አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


ትላንት በፅሁፍ ስህተት ክፍል 26 የተባመው ክፍል 16 ተብሎ ይነበብ።


..ዕለቱ ቅዳሜ ነው::መርካቶ የተለመደ የትርምስ የግርግርና የጫጫታ ሂደቷን ቀጥላለች። የገበያ ልውውጡ ተጧጡፏል። የበዓል ሰሞን ሩጫ
ጥድፊያ ግፊያ መዋከብ ነው፡፡ የቅቤ ተራም እንደዚሁ። ቅቤ በገረወይና እየወረደ እየተመዘነ አንዱ በሌላው ላይ ይመረጋል። የቅቤ ተራራ ገዥው በጣቱ ይቧጥጥና ወደ አፍንጫው እየወሰደ ለጋ ነው?ስማ ነው
?የቱ ይሻላል?" ይላል።
“እዚህ ይምጡ!ቆንጆ የወለጋ ቅቤ አለ!"
“ይኸው ለጋ የጎጃም! ለወጥ ከፈለጉ ደግሞ ዋጋው ይቀንሳል። ወደዚህ!'የ
ቅቤ ነጋዴዎች ከፊት ለፊታቸው በተከመረው የቅቤ ተራራ አናት ላይ እየ
ትንጠራሩ ይጣራሉ፡፡ በዚሁ መሀል ቅቤ ለመግዛት ሳይሆን የቅቤ ነጋዴ
የሚፈልግ ወጣት እዚህም እዚያም ይራወጥ ነበር፡፡ ጌትነት መኩሪያ. ..
“እባክህ የኔ ወንድም ከባሌ ጠቅላይ ግዛት ቅቤ የሚያመጡ ነጋዴ አቶ
ዓለሙ ተመስገን የሚባሉ ታውቃለህ?"
“አላውቃቸውም" ይሄንን ይተውና ደግሞ ሌሎቹን ይጠይቃል። "አናውቅም ይሉታል፡፡ ደግሞ ያስረዳል ልዩ ምልክታቸውን ቀይ ሽማግሌ መካከለኛ ቁመት ፀጉራቸው ትንሽ ወደ ውስጥ ገባ ያለ" ከዚህ ሁሉ መባዞንና ውትወታ በኋላ ባይቀናው ኖሮ አንጀቱ በተቃጠለ ነበር፡፡ በመጨረሻ ላይ አንድ የባሌ ሰው አገኘ፡፡
“እንዴ? ጋሼ አለሙ! ደንበኛዬ ናቸው ሰሞኑን ይመጣሉ ምነው በሰላም
ፈለካቸው?" የቅቤ ነጋዴው ከዲር ነበር፡፡
“ዘመዴ ናቸው በጣም ነው የምፈልጋቸው እንዴት አድርጌ ላገኛቸው እች
ላለሁ ባክህ?"
“ምን ችግር አለ ታዲያ ? እኔ አገናኝሃለሁ። ደንበኛዬ ናቸው እኔጋ ሳይደርሱ አይመለሱም። እስከዛሬ ድረስ መቆየታቸው ራሱ ገርሞኛል።
ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚመጡ እርግጠኛ ነኝ"
“እንግዲያውስ እየተመላለስኩ እጠይቅሃለሁ። ለማንኛውም ጌትነት
መኩሪያ ብለህ ንገርልኝ" የከዲርን አድራሻ ተቀብሎ የራሱን አድራሻ ትቶ ተመለሰ፡፡ ጌትነት እንደዚያ በደስታ እየፈነደቀ ሽማግሌውን ፍለጋ የተሯሯጠው ያለምክንያት አልነበረም። የምስራቹን ሊያበስር ተጣድፎ ነበር፡፡ በሯን ጥርቅም አድርጋ ዘግታ ደጅ ስታስጠናው የከረመችው የስራ እድል የተረታችበት ያ ሁሉ ጭንቀት በሀሴት የተደመደመበት የሽመልስ ድካም በድል የተቋጨበት አስደሳች ቀን ነበር፡፡ ፈፅሞ ውድድር ሊባል በማያስችል ልዩነት ፈተናውን በማለፍ አድልዎ ወዳጆቿን ክፉኛ እንድ
ታጋልጣቸው ያደረገበት ልዩ ቀን... የዘመናት ወዳጃቸው ሀሰት ለነአቶ
አባይነህ ጀርባዋን የሰጠችበት ቀን! ጌትነት የተሰማው ደስታ ይህ ነው
አይባልም፡፡ በደስታው ላይ ደስታ የተሰማው ደግሞ ፀሀይ አስፋው ክፍት
ቦታ ሲገኝ በምትመጥንበት የስራ ደረጃ ላይ እንድትቀጠር የተሰጠውን
ተያያዥ ውሳኔ ሲሰማ ነበር። አንዱ ሲደሰት ሌላው መከፋቱ የማይቀር
ነው። ፀሀይ ፈተናውን አልፈሻል ተብላ ሥራውን ለመጀመር በተዘጋጀችበት
ወቅት በተፈጠረ ውዝግብ ምክንያት በጅዋ የገባው ሲሳይ ሲያመልጣት
ማዘኗ መሳቀቁ የማይቀር ነው። በሷ እግር ተተክቶ እሱ ኑሮውን ሲያሻሽል እሷ ደግሞ ልታዝን ልትከፋ በመሆኑ ደስታው ሙሉ ደስታ አይሆንለትም ነበር፡፡ ሽመልስ የፈተናውን ውጤትና የተወሰነውን ውሳኔ እንደ ሰማ ሳይውል ሳያድር ነበር ስልክ ደውሎ የጠራው፡፡

“እንኳን ደስ አለህ ጌትነት ዛሬ መንፈሴ እጅግ የረካበት ቀን ነው። ዛሬ ለኔ ትልቅ የድል ቀን ነው፡፡ ዐባይነህን ከመሰለ ዝሆን ጋር ታግዬ ልጥለው የቻልኩት በፈጣሪ ድጋፍና ባንተ ጥረት ነው። ሰራተኛው
በሙሉ ውጤቱን በጉጉት ሲጠባበቅ ነበር የከረመው፡፡ ግማሹ አድናቆቱን
ሲገልፅ ግማሹ ደግሞ የአቶ አባይነህ ቲፎዞ በመሆን ጭፍን ጥላቻውን
ሲያንፀባርቅ ቆይቷል። እንደዚያ መሆኑ ግን በነገሩ እንድገፋበት ብርታት
ሆኖኝ እንጂ አላንበረከከኝም፡፡ አንተም አላሳፈርከኝም፡፡ ይሄ የጋራ ድካማችንና የጋራ ውጤታችን ነው፡፡ ከዚህ በሁዋላ
የዚህ ድርጅት አባል ነህ ትንሽ ነገር ልበልህ፡፡ በተቻለህ መጠን ከስራህ በስተቀር ሰዎች ለተንኮል
ለሌለብነት እንዲያመቻቸው ከሚፈጥሩት ቡድን ራስህን ጠብቅ። ስራህን
አክብር፡ ስራህ ያከብርሀል፡፡ በአለቃህ ፊት ብቻ ሰራተኛ መስለህ ለመታየት አትሞክር፡፡ አለቃህን በስርዓቱ ማክበር የሥራ ድርሻህን በብቃት መወጣት ተገቢ ነው፡፡ በማጎብደድ በእወደድ ባይነትና በወሬ አቀባባይነት ለመሾም ወይም ለማደግ የሚፈልጉ ሰዎች አርአያም ተከታይም ከመሆን ግን ራስህን ጠብቅ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ አለቃህ ስራህ መሆኑን ጠንቅቅህ መረዳት ይኖርብሃል፡፡ የአቶ አባይነህ ቲፎዞዎችና አንዳንድ ጭፍን አመለካከት ያላቸው ሰራተኞች ሊጠሉህና ሊተናኮሉህ ይችሉ ይሆናል።
መተናኮል ብቻም ሳይሆን ፊት ለፊት ሊበድሉህ ወይም ሊያጠቁህ ይሞክሩም ይሆናል ነገር ግን ጥቃትን በመፍራት ህሊናህ የማይፈቅደውን ነገር ከመስራት መቆጠብ ይኖርብሃል። አንተም አንድ ቀን በሃላፊነት ቦታ ላይ ስትቀመጥ ምን ማድረግ እንዳለብህ ከዚህ ትምህርት ልትወስድ ይገባል። ለማንኛውም መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ" በማለት የምስራቹን ካበሰረውና ተገቢውን ምክር ከለገሰው በኋላ አቅፎ ጀርባውን ቸብ
ቸብ አደረገው።

"በእውነት ነው የምልህ ሽመልስ አዲስ ህይወት የፈነጠቅክልኝ ስለኔ ሆነህ ራስህን ጎድተህ የተሟገትክልኝ ምንጊዜም የማከብርህ ወንድሜ
ነህ፡፡ ዓላማዬ የተሰጠኝን የሥራ ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት ትምህርቴን መቀጠልና የተሻለ ዕውቀት በመገብየት ራሴንም ቤተሰቤንም አገሬንም መርዳት ነው። ወደፊት ይህ ሁሉ ምኞቴ ተሳክቶ ለበለጠ ሀላፊነት በቅቼ ስዎችን ለመጥቀም ወይንም ለመጉዳት በሚያስችል የሥራ ሀላፊነት ላይ የመገኘት ዕድሉ የሚገጥመኝ ከሆነ ካንተ ከወንድሜ ያገኘሁት ትልቅ ትምህርት ምንጊዜም ከአእምሮዬ የሚጠፋ አይደለምና ስለ እውነት ለመሥራት ቃል እገባልሃለሁ" አለው።

ጌትነት የቅጥር ፎርማሊቲውን አሟልቶ ጨረስ፡፡ ስራ ይዞ ስው ለመሆን
ያደረገው ረጅም ሩጫ ዳር በመድረሱና ራሱን ችሎ ሌላውን የመርዳት ህልሙ እውን በመሆኑ ደስታው ወደር አልነበረውም፡፡ ልቡ ወደ ባሌ ወደ እናቱ ዘንድ በረረች፡፡ እህቱ ዘይኑን በቅርብ ክትትል የማስተማር ዕቅዱን በማሳካት ጉጉት ተውጦ ወደ ትውልድ መንደሩ በሀሳብ ከነፈ ያንን አስደሳች ዜና ለእናትና እህቱ ሊያሰማቸው ተጣድፎ አቶ አለሙን ለማግኘት በየቀኑና ቅቤና ነጋዴው ከዲር ዘንድ ሲመላለስ ከቆየ በኋላ ቀናው። በመጨረሻ ላይ አቶ አለሙ ዠ መምጣታቸውን አረጋገጠና በከዲር
አማካኝነት ተገናኙ።

“ጌትዬ! አንተ?! ደህና ነህ?! እንደው ነፍስህ አለ ልጄ?" የእናቱን ናፍቆት
ጭምር እቅፍ አድርገው አገላብጠው ሳሙት፡፡
"ደስ ብሎኛል አባባ ደስ ይበልዎ! የድሃዋ እናቴ አምላክ ጥሎ አልጣለኝም። ሥራ አገኘሁ! ሁሉንም ነገር ጨረስኩ! ሁሉንም ነገር ጨረስኩ!”
ሁለመናው ስቆ ደስታውን ገለፀላቸው፡፡ አቶ ዓለሙ በደስታ ዘለሉ፡፡
"ጎሽ! ጎሽ! እሰይ የኔ አንበሳ! እንኳን ደስ አለህ! እንዴት ያለውን የምስራች ነው የነገርከኝ ባክህ?! እሰይ! እስይ! እኔም ገዳም ሆንኩ ማለት ነው፡፡ የምስራች ሰምቼ የምስራች አብሳሪ ሆንኩ ማለት ነው። ጭንቅጰሲለኝ የከረመው የሷ ጉዳይ ነበር፡፡ መልካም ዜና አመጣልሻለሁ እንዳልኳት እንደፎከርኩት ተሳካልኝ ማለት ነው። ደስታው የሁላችንም ነው!” ፍንድቅድቅ አሉ።

"አባባ ለመሆኑ የጤናዋ ነገር እንዴት ነው? ሃሳቡ ገድሏታል መቼም
ጭንቅ ጥበብ እያለው ጠየቃቸው
“ደህና ነች ምንም አትልም ያንተ ነገር ነበር ሲያሳስባት የከረመው ከንግዲህ በኋላማ ምን ትጠይቀኛለህ?
👍3
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


... ታፈሡና መርዕድ መናኸሪያ ሲደርሱ ከምሽቱ አሥራ አንድ ሠዓት እየተጠጋ ነው:: ሁኔታው ግን የበለጠ ተባብሷል። እንዲያውም ሁለተኛው በራሪ
አውቶብስ ገብቶ ነገር ግን አሁንም ተላልፈው ኖራልና የተጠበቀው መረጃ ባለመገኘቱ ህገቡ ግራ ተጋብቶ ወለሌ ይላል። ይተረማመሳል፡፡ ይላቀሳል፡፡
ታፈሡ በሕዝቡ መሀል ክወዲያ ወዲህ እየተሯሯጠች «እህ እንዴት ነው? ምን ሰማችሁ! እንዴት ሰማችሁ ሰው ተርፎ ይሆን?» በማለት ስትርገበገብ ከኳኋኗን ይመለከት የነበረ አንድ ቀደም ብሎ ያውቃት የነበረ ሰው እጇን ያዝ አደረገና «ወይዘሮ ታፈሡ፣ አንቺም ሰው ሸኝተሽ ኖሯል? » ሲል ጠየቃት
«አዎ ጋሽ ዓለሙ! ወንድሜን፡፡» አለችው እጆቿን እያርገበገበች::
እግዜር ይጠብቅልሽ እንጂ የጉዳቱ መጠን እንኳ በጣም አሳሳቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይኸው እስከ አሁን እንኳ የሰባት ሰው መርዶ ደረሰ፡፡»
ታፈሡ ወዲያው እጆቿን ወደ ላይ ዘርግታ «ወየው! ወየው ወየው
እያለች ልክ መርዶ የደረሳት ያህል ለይቶላት ታለቅስ ጀመር፡፡ እንባዋ በጉንጫ ላይ ቦይ ሰርቶ ይንቆረቆር ጀመር፡፡ ጭንቅ ጥብብ፣ ብክን ክርትት ስትል የሚያያት ሁሉ
ልክ እንደ እሷው እንባውን ያዘራው ጀመር። በከተማው ውስጥ ታዋቂ እንደ መሆኗ ሴት ወንዱ ዙሪያዋን እየከበበ ሊያጽናናት ቢሞክርም እሷ ግን አንጀቷ እየተንሰፈሰፈ
አልረጋጋ ብላ አስቸገረች፡፡

