አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ሰልቸት ስላለው ምናልባት ከሚስተር ካርላይል ምንም ነገር ማወጣጣት ባለመቻሉ
ጭምር ይሆናል ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሰው ሠራሽ ጸጉሩን በመስተዋት እያየ አስተካክሎ ሁል ጊዜ ወደሚያመሽበት ወደ በክስ ሔድ አመራ። ባርባራ አቆልቁላ ትመለከተው ስለ ነበር ልክ ከአጥሩ ሥር ሲደርስ ከአንድ ሰው ጋር ተገናኝቶ ሲነጋገር
አየችው " ማን መሆኑን ለመለየት ስትቸገር ከቆየች በኋላ ስዎቹ ቁመው ሲያወጉ አቋቋማቸውን ለወጡ። ልክ በዚህ ጊዜ ስለ ሆሊጆን መገደል በወንድሟ ዋና ምስክር
ሆኖ ቀርቦ የነበረው ሎክስሌይ የተባለ ሰው መሆኑን ዐወቀችው

“ አባባ ምን ሆነ ? አለች ባርባራ'“ሎክስሌይ የሚያስቆጣ ነገር ነግሮታል"
በጣም ተበሳጭቶ እጆቹን እያወናጨፈ ወደ ቤት ተመለሰ ... እማማ ።

ገባና መዝጊያውን ዘግቶ ከክፍሉ መኻል ቁሞ አንድ ጊዜ ወደ ባርባራ አንድ
ጊዜ ወደ ሚስዝ ሔር እያለዋወጠ ይመለከት ጀምር

“እንዴት ያለ ወሬ ነው በዚህ አካባቢ በሹክሹክታ የሚነፍሰው ? ”

ሚስዝ ሔር መናገር አልቻለችም ባርባራም ቀደም ሲል ሲጨቃጨቅ በት የነበረውን ጉዳይ የሚያነሣባት መስሏት አደፈጠች " በዚህ ጊዜ “ ምን ወሬ አለ? ካርላይል "

“የጉልበት ሠራተኛ መስሎ ኋላ ሊሰቀል ወደሚመጣበት ወደዚህ ቦታ ዘልቆ ነበር አሎሳ ? ”

ሚስዝ ሔር ፊቷ ባንዴ ደም መሰለ ። ሚስተር ካርላይል እንደዚያ ሆና በአንዴ
መለዋወጧን ባሏ እንዳያይ ብሎ ተነሣና ከፊቷ ቆመ " ባርባራ እጆቿን አቆላልፋ
ወደ መስኮቱ ዞረች።

“ስለ ማን ነው የሚናገሩት?” አለ ሚስተር ካርላይል ስለ ማን እንደ ተናገረ በደንብ ቢገባውም ለሚስዝ ሔር ሲል ለማዘናጋት በመፈለግ

“ ስለዚያ ከውካዋ ዲቃላ ነው እንጂ ስለ ማን እናገራለሁ ? ”

“ ሪቻርድ ! ” አለች ሚስዝ ሔር ባሏን። “ እባክህን ራራለት " ልጃችን ኮ ነው "

አይደለም እሱ የሔር ልጅ አይደለም እሱ የጭካኔ የመዓት የፍራት እውነተኛ ልጅ ነው ወደ ኢስት ሊን ብቅ ለማለት ከደፈረ የኢንግላንድ ፖሊሶች የትም አድነው እንዲያመጡት በየቦታው አሠማራቸዋለሁ " እኔ በውነቱ ሎክስሌይ አሁን ሲነግረኝ ውሸት ነው ብዬ ልመታው ነበር " እዚህ አካባቢ ስለ መምጣቱ የምታውቂው አለ ? " አላት ሚስቱን "

ሚስዝ ሔር የጥያቄ ዱብ ዕዳ ሲወርድባት ተጨንቃ ሳለ ሚስተር ካርላይል ወደሱ ተጠጋና '“ምነው ጌታ ሚስዝ ሔርን እኮ አስደነገጧቸው መጀመሪያ
ነገሩ ሲነሣ እንኳን ያን ያህል ፊታቸው እንደ ተለዋወጠና በሽታቸውን ሊቀሰቅስባ
ቸው እንደ ጀመረ አይመለከቱም? ግን እስቲ ለመጠየቅ ይፈቀድልኝና ሎክስሌይ ምን ብሎ ነው የነገረዎት ? "

“ እየውልህ ብሎ ጀመረ ።
እኔ ስወጣ እሱ ሲያልፍ ተገናኘንና “ኧረ እንኳን አገኘሁዎ ሪቻርድ በዚህ አካባቢ ታይቷል” እየተባለ ይወራል " ይህ ጉዳይ
ደኅና የተረሳውን እንደገና የፖሊስን ክትትል የሚቀሰቅስ ስለሆነ · እኔ እርስዎን ብሆን ነገሩ ጭራሽ የማይወሳበትን መንገድ እፈልግ ነበር አይለኝም መስለህ! እኔ ደግሞ የመንደሩን ተራ ሐሜት እንደገና እሱ በመድገሙ አናደደኝና እዛው ላጋጨው ካሰብኩ በኋላ መልሸ ትቸው የሰማውን እንዲያብራራልኝ ጠየቅሁት "

“ ሰውየው የዛፊ ዓመት አካባቢ የጉልበት ሠራተኛ መስሎ ዘልቆ ነበር ይላሉ "
አውነት አድርጎት ከሆነ አብዷል ማለት ነው "

“ በርግጥ ዕብደቱ ነው " ነገር ግን እንዲህ ያለውን ነገር አያደርገውም "
ድፍን ዌስት ሊን የፈለገውን ቢያወራ አይቀበሉት እኔ ብሆን አልቀበለውም "
ምስኪኑ ሪቻርድ ደግሞ የትም ይሁን የት "

እኔ ፊት ሲታዘንለት ለመስማት አልፈልግም! “ምስኪን ሪቻርድ?“ሌባው”
ሪቻርድ በለው "

“ ብቻ በአሜሪካ ጫካዎች ይግባ ወይም ካሊፎርኒያ ወርቅ ቁፋሮ ይጀምር
ወይም ኢንግላንድ ውስጥ አገር ላገር ይንከራተት ከተወሰረበት ቦታ ወጥቶ ዌስት ሊንን ይረግጣል ተብሎ አይታሰብም " እኔስ እርስዎን ብሆን ሎክስሌይን በንግግሩ እሥቅበት ነበር "

ታዲያ ዌስት ሊን ለምን እንደዚህ ያለውን ውሸት ይፈጥራል ? ”

“ ይኸ አስቸጋሪ ነው። ዌስት ሊን ደግሞ ይህን ገንዘብ ቢከፍለው እንኳን ለምን
እንደዚህ ብሎ እንደሚያወራ ሊነግረዎ አይችልም ግን መሠረት የሌለው ነው " ካዩት ለምን ያምናውን
ያወራሉ? አምና ያዩትን ለምን አስከ ዛሬ አልተናገሩም ? ለምን ዛሬ ወይም ትናንት አየነው አይሉም እኔ ብሆን እንደዚህ ያለ ወሬ ብሰማ ከቁም ነገር አልቆጥረውም " ንቄው ዝም እላለሁ "

ሚስተር ጃስቲስ ሔር እንኳን ንቆ ዝም ከማለት ይልቅ ሰምቶ መደንፋት ነበር
የሚቀናው ነገር ግን፡ሚስተር ካርላይልን በጣም ያከብረው ስለ ነበር በሱ አባባል መስማማቱን ለመግለጽ አጕረመረመና ወደሚያመሽበት ለመሔድ እንደገና ወጣ

“ አርኪባልድ!” አለች ሚስዝ ሔር ባሏ ራቅ ብሎ ከሔደ በኋላ “ዛሬ እዚህ በመገኘትህ ከጉድ አወጣኸኝ " እውነቱን ተናግሬ ዐርፈው ነበር

ግን ሎክስሌይ ለምን ተናገረ ? ” አለች ባርባራ ከቆመችበት መስኰት ፊቷን
መልሳ "

ሎክስሌይ መቸም የሪቻርድ ጠላት አይደለም " ስለዚህ ሚስተር ሔር የሰሙ
እንደሆነ አሉባልታውን ያስቆሙታል መስሎት በቅንነት ተነሥቶ ይመስለኛል ወሬውን ኮ እኔም ሰምቸዋለሁ " "

“ እንዴት ሊታወቅ ቻለ ? '
“ እኔም ገርሞኛል " ትናንት ቶም ሔርበትርን አገኘሁትና ሪቻርድ ሔር ገበሬ መስሎ ዌስት ሊን ላይ ስለ መታየቱ መወራቱን ነገረኝ ስሰማ ሣቅሁ እሱም ቢሆን ይህን ወሬ ብሎ እንዳያወራ ሊሆን እንደማይችል እንዲንቀው እደረግሁት " ወሬው እሱ እዚህ በነበረበት ጊዜ ቢሆን ኖሮ እንኳን ዴስ አይልም ነበር " አሁን ግን ሁለት
ዓመት ሊያልፈው ነው " ስለዚህ ምንም የሚያሠጋ ነገር የለም " አለ ሚስተር ካርላይል።

ሚስዝ ሔር በረጅሙ ተነፈሰችና †ነሥታ ወዶ መኝታ ቤቷ ስትሔድ ካርላይልና ባርባራ ቀሩ "

“ አዬ ምነው እውነተኛዉ ወንጀለኛ ቢገኝ በዚህ ዐይነት እማማ ከጥቂት
ጊዜ በኋላ ሰው አትሆንም!"

“ትክከለኛው ሰው ቢገኝ የኔም ምኞቴ ነበር ! ነገር ግን ያለው ተስፋ በጣም
ሩቅ ነው ” አላት ' ሚስተር ካርይል "

ባርባራ ተቀምጣ ነገር ታሰላስል ጀመር ለሚስተር ካርይል ልትገልጽት የፈለገችው ነገር አላት " ነገር ግን እንዳትናገር ያገዳት ምክንያት ያላት ትመስላለች በመጨረሻ ድምጿን ዝቅ አድርጋ ፍራት ፍራት ያላት ተነፈሰችው "

“ያን ጊዜ ሪቻርድ ቶርንን አገኘሁት ሲለን ሰውየው ምን እንደሚመስል ?
የሰጠን ምልክት ትዝ ይልሃል ? ”

"አዎን ”

“ ታዲያ በዚያ ገለፃ ማንን እንደሚመስል ያሰብከው ነገር የለም ? ''

የሱ አባባልማ ከቶርን ጋር ይስማማል "

“ሪቻርድ ሰውዬው ጸጉሩን ወደ ኋላው ሲመልስ ስለሚያደርገው ልዩ
እንቅስቃሴ ሁሉ ነግሮን ነበር " ታዲያ ያንን እንቅስቃሌ ከነጭ እጀና ከአልማዝ ቀለበት ጋር አገናዝበህ በሌላ ሰው አላየኸውም ? ”

“ ጸጉራቸውን ወደኋላ የመመለስ ልማድ ያላቸው ብዙ ናቸው " እኔም አንዳንድ ጊዜ አደርጋለሁ " ምነው ጠየቅሽኝ ?የምትጠራጠሪው ሰው አለ ? ”

“ አንተ የጠረጠርከው የለህም ወይ ? ”

“ እኔ የምጠረጥረው የለኝም " ካፒቴን ቶርን እሱ ያለመሆኑን ካወቅን ወዲህ
ማንንም ጠርጥሬ አላውቅም ” አላት "
👍12
ባርባራ ይሀን ስትሰማ አፋን ይዛ ዝም አለች " እሷ ግን የጠረጠረችው ነበራት"
አንዳንድ ግልጽ ያልሆኑ ጥርጣሬዎች በሐሳቧ እየመጡ ራሷንም በጣም ያስገርማታል ታድያ ለእሷ የታይዋት ነገሮች ለሚስተር ካርላይልም በሐሳቡ ሳይመጡበት አይቀሩም የሚል ግምት ነበራት " አሁን ግን ምንም እንዳልመጡለት ተረዳች " ሪቻርድ ሔር ቶርንን አየሁት ብሎ በተናገረ ጊዜ ሌሊቱን በሚስተር ካርላይል ትዳር ላይ አስዶንጋጭ አደጋ ደረሰ " ይህ ድንገተኛ ነገር ባርባራ ስለ ተሰማት ጥርጣሪ ከሚስስተር ካርላይል ጋር እንድትነጋገርበት ምክንያት ሆኖ አገዳት " ከዚያ ወዲህም አንሥታበት አታውቅም " ሪቻርድም ወሬው ጠፋ " የሱ ጉዳይም ቀዘቀዘ "

እኔስ የወንጀለኛው መገኘት ተስፋ እያስቆረጠኝ ሔዷል" አሁን የሪቻርድ ነገር መጨረሻው ምንድነው ?”

ቶርን ተፈላጊው ቶርን ያለመሆኑን ካወቅን ወዲህ እኮ ፍንጬ ጠፋን " ፍለጋችን ቆመ ”

ሪቻርድ የሱን “ቶርን ባያየው ኖሮ እንዳልከው በዚህ ይቆም ነበር "

“ የሪቻርድ አእምሮ በቶርን ሐሳብና ምስል የተያዘ ስለሆነ ' ማንም መንገደኛ
እሱ መስሎ ሊታየው ይችላል ።

“ ይኸ እንኳን በጭራሽ ሊሆን አይችልም " እኔ ምንም አልጠራጠርም
አንተም ራስህን ያን ጊዜ አምነኸው ነበር።

አዎን ቅን አነጋሩ አሳመነኝ " በነገሩ ለማሰብ ጊዜ አጣሁ " ከሪቻርድ አገላለጽ ጋር የሚስማማ ሰው ደግሞ ከካፒቴን ቶርን በቀር ዌስት ሊን ውስጥ ማንም
አልነበረም " ስለዚህ ጊዜ እስኪገልጠው ድረስ ከመጠበቅ በቀር ሌላ ምንም ማድረግ አንችልም "

“ ግን መጠበቁ እኮ ያስጨንቃል መጠበቅ

“ ከአባትሽ ጋር የሚያጣላሽ ምንድነው ? '' አላት ፈታ ብሎ ። ፊቷ ፍም መሰለ “ እሷም ፈግግ ብላ አየችውና ዝም አለች "

“ አባትሽ ያነሡት “ሻለቃ ቶርን” ያ እኛ የምናውቀው መሰለኝ?” ሲላት ራሷን
በአዎንታ ነቀነቀች "

እሱ ከሆነ የደስ ደስ ያለው ብዙ ሴቶች ባላቸው ቢሆን የሚኮሩበት ሰው ነው።

“ አዎን ደስ የሚል ሰው ነው ” ብላ ንግግር ዘጋች "

ካፒቴን ቶርን አንድ ቀን ሔርበርት ቤት እንግድነት በሔደበት ነበር ባርባራን
ገና ሲያያት ልቡ የደነገጠላት " ያን ጊዜ ሁኔታዎች ቢመቻቹለት ኖሮ ለጋብቻ ይጠይቃት ነበር አሁን በቅርቡ ሀብት ከመውረሱም በላይ በሙያውም አንድ ደረጃ
ከፍ ብሏል ስለዚህ እሷንና አባቷን በደብዳቤ ቢጠይቅ ወዲያው አይሆንም አለ
ችው » አባቷ ደግሞ ለጊዜው እሷ እንዳትሰማ ብሎ ደብቆ ይዞት ነበር ።

“ይኸን ስለ ሪቻርድ የሚነፍሰውን ወሬ ለማስቆም የምትችለውን ሁሉ ታደርጋለህ አይደለም ?

“ አታስቢ " የሪቻርድ ስም ዌስት ሊን ላይ ባይነሣ የተሻለ ነው ግን አሁንም
እንዴት ሊወራ እንደቻለ እየገረመኝ ነው ”

ከዚያም ሁለቱም ዝም ብለው ከቆዩ በኋላ ' “ ሌላው ወሬስ” አለችው ወደሚስተር ካርላይል ሳታይ ' “ እውነት ነው ? ”

“ የምን ሌላ ወሬ? ”
ሉዊዝ ዶቢድን ልታገባ ነው መባሉ ? ”
አይደለም " እኔ ማንንም ለማግባት ሐሳብ የለኝም " እንዳለሁ እቆያለሁ "
ባርባራ በመግረም ቀና ብላ ተመለከተችው "

“ ምነው ገረመሽ ... ባርባራ ? አየሽ ያቺ ሚስቴ የነበረችው እኮ በሕይወት
አለች " ”

እና ምናለበት ?”

ለጊዜው ዝም ብሎ ቆየና ባርባራ አጠገብ ቆሞ ቁልቁል ወዶ እሷ እያየ ዝግ ባለ ድምፅ “ ማንም ሰው ሚስቱን ሰዶ ሌላይቱን ካገባ አመነዘረ ” አላትና መልስ
ለመስጠት ከመቻሏ በፊት
ምናልባት የምትሰጠው መልስ ቢኖራት ወይም
ከድንጋጤዋ ከመመለሷ በፊት ባርኔጣውን አንሥቶ ሔደ ....

💫ይቀጥላል💫
👍13🥰51👏1
#ጠላፊዎቹ የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ በተለመደው ሰአት በቅርቡ እጀምራለው እንደተለመደው በመከታተልና አስተያየት በመስጠት አብራችሁኝ ሁኑ።
👍57
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


ጦርነቱ የፈነዳው በአንዱ ፀሐያማ እሁድ ቀን ነበር፡
አይሮፕላኑ እስካሁን ከተሰሩት ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ጦርነቱ የታወጀ ቀን ስድስት ሰዓት ከሰላሳ ላይ አይሮፕላኑ ብቅ ይል ይሆን እያለ ቶም ሉተር ልቡ ተሰቅሎ ወደ ሰማይ አንጋጦ እየጠበቀ ነው።

ቶም ወሬ ለማየት ባሰፈሰፉ ሰዎች ተከቧል፡ የፓን አሜሪካን ኩባንያ ንብረት የሆነው ባህር ላይ ማረፍና መነሳት የሚችለው አይሮፕላን ሳውዝ ሃምፕተን ወደብ ላይ ሲያርፍ ይህ ዘጠነኛው ጊዜ ቢሆንም አሁንም ማራኪነቱ አልደበዘዘም፡፡ ይህ አይሮፕላን አስደናቂ በመሆኑ አገሪቱ ጦርነት
ባወጀችበት ቀን እንኳን ሰዎች እሱን ለማየት ወደሚያርፍበት ቦታ
እየተንጋጉ ነው፡፡ በዚሁ ወደብ ዳርቻ አንዳች የሚያካክሉ ሁለት መርከቦች መልህቃቸውን ጥለው ቢቆሙም እነሱን ነገሬ ያለ የለም፡፡

ታዲያ አይሮፕላኑን እየጠበቁም ቢሆን ሰዎች የሚያወሩት ስለጦርነቱ
ነው ወንዶቹ ስለታንክና መድፎች ሲያወሩ ሴቶቹ በአርምሞ ይመለከታሉ፤
ከፍቷቸዋል። ሉተር አሜሪካዊ እንደመሆኑ ፍላጎቱ ሀገሩ በጦርነቱ እጇን እንዳታስገባ ነው፡፡ ጦርነቱ የእሷ ጉዳይ አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ ናዚዎች በኮሚኒስቶች መጨከናቸው ተገቢ ነው፡፡

ሉተር በንግድ ሥራ የሚተዳደር ሲሆን የልብስ ስፌት ፋብሪው ውስጥ የሚሰሩት ኮሚኒስቶች አንድ ወቅት ላይ ችግር ፈጥረውበት ሊያጠፉት ሁሉ ምንም አልቀራቸውም ነበር፡፡ ትዝ ሲለው በንዴት
ይንቀጠቀጣል፡፡ የአባቱ የልብስ መሸጫ መደብር በይሁዳውያን ተቀናቃኞች
አፈር ድሜ ሊበላ ነበር፡፡ ሉተር ሬይ ፓትሪያርካን በጡት አባትነት ሲይዝ
ግን ህይወቱ ባንድ ጊዜ ተለወጠ የፓትሪያርካ ሰዎች እዚህም እዚያም
አደጋ በመፍጠር ኮሚኒስቶችን ልክ ማስገባት ያውቃሉ አንዱ ከውካዋ
ኮሚኒስት እጁ በማዳወሪያ ማሽን ውስጥ ተወትፎ እንዲቀር ተደረገ፡፡ የሰራተኛ ማህበር ቀስቃሽ አባል በመኪና ተገጭቶ ህይወቱ አለፈ፡ በፋብሪካ ውስጥ ስላለው የደህንነት ደምብ መጣስ ቅሬታ ያቀረቡ ሁለት ሰዎች ቡና ቤት ውስጥ በተፈጠረ ጠብ ቆስለው የአልጋ ቁራኛ ሆኑ፡ አንዷ ችግር ፈጣሪ ቤቷ በእሳት እንዲጋይ በመደረጉ በኩባንያው ላይ ያቀረበችውን ክስ ለማንሳት
ተገደደች፡፡ ከዚህ በኋላ ሰላም ሰፈነ፡፡ ፓትሪያርካ ሂትለር የሚያውቀውን
ያውቃል፡፡ ኮሚኒስቶችን ልክ ለማስገባት እንደ በረሮ መንጋ መደምሰስ ነው::

ሉተር ይህን እያሰላሰለ እግሩን ወለሉ ላይ ይጠበጥባል፡፡ አንዲት ጀልባ
አይሮፕላኑ የሚያርፍበት የባህር ክፍል አካባቢ ለማረፍ ችግር የሚፈጥርበት
አንዳች የተንሳፈፈ ነገር እንዳለ ለማየት ወደ ቦታው በረረች፡፡ የተሰበሰበው
ሰው ይህን ሲያይ በጉጉት አጉተመተመ አይሮፕላኑ እየመጣ ነው ማለት
ነው፡፡

