አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


..መርቪንም ‹‹ጌታዬ፣ ሰላም ልሎት ነው የመጣሁት፡፡ እርስዎን በአካል ማግኘት መቻሌ ክብር ይሰማኛል›› አላቸው ከሰውነት ጎዳና የወጡትን ሰው፡፡
ሃርትማን ጥንቃቄ ሳይለያቸው እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉ፡፡ናንሲ የመርቪን ባህሪ በአንድ ጊዜ መለወጡ አስደንቋታል፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ባህሪውን እንዳየችው ከሆነ በዓለም ላይ ከሱ በላይ ሰው እንደሌለ አድርጎ የሚገምት ሰው ነበር፡፡ አሁን ግን ያየችው ባህሪ እንደየቤዝቦል ጨዋታ ኮከብ ተጫዋችን የአድናቂነት ፊርማ እንዲፈርምሉት
የሚለማመጥ አንድ ተማሪን ነው ያስታወሳት.

መርቪንም ‹‹ከእዚያ ማጥ ውስጥ ወጥተው በዓይኔ በብረቱ ማየቴ ደስ
ብሎኛል፡ አዩ ጠፉ ሲባል እኛ ክፉ ነገር ደርሶባቸዋል ብለን ነበር የገመትነው በነገራችን ላይ እኔ መርቪን
ላቭሴይ እባላለሁ›› አላቸው:

‹‹ይሄ ጓደኛዬ ባሮን ጋቦን ይባላል፡ በህይወት እንዳመልጥ የረዳኝ እሱ
ነው አሉ ሃርትማንም።

መርቪንም ሁለቱንም ለስንብት ጨበጠና ‹‹ከዚህ በላይ አልረብሻችሁም
ናንሲ ከጥቂት ደቂቃ በፊት የተከሰተው ነገር ገርሟት የሚስቱን እግር በእግር መከታተል ተግባር ለደቂቃዎችም ቢሆን ያዘናጉት ሃርትማን
የተባሉት ሰው ታዋቂ ሰው ሳይሆኑ አይቀርም ስትል አስበችና ‹‹ማናቸው እኒህ ሰው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ፕሮፌሰር ካርል ሃርትማን በዓለም ታዋቂው የፊዚክስ ሳይንቲስት›› አላት፡ ‹‹አቶምን ለሁለት ለመሰንጠቅ በሚደረገው ምርምር ላይ የሚሰሩ
ሰው ነበሩ፡፡ ከናዚዎች ጋር የፖለቲካ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው ስለነበር
ዓለም በሙሉ ከአፈር ተደባልቀዋል ብሎ ነው የገመተው አላት
‹‹ዩኒቨርሲቲ እያለሁ ፊዚክስ ነበር የማጠናው፡፡ በዚያ ጊዜ ሳይንቲስት ለመሆን ነበር ምኞቴ፡፡ ግን ለዚህ ዓይነት ስራ ትዕግስት አልነበረኝም: ይሁን እንጂ በዚህ መስክ አልተውኩም፡፡ ታዲያ በዚህ የሳይንስ ዘርፍ ላለፉት አስር ዓመታት አስደናቂ የሚደረጉትን ግስጋሴዎች መከታተል
ግኝቶች ተገኝተዋል፡፡››

‹‹ለምሳሌ?›› ስትል ጠየቀች ናንሲ፡

‹‹ሊዝ ሜይትነር የምትባል ኦስትሪያዊት ሳይንቲስት ከናዚዎች አምልጣ
በኮፐንሄገን በስደት የምትኖር ተጠቃሽ ናት፡፡ እሷም በምርምር ስራዋ
የዩራኒየምን አተም ባሪየምና ክሪፕተን ወደተባሉ ትንንሽ አተሞች መከፋፈል
ችላለች፡፡››

‹‹አተሞች የማይከፋፈሉ ነበር የሚመስለኝ›› አለች ናንሲ፡

‹‹እስከቅርብ ጊዜ እኛም እንዲህ ነበር የሚመስለን፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ራበሳይንስ ትልቅ ግስጋሴ ተደረገ ማለት ነው፡፡
ለዚህም ነው የወታደራዊው መስክ ይህን የሳይንስ ውጤት በእጅጉ የሚፈለገው፡፡ ስለዚህ የዚህን ሂደት መቆጣጠር ከቻሉ በዓለም ከፍተኛ የማጥፋት ኃይል ያለውን ቦምብ መስራት ቻሉ ማለት ነው፡››

ናንሲ እንደ ቆቅ የሚደነብሩትንና ሰውን ሁሉ በፍርሃት የሚመለከቱትን እኒህን ሰው አንገቷን አዙራ አየት አደረገቻቸው፡፡ ‹‹እንዲህ ያሉ ሰው ያለ ጠባቂ ብቻቸውን እንዲሄዱ እንዴት እንደፈቀዱ የሚገርም ነው!›› አለች።

‹‹ብቻቸውን ናቸው ብዬ አልገምትም›› አለ መርቪን እዚያ ፈንጠር ብሎ የቆመውን ሰው ተመልከቺ፡፡,

የመርቪንን የግምባር ጥቅሻ ተከትላ ከመንገዱ ባሻገር አይኗን አማተረች፡ ሌላ ረጅም ቆብ የደፋና
ሙሉ ልብስ ከነሰደርያው የለበሰ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ ተመለከተች፡:

‹‹ይህ ሰው የሳይንቲስቱ ጠባቂ ነው ብለህ ትገምታለህ?››

መርቪን ትከሻውን ነቀነቀና
‹‹ነጭ ለባሽ ይመስላል፡፡ ሃርትማን የሚጠበቁ መሆናቸውን አያውቁም ይሆናል፡፡ ሆኖም ጠባቂ ሳይኖራቸው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ›› አላት፡

hዚህ ቀደም መርቪን ያን ያክል ነገሮችን ይከታተላል ብላ አትገምትም ነበር፡፡

‹‹ቡና ቤቱ ይሄ ሳይሆን አይቀርም›› አለ መርቪን የውይይታቸውን ርዕስ ለውጦ፡፡ በኋላም በሩጋ ደርሶ ቆመ።

‹‹መልካም ዕድል›› አለችው ናንሲ ከልቧ፡ አናዳጅ ባህሪ ቢኖረውም ሰውየውን እየወደደችው እንደመጣች አሰበች፡፡

ፈገግ አለና ‹‹አመሰግናለሁ ላንቺም መልካም ዕድል እመኝልሻለሁ›› አላትና እሱ ወደ ቡና ቤቱ ሲገባ እሷ መንገዱን ይዛ ነጎደች።

ህንጻው ውስጥ አንድ ወጣት የፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኛ ወዳለበት እንደነገሩ የተሰራ ቢሮ አየችና ወደ እሱ ሄደች፡
‹‹ወደ ኒውዮርክ ነው የምሄደው ቲኬት ብትሰጠኝ›› አለች፡
‹‹ቲኬት ፈልገው ነው? አልቋል›› አላት

ናንሲ ለወጣቱ ፈገግ አለችለት፡፡ ፈገግ ማለት የቢሮክራሲውን ማነቆ
ሊያለዝብ የሚችልበት ጊዜ አለ፡፡

‹‹አየህ የኔ ወንድም፤ ቲኬት ማለት ብጣሽ ወረቀት ነው›› አለችው
‹የቲኬቱን ዋጋ ልስጥህና አይሮፕላኑ ላይ ጫነኝ አይመስልህም?››

እሱም በፈገግታ ጥርሱን ብልጭ አደረገ፡ የሚችል ከሆነ እንደሚረዳት
ገመተች፡፡

‹‹አይሮፕላኑ ሙሉ ባይሆን እጭንዎት ነበር›› አላት፡፡

“ምን አይነት ነገር ነው! ስትል አጉተመተመች፡ ሰማይ የተደፋባት መሰላት፡፡ እስካሁን የደከመችው እንዲያው ነው እንዴ! ሆኖም ገና እጇን አልሰጠችም፡፡ በፍጹም ተስፋ መቁረጥ የለባትም፡፡

‹‹አንድ የሆነ ነገር መኖር አለበት›› አለች፡፡ ለመኝታ የሚሆን ቦታ ባይኖርም ግዴለም መቀመጫ ላይ እተኛለሁ፡፡ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች
ወንበር ቢሆንም ግድ የለኝም››
‹‹የሰራተኛ ወንበር ላይ ተሳፋሪ እንዲቀመጥ አይፈቀድም አንድ ያልተያዘ ቦታ ያለው የሙሽሮች ክፍል ብቻ ነው።
‹‹እሱን ቦታ ትሰጡኛላችሁ?›› ስትል ጠየቀች ተስፋዋ ለምልሞ
‹‹ምን ችግር አለ፤ ዋጋው ስንት እንደሆነ አላውቅም እንጂ››
‹‹እባክህ ጠይቅልኝ›› አለችው አስተዛዝና፡

‹‹ምናልባትም የሁለት መቀመጫ ዋጋ ሳይኖረው አይቀርም፡፡ ማለትም
ሰባት መቶ ሃምሳ ዶላር የመሄጃ ብቻ፡፡ ምናልባትም ይበልጥ ይሆናል› አላት፡፡

ናንሲ ዋጋው ሰባት ሺ አምስት መቶ ዶላር ቢሆን ግድ የላትም፡፡ ‹‹ባዶ ቼክ እሰጥሃለሁ የፈለከውን ዋጋ መሙላት እንድትችል›› አለች በጉጉት ‹‹ነገ ኒውዮርክ መድረስ የምፈልግበት ብርቱ ጉዳይ አለብኝ›› አለች
የምትሄድበትን ጉዳይ ለመግለጽ ከዚህ የተሻለ አባባል አጥታ፡

‹‹እስቲ ካፒቴኑን ልጠይቅ›› አለ ወጣቱ ‹‹ከኔ ጋር ይምጡ፣ የኔ እመቤት››

ናንሲ የመወሰን ስልጣን የሌለው ሰው ጥረቴን ሁሉ መና ያስቀርብኝ
ይሆን ብላ እየሰጋች ሰውየውን ተከተለችው ምን ምርጫ አላት፡

አንድ ፎቅ ላይ የሚገኝ ቢሮ ውስጥ ገቡ፡፡ ቢሮው ውስጥ ሲጋራ እያጨሱና ቡና እየጠጡ የአየር ጠባይ ሁኔታ ቻርት ይዘው የሚወያዩ ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑ የአዘቦት ልብሳቸውን የለበሱ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች አሉ፡፡ ወጣቱ ሰራተኛም ናንሲን የአይሮፕላኑ ካፒቴን መርቪን ቤከር ጋ ወስዶ አቀረባት፡

ወጣቱ ሰው ‹‹ካፒቴን ወይዘሮ ሌኔሃን ወደ ኒውዮርክ የሚያስኬደኝ
ብርቱ ጉዳይ ስላለኝ የሙሽሮችን ክፍል ዋጋ ከፍዬም ቢሆን እሄዳለሁ እያሉ ነው፡፡ እንውሰዳቸው?›› ሲል ጠየቀ፡

ናንሲ የካፒቴኑን መልስ በጉጉት ጠበቀች፡፡ ካፒቴኑም ‹‹ወይዘሮ ሌኔሃን
ባለቤትሽ አብሮሽ አለ?›› ሲል ጠየቃት፡

‹‹ባለቤቴ ሞቷል ካፒቴን››
👍102👎1😁1
‹‹ይቅርታ የኔ እመቤት፡፡ ሻንጣ ይዘሻል?››
‹‹ይሄ ትራቭሊንግ ባግ ብቻ ነው ያለኝ››
‹‹እንወስድሻለን ወይዘሮ ሌኔሃን››
‹‹እግዜር ይስጥህ ካፒቴን›› አለች ናንሲ በደስታ እየተርበተበተች፡
‹‹ይሄ ጉዞ ለእኔ ምን ያህል ጠቃሚዬ እንደሆነ መግለጽ ይከብደኛል፡››
ናንሲ በደስታ እግሮቿ ሊከዷት ምንም አልቀራቸውም ያገኘችው
ወንበር ላይ ዘፍ አለች። ነፍሷን ስትገዛ በስሜት እንዲህ መሆኗ አሳፈራት፡
መርበትበቷን እንዳያውቁባት ቦርሳዋ
በረበረችና ቼኳን መዛ እጇ እየተንቀጠቀጠ ባዶ ቼክ ፈርማ ለወጣቱ ሰጠችው፡፡
አሁን ፒተርን ፊት ለፊት የምትጋፈጥበት ጊዜ ደረሰ፡፡
መንደሩ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ናቸው የሚታዩት የተቀረው ተሳፋሪ
የት ደረሰ?›› ስትል ጠየቀች

‹‹አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች ቡና ቤት ናቸው›› ሲል መለሰ ወጣቱ። ቡና
ቤቱ እዚሁ ህንፃ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ መግቢያው በጎን በኩል ነው፡፡››

ናንሲ ተነስታ ቆመች: አሁን ድንጋጤው ለቋታል፡፡

‹‹የኔ ልጅ እግዚአብሔር ውለታህን ይክፈልህ››

‹‹እኔም እርስዎን መርዳት መቻሌ ደስ ብሎኛል›› አለ ወጣቱ ሰው፡፡

በበሩ ስትወጣ ክፍሉ ውስጥ ያሉት ሰራተኞች ባዶ ቼክ ላይ የምትፈርም የምታምር ሴት እያሉ በነገር ሲሸነቁጧት ሰማች፡፡ ናንሲ ወደ ውጭ ስትወጣ ደከም ያለ ጸሃይና ለስለስ ያለ አየር ተቀበላት፡፡ አየሩ ከባህሩ
በሚወጣ ጨዋማ መዓዛ ታውዷል፡፡ አሁን እምነተ ቢሱን ወንድሟንልትገጥም ነው፡

ከዚያም በህንጻው ጎን ሄዳ ቡና ቤት ውስጥ ዘው አለች፡፡ ቡና ቤቱ እሷ
የምትገባበት ዓይነት አይደለም፡፡ ትንሽ ጨለምለም ያለ፣ ወምበሮቹና ጠረጴዛዎቹ ተራ፣ ወንዶች ብቻ የሚዝናኑበት ዓይነት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ቡና ቤቱ
ለዓሳ አጥማጆችና ለገበሬዎች ቢራ መጠጫነት ነበር የሚሆነው፡፡ አሁን ግን
ኮክቴል በሚጠጡ ሚሊየነሮች ከጥግ እስከ ጥግ ተሞልቷል፡፡ አየሩ በሰዎች ትንፋሽ የታፈነና ሁካታ የበዛበት ነው፡፡ የሚነገረው ቋንቋ የተለያየ ሲሆን ተሳፋሪዎቹ ፌሽታ እያደረጉ ይመስላል፡፡ ምናልባትም ተሳፋሪዎቹ አብረው የሚዝናኑ በውቅያኖስ ላይ ረጅም ጉዞ ስለሚጠብቃቸው ይሆናል፡፡

ቡና ቤቱ ውስጥ ያለውን ሰው ሁሉ በዓይኗ ስታማትር ፒተርን አየችው፡፡ እሱ ግን አላያትም፡፡ በቁጣ ሰውነቷ እየነደደ ለተወሰኑ ሰከንዶች
አፈጠጠችበት፡፡ ጉንጮቿ በንዴት ቲማቲም መስለዋል፡ ፊቱን በጥፊ አጩይው! አጩይው! አላት፡፡ ሆኖም ንዴቷን በሆዷ አምቃ በጥፊ
ከመጠፍጠፍ ተቆጠበች፡፡ የተናደደችበት መሆኗን እንዲያውቅ አልፈለገችም፡፡
ሁልጊዜም አንድን ነገር ረጋ ብሎ ማስኬድ እንዳለባት ታውቃለች፡፡

የተቀመጠው ጥግ ላይ ሲሆን አብሮት ናት ሪጅዌይ አለ፡፡ ይሄ ደግሞ ድንጋጤ ውስጥ ጥሏታል፡፡ ናት የጫማ ናሙናዎች ለመሰብሰብ ፓሪስ
እንዳለ ነው የምታውቀው፡፡ ከፒተር ጋር ወደ አሜሪካ አብሮ ይበራል ብላ
አልጠበቀችም፡፡ ናት እዚህ ቦታ ባይኖር በወደደች፡፡ የቀድሞ ፍቅረኛ እንደዚህ
ያለ ግጭት ላይ ከተገኘ ነገሮች ይዛባሉ ከዚህ በፊት ፍቅረኛዋ መሆኑን ከአዕምሮዋ ፋቀች፡፡

ቡና ቤቱ ውስጥ የተገጠገጠውን ሰው ገፋ ገፋ እያደረገች ፒተርና ናት
ያሉበት ጠረጴዛ ጋ ደረሰች፡፡ ናት ነው መጀመሪያ ያያት፡፡ እንዳያት ፊቱ ላይ
ያየችው ድንጋጤና የጥፋተኛነት ስሜት አንጀቷን ቅቤ አጠጣው፡፡ የናትን
ዕይታ ተከትሎ ፒተር ቀና ሲል እሱም አያት፡፡ የፒተር ፊት በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ‹‹የአምላክ ያለህ!›› አለ ከመቀመጫው ተነስቶ፡ ሁነቱ የፈጠረበት ድንጋጤ የሚነገር አይደለም፡፡

‹ምን አስደነገጠህ ፒተር?›› አለች ናንሲ ሆዷ በደስታ እየሞቀ፡፡

ፒተር ምራቁን ዋጠና ተመልሶ ወምበሩ ላይ ዘፍ አለ፡፡

ናንሲም ‹‹እንደማትጓዝበት እያወቅህ በመርከብ ለመጓዝ ቲኬት አዴልፊ ሆቴል ተመዘገብክ፡፡ ይህን ሁሉ የምታደርገው በፓን አሜሪን ገዝተሃል። ከኔ ጋር ሊቨርፑል ድረስ መጥተህ፣ እንደማታርፍበተ እያወቅህ
አይሮፕላን እንደምትበር እንዳላውቅብህ ነው፡፡››

ፒተር ፊቱ በድንጋጤ አመድ እንደመሰለ በጸጥታ እህቱን ዓይን ዓይኗን ያያል

ንግግር ለማድረግ የተዘጋጀች ባትሆንም ቃላቱ ሁሉ እየተከታተሉ
ከአንደበቷ ይወጡ ጀመር፡ ‹‹ትናንት እኔ የማላውቀው መስሎህ ከሆቴሉ ሹክክ ብለህ ወጥተህ ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ሄድክ፡፡›› ጠረጴዛውን ደገፍ
ስትል ፒተር በደመነፍስ ሽምቅቅ አለ፡፡
‹‹ምንድነው የሚያስፈራህ?
አልነክስህምl›› ስትለው ከምር እንደምትነክሰው ሁሉ ወደ ኋላው አፈገፈገ፡፡

ጮክ ብላ ስትናገር ድምጿን ቡና ቤቱ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ ይሰማል ብላ አልተጨነቀችም፡ ሰዉ ጸጥ ረጭ ብሎ ያዳምጣል፡ ፒተር በበኩሉ በእፍረት ዙሪያ ገባውን ይገረምማል፡

‹‹ላንተ ካደረኩልህ አንጻር ያንተ ጅልነት አያስደንቀኝም፡፡ ጥፋቶችህን ሰው እንዳያውቅብህ እድሜህን በሙሉ ስጠብቅህ ኖርኩ፡፡ የአንድ ባዛር ስራ እንኳን ለማስተባበር አቅም እንደሌለህ እያወቅሁ ነው የኩባንያውን ኃላፊነት
የለቀቅሁልህ፡ ይህን ሁሉ አድርጌልህም ንግዱን ከእጄ ፈልቅቀህ ለማውጣት
ጉድጓድ ከመማስ አልቦዘንክም፡፡ እንዴት ይህን ግፍ በኔ ላይ ትፈጽማለህ?
እንደ ትል ውስጥ ውስጡን መሹለክለክህ ለምንድነው?›› አለች ናንሲ

ፒተር ፊቱ በድንጋጤ እንደገረጣ ‹‹እኔን ከክፉ ነገር ስትጠብቂኝ
አልነበረም፡፡ ሁልጊዜም የራስሽን ጥቅም ስትጠብቂ ነው የኖርሽው›› አለ
‹‹ሁልጊዜም የበላይ ለመሆን ትፈልጊያለሽ ነገር ግን ኃላፊነቱን አላገኘሽም፡፡
ከዚያ ወዲህ ቦታውን ከኔ ለመውሰድ እንቅልፍ አጥተሽ ትፍጨረጨሪያለሽ፡››

ፒተር የተናገረው ተገቢ ባለመሆኑ መሳቅ ይሁን ማልቀስ ወይም ፊቱ
ላይ መትፋት ይሻል እንደሆን አላወቀችም፡፡

‹‹አንተ ደደብ ከኃላፊነት እንድትነሳ ሳይሆን ኃላፊነቱን እንደያዝክ
እንድትቆይ ሳልም ነበር፤ አንተ አይገባህም እንጂ፡፡››

ፒተር ከኪሱ ወረቀት አወጣና በድል አድራጊነት ‹‹እንደዚህ ያለ?››
አላት፡

ናንሲ እሷ የጻፈችው ሪፖርት መሆኑን አወቀችና ‹‹ታዲያ ይሄ ልክ አይደለም ትላለህ?›› አለች ይህ ዕቅድ እኮ በስራህ ላይ የሚያቆይህ ዕቅድ ነው