ጀምበር ጠልቃ ለዓይን መያዝ ጀምረ፡፡ ቀሪው የዚያ ቦታ ትርዒች ስለ ነገው አስክሬን ፍለጋ ጉዞ መነጋገር ብቻ ሆነ። አንዱ ከሌላው ጋር ይመካከር ጀመር፡፡ ታፈሡና መርዕድም ሊሄዱ በጋራ ወሰኑ፡፡
ታፈሡና መርዕድ ወደ መናኸሪያ ከሄዱበት ሠዓት ጀምሮ ሄዋን ቢያንስ አሥር ጊዜ ከቤት እደጅ ወጣ ገባ ስትል ቆይታለች። ስጋት እያቁነጠነጣት ከተቀመጠችበት ይልቅ ስትቆም ስትራመድ ያሳለፈችው ጊዜ ይበልጣል:: መርዶ ይሆን ብሥራት የሚመጣላትን አታውቀውም፡፡ እነሱ ደግሞ ለእሷ ምንም ዓይነት
ፍንጭ ላለመስጠት እየተዘጋጁ ናቸው:: ሁለቱም ወደ ቤት እየተመለሱ በአሉባት ሰዓት ታፈሡ ያለቀስችበትን ዓይኗን ጭምቅ፣ ፊቷን ጥርግርግ አረገች። እንዲሁም ስለ ሁለት ሠዓት ዜና አስማም ተመካከሩ። በታፈሡ ቤት ሬዲዮ ላይከፈት፣ በዚያ ምትክ መርዕድ ቴፕ ሊከፍት፣ ታፈሡ ወደ ጎረቤት ሄዳ ዜና ሰምታ ልትመለስ።
የጠዋቱን ጉዞ በተመለከተ ታፈሡ ከባለቤቷ መልዕክት ተልኮላት ያን ልትቀበል ወደ አዲስ ኣበባ ልትሄድ መሆኗንና መርዕድ ጠዋት ይሸኛት ዘንድ እሷው ቤት ሊያድር ሆኖ የሔዋንን ጥርጣሬ ለመቀነስ ተዘጋጅተዋል፡፡
ከምሽቱ አንድ ሠዓት ላይ ታፈሡና መርዕድ ከቤት ሲደርሱ ሔዋን በር
ላይ ቆማ ስትጠብቃቸው አዩዋት፡፡ ታፈሡ የመጀመሪያውን ሔዋንን “ማረጋጊያ ዘዴ ወዲያው ፈጠረችና “ሔዩ! ቡና አላፈላች ይሆን? ብታይ የረባ ወሬ ላይገኝ ነገር ወዲያ ወዲህ ስንከራተት ስለ ቆየን ራሴን እንዴት ቀስፎ ይዞኛል መስለሽ አለቻት ወደ በር እየተራመደኝ፡፡ መርዕድ አጎንብሶ ከኋላዋ ይከተላል፡፡

«ምንም የለም?» አለች ሔዋን የበሩን መቃን ደገፍ ብላ እንደቆመች።
«ወሬማ ሞልቷል!ግን እርስ በእርሱ ይጋጫል»
«ምን ምን ይባላል ታፈሡዬ?»
«ጭራሽ የትኛው መኪና እንደተጋጨ እንኳ እልታወቀም»
ሦስቱም ወደ ቤት ገቡ፡፡ ሔዋንና መርዕድ ሶፋ ላይ ሲቀመጡ ታፈሡ ወደ ጓዳ ገባች ሠራተኛዋ የእራት ወጥ እየሰራች ነበርና ቶሎ በይና ቡና አፍይልኝ አለቻት ድምጿ ወደ ሳሎን እንዲሰማ አድርጋ ጮክ በማለት፡፡ ልብሷን ቀያይራ ወደ ሳሎን እየተመለሰች ሳለች መርዕድን «አዲስ እበባ የምትልከኝ ነገር ካለ አሁኑ ተዘጋጅ መርዕድ እያላችው ወደ ሶፋ ሄዳ ከሔዋን ጎን ተቀመጠች።
«መቼ ልትሄጂ?» አለቻት ሔዋን አዲስ ወሬ ሆኖባት በርገግ ብላ፡፡
ባለቤቴ ከርሞ ከርሞ ከውጭ ሀገር የሆነ ነገር ሳያልክ አይቀርም አዲስ አበባ መጥተሽ ወሰጂ ብለው ዛሬ በትምህርት ቤት በኩል ስልክ ደወሉልኝ»
«እና ነገ ልትሄጂ» አለች ሔዋን አሁንም ጭንቅ ጥብብ እያላት፡፡
«አዎ፣ ግን በጠዋት እንድትቀስቅሱኝ። መርዕድም እንዳሸኘኝ ብዬ እዚሁ ላሳድረው ነው ይዤው የመጣሁት። አለቻት ወደ መርዕድ አየት እያደረገች፡፡
«የኔስ ነገር ታፈሡዬ?»
«የአስቻለው ቁርጥ ሳይታወቅ ትሄጃለሽ እንዴ?» አለችና ታፈሡ እኔም እኮ ነገ ሄጂ ከነገ ወዲያ እመጣለሁ፡፡ እስከዚያው እዚሁ እኔ ቤት ሆነሽ ጠብቂኝ፡፡ አለቻት።

ሔዋን ነገሮች ሁሉ ተምታቱባት፡፡ ቀደም ሲል ያየችባቸው አስደንጋጭ ሁኔታና የአሁኑ እርጋታቸው ፈጽሞ ሊጣጣምላት አልቻለም። ጭራሽ የአስቻለውን
ነገር ማንሳት የነገር ደባል መፍጠር ሊመስልባት እንደሚችል እስከ መስጋት ደረሰች፡፡ ግን ደግሞ ሆድ ሆዷን በላትና «በዚያው ስለ አደጋውም ትሰሚያለሽ?» ስትል ታፈሡን ጠየቀቻት።

«የሆነ ነገር ካለማ ማየቴም አይቀርም፡፡ »አለችና ታፈሡ በተለይ ወደ መርዕድ አየት እያደረገች። «ግን እንደው ወሬው ሁሉ የማይጨበጥ ሆነና ግራ አጋባን እንጂ» አለች።

«ሰው ደሞ ዝም ብሎ ማዳነቅ ይወዳል፡፡» አለ መርዕድም ጣሪያ ጣሪያ እያየ የምንተ እፍረቱን ወዲያው ብድግ አለና ወደ ብፌው በመሄድ ሙዚቃ ከፈተ።
ከሌለህማን አለ እጀፈደጅህ ኪስህ ነው የቅርብ ወዳጅ» የሚለው ዜማ ሠሰማት ጀመረ።

እራት በልተው ሲጨርሱ ሁለት ሠዓት ሊሆን ተቃርቧል። የታፈሡ
"ሠራተኛ ቡና እያፈላች ሳለች ታፈሡ በጉጉት የምትጠብቀው የዜና ሠዓት ደረሰና መጣሁ ብላ ከቤት ውልቅ አለች፡፡ ከጎረቤቶቿ ቤት ስትደርስ ሬዲዮ ተከፍቶ የዜና
ንባብ ተጀምሯል። ታፈሡ በዚያ ቤት የተከበረች እንግዳ ናትና ከቤት ስትገባ ቤተሰቡ በሙሉ ተነስቶ ተቀበላት፡፡ ከሰላምታ በኋላ ሬዲዮው ሥር ቁጭ አለች።
ዜና ንባበ ቀጠለ። ዋና ዋና ዜናዎች ከአለቁ በኋላ «በመጨረሻም» እለ ዜና
አንባቢው ጋዜጠኛ
ዛሬ ከዲላ ወደ አዲስ እበባ ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከሞጆ ወደ ሻሸመኔ ይጓዝ ከነበረ መለስተኛ የህዝብ ሚመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ በደረሰ አደጋ በትንሹ ሰላሳ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ አርባ ስምንት ያህሉ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የዝዋይ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ገለፁ:: ጽፈህት ቤቱ እንዳለው» ብሎ ሳይጨርስ ታፈሡ
ያንን ቤት በጨኸት አደበላለቀችው
እየዩ እኔ.. እየየ እኔ.. እየየ እኔ እያለች በወለሉ ላይ ድፍት አለች
ከዜናው ይልቅ በታፈሡ ሁኔታ የደነገጠው የዚያ ቤት ቤተሰብ በሙሉ ተረባርቦ ከተደፋችበት ቀና አድርጎ አስቀመጠ፡፡ «ምነው? ምነው?» አለ ሁሉም ሰው በማክታትል። ታፈሡ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ፋታ አላገኘችም፣ ስቅስቅ ብላ ታለቅስ ጀመር። አስቹ አርፈኸዋል! ተገላግለሃል ወንድሜ! የኔ ግልቱ የኔ ብስጨ! ወይኔ ! ወይኔ ! ወይኔ!» አለች በማከታተል::
«ምነው ወይዘሮ ታፈሡ ገና በግምት?» አሏት የቤቱ አባወራ ቀደ ብለው። «ምንሽ ነው ወይዘሮ ታፈሡ?» ሲሉ የቤቱ እማወራ ቀጠሉ፡፡ታፈሡ ግን ወደ ዝርዝር መግባት አልቻለችም፡፡ ተዉኝተዉኝ ተዉ በቃ ሌላ ሰው እይስማብኝ!» አለችና አደራ ጎረቤቶቼ ነገ እኔ እዚህ አልውልም ወደ ናዝሬት እሄዳለሁ:: ግን እዚህ እኔ ቤት ወስጥ ይኸን ጉድ መስማት የሌለባት ልጅ አለችና አደራ! የአሁኑን አኳኋኔን ለሠራተኛዬ እንኳ እንዳትነግሩብኝ አለቻቸውና እያለቀሰች ተስናብታቸው ወደ ቤቷ ተመለሰች::
👍7
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ምንም እንኳን ልጇ ደሕና መሆኑንና ትምህርትና ዋናም እየተማረ እንደሆነ፣ ከፍ ሲል ደግሞ ቀስት ውርወራ፣ ጉግስና አደን እንደሚማር ብትሰማም፣ ጭንቀቷ እምብዛም ሊቀንስላት አልቻለም። ሳታስበው ግን ሁኔታዎች ተቀየሩ። ለንጉሠ ነገሥቱ ቅርብ የሆነው ዐቃቤ ሰዐቱ ዲዮስቆሮስ ንጉሠ ነገሥቱን፣ “ኢያሱ መጥቶ የቤተመንግሥት ወግ፣
አስተዳደርና ትምርት በአግባቡ ይማር፤ ባባትዎ አጥንት ይዤዎታለሁ”እያለ አላስቆም አላስቀምጥ አላቸው።

ምንትዋብ አጋዥ ያገኘች መሰላት

አንድ ቀን ያልታሰበ ነገር ተፈጠረ። የስድስት ዓመቱ ኢያሱ ሲጫወት ድንገት በቀስት የሰው ጊደር ወጋ። የጊደሩን ባለቤት ፈርቶ ከዐይን ተሰወረ። ሲፈለግ በመጥፋቱ ክርስትና አባቱ፣ የእህቱ ባል
ደጃዝማች ባስልዮስና የአካባቢው ነዋሪ በጭንቀት አካባቢውን አሰሱ::ሰፈርተኛው ሁሉ በደቦ ተከፋፍሎ ቀየውን፣ ወንዙንና ጫካውን ፈተሽ::ኢያሱ የውሃ ሽታ ሆነ። ሰዉ ተደናገጠ፣ የሚያደርገው ጠፋው። ብሎም
ኡኡታ፣ ለቅሶና ጩኸት በረከተ። ለንጉሠ ነገሥቱና ለምንትዋብ
እንዴት እንደሚነገራቸው ተመከረ።

ኢያሱ ከተደበቀበት ሲወጣ ዕልልታና ደስታ ጩኸትንና ለቅሶን
ተኩ። ማንነቱ ተደብቆ የኖረው ልጅ በዚህ አጋጣሚ ማንነቱ ታወቀ።

ደጃዝማች ባስልዮስ ግን የኢያሱ ማንነት መታወቁ አደገኛና አሳሳቢ
መሆኑን ተረድቶ በሐሳብ ማሰነ። አፄ በካፋ ጉዳዩን እንዲሰሙ አደረገ።ኢያሱም በፍጥነት ጐንደር እንዲመለስ ተደረገ። ምንትዋብ፣ እናቷና አያቷ የደስታና የእፎይታ እንባ አነቡ።