አይሮፕላኑን ቀድሞ ያየው አንድ ትንሽ ልጅ ነው፡፡ አጉልቶ የሚያሳይ
መነጽር ባይዝም ‹‹ያውላችሁ!›› ሲል ጮኸ፡፡ ‹‹ባህር ላይ የሚያርፈው
አይሮፕላን መጣ!›› በማለት ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሲያመለክት ሁሉም
ዓይኑን ወደዚያው ወረወረ፡፡ ሉተር በመጀመሪያ አሞራ የመሰለ ነገር ደብዘዝ
ብሎ ታየው፡፡ በኋላ እየጎላ መጣ ‹‹ልጁ እውነቱን ነው! እውነቱን ነው!››በማለት የተሰበሰበው ህዝብ አውካካ፡፡

ፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰዎችን በምቾት አሳፍሮ አትላንቲክ ውቅያኖስን ማቋረጥ የሚችል ቦይንግ B 134 የተሰኘ አይሮፕላን በቦይንግ ኩባንያ አሰርቷል፤ ግዙፍ፣ ማራኪና ጉልበቱ ከፍተኛ የሆነ የአየር ላይ ቤተ መንግስት፡፡ አየር መንገዱ ስድስት አይሮፕላኖችን ያስመጣ ሲሆን ሌሎች ስድስት ደግሞ እንዲሰሩለት አዟል። በምቾትና በማራኪነት በወደቡ ላይ ከቆሙት የመንገደኛ መርከቦቹ አይተናነሱም፡፡ ነገር ግን መርከቦቹ አትላንቲክን ለማቋረጥ አራት ወይም አምስት ቀን ሲወስድባቸው ይህ ባህር ላይ ማረፍና ከባህር ላይ መነሳት የሚችል አይሮፕላን ግን ይህን ጉዞ በሃያ አራት ወይም በሰላሳ ሰዓት ያጠናቅቀዋል፡፡

ልክ ክንፍ ያለው ዓሳ ነባሪ ይመስላል› አለ ሉተር በሆዱ አይሮፕላኑ እየቀረበ ሲመጣ፡፡ ከወደ ፊቱ ሾል ያለ ግዙፍ ነው፡፡ ክንፎቹ ውስጥ ኃይለኛ
ሞተሮች ተሰክተዋል፡ አይሮፕላኑ ውሃ ላይ ሲያርፍ ሚዛኑን እንዲጠብቅ
የሚያስችሉት ከክንፎቹ በታች አጠር ወፈር ያሉ ትናንሽ ክንፎች
ተገጥመውለታል፡፡ የአይሮፕላኑ የታችኛው ክፍል እንደ ፈጣን ጀልባ
ውሃውን መሰንጠቅ እንዲያስችለው ጫፉ እንደ ቢላ የሰላ ነው፡፡

አይሮፕላኑ ፎቅና ምድር አለው፡ ሉተር ባለፈው ሳምንት ስለመጣበት
የአይሮፕላኑን ውስጣዊና ውጫዊ ገጽታ በሚገባ ያውቀዋል፡ የላይኛው ፎቅ
ፓይለቶቹንና የዕቃ ማስቀመጫ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን የታችኛው ክፍል
ተሳፋሪዎች የሚቀመጡበት ነው፡፡ ተሳፋሪዎች የሚቀመጡባቸው ክፍሎች
በመደዳ በተደረደሩ የእንግዳ ማረፊያ ሶፋዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ በመብል ጊዜ እነዚህ ክፍሎች ወደ መብል ቤትነት የሚለወጡ ሲሆን በመኝታ ጊዜ ደግሞ
ሶፋዎቹ እንደ አልጋ ይዘረጋሉ፡

ተሳፋሪዎቹን ከሙቀትና ከብርድ ለመጠበቅ አይሮፕላኑ ውስጡ
ተለብጧል፡ ወለሉ ወፋፍራም ምንጣፍ የተነጠፈበት ሲሆን ክፍሉ ዓይን የማይወጉ መብራቶች ተገጥመውለታል፡፡ በሃር ጨርቅ የተሸፈኑ ሶፋዎቹ
ድሎታቸው ልክ የለውም፡ የአይሮፕላኑ ግድግዳ ላይ የተገጠመው ድምጽ
ማፈኛ የሞተሮቹን ድምጽ ይውጣል፡ የአይሮፕላኑ ካፒቴን የአዛዥነት ባህሪ
የተላበሰ ሲሆን ባልደረቦቹ ደግሞ ጸዳ ያለና ማራኪ የፓን አሜሪካን አየር
መንገድ ዩኒፎርም ለብሰዋል፡፡ አስተናጋጆቹ የተሳፋሪዎቹን ፍላጎት ለማርካት ተፍ ተፍ ይላሉ፡ ምግብና መጠጥ ያለማቋረጥ ይጋዛል፡፡ ተሳፋሪዎች የጠየቁት ነገር በሙሉ ልክ በአስማት የሚመጣ እንደሆነ ሁሉ እፊታቸው ዱብ ይላል፡ እንዲህ አይነት ድሎት በቀላል ዋጋ አይገኝም፡ ተሳፋሪዎቹ አብዛኛውን ጊዜ የንጉሣውያን ቤተሰቦች፣ የፊልም ተዋናዮች፣ የትላልቅ ኮርፖሬሽኖች ኃላፊዎች እና የአገር መሪዎች ናቸው፡፡ ቶም ሉተር ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች ጋር የሚመደብ አይደለም፡ ሀብታም ቢሆንም እዚህ ደረጃ ለመድረስ ብዙ የለፋ በመሆኑ ለድሎት ሲል ብቻ ገንዘቡን አይረጭም: ቢሆንም ራሱን ከአይሮፕላኑ ጋራ ለማለማመድ ፈልጓል፡፡
አንድ ኃያል ሰው በጣም ኃያል የሆነ አንድ አደገኛ ተግባር እንዲፈጽምለት
ውለታ ጠይቆታል፤ ለዚህ ስራው ሉተር የሚከፈለው ነገር የለም፡ ነገር ግን
ለዚህ ሰው ውለታ መዋል ከገንዘብ ይልቃል፡

ይሄ ዕቅድ ምናልባት ይሰረዝ ይሆናል፡ ሉተር ‹‹ስራውን ቀጥል››
የሚለውን የመጨረሻውን ትዕዛዝ እየጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን አዕምሮው
ዕቅዱን ቶሎ ለመፈጸም በመጓጓትና ምነው ባልሰራሁት! ብሎ በመመኘት መካከል ይዋልልበታል፡

አይሮፕላኑ ከአፍንጫው ከፍ ከጭራው ዝቅ እያለ ወደ መሬት እየወረደ
ነው፡፡ አሁን ለማረፍ ተቃርቧል፡ ሉተር በአይሮፕላኑ እንደአዲስ ተደንቋል፡፡

ለአፍታ ያህል አይሮፕላኑ እየተንሳፈፈ ይሆን እየወደቀ ሳይለይ አንዳንዴ ደግሞ ወደ ላይ ከፍ እያለ በመጨረሻም ባህር ላይ እንደተወረወረ ዝይ እዚህም እዚያም እየነጠረና ውሃውን ሁለት ቦታ እየከፈለ ፍጥነቱን በመቀነስ ውሃው ላይ አረፈና እንደ ጀልባ ይሄድ ጀመር፡

ሉተር ትንፋሹን ውጦ ቆይቶ ስለነበር በእፎይታ ለቀቀው፡ አይሮፕላኑ ወደ መቆሚያው ተጠግቶ ቆመ፡ ሉተር ከሳምንት በፊት እዚህ ቦታ ላይ ነው ከአይሮፕላኑ የወረደው:፡ ከአፍታ በኋላ አይሮፕላኑ ከፊትና ከኋላ
በገመድ ከወደቡ ምሰሶ ጋር ይታሰራል፡
👍593👎1🔥1
ሉተር ፊቱን አዙሮ መንገድ ጀመረና ድንገት ቆም አለ፡፡ ከኋላው ከዚህ በፊት የማያውቀው ሰው ተገትሯል ሰውየው ቁመቱ ከሱ አይበልጥም፡፡ጠቆር ያለ ሱፍ ልብስ ለብሷል፤ ባርኔጣ አናቱ ላይ ደፍቷል፡፡ የቢሮ ሰራተኛ ነው የሚመስለው፡፡ ሉተር አልፎ ሊሄድ አለና እንደገና ሰውየውን መልከት
አደረገው ከባርኔጣው በታች የሚታየው ፊት የቢሮ ሰራተኛ ፊት አይመስልም፡፡ ሰውየው አርባዎቹ ግድም ሲሆን ግምባሩ የፈጠጠ፣ ዓይኖቹ ሰማያዊ፣ አገጩ ደግሞ የሾለ ነው: የጨካኝ ሰው የሚመስል ከንፈር አለው፡፡ ሲያዩት አደገኛ ሰው ይመስላል፡፡ ሉተር ላይም
አፍጥጦ ‹‹ሄንሪ ፋበር እባላለሁ›› አለው፡፡

‹‹ቶም ሉተር››

‹‹ለአንተ የተላከ መልዕክት ይዣለሁ››

የሉተር ልብ ደለቀ ‹‹ጥሩ ቀጥል›› አለ

‹‹አንተ የምትፈልገው ሰው ረቡዕ ዕለት ይመጣና በዚሁ አይሮፕላን ወደ ኒውዮርክ ይበራል››

‹‹እርግጠኛ ነህ?›› ሲል ጠየቀ ሉተር

ሰውየው ሉተርን ገላመጠው እንጂ ለጥያቄው መልስ አልሰጠውም::ሉተር በመረዳት ራሱን እየነቀነቀ ስራው ቀጥሏል ማለት ነው፣ ብሎ አሰበና
‹‹አመሰግናለሁ›› አለ

‹‹ሌላም ነገር አለ›› አለ ሰውየው።

‹‹እያዳመጥኩ ነው››

‹‹ሁለተኛው መልዕክት…... አደራ ይህን ሳትፈጽም እንዳትመጣ ተብለሃል›› አለ ሰውየው

‹‹ሃሳብ አይግባችሁ በላቸው›› አለ ሉተር በረጅሙ ተነፈሰና ‹‹ሰውያችን ከሳውዝ ሃምፕተን ወደብ ሊነሳ ይችላል፣ ግን በፍፁም ኒውዮርክን አይረግጣትም!›› አለ በከፍተኛ ራስ መተማመን፡፡

ኢምፔሪያል አየር መንገድ በሳውዝ ሃምፕተን ወደብ የአየር ጉዞ አገልግሎት መስጫ ተቋም አለው፡፡ የአየር መንገዱ መካኒኮች አይሮፕላኑን በፓን አሜሪካን አየር መንገድ የበረራ መሃንዲሶች ተቆጣጣሪነት ሰርቪስ ያደርጋሉ፡፡ የፓን አሜሪካን የዚህ በረራ የበረራ መሃንዲስ ምድብተኛ ኤዲ ዲኪን ነው፡፡

ስራው ከባድ ነው፡፡ ያላቸው ሶስት ቀን ብቻ ነው፡፡ የአትላንቲክ አቋራጭ በረራ በአይሮፕላኑ ሞተሮች ላይ የሚያደርሰው ጫና በቀላል
የሚታይ አይደለም፡፡ ከኒውፋውንድ ላንድ (ካናዳ) እስከ አየርላንድ አይሮፕላኖቹ ሳያቋርጡ ለ9፡00 ሰዓት በረራ ያደርጋሉ፡፡ በምላሹ ጉዞ
አይሮፕላኑ ከንፋሱ በተቃራኒ ስለሚጓዝ 16፡00 ሰዓት ይወስድበታል፡፡

ረቡዕ ጧት አይሮፕላኑ ለመልስ ጉዞ ዝግጁ ይሆናል፡፡.....

ይቀጥላል
👍30
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

አንዳፍታ ወደ ሳቤላ እንመለስ ዓመቱ እየተዋግደ ሲሔድ እሷም እየበረታች
እየተሻላት መጣች የበጋው መገባደጃ ሲቃረብ ግረኖብልን ለመልቀቅ ተዘጋጀች መኖሪያዋን የት እንደምታደርግ ወይም ምን እንደምትሠራ ግን አላወቀችም ከሥቃይዋ ብርታት ከኀዘኗ ብዛት ከጸጸቷ ጥናት የተነሣ በራሷ ላይ ሊደርስባት ስለሚችል ነገር ማሰቡን ትተዋለች የመጣው ቢመጣባት ግድ አልበራትም እንደምኟቷማ እጅግ ከራቀው የዓለም ዳርቻ የሠለጠነ ሰው ያልረገጠው ትንሽ ሥፍራ
ብታገኝ ትወድ ነበር ። ግን እንደዚህ ያለ ቦታ እንዴት ታግኘው ?

ሱዛን ግሮኖብል ውስጥ ፍቅረኛ አበጀችና ከዚያ ለመልቀቅ አልፈለገችም
ስለዚህ ሳቤላ በሷ ምትክ አንዲት ልጅ እግር ገጠሬ በሞግዚትነት ቀጥራ ልጅዋን ይዛ የሚስማማትን ፍለጋ ተነሣች በግድ ከሚያስፈልጓት ነገሮች በቀር የነበራትን ዕቃ በሙሉ እሷ ሌላ ትእዛዝ እስክትሰጥ ድረስ ከመጋዘን እንዲቀመጥ አስቀድማ
ወደ ፓሪስ ልካዋለች ከግረኖብል ስትወጣ ቀኑ በጣም ደስ የሚል ነበር ።
መምሸት ጀምሮ ለዐይን እስኪይዝ ድረስ ሳቤላ አንድ ሁለት ቀን ልታድርበት አስባው ከነበረው ካመር ከተባለው ቦታ እስኪጠጋ ድረስ ባቡሩ በደኅና ተጓዘ የፈረንሳይ የባቡር አደጋዎች የእንግሊዝ አገርን ያህል አይበዙም እንጂ ኑረው ኑረው ሲደርሱ ግን የሚያስከትሉት ጉዳት ለጆሮ የሚቀፍ ነው። ትዝታው እስከ ዕድሜ ልክ ከአእምሮ አይጠፋም ። ባቡሩ ከጣቢያው ሊደርስ ጥቂት ሲቀረው የምጽአት ቀን የመሰለ ድንገተኛ ግጭትና ነወጥ ደረስ የባቡሩ ሠረገላዎችና መንገደኞች አንድነት ተደባልቀው ከአንድ ትልቅ ግድብ ሥር ወደቁ።

እየከበደ የመጣ ጨለማ አሠቃቂውን ሽብርና ድብልቅልቅ አባባሰው ። ሳቤላ ከልጅዋና ከሠራተኛዋ ጋር የተሳፈሩበት የባቡር ሠረገላ በብዙ ናዳና ስብርባሪ ሥር ወደቀ " ሦስቱም በብዙ ድካም ከተዳፈኑበት ተፈልገው በመጨረሻም ከወጡት መንገደኞች ውስጥ ነበሩ ምስኪኑ ሕፃንና ሞግዚቱ ሙተው ተገኙ ሳቤላ ግን አልሞተችም እንዲያውም በደንብ ነፍሷን ታውቅ ነበር ባስቸኳይ ተጠርተው የመጡ የሕክምና ሰዎች ካዬዋት በኋላ እሷ እግሯን ብትቆረጥ እንኳን እንደማትርፍ ሌላ ሕክምናም ሊደረግላት እንደ
ማይችል ቀዶ ጥገና ደደደ ዳ መሞቷ ዴ ዳዳደ
ሰማቻቸው ከሷ የተሻለ ተስፋ የነበራቸው ሥቃይተኞችን ለመርዳት ጥለዋት ሲሔዱ አየቻቸው ጉዳቷ ከፊቷ የታችኛው ክፍልና አንድ እግሯ ላይ ነበር ከደረሰባት የኑሮ ሥቃይ ለመላቀቅ ብዙ ጊዜ ሞትን ተመኝታለች።ነገር ግን እንደዚህ የመሰለ አስጨናቂ ሥቃይ አስከትሎ ይመጣል ብላ አላሰበችውም መንቀሳቀስ አትችልም የደረሰባት ከባድ ነውጥ ስሜቷን አደንዝዞታል ሕመም ገና አልተሰማትም ከሁሉ የሚያስደንቀው ግን አእምሮዋ ዝንፍ አላለም ላጭር ጊዜ አስተካክላ ማዳመጥና መመለስ ትችል ነበር አንዲት የበጎ አድራጎት ገዳም አባል የሆነች መነኰሲት ሳቤላ ወደተኛችበት የቁስለኛ ማንሻ አልጋ ተጠግታ ውሃ
ሰጠቻት ሳቤላ ተቀብላ ልክክ አድርጋ ጠጣችው

“ ሌላ የማደርግልሽ ነገር የለም ? ” አለች መነኩሴይቱ

ሕፃኑ ልጄና ሞግዚቱ አብረውኝ ተሳፍረው ነበር ። ተገኝተው እንደ ሆነ ልጄም ሞቶ እንደሆነ ንግሪኝ
መነኩሲይቱም በዚያ ሁሉ ግርግርና ጩኽት መኻል ፍለጋ ሔደች። የአንድ ሕፃን አስከሬን ሳቤላ ከነበረችበት ብዙም ሳይርቅ ከባቡር ጣቢያው መጠለያ አኑረውት አገኘች ቀስ አድርጋ አንሥታ ወሰደችውና “ልጅሽ ይኸ ነው ? አለቻት።

ያ ያልታደለው የሳቤላ ልጅ ነበር ። ትንሿን ፊቱን ከደረቷ እቅፍ አደረችና በመጀመሪያ ወደፊት ከሚጠበቀው አሰቃቂ ኑሮ አስቀድሞ በመላቀቄ ከልቧ አመሰገነች እሷም ከጥቂት ሰዓቶች በኋላ እንደምከተለው ታወቃት ስለዚህ ሞት ሲመጣ ብዙ ጊዜ
እንደሚከሰተው ሁሉ ከዚህ ዓለም ሕይወት ጋር የተያያዘውን ጥሪት ቸል የሚላት ስሜት ቀስ በቀስ ተዳደራት “ድሮውንም ልመኝለት የሚገባኝ እንዲህ ሆኖ እንዲገላገል ነበር ” ብላ እንድታነሣው ምልክት ሰጠቻት "

ያቺ ደግ መነኩሲት ሐኪሞች ስለ ቁስለኛይቱ የተናገሩትን ሰምታ ስለ ነበር
“ምናልባት ለዘመድ ወዳጆችሽ የምታስተላልፊው መልእክት ቢኖርሽና የምታምኚኝ ከሆነ ፍላጐትሽን እፈጽማለሁ ከኋላ ለሚቀሩ ሰዎችሽ የምትተይላቸው መልክት
ካለሽ አሁን አእምሮሽ እንደ ተስተካከለ አንደበትሽ ሰልቶ ሳለ ብትነግሪኝ ጥሩ ነው ' አለቻት ።

“ እኔን የሚያውቁ ሁሉ መሞቴን ሲሰሙ ደስ ይላቸዋል " ከኀዘንና ከኃፍረት ለከተትኩዋቸው ዘመዶቼ የምሰጣቸው ካሳ ሞቴን ብቻ ነው " እኔ ከባድ በደለኛ ነበርኩ ”

“ሞትን እንደ በደል ዋጋ አድርገሽ ለመቀበል ሞክሪ መከራዎቻችንም እንደ ደስታዎቻችን ተሰጥዋችን ናቸውና።

“እሺ እርስዎ እንደሚሉኝ አደርጋለሁ ” አለች ሳቤላ ሕመሙ ሊሰማት ስለ
ጀመረ ድምጿ ድክምክም እያለ

"ንገሪኝ ለምትፈልጊው ልጻፍልሽ"

ወረቀቱን ከያዙልኝ ሐሳቤም ግልጽ እጆቼም ደህና ስለሆኑ እኔ ልሞክረው
እችላለሁ ስትላት መነኩሲቱ እንዳለቻት አመቻችታ ያዘችላት " መጀመሪያ አድራሻውን ለሎርድ ማውንት እስቨርን በማድረግ እንደ ተጋደመች ጥቂት ቃላት መሞነጫጨር ጀመረች በባቡር አደጋ ምክንያት በደረሰባት ከባድ ጉዳት ከሞት አፋፍ መሆንዋን ልጂዋና ሞግዚቷ መሞታቸውን ጻፈች ሎርድ ማውንት እስቨርን ለዋለላት በጐ ተግባር ሁሉ አመሰግና ለሱና ለሌሎችም ወገኖች ሁሉ ማፈሪያ ከምትሆንባቸው ሙታ ማረፉን እንደምትወድ ገለጸችለት "

ሚስተር ካርላይል ዘንድ ሒድና ብላ በመቀጠል “ ይቅር እንዲለኝ በትሕትና መለመኔን ንገረው እንደዚሁም ልጆቼ አድገው ምን ያህል እንደ በደል
ኳቸው ሲያውቁ እንዳይረግሙኝ ይቅርታቸውን መለመኔን ንገረው በራሴ ማዘኔን እርር ድብን ብዬ ስሜቴን የምገልጽበት ቋንቋ እስኪያጥረኝ ድረስ መጸጸቴን ንገረው ብላ ከጻፈች በኋላ የሕመሙ ሥቃይ ጀመራትና እያባሰባት ሔደ እንደ ምንም ብላ ተጠናክራ“ ሳቤላን ይቅር በልዋት ብላ ሞጭራ ስታበቃ “ይበሉ
እንግዲህ ከሞትኩ በኋላ በፊት አይደለም ጥቂት የማረጋገጫ ቃላት ጨምረው ይላኩት ”
አለቻት

ኋላ ቆይተው ሳቤላ የደረሰባትን ጉዳት ምንና ምን ያህል እንደሆነ በዝርዝር ለመመርመር የቀዶ ጥግና ሐኪሞች በመጨረሻ ሲመጡ ፈጽማ ነፍሷን ስታ አገኟት ስለዚህም መሞቷን አምነው ይኽንኑ ከጐኗ ተንበርክካ ከሥጋዋ ለምትለየው ነፍስ
ስትጸልይላት ለነበረችው መነኰሲት ነገርዋት ጸሎቷን ጨርሳ እርዳታዋን ወደ ሚያስፈልጋቸው ወደ ሌሎች ቁስለኞች ሔደች "
ከዚያ በኋላም ሞታለች ብላ
ወደ ሳቤላ አልተመለሰችም " ደብዳቤውንም እንደ ነገረቻት የማረጋገጫ ቃላት ጨምራ ላከችው። የሞቱት ተቀበሩ ከሞት የተረፉት ቁስለኞች ወደ ሆስፒታል ተላኩ

ሳቤላ ቀስ በቀስ ነፍሷን አወቀች ከአንድ ሆስፒታል መደዳ ክፍል ከአንድ
አልጋ ብጤ ርብራብ ላይ መተኛቷንም ተረዳች የደረሰባትን ነገር ስታስታውስ አለመሞቷንም ሳታረጋግጥ ብዙ ጊዜ ቆየች ሐኪሞቹም እየቆየ ባደረጉት ምርመራ የተሰባበረው ሰነቷ ነፍስ እንዳልተለየው ተገነዘቡ ለሞት ባያደርስም ጉዳቱ ግን ከባድና የመዳኑም ተስፋ የመነመነ መሆኑን አዩ ከነበረችበት አሥጊ ሁኔታ
የሚያበረታታ ውጤት ማየት ጀመሩ ሳቤላ አሁንም ገና በሕይወትና በሞት መካከል ብቅ እልም ስትል ቆየችና ቀስ በቀስ ሕይወት እየዘራች ሔደች ከአደጋው ጀምሮ እስከ ሦስት ወር ድረስ የነበረችበት ሁኔታ ከሞት ያልተሻለ ነበር" ምንምን
ብሎ ከስቶ ገርጥቶ : የወላለቀው ሰውነት የሳቤላ ቬን ነው የሚል አይገኝም ነበር"
👍19
ሎርድ ማውንት እስቨርን ወደ ስኮትላንድ ሔዶ ስለ ነበረ የተላከው ደብዳቤ ለሚስቲቱ ደረሰ " እሷ ደግሞ ጽሑፉም የመጣበት አገርም እንግዳ ስለሆነባት ሳቤላ ቬን ባል አግብታ የሔደች መሰላት ስለዚህም ከፍታ እስክታየው ድረስ ጓጓች "ዠ

ልክፍተው ነው

“ እንዴ ! ለአባባ እኮ ነው አድራሻው " አላት አብሯት ቁርስ በመብላት ላይ
የነበረው ልጅዋ ዊልያም ልክ እንደ አባቱ የረጋና ሥነ ሥርዓት ያለው ልጅ ነበር "
“ የለም የደብዳቤው አጻጻፍ አዲስ ነው የሆነብኝ ስለዚህ ምናልባት ፈጣን
መልስ የሚፈልግ ይሆናል " አንተ ቁርስህን ብላ ” አለችና ደብዳቤውን ከፍታ በግድ
እየቈጠረች አነበበችው " እሷም ተንቀጠቀጠች "

“ አቤት ! አቤት ! እንዴት ያለ አሳዛኝ ነገር ነው ! ”

ምንድነው?” አለ ዊልያም ከቁርሱ ላይ ቀና ብሎ ወደ እናቱ እየተመለከተ።

“ እመቤት ሳቤላ ሳቤላ ቬንን” ታስታውሳታለህ ? "
“ እንዴ ደሞ እሷን እረሳታለሁ? አስታውሳታለሁ እንጂ

“ ሞተች በፈረንሳይ ውስጥ ባቡር አደጋ ሞተች !”

