብቻችሁን አውሩ፡፡ ሌላ ቡና ቤት
ካለ እዚያ እሄዳለሁ›› አለች ያልተከፋች መስላ ማርክም ‹‹ሉሉ ይቅርታ›› አላት እየፈራ፡፡

ዳያና፣ ሉሉን ይቅርታ መጠየቁን አላስደሰታትም፡፡ ከመቀመጫዋ ምንቅር ብላ ተነስታ ጥላው ሄደች፡፡

ቦታው ጨለምለም ያለና ቀዝቃዛ ነው:: ቡና ቤቱ ውስጥ ጠርሙስና
በርሜል ተገጥግጦበታል፡ ከእንጨት የተሰሩ ጠረጴዛዎችና ወምበሮ
ከጣውላ በተሰራው ወለል ላይ ተደርድረዋል፡፡ ቡና ቤቱ ውስጥ የተቀመጡ
ሁለት ጠና ያሉ ሰዎች ዳያና ላይ ዓይናቸውን ተክለዋል፡፡
👍12
አንድ አጠር ያለች ያሸረጠች ሴት ወደ ባንኮኒው መጣችና ‹‹ምን ልታዘዝ?›› ስትል ‹‹አንድ መለኪያ ብራንዲ ስጪኝ›› አለችና ዳያና ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

ማርክ ተከትሏት መጣ፡፡ አጠገቧ ተቀመጠና ‹‹ዳያና ምን ነካሽ?›› አላት
‹‹ሉሉ በቅታኛለች››
‹‹ይሄ ብልግና ነው፡››
‹‹ብልግና አይደለም በወሬ ጠምዳህ አንተን እንዳላናግር አድርጋኛለች፡
አንተ የኔ ብቻ ነህ››
‹‹ታዲያ ምናለ ይህንን በጨዋ ደምብ ብትናገሪው››
‹‹ሁኔታዬን አይታ ወሬዋን ማቆም ነበረባት›› አለች፡፡
ማርክ ተናደደ፡፡ ‹‹ተሳስተሻል የኔ ማር ሉሉ ሳቂታ ብትሆንም ሆደ
ባሻ ናት፤ ይሰማታል››
‹የሆነ ሆኖ አንዴ ሆኗል፤ የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም››
እንዴት እንዲያ ትያለሽ፧ ያስቀየምሽው እኮ የልጅነት ጓደኛዬን ነው›› አላት

አስተናጋጇ ዳያና ያዘዘችውን ብራንዲ አመጣችላት፡ ንዴቷን ለማብረድ ትንሽ ተጎነጨችለት፡፡ ማርክ ቢራ ነው ያዘዘው፡

ዳያናም ቀጠለችና ‹‹ያልኩትን ብልም ከዚህ በኋላ የሚያመጣው ለውጥ
የለም፧ ሃሳቤን ስለለወጥኩ አሜሪካ ካንተ ጋር አልሄድም››

ማርክ ይህን ሲሰማ ፊቱ አመድ መሰለ፡፡ ‹‹እውነትሽን ነው?›› ሲል ጠየቀ።

‹‹ይህን ሳስብበት ነው የቆየሁት አብሬህ አልሄድም፧ ወደ ባሌ
እመለሳለሁ፧ እቤቱ የሚያስገባኝ ከሆነ›› አለች ዳያና ተመልሳ ብትመጣ ባሏ እንደሚቀበላት እርግጠኛ ባትሆንም፡፡

‹‹እንደማትወጂው ነግረሽኛል፧ እኔም ይህን አውቃለሁ››

‹‹አንተ እንዴት ታውቃለህ፤ ትዳር መስርተህ አታውቅ›› አለችው፡፡ይህን ስትለው ማርክ መከፋቱን አየችና እጇን ጭኑ ላይ ጣል አድርጋ ለስለስ ባለ አንደበት ‹‹ልክ ነህ አንተን የምወድህን ያህል መርቪንን አልወደውም›› አለች፡፡ በአድራጎቷም አፈረችና እጇን ከጭኑ ላይ አነሳች፡፡

“ባሌን ትቼ መምጣቴን እግዚአብሔር አይወደውም፡፡››

‹‹ከሉሉ ጋ ስጫወት አንቺን ዘነጋሁሽ›› አለ ማርክ በመጸጸት፡፡ ይቅርታ አድርጊልኝ የኔ ቆንጆ ካገኘኋት ረጅም ጊዜ ስለሆነኝ አንቺን ረስቼ
ከእሷ ጋር ስጫወት ዋልኩ አንቺን ፊት ለመንሳት ብዬ አይደለም ይህ ደግሞ እኔና አንቺ አዲስ ምዕራፍ የምንከፍትበት ጊዜ ነው፡፡ ስላጠፋሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ››

ስህተቱን አምኖ አጥብቆ ይቅርታ ስለጠየቃት ሆዷ ተንቦጫቦጨ፡ ከአንድ ሰዓት በፊት ምን ያህል ደስተኛ እንደነበረች አስታወሰች፡፡ ‹‹ሉሉ አይደለችም ችግሬ፤ ግዴለሽነትህ አስገርሞኝ እንጂ›› አለችው፡፡

አስተናጋጇ ማርክ ያዘዘውን ብታመጣለትም አልነካውም፡፡ ዳያና
ቀጠለችና ‹‹ያለኝን በሙሉ ማለትም ቤቴን፣ ባሌን፣ ጓደኞቼን፣ ዘመዶቼንና
አገሬን ትቼ አንተን ተከትዬ ወጣሁ፡ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ በአየር
መጓዝ አደገኛ ነው፡፡ የምሄደውም የማላውቀው አገር ከመሆኑም በላይ
ለአገሩ ባዳ ለሰው እንግዳ እሆናለሁ››

ማርክ በእጅጉ አዘነና ‹‹ምን ያህል ስህተት እንደሰራሁ አሁን ነው የገባኝ፡፡ ለካ ብቻሽን ትቼሽ አበሳጭቼሻለሁ የኔ ማር፡፡ ምን አይነት ድንጋይ
ራስ ነኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ይህን ስህተት አልደግመውም›› አለ፡፡

ማርክ ቃሉን ይጠብቅ ወይም አይጠብቅ ይሆናል፡፡ ጥሩ አፍቃሪ ቢሆንም ግዴለሽነት ያጠቃዋል ለምንም ነገር አይጨነቅም፡ በአንድ ሀሳብ ላይ መርጋት ብሎ ነገር አያውቅም፡፡
አሁን ሃቀኛ ቢመስልም ሌላ ጓደኛው ቢመጣ ቃሉን አያፈርስም? በመጀመሪያ ደረጃ የሳባት ተጫዋችነቱ
ለህይወት ቁብ አለመስጠቱ አይደለም እንዴ? ነገር ግን ይህ ተለዋዋጭ ባህሪ አለው ከተባለ እምነት የሚጣልበት መሆኑ ነው፡፡ መጥፎም ሆነ ጥሩ
ባህሪው አይለወጠም።

‹‹ባንተ መተማመን የምችል አይመስለኝም›› አለችው ዳያና፡፡

ንግግሯ አበሳጨውና ‹‹መቼ ነው ቃሌን ሳላከብር የቀረሁት እባክሽ?››

‹‹ማድረግህ አይቀርም›› አለች ለምሳሌ ያህል ብላ የምታቀርበው ነገር ባይኖራትም።

‹‹የሆነ ሆኖ ሁሉን ነገር ትተሽ መሄድ ትፈልጊያለሽ፤ መቼም ይህን አትክጂም ትዳርሽ እክል አለበት አገርሽ በጠላት ተወራለች፤ በኑሮሽ
መንገሽገሽሽን ነግረሽኛል፡››
አለ፡፡

‹‹አንገሽግሾኛል አልኩህ እንጂ ወደ አሜሪካ መሄድ አያስፈራኝም አላልኩህም››

‹‹አሜሪካ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም፤ አሜሪካ እንደ እንግሊዝ
ነው፡፡ ህዝቡ እንግሊዝኛ ነው የሚናገረው፡ እዚያ የሚታየው ፊልም እዚ"
ከሚታየው ጋር አንድ ነው: እንግሊዝ አገር የሚደመጠው ጃዝ ሙዚቃ
አሜሪካም አለ፡፡ አሜሪካንን ገና ስታያት ትወጂያታለሽ፡ እኔም እየተንከባከብኩሽ የባልነት ግዴታዬን እወጣለሁ፡፡››

ማርክ የሚለው ሁሉ እውነት እንዲሆን ዳያና ተመኘች፡፡
‹‹ሌላም ነገር አለ፤ ልጅ እንወልዳለን›› አላት፡
ይህን ሲል በሃሳቧ ወደ ቤቷ ነጎደች፡፡ እሷ ልጅ መውለድ ብትፈልግም መርቪን ልጅ እንደማይፈልግ እንቅጩን ነው የነገራት፡ ማርክ ጥሩና
አፍቃሪ አባት ሳይሆን አይቀርም፡፡ አሁን ግራ ገብቷት ለመወሰን ተቸገረች
ቆራጥነቷ እየከዳት መጥቷል፡ ምናልባትም ሁሉን ነገር ጣጥላ ማርክን
ተከትላ መሄድ ሳይኖርባት አይቀርም፡፡ የልጅ እናት ካልሆነች ትዳር ማለት
ምንድነው ትርጉሙ? ካሊፎርኒያ ሲደርሱ ማርክ ጥሏት እብስ ቢልስ? ሌላ
ሴት የማርክን ልብ አሸንፋ ብትነጥቃት በሰው አገር ምን ይውጣታል? አሜሪካ ውስጥ ያለ ባል፣ ያለ ገንዘብ፣ ያለ ቤት ብቻዋን መቅረቷም አይደል?
ቶሎ እጇን መስጠት አልፈለገችም፡፡ ማርክን ተከትላ ከመሄዷ በፊት
ወደፊት ሊገጥሟት የሚችሉትን ችግሮች በጥንቃቄ መመርመርና ከማርክ ጋር በሚገባ መነጋገር እንዳለባት ተገንዝባለች፡ ድንገት አንድ ነገር የሚከስት ከሆነ በሚል የመመለሻ ትኬቷን መግዣ ገንዘብ መጠየቅ ሊኖርባት ይችላል ነገር ግን ይህ ጥያቄ ማርክን ሊያበሳጨው ይችላል፡

በተቃራኒው ጦርነት
ወደ ተዘፈቀች አገር መመለሱ ራሱ አንድ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው፡.... እዚህ ነገር ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ለምን ገባሁ? አለች ልቧ
እየተሰበረ ሁን ለመጸጸት ጊዜ የለም፡ አንዴ ስለወሰንኩ ወደ ኋላ
የምልበት ነገር የለም፡፡ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥም አለች መልሳ
በሆዷ ሀሳቧ አንድ ቦታ አልረጋ ብሏት፡...

ይቀጥላል
👍13
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ ዘጠኝ (19)

«ደሞ ሌላ ነገር የድምፅ አወጣጥ ልምምድ ለማድረግ ይህ ሙያ ካለው ሰው ጋር ተዋውዬ ጨርሻለሁ» ፌ አሊሰን በአድናቆት ተመለከተቻት ።
« ለፒተር ነግፊዋለሁ ። የሙሉ አካል አንድ ብልት ነው የድምፅ ጉዳይ ብሎ አስፈላጊ መሆኑን ነገረኝ ። ነገ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ልምምዱን እጀምራለሁ ። ዳንስ ግን ትንሽ አስቸጋሪ ነገር ሆኗል ። ኦፕራሲዮን ስላልጨረስኩ መቆየት ይኖርበታል ። በሚቀጥለው ዓመት በጋ ላይ የዳንስ ልምምዴን ልጀምር እንደምችል ፒተር ነግሮኛል »

« በጣም ሊኮራብሽ የሚገባ ጓደኛ ነሽኮ ናንሲ! » አለች ፌ
« እኔም እንኳ በራሴ ኩራት ይሰማኛል »

ያንለት ፌ አሊሰንና ናንሲ ማክአሊስተር ብዙ ተነጋገሩ። ዶክተር ፌ አሊሰን የናንሲን የመንፈስ ጥንካሬ ለመገንባት የተቻላትን ያህል ስታደርግ ፤ ዶክተር ፒተር ግሬግሰን ዶሞ የናንሲን ፊት ለመጠገን ብቻ ሳይሆን እንደ አዲስ ለመስራት ያለውን ዕውቀት ፤ የተሰጠውን ጥበብ ሁሉ በሥራ ላይ ለማዋል ቆርጦ ተነስቶ ነበር ።

ከላይ በተባለው ቀን የፌ አሊሰንና የናንሲ ውድይት የተቃና ነበር ። የሚገርመው ደግሞ በዕለቱ የማይክል ሂልያርድ ስም አልተነሳም ። ይገርማል የተባለውም ሁለቱ ሴቶች ፌ እና ናንሲ ስምንት ወራት ያህል ሲወያዩ የማይክል ስም ያልተነሳው በዚህ ቀን ብቻ ነበርና ነው።

ከዚያ ቀን በኋላ ግን ሙሉ የዝናሙ ወቅት እስኪያልፍ ናንሲ ስለማይክል ፈዕሞ አላነሳችም ። የምታወራው ለወደፊት ስላቀደችው የዳንስ ትምህርት ፤ የድምዕ አወጣጥና የዘፈን አሰልጣኟ ስለሰጣት አስተያዬት ፤ ስለመሳሰሉትና በተለይም በፎቶግራፍ ማንሳት ጥበብ እየረቀቀች ስትሄድ ፤ ስለ «ፎቶግራፍ አነሳስና ስለኪነጥበብነቱ ፤ ለወደፊት ይህን ሙያ በምን ሁኔታ ልትሞክረው እንደምትሻ ብቻ ነበር ።። ክረምቱ ኣልፎ የጸደይ ወራት ሲገባ፤ ናንሲና ፍሬድ ወደ ተለያዩ መናፈሻዎች ፣ የአበባ ቦታዎችና መዝናኛዎች እየሄዱ ሽርሽር ያደርጉ ጆመር ። አንዳንድ ቀን ደግሞ ፒተር ግሬግሰን (ሐኪሙ) ናንሲን ጭር ወዳሉ የወደብ መናፈሻዎች ይወስዳታል ። ይህም ናንሲ ስለ ፊቷና ፋሻው ብዙ እንዳይሰማት ለማድረግ ነው ። ጊዜ እየገፋ ሲሄድ የናንሲ ፊትም ብቅ እያለ ሄደ ። ከናፍሯን ፤ አፍንጫዋን ፤ ጉንጯን በሕክምና ጥበብ እስትካክሎ ሲሠራ ፤ እነዚህ ነገሮች አዲስ ሆነው ብቅ ሲሉ ፤ ሰብአዊ ባህሪዋም ውስጣዊ ነፍሷም ብቅ ማለት ጀመረች። ያች ባለፈው ዓመት ብዙ ችሎታዎችን የማታውቀው ናንሲ ፤ ያች ያላትን ብርቅ ድንቅ የሆነች ንጹህ ነፍስ ያልተትገነዘበች ናንሲ በመጪው ወር ማለት አደጋው በደረሰ ባመቱ የበሰለች በጣም በርካታ ነገሮችን ተገንዝባ ፤ ራሷን ችላ በርካታ ነገሮችን መፈጸም የምትችል አዲስ ሰው ሆና ብቅ ስትል አየቻት ፌ አሊሰን ። ፌ የጊዜውን መንጎድ ስታስበው ደነቃት ።
« አንድ ዓመት ሆነ ማለት ነው? » ኣለች ፌ።
« እዎ ልክ አንድ ዓመት ። አምና በግንቦት ወር ላይ አይደለም አደጋው የደረሰው ?»
‹‹ይገርማል።ጊዜኮ...»
«ፌ፣ ካንች ጋር ከተገናኘን ደግሞ ልክ ስምንተኛ ወራችን ሞላ ። እንዴት ነው ፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ብዙ ያሻሻልኩት ነገር ያለ ይመስልሻል ?» ናንሲ ይህን ስትል ትንሽ የመሰላቸትና ጥስፋ የመቁረጥ ቃና በድምጺ ውስጥ ይሰማ ነበር ። ምንም አይደለም ። ያለፈው ቀን ኦፕራሲዮን ስላደከማት ነው። ድካሙ ለቀቅ ቢያደርጋትቸ መንፈሷም ይነፃል ስትል አሰበች ፌ ። ፒተር በዚያ ሰሞን ዓይኗንና የዓይኗን አካባቢ በመጠገን በማስተካከል ላይ ነበር ። እፊቷ ላይ ያለው ፋሻ ተነስቶ ሰፊ ጥቁር መነፅር አድርጋለች ። ዓይኗን እጉንጭ አጥንቷ ድረስ ይሸፍናል፤ መነፅሩ። « ትጠራጠሪያለሽ ናንሲ ?» አለች ፌ ያሻሻልኩት ነገር ያለ ይመስልሻል ? ስትል ለጠየቀቻት ጥያቄ ስትመልስ ።
« እንዳንዴ እጠራጠራለሁ ። ምክንያቱም ደርሼ ስለማይክል አስባለሁ ፤ እየሽ የሚመጣ ፤ የማሪዮንንም ውል ገደል ይግባ ብሎ የሚመጣ፤ አብረን የምንሆን ይመስለኛል» ዝም አለች ፌ አሊሰን። « አየሽ» ቀጠለች ናንሲ ማክአሊስተር « ስለማይክል ማሰብ ምንም እንደማይጠቅመኝ ፤እንዲያውም እንደሚጎዳኝ ይገባኛል ። ግን አልችልም ። እኔ እንጃ ብቻ. . .›› ናንሲ ንግግሯን አቋርጣ ፌን ትመለከታት ጀመር ። « አይዞሽ» አለች ፌ አሊሰን « ትንሽ ጊዜ ታገሽማ እና ታያለሽ ። እሁን ሁሉ ነገር ሊነሳ ፤ ከሰው ጋር መዋል ስችጀምሪ ፤ አድርገሽው የማታውቂውን ነገር ስታደርጊ ፤ ሌላ ሰው ልዩ ሰው ስትሆኝ ትረሽዋለሽ ። ሀሳቡ ራሱ አሁን የሚመጣውን ያህል ያኔ ራሱ ይቀራል ። አትስጊ ። ትንሽ ታገሽ ግን »
« መታገስ ፤ መታገስ እሁንስ እንደመታገስ የሰለቸኝ ነገር የለም ! » አለች ናንሲ ። ፌ አሊሰን በጸጥታ ታዳምጣት ነበር ።