ምንትዋብ ሳትውል ሳታድር፣ ኢያሱ በተመረጡ አስተማሪዎች
ትምህርት እንዲማር አደረገች። የመንፈስ፣ የግብረገብ፣ የአካል ግንባታና የቤተመንግሥት ወግ ትምህርትም ላይ አተኮረች።
አፄ በካፋ ጠላቶቼ ይገድሉብኛል ብለው ስጋት ቢገባቸውም፣ ዝምታን ፈቀዱ። በሌላ በኩል ግን ከእሷ፣ ከእመቤት እንኰዬ፣ ከእመቤት ዮልያናና ከግራዝማች ኒቆላዎስ ጋር ብዙ ጊዜ ቆይታ መያዝ አዘወተሩ።

በተለይ ምንትዋብን፣ “አንቺ ብልህና አስተዋይ ስለ ሆንሽ እኔ ሳልኖር ኸልዤ ጋር ሁነሽ አገሬን ባግባቡ እንድትመሪ፣ እንድታስተዳድሪ።
የባሕር ማዶ አረመኔዎች አገሬ ገብተው እንዳይበጠብጡ፤ ሕዝቤንም በሃይማኖት ሆነ በሌላ እንዳይበክሉ ዐደራ” ይሏታል።

በነገሡ በዘጠነኛው ዓመት መጀመሪያ ላይ ጥቅምት ወር ውስጥ ግን፣
“ወዳጅ ዘመዴን እለያለሁ” በሚል ታመምኩ ብለው ሲደበቁ ምንትዋብ
ምሥጢር ጠበቀች። ወዲያው፣ “ንጉሡ ሊሞቱ ነው”፣ “ንጉሡ ሙተዋል” የሚል ወሬ ጐንደርን አወዛገባት። የጐንደር ከንቲባ ብላቴን ጌታ ኩቾ ከወህኒ አምባ ንጋሢ አመጣለሁ' ብሎ ሠራዊት አዘጋጀ። ወህኒ አምባዎች በበኩላቸው ወሬውን ሲሰሙ እኔ ልንገሥ፣ አንተ ንገሥ፣ የለም እሱ ይንገሥ ተባባሉ፤ ተመራረጡ፤ ተፎካከሩ።

ጐንደር እንደ ልማዷ ልትታመስ ሆነ።

በካፋ ይህን ሲሰሙ አለመታመማቸውን ለማሳየት ሐሙስ ቀን ደብረብርሃን ሥላሤ ሲሄዱ፣ መኳንንቱ በርቀት ከጋሻ ጃግሬዎች ኋላ በፈረስ ተከተሏቸው። ሕዝቡም ከየቤቱ እንደ ጎርፍ ፍንቅል ብሎ
ወጣ፡፡

በካፋ፣ ሕዝቡን፣ “ታዩኛላችሁና ወደየቤታችሁ ግቡ” ብለው አሰናበቱ።ሊቃውንት ንጉሠ ነገሥቱን በሕይወት በማየታቸው መሬት ሳሙ፤ካህናት ዘመሩ፤ ሕዝቡ ተደሰተ። ከረብሻ ዳነ። በካፋ ግን ብዙ ታዘቡ።
ወዳጅ መሳይ ሁሉ ከበስተጀርባቸው ምን እንደሚያስብ ተረዱ።

መኳንንቱን ወርቅ ሰቀላ ጠርተው፣ በአፈ ንጉሥ በኩል፣ “ምነው
ባካችሁ እንዳው ጥቂት ቀን ታምሜ ብተኛ ሽብር ማስነሳታችሁ? ስለምን ከተማዬን አስደነገጣችኋት? ሞተ ብላችሁ እንደዝኸ መሆናችሁ ተገቢ ነውን?” ሲሉ ጠየቋቸው። እንደማይተኙላቸውም ተረዱ። ሆኖም፣“እነዝኸ በልባቸው ክፋት የለም” ብለው ይቅርታ አደረጉላቸው።መሣሪያ ያነሳው ኩቾ ግን ከነተከታዮቹ ተይዞ ጊዜያዊ እስር ቤት ገብቶ ለፍርድ እንዲቀርብ ተወስኖበት ፍርድ ሸንጎ ቀረበ።

የሃገር ክህደት ወይም ሌላ ከፍተኛ ወንጀል ካልሆነ በስተቀር የዙፋን
ችሎት የማይዙት ንጉሠ ነገሥት፡ ጃን ተከል ተገኝተው ከምንትዋብ ጋር እንደወትሯቸው ቀይ ድባብ ተይዞላቸው፣ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተቀመጡ።መሣፍንቱ፣ መኳንንቱና ሊቃውንቱ እንደየደረጃቸው ተሰየሙ። ፍትሐ ነገሥት ተርጓሚዎቹ፣ ፍርድ ሰጭዎቹና አዛዦቹ፣ ግራ ቀኝ ተችዎቹ
ሁሉ ተገኝተዋል። ዐራቱ ሊቃውንት ፍትሐ ነገሥት ይዘው ቦታቸው
ላይ ተቀመጡ። አቡኑ፣ ዐቃቤ ሰዐቱና መኳንንቱ የተለመደ ቦታቸው ላይ ሆኑ።

ኩቾና ተከታዮቹ እግራቸው በእግረ ሙቅ ታስሮ፣ ጋሻ ጃግሬዎች
ግራና ቀኝ እየጠበቋቸው በንጉሠ ነገሥቱ ትይዩ ቆሙ።ከአዛዦቹ አንደኛው፣ “ጠበቃ ኸፈለግህ ይፈቀድልኻል” አለው፣
ኩቾን።

“አያሻኝም።”

“እንግዲያማ ተጠየቅ።”

“ልጠየቅ!”

“አንድ ስጠይቅህ አንድ፣ ሁለት ስሰጥህ ሁለት መልስልኝ። ኸዝኽ
እንዳትዛነፍ በቅሎ ያግድህ። ጃንሆይ ትንሽ አሟቸው ሰንብተው
እንደነበር አልሰማህም?”

“ሰምቻለሁ።”

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ጃንሆይን አደባባይ ባታያቸው ሊሞቱ ነው ብለህ አላወራህም?”

“አላወራሁም።”

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ያለ ጃንሆይ ፈቃድ ሠራዊትህን ማንቀሳቀስ እንደማትችል
ታውቃለህ አታውቅም?”

“አውቃለሁ ።"

“ተጠየቅ!"

“ልጠየቅ!”

“ዛዲያ ስለምን ሠራዊትህን አንቀሳቅሰህ ለአመጥ ተነሳህ?”

“ለአመጥ አልተነሳሁም።”

“ምስክር ይጠራብህ?”

“ሠራዊት...”

"አንድ ስጠይቅህ አንድ፣ ሁለት ስሰጥህ ሁለት መልስልኝ ያልኩህን አጣርሰኻል። ለበቅሎ ዋስ ጥራ።”

“አላጣረስሁም።”

“አጣርሰኻል። ምስክር ይጠራብኝ ወይንም አይጠራብኝ ነበር
መልሱ።”

“ኸጥያቄህ አልወጣሁም። እማኞች ይጠሩልኝ” እያለ ወደ ሰዉ ተመለከተ ኩቾ።

“አጣርሷል! አጣርሷል! በቅሎዋን ይክፈል!” አለ፣ ሰዉ።

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ለአመጥ መሣሪያ አላነሳህም?”

“ራስ ተስፋ ኢየሱስና ቢትወደድ ስኩት ጃንሆይ ያስሩኻል ቢሉኝ
መሣሪያ አነሳሁ።”

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ምንም ሳታደርግ ጃንሆይ ስለምን ያስሩኻል? ሞተዋል ብለህ
ስላስወራህና ኸወህኒ ነጋሢ ልታመጣ ስለፈለግህ ነው እነራስ ተስፋ ኢየሱስ ያስሩኻል ያሉህ።”

ኩቾ ወደ እፄ በካፋ ተመለከተ። ሁለት እጆቹን ዘርግቶ፣ “ጃንሆይ
ይማሩኝ” ብሎ አጎነበሰ።

“ምትጠይቀው ጥያቄ አለ?” ሲል ጠየቀው አንደኛው አዛዥ ።

“የለኝም። ምሕረት ያርጉልኝ ጃንሆይ!” አለ፣ ኩቾ፣ አጎንብሶ።

ከአዛዦቹ አንደኛው ጋቢውን አስተካከለና ወደ ንጉሠ ነገሥቱ
ተመለከተ፣ “ጃንሆይ ኩቾ የቀረበበት ክስ ክህደት ነው። ክህደት ደሞ በሞት ያስቀጣል” አለ፣ ፍትሐ ነገሥቱን እያገላበጠ። “ፍታ ነገሥቱ ሚለው በንጉሥ ላይ ያመጠና ያሳመጠ በሞት ይቀጣ ነው።”

ይህን ዓይነቱ የሞት ብይን ይገባዋል አይገባውም፤ ወይንም ደግሞ ሌላ ቅጣት ይቀጣ ብለው ለመወሰን መኳንንት እንደየማዕረጋቸው እየቆሙ ከዝቅተኛው ጀምሮ እስከ ከፍተኛው ድረስ አስተያየት ሰጡ።

“ክህደት ነውና ሞት ይገባዋል!” አሉ፣ አንደኛው መኰንን።

“ግዞት ይላክ!” አሉ፣ ሌላው።

“በግርፋት ይቀየርለት!” ብለው ተቀመጡ፣ አንደኛው
“ጃንሆይ መሐሪ ናቸውና ምህረት ይደረግለትና ሹመቱን ይገፈፍ”
አሉ፣ ሌላኛው።

እንደዚህ እያለ ሁሉም ተናግረው ከጨረሱ በኋላ፣ የማሳረጊያው
ንግግር የንጉሠ ነገሥቱ በመሆኑ፣ አፈ ንጉሡ አጎንብሶ ጆሮውን
ሲሰጣቸው ሁሉም ለመስማት ጆሯቸውን ሲያቀኑ ኩቾና ተከታዮቹ
ትንፋሻቸውን ውጠው ተጠባበቁ። ይህን ሁሉ በአንክሮ የምትመለከተው ምንትዋብም ተጠባበቀች።
👍20🤩1
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...እኔና ባህራም መውጫው በር አጠገብ ያለችው ጠረጴዛ ጋ
ቁጭ ብለን ቢራ ጠጥተን ሂሳቡን ከከፈልን በኋላ፣ ባህራም
ምንም ቢመጣ ምንም፣ ከተቀመጥክበት እንዳትነሳም አለኝ
“ምን ልታረግ ነው?» ስለው

«ታያለህ» አለኝ.

ተነሳና ወደ ሽንት ቤት በኩል መራመድ ጀመረ። አንዱ
ጎረምሳ ፋሺስት ከዚያው ሲመለስ ነበር ባህራምን የገጨው፡፡ ፋሺስቴ ሳያስብበት በልማድ “Pardon” ብሎት ሲያልፍ፣ ባህራም

«አንተ!» ብሎ ጮኸበት። ፋሺስቶቹ ወሬያቸውን አቆሙ::
ካፌው በሙሉ በፀጥታ ባህራምን ማየት ጀመረ። የገጨው ፋሺስት
ወደ ባህራም ዞሯል ባህራም

«ለምን ገጨኸኝ?» አለው

ፋሺስቱ «አንተ ነህ እንጂ የገጨኸኝ አለው

«ውሽታም ፋሺስት! ውሻ ፋሺስት! ፈሪ ፋሺስት! ወንድ ከሆንክ ተከላከል። ልገርፍህ ነው» አለና ዘሎ ትግል ያዘው። የፋሺስቱ ጀርባ ወደኔ ስለነበረ፣ ባህራም ምን እንዳደረገው ለማየት
አልቻልኩም፡፡ ብቻ ምንም ያህል ሳይታገሉ ፋሺስቱ ፍስስ ብሎ ወደ
መሬት ወደቀ፡፡ ባህራም ከበላዩ እንደቆመ ዙሪያውን ተመለከተ፡፡
ከፋሺስቶቹ ማንም አልተነሳም
ባህራም ፋሺስቶቹን እያየ «ማንም ፋሽስት እንዲገጨኝ አልፈቅድለትም፡፡ ከንግዲህ ሌላ ፋሺስት የገጨኝ እንደሆነ፣ ፂሙን
ነው ምላጭለት አለና የወደቀውን ፋሺስት ተሻግሮ ወደኔ መጣ፡፡
አብረን ወጣን
(ፋሺስቶቹ እኔን ሌላ ጊዜ ቢያገኙኝ ይደበድቡኝ ይሆን? ብዬ
ትንሽ ፈራሁ፡፡ ግን ደፍረው ጥቁር ተማሪ የሚደበድቡ አልመሰለኝም፡፡ ምክንያቱም እኛ የፈረንሳይ መንግስት እንግዶች
ማለት ነን፡፡)
ባህራም ኤክስ ውስጥ አራት ቀን ቆየ፡፡ ቀን ቀን ኮሙኒስቶቹን
ሲመካክራቸው፣ እንዴት አድርገው መከላከል ፅሁፎቻቸውን እንዴት ቢያሰራጩ እንደሚሻል፣ እና ይህን የመሳሰለ ነገር ሲነግራቸው ይውላል። ማታ ማታ ፋሺስቶቹን በየጠባቡ መንገድ ሲደበድባቸው ያመሻል፡፡ በአምስተኛው ቀን ትምህርት ቤቱ ድረስ ሸኘሁት፡፡ ስለአምቧጓሮው ሲነግረኝ፣ ስለኳስ ጨዋታ የሚያወራልኝ መስሎ ተሰማኝ፡፡ በደስታ እየገነፈለ፣ ማድፊጡን መዝለሉን፣ እጁን እንደ ሰይፍ አርጎ አንገት መምታቱን፣ እንደ ዳንስ አድርጎ ገለፀልኝ

"ማኑ ይህን ሁሉ ስስራ አይቶኝ ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር!
ያስተማረኝን ብልሀት በሙሉ ተጠቅሜበታለሁ» አለ