ትልልቅ ዐይኖቹ እንባ አንቆረዘዙ " መንፈሱ በጣም ተረበሸበትና ድርቅ አለ "

“ ነገሩ አሳዛኝ ቢሆንም ይሻላታል " ወደፊትስ ቢሆን ከመከራ ኑሮ ሌላ ምን?
ተስፋ ነበራት ? በራሷ ውድቀትና ውርደት በቤተ ዘመድም ኃፍረት ስላመጣች
በት ተንግዲህ ማን ወድቀሽ ተነሽ ይላት ነበር ? ”

“ እኔ እላት ነበር " እኔ የሷን ግማሽ ያሀል እንኳን የምወደው ሰው አልነበረኝም

“ እሱ ያለፈ ነገር ነው" ያንን የውርደት ሥራ ከፈጸመች ወዲህ ግን አንተም ብትሆን አትወዳትም ነበር”

ጥፋቱ የሷ ሳይሆን የሌላ ሰው ነው ትልቅ ሰው ብሆን ኖሮ በጥይት እገድለው ነበር
አለና ደብዳቤውን ከናቱ ተቀብሎ እናቱ እየመራችው በመቁጠር ካነበበ በኋላ ጠረጴዛው ላይ ጣል አደረገው "

“ ደብዳቤውን ዛሬ ወዶ አባባ ትሰጅዋለሽ አይደለም ? "

“ አሁን አባትህ የት እንዳለም ስለማላውቅ ቀስ ብየ እልከዋለሁ " ማስታወቂያው በጋዜጣ እንዲወጣ እልከዋለሁ ከቤተሰቡ እንደ ለምጽ እንደ ማላቀቅ የሚቆጠር ስለሆነ በጋዜጣ ማውጣቱ ደስ ይለኛል

“ እማማ . . . አንቺ የሕይወት እስትንፋስ ካላቸው ሴቶች ሁሉ የበለጥሽ ጨካኝ ነሽ መሰለኝ ሲላት ፊቷ በቁጣ ተለዋወጠ ።
“ይህን ምላስህን ካላሳረፍክ ዕረፍትህን አቋርጬ ነው ጠፍሬ ወደ አዳሪ ትምህርት ቤትህ የምመልስህ ብላ አስጠነቀቀችው

ከዚህ በኋላ ጥቂት ሰንብቶ ሚስተር ካርላይል ጧት ከኢስት ሊን ተነሥቶ እንደ
ተለመደው ወደ ቢሮው አመራ ገና ከመቀመጡ ሚስተር ዲል ተከትሎት ገባ
እንደ ሁልጊዜው ከሆነ ሚስተር ካርላይል ከቢሮ የቆዬትን ደብዳቤዎች ከፍቶ አይቶ ካበቃ በኋላ ይደውልና ሚስተር ዲልን ይጠራዋል ይህን ያሠራር ልምድ ማንም ጥሶትና አቋርጦት አያውቅም። ስለዚህ ሚስተር ካርላይል ትክ ብሎ በጥያቄ ስሜት ተመለከተው ደብዳቤዎቹና የታይምስ ጋዜጣ ከፊቱ ነበሩ

ይቅርታ ጌታዬ አዲስ የሰማኸው ነገር አለ ? ''

“ አዎን ሰምቻለሁ አለ ሚስተር ካርላይል ።

ደኅና እኔማ ያልሰማህ መስሎኝ እንድትሰማው ላዘጋጅህ አስቤ ነበር
አለና ሊወጣ ዞር አለ።

“ምን ታዘጋጀኛለህ ? ምን ነካህ ዲል ? ገና አንድ መቶ ፓውንድ ከሰረና ልቤ
የሚቆም መሰለህ ?

ሊወጣ የነበረው ዲል ምልስ አለ “አንተ የምትለው ስለ ኬንትና ግሪን መክሰር መሰለኝ" እኔ የመጣሁት ለሱ አይደለም ሚስተር አርኪባልድ እሱ ብዙም አይጐዳንም ።

“ ታዲያ ምንድነው ? ''

“አልሰማህም ማለት ነው ? እንኳንም አልቀደምከኝ ሳታስበው ማየቱ ግን
ጥሩ አይደለም አለና ዲል እጁን ከታይምስ ጋዜጣ ላይ አኑሮ '' በል ስለ ሞት
ከሚገልጸው ዓምድ ላይ ከዝርዝሩ የመጀመሪያውን ተመልከት " ግን ከማንበብህ በፊት ራስህን አዘጋጅ ብሎት ወደ ራሱ ቢሮ ሔደ ።

ሚስተር ካርላይል ጋዜጣውን ቶሎ ዘረጋና ሳይቆይ አነበበው ዲል እንዳለው ከሊስቱ መጀመሪያ ላይ አገኘው ።

“ ካሜር ላይ ፈረንሳይ በዚህ ወር በዐሥራ ስምንተኛው ቀን ሳቤላ ሜሪ
የሟቹ የማውንት እስቨርን ኧርል የ ዊልያም ቬን ብቸኛ ሴት ልጅ የሚል አነበበ ።

ሎርድ ማውንት እስቨርን የሳቤላ ቬንን ጋብቻ በጋዜጣ እንደ ሰማው ሁሉ እንዳጋጣሚ ሆነና ሞቷንም በጋዜጣ ተረዳ ደብዳቤውን ሚስቱ አዘግይታ ስለላከችለት በተከታዩ የፖስታ ቀን ደረሰው ። ሆኖም ደብዳቤውን ሲያይ የሩቅ ዜና ቀጥታ ማመን
አስቸጋሪ መሆኑን አሰበና ነገሩን አጣርተው መሞቷን አረጋግጠው እንዲጽፉለት
ለካሜር ከተማ ባለሥልጣኖች በሚችላት ፈረንሳይኛ ተጠንቅቆ ጻፈላቸው ።

ባለሥልጣኖቹም እሱ የጻፈላቸውን ይዘው ከሞት ከተረፉት ውስጥ እመቤት
ሳቤላ ቬን የምትባል እንዳለች ፈልገው ስለ አጡ መሞቷን አመኑ የተባለው
ሕፃንና ሞግዚቱ እዚያው አደጋው ቦታ መሞታቸውን ወዲያው መልስው ጻፉለት " እነዚህ ሁለቱ ከተሳፈሩበት ሠረገላ የነበሩ ሴቶችም ስለ ሞቱ አንዷ የሕፃኑ እናት ለመሆኗ እንደማያጠራጥር ጨምረው ገለጹለት ሙታ መቀበሯንና ለቀብሯ ለሚያስፈልጉ አንዳንድ ነገሮች ወጭም በቂ ገንዘብ አብሯት መገኘቱን ጭምር
አብራሩለት። የተጠቀሰችው ሴት ከሳቤላ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ የነበረች መሆኗን በቀላሉ ለመግንዘብ ይቻላል

እነሆ ወይዘሮ ሳቤላ ቬን የመሞቷ ወሬ እሷ ሳታስበው ሎርድ ማውንት እስቨርን ሰማው ዓለም ዐወቀው ፣ እሷም ሞተች መባሏን ያወቀችው ሎርድ ማውንት እስበርንና ሚስተር ካርይል ካነበቡት የታይምዝ ጋዜጣ ቅጅ ነበር ። ቆስለው ሆስፒታል ከተኙት መንግደኞች መኻል አንድ እንግሊዛዊ ነበር የእንግሊዝ ጋዜጦች
ስለሚደርሱት አንዳንዴ ለማንበብ ያውሳት ነበር ። በስሟ ብትጠራ አንዳንድ መንገደኞች ሊያውቋት ስለሚችሉና እሷ ደግሞ ይኸንን ስላልፈለገች ገና ከግረኖብል ስትነሣ አዲስ ስም ቀየረች ስለዚህ ይህች ከሆስፒታል ውስጥ የምታገግመው ዝምተኛና ዐይን አፋር ሴት አንድ ታላቅ የእንግሊዝ መስፍን በደብዳቤ የሚያስፈልጋት ሳቤላ ቬን የምትባለው ወይዘሮ ትሆናለች ብለው የካሜር ባለሥልጣኖች
አልጠጠሩም።

ወይዘሮ ሳቤላ የመሞቷ ዜና ምንጭ የሆነው መነኩሴቷ የላከችው ደብዳቤ መሆኑን ተረዳች ከሆነም ዘንድ ስሕተቱ እንዲታረም አልፈለገችም " እሷ እንደሆነች ማንነቷንና ያለችበትን ቦታ ሰውራ ለመኖር ከውድቀቷ በኋላ ስትመኘው የነበረ ነገር ነው እንግዲህ የምታሳድገው ልጅ የለም ። ከራሷ በቀር የምትረዳው ሰው የላትም ለራሷ ከሆነ በቀላሉ ሠርታ መኖር ትችላለች ብትራብም ግድ የላትም ። ያላት የሎርድ ማውንት እስቨርንን እርዳታ መቀበልም አላስፈለጋትም ስለዚህ እሱም ሆነ ሌላው ሁሉ ሙታለች ብሎ አምኖ ይኑር አለችና ለወደፊቱም
ማዳም ቬን እየተባለች ለመጠራት ወሰነች

ስለዚህ የዚያች ያልታደለች ወይዘሮ ሕይወት በዚህ ተወሰነ ሎርድ ማውንት
እስቨርን መሞቷን ያረጋገጠበትን ከካሜር የመጣለትን ደብዳቤ ለሚስተር ካርላይል
ላከለት ዜናው ለአንድ ሳምንት ብርቅና ድንቅ ሆነ ። ያቺ ምስኪን ስሕተተኛ
ወይዘሮ ሞተች በመራራው ዕድሏ ጥርስ በተያዘችባት ቅጽበት እንኳን ስሟ አልተነሣም አከተመ ። እመቤት ሳቤላ ቬን እንደ ተረሳች ቀረች....

💫ይቀጥላል💫
👍21😢10
የጠንቋዩ ዋሻ
ክፍል 10

ዋሻው ከዎትሮው ፡በተለየ ጩኽትና ማጓራት ፡ አይሎበታል ፡ መሳይ ሰውነቱን ውርር አደርጎታል ፡ ስለጠንቋዩ የሚሰማው ነገር ውሸት ቢሆንም ፡ አንዳንዴ ግን ፡ የሚያወጣው ፡ድምፅና ፡ ግዝፈቱ ያሸብረዋል ፡ የዛሬው ደሞ ብሷል ፡ አሁናውን ደሞ በዋሻውስጥ ነፃ ስለተለቀቀ ፡ አልፎ አይሂድ እንጂ ይንቀሳቀሳል ፡እና ዋሻው ፡ውስጥ ፡ የተለያዩ ተፈልፍለው ፡የተሰሩ ቤቶች ፡ አይቷል ፡ ነገርግን ፡እያንዳንዱ ክፍል ፡ በቀያይ ፡ጨርቆች ፡ስለተጋረዱ ሽብርን ፡ይለቃሉ ፡ በዛላይ ምንነታቸውን ፡በግልፅ ፡የማይለያቸው ፡ጥንስሳቶች ፡ በሳምንት ፡ውስጥ ፡ለሦስት ጊዜ ፡እየታረዱ ዋሻው ፡ይረጫል ይሄበራሱ ይሰቀጥጠዋል ፡ ጓደኞቹ ደሞ ይባስ ፡ብለው ፡የእንስሳቶቹን ፡ደም በአቢያራ ትህዛዝ ፡በነጭ ፡ጎድጓዳ ሰአን ፡መጠጣት ፡ጀምረዋል ፡ ይሄን ፡እንዲያደርጉ የገፋፋቸው ፡አይልና ጥንካሬ እንደሚሰጣቸው ፡በአቢያራ ስለተነገራቸው ነው ፡ የአቢያራ ሴቶች ፡ደሞ ፡በሱ አማካኝነት ፡ከደሙ ግንባራቸውን ፡ይቀባሉ የተቀቡትም ደም እስከማታ ድረስ እንዲጠፋ አይፈለግም ስለዚ ፊታቸውን ምንም እንዳይነካቸው ይጠነቀቃሉ ፡
መሳይ ሲፈራ ሲቸር አስፈሪውን የአቢያረ ድምፅ ወደሚሰማበት አቅጣጫ ሄደ በቀረበ ቁጥር አስፈሪነቱ ቢያይልም ልቡን በቀኝ እጁ ደግፎ ደጋግሞ የአምላኩን ስም እየጠራ አቢያራ ከሚጮህበት ክፍል ደርሶ የዋሻውን ግድግዳ ተደግፎ ቆመ ፡ ከዛም በቀስታ የተጋረደውን ቀይ መጋረጃ በመጠኑ ገለፅ አድርጎ ወደውስጥ አየ ከውስጥ የአቢያራ ሴቶች ክብ ሰርተው ተያይዘው ይሽከረከራሉ የሆነ የማይገባ ነገር ያጉተመትማሉም ፡ አቢያራ መሃል ላይ ተንበርክኮ ያጓራል ፡ወደ ሌላ አቅጣጫ ሲመለከት ፡አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት በደም ተጨማልቀው ወድቀዋል ፡ በሰውዬው አጠገብ ግራና ቀኝ ጓደኞቹ መስፍንና ዳንኤል ፡ እጆቻቸው ፡በደም እንደተበከለ ፡ የጩኽት ድምፅ እያወጡ አቢያራን ያጅባሉ ፡ አድማስ በእጁ ስለት እንደያዘ ፡ እንደበሽተኛ አንገቱን በፍጥነት እያንቀሳቀሰ ቆሟል ፡ መሳይ የሚያየውን ነገር ለማመን ከበደው ፡ አቅለሸለሸው ፡ ሊያስታውከው ፡ሲታገለው ፡ በፍጥነት ወደዋላው ፡በመመለስ ፡ ተደበቀ ፡ በዋሻው ፡ውስጥ ፡ከምትገኘው ፡ለአንድ ሰው ፡ብቻ የምትበቃ ፡ ጠባብ ፡ስፍራ ወስጥ ፡ውትፍ ፡አለ ፡ ልቡ በፍጥነት ፡ሲመታ ፡ ይሰማዋል ፡ የዋሻው ፡ የጭካኔ በትር ፡ዛሬ ገና የተጀመረ መሰለው ፡ ስለ ተገደሉት ሰው ፡አሰበ ፡ አሳዘኑት ፡ ይሄኔ የሀነሰው ፡ባል ፡አባት ይሆናሉ ፡አቢያራ ግን በጭካኔ መስዋት አደረጋቸው ፡ ኧረ ፈጣሪዬ ተው ፡አንድ ነገር አድርግልኝ እባክህ እባክህ ፡ የነዚን ፡ እብዶች ፡ ስህተት ግለፅ ፡ እባክህ እያለ ተማፀነ ፡
ከብዙ ውጥረት በዋላ ዋሻው ፡ሰላም ፡አገኘ ፡ መሳይም ባለበት እንዳለ የሰመመን እንቅልፍ ፡አሸለበ ፡ ግራ የሚያጋባ ፡ አስፈሪ ቅዠት እያየ ሲወዛገብ ፡ ድንገተኛ ጥሪ ቀሰቀሰው ፡ በድንጋጤና በመረበሽ ፡አይኑን አፈጠጠ፡
"መሳይ ለረጅም ሰአት ስፈልግህ ነበር ፡ በጣም ነበር ያሳሰብከኝ " እንደ ሙዚቃ የሚስብ የሴት ድምፅ ፡ ኤዛ ነበረች
"እእ ለምምን ፈለግሺኝ ?"
"ዝምብዬ ላይህ ፈልጌ "
"እዚ ነበርኩ"
"እኮ እያየውህ ነው ፡ምን ትሰራለህ እዚ ?በጣም አደገኛ ቦታ እኮ ነው ፡መርዛማ እባቦች ሊኖሩ ይችላሉ በል አሁን በፍጥነት ከሱ ውስጥ ውጣ "ስትለው ፡መሳይ ፡የማይወደው ፡የእባብ ስም ሲጠራ ፡ ዘሎ ፡ወጥቶ ፡ኤዛላይ ተለጠፈ፡ኤዛ ሳቀች ፡ ነገርግን ደሞ ሲጠጋት የተለየ ስሜት ውስጥ ስለከተታት አቅፋ ያዘችው ፡ አያያዟን ልብ አላለውም ፡ለጊዜው ፡ከጠራችበት ፡እባብ ፡ማምለጥ ነው ፡የፈለገው ፡ እናም ፡ እንዳቀፈችው ፡በጆሮዋ "ከዚ ስፍራ አስወጪኝ እባክሽ ፡እኔ እየዘገነነኝ ነው "አላት ፡ ኤዛ አንገቱ ስር ስታሸተው ፡ ትንፋሿን ፡ስለሰማ ፡ደነገጠ የባስ ፡ልትቀየርበት መሰለው ፡እሷው ፡የባሰ ፡ ቀና ብሎ ሲያያት ግን አይኖቿውስጥ ፡ያየው ፡ሰላም እና እርህራሄ ነው ፡ በልምምጥ ፡ ሲቁለጨለጭባት ፡ ከስሜቷ ጋር ታግላ ፡ እራሰን ፡በማረጋጋት ፡ እጁን ይዛ ፡በጥንቃቄ ፡ ወደ ዋሻው ፡በስተጀርባ አመራች ፡ ወደመናፈሻው ፡ሲወጡ ፡ ከርቀት ፡ ጓደኞቹን ፡አየ እነሱም ፡በመገረም ፡እያዩት ፡ነበረ ፡ እንዴት ፡ከዋሻው ፡ሴት ፡ጋር ፡እጅለእጅ ፡ተያያዘ ፡ ጠረጠሩት፡ እናም ፡መስፍን ፡ተንኮል ፡አሰበበት,,,,,,,,


ሙና መሀመድ

ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍43🤔2
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሁለት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

ጦርነቱ የታወጀው የበጋው ወቅት ማብቂያ አካባቢ በአንድ ፀሃያማና ቀለል ያለ እሁድ ነበር፡፡

የጦርነቱ ዜና ሲታወጅ ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ ቤት ውስጥ ነበረች፡፡ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ተዘጋጂ በመባሏ ጨሳለች፡፡ ከርቀት ያለማቋረጥ
የሚሰማት የቤተክርስቲያን ደወል አሰልቺ ሆኖባታል፡ የ19 ዓመት ልጅ በመሆኗ ስለሃይማኖት የራሷን ውሳኔ መወሰን ብትችልም አባቷ ከቤተክርስቲያን እንድትቀር አይፈቅዱላትም፡፡ ከዓመት በፊት ቤተክርስቲያን መሄድ
እንደማትፈልግ ነግራቸው ነበር፡፡ እሳቸው ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል።