« ታውቂያለሽ» አለች ናንሲ « አንዳንዴ ይኸ ፋሻ መቼ ነው የሚነሳ ? እላለሁ ። ይነሳል ትንሽ ታገሽ ይለኛል ፒተር ። ይህን ሲለኝ ፤ይህን ሲደጋግም መታገስ አስጠላኝ ፡ ሰለቸኝ ። እንዳንዴ ፊቲን ሲያፈርስ ሲሠራ ፤ ሲለጥፍ ሲለስን ፤ ሲቆልል ሲያድቦለቡል ዘላለም የሚኖር መስሎ ይሰማኛል ። ፒተርን ምርዝ አድርጌ እጠላለሁ ። ሞኝ አትሁኝ ። ፒትር እንዳልቦዘነ ፤ ወይም እንዳልለገመ እውቃለሁ ። ግን ዝም ብዬ እለ አይደል እጠዋለሁ»

«ግንኮ ብታስቢው የፈጀው ጊዜና ያስገኘው ፍሬ የትናየት ነው። ይህችን የመሰለች ቆንጆ ስትወጣ ? » አለች ፌ የናንሲን ፊች እየተመለከተች ። ሁለቱም በደስታ ፈገግታ በሩ

የናንሲ ፊት ተስተካክሎ እየወጣ ሲሄድ ድምጺም ለስለስተኛና የሙዚቀኛ ቃና ያለው ሆኖ ነበር ። ናንሲ ስትናገር ስትስማ ፌ እጅግ ተገረመች። የሰው ልጅ ምንም ያህል ጎበዝ አሰልጣኝ ቢያጋጥመው ይህን የመሰለ ጥዑም ድምፅ ይኖረዋል ብላ አስባ እንደማታውቅ በልቧ እያሰበች ። «ለምን የተዋናይነት ሙያ አትሞክሪም ? ጥሩ ሙያ ነው። ይህ ሁሉ ነገር ከደረሰብሽ በኋላ » አለች ፌ ። « ተዋናይነትንኳ እንጃ ። ግን ከካሜራዬ ጀርባ ቆሜ ፎቶግራፍ እንሺነትን አልጠላውም » አለች ናንሲ ። « ደስ እንዳለሽ ። ድንገት ብልጭ ስላለብኝ ነው ። የዚህ ሳምንት ዕቅድሽ ምንድነው ?»
« ፒተርን ፎቶ ላነሳው አስቤአለሁ ። ነግሬዋለሁ ። እሱ ደግሞ ወደ ሳንታ ባርባራ ሰዎች ሊጠይቅ እንደሚሄድ ነግሮኝ አብረን ልንሄድ ተስማምተናል »
« እናንተ ዓለማችሁን ቅጩ እኔ ምን ይዋጠኝ?... ደግ እንግዲህ ማክሰኞ ፤ የለም ረቡዕ ለት አንገናኝ »
« እሺ እመቤቴ »

ከፌ አሊሰን ቢሮ ወጥታ ምን ጊዜም የማይለያትን ፍሬድን አስከትላ አንድ ሁለት ሕንፃዎች አልፎ ወደሚገኝ የሕፃናት መጫወቻ ቦታ አመራች ። በቅርብ ልጆችን ፎቶ ኦንስታ አታውቅም ነበረ ። ልጆች ነበሩ ። እንደደረሰች ኣንድ ማረፊያ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ሲጫወቱ ትመለከት ጀመረ፡፡ ከየት መጡ ? የማናቸው ? ለማን ነው የሚለፉት ? አለች በሀሳቧ የማንም ሆኑ የማን ሲጫወቱ ደስ ይላሉ

ልጆች ደስ ይላሉ
ቀኑም ደስ የሚል ቀን ነበር ።
ስለዚሀ እሷም ደስ አላት ።

•••••••••••••••••••••
👍131
«እዚህ ቦታ ሁልጊዜ ትመጣለህ?›› ማይክል በድንጋጤ ባንኖ ቀና አለ ። አንዲህ የጸደይ ወር ሲመጣ በፊትም ነጭ ሆኖ የከረመው ፤ በኋላም ወደግራጫነት የተለወጠው ነገር ሁሉ ደርሶ ሲለመልምና አረንጓዴ ሲሆን መንፈስን የሚያድስ ኃይል አለው ። ማይክል ሂልያርድ የቢሮው መታፈን ሲበዛበት ጊዜ ትንሽ መንፈሴ ዘና ቢል ብሎ ባቅራቢያው ወደሚገኘው መናፈሻ ቦታ ሄዶ ቁጭ ብሎ ነበር ። እዚያ ቦታ ማንም እንደማይረብሸው ተስፋ ነበረው ። ተሳስቶ ኖሮ ከላይ የጠቀስናቸውን ቃላት ሰማ ። ቀና ሲል ዌንዲ ታውንሴንድ አጠገቡ ቆማ ተመለከተ። «የ...የለም… ሁልጊዜስ አልመጣም ። እንዲያው የሆነ የጸደይን ፍስሀ የመቅመስ ድንገተኛ አባዜ ያዘኝና መጣሁ እንጂ... »
«እኔንም ልክ ያንተው ዓይነት ነገር ነው ያመጣኝ›› አይስክሬም ይዛ ነበረና እንደማፈር ያለች መሰለች ። ይባስ ብሎ ከላይ ቸኮላቱ ተፈርክሶ ሊወድቅ ሲል እንደምንም ብላ ባፏ ተቀበለችው ።
« ሲያዩት በጣም የሚጥም ይመስላል» አለ ማይክል ከፈላው የጸደይ አየር ጋር ፈካ ያለ ፈገግታ እያሳያት ።
« ላካፍልሀ ?»
« ተይው ይቅርብኝ ። ስለልግስና'ሽ አመሰግናለሁ ። መቀመጥ ትፈልጊያለሽ ? »

እንደሥራ ፈት በሥራ ሰዓት እመናፈሻ ውስጥ ሲያወደለድል በመያዙ እፍረት ተሰምቶታል ። የገና በዓል ዋዜማ ዕለት እቢሮው ድረስ ሄዳ እንኳን አደረሰህ ካለችው በኋላ በየጊዜው ሲተያዩ፤ በአንዳንድ ምክንያትም ሲገናኙ ቆይተዋል ። ደስ የምትል ልጅ ናት የሚል ሃሳብ በልቡ ውስጥ እየፀነሰ ሲሄድ ቆይቷል። አጠገቡ ቁጭ ብላ አይስክሬሟን ጨረሰች ። « ሥራ እንዴት ነው ? ለመሆኑ አሁን ምን እየሠራሽ ነው አላት ። « የህውስተንና የካንሳስ ሲቲ ፕሮጀክቶችን እየሠራሁ ነው። አንድ ፕሮጀክት ላይ የኔ ሥራ ሁልጊዜም አንተ ከጨረስክ ከመንፈቅ በኋላ ነው የሚጀምረው ። የአንተን ዱካ እየተከታተሉ መሥራት በጣም ያስደስተኛል »
« ይኸን ንግግር ምን እንደምለው አላውቅም »
‹‹ምስጋና በለው »
« እግዜር ይስጥልኝ ። በነገራችን ላይ ቤን ምን ዓይነት አለቃ ነው ?ማለቴ ደግ ነው ወይስ መሆን አለብህ ብዬ ባስጠነቀቅሁት መሰረት ጨካኝ ባሪያ ፈንጋይ ነው ? »
« ጭካኔ የሚባል ነገር ቢሞክርም አይሳካለት » |
« ይገባኛል ። አውቃለሁ » አለ ማይክል በትዝታ ፈገግታ ተውጦ ። « ታውቂያለሽ፤እኔና ቤን የረጅም ጊዜ ትውውቅ አለን ። እንዲያውም ወንድማማች ማለት ነን»
« በጣም ግሩም ሊወደድ የሚገባ ሰው ነው » ማይክል ራሱን በአወንታ ነቀነቀ ፤ በጸጥታ ። ወደ ሀሳብ ውስጥ ገባ ። ቤንን ካየው ምን ያህል ሩቅ ነው ይህን ሥራ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ እንደዱሮው እይገናኙም ። ጊዜም የለም ። ወይም አመቺ ጊዜ አይፈጠርም ። ቤን እንዴት እንደሚኖር እንኳ አያውቅም ። ሁልጊዜ ተገናኝተን የምንነጋገርበትን መንገድ እፈጥራለሁ ይላል ። ግን አይሳካለትም ። ማይክል የዱሮው ማይክል አይደለም። ተለውጧል ። በህይወቱ ብዙ ነገር ሲለወጥ እሱም ተለውጧል ።

«በሕሳብህ እሩቅ አገር የሄድህ ትመስላለህ ሜስተር ሂልያርድ ። ደስ የሚል አገር ይሆን?» ትከሻውን ነቅንቆ፣« የጸደይ ወራት ሁሌም እንዲህ ያደርገኛል ። እንዲህ ባለሁበት ላይ እንድቆም ያደርገኝና ያለፈውን ኑሮዬን እንድቃኝ ይገፋፋኛል ። ያን እያደረግሁ ነው መሰለኝ ዛሬም »
« ነገሩ አይከፋም ። እኔም እንደሱ ዓይነት ነገር አለብኝ ። ግን እኔ እንዲህ እማደርገው ባመት ባመት በመስከረም ወር ላይ ነው። ምናልባት ከትምህርት ቤት መከፈት ጋር ተያይዞ ፤ በዚያው ልማድ ሆኖብኝ ቀርቶ ይሆናል። አብዛኛው ሰው የዚህ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል የሚለው በጥር ወር ላይ ነው። ግን አሁን ስትለኝ እንደገባኝ ይህ መሆን የሚገባው በጸደይ ወራት ነው ። ያኔ ነዋ ሁሉ ነገር ለምልሞ አዲስ ሆኖ የሚወጣው። ያኔ አብሮ ኑሮን እንደ አዲስ መጀመሩ መልካም ሳይሆን አይቀርም። »

ይህን ስትል እያትና ፈገግታ ተለዋወጡ ። ከዚያም ዓይኑን ፊት ለፊቱ እሚገኘው ኩሬ ላይ ተከለ። ሁለት ዳክዬዎች በጸጥታ ይንሳፈፋሉ ። በተረፈ ግን ጸጥ ብሏል ።
« አምና ይኽኔ ምንድን ትሰራ ነበር ?» አለች ዌንዲ ታውንሴንድ። እሷ አፏ እንዳመጣላት ጠየቀች ። ክፉም ፣ ደግም አላሰበች ግን ይህ ጥያቄ ማይክልን እንደስል ካራ ከላይ እስከ ታች ስንጥቅ አደረገው ።


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍12
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...“ አዬ ሚስተር ካርላይል እኛ ሥጋ ለባሾች ምስኪን ሐኪሞች ታላቁ ሐኪም ብቻ ሊፈጽመው የሚችለውን ተአምር መሥራት ብንችል ፈሊያጊያችን ምን ያህል
በበዛ ነበር ? በጥቁሩ ዳመና ውስጥም ስውር ትኩረት መኖሩን አስታውስ አትርሳ በል ደህና ሁን ወንድሜ

ሚስተር ካርላይል ተመልሶ ገባ ወደ ሳቤላ ቀረበና
እንደ ተቀመጠች ቁል
ቁል ተመለከታት » ፊቷን ደህና አድርጋ በመነጽሯ ሸፍናው ስለ ነበር በጣም
ሊታየው አልቻለም የሱም ሐሳብ እሷን ለማነጋገር
እንጂ ፊቷን ለማጥናት አልነበረም “ይኸ በጣም ከባድ መርዶ ነው " አንቺ ግን ከኔ ይበልጥ የተገነዘብሺውና
ያሰብሽበት ይመስለኛል ”

ከተቀመጠችበት ድንገት ብድግ አለችና ወደ መስኮቱ ሔደች " አንድ የምትፈልገው ሰው በመንገዱ ሲያልፍ ያየች ይመስል ወደ ውጭ ትመለከት ጀመር "
ስሜቷ በሙሉ በሠራ አካላቷ ተማሰለ " ቅንጦቿ ይነዝራሉ ጉሮሮዋ ለብቻው
ይመታል ትንፋቯ ቁርጥ ቁርጥ ይላል " ምን ትሁን ? በልጃቸው ጤንነት ከሱ
ካባቱ ጋር በምስጢር መነጋገሩን እንዴት ትቻለው የእጅ ሹራቦቹን እንደ አሳት
ከሚፈጃት እጆቹ አወለቀቻቸው " ላቧን ከግንባሯ ጠረገች ለመረጋጋት ሞክረች
ለሚስተር ካርላይል ምን ምክንያት ትስጠው ?

“ልጁን በጣም ነው የምወደው ...ጌታዬ ” አለችው በከፊል ፊቷን ወደሱ መለስ አድርጋ“ ስለዚህ የሐኪሙ ግልጽና ቁርጥ አነጋገር አንጀቴን አላወሰው !የምሆነውን አሳጣኝ ለሕመም ሰጠኝ "

አሁንም ሚስተር ካርይል ወደ ቆመችበት ተጠጋና “በውነቱ ለኔ ልጅ ይህን
ያህል መጪነቅሽ ሲበዛ ደግ ሰው ነሽ ” አላት "

እሷ ግን ምንም አልመለሰችለትም "

“ በይ እንግዲህ ይህን ነገር ለሚስዝ ካርላይል እንዳትነግሪያት " አላትና
ነገሩን በመቀጠል፡“እኔው ራሴ ብነግራት ይሻላል " በአሁኑ ሰዓት በድንገት ማዘንም መደንገጥም አይኖርባትም።”

“ምን የሚያሳዝናቸው ወይም የሚያስደነግጣቸው ነግር አለ እናቱ አይደሉ?”
አለችው " አነጋገሯ በቁጭት በንዴትና በግለት ስለነበር ባርባራን የምታጥላላ መሰለባት " ልትጨምርበት ስትል የሷንና የባርባራን ያሁኑ ማንነት ትውስ አላት "
በገጽታዋ ሳታሳይ ድንግጥ አለችና መደምደሚያውን በጣም አለዘበች " ሚስተር ካርላይል ዐይኖቹን አፈጠጠ " ድምፁ ተለዋወጠ "

“ ሳታስተውይ በችኮላ ትናገሪያለሽ ... ማዳም " አላት "

በተናገረችው መልስ ደነገጠች " ማን መሆኗን አሰበች " ኃፍረትም ውርደትም ተሰማት ። እሷ ስለ ሚስቱ እንደዚህ ብላ ሳትናገር ሚስተር ካርላይል ከዕብድ የባሰች አድርጎ ሊገምታት እንደሚችል ተሰማት ትቷት ሲሔድ የልመና ከንፈሮቿን
እያንቀጠቀጠች ወደሱ ምልስ አለች "

“በትክክል ገብቶኝ ከሆነ የሚወስደው ስለሌለ ወደ ሙቀት አገር ሊሔድ አይችልም ስትባባሉ የሰማሁ መሰለኝ " ይህ ከሆነ ለምን እኔ ይዤው አልሔድም ?አደራውን ለኔ ይስጡኝ "

“ አይሔድም ዶክተር ማርቲን የረባ ዕድሜ ስለማይጨምርለት ባይሔድ
ይሻላል ማለቱን ሰምተሻል "
“እሱማ ለጥቂት ሳምንት ብቻ ነው ብሏል " ታዲያ እነሱስ ቢሆኑ ዋጋ የላቸውም አለችው።

“ሊኖራቸው ይችላል # ግን ጥቅማቸው ከምኑ ላይ ነው ? ለሱ ኮ ከቤተሰቡ
ተነጥሎ በብቸነት የሚሠቃይባቸው ሳምንቶች ይሆኑበታል" ስለዚህ ልጄ ከኔ መለየቱ የማይቀርለት ከሆነ እስከ መጨረሻው የመለያያ ቅጽበት አብሮኝ መቆየት አለበት።

ዊልያም በሩን ከፈት አደረገና ጭንቅላቱን ብቅ አድርጎ ተመለከተ "ሔደ
አይደለም እኔ ኮ የዓሳ ዘይት እንዳይሰጠኝ ካልወጣ ኤልመጣም ብዬ ነው የቆየሁት” አለ።

ሚስተር ካርላይል ተቀመጠና ዊልያምን ከጉልበቱ ላይ ቁጭ አድርጎ ግንባሩን ከልጁ ሐርማ ጸጉር አሳርፎ ሰማህ ልጄ!ዘይቱ በጎ እንዲያደርግህና እንዲያበረታህ መሆኑን ታውቃለህ?። አለው

"እኔ ግን የሚያጠነክረኝ አይመስለኝም " ዶክተር “ማርቲን እኔን ይሞታል
አለኝ ?

"ስለ መሞት ደግሞ ማን ነገረህ ?”

“ አንዳንዶቹ ያወሩታል "

“ ዝም ብለህ እንድትሞት አናደርግም " አንተን ለማዳን ምን ማድረግ እንዳለብን ለማወቅ እንሞክራለን ይኸን ታውቃለህ ዊልያም ?