«ደህና ሁን» ብዬው ወደ ኤክስ ልመለስ ስል፣ ከኪሱ አንድ
እቃ አውጥቶ አሳየኝ። የፀጉር መቁረጫ መኪና «ቶንዶዝ»፡፡
ምንድነው? አልኩት፡፡ እየሳቀ «ፋሺስቶቹ ካፌ ሂድና እቺ ነገር
ኮሙኒስት መሆንዋን ትገነዘባለህ» ብሎኝ ተለያየን ኤክስ እንደደረስኩ ፋሺሰቶቹ ካፌ ገባሁ። ብዙዎቹ እጃቸውን ወይም ጭንቅላታቸውን በፋሻ ጠምጥመዋል፡፡ ግማሾቹ ፂማቸውን ላጭተዋል። ፂማቸውን ያልላጩት ደሞ ጥቁር «ቤሬ ቆብ
አርገዋል። ለካ ባህራም ኣንድ ፋሺስት በደበደበ ቁጥር ራሱን
ወይም ፂሙን ይላጭለት ኖሯል
(እኔና ባህራም ኣንድ ግሩም የሆነ ሀራኪሪ» የተባለ የጃፓን ፊልም አይተን ነበር። እዚያ ፊልም አንዱ ጎበዝ እየዞረ የጠላቶቹን
ፀጉር ይላጫል።)

ባሀራም በሄደ በአራተኛው ቀን፣ አንዲት ኮሙኒስት ልጅ ካፌ
ቁጭ ብዬ ሳለሁ መጣችና ወደ ኤክስ አንድ ነብሰ ገዳይ መጥቷል
አለችኝ። ምን አንደሆነ ማለቴ የቱ እንደሆነ አናውቅም። ግን መምጣቱን እናውቃለን፡፡ ፋሺስቶቹ ናቸው ከማርሰይ ያስመጡት። ባህራምን ሊደበድበው ወይም ሊገድለው ነው የመጣው::»
«ፋሺስት ነው?» አልኳት
«አይደለም። የተገዛ ነብሰ ገዳይ ነው» አለችኝ
ያን ጊዜውኑ ሲልቪ ቤት ሄድኩ። በአቶቡስ እንዳልሄድ
ምናልባት ፋሺስቶቹ ይከታተሉኛልና፡ ካንቺ ጋር ለሽርሽር የምንወጣ አስመስለን እንሂድ አልኳት።በመኪናዋ ሄድን። ለባህራም ነገርኩት።
ሲልቪ ቤቷ ወስዳን እራት በላን። ከዚያ ሶስታችንም ሄደን
ፋሺስቶቹ ካፌ ገብተን ሁለት ሰአት ያህል አሳለፍን። ይህን ሁሉ
ጊዜ ባህራምና ሲልቪ ያወሩ፣ ይቀልዱ፣ ይስቁ ነበር፡፡ እኔ ግን
ምንም ያህል አላወራሁም። ለባህራም ፈርቼለት ነበር፡፡ ሰውየው የቱ እንደሆነ ብናውቅ እንኳ ለመከላከል እንሞክር ነበር። አሁን ግን ከማንኛውም አቅጣጫ ጦር ሊወረወርበት በሚችልበት
ውስጥ፣ ባህራም ብቻውን የሚራመድ መስሎ ተሰማኝ
አብሬያቸው ባለማውራቴ፣ የኔ ፍርሀት ቀስ እያለ ወደ ሲልቫ
ተላለፈባት

“ፈራሁ። በጣም ፈራሁ» አለች

ባህራም «ምን ያስፈራሻል?» አላት፡፡ ግን ድምፁ እንደ ድሮ
ልዝብ መሆኑ ቀርቶ፣ ትንሽ እሾህም ሆኗል

«ማን እንደሆነ ወይም የት እንደሆነ አናውቅም፡፡ አንድ
ብቻውን መሆኑን እንኳ በእርግጥ አናውቅም፡፡»

«እና?»

አንድ ነገር ብትሆንስ? ብትሞትስ?» አለችው

እኔ? ትቀልጂያለሽ? የኛ ቤተሰብ”ኮ እስኪጃጅ ካላረጀ
አይሞትም፡፡ የኔ ወንድ አያት፣ ያባቴ አባት፣ በዘጠና ሰባት
አመታቸው ብቻቸውን ሜካ መዲና ደርሰው ተመልስዋል። ታድያ
እንደተመለሱ የቤታችን ጣራ ዝናብ ማስገባት ሲጀምር ጊዜ፣
ሊያበጁት በመስሳል ወጡ። አበጅተውት ሲወርዱ ከመሰላል ወደቁና እግራቸው ወለም ብሏቸው ሁለት ሳምንት ሙሉ እንዲተኙ ሀኪም አዘዛቸው:: ታድያ ሁለት ሳምንት እንዴት ይለፍ? ውሽማቸው ናፈቀቻቸው። እና ገና አንድ ሳምንት ሳይተኙ፣ ሌሊት ጠፍተው ውሽማቸው ቤት ሄዱ። መኝታ ቤቷ በመስኮት እገባለሁ ሲሉ ባልየው በጥይት ልባቸውን አፈረሰላቸው:: ስንቀብራቸው የኔ አባት
«አይ አባባ! አይ አባባ! እኛ ያረጀነው እያለን አንተ ወጣት
ተቀጨህ!» ብሎ አለቀሰ፡»
ስንስቅ ሲልቪ በጆሮዬ እኔ ፍርሀት አቁነጠነጠኝ፡፡ ሽንቴ መጣ» ብላኝ ወደ ሽንት ቤት ሄደች
ባህራምን «የጀምሺድን የሚመስል ታሪክ ከየት አመጣህ?» አልኩት
( ከጀምሺድ ነዋ!» አለኝ «ስማኝ፡፡ እንድ ነገር አርግልኝ።
እዚያው ትደር፡፡ እና ነገ በሌሊት ተነስቶ ማርሰይ እንዲወስዳትና
ለአንድ ሳምንት ያህል ተደብቀው እንዲቆዩ ንገረው::

ቀፈፈኝ። በባህራም ትእዛዝ ኒኮልን ጀምሺድ ቤት ወስጄ ለጀምሺድ ላስረክበው ለአንድ ሳምንት ሙሉ! በጣም ቀፈፈኝ፡፡ ግን
ምን ማድረግ እችላለሁ?
አንተም ይህን ሰሞን ተጠንቀቅ። ማታ ብቻህን አትውጣ»
አለኝ። ሲጋራ አቀጣጠለ። እጁ ትንሽ ትንሽ ይንቀጠቀጣል። ፍርሀት አሳደረብኝ
ሲልቪ ተመለሰች። ደህና እደሩ ብያቸው ሄድኩ ኒኮልን ቤቷ እገኘኋት። ጀምሺድ ቤት ስንሄድ አጣነው፡፡ ቤቱ ቁልፍ ነው። ካፌ ዶርቢቴል ሄደን ጠያየቅን፡፡ ተካ፣ ጀምሺድና ሉልሰገድ ኒስ ሄደዋል አሉን። ኒኮልና እኔ የመጨረሻውን የማታ አቶቡስ ተሳፍረን ማርሰይ ወረድን፡፡ አንድ ወሻቃ ቦታ ሆቴል
አገኘን። ባለ ሁለት አልጋ ክፍል ተከራየን። ሁለታችንም ለባህራም
ሰግተናል። አንቅልፋችን እንደማይመጣ ግልጽ ነው:: አንድ ቆሻሻ ብጤ ጭር ያለ ካፌ ገብተን ከልቫዶስ እየጠጣን፣ እያወራን፣
እየተያየን ሳቃችን እየመጣ፤ እየተሳሳቅን፣ ድንገት ሳቃችንን
አቋርጠን በፀጥታ እየተያየን፣ ስንተያይ ኒኮል በሚያስጐመጅ አኳኋን እየቀላች፣ እየቀላች፣ እየጠጣን እያወራን፤ ከአንድ ሰእት በላይ አሳለፍን፡ ሰከርን፡፡ የተረፈንን ግማሽ ጠርሙስ ካልቫዶስ ይዘነው ሞቃት ሰማይ መሀል
ሆቴላችን ስንደርስ፤ እንዳንተያይ መብራቱን አጥፍተን፣
👍20
#ምንዱባን


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እንደዚያ ልብ ዘርታ ትጫወት የነበረችው ሴትዮ አሁን በድንገት ተለዋወጣ ዝልፍልፍ አለች::

«ያንተ ያለህ! ምነው ፋንቲን፤ ምን ነካሽ?» ሲል መሴይ ማንደላይን
ጠየቃት::

መልስ አልሰጠችውም:: አፍጥጣ ትመለከትበት ከነበረው አቅጣጫ
ዓይንዋን አላዞረችም:: በአንድ እጅዋ የመሴይ ማንደላይንን እጅ ጨብጣ በሌላው እጅዋ ወደኋላው እንዲያይ አመለከተችው::

ፊቱን አዞረ:: ገናቬርን ከዚያ ቆሞ አየው::


ከዚያ በኋላ ምን እንደሆነ እንመልከት::

በጣም ከመሸ ነበር መሴይ ማንደላይን ፍርድ ቤቱን ለቅቆ የወጣው::ወዲያው እንደወጣ ከበራፍ ይጠብቀው በነበረው ሠረገላ በቀጥታ ወደ ቤቱ
ተመለሰ፡፡ ሊነጋጋ ሲል ነበር ሞንቴስ ሰር ሞንቴስ ከተባለ ሥፍራ የደረሰው::ከዚያም እንደደረሰ ለመሴይ ላፌት ደብዳቤ ከላከ በኋላ ነበር ፋንቲንን
ለመጠየቅ ወደ ተኛችበት ክፍል የሄደው::

ፍርድ ቤቱ ሻምፕማቲዩን በነፃ ካሰናበተ በኋላ ሕግ አስከባሪውና
ዳኞቹ ተመካከሩ፡፡ የተመካከሩት መሴይ ማንደላይንን ያሳሰሩት ወይም አያሳስሩት እንደሆነ ነበር፡፡ መታሰር እንዳለበት ወስነው በአለበት እንዲያዝ ትእዛዝ ሰጡ፡፡ ሕግ አስከባሪው በአስቸኳይ ወደ ከተማው ፖሊስ አዛዥ
ወደ ዣቬር ወዲያውኑ መልክተኛ ልኮ ከንቲባውን እንዲይዝ ትእዛዝ
አስተላለፈለት::

ዣቬር ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነሳ መልእክተኛው ደርሶ ትእዛዙን
ሰጠው:: መልእክተኛው የፖሊስ አባል ሲሆን ይህም መለዮ ለባሽ ፍርድ ቤቱ ውስጥ ምን እንደተከሰተ ለዣቬር ባጭሩ አስረዳው::

የትእዛዙ ፍሬ አሳብ «የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ከንቲባ መሴይ ማንደላይን ከእስር ቤት ያመለጠው ዣን ቫልዣ መሆኑ ስለታወቀ የፖሊሱ ኣዛዥ
በቁጥጥር ስር እንዲያውለው ፍርድ ቤቱ አዟል» የሚል ነበር፡፡

ዣቬር አንድ የአስር አለቃና አራት ወታደሮችን አስከትሎ ከከንቲባው
ቤት ሄደ:: መሴይ ማንደላይን ፋንቲን ከነበረችበት ክፍል መሆኑን ጠይቆ ከተረዳ በኋላ በቀጥታ ወደዚያ ሄዶ በሩ ላይ ተሰክቶ በነበረው ቁልፍ በሩን ቀስ ብሎ ከፍቶ ገባ፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ በሩን ከፈተው እንጂ ወደ ውስጥ ለመግባት
አልደፈረም:: ካፖርቱን እስከ አንገቱ ግጥም አድርጎ ቆልፎ ቆቡን አጥልቆአል፡፡ወደ ክፍሉ ያስገባው መላ ሰውነቱን ሳይሆን አንገቱን ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም
በሩ ስለተከፈተ ማን እንደሆነ በግልጽ ይታያል፡፡ እንደዚያ ሆኖ ምናልባት ለአንድ ደቂቃ ያህል ዝም ብሎ ቆሞ ይሆናል:: ይሄኔ ነው ፋንቲን አይታው

ለመሴይ ማንደላይን የጠቆመችው፡፡ ሁለቱ ተያዩ:: ዣቬር አልተነቃነቀም:: ያ ግዙፍ ሰውነቱ እንኳን ካፖርት ደርቦበት እንዲሁም ይከብዳል፡፡ ፊቱን አጠቋቁሮ ፧ ጥርሱን አግጥጦና
ዓይኑን አፍጥጦ «አገኘሁህ» በማለት ሲያይ በጣም ያስፈራል፡፡

በመጨረሻ ዣን ቫልዣን በመያዙ አካሉ ውስጥ የነበረው ያንን ሰው
አሳድዶ የመያዝ ጽኑ ፍላጎትና ምኞት ተጎልጉሎ ወጥቶ ገጹ ላይ ታየ:: «ዛሬስ ድል መታሁ» የሚለው ደስታው ደግሞ ከዚያች ከጠባብ ግምባሩ ላይ በጉልህ ወጣ፡፡