‹‹በእግዚአብሔር የማላምን መሆኔን እያወቅሁ ቤተክርስቲያን መሄድ
ማስመሰል አይመስልም ወይ?›› አለቻቸው አንድ ቀን፡፡

‹‹ጅል አትሁኚ›› አሏት አባቷ ሎርድ ኦክሰንፎርድ፡
ትልቅ ስትሆን እንደማትሄድ ለእናቷ ነገረቻቸው፡፡
‹‹ባልሽ ይጨነቅበት የኔ ማር›› አሏት እናቷ፡፡ ከዚያ ቀን በኋላ ስለዚሁ ጉዳይ ተነጋግረው ባያውቁም እሁድ በመጣ ቁጥር ማርጋሬት ጥላቻዋ
ይጠነክራል፡

እህቷና ወንድሟ ከቤት ሲወጡ ሰማች። ኤልሳቤት 21 ዓመቷ ነው፡፡ ቁመቷ የብቅል አውራጅ ሲሆን መልክ አልፈጠረባትም፡፡ በልጅነታቸው እህትማማቾቹ ምስጢረኞች ስለነበሩ አይለያዩም፡፡ ካደጉ በኋላ ግን ተራራቁ፡፡
ትምህርት የተማሩት እንደሌሎች እኩዮቻቸው ትምህርት ቤት ሄደው
ሳይሆን አስተማሪ ተቀጥሮላቸው ቤት ውስጥ ነው፡ ኤልሳቤት በጉርምስና
ጊዜ የምታራምደው የወላጆቿን ግትር ልማዳዊ አስተሳሰብ ነበር፡፡
አመለካከቷ አክራሪ ሲሆን ከመኳንንት ዘር በመገኘቷ በእጅጉ ትመካለች፡
አዳዲስ ሃሳቦችና ለውጥ ጠላቶቿ ናቸው፡፡ በአንጻሩ ማርጋሬት የእሷ ተቃራኒ ናት፡ የሴቶች መብት ተሟጋችና የሶሻሊስት ፖለቲካ አቀንቃኝ
ስትሆን ጃዝ ሙዚቃ ትወዳለች፡ ኤልሳቤት ማርጋሬት ተራማጅ አስተሳሰብ በማፍቀሯ ለወላጆቿ ታማኝ አይደለችም ብላ ታምናለች፡፡ ማርጋሬት ደግሞ በእህቷ ጅልነት ትናደዳለች፡፡ በዚህ ምክንያት የልብ ወዳጆች ባለመሆናቸው ታዝናለች፡፡ የልብ ጓደኞች ደግሞ የሏትም፡፡

የእሷ ተከታይ ፔርሲ 14 ዓመቱ ነው፡፡ ተራማጅ ሃሳቦችን ወይ አይወድ ወይ አይቃወም፡፡ በተፈጥሮው ሸረኛ ነው፡፡ የማርጋሬት አመጸኝነት ባህሪ ግን ደስ ይለዋል፡፡ በአባታቸው አምባገነንነት ሁለቱም ተጎጂዎች በመሆናቸው ይተዛዘናሉ፣ ይደጋገፋሉ፡ ማርጋሬትም ለእሱ ልዩ ፍቅር አላት፡

ሎርድና ሌዲ ኦክሰንፎርድ ቀድመው ከቤት ወጥተዋል፡፡ ሎርድ
ዥንጉርጉር ክራቫት አስረዋል፡፡ እመቤቲቱ ጸጉራቸው ቀይ፣ ዓይኖቻቸው አረንጓዴ ሲሆን ፊታቸው የገረጣ ነው፡፡ ጌቶች ጥቁር ጸጉራቸው ላይ ሽበት ጣል ጣል አድርጎባቸዋል፡ ፊታቸው ደግሞ እንደ ቲማቲም የቀላ ነው።

ኤልሳቤት የአባቷን ጥቁር ጸጉርና ቅርጸ ቢስ መልክ የያዘች ስትሆን ማርጋሬት ደግሞ የእናቷን ግርጣት ወርሳለች፡ ፔርሲ መልኩ በየጊዜው ስለሚለዋወጥ የማንን መልክ እንደሚይዝ በውል አይታወቅም:

መላው ቤተሰቡ ከግቢው ወጣና በእግር ጉዞ ጀመረ፡፡ ከቤታቸው በአንድ
ኪሎ ሜትር ርቀት ከሚገኙት አብዛኛዎቹ ቤቶችና መሬቱ በሙሉ
የአባትየው ሀብት ሲሆን ይህንን ሀብት ያገኙት ያለምንም ድካም ነው፡
በአገሪቱ ያሉት ባለመሬት ቤተሰቦች በጋብቻ በመተሳሰራቸው የፈጠሩት
ርስት ይኸው ከዘር ወደ ዘር ተላልፎ በአባትየው እጅ ገብቷል፡

በመንደሩ ውስጥ ለውስጥ ተጉዘው ከድንጋይ ጥርብ የተሰራው ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ደረሱ።
ከዚያም አባትና እናት ከፊት፣ማርጋሬትና ኤልሳቤት በመከተል ፔርሲ ደግሞ ከእነሱ ኋላ ተከታትለው
ገቡ፡ የኦክሰንፎርድን መሬት የተከራዩ ገበሬዎች በአክብሮት እጅ ነሷቸው፡
ማርጋሬት ይሄ ኋላቀር ልማድ ሲፈጸም ስታይ በእፍረት ትሽማቀቃለች፡
‹‹ሁሉም ሰው በእግዜር ፊት እኩል ነው! በይ በይ ይላታል፡፡ አንድ ቀን
ድፍረቱ ይኖራትና እዚያ ሁሉ ሰው ፊት ትናገር ይሆናል፡፡ ነገር ግን አባቷ
የሚያደርሱትን ነገር ስታስብ አስፈራት፡፡

የሰው ሁሉ አይን እየተከተላቸው ቤተክርስቲያኑ ውስጥ የቤተሰቡ መቀመጫ ጋ እንደደረሱ ፔርሲ አባቱን ‹‹ክራቫትህ ታምራለች አ
አላቸው፡፡ ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ሳቅ አፈናት፡፡ እሷና ፔርሲ ቶሎ ቁጭ አሉና ሳቃቸው እስኪጠፋ የሚጸልዩ ለመምሰል ራሳቸውን አጎነበሱ፡
ሰባኪ ወንጌሉ ገንዘቡን በዋዛ ፈዛዛ ስላባከነውና በመጨረሻም ወደ
ቤተሰቡ ስለተመለሰው ልጅ ታሪክ አስተማሩ፡፡ ማርጋሬት ጨርጫሳው ቄስ!
በእያንዳንዱ ሰው ጭንቅላት ውስጥ ስለሚጉላላው ጦርነት ቢሰብኩ ምናለ
ስትል አሰበች፡፡

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሂትለር ማስጠንቀቂያ ቢልኩለትም
ሂትለር ማስጠንቀቂያውን ከምንም ባለመቁጠሩ የጦርነቱ እወጃ የማይቀር
ሆነ፡

ማርጋሬት እንደ ጦርነት የምትፈራው ነገር የለም፡፡ የእስፓኒሽ እር በእርስ ጦርነት ፍቅረኛዋን ነጥቋታል ዓመት ያለፈው ቢሆንም ትዝ ሲላት
ትሳቀቃለች፡፡ ጦርነት ለሷ አስጨናቂ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ጦርነትን ትሻለች፡፡ ለብዙ ዓመታት በእስፓኒሽ
ጦርነት እንግሊዝ ያሳየችው ቦቅቧቃነት ያሳፍራታል
በሂትለርና በሙሶሊኒ
የታጠቁ ወሮበሎች የተመረጠውን ሶሻሊስት መንግስት ሲገለብጡ አገሯ ዳር ቆማ ተመልክታለች፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ሶሻሊስት ወጣቶች ከመላው አውሮፓ
ዲሞክራሲን ለመታገል ወደ ስፔን ዘምተዋል፡፡ ነገር ግን በቂ መሳሪያ አልነበራቸውም፡፡ በመላው ዓለም ያሉ ዲሞክራቲክ መንግሥታት ፊታቸውን ቢያዞሩባቸውም ወጣቶቹ ግን ህይወታቸውን ሰዉ፡፡ እንደማርጋሬት ያሉ ሴቶችም
አንገታቸውን በሃዘን ደፉ፤ እፍረትንም ተከናነቡ፡፡ ብሪታንያ ፋሺስቶችን
ተቃውማ ብትነሳ ማርጋሬት በአገሯ እንደገና እንደምትኮራ ተማመነች፡፡

የጦርነቱ አይቀሬነት ልቧ ውስጥ ሌላም ደስታ አጫረባት፡፡ የዚህ ነፃነት
የሌለውና የተጨናነቀው የቤተሰብ ህይወቷ ማብቂያ ይሆናል ስትል አሰበች፡
ይሄ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ የማይታይበት ልማዳዊና ትርጉም የለሽ አኗኗሯ
አንገቷ ጋ ደርሷል፡ ከዚህ አሰልቺና ተስፋ አስቆራጭ ማህበራዊ ሕይወት
አምልጣ ወጥታ የራሷን ህይወት ለመኖር ፈልጋለች። ነገር ግን የሚሆን
የሚሆን አልመስልሽ ብሏታል፡፡ ዕድሜዋ ገና ነው ቤተሰቧን ለቃ ለመውጣት አይፈቀደላትም፡፡ ገንዘብም የላትም፡፡ ለየትኛውም የስራ ዓይነት ደግሞ ብቁ አይደለችም፡፡ ነገር ግን በጦርነት ጊዜ ሁሉ ነገር የተለየ ይሆናል ስትል አሰበች፡፡

ባለፈው ጦርነት ወቅት ሴቶች ሱሪ ታጥቀው ፋብሪካ ውስጥ እንዴት
ይሰሩ እንደነበር በአድናቆት አንብባለች፡፡ ባሁኑ ጊዜ ምድር ጦር፣ ባህር ኃይልና አየር ኃይል የሴቶች ቅርንጫፍ አላቸው፡ ማርጋሬት ምድር ጦርን
መቀላቀል ፈልጋለች፡ አንድ የምታውቀው ስራ መኪና መንዳት ብቻ ነው፡
የአባቷ ሾፌር መኪና መንዳት አስተምሯታል፡ የሞተው ፍቅረኛዋ ሞተር
ሳይክል አስነድቷታል፡ የሞተር ጀልባ መንዳት አያቅታትም፡ የምድር ጦር
መምሪያ የአምቡላንስ ሾፌሮችንና ፖስታ አመላላሽ ሞተር ሳይክል ነጂዎችን
ይፈልጋሉ፡ ዩኒፎርም ለብሳ ብረት ቆብ አድርጋ በሞተር ሳይክል ከጦር ሜዳ ወደ ጦር ሜዳ እየበረረች አገልግሎት መስጠት እንደምትችል እርግጠኛ ሆናለች፡
👍24👎1🔥1
ስብከቱ እየተካሄደ እያለ ከዓየር የቦምብ ድብደባ መጀመሩን የሚያስጠነቅቅ ጩኸት ተሰማ፡፡እነሱ
መንደር ግን አልደረሰም፡፡
የማስጠንቀቂያው ጩኸትም የእውነት አልነበረም፡፡ ሰዎች የእውነተኛ ቦምብ ድብደባ ቢመጣ እንዴት አድርገው ህይወታቸውን
እንደሚያተርፉ
አለማድረጋቸውን
ለመፈተን የተነገረውን ተግባራዊ ማድረግ
ነው።በመሆኑም የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ጦርነት መጀመሩን እንኳን ሳያስተውለው ወደ ቤታቸው በእግር አዘገሙ፡

መንገድ ላይ ፔርሲ ጫካ ሄዶ ጥንቸል ማደን አማረው፡ ሁሉም ተኩስ ይችላሉ፡ የቤተሰቡ ጊዜ ማሳለፊያ ተኩስ ነው፡፡ እንዲያውም ተጠናውቷቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ አባት ቀኑ እሁድ በመሆኑ የፔርሲን ሀሳብ
አልተቀበሉትም ፔርሲም ቢያዝንም የአባቱን ትዕዛዝ መጣስ አይችልም::የአባቱን ትዕዛዝ ፊት ለፊት ለመቃወም ገና ዕድሜው አልደረሰም፡፡

ማርጋሬት የወንድሟን ተጫዋችነት ትወዳለች፡፡ በተዳፈነው ህይወቷ
ውስጥ ጸሐይ የሚፈነጥቅላት እሱ ብቻ ነው ፔርሲ እንደሚያደርገው ማላገጥና ከጀርባቸው ሆና መቀለድ ትመኛለች፡፡

ቤት ሲደርሱ አትክልት የምታጠጣ እግረ ባዶ የቤት ሰራተኛ ሲያዩ አባት ተደነቁ፡፡ አያውቋትም፡፡ ‹‹ማነሽ?›› ሲሉ ጠየቁ፡

በአሜሪካውያን የአነጋገር ቅላፄ ልጅቷ ለጥ ብላ እጅ ነሳች፡፡
አባት ቀጠል አድርገው ‹‹ጫማዋ የት ሄደ?›› ሲሉ ጠየቁ
ልጅቷ በጥርጣሬ ዓይኗን ወደ ፔርሲ ወረወረች:
‹‹ልጅ ፔርሲ የቤት ሰራተኞች በእሁድ ቀን ጫማ ማውለቃቸው
የአክብሮት ምልክት ነው ስላሉኝ ነው ጫማዬን ያወለቅሁት ጌቶች አለች
ሰራተኛዋ እየተሽቆጠቆጠች
አባትና እናት በፔርሲ ተንኮል ሲበሳጩ ማርጋሬት በሳቅ ተንከተከተች ይሄ የፔርሲ የዘወትር ሽወዳ ነው፡፡ አዳዲስ ሰራተኞች ሲቀጠሩ የሌለ የቤት ደንብ በመንገር ያሞኛቸዋል፡፡

ማርጋሬት የፔርሲ አድራጎት
በመሆንዋ አዝናለች፡፡
ቢያስቃትም ሰራተኛዋ ባዶ እግሯን በመሆኗ አዝናለች

‹‹ጫማሽን አድርጊ›› አሉ እናት፡፡
‹‹ልጅ ፔርሲንም ከዚህ በኋላ አትመኚው›› ስትል ማርጋሬት ጨመረችበትና የፔርሲን ፀጉር እየጎተተች ‹‹እንዲህ ማድረግ ተገቢ
አይደለም›› አለችው:: ፔርሲ ከዚህ አድራጎቱ ምንም ቢሆን አይታቀብም፡
አንድ ጊዜ አባቱ በልብ ድካም የሞቱ መሆናቸውን ‹‹ለካህኑ ነግሯቸው መላው የመንደሩ ነዋሪ ለቅሶ ደረሰ ሀሰት መሆኑን ያረጋገጡት
በኋላ ነው፡፡

ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ከደስታ ብዛት መኪና በፍጥነት ንጂ! ንጂ!
ትልቅ ዛፍ ላይ ውጪ! ውጪ!› አላት፡ ጦርነቱ ሞት፣ ስቃይና እንግልት
የሚያስከትል ቢሆንም ወደ ኋላ የሚባልበት አይደለም፡፡ እንግዲህ አንዴ ወስናለች፡: አሁን መዝመት ብቻ ነው የሚቀራት፡፡ ስታስበው ልቧ ድው ድው ይላል፤ እንቅስቃሴዋ ሁሉ ይለወጣል፡፡ ፓርቲና ድግስ ይቀርና ሴቶች የትግሉን ጎራ ይቀላቀላሉ፡፡ የመደብ ልዩነት ይቀርና ሁሉም አንድ ላይ ይሰራል፡፡ ማርጋሬት የነፃነትን አየር መተንፈስ ጀምራለች፡፡ ፍቅረኛዋን
ኢያንና ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን የፈጁትን ፋሺስቶች ልትዋጋቸው ነው ማርጋሬት የተበቃይነት ስሜት የሌላት ብትሆንም ናዚዎችን
መዋጋትን ስታስበው ግን በቀል በቀል ይላታል፡፡ ውስጧ የተቀጣጠለው
ስሜት በቀላሉ የሚበርድ አይመስልም፡፡ ስሜቱም ለራሷም እንግዳ፣ አስፈሪ፣
ደግሞም አስደሳች ሆኖባታል፡

አባት ግን በንዴት ጦፈዋል፡፡ ‹‹እግዚአብሔር የረገመው ጠቅላይ ሚኒስትር!›› አሉተ ሎርድ ኦክሰንፎርድ የብሪታኒያ የፋሽስቶች ህብረትን ካቋቋሙት መስራች አባላት አንዱ ናቸው፡፡ ይህም የሆነው በወጣትነታቸው
ጊዜ ሲሆን በዚያን ጊዜ ሰዎችን ማስደሰት የሚችል ባህሪ የነበራቸውና
ተከታይም ያፈሩበት ጊዜ ነበር፡፡ በወቅቱ "The Threat of Racial
Pollution" የተሰኘ ነጮች ከይሁዳውያን፣ከእስያውያን፣ ከምስራቃውያንና
ከጥቁሮች ጋር ሳይቀር መዳቀል ሲጀምሩ ስልጣኔ ምን ያህል እየዘቀጠ
እንደመጣና የዘር ብክለት አደጋ ማንዣበቡን የሚያትት መጽሐፍ ጽፈዋል ከናፖሊዮን ቀጥሎ ታላቅ የአገር መሪ ነው ብለው ከሚያስቡት ኦዶልፍ ሂትለር ጋር ሃሳብ ተለዋውጠዋል እቤታቸው በየሳምንቱ ፓርቲ እየደገሱ
ፖለቲከኞችንና የውጭ አገር ባለስልጣናትን ይጋብዙ ነበር፡፡ አንድ ወቅት ላይ
ንጉሡ እንኳን ሳይቀሩ እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፓርቲው
ሌሊቱን በሙሉ የሚካሄድበት ጊዜ ነበር፡፡ አገሪቱ በችግሯ ጊዜ ከማጥ
ጠብቀው ነበር፡፡ ሃገሪቱን
እንዲያወጧት ጥሪ ታደርግልኛለች ብለው
ለመገንባት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ እንደሚወስዱም እንዲሁ ነገር ግን አገሪቱ ጥሪ አላደረገችላቸውም፡፡ እንዲያውም በየሳምንቱ ይደረግ የነበረው
ድግስ እየቀነሰ መጣ፡፡ ቀድሞ ይመጡ የነበሩ የተከበሩ እንግዶች ራሳቸውን ከብሪታንያ ፋሽስቶች ማራቅ ጀመሩ፡ ሎርድ ኦክሰንፎርድም ብስጭት ቀለባቸው እየሆነ መጣ፡፡ ግርማ ሞገሳቸው ተገፈፈ፡ ገጽታቸው በብስጭት፣ በመሰላቸትና በመጠጥ ብዛት ወየበ፡ ማርጋሬት የጻፉትን መጽሐፍ ስታነብ በድንጋጤ ክው አለች። መጽሐፉ ላይ የሰፈረው ሃሳብ ተገቢ ካለመሆኑም በላይ ጅል አስተሳሰብ የተሞጀረበት ሆኖ ታያት፡፡

አባቷ አሁን የያዙት አስተሳሰብ ደግሞ ‹‹ብሪታንያ ሶቭየት ህብረትን
ለመቃወም ከጀርመን ጋር ማበር አለባት›› የሚል ሆኗል፡፡ ይህን አስተሳሰብ
በመጽሔቶችና በጋዜጦች ላይ በመጻፍና አልፎ አልፎ ለፖለቲካ ክርክር በሚጋበዙበት የዩኒቨርስቲ ውይይት መድረኮች ላይ አራምደዋል፡ ይህ
አስተሳሰብ በአውሮፓ ተቀባይነት ባጣበት ጊዜም ቢሆን እሳቸው አጥብቀው
ይዘውት ቆይተዋል፡፡ በብሪታኒያና በጀርመን መካከል ጦርነት ሲታወጅ ግን ተስፋቸው መቀመቅ ወረደ፡፡ ማርጋሬትም ለአባቷ ሀዘን ተሰማት፡፡

‹‹ብሪታንያና ጀርመን እርስ በእርስ ይጠፋፉና አውሮፓ በሃይማኖት የለሹ ኮሙኒዩዝም ጫማ ስር ትወድቃለች›› አሉ ሎርድ ኦክሰንፎርድ፡፡

ማርጋሬት ‹‹ሃይማኖት የለሹ›› የሚለው አባባል ወደ ቤተክርስቲያን ተገዳ መሄዷን ስላስታወሳት ‹‹እኔ ግድ የለኝም፤ በእግዚአብሔር አላምንም››
አለች:
👍19
‹‹እኔ ቦልሼቪክ አይደለሁም፤ ሶሺያሊስት ነኝ›› አለች ማርጋሬት፡
ፔርሲ ጣልቃ ገባና በእናቱ የአነጋገር ቅላፄ ‹‹አትችይም የኔ ውድ የቸርች ኦፍ ኢንግላንድ ቤተክርስቲያን ተከታይ ነሽ›› አላት፡፡

ማርጋሬት እንደገና ሳቀች፤ ሳቋም እህቷን አንጨረጨራት።
‹‹ጥሩና ንፁሁን ለማጥፋት ትፈልጊያለሽ በዚህም ትደሰችያለሽ›› አለች
ኤልሳቤት፡፡

ማርጋሬት ይህ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጠው ፈልጋለች፡፡ ወደ አባቷ
ዞረችና ‹‹ምንም ሆነምንም ስለጠቅላይ ሚኒስትር ኔቪል ቻምበርሌይን
በተናገርከው እስማማለሁ፡፡ ፋሺስቶች እስፔንን ሲቆጣጠሩ በዝምታ
አልፈዋቸዋል፡፡ አሁን ጠላት በምዕራብም በምስራቁም ይገኛል፡››

‹‹ቻምበርሌይን ፋሽስቶች
ስፔንን ሲቆጣጠሩ ዝም
ብለው አልተመለከቱም›› አሉ ሎርድ፡፡ ብሪታንያ ከጀርመን፣ ከጣሊያንና ከፈረንሳይ ጋር ጣልቃ ያለመግባት ስምምነት አድርጋለች፡፡ እናም እሳቸው ያደረጉት ነገር ቃልን መጠበቅ ነበር››
አባት የተናገሩት ለይምሰል ነው እኛ ቃላችንን ስንጠብቅ ጀርመኖችና ጣሊያኖች ቃላቸውን አፍርሰዋል›› ስትል ተቃወመች ማርጋሬት በመሆኑም እነሱ መድፍ
ታጠቁ፤ ዲሞክራቶቹን ግን ባዶ እጃቸውን ሆኑ፡››

እናትም ‹‹በኢያን ሞት ከልቤ አዝኛለሁ የኔ ውድ፧ እሱ ግን በአንቺ ላይ መጥፎ ተፅዕኖ አሳድሮብሻል›› አሉ፡፡

ማርጋሬት እንባ አነቃት፡ ኢያን ሮችዴል በህይወቷ ውስጥ ታላቁ ክስተት ነበር ሞቱ አሁንም ስቃይ ሆኖባታል፡፡ ለአመታት ዶሮ ጭንቅላት ከሆኑ የባላባት ልጆች ጋር ፓርቲ ደንሳለች እነዚህ ልጆች ከመጠጥና
ከአደን በስተቀር አእምሮአቸው ምንም አያስብም፡፡ የእሷን አስተሳሰብ የሚጋራ የእድሜ አቻዋ የሆነ ሰው በእጅጉ ትመኝ ነበር፡፡ አንድ ቀን ኢያን በድንገትና በህይወቷ ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል፧ እሱ ከሞተ
ወዲህ እንደገና ህይወቷን ጨለማ ወርሶታል፡...

