አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ዳኛው ሔር ገባ " ቁመቱ መካከለኛ ሲራመድ ጅንን የሚል ፊቱም የማይፈታ ሰው ነው ከጫፉ ቁልቁል ቁልምም ያለው አፍንጫው ስብስብ ያሉት ከንፈሮቹንና ሾጠጥ ያሉት አገጩን ሲያዩት ትንሽ ባርባራን ሊመስል ሲል ' ባጠቃላይ መልክ ግን እሷ በጣም ትበልጠው ነበር "
« ሪቻርድ» አለች ሚሲዝ ሔር በደራረበቻቸው ልብሶች እንደ ተሸፋፈነች ገና በሩን ከፍቶ ሲገባ "

« ምነው ? » አላት

« ሻይ አምሮኛል ዛሬ ከወትሮው ጥቂት ቀደም ብለን ብንጠጣስ ? ይሽውልህ ሰውነቴን እንደገና አተኮሰኝ ምላሴ ቅጥል ብሎ አሯል " አሁንስ ከነመናገሩም
ሊከለክለኝ ምንም አልቀረው " »

« አይ አሁን እኮ ለአንድ ስዓት ምንም ያህል አልቀረውም " እስከዚያ ታገሽ » አላትና • ለዚያች ያልጋ ቁራኛ በሽተኛ ሚስቱ 'ይህን የመሰለ ከልክ ያለፈ ከበሬታና አዘኔታ የተመላበት መልስ ሰጥቶ ክፉ ነገር ሳይናገር መጊያውን ግው አድርጎ በመዝጋት ወጥቶ ሄደ። "

ሚሲዝ ሔር ጨርሳ ባላሰበችሙ ተስፋ አስቆራጭ መልስ የተሰማት ኀዘን ግና ሳይወጣላት ተመልሶ ገባና: «እንዲያውም ዛሬ ጥሩ ጨረቃ ስላለች ከፒነር ጋር ሆነን
ቦሻ ዘንድ ትምባሆ ስናጤስ ለማምሸት የተመቸ ነው " ስለዚህ አሁን ብጠጣም ግድ የለኝም » በይ ባርባራ... ሻዩን አስመጪልን » አላት ሻይ ተጠጥቶ እንዳበቃ የሚስተር ቦሻ የርስት ሹም ሚስተር ስፒነር ከደጅ ሆኖ ተጣራና ከዳኛው ሔር ጋር ተያይዘው ሔዱ " hኢስት ሊን ማዶ ከነበረው አፋፍ ላይ ይኖር የነበረው ሚስተር ቦሻም ብዙ መሬት የሚያሳርስና ለዊልያም ቬንም የኢስት ሊን ወኪሉ የነበረ ሰው ነው «ባርባራ · በረደኝ » አለች ሚስዝ ሔር እየተንቀጠቀጠችና ባሏም በጠጠሩ መንገድ ዘቅዝቆ ሲሔድ እየተመለከተች « እሳት ባስነድድ አባትሽ ይቆጣኝ ይሆን ? »

« ከፌለግሽ አስነድጂ » አለቻት
ባርባራ መጥሪያውን እየደወለች » « አባባ የሚመለሰው ከተኛን በኋላ ስለሆነ ምንም ሊያውቅ አይችልም " ጃስፐር …....
እማማን ስለ በረዳት እሳት ትፈልጋለች " »

« አዴራህን ጃስፐር...ቶሎ እንዲያያዝና በደንብ እንዲነድ ከዕንጨቱ በርከትከት አድርግበት» አለችው ሚሲዝ ሔር ዕንጨቱ የሷም መሆኑ ቀርቶ የጃስፐር እንደሆነ ሁሉ በሚያሳዝን የልመና ድምፅ ....

💫ይቀጥላል💫
👍112
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በታደለ_አያሌው



“ምንድነዉ እመ?”

እየቆየ ፍርሐት እየለቀቀብኝ፣ ላብ እያጠመቀኝ መጣ፡ ቢያንስ ቢያንስ እንዴት ድምፅዋን እንኳን አልሰማሁትም? ለምን አላለቀሰችም? “ኧረ ልጄስ? ልጄ አታመጡልኝም?” አልሁኝ ከአሁን አሁን ቱናትን አምጥተዉ ያስታቅፉኛል ብዬ ብጠብቅ ዝም ስላሉኝ፡ አጭር ጊዜ በፈጀ
ቀዶ ሕክምና ቢሆንም የወለድሁት፣ የእናት ወጉ ደርሶኝ ገና ጡቴን ለልጄ አላጠባኋትም ጡት ማጥባት ቀርቶ ለዓይኔ እንኳን አላሳዩኝም፡

“አይ፣ ለትንሽ ጊዜማ ማሞቂያ ክፍል አትቆይም ብለሽ ነዉ? እንግዲህ ዶክተርሽ ያለችን እንደዚያ ነዉ” አለች እመዋ፣ ከእሸቴና ባልቻ ጋር የያዘችዉን ሞቅ ያለ ጨዋታ አቋርጣ ትኩረት እየሰጠችኝ፡

“እኮ ባይሆን አሳዩኛ። ላያት እፈልጋለሁ”

“ቆይ ትንሽ ተብለሽ እኮ ነዉ: አንቺም ትንሽ አረፍ በይ እስኪ ፊት”

“እመዋ፤ ወይ ወደ ልጄ ዉሰጅኝ ወይ ደሞ ልጄን አምጭልኝ” አልሁኝ፣ ከአልጋዬ ላይ ለመነሳት እየተገለገልሁ አቅም አጣሁ እንጂ ማንም አይመልሰኝም ነበር ለምንም ነገር እንዲህ ሆኜ አላዉቅም ለካ እንዲህ ነዉ የሚያደርገዉ? አሁን በአሁን እናት ሆኜ እርፍ! የእናት ሆድ ኖሮኝ
ቁጭ! ጭራሹን ያላየኋት ልጄ በዓይን በዓይኔ ዞረች᎓᎓ ናፈቀችኝ፡ ራበችኝ፡ ደግሞ ልቤ እንዴት ነዉ የሚደልቀዉ? ልጄን እንጂ የፍርድ ቤት ዳኛ አይደል የምተያየዉ፡

የናፍቆቱስ እሺ ይገባኛል፤ ፍርሃቱን ግን ምን አመጣዉ?
የልቤ መንቀጥቀጥ ቆዳዬ ላይ እስከሚታወቅ ድረስ በጣም ፈርቻለሁ ጭንቅላቷን ማየት ነዉ ፤ያስፈራኝ: ትልቅነቱ ምን አህሎ ይሆን? ራሷስ ምን ታህል ይሆን? ኹለት ኪሎ እንኳን መሙላቷን እንጃ አተነፋፈሷ ልክ ነዉ? በቅድመ ወሊድ እንደ ተፈራዉ፣ የጀርባዋ ነርቭ ክፍተት ፈጥሮ ይሆን? ቢያንስ እግሮቿን ማንቀሳቀስ ትችልም እንደሆነ
እኮ ገና የነገረኝ የለም: ዓይኖቿም በትክክል ማየታቸዉን አላወቅሁም
ወይስ እግዚአብሔር ተአምር ሠራ? ባልቻ እና እመዋ እንደ ተማመበት ድንቅ ሥራዉን አሳይቷቸዉ ይሆን? በተአምሩ የሰዉ መልክ፣ የሰዉ ጤና፣ የሰዉ ትንፋሽ ሰጥቷትስ ቢሆን! እሱንስ ቢሆን ማን ነገረኝ?
እግዚአብሔር እኮ ሥራዉ የሚታወቀዉ አንድም በጨቅላዎች ነዉ ይባላል፡፡ ከማሕጸን እንደ ወጡ ገና የጡትን ቦታ እና ጥቅም አጥተዉት
አያዉቁም: ልጄንስ ጡት አያምራት ይሆን? ካላየኋትማ መሞቴ ነዉ፡

እንደገና ፈራኋት ፡ እንደገና ናፈቅኋት።

“አንቺ ግን አየሻት ወይ እመ?” አልኋት፣ እጆቼን ከጡቶቼ ላይ ሳላነሳ።

“ማንን፣ ቱናትን?”

“አሃ፤ ስምም አዉጥታችሁላታላ?” አለ ባልቻ፣ ከእመዋ አፍ ተቃምቶ።

“ቱናት ብያታለሁ በበኩሌ” አለች፣ እመዋ:

“እመዋ” ስል ጠራኋት ቆጣ ብዬ፣ የባልቻ አጠያየቅ ወሬ ለመለወጥ
መሆኑ ስለ ገባኝ፡

“ዉብዬዋ” አለችኝ፣ የእናት እጇን ጭምር እየሰጠችኝ ይኼዋ እንዴት
እንደምታቆለማምጠኝ! ቁልምጫዋንስ ማቆላመጥ ታዉቅበት የለ? እሷ እናትነቷን እንዲህ ባጠጣችኝ ቁጥር፣ የእኔም ጉጉት ሰማይ ይደርሳል
እሷ ለእኔ እንደምትሆነዉ፣ እኔም ለልጄ ለመሆን ቋምጫለሁ

“እመዋ”

“እመት ዓለሜዋ”

“ስሞትልሽ! ስሞትልሽ ልጄን አምጭልኝ'

“ኧረ ቀስ! ምነዉ ልጄ? ወዲያዉስ የሐኪምሽ ወዳጅነት ላንቺ መስሎኝ! እንዲህ ሆነሽ ትወስድሽ ሆይ ወይ ደግሞ ቱናትን እንዲያ እዳለች ታመጣልሽ እንደሆነ፤ ሐኪምሽን ራስሽ የማትጠይቂያት”

"እኮ ጥሪልኛ እመዋ ዶክተሯን ጥሪልኝ እሺ”

እንደማልለቃቸዉ ሲያዉቁ ዶክተሯን ማስፈለግ ጀመሩ፡ ነገር ግን ሌላ ተረኛ ነፍሰ ጡር ለማዋለድ፣ ወደ ማዋለጃ ክፍል ቅርብ ጊዜ እንደ ገባች ከነርሶቹ መስማታቸዉን ነገሩኝ፡
አላመንኋቸዉም በይበልጥ
እየፈራሁላት፣ በይበልጥ እየተጠራጠርኋቸዉ መጣሁ ቅጽበት በቆየሁ ቁጥር ክፉ ክፉዉን ለሚያሳስበኝ መንፈስ መረታት ያዝሁ፡ ጭራሽ በሕይወት ባትኖር ይሆናል እንጂ፣ ቢያንስ እንዴት ድምፁዋን እንኳን
አያሰሙኝም?

“አአአ..አንድ ሐሳብ መመመመ..መጣልኝ” ሲል ሰማሁት እሸቴን፣ እስከ
አሁን ዓይኖቹን ከማንከራተት በቀር ትንፍሽ ሳይል ቆይቶ፡ “ዉዉዉ..
ዉቤ? ”

“እየሰማሁህ ነዉ”

ሐሳቡን አንድ ብሎ ሊነግረኝ ሲጀምር ገና፣ ልታዋልድ ኦፕራሲዮን ክፍል ገብታለች የተባለችዋ ዶክተር የክፍሉን በር ከፍታ ገባች፡

“ኦንኳን ማርያም ማረችሽ” አለችኝ፡

“ማርያም ታኑርሽ” አለች እመዋ ቀድማኝ ወዲያዉም ከጎኔ ቁጭ
ካለችበት የአልጋዉ ጫፍ ብድግ ብላ፡ ዶክተር ሸዊት ያ ብዙም
የማይለያትን ፈገግታዋን
ሳትቀንስ ሁሉንም እያቀፈች ሰላምታ ከተለዋወጠች በኋላ፣ እኔንም ጎንብስ ብላ ሳመችኝ፡፡ ግንባሬን አንገቴን እና እጆቼን እየደባበሰችኝ ሳለ፣ ለምን ልጄን እንደማያመጡልኝ ልጠይቃት ስል ቀልቧን ወደ እመዋ አደረገችብኝ፡፡

“እመዋ? እንኳን ደስ አለዎ”

“በአምላክሽ!”

“መቼስ ረስተዉኝ አይሆንም፤ ረሱኝ እንዴ ? "

“ተይ እንጂ! ምን ብረሳ ብረሳ፣ አንቺን እረሳ ብለሽኝ ነዉ? ምነው
አንድዜ እንኳ ከዉብዬ ጋ ለክረምቱ ይሁን ለገናዉ ዕረፍት
መጥታችሁ አብረንም አልሰነበትን?”

“አልረሱኝማ”

“ አንቺን? እንዲያዉ ያቺን ጨዋታሽ የምረሳልሽ መስሎሻል?”

“የቷን?” አለች፣ ለመፍካት ችኩል የሆኑ ጥርሶቿን እየገለጠች

“ምነዉ እንኳን አንድዜ፣ የሩስያ ምንቴስ ነዉ ያልሽኝ ሰዉ በዉብርስቴ ደም ግባት የሆነዉን ሁሉ አጫዉተሽኝ?”

“ስለ እሱ ጉድ ነግሬሽ ነበር ወይ እመዋ?”

“እህሳ”

“ለእኛም ንገሪን እንጂ ዶክተር” አለ ባልቻ፣ ያለ ወትሮዉ ለወሬ ሰፍ ብሎ፡ የእሸቴም ጆሮ ከምኔዉ ቀጥ እንዳለ! የእሸቴ እና የባልቻስ ይሁን እሺ፣ እመዋ እንኳን እንደ አዲስ ለመስማት በዓይኖቿ ደጅ ስትጠናት ሳይ እኔም የልጄ ናፍቆት በረድ አለልኝ፡፡

“ጉዷ ያልቅ መስሏችኋል?” ብላ ጀመረች፡ “ይቺ ጉደኛ! የተመረቅን
ሰሞን ነዉ ነገሩ። ቀድሞዉንም ቢሆን በዉጤት እንደ ምንም እቀራረባት እንደሆነ እንጂ ደርሼባት አላውቅም:: በተለይ የመመረቂያ ጥናቷን ያዩላት ሰዎች ሁሉ እዴት ይደነቁባት እንደነበር አትጠይቁኝ። እና እንደ አጋጣሚ፣ በዚያ ሰሞን የሩስያ አምባሳደር ከሀገራቸዉ የመጡ በጎ ፈቃደኛ
ሀኪሞችን እየመሩ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መጥተዋል። ጠሪዉ ደግሞ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ነዉ: የዚያን ዕለት ታዲያ፣ የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዜዳንት ራሱ ስልክ ደዉሎላት ኹለት ሁነኛ ሰዎች እንድትመርጥ እና በጎ ፈቃደኛ ሩስያዊ ሀኪሞችን እንድታግዝ ያዝዟታል”

“ማንን?”

“ይቺን ነዋ፤ ዉብርስትን''

“እሺ”

"እሷ ደግሞ እኔን እና አንድ ሌላ ሐኪም ስትጠይቀን፣ እናግዛለን ብለን ሳይሆን እንጠቀማለን ብለን ወደ ተባሉት በጎ አድራጊዎች በጠዋት †ነስተን ተከተልናት።
በዚያች አንድ ቀን ታዲያ፣ ሩስያዉያኑ ያልደረሱበት የጎንደር ዙሪያ ጤና ጣቢያ የለም። እኛም አብረናቸዉ እየዞርን እነሱ ለጤና ጣቢያዎቹ ያመጡልን መድኃኒት ስናድል እና ለጥቂት አበሻ ሕመምተኞች ደግሞ መጠነኛ ሕክምና ሲሰጡ ስናይ ዋልን
ማታዉኑ፣ ዩኒቨርስቲዉ እንግዶቹን እራት ካልጋበዝሁ አለ። አምባሳደሩ ግን አመሻሹ ላይ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ቢሆንም ዕቅዳቸዉ፣ ከስንት መለመን በኋላ የበረራ ሰዓታቸዉ እንዲዘገይ ተስማምተዉ በግብዣዉ ላይ
ተገኙ። እኛም እንደ እንግዶች በክብር ተጠርተን፣ መጥሪያዉ ላይ በተጠቀሰዉ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ተገኝተናል። የከተማዉ ከንቲባ፣ የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዜዳንት፣ምክትሎቻቸዉ እና ዘመዶቻቸዉ ጭምር
መጥተዉ ሳይሆን አይቀርም፣ ያን የሚያህል አዳራሽ ጢም ብሏል።
የጎንደር መታወቂያ የሚባሉ አዝማሪዎችም መድረኩን ሞልተዉታል።ብርቆዎች፣ ጨዋታዎች፣ ሳቆች ድብልቅልቅ አድር ገዉታል”
👍33
“እዚህ ላይ አይደል ጉዱ?” አለች እመዋ፣
እየደረደረች፡ ሸዊት ቀጠለች፡፡

“መቼም አዝማሪዎች የታወቁ ናቸዉ በዚህ በዚህ: አሽሙሩንም፣
ሙገሳዉንም፣ ትንቢቱንም፣ ታሪኩንም እየቀላቀሉ ያመጡታል። ቋንቋዉ ባይገባቸዉም፣ ሩስያዉያኑ እንግዶች እጃቸዉን አፋቸዉ ላይ ጭነው
በአድናቆት ይመለከቷቸዋል። የእነሱ ነገረ ሥራ ደንቆኝ፣ ወደ ዉቤ ዞር ስል ትቁነጠነጣለች። የአዝማሪዎቹ የዜማ አወራረድ እና የግጥም አካሄድ በኃይል ነሽጧት
ኖሮ፣ ብቻ እንዴት እንዴት አትጠይቁኝ። ምን ሊያደርጋት ነዉ ስል ድጓገት ተስፈጥራ ከአጠገቤ ተነሳች። በዚያ ጊዜ ራሷንም ማወቋን እንጃ ብቻ፣ ቀጥ ብላ ወደ መድረኩ ሄደች። እኔ ሰዉ እንደሷ ሲሆን ያየሁት፣ ዲማ ቅኔ ቤት የጎበኘሁ ጊዜ ነዉ። የቅኔ ተማሪዎችን ብቻ ነዉ እንደሷ እየዘለሉ እልም ብለዉ ስሜት
ዉስጥ ሲገቡ ያየኋቸዉ: አንዱ አዱን ነጥቆ ሲዘርፍ ያሁት እነሱ
ነበር። ያኔ ግን ኋደኛዬ በቅጡ እደማላዉቃት ገባኝ። በእሷ የሚደርስ ማንም የለም ኖሯል ለካ: እየተንደረደረች ሄደችና
ከአዝማሪዎ መካከል ቆሞ የሚያዜመዉን ሰዉ ክራር ነጠቀችዉ: ደግነቱ እሱም
አልከላከላትም: ይልቁስ እሱ ጀምሮት ከነበረዉ ሐረግ ላይ ተነስታ እስካሁንም ድረስ ፍቺዉ ያልገባኝ ቅኔ ስትቀኝ በአድናቆት ተመለከታት:መመልከት ብቻም ሳይሆን እጁ እስኪዝል ድረስ ቆሞ አጨበጨበላት::አዳራሹ ዉስጥ ተቀምጬ የቀረሁት እኔ ብቻ ነበሁ ብላችሁ ታምኑኛላችሁ? በስመአብ!ሩስያዉያኑ እንግዶች ሳይቀር ትርጉሙ የገባቸዉ ይመስል፣ አፋቸዉን ከፍተዉ ቀሩ: አምባሳደሩም እንዲያ ወደ
አዲስ አበባ ለመሄድ ቸኩለዉ የበረራ ሰዓታቸዉ ትንሽ በመራዘሙ ለንቦጫቸዉ ጥለዉ እዳልነበር ፣ አሁን ግን ተለዉጠዉ ጉድ አላመጡም?”

“የምን ጉድ?” አለ ባልቻ፣ እሱም እንደ እመዋ እና እንደ እሸቴ ቁጭ
ብድግ እያለ ሲያዳምጣት ቆይቶ፡
አይ እሷ! አቤት አገላለጽ! በምታወራዉ ላይ ዉሸት ባላገኝበትም፣ አገላለጽዋ ላይ የምትጨማምራቸዉ ነገሮች ግን፣ የምትለዉ ዉሸት እንኳን ቢሆን ኖሮ ከማመን አያተርፈኝም ነበር፡ እንኳንስ እነ ባልቻን እኔን ባለ ታሪኳን ሁሉ ስሚኝ ስሚኝ አስብለኛለች ያዉም በልጄ ናፍቆት
ክፉና ደጉን ከማሰብ አዉጥታኝ፡

“አምባሳደሩ?” አለ እሸቴ፣ እሱም ጉጉት እንደ ባልቻ እና እንደ እመዋ
እያደረገዉ፡

“አምባሳደሩ ጉድ አመጡ: (በስመ አብ! አሉበአማርኛ: እዉነትም
አዝማሪዎቹ እንደ ከዋክብት፣ ዉብዬ ግን እንደ ጨረቃ ሆነዋል። የዉበት ዳርቻ እኮ ናት ጓደኛዬ! አንዳንዱማ እንዲያዉም (በዚህ ድቅድቅ ጨለማ ፀሐይ ከየት ወጣች እስከ ማለት ነበር የደረሰዉ። መድረኩ ላይ ብቻ
ሳይሆን በአዳራሹ ሙሉ፣ በአዳራሹም ብቻ ሳይሆን በመላ ከተማዉ፣ በዚያም ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሩ እሷን የሚተካከል ቆጓጆ አለመኖሩን እየማለ ተወራረደ። ለቆንጆ ሰዉ ቆንጆ ጭንቅላት እና ቆንጆ ድምፅ ሰጥቶ
የፈጠራትን አምላክ፣ሁሉም ቀና እያለ አደነቀ። ‹ኧረረረረ አሉ
አምባሳደሩ እንደገና፣ በጎንደርኛ: ይኼ ሲገርመ እኔ፣ ሰተት ብለዉ ወደ መድረኩ ወጧ''

“ምን ሊሆኑ?”

“ሊስሟት”

“ምን?” አሉ ሁሉም እኩል፣ ግርምም ቅፍፍም እያላቸዉ፡
“ካልሳምሁሽ አሉ። አምባሳደሩ ለመሳም፣ ዉብዬ ላለመሳም የሆኑትን መሆን እያየ የሆቴሉ ታዳሚ ዝንታለም ተስቆ የማያዉቅ ሳቅ ሳቀባቸዉ”

“እእእ እሰይ! ማን ቅለል ብሎታል? የት አባቱ!” አለ እሸቴ፣ በአሸናፊነት

“እንጃለት!” አለ ባልቻም፣ ቀበል አድርጎ፡ “አምባሳደር ሆኖ ሲያበቃ፣ ባህላችንን ማወቅ አልነበረበትም? ሮጦ ወደ ሀገራች ከመምጣቱ አስቀድሞ፤ እንኳንስ የሰዉ ሰዉ የገዛ ሚስቱን እንኳን በአደባባይ መሳም ነዉር መሆኑን አያውቅም ኖሯል? ይበለዉ!''

ሸዊት እኔን ስትጠቅሰኝ ባላጅባትም፣ በኹለቱም ፍርስ ብላ ሳቀችባቸዉ

“እንደሱ እኮ አይደለም:: ሌላ ነገር ፈልጎ መስሏችኋል?

“ኧረ ባክሽi እና እዴት ኖሯል በይ?”

“ለካንስ፣ በሩስያዉያን ባህል መሠረት አድናቆት የሚገለጸዉ ወይ ጉንጭን ግጥም አድርጎ በመሳም ወይ ደግሞ አንድ ሸክም አበባ በማስታቀፍ ኖሯል። በሱ ቤት እንግዲህ አድናቆቱን፣ መግለጹ ነዉ''

“በሩስያ ባህል?” አለ ባልቻ፣ እሱ ስለ ሩስያዊያን ከሚያዉቀዉ የተለየ ሆኖበት ባልቻ ሩስያን በደንብ እንደሚያዉቃት፣ የማዉቀዉ እኔ ብቻ ሳልሆን አልቀርም ሩስያዉያን በተዘዋዋሪ፣ የሩስያ መንግሥት ደግሞ
በቀጥታ የሲራክ ፯ ወደር የለሽ አጋር በመሆናቸዉ፣ ቋንቋቸዉን ሳይቀር አቀላጥፎ ይነጋገርበታል
“እርፍ!” አለች ዶክተር፣ አጠገቧ ያለዉ ሰዉ ባልቻ መሆኑን አሁን ገና ልብ አድርጋ እያየችዉ: “አንቺ” አለችኝ፣ ከንፈሯን ነክሳ ወደኔ
እያንሾካሾከች። “ይኼ ሰዉ ባልቻ ነዉ እንዳትዪኝ ብቻ!”

“አልተዋወቃችሁም እንዴ እስከ አሁን? ኋደኛዬን ሳትተዋወቅ ነዉ እንዴ እስከ አሁን የምታስለፈልፋት አባትዮዉ ?” አልሁት ባልቻን፣ ቀብረር ብዬ በመጽሐፍቱ የተነሳ፣ ከድሮም ጀምሮ ለባልቻ እጅግ ከፍ ያለ ከበሬታ እንዳላት ስለማዉቅ እና በእኔ የተነሳ ልትተዋወቀዉ መሆኑ ኩራት እንደ ለቀቀብኝ ግንባሬ ላይ እያሳየኋት፡

“ባልቻ እባላለሁ”

“ኧረ አዉቅሃለሁ: አንተን የማያዉቅ ሐበሻ ይኖራል ብለህ ነዉ? ያላወቅሁትስ በምን ተአምር የዉብርስት ቤተሰብ ሆነህ እንደ ተገኘህ ብቻ ነዉ'

“እሱስ ቢሆን ምኑ ይገርማል?”
“ይገርማል እንጂ! በእርግጥ ግቢ እያለንም ያንተ መጻሕፍት
አልፈዉን አያዉቁም: ያንጊዜ ለእነም ለዉብርስትም ያዉ ነበርህ
እኔም እሷም እናውቅህ የነበረዉ ወይ በቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ስታደርግ ነዉ፣ ያለበዚያም በጽሑፎችህ ብቻ ነበር። አሁን ግን የእሷ አስታማሚ ሆነህ ከመጣህ፣ በመሀሉ ያለፈኝ ሌላ ታሪክ አለ ማለትም አይደል?''

“የሥራ ባልደረባዬ ነዉ” አልኋት፣ ነገሩን በአጭር ያስቀረሁ መስሎኝ፡፡መቼስ አንቺ የማታዉቂዉ ሲራክ-፯ የሚባል የደኅንነት ማዕከል አለ፡
እኔና ባልቻ የተዋወቅነዉ እዚያ ነዉ አልላት ነገር። “የሥራ ባልደረባዬ ነዉ” አልኋት፣ በደፈናዉ:

“ሥራ?”

“አዎ፣ አብረን ነዉ የምንሠራዉ”
ተይ እንጂ ! ሌላዉ ቢቀር ትናትና እኮ፣ሥራ እንደ ሌለሽ ነበር
የነገርሽኝ። ታዲያ ዛሬ ደግሞ የሥራ ባልደረባነቱን ከየት አመጣሽዉ በይ? አንድ የደበቅሽኝ ነገርማ አለች። የሆነዉሆኖ፣ እንዲህ ገጽ ለገጽ ስላሁህ በጣም ደስ ብሎኛል። በሀገራችን ልዩ ሥፍራ ከምሰጣቸዉ
አሳቢዎች መካከል፣ አንተን የሚያህልልኝ የለም”

እግዜር ያክብርልኝ” አለ ባልቻ፣ በትክክለኛ ትሕትና

ባልቻን በአካል አገኘሁት? ላምን አልችልም: እኔ አላምንም” አለች፣
እንዳዲስ ጥርስ በጥርስ እየሆነች፡ ወደ እኔ እየዞረች፣ በዓይኖቿ ሳይቀር ተፍነከነከች እኔም ከባልቻ ጋር ባለን ቀረቤታ ተኩራራሁባት የዋዛ ሰዉ መስየሽ ኖሯል? በሚል ትከሻዬን ነቀነቅሁባት

ቀናችብኝ፡

“እኔ ምልሽ” አላት ባልቻ፣ እሷ ገና ተገርማ ሳትጠግብ፡፡

“አቤት”

“ዉብርስት የሩስያዉን አምባሳደር ሳይቀር ምን ብላ እንዳስደነቀችዉ እኮ አልነገር ሽንም: መቼስ እሷ አያልቅባት፣ ለመሆኑ ምን ብትልላችሁ ነዉ ያን ያህል?”

“አይ እሱን እንኳን… ”

“እባክሽ እባክሽ”

“ከራሷ አፍ ይሻላችኋል ብዬ ነዉ። ራሷ እያለች? እሺ ካለችስ፣ ከዚያ
ክራሯ ጋር በዚያ ድምፁዋ ለኔም ብትደግምልኝ ደስታዉን አልችለዉም::ደግሞ አለቃትም፣ ማርያም በሽልም ታዉጣልን ብቻ!” አለች፣ የሙቀት መጠኔን ለመገመት መዳፏን ግንባሬ
ላይ እያኖረችብኝ፡ “ቃል
አትገቢልንም ዉቤ?”
👍29
መልስ አልሰጠኋትም፡ በሽልም ስለመዉጣት ስታነሳ፣ ልጄ በሐሳቤ መጣችብኝና፣ የቅድሙ ናፍቆት እና ፍርሃቴ እንደገና መጣብኝ፡ የፊቴን መለዋወጥ አይተዉ ኖሯል፣ ሁላቸዉም ትንፋሻቸዉን ዉጠዉ ወዲያ
ወዲህ ተቁለጨለጩ።

“እስኪ…” አለች ዶክተር ከብዙ ዝምታ በኋላ፣ ወደ በሩ እያመለከተቻቸዉ። “እስኪ አድ አፍታ ላስቸግራችሁ፣ ዉጪ ጠብቁ ያለ ምንም ጥያቄ ሁሉም ምሰስ እያሉ ሲወጡ፣ በክፍሉ እኔና እሷ ብቻ ቀረንበት....

ይቀጥላል
👍175
#ሳቤላ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

... ሚሲዝ ሔር እሳቷን አስነድዳ ወንበሯን አስጠጋችና አግሮቿን ከምድጃውጠርዝ ዘርግታ ስትሞቅ ባርባራ ግን አሁንም ሐሳቧ እንደ ተበተነ ልቧ እንደ ተሰቀለ ነበር " በመጨረሻ ከልብስ መስቀያው አንድ የሱፍ ያንገት ልብስ አውርዳ ከትከሻዋ ደረበችና ወጥታ ሔደች የግቢውን የአግር መንገድ ይዛ በቀጥታ ሔዳ ከብረቱ በር ስትደርስ ቆም ብላ ወደ ሕዝቡ ጐዳና ትመለከት ጀመር " ነገር ግን ያ ጐዳና በዚያ ሰዓትና ቦታ፡እንደ ሌላው ጊዜ ሕዝብ አልነበረበትም!ጸጥ ብሎ ነበር
የግንቦት መጀመሪያ ላይ ስለ ነበረ በጣም ቀዝቃዛ ይሁን እንጂ ጸጥ ያለ አስደሳች የጨረቃ ምሽት ነበር።

“ ከቶ መቸ....ይመለስ ይሆን ? አለች ባርባራ ከበሩ ተደግፋ ብቻዋን ስታወራ (እሱ የሌለበት ሕይወት ምን ሕይወት ነው ! አሁን በነዚህ ጥቂት ቀኖች ውስጥ ምን ያህል ተጨነቅሁ ? እንደ ኮርኒሊያ አባባል ከሆነ ለአንድ ቀን ብቻ ነበር የሔደው " ለመሆኑ ወደዚያ ምን ጉዳይ ቢኖረው ነው የሔደው ?

የእግር ዳና ከጆሮዋ ጥልቅ አለ በዚያ ሰዓትና ቦታ ማንም መንገደኛ እንዲያያት አልፈለገችም ስለዚህ ወደ ኋላዋ ምልስ ብላ ከዛፎቹ ጥላ ሥር ተከለለች "
የኮቴው ድምፅ እየቀረበ ሲመጣ ከዚያ በፊት የምታውቀው አረጋጥ መሆኑን ለየችው ስሜቷ ተለዋወጠ ዐይኖቿ በሩ ጉንጮቿ ፍም መሰሉየደም ሥሮቿ
ከደስታዋ ብዛት ነዘሩ እንዳትታይ ተጠንቅቃ በበሩ ቁልቁል ስትመለከት አንድ ረጅም ሰውዬ ከወደ ዌስት ሊን ሲመጣ አየች " የኋሊት ሽሽት አለች እውነተኛ
ፍቅር ድንጉጥ ነው " የባርባራ ሔር ሌሎች ተስጥዎች ያፈቀደውን ቢባሉም ፍቅሯ
ግን ልባዊና ጥልቅ ነበር ከበሩ ሲደርስ ይገባል ብላ ስትጠብቀው ዐልፎ የሚሔድ ይመስል ወደ በሩ እንኳን ዞር ብሎ አላየም " ባርባራ ሐሞቷ ፍስስ አለ እንደገና
ወደበሩ ተጠግታ ፍዝዝ ብላ በጕጒት መመልከት ጀመረች።

በርግጥም ስለሷ ምንም ሳያስብ ወደሷ ዘወር ሳይል ዐልፎ ወደፊቱ ሲገሠግሥ ስታይ በዚያች ቅጽበት በመጣበት የስሜት ግፊት «አርኪባልድ» ብላ ጠራችው።
« ባርባራ ... ሌቦችና ሕገ ወጥ አዳኞች እንዳይቡ እየጠበቅሽ ነው እንዴ ? እንደምነሽ ? » አለ

«እንደምነህ?» አለችው በአንድ በኩል በሩን ከፍታ ይዛ ስታስገባው በሌላ በኩል ደግሞ ከሱ ጋር እጅ ለእጅ ስትጨባበጥ እየገነፈለ ያስጨነቃትን ስሜት ለማመቅ ከራሷ ጋር እየተናነቀች » « መቸ መጣህ ? » አለችው " « አሁን በሁለት ሰዓቱ ባቡር መድረሴ ነው " ላንዳፍታ ከቢሮ ገባሁና አሁን ደግሞ ሚስተር ቦሻምን ለአንድ ጉዳይ ስለምፈልገው ወደሱ እየሔድኩ ነው " በይ ስመለስ እገባ ይሆናል " አሁን ግን ቸኩያለሁ አመሰግናለሁ " »

አዬ አባባና ሚስተር ስፒርነርም ከዚያ ስለአሉ ' ከነሱ ጋር ቆይተው ወደዚህ ለመምጣት በጣም ይመሽብሃል “ እነሱ እንዶሆኑ ከአምስትና ከስድስት ሰዓት በፊት
አይላቀቁም " »

« እነሱ እዚያ ካሉስ ከሚስተር ቦሻም ጋር ያለኝ ጉዳይ የግል ስለሆነ ለነገ ማስተላለፌ ነው » የያዘችውን በር ተቀብሎ ዘጋውና ክንዷን በክንዱ ይዞ ወደቤት
አመሩ እሱ ይህን ያህል የሚቀርባትና የሚይዛት በምንም ስሜታዊ ግፊት ሳይሆን
ከልማዳዊው ትሕትና በመነሣት ማክበሩ ነበር ባርባራ ሔር ግን ክንዷን ከክንዱ አቆላልፋ ጐን ለጐን ሆነው እያነጋገራት ሲሔዱ ኤደን ገነት ውስጥ እንደ ገባች ሆና ሀይሰማት ነበር "

«ታዲያስ ባርባራ ... ... ... በነዚህ ጥቂት ቀኖች ውስጥ እንዴት ሰነበታችሁ?
« መሔድህን ሳንሰማ ምን ነገር ነው ድንገት ብድግ አድርጎ የወሰደህ ? »
« ተናርሺው እኮ ባርባራ!...... ... አንድ ያልታሰበ የሥራ ጉዳይ ተፈጠረ ሔድኩ »
« ኮርኒሊያ ግን ለአንድ ቀን ብቻ መሔድን ነበር የነገረችኝ»

« አለችሽ እንዴ ? ለንደን ከደረስኰ በኋላ ብዙ የምፈጽማቸው ነገሮች
ገጠሙኝና ቆየሁ " ሚስዝ ሔር እንደምን ስነበቱ ? »

« እሷ ያው ናት እኔስ ግማሾቹ በሽታዎቿን በሐሳቧ የፈጠረቻቸው ይመስሉኛል " አሁን በግድ እየተነሣች ብትንቀሳቀስ ይሻላት ነበር " ምንድነው ከሱ ጠቅለህ የያዝከው ? »

« ሚሲዝ ሔርን እንጂ አንቺን ስለማይመለከት አትጠይቂኝ " »
« ለእማማ ያመጣህላት ነገር ነው ማለት ነው አርኪባልድ ? »

« አዎን ' አንድ ገጠሬ ለንደን ከደረሰ ለወዳጆቹ ምን ስጦታ ይዞላቸው እንደሚመለስ ነው የሚያስበው " የጥንት ወጉ ይኸ ነበር " »

« እና አሁን በርግጥ ለእማማ ያመጣህላት ነው? »

« ምነው እየነገርኩሽ …. ባርባራ ላንቺም እንድ ነገር አምጥቼልሻለሁ»

« ምን አመጣልኝ ? » አለችው ፊቷ እንዳመሉ እየቀላ ቀልዱን ይሁን እውነቱን እስክታውቅ ድረስ ሐሳቧ በጕጒት እየተንጓለለ "

« ቀስ በይ እኮ አትቸኩይ !ምን እንደሆነማ ልታይው አይደል » አላትና የያዘውን ጥቅል አጠገባቸው ከነበረ ከአንድ ያትክልት ቦታ ወንበር ላይ አስቀመጠና ኪሶቹን ሁሉ ቢዳብስ አጣ "

« ባርባራ ... ካንዱ ሳልጥለው ቀረሁ ብለሽ ? » አለና እንደገና
ኪሶቹን ሁሉ ፈለገ አራገፈ " በመጨረሻ አንድ ያልታሰበ ኪስ ውስጥ አንድ ነገር ጐረበጠው
«አይ እዚህ አለ መሰለኝ ። ግን እዚህ ምን አመጣው ? » አለና አንዲት ትንሽ ሣጥን አውጥቶ በመክፈት ከውስጧ አንድ ረጂም የወርቅ ሐብል አንሥቶ ባንገቷ አጠለቀላት ከሐብሉ ጋር ባንድ በኰል ጌጥ በሌላ በኩል የጥቃቅን መታስቢያዎች ለመያዣ የሚያገለግል ትንሽ የወርቅ ሙዳይ ተያይዞ ነበር ።

ልቧ በኃይል ሲመታ የፊቷ ቅላት እንደ ልቧ አመታት ቦግ እልም ይል ጀመር አንዲት የምስጋና ቃል እንኳን መተንፈስ አልቻለችም " ሚስተር ካርላይል ያኖረውን ጥቅል አንሥቶ ወደ ሚስዝ ሔር ዘንድ ገባ። ሻማ ባይያያዝም በክፍሉ ሲነድ የነበረው እሳት ቦግ ብሎ በርቶ ነበርዠ።

« መቸም እንዳይሥቁብኝ» አለ ያመጣውን ጥቅል እየፈታ እስከዚህም የረባ ስጦታ አይደለም ብቻ ብዙ ጊዜ ሲመኙት እሰማ ስለ ነበር ከአንድ ሱቅ መስኮት ላይ አይቼ በአየር የሚሞላ መከዳ ነው ያመጣሁለዎ » ብሎ ሰጣት » በመጋደምና በመቀመጥ ሰውነቷ ያለቀው ሚሲዝ ሔር እንደዚያ ያለ ዕቃ ለንደን እንደሚገኝ
ከመስማቷ በቀር ከነማየቷም አታስታውሰውም እንደ ጓጓች ተቀበለችውና በምስጋና ትክ ብላ ተመለከተችው "

« አንዴት ብዬ ነው የማመሰግንህ? » አለችው የደስታ ዕንባ እየተናነቃት
« አስበህ ስለ አመጣሀልኝ አመሰግንሃለሁ»

« አሁን ለባርባራ ስነግራት ነበር " ወደ ለንደን ከሔድን ለወዳጆቻችን ምን ይዘን መመለስ እንደሚገባን ማሰብ እንጀምራለን ባርባራንስ እንዴት እንዳሳመርኳት አዩዋት አይደል ? » አላት ሚስተር ካርላይል "

ባርባራ ሐብሉን ካንገቷ ቶሎ አወለቀችና ከናቷ ፊት አኖረችው "
«አቤት እንዴት ያምራል ልጄ!መቸም ለዚህ ያወጣኸው ገንዘብ ልክ አይኖረውም»

« ኧረ እሱስ ጥቂት ነው ፍሬም የለው» አለ ሚስተር ካርላይል እንደ መሳቅ ብሎ " « እንዴት እንደገዛሁት ላጫውታችሁ የጅ ስዓቴ ማሰሪያ እየተፊታ አስ
ቸገረኝና ወደ አንድ ወርቅ ሠሪ ዘንድ ጎራ ብዬ ነበር በዚያ ብዙ አይነት ሐብሎች ተሰቅለው ሳይ ኮርነሊያና ባርባራ አብረውኝወደ ሊንቦራ ሔደው በነበረ ጊዜ ባርባራ የጠፋባትን ሐብል አስታወሱኝ " ስለዚህ ለባርባራ አንገት የሚስማማውን መርጬ
👍23
ገዛሁ ባለሱቁ ደግሞ ከሐብሉ ጋር ሊያያዙ የሚችሉ የተለዩ ዘመድም ሆነ የፍ ቅረኛ