‹‹አንቺ የኃላፊነቱን ቦታ ወስደሽ ነዋ! እውነቱን ወዲያው ነበር ያወቅሁት፡፡ ስለዚህ የራሴን መፍትሄ ፈጠርኩ››

Uነገር ግን ‹መፍትሄ ያልከው ነገር አልሰራም አለች ናንሲ በድል አድራጊነት፡፡ ‹‹የአይሮፕላን ቲኬት ስለገዛሁ ለቦርዱ ስብሰባ እደርሳለሁ››
አለች ለመጀመሪያ ጊዜ በጸጥታ የወንድምና እህቱን ክርክር ወደሚያደምጠው ናት ሪጅዌይ ዞር አለችና ‹‹የብላክ ጫማዎች ኩባንያን እጅህ ለማስገባት
ትቋምጣለህ እንጂ አታገኘውም፡፡ ሲያምርህ ይቅር ናት›› አለችው:

‹‹ሁሉም ነገር እጅሽ እንደገባ አታስቢ›› አላት ፒተር፡ ይህን ሲል ባንድ
ነገር እርግጠኛ የሆነ ይመስላል፡ ፒተር እሷ የማታውቀው ነገር ለማድረግ አውጥቶ አውርዶ የማቀድ ችሎታ እንደሌለው ታውቃለች፡፡

‹‹እኔና አንተ እያንዳንዳችን አርባ በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ይዘናል፡፡ቲሊና ዳኒ ሪሌይ የቀረውን አስር አስር በመቶ አክሲዮኖች ይዘዋል፡ ሁለቱ የእኔን ፈለግ ተከታዮች ናቸው፡፡ እኔና አንተ ምን አይነት አቅም እንዳለን ልቅም አድርገው ያውቃሉ፡፡ ለአባባ ታማኝነት ለማሳየት ቢፈልጉም አንተ
ኩባንያውን እንዳከሰርክ እኔ ደግሞ አትራፊ እንዳደረኩት ያውቃሉ፡ ለኔ ድምጽ ስጡኝ ብል አያሳፍሩኝም››

‹‹ሪሌይ ለኔ ነው ድምፅ የሚሰጠው›› አለ ፒተር ፈርጠም ብሎ፡

ናንሲ የፒተር ልበ ሙሉ አነጋገር ጥርጣሬ ውስጥ ጣላት ‹‹ኩባንያውን
ድምጽ ገደል እየጨመርከው
ለምንድነው ላንተ
እንደሆነ እያወቀ
የሚሰጠው?›› አለች በንቀት፡፡ ሆኖም የውስጧ ጥርጣሬ እንደ ድምጿ
ጠንካራ እንዳልሆነ ልቦናዋ አውቋል፡
👍14
ፒተር ስጋቷን አወቀና ‹‹ፈራሽ አይደል?›› አላት በንቀት በተራው፡ ናንሲ መፍራቷ እውነት ነው፡፡ በምትናገረው ነገር ሙሉ እምነት እንደሌላት እየተሰማት ነው፡፡ እሱም የልብ ልብ እያገኘ መጥቷል፡ ከፒተር ጉራ በስተጀርባ ምን እንዳለ ማወቅ ሊኖርባት ነው፡፡

‹‹ያልተጨበጠ ነገር ነው የምታወራው›› አለች በፌዝ፡፡

‹‹አይደለም›› አለ ኮራ ብሎ፡፡

በዚህ አይነት ልታውጣጣው ብትሞክር የተናገረው ስህተት ለመሆኑ
የመልስ ምት እንደማይኖራት ናንሲ ታውቃለች፡፡

‹‹ሁልጊዜ አንድ የተደበቀ ምስጢር እንዳለ ታስመስላለህ። ነገር ግን
አንድም ቀን ተግባራዊ አድርገኸው አታውቅም››
‹‹ሪሌይ ለኔ ድምጽ እንደሚሰጠኝ ቃል ገብቶልኛል››
‹‹ሪሌይ ለኔ ታማኝ ነው›› አለችው ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ
ፒተር አልለቀቃትም ‹‹ማበረታቻ ካገኘስ?››
ይሄ ነው ለካ የፒተርን ልብ እንዲህ ያሳበጠው አለች ናንሲ በሃሳቧ ዳኒ ሪሌይ ጉቦ በልቷል፡፡ አሁን የምር ጭንቅ ጭንቅ አላት፡ ራሊይ እልም ያለ ሙሰኛ ስለሆነ ጉቦ ከመብላት እንደማይመልስ ታውቃለች፡፡ ፒተር ምን ቢሰጠው ነው ሪሌይ እንደዚህ የተንበረከከለት?› ይህን ማወቅ አለባት፡ ይህን
ጉቦ ሳይበላው ከአፉ ትነጥቀዋለች ወይም ፒተር ከሰጠው የበለጠ ጉቦ
ታቀርብለታለች፡:.....

ይቀጥላል
👍102
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አራት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ..መርቪንም ‹‹ጌታዬ፣ ሰላም ልሎት ነው የመጣሁት፡፡ እርስዎን በአካል ማግኘት መቻሌ ክብር ይሰማኛል›› አላቸው ከሰውነት ጎዳና የወጡትን ሰው፡፡ ሃርትማን ጥንቃቄ ሳይለያቸው እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉ፡፡ናንሲ የመርቪን ባህሪ በአንድ ጊዜ መለወጡ አስደንቋታል፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ባህሪውን እንዳየችው ከሆነ በዓለም…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


“ቶርን” የሚለውን ስም ለምን አንደ ፈለገው ነግሮሽ ያውቃል '

"እሱ እንደ ነገረኝ ካፉ ስለ ገባለት ብቻ ነበር " ስዊሰን በተገናኘን ጊዜ እውነተኛ ስሙን ሊነግረኝ ደስ ስለ አላለው ይህ ስም መጣለት ነገረኝ እሱም ለሁል ጊዜ እንዲጠራበት ሌሎችም እንዲሰሙበት አይፈልግም ነበር "

ሚስ አፌ ለጊዜው ያለኝ ይኸው ነው " ኤበንዘር ጀምስ እንዲገባ እፈልጋለሁ።

ኧቤንዘር ጀምስ ገብቶ የአፊን ቦታ ያዘ "ግድያው ከተፈጸመ ከአሥራ ስምነት ወሮች በኋላ ቶርንን ለንደን ላይ እንዳየኸው ለፍርድ ቤቱ ገልጸሃል” ብሎደ ጀመረ ጠበቃው ቦል “ ይኸም አፊ ሆሊጆን አብራው የነበረችበት ጊዜ መሆን
አለበት እሷንም አይተሃት
ነበር?።

ኤቤንር ጀምስ ዐይኖቹን አፈጠጠ "አፊ ምን ብላ እንደ መስከረች አላወቀም
እሷ ከቶርን ጋር እንደ ነበረች ከዚያ በፊት ለማንም ተናግሮት አያውቅም
እንዴት ሊታወቅ እንደቻለ ገረመው ።

" አፊን ?

“አዎን አፊን አይተሃት ነበር ወይ?” አለ ጠበቃው ኮስተር ብሎ - “ ከዌስት ሊን ስትጠፋ ሪቻርድ ሔርን ተከትላ ሔዳ ነው ተብሎ ተወርቶ ነበር“ እሷ ግን
ሪቻርድን ሳይሆን ቶርንን ፍለጋ እንደሔደች ፍርድ ቤቱ ዐውቋል " ስለዚህ
አንተ ቶርንን ባገኘኸው ጊዜ እሷንም አይተሃት ነበር ወይ ? ነው የምልህ ''

“አዎን አይቻታለሁ እንዲያውም በመጀመሪያ ያየሁት እሷን ነበር ”

“ እስኪ ሁኔታውን ለፍርድ ቤቱ አስረዳው ”

“አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ እዛው ለንደን ፖዲንግተን ከሚባለው ቦታ በመንገድ ሳልፍ አንዲት ሴት ወደ ቤት ስትገባ አየሁ " አፊ ሆሊጆን ነበረች እሷም አየችኝና ሻይ ጋበዘችኝ " እንግዳ ስለሚመጣባት በሁለት ሰዓት መውጣት አንዳለብኝ ነግራኝ ነበር ስለ ዌስት ሊን እሷ ስትወጣ የወጣሁ ስለሆነ አዲስ ነገር
ነግራትም - እየተጫወትን የተባለው ስዓት ደርሶ ወጣሁ " ከውጭ በር ስድረስ ቶርን በሠረገላ መጥቶ ሲገባ አየሁት "

“ታድያ አፊ የኮበለችው ከሪቻርድ ሔር ነው መባሉን እያወቅህ ወደ ዌስት ሊን እንደ ተመለስክ ለምን አልተናገርክም ?”

“መጀመሪያ ይህን ነገር መናገር የኔ ተግባር አይደለም አፊ ደግሞ ' አይቻታለሁ ብዬ ለማንም እንዳልናገር ቃል አስገብታኝ ስለ ነበር ለማንም አልተናገርኩም ”

“ ቆይ ” አለ ሚስተር ሩቢኒ ምስክሩ ሊወጣ ሲል “ ስዓቱ ከምሽቱ ሁለት
ሰዓት አንደ ነበር ተናግረሃል "ጨልሞ ነበር ?”

"አዎን ”

"ታድያ ከሠረገላ ወርዳ ወደ ቤት የገባው ቶርን መሆኑን እንዴት ልታረጋግጥ ቻልክ ?”

“በደንብ አረጋግጫለሁ " ከሠረገላ ከወረደበት ላይ የጋዝ መብራት ስለ ነበር
ልክ በፀሐይ ብርሃን የማየውን ያህል አድርጌ አይቸዋለሁ " ከዚህም ሌላ ድምፁን አውቀዋለሁ " የትም ቢሆን በድምፁና በቀለበቱ ብቻ በሚገባ ልለየው እችለሁ "
ደማቁ ቀለበቱ በመብራቱ ሲፍለቀለቅ አይቸዋለሁ …”

ድምፁንስ በምን ስማኸው? አነጋግሮህ ነበር ?

« ከኔ ሳይሆን ከባለ ሠረገላው ጋር ሲነጋገር ሰምቸዋለሁ " በመካከላቸው
አንድ ክርክር ነበር " ሰውዬው ኻያ ደቂቃ ሙሎ ከመንገድ ካስጠበቀው በኋላ የሰጠው ግን እንደማይበቃው ቅሬታውን ገለጸለት ቶርንም ጥቂት ከተጨቃጨቁ በኋላ አንድ ሽልንግ ተጨማሪ ወረወረለት።

ከኧቤንዘር ጄምሰ ቀጥሎ የሟቹ የሰር ፒተር ሌሺሰን ባልደራስ የነበረ አንድ
ሰው ተጠራ“ እሱም ሆሊጆን በተገደለበት ዘመን ወደ በጋው መጨረሻ ሲል ፍራንሲዝ ሌሺስን ስር ፒተርን ለመጠየቅ መጥቶ መስንበቱን መሰከረ እዚያም ሲሰነብት ብዙ ጊዜ በተለይ ወደ ማታ ሲሆን የዌስት ሊንን አቅጣጫ ይዞ በፈረሱ ይሔድና ሦስት ወይም አራት ስዓት ያህል ቆይቶ ፈረሱ ላብ በላብ እስኪሆን ድረስ እየጋለበ ይመለስ እንደ ነበር ጨምሮ አስረዳ ከሚስተር ሌቪሰን ኪስ የወደቀ ሁለት ደብዳቤዎች በተለዩ ጊዜያት አግኝቶ እንደ ስጠው ገለጸ " የሁለቱም ደብዳቤዎች አድራሻ • ለካፒቴን ቶርን ሲል የፖስታ ቤት ምልክት አልነበራቸውም
ከተቀባዩ ስም በቀር በፖስታዎቹ ላይ ምንም ነገር አልተጻፈባቸውም ጽሕፈቱ የሴት ይመስል ነበር " ምስክሩ ተጠይቆ በሰጠው ማብራሪያ የሆሊጆን መገደል ዳር እስከ ዳር ትልቅና አስደንጋጭ ዜና ሆኖ እንደሰነበተ በደንብ ማስታወሱንና ፍራንሲዝ ሌቪሰንም ሰር ፒተር ዘንድ ቆይታውን ጨርሶ ወደ ለንደን መመለሱን ተናገረ ።

እንዴት ያለ የማስታወስ ችሎታ አለህ ! አለና ሩብኒ አፌዘበት "

ምስክሩ ሞግስ ያለው ከባድ ሰው ነበር በርግጥ ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንደነበረው ራሱም አልሸሸገም በተለይ ግን ሚስተር ሌቪስን ሆሊጆን እንደ ተገደለ ከዚያ አካባቢ በመልቀቁና ሌሎችም አብረው የተከሠቱ አንዳንድ ነገሮች ከአእምሮው መቀረጸቸውን ገለጸ "

“ ምን ምን ነገሮች ናቸው? አለ ፍርድ ቤቱ "

“አንድ ቀን ሰር ፒተር የፈረሶችን ጋጣ እየዞሩ ሲያዩ ሚስተር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ትንሽ ቀን እንዲሰነብት አጥብቀው ቢጠይቁት ባልታሰበ ጉዳይ ወደ ለንደን መጠራቱን ነገራቸው እነሱ ሲነጋገሩ ሠረገላ ነጂው እየቃተተ መጣና የዌስት ሊኑ
ሆሊጆን በሪቻርድ ሔር መገደሉን ተናገረ “ ሰር ፒተር በድንተኛ አደጋ ካልሆነ በቀር ሆነ ተብሎ የተደረገ ነው ብለው ሊያምኑ እደማይችሉ መናገራቸውን አስታውሳለሁ

ሚስተር ሌቪሰን መሔድ እንዳለበት ከነገራቸው በኋላ አንድ ዐሥር ፓውንድ እንዲሰጡት ጠየቃቸው - እሳቸውም ትናንቱን ጧት ስለ ስጡት አምሳ ፓውንድ በቁጣ ሲጠይቁት የአንድ ጓደኛው መኮንን ዕዳ ስለ ነበረበት በፖስታ እንደ ላከለት ነገራቸው እሳቸው ግን የትም ሲያብድ ካላባከነው በቀር ለሰጠው ምክንያት ማዋሎን ማመን አልቻሉም » በዚህ ጊዜ ግራ የመጋባት ምልክት ታየበት " የኔጌታ ለጊዜ ቶሎ ቢቆጡም ከለመንዋቸው ልባቸው አይጠናም ነበር እንደ ሴት ምልስ ባይ ነበሩ " በርግጥ በዐይኔ አላየሁም ' ግን የጠየቃቸውን ገንዘብ ሳይሰጡት የቀሩ አልመሰለኝም " ሚስተር ሌቪዞን የዚያን ለት ሌሊት ወደ ለንደን ሔደ።

የመጨረሻው ምስክር ሚስተር ዲል ነበር " ባለፈው ማክስኞ ማታ ሚስተር ቦሻ ቤት ቆይቶ ሲመለስ ከሚስተር ጆስቲስ ቤት ፊት ለፊት አንድ ጭቅጭቅ ሰማ የነገሩ መነሻ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንና ኦትዌይ ቤቴል ድንገት መግናኘት
ኖሯል " ቤቴል ለምን እንደሚያርቀው ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ሲወቅሰው ያኛው
ስለሱ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለና ለማወቅም እንደማይፈልግ ነገረው "
.
ሆሊጆን የተግደለ ዕለት ማታ ግን ' ስለኔ አንድ ነገር በማወቅህ ደስ ብሎህ
ነበር " ሰመሆኑ ላሰቅልሀ እችል እንደ ነበር ታስታውሳለህ አንዲት ትንሽ ቃል ብናግርብህ በዲክ ሔር ቦታ ልትቆም ትችል እንደ ነበር ዘነጋኸው? አሁን ያ ሁሎ አለፈና አላውቅህም ትለኛለህ ? አለው »

“አንተ ከብት አለው ሰር ፍራንሲዝ ፡ “ የራስህን አንገት ከሸምቀቆ ሴታስገባ ልታሰቅለኝ እንደማትችል ጠፋህ ? ያፍ መዝጊያ ገንዘብ አልተቀበልክም
ይግሞ እንድጨምርልህ ትፌልጋህ ?

“ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምነው ያንን የተረገመ አምሳ ፓውንድ ስቀበልህ እጆቼ
በረገፉ እያልኩ ነው የኖርኩት " ለጊዜው ግራ ግብቶኝ • የማደርገው ጠፍቶኝ ሳለ ባታግኘኝ ኖሮ አልነካልህም ነበር ልጃቸውን ከመሰቀል የሚያድኑበትን ምስጢር
ደብቁ በመያዜ እስከዛሬ ድረስ የሚስዝ ሔርን ፊት ማየት አልቻልኰም ”

“በሱ ገመድ ራስህን ለማስገባት " አለና አሾፈበት ሰር ፍራንሲዝ።

“የለም አንተን ለማስገባት ”
👍19
“እሱ ሊሆን ይችላል" ነገር ግን እኔ ወደ ባለወግ (ፍርድ ፈጻሚ) ስሔድ አንተ
ነጥለህ አትቀርም " ይቅርታም ማምለጫም እንደማይኖርህ ታውቀዋለህ

ንትርኩ ረጂም ቢሆንም ፍሬ ነገሩ ይኸው ነበር ዲል ተጀምሮ እስኪጨረስ
አዳምጦታል ለፍርድ ቤቱም አንድ ባንድ መልሶ ተናገረው ሩቢኒ “ሕጋዊ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም ፤ተራ አሎባልታ ነው” ብሎ አመለከተ።

ፍርድ ቤቱ ግን ማንም እየመጣ ምን መሥራት እንዳለበት እንዲነግረው የማይፈልግ መሆኑን ነግሮ ዝም አሰኘው "

ኮሎኔል ቤቴል ' አንገቱን ወደፊት አስግጎ የሚስተር ዲልን ምስክርነት ሲያዳምጥ ከቆየ በኋላ ፊቱ ተለዋወጠ አልተሳሳትክም ? አንደኛው ተናጋሪ ኦትዌይ ቤቴል መሆኑን እርግጠኛ ነህ ? አለው።

ሚስተር ዲል አንቱን ነቀነቀ “ያልሆነውን ሰው እሱ ነው ብዬ'ምዬ የምመስክር ሰው ነው ተብዬ እገመታለሁ ? እኔም ምነው ባልሰማሁት ብዬ አዝኛለሁ ።

ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መቃ የመሳሰሉ ጣቶቹንና ያልማዝ ቀለበቱን እያሳየ
ሲንቀባረር ቆየ " ምናልባት አፊን በማስኮብለል ካልሆነ በቀር በነፍስ ግዳይ
የሚጠየቅ አልመሰለውም የሚስተር ዲል ምስክርነት ከተሰማ በኋ ነገሩ ባንድ
ጊዜ ተለወጠ » ሲጀነን የነበረው ኩምሽሽ አለ ኩራቱ ቀረና በአስጨናቂ ፍርሃት ተዋጠ "

ችሎቱ ሊፈጸም ሲቃረብ'“ አሁን ክቡር ፍርድ ቤቱ ለሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን
የዋስ መብታቸውን አንዲያስጠብቅላቸው እለምናለሁ ” አለ ሩቢኒ =
ዳኞቹ እርስ በርሳቸው ተያዩ
“ ክቡራን ዳኞች ... በስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ደረጃ ለሚገኝ ታላቅ መኮንን
እንዲህ ያለውን መብት አይከለክልም ”

ፍርድ ቤቱ እንደዚያ ያለ የድፍረት ጥያቄ ቀርቦለት እንደማያውቅ በማሰብ :
ይህን በመሰለ ወንጀል ለተከስሰ ሰው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቀርበው ቢጠይቁም በዋስ ሊያስለቅቁት እንደማይችሉ ገልጾ ጥያቄውን ውድቅ
አደረገው

ኦትዌይ ቤቴል ግን ከኮሎኔሉ ጀምሮ ማንም ሊዋሰው እንደማይችል ገምቶ ምንም አልጠየቀም " ስለዚህ ሁለቱም በጆርጅ ሆሊጆን ግድያ ፍርዳቸውን አስኪያገኙ ድረስ በማረፊያ ቤት እንዲቆዬ በየነባቸው "

አፊ ቃሏን ከሰጠች በኋላ ሌላ ክፍል እንድትቆይ ተደረገ " እሷም ችሉቱ
እስኪያበቃ ወደ ለንደን ሔዳ ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር መቀመጧን ስለማመኗ
ጉዳይ የዌስት ሊን ሕዝብ ምን እንደሚላት ስታወጣ ስታወርድ ቆየች " በመረጨሻ ግን ማንም ስለዚህ ነገር ሊነቅፋት ቢሞክር ልክ ልኩን እየነገረች እንደምታሳርፈው በማስብ ደመደመች " ችሎቱ እስኪያበቃ ከተወሰነላት ክፍል ቆየች።

ችሎቱ አበቃ " ሚስተር ቦልን ሲወጣ አገኘችው " እንደሚታወሰው ጠበቃው
ወንደላጤ ነበር " አጅሪት ደግሞ ዐይኗን ስለ ጣለችበት ሚስተር ጂፍንን አስተማማኝ መጠባበቂያ አድርጋ የተሻለ ዕድል ቢያጋጥማት ታሻትር ነበር።

ስለዚህ ቀደም ብላ ዐይኖቿን ጥላበት ወደ ነበረው ጠበቃ እየተቅለስለሰች ጠጋ ብላ ' “በመጨረሻ ምን ተባለ ? አለችው "

ሁለቱም በነፍስ መግደል ተመስክሮባቸዋል " ከአንድ ሰዓት በኋላ ወደ ሊንበራ ይሔዳሉ ”

“ ሁለት ንጹሐን ይኸን በመሰለ ክስ መወንጀል አሳፋሪ ነገር ነው አለች "

“ ይኸን አስተሳሰብሺን ከአእምሮሽ ቶሎ ብታወጭ ይሻላል " የሌቪሰን ወንጀለኝነት በሚገባ ተረጋግጧል " ከዚህ በላይ ደግሞ ሁለቱ እርስ በርሳቸው ተወነጃጅለዋል “ወረበሎች እርስ በርሳቸው ሲጣሉ ሐቀኞች የጃቸውን ያገኛሉ' ብሎ ተረተላትና የራሳቸውን ወንጀለኝነት ሲያጋልጡ የሪቻርድንም ንጹሕነት እንዳረጋገጡ ገለጸላት

አንቺም ለቶርን የሰጠሺውን ሚና የተጫወተው ሪቻርድ ሔር ነው "ከዳሩ ሆኖ ተኰስ ሰማ "ከዚያ ቶርንን ደንግጦ እየተርበተበተ ሲሮጥ አየው
ምንም አትጠራጠሪ • አባትሽን የገደለው ቶርን ነው” አላት "

አፊ ዐይኖቿ ስልምልም ፡ ጭልምልም አሉ ፤ ራሷ ዞረ ልቧን አጥወለወላት "
አንድ ጊዜ የጣር ጩኽት ጮኽችና ዝልፍልፍ ብላ ወደቀች አፊ በአንድ
ጀንበር ሁለት ጊዜ ነፍሷን ሳተች "

እስረኞቹ ወደ ሊንበራ ሊወሰዱ ሲንቀሳቀሱ በተለይ ፍራንሲዝ ሌቪሰንን
ከሕዝቡ ቁጣ የሚጠብቅ ከፍተኛ የጥበቃ ኃይል †መደበ " እሱም የሕዝቡን
ጩኽት ፉጨትና እርግማን ሲሰማ አረንዴው ጥምቀት የሚደገም ወይም
ትንሽ በትንሽ እያሉ እየቦጫጨቁ የሚጥሉት መሰለውና ከፍራቱ የተነሣ ዐመድ የመሰለውን ፊቱን ሸፍኖ እየተንቀጠቀጠ መሬት ከፍታ ብትውጠው ተመኘ ''....