ይቀጥላል
👍18
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሶስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


...ማርጋሬት እንባ አነቃት፡ ኢያን ሮችዴል በህይወቷ ውስጥ ታላቁ ክስተት ነበር ሞቱ አሁንም ስቃይ ሆኖባታል፡፡ ለአመታት ዶሮ ጭንቅላት ከሆኑ የባላባት ልጆች ጋር ፓርቲ ደንሳለች እነዚህ ልጆች ከመጠጥና
ከአደን በስተቀር አእምሮአቸው ምንም አያስብም፡፡ የእሷን አስተሳሰብ የሚጋራ የእድሜ አቻዋ የሆነ ሰው በእጅጉ ትመኝ ነበር፡፡ አንድ ቀን ኢያን በድንገትና በህይወቷ ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል፧ እሱ ከሞተ
ወዲህ እንደገና ህይወቷን ጨለማ ወርሶታል

ኢያን በኦክሰንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ አመት ተማሪ ነበር፡
ማርጋሬትም ዩኒቨርሲቲ መግባት ምኞቷ ቢሆንም መስፈርቱን አላሟላችም፡፡አንብባለች፡ ሌላ ትምህርት ቤት ሄዳም አታውቅም ሆኖም ብዙ የምታደርገው ነገር አልነበረም:: በሀሳብ መፋጨት የምትወድ መሆኗ
ይገርማታል፡ ሀሳቡን በፍጹም ትህትና የሚገልፅላትና እስካሁን ከገጠሟት ሰዎች ሁሉ ነፃ አስተሳሰብ ያለው ሆኖ ያገኘችው ኢያንን ብቻ ነበር፡፡በውይይት ወቅት ታላቅ ትዕግስት ያሳያል፤ ባለው አቅም አይኮራም፣ያልገባውን ገብቶኛል አይልም፤ ካየችው ጊዜ አንስቶ ነበር የወደደችው፡
ለረጅም ጊዜ በመሀከላቸው የነበረው ስሜት ፍቅር ነው ብላ አታስብም ነበር፡ አንድ ቀን በማፈር እየተንተባተበ ‹‹ካንቺ ፍቅር ይዞኛል፧
ጓደኝነታችንን ያበላሽብን ይሆን?›› በማለት ተናዘዘላት፡ ያኔም እሷ በፍቅሩ መነደፏን ተረዳች፡

በዚህም ህይወቷን ለወጠው፤ ልክ ሁሉም ነገር ልዩ ወደሆነበት ሌላ
አገር የሄደች መሰላት፤ ሁሉም ነገር የሚያስደስት መሆን ጀመረ፤ ከቤተሰቦቿ ጋር የምትኖረው አጣብቂኝ የበዛበት ህይወትና ብስጭቱ ሁሉ ተረሳት፡ የዓለም አቀፉን ብርጌድ ተቀላቅሎ ህዝብ የመረጠውን ሶሻሊስት መንግሥት ለመታደግ ወደ ስፔን ሄዶም እንኳን ለህይወቷ ብርሀን ይፈነጥቅበት ነበር፡ ላመነበት ዓላማ ህይወቱን ለመስጠት በመዘጋጀቱ
ኮርታበታለች: አንዳንድ ጊዜ ደብዳቤው ይደርሳት ነበር፡ አንድ ጊዜ ግጥም ልኮላታል፡ በኋላ የመጣው ደብዳቤ ግን አስደንጋጭ ነበር፡፡ ከጠላት በተተኮሰ
ላውንቸር ሰውነቱ ተበጣጥሶ መሞቱን አረዷት፡ ማርጋሬት ከእንግዲህ አበቃልኝ! ስትል ደመደመች፡፡

‹‹መጥፎ ተፅዕኖ አሳድሮብኛል›› ስትል አስተጋባች የእናቷን አባባል
በመድገም፡፡ ‹‹ቀኖናን እንዳልቀበል፣ ሐሰትን እንድፀየፍ፣ ድንቁርናን
እንዳወግዝና ማስመሰልን እንድጠላ አስተምሮኛል፡
በመሆኑም በሚባለው ህብረተሰብ ውስጥ ቦታ የለኝም፡››

አባት፣ እናትና ኤልሳቤት በአንድ ላይ መናገር ጀመሩና ሁሉም ሰሚ
አለመኖሩን አውቀው ድንገት ዝም አሉ፡ ፔርሲ ድንገተኛውን ዝምታ
በመጠቀም ‹‹ይሁዳውያንን በተመለከተ›› አለ ‹‹ከስታንፎርድ ከመጡት ሻንጣዎች ውስጥ አንድ የሚገርም ፎቶግራፍ አገኘሁ፡፡››
ስታንፎርድ በአሜሪካ ኮኔክቲከት ክፍለ ሀገር የእናትዬው አገር ነው፡፡ ከደረት ኪሱ ውስጥ አንድ የተጨማደደና ቀለሙ የፈዘዘ ፎቶግራፍ አወጣና ‹‹ሩዝግሌንኬር
የሚባሉ ቅድመ አያት ነበሩኝ አይደለም?›› አለ።

እናትም ‹‹አዎ የእናቴ እናት ነች ታዲያ ምን አገኘህ የኔ ማር
አሉ።

ፔርሲ ፎቶውን ለአባቱ ሰጣቸው: ሁሉም ለማየት ተሰበሰቡ
ፎቶግራፉ ላይ በግምት ከሰባ አመት በፊት በአሜሪካ ውስጥ ምናልባት ኒውዮርክ ውስጥ አንድ አዳፋ የስራ ልብስ የለበሰና ኮፍያ ያደረገ ዕድሜው በግምት ሰላሳ ዓመት የሚሆነው ጢማም ሰው መንገድ ላይ ቆሞ ይታያል
ሰውየው የሞረድና ቢላ መስሪያ ጋሪ ይገፋል ጋሪው ላይ በግልፅ ሩቤንራሽቤን ብረት ቀጥቃጭ›› ይላል። አጠገቡ አስር አመት የሚሆናት ቀሚስና ቦት ጫማ ያደረገች ልጅ ቆማለች፡፡

‹‹ምንድነው ይሄ ፔርሲ? እነዚህ ድሆች እነማን ናቸው?›› ሲሉ አባት ጠየቁ።

‹‹ጀርባው ላይ የተጻፈውን እየው፣ አባባ›› አለ ፔርሲ።
አባት ፎቶውን ገለበጡ፤ ፎቶው ጀርባ ላይ ‹‹ሩዝግሌንኬር ራሽቤ
ዕድሜ 10›› የሚል ተፅፏል።

ማርጋሬት አባቷን ተመለከተች በጣም ተናደዋል፡

‹‹የእናታችን ቅድም አያት በየመንገዱ እየዞረ ቢላ የሚሰራ ሰው ልጅ ማግባቱ የሚገርም ነው፤ አሜሪካ ደግሞ እንደዚህ ናት ይላሉ›› አለ ፔርሲ

‹‹ይሄ የማይሆን ነው!›› አሉ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ድምፃቸው ሻክሮ
ማርጋሬት ግን አባቷ ሊሆን ይችላል ብለው እንደሚያስቡ ገመተች፡
ፔርሲም በግድ የለሽነት ‹‹የሆነ ሆኖ ይሁዳነት የሚተላለፈው በእናት
በኩል ነው ስለዚህ የእናቴ ቅድም አያት ይሁዳዊ ናት፤ ይህም እኔን
ይሁዳዊ ያደርገኛል›› አለ፡፡

አባት ፊታቸው በንዴት አመድ መሰለ፡፡ እናት ፊታቸው ላይ ጥርጣሬ ተነበበበት ግምባራቸውን በመጠኑ አኮማተሩ፡፡

ፔርሲም ‹‹ጀርመኖች ይህን ጦርነት ያሸንፋሉ፡፡ ማርጋሬት ሲኒማ ቤት
መሄድ አይፈቀድልሽም፤ እማማም በዳንስ ልብሶቿ ላይ በሙሉ ቢጫ ኮከብ ትሰፋለች›› አለ፡፡
ማርጋሬት ፎቶው ጀርባ ላይ የተፃፈውን ጽሁፍ በአትኩሮት ስታይ
እውነቱ ተገለፀላት፤ ‹‹ፔርሲ!›› አለች በመደሰት ‹‹ይሄ ያንተ ጽህፈት ነው!››
‹‹አይደለም›› አለ ፔርሲ፡
ጽሁፉ የእሱ መሆኑን አውቃ ማርጋሬት በሳቅ ተንከተከተች፡፡ ፔርሲ አባቱን ለማሞኘት መሬት ላይ ወድቆ ያገኘው ፎቶ ጀርባ ላይ ፃፈበት ፧አባትም አመኑት፡ ዘረኛ ሁሉ የእኔም ዘር የተደባለቀ ይሆን እያለ ሲባንን ይኖራል፤ ይገባዋልም ስትል ማርጋሬት አሰበች።

አባት ፎቶውን ጠረጴዛ ላይ ወረወሩት፡፡
የቤት አሽከራቸው ‹‹ምሳ ቀርቧል ጌቶች›› አለ፡፡ ቤተሰቡ ተያይዞ ወደ
መብል ቤት ሄደ፡ ሲጠበስ ፕሮቲኑ ይጠፋል በሚል የተጠበሰ ምግብ
አይበሉም፡፡ እሁድ እሁድ የሚበሉት የተቀቀለ ስጋ ነው።

አባት ‹‹ፀሎት እናድርስ›› አሉ፡፡

‹‹አንድ ነገር ማድረግ ይቀረናል›› አሉ እናት ሳይታሰብ ለንግግራቸው
ትኩረት እንዲሰጥ በማሰብ ‹‹ሁላችንም ይሄ የሞኛሞኞች ጦርነት እስኪያበቃ አሜሪካ እንሄዳለን››

ለአፍታ ሁሉም በድንጋጤ ዝም አሉ፡፡

ማርጋሬት በንዴት ‹‹አይሆንም!›› ስትል ጮኸች፡፡

እናትም ‹‹ለዛሬ የሚበቃንን ያህል ተጨቃጭቀናል፤ አሁን ምሳችንን
በሰላም እንብላ›› አሉ
‹‹አይሆንም›› አለች ማርጋሬት እንደገና በንዴት አፏ መናገር
አቃተው፡ ‹‹ይህን ማድረግ አትችሉም! ይሄ . .›› ልትወርድባቸው ፈለገች።
በአገር ክዳት ብትወነጅላቸው ተመኘች፡፡ ነገር ግን ከአፏ አውጥታ መናገር አቃታት፧ ማለት የቻለችው ‹‹ይህ ጥሩ አይደለም›› ብቻ ነበር፡

‹‹አፍሽን ካልያዝሽ ውጪ ከቤት!››
አሉ አባት።

ማርጋሬት በመሐረብ አፏን ጠርጋ ከወንበሯ ተነሳችና እያለቀሰች ከመብል ቤቱ ወጥታ ሄደች፡

የአሜሪካውን ጉዞ ያቀዱት ከወራት በፊት ነው፡፡

ፔርሲ ወደ ማርጋሬት ክፍል መጣና ዝርዝሩን ነገራት ‹‹ቤቱ ተዘግቶ
የሚቆይ ሲሆን የቤት ዕቃዎች በሙሉ በአቧራ መከላከያ ጨርቅ ይሸፈናሉ ሰራተኞቹ ይሰናበቱና ርስቱ ለሰው በአደራ ይተዋል፡ ገንዘቡ ባንክ ይቀመጣል፡፡ በመንግሥት በተላለፈው የውጭ ምንዛሬ ቁጥጥር ምክንያት
ገንዘብ ወደ አሜሪካ መላክ አይቻልም፡፡ ፈረሶቹ በሙሉ ይሸጣሉ፤ ጌጣጌጦቹ
ይቆለፍባቸዋል፡››

ኤልሳቤት፣ ማርጋሬትና ፔርሲ አንዳንድ ሻንጣ ውስጥ ዕቃዎቻቸውን ከተዋል፡፡ የቀረው ዕቃ በዕቃ ወሳጅ ኩባንያ ይላክላቸዋል፡ አባት ለሁሉም
በፓን አሜሪካ አውሮፕላን የሚጓዙበትን የአውሮፕላን ቲኬት ገዝተዋል የጉዟቸው ቀን ረቡዕ ዕለት ነው።
👍28🤔31👎1
ፔርሲ በደስታ ፈንድቋል፡ ከዚህ በፊት በአይሮፕላን አንድ ሁለቴ
ተጉዟል፡ ከባህር ላይ በሚነሳና ባህር ላይ በሚያርፍ አይሮፕላን ለመጓዝ ግን የመጀመሪያው ሊሆን ነው፡፡ አይሮፕላኑ ትልቅና በጣም ምቹ መሆኑን ከጥቂት ሳምንታት በፊት ስራውን በይፋ የጀመረ ጊዜ ጋዜጦች በስፋት ዘግበው ነበር፡፡ ወደ ኒውዮርክ የሚደረገው በረራ ሃያ ዘጠኝ ሰዓት የሚፈጅ ሲሆን በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ በምሽት በሚደረገው በረራ ተሳፋሪዎችይተኛሉ።

ያገራቸው ዜጎች በችግር፣ በመከራና በጦርነት ውስጥ ሆነው እነሱ በምቾት ሀገራቸውን ጥለው መሄዳቸው ተገቢ አይደለም ስትል አሰበች ማርጋሬት።

ፔርሲ ሻንጣውን ሲሸክፍ ማርጋሬት አልጋዋ ላይ ተጋድማ ኮርኒሱ ላይ
አፍጥጣ በንዴት እየጦፈች ዕድሏን ረገመች።

እስከ መኝታ ሰአት ክፍሏ ውስጥ ዘግታ ቁጭ አለች፡

ሰኞ ጠዋት አልጋ ውስጥ እንዳለች እናቷ ወደ ክፍሏ መጡ።

ባለ መስታዎቱ የፀጉር ማበጠሪያ ቡፌ አጠገብ ተቀምጠው ማርጋሬትን በመስታዎት እያዩ ‹በዚህ ጉዳይ ከአባትሽ ጋር ጭቅጭቅ እንዳትፈጥሪ አደራ›› አሉ፡፡

ማርጋሬት እናቷ እንደተረበሹ ተገንዝባለች፡፡ ነገር ግን በጣም በመበሳጨቷ ለእናቷ ሳታዝን ‹‹ይሄ የፈሪ ስራ ነው›› ስትል አፈነዳችው፡

‹‹ፈሪ ሆነን አይደለም›› አሉ ‹‹ጦርነት ሲጀመር ከአገር መውጣት ፍርሃት አይደለም ምርጫ የለንም፧ መሄድ አለብን››

ማርጋሬት እንቆቅልሽ ሆነባት ‹‹ለምን?››
እናት ፊታቸውን ወደ ልጃቸው መለሱና ‹‹ካልሄድን አባትሽን እስር
ቤት ይጨምሩታል›› አሉ፡

ማርጋሬት ተደነቀች ‹‹ለምን? ፋሺስት መሆን ወንጀል አይደል
አለች

‹ብአገር ውስጥ ሚኒስቴር ውስጥ የሚሰራ የፋሺስት ደጋፊ
አስጠንቅቆናል አባትሽ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ካገር ካልወጣ ይታሰራ? አሉ።

ማርጋሬት አባቷን እንደ ሌባ እስር ቤት ይገባል መባሉን ማመን
ተቸገረች፡ ጦርነት የተለመደውን ህይወት ሊለውጥ እንደሚች
አልተገነዘበችም።

‹‹ገንዘብ ይዘን እንድንሄድ አይፈቅዱልንም›› አሉ እናት በብስጭት አሁን ማርጋሬትን የገንዘብ ጉዳይ አያስጨንቃትም፡ ድንገት በአእምሮዋ እውነቱን ለእናቷ ለመናገር ወሰነች፡ ትንፋሿን ዋጥ አደረገችና ‹‹እማማ ከእናንተ ጋር መሄድ አልፈልግም›› አለች፡፡

እናት ምንም አልገረማቸውም፡ ምናልባትም እንዲህ አይነት ነገር
ስለጠበቁ ይሆናል፡ ጭቅጭቅ በመፍራት ‹‹ከኛ ጋር መሄድሽ አይቀር!›› አሉ ለስለስ ባለ አነጋገር፡፡

‹‹እኔን አያስፈራኝም፡፡ ከአክስቴ ማርታ ወይም ከአክስቴ ልጅ ከቴሪ ጋር መቆየት እችላለሁ: ከአባባ ጋር አትነጋገሪም በዚህ ጉዳይ?›› አለች
ማርጋሬት፡

ድንገት እናት ቱግ ብለው ‹‹አምጬ ተጨንቄ ወልጄሽ ማዳን ስችል
ህይወትሽን ለአደጋ አጋልጬ እንድተውሽ ትጠይቂኛለሽ?›› አሉ፣
ለአፍታ ያህል ማርጋሬት በእናቷ አባባል ልቧ ተነካና ‹‹እኔንም እኮ
ፈቃደኝነቴን መጠየቅ ነበረብሽ፤ መብት አለኝ፤ ህይወቴ ነው›› አለች፡
እናት ወደ ቀድሞው ለስላሳነት መለስ ብለው ‹‹አንቺ የምታስቢው ዋጋ የለውም፡፡ አባትሽ እዚህ እንድትቀሪ አይፈቅድልሽም፤ ምንም አልን ምን››

የእናቷ ዳር ቆሞ ማየት ማርጋሬትን ስላናደዳት እርምጃ ለመውሰድ
ወሰነች ‹‹ራሴ እጠይቀዋለሁ›› አለች
‹‹ባትጠይቂው ነው ጥሩ›› አሉ እናት ባሳዛኝ ድምፅ፡፡ ‹‹አሁን ባለው
ሁኔታ ደስተኛ አይደለም እንኳን አንቺ ተጨምረሽ፤ አገሩን ይወዳል፡ ልቡ
ተሰብሯል››

‹‹የኔስ ልብ?››

‹‹እንዳንቺ አይደለም አንቺ ገና ልጅ ነሽ፡፡ ብዙ እድል ይጠብቅሻል፡፡
እሱ ግን የተስፋው ሁሉ ማብቂያ ሆኖበታል››

‹‹ፋሺስት ያደረኩት እኔ አይደለሁም›› አለች ማርጋሬት በጭካኔ። እናት ተነሱ ‹‹ምነው እንደዚህ ክፉ አደረገሽ›› አሉና ወጥተው ሄዱ፡ፈ ማርጋሬት የፀፀትም የንዴትም ስሜት በአንድ ላይ ተሰማት አስተያየት
በሰጠች ቁጥር አባቷ የስድብ ናዳ ያወርዱባት ነበር፡

እናቷ ውብ ሲሆኑ አቋም የለሽ ባህሪ ያላቸው ሴት ናቸው: ከሀብታም ቤተሰብ የተወለዱ ሲሆን ያረጀ ያፈጀ ሃሳብ አራማጅ ናቸው፡ ይህ ባህሪያቸው የወንድን የበላይነት ከመቀበል ጠንካራ ፈቃደኝነት የመነጨ ነው:፡ ባላቸውን ለመቃወም አይፈቀድላቸውም፡:
ማርጋሬት እናቷን ስለምትወድ የእናቷን ኋላ ቀር ባህሪ ለመታገስ
ዝግጁ ናት፡፡ አካላዊ ቅርፃቸው ቢመሳሰልም በባህሪ አትመስላቸውም ቤተሰቦቿ ትምህርት ቤት እንድትሄድ ባያደርጓትም ራሷን ለማስተማር
ጥራለች፡፡ እንደ ቤቱ ገረድ ሊያያት መብት ያለው የሚመስለው አሳማ ባል ከምታገባ ቆማ ብትቀር ትመርጣለች
አንዳንድ ጊዜ ማርጋሬት ከእናቷ ጋር የተለየ ግንኙነት እንዲኖራት ትመኛለች፡፡ እናቷን ምስጥረኛዋ ማድረግና የሚስጥራቸው ተካፋይ ለመሆን ትፈልጋለች እንደ ጌጣጌጥ ሊቆጥራቸው በሚፈልግ አለም ላይ በአንድነት ክንዳቸውን ማንሳት እንዲችሉ አጋር እንዲሆኗት ታስባለች። ነገር ግን እናቷ ይህን ትግል ከተዉ ዘመናት ተቆጥረዋል፤ እሷም የእሳቸውን ፈለግ እንድትከተል ይፈልጋሉ፡ ይሄ ደግሞ አይዋጥላትም፡፡ ማርጋሬት እራሷን
መሆን ትሻለች፤ ለዚህም እራሷን አሳምናዋለች፤ ነገር ግን እንዴት?