ዣቬር በዚያች ቅጽበት መንግሥተ ሰማይ ገብቷል፡፡ የዣቬርን
ቁመናና ሁኔታ ረስተን የዘወትር ፍላጎቱና ምኞቱ ምን እንደሆነ ብናጤን «ትክክለኛ ፍርድ ፤ እውነትና ብርሃን የክፉ ሥራ አጥፊዎች ናቸው የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እነዚህም የሕግ፣ የሥልጣን፣ የሕሊናና
የመሳሰሉት የበቀል መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ከዚያ ክፍል ውስጥ ቆሞ : የሚታየው ይህን ለማስፈጸም ነበር፡፡ በእርሱ ዓይን ርህራሄ፣ ፍርሃትና ይሉኝታ የሕግ ጠላቶችና የትክክለኛ ፍርድ እንቅፋቶች ሲሆኑ ይህ ሰው
ፍርድን ላለማዛባት ምንም ነገር ያደርጋል፡፡ የዘወትር እምነቱ ከህብረተሰብ መካከል ቅጥፈት፣ ተንኮልና ወንጀል ጨርሶ ማስወገድ ሲሆን ይህን
ከማስፈጸም ወደኋላ ስለማይል «የነገሮች መነሻዎች ምንድናቸው» የሚል አስተያየት አያውቅም:: ዓላማውና ምኞቱ ሕግን ማስከበር ነው:: ይህ
እምነቱ ነው ፊቱ ላይ እየታየ ገና ሲመለከቱት የሚዋጋ በሬ ያስመሰለው።

መሴይ ማንደላይን ከመንጋጋው ፈልቅቆ ካወጣት ወዲህ ፋንቲን
ዣቬርን አላየችውም፡፡ ስለዚህ በጠዋት የመጣው እርስዋን ለመያዝ እንጂ ለሌላ ነገር ነው ብላ አልገመተችም:: ፊቱ ያስጠላታል፡፡ የእርሱን ፊት
ለረጅም ጊዜ ካየች ሞትዋ የተቃረበ ይመስላታል:: ስለዚህ ፊትዋን በእጅዋ ሽፈነችው::

«መሴይ ማንደላይን ያድኑኝ፧ ከዚህ ጉድ ያወጡኝ» ስትል ጮኸች፡፡

«አይዞሽ፣ አንቺን ሳይሆን እኔን ፍለጋ ነው የመጣው::»

ከዚያም ወደ ዣቬር ዞር ብሎ «ምን እንደምትፈልግ አውቃለሁ
አለው::

ዣቬር «ፈጠን በል» ሲል መለሰ፡፡
ዣቬር ይህን ሲናገር ከቆመበት አልተነቃነቀም:: ግን ዘወትር
የጠላቸውን በሚያይበት ዓይን ነበር ዣን ቫልዣን ያየው:: ከሁለት ወር በፊት ፋንቲንን ያያት ልክ እንዳሁኑ አጥንት ሰርስሮ በሚገባ ዓይነት አስተያየተ ነበር፡፡ ለዚህ ነው አሁንም የፈራችውና «አድነኝ ብላ» የጮኸችው::

ዣቬር እንድ እርምጃ ወደፊት ተራመደ::
«እንሂድ፣ ምነው ወደኋላ!» ሲል ጠየቀ፡፡ ያቺ የተከፋች ሴት ኣካባቢዋን ቃኘች፡፡ ከክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሴርዋና ከንቲባው መሆናቸውን ተገነዘበች፡፡
ይህ ሰው የመጣው «እኔን ሊወስድ እንጂ ለሌላ ሰው አልመጣም» ብላ ስለደመደመች ሰውነትዋ ተንቀጠቀጠ፡፡ ሆኖም ወዲያው ጨርሶ የማይታሰብ
ነገር አየች:: ያየችው ነገር በእውን ሳይሆን በቅዠት እንኳን ሊታያት
የማይችል እንደሆነ ገመተች::

የፖሊሶ አዛኝዥ ዣቬር የመሴይ ማንደላይንን ማንቁርት ይዞ ሲጎትትና መሴይ ማንደላይን አንገቱን ሲደፋ ተመለከተች:: ዓለም ከፊትዋ የተደፋ
መሰላት::

ዣቬር ሰላሣ ሁለት ጥርሶቹን በመሉ እያሳየ ከት ብሎ ሳቀ::

«የእኛ ከንቲባ!» በማለት በይበልጥ አንቆ ያዘው::

መሴይ ማንደላይን አንገቱን ለማስለቀቅ አልሞከረም፡፡ ግን «ዣቬር» ሲል ተናገረ::

ዣቬር ጣልቃ በመግባት አቋረጠው:: ክቡር የፖሊስ አዛዥ ብለህ ጥራኝ» አለው::
«ክቡር» አለ ዣን ቫልዣ ፧ ብቻችንን ብንሆን አንድ የምጠይቅህ ነገር
ነበረኝ::
«ጮክ በል፣ ድምፅህን ከፍ ኣድርገህ ተናገር:: ሰዎች እኔን ሲያናግሩ ጮክ እያሉ ነው የሚያነጋግሩኝ» አለ ዣቬር፡፡
ድምፁን ዝቅ አድርጎ ዣን ቫልዣ ንግግሩን ቀጠለ::

«አንተን በግል የምለምንህ ጉዳይ አለኝ፡፡››
‹‹ጮክ ብለህ ተናገር ብዬህ እኮ ነበር፡፡»
«ግን የምነግርህ ነገር እኔና አንተ እንጂ ሌላ ሰው መስማት ስለሌለበት ነው::

“ጉዳዩ መሰለህ፤ በአንተ ጉዳይ እኔን ምን አስጨነቀኝ፣ አልሰማም::

ዣን ቫልዣ ጠጋ ብሎ በችኮላ አሁንም ድምፁን ዝቅ እድርጎ
የሚከተለውን ተናገረ::

« ሦስት ቀን ብቻ ስጠኝ! የዚህች የተከፋች ሴት ልጅ ሄጄ ላምጣላት::የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ እኔ እከፍላለሁ:: ከፈለግክ አብረን ልንሄድ እንችላለን፡፡

«በእኔ ላይ ነው የምታሾፈው» አለ ዣቬር፡፡ «እስከዚህ ሞኝ
አትመሰለኝም ነበር:: ሦስት ቀን ስጠኝና የዚህችን ሴት ልጅ ላምጣ' ትለኛለህ:: በጣም ታስቃለህ፡፡»

የፋንቲን ሰውነት ተንቀጠቀጠ፡፡

«ልጄን» ስትል ጮኸች፡፡ «ልጄ ዘንድ ሊሄዱ ነዋ! ወይኔ ልጄ፧
አልመጣችም ማለት ነዋ! ሲስተር ይንገሩኝ፤ ልጄ የት ናት? መሴይ
ማንደላይን፤ ክቡር ከንቲባ ልጄን እፈልጋታለሁ!»

ዣቬር ከፍተኛ ድምፅ በማሰማት መሬቱን በጫማው ረገጠው::
👍18
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በታደለ_አያሌው



“ምንድነዉ እመ?”

እየቆየ ፍርሐት እየለቀቀብኝ፣ ላብ እያጠመቀኝ መጣ፡ ቢያንስ ቢያንስ እንዴት ድምፅዋን እንኳን አልሰማሁትም? ለምን አላለቀሰችም? “ኧረ ልጄስ? ልጄ አታመጡልኝም?” አልሁኝ ከአሁን አሁን ቱናትን አምጥተዉ ያስታቅፉኛል ብዬ ብጠብቅ ዝም ስላሉኝ፡ አጭር ጊዜ በፈጀ
ቀዶ ሕክምና ቢሆንም የወለድሁት፣ የእናት ወጉ ደርሶኝ ገና ጡቴን ለልጄ አላጠባኋትም ጡት ማጥባት ቀርቶ ለዓይኔ እንኳን አላሳዩኝም፡

“አይ፣ ለትንሽ ጊዜማ ማሞቂያ ክፍል አትቆይም ብለሽ ነዉ? እንግዲህ ዶክተርሽ ያለችን እንደዚያ ነዉ” አለች እመዋ፣ ከእሸቴና ባልቻ ጋር የያዘችዉን ሞቅ ያለ ጨዋታ አቋርጣ ትኩረት እየሰጠችኝ፡

“እኮ ባይሆን አሳዩኛ። ላያት እፈልጋለሁ”

“ቆይ ትንሽ ተብለሽ እኮ ነዉ: አንቺም ትንሽ አረፍ በይ እስኪ ፊት”

“እመዋ፤ ወይ ወደ ልጄ ዉሰጅኝ ወይ ደሞ ልጄን አምጭልኝ” አልሁኝ፣ ከአልጋዬ ላይ ለመነሳት እየተገለገልሁ አቅም አጣሁ እንጂ ማንም አይመልሰኝም ነበር ለምንም ነገር እንዲህ ሆኜ አላዉቅም ለካ እንዲህ ነዉ የሚያደርገዉ? አሁን በአሁን እናት ሆኜ እርፍ! የእናት ሆድ ኖሮኝ
ቁጭ! ጭራሹን ያላየኋት ልጄ በዓይን በዓይኔ ዞረች᎓᎓ ናፈቀችኝ፡ ራበችኝ፡ ደግሞ ልቤ እንዴት ነዉ የሚደልቀዉ? ልጄን እንጂ የፍርድ ቤት ዳኛ አይደል የምተያየዉ፡

የናፍቆቱስ እሺ ይገባኛል፤ ፍርሃቱን ግን ምን አመጣዉ?
የልቤ መንቀጥቀጥ ቆዳዬ ላይ እስከሚታወቅ ድረስ በጣም ፈርቻለሁ ጭንቅላቷን ማየት ነዉ ፤ያስፈራኝ: ትልቅነቱ ምን አህሎ ይሆን? ራሷስ ምን ታህል ይሆን? ኹለት ኪሎ እንኳን መሙላቷን እንጃ አተነፋፈሷ ልክ ነዉ? በቅድመ ወሊድ እንደ ተፈራዉ፣ የጀርባዋ ነርቭ ክፍተት ፈጥሮ ይሆን? ቢያንስ እግሮቿን ማንቀሳቀስ ትችልም እንደሆነ
እኮ ገና የነገረኝ የለም: ዓይኖቿም በትክክል ማየታቸዉን አላወቅሁም
ወይስ እግዚአብሔር ተአምር ሠራ? ባልቻ እና እመዋ እንደ ተማመበት ድንቅ ሥራዉን አሳይቷቸዉ ይሆን? በተአምሩ የሰዉ መልክ፣ የሰዉ ጤና፣ የሰዉ ትንፋሽ ሰጥቷትስ ቢሆን! እሱንስ ቢሆን ማን ነገረኝ?
እግዚአብሔር እኮ ሥራዉ የሚታወቀዉ አንድም በጨቅላዎች ነዉ ይባላል፡፡ ከማሕጸን እንደ ወጡ ገና የጡትን ቦታ እና ጥቅም አጥተዉት
አያዉቁም: ልጄንስ ጡት አያምራት ይሆን? ካላየኋትማ መሞቴ ነዉ፡

እንደገና ፈራኋት ፡ እንደገና ናፈቅኋት።

“አንቺ ግን አየሻት ወይ እመ?” አልኋት፣ እጆቼን ከጡቶቼ ላይ ሳላነሳ።

“ማንን፣ ቱናትን?”

“አሃ፤ ስምም አዉጥታችሁላታላ?” አለ ባልቻ፣ ከእመዋ አፍ ተቃምቶ።

“ቱናት ብያታለሁ በበኩሌ” አለች፣ እመዋ:

“እመዋ” ስል ጠራኋት ቆጣ ብዬ፣ የባልቻ አጠያየቅ ወሬ ለመለወጥ
መሆኑ ስለ ገባኝ፡

“ዉብዬዋ” አለችኝ፣ የእናት እጇን ጭምር እየሰጠችኝ ይኼዋ እንዴት
እንደምታቆለማምጠኝ! ቁልምጫዋንስ ማቆላመጥ ታዉቅበት የለ? እሷ እናትነቷን እንዲህ ባጠጣችኝ ቁጥር፣ የእኔም ጉጉት ሰማይ ይደርሳል
እሷ ለእኔ እንደምትሆነዉ፣ እኔም ለልጄ ለመሆን ቋምጫለሁ

“እመዋ”

“እመት ዓለሜዋ”

“ስሞትልሽ! ስሞትልሽ ልጄን አምጭልኝ'

“ኧረ ቀስ! ምነዉ ልጄ? ወዲያዉስ የሐኪምሽ ወዳጅነት ላንቺ መስሎኝ! እንዲህ ሆነሽ ትወስድሽ ሆይ ወይ ደግሞ ቱናትን እንዲያ እዳለች ታመጣልሽ እንደሆነ፤ ሐኪምሽን ራስሽ የማትጠይቂያት”

"እኮ ጥሪልኛ እመዋ ዶክተሯን ጥሪልኝ እሺ”

እንደማልለቃቸዉ ሲያዉቁ ዶክተሯን ማስፈለግ ጀመሩ፡ ነገር ግን ሌላ ተረኛ ነፍሰ ጡር ለማዋለድ፣ ወደ ማዋለጃ ክፍል ቅርብ ጊዜ እንደ ገባች ከነርሶቹ መስማታቸዉን ነገሩኝ፡
አላመንኋቸዉም በይበልጥ
እየፈራሁላት፣ በይበልጥ እየተጠራጠርኋቸዉ መጣሁ ቅጽበት በቆየሁ ቁጥር ክፉ ክፉዉን ለሚያሳስበኝ መንፈስ መረታት ያዝሁ፡ ጭራሽ በሕይወት ባትኖር ይሆናል እንጂ፣ ቢያንስ እንዴት ድምፁዋን እንኳን
አያሰሙኝም?