“ አዎን ዐውቃለሁ ”

ሚስተር ካርላይል ተነሣና ልጁን ለማዳም ቬን ስጥቶ'“ በይ ደህና አድርገሽ
ተጠንቅቀሽ ያዥው ብሏት ወደ ኮሪደሩ ዐለፈ

“ አባባ ! ... አባባ!እፈልግሃለሁ ” አለና ማዳም ቬንን ትቶ ወደሱ እየሮጠ
በእግርህ ነው ወደ ቤት የምትመለሰው ? አብሬህ በእግሬ ልምጣ ?”

በዚያ ሰዓት በዚያ ስሜት የልጁን ጥያቄ ለመቀበል እምቢ የሚልበት አንጀት አልነበረውም “ እሺ እስክመለስ ድረስ እዚህ ጠብቀኝ ” ብሎት ወጣና
ደርሶ ተመለሰ " እሱ የዊልያምን እጅ ይዞ ማዳም ቬን ከዊልያም ቀጥላ ፈንጠር ብላ ጉዞ ቀጠሉ "

በዚህ ዐይነት እየሔዱ ሳለ ትንሹ ሰውዬ ከፖስታ ቤት እየሮጠ ወጣና ከነሱ
ጋር ፊት ለፊት ግጥም አሉ ሰውየው የተደናገጠ ይመስል ነበር መንገደኞችንም
ድንገት ድቅን በማለት ካደናገራቸው በኋላ ወደ ጐርፍ መሔጃው ዘወር አለ " ሰውየው ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነበር !

ዊልያም በልጅነት ቅንነቱ ዞር ብሎ አይቶት እኔ እንደዚህ ሰውዬ አስቀ
ያሚና መጥፎ ሰው አልሆንም " አንተሳ . . . አባባ ?

ሚስተ ካርላይል አልመለሰለትም " ማዳም ቬንም ሳታስበው ድንገት አይታዋለች » ከዚያም መንግዳቸውን ቀጠሎና ሚስተር ጀስቲስ ሔር በር ሲደርሱ ባለቤቱንም ከዚያው ቁሞ አገኙት ዊልያም' ሚስዝ ሔርን ከአትክልቱ ቦታ ወንበር
ላይ ተቀምጣ አያትና ሊስማት ሔደ ሚስዝ ሔርን ልጆቹ ሁሉ ይወዷት ነበር "
“ እኔ የምለው ሚስተር ካርላይል ዛሬ ወደ ፍርድ ቤት አልሔድኩም ነበር "
አንድ ማመልከቻ በምስጢር እንደ ቀረበላቸው ፒነር ነገረኝ ዝም ብለው የማይታመን የማይሆን ነገርኮ ነው " አንተስ ምን የምታውቀው ነገር አለ ?

" እኔ ያወቅሁት ነገር የለም ”

ነገሩ ዲክ ሆሊጆንን ያለመግደሉን ለማሳወቅ የታሰበ ይመስላል” አለ በዛፎቹ ሥር በስውር የሚያዳምጡ እንዳይኖሩ የሠጋ ይመስል ድምፁን ዝቅ አድርጎ "
የገደለው ሌቪሰን እንጂ ... ትሰማኛለህ ? ሌቪሰን እንጂ እሱ አይደለም " የሚል
ነገር አቅርበዋል አሉ " ግን በጭራሽ የማይሆን የማይመስል ወሬ ነው”

“ ስለ ሪቻርድ ከደሙ ንጹሕነት ” አለ ሚስተር ካርላይል !“ እኔም ካመንኩበት ብዙ ዘመኔ ነው

“ስለ ሌቪስን ወንጀለኝነትሳ ? አለ ጀስቲስ ሔር ዐይኖቹን በመገረም አፍጦ።

“ ስለሱ የምሰጠው አስተያየት አይኖረኝም ” አለው ሚስተር ካርላይል ቀዝቀዝ ብሎ።

“ ሊሆን አይችልም ። ዲክ ነጻ ሊሆን አይችልም ዲክ ነጻ ሆነ ማለት ዓለም
ተገለበጠች ማለት ነው !! ”

“ አንዳንዴም አይሆንም ያሉት ይሆናል " ሪቻርድ ንጹሕ የመሆኑ ነገር በፀሐይ ባደባባይ ሊረጋገጥ ነው” አለ ሚስተር ካርላይል

“ በዚያኛው ከተመሰከረበት ደግሞ የመያዣውን ከፖሊስ ወስደህ አንተው ራስህ ትይዘዋለህ ”

“ እኔስ በእንጨትም አልነካው ሰውየው ከተቀጣ ይቀጣል እኔ ግን የቅጣቱን መንገድ ጠራጊ በመሆን አልረዳም ”

“ እና ዲክ ነጻ ሊሆን ይችላል ?” ታዲያ ለምን ጠፋ ? ለምን ቀርቦ እንደዚህ ብሎ አላመለከተም ?”

"እርስዎ አንቀው ለፍርድ እንዲያቀርቡት ነው? ለማቅረብ መማለልዎን ያውቃሉ ? አለው ሚስተር ካርላይል "

ጀስቲስ ሔር በጣም እየበረዶ ሔዶ ።

“ እንዴ ግን ካርላይል
ያቺ ከንቱ በሕይወት ቆይታ ብታይ ኖሮ አንጀትህ
እንዴት በሻረ ! ያ የተሳሳተ አድራጎቷ ምን ያህል ይቆጫት ምን ያህል ያሳርራት ነበር !”
👍14
“ ብዙ ሰዎች የየጃቸውን ያገኛሉ " አለና ሚስተር ካርላይል ለሚስዝ ሔር
ባርኔጣውን በሩቅ አንሥቶላት ቶሎ የተመለሰውን ዊልያምን በጁ ይዞ መንገዱን ቀጠለ።

ሳቤላ አካላቷ ሙሉ እየራደ አንጀቷ እያረረ • ከዊልያም ጐን ሆና አብራው ተጓዘች ጀስቲስ ሔር አእምሮው በሐሳብ ተውጦ በሰማው ነገር ተደናግጦ ስለ
ሁኔታው እያሰበ ከዐይኑ እስኪጠፉ ይመለከታቸው ጀመር " 'ሪቻርድ ነጻ ሲሆን
ሪቻርድ ከሚያሳፍረው ውድቀት ሊጥለው ሲያባርረው ከኖረው ወንጀል ነጻ ሊሆን? ያኛው ደግሞ ወንጀለኛ ሊሆን ? ይህ ከሆነ ዓለም ተገለበጠች ማለት ነው "

ሐሙስ ጧት የዌስት ሊን መሪዎች የደስታ ድምፅ ያስተጋቡ ጀመር » መንገዶች በሰዎች ግጥም አሉ " መስኮቶች ከውስጥ ወደ ውጭ በሚመለከቱ ራሶች ተጠሉ" ቀኑ የተወዳዳሪዎች ስም ተጠርቶ ለሕዝብ የሚገለጽበት ነበር የገጠሩ
ሕዝብም ግልብጥ ብሎ ገባ ሀብታም ድሃ ታዋቂ የማይታወቅ መምረጥ የሚችል የማይችል ሳይል ሁሉም ድብልቅልቅ ብሎ የዕለቱን ውጤት ለማወቅ በጕጕት የሚጠባበቅበት ዕለት ነው " ነገሩን ከመቸም ጊዜ ለየት ያደረገው ስመ ጥፉ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ሚስተር ካርላይልን ለመወዳደር በመቅረቡና ሁኔታውና ታሪኩም እስከ አገር ቤት ድረስ በመስማቱ ነበር " ሕዝቡ የዚያን ምርጫ ሁኔታና ሒደት
ለማወቅ ሲል ዳር እስከ ዳር እየተናደ ገብቶ ዌስት ሊንን አጥለቅልቆታል ባርባራ ሁለቱን ልጆችና ያቺን የልጆች አስተማሪ አስከትላ በሠረገላዋ ሁና መጣች "
አስተማሪቱ እንኳን ከቤት ለመቀረት ፈልጋ ነበር " ባርባራ ግን ነገሯን አልተቀበለቻትም » እንዲያውም ነገሩን እንደ ናቀችው አድርጋ ቆጠረችባት " ስለ ሚስተር
ካርሳይል መመረጥ አለመመረጥ ግድ ከሌላትም ባርባራ ልጆቹን ለመጠበቅ ፋታ ስለማታግኝ ባይሆን ሎሲን እንድትጠብቅላት አብራት መሔድ እንዳለባት ስትነግራት በግድ ማዳም ቬን ሳትወድ ከሠረገላው ገባችና ከሚስዝ ካርላይል
ፊት ለፊት ተቀመጠች "

ከሚስ ኮርኒሊያ ካርላይል ቤት ወረዱ » የቤቱ አቀማመጥ የምርጫውን ሁኔታ ለማየት አመቺ በመሆኑ ብዙዎች የቅርብ ወዳጆቻቸው እዚያ ተሰብስበው ነበር
ሚስ ካርላይልም በረቂቅ ጉንጉን ከተሠራ ጨርቅ የተሰፋ ጌጠኝነቱና ማማሩ ልዩ የሆነ ቀሚስ ለብሳ ከቀይና ከወይን ጠጅ ቀለሞች የተሠራ የአበባ ቅጠል ደረቷ ላይ አድርጋለች " ሚስ ካርላይል በደንብ ለብሳ መታየቱ አስፈጊ ሆኖ የታያት በዚህ ቀን ብቻ ነበር በሕይወቷ !

ሚስተር ካርላይልም ወደ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ሲያልፍ ሁሉንም በኮርኒሊያ
ታላቁ ሳሎን መስኮት አያቸውና ወርዶ ሰላም ብሏቸው መልካም ምኞታቸውን ተቀብሎ ሔዶ

የዕለቱ ሥራ ተጀመረ ሰር ጆን ዶቢዴ ሚስተር ካርላይልን ለእጮነት አቀረበው » ሚስተር ሐርበርት ደገፈው " ስር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን አንድ መኮንን ጠቆመው" ሌላ መኮንን ጥቆማውን ደገፈው እጅ በማንሣት ቢታይ ለሚስተር ካርላይል
አድልቶ ስለታየ የሌቪሰን ሰዎች ድምፅ እንዲሰጥ ጠየቁ ስለዚህ የማዘጋጃ ቤቱ አዳራሽ ለድምፅ አሰጣጥ የማይበቃ ስለሆነ ሌላ ተስማሚ ቦታ ተመረጠ " ሕዝቡ ወደዚያው ግልብጥ ብሎ ነጎደ። መንገዱ በሚስ ካርላይል ቤት በኩል ስለ ነበር ሚስተር ካርላይል በደጋፊዎቹ ታጅቦ ሲያልፍ ሚስ ካርላይል ቤት የተሰበሰቡ ሴቶች መሐረቦቻቸውን አውለበለቡላቸው "

“ ካርሳይልና ክብር ለዘለዓለም ይኑሩ ” ብሎ ወጣቱ ሎርድ ቬን ሲጮህ
ህዝቡ እየተቀበለ አስተጋባ

“ ወይ ጉድ ' ይሀ ሁሉ ክዋክብት የመሰለ ሴት ለሚስተር ካርላይል እንዴት
እንደሚሆንለት አየህ ? አለው ሚስተር ድሬክ ለሌቪሰን በጆሮው “ “ አንተን ከዚህ ውድድር እንድትገባ ያደፋፈሩህ ሰዎች ከብቶች ናችሁ " እኔ በፊትም ተናግሬ ነበር የማሸነፍ ዕድልህ ኃይለኛ ነፋስ ጥላ ለማለፍ ከምትሞክር የለባ ቁራጭ
አይሻልም " ቀደም ብለህ መተው ነበረብህ።

“ እንዴት.. ፈሪ ይመስል ! አለ ስር ፍራንሲዝ ቆጣ ብሎ “ እስከ መጨረሻው እገፋበታለሁ ”

“ ሚስቱ እንዴት ታምራለች ! ቀጠለ ድሬክ ዐይኖቹን በአድናቆት ባርባራ
ላይ ጣል አድርጎ “ እኔ የምልህ የፊተኛይቱም እንደዚች ታምር ነበር?” አለው።

ሰር ፍራንሲዝ ፊቱን ከሰከሰ የሷን ነገር እንዲነሣበት አልወደደም ። ነገር ግን ለዚሁ ምላሽም ሆነ ተጨማሪ ቃል ሳይናገር አንድ የፖሊስ ልብስ የለበሰ ሰውዬ በሕዝቡ መኻል እየተጋፋና እየጣሰ ደረሰና እጁን አሳረፈበት "

“ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን እስረኛዬ ነዎት ”

በዚህ ጊዜ ከዕዳ የከፋ ነገር ይመጣል ብሎ አላስበውም " ያም ቢሆን አላነሰውም የፊቱ ቀለም በንዴት ተለዋወጠ ።

“ እጅሀን ወዲያ በል .. ተባይ ! እንዴት ደፈርከኝ”

ወዲያው ካቴና አገባበትና ' በዚህ ሁኔታ ስይዝዎ በጣም እያዘንኩ ነው " የመያዣው ትእዛዝ የተሰጠኝ ትናንት በዐሥራ አንድ ስዓት ነው " ላገኝዎ
አልቻልኩም ። ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን .. አቅደውና ነፍስ ለማጥፋት ብለው ጆርጅ
ሆሊጆንን በመግደል ወንጀል ተይዘዋል ” አለው "
የከበቡት አፈገፈጉ እዚያው ሆነው የሰሙት ደነገጡ " ወሬው እየተራባ ዳር እስከ ዳር ደረሰ ፍራንሲዝ ሌቪስን ፊቱ ተለዋወጠ " አቅሉን እስኪስት ድረስ ደነግጠ በዚህ እንዳለ ኦትዌይ ቤቴልን ካጠገቡ አየው "

“ አንተ ውሻ ! አንተ ነህ
ይህን ሁሉ የምታደርግ !"

“ ኧረ እኔ አይደለሁም ! ብሎ ሊቀጥል ሲል አንድ ፖሊስ መጣና አንድ ሌላ ጥንድ ካቴና በእጆቹ አስገባበት

“ ሚስተር ኦትዌይ ቤቴል ፤ በጆርጅ ሆሊጆን ግድያ ተባባሪ በመሆንዎ በሕግ
ፊት ተይዘዋል "

እዚያ የነበረው ሕዝብ ሁሉ አብሮ የተያዘ ይመስል ዐይኑን አፍጦ ጆሮውን
ሰጥቶ ድርቅ ብሎ ቆመ "

ኮሎኔል ቤቴል ዘመዱ እንደዚያ ሆኖ ሲታሰር አይቶ ወደ ባለ ብጫዎቹ ዘንድ
ሔደና '' ምን ማለት ነው እንዶዚህ ያለ አሠራር ? ” አለ የሥልጣን ተጽዕኖ
ባለው አነጋገር "

“ የእኛ ጥፋትኮ አይደለም . . . . ኮሎኔል " እኛ እንድንይዝ የተሰጠንን ትእዛዝ ነው የፈጸምን ” አለ አንደኛዉ “ ፍርድ ቤቱ እነዚህ ሁለት ሰዎች በሆሊጆን ግድያ ስለ ተጠረጠሩ እንዲያዙ ትናንት ትእዛዝ ሰጥቷል "

“ ከሪቻርድ ሔር ጋር በመተባበር ነው ? አለ ነገሩ በጣም ያስደነገጠው መኮንን ወዶ ፖሊሶቹና ወደ እስረኞቹ እየተመለከተ "

“ሪቻርድ በነገሩ የለበትም ይባላል " አለ አንደኛዉ ፖሊስ እኔ ግን ያረጋገጥኩት ነገር የለም ”

' ኧረ እኔም ምንም የለሁበትም " እለ ኦትዌይ ቤቴል "

“ይህ ከፍርድ ቤት ሲቀርቡ በመረጃ የምያረጋግጡት ይሆኖል” እለው ፖሊሱ
በትሕትና " ሚስ ካርላይልና ወይዘሮ ዶቢዴ በመስኮቱ በኩል በጕጕት ሲመለከ ከነሱ በታች የነበሩትን ሰዎች ነገሩ ምን እንደሆነ ጠየቁ " “ የምርጫው
ተወዳዳሪና ትንሹ ቤቴል በነፍስ ገዳይነት ተያዙ እነሱ ገድለው ጥፋታቸውን በዲክ
ሔር አላከኰበት እሱ ግን በነግሩ አልነበረበትም እየተባለ ይወራል " አላቸው
ነገሩን ቁማ ታዳምጥ የነበረችው ሚስዝ ሔር በድንጋጤ ጮኸች » እዚያው እንዳለች ድክምክም አለች ባርባራ ሮጣ ደገፈቻት » ነገሩን በጣም ተጠራጠረችው
ሚስተር ካርላይል ከውጭ በአካባቢው ስለ ነበሮ ተጠርቶ መጣ ባልና
ሚስቱ ደግፈው አንድ ክፍል ውስጥ አስገብተው አጽናኑዋት "

አርኪባልድ እውነቱን ንገረኝ " አንተን አምንሃለሁ " እውነት ልጄ ነጻ የሚወጣበት ቀን መጣ ? ያ ክፉ አታላይ ስውዬ በገመዱ ሊገባ ነው ?”

“ስለ ሰውዬው ወንጀል እኔ አላውቅም " ልጅዎ ግን ነጻ እንዲሚወጣ አይጠራጠሩ አይዞዎ ፤አይጨነቁ " የደስታ ዘመን እየመጣልዎ ነው” ብሎ አበራታቷትና አስምኗት ወጣ...