ሰኞ ሙሉ ቀን ምግብ በጉሮሮዋ አልወርድ ብሎ ዋለ፡፡ አሽከሮች ቤቱን ሲዘጋጉ እሷ ሻይዋን ስትለጋ ዋለች፡፡ ማክሰኞ እለት እናቷ ማርጋሬት ሻንጣዋን አለመሸካከፏን ሲያዩ አዲሷን ገረዳቸውን ጀንኪንስን ሻንጣዋን እንድታዘጋጅላት አዘዟት፡፡

‹‹ሳምንት እንኳን ሳትሰሪ መሰናበትሽ መጥፎ አጋጣሚ ነው›› አለቻh ማርጋሬት ገረዲቷን ‹‹ምን እየሰራሽ ልትኖሪ ነው ፋብሪካ ውስጥ ልትሰሪ ነው?›› አለች ማርጋሬት ነገሩን ለመፈተሽ በመፈለግ አይነት፡፡

‹‹ጦሩን እቀላቀላለሁ፡: አስራ ሰባት ሺህ ሴቶች ጦር ሰራዊት
እንደተቀበላቸው ትናንት በሬዲዮ ተናግሯል፤ በየከተማው ማዘጋጃ ቤት ለመመዝገብ የሰልፉ ርዝመት ልክ እንደሌለው ጋዜጣ ላይ አንብቤያለሁ››

‹‹አንቺ እድለኛ ነሽ›› አለች ማርጋሬት ተስፋ በማጣት ‹‹እኔ ወረፋ
የምይዘው ወደ አሜሪካ ለመብረር ነው››

‹‹ጌቶች የሚፈልጉትን ነው ማድረግ ያለብሽ›› አለች ጀንኪንስ፡፡

‹‹አንቺ ሰራዊቱ ውስጥ ስትገቢ አባትሽ ምን አሉ?››

‹‹ለሱ አልነግረውም፧ ዝም ብዬ ነው የምሄደው››

‹‹መልሶ ቢወስድሽስ?››

‹‹አይችልም፧ አስራ ስምንት አመት ሞልቶኛል፡፡ አንዴ ከገባሽ አለቀ
እድሜሽ ከደረሰ ወላጆችሽ ምንም ማድረግ አይችሉም››

ጀንኪንስ የማርጋሬትን ሻንጣ እታች ቤት ወሰደች፡፡ ረቡዕ በጠዋት ጉዞ
ይጀምራሉ፡ ሻንጣዎቹ ተደርድረው ስታይ ማርጋሬት ጦርነቱ እስኪያልፍ
አሜሪካ ኮኔክቲከት ውስጥ በኩርፊያ እንደምታሳልፍ ገባት፡፡ እናቷ በዚህ ጉዳይ ከአባቷ ጋር ጭቅጭቅ እንዳትፈጥር ቢለምኗትም አባቷን መጋፈጥ
አለባት፡፡

ይህንን ማሰቡ በራሱ አንቀጠቀጣት፡፡ ወደ ክፍሏ ተመለሰችና ራሷን አረጋግታ ለአባቷ የምትለውን ነገር አሰላሰለች፡፡ ረጋ ማለት አለባት፡፡ እምባ እንደማያሳዝናቸውና ቁጣ ለስድብ እንደሚጋብዛቸው ታውቃለች፡፡ ምራቁን እንደዋጠ ሰው ነው መናገር ያለባት፡፡ ተጨቃጫቂ ከሆነች ቁጣቸውን ይቀሰቅስባቸውና ፍርሃት ተሰምቷት ያሰበችውን ከመናገር ልትታቀብ ትችላለች፡.....

ይቀጥላል
👍313
የጠንቋዩ ዋሻ
**ክፍል 11**

ምሽት ላይ ነው ከዋሻው በስተጀርባ ካለው አትክልት ስፍራ አንድ ጥቁር ድንጋይ ላይ መሰይ በፀጥታና በትካዜ ተቀምጧል ፡ ነገሮች ፡በሆነታምር ፡ተቀይረው ፡አልፈው ከቤተሰቡ ጋር እንዲገናኝ ፈጣሪውን እየለመነም ጭምር ነው ፡ ይሄን አስፈሪ ና ባለማወቅ የሚፈፀም የዋሻው ውጥ ትርሂት ፡ ማብቂያ እየናፈቀ ፡ ነበር ፡ ከርቀት ጓደኞቹ ፡ ለብቻቸው ፡ተነጥለው ፡ተቀምጠው ፡ወደሱ እያዩ ሲያወሩ ፡ አልፎ አልፎ ቀና እያለ ያያቸዋል ፡ የገዛ ጓደኞቹ ወደ አስፈሪ አውሬነት የመቀየራቸው ፡ጉዳይ ፡አሳስቦታል ፡ አብሮ ፡አደገቹና በጣም ፡የሚግባቡ ፡ ነበሩ ፡ዛሬ ፡ሕይወት ባልጠበቁት ሁኔታ አምጥታ ከማያውቁት ዋሻ ፡ ጥላቸዋለች ፡ ይሁኔታ ሦስቱንም ፡ ቀያይራ ፡ ለዚ አብቅታቸዋለች ፡ መሳይ ነገሮች ሁሉ ፡ በዚመልኩ እዚጋር መድረሳቸውን ሲያስበው ፡ጩህ ጩህ ይለዋል ፡ ጓደኞቹ በሰው ደም እስከመታጠብ ፡ደርሰዋል ፡ የአቢያራ ፡አይል፡ይበልጥ ፡የጨመረ ፡ይመስላል ፡ አንዳንዴ ፡ከሁኔታው ፡አንፃር ፡ምን ፡አልባት ፡አቢያራ ፡ለየት ፡ያለ ፡የሴጣን ፡መንፈስ ፡ይኖረው ፡ይሆን ፡ብሎ ፡እንዲጠራጠር ፡ያደርገዋል ፡እዛ ዋሻውስጥ ፡ትንሽም ፡ቢሆን ፡ተስፋው ፡ኤዛ ናት፡ ፡በጣም ፡እየመሸ ሲመጣ ፡ ከአትክልቱ ስፍራ ተነስቶ ፡ወደ ዋሻው ፡ ሊገባ ተረመደ ፡ ጥቂት እንደሄደ ኤዘን አይቷት ፡ቆም አለ ያንን ቀዩን ቀሚሷን ፡እየጎተተች ፡ ደስ ፡በሚል ፡ፈገግታ ታጅባ ወደሱ ስትመጣ ፡ በመገረም ፡አያት ፡ለመጀመሪያ ጊዜ ፡ያገኛት ፡ይመስል ፡በውበቷ ፡ተደነቀ ፡ በልቡም ፡እቺ ሴት ፡ግን ፡ የሆነ የተለየ ነገር አላት ልበል አለ ፡ ደሞም ፡የሌላ አገር ደም ያላት ነው የምትመስለው ፡ ነው ፡አድማስ ፡በዛች ፡ቆሼ መኪናው ፡ በሆነታምር ፡ከአገር ፡ይዞን ፡ወጥቶ ፡ይሆን ፡ ግን ደሞ ፡አማርኛ ፡እንዴት ፡ሊያውቁ ቻሉ ፡ ወይ አምላኬ ፡ብሎ ፡ተወዛገበ......
"መሳይ ልትገባ ነው?"አለችው ፡ኤዛ ደርሳ
"አዎ "አለ ቀና ብሎ ለማየት እየከበደው
"በዚ ሰአት እንቅልፍ መተኛት ይከብዳል ጥቂት ከኔጋር አትቀይም"አለችው አገጩን ያዝ አድርጋ
"አይ አውሬ ቢኖርስ "አለ ቀና ብሎ እያያትና አገጩላይ ያሳረፈችውን እጇን ለመሸሽ እየሞከረ
"አይ እዚ አውሬ አይገባም የአቢያራ መንፈስ ይጠብቀናል ፡በዛላይ እኔ እስካለው ፡አትፍራ ፡"አለች
"ኤዛ እባክሽ ስሚኝ አቢያራ የሚባል መንፈስ የለም ፡ አትሞኚ በተሳሳተ መንገድ ላይ ነሽ ፡ አንድ አምላክ ፡ነው ፡ያለን ፡እሱም ፡በሰማይ ፡ነው ፡ቤቱ እና ደሞ ፡በእያንዳንዳችን ፡ልብ ፡ውስጥ ፡ እሱን ማመን ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ ፡ ታጋሽ ፡ አምላክ ፡አላት ፡ለዝች ፡ምድር ፡ ብዙ ስእተቶችን ፡ብንሰራ ፡ብናጭበረብር ፡ አንድቀን ፡እንደምንመለስ ፡አስቦልን ፡በትህግስት ፡ይጠብቀናል ፡ እሱ ከኛ የሚፈልገው ፡ታማኝነትን ተስፋን ፍቅርን ፡ ይቅር ባይነትን ምስጋናን ነው ፡ አሰተኛ እና ጠንቋይ ፡ግን ሁሌም ፡ ካንቺ ይፈልጉብሻል ፡ በውሸት ፡ይገነቡሻል ፡ አይለኝነትና እንቢተኝነትን ፡ ጥሎ ማለፍን ፡ ያልደከምሽበትን ሀብት እያሳዩ ገደል መክተትን፡ክቡሩን የሰው ልጅ ደም ፡ መስዋት ማድረግን ፡እያስተማሩ ወደውቀት ነው የሚመሩሽ ፡ ስለዚ እባክሽ ፡ከዚ ሕይወት ፡እንድትወጪ ፀሎት አድርጊ ስፀልዪ ግን አምላኬ ሆይ ሰማይና ምድርን ዘረጋህ ,,,,,,,,እያልሽ እንጂ፡ አጠገብሽ ፡ቁጭብሎ እንዳንቺ የሚበላና ፡ እንደ አውሬ ፡የሰው ደም ፡ ለሚጠጣ አቢያራ ስለተባለ ጠንቋይ ብለሽ አይደለም ፡ ለዚ ጠንቋይ መፀለይም ምስጋናም ማቅረብ ፡አይጠበቅብሽም ፡!!"አላት መሳይ አይኖቿን በድፍረት፡እያስተዋለ ፡ ኤዛ በፀጥታ ስታዳምጠው ፡ቆይታ ፡አገጩን ፡በመልቀቅ ፡አፉን ፡እፍን ፡አድርጋ ፡ያዘችው ፡በጣም ፡የደነገጠች ፡ትመስላለች ፡ እናም ፡ዙሪያ ገባውን ፡አየች ፡ ማንም የለም ፡እነመስፍንም ፡ወደዋሻው ፡ገብተዋል ፡ የአቢያራን ፡መንፈስ ፡የተቆጣ እንደሆን ፡ብላ እንደምታጣራ ፡መሳይ ፡ገባው ፡ እጁን ፡ወገቧ ፡ላይ ፡በማሳረፍ ፡ትኩረቷን ፡ሳበ ፡ ኤዛ ፡ ወደሱ ተመለሰች ፡አየች ፡ በጨረቃዋ ፡ብርሃን ፡የታገዙት ፡አይኖቿ ፡አይኖቹ ውስጥ ፡አንፀባረቁ ፡ የመሳይ ፡አሳዛኝ ፡አስተያየት ፡ኤዛን ፡ፈተናት ፡ የሆነ አይል ፡ ወደሱ ጎተታት ቀረበችው ፡ ወደማታውቀው ዓለም ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ፡ ,,,,,,,,,,,,


ሙና መሀመድ

ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍37😁6😱2🤩1
የጠንቋዩ ዋሻ
ክፍል 12
°❖°❖°❖°❖°❖°❖°
መሳይ በኤዛ ቀጭን ወገብ ላይ እጆቹን ጠምጥሞ ወደራሱ እያስጠጋ ቀልቧን ይገዛው ጀመረ ፡ ኤዛ የስሜት ቁንጥጫውን ተቆጣጥራ ማስቆም እስኪሳናት ሆና በዝምታ ተከተለችው ፡ የልቧ ምት ለራሷም እስኪገርማት ሆነች ፡ መሳይ በአሳዛኝ አይኖቹ አይኖቿን ፈልጎ አተኮረባቸው ፡ ኤዛ አይኖቹን ተከትላ ወደ ከንፈሮቹ ዝቅ አለች ፡መሳይ ያቀረበችለትን እነዛን እንጆሪ የመሱሉ ከንፈሮቿን በፍጥነት ተቀበላቸው ፡ እሱ እንደተራበ ሰው ሲሆንባት እሷ በማታውቀው አዲስ ስሜት ተቀጣጠለች ፡ ይሄ ለሷ ለየት ያለ ሌላ አዲስ የሕይወት መንገድ ነው ፡ ተስሞ የማያውቀው ከንፈሯ ፡ግን ቦታውን አልሳተም ፡ እሱ የሚያደርገውን እየተከተለች ፡ በመሳይ ከንፈሮች ላይ ፈሰሰች ፡ መሳይ ጠበቅ እያደረገ ልቧን አጠፋው ፡ ፡ እንዲ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጠፍተው ሲወዛወዙ ፡ከወደዋሻው ደውል ተሰማ ፡ኤዛ ብርግግ ብላ መሳይን ገፍትራው ድንብርብር ብላ ቆመች ፡ መሳይ በድንጋጤ ቀጥሎ የምታደርገውን ጠበቀ፡ ትንሽ ስታየው ፡ቆይታ "ና ቶሎ እንግባ ፡አባት አቢያራ ነው የደወለው ፡ እኔ እንዳልገባው አውቋል ፡ ይቅር ይበለኝ አባቴ "አለች እየተርበተበተችና የመሳይን አጅ እየያዘች ፡
"እኔ ለብቻዬ ልሂዳ ፡አብረን ካየን ሊቆጣ ይችላል"አላት እጁን አይዛ ወደዋሻው እየጎተተች ስትወስደው
"አይቶናል ፡ቀጣይ የምቀጣውን ቅጣት መቀበል ብቻ ነው "አለች ትንፋሿ ቁርጥቁርጥ እያለ
"ኧረ አላየንም እዚ ማንም አልነበረም እኮ"አለ መሳይ
"አይ አይ አቢያራ በልባችን ውስጥ አለ ጌታዬ "አለች በቁጭት
"እንዲማ መቼም ሊሆን አይችልም በልባችን የሚኖረው ፈጣሪ ብቻ ነው ፡ ፈጣሪ ደሞ ብርሃን ነው ፡ እንደ አቢያራሽ ጨለምተኛ እና ሰውም አይደለም ......."ብሎ ሊቀጥል ሲል
"ዝም በል አንተ ልጅ ችግር ውስጥ አትክተተኝ ፡አፍህን ዘግተህ ወደውስጥ ግባ ነገ እንገናኛለን በ"ብላው ፡በስተግራ ካለው የዋሻው ጨለማ ክፍል ውስጥ ገብታ ተሰወረች ፡ መሳይ ቀስ እያለ ወደማደሪያው ለመግባት የዋሻውን ግድግዳ እየታከከ በጨለማው ተጓዘ ፡ የዋሻው ውስጥ ነብሳቶች ሲርርርር ማለት ጀምረዋል ፡ የተለያየ ደምፅ ሲሰማ ልቡ መምታቱን ዛሬም አላቆመም፡ ሊለምደውም አልቻለ ፡ በፍርሃት ፡ እንደተወጠረ ፡ ግድግዳውን እየታከከ ሲሄድ ፡ ለየት ያለ ድምፅ የሰማ መሰለውና ወደዋላው ለመመለስ ቃጣው ፡ እናም ባለበት ቆመ ፡ ድምፁ ደሞ እየቀረበው መጣ ፍርሃቱ ጨመረ ኦርርርር ኡኡኡኡኡ ስስስስስስ ሽሽሽሽሽሽሽ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,


ሙና መሀመድ

ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍21🤔3😢3
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


..ወሩ ጥር ሰዓቱ ማታ ነው ከደጅ ያለው ብርድ ነፍስ ያወጣል ሚስተር ካርላይል እና እህቱ ኢስት ሊን ውስጥ ከምቹ ሳሎን ተቀምጠዋል ቤት ሙስጥ ያለው ሁኔታ ከውጭው የተለየ ነው የሚንቀለቀለው እሳት ብርሃኑ ከሚያምረው ምንጣፍ ላይ ያንጸባርቃል ። ወንበርና ጠረጴዛ የመሳሰሉ የቤት ዕቃዎች እጅግ ባማረና የቀንዲሉ ብርሃን ክፍሉን በሙሉ ቦግ አድርጎታል ይህ ሁሉ
አንድ ቦታ ላይ ሲታይ ቅንጦት ለመባል ባይበቃም የቤት ሰላም ገጽታ አለው ። በደጅ ግን በብዛት የሚወርደው በረዶ አየሩን ጥቅጥቅ አድርጎ ስላ
አጨለመው አንድ ሰው ከአንድ ሜትር የራቀ ማየት አይችልም ሚስተር ካርላይል በድንክ ፈረሶች በሚሳበው ሠረገላው ነው ወደቤት የመጣው " የተጓዘበት መንገድ አጭር ቢሆንም ከላዩ ላይ በረዶ ተቆልሎበት ስለነበር ልጁ ሉሲ ወደ ነጭነት ተለወጠ እያለች ነበር የገባው እየሣቀችበት ነበር የገባው አሁን ሰዓቱ መሽቷል
"ልጆቹ ተኝተዋል " አስተማሪያቸውም ከራሷ ሳሎን ገብታ ተቀምጣለች "
ቤቱ ጸጥ ብሏል ሚስተር ካርላይል አንድ ወርኃዊ መጽሔት በተመስጦ ያነባል
ሚስ ካርላይል ጉሮሮዋ እየታፈነ አፍንጫዋ እየተነፋነፈ ከእሳት ዳር ተቀምጣ ታጉረመርማለች "

ሚስ ካርላይል'ክብራቸውን ለበሽታ ሰጥተው ከማያውቁት ልበ ብርቱ ወይዛዝርት አንዷ ነበረች » በርግጥ ጠበቅ ያለ በሽታ ከያዛት መሸነፏ አይቀርም " በተረፈ ሌላውን ሰው ሁሉ የሚያጠቁት እንደ ራስ ምታት ከባድ ጉንፋንና የጉሮሮ መቁሰል የመሳሰሉ ጥቃቅን ሕመሞች ነክተዋት አያውቁም እንደዚህ ተከብራ የኖረች እመቤት ራስዋን ሲከብዳት ደረቷ ሲቆሳስል ድምጿ ሲዘጋ ባጭሩ በሕይወቷ
ለመጀመሪያ ጊዜ ጉንፋን ሲይዛት ምን ያህል እንደምትረበሽ ለመገመት አያዳግትም "

“ ያ ቢራ ነው”ኮ እንደዚህ ጉድ የሠራኝ ” ስትለው ሚስተር ካርላይል ከሚያነብበት ቀና ብሎ አያት "

“ አዎ ቢራው !” አለች እንደገና ኮስተር ብላ ። አርኪባልድ ... ጨረቃ
ናት ጉንፋን ያሲያዘችኝ ያልኩህ ይመስል እንደዚህ አፍጠህ አትየኛ » "

“ ታድያ አልቦሽ ሳለ በርከት አድርገሽ ባንድ ጊዜ ካልጠጣሽ ቢራ እንዴት
ጉንፋን ሊያስይዝሽ ይችላል ? ”

ዕድሜ ልክህን ሕፃን እንደ ሆንክ መቅረትህ ነው ኮ ... አርኪባልድ ብዙ ቢራ መቸ ጠጥቸ ዐውቃለሁ ? በመጨረሻ የተረፉት ሁለት በርሜሎች ያፈሳሉ መባላቸውን አልስማህም ?

"እናሳ ?