💫ይቀጥላል💫
👍15
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ አንድ (21)


«ሲሻለኝ ከሁለት ሣምንት በኋላ ቦስተን ነበርኩ ... ቦስተን ነበር እምትኖረው ወደመኖሪያ ቤቷ ሄድኩ ። ግን ማንም አልነበረም… ምንም አልነበረም ። እቃዋም ፤ ስእሎቹም ተሰርቀው ደረስኩ ። ሰአሊ ነበረች.. ነርሶች ናቸው አሉ የ...የወ...የሰረቋቸው ስእሎቿን...» ዝምታ ሆነ ። ለረጅም ጊዜ ሁለቱም ፀጥ ብለው ተቀመጡ ከዚያ ቀጠለ

«የቀረ ነገር አልነበረም ። የለም እኔም ውስጥ ማለቴ ነው›› አለ። ይህን ብሎ ቀና ሲል የዌንዲ ፊት በእንባ ርሶ ተመለከተ። «ማይክል በጣም አሳዛኝ ነገር ነው። ይህ ስለደረሰብህ በጣም አዝናለሁ» አለች እግዜር ያጥናህ እንደማለት ነበረና ማጥናኛውን እራሱን በማወዛወዝ ተቀበለ። ቀጥሎ ለአንድ ዓመት ያህል እምቢ ያለው እንባ ፈሰሰ ፤ አለቀሰ ። ዌንዲን እቅፍ ሲያደርጋት የእንባ ዘለላዎች ፊቴን እያቋረጡ ወደ አንገቱ ፈሰሱ።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

«ማይክ የካንሳስ ሲቲውን ፕሮጀክት ስለምትመራው ሴትዮ ምን አስተያየት አለህ ... ማለት ..» አለች ዌንዲ ታውንሴንድ። ማይክልና ዌንዲ እዌንዲ ቤት በስተጀርባ ባለችው አትክክልት ቦታ ነበሩ ። በታጣፊ ወንበር ላይ ተቀምጦ የእሁድን ጋዜጣ ይመለከት ነበረና ቀና ብላ አየችው ። ሁለቱም የዋና ልብስ ለብሰው የኒውዮርክን ፀሐይ ይጠጣሉ ። «ስለ ሴትዮዋ» አለች ወሬ የመቀጠል ሙከራዋን ። አልሰማትም ። እጋዜጣው ላይ አፍጥጧል ። ጋዜጣውንም እንደማያነበው ዌንዲ ታውቃለች ። « ማይክ»
«እ ? ምን አልሺኝ››
«ስለ ካንሳሷ ሴትዮ እየጠየቅኩህ ነበረ » መልስ አልሰጣትም ። እንደገና ሀሳብ ውስጥ ገባ ።ሙከራዋ ሁሉ ተስፋ የሌለው ነገር እንደሆነ ገብቷታል ። በመረበሽና በብስጭት አይን አየችው ።
«ዊስኪውን ልጨምርልህ? » አለች።
«እ?አ...አዎን።ወደ ቢሮ መሄድ ይኖርብኛል መሰል» አለና በሷ ላይ አሳልፎ አይኑን እሆነ ባዶ ላይ ተከለ ።
«ግሩም ድንቅ ሀሳብ ነው» አሎች በፌዝ።
«ምን ማለትሽ ነው ?» አሁን ያያት ጀመረ ። እንዲያ ሲያያት እፊቷ ላይ እንግዳ ነገር አየባት ።ምን እንደሆነ ሳያውቀው ሀሳቡ ተከፈለ ። ጥቂት ቢያጤናት ኖሮ እፈቷ ላይ ያየውን ነገር ትርገም ሊያገኘው ይችል ነበር።
«ምንም» አለች›› ምን ለማለት ነው ሲል የጠየቃትን እየመለሰች ። «ዊንዲ ልንግባባ ያስፈልጋል ። ቢሮ መሄድ እንዳለብኝ ልትረጂልኝ ይገባል። የሳንፍራንሲስኮው የሕክምና ማእከል ብዙ ጉልበት ይጠይቃል። ነጭ ላብ እስኪወጣኝ መስራት አለብኝ ማለት ነው በሚቀጥሉት ሁለት አመቶች። ባገሪቱ ውስጥ ካሉት ትልቅ ፕሮጀክቶች አንዱ እንደሆነ ታውቂያለሽ ፤አይደለም ?»
«ምን ምክንያት መደርደር ያስፈልጋል? ማለት ይህ የምትለው ሥራ ባይኖርም ሌላ ነገር መፍጠርህ አይቀርም ነበር ። ዝም ብለህ የመሰለህን ማድረግ ትችል የለም እንዴ »
«እንዲያም ታልሽ ደግ። እኔ የጠላሁት ይህን የመስሪያ ቤት ፊርማ ይመስል በዚህ ሰዓት ወጣህ ፤በዚህ ገባህ የምትይውን 'ነገር ነው» አለና ጋዜጣወን አሸቀንጥሮ ጥሎ አፈጣጠባት። ይህን ስታይ መጨስ ጀመረች። «ፊርማ ?ማነው ፈራሚው ?አንተ? ለመሆኑ ትናንት በስንት ሰዓት እንደመጣህ ታውቃለህ ? ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ተኩል። እኔደሞ ሰው ነህ ብዬ የሰው የራት ግብዣ ተቀብዬ እዚህ ስንቃቃ ማምሸቴ። ለእራት ትደርሳለህ የተባልከው ሰው ለመኝታም አልሆነልህ ። ብቻ ጥፋተኛዋ እራሴ ነኝ። ዝም ብዬ መሄድ ነበረብኝ!»
«እኮ! እዚህ ቁጭ ብለሽ እንድትጠብቂኝ የገባሽው ውል አለ እንዴ ?»
«ውልስ የለም ። ግን አጋጣሚ ሆነና ፍቅር ያዘኝ ካንተ… ግን ይች ልጅ ፍቅር ይዟታል ። ትጎዳለች መውደድ ይቅር ፤ ይህ ያህል ማሰብ እንኳ አትችልም። ምን ሆንክ ማይክል ? ምን ነካህ ከቢሮህ ብቅ ስትል አንገትህ ውስጥ ሸምቀቆ ሊያስገባ ያጠመመደ ሰው አለ አሉህ ?ወይስ ከሷም ጋር ፍቅር ይይዝሀል የሚል ልብህን አስፈራው? ፍቅር ይህን ያህል አስፈሪ ነገር ነውን››

«እንዲህ ደርሰሽ ተራ ነገር አትሁኝ ዌንዲ ። ሥራዬን ታውቂያለሽ ። ከማንም ሰው የበለጠ ታውቂያለሽ ስለዚህ እንዲህ አትበይኝ»
«ስራህን ስለማውቀውና ሥራ ብለህ ቢሮ ከምትቆይበት ጊዜ ቢያንስ ግማሹ ዝም ብሎ፤ ዋጋ ቢስ እንደሆነ ስለሚገባኝማ ነው እምነግርህ ። አንተ ስራህን ለስራነቱ ሳይሆን መደበቂያ አድርገኸዋል ። ከሕይወት የምትደበቀው በስራህ ነው። እኔን ለመሸሽ የምታመካኘው በስራህ ነው ። እራስህን ለመሸወድ ምክንያትህ ስራህ ነው በቃ» አለች ። በሀሳቧ ስለናንሲ ላለማሰብ መሸሺያህ ስራህ ነው ብላ ጨመረች።

«ይኸ እዚህ ግባ የማይሉት አስቂኝ ወሬ ነው፤ ዌንዲ» ይህን ብሎ ከታጣፊው ሸራ ወንበር ላይ ተነስቶ ባትክልቶቹ መካከል በድንጋይ ንጣፍ በተሰራው የእግር መንገድ ላይ በባዶ እግሩ ወዲያ ወዲህ ይል ጀመረ ። የድንጋዩ ግለት ተሰማው።

ወሩ መስከረም የበልግ ወራት መባቻ ቢሆንም የኒውዮርክ ፀሐይ ጋብ አላለም ። ማይክልና ዌንዲ የተገናኙት ባለፈው የፀደይ ወራት መዳፊያ ላይ ሲሆን ለጥቂት ሳምንት ፍቅራቸው ግሎ በደስታ ሲዋኙ ከቆዩ በኋላ ያን ሁኔታ መቀጠል ሳይችሉ ቀሩ። ሙሉውን በጋ እንዲሁ ቅጥ አምባሩ የጠፋው ኑሮ በመኖር አሳልፈው እዚህ ደርሰዋል ። ማይክል ወደ ቢሮ ይላል ። ዌንዲ ወደ መዝናኛ ። ዌንዲ አልቻለችም ። አንዲት ቅዳሜና እሁድ ሎንግ አይላንድ አካባቢ አብረው ሲያሳልፉ ሌላውን ጊዜ ግን ዌንዲ ስታዝን ፤ ስትበሳጭ ፤ ማይክል እቢሮው ውስጥ ስራውን በማከናወን ነው ያሳለፉት ።
«ደሞስ ሲጀመር ነግሬሽ የለምንዴ ? ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ ?»
«ነግረኸኛል ። ግን የነገርከኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ? ሁለተኛ ፍቅር የሚሉት ነገር ይዞህ የሆነ ያልሆነ ክፉ ነገር እንዳይገጥምህ ፤ ዳግም እንዳትጎዳ ስለምትፈራ ፍቅር እንዳይዝህ እንደምትጠነቀቅ ፤ ልታገባ እንደማትፈልግ ፤ ይህን ነገርኸኝ እንጂ መኖር እንደምትፈራ ነገርከኝ በስላሴ ? ስለሰው ማሰብ ፤ ሰው መሆን ይኸ እንደሚያስፈራህ ነገርከኝ ? ማይክል ብዙውን ጊዜህን ከማስመሪያህ ጋር ኮ ነው እምታሳልፈው! ምናልባት ለኔ፤፤ ሰው ለሆንኩት ሳይሆን ለዚያ እቃ የምትስማማ ፍጡር ሳትሆን አትቀርም
« እና?»

ይህን ያለበትን ድምፅ ስትሰማና ቀና ብላ ስታየው እፈቱ ላይ የተሳለውን ነገርም ስትመለከት መላ አካላቷን ዝፋት አንድ ነገር ስለተረዳች ፤ ስለሷ ምንም ግድ እንደሌለው ከስለገባት ። ጅል ብትሆን ነው ከሱ ጋር መኖሯ ። ጅል ብትሆን ነው ከሱ ጋር መኖር ይቻላል ብላ መገመቷ ። ግን ደግሞ ጅልነት ብቻም አይደል ። የምትወድለት ነገር አላት ። የምትወደውን አይለመዴነት ፤ የአራዊትነት ባህርይ ታይበታለች ። ይህ ብቻ ሳይሆን ስር የሰደደ ትካዜም ታይበታለች ። ቆስሏል ። የሚያክመው ፤ የሚጠግነው ይሻል ። ልትደርስለት እንደሚፈለግ እንደሚወደድ ልታሳየውም ትፈልጋለች ። እሷ ይህን ታስብ እንጂ እሱ ለምንም ነገር ደንታ የለውም ። ዌንዲ ናንሲ አይደለችማ! ይህን ደግሞ እሷም እሱም በሚገባ ያውቁታል ። ዌንዲ ይህን ስታስብ እንባዋ ቅርዝዝ አለ ። ቀስ ብላ ተነስታ ወደ ቤት ገባች ። በሸሽፋሎቿ ላይ ያጤዘውን እንባ እንዳያይባት ። ኩሽና ገብታ መጠጥ ቀዳች ። መጠጡን አስቀምጣ ዓይኗን ከድና ብደርስበት ፤ባገኘው እያለችና አካሏን እየገዘፋት ባለችበት ቆማ ቀረች ። ግን እንደሌለ ማንም ሊደርስበት እንደማይችል ማሰብ ጀምራ ነበረና አዎ ለማንም እጁን አይሰጥም ፤ ስትል ደመደመች ።
👍20
መጠጡን አንስታ በርከት እያደረገች ከተጎነጨችለት በኋላ ባዶውን ብርጭቆ እባንኮኒው ላይ ስታኖር መዳብማ ቀለም በያዘው ለስላሳ ቆዳዋ ላይ እጁ ቀስ ብሎ ሲሰፍ ተሰማት ። በየሳምንቱ እሁድ እጓሮዋ ቁጭ ብላ ፀሐይ ሲመታት ስለሚውል የቆዳዋ መልክ መዳብማ ሆኗል ። እንዲህ ከኋላዋ መጥቶ ሲዳብሳት ዝም ብላ ባለችበት ቆመች ። የገላው ግለት ተሰማት በጣም በጣም ፈለገችው ። ይህን ፍላጐቷን አስቀድሞ ማወቁን ብታውቅም ይህን ማወቋ ሰልችቷት ነበረና ። ልታስበው አቅም አጣች ። ብትችል ኖሮ ገላዋን መከልከል ነበረባት ። ብትችል ያን ለማድረግ ጊዜው አሁን ነበር ።
« ዌንዲ በጣም ታስፈልጊኛለሽ » አለ ። ቃሉን ስትሰማው መላ አካሏን ፍትወት አቅበጠበጣት ። ግን ደግሞ ይህ መሆኑ እንዳይታወቅባት ራሷን መቆጣጠሯም አልቀረም ። ፊቷን እንዳዞረች ፤ በጀርባዋ ላይ ቀስ እያሉ እየደባበሱ የሚወርዱትን እጆቹን ልስላሴ ጠላች ።
« እና ልበልሀ ቅድም አንተ እንዳልከው» አለች ። በጣም ታስፈልጊኛለሽ ላላት ስትመልስ ።
« ፍላጐቴን መቆጣጠር እንደማልችል ታውቂያለሽ ማለቴ ነው» አለ ። ድምጹ እንደገላው ልስልስ ያለና የላመ ነበር ።
«ማይክል የፍላጐቴ ግለት ሳይሆን ፍቅር ነው ። ዳሩ አንተ በፍቅርና በባዶ የፍላጐት ግለት መካከል ያለውሰን ልዩነት አታውቀውም ። ከሷም ጋር ሳለህ እንዲሁ ነበርክ ? » ይሀን ስትል የሚዳስሷት እጆች ቀጥ አሉ ። ክንዱም ጥንክር ሲል ተሰማት ። አደጋ አለ ። ሆኖም ራሷን ተቆጣጥራ ዝም ልትል አልቻለችም ። ልትጐዳውም ፈልጋለች ። «እሷንም ለማፍቀር ለመውደድ ትፈራ ነበር ? ዛሬ ማንንም መውደድ ስለሌለብሀ ፤ እሷን በማጣትህ የተነሣ በደረሰብህ ሀዘን ጀርባ ተከልለህ እንድትኖር ስለረዳህ ፤ ሞቷ ችግርህን ቀላል አድርጐልሀል ልበል ? የሷ ሞት ከፍርጃም ፤ ከንትርክም ነፃ አድርጐሃል ፤ አይደለም ? » ይህን ብላ ዞረችና ፊት ለፊት ተጋፈጠችው። በዓይኑ ውስጥ
የጥላቻ ጥንስስ ሲፈላ ተመለከተች ።


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍10
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

...‹‹ሪሌይ ለኔ ታማኝ ነው›› አለችው ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ
ፒተር አልለቀቃትም ‹‹ማበረታቻ ካገኘስ?››
ይሄ ነው ለካ የፒተርን ልብ እንዲህ ያሳበጠው አለች ናንሲ በሃሳቧ ዳኒ ሪሌይ ጉቦ በልቷል፡፡ አሁን የምር ጭንቅ ጭንቅ አላት፡ ራሊይ እልም ያለ ሙሰኛ ስለሆነ ጉቦ ከመብላት እንደማይመልስ ታውቃለች፡፡ ፒተር ምን ቢሰጠው ነው ሪሌይ እንደዚህ የተንበረከከለት?› ይህን ማወቅ አለባት፡ ይህን"
ጉቦ ሳይበላው ከአፉ ትነጥቀዋለች ወይም ፒተር ከሰጠው የበለጠ ጉቦ
ታቀርብለታለች፡
‹‹ዕቅድህ ዳኒ ሪሌይ ላይ ላንተ ባለው ታማኝነት ላይ የተንጠለጠለ
ከሆነ እኔን አያስጨንቀኝም›› አለችና በንቀት ሳቀችበት፡

‹‹አዎ ዕቅዴ ዳኒ ሪሌይ በሚሰጠኝ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ዳኒ
ምን ያህል ገንዘብ እንደሚወድ ታውቂ የለም›› አለ በድል አድራጊነት
መንፈስ፡፡

ናንሲ ወደ ናት ፊቷን አዞረችና ‹‹እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ይሄን እውነት ነው ብሎ መቀበል ይከብደኝ ነበር›› አለችው፡፡

‹‹ናት በዚህ በኩል ምንም ጥርጥር የለበትም›› አለ ፒተር ፈርጠም ብሎ፡፡

ናት በወንድምና እህቱ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባት ተቆጥቧል፡
ፒተር ቀጠለና ‹‹ናት ለሪሌይ ከጄኔራል ቴክስታይል ኩባንያው ጠቀም
ያለ የአክሲዮን ድርሻ ሊሰጠው ነው፡፡››

ፒተር በመጨረሻ የተናገረው ለናንሲ አቅል እንደሚያስት ምት ነበር፡
ናንሲ በንዴት ጉሮሮዋ ተዘግቶ መተንፈስ አቃታት፡፡ ለዳኒ ሪሌይ ጄኔራል
ቴክስታይልስን በመሰለ ግዙፍ ኩባንያ ውስጥ እግሩን ከመትከል በላይ
የሚያጓጓ ነገር አይኖርም፡፡ ኒውዮርክ ውስጥ ከሚገኝ ትንሽ የህግ ጥብቅና
ተቋም ጋር ሲነጻጸር ይሄ በሳህን የቀረበለት ስጦታ የዕድሜ ልክ ገቢ
የሚያስገኝ በመሆኑ ሪሌይ ይህን ስጦታ ላለመቀበል ወደ ኋላ አይልም፡፡
ሪሌይ እንደዚህ አይነት እጅ መንሻ ከቀረበለት እናቱን ከመሸጥ አይመለስም፡፡

የፒተር 40 በመቶና የሪሌይ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በድምሩ 50 በመቶ ነው፡፡ የናንሲ 40 በመቶ ከአክስታቸው 10 በመቶ ጋር ሲደመር እንደዚሁ ሃምሳ በመቶ ነው፡፡ ሆኖም የቦርድ አባላት ድምጽ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ አሸናፊውን ለመለየት የኩባንያው ኃላፊ (ሊቀመንበሩ)
የሚሰጠው ድምጽ ወሳኝነት አለው፡፡ የኩባንያው ኃላፊ ደግሞ ፒተር ነው፡

ፒተር ናንሲን መደፍጠጥ በመቻሉ በኩራት ፈገግ አለ፡፡

ናንሲ ገና እጇን አልሰጠችም፡ አጠገባቸው ያለውን ወንበር ሳበችና
ቁጭ አለች፡ ፊቷንም ወደ ናት አዞረች፡ ከወንድሟ ጋር ይህን ያህል ስትከራከር የእሷን አባባል እንዳልወደደ አውቃለች፡፡ ፒተር በድብቅ ነገር ሲጎነጉን ናት ያውቅ ነበር ስትል አሰበች፡፡ ስለዚህ ነገር ናትን ልትጠይቀው ወደደች፡

‹‹ፒተር የሚለው እውነት ይመስልሃል?››
በአንድ ወቅት ፍቅረኛው የነበረችው ሴት ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ እሷም በጸጥታ ምንም ሳትናገር ምላሹን ጠበቀች፡፡ በመጨረሻም የዓይኗን ፍጥጫ መቋቋም አቅቶት ‹‹እኔ አልጠየቅሁትም፡፡ ደግሞ በቤተሰባችሁ ጠብ ውስጥ
እኔን ምን ያገባኛል? እዚያው በጠበላችሁ፡ እኔ የንግድ ሰው እንጂ የእርዳታ
ድርጅት ሰራተኛ አይደለሁ›› አላት፡

‹‹ናት አንተ እውነተኛ የንግድ ሰው ነህ?