💫ይቀጥላል💫
👍193🔥1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


በተቃራኒው ጦርነት
ወደ ተዘፈቀች አገር መመለሱ ራሱ አንድ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው፡.... እዚህ ነገር ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ለምን ገባሁ? አለች ልቧ
እየተሰበረ ሁን ለመጸጸት ጊዜ የለም፡ አንዴ ስለወሰንኩ ወደ ኋላ
የምልበት ነገር የለም፡፡ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥም አለች መልሳ
በሆዷ ሀሳቧ አንድ ቦታ አልረጋ ብሏት፡

ማርክ እጇን ለቀም አድርጎ ሲይዝ እንዳይለቃት ፈራች፡፡ ‹አንድ ጊዜ ሃሳብሽን ለውጠሻል። አሁንም ደግመሽ መለወጥ ትችያለሽ›› አለ ለማሳመን፡፡
ከኔ ጋር አሜሪካ እንሂድና ላግባሽ፡፡ ልጆቻችንን ይዘን ባህር ዳር እንጫወታለን የምንወልዳቸው ልጆች ቴኒስ እየተጫወቱ፣ እየዋኙ ብስክሌት እየነዱ ያድጋሉ፡ ስንት ልጅ ነው መውለድ የምትፈልጊው?››

አሁን መወላወሉን አቁማለች፡፡ ‹‹ማርክ እያደረኩት ያለሁት ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ ተመልሼ ወዳገሬ እሄዳለሁ›› አለች፡፡
ያለችውን የተቀበለ መሆኑን ተረዳች፡፡ ሁለቱም ሀዘን ገብቷቸውና የሚሰሩትን አጥተው ዓይን ላይን ይተያያሉ፡፡ የሚናገሩት ጠፍቷቸው ዝም
ዝም ብለዋል፡

ከዚያም መርቪን ቡና ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፡፡

ዳያና ባሏ ፊቷ መጥቶ ድቅን ሲልባት ዓይኗን ማመን አቃታት፡ ልክ
አንድ የሆነ መንፈስ ፊት የቆመ ይመስል አፈጠጠችበት፡ እንዴት እዚህ ሊመጣ ቻለ? ሊሆን አይችልም

‹‹እዚህ ተገኘሽ አይደል!›› አለ መርቪን በተለመደው አስገምጋሚ ድምጹ
ዳያና ግራ ተጋባች፡፡ መርቪን እዚህ መገኘቱ አስደንቋታል፣ አስፈርቷታል፣ እፎይታ ሆኗታል፣ ቅሌት ውስጥም ከቷታል፡፡ ከሌላ ወንድ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ ባሏ ሲደርስባት በደመነፍስ እጇን ከማርክ እጅ መንጭቃ አላቀቀች

ማርክም ‹‹ምንድነው እሱ?›› ሲል ጠየቃት ነገሩ ስላልገባው፡

መርቪን ሁለት እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ ፊታቸው ተገትሯል፡

‹‹ማነው ይሄ ፊታችን የተገተረው?›› ሲል ጠየቀ ማርክ፡፡

‹‹ባሌ መርቪን ነው›› አለች በደከመ ድምጽ፡

‹‹ወይ አምላኬ!›› አለ ማርክ፡

‹‹እንዴት እዚህ ልትመጣ ቻልክ መርቪን?›› ስትል ጠየቀች ዳያና የምንተ እፍረቷን፡፡

‹‹ብራሴ አይሮፕላን በርሬ መጣሁ›› አለ ቁርጥ ባለ የአነጋገር ባህሪው:
ቆዳ ጃኬት የለበሰ ሲሆን በእጁ የሞተር ሳይክል ነጂ ቆብ አንጠልጥሏል፡፡
‹‹ኧረ ለመሆኑ እዚህ መሆናችንን እንዴት አወቅህ?›› ስትል ጥያቄዋን
ደገመች፡፡

‹በጻፍሽልኝ ደብዳቤ አሜሪካ እንደምትሄጂ ገልጸሻል፡ ወደ አሜሪካ
የሚኬደው ደግሞ በሰማይ በራሪ ጀልባ ብቻ መሆኑ ይታወቃል›› አለ በድል
አድራጊነት፡፡

የሷን ዱካ ተከታትሎ የምትሄድበትን መንገድ ገምቶ እሷ ጋ በመድረሱ ደስ እንዳለው ከገጽታው ይነበባል፡ በራሱ አይሮፕላን በርሮ ሊደርስባቸው
እንደሚችል ፈጽሞ አልጠረጠረችም፡፡ በዚህ መንገድ ተከታትሎ ስለደረሰባት ደካማ ነኝ ስትል አሰበች፡፡

ከእነሱ ትይዩ ባለው
ወንበር ላይ ተቀመጠና
‹‹እስቲ ዊስኪ አምጪልኝ›› ሲል አዘዘ አስተናጋጇን፡፡

ማርክ ብርጭቆውን አንስቶ ባንዴ ሲጨልጥ ዳያና ታየዋለች::በመጀመሪያ መርቪንን ሲያየው ተርበትብቶ ነበር፡፡ በኋላ ግን መርቪን አምባጓሮ እንደማያነሳ ሲገነዘብ ተረጋጋ ሆኖም ወምበሩን ገፋ አደረገና ከዳያና ፈንጠር ብሎ ተቀመጠ፡፡ የሰው ሚስት እጅ እንደያዝ ባሏ ከተፍ ሲልበት ሳያፍር አልቀረም፡

ዳያና ድፍረት እንዲሰጣት ብላ ከአልኮሉ ተጎነጨች፡ መርቪን በጭንቀት ያያታል። ግራ መጋባቱንና መጎዳቱን ከፊቱ ስታይ ደረቱ ውስጥ
ተወሸቂ! ተወሸቂ! አላት፡፡ ከፊቱ ምን እንደሚጠብቀው ሳያውቅ እሷን ፍለጋ
አገር አቋርጦ መጥቷል፡፡ እጇን ሰዳ በማጽናናት ሁኔታ ክንዱን ያዝ አደረገችው፡፡

ሚስቱ በውሽማዋ ፊት ያዝ ስታደርገው መርቪን ማርክን በእፍረት አየት አደረገው፡፡ ዊስኪው ሲመጣለት አንስቶ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠው::
ማርክ በበኩሉ ዳያናን የሚያጣ መስሎት ወምበሩን ወደ እሷ አስጠጋ
ዳያና በሁኔታው ግራ ተጋባች፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ከዚህ በፊት
ገጥሟት አያውቅም:: ሁለቱም ሰዎች ይወዱዋታል ከሁለቱም ጋር ተኝታለች፡ ሁለቱም ይህን ያውቃሉ፡፡ በጣም አሳፋሪ፡፡ ሁለቱንም ማጽናናት ፈለገች፧ ሆኖም ፈራች፡፡ አሁን ወደ መከላከሉ አዘምብላለች። ከሁለቱም ራቅ ብላ ተቀመጠችና ‹‹መርቪን አንተን ልጎዳ ብዬ አይደለም እዚህ መዘዝ ውስጥ የገባሁት›› አለች

መርቪን ፊቱን ቅጭም አድርጎ ‹‹አምንሻለሁ›› አለ
‹‹ታምነኛለህ? የሆነውን ሁሉ ትቀበለዋለህ?›› አለች ዳያና፡፡

መርቪን ማርክ ላይ አፍጥጦ ነገር ለመፈለግ በሚመስል ሁኔታ
ተጠጋውና ውሽማሽ አሜሪካዊ ይመስላል፤ከአፍ የወደቀ ጥሬ!
የተመኘሺውን አግኘተሻል›› አለ፡፡

ማርክ አፈገፈገ፤ ምንም ቃል ሳይተነፍስ መርቪንን አፍጥጦ ያየዋል ማርክ ጠብ ፈላጊ አይነት ሰው አይደለም፡፡ ሁኔታው ግራ አጋብቶታል፡ ከዚህ በፊት ተገናኝተው ባያውቁም መርቪን ዋና ባላንጣው ነው፡፡ ማታ ማታ ዳያና አቅፋው የምትተኛው ሰው ማን ይሆን?› ሲል ራሱን ሲጠይቅ ከርሟል፡፡ አሁን ማን እንደሆነ አውቆታል። ከማርክ ጋር ሲተያይ መርቪን ስለማርክ ምንም የተጨነቀ አይመስልም፡፡
ዳያና ሁለቱን ባላንጣዎች ተመለከተቻቸው፡ ምንም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም መርቪን ዘንካታ፣ ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚል፣ ኮስታራና ነርቨስ ነው ማርክ
ደግሞ አጭር፣ ሽክ ያለ፣ ነቃ ያለና ስው ሲናገር ጆሮ የሚሰጥ ሰው ነው ማርክ
አንድ ቀን ይህን ታሪክ በኮመዲ ስራው ውስጥ አካቶ ሳያቀርበው አይቀርም ስትል ዳያና አሰበች፡

አይኖቿ እምባ አንቆርዝዘዋል፡ መሃረብ አውጥታ ንፍጧን ተናፈጠች
«ልክስክስ መሆኔን አውቄዋለሁ›› አለች፡

‹‹ልክስክስ!›› ሲል አሾፈ መርቪን ቃሉ አንሶበት፡፡ ‹‹በጣም የጅል ስራ
ዳያና ባሏ በተናገረው ተሸማቀቀች፡ ብዙ ጊዜ ስድቡ አፏን እንዳዘጋት
ነው፡፡ ዛሬ ግን ከስድብም በላይ ይገባታል፡፡

አስተናጋጇና ጥግ ተቀምጠው መጠጣቸውን የሚኮመኩሙት ሁለት
ሰዎች ሁሉን ነገር ጣጥለው ትእይንቱን በጉጉት ይመለከታሉ፤ ‹‹ምን ይከተል ይሆን?› እያሉ።

መርቪን አስተናጋጇን ጠራና ‹የኔ ቆንጆ ሳንድዊች ብታመጪልኝ›› ሲል አዘዛት እሷም ‹‹እሺ የኔ ጌታ›› አለችው በፍጹም ትህትና፡፡
አስተናጋጆች መርቪንን ይወዱታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሮ እያስጠላኝ መጥቷል ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው አሜሪካ ለመሄድ የወሰንኩት›› አለች ዳያና፡፡

"ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው ያልሽው! አሜሪካ ጓደኛ የለሽ፣ ዘመድ የለሽ፣ ቤት የለሽ. . .አዕምሮሽ ማሰብ አቆመ እንዴ!›› አለ መርቪን፡፡

ዳያና መርቪን ስለደረሰላት አምላኳን ብታመሰግንም እንዳይጨክንባት
ፈርታለች ማርክ በእጁ ትከሻዋን ነካ አደረገና ‹‹ለምንድነው አሜሪካ ደስታ
የማታገኚው፧ እዚያ ለመሄድ ማሰብሽ ስህተት አይደለም›› አላት ድምጹን
ዝቅ አድርጎ፡፡

መርቪንን ከዚህ በላይ ማናደዱ አስፈርቷታል፡፡ ምናልባትም ትቷት
ተመልሶ ይሄድ ይሆናል፡ በማርክና በሉሉ ቤል ፊት ‹‹አልፈልግሽም›› ብሎ
ቢላት እንዴት እንደሚያበሳጫት መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ አያደርግም
አይባልም፡፡ መርቪን ተከትሏት ባይመጣ ጥሩ ነበር፡፡ ይህ ማለት ደግሞ
እዚሁ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ ይኖርበታል፡፡ ከዚያም ብርጭቆዋን አነሳችና ከንፈሯን አስነክታ ‹‹ይህን መጠጥ አልፈልግም›› ብላ መልሳ አስቀመጠችው

በዚህ ጊዜ ማርክ ‹‹ሻይ ላምጣልሽ?›› አላት፡፡
👍204🥰1
የፈለገችው ሻይ ስለነበር ‹‹አዎ አምጣልኝ›› አለችው፡
ማርክ ባሬስታውጋ ቀልጠፍ ብሎ በመሄድ ሻይ አዘዘላት፡ መርቪን እንዲህ ያለ ነገር አይነካካውም፡ ማርክን በጥላቻ ዓይን አየው፡፡
‹የኔ ችግር ይሄ ነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡ አንድ ነገር ስትፈልጊ ተነስቼ
ስለማላመጣልሽ፡፡ አባወራም የቤት አሽከርሽም እንድሆን ትፈልጊያለሽ?››

መርቪን የመጣለትን ሳንድዊች አልነካውም፡፡

‹አሁን መጨቃጨቅ አያስፈልግም ትይኛለሽ? አሁን ያልተጨቃጨቅን
መቼ ልንጨቃጨቅ ነው? ደህና ሁን ሳትይኝ ይህን ጅላጅል ደብዳቤ ትተሽልኝ ከዚህ የማይረባ ሰው ጋር ኮበለልሽ›› አለና አንድ ቁራጭ ወረቀት
አውጥቶ ዳያና ፊት አስቀመጠው፡፡ ዳያና ጽሑፉ የሷ መሆኑን አወቀች፡
ይህን ስታይ ፊቷ በሃፍረት ቲማቲም መሰለ፡፡ ደብዳቤውን ይዛ አነባች
‹እንዴት ቡና ቤት ውስጥ ሰው ፊት እንዲህ ያሳጣኛል?› አለችና ፈንጠር
ብላ ተቀመጠች፡ አሁን በንዴት ነርቭ ሆናለች፡፡

ሻዩ ሲመጣ ማርክ ጀበናውን አነሳና ‹‹በማይረባ ሰው የተቀዳ ሻይ ልስጥህ?›› ሲል ጠየቀው መርቪንን፡፡
ቡና ቤት ውስጥ ያሉት አይሪሻውያን በሳቅ ፈነዱ መርቪን ግን በንዴት ተወጥሮ ምንም አልተነፈሰም፡፡

ዳያና እየተናደደች ‹‹እኔ ጅል ልሆን እችላለሁ፡ ራሴን ለማስደሰት ግን መብት አለኝ›› አለች፡

መርቪን ጣቱን ወደ ዳያና ቀስሮ ‹‹እኔን ስታገቢ ቃል ገብተሽ ነበር: ስለዚህ ፈርጥጠሸ መሄድ የለብሽም›› አለ፡፡

በንዴት ተብከነከነች በአቋሙ ሙጭጭ እንዳለ ነው፡፡ ለድንጋይ እንደመናገር ይቆጠራል፡፡ ለምን አያመዛዝንም? ሁልጊዜ እሱ ትክክል
ሌላውን ስህተተኛ አድርጎ ለምን ይቆጥራል?› ወዲያው ይህን ባህሪውን ችላ እንደኖረች በህሊናዋ መጥቶ ድቅን አለባት፡ ለአምስት አመት ያህል ቢያንስ በየሳምንቱ እንዲህ ሲያበሳጫት እንደነበር ታሰባት፡፡ እሱ ከመምጣቱ በፊት ከአዲሱ ፍቅረኛዋ ጋር ዓለሟን ስትቀጭ ስለነበር ባሏ ምን ያህል አስቸጋሪ ሰው እንደነበር ረስታዋለች፡፡

ማርክም ጣልቃ ገባና ‹‹ማድረግ የምትፈልገውን ነገር እንዳታደርግ
ልትከለክላት አትችልም፡፡ ካንተ ጋር ወደ ቤቴ ተመልሼ ልሂድ ካለች እኔ አልከለክላትም፡፡ አሜሪካን አገር ሄዳ እኔን ማግባት ከፈለገች ማንም
ሊከለክላት አይችልም›› አለ፡፡

መርቪን ጠረጴዛውን በጡጫ ጠለዘና ‹‹አንተን ልታገባ አትችልም፤ የኔ
ሚስት ናት!›› አለ፡፡

‹‹ልትፈታህ ትችላለች››
‹‹በምን ምክንያት?››
‹‹በአሜሪካን አገር
የትዳር ጓደኛን ለመፍታት ምክንያት አያስፈልግህም›› አለ ማርክ፡፡

መርቪን ወደ ሚስቱ ዞር አለና ወደ አሜሪካ እግርሽ ንቅንቅ አይልም፡፡ ከኔ ጋር ወደ ማንቼስተር ትመለሻለሽ›› አለ ማርክን አየት ስታደርገው በስስት ፈገግ አለላትና ‹የሚልሽን የመቀበል ግዴታ የለብሽም›› አላት ‹‹ልብሽ የሻተውን አድርጊ››

‹ኮትሽን ልበሽና እንሂድ›› ሲል አዘዘ መርቪን፡፡

የመርቪን ቁጡ ባህሪ እንደገና ነገሮችን እንድትመረምር አደረጋት፡
ዋናው ጉዳይ ማለትም ከማን ጋ ልኑር› የሚለው ጥያቄ በሁለቱ ወንዶች
መካከል ሊነሳ ከነበረው አምባጓሮና በአሜሪካ የመኖር ስጋት ጋር ሲነጻጸር
ሚዛን የሚደፋ ነበር፡ ማርክ ይወዳታል እሷም ትወደዋለች፡፡ ሌላው ነገር
ሁሉ ሁለተኛ ደረጃ ነው፡፡ ውሳኔዋ በአዕምሮዋ ሲመሰረት ትልቅ እፎይታ
ተሰማት፡ ትንፋሿን በረጅሙ ለቀቀችና ‹‹ይቅርታ መርቪን›› አለች ‹‹ጥዬህ
ከማርክ ጋር እሄዳለሁ፡››
....................................