ከሠራተኞች ያገጣጠም ጉድለት መሆኑን ወዲያው ዐወቅሁት ዛሬ ጧት
ከቁርስ በኋላ ከሚሞቁት ክፍሎች ወጥቸ ወደ ቤቱ ራሴ ወርጄ ተመለከትኩ ክፍሉ በራሱ የበረዶ ቤት ይመስል ነበር ኻያ ደቂ ሙሉ ከዚያ ውስጥ ስለ ቆየሁ ጉንፋን ያዘኝ።"

ሚስተር ካርይል አልመለስላትም ፒተር የሚሰራውን የሚያውቅ ስለ
ሆነ በነሱ ሥራ ጣልቃ መግባት አልነረብሽም ቢላት ኖሮ መዓቷን ታወርድበት ነበር » አሁን እሷ ስትጨነቅበት አፍንጫዋን ሲዘጋት ጉሮሮዋን ሲፍቃት ወንበሯን ወደ አሳቱ ስታስጠጋ መልሳ ስታሸሽ እጆችዋን ስታፋትግ እግሮችዋን ስታወራጭ ሚስተር ካርላይል ዝም ብሎ ያነብ ነበር "

“ስንት ሰዓት ሆነ ? ” አለችው

ሚስተር ካርላይል ስዓቱን አይቶ ከምሽቱ ሶስት መሆኑን ነገራት

“ እንግዲያውስ እስከ ዛሬ ይህን የበሽተኞች ምግብ ደኅና ሳልቀምስ የኖርኩትን ያህል አንድ ሣህን ሾርባ ልጠጣና ልተኛ።

"ጥሩ ነው ( ይበጅሽ ይሆናል " አላትና ሚስተር ካርላይል ንባቡን ቀጠለ „
ከዚያ በኋላ አምስት ደቂቃ ያህል ተቀምጣ ወጣች እሱም ማንበቡን ቀጥሎ አንድ ሁለት ጊዜ ከገለበጠ በኋላ መጽሔቱን ከጠረጴዛው ላይ ጥሎ ብድግ ብሎ ተንጠራራ

የሳሎኑን አሳት ቆስቁሶ አቀጣጠለና ከምድጃው ዳር ትንሽ ቆም አለ " ከደጅ
በረዶው መጣሉን አላቆመ እንደሆነ ለማየት ወደ መስኮቱ ሔዶ መጋረጃውን ገለጥ አድርጎ ቢመለከት • ከመጨለሙ የተነሣ ምንም ነገር ማየት አልቻለም " የአየሩን ሁኔታ ማወቅ ስላልቻለ መስኮቱን ከፈተውና አንገቱን ወደውጭ አውጥቶ ተመለከተ"

በረዶው በኃይልና በብዛት ይወርድ ነበር " ሚስተር ካርላይል የአንድ ሰው
እጅ እጁን ሲነካው ፊቱንም ከሌላው ሰው ፊት ጋር እስኪላተም ድረስ ተጠግቶ
ድንገት ድቅን ሲልበት ክው ብሎ ደነገጠ "

“ልግባ ሚስተር ካርላይል ስለ ነፍስ ! ብቻህን መሆንህን አይቻለሁ
ሙቻለሁ ደግሞ ነገሩን አላውቅም ተሸሽጎ ያሳለፈኝ ሰው ያለም መስሎኛል "

የተናገረው ድምፅ የማን መሆኑን ቢያውቅም ለጊዜው የደመ ነፍሱን ወደ ኋላ ሸሸት አለ ። ስውየው ደግሞ ተከተለው " ያን የመሰለ ዱቄት በረዶ እየጣለ ብዙ ሰዓት በእግሩ ተጉዞ ስለ መጣ ባርኔጣው ልብሱ ቅንድቡ የውሸት ሪዙ ሳይቀር ንድፍ ጥጥ የተቆለለበት ይመስል ነበር " ገና እንደ ገባ በሩን እንዲቆልፍለት ጠየቀው
ሚስተር ካርላይል ' መስኮቱን ዘግቶ መጋረጃውን ሳበውና ከውጭ ወደ ሳሎን
የሚያስገባውን ከሳሎን ወደሚቀጥለው ክፍል የሚያሳልፈውን ሁለቱ በሮች
ቆለፈ " ሪቻርድ የደረበውን ልብስ ባርኔጣውንና የውሸት ጢሙን አውልቆ በሮዶውን አራገፈ "

“ ሪቻርድ” አለው ሚስተር ካርላይል “ በጣም አስደነገጥከኝ " ወዲህ በመ
ምጣትህ በጣም ተሳስተሃል

“ አስቸኳይ ማሳሰቢያ ደረሰኝና ” አለ ሪቻርድ ' ከቅዝቃዜው የተነሣ እየተንቀጠቀጠ ' ከለንደን እስከዚህ መንገድ እያሳበርኩ ነው የመጣሁ አሁንም ቢሆን እያሳደዱኝ ነው " ያ የተረገመ ቶርን የላካቸው ፖሊሶች አሁንም ይከተሉኛል

ሚስተር ካርላይል ወደ ቁም ሳጥኑ ምልስ ብሎ አንድ ብርጭቆ ብራንዲ ቀዳለትና
ጠጣ . . . ሪቻርድ ጠጣ ያሞቅሃል " አለው።

‹ ኧረ እኔስ በትኩስ ውሃ ቢሰጠኝ "

“ ትኩስ ወሃ እንዴት አድርጌ ላስመጣልህ እችላለሁ ? በል ይኸን ጠጣው ግን
ምነው እንደዚህ መንቀጥቀጥህ?

“ ጠንካራ የተባለውን ሰው ለማንቀጥቀጥ ኮ በዚያ ቀዝቃዛ በረዶ ውስጥ ጥቂት ሰዓት መቆየት ይበቃል ከአንድ አንድ ቦታማ በረዶው በጣም ተቆልሎ እግር እየዋጠ እንደ ልብ አያስኬድም ። እንደ ቀንድ አውጣ እየተጐተትክ እንድትጓዝ ያስገድድሃል አሁን እንደ መጣሁ የዛሬ ሁለት ሳምንት ዌስት ኤንድ ላይ ካላው የሠረገላ ተራ ሔጄ ካንድ ነጅ ጋር ስነጋገር ዝናብ ማካፋት ጀመረ " በዚህ ጊዜ አንድ መኮንንና አንዲት ወይዘሮ ሲያልፉ እኔ ለራሴ ልብ ብዬ አላስተዋልኳቸውም እሱ ግን ኧረ እኔስ ነገሩ ቀፈፈኝ በሠረገላ ብንሔድ ይሻላል የኔ ፍቅር '' ሲላት ሰማሁት ሳወጋው የነበረው ሠረገላ ነጂ ይህን ሲሰማ በሩን ከፈተላትና ሴትዮይቱ
ገባች መቼም ልጂቱ ስታምር ሌላ ነገር ናት " እኔ ደግሞ እሷን አይቸ ሰውየውን ልብ ብዬ ለማየት ፊቴን ሳዞር ማንን እንዳየሁ ታውቃለህ ? .... ቶርንን " '

“ እውነት ? ”

ያን ጊዜ በጨረቃ ልሳሳት እንደምችል አስበህ ነበር " በቀን ግን ልሳሳት አልችልም " ዐይኔን ሞልቸ ፊቱን ስመለከተው 0መድ ለበሰ እኔም ምናልባት እንደሱ ሁኘ ይሆናል " አልታወቀኝም " "
“ አለባበሱ ጥሩ ነበር ? '
ያለባበሱ ነገርማ ምኑ ይጠየቃል " ከዚያ በኋላ ሠረገላው ሲንቀሳቀስ በስተኋላ ተንጠላጥዩ ተሳፈርኩ ። ነጂው ልጆቹ የገቡ መሰለውና ከነአለንጋው ወደኔ
በኩል ፊቱን ሲመልስ ምልክት ሰጠሁት " ብዙ መንገድ ሳንሔድ አንድ ቦታ ላይ ሠረገላው ገና ሊቆም ሲል ወረድኩና ስመለከተው ጊዜ አሁንም ፊቱ 0መድ እንደመሰለ ነበር የሚኖረው እዚያ ሳይሆን አይቀርም በማለት የገባበትን ቤት ልብ ብዬ አስተዋልኩት ”

“ ለምንድነው ያላስያዝከው
ሪቻርድ ” አለ ሚስተር ካርላይል "
👍12
ሪቻርድ ራሱን ነቀነቀ ስለ ጥፋተኛነቱ የተጨበጠ መረጃ በእጄ ሳልይዝ
እንዴት አድርጌ . . .ሚስተር ካርላይል ? ራሱን ለማዳን ሲል ሲገድል አይቸዋለሁ ብሎ በኔ አዙሮ ሊጠመጥምብኝ ይችላል " እኔ የቶርንን ትክክለኛ ስም የማገኘው ዛሬ ነው
አልኩና ከመሸ በኋላ ወደዚያ ቀን ሲገባበት ወዳየሁት ቤት ሔጀ አንዱን አሽከር አግኝቼ አነጋገርኩት

“ ካፒቴን ቶርን እዚህ ነው የሚኖረው?ስለው' “ እኔ ካፒ
ቱን ቶርን የሚባል ሰው አላውቅም "ይህ የሚስተር
ዌስተርቢ መኖሪያ ነው አለኝ "እኔም እንግዲያውስ ትክክኛ ስሙ ይኸው ነው ብዬ አሰብኩና ቆንጆ ሚስት አለችው አለባበሷ ጥሩ የሆነ ልጅ እግር ” አልኩት "አንተ ልጅ እግር
የምትለውን አላውቅም የኔ ጌታ ስልሳ ዓመት ይሆናቸዋል " ሚስቲቱም ከሳቸው አያንሱም ” ሲለኝ መልሼ ደነገጥኩ ። ምናልባት ልጆች እንዳሉዋቸው? ብለው
ከሁለቱ በቀር ማንም እንደሌላቸው አረጋገጠልኝ " እኔም የዚያኑ ለት ቀን አንድ
ወጣት መኮንን ከነሚስቱ በኪራይ ሠረገላ መጥተው ከዚያ ቤት ሲገቡ ማየቴን ገልጬ የሰውየውን ስም ለማወቅ መፈለጌን ነገርኩት " ጌታው ከብዙ ጊዜ ሕመም በኋላ ያን ለት ገና መነሣቱ ስለነበር ብዙ ጠያቂ ሲመላለስ በመዋሉ የመጡትን ሁሉ ለይቶ ማወቅ እንደማይችል ነገረኝ

ይኸው ብቻ ነው ሪቻርድ ? ''

ይኸው ብቻ! ለኔማ በሆነል እንዴት ጥሩ ነበር ? ከዚያ በየደኅናው መንገድ ስፈልገው...."

ግን ይህ ሰው አንተ ባየኸው ሁኔታ ሎንደን የሚኖር ከሆነ ለምን አይተኸው እንደማታውቅው


ሪቻርድ ራሱን ነቀነቀ ስለ ጥፋተኛነቱ የተጨበጠ መረጃ በእጄ ሳልይዝ
እንዴት አድርጌ . . .ሚስተር ካርላይል ? ራሱን ለማዳን ሲል ሲገድል አይቸዋለሁ ብሎ በኔ አዙሮ ሊጠመጥምብኝ ይችላል " እኔ የቶርንን ትክክለኛ ስም የማገኘው ዛሬ ነው
አልኩና ከመሸ በኋላ ወደዚያ ቀን ሲገባበት ወዳየሁት ቤት ሔጀ አንዱን አሽከር አግኝቼ አነጋገርኩት

“ ካፒቴን ቶርን እዚህ ነው የሚኖረው?ስለው' “ እኔ ካፒ
ቱን ቶርን የሚባል ሰው አላውቅም "ይህ የሚስተር
ዌስተርቢ መኖሪያ ነው ' አለኝ "እኔም እንግዲያውስ ትክክኛ ስሙ ይኸው ነው ብዬ አሰብኩና ቆንጆ ሚስት አለችው አለባበሷ ጥሩ የሆነ ልጅ እግር ” አልኩት "አንተ ልጅ እግር
የምትለውን አላውቅም የኔ ጌታ ስልሳ ዓመት ይሆናቸዋል " ሚስቲቱም ከሳቸው አያንሱም ” ሲለኝ መልሼ ደነገጥኩ ። ምናልባት ልጆች እንዳሉዋቸው? ብለው
ከሁለቱ በቀር ማንም እንደሌላቸው አረጋገጠልኝ " እኔም የዚያኑ ለት ቀን አንድ
ወጣት መኮንን ከነሚስቱ በኪራይ ሠረገላ መጥተው ከዚያ ቤት ሲገቡ ማየቴን ገልጬ የሰውየውን ስም ለማወቅ መፈለጌን ነገርኩት " ጌታው ከብዙ ጊዜ ሕመም በኋላ ያን ለት ገና መነሣቱ ስለነበር ብዙ ጠያቂ ሲመላለስ በመዋሉ የመጡትን ሁሉ ለይቶ ማወቅ እንደማይችል ነገረኝ

ይኸው ብቻ ነው ሪቻርድ ? ''

ይኸው ብቻ! ለኔማ በሆነል እንዴት ጥሩ ነበር ? ከዚያ በየደኅናው መንገድ ስፈልገው...."

ግን ይህ ሰው አንተ ባየኸው ሁኔታ ሎንደን የሚኖር ከሆነ ለምን አይተኸው እንደማታውቅ ስታስበው ምን ተሰማህ?
አለው ጅምር ንግግሩን ከቋርጦ።

ምናልባት ዌስት ሊን ሳለሁ የሚያውቀኝ ሰው እንዳያገኘኝ ባልባሌ
ቦታዎችና በፈረስ ጋሬጣዎች ካልሆነ በቀር ወደ ጎዳና መንገዶች ስለማልዘልቅ ለምን
አይቸው አላውቅም ብዬ አልተደነቅሁበትም ።

“አሁን ደግሞ፡በዚያው ሳምንት ውስጥ እንደገና አገኘሁት ። ማታ ነበር ።
እሱ ከአንድ ቲያትር ቤት ሲወጣ አየሁትና ከፊቱ ሔጄ ቆምኩ ። ስውዬ ምን ትፈልጋለህ ? ከዚህ በፊትም ስትከታተለኝ አይቸሃለሁ አለኝ ። እኔም ለጊዜው ስምህን ለማወቅ ነው የምጸልገው ስለው እብድ ሆነብኝ ሁለተኛ ከአጠገቡ ቢያየኝ
በፖሊስ እንደሚያስይዘኝ ዛተብኝ። ልብ በል አለኝ ሰዎች በፖሊስ የሚያስይዙት
ሌሎችን ስለ ተመለከተ አይደለም ። አንተን ዐወቅሃለሁ ስለዚህ ለራስህ ደኅንት የምታስብ ከሆነ እኔ በምሔድበት ዞር እንዳትል ብሎኝ ከአንድ የግል ሠረገላ ተሳፈረና ሔደ”

“መቸ ነው አልከኝ እንዲህ የሆነው ?

“ የዛሬ ሳምንት ! አንድ ጊዜ ካየሁት በኋላ ስሙን ለማወቅ ብዙ ለፋሁ ።በየ
ቦታው ዞርኩ ። አሁንም አንድ ቀን አገኘሁት " ከአንድ ሌላ ሰው እጅ ለእጅ ተያይዞ በፍጥነት ይራመድ ነበር ። ከዚያም በኋላ አንድ ቦታ ላይ ከዚያው ሰው ጋር ቁሞ
ሲያወራ አገኘሁት። የዚያን ጊዜ ሲያየኝ ፡ ፍራትና ቁጣ የተደባለቀበት ይመስል ነበር። አንበሳ ሆነብኝ ትንሽ አመነታና አንድ ፖሊስ ወደሱ ጠርቶ በእጁ ወደኔ እያመለከተ አንድ ነገር ነገረው ። በዚህ ጊዜ እኔም ፈራሁ ። ከሁለት ሰዓት በኋላ ከሌላ ቦታ
ሔጄ ዞር ብዬ ወደኋላየ ባይ ፖሊስ ሲከተለኝ አየሁ። ሠረገላ እየሳቡ በሚያልፉ ፈረሶች ሥር ተወርውሬ አለፍኩና ባቋራጭ በአልባሌ መንገዶች እየተሽሎከለክሁ
ትንሽ እንዴ ሔድኩ አንድ ሠረገላ አገኘሁ " ከጐኑ አስቀምጦኝ በዶኅና ከሰፈሬ ደረስኩ ብዬ ሳስብ ወደቤቴ ከመግባቴ በፊት አሁንም ዞር ብዬ ወደ መንገድ ተመለከትኩ " አሁንም ሰውዬው ተከትሎኝ መጥቶ የኔን መኖሪያ ሲያጠና የነበረ መሰለኝ ከሩቅ ሆኖ ሲመለከት አየሁት ከቤት ስመጣ እርቦኝ የነበረውን ይህን ሁኔታ ላይ ዘጋኝ " ማሳሳቻ ልብሴን ከሳጥን ኣውጥቼ ለባበስኩና በጓሮ በር ወጥቸ ሔድኩ ዐልፎ ዐልፎ ብቻ አንዳንድ ሠረገላዎች ትንሽ መንገድ ሲረዱኝ በቀር አብዛኛውን
መንገድ የመጣሁት በእግሬ ነው።

“ ግን ሪቻርድ
ልትሸሸግባቸው ከምትችል ቦታዎች ሁሉ ዌስት ሊን
የከፋ መሆኑን ታውቃለህ ? '' ከዚህ ቀደም አራሽ መስለህ ከዚህ መምጣትህን አገር
ሰምቶታል።

“ ይኸን ደግሞ ማን ነገረብኝ ? ”

“ ማን እንዳወጣው እኔም አላወቅሁም ነገር ግን ወሬው ይፋ ሆኖ ስለ ነበር
ካባትሀ ጆሮ ሳይቀር ደርሷል አሁን ሰው በዚህ ወሬ ተቀስቅሶ የማሳሳቻ ልብስህን እነደለበስክ ሊያይህ በመጓጓት ነቅቶ ይጠብቅህ ይሆናል ።”

“ ታዲያ ምን አባቴ ልሁን ? ወደዚህ እንድመጣ ያስገደደኝ ዋነኛው ምክንያትም የገንዘብ ችግር ነው ከለንደን ለቅቄ ራቅ ወዳለ ትልቅ ከተማ ማለት ወደ ሊቨርፑል ወይም ወደ ማንቸስተር ሒጄ ሥራ እፈልግ ነበር ግን በእጄ ምንም ገንዘብ የለኝም " የመጨረሻዎቹን ሳንቲሞቼን ዛሬ ዳቦ አይብና አንድ ብርጭቆ ቢራ ገዛሁበት ከዚህ መስኮት ውጭ ከአንድ ሰዓት በላይ ቆምኩ

“ገና ዌስት ሊን ልገባ ስቃረብ ምን እንደማደርግ ማሰብ ጀመርኩ " በዚህ
ጨለማ ወደ 0ጽዱ ሔጄ ባርባራን በምልክት መጥራት ከንቱ መሆኑን ተረዳሁ ግን ዘብ ከፍዬ እንዳላድር ባዶ እጄን ሆንኩ ስለዚህ አንተን ባገኝህ ብዬ ወደዚህ መጣሁ መስኮቱ በደንብ ስለ አልተዘጋ ተለጥፌ ስመለከት ቆየሁ " ሚስ ካርላይል ወጥታ ስትሔድ አየኋት " ከዚያ ደግሞ አንተም ተነሣና መስኮቱን ከፈትከው "ያኔ
ተናገርኩ " እንግዲህ ሚስተር ካርላይል . . . . . የኔ ኑሮ እስከ መጨረሻው ይኸው መሆኑ ነው።

“ ያንተ ነገር በጣም እያሳዘነኝ ነው . . . . . ሪቻርድ ከዚህ ሥቃይ ላወጣህ ብችል በጣም ደስ ይለኝ ነበር "

ሌላ ቃል ከመናሩ በፊት መዝጊያው ለመከፈት ከተሞከረ በኋላ በቀስታ ተንኳኳ ሪቻርድ በጣም ፈራና የሚሆነውን አጣ "

"ረጋ በል አይዞህ አትሸበር
ከዚህ ማንም አይገባም አሁን ፒተር ነው ሊከፍት የሞከረው ” አለው " ነገር ግን ወዲያው "ማነው” ሲል ጆይስ መሆኗ ዐወቀ "

“ ሚስ ኮርኒሊያ ' መሐረብ ከሱ ስለረሱ እንዳመጣላቸው ልከውኝ ነው? ” አለችው።
👍103
አሁን ሥራ ስለ ያዝኩ መግባት አትችይም ” አላት በማያዳግም ድምፅ "
“ ማናት ? ” አለ ሪቻርድ አሁንም እየተንቀጠቀጠ "
ጆይስ ናት"
“ እስከ ዛሬ እዚህ አለች ? ለመሆኑ ያቺ አፊ ወሬዋ ተሰምቶ ያቃል?”

“የዛሬ ሦስት ወር ገደማ መሰለኝ እዚህ መጥታ ነበር እንደሷ አባባል ቶርን
አብሯት ስለ ነበረ ከግድያው የለበትም አንተም በዐይንህ እስካላየህ ድረስ የሷን አባባል ልታስተባብል አትችልም "

“መጀመሪያ እሱ ከነገሩ ንጹሕ ከሆነ ልቡ እስኪጠፋ አይሮጥም እንደዚያም ሆኖ አይደነግጥም ሁለተኛ ደግሞ ነገር ከሌለበት እኔን ምን አድርግ ብሎ ነው የሚያሳድደኝ? ለምንስ ባየኝ ቁጥር እንደዚያ እየሆነ ይደነግጣል ደግሞስ ይኸስ ይቅርና በግድያው ጊዜ ከቤቱ በስተጀርባ ከነበረው ጫካ ውስጥ ብቻዋን እንደ ነበረችና ስለ ግድያውም በወቅቱ ምንም እንዳላወቀች ምላ መስክራ የለ? ከሱ ከነበረች ለምን ብቻዬን ነበርኩ ብላ ምላ መስከረች ዛሬ ለአፊ የነበረኝ የጋለ ስሜት በርዷል እንከኖቿን ሁሉ ማየት ችያለሁ ...ሚስተር ካርላይል " በሙሸቷ እንኳ አትፀናም እሷ።

የነበሩበት ክፍል መዝጊያው ቤቱን ሊያፈርስ የሚችል በመሰለ ' እንደ ነጎድጎድ
በሚጮህ ድምፅ ተንኳኳ ወንጀለኛን አስሰሙ እንዲያመጡ ሕጋዊ ትእዛዝ
የያዙ የሕግ አስከባሪዎች እንኳን ከዚህ የበለጠ አስደንጋጭ ድምፅ አሰሙ ተብለው አያውቁም " ሪቻርድ ሔር ፊቱ ባንድ ጊዜ ዐመድ መሰለ » ዐይኖቹ ተጎለጎሉ......

💫ይቀጥላል💫
👍155👏3
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


...ይህንን ማሰቡ በራሱ አንቀጠቀጣት፡፡ ወደ ክፍሏ ተመለሰችና ራሷን አረጋግታ ለአባቷ የምትለውን ነገር አሰላሰለች፡፡ ረጋ ማለት አለባት፡፡ እምባ እንደማያሳዝናቸውና ቁጣ ለስድብ እንደሚጋብዛቸው ታውቃለች፡፡ ምራቁን እንደዋጠ ሰው ነው መናገር ያለባት፡፡ ተጨቃጫቂ ከሆነች ቁጣቸውን ይቀሰቅስባቸውና ፍርሃት ተሰምቷት ያሰበችውን ከመናገር ልትታቀብ ትችላለች፡.
እንዴት ብላ ትጀምር? ስለ ወደፊቱ አንድ ነገር ለመናገር መብት
አለኝ?.ትበል።

አይደለም ይሄ ጥሩ አይደለም፡፡ ለአንቺ ህይወት ሀላፊው እኔ ነኝ፧ እኔ ነኝ መወሰን ያለብኝ ይሏታል፡

ምናልባትም ስለአሜሪካ ጉዞ ላናግርህ› ብትል ይሻል ይሆን?