‹‹እንደሆንኩ ታውቂያለሽ›› አላት ፈርጠም ብሎ፡፡

‹‹ከሆንክ አንተ
እንደዚህ ያለ ሸፍጥ ቢፈጸምብህ ዝም ብለህ
ታልፋለህ?››

ናት ትንሽ አሰብ አደረገና ይሄ የአንድን ኩባንያ ባለቤትነት ለሌላ
የማዛወር ሂደት እንጂ የሻይ ግብዣ አይደለም›› አለ፡፡
ናት ብዙ ሊል ፈልጎ አቋረጠችውና በወንድሜ እምነተ ቢስነት
እጠቀማለሁ ብለህ አስበህ ከሆነ አንተም እምነተ ቢስ ነህ ማለት ነው የአባታችን ምክትል ሆነህ በመስራትህ
ነው ዛሬ እዚህ ደረጃ የደረስከው››አለችና ናት መልስ ከመስጠቱ በፊት ወደ ፒተር ዞረችና ‹‹ለሁለት ዓመት ያህል የኔ ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ብትረዳኝ አሁን
በመሸጥ ከምታገኘው እጥፍ እንደምታገኝ አታውቅም?›› አለችው::

‹‹ይሄን እቅድሽን አልቀበለውም፡፡››

‹‹ኩባንያው የአወቃቀር ለውጥ እንኳን ባይደረግበት በጦርነቱ ምክንያት
የአክሲዮን ዋጋው ሰማይ ሊነካ ይችላል፡ የወታደር ጫማ በማቅረብ በኩል
የሚስተካከለን የለም፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ብትገባ ደግሞ የምናገኘው ገቢ የትየሌለ ነው›› አለች፡፡

‹‹አሜሪካንን ደግሞ ጦርነቱ ውስጥ ምን ይጨምራታል?››

‹‹ባይሆንስ? አሁን አውሮፓ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት ብቻ እንኳን ለእኛ ንግድ ጥሩ ገቢ ያስገኝልናል›› አለችና ወደ ናት ዞር ብላ ‹‹ይሄን ታውቃለህ አይደለም? ለዚህ አይደል የእኛን ኩባንያ መግዛት
የምትፈልገው?›› ስትል አፋጠጠችው፡፡

ናት ምንም አልተነፈሰም፡፡

ቀጥሎ ወደ ወንድሟ ዞር ብላ ‹‹ትንሽ ብትቆይ ትልቅ ቢዝነስ ፊታችን ይጠብቀናል፡፡ አድምጠኝ ወንድምዬ፧ የምለው ሁሉ ስህተት ነው? የኔን
ምክር በመከተልህ የከሰርክበት ጊዜ አለ? የኔን ምክር ገሸሽ በማድረግህ
ደግሞ ገቢ ያገኘህበት ጊዜ አለ?›› ስትል በጥያቄ አጣደፈችው፡፡

‹‹አንቺ ምንም አይገባሽም›› አለ ፒተር፡፡

አሁን ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ አታውቅም፡፡

‹‹ምንድነው የማይገባኝ?››

“ለምን ኩባንያው ከናት ሪጅዌይ ኩባንያ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ጋር እንዲዋሃድ እንደፈለኩ? ለምን እንደዚህ እንደማደርግ አይገባሽም፡፡››

‹‹እሺ ለምንድነው?››
ፒተር አንድ ነገር ሳይተነፍስ ትክ ብሎ ተመለከታት፡፡ እሷም መልሱን
ከዓይኑ አይታ አገኘች::

ለእሷ ከፍተኛ ጥላቻ አለው፡:

በጣም ደነገጠች፡፡ ልክ ከማይታይ ግድግዳ ጋር የተጋጨች መሰላት፡
ይህን ሃቅ በእጅጉ ማመን አልፈለገችም:: ሆኖም ይህን በፊቱ ላይ ያየችውን
እንግዳ የሆነ የጭካኔ ገጽታ እንደሌለ አድርጋ መቀበል አስቸገራት፡፡ በታላቅና
በታናሽ መካከል ያለው ተፈጥሮአዊ ባላንጣነት ድሮም አለ፡፡ ይሄኛው ግን
ከዚያ ይለያል። ይሄ አስፈሪ፣ ለመግለጽ አስቸጋሪና እንግዳ የሆነ የጥላቻ
ገጽታ ነው፡፡ ይህን ከዚህ ቀደም ጠርጥራ አታውቅም፡፡ ታናሽ ወንድሟ
በጣም ይጠላታል፡ ልክ ከሆነ ነገር ጋር የተጋጨች ይመስል ደነዘዛት፡ ይን
እውነታ አምኖ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ይፈጃል።

ፒተር ጅል ወይም ስስታም ወይም ንፉግ ስለሆነ አይደለም ይህን
የሚያደርገው፡፡ እህቱን ለማጥፋት ሲል ራሱን ከመጉዳት አይመለስም፡ ይሄ ደግሞ የለየለት ጥላቻ ነው፡፡ ወንድሟ ትንሽ አዕምሮው ሳይነካ አይቀርም፡

ትንሽ ማሰብ ፈለገች፡ ንጹህ አየር ለማግኘት ብላ በጭስ ከታፈነው ቡና ቤት ወጣች፡ ከቡና ቤቱ እንደወጣች ቀለል አላት፡፡ ከባህር የሚወጣው ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበላት፡፡ መንገዱን አቋረጠችና ወደ ወደቡ ሄደች፡

የሰማይ በራሪው ጀልባ ወደቡ ጥግ ተኮፍሷል፡ አይሮፕላኑ ከጠበቀችው
በላይ ግዙፍ ነው፡፡ የአይሮፕላኑን ነዳጅ የሚሞሉት ሰዎች ከሩቅ ሲታዩ ጉንዳን ያካክላሉ፡፡ ግዙፎቹ ሞተሮች በአይሮፕላኑ ላይ እምነት እንድትጥል አድርገዋታል፡፡ በዚህ አይሮፕላን ላይ ፍርሃት አይሰማኝም› ስትል አሰበች፡ በዚያች ሚጢጢ አይሮፕላን እንኳን ህይወቷን ሸጣ መጥታ የለም፡፡

አገሯ ስትደርስ ምንድነው የምታደርገው? ፒተር ይህን እቅዱን እንዲለውጥ ማሳመን አይቻልም: አሁን ካሳየው ባህሪ በስተጀርባ ለረጅም ዓመት አምቆ የያዘው ድብቅ ጥላቻ እንዳለ አውቃለች፡፡ ለወንድሟ አዘነችለት፡፡ ይህን ያህል ዓመት ከቅናት የተነሳ ጥላቻ በሆዱ ሲያስታምም ቆይቷል፡፡ እጇን ልትሰጥ አልፈለገችም፡፡ የተወላጅነት መብቷን ለማስከበር
‹ሌላ መንገድ ይኖር ይሆን?› ብላ አሰበች፡፡
👍16
ዳኒ ሪሌይ መንፈሰ ደካማ ሰው ነው፡፡ በአንድ ሰው በጉቦ የተደለለ ሰው
በሌላ ሰው መደለሉ አይቀርም፡፡ ናንሲ ድምፁን ለእሷ እንዲሰጥ የሚያደርገው ትልቅ ስጦታ
ማሰብ አለባት: የጄኔራል
ቴክስታይልስ ኩባንያ የህግ ጠበቃነት ከሚያስገኘው ጥቅም ካልበለጠ ግን
ለማቅረብ ድካሟ ሁሉ መና መቅረቱ ነው፡፡

ምናልባት የሰራኸውን ወንጀል አጋልጣለሁ ብላ ማስፈራራት ሳያዋጣት አይቀርም፡፡ ይሄ እንደውም ብዙ ገንዘብ አያስወጣትም፡፡ ግን
እንዴት? ምናልባትም ለቤተሰቡና ለእሷ ጥብቅና እንዳይቆም ማገድ ትችል
ይሆናል፡ ይህም ቃል ከተገባለት የጥብቅና ስራ ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ
የሚባል አይደለም፡፡ ዳኒ በጣም የሚወደው በቀጥታ ጥሬ ገንዘብ ቢሰጠው
ቢሆንም አሁን በእጇ ያለው ጥቂት ሺህ ብር ብቻ ነው፡ አብዛኛው ገንዘቧ
በብላክ ጫማ ኩባንያ ውስጥ ታስሯል፡፡ ብዙም ሳይታወቅ ከኩባንያው ጥቂት ገንዘብ አውጥታ መስጠት ትችል ይሆናል፡ ነገር ግን ዳኒ ብዙ ገንዘብ
መጠየቁ አይቀርም፤ ምናልባትም አንድ መቶ ሺ ዶላር፡፡ ይህን ያክል ገንዘብ
ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከየት ታመጣለች?

ይህን በአዕምሮዋ ስታወጣ ስታወርድ ስሟ ሲጠራ ሰማችና ዞር ስትል
ያ የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ሰራተኛ እጁን ሲያውለበልብ አየች
ሌኔሃን›› ሲል ጮኸ ‹‹ከቦስተን ስልክ ይፈልግሻል ወይዘሮ
ማክብራይድ የሚባል ሰው፡፡››

ድንገት የመጣው የማክብራይድ የስልክ ጥሪ ትንሽ ተስፋ አጫረባት፡፡
ምናልባትም ማክብራይድ አንድ መላ ይነግራት ይሆናል፡፡ ዳኒ ሪሌይን እንደ
እጁ መዳፍ ያውቀዋል፡፡ ሁለቱም ሰዎች እንደ አባቷ አይሪሾች ሲሆኑ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን ሁልጊዜ ይጠራጠራሉ አይሪሾችም
ቢሆኑ፡ ማክብራይድ ሃቀኛ ሲሆን ዳኒ ግን አይደለም፡፡ በሌላው ነገር ግን
አንድ ናቸው፡፡ የናንሲ አባት ሃቀኛ ቢሆንም አይሪሻውያንን የሚጠቅም ከሆነ የተጭበረበረ ተግባር ቢሆንም እንዳላየ ነው የሚያልፈው፡፡

ናንሲ ወደ ስልኩ እየሮጠች አባታቸው አንድ ጊዜ ዳኒን ከገባበት ማጥ ውስጥ እንዳወጡት አስታወሰች፡፡ ከጥቂት ዓመት በፊት ነው፡፡ አባቷ ሊሞቱ አካባቢ፡፡ ዳኒ አንድ ጥብቅና የቆመለት ጉዳይ ነበረው: ቢያሸንፍ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝለት፡፡ ይህን ጉዳይ እንደማያሸንፍ ሲያውቅ ለዳኛው ጉቦ
ሊሰጥ ሞከረ፡፡ ዳኛው ደግሞ በጉቦ የሚደለሉ አይነት ስላልነበሩ ‹‹ዳኒ ወይስራህን ልቀቅ አሊያም ከጥብቅና ስራ ትታገዳለህ›› የሚል ምርጫ ሰጡት፡፡
በዚህ ጊዜ የናንሲ አባት ዳኛው እግር ላይ ወድቀው ምህረት አሰጡት፡፡ ናንሲ
ይህን ታውቃለች፡፡ አባቷ ሊሞቱ ሰሞን በሆዳቸው የቋጠሩትን ምስጢር
ሁሉ ይነግሯት ነበር፡፡

ዳኒ ማለት እንግዲህ እንዲህ ያለ ሰው ነው እንደ ተልባ ሙልጭልጭ፣ እምነት የማይጣልበት፣ እጅግ ሲበዛ ጅልና በቀላሉ
ሊጠመዘዝ የሚችል ሰው፡፡ የእሷ ደጋፊ እንደምታደርገው ጥርጣሬዋ ጠፋ፡

ሆኖም ቦስተን ለሚደረገው የቦርድ ስብሰባ የቀራት ሁለት ቀን ብቻ ነው፡፡

ህንጻው ውስጥ እንደገባች ወጣቱ ሰው የስልኩን እጀታ አቀበላት። ስልኩን ጆሮዋ ላይ ስታደርግ በቀጭኑ ሽቦ የማክብራይድ ድምጽ ተንቆረቆረ ማክብራይድ ሲያናግራት ለእሷ ፍቅር እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ ‹‹የሰማይ በራሪው ጀልባ ላይ ደረሽበት የኔ ጀግና!›› አላት የማታ ማታ ልፋቷ ፍሬ
ሲያፈራ ስላየ ደስ ብሎት፡፡
‹‹የቦርዱ ስብሰባ ላይ እገኛለሁ፡ መጥፎነቱ ፒተር የዳኒን የድጋፍ ድምጽ አግኝቷል›› አለች

‹‹ታዲያ አመንሽው?››

‹‹ድምጹን ለፒተር የሚሰጥ ከሆነ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ
የጥብቅናውን ስራ ሊሰጠው ተስማምቷል፡፡››

‹‹እርግጠኛ ነሽ?›› አለ ማክብራይድ በተስፋ መቁረጥ፡፡

‹‹ናት ሪጁዌይ ከፒተር ጋ ነው አሁን››

‹‹ይሄ እባብ›› አለ ማክ፡፡
ማክ ናት ሪጅዌይን አይወደውም፡፡ ናንሲን በፍቅር ያጠመደ ጊዜ ደግሞ በጣም ጠላው፡፡ ማክ የሞቀ ትዳር ቢኖረውም ናንሲን ከመውደዱ የተነሳ
እሷን በፍቅር የሚፈልግ ወንድ ሲገጥመው በቅናት ይንጨረጨራል፡

‹‹ጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ የጥብቅና ስራውን እንዲሰራለት ዳኒን መምረጡ ያሳዝናል›› አለ ማክ፡፡

‹‹ምናልባትም ትንሽ የጥብቅና ስራ ይሰጡት ይሆናል፡ ነገር ግን
የእሱን ድምጽ ለማግኘት ሲሉ የጥብቅና ስራውን መስጠታቸው ህግ መጣስ
አይደለም?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ህግ መጣስ ነው: ነገር ግን ህግ መጣሱን በማስረጃ ማረጋገጡ
አስቸጋሪ ነው፡፡››
‹‹ስለዚህ መቀመቅ መውረዴ ነው ማለት ነው?›› አለች፡

‹‹ሳይሆን አይቀርም፤ አዝናለሁ ናንሲ››

‹‹አመሰግናለሁ የጥንቱ ጓደኛዬ፡ ድሮም ፒተር ኃላፊ እንዳይሆን አስጠንቅቀኸኝ ነበር፡››

‹‹አዎ››

‹‹ከዚህ በላይ ላለፈ ነገር መጨነቅ አያስፈልግም፤ ዳኒ ከሆነ ቁልፉ አሁን መጨነቅ ስለእሱ ነው፡፡››

‹‹እውነትሽን ነው፡፡››

‹‹የሚያስጨንቀው ነገር ዳኒ አቋሙ መለዋወጡ ነው፡፡ ባላንጣዎቻችን እኛ ከምንሰጠው የበለጠ መደለያ ከሰጡት ወደ እነሱ መሄዱ አይቀርም
ስለዚህ ምን ያህል ብንሰጠው ነው ወደ እኛ ልናመጣው የምንችለው?››
ስትል ጠየቀችው፡፡

ማክ ለጥቂት ደቂቃዎች ጸጥ አለና ‹‹ምንም ሃሳብ አልመጣ አለኝ አላት፡፡

‹‹ዳኒ አንድ ወቅት ላይ ለዳኛ ጉቦ ሊሰጥ ሲል ተይዞ አባባ እንዴት
አድርጎ ከችግር እንዳወጣው ታስታውሳለህ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹በደምብ አስታውሳለሁ፡››
‹‹እሺ ይህን ጉዳይ እሱን ለማስፈራራትና ለእኔ ድምጽ እንዲሰጥ ለማድረግ መጠቀም አንችልም?››

‹‹እንችላለን››
‹‹ከፒተር ስር ስር የምትለውን ነገር ካላቆምክ እናጋልጥሃለን ብንለውስ?››

‹‹የሰነድ ማስረጃ አለን?››

‹‹አባባ ካስቀመጣቸው ወረቀቶች መሃል ሳይኖር አይቀርም፡›››

‹‹ሁሉም ሰነዶች አሉ? አልጠፉም ናንሲ?››
ቦስተን ናንሲ መኖሪያ ቤት ውስጥ የአባቷ ወረቀቶች የታጨቁባቸው
ካርቶኖች አሉ፡፡
‹‹ምን እንዳለባቸው አላውቅም›› አለች።
‹‹ቢኖሩስ አሁን ምን ጊዜ አለን?››
‹‹ሰነዱን አውጥተን እናጋልጥሃለን ብንለውስ?››
‹‹አልገባኝም ያልሽው?››
‹‹አባባ ካስቀመጣቸው ሰነዶች መካከል ያንተን ጉድ የሚመለከቱ ሰነዶች
አግኝተናል ብለን እናስፈራራው፡፡ አንዴ አድምጠኝ ማክ፡፡ ይሄ ሃሳብ ነው›› አለች፡፡ ናንሲ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላትና ደስ አላት፡፡

የጠበቆች ማህበር ወይም ሌላ አካል ዳኒ የሰራውን ህገወጥ ስራ ሊቀሰቅሰው እንደተነሳ አድርገን ሹክ ብንለውስ? አንድ የሆነ አጠራጣሪ ነገር
እንደተገኘበት እንዲነግረው አንድ ሰው እንላክበት››

‹‹እሺ ሆነ እንበል፡፡ ቀጥሎስ?››

‹‹አንድ ሊታመን የሚችል ነገር እንፍጠር፡፡ ለምሳሌ ማህበሩ በአባባ ሰነዶች ውስጥ አንድ ዋና ማስረጃ እንዳለ ሰምቷል ብንለውስ?››

‹‹ሰነዶቹን እንመርምር ብለው ሊጠይቁሽ ይችላሉ››
‹‹ከጠየቁ መስጠት ግዴታ አለብኝ?››
“ቀላል ምርመራ ከሆነ ላይጠይቁሽ ይችላሉ፡፡ የወንጀል ምርመራ ከሆነ
ግን ፍርድ ቤቱ ለምስክርነት ሊጠራሽ ይችላል፡ ያኔ ምርጫ አይኖርሽም››
አለ ማክ፡፡

መስራቱ ቢያጠራጥራትም በናንሲ አዕምሮ ውስጥ አንድ ውጥን ተቀረጸ፡፡ ‹‹ስማኝ ማክ! ዳኒጋ ደውልና የሚከተለውን ጥያቄ አቅርብለት›› አለች ፈጠን ብላ
‹‹ናንሲ ቆዪ ልጻፈው›› አለና ትንሽ ቆይቶ ‹‹ቀጥይ›› አለ፡፡
‹‹ብዚህ ጉዳይ የጠበቆች ማህበር ሰነዶች ጠይቆኛል ልስጣቸው እንዴ?
ብለህ ጠይቀው፡፡››

ማክ ግራ ገባው ‹‹አይ አትስጪብኝ ሊልሽ ነው?››

‹‹እንደኔ ግምት በፍርሃት ሱሪው ላይ ይቀዝናል ማክ፡፡ እዚያ ካርቶን ውስጥ ምን ምን እንዳለ አያውቅም ማስታወሻ ይኑር ደብዳቤ ይኑር ወይም ሌላ ነገር ይኑር የሚያውቀው ነገር የለም፡፡››
👍6
‹‹አሁን ትንሽ ግልጽ እየሆነልኝ መጣ›› ሲል ማክ ናንሲም ካነጋገሩ ተስፋ አጫረች፡፡ ‹‹ዳኒ አንድ ነገር ሳይኖራት አይቀርም ብሎ ይገምታል››

‹‹አባባ እንዳደረገው መረጃውን እንድደብቅለት ይማጸነኛል፤ ሰነዶቹን
ለማህበሩ እንዳልሰጥበት ይለምነኛል፤ እኔ ደግሞ እስማማለሁ፤ ለኔ ድምጽ
የሚሰጥ ከሆነ፡፡››

‹‹ቆይ እስቲ አትቸኩይ፡፡ ዳኒ ገንዘብ ይወዳል እንጂ ደደብ አይደለም: ምናልባትም እሱ ላይ ግፊት ለማድረግ ስንል ይህን ሁሉ እንደምናደርግ
ሊጠረጥር ይችላል፡››

‹‹መጠርጠሩ አይቀርም›› አለች ናንሲ ‹‹እርግጠኛ መሆን ግን አይችልም፡ ነገር ግን የማሰቢያ ጊዜ አንሰጠውም››

‹‹አዎ፡፡ አሁን ለጊዜው ሌላ ምርጫ የለንም››
‹‹እንሞክረው?››
‹‹እሺ›› አለ ማክ፡፡
ናንሲ አሁን ቀለል ብሏታል፡፡ ተስፋዋ ለምልሟል፡ እንደምትረታ ታውቋታል፡፡
‹‹አይሮፕላኑ የሚያርፍበት የሚቀጥለው ቦታ ስደርስ ደውልልኝ ማክ››
አለች::
‹‹የት ነው?››
‹‹ቦት ውድ ኒው ፋንድላንድ (ካናዳ)፡፡ እዚያ ከአስራ ሰባት ሰዓት በረራ
በኋላ እንደርሳለን››
‹‹ስልክ አለ እዚያ?››
‹‹ሳይኖራቸው አይቀርም አይሮፕላን ማረፊያ ካለ፡ አስቀድመህ ለመደወል መመዝገብ አለብህ››
‹‹እሺ ናንሲ፤ መልካም ጉዞ››

‹‹ባይ ማክ›› አለችና ስልኩን ዘጋች፡፡ አሁን ስሜቷ ተነቃቅቷል ዳኒ በዚህ ስራ እጁን ላይሰጥ ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም አንዳች ውጥን መፍጠር መቻሏ አስደስቷታል፡፡

አሁን ሰዓቱ አስር ሰዓት ከሃያ ሆኗል፡ የመሳፈሪያው ሰዓት ደርሷል። ከስልክ መደወያው ኪዮስክ ወጣችና መርቪን ስልክ ወደሚነጋገርበት ክፍል ሄደች።.....