ናንሲ ሌኔሃን ከመርቪን ላቭሴይ ሚጢጢ አይሮፕላን ላይ ሆና ቁልቁል
የፓን አሜሪካን የሰማይ በራሪ ጀልባ ለበረራ ዝግጁ ሆኖ በባህር ዳርቻ ላይ
"በኩራት ቆሞ ስታየው ቅጽበታዊ ደስታ ተሰማት፡ ከተወሰኑ ሰዓታት በፊት
ዕድል ጠሞባት የምታደርገውን አጥታ ነበር፡ ነገር ግን የወንድሟን ዕቅድ
በከፊልም ቢሆን ለማጨናገፍ ትንሽ ቀርቷታል፡ ናንሲ ሌኔሃን እንዲህ በቀላል እጇን የምትሰጥ ሴት አይደለችም› ስትል ለራሷ አድናቆት ቸረች፡

ትንሿ አይሮፕላን የመቆሚያ ቦታ ፍለጋ ስትሽከረከር ናንሲ ከወንድሟ
ሊገጥማት የሚችለውን እሰጥ አገባ ስታስበው ሰውነቷ በንዴት ተወጣጠረ፡
ወንድሟ እሷን ለማታለል ይህን ያህል ለምን ፈ እንደጨከነ ማመን አሁንም
አቅቷታል፡ እንዴት ይሄ ሀሳብ በአእምሮው ሊመጣ ቻለ?
በህጻንነታቸው አብረው ገላቸውን ይታጠቡ ነበር፡፡ መሬት ወድቆ እግሩ
ሲቆስል ፋሻ ወይም የቁስል ፕላስተር ታስርለት ነበር፡ ማስቲካ ቆርጣ ታካፍለው ነበር፡ ጥፋቱን ለሰው ነግራበት አታውቅም፡፡ የእሷን ሚስጥር ሳትደብቅ ትነግረው ነበር፡ ካደጉም በኋላ ምንም እንኳን ሴት ብትሆንም በሁሉም ነገር ትበልጠው ዕድሜውን በሙሉ እሱን ትንከባከበው ነበር፡

አባታቸው ሲሞቱ ፒተር የኩባንያው ኃላፊ እንዲሆን ፈቀደችለት፡ ይሄ ደግሞ በኋላ በእጅጉ ዋጋ አስከፍሏታል፡ የአባታቸው ምክትል ከነበረው ናት
ሪጅዌይ ጋር አፍላ ፍቅር ላይ በነበረችበት ወቅት የኩባንያውን ኃላፊነት
ፒተር እንዲይዝ ስትስማማ ናት ሪጅዌይ በድርጊቷ አኩርፎ ኩባንያውን ለቆ
ወጣ፡፡ እሷንም አይንሽ ላፈር አላት፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ ፍቅሯን
ሳያስጨርሳት ሌላ ሴት ያገባው፡፡

ጓደኛዋና የኩባንያው ጠበቃ ማክ ማክብራይድ ፒተር የኩባንያው ኃላፊ እንዳይሆን ቢመክራትም ወንድሟ ፒተርን ሰዎች በአባቱ እግር ሊተካ
ማርክን አየት ስታደርገው በስስት ፈገግ አለላትና ‹የሚልሽን የመቀበል
ግዴታ የለብሽም›› አላት ‹‹ልብሽ የሻተውን አድርጊ››
‹ኮትሽን ልበሽና እንሂድ›› ሲል አዘዘ መርቪን፡፡
የመርቪን ቁጡ ባህሪ እንደገና ነገሮችን እንድትመረምር አደረጋት፡
ዋናው ጉዳይ ማለትም ከማን ጋ ልኑር› የሚለው ጥያቄ በሁለቱ ወንዶች
መካከል ሊነሳ ከነበረው አምባጓሮና በአሜሪካ የመኖር ስጋት ጋር ሲነጻጸር
ሚዛን የሚደፋ ነበር፡ ማርክ ይወዳታል እሷም ትወደዋለች፡፡ ሌላው ነገር
ሁሉ ሁለተኛ ደረጃ ነው፡፡ ውሳኔዋ በአዕምሮዋ ሲመሰረት ትልቅ እፎይታ
ተሰማት፡ ትንፋሿን በረጅሙ ለቀቀችና ‹‹ይቅርታ መርቪን›› አለች ‹‹ጥዬህ
ከማርክ ጋር እሄዳለሁ፡››
ምዕራፍ አስራ ሁለት
ናንሲ ሌኔሃን ከመርቪን ላቭሴይ ሚጢጢ አይሮፕላን ላይ ሆና ቁልቁል
የፓን አሜሪካን የሰማይ በራሪ ጀልባ ለበረራ ዝግጁ ሆኖ በባህር ዳርቻ ላይ
"ኩራት ቆሞ ስታየው ቅጽበታዊ ደስታ ተሰማት፡ ከተወሰኑ ሰዓታት በፊት
oድል ጠሞባት የምታደርገውን አጥታ ነበር፡ ነገር ግን የወንድሟን ዕቅድ
በከፊልም ቢሆን ለማጨናገፍ ትንሽ ቀርቷታል፡ ናንሲ ሌኔሃን እንዲህ
በቀላል እጇን የምትሰጥ ሴት አይደለችም› ስትል ለራሷ አድናቆት ቸረች፡
ትንሿ አይሮፕላን የመቆሚያ ቦታ ፍለጋ ስትሽከረከር ናንሲ ከወንድሟ
ሊገጥማት የሚችለውን እሰጥ አገባ ስታስበው ሰውነቷ በንዴት ተወጣጠረ፡
ወንድሟ እሷን ለማታለል ይህን ያህል ለምን እንደጨከነ ማመን አሁንም
አቅቷታል፡ እንዴት ይሄ ሀሳብ በአእምሮው ሊመጣ ቻለ?
በህጻንነታቸው አብረው ገላቸውን ይታጠቡ ነበር፡፡ መሬት ወድቆ እግሩ
ሲቆስል ፋሻ ወይም የቁስል ፕላስተር ታስርለት ነበር፡ ማስቲካ ቆርጣ ታካፍለው ነበር፡

ጥፋቱን ለሰው ነግራበት አታውቅም፡፡ የእሷን ፈ ሚስጥር ሳትደብቅ ትነግረው ነበር፡ ካደጉም በኋላ ምንም እንኳን ሴት ብትሆንም በሁሉም ነገር ትበልጠው ዕድሜውን በሙሉ እሱን ትንከባከበው ነበር፡
👍20
አባታቸው ሲሞቱ ፒተር የኩባንያው ኃላፊ እንዲሆን ፈቀደችለት፡ ይሄ ደግሞ በኋላ በእጅጉ ዋጋ አስከፍሏታል፡ የአባታቸው ምክትል ከነበረው ናት
ሪጅዌይ ጋር አፍላ ፍቅር ላይ በነበረችበት ወቅት የኩባንያውን ኃላፊነት
ፒተር እንዲይዝ ስትስማማ ናት ሪጅዌይ በድርጊቷ አኩርፎ ኩባንያውን ለቆ
ወጣ፡፡ እሷንም አይንሽ ላፈር አላት፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ ፍቅሯን
ሳያስጨርሳት ሌላ ሴት ያገባው፡፡

ጓደኛዋና የኩባንያው ጠበቃ ማክ ማክብራይድ ፒተር የኩባንያው ኃላፊ
እንዳይሆን ቢመክራትም ወንድሟ ፒተርን ሰዎች በአባቱ እግር ሊተካ የሚችል ብቃት ያለው ሰው አይደለም ብለው እንዳያስቡ የማክብራይድን ምክርና የራሷን ፍላጎት ወደ ጎን ትታ ያደረገችለትን ያን ሁሉ ደግነት ከምንም ሳይቆጥር እሷን ለማታለል የሚያደርገውን መፍጨርጨር ስታስብ
እሱን ፊት ለፊት አግኝታና አናግራ እውነቱን ለማወቅ በእጅጉ ጓጉታለች፡፡ ገጽ ለገጽ ተገናኝተው ምን እንደሚል ለማወቅ ትዕግስት አጥታለች።

ስለዚህ ከፒተር ጋር የሚገጥማትን ጦርነትን በድል ለመወጣት
ፒተር አይሮፕላኑ ላይ ሳይሳፈር መድረስ ብቻ አይደለም ዓላማዋ ይሄ
የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡
አይሮፕላኑ ላይ መሳፈር አለባት፡፡ ነገር ግን
አይሮፕላኑ ቦታ ከሌለው ከአንዱ ተሳፋሪ ላይ ቲኬት በጭማሪ ዋጋም ቢሆን
መግዛት ይኖርባታል፡፡ ወይም አማላይነቷን ተጠቅማ ፓይለቱ እንዲጭናት ማግባባት ይኖርባታል፡፡ አለበለዚያም ጉቦም ሰጥታም ቢሆን አይሮፕላኑ ላይ መውጣቷ የግድ ነው፡ አገሯ ቦስተን ስትደርስም ትንንሽ የአክሲዮን ድርሻ
ያላቸው አክስቷን ቲሊሊና የአባቷ የቀድሞ ጠበቃ ዳኒ ሪሌይ ድርሻቸውን
ለናት ሪጅዌይ እንዳይሽጡለት ማግባባትም የሚጠበቅባት ተግባር ነው፡ ይህን
ማድረግ ባያቅታትም ፒተር በቀላሉ እጅ አይሰጥም፡፡ ምክንያቱም ናት
ሪጅዌይን የመሰለ ባላንጣ በኋላ ደጀንነት አሰልፏልና፡

መርቪን ትንሿን አይሮፕላን ሜዳ ላይ አሳረፋት፡፡ ከእሱ በማይጠበቅ ጨዋነት ናንሲ ከአይሮፕላኗ ስትወርድ እጇን በመያዝ ረዳት፡፡ የአየርላንድ መሬት ለሁለተኛ ጊዜ ስትረግጥ አባቷ ትዝ አሏት፡፡ አባቷ ሁልጊዜ
እትብታቸው ስለተቀበረበት አገር አውርተው ባይጠግቡም አንድም ቀን ዝር ብለው አያውቁም፡፡
በዚህም ሀዘን ተሰማት፡፡ በአንጻሩ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ ልጆቹ ከአባታቸው ቀድመው የአያት ቅድመ
መርገጣቸውን ቢያውቁ ምንኛ ደስ እንደሚላቸው አሰበች፡፡ በሌላ በኩል ግን
አያቶቻቸውን አገር የገዛ ልጃቸው እድሜ ልክ የደከሙበትን ኩባንያቸውን ለማፈራረስ ትግል
እያደረገ መሆኑን ሳያዩ አፈር መልበሳቸው ጥሩ ነው ስትል አሰበች ናንሲ
ሌኔሃን፡፡

መርቪን አይሮፕላኗን ሲያሳርፋት ልቧ አረፍ አለ፡፡ ምንም እንኳን
የሚፈልጉት ቦታ ብታደርሳቸውም ከሞት የተረፉት ለጥቂት ነው፡፡ አይሮፕላኗ ከዚያ ገደል ጋር ልትጋጭ የነበረው በዓይነ ህሊናዋ ሲመጣ አንቀጠቀጣት፡፡ ከዚህ በኋላ እስከ ዕለተሞቷ በትንሽ አይሮፕላን እንደማትበር ማለች፡

ከፊት ለፊታቸው የሚሄደውን ድንች የጫነ በፈረስ የሚጎተት
እየተከተሉ በፍጥነት በመንደሯ ተጓዙ፡ መርቪን ከሁኔታው ድል የማድረግም የፍርሃትም ስሜት እንደሚታይበት ናንሲ ተገንዝባለች፡ እንደ
እሷው ሁሉ እሱም ክህደት ተፈጽሞበታል፡፡ እሷ እንዳልተቀበለችው ሁሉ
እሱም ክህደትን በጸጋ አልተቀበለውም፡፡ እሷ ላይ እንደተፈጸመው ከጀርባው
ሆነው ሲዶልቱ የነበሩ ሰዎች ደስ አይበላቸውና ጥረታቸውን ድባቅ
ለመምታት ትንሽ እንደቀረው ሲያስብ ልቡ ቅቤ ይጠጣል፡

ፎየንስ መንደር ያለው አንድ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ግማሽ መንገድ ያህል እንደሄዱ የፓን አሜሪካን አየር መንገድ ተሳፋሪዎች የሚመስሉ ማለፊያ
የለበሱ ዘመናዊ ሰዎች ወደ እነሱ ሲመጡ አዩና መርቪን ወደ ሰዎቹ ጠጋ ብሎ ‹‹ወይዘሮ ዳያና ላቭሴይ የምትባል ሴት ታውቃላችሁ? የፓን አሜሪን
ተሳፋሪ ሳትሆን አትቀርም›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አዎ እናውቃታለን›› አለች ከሴቶቹ መካከል አንዷ፡ ናንሲ መልስ የሰጠችው ሴት ታዋቂዋ የፊልም አክተር ሉሉ ቤል እንደሆነች ወዲያው አወቀች: ዳያና ላቭሴይን እንደማትወዳት ካመላለሷ ተረዳች - ናንሲ፡
የመርቪን ሚስት ምን ትመስል ይሆን? ስትል አሰበች ናንሲ፡
ሉሉ ቤልም ቀጠለችና ‹‹ወይዘሮ ዳያና ላቭሴይ እና አብሯት ያለው ጓደኛዋ ከመንገዱ ባሻገር ያለው ቡና ቤት ውስጥ ናቸው›› አለች፡፡

‹‹እባክሽ የቲኬት መሽጫውን ቦታ ብታሳይኝ?›› ስትል ናንሲ፣ ሉሉ ቤልን ጠየቀቻት
‹‹አንድ የቱሪስት አስተናጋጅነት ገጸባህሪን ወክዬ የምሰራ hሆነ ስራውን ደጋግሜ ማጥናት አይኖርብኝም›› ስትል ሉሉ አብረዋት የነበሩ ሰዎች በሳቅ ፈነዱ፡ ቀጠለችና ‹‹የአየር መንገዱ ህንጻ ከባቡር ጣቢያው አልፎ ከወደቡ ፊት ለፊት መንገዱ መጨረሻ ላይ የሚገኘው ህንጻ ውስጥ ነው›› አለች፡
ናንሲ ሉሉን አመሰገነችና መንገዷን ቀጠለች። መርቪን እየገሰገሰ ስለነበር
እሱጋ ለመድረስ የሩጫ ያህል ተራመደች። ብዙም ሳይሄዱ መርቪን ሁለት
ሰዎች በተመስጦ እየተነጋገሩ ከመንገዱ አቅጣጫ ሲሄዱ አየና አይኑን ማመን አቅቶት ቆመ: ናንሲ መርቪንን በድንገት ከመንገዱ ያስቆሙት
ሰዎች እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ጓጓች፡ አንደኛው ሰው ጥቁር ሱፍ ልብስ
የለበሰ ጸጉረ ነጭ ቦርጫም ሲሆን የፓን አሜሪካን አየር መንገድ ተሳፋሪ
ለመሆናቸው ጥርጥር የለውም፡፡ አብሯቸው ያሉት ረጅም ሰው በማሳ ላይ
የተተከለ የወፍ ማባረሪያ አሻንጉሊት የመሰሉ፣ አጥንታቸው የገጠጠ ራሰ
በራ ሲሆኑ አስፈሪ ቅዥት አስደንግጧቸው ከእንቅልፋቸው የባነኑ ሰው
ይመስላሉ፡፡ መርቪን ሊጠጋቸው ሰውየው ደነበሩ፡፡ መርቪን ሊተናኮላቸው
የመጣ ሰው መስሏቸው ለመከላከል እጃቸውን በደመነፍስ አወናጨፉ፡፡
ሁለተኛው ሰው ‹‹ችግር የለም ካርል፤ ተረጋጋ›› አላቸው፡፡

መርቪንም ‹‹ጌታዬ፣ ሰላም ልሎት ነው የመጣሁት፡፡ እርስዎን በአካል ማግኘት መቻሌ ክብር ይሰማኛል›› አላቸው ከሰውነት ጎዳና የወጡትን ሰው፡፡
ሃርትማን ጥንቃቄ ሳይለያቸው እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉ፡፡ናንሲ የመርቪን ባህሪ በአንድ ጊዜ መለወጡ አስደንቋታል፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ባህሪውን እንዳየችው ከሆነ በዓለም ላይ ከሱ በላይ ሰው እንደሌለ አድርጎ የሚገምት ሰው ነበር፡፡ አሁን ግን ያየችው ባህሪ እንደየቤዝቦል ጨዋታ ኮከብ ተጫዋችን የአድናቂነት ፊርማ እንዲፈርምሉት
የሚለማመጥ አንድ ተማሪን ነው ያስታወሳት....