“አአአ..አንድ ሐሳብ መመመመ..መጣልኝ” ሲል ሰማሁት እሸቴን፣ እስከ
አሁን ዓይኖቹን ከማንከራተት በቀር ትንፍሽ ሳይል ቆይቶ፡ “ዉዉዉ..
ዉቤ? ”

“እየሰማሁህ ነዉ”

ሐሳቡን አንድ ብሎ ሊነግረኝ ሲጀምር ገና፣ ልታዋልድ ኦፕራሲዮን ክፍል ገብታለች የተባለችዋ ዶክተር የክፍሉን በር ከፍታ ገባች፡

“ኦንኳን ማርያም ማረችሽ” አለችኝ፡

“ማርያም ታኑርሽ” አለች እመዋ ቀድማኝ ወዲያዉም ከጎኔ ቁጭ
ካለችበት የአልጋዉ ጫፍ ብድግ ብላ፡ ዶክተር ሸዊት ያ ብዙም
የማይለያትን ፈገግታዋን
ሳትቀንስ ሁሉንም እያቀፈች ሰላምታ ከተለዋወጠች በኋላ፣ እኔንም ጎንብስ ብላ ሳመችኝ፡፡ ግንባሬን አንገቴን እና እጆቼን እየደባበሰችኝ ሳለ፣ ለምን ልጄን እንደማያመጡልኝ ልጠይቃት ስል ቀልቧን ወደ እመዋ አደረገችብኝ፡፡

“እመዋ? እንኳን ደስ አለዎ”

“በአምላክሽ!”

“መቼስ ረስተዉኝ አይሆንም፤ ረሱኝ እንዴ ? "

“ተይ እንጂ! ምን ብረሳ ብረሳ፣ አንቺን እረሳ ብለሽኝ ነዉ? ምነው
አንድዜ እንኳ ከዉብዬ ጋ ለክረምቱ ይሁን ለገናዉ ዕረፍት
መጥታችሁ አብረንም አልሰነበትን?”

“አልረሱኝማ”

“ አንቺን? እንዲያዉ ያቺን ጨዋታሽ የምረሳልሽ መስሎሻል?”

“የቷን?” አለች፣ ለመፍካት ችኩል የሆኑ ጥርሶቿን እየገለጠች

“ምነዉ እንኳን አንድዜ፣ የሩስያ ምንቴስ ነዉ ያልሽኝ ሰዉ በዉብርስቴ ደም ግባት የሆነዉን ሁሉ አጫዉተሽኝ?”

“ስለ እሱ ጉድ ነግሬሽ ነበር ወይ እመዋ?”

“እህሳ”

“ለእኛም ንገሪን እንጂ ዶክተር” አለ ባልቻ፣ ያለ ወትሮዉ ለወሬ ሰፍ ብሎ፡ የእሸቴም ጆሮ ከምኔዉ ቀጥ እንዳለ! የእሸቴ እና የባልቻስ ይሁን እሺ፣ እመዋ እንኳን እንደ አዲስ ለመስማት በዓይኖቿ ደጅ ስትጠናት ሳይ እኔም የልጄ ናፍቆት በረድ አለልኝ፡፡

“ጉዷ ያልቅ መስሏችኋል?” ብላ ጀመረች፡ “ይቺ ጉደኛ! የተመረቅን
ሰሞን ነዉ ነገሩ። ቀድሞዉንም ቢሆን በዉጤት እንደ ምንም እቀራረባት እንደሆነ እንጂ ደርሼባት አላውቅም:: በተለይ የመመረቂያ ጥናቷን ያዩላት ሰዎች ሁሉ እዴት ይደነቁባት እንደነበር አትጠይቁኝ። እና እንደ አጋጣሚ፣ በዚያ ሰሞን የሩስያ አምባሳደር ከሀገራቸዉ የመጡ በጎ ፈቃደኛ
ሀኪሞችን እየመሩ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መጥተዋል። ጠሪዉ ደግሞ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ነዉ: የዚያን ዕለት ታዲያ፣ የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዜዳንት ራሱ ስልክ ደዉሎላት ኹለት ሁነኛ ሰዎች እንድትመርጥ እና በጎ ፈቃደኛ ሩስያዊ ሀኪሞችን እንድታግዝ ያዝዟታል”

“ማንን?”

“ይቺን ነዋ፤ ዉብርስትን''

“እሺ”

"እሷ ደግሞ እኔን እና አንድ ሌላ ሐኪም ስትጠይቀን፣ እናግዛለን ብለን ሳይሆን እንጠቀማለን ብለን ወደ ተባሉት በጎ አድራጊዎች በጠዋት †ነስተን ተከተልናት።
በዚያች አንድ ቀን ታዲያ፣ ሩስያዉያኑ ያልደረሱበት የጎንደር ዙሪያ ጤና ጣቢያ የለም። እኛም አብረናቸዉ እየዞርን እነሱ ለጤና ጣቢያዎቹ ያመጡልን መድኃኒት ስናድል እና ለጥቂት አበሻ ሕመምተኞች ደግሞ መጠነኛ ሕክምና ሲሰጡ ስናይ ዋልን
ማታዉኑ፣ ዩኒቨርስቲዉ እንግዶቹን እራት ካልጋበዝሁ አለ። አምባሳደሩ ግን አመሻሹ ላይ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ቢሆንም ዕቅዳቸዉ፣ ከስንት መለመን በኋላ የበረራ ሰዓታቸዉ እንዲዘገይ ተስማምተዉ በግብዣዉ ላይ
ተገኙ። እኛም እንደ እንግዶች በክብር ተጠርተን፣ መጥሪያዉ ላይ በተጠቀሰዉ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ተገኝተናል። የከተማዉ ከንቲባ፣ የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዜዳንት፣ምክትሎቻቸዉ እና ዘመዶቻቸዉ ጭምር
መጥተዉ ሳይሆን አይቀርም፣ ያን የሚያህል አዳራሽ ጢም ብሏል።
የጎንደር መታወቂያ የሚባሉ አዝማሪዎችም መድረኩን ሞልተዉታል።ብርቆዎች፣ ጨዋታዎች፣ ሳቆች ድብልቅልቅ አድር ገዉታል”
👍33
#ሳቤላ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


....ቀና አለችና እስከ መቸም ከልቡ በማይጠፋ አመለካከት አየችው " እሱም የተስፋ መቁረጥ አስተያየት መሆኑ ቶሎ ገባው "

“ አይደለም ” አለችው ራሷን ነቅንቃ ። “የሥቃይ ቤት ነው እኔም ከእንግዲህ ከዚህ ቤት መኖር አልችልም " ወዴት አባቴ እንደምሔድ ዛሬ ሌሊት ሳስብ
አንዳችም ብልሃት ሳላገኝ ተጎልቸ አደርኩ " እኔ በዚህ ሰፊ ዓለም አንድም ሁነኛ ሰው የለኝም "

ከልጆች ፌት ምስጢር መጫወት ተገቢ አይደለም ከሚገምቱት በላይ መስማትና ማስተዋል እንደሚችሉ ማወቁ ተገቢ ነው ትንንሽ ጋኖች ትልልቅ ጆሮዎች
አሏቸው የሚባለው አነጋገር የሚያስገርም ሐቅ ነው ሎርድ ቬን አንገቱን ቀና አድርጎ ሚስተር ካርላይልን ሽቅብ ይመለከተው ጀመር "

“ ሳቤላ “ ኮ ከኛ ቤት እወጣለሁ ብላ ዛሬ ጧት ነገረችኝ " ለምን እንደሆነ ልንገርዎት ? ትናንት ማታ እማማ ተናድዳ ስለ መታቻት ነው "

“ ዝም በል ዊልያም ” ብላ አቋረጠችው ሳቤላ „ “ ሁለት ጊዜ በጥፌ መታቻት ጉንጮ ላይ ” አለና ልጁ ነገሩን በመቀጠል “ሳቤላም አለቀሰች እኔም ጮህኩ በዚህ ጊዜ እማማ እኔንም አጮለችኝ " ልጆች ለመመታት ነዉ የተፈጠሩት ትላለች ሞግዜቴ። ሻይ ስንጠጣ ማርቨል መጥታ ለሞግዚቴ ነገረቻት እማማ ሳቤላን የምትመታት እኮ ሳቤላ በመልክ ስለምትበልጣት ...>>

ሳቤላ ፡ አፉን ይዛ አቋረጠችውና አንዲት ሠራተኛ ጠርታ ወደ ልጆች ክፍል አስወሰደችው : የሚስተር ካርላይል ዐይኖች በንዴትና በኅዘን ብርዝ አሎ „ “ እውነት ነው ? ” አላት ፊቷን ወደሱ ምልስ ስታደርግ “ እውነትም ሁነኛ ሰው ያስፈልግሻል።

ዕድሌ የጣለብኝን ዕጣ መቀበል አለብኝ ' ሲቀር ሲውል ሎርድ ማውንት እስቨርን እስኪመለስ ድረስ ”

“ ከዚያ በኋላስ ምን ትሆኛለሽ ? ''

ከዚያ በኋላ የምሆነውን ምንም አላውቅም ” አለችው ልማደኛው እንባዋ ልትቈጣጠረው ከማትችለው ፍጥነት በላይ እየገነፈለ „ “ እሱ ለኔ የሚሰጠኝ ሌላ ቤት የለውም ። እኔ ደግሞ ከወይዘሮ ማውንት እስቨርን ጋር አብሬ መኖር አልችልም "
መንፈሴን ድቅቅ አድርጋ እንደ ስበረችው ሁሉ አሁንም ልቤን ታፈሰዋለች » እኔ በሷ ይህን ያሀል መበደል የሚገባኝ ስው አልነበርኩም ... ሚስተር ካርላይል

በርግጥ አልነበርሽም ” አላት ሚስተር ካርላይል “ አሁን ምን ላድርግልሽ እችላለሁ ? ''

“ አሁን አንተም ሆንክ ሌላ ምንም ሊያደርግልኝ አይችልም : ”
“ አንቺን መርዳት የምችልበት መንገድ ባገኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር " መቸም ኢስትሊንም ላንቺ የደስታ ቤት አልነበረም ነገር ግን ከለቀቅሺው ወዲህ የባሰ ተጐሳቁለሻል

የደስታ ቤት አልነበረም አልከኝ ? ” አለችው የኢስትሊን የኑሮ ትዝታ ድቅን እያለባት “ ኧረ እሱስ ነበረ እንግዲህም እንደሱ ደስ የሚል ኑሮ የማገኝ አይመስለኝም ሚስርተር ካርላይል ኢስትሊንን አቃለህ አትንገረኝ " ምነው አሁን
እነዚያ ያሳለፍኩዋቸው የመከራ ወሮች ወደ ሕልም በተለወጡና አባቴን በሕይወቱ አግኝቸው ኢስትሊን ውስጥ እንደ ዱሮአችን በሰላም ስኖር ከእንቅልፌ በነቃሁ . .

“ ወደ ኢስትሊን የምትመለሽበት አንድ መንገድ ብቻ አለ ” አላት መንፈሱ ጭንቅ ጭንቅ እያለው ልቡ በጣም እየመታ እጂዋን ያዝ አድርጎ ምናልባትም ሳይታወቀው ሊሆን ይችላል · ጣቶቹ ከጣቶቿ ጋር እየተጫወቱ " ንግግሬ የሚያስከፋሽ ከሆነ መልሽኝ : በጥፋቴም ይቅርታ አድርጊልኝ "የኢስትሊን እመቤት ሆነሽ
እንድትመለሽበት ብጠይቅሽ ድፍሬት ይሆንብኛል ? ”

ምን ለማለት እንደ ፈለገ ፍጹም አልገባትም „ “እመቤት ሁኜ ወደ ኢስትሊን መመለስ ? ” አለችው ድንግጥ ብላ "

“ አዎን ' የኢስትሊን እመቤት የኔ ባለቤት ሆነሽ " ብሎ መላሰላት
አሁን ገባት መገረምም መደንገጥም †ነባበሩባት " በርግጥ ሚስተር ካርላይል
ብዙ ውለታ የዋለላት ከደግንቱ እንከን ያላገኘችበት ሰው ስለነበር ትወደው ነበር ሚስቱ የመሆን ጉዳይግን እሱ አፍ አውጥቶ እስከ ጠየቀበት ሰዓትድረስ አሰባው
አታውቅም ደነገጠችም ለዚሁ ነበር እጅዋንም ከእጁ አስለቅቃ ሊሆን እንደማይችል ልትነግረው ቃጣትና እጅዋን ሳብ ስታደርግ እሱ ደግሞ ጠበቅ አደረጋት።

የመናገር ፈራ ተባው ለቀቀው " ጠቅላላ ስለሷ ያለውን ስሜት የትዳሩን ዓላማና የፍቅሩን ነገር በማይስቱና ልብን በሚወጉ የቃላት ቀስት ነደፋት ልብን በሚነካ ንግግር ሐሳቡን በሙሉ በምታውቀው ሐቀኝነቱ ግልጽልጽ አድርጎ አጫታት ሁለቱ በዚህ ሁኔታ እንዳሉ ወይዘሮ ማውንት እስቨርን ገባች ደነገጠችና ምንም ሳትናገር በሐሳቧ ብቻ ላቀረበችው ጥያቄ መልስ የምትጠብቅ
ይመስል ቀጥ ብላ ቆመች።

ሚስተር ካርላይል ሳቤላን ያዳነ መሰለውና ራሱን ለማስተዋወቅ ወደሷ ቀረብ ሲል ሳቤላ ደግሞ ተረጋጋችና “ ወይዘሮ ማውንት እስቨርን ” ብላ አስተዋወቀች ,
ሎርድ ማውንት እስቨርን ባለመኖራቸው በጣም አዝናለሁ " እሳቸው ያውቁኝ ነበር እኔ ሚስተር ካርላይል እባላለሁ ” አላት "

“እኔም ስለአንተ ሰምቻለሁ " አለችው ሸጋ መልኩን እየቃኘችና አክብሮቴን ለማትወዳት ሴት ሲሰጥ በማየቷ ቅር እያላት “ከወይዘሮ ሳቤላ ቬን ጋር ይኸን ያህል የቀረበ ወዳጅነት እንዳላችሁ ግን አልሰማሁም " ”