‹ምንም የምንነጋገረው የለም› ይሏት ይሆናል፡

አጀማመሯ ተቃውሞ የማይቀሰቅስ መሆን አለበት፡፡

‹አንድ ነገር ልጠይቅህ› ልትላቸው ወሰነች፡፡ ለዚህም እሺ› ይሏታል፡ ከዚያ በኋላስ? ቁጣቸውን ሳትቀሰቅስ እቅዷ ጋ እንዴት ትጠጋ፡፡ባለፈው ጦርነት የጦር ሰራዊቱ ውስጥ ነበርክ ትበላቸው ይሆን? ፈረንሳይ ውስጥ መዋጋታቸውን ታውቃለች፡፡ እናታችንስ ነበረችበት?› ትበል ይሆን?እናታቸው የቆሰሉ የአሜሪካ ወታደሮችን በፈቃደኝነት ለማከም ለንደን ውስጥ
አገራዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ሁለታችሁም ሀገራችሁን አገልግላችኋል፧ መቼም እኔም ይህን ለማድረግ እንደምፈልግ ልትረዱት ይገባል፣› ማለት ሊኖርባት ነው።

ይህን የአገር ማገልገልን መርህ የሚቀበሉ ቢሆን እንኳን ሌላ ተቃውሟቸውን ሊቀሰቅስ የሚችለውንም ነገር አሰበች፡፡ ጦር ሰራዊቱን እስክትቀላቀል ዘመድ ጋ መቆየት ትችላለች፡ ይህም ለተወሰኑ ቀናት ነው፡፡አሁን አስራ ዘጠኝ አመቷ ነው፡ በዚህ እድሜ ላይ ያሉ ሴት ወጣቶች በቀን
ስድስት ሰዓት ይሰራሉ፡፡ መኪና ለመንዳት፣ ለትዳርም ሆነ ወህኒ ለመውረድ
እድሜዋ ይፈቅድላታል፡ እንግሊዝ ውስጥ እንዳትቆይ የማይፈቅዱበት
ምንም ምክንያት የለም፡

አሁን ያሰበችው ነገር ትክክል እንደሆነ ገመተች። የሚያስፈልጋት ድፍረት ብቻ ነው፡

አባቷ ከንግድ ድርጅታቸው ኃላፊ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ ማርጋሬት ከክፍሏ ወጣች፡ ደረጃውን ስትወርድ በፍርሃት እግሮቿ ራዱ፡፡
አባቷ ለሚቃወማቸው ንዴታቸው የከረረ ሲሆን ቅጣታቸውም የከፋ
ነው፡፡ በሰባት አመቷ አልጋ ላይ በመሽናቷ አሻንጉሊቷን ተነጥቃለች፡፡የአስራ አንድ አመት ልጅ ሳለች አንድ እንግዳ አንጓጣ ቀኑን ሙሉ ፊቷን ወደ ግድግዳ አዙራ እንድትቆይ አድርገዋታል፡ አንድ ጊዜ ተናደው ድመቷን
ከፎቅ በመስኮት ወርውረውባታል፡
አሁን እንግሊዝ ውስጥ
እንደምትቀርና ናዚዎችን እንደምትዋጋ ለአባቷ ብትናገር ምን ያደርጋሉ?

ደረጃውን በፍጥነት ወረደች፤ ነገር ግን የንባብ ክፍላቸው ጋ ስትደርስ
ፍርሃት ዋጣት፡፡ ሲናደዱ፣ ፊታቸው ሲቀላና አይናቸው ሲጎለጎል ታያት፤ጉልበቶቿ ተብረከረኩ፡፡ ራሷን ለማረጋጋት ሞከረች፡፡
አባቷ ያሉበት ክፍል በር ላይ ስትደርስ ቤት ጠባቂዋ ሚስስ አለን አዳራሹን አቋርጣ መጣች፡ ሚስስ አለን የቤት ሰራተኞች አለቃ ስትሆ በስሯ ያሉትን ሰራተኞች አሽቆጥቁጣ ነው የምታስተዳድረው፡፡ ቤተሰቡን በሙሉ ስለምትወድ አገር ለቀው መሄዳቸው በጣም አሳዝኗታል“ የእንጀራ ገመድ ተበጠሰ ማለት ነው፡፡ ለማርጋሬት ያሳየችው ፈገግታ በእምባ የታጀበ ነበር፡፡

ማርጋሬትም ሚስስ አለንን ስታይ ልቧ ተነካ፡፡ ወዲያውኑም የመጥፋት
ዕቅዷ በአዕምሮዋ ውስጥ ቅርፅ እየያዘ መጣ፡፡ ከሚስስ አለን ገንዘብ ትበደርና ቤቱን አሁኑኑ ለቃ የአስር ሰዓት ከሃምሳ ደቂቃውን ባቡር ተሳፍራ ወደ ለንደን ትሄዳለች፧ በአክስቷ በካትሪን ቤት ሌሊቱን ታሳልፍና በጧት የምድር ጦር መምሪያን ትቀላቀላለች፡፡ አባቷ ሲደርሱ እሷ ሰራዊቱን ስለምትቀላቀል ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡
‹እቅዱ በጣም አደገኛና ድፍረት የሚጠይቅ በመሆኑ ሊሳካ አይችልም ብላ ሃሳቧን ከመለወጧ በፊት ‹‹ኦ ሚስስ አለን ትንሽ ገንዘብ ትስጪኛለሽ?
አንድ ነገር ገበያ ሄጄ ልገዛ አስቤ ነበር፤ አባባን ደግሞ መረበሽ አልፈለኩም በስራ ተጠምዷል፣›› አለቻት፡

ሚስስ አለን ሳታመነታ ‹‹እሺ እመቤቴ ምን ያህል ነው የሚፈልጉት? ማርጋሬት ወደ ለንደን ለመጓዝ የባቡሩን ዋጋ አታውቀውም፡፡ ትኬት
ገዝታ አታውቅም፡፡

እንዲያው በግምት ‹‹አንድ ፓውንድ ይበቃኛል›› አለቸ
ወዲያው በሃሳቧ ላደርገው ነው?› አለች፡፡
ሚስስ አለን ከቦርሳዋ ውስጥ ሁለት የአስር ሽልንግ ኖቶት አወጣች
ብትጠይቃት ዕድሜዋን ሙሉ ያጠራቀመችውን ገንዘብ ትሰጣት ነበር፡
ማርጋሬት ገንዘቡን እየተንቀጠቀጠች ተቀበለች፡፡ ይሄ የነፃነቴ ትኬት ይሆን ይሆናል› ስትል አሰበች፡፡ ፍርሃት ልቧን ቢያርደውም እንደ እሳ
የሚንቀለቀል ተስፋ ልቧ ውስጥ ተጫረ፡፡

ሚስስ አለን አገር ለቀው መሄዳቸው አሳዝኗት የማርጋሬትን እጅ
ጭምቅ አደረገች፡፡
‹‹ክፉ ቀን ነው የመጣብን እመቤት ማርጋሬት ለሁላችንም›› አለችና
ሽበት የወረረውን ጭንቅላቷን በሃዘን እየወዘወዘች ወደ ማድቤቷ ሮጠች።

ማርጋሬት በመረበሽ ዙሪያውን ቃኘች፤ አንድም ሰው አይታይም፡፡ ልቧ
ይደልቃል፧ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል፡፡ከተጠራጠረች እቅዷ አፈር ድሜ መብላቱ ነው፡፡ ኮቷን ለመልበስ ጊዜ ሳታጠፋ ገንዘቧን በእጇ ጨብጣ በፊት ለፊቱ በር ወጥታ ሄደች፡፡

የባቡር ጣቢያው ከቤታቸው ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ይርቃል፡፡በመንገድ ላይ የአባቷ ሮልስ ሮይስ መኪና ከኋላ የሚመጣ እየመሰላት
ትደነብራለች፡፡ ምን እንዳደረገች እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ? መጥፋቷ ቢያንስ ከራት ሰዓት በፊት ሊታወቅ አይችልም፡፡ ሚስስ አለን ገበያ መሄዷን ትነግራቸዋለች፡፡

ባቡር ጣቢያ ቶሎ ደረሰች ቲኬት ገዝታ ብዙ ገንዘብ ተርፏታል፡ የሴቶች መቆያ ክፍል ገብታ የግርግዳ ሰዓቱን አየች፡
ባቡሩ ዘግይቷል፡
አስር ሰዓት ከሃምሳ አምስት ሆነ ከዚያም አስራ አንድ እያለ አስራ አንድ ከአምስት ሆነ፡ በዚህ ጊዜ ማርጋሬት ከመፍራቷ የተነሳ እቅዷን ሰርዛ ወደ ቤቷ በመመለስ ጭንቀቷን ማስወገድ እንደሚሻል ተሰማት፡፡

ባቡሩ አስራ አንድ ሰዓት ከአስራ አራት ደቂቃ ላይ መጣ፡፡ አባቷ በአካባቢው አይታዩም፡፡

ማርጋሬት ልቧ በጉሮሮዋ ተወትፎ ባቡር ላይ ተሳፈረችና መስኮቱ ጋ
ቆማ ‹አባቴ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ መጥቶ ይወስደኛል› ስትል ተጨነቀች፡፡

በመጨረሻም ባቡሩ ተንቀሳቀሰ፡፡

ማምለጧን ማመን አቃታት፡፡
ባቡሩ ፍጥነቱን ሲጨምር የመጀመሪያው የደስታ ፍንጣቂ በልቧ ተጫረ፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባቡሩ ጣቢያውን ለቆ ተጓዘ፡፡ ማርጋሬት
መንደሩ ወደ ኋላ ሲጓዝ ስትመለከት ልቧ በድል አድራጊነት ሲግል
ተሰማት፤ አደረገችው፤ አመለጠች፡፡

ወዲያው ጉልበቷ በድካም ተብረከረከ፡፡ መቀመጫ
ዙሪያውን ሲማትር ባቡሩ ሙሉ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ተገነዘበች፡:ሁሉም ወንበሮች ተይዘዋል፤ አንደኛ ማዕረግም ቢሆን፡፡
ወለሉ ላይም የተቀመጡ ወታደሮች ነበሩ፡፡ እሷ ግን እንደቆመች ቀረች፡ ጉዞዋ ቅዠት ቢመስልም በልቧ የሚሰማት ደስታ አልቀነሰም፡፡

በየጣቢያው ባቡሩ ውስጥ ሰዎች ይጠቀጠቃሉ፡ ሪዲንግ ከተማ ላይ
ባቡሩ ሶስት ሰዓት ተገተረና አረፈው፡፡
👍21👎2
ከአየር ቦምብ ዱብዳ ለመዳን ሲባል መብራት እንዳይበራ በመከልከሉ
የባቡሩ አምፑሎች ተነቅለዋል፡ በመሆኑም አንዳንድ ጊዜ የጥበቃ አባሉ
ህዝብ በተቀመጠበትና በተጋደመበት ወለል ላይ ሲያልፍና ሲያገድም
ባትሪውን ከሚያበራው በስተቀር ምሽቱን በፍፁም ጭለማ ነበር የሚጓዙት፡፡
ማርጋሬት ይሄ ምንም አይደለም› በማለት ራሷን አሳመነች፡ ቀሚሷ
በመረጋገጡና ወለሉ ላይ በመቀመጧ ቢቆሽሽም ነገ ወታደራዊ ዩኒፎርም
ትለብሳለች፡፡ አገሪቱ ጦርነት ላይ ነች፡፡

ማርጋሬት አባቷ መጥፋቷን አውቀው ባቡር ተሳፍራ ይሆናል ብለው
በመገመት ከለንደን በከፍተኛ ፍጥነት በመብረር ፓዲንግተን ጣቢያ ላይ
ያቆሙኝ ይሆን? ብላ ገመተች፡፡ የመሆን ዕድሉ ጠባብ ቢሆንም ባቡሩ
ጣቢያው ላይ ሲደርስ ልቧ በሀይል ደለቀ፡፡
ከባቡሩ ስትወርድ አባቷ አሁንም በጣቢያው አይታዩም ሌላ ድል ተሰማት፡ እሳቸው ሁሉን ማድረግ የሚችሉ አምላክ አይደሉም::

ድንግዝግዝ ባለው ጣቢያ ታክሲ አገኘች፡፡ ታክሲው የጎን መብራቱ ብቻ አብርቶ ወደ ባይስ ዎተር ወሰዳት፡፡ ታክሲ ነጂው ካትሪን የምትኖርበት ህንፃ ጋር ሲደርስ ባትሪውን አብርቶ
ወደ ህንፃው መራት።

የህንፃው መስኮቶች በሙሉ መብራት አይታይባቸውም፡፡ ኮሪደሩ ውስጥ ንግንባር መብራት በርቷል፡፡ ጥበቃው ስራውን ጨርሶ ወደ ቤቱ ሄዷል፡ እኩለ ለሊት ሊሆን
ምንም አልቀረው ማርጋሬት
የካትሪን አፓርታማ
የሚገኝበትን ታውቃለች፡ ደውሉን ተጫነች፡፡

ምንም መልስ የለም፡፡

ልቧ ስንጥቅ አለ፡፡

እንደገና ደውሉን ተጫነች ሆኖም ዋጋ እንደሌለው ተረዳች የአፓርታማው የደወል ድምፅ ጆሮ ይሰነጥቃል፡፡ ስለዚህ ካትሪን የለችም

ካትሪን የምትኖረው ኬንት ውስጥ ከወላጆቿ ጋር ነው: ይህ አፓርታማ የምትጠቀመው አንዳንዴ መዝናናት ሲያምራት ለማረፊያነ ነው:: የለንደን ማህበራዊ ህይወት ቆሟል እየላላ በመምጣቱ ካትሪን እዚ የምትቆይበት ምንም ምክንያት አልታይሽ ብሏት ይሆናል፡ ማርጋሬት
አስቀድማ ይህን አላሰበችበትም ነበር፡፡
ሀዘን ተሰማት፣ ከካትሪን ጋር ቁጭ ብላ ኮኮዋ እየጠጡ የሰራችውን ጅብድ ልታካፍላት ጓጉታ ነበር፡
ቀጥሎ የምታደርገውን አሰበች፡፡ ለንደን ውስጥ ብዙ ዘመዶች አሏት።
ነገር ግን እነሱ ጋር ብትሄድ አባቷ ጋ ስልክ ከመደወል ወደኋላ አይሉም
ካትሪን ግን የእሷ አጋር ትሆን ነበር፡፡ ሌሎቹን ዘመዶቿን አታምናቸውም:
ሌላም ነገር አስታወሰች፡ አክስቷ ማርታ፡ ወዲያው ስልክ እንደሌላቸው
ትዝ አላት አክስቷ በትንሹ በትልቁ የሚቆጡ የሰባ አመት ቆሞ ቀር ባልቴት ናቸው፡ የሚኖሩት ማርጋሬት አሁን ካለችበት አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ርቀው ነው፡፡ ይኼኔ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ላይ ይሆናሉ፡፡ እናም
ቢቀሰቀሱ ይናደዳሉ፡፡

ማርጋሬት ተመልሳ ደረጃውን ወርዳ መንገድ ላይ ስትወጣ ድቅድቅ ያለ
ጨለማ ገጠማት፡፡

ጨለማው ያስፈራል፡፡ ዓይኗን በልጥጣ ዙሪያውን ተመለከተች ነገር
ግን ዓይን ቢወጉ አይታይም፡ ሆዷ ታወከ፤ የመደንዘዝ ስሜትም ተሰማት፡፡

አሁንም አይኗን ገለጠች ነገር ግን ምንም አይታያትም፡፡
ጨለማው አንጎል ያደርጋል፡ ራሷን አረጋጋችና ወደ አክስቷ ቤት የሚወስደውን መንገድ በዓይነ ህሊናዋ ቃኘች፡
የምስራቅን አቅጣጫ ይዤ እሄድና በሁለተኛው መጠምዘዣ መንገድ
ላይ በግራ በኩል እሄዳለሁ የአክስቴ ቤት እመጨረሻው ህንፃ ላይ ነው በጨለማም ቢሆን ቀላል ነው አለች በሆዷ

አንዳች ከዚህ ማጥ የሚያወጣ ነገር ተመኘች መብራት የሚያበራ
ታክሲ፣ሙሉ ጨረቃ ወይም ፖሊስ፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ፀሎቷ ተሰማላት፡፡
አንዲት በጥቅጥቅ
መኪና ጭለማ ውስጥ አይኗን እንደምታቁለጨልጭ ድመት የጎን መብራቷን ጭልጭል እያደረገች በዝግታ መጣች፣ በዚህ ጊዜ እስከ መንገዱ መጠምዘዣ ድረስ የመንገዱን ጠርዝ
ማየት ቻለች።

መራመድ ጀመረች፡፡

መኪናዋ ቀይ መብራቷን በርቀት እያብለጨለጨች ከአይን ተሰወረች፡፡
ማርጋሬት መጠምዘዣው ጋር ለመድረስ ሶስት ወይም አራት እርምጃ
እንደቀራት የመንገዱ ጠርዝ አደናቀፋት፡፡ መንገዱን አቋረጠችና እግረኛ
መንገዱ ላይ ያለምንም ችግር ወጣች፡፡ ይህም ድፍረቷን ጨመረላትና
ያለስጋት መራመድ ቀጠለች፡፡

ድንገት ፊቷን የገጫት ነገር ከፍተኛ ህመም ለቀቀባት፡፡

በስቃይና በፍርሃት አንዴ ጩኸቷን አስነካችው፡፡ በመሸበሯ ሩጭ ሩጭ
አላት፡፡

እራሷን እንደምንም አረጋጋችና ህመሙ የሚሰማትን ጉንጯን መዳበስ ጀመረች፡፡

‹መንገዱ መሐል የሰው ቁመት ያለው ምን ነገር ነው ፊቷን የመታት?› በሁለቱም እጆቿ የመታትን ነገር ደባበሰች፡፡ አንድ ነገር በእጆቿ ነካችና በድንጋጤ እጇን ሰበሰበች፡፡ ጥርሷ በፍርሃት እየተንቀጫቀጨ እንደገና እጇን ሰደደች፡ አንድ የሚቀዘቅዝ፣ ጠንካራና ክብ የሆነ ነገር ነካች፡ እጇን በደንብ ዘርግታ ደባበሰች ፊቷ ላይ ህመም ቢሰማትም ምን እንደሆነ
ስታውቅ ከት ብላ ሳቀች፡፡ ፊቷን የገጫት የመንገድ ዳር ፖስታ መክተቻ
ሳጥን ነው፡፡

ዙሪያውን ዞረችና እጆቿን ዘርግታ ርምጃዋን ቀጠለች፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ሌላ የመንገድ ጠርዝ አደናቀፋት፡፡ ሚዛኗን
እንደምንም መጠበቅ ስትችል ልቧ ምልስ አለ፡፡ የአክስቷ ቤት ያለበት
መንገድ ላይ ደረሰችና ወደ ግራ ታጠፈች::

አክስቷ የበሩን የደወል ድምፅ ይሰሙ ይሆናል ብላ ገምታለች፡፡ብቻቸውን ስለሚኖሩ ካለሳቸው በር የሚከፍት የለም፡፡ ካልሰሙ ግን ወደ ካትሪን ቤት ተመልሳ ትሄድና ኮሪደሩ ውስጥ ትተኛለች፡፡ መቼም ወለሉ ላይ መተኛቱን ትችለዋለች፡፡ ነገር ግን እንደገና ጨለማ ውስጥ መግባት ፈራች፡፡

ምናልባትም አክስቷ በር ላይ ጥቅልል ብላ ተኝታ እስኪነጋ መጠበቁ ሳይሻል
አይቀርም፡ የአክስቷ ቤት በህንፃው ዳር ነው የሚገኘው፡ ማርጋሬት ቀስ
እያለች ተራመደች።

መንገዱ ፀጥ ያለ ቢሆንም በአካባቢው ከየቦታው የሚያፈተልክ ድምፅ
ይሰማል፡ ከርቀት የመኪና ድምፅ አልፎ አልፎ
ይሰማል። ውሾች በበራቸው ስታልፍ ይጮሃሉ፤ ድመቶችም ስትቀርባቸው እንዲሁ፡ የጭፈራ ቤት ሙዚቃና የሰዎች ጭቅጭቅ ከሩቅ ይሰማታል፡ መብራት፣ ለብርዱ የምድጃ እሳት፣ ለቆፈኑ ደግሞ የጀበና ሻይ ፈለገች፡፡

ህንፃው ካሰበችው በላይ ወደ ጎን ረዘመባት፡፡ መንገድ የሳተች አልመሰላትም፡ በሁለተኛው ማቋረጫ ወደ ግራ ታጥፋለች፡ ሰዓቱ ስንት
እንደሆነ አታውቅም፡
በአካባቢው ቤቶች ይኑሩ አይኑሩ እርግጠኛ
አልሆነችም: ምናልባትም መናፈሻ ውስጥ ገብታ እየተደናበረች ይሆናል፡

ማሰብ ጀመረች፡ የት ጋ ነው የተሳሳተችው? በአሁኑ ጊዜ ተሳስታ ከአንድ ኪ.ሜ በላይ ሳትሄድ አትቀርም::

ባቡሩ ላይ የተሰማትን የድል አድራጊነት የደስታ ስሜት ለማስታወስ ሞከረች: አሁን ግን ያ ሁሉ የለም፡ አሁን ብቸኝነትና ፍርሃት ነግሶባታል። ጉዞዋን አቁማ መገተር አለብኝ ብላ ወሰነች፡ በዚህ አይነት ምንም ጉዳት አይደርስባትም
እንደቆመች ረጅም ጊዜ ቆየች፡ አሁንም ቢሆን መንቀሳቀሱን ፈራች:
ፍርሃት ጠፍንጓታል፡ እስከምትወድቅ ወይም እስከሚነጋ ድረስ እቆማለሁ
ስትል አሰበች፡

ከዚያም መኪና መጣ፡፡

የመኪናዋ የጎን መብራቶች ትንሽ ብርሃን ሲፈነጥቁ ቀድሞ ከነበረው ድቅድቅ ጨለማ ጋር ሲነጻጸር ጸሃይ የወጣ ያህል መሰለ፡፡ የመኪና መብራቱ መንገዱ መሐል መሆኗን ስላሳወቃት ሮጣ መንገዱ ዳር ወጣች፡ አንድ የምታውቀው አደባባይ ታያት፡

መኪናው አለፋትና በኩርባው ሲጠመዘዝ የሆነ የሚታወቅ ነገር አገኛለሁ ብላ መኪናውን ተከትላ ሮጠች፡፡ እንዳሰበችው የምታውቀው ቦታ
አየችና በደስታ አነባች
👍18