ይቀጥላል
👍19
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ በተቃራኒው ጦርነት ወደ ተዘፈቀች አገር መመለሱ ራሱ አንድ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው፡.... እዚህ ነገር ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ለምን ገባሁ? አለች ልቧ እየተሰበረ ሁን ለመጸጸት ጊዜ የለም፡ አንዴ ስለወሰንኩ ወደ ኋላ የምልበት ነገር የለም፡፡ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥም አለች መልሳ በሆዷ ሀሳቧ አንድ…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ (20)

‹‹ምክንያቱም ባለፈው ዓመት ይኸኔ… ባለፈው ዓመት በዚህቀን…››
«ምን ... ያው አሁን ከምሰራው የተለየ ምንም ነገር አልነበረም » አላት እንደምንም ። ፊቱ ልውጥውጥ አለ ። ግንባሩ መስመር ብቻ ሆነ ። ክመቀመጫው ብድግ ብሎ «ትንሽ ብናወራ መልካም ነበር ። ደስ ይለኝ ነበር ። ሆኖም ካስር ደቂቃ በኋላ ስብሰባ መግባት አለብኝ ። ስለዚህ ልሂድ አለና ፈገግ ሳይል ጨብጧት ሄደ ። ሁኔታው ድንገት ልውጥ ማለቱን የተገነዘበችው ዌንዲ ምን ብዬ ይሆን ? ምን የሚያስከፋ ነገር ተናገርኩ ይሆን? ስትል አሰበች ። የለም ስለሰውየው ጠባይ ቤንን መጠየቅ ይኖርባታል። እወቅሁት ስትል ድንገት የትናየት ርቀህ እንደምትገኝ ያሳይሀል»

ከአሥር ደቂቃ በኋላ በተጀመረው ስብሰባ ላይ ዌንዲም ተካፋይ እንደነበረች ሲረዳ ማይክል በጣም ተገረመ ። ዌንዲ እስብሰባው ላይ እንድትገኝ ያደረገው ቤን ኣቭሪ ነበር። ምክንቱም ስብሰባው የሳንፍራንሲስኮ ሕክምና ማዕከልን ሥራ ለመጀመር በሚቻልበት ዕቅድ ላይ ለመነጋገር ሲሆን አስቀድሞ መነጋገርን ከሚሹ ሥራዎች አንዱ የሕንፃው የውስጥ አሠራር ንድፍ ሥራ ነው። የዚህ ባለሙያ ደግሞ ዌንዲ ታውንሴንድ ናት ። በእርግጥ አስቀድሞ በታወቀው መሠረት መሠረታዊውን ፕላንና ንድፍ ተከትሎ ሕንፃው ይሠራል ። ግን ይህ በቂ አይሆንም ። ውበቱን ከፍ ለማድረግና ድንቅ የጥበብ ሥራ ለመፍጠር በሥነ ጥበብ ሥራዎች ማስጌጥ ያስፈልጋል ። እነዚያን የሥነ ጥበብ ሥራዎች ቤን ራሱ ወደ ሳንፍራንሲስኮ በመሄድ ሲፈልግና ሊመርጥ ወስኗል ። ስለዚሀም ዌንዲ ኒውዮርክ ውስጥ የሚከናወነውን ሥራ በጥብቅ መከታተል አለባት ።

ሥራው ዛሬና ነገ ይጀመራል የሚባል ባይሆንም ስብሰባው የተደረገው አስቀድሞ የተቻለውን ያህል ሁኔታዎችን ለማጥናት ፤ ውሳኔዎችን ለመስጠትና ይደርሳሉ የተባሉ ችግሮችን ለመመልከትና ዕቅዱን አበጥሮ ለመተንተን ነው ። ይህ ዝግጅት ተደርጐ ከቆዬ ሥራው ሲጀመር የሚመጣው ችግር አነስተኛ ይሆናል ። ስብሰባው ረጅም ግን ምንም ዓይነት ዘበዘባ የሌለበት ሲሆን በማሪዮን ሒልያርድ መሪነት ፤ በጆርጅ ኮሎዌ ረዳትነት ነበር የተካሄደው ። ይህ ይባል እንጂ የማይክል ተሳትፎ ከነዚህ ከሁለቱ የሚያንስ አልነበረም ። ምክንያቱም የዚያ ፕሮጀክት ኃላፊ ራሱ ማይክል ሒልያርድ ሆኖ ተሾማል ። ማሪዮን ሒልያርድ የዚህን ትልቅ ፕሮጀክት ኃላፊነት ለማይክል መስጠቷ በከንቱ አልነበረም ። በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ታላላቅ የሚባሉ የአርኪቴክቸር ድርጅቶች ሁሉ የዚህን ፕሮጀክት ሥራ ለማግኘት ቋምጠው ነበር። ኮተር ሂልያርድን ማሸነፍ የማይቻል ሆነና ሳያገኙት ቀሩ ። የሥራውን ሁኔታ የማይከታተል ባለሙያ ድርጅት አይኖርም ማለት ነው ። እንደሚያዋጣ ማሪዮን ሙሉ በሙሉ ታምናለች ። ይህ ደግሞ የፕሮጀክት ኃላፊ የሆነውን አርኪቴክት ስምና ዝና የሚተክል እንደሆነ ይገባታል ። ስለዚህም ኃላፊነቱን ለማይክል ሰጠችው ።

ስብሰባው ሲያበቃ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ሊሆን ምንም ያህል አልቀረውም ነበር ። በዕለቱ ዌንዲ ታውንሴንድ በሀሳብ አቀራረቧ ሲያስፈልግም ማሪዮንን እስከመጋተር በመድረስ በሙያዋ ምን ያህል የበሰለች እንደሆነች አሳይታለች። ስብሰባው ሲያልቅ ድክምክም ብላ ነበር። ከስብሰባው ሲወጣ ቤን ትከሻዋን መታ መታ እያደረገ « እሰይ የኔ ልጅ ! የዛሬ ሁኔታሽ የሚደነቅ ነበር » አላት። ወዲያው ጸሐፊው ስለጠራችው ቀድሟት ሄደ ። ዌንዲ ስለሁኔታው እያሰበች በኮሪደሩ ውስጥ ብቻዋን በመጓዝ ላይ እንዳለች ማይክል አስቆማት ። ገረማት ።»

« የሥራሽን ሁኔታ ጥልቀት ሳይ በጣም ተገረምኩ ዌንዲ እንዲህ ከሆነ በመተባበር ግሩም የሆነ ነገር እንደምንፈጥር ይታየኛል » አለ ማይክል ። « እኔም እንደዚያ ብዬ እገምታለሁ » አለች ፤ ኩራት እየተሰማት ። ሌላ ሰው ሳይሆን ማይክል ነውኮ ያመሰገናት ። « አትጠራጠሪ » አለ ማይክል ። ድንገት ሁለቱም ዝም አሉ፤ ጎን ለጎን እየሄዱ። «ማይክል…. ማይክል... ቅ... ቅድም ማለት ምን እንዳልኩህ እንጃ። ግን ሆነ ብዬ… በፍጹም አውቄ ሳይሆን… አስቀየምኩህ መሰል ፤ አደል ? ማለት… ሚስጥር ለማስወጣት ወይም በግል ሕይወትህ ለመግባት ሳይሆን… አጠያየቄ.. በጣም በጣም አዝና…» ስትጨነቅ ሲያያት አዘነላት ፤ «የለም ዊንዲ ፤ አንቺ ምንም አላጠፋሽም ። እኔ ነኝ ጋጠወጥ ሥራ የሠራሁት። እና ይቅርታ አድርጊልኝ ። የጸደዩ ወራት ከሕልሙ ጋር ደባልቆ የማይገባ ባህሪ ሳይሰጠኝ አልቀረም ። ለምን ዛሬ እራት አልጋብዝሽም? ካሳ » አለ ። ይህ የራት ግብዣ ጉዳይ ካፉ ሲወጣ ደነገጠ። እሷም ገፅታ ላይ አድናቆትና ጥርጣሬ አብረው ተስለው መታየት ጀመሩ፡፡ «እኔ ማለት አየህ? ልካስ ብለህ... » ኣለች «ማን ግድ አለኝ ? ! ደስ ስለሚለኝ ነው » አላትና ፈገግ ብሎ « ያንችን ንገሬኝ ይመችሻል ?»
«ምንም ችግር የለም… እንዲያውም ደስ ይለኛል ።»
«ደግ እንግዲህ ። ካሁን ጀምሮ ካንድ ሰዓት በኋላ እቤትሽ ድረስ መጥቼ እወስድሻለሁ » አድራሻዋን ለስብለባ በያዘው ማስታወሻ ጀርባ ላይ ጫር ጫር አደረገና ያዘ። ወደ ቢሮው ሲሄድ ምን ዓይነት ዕብደት ነው ሲል አሰበ። ወዲያው ግን ለምን ዕብደት ይሆናል አለ። ልክ ባላት ሰዓት እቤቷ ይረሰ ። ቤቷን ገና ሲያየው ወደደው። ቡናማ ቀለም ካለው ድንጋይ የተሠራ ሕንፃ ሲሆን የበሩ ማዕዘን የተሠራው ከሚያብለጨልጭ ጥቁር ድንጋይ ነው ። እመዝጊያው ላይ ከነሐስ የተሠራ በር መምቻ ተንጠልጥሏል ። ቤቱ በጠቅላላ ለአራት ቤተሰብ መኖሪያ እንዲሆን የተከፋፈለ ሲሆን የዌንዲ መኖረያ ከሁሉም ጠበብ የምትለዋ ናት ። ሆኖም ይህች የሷ መኖሪያ ብቻ ናት ከበስተኋላዋ የአትክልት ቦታ ያላት። እቤት ውስጥ ሲገባ ሁሉም አይነት እቃ የሚሸጥበት ሱቅ መስሎ ታየው ። ታሪካዊ የሆኑ አንቲካ እቃዎች አሉ ፤ ዘመናዊ እቃዎችም አሉ ። ለየት ያሉ እቃዎችም አሉ። በተለያዩ መብራቶች በመጠቀም የክፍሉ ቀለም እምብዛም የማያብረቀርቅ ግን ስሜት ሞቅ የሚያደርግ እንዲሆን አድርጋዋለች ። እዚያ ቤት ያየው ሁሉ ደስ አሰኘው ። የአበባ አተካከሏ ሁሉ ነገር።
👍15
ሆድ የሚከፍት ቀላል ምግብና መጠጥም አዘጋጅታ ነበር የጠበቀችው ። ያን እየቀማመሰ እያወራት እያወራችው ያላሰቡትን ያህል ጊዜ ቆዩ ። እንደ እውነቱ ከሆነ ፤ ማይክል አስቀድሞ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ቦታ ባያስይዝ ኖሮ ከዚያ ቤት ባይወጣ ደስ ይለው ነበር። ሆኖም አሁን አይቻልም። ያ የተባለው ምግብ ቤት ደግሞ አንድ ሰው ቦታ ያዙልኝ ቢልና አምስት ደቂቃ ቢዘገይ ቦታው ለሌላ እንግዳ ይሰጣል ፤ የታወቀ ነው ። ስለዚህ «ወይ መሮጥ ይኖርብናል ወይ ቦታችን መያዙ ነው። ወይስ ቢያዝ ባይያዝ ይህን ያህል አያሳስበንም ?» አለች ዌንዲ። እሱ ሲያስበው የነበረውን ነገር ስትናገር በጣም ደነገጠ ። ተገረመ። ቀና ብሎ ሲያያት የሆነ ተንኮል ነገር አይኗ ውስጥ ያየ መሰለው። ሁሉም ነገር እንግዳ ሆነበት ። ከሴት ጋር መውጣት ካቆመ ጊዜው ረጅም ሆኖበት ነበረና ፤የሆነ ስህተት እንዳይፈፅም ፈራ፡፡ «እንሩጥ ወይስ...ያንች ሀሳብ ምንድነው ሚስ ታውንሴንደ!?» አለ እንደመቀለድ እያለ «ሀሳብሽም እንደፊትሽ ያስፈራ ይሆን ?» «ሀሳቤማ ከፊቴ የባሰ ነው » አለች «ምን ሳስብ ነበር መሰለህ ምግባችንን ቋጥረን ፤ ወደ ወደብ ሄደን ፤ ጀልባዎችን እየተመለከትን እዚያ እንድናመሽ»
«እንዴት ያለውን መላቅጥ ያጣ ሀሳብ አሰብሽው ልጄ›› እንዲህ ቢልም አላመለጠም ። ወደ ተባለው ሆቴል አልሄዱም የተባለውን ምግብ አዘጋጅተው ወደ ተባለው ወደብ ሄዱ። ብቻቸውን አልነበሩም ። እንደሷ መላ ቅጥ ያጣ ሀሳብ ያቀረቡ እንደሱ መላቅጥ ያጣውን ሀሳብ የተቀበሉ ብዙ ጥንዶች በወደቡ አካባቢ ነበሩ። በወደቡ አካባቢ ሲንሸራሸሩ ፤ የመጣላቸውን ሲያወሩ አመሹ፡፡ ወደ መጨረሻው ላይ በወሬ ወሬ የጋብቻ ጉዳይ ተነሳ። «መቼ ነው… ማለት ሚስት የማግባት ሀሳብ አለህ ? »አለችው። ፊቱን አቅጭሞ አንገቱን በአሉታ ነቀነቀ ። «እስከ ዘለአለም ?» አለች ። «እስከመቼም »
«ለምን ? መጠየቅ ይፈቀድልኛል ወይስ...»
«ጠይቂ» አላት «እነግርሻለሁ ምክንያቱን »
«እስከመቼ ሸሽቶ ይኖራል»
«በምሣ ሰዓት ያስደነገጥኩሽ በዚያ የተነሳ ነው ። ራት አብረን እንድንበላ ያደረገኝም ይኸው ጉዳይ ነው ። አምና ፤ በዚህ እለት ላገባ ነበር ።እኔ... ቤን አቭረ ሆነን ስንሄድ መኪናችን ተገጭታ ትልቅ የጭነት መኪና ፤ እኔና...ቤን ዳንን ።... የዚያኛው መኪና ሹፌር እና... እሷ ግን ሞቱ» አለ። ይህን ሲል እንባ እሚባል አልወጣውም ፤ አላለቀሰም ። ግን ሰውነቱን አንድ ነገር የሸረካከተው ፤ የበጣጠሰው መሰለው ። ዌንዲ በፍርሀት እና በመሳቀቅ እያየችው እንዲህ አለች።

«ማይክ ! በስማብ ! የምትነግረኝ ነገር እውን ሳይሆን ቅዠት ይመስላል! »
«ቅዝት ነበር ። አየሽ ለሶስት ቀን... አደጋው ከደረሰ በኋላ አልሰማ አልለማ ስነቃ ማለት ነፍሴን ሳውቅ...አልፋለች።ምን ልሁን...እ...እ...ኔ...» መናገር አልቻለም ። ቃላቱ አልወጣልህ አሉት ። ግን ጀምሮታልና መናገር አለበት፡፡

«ሲሻለኝ ከሁለት ሣምንት በኋላ ቦስተን ነበርኩ ... ቦስተን ነበር እምትኖረው ወደመኖሪያ ቤቷ ሄድኩ ። ግን ማንም አልነበረም… ምንም አልነበረም ። እቃዋም ፤ ስእሎቹም ተሰርቀጡ ደረስኩ ። ሰአሊ ነበረች.. ነርሶች ናቸው አሉ የ...የወ...የሰረቋቸው ስእሎቿን...» ዝምታ ሆነ ። ለረጅም ጊዜ ሁለቱም ፀጥ ብለው ተቀመጡ ከዚያ ቀጠለ…

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍11😢3
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


“ስለ ሰውዬው ወንጀል እኔ አላውቅም " ልጅዎ ግን ነጻ እንዲሚወጣ አይጠራጠሩ አይዞዎ ፤አይጨነቁ " የደስታ ዘመን እየመጣልዎ ነው” ብሎ አበራታቷትና አሳምኗት ወጣ

ሚስ ካርላይል የወንድሟን የምርጫ ቀን ምክንያት በማድረግ በሕይወቷ
አድርጋው የማታውቀውን እስከ መጨረሻው አጊጣ ለብሳ ስትንጎራደድ በነበረችበት ወቅት ዐይን አውጣዋ አፊ ሆሊጆንም በበኩሏ ከሚስ ካርላይል አሽከሮች ጋር ተመሳጥራ ሾልካ በመግባት ሚስ ካርላይል ከነበረችበት በላይ ከነበረው ፎቅ ወጣች " በተጐነጐነው ጸጉሯ ላይ ቆብ ደፍታ እስከ ሽንጧ ድረስ ደረጃ እየመጣለት የተሰፋው የነጭና የአረንጓዴ ዝንጉርጉር ቀሚስ ለብሳለች » ዐይነ ርግብና ለስላሳ ነጫጭ የጅ ጓንቲዎች አጥልቃ በዳንቴል የተከፈፈና ሽቶ የተርከፈከፈ መሐረብ ይዛ ባጠቃላይ ውድና ቀለመ ደማቅ በሆነ ሙሉ ልብስ አጊጣ እንደ ሱፍ አበባ ጐልታና ደምቃ በአደባባይ ለመላው ሕዝብ እየተጐማለለች ስትታይ ቆየች ደግነቱ ግን ሚስ ካርሳይል አላየቻትም ።

“ መልከ መልካም ነውኮ !” አለች ለሚስ ካርላይል ገረዶች ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ከፊት ለፊታቸው ሲደርስ አየችውና "

ግን መጥፎ ሰው ነው የሚል ነበር ያገኘችው መልስ ። ሚስተር አርኪባልድ ጋር ተወዳድሬ “አሸንፋለሁ ብሎ ማሰቡና እዚህ መምጣቱም ያስገርማል” አሏት"

“ምን እያደረጉ ነው?” አለችና'“እንዴ ኧረ ፖሊሶችም አሉ !” ብላ ጮኸችና'' እጁን በካቴና እያሰሩት ነው ምን አደረጋቸው ? እያለች ለፈለፈች።

ለጩኸቷ መልስ አላገኘችም ። ፊቷ ዐሥር ጊዜ እየተለዋወጠ በጭንቀት ስትመለከት ቆየችና “ አንዴ ” አለች ሰዎች ሲናገሩ ነገሩን ከአፊ ቀድማ የሰማችው
አንዷ ሠራተኛ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪስንና ኦትዌይ ቤቴል አባትሽን ሆን ብለው
ስለ ገደሉ ተይዘዋል ነው የሚባል ”አለቻት "

ምን ! ” ብላ ጮኸች አፊ "

“ ገዳዬ ሴቪሰን ነው " ሪቻርድ ሔር ከደሙ ንጹሕ ነው ይላሉ " አለቻት።

አፊ ነገሩን አዳመጠች " ምን ማለት እንደሆነ አሰበች " ከዚያ እየተንገዳገደችና እየተንቀጠቀጠች ሙሉ ለሙሉ መሬት ላይ ተዘረረች አፊ ሆሊጆን ሕሊና
ዋን ሳተች።

አፊ ሆሊጆን አቅሏን ስታ የነበረችው ለቋት ወደ ሚስ ካርይል ቤት ተሸሽጋ
እንደ ገባች ሁሉ ተሸሽጋ ወጣች " ከሚስ ካርላይል ቤት ትንሽ ራቅ ብሎ ዐይብ ያሣማ ሥጋና ልዩ ልዩ የምግብ ቅባቶች የሚሸጡበት ሱቅ አለ » ሱቁ ጥሩ ታዋቂነት እንዳለው ካጠና በኋላ ገዝቶ
የሚሠራበት አንድ ከለንደን የመጣ መልከኛ ልጅ እግር ነጋዴ ነው ሱቁ ምርጥ
ዕቃ በማቅረቡ የታወቀ ለመሆኑ የሚስ ካርላይል ደንበኛ ለመሆን መብቃቱ ብቻ መረጃ ነበር " የፊተኛው ባለቤቱ በቂ ገንዘብ ስለ አጠራቀመ ለሚስተር ጂፍን
ሲሸጠው ሰዎች እሱም ሠርቶ የሚበቃውን ያህል ገንዘብ ሲይዝ እንደ ፊተኛው
ሰውዬ ይሸጠዋል " እያሉ ተንብየውበታል "