ይቀጥላል
👍11🥰1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ሁለት (22)

« እንዴት እንዲህ ትይኛለሽ? እንዴት ይህን የመሰለ ነገር ደፍረሽ ትናገርያለሽ ? አለ ። ለቅፅበት ያህል የእናቱን ገፅታ እየችበት ። ልክ እንደማሪዮን ጨካኝ ፤ ልክ እንደማሪዮን ስሜት አልባ አረመኔ ሁኖ ታያት ። ሆኖም አልቆየም ። ሆኖም ይህ ገፅታው የእናቱን ያህል የፀና አልነበረም ። በዚሀ በኩል ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር የሚወዳደር ሰብዓዊ ፍጡር አይገኝም ። «የነገርኩሽን ነገር እንዴት እንዴት አድርገሽ ጠመዘዝሽው! ምን ያህል ብትጨክኝ በዚህ መልክ ተረጐምሽው ?» አለ።! «መጠምዘዘም መተርጐሜም ሳይሆን መጠየቄ ነው። ጥያቄው የማይገባ ከሆነ ስሀተት ነው። በመሳሳቴ ቅር ስላሰኘሁህ ይቅርታ። እውን ተሳስቼ ይሆን ማለትም ጀምሬአለሁ ባንኮኒውን ደገፍ ብላ ቆማ ፊት ለፊት አይኗን ሳትሰብር ስትመለከተው ድንገት ትከሻዋን ይዞ አፈፍ አድርጐ ወደ ገላው አስጠጋት ። « ማይክል » አለች ። ካስር ደቂቃ በኋላ እዘመናዊው ኩሽና ወለል ላይ ተጋድመው ከላይ ከላይ ሲቃትቱ ያለነሱ ትንፋሽ በስተተር ሌላ ድምፅ አልነበረም ። ትንፋሻቸው ደርሶ ፀጥ ሲል እኩሽናው ውስጥ የተቀመጠው የጠረጴዛ ሰዓት ትክ ፣ ትክ ፣ትክ የሚል ድምፅ ጥርት ብሎ ተሰማት ። ማይክል ግን በመስኮቱ አሻግሮ የአትክልት ቦታውን ይመለከት ነበር ፤ በገፅታው ላይ ጥልቅ የሆነ ሀዘን ተስሎ ።

« ማይክል ደህና ነህ ? » አለችው። ወዲያው ነገሬ ሁሉ የእብደት ነው ። እሱ መጠየቅ የሚገባውን እኔ ጠየቅኩት ስትል አሰበች ። ግን ሁሉም የተገላቢጦሽ ሆኗል ። ላይሆንም ይችላል ። እሷ ግን አትችልም።አልቻለችም ። አንድ ቀን ይኸ ሁሉ ያበቃል ። ያኔ ምን ይውጣት ይሆን ? ምን ይደርስባት ይሆን ? ምናልባትም ቤን አቭሪን ጠርቶ ከስራ እንድታባርራት ብሎ ትዕዛዝ ይሰጠው ይሆናል። ይህ ሁሉ በሀሳቧ መጣባት ።
«ማይክ» አለች ድንገት ።
«እእ!--አ... አቤት። በ. . . በጣም ይቅርታ ዊንዲ አንዳንዴ መላ ቅጡ የጠፋኝ ወደር የሌለኝ ወደል አህያ እሆናለሁ» አለ
«እዚህ ላይ ነህ እይደለህም ብዬ ልከራከርህ እንደማልችል ርግጠኛ ነኝ ። አለችና በመከፋት ፈገግታ አየችው ። ከዚያም ጉንጩን ሳም አድርጋ ፤ « የምወድህ ግን ይመስለኛል ፤ ምንም ብትሆን » አለች።
«ሌላ ብዙ ነገር ማድረግ ትችይ ነበር ። መውደድ ብቻ አይደለም ። ግን ፍሬ ቢስ ነገር ነው » አለና ቀና ብላ ስታየው ቁልቁል ተመለከታት ። እንዲህ ሙሉ በሙሉ ካያት ስንት ጊዜ ሆነ። ሩቅ. . . ሩቅ ነው። « አንዳንዴ የምሰራውን ስራ ሳስበው ፤ በተለይ አንችን የማስቀይምሽ ትዝ ሲለኝ ራሴን እጠላለሁ ። እንዲያውም አንድ ነገር ሁን .. .» ሊቀጥል አልቻለም ። ዝም ። አትናገር ! ስትል አመልካች ጣቷን እተገጠመ ከንፈሯ ላይ በማስቀመጥ አሳየችው። « አውቃለሁ» አለ አንገቱን በአዎንታ እየነቀነቀ ። ከተጋደመበት ተነስቶ ቆመ ። እወለሉ ላይ እንደተዘረጋች ሽቅብ ተመለከተችው ። በፊቱ ላይ የነበረው ሀዘን ቀንሷል ። ቢያንስ ቢያንስ ስጋዋን በመስጠት ትንሽ ሰላም ፈጠረችለት ።
« ማይክል››
« ወይ››
«ማይክል ፤ አሁንም እሷን ብቻ ነው እምታስበው ? አሁንም ሴላ ሴት አታምርሀም ? » መልስ አልሰጠም ። ፀጥ ብሎ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ በመጨረሻ አዎንታውን በአንገቱ ገለፀ ። ዓይኑ ውስጥ ግን ከፍተኛ ስቃይ ተስሎ ይታይ ነበር ። ይህን ብሎ ሌላ ቃል ሳይጩምር ወደ መኝታ ቤት ገባ። ዌንዲ ቀስ ብላ ከተጋደመችበት ወለል ላይ ተነሳች ። በኩሽናው ውስጥ ከሚገኙ ረጅም ብርጩማዎች ባንዱ ላይ ተንጠላጥላ ባንኮኒውን ተደግፋ ከተቀመጠች በኋላ በዓይኑ ውስጥ ተስሎ ስላየችው ስቃይ ማሰላሰል ጀመረች ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከመኝታ ቤት ወጥቶ ወደ ኩሽና ሲገባ እዚያው ጋ በሀሳብ ተውጣ እንደ ተቀመጠች አገኛት ። ከሀሳቧ ባንና ነቃች ። ቀና ብላ ስታየው ልቧ በኃዘን ተሰበረ ። ምክንያቱም ጂንሱን ታጥቆ ፤ ስፖርት ሸሚዝ ለብሶ በአንድ እጁ ሳምሶናይት የእጅ ቦርሳ ይዞ በሌላው ክንዱ ላይ ደግሞ ሹራቡን አንግቦ ነበር ። አለባበሱ ሊወጣ መሆኑን ነገራት ። ቦርሳዉን ይዞ ስታይ ምንም እንኳን ቀኑ እሁድ ቢሆንም ወደ መስሪያ ቤት ሊሄድ እንደሆነ ተረዳች ። ሹራቡን መያዙ ደግሞ እዚያው ቢሮው ሊያመሽ መወሰኑን ገለፀላት ።

« ትመጣለህ ? እንገናኛለን ?››
ይህን የተናገረውን እሷን ጠላችው ። ይህ መናገርም እይደለም ። መጠየቅ ። መለመን ነው አለች በሀሳቧ ። መልሱ ቢያምር መለመኗ ባልክፋ ። ግን ለጥያቄዋ የሰጣት መልስ በአሉታ ራሱን በመነቅነቅ ነበር ። አፈር ይብላ ! «እስከ ምሽቱ ስምንት ወይም ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ቢሮዬ ቆይቼ እሰራ ይሆናል ። ከዚያ ከቻልኩ ወደ ቤቴ ብደርስ አይከፋም ። ልብስ መቀየርም አለብኝ ፤ አደል » አለ ። ያ ለጥቂት ሰዓት ያህል ብቅ ብሎ የነበረው ለስላሳ ባህርይ ደብዛው ጠፍቶ ሰውየው ማይክል ሂልያርድ ሆነ። መሸሹን ጀመረ ። ሩካቤ ስጋ ካደረጉ በኋላ ባሉት አስር ወይም አሥራ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ አንዴ አግኝታው አጣችው ። ሁኔታው ሁሉ የሚያፈናፍን አይደለም ። ማግኘት የሚሉት ነገር ተስፋ የሌለበት ባዶ ነው ። ሆኖም . . . ሆኖም ተስፋ መቁረጥ የሚሉት ነገር ያስጠላታል ። እንዲህ ሲገፏት ፤ ችላ ሲሏትማ ይበልጥ እንድትሞክር የሚወተውት ነገር አለባት ።

«ያው ነገ እቢሮ ነህ አይደለም… እዚያ እንገናኛለና» አለች መከፋቷን ፣ መስቃየቷን ድምጺ እንዳያውጅባት ልትጠነቀት እየሞከረች እበር ድረስ ስትሸኘውና ቻዎ ስትለው እንዲያውም ፈገግታ ቢጤ ሞክራ ነበር ፤ ይሳካም አይሳካም ። ደግነቱ እሱ ይህን ሁሉ ለማየት ጊዜ አልነበረውም ። እግንባሯ ላይ በከንፈሩ ትንሽ ነካ አድርጓት ዞሮ ሳይመለከታት መሄዱ አስደሰታት ። ምክንያቱም ገና በሩን ዘግታ ሳትሸጉረው ማልቀስ ፤ መንሰቅሰቅ ጀምራ ነበርና ። የማይክል ሂልያርድ ነገር ሊሳካ የማይችል መሆኑ ገብቷታል ።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በመንገዱ ላይ አንዳች ነገር አልነበረም ። ዝር አይልም። ይህን ሲገነዘብ የቤንዚን መስጫውን እስከ መጨረሻው ረገጠው። ጥቁር ቀለም ያለው ፖርሽ አውቶሞቢል ከነፈ ። የገጠሩ ምድርና በላዩ ላይ የተሸከመው ነገር ሁሉ እየሰፈሰፈ ያልፋቸዉ ነበር ። ልባቸው በደስታ ተሞላ ። በመኪና የመጓዝ ሳይሆን የመንሳፈፍ ስሜት ተሰማቸው ። በአምስት ሰዓት አካባቢ ረፋዱ ላይ እቤቷ ድረስ መጥቶ በአውቶሞቢሉ ከተሳፈረች በኋላ ከሳንፍራንሲስኮ ተነስተው ወደ ደቡብ ጉዞአቸውን ቀጠሉ። ሁልጊዜም እሁድ እሁድ በመጀመሪያ እንዲሁ ይጓዛሉ ። መድረሻቸውን አያውቁትም ። ሲሰለቻቸው ወይም ሲርባቸው ከመኪናቸው ወርደው ምሳ ይበላሉ ። ካረፉ በኋላ እጅ ለእጅ ተያይዘው እየተንሸራሸሩ ፤ ስላለፈው ሕይወታቸው እያወሩ ፤ ባለፈው ስላጋጠማቸው አስቂኝ ሁኔታ እያነሱ ከልባቸው ይስቃሉ። ሽርሽሩ ሲበቃቸው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ ። ይህ የተለመደ እንደ ጸሎት ሥርዓቱን ጠብቆ የሚደጋገም ነገር ነውና ለምዳዋለች ፤ ወዳዋለች ። ይህን ድርጊት ብቻ ሳይሆን ፒተርንም በተዘዋዋሪ መንገድ ማፍቀር ጀምራለች ።
👍20
ፒተር ግሬግሰን ተዝቆ የማያልቅ ችሎታ ያለው ሰው ነው። ባንደኛው ችሎታው አካሏን እየመለሰላት ነው። ምንም እንኳ ገና ኦፕራሲዮኑን ባይጨርስም ዛሬ የናንሲ ፊት ቁልጭ ብሎ ወጥቷል ። ፋሻው ዓይኗ አካባቢ ብቻ ሲሆን የሚገኘው ፣ ሌላውን ፊቷንም ያደረገችው ሰፊ ጥቁር መነፅር ሙሉ በሙሉም ባይሆንም ሸፍኖታል ። ግንባሯ ላይ ያለውን ፋሻም ባርኔጣዋ ጋርዶታል ። ያም ባይሆን ከፒተር ጋር ስትሆን ይህ ሁሉ ኦይሰማትም፡፡ ፒተር ይህ ሁሉ እንዳይሰማት የሚያደርግ ኃይል አለው ። ይህን ሁሉ የሚያደርግላትን ፤ ምቾቷንና ሕልሟን እውን ያደረገላትን ፒተር ላለመውደድ ችሎታ ይኖራታልን? አንዲት ትንሽ ምግብ ቤት ሲያዩ መኪናቸውን አቁመው ምሳ ለመብላትና ዕረፍት ለማድረግ ወሰኑ ። ምግብ ቤቷ በፈረንሳይ የመንገድ ዳር ማረፊያና መመገቢያ ቤቶች ዕቅድ የተሠራችና የተሽሞነሞነች ነበረች ። በውስጧም የፈረንሳይ ምግቦችና ነጭ ደረቅ የወይን ጠጅ የሚሸጥባት ነበረች ። ምሳቸውን በሉ። ነጭ፤ደረቅ የወይን ጠጃቸውን ጠጡ ። ይህ ደግሞ ናንሲን ያስደስታታል ። ለምዳዋለች ። እዚህ እንደመጣችበት ምሥራቃዊው ግዛት ያሉ መዝናኛዎች የሉም ። ባዛሮች በብዛት አይገኙም ። የሚያብለጨልጩ ሰማያዊ ያንገት ጌጥ መቁጠሪያዎችም አይገኙም ። ስለዚህ እንደ ሀገሩ ያገሩን መዝናኛ መቀበልና መልመድ አለባት ። አንድን ነገር መልመድ በግዴታ የሚቻል ነገር ባይሆንም በውዴታ ለምዳ ወዳዋለች።

ይህ ብቻ ሳይሆን ናንሲ አዲስ ሰውነቷን ፤ አዲስ ገፅታዋንም ተቀብላ ወዳዋለች ። አዲስ ድምጺን በመቃኘት አዲስ እሷን መሆን ጀምራለች ። «ፒተር ስሜን ለመለወጥ እንዳሰብኩ ነግሬሃለሁ!» አለች። ይህን ያለችው ምሳቸውን በልተው ጨርሰው ወይን ጠጃቸውን እየጠጡ ሲዝናኑ ከቆዩ በኋላ ጠርሙሱን ሲያጠነፍፉት አካባቢ ነበር ።። ነገሩን ከፌ አሊሰን ጋር ተወያይተውበታል ። ያኔ ግን ይህን ያህልም የሚያስፈራ መስሎ አልተሰማትም ። ለፒተር ስትነግረው ዕፍረቷ በገፅታዋ ላይ ተስሎ ታዬ። ምነው ባላነሳሁት ኖሮ ስትል አሰበች። ግን ፒተር ዕፍረቷን ሁሉ በፍጥነት ከለላት ። « እንዲያ ስትይ ፈፅሞ አላስገረመኝም ታውቂያሽ ። ምክንያቱም አንቺኮ የድሮዋ ናንሲ አይደለሽም ። አዲስ ሰው ነሽ ሌላ ቆንጆ ። ያሰብሽው ደስ የሚል ስም አለ! » አለ ፒተር፡፡ ይህን ብሎ ምርጥ ሲጋራውን አቀጣጠለ ። በፍቅር ዓይን አያት የሲጋራውን ሽታ መውደድ ጀምራለች ። በተለይ ከምግብ በኋላ ሽታው ያስደስታታል ። ፒተርም ይህን የተረዳ ይመስላል ። ዓላማው ደግሞ ግልፅ ነው። በሕይወት ውስጥ አንድ ነገር ከተደረገ ጥራት ያለው መሆን አለበት ። ነገሩ ለናንሲ አዲስ ስለሆነ ይህንንም እንድትለማመድ ይፈልጋል ። ከፍ ከፍ እንደማለት የሚያስደስት ምን ነገር ሊኖር ይችላል ?።

« ታዲያ አዲሷ ወዳጃችን ማን ትባላለች ? ስሟን ትንገረና »አለ። «ለጊዜው ሜሪ አዳምሰን የሚል ስም ነው የመጣልኝ ። እንዴት ነው ይስማማል ?» ትንሽ አሰበና አንገቱን በስምምነት እየነቀነቀ… « መጥፎ ስም አይደለም ። እንዲያውም ወድጀዋለሁ ። ግን... ግን ለምንድነው ሜሪ አዳምሰንን የመረጥሽው ?››
« የናቴ ስም ማለት ከማግባቷ በፊት ሜሪ አዳምሰን ነበር። እንዳጋጣሚ ሆኖ ዕጓለማውታን ማሳደጊያው ውስጥ እወዳቸው የነበሩ መነኩሲትም ሜሪ አዳምሰን ይባሉ ነበረ››