“ እስካሁን እንኩዋን ለእርስዎ የመሰለዎትን ያህል የጠና ወዳጅነት አልነበረንም” አላት ወንበር ጠጋ ካዪረገላት በኋላ ለራሱም ሌላ እያስተካከለ „ “ አሁን ግን ወዳጅነታችንን የጠና ለማድረግ ሚስቴ እንድትሆን እየለመንኳት ነበር '

እመቤቲቱ ከዚያች ከምትጠላት ልጅ የምትላቀቅበት ፍንጭ በማግኘቷ የከፋው ፊቷ የደስታ ብርሃን ፈነጠቀበት " ሚስተር ካርላይልን እንደ ትልቅ ባለውለታዋ
አድርጋ አየችው ።

“ግድ የለሹ አባቷ ያለምንም አለኝታ ጥለዋት እንደሞቱ • አንተም ታውቃለህ ስለዚህ እንደዚህ ያለ ከፍተኛ የጋብቻ ጥያቄ ሲቀርብላት ሳቤላ በደስታ መቀበል አለባት " ደግሞም እንደ ሰማሁት ኢስትሊን በጣም የሚያምር ቦታ ነው ይባላል
አለችውና ፊቷን ወደ ሳቤላ መልሳ “ ለመሆኑ የሷ መልስ ምንድነው? ” ብላ ጠየቀችው።

ኅቤላ ለሷ በቀጥታ መልስ እንደ መስጠት ራሷን ዝቅ እንደ ማድረግ ቆጠረችውና ሚስተር ካርላይልን 'እንዳስብበት ጥቂት ሰዓት ልትሰጠኝ ትችላለህ ? '' አለችው "

“ በነገሩ በደንብ ብታስቢበት ለኔም በጣም ደስ ይለኛል " ስለዚህ ከሰዓት በኋላ እመለሳለሁ ” ብሏት ሔደ ።

ሚስተር ካርይል ከወይዘሮ ማውንት እስቨርን ጋር ሲነጋገር ሳቤላ ከክፍሏ ግብታ ብቻዋን በጣም ግራ የሚያጋባ ሙግት ጀመረች " ሳቤላ ከልጅ እምብዛም
አትሻልም ነበር አስተሳሰቧና ክርክሯ ሁሉ እንዶ ልጅ ላይ ላዩን እንጂ ጥልቀትና ብስለት አልነበረውም " ሚስተር ካርላይል የተራ ቤተሰብ ልጅ መሆኑንና እንደሷ ከትልቅ ሰው ባለወለዱ አቻዋ ያለመሆኑን ነገር አላሰበችውም " ኢስትሊን ለዘለቄታ መኖሪያነት ጥሩ ቦታ ነበር " በመጠን በውበትና በጠቃሚነትም ረገድ
አሁን ከምትኖርበት ከካስል ማርሊንግ በጣም የላቀ ነበር " ነገር ግን ኢስትሊንን የሚስተር ካርላይል ሚስት ሆና ስትገባበት የሎርድ ማውንት እስቨርን ልጅ ሆና እንደ ኖረችበት እንደማይሆንላት አላሰበችውም " ተወልዳ ካደገችበት ድምቀት
👍192
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

....አንድ ጊዜ የማጠቃለያ እንቅስቃሴዬን ስሰራ፣ ክሪስ እንግዳ ስሜት ፊቱ ላይ እየተነበበ ሲመለከተኝ አየሁ: በቅርቡ አስራ አምስት አመት ልደቱን ያከብራል፡ እንዴት ይሆናል? ትልቅ ሰው እንጂ በጭራሽ ልጅ አይመስልም
ከልጅነት በፍጥነት እየወጣ እንደሆነ የሚናገሩት እነዚያ አይኖቹ ናቸው?ከዚያ ወደ ክሪስ ሄድኩና እጆቼን ወደ እሱ ዘርግቼ “ክሪስ ና ከእኔ ጋር እንደንስ፧ እንዴት እንደሆነ ላስተምርህ?” አልኩት።በመገረም ፈገግ አለና ጭንቅላቱን በመነቅነቅ እንደማይችል ነገረኝ፡ “ባሌት ዳንስ ለእኔ አይሆንም ቫልስ ግን መማር እፈልጋለሁ” አለ፡ አሳቀኝ በዚያን ወቅት የነበረን ብቸኛው የቫልስ ሙዚቃ አሮጌ ነበር፡ ወደ ማጫወቻው እየፈጠንኩ ሄጄ እየተጫወተ የነበረውን አወጣሁና የቫልሱን ከተትኩት ክሪስ ገልጃጃ ሆኖ ነበር የያዘኝ በሚያስቅ አይነት አያያዝ ነበር። በዚያ ላይ ያፈረ ይመስላል ደጋግሞ እየተደነቃቀፈ ሮዝ ቀለም ያለው ሹል ጫማዬ ላይ ይቆማል። ቀላል የሆኑትን እንቅስቃሴዎች ላለመሳሳት ጠንክሮ መሞከሩ ልብ የሚነካ ነበር ተሰጥኦው አእምሮው ውስጥና በጥበበኛ እጆቹ ክህሎት
ላይ እንጂ አንዳቸውም ወደ ቅልጥሞቹና ወደ እግሮቹ እንዳልወረዱ ልነግረው
አልቻልኩም::

በመጨረሻ እናታችን የሚያምሩ ላባዎች ያሉበት ጠባብ ኮፍያ፣ ነጭ ጫማና ቀሚስ ያለበት የዳንስ ልብስ ይዛ በበሩ ስትገባ በከባዱ ተነፈስኩ ፍቅር፣ ተስፋና ደስታ በአንድ ሀምራዊ ሪባን በታሰረበት ትልቅ ካርቶን በኩል
በጣም በሚያስብልኝ አንድ ሰውና ሀሳቡን ውስጧ በከተተው በሌላ ሰው አማካይነት ወደ ፎቁ የመጣ ይመስል ነበር በመጨረሻ ክሪስን ሌሎች ዳንሶችን ላስተምረው ስል ተቃወመኝ፡፡ “እንዳንቺ ሁሉንም የዳንስ አይነቶች መማር አያስፈልገኝም: ምክንያቱም እኔ መድረክ ላይ አልደንስም የምፈልገው ከሴት ጋር የመደነስ አጋጣሚ ቢመጣ መቀለጃ
እንዳልሆን ብቻ ነው:" አለኝ፡

“ክሪስ፣ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ በየአመቱ የዳንስ አይነቶች ልክ እንደ ልብስ ፋሽን ይለዋወጣሉ፡ ስለዚህ ከጊዜው ጋር መሄድ አለብህ አለበለዚያ
ማንም ሴት አታፈቅርህም::”

“ልታፈቅረኝ የምትችል ሴት አትኖርም:”

እንደዚያ አይነት ሰው ፋሽን ያለፈበት ቢሆንም እሱ ግን ማንም ሰው ለራሱ ያለውን ምስል እንዲለውጥ እንዲያስገድደው አይፈቅድም የራሱ ሰው
በመሆኑ እወደዋለሁ የኔ ሰር ክሪስቶፈር

ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ እንደሆንን ወቅቶች ለወጥን፡ የለጠፍናቸውን አበቦች አውርደን በበልግ ቅጠሎች ተካናቸው ክረምት ሲመጣም እዚህ
የምንሆን ከሆነ በረዶ መጣል ሲጀምር የቆራረጥናቸውን ነጫጭ ንድፎች እንሰቅላቸዋለን፡፡
ክሪስ መፅሀፍ በማያነብበት ጊዜ ስዕሎችን በውሀ ቀለም ይስላል በበረዶ የተሸፈኑ ኮረብታዎች፣ የበረዶ ሸርታቴ የሚጫወቱ ሰዎች የሚያቋርጧቸውን ሀይቆች፣ በረዶ ውስጥ የተቀበሩ ቢጫና ሮዝ ትንንሽ ቤቶችና ከጭስ መውጫው ውስጥ የተጥመለመለ ጭስ ሲወጣ የሚያሳይ ይሰራል። ሲጨርስ የመስኮቱን ጥቁር ፍሬም ቀለም ይቀባና ስዕሉን ግድግዳው ላይ ሲለጥፈው ደስ የሚል እይታ ያለው ክፍል ይሆንልናል

አንድ ጊዜ እኔና ክሪስ አሮጌው ፍራሽ ላይ ጎን ለጎን ተጋድመን እያወራን ነበር ነፃና ሀብታም ስንሆን ስለምንኖረው ኑሮ እቅድ ስናወጣ “በዓለም ዙሪያ እንጓዛለን፤ በጣም ቆንጆ፣ አስተዋይና የምትስብ ሴት አገኝና ፍቅር ይይዘኛል። ልጅቷ ታማኝ፣ ቤት አያያዝ ላይ ጎበዝ የሆነች፣ የማትጨቃጨቅ፣የማታማርር፣ የማትጮህ... ትሆናለች” ብሎ ሲናገር የበታችነት እንዲሰማኝ
አደረገኝ የወደፊት ትዳር ጠያቂዎቼን የምመዝንበት ደረጃ እያወጣልኝ እንደሆነ አውቄያለሁ: ታዲያ እንደ ክሪስ ያለ ወንድን ፍላጎት ማሟላት የምችለው እንዴት ነው?

ክሪስ… ይቺ ጎበዝ፣ ማራኪ፣ እውቀት ያላትና ቆንጆ ሴት ያልካት አንድ ትንሽ ጉድለት እንኳን የላትም?”

“ለምን ጉድለት ይኖራታል?”

“ለምሳሌ እናታችንን ውሰድ። ምናልባት ጎበዝ ከሚለው በስተቀር በሁሉም ነገር የምታስባት አይነት ሴት ናት።”

“እናታችን ደደብ አይደለችም!” ተከላከለላት᎓ “በተሳሳተ አይነት አካባቢ ስላደገች ብቻ ነው! በልጅነቷ ዝቅ ተደርጋ ትታይ ነበር። ሴት በመሆኗ ዝቅተኝነት
እንዲሰማት አድርገዋታል"

በበኩሌ ለተወሰኑ አመታት ታዋቂ ዳንሰኛ ከሆንኩኝ በኋላ ለማግባት
ስፈልግ ክሪስ ጋ ወይም አባቴ ጋ ካልደረሰ ምን እንደማደርግ አላውቅም።መልከመልካም እንደሚሆን አውቃለሁ- ምክንያቱም ልጆቼ ቆንጆዎች
እንዲሆኑ እፈልጋለሁና። ጎበዝ እንዲሆን እፈልጋለሁ አለበለዚያ ላላከብረው እችላለሁ የመተጫጫ የአልማዝ ቀለበቱን ከመቀበሌ በፊት ቁጭ እንዲል
አደርግና ጨዋታ እንጫወታለን፡ ደጋግሜ ካሸነፍኩት ፈገግ እልና ጭንቅላቴን ነቅንቄ ቀለበቱን ወስዶ የገዛበት ሱቅ እንዲመልሰው እነግረዋለሁ

ማሰሮ ውስጥ የተተከሉት አበቦቻችን ጠወለጉ ለአትክልቶቻችን የፍቅር
እንክብካቤ እናደርግላቸዋለን እናወራቸዋለን፣መምሰል አቁሙ እንላቸዋለን አንገቶቻቸውን ቀጥ እናደርግላቸዋለን ከሁሉም በላይ በጣም ጤናማ የሆነውን የምስራቅ የጠዋት ፀሀይ ያገኙ ነበር።ቅጠሎቹ ግን እየሞቱ ነበር‥. ቢጫ፡ እየሆኑ ይሄዱ ጀመር ።

እያደር ኮሪና ኬሪ ውጪ ለመውጣት መጠየቃቸውን አቆሙ፡ ኬሪ በትንንሽ
እጆቿ ቡጢ ጨብጣ በሩን መደብደቧን ተወች:: ኮሪ በእግሮቹ መሬቱን መደብደብ አቁሞ ትንንሽ የእግሮቹን ጣቶች የማያጣብቃቸውን ለስላሳ
ጫማዎች ማድረግ ጀመረ

አሁን የሚያገኙት ብቸኛው “ውጪ” ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ የሚገኘው የአትክልት ስፍራ ብቻ መሆኑን ተቀበሉ። ምስኪን መንትዮቹ...ከጊዜ በኋላ በሚያሳዝን ሁኔታ ከዚህ ከተቆለፍንበት ክፍል ውጪ ሌላ አለም ከነመኖሩም ይረሳሉ
ልጆች ለማደግ የፀሀይ ብርሀን ያስፈልጋቸዋል እኛ ማድረግ ያለብን እየሞቁ ያሉትን ተክሎች መመልከትና የጣሪያው ስር ክፍል ውስጥ የአትክልት ቦታችን ላይ ያደረግነውን ነገር መታዘብ ብቻ ነው: ፀሀይዋ እኛ ክፍል
ውስጥ ስለማትገባ ፀሀይ ለማግኘት ፍራሾችን መስኮቱ ስር እንከምርና ላዩ ላይ እንሆናለን

በአጭር ጊዜ ውስጥ ፀሀዩዋ መስኮታችን ጋ ስትደርስ ምንም ሳናፍር ልብሶቻችንን ሁሉ አወላልቀን ፀሀይ እንሞቃለን፡፡ የእያንዳንዳችንን ልዩነት
አየንና ስለነገሩ ብዙም ሳናስብ ያደረግነውን በግልፅ ለእናታችን ነገርናት ምክንያቱም የፀሀይ ብርሀን በማጣት መሞት የለብንምና፡ እናታችን እይታዋን
ከክሪስ ወደ እኔ እያደረገች ደካማ ፈገግታ አሳየችን፡ “ምንም አይደለም ግን አደራ አያታችሁ እንዳትሰማ! ሁላችሁም እንደምታውቁት እሷ በዚህ ደስ
አይላትም” አለች።