አፊ ከሚስ ካርላይል ቤት ወጥታ ከሱቁ ፊት ለፊት ስትደርስ ሚስተር ጀፊንን ከሱቁ በር ቁሞ ታየዋለች ከውስጥ ረዳቱ ከዕንጨት በርሜል እያወጣ ቅቤ
ይሸጣል " አፊ ቆም አለች " ሚስተር ጂፊን መቸም የሷ ነገር ጭንቁ ነው " ልቡ
እስኪጠፋ ይወዳታል እሷም እሱ ሲያወዳድሳት ደስ ደስ ይላታል "

“ እንደ ምን ዋልሽ ... አፊ” አላት ነጭ ሽርጡ እንዳይታይበት ተጠንቅቆ
አጣጥፎ ከደበቀ በኋላ እጁን ወደሷ ዘረጋ ። ምክንያቱም ስለ ሽርጡ አሳፋሪነት አንድ ጊዜ ጠቆም አድርጋው ነበር "

“ ደኅና ነህ ጄፈን" አለችውና ነጫጭ ጓንቲዎቿን እንዳደረገች ራሷን ዝቅ በማድረግ ለሰላምታ የቀረበላትን እጅ በጣቷ ጫፍ ነካ አደረገችው “እኔ
ደሞ ” አለችው የጅ መሐረቧን ዐይነ ርግቧንና ( ቀለበትኛ የተሠራውን ጸጉሯን በማሳየት እየተውረገረገች “ዛሬ ሱቅህን ዘግተህ ዕረፍት ያደረግህ መስሎኝ ነበር
ሚስተር ጂፊን ” አለችው።

“ ሥራ መከበር አለበት” አላት ጂፍን ሐሳቡ በሷ ፍቅር ተይዞ ነጻ ሆነሽ በሽርሽር ላይ መሆን መቻልሽን ባውቅ ኖሮ ምናልባት ባጋጣሚ እንደማገኝሽ ተስፋ በማድረግ እኔም ዕረፍት እወስድ ነበር"

አባባሉ ከእውነተኛ ፍቅር የመነጨ መሆኑን ተገንዝባ ' “ ምንም እኮ አያውቅም ሥራው ሁሉ እንደ ከብት ነው ' አለች ' በሐሳቧ "

“ እኔ በሕይወቴ ያለኝ ታላቅ ደስታ .. ሚስ አፊ አንቺ ስታልፊ በሱቁ መስኮት አሻግሬ ማየት ነው ”

“ ኧረ ጉዴ !” አለች አፊ ገፍቶ የመጣባትን ሣቅ ለማገድ እየሞከረች : “ለምን እንደሚጠቅምህ አላውቅም "ዐይን ካለህ ከአንድ ሁለት ሰዓት በፊት ወደ ሚስ ካርላይል ዘንድ ስሔድ አይተኸኝ ይሆናል”

“ አዬ ! ዐይኖቼ የት ሔደው ኖሮ ይሆን?” አለ እየተጸጸተ “ አሃ ! ገባኝ እነዚያ የቅቤ በርሜሎችን ስመረምር ነው ይገርምሻል . . . ሚስ ሆሊጆን የተበላሹትን ስለ ላኩልኝ መልሼ ልልክላቸው ነው ”

“ አ ... ይ ! እኔ የቅቤ በርሜሎች ብሎ ነገር አላውቅም " እንዲህ እንዲህ ያለው ነገር ከክብሬ በታች ነው
“ እንዴታ እሱስ እውነትሽን ነው ... ሚስ ሆሊጆን “ ምንም እንኳን የገበያውን ጥቅም ለሚገባው ከፍተኛ ትርፍ ቢኖረሙም ካንቺ ክብር ጋር አይስማማም »

“ የምን ጩኽት ነው የምሰማው ? አለች አፊ "
"መራጮች ለሚስተር ካርላይል ሲያጨበጭቡ ነው መመረጡን ስምተሻል
ይመስለኛል

" የለም አልሰማሁም ”

ያኛውማ የገዛ ወዳጆቹ አስወጡትና ተገላገሉት » እንግዲህ እንደራሴአችን
ሚስተር ካርይል መሆኑ ነ&ዘው " ይባዋል ... መቸም እንደሱ ያለ ሰው የለም ‥

“እነዚህ ሁሉ ደንበኞችህ ናቸው እንዴ ? ሁሉንም ማስተናድ ከባድ ሥራ
ነው ሰውዬህ ብቻውን አይዘልቀውም " ስለዚህ እያወራሁ ጊዜ ልወስድብህ አልፈልግም ሔድኩልህ "
አለችውና እየተንሳፈፈች ሔደች " ጂፊን ፍዝዝ ብሎ
ሲያያት ከቆየ በኋላ ከይኑ ስትጠፋ የግዱን ደንበኞቹን ወደ ማስተናገድ ዞረ »

ጂፊን በፍቅሯ ወጥመድ መግባቱን ዐውቃና እንደሚያገባትም ተማምና አፊ በዚያ በቅባት በተባላሸው ሱቅ በኩል ሳይሆን በጓዳ በር እየገባች ጠቅላላ የቤቱንና የእቃውን አያያዝና አቀማመጥ ' ባሏንም እንዴት እንደምትንከባከበውና እንዴት አድርጋ በፍቅሯ ዐሥሬ የመሽቀርቀርያ መሣሪያ እንደምታደርገው እያሰላሰለች በምኞት አየር ላይ ሰገነት ሠርታ በሐሳቧ እየተሽሞነሞነች ስትራመድ ኧበንዘር ጀምዝ ደርሶ ለቀም አደረጋት ።

“ እንደምነሽ . . አፊ ? ዛሬ ጧት ሚስ ኮርኒ መስኮቶች ላይ አየሁሽ "

“ ያንተ ነገር እንግዲህ በቃኝ . . . ኧበንዘር ጀምዝ በቀደም ለሚስተር ጀፊን የዱሮ ወዳጄ ነበረች ማለትህን እኮ ሰምቸሃለሁ ”

“ አዎን ነበርሽና ” አላት እየሣቀ "

“ አልነበርኩም " እኔ በዚያን ጊዜ ከበላዮችህ ጋር እንጂ ካንተ ጋር ምንም ግኙነት አልነበረኝም አሁንም እኔን ለመጉዳት ብለህ በሐሰት ስሜን ለማጥፋት ብታስብ ተሳስተሃል ... ኧበንዘር ጀምዝ " እኔ በዚህ ቦታ የተከበርኩ ሰው ነኝ " ስለዚሀ ዐርፈህ ተቀመጥ ”

“ ምነው አፊ ? ለምን እንደዚህ ትሆኛለሽ ? እኔ አንቺን ለመጉዳት አልፈልግም አንቺ እንደምትይው ብሞክርም አይሆንልኝም " አላት እየሣቀ "

ይኸው ነው ይበቃሃል አሁን ከኔ ራቅ የአንተ ህዝብ መሀል መታየትህ ለስሜ ደግ አይደለም " አለችው።

ደኅና መልእክቴን ከተቀበልሺኝ እሔድልሻለሁ " በይ አሁን ለዛሬ በዘጠኝ ሰዓት ፍርድ ቤት ከችሎቱ አዳራሽ ስለምትፈለጊ እንዳትቀሪ "

ከችሎት አዳራሽ ? እኔን ? ለምን ?
👍19
“ እንዳትቀሪ ነግሬሻለሁ” አላት ሚስተር ኧበንዘር “ “ሌሺሰን ሲያዝ አይተሽዋል " ቶርን ይባል የነበረው ሌቪሰን አባትሺን በመግደል ስለ ተከሰሰ ለምስክርነት ትፈለጊያለሽ።

" እኔ ስለ ግድያው ምንም አላቅም " ስለዚህ አልሔድም ።

መሔድ አለብሽ ... አፊ” አላትና ወረቀቱን በእጅዋ አደረገላት "

ይሄ መጥሪያሽ ነው " "

“እኔ በሌቪሰን ምንም አልመሰክርበትም " ጥፋተኛው ዲክ ሔር እያለ ንጹሁን ሰው ለማሰቀል አልረዳም እኔ እልም ብዬ ጠፍቸ ነገሩ እስኪያልቅ ካንዱ ከተደብቄ እቆያለሁ
እንጂ አልመጣም
"አንተ የሠራኸኝን
ግን ኧበንዘር ምንጊዜም አልረሳውም " ብላ የተቀበለችውን ወረቀት በጣጥሳ ጣለችውና ሚሲዝ
ላቲመርን ለማግኘት ወደ ቤት እየገሠግሠች ሔዶች " ካደረችው ጌጥና አለባበስ
ጥቂቱን ቀናንሳ ታማ ተኝታ ወደ ነበረችው እመቤቷ ዘንድ ገባች „

“ እሜቴ ” አለች “ ኧረ በጣም የሚያሳዝን ወሬ ደረስኝ አንዲት ዘመዴ
ታማ በጣም ስለ ደከመች ልታየኝ ትፈልጋለች አሉ" ስለዚህ በሚለጥቀው ባቡሮ ለመሔድ ፈቃድ ቢሰጡኝ ብዬ ነው " እንኳን እሷ ልካብኝና ባትልክብኝም እየሰማሁ የማልቀርበት ጉዳይ ነው "

«አዬ ! እኔስ አንቺ ከሌለሽ ምን ይበጀኛል ?

" ነገሩ የሞት ጕዳይ ሆኖ ነው እንጂ እኔም እርስዎ እንደዚህ ተይዘው"
እያየሁ ፈቃድ አልጠይቅዎትም ነበር "

“ ዘመድሽ የምትኖረው የት ነው ?ስንት ቀን ትቆለሽ ? አለቻት "

አፊ ካፍ የገባላትን አንዱን ከተማ ጠራችላትና በበነጋው ለመመለስ ተስፋ
ማድረጓን ነገረቻት "

“ የምን ዘመድ ናት
ለመሆኑ ? አለ ጆይስ እኅት ያለ ሚስዝ ኬን አክስት
እንልነበረሽ የነግርሺኝ መስሎኝ ነበር "

“ጥቂት ተቀያይመን ስለ ነበር • ስሟንም አንሥቸው አላውቅም እንጂ እሷም
ሌላይቱ አክስቴ ናት እንዲያውም አሁን በነፍሷ እንድደርስ ያስግደደኝ እንደተቀያየምን ሳንተያይ እንዳትሞት ነው”

ሚስዝ ላቲመርም ሁኔታዋን መዝና ፈቀደችላት " አፊ ልብሷን ቀያይራ በቦርሳዋ ጥቂት ገንዘብ ያዘች » አንዲያውም ትንሽ የቆዳ ሻንጣ አንጠልጥላ ወጣች ከፊት ለፊቷ አንድ የምታውቀው ፖሊስ ከመንገድ ዳር ሲንጐራደድ አገኘች "

“ ስሚ ሆሊጆን
እንዴት ዋልሽ ? ዛሬ ጥሩ ቀን ነው አይመስልሽም ? ”
ጥሩ ነው ” አለችው ስለ አቆማት እየከፋት „ “ አሁን ስለ ቸኮልኩ አላነጋግርሀም” ብላው መንግዷን ቀጠለች - እሱም አረማመዷን ከእሷ ጋር እያስተካከለ ጐን ጐኗ ይሔድ ጀመር። ፍጥነት ስትጨምር አብሮ እየጨመረ እንዶ መሮጥ ሲቃት እሱም እንደ መሮጥ እያለ ፡ “ምንድነው እንደዚህ ያስቸኮለሽ?” አላት "

“ አንተን አይመለከትም እኔ አሁን ያንተ አጀብ አስፈልገኝም" ለሁሉም
ጊዜ አለውና በሌላ ጊዜ ቁጭ ብለን እንጫወታለን

“ በባቡር ለመድረስ የቸኮልሽ ትመስያለሽ”

“ ነውና ይህ መልስ የሚያረካህ ከሆነ ወዳንዱ ተንሸራሽሬ ልመጣ ነው
አቶ አጥብቄ ጠያቂ"

ብዙ ትቆያለሽ ?”

“አ...አ ነ ገ ሳልመለስ አልቀርም ስማ እስቲ ሚስተር ካርላይል መመረጡ እውነት ሆነ?”

“ አምን እውነት ነው" ተይ በዚያ በኩል አትሒጅ እባክሺን

" በዚያ በኩል አትሒሂጂ ” አለች አፊ የሱን አነጋገር በመድግም " ወደ ባቡር ጣቢያ የሚቀርበኝ ይኸ ነው
ዙርያውን መንገድ ይቀንስልኛል

መኮንኑ ቀስ አድርጎ እጁን ጣል አደረገባት "
አፊ ከሱ ለመለየት የጨነቀውና ለመዳራት የፌለገ መሰላት
“ ምን መሆንሀ ነው አንተ ደግሞ እኔ አሁን ለዚህ ጊዜ የለም እጅህን ወዲያ በል አለችው ጠበቅ እያደረጋት ስለ ሔዶ ቆጣ ብላ"

ሴት ልጅን ማስቀየም በተለይም አንቺን ..ሚስ ሆሊጆን ደስ አይለኝም
ነገር ግን እጄን ካንቺ ላይ ማንሣት አልችልም ። እኔም ካንቺ አልለይም ወደ ፍርድ ቤት አዳራሽ በቶሎ እንዳቀርብሽ ትዛዝ ተሰጥቶኛል ዛሬ ከቀትር በኋላ ለምስክርነት
ትፈለጊያለሽ ”

" እኔ የማወቀውም የምመሰክረም የለኝም ”

“የተሰጠኝን ትእዛዝ ተቀብዬ መፈጸም እንጂ ምንና ለምን ብዬ አልጠይቅም
ስለዚህ ከከተማ እንዳትወጭ ጠብቄ ወደ ፍርድ ቤት እንዳቀርብሽ የታዘዝኩትን ለመፈጸም በተቻለኝ መጠን ላስረዳሽ ሞክሬአለሁ ”

“ መቸም እንደዚህ ይዘኸኝ በዌስት ሊን መንገዶች ታልፋለች ብለህ እንደ
ማታስበኝ አርግጠኛ ነኝ ”

“ ላለመሸሽ ቃል ከባሽልኝ እለቅሻለሁ " ለመሮጥ ብትሞክሪ ደግሞ ላልሰሙት ለማሰማት ካልሆነ በቀር ሁለት ሜትር እንኳን ሳትሔጅ ስለምይዝሽ
ሙከራሽ ዋጋ የለውም"

“ በል ልቀቀኝ ዝም ብዬ እሔዳለሁ”

ከዚያ ፖሊሱ ቫንጣዋን ይዞ ለሽርሽር የወጡ መስለው ቀስ ብለሙ እያወሩ ሄዱና ከቃል መቀቢያው ክፍል ገቡ በምስክርነቷ ለዳኞቹ ከቤት ደግሞ ለሚስዝ
ላቲመር ምን እንደምትመልስ እያሰበች ተቀመጠች።....

💫ይቀጥላል💫
👍21
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


የሕግ ባሥልጣኖቹ ገብተው ቦታቸውን ያዙ " በሌላ ጊዜ ቢሆን ዌስት ሊን
የማይረግጡት የሰላም ኮሚሺን አባሎች የሆኑ ሁሉ መጥተው ስለ ነበር መቀመጫ እንኳን
ሊበቃቸው አልቻለም " ምናልባት በተቃዋሚ ወገኖች የተሸረበ ደባ ይሆናል በማለት የተመሠረተበትን ክስ ስላላመኑበት የሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወዳጆቾ
ሁሉ ተሰባስበው ከችሎት ተገኙ " ሎርድ ማውንት
እስቨርንም ከኮሚሽኑ አባሎች ጋር መቀመጫ ተሰጠው" ልጁ ሎርድ ቬንም ከሕዝቡ መኻል ገብቶ ተቀመጠ ሰብሳቢው ሚስተር ጀስቲስ ሔር እየተጀነነ ቦታውን ያዘ" ልጁን ከስቅላት ለማዳን
ቢሆንም በይሉኝታ ይበድለዋል ወይም ባባትነቱ ይጠቅመዋል ተብሎ አይታሰብም ነበር" ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንንም ቢሆን ከሕሊናው ውጭ ጥፋተኛ ያደርገዋል ተብሎ
አይገመትም " ከጐኑ የተቀመጠው ሌላዉ ዳኛ ኮሎኔል ቤቴል ነበር " ሚስተር ሩቢኒ ለሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጥብቅና ቆመለት።

ሚስተር ቦል ከሪቻርድ የሰማውን መሠረት በማድረግና የፍንጩ መሠረት ግን ሪቻርድ መሆኑን ሳያነሣ ጭብጡን ብቻ በማቅረብ አስረዳ። ጭብጡን ከየት እንዳገኘው ተጠይቆ 'ምንጮን ለጊዜው ለመግለጽ ነገሩን የሚያበላሽበት መሆኑን
ግለጾ ሌቪስን ቶርን መሆኑን ማረጋገጥ ስለ ፈለገ በመጀመሪያ ኤበንዘር ጄምስ ተጠራ .

“ ስለ እስረኛው ስለ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ምን ታውቃለሀ ? ” አለው ጀስ
ቲስ ሔር።

.“ ብዙ አላውቅም ” አለ ኧበንዘር ጄምስ ' “ በርግጥ ካፒቴን ቶርን ሲባል
ዐውቀው ነበር ”

“ ካፒቴን ቶርን ?”