« አረ በስላሴ ፤ እንዴት የሚያስደንቅ ጉድ ነው እባክሽ » ሁለቱም በጉዳዩ ሳቁ ....» ሜሪ አዳምሰን ። ይህን ስም ስታስበው በጣም ወደደችው ። «ከመቼ ጀምሮ ነው ባዲሱ ስም መጠራት የምትፈልጊው?»
« እኔንጃ. . . ገና አልወሰንኩም »
«እኔ ምለው ከወደድሽው ምን ዛሬ ነገ ማለት ያስፈልጋል። ዛሬ ፤ ከአሁን ጀምረን ለምን ሜሪ አንልሽም? እስራዎችሽ ላይም ሜሪ አዳምሰን እያልሽ ብትፅፊ ጥሩ ነው ። አይመስልሽም ?» ፒተር ይህን የተናገረው በከፍተኛ ስሜትና የልብ ሲቃ ነበር ። ሁልጊዜም ስለሷ ወይም ስለራሱ ሥራ ሲያነሳ የሚናገረው በከፍተኛ ሲቃ ነበር ። « ናንሲ እውነቴን ነው ፤ ለምን እሁኑኑ ሜሪ እትባይም እስራሽ ላይም ይህንኑ ስም አስገቢ »
« እንዴት ማለት እሰራሽ ላይ ? ፎቶግራፎቹ ግርጌ ፎቶ በሜሪ አዳምሰን ብዬ ልፅፍ ? »
‹‹ይመስለኛል ። ማለት ስራሽ እኔንና ፌ አሊሰንን ብቻ አስደስቶ መቅረት የለበትም ። ትንሽ ወጣ ማለት ፤ አድጣስሽን ማስፋት ያለብሽ መሰለኝ » በፒተርና በናንሲ መካከል አለመግባባት አለ ቢባል የማይግባቡበት አንደኛው ጉዳይ ይኸ ነው.። ፒተር ግሬግሰን ናንሲ ማክአሊስተር ትልቅ እንድትሆን ፤ ታዋቂ እንድትሆን ይፈልጋል ። ስራሽን ዓለም ሊያየው ይገባል ይላል ። ናንሲ ግን ለጊዜው ይህን አትሻም ።ሁሌም ይከራከራሉ ። « እንደገና ይህን ነገር እንስተን ባንጨቃጨቅ ይሻላል አለች። መዳፏን «ታገድ» በሚል መልክ እያሳየችው ። «ካልሽ ይሁንልሽ። ለጊዜው ማለቴ ነው። ግን ባጠቃላይ አነጋገር ካልን ይኸ የጋን መብራት ሆኘ ልቅር የምትይው ነገር አይስማማኝም ። ይህን የመሰለ ሥራ ተሠርቶ ማንም ሳያየው ይቅር ብትይኝ እሺ ማለት የሚቻለኝ አይመስሰኝም ። ስራሽ መውጣት ፤መታየት አለበት ።»
‹‹የማይሆነውን !»
« ስሚ ናንሲ ። ደግሜ ልንገርሽ ። አንቺ ወጥ የሆንሽ የኪነጥበብ ሰው ነሽ። እንደፊልም ተዋናይ ይሁን እንደ ፎቶግራፈር ወይም ሌላ ፤ ስራሽም አንችም በአደባባይ መታየት አለባችሁ። ይህ የኔ እምነት ነው። ፅኑ ዕምነቴ ነው »
« አትልፋ ፒተር » አለችና ከወይኑ ተጎነጨች ። ከዚያም ቡዝዝ ብላ በመስኮት ወደወጭ እየተመለከትች « ቅር አይበልህ» ግን ከእንግዲህ አደባባይ መውጣት የማይቻለኝ ሰው ነኝ››
« ለምን ናንሲ? ለምን?››
« ላለም ላሳየው የምፈልገውን ያህል ፤ ዓለም ሊያየኝ የሚፈልገውን ያህል አሳይቻለሁ ። አይቶኛል ። በቃኝ ። ካሁን በኋላ የሚታይ ነገር የለኝም »
« በጣም ጥሩ ፣ የተቻለኝን ያህል ለፍቼ ገፅታሽን የሰጠሁሽ ለካ ዕድሜ ልክሽን እማጀት ተደብቀሽ በኔ ብቻ የሚታዩ ድንቅ ፎቶግራፎችን እንድታነሺልኝ ኖሯል?»
« ይህ ታዲያ በጣም የሚያምር ነገር ነው እንዴ ?»
«ለኔ. . . ለኔ ብቻ ቢሆን ድንቅ ዕድል ነው። ላንች ግን ከዚህ የከፋ ፅጣ ሊኖር ኦይችልም። ናንሲ ፤በጣም ትልቅ ሰው ነሽ እኮ ! ተዝቆ የማያልቅ ችሎታ አለሽ ። ታዲያ ይህን ችሎታሽን መደበቁ ምን ይጠቅማል ? ስምሽ እንዲወጣ ካልፈለግሽ ሜሪ አዳምሰን በሚለው ስም ኤግዚብሽን ማሳየት ትችያለሽ አንዴ ብቻ ለሙከራ ያህል ። አየሽ ፣ ግሬታ ጋርቦም ወደ ምናኔዋ ከመግባቷ በፊት ድንቅ ተዋናይ ተብላለችኮ ። አንዴ ብቻ ምን እንደሚሆን ለማየት ዕድልሽን ሞክሪ » አለ ፒተር በልመና ፣ በማግባባትና በመለማመጥ ድምፅ።

ፒተር በዚህ ሁኔታ ከልቡ በነገራት ቁጥር ልቧ ይዋልላል ። ልሞክረው ? ትላለች ። በተለይ በሌላ ስም መሞከሩ አይከፋም ልበል ? አለች። ግን እንደገና ታዋቂ መሆን ፤እንደገና ኤግዚብሽን ማሳዬት የማይሞከር ሆኖ ተሰማት ። ስትታወቅ ፤ ለክፉ ነገር ስትጋለጥ ፤ መጥፎ ነገር ሲደርስባት ታያት ። ከዚህ በፊት ይሀን ሳትሆን የተጓዘችበት መንገድ ስለሆነ ወዶዚያው ብትመለስ አዲስ መሆን እንደማትችል ተገነዘበች ። ብዙ ነገር እንደሚያሳስባት ማይክል አሳሰባት ።
«እሺ አስብበታለሁ» አለች ።
👍14
በዚህ ጉዳይ ላይ በተነጋገሩ ቁጥር ይህን ያህል ወደ እሺታ የቀረበ መልስ ሰጥታው አታውቅም ነበረና ደስ አለው፡፡
«አዎ በሚገባ አስቢበት ፤ሜሪ » አለ ።
ሜሪ ብሎ በሰፊው ፈገግ አለ። እሷም የልጅ ዕፍረት ላቅ ሳቀች ። እና…. « ካደግክ በኋላ በአዲስ ስም ስትጠራ የቀልድ የቀልድ ይመስላል » አለች።
« ግንኮ ፊትሽም አዲስ ነው ። እሱም የቀልድ ይመስላል ?» አለና ጠየቃት ።
« ፊቴ እንኳ አይመስለኝም ። አሁን አሁን ለምጄዋለሁ። ዕድሜ ለፌ አሊሰንና ላንተ እንጂ ፊቴ የራሴ ሆኖ ነው የሚሰማኝ »አለች። « ሁልጊዜ ፤ካሁን ጀምሮ ሜሪ እያልኩ ልጥራሽ !? »
«ደግ ። ቢያንስ ስሙ ማጠሩንና መጥበቡን ለመለካት ይረዳኛል ፤ ባደባባይ ከመልበሴ በፊት » አለች ። ሁለቱም ደስ ብሏቸዋል ። ሁለቱም የሆነ የመደባበቅ ስሜት ይታይባቸዋል ። ሁለቱም»


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍8👎1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስ ሉሲ ከአክስቷ ከኮርኒሊያ ቤት ሔዳ አንድ ጥፋት ፈጸመች ከቤት እንደተመለሱ ጥፋቷ ከሚስዝ ካርላይል ጆሮ ደረሰ " እሷም እስኪመሽ ድረስ ከልጆች ቤት እንዳትወጣና ምግብም ከዳቦና ከውሃ በቀር ሌላ እንዳይሰጣት አዘዘች "

የዚያን ለት ማታ ኢስት ሊን ውስጥ የራት ግብዣ ነበር ባርባራ ከመልበሻ
ክፍል ገብታ የራት ልብስ ለብሳ አዲስ የተቀጠፉ ቀይና ወይን ጠጅ አበባዎች
ከጸጉሯ ሰካች " ከደረቷም ተመሳሳይ ቀለም ያለው አበባ አድርጋ ፀሐይ መስላ
አሸበረቀች " ራት የሚበላው በአንድ ሰዓት ነው " አሁን 0ሥራ ሁለት ተኰል ቢሆንም ከሚጠብቁት እንግዶች አንድም ብቅ አላለም " ባርባራ አሁንም ሰዓቷን በጉጉት ትመለከታለች "

ማዳም ቬን ቀስ አድርጋ በሩን መታ መታ አደረገችው " ራት ተበልቶ
ከበቃ በኋላ ወይዛዝርቱ ወደ ሳሎን ሲመለሱ ' አብራቸው ለግማሽ ስዓት እንደትቆይ ቃል ተገብቶላት የነበረችው ሉሲ በተወሰነባት ቅጣት የተገባላት ቃል ሊቀርባት ስለሆነ በጣም ተጨነቀች " ማዳም ቬን ጭንቀቷን አይታ ይቅርታ ልትለምንላት መጣችና እየፈራች እየቸረች በሩን መታ መታ አድርጋ ገብታ ለሚስዝ ካርላይል ነገረችላት "

“ ማዳም .ይህችን ልጅ ልቅ ሰደሽ አበላሸሻት የምትቀጭያትም
አይመስለኝም » ስታጠፋም መታረም አለባት ” አለቻት ባርባራ

“ በጥፋቷ ተጸጽታለች ” አለች ማዳም ቬን " “ እንግዲህ ምንም ላታጠፋ ቃል ትገባለች " አሁንም በልቅሶ ፈርሳ ልትሞት ነው።

“የምታለቅሰው በሠራችው ጥፋት ተጸጽታ ሳይሆን ከሳሎን መግባቱ እንዳያመልጣት ፈርታ ነው "

“ አባክዎን ይቅር ይበሏት ” ብላ ለመነች ማዳም ቬን "

“ እስኪ አስብበታለሁ " እይውማ ማዳም ቬን ይኽ አሁን ተሰበረብኝ ' አያሳዝንም ? አለችና ባርባራ አንድ የወርቅ ሥራ ያለበት ጌጥ አሳየቻት "

ማዳም ቬን ተቀብላ መረመረችው አጣብቆ ሊይዘው የሚችል ማጣበቂያ ከላይ ከፎቅ አለኝ " በሁለት ደቂቃ ውስጥ አላቅቀዋለሁ” አለቻት "

“ ኧረ እንግዲያውስ በይ እስቲ ማጣበቂያውን እዚህ አምጪና ሥሪው " ጉቦ ልስጥሽ ” አለቻት እየሣቀች
እሱን መልሰሽ እንደ ነበረው አድርጊውና ለሉሲ ምሕረት መልእክት ይዘሽላት ትሔጃለሽ " መቸም ልብሽ የቆመው ለዚሁ ነው።

ማዳም ቬን ሔዳ ማጣበቂያውን አመጣችና ስባሪዎቹን አንሥታ እንዴት
ሊገጣጠሙ እንደሚችሉ እያየች ስታስብ ባርባራ ተመለከታለች "

“በፊትም ተሰብሮ ነበር ብላ ጆይስ ነግራኛለች” አለች ባርባራ ነገር ግን እንደማይታወቅ ሆኖ ተገጣጥሞ ይመስለኛል የት ላይ ተሰብሮ እንደ ነበር
እንኳን ለማግኘት አልቻልኩም " ይህ ዕቃ ሚስተር ካርይል የመጀመሪያ ሚስቱን ያገባ ጊዜ ለንደን ሳሉ የገዛላት ነበር " ኋላም እሷ ሰበረችው "እንዴ ምን ነካሽ ማዳም ቬን ? እጅሽ እንደሱ ከተንቀጠጠ ምንም ልትሠሪው አትችይም „

መጀመሪያም የት እንደተሰበረ ልትነግራትና ልታሳያት ስትል የሚያስከትለው ጥያቄም ወዲያው ትዝ አላትና ቃሉን ካፏ አድርሳ ተወችው » ቀጥሎም ይህን ዕቃ መጀመሪያ የሰበረችው ጊዜ እንዴት እንዳዘነችና ሚስተር ካርላይልም አብሮ ስለ ነበር ከዚሁ ክፍል ሆነው እያባበለና እየሳመ እንዴት እንዳጽናናት ስታስታውስ አሁን ደግሞ የጌጡ ዕቃም የካርላይል መሳምም የሷ መሆናቸው ቀርቶ
የባርባራ መሆናቸውን ስታስበው ቆጫት እጆቿም ተንቀጠቀጡ "

“ስሚንቶውን ከፎቅ ሳመጣ በጣም ስለ ሮጥኩ ነው እጆቼ የሚንቀጠቀጡት”
ብላ አመካኘች » በዚህ ጊዜ ሚስተር ካርላይልና እንግዶቹ ሲመጡ ተሰሙ
ሚስተር ካርይል ወደ ሚስቱ መልበሻ ክፍል ሲመጣ ማዳም ቬን ተነሥታ ልትሔድ ፈለገች

“የለም ! የለም !” አለች ባራባራ " “ጀምረሽዋል እኮ ጨርሺው አንጂ !
ሚስተር ካርላይል ወደ ክፍሉ ይሔዳል " ጉዴን አየኸው .... አርኪባልድ ? ይኸውልህ ተሰበረብኝ ”
ሚስተር ካርላይል የማዳም ቬንን ነጫጭ እጆችና የምትጠግነውን ዕቃ
እንደ ዋዛ አየት አድርጎ ወደ ራሱ መልበሻ ክፍል ሔደና በሩን ከፍቶ ባርባራን በጁ ጠቅሶ ጠራት ስትመጣ ሳብ አድርጎ አስገባት " ማዳም ቬን ሥራዋን
ቀጠሰች።

ባርባራ ቶሎ ተመልሳ ማዳም ቬን አጆቿን ከጓንቲዎ ስትከት ቁማበት
ወደ ነበረው ጠረጴዛ መጣች ዐይኖቿ ረጥበው ነበር "

“ዐይኖቼ የደስታ እንባ ሲያለቅሱ መግታት አልቻልኩም” አለቻት ባርባራ ምልክቱን እንዳየችባት ስትገነዘብ “ሚስተር ካርሳፈላይል ወንድሜ ነጻ መሆኑን ተከሳሾቹ አርስ በርላቸው መወነጃጀላቸውን ሎርድ ማውንት እስቨርንም ከችሎቱ መኖራቸውን ' አባባም ሰብሳቢ ሆኖ መዋሉን ነው አሁን የሚነግረኝ" አለቻት ' ለማዳም ቬን "

ማዳም ቬን ይበልጡን ወደ ያዘችው ሥራ አቀረቀረች "

“ማረጋገጫ ተገኘባቸው ? አለች ዝግ ባለ ደካማ ድምጿ "

“ የሌቪሰን ጥፋተኛነት ምንም አያጠራጥርም " ኦትዌይ ቤቴል ግን ምን
ያህል በነገሩ እንደ ገባ እስካሁን ገና አልታወቀም ግን ሁለቱም ለፍርድ እንዲቀርቡ ተወስኗል " በተለይ ያ እርኩስ ያ መናጢ ! በደሉ ሁሉ ባደባባይ ተገለጠበት” እያለች የደስታው ሲቃ ሲተናነቃት' ማዳም ቬን ቀና ብላ አየት አደረጋቻት

“ከሁሊ የሚገርመው ደግሞ ” አለች ባርባራ ድምጿን ዝቅ አድርጋ ''ያቺ
ክልፍልፍ አፊ ድፍን ዌስት ሊንና እኛ ሳንቀር ( ከሪቻርድ ጋር ኮበለለች ስንል
እሷ ግን ይህን ያህል ጊዜ ' ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር አንደ ነበረች ገና ዛሬ ሚስተር ቦል ሲያናዝዛት ታወቀባት ”

“መቸም እኔ ሚስተር ካርይል ቢሰማው ደስ አይለም እንጂ እሱም ልክ
እንደ ሎርድ ማውንት እስቨርን በጣም ነው የሚሰማው " ምንም ቢሆን ሚስቱ ነበረች » ይህን ታውቂያለሽ አይደለም ? ልጆቹም ሁሉ የሷ ናቸው " አሁን የተመሰገነና የተከበረ ነው • ወይዘሮ ሳቤላ የጣለችበትን የመሰለ : ውርደት ሊጠጋውና ሊነካው የማይችል ንጹሕ ሰው ነው ”

የመጀመሪያው እንግዳ ሠረገላ ሲገባ ተሰማ " ባርባራ በረረችና ከሚስተር
ካርላይል ክፍል አንኳኰታ “ አርኪባልድ ... ትሰማለህ ? አለችው "
“እሺ እመጣለሁ ደሞ እኮ አዲስ የሕዝብ እንደራሴ ለሆነ ሰው ትንሽ ጊዜ
አላት እየሣቀ

ባርባራ ያችን መከረኛ ሴትዮ በማጣበቂያው የተሰበረን የሽክላ ጌጥ
እየጠጋገነች : ጭንቀቱ ካላለቀለት ልቧ ጋር የቻለችውን ያህል እንድትታገል ትቴት ወደ ሳሎን ወረደች " ሁልጊዜ በማንኛው አጋጣሚ በነገር ስለት መወጋቱ አላቋርጥ አለ " ጠቅ ጠቅ በጊዜው በየምክንያቱ ጠቅ « መቸም እሷም ኢስት ሊን ለመመለስ የወሰነች ጊዜ ለቅጣቷ መቆሚያ እንዳይኖረው አድርጋዋለች " ዘለዓለም በትዝታ ' በነገር መወጋት ' በጸጸት አለንጋ መገረፍ ልማድ ሆነ።

ከሚስተርና ከሚስዝ ሔር በሸር እንግዶቹ ሁሉ ገቡ " ጆስቲስ ሔር ጤንነት
ስለ አልተሰማው ሁለቱም መቅረታቸውን የሚገልጽ ማስታወሻ ለባርባራ ደረሳት

ሳቤላ በሠራችው ሥራ ቅጣቷን እጅግ በከፋ አጠፌታ እንደ ተቀበለችው
ሁሉ ጀስቲስ ሔርም በመጠኑ የሥራ ዋጋ ሳይደርሰው አልቀረም " ስለዚህ ጤንነት ባይሰማው የሚያስግርም አይሆም " በማንኛው ነገር አንድ ጊዜ ተስቶት ከአፊ ፍቅር ሲይዘው በቀር ምንም የማያስቀይመውን ልጁን በድሎታል አንገላቶታል " የሱን ሥራ ዌስት ሊን አይዘነጋውም " ያ በልጁ ላይ ያሳየው ጥላቻ
አሁን ደግሞ መልኩን ለውጦ ደስ የማይል ኃይል ሆኖ ተመልሶበታል ሀይሉ
ከሕሊናው ጋር የመረረና የከረረ ጦርነት ገጥሟል "

“እእ...እኔ እኮ አሳድኜ አስገድየው ነበር ! አየሽ ' አን” አለ ጀስቲስ
ሔር ከወንበሩ ላይ ተቀምጦ ላቡን ከግንባሩ እየጠረገ ፥
👍122👏1
“አሁን እኮ ሁሉ ነገር ዐለፈ ...የኔ ሪቻርድ " አለችው ባሏን ወዳድ ደግ
ሚስቱ ዕንባዋ በአራት መዕዘን እየወረደ "

“እኔ ግን እሱ ከዚህ ግድም መጥቶ ቢሆን ኖሮ አልተወውም ነበር " በውነት አሳልፌ ለሞት እሰጠው ነበር !”

“አትዘን ሪቻርድ I ያለፌውን አታስብ ፤ እሱንም አንድ ቀን ከመኻከላችን አከቀምጠነው እናየው ይሆናል " ያን ጊዜ ሁለታችንም እንክሰዋለን „”

“እንዴት አድርገን እናገኘዋለን ? የት እንዳለስ ማን ያውቃል ? ምናልባት
ሞቶ ይሆናል።

“አለ አልሞተም " ጊዜው ሲፈቅድ እናግኘዋለን ሚስተር ካርይል ያለበትን ያውቃል ”

“ግን አሁንም እውነት መሆኑን እጠራጠራለሁ...አን " እውነት ጥፋት
ከሌለበት ለምን እስከ ዛሬ ቀርቦ ነጻነቱን እንዲያግኝ አልሞከረም ከወንጀሉ
ንጹሕ ነው ብለሽ ታስቢያለሽ ?

“ሪቻርድ ... ንጹሕነቱንስ ዐውቃለሁ” አለችው ፈግግ ብላ : “ እኔ ግና በፊት ነበር ያወቅሁት " ሚስተር ካርላይልም ደኅና አድርጎ ያውቃል ”

“በይ እንደዚህ ከሆነስ ደግ ነው " ሚስተር ካርላይልም ካመነበት ጥሩ ነው " ለመሆኑ መኝታውና ሌላውም የሚያስፈልገው ነገር ተዘጋጀለት ?

“ለማን ? አለች ሚ0ዝ ሔር

“ለሪቻርድ እንጂ ደሞ ለማን?”