መጀመሪያ ክሪስን ከዚያ እኔን እያፈራረቀች ትመለከተን የነበረው ንፁሁነታችንን የሚያሳይ ወይም ስለ ፆታዊ ግንኙነቶች መንቃታችንን የሚያመለክት ምልክት ለመፈለግ መሆኑን አውቄያለሁ መንትዮቹ እርቃናቸውን ሆነው እንደ ህፃናት መጫወት ይወዳሉ አንድ
ቀን ኬሪ “ለምን ክሪስ…?” ብላ ጠየቀች᎓ እሱና ኮሪ ያላቸውና እሷ የሌላትን የሰውነት ክፍል እየጠቆመች። ክሪስ ትክክለኛና እውነተኛ የሆነውን መልስ
ለመመለስ በመሞከር “ሁሉም ወንድ ፍጥረታት የመራቢያ አካላቸው የሚገኘው
ከውጪ ነው: የሴቶች ደግሞ ከውስጥ ስለሆነ ነው። ወላጆቻችን እርቃን ሰውነታችንን ልክ እንደ አይኖቻችንና ፀጉራችን ተቀብለውታል ስለዚህ ባለን
መደሰት አለብን” አላት

“ወንድ ወፎች ደግሞ ልክ እንደ ሴቶች የመራቢያ አካላቸው ያለው ከውስጥ በኩል ነው: አለች ኬሪ

ተገርሜ “እንዴት አወቅሽ?" ብዬ ጠየቅኳት᎓

“በቃ አወቅኩ፡”

“መፅሀፍ ላይ አንብበሽ ነው?”
👍26👏2👎1🥰1😁1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ሄሪ ፍርድ ቤቱ የጣለበትን የዋስ ክፍያ ሳያስይዝ፣ በሃሰት ፓስፖርትና
ስም ተጠቅሞ አሜሪካዊ ነኝ እያለ እንዳልመጣ አሁን ሌባ መሆኑን የምታውቅ ልክ በስሙ ስትጠራው አመዱ ቡን አለ፡፡

ካገር ያሰደደው አስከፊ ነገር ሁሉ ዓይኑ ላይ ድቅን አለበት፡ የፍርድ ቤቱ እሰጥ አገባ፣ እስር ቤት የቆየባቸው ቀናትና የግዴታ ውትድርና
አገልግሎት፡

በኋላ ግን ዕድለኛነቱ ትዝ አለውና ፈገግ አለ፡፡

ሄሪ ልጅቷ ግራ እንደገባት አየ፡፡ ስሟን ለስታወስ ሞከረና መጣለት
እመቤት ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ፡

ልጅቷ በመገረም አፈጠጠችበት።

‹‹ስሜ ሄሪ ቫንዴርፖስት ነው›› አላት፤ ካንቺ ይልቅ እኔ የተሻለ አስታውሳለሁ፡ አንቺ ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ አይደለሽም? እንዴነት ነሽ?››

‹‹ደህና ነኝ›› አለች በድንጋጤ ደንዝዛ
ለሰላምታ እጁን ሲዘረጋላት ልትጨብጠው እጇን ስትሰድ መጨበጡን
ትቶ ‹‹ከዚህ በፊት ፖሊስ ጣቢያ እንዳላየሽኝ ሁኚ፧ እኔም እንዲሁ አደርጋለሁ›› አላት፡፡

ግራ መጋባቷ ሲለቃት ፈገግ አለች፡፡ የነገራት ገባትና ‹‹እንዴ ምን ነካኝ
ሄሪ ቫንዴርፖስት›› አለች፡

ሄሪ አሁን ቀለል አለው፡፡ በዓለም ላይ መቼም እንደኔ እድለኛ የለም አለ በሆዱ፡፡

ማርጋሬትም ‹የሆኖ ሆኖ የት ነበር የምንተዋወቀው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አንድ ዳንስ ቤት የተገናኘን ይመስለኛል›› አላት፡፡

‹‹ልክ ነው እዚያ ነው የማውቅህ›› አለች
በዚህ ጊዜ ፈገግ አለ፡፡
የሴራው ተካፋይ አደረጋት፡፡

በመቀጠልም ‹‹ቤተሰቦቼን ላስተዋውቅህ›› አለችና ‹‹እማማ አባባ ሚስተር ቫንዴርፖስትን ተዋወቁት ከ. . . ስትል ከአፏ ነጥቆ ‹‹ከአሜሪካ
ፔንሲልቫኒያ›› አለና ንግግሯን ጨረሰላት፡፡
ፔንሲልቫንያ የሚለው ቃል ካፉ ሲወጣ ዕድሉን ረገመ፡፡ ፔንሲልቫኒያ የት እንደሚገኝ አያውቅም፡፡

‹‹ይቺ እናቴ ናት፤ ይሄ አባቴ፤ ይሄ ደግሞ ወንድሜ ነው›› በማለት በማዕረግ ስማቸው አስተዋወቀችው:: ሄሪ ሁሉንም በዝና ያውቃቸዋል፡ ሄሪ የማርጋሬትን ቤተሰቦች ልባዊ በሆነ በአሜሪካውያን ተግባቢነት ባህሪ ሰላምታ
ሰጣቸው፡፡


ሎርድ ኦክሰንፎርድ እንደልማዳቸው በትዕቢት ተጀንነው ተኮፍሰዋል:
ሄሪ እናቷን ማነጋገር መረጠና ‹‹እንደም ነዎት የኔ፧ እመቤት? የተሰማራሁት
በእንቁ ጌጣጌጥ ንግድ ላይ ነው፤ እርስዎም በዓለም ላይ አለ የሚባል የዕንቁ ስብስብ እንዳለዎት ሰምቻለሁ›› አላቸው፡፡

‹‹እውነት ነው፤ ዕንቁ እወዳለሁ›› አሉት፡፡

ሄሪ የእመቤት ኦክሰንፎርድን የአሜሪካውያን የአነጋገር ቅላጼ ሲሰማ ቀልቡ ተገፈፈ፡፡ ስለእኚህ እመቤት መጽሔት ላይ አንብቧል፡፡ሴትየዋ እንግሊዛዊት ይመስሉት ነበር፡፡ መጽሔቶች ላይ ስለ ኦክሰንፎርድ የተጻፈው ሃሜት ትዝ አለው፡፡ የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ በጦርነት ምክንያት እህል መሸጥ
ባለመቻሉ ምክንያት ከርስታቸው የሚያገኙት ገቢ በመቆሙ ኪሳራ ላይ መውደቁን፣ ሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት የቀራቸውን ሀብት ይዘው በጣሊያንና በፈረንሳይ መኖር እንደጀመሩ፣ ነገር ግን ሎርድ ኦክሰንፎርድ አንድ የአሜሪካ
የባንክ ባለንብረት ቤተሰብ ልጅ በማግባታቸው የተንደላቀቀ ኑሮዋቸው እንዳልተቋረጠባቸው አንብቧል፡፡ ስለዚህ እኚህን አሜሪካዊ ሴት ለማታለል
ከመነሳቱ በፊት መጠንቀቅ እንዳለበት ተረዳ፤ ቢያንስ ለሚቀጥሉት የበረራ ሰዓቶች፡፡

ለእኚህ ሴት መልካም ባህሪ ማሳየት እንዳለበት አውቋል፡ መቼም
ወይዘሮዋ ከመልከ መልካም ወጣት የሚጎርፍላቸውን የሙገሳ ቃላት የሚጠሉ አይመስሉም፡፡ አንገታቸው ላይ የተንጠለጠለውን ውድ የአንገት ጌጥ ጠጋ ብሎ አየው፡፡ እውነተኛ ጌጥ ነው፡፡ የፈረንሳይ አገር ስሪት ሲሆን
በ1880 ዓ.ም የተሰራ መሆኑን ገመተ፡፡

‹‹የአንገት ጌጥዎ የተሰራው በኦስካር ሚኒን አይደለም?›› ሲል
ጠየቃቸው እመቤቲቱን፡

‹‹ልክ ብለሃል››

‹‹በጣም ግሩም ጌጥ ነው››

‹‹አመሰግናለሁ፡፡››

እመቤት ኦክሰንፎርድ ቆንጆ ናቸው፡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ለምን
እንዳገቧቸው አወቀ፡፡ ነገር ግን ሴትየዋ ለምን እሳቸውን እንዳገቧቸው ሊገባው አልቻለም፤ ምናልባትም ከሃያ ዓመት በፊት ሰውየው የሴትየዋን ልብ መስረቅ ችለው ይሆናል፡

‹‹ፊላደልፊያ ውስጥ
የማውቃቸው መሰለኝ፤ የኔ ቤተሰቦች ስታንፎርድ ኮኔክቲከት ውስጥ ነው የሚኖሩትን የቫንዴርፖስት ቤተሰብን
የሚኖሩት›› አሉት እመቤት ኦክሰንፎርድ

‹‹በውነት!›› አለ ሄሪ የተደነቀ ይመስል፡፡ አሁንም ስለፊላደልፊያ ነው የሚያስበው ቅድም አገሬ ፊላደልፊያ ነው ወይስ ፔንሲልቫኒያ ነው ያለው? ጠፋበት፡፡ ወይ የተለያየ ስም ያለው አንድ ዓይነት ቦታ ይሁን ወይም አይሁን የሚያውቀው ነገር የለም፡፡

ትንሹ ልጅ ‹‹እኔ ፔርሲ እባላለሁ›› አለው፡፡

‹‹እኔ ሄሪ እባላለሁ›› አለው ሄሪም፡፡ ፔርሲ የራሱ የማዕረግ ስም
አለው የባላባት ዘር ስለሆነ፡፡ ይህን የማዕረግ ስም አባቱ እስኪሞት ይዞ
ይቆይና ከአባቱ ሞት በኋላ ሎርድ› የተባለውን የማዕረግ ስም ይወርሳል፡፡እነዚህ ሰዎች በማዕረግ ስማቸው ይኮራሉ፡፡ ፔርሲ ግን ለየት ይላል፡ በማዕረግ ስሙ መጠራት እንደማይፈልግ ለሄሪ ነግሮታል፡

ሄሪ ተቀመጠ፡፡ ማርጋሬት አጠገቡ ስለተቀመጠች ሌሎች ሳይሰሙ
ሊያናግራት እንደሚችል ተረድቷል፡፡ አይሮፕላኑ ጸጥ ረጭ ብሏል፡፡ ሁሉም ሰው በአግራሞት አይሮፕላኑን ይቃኛል፡፡

ሄሪ ዘና ለማለት ሞከረ፡፡ ጉዞው ውጥረት የበዛበት ሊሆን እንደሚችል አውቋል፡ ማርጋሬት እውነተኛ ማንነቱን ስላወቀች መጠነኛ ችግር ይገጥመው ይሆናል፡፡ ያቀረበላትን ሃሳብ የተቀበለች ቢሆንም ሀሳቧን
ልትለውጥ ወይም አፏ ሊያመልጣት ይችላል አምርረው ካልጠየቁት የአሜሪካን አገርን ኬላ ማለፍ አያቅተውም፡: ነገር ግን አሜሪካዊነቱን
ከተጠራጠሩትና አጥብቀው ከመረመሩት በሃሰት ፓስፖርት እንደሚሄድ
ያውቁበትና አለቀለት ማለት ነው፡

አንድ ሌላ ተሳፋሪ ሄሪ ፊት ለፊት ያለው መቀመጫ ላይ ተቀመጠ፡፡
ሰውየው ረጅም ሲሆን ራሱ ላይ ኮፍያ ደፍቷል። የለበሰው ሱፍ ልብስ
በጊዜው አሪፍ ልብስ ነበር፡ አሁን ግን ጊዜው አልፎበታል ጫማው ያረጀ
ሲሆን ክራቫቱ ካንገቱ ላይ ሳይወርድ አስር ዓመት የሞላው ይመስላል፡
ሰውየው ፖሊስ ይመስላል - ነጭ ለባሽ ፖሊስ፡፡

ሄሪ ከአይሮፕላኑ ወጥቶ መሄድ እንደሚችል ያውቃል፤ ማንም ተው
ሊለው አይችልም፤ ከአይሮፕላኑ መውጣት ከዚያም መጥፋት፡፡

ነገር ግን ለጉዞው የከፈለው 90 ፓውንድ አሳዘነው፡ ከዚያም በላይ ሌላ
የጉዞ ተራ ለማግኘት ሳምንታት ሊጠብቅ ይችላል፡፡ በዚያ መሃል ቢያዝስ!?

ሌላ ሃሳብ መጣለት፤ እንግሊዝ አገር እየተሽሎከለከ መኖር፡፡ ወዲያው ይህን ሀሳብ ከአዕምሮው አወጣው፡፡ በጦርነት ወቅት አገር ላገር መንከራተት ደግ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የውጭ አገር ሰላይ ካለ ብሎ ሲያማትር ይውላል፡፡ ከዚያም በላይ ደግሞ የስደተኛ ኑሮ ቀላል አይደለም፡፡ በየቀኑ
የተለያየ ሆቴል ማደር፤ ፖሊስ ሲመጣ መደበቅና ሁልጊዜ መንከራተት፡

ፊት ለፊት የተቀመጠው ሰው ፖሊስ ቢሆንም እሱን ሊፈልግ እንዳልመጣ አውቋል፡ ምክንያቱም ሰውየው ተመቻችቶ ተቀምጦ ጉዞውን
ይጠብቃል፡ ለጊዜው የጎን ውጋት የሆነችበት ማርጋሬት ናት፡፡
👍27👏2