“ አፊ '“ ካፒቴን ቶርን ትለው ነበር " ኋላ ግን መቶ አለቃ እንደ ነበር ለማመቅ ችያለሁ

“ ይኸንን ከማን ልታውቀ ቻልክ ?”

“ ከአፊ! ስለሱ ስትናገር የሰማኋት እሷ ብቻ ነበረች ”
“ እና “ ከዚያ አይጫካ ከተባለው ቦታ ሁልጊዜ ታየው ነበር ?”

“ ከዚያና ከሆሊጆን ቤት ብዙ ጊዜ አየው ነበር "

“ ቶርን ብለህ አነጋግረኸው ታውቃለህ ?

“ ሁለት ሦስት ጊዜ ቶርን ብዬ ስጠራው መልሶልኛል " እኔ ስሙ መሰለኝ እንጂ
እኔ የሽፋን ስም ነው ብዬ አልጠረጠርኩም "ኦትዌይ ቤቴልና ሎክስሌይም
በዚሁ ስም ይጠሩት ነበር“ በተለይ ሉክስሌይ ከዱሩ ተለይቶ ስለማያውቅ • ቶርን
ስለ መሆኑ በሚግባ የሚያውቀው ይመስለኝ ነበር

“ ሌላስ ማን ያቀሙ ነበር ?
"ሟቹ ሚስተር ሆሊጆንም ቶርንን ከቤቱ እንዲመጣበት እንደማይፈልግ ለአፊ ሲነግራት ሰምቻለሁ።
“ቶርን ጋር የሚተዋወቁ ሌሎችስ ነበሩ ?”
“ ትልቅ እህቷ ጆይስ የምታወቀው መሰለኝ ከሁሎ የበለጠ የሚያውቀው ግን ሪቻርድ ሔር ነበር „”

ዳኛው ሪቻርድ ሔር የልጁን ስም ሲሰማ ግብሩ ከነመልኩ በዐይነ ሕሊናው
መጣበትና ከመቀመጫው እንዳለ ፊቱን ኮሶ አስመሰለው "

“ ቶርን ወደ ጫካው ይመላለስበት የነበረው ምክንያቱ ምን ነበር ?

“ አፊን በወዳጅነት ይዟት ነበር " "

“ ሊያገባት ሐሳብ ነበረው ?

“የዚህ ሐሳብ እንኳን የነበረው አልመሰለኝም ”
ሆሊጆን የተገደለ ዕለት አይተኸው ነበር ?

ሆሊጆን የተገደለ እለት አይተኸው ነበር?

የዚያን ዕለት እኔ ራሴም በዚያ አካባቢ ስላልነበርኩ አላየሁትም „”

“ግድያውን የፈጸመው እሱ ይሆናል ብለህ ጠርጥረህ ነበር ?”

"ኧረ በጭራሽ ! ሪቻርድ ሔር በወንጀሉ ተከሰሰበት እኔም አልገደለም የሚል ጥርጣሬ አልነበረኝም ”

“ ይኸ ከሆነ ስንት ዓመት ይሆናል ? አለ ሚስተር ሩቢኒ አቋርጦ ምስክር
ነቱ ያበቃ መስሎት

“ አንድ ዐሥራ ሁለት ዓመት ይሆናል ያውም ባይበልጥ ”
ታዲያ ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ' ያ ሰው ፍራንሲዝ ቪስን ለመሆኑ ምለህ
ማረጋግጥ ትችላለህ ?

“ የሱን ማንነት የራሴን ማነት ያህል ስለማውቍው
ማረጋገጥ እችላለሁ

“ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስተ ዛሬ አንድም ጊዜ ሳታየው
እንዴት አሁን ልታውቀው ትችላለህ ? እንዲህ ያለ ምስክርም አላየንም

“ በመኻሉ አይተኸው ታውቃለህ ? አለ ዳኛው "

“ ሚስተር ሆሊጆን ከተገደለ ከአሥራ ስምንት ወር በኋላ በአጋጣሚ ለንደን ላይ አይቸዋለሁ ”

“ ያን ጊዜ ስታየው ቶርን ነበር ወይስ ሌቪሰን የመስለህ ?

ቶርን ነው እንጂ !አሁን ለሕዝብ እንደራሴነት ሲወጻደር እኮ ነው ሌቪስን መሆኑን ያወኩት።

አፍሮዳይቴ ሆሊጆንን ጥራ ” አለ ዳኛው "

ሴትዮዋ ይዟት በመጣው ፖሊስ ተደግፋ ገባች እሷ የምስክርነት ቃሏን ከመስጠቷ በፊት ሚስተር ኤበንዘር ጄምስ ከችሎቱ አዳራሽ እንዲወጣ ሚስተር ቦል ፍርድ ቤቱን ጠየቀ " ለዚሁም የራሱ የሆነ ምክንያት ነበረው "

ስምሽ ማነው ?”
"አፊ ” አለች ጀርባዋን ወደ ፍራንሲዝ ሌቬሰንና ወደ ኦትዌይ ቤቴል አድርጋ።

ሙሉ ስምሽን ” አለ ዳኛዉ"
“ አፍሮዳይቴ ሆሊጆን " ስሜን ሁላችሁም ታውቁታላችሁ የማይረቡ ጥያዎችን መጠየቅ ምን ጥቅም አለው ?

“ መስካሪቱን አስምላት " አለ ጀስቲስ ሔር "

የመጀመሪያ ቃሉን መናገሩ
ነበር "

" እኔ አልምልም ”
“ መማል አለብሽ” አለ ጀስቲስ ሔር ።
“ እኔ ምንም ቢሆን አልምልም ብያለሁ „”
“ እንግዲያሙስ ፍርድ ቤቱን በመድፈር ወሀኒ ቤት ትላኪያለሽ” አላት " ከተናግረ ወደ ኋላ እንደማይል ካነጋግሩ ገባትና ደነገጠች "
ሰር ጆን ዶቢዶም ተጨመረና “ትሰሚያለሽ ' ሴትዮ ' በአባትሽ መጠደል
ያንቺም እጅ አለበት እንዴ ?

“ እኔ !” አለች በቁጣና በድንጋጤ ከገነፈለው ስሜቷ ጋር እየተናነቀች ደ
“ እንዴት እንደዚህ የመሰለ ተግቢ ያልሆነ ጥያቄ እጠየቃለሁ ? እሱ ለራሱ ደግ አባት ነበር ” አለች እንባዋ እየተናነቃት “ ሕይወቱን በሕይወቴ ለውጨም ባዳንኩት ”

“ የሱን ገዳይ ለፍርድ ለማቅረብ የሚረዳውን ምስክርነት ለመስጠት ግን ፈቃደኛ አይደለሽም ”

“ እኔ እምቢ አላልኩም " እንዲያውም ያባቴ አጥፊ ሲሰቀል ለማየት እፈልጋለሁ " እ እናንተ የማይሆን የማይሆን ጥያቄ ካልጠየቃችሁኝ እምላለሁ” አለች ቅር እያላት " ለመማል ያልፈለገችው ዋሽታ ለመመስከር አስባ ስለ ነበር ነው " ኋላ ግን በግድ ማለች። መሓላንም ትፈራ ስለ ነበር እውነቱን ለመናግር ተገደደች

“ በዚያ ዘመን ካፒቴን ቶርን የሚባል ሰው ሁልጊዜ እየመጣ ትገናኙ ነበር »
እንዴት ተዋወቅሺው ?”

“ይኽው የፈራሁትን ነገር ጀመራችሁ " እሱ በነገሩ የለበትም አልገደለም ”
"የተጠየቅሺውን ለመመለስ ነው የማልሺው » ከዚህ ሰውዬ ጋር እንዴት
ተዋወቃችሁ ?”

“ አንድ ቀን ወደ ዌስት ሊን ሔጄ በነበረ ጊዜ አንድ ብስኩት ቤት ተግናኘን”

“ ሲያይሽ በውበትሽ ተማረከና ፍቅር ያዘው ?”

የውበቷ ነገር ሲነሣ ያሰበችውን ጥንቃቄ ሁሉ ረሳችው " “ አዎን” አለች
ክፍሉን በፈገግታ እየቃኘች "

“ ከዚያ በኋላ የት እንደምትኖሪ ነገርሺውና ማታ ማታ ፈረሱን እየጋለበ
መምጣት ጀመረ ”

“ አዎን ታዲያ ይኽ ምን አለበት

"እሱስ ምንም የለበትም ”
አላት ተዝናንታ እንድትመልስለት የፈለገው ጠበቃ" “እንዲያውም መታደል ነው » ምነው እኔም እንደሱ በታደልኩ"

ያን ጊዜ ሌቪሰን ሲባል ነበር የምታቂሙ ???

የለም ካፒቴን ቶርን እንደሚባል ነገረኝና እኔም አመንኩት ”

“ የሚኖርበትን ቦታ ታውቂው ነበር?”

ለጊዜው ስዌንስን ያረፈ መሰለኝ እንጂ እኔም ጠይቄ እሱም ነግሮኝ አያውቅም

“ እንዴ ለመሆኑ እንዴት ያለ ቆንጆ የራስ መሸፈኛ ነው ያጠለቅሺው ?
ሲላት መችም የነበራት የመወደድ ፍላጎት ላሥር ሴቶች ይበቃ ነበርና በደስታሞተች " አንዱ ትልቁ ድክመቷ ይኸው ነበር " የተመሰገነውን መሸፈኛ በዕይኗ
ጠቀስ አድርጋ አይታ ሙሉ በሙሉ ከሚስተር ቦል መዳፍ ገባች "
👍22
“ ከእሱ ጋር ከተዋወቅሽ በኋላ ምን ያህል ጊዜ ቆይተሽ ነበር ትክክላኛ
ስሙን ያወኞሺው ?

ከብዙ ወሮች በኋላ ነው „

"ከግድያው በኋላ ነው አይደለም ?

" አዎን የትና የት ቆይቶ ነው „

" በግድያው ጊዜ ከካፒቴን ቶርን ሌላ በዚያ አካባቢ እነማን ነበሩ ?

“ ሪቻርድ ሔር ኦትዌይ ቤቴልና ሎክስሌይ ነበሩ " ሕዝቡ እስኪስባሰብ ድረስ እነዚህን ብቻ ነበር ያየሁ ”

“ሎክስሌይና ኦትዌይ ቤቴልም እንደዚያኞቹ የውበትሽ ሰማዕታት ነበሩ ?”

“ ኧረ የለም ” አለች ራሷን በቁጣ ነቅንቃ “እነዚህኮ እየተሽሎከለኩ አውሬ የሚያድኑ ሌቦች ናቸው ‥

“ ያን ለት ማታ ከቤት አብሮሽ ያመሸው ቶርን ነበር ወይስ ሪቻርድ ሔር ?”

አፊ የዚህ ጥያቄ መልስ ወዴት አንደሚያመራ እያሰበች ጥቂት ስታመነታ እውነት ለመናገር መማልሺን አትርሺ ምስክር " አብሮሽ የነበረው ሰው ሪቻርድ ሔር ከሆነም ተናገሪ " መወላወል ግን የለም” አለ ጀስቲስ ሔር "

አፊ እንደ መደን?ጥ ብላ ! “ቶርን ነበር” አለች "

“ ሪቻርድስ የት ነበር ?

“ እንጃ መምጣቱን መጥቶ ነበር ግን አላስገባሁትም " መልሼ ሰደድኩት ምናልባት ከጫካው ሲንገዋለል ያመሸ ይመስለኛል ”
አንቺ ዘንድ ጠብመንጃ ትቶ ነበር ?”

“ አዎን ለአባቴ ሊያውሰው የነበረ ጠብመንጃ ነበር " ተቀበልኩና በስተውስጥ ከመዝጊያው ሥር አኖርኩት " ጥይት መጉረሱንም ነግሮኝ ነበር ”

ከዚያ ኣባትሽ መጥቶ ጫወታችሁን ያቋረጣችሁት ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ነበር ?”

“ አርሱ አላቋረጠንም እንዲያውም አባቴን ያየሁት ከሞተ በኋላ ነበር ።”

“ እስከ መጨረሻው ድረስ ከቤት አልነበራችሁም ?”

“አልነበርንም ! አየር ለመቀበል ከቤቱ በስተኋላ አድርገን ወደ ዱሩ ወጣን"

ከዚያ ትንሽ እንደ ቆየን ካፒቴን ቶርን ተሰናብቶኝ ሲመለስ እኔ ከዚያው ቆየሁ ”

“ እሺ ከዚያ በኋላሳ ጠብመንጃ ሲተኮስ ሰማሽ ?”

“ አንድ ጉቶ ላይ ዐረፍ ብዬ እንዳለ ተኩስ ሰማሁ " እኔ ግን ከቤት ይሆናል ብዬ ባለመጠርጠሬ ከቁም, ነገር አልጻፍኩትም ”

“ ከካፒቴን ቶርን ጋር አብራችሁ ስትወጡ ከቤት የተወው ነገር ነበር ?

ስንወጣ ጊዜው ሞቃት ነበርና ባርኔጣውን ከቤት ትቶት ወጣ እንጂ ሌላ ምንም አልተወም …”

ሪቻርድ አባትሽን እንደ ገደለው ካፒቴን ቶርን በደንብ ነበር የነገረሽ ?”

“ ስለዚህ ነገር ምንም ነጋሪ አላስፈለገኝም " እኔው ዐውቄው ነበር " ሁሉም ዐውቆት ነበር "

“ ካፒቴን ቶርን ሲተኩስ አይቶት ነበር ? ማየቱን ነገረሽ ?”

“ ባርኔጣውን አንሥቶ ሔደና ጥቂት ራቅ እንዳለ ሰዎች ከቤት ውስጥ ሲጪቃጨቁ ሰማ " የአንደኛው ድምፅ የአባቴ መሆኑን ዐወቀው " ወዲያው ጥይት ተተኮሰ " ምን እንደሆነ ባያውቅም አንድ ነገር እንደ ደረሰ በግምት ገባው ‥‥

« መቸም ይህን ሁሉ የነገረሽ ቶርን ነው " ምንጊዜ ነበር የነገረሽ ?
የዚያኑ ዕለት ማታ በጣም ቆየት ብሎ ”
"እንዴት ተገናኛችሁ ?

አመነታች " ነገር ግን የተጠየቀችውን ቀጥታ መመለስ እንዳለባት ስለተነገራት “አንድ ልጅ ከቤት ድረስ መጥቶ ከውጭ ሰው
እንደሚፈልገኝ ነገረኝና
ብወጣ እሱን ከዱር አገኘሁት ልጁን ወደኔ የላከው ግማሽ ሽልንግ ከፍሎ ነበር " ሽብሩ ስለ ምን እንደነበር ጠየቀኝና ሪቻርድ ሔር አባቴን እንደ ገደለው ነገርኩት
እሱም ሲጨቃጨቁ ከነበሩት አንዱ ሪቻርድ መሆኑን በድምፅ ለይቶት እንደ ነበር ነገረኝ …”

“ እስረኛው ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ተመልከችው " ቶርን ትይው የነበረው እሱ ነው ?

“ አዎን ታዲያኮ ይኸ ስለ ግድያው ተጠያቂ አያደርገውም ”

“ የለም እሱስ አያደርገውም ለንደን ላይ ከካፒቴን ቶርን ጋር ለምን ያህል
ጊዜ ቆየሽ ?

አፊ አይኗን አፍጥጣ ዝም አለች።

"ከግድያው በኋላ ከዚህ ቦታ የሔድሽው ከካፒቴን ቶርን ጋር ለንደን ላይ ለመግናኘት ነበር እዚያ ሔደሽ ከሱ ጋር ምን ያህል ጊዜ ቆየሽ ?”

አፊ መልስ ላለመስጠትም ለመካድም ሞከረች ክው
ብላለች!

“ምለሽኮ ነው የምትመሰክሪው ሴትዮ ! ከቶርን ጋር ነበርሽ? ወይስ
ከሪቻርድ ሔር ? መልስ ስጭ ” አለ ሰብላቢው ፥

“ ከቶርን ጋር ነበርኩ ” ከብዙ ማመንታት በኋላ አመነች "

“ ምን ያህል ጊዜ ቆየሽ ? ሁለት ወይስ ሦስት ዓመት ?”

“ሦስትስ አይሞላም ” አለች

“ ከሁለት ዓመት ግን ይበልጣል አይደለም ?”

“ ታዲያ ምናለበት? በለንደን ለመቀመጥ ፈልጌ ብሔድና እሱም የቀድሞ ጓደኛዬ ስለሆነ አንዳንድ ቀን ጧት ብቅ እያለ ቢጠይቀኝ ለሌላው ሰው ምኑ ነው
ጥፋቱስ ምንድነው ?

“ ምንም ጉዳት የለውም
እንዳልሺው አንዳንድ ጊዜ ጧት ጧት ይጠይቐሽ
በነበረ ጊዜ ሌቪሰን መሆኑን ታውቂ ነበር ?”

“አዎ ካፒቴን ሌቪሰን መሆኑን ዐውቅ ነበር "

“ “ቶርን” የሚለውን ስም ለምን አንደ ፈለገው ነግሮሽ ያውቃል '

"እሱ እንደ ነገረኝ ካፉ ስለ ገባለት ብቻ ነበር " ስዊሰን በተገናኘን ጊዜ እውነተኛ ስሙን ሊነግረኝ ደስ ስለ አላለው ይህ ስም መጣለት ነገረኝ እሱም ለሁል ጊዜ እንዲጠራበት ሌሎችም እንዲሰሙበት አይፈልግም ነበር "

ሚስ አፌ ለጊዜው ያለኝ ይኸው ነው " ኤበንዘር ጀምስ እንዲገባ እፈልጋለሁ


💫ይቀጥላል💫
👍16