“ምን ነካህ የኔ ፍቅር ? ነገር እየረሳህ ሔድክሳ ? ዛሬኮ ገና ምስክርነት ነው
የተሰማው ስለዚህ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሱም በነዚያም የሚሰጠው ፍርድ
ሳይታወቅ ሊመጣ አይችልም ”

“እህም እውነትሽ ነው ልጄ ” አለ ጀስቲስ ሔር "

ኢስት ሊን ላይ ግሩም የሆነ የራት ግብዣ ተደርጎ ነበር " የመጨረሻው እንግዳ ከመውጣቱ በፊት ዕኩለ ሌሊት ተደወለ ከዚያ በኋላ ሁለት ሰዓት ያህል ቆይቶ ሁሉ ነገር ጸጥ አለ " ሰው ሁሉ በየመኝታው ገብቶ እንቅልፍ ወሰደው
ጨረቃ ፀሐይ መስላ ወጣች " ብርሃኗ ቤቱን ሁሉ አጥለቀለቀው " የመተላለፊ
ያው ኮሪደሩ ደወል ጮኸ "

ከዚያ ሁሉ ቀድማ በንቃት ዊልሰን አንገቷን በመስኮት ብቅ አድርጋ ወደ ውጭ ተመለከተች „ “ እሳት ነው እንዴ ?” አለችና በጣም ጮኻ ጠየቀች "ዊልሰን እሳት የመፍራት ጠባይ ነበራት " ብዙ ጊዜ እንዲያው ከመሬት ተነሥታ
“እሳት ሸተተኝ እያለች ራሷ ደንግጣ ሌላውን ሁሉ ታስደነግጥ ነበር ።

ከዚያ ዊልስን አንድ ዓመት እንኳን ያልሞላው ልጅ በአንድ እጅዋ አንጠልጥላ
እሳት ! እሳት ! እያለች ትጮህ ጀመር " ከዊልያምና ከሎሲ መኝታ ቤቶች እየገባች ከየአልጋቸው እየጎተተች አወረደቻቸው » ቀጥላም የማዳም ቬንን
መዝጊያ ደበደበችው " ይኸን ሁሉ ስታደርግ “ እሳት ! እሳት ! ተቃጠልን
ነዶድን!” እያለች መጮኹዋን አላቆረጠችም ነበር" ሁሉም እየተደናገጡ የሌሊት ልብሶቻቸውን እንደ ለበሱ ወጡ " ማዳም ቬንም ቤቱ ግማሽ በግማሽ በእሳት የተያያዘ መሰላትና ባጠገቧ ያግኘችውን መደረቢያዋን አንሥታ ወጣች ከሷ ቀጥላ
ጆይስ ብቅ አለች ዊልሰን አሁን ግን ኧረ እሳት ! " እያለች ጩኸቷን ቀጠለች » ሰዎች ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሉዐበሚሯሯጡበት ጊዜ በእጃቸው የገባላቸውን ከማንጠልጠል በቀር የሚያስፈልጋቸውንና የማያስፈልጋቸውን የልብስ
ዐይነት ሊመርጡ አይችሉም » ስለዚህ ባርባራም የሌሊት ፒጃማዋን እንደ ለበሰች ወጣች "

ቀጠለና ሚስተር ካርላይል ወጣ " ወደ ደረጃው ቢመለከት ምንም እሳት
አልነበረም " ገና ባይደርስበት ነው አለና በዚያ በኩል ለማምለጥ የተመቸ ሆኖ ሲያገኘው ጊዜ ሮጠና ዐለፈ " በዙሪያው ከበው የነበሩት ሁሉ " አሳት ” እያሉ
በአንድ ድምፅ ይጮኻሉ - ነገር ግን ፍንትው ብላ ወጥታ ከነበረችው ጨረቃ
ብርሃን በቀር ሌላ ብርሃን አልታየም "

“እሳቱ የት አለ ? አለ ሚስተር ካርላይል " " እኔ እስካሁን ምንም አይታየኝም " ማነው መጀመሪያ እሳት ብሎ የጮኸው ?

አሁን ደወል ተደወለ " ሚስተር ካርላይል በአንድ መስኮት በኩል ወደ
ውጭ ተመለከተና “ ማነው? አለ " ማዳም ቬን ሕፃኑን አርኪባልድን አቅፋ ይዛ ነበር።

“እኔ ነኝ ..ጌታዬ ” አለ አንድ ሰው ከውጭ " ሚስተር ካርላይል ሰውየው የሚስተር ጆስቲስ ሔር አሽከር ጃስፐር መሆኑን በድምፁ ዐወቀው "ጌቶች
በድንገት ስለ ታመሙ ለናንተ እንድነግር እሜቴ ልከውኝ ነው » ጌታዬ... በነፍሳቸው ለመድረስ ቶሎ ብትመጡ ይሻላል ”

“ስማ ጃስፐር!” አለው ሚስተር ካርላይል. “ይህ ቤት በእሳት ተያይዟል?”

“ እኔ እንጃ . . . ጌታዬ እሳት የሚል ጩኸት እሰማለሁ ”

ሚስተር ካርላይል መስኮቱን ወግቶ ወደ ዊልስን ዞር በማለት: “ማነው እሳት ነው ያለሽ ? አላት

“ ይኽ ከበር ሆኖ የደወለው ሰውዬ አለችውና አየተንሰቀሰቀች “ ተመስገን
አምላኬ ! ልጆቹን ከመቃጠል አተረፍኳቸው " አለች "

ሚስተር ካርላይል በተፈጠረው ስሕተት በጣም ተበሳጨ » ሚስቱ የሌሊት ልብሷን እንደ ለበሰች ካጠገቡ ሁና ከግር እስከ ራሷ ትንዘፈዘፍ ጀመር እሱ ደግሞ በማንኛውም ምክንያት ቢሆን መደንገጥ በሌለባት ሁኔታ ላይ እንደ ነበረች ያውቅ ነበር » አሷም እንደ ደነገጠች ከሱ ላይ ልጥፍ አለች

ባርባራ ግና ከድንጋጤዋ ስላልተመለሰች እሱን ለቃ ባጠገባቸው የነበረውን
መሰኮት ልትከፍተው ሞከረች ሚስተር ካርይል ብርድ እንዳይመታት ሰግቶ
ይንደረደርና በአንድ እጁ እሷን ይዞ ቀሌላው እጁ መስኮቱን ዘጋው ከዚያ ወደ
መኝታ ቤት ወስዶ ጃስፐር የመጣበትን ነገር አለሳልሶ ነገራት " እሷ ማመን አቃታት በእውነት አባቷ በሕይወት ያለ አልመስላትም " የሆነ ሆኖ ለመሔድ መዘጋጀት ጀመሩ "

በዚህ ጊዜ ዊልያም ትዝ አላትና ባርባራ ወደ ኮሬደሩ ስትሮጥ ብትሔድ ቁሞ
ሲንቀቀጥ አገኘችው ከሷ ሌላ ማንም ያሰበው አልነበረም " “ ወይ ጕድ
ሙቶ ነበር እንጂ ” አለችና ከቆመበት አፈፍ አድርጋ አነሣችው “ ዊልሰን ምነው እንደዚህ ታደርጊያለሽ? የሌሊት ልብሱ ብስብስ ብሎ ረጥቦ በረዶ ሆኗል”
ብላ ጮኸችባት "

ልጁን አቅፋ ከመኝታ ቤቱ ልታደርሰው ዐቅም ስለ አጣች ወደ መኝታዋ ወሰደችው " ዊልሰን በበኩሏ ወቀሳና ተግሣጽ ለመስማት ጊዜ አልነበራትም "በረንዳ ማገር ተደግፋ ከጃስፐር ጋር የቃሳት ጦርነት ጀምራ ነበር

“ እኔ መቸ እሳት ተነሳ ብዬ ነገርኰሽ ? አላት ቆጣ ብሎ

ነግረኽኛል " ምነው መስኮት ከፈትኩና “እሳት ነወይ” ብዬ ብጠይቅህ
አዎን አላልከኝም

"ጃስፐር ነህ ወይ ብለሽ ስትጣሪ አዎን” ኤልኩሽ ሌላ ምን ልል ኖሯል?

እሷ እሳት ነወይ' ስትል 'ጃስፐር ነህ ወይ ያለችው መስሎት 'አዎን እንዳላት ግልጽ ሆነ "

ዊልሰን ልጆቹን አስተኚያቸው " አለ ሚስተር ካርይል ጠበቅ ባለ ትዛዝ … " ጆን..ዝጉን ሠሪገላ ቶሎ ጫነው " አባክሺን ፈጠን በይ " ማዳም ቬን " መደፊት ይህንን ከባድ ልጅ አንሥተሽ መያዝሺን ተይ ጆይስ. . .ምናለ ብትቀቢያትና ብታሳርፊያት ?”

ሚስተሮ ካርይልም ወደ መኝታ ቤቱ ሲመለስ በማዳም ቬን አጠግብ ዐለፈ ክፉኛ ስትንቀጠቀጥ አያት " እስካሁን የሁከቱ ምክንያት አልግባትም ከድንጋጤዋም አልተመለሰችም " ጆይስም ብትሆን ነገሩ እንደሷው አልገባትም"እሷም
ከድንጋጤዋ አልተመለሰችም ከራሷ አስጠግታ ይዛት ቁማ የነበረችውን ሎሲን
ትታ አርኪባልድን ለመቀበል ሔደች " ሚስተር ካርላይል ሚስቱ ዘንድ ገባ ሚስዝ ካርላይል የሌሊት ልብሷን አውልቃ ዊልያም ላይ ጣል አደረገችበትና መብራት አብርታ መልበስ ጀመረች "
👍11👏1
“ የሌሊት ልብሱን በጅህ ንካውማ አርኪባልድ | ይህች ዊልሰን ” ስትል ሌላ ጩኽት ነገሯን አቋረጣትና ሚስተር ካርላይል ዘሎ ወጣ " ባርባራ ተከተለችው " ዊልሰን ሕፃኑን መተላለፊያው ላይ የጣለችው መሰላት " ነገሩ ግን ሌላ ነበር ዊልሰን ሕፃኑን አቅፋ ሉሲን ይዛ በደረጃው ወጥታ ወደ መኝታቸው ከወሰደቻቸው ቆየት ብላ ነበር " ማዳም ቬንም በመግባት ላይ ነበረች » አርኪባልድ ከኮሪደሩ ሥጋጃ ላይ ተጋድሟል " ጆይስ ልጁን አንሥታ ለመውስድ ብድግ ስታደርገው አንድ ነገር ድንገት አስደነገጣትና በቁሟ ለቀቀችው » የበረንዳውን ማገር ተደግፋ ፊቷን በጣር የተያዘች አስመስላ አፋን ከፍታ ዐይኖቿን አፍጥጣ
ቆመች " አርኪባልድ ከወደቀበት ቀስ ብሎ ተነሥቶ በጠንካራ እግሮቹ ቀጥ ብሎ ቆመ።

“ምነው ጆይስ .. .ምን ነካሽ ? ጣረምት ያየሽ ትመስያለሽ ?” አላት
ሚስተር ካርላይል አዬ ጌታዬ ! አለች እየተርበተበተች !“ አይቸማ ነው ! ”

“ሁላችሁም ባንድነት ማበዳችሁ ነው ? አላት በቤቱ ምን ዐይነት ግራ
መጋባት እንደ ወረደበት እየተገረመ „ “ ጣረሞት አየሁ ? ጆይስ

ጆይስ መቆም ያቃታት ይመስል ተንበረከከች - የሚንቀጠቀጡት እጆን
ከደረቷ ላይ አመሳቀለች » በቤቱ ልበኛና ታማኝ በቀላሉ የማትበገር የረጋች
ሠራተኛ ነበረች » ሚስተር ካርላይል ፈዞ በጣም ተገርሞ ተመለከታት "

ጆይስ..ምን ሆነሽ ነው ? ” አላት ወደሷ ጐንበስ ብሎ በርኅሩህ አነጋግሩ "

እግዚኦ ጌታዬ ... ሁላችንም ይቅር በለን !” ብቻ ነበር መልሷ"

ጆይስ . . . ምን ሆንሽ እኮ ነው የምልሽ ?”

“መልስ አልሰጠችውም እየተንቀጠቀጠች ተነሳች " የአርኪባልድን እጅ ይዛ
ቀስ እያለች ወደ ፎቅ ወጣች

“ ምን አግኝቷት ይሆን ?” አለች ባርባራ በዐይኗ እየተክታተለቻት "
ጣረሞት ስትል ምን ማለቷ ነው ?” አለች በጆሮው "

" የጣረሞት ታሪክ ስታነብ ቆይታ ይሆናል” አለ ሚስተር ካርላይል »

“የዊልሰን መንቀዥቀዥ እኮ ቤቱን አተረማመሰው ቶሎ በይ ባርባራ እንሒድ!”....

💫ይቀጥላል💫
👍15👎1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ፀደይ ዐለፈ " በጋ ተተካ " እሱም ያልፋል : አሁን ሞቃቶቹ የሰኔ ቀኖች
ገብተዋልና መውጫቸውም ይደርሳል " ሚስተር ካርላይል ከተመረጠበት ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ወሮች ሲለዋወጡ ምን ክሥተቶች ታይተውባቸዋል ?

የሚስተር ሔር በሽታ ከመሰለል አደረሰው " ሰዎች ልጅን ያለአግባብ
ሲበድሉ ኖረው መሳሳታቸውን በሚገነዘበቡት ጊዜ ' ' ተሳስቼ ኖሯል በማለት ብቻ የጃቸውን ሳያገኙ ይቀራሉ ማለት ዘበት ነው " ይህ ሁኔታ በሚስ ጀስቲስ ሔር
ላይም ታይቷል ። ከበሽታው በጎ እየሆነ ሔዷል " ነገር ግን የበፊቱ ጀስቲስ ሄር መሆን አይችልም : ጃስፐር የጌታውን መታመም ሊነግር ኢስት ሊን ሔዶ በነበረ ጊዜ የተፈጠረው የእሳት ድንጋጤም ከዊልያምና ከጆይስ በቀር ማንንም አልጐዳም " ዊልያምን ብርድ መታውና የሳንባ በሽታውን አባባሰበት ጆይስ ከዚያ ወዲህ ፍራት አደረባት " በውኗ እያለች በሕልም ያለች ትመስላለች " ድንገት ሲናገሯት ትበረግጋለች አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰዓት
ሙሉ ሐሳቧ ይዟት ጭልጥ ይላል።

ሚስተር ካርላይልና ሚስቱ የሚስተር ሔር በሽታ ለክፉ እንደማይሰጠውዐእንዴረጋገጡ ወዲያውም ወደ ለንደን ሔዱ : ዊልያም አባቱ ከሱ እንዲለየው ስላልፈለገና የለንደን ሐኪሞች እርዳታ ይጠቅመው ይሆናል በማሉት አብሮ ሄዷል " ጆይስ ከሌሎች ሠራተኞች ጋር ተከትላ ሔዳለች "

ለንደን ሲደርሱ የስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መያዝ አፍላ ወሬ ሆኖ አገኙት "
ነገሩ ለለንደን ስዎች ሊገባቸው አልቻለም : ብዙ የማይመስሉና የማይሆኑ ነገሮች ሲወሩ ዜናው ለዘጠኝ ቀኖች ያህል ብርቅና ድንቅ ሆኖ ሰነበተ እነሱ ለንደን የገቡ ዕለት ማታ አንዲት ልጅ እግር ቆንጆ ሴት፡ ንገሩልኝ ብላ እነሱ ከነበሩበት ክፍል ገባች ስሟን መግለጽ ባትፈልግም ሚስተር ካርላይል ሲያያት
የመጀመሪያ ሚስቱ ባልንጀራ የነበረችው የብላንሽ ሻሎነር መልክ ትዝ አለው እሷ ግን ብላንሽ አልነበረችም "

እንግዳይቱ ባርኔጣውን በጁ ይዞ ሊወጣ ቁሞ ያገኘችውን ሚስተር ካርላይልን እያየች ' “ በአጉል ሰዓት በማስቸገሬ ይቅርታ ያድርጉልኝ " የመጣሁት አንድ የሰው ልጅ ከሌላው ለማግኘት የሚፈልገውን እርዳታ ለመለመን ነው " እኔ
አመቤት ሌቪሰን ነኝ ” አለችው"

ባርባራ ፊቷ ደም መስለ ። ሚስተር ካርላይል እንግዳይቱን በአክብሮት
ወንበር ላይ አስቀምጦ እሱ ቈሞ ዝም አለ ። እሷም ትንሽ ተቀምጣ ከመጨነቋ የተነሳ ተመልሳ ብድግ አለች

“ኣዎንታ እኔ ያን ሰው ባሌ ለማለት የተገደድኩት እመቤት ሌሺሰን ነኝ " ክፋቱን በፊትም ዐውቀዋለሁ አሁን ደግሞ ወንጀለኛ ሆነ ይባላል ትክክለኛነቱን ግን የሚያረጋግጥልኝ አጣሁ " ሎርድ ማውንት እስቨርን ዘንድ ሑጄ ብጠይቃቸውም ሊነግሩኝ አልፈቀዱም " ስለዚህ ሚስተር ካርላይል ዛሬ ለንደን ይገባሉ ሲባል ስምቸ ለመጠየቅ መጣሀ "
ስትናገር ሰውነቷ እየተርገፈገጸ ድምጿ እየተቆራረጠ ስለ ነበር ከውስጧ የሚገነፍልባት የስሜት ግፊት ይታወቅባት ነበር "

“ ይህ ሰው ሁለታችንንም በድሎናል ...ሚስተር ካርላይል ሰውየው እንዲበድለኝ ያደረግሁ እኔ በገዛ እጄ ነው እርስዎ ግን አይደሉም « የሱ በደል
የደረሰባት እኅቴና አሁን ዘጠና ዓመት የሚጠጋቸው አያቱ ሚስዝ ሌቪሰን አስ
ጠንቅቀውኝ ነበር ከማግባቴ አንድ ቀን ቀደም ብለው አያቱ እኔ ድረስ ለዚ
ሲሉ መጥተው ፍራንሲዝ ሌቪስን ባገባ ዕድሜ ልኬን ሳለቅስ አንደምኖር አሁንም የገባሁትን ቃል ለማጠፍ በቂ ጊዜ እንደ ነበረኝ ሲነግሩኝ አልተቀበልኳቸውም " ጊዜ ነበረኝ ፍላጎት ግን አልነበረኝም " በግብዝነት ' በሞኝነት በተለይም ለመካር እኅቴ እልክ ስል አገባሁት የሱን ስም የሚወርስ ልጅም ወልጃለሁ ... ይፈርድበት ይሆን ሚስተር ካርላይል ?”

እስከ አሁን በደንብ የተረጋገጠበት ነገር የለም” አላት ሁኔታዋ እያሳዘነው

“አሁን ከሱ የምፋታበትን መንገድ ባገኘሁ " አለች ራሷን መቈጣጠር እንደ ተሳናት በግልጽ እየታየባት “ የልጄን ስም መለወጥ ብችል እንግዲህ ይህን የገባሁበትን ዘንቅ ለማረም የቀረኝ ዕድል ይኖር ይሆን ?”

ምንም አልነበራትም ። ሚስተር ካርላይልም መላ መናገር አልሞከረም "
ጥቂት የማስተዛዘኛ ቃላት ተናግሮ ሊወጣ ሲል ዐለፈችና ከፊቱ ቆመች

ለዚህ መፍትሔ ሳይነግሩኝ አይውጡብኝ ። እርስዎን አምኘ መልስ እንዶገማኝ ተስፋ አድርጌ ነው የመጣሁት

“ከባድ ቀጠሮ አለብኝ " ባይኖረኝም በራሴም ሆነ ባንቺ ምክንያት መልስ
ልስጥሽ አልፈቅድም ነበር " ነገርሽን እንዳቃለልኩብሽ አድርገሽ አትይው
እመቤት ሌቪሰን ስለ ሰውዬው ግን ላንቺ እንኳን ስናገር ስሙ ራሱ ከንፈሮቼን
ያቆስልብኛል

እርስዎ የሚናገሩት እያንዳንዱ የጥላቻ ቃል ' ቃሌ ነው የርሶዎን የንቀት አባባል ሁሉ ተቀብዬ አስተጋባለሁ ”

ባርባራ ዘገነናት ምንም ቢሆን እኮ ባልሽ ነው ! " አለቻት "ባርባራ

“ባሌ ! የበደለኝን በደልሳ ዐውቀሺዋል ? እሱ ራሱ ምን እንደ ነበርና ምን
እንዳደረገ እያወቀ ለምን ሚስት እንድሆን አሳሳተኝ ? አንቺም እንደኔ ሚስትም
እናትም ስለሆንሽ
እንደገና...ሚስዝ ካርላይል በደሌ ሊገባሽና ልታዝኝልኝ ይገባል" እነዚህ መጥፎ ሰዎች ለምን ያገባሉ ? ወንጀሉ ሕሊናውን እያኘከው
እኔን ለማግባት ሰብኮ ሰብኮ ያሳሳተኝ! ያለፈው ኃጢአቱ አነሰው የማይቴረም ከባድ ግፍ ውሎብኛል " በልጄም ላይ ተፍቆ የማይጣል አሳፋሪ ውርደት ጥሎ
በታል ”

“ ቢሆንም ባልሽ ነው
አለቻት ባርባራ "

“ እታሎኝ እኮ ነሙ ባሌ የሆነው " ስለዚህ በአደባባይ ብጠላው የሚያግደኝ የሞራል ግዴታ የለብኝም " በኔና በልጁ ይህ ነው የማይባል ጥፋትና ክፋት አድርሶብናል ኧረ ለመሆኑ” አለች ወደ ሚስተር ካርላይል ዞር ብላ' “ከእርስዎ ጋር ለመወዳደር ዌስት ሊን ሲመጣ እንዴት አስቻለዎትና ዝም አሉት

“እሱን ልነግርሽ አልችልም » ለራሴም ብዙ ጊዜ ሳስበ ገርሞኛል” አላትና በትሕትና አነጋግሮ ከሚስቱ ጋር ትቷት ሔደ " ሁለቱ ሴቶች ብቻቸውን ሲቀሩ' ባርባራ የሚስዝ ሌቪሰንን ጥያቄ ባጠቃላይ መልኩ ባጭሩ ገለጸችላት

“አንቺና ሚስተር ካርላይል በጥፋተኛነቱ አምናችሁበታል ? አለቻት "
“ አዎን ” ያንቺ የመጀመሪያ ሚስቱ ሳቤላ ቬን ዕብድ ነበረች ?
"ዕብድ ? አለች ባርባራ በመገረም "

' አዎን ' ሚስተር ካርላይልን በሱ መለወጧ!እሱን ለዚያኛው መለወጧ
ዕብዶት እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል ? አንዲት ሴት ከቪሰን ከድታ ሚስተር ካርላይልን አፍቅራ ብትሔድ ሊገባኝ ይችላል ? አሁን ያንቺን ባል ሳየው በተለይ እሱን ጥሎ ወደ ሌቪሰን የሚሔድበት ምክንያት ሊገባኝ አይችልም”
አለቻት » ከዚያ ጥቂት ተነጋግረው አሊስ ሌቪሰን ወጥታ ሔደች "

በርባራ ' ሦስት ሳምንት ያህል ለንደን ቆይታ ለጤንነቷ ለምቾቷ ተብሎ ወደ ኢስት ሊን ተመለሰች ሚስተር ካርላይልም ለንደን ከቆየ በኋላ በሐምሌ ጠቅልሎ ሲመጣ አንድ ወር የሞላት ሴት ልጅ ተወልዳ ቆየችው :

የዊልያም ሁኔታ አሽቆልቁሎ ሔደ " የዶክተር ማርቲን አባባል የለንደኑ
ሐኪምም አረጋግጦ ደገመው " ስለዚህ መጨረሻው ብዙ እንደማይቆይ ግልጽ
እየሆነ ሔደ"
👍16
አንድ ሌላ ሰውም እየከሰመ ይሔድ ነበር ሳቤላ የተሸከመችው የሥቃይ መስቀል ከመጠን ያለፈ ሆኖ ስለ ከበዳት ቁልቁል እየሰጠመችና በሥቃይ ጭነት እየደቀቀች ትሔድ ጀመር። ወደ ኢስት ሊን ልትመለስ ስትል እንዳሰበችው ያን ክብደት
በትግሥት ለመሸከም ብትጥር ኖሮ ነገሩ ሊለወጥ ይችል ነበር " እሷ ግን አስባ
ለራሷ የገባችውን ቃል ማክበር አልቻለችም " የሽክሟን ክብደት በዝምታ አልተቀበለችውም " ታገለችው !ዐመፀችበት " ይህም ከዐቅም በላይ የሆነ ከባድ ትግል ሕይወትን ያህል ዋጋ የሚጠይቅ ሆኖ ተገኘ" ወደ ኢስት ሊን ከተመለስች ጀምሮ በየሰዓቱ በየቀኑ ልዩ ልዩ ሰበቦች በማየትና በመስማት ልቧን እያነጠረ አንጀቷን እያሳረረ " ፊቷን አየቀያየረ ሲያስጨንቃትና ሲያንገበግባት ይውል
የነበረው ስሜት ሚስተርና ሚስዝ ካርላይል ወደ ለንደን ሲሔዱ ጋብ ብሎላት
ነበር ከዚያ በኋላ ደግሞ ከፊተኛው ስሜቷ ጋር የሚፃረር አዲስ ስሜት አደረባት መቁረጫ የሌለው የአእምሮ መትከንከን ስሜትና ትንቅንቅ ሁሉ ለቆ በቦታው ተስፋ መቁረጥና ደንታ ቢስነት ተተካበት " ስሜቷ ተግ እያለ ብስጭትጭት ያደርጋት የነበረው ቀረና በሚያስደነግጥ ፍጥነት መስጠም ጀመረች የሚያሠጋ በሺታ አልታየባትም እሷ ግን ከቀን ወደ ቀን እየመነመነችና እየሰለስለች ሔደች ይሁንና አዲሱን የአካልና የመንፈስ ለውጥ የተነገነዘበ አልነበረም " አንዳንድ ጊዜ ዊልያም ዘንድ ብቅ እያለች ጥቂት ጊዜ ብታሳልፍም ሎሲን የማስተማር ተግባሯን በሚገባ ትፈጽም ነበር "

አንድ ቀን ፀሐዩ እንደ እሳት በሚቃጥልበት በሐምሌ ውስጥ አፊ ሆሊጆን ከምን ጊዜም የበለጠ ሽክ ብላ ለብሳ በመንግዱ እየተሽከረhረች ትጓዛለች » አፊ በተለይ ከምርመራው በኋላ በብዙ ሰው ዘንድ
ከበፊቱ የበለጠ ተንቃ ነበር
ሚስዝ ላቲመር እንኳን በሷ ላይ የነበራትን እምነት ለወጠች " የአንድ ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ስጥታ አሰናበተቻት "

በያቅጣጫው ዐይንሽ
ላፈር በተባለችበት ጊዜ ሚስተር ጂፊን ፊት ግን ደፍሮ ስለሷ ክፉ የሚያነሳ ሰው ቢግኝ እንኳን ምንም
ቢደረግ አይሰማውም አይቀበለውም " ዌስት ሊኖችን ቅጣፊዎች ለራሷ መልአክ ናት” ይላቸው ነበር

በመንገዱ እየተንሳፈፈች በሚስተር ጂፊን ቤት አጠገብ ስታልፍ እሷን ለመቀበል ይደረግ የነበረውን የቤት እድሳት ተመልክታ ደስ አላት " ሁልጊዜ በዚያ በኩል ባለፈች ቁጥር አንዳንድ ነገር እንዲሟላ ስትጠቁመው በደስታ የሚፍነከነከው የወደፊቱ ሙሽራ ወዲያው ይፈጽማል ባቡር በመጣ ቁጥር ልዩ ልዩ የቤት ዕቃዎች በጥቅል በጥቅል እየሆኑ ይመጡለታል “

እዕድገቱ እኮ በደንብ ቀጥሏል.. ሚስ አፊ በዚህ ሳምንት ያልቃል የሳሎኑ ጌጥ ብታይው መቸም ሌላ ነው " እንግባና እይው እስቲ ” አላት

"እንዴ ! ከአንተ ጋር ልገባ ? ዌስት ሊን ምን ይለናል ?”

“ የሚከፋሽ ከሆነስ ይቅር :ይቅርታ አድርጊልኝ ሚስ አፊ

“ እንዲያው በፈጠረህ ይህን ነጭ ሽርጥህን ብትጥለው ምነው ?

“ ይህ አስቸጋሪ ነገር ነው " የጠየቅሺኝን ሁሉ እንደምፈጽምልሽ ታኸ
ዉቂያለሽ » አሁን ይህን ባወልቀው ግን ከሥሩ ያለው ልብሴ እንዴት እንደሚበላሽ
ጠፋሽ ? የሰደርያየን ነገርማ ተይው አየሽ ቅቤ ከመያዣው እየከፈልኩ
ስሸጥ የዓሣማውን ሥጋ ስቆርጥ ዓይቡን ስለካ የዓሣማው ሥጋ በበርሜል
የተነከረበት ሆምጣጤ ሲረጨኝ ሌላም ሌላም ብዙ አስቸጋሪ ሥራዎች አሉ "
ስለዚህ ሚስ አፊ ሽርጤን ካወለቅሁ በየሳምንቱ አዲስ ልብስ ብለብስም ንጹሕ
ልሆን አልችልም ” ብሎ ገለጸላትና የንግግራቸውን ርዕስ ለመለወጥ ሲል
ብቻ ነገ ጧት ወደ ሊንበራ ትሔጃለሽ ?” አላት ።

“ የታወቀ አይደል ብዙዎቻችን እንሔዳለን ። ፍርዱ የሚጀመረው በሦስት ሰዓት ነው " ስለ ሪቻርድ ሔር የሚወራውን ሰምተሃል ?”

“የለም ” አለ ጃፊን “ ምን ወሬ ነው እሱ ?”

" እሱም ለፍርድ ሊቀርብ ነው እያለ ዌስት ሊን ያወራል

“ ለመሆኑ አለ እንዴ ? አለ ሚስተር ጂፊን "

“እኔ ስለሱ ምንም አላውቅም " በቅርቡ ሙቷል እየተባለ ሲወራ ታውቃለህ ጥፋተኛው እሱ ወይም ሌቪሰን ቢሆኑ ግድ የለኝም " ምንጊዜም አነሱ
እንደማይረቡ ዐውቃቸዋለሁ " እነሱን ላስጠጋቸው ቀርቶ በረጂም አንጨት
እንኳን አልነካቸውም
አለችው

ከጂፊን ተሰነባብታ ጥቂት እንደ ሔዶች ከሚስተር ካርላይል ጋር ተገናናኙ "

“ ታዲያስ አፊ . . .ልታገቢ ነው አሉ ”አላት "

ጀፊን ያስባል እኔ ግን ምናልባት ሐሳቤን እለውጥ ይሆናል . ገና እርግጠኛ አደለሁም እርሱም ደሞ እንደኔ ያለች ሴት የተፈጠረች አይመለውም
ብርና ወርቅ የምበላ ብሆን ያቀርብልኝ ነበር " ሰውዬው እንደ ነዱት ነው „

“ላንቺ ነው እንደ ነዳሺው የሚሆንልሽ እንጂ እሱ በኔ አስተያየት ሥነ ሥርዓት ያለውና የተወደደ ሰው ነው

“እኔ ከመጀመሪያ ክብር ያለው ከፍ ያለ ሰው እንጂ ከሱቅ ተቀምጦ ሲቸረችር የሚውል ባል ለማግባት ሐሳብ አልነበረኝም " እንዲያውም . . ነጭ ሽርጥ አስሮ የሚውል ባል።

"ይገርማል ! አላት ሚስተር ካርላይል ፊቱን ቁጥር አድርጎ

" ቢሆንም ከፍቶም አይከፋ ” አለችው መልሳ . “ ቤቱን ዘመናዊ አድርጎ እያሠራ ነው " ሁለት ጥሩ ጥሩ ሠራተኞች እቀጥርና እኔ ቁጭ ብዬ ልብስ
መቀየር ' ከቤተ መጻሕፍት ማኅበርተኛ ሁኜ መመዝግብ "ገንዘብ እንደሆነ ሞልቶታል
አለች አፊ።

“ገንዘቡን እንዳትጨርሽበት ተጠንቀቂ . : .አፊ ” አላት

“ለዚያ ግድ የለም እጠነቀቅበታለሁ .....

💫ይቀጥላል💫
👍151🥰1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ሶስት (23)

«ደግ ። ቢያንስ ስሙ ማጠሩንና መጥበቡን ለመለካት ይረዳኛል ፤ ባደባባይ ከመልበሴ በፊት » አለች ። ሁለቱም ደስ ብሏቸዋል ። ሁለቱም የሆነ የመደባበቅ ስሜት ይታይባቸዋል ። ሁለቱም»
ሂሣባቸውን ከፍለው ከሆቴሉ ወጡ። መኪናው ዘንድ ሲደርሱ ፍሬድ አይቷቸው ሲጨፍር ተመለከቱት ። ፍሬድ በእሁድ እሁድ ሽርሽር ላይ ተካፋይ ነው። ሁሌም በምሳ ሰዓት እመኪናው ውስጥ ይጠብቃቸዋል ። ሽርሽር ሲሄዱ ግን አብሯቸው ይሄዳል። የመኪናው በር ተከፍቶለት ከወጣና የውሻ ሰላምታውን ካቀረበላቸው በኋላ ተከተላቸው ። «እንዴት ነው ፤ ደከመሽ!? » አለ ፒተር ፤ ለአንድ ሰዓት ያህል በእግራቸው ከተጓዙ በኋላ ። «እንመለስ? ወይስ እንቀጥል?»
«እንመለስ ማለቱ ትንሽ ቢያሳፍርም መመለሱ አይከፋም» አለች። «ምን አሳፈረሽ ሜሪ? እስከ አመት ድረስ እኔና አንች የሩጫ ውድድር ብንጋጠም ጥለሺኝ እንደምትሄጂ እያወኩት» አለ ፒተር፡፡ ትቀድሚኛለሽ ስላላትም፤ በአዲስ ስሟ ሲጠራት ዘላለም በዚያ ስም ሲጠራት የኖረ ያህል ስለጠራትም ተገርማ ሳቀች። «የሩጫውን ውድድር ተቀብያለሁ» አለች። «እትጠራጠሪ ታሸነፊኛለሽ። ከኔ የምትሻይበት ነገር አለሻ»
‹‹ምን ? »
«ወጣትነት ፤ ጥንካሬ»
«አንተስ? አንተም ገና ወጣት ነህ» ይህን ያለችው ከልቧ ነበረና ራሱን በአሉታ እየነቀነቀ ሳቅባት። «እንዲህ አፅናኚኝ እንጂ። ምን ጊዜም ይህን አይንሽን አይቀይርብኝ፤ የኔዋ ተወዳጅ» አለ ። እንዲህ ብሎ አይኑን እወዲያ ላይ ተከለ ። እንዲያ ወዲያ ወዲያ ሲያይ በፊቱ ላይ አንድ አይነት የትካዜ ጥላ ያንዣብበት ነበር ። የትካዜውን ጥላ ናንሲ ያየችው እንደ ውልብታ ብቻ ቢሆንም አይታዋለች ። የተከዘበት ምክንያቱም ገብቷታል ። የዕድሜው ጉዳይ ነበር ። ምንም እንኳን በመካከላቸው ያለውን የ24 ዓመት የእድሜ ልዩነት እንዳለ ባትቆጥረው ልዩነቱ ግን እንዳለ ገባት። ይግባት እንጂ አልተከፋችም። እንዲያውም የልዩነቱን መኖር የምትወደው ይመስላታል። ይህንንም ደጋግማ ለፒተር ነግራዋለች። አንዳንድ ቀን ይቀበላትና ደስ ይለዋል ። አንዳንድ ቀን ግን ይከፋዋል ። እንደተነገረበት እለት የባህርይ ይዞታው ይለዋወጣል ። ይህ ደግሞ ለፒተር አዲስ አይደለም ። ከዚህ በፊትም አጋጥሞታል ። ስንት ጊዜ ነው አስር ወይም ሃያ ዓመት ያህል እድሜው ዝቅ ቢል የተመኘው ?

«ናንሲ» አለ ፒተር አዲሱን ስሟን ፈፅሞ ዘንግቶ ።
«አቤት»
«ናንሲ. . . እስቲ ንገሪኝ. . . ማለት. . . አሁንም. . . ማለት እስከ ዛሬ ታስታውሺዋለሽ? . . . ማለት ይናፍቅሻል ?» እፊቱ ላይ የተሳለውን ጭንቀትና ስቃይ ስታይ አዘነችለት። አንገቱን እቅፍ አድርጋ በአሉታ ልትመልስለት ፈለገች፣ ለማፅናናት ። ግን ደግሞ ከበዳት ። ለፒተር ውሸት መንገሩ ከማንኛውም ነገር የከበደ ሆኖ ታያት ። «አዎ አንዳንዴ... ሁልጊዜ ግን አይደለም» አለች፡፡ «አሁንም ፍቅሩ አልለቀቀሽም?»

ቀና ብላ አየችው፤ ከመመለሷ በፊት ። አይኑን ትኩር ብላ ተመለከተች። ከዚያም እንዲህ ስትል ጥያቄውን መለሰችለት ። «እኔ እንጃ ። በቅጡ እማውቀው ነገር የለም. . .ግን ምን መሰለህ… አንዳንዴ ሳስበው ሁሉ ነገር ህልም መስሎ ይታየኛል። ለምን ብትለኝ፤ ዛሬ እሱም እሱ አይደለ ። እኔም እኔ አይደለሁ። ተለውጠናል ። አደጋው እሁለታችንም ላይ ምልክት ጥሎ ያለፈ ይመስለኛል ። ማለት እሱም ጠባሳ ይኖርበት ይሆናል ። ምናልባት እኮ አየህ ያ ጠባሳ ያጠፋውን ይሆናል እወደው የነበረው፡፡ እሱም እኔ ላይ ይወደው የነበረውን ነገር ሊያጣ ይችላል ። ያ የሚወደው ነገር ተሰርዞ ይሆናል ። እና ብንገናኝ ፤ ብንተያይ የሚያስተሳስረን የነበረውን ነገር ልናጣው እንችል ይሆናል ። ስለዚህ አሁንም ማይክልን አፈቅረዋለሁ ማለት ይከብደኛል ። ህልም ነው። ያለፈ ጊዜ ትዝታ የዛሬ እውነት ሊሆን አይችልም ። ይህን ሳስብ ምነው አንዴ በተገናኘንና ባየሁት ፤ በወጣልኝ እላለሁ ። አሁን አሁን ግን ገብቶኛል ። ላገኘው... . ፤ ላየው እንደማልችል ገብቶኛል» አለች ቃላቱን ለመናገር እየተቸገረች ።
ዝምታ…..

«ህልም ነው» አለች ቆይታ «እና ወዳሁኑ ፤ህልሙን ራሱን ላለማሰብ ቆርጫለሁ»
«ያማ ... እንዲህ በቀላሉ መቼ ይቻላል» አለ ፒተር። ይህን ሲናገር አይኖቹ በሀዘን ተሰብረው ነበር ። የነገረችው ሁሉ እንደገባው ስለተረዳች ገረማት። ምናልባት እሱም የኔ አይነት ችግር ደርሶበት ነበር ይሆን? መሆን አለበት ። ያ ባይሆን የምነግረው ነገር እንዲህ በቀላሉ ሊገባው፤ ይህን ያህል ሊሰማው አይችልም ነበር፡፡ አለች በሀሳቧ እና ፣ «ፒተር» አለች ። «ፒተር ለምንድነው ሚስት ሳታገባ የኖርከው?» ጎን ለጎን በፀጥታ ጉዟቸውን ቀጠሉ ። ፍሬድ ኋላ ኃላቸው ቱስ ቱስ ይላል ። ፈፅመው ዘንግተውታል ። ፀጥታው ሲገን ጊዜ «ወይስ መጠየቅ አልነበረብኝም ? » አለች ናንሲ ። «መጠየቅሽ ምንም ጥፋት የለበትም ። መልሱን ግን በቅጡ እማውቀው አይመስለኝም» ሲል መለሰላት። ቀጥሎም ‹‹ምክንያቱም ብዙ ነገር አለ» አለ ። «ምናልባት ራሴን በጣም ስለምወድ ሊሆን ይችላል ። አየሽ ሚስት አግብቼ ለሷ ማሰብ ይከብደኝ ይሆናል። ምናልባትም ስራዬን ስለምወድ ይሆናል። ምርምሬን ለማካሄድ ስፈልግ ሴት መሰናክል ትሆናለች ብዬ በማሰብ ማለቴ ነው፡፡ አይታወቅም ። ምናልባትም ረግቼ መቀመጥ የምችል ሰው ስላልሆንኩ . . .ወይም ያልኩሽ ሁሉ ባንድነት ሆነው...»

«የተባለው ሁሉ ግን ለኔ እውነት ሊመስለኝ አልቻለም» አለች ናንሲ በአቅርቦት እያየችውና የነቅቸብሀለሁ… ዋሽትሀል ፈገግታ እያሳየችው። «ልክ ነሽ። የነገርኩሽ ሁሉ የምገምተው ነው እንጂ እኔም ራሴ እማምንበት አይደለም ። ያም ሆኖ ግን አንዳንድ እውነትም አይጠፋበትም » ይህን ብሎ ለረጂም ጊዜ ቆየና በረጅሙ ተንፍሶ የሚከተለውን አጫወታት ።

«ሌሎች ምክንያቶችም አሉ» አለና እንደገና በረጂሙ ተነፈሰ «አንደኛው ምክንያት ፍቅር ነው ። እስራ ሁለት ዓመት የወሰደ ፍቅር ። የወደድኳትን ሴት የተዋወቅኋት ሐኪም ቤት በታካሚነት ገብታ ነው ። እንዳየኋት ልቤ ትርትር እለ ። ግን ልቤን ተው አልኩት ። ተው እንጂ እንዲህ ዝም ብሎ መፍሰስ ምን ይባላል ? አልኩት ። እሷ ደግሞ ይህ መሆኑን ያወቀችው በኋላ ነው። በጣም ዘግይቶ ።››

«ሕክምናዋን ከጨረሰች በኋላ ይህ ነው የማትይው አጋጣሚ እየተፈጠረ ዘወትር እንገናኝ ጀመር ። ፓርቲ ተጠርቼ ስሄድ ፓርቲው ላይ እሷም አለች። ምሳ ግብዣ እዚያም አንኛታለሁ። ምን ይኽ ብቻ አንዳንድ የስራ ጉዳይም ያገጣጥመን ጀመር እንጂ።››

«እሷ እንኳ ሕኪም አይደለችም ። ግን ባሏ ሐኪም ነው ያልነገርኩሽ ነገር ሴትዮዋ እኮ ባለትዳር ነበረች። በዚህ ሁኔታ ወደ ፈትናም አታግባኝ እያልኩ አንድ አመት ሙሉ ከስሜቴ ጋር ታገልኩ። ከዚያ በኋላ ግን አልሆነልኝም።ተሸነፍኩ ። ስሜቴን ነገርኳት ። ምን ልበልሽ፡፡ ሆነ… ሁለታችንም በፍቅር ቀንበር ተጠመድን ። እይከፋኝም ። ሳስበው ለምን ሆነ አልልም ። በጣም ያሚጥም ፍቅር መስረትን በጣም የሚጣፍጥ ጊዜ እሳለፍን ።
👍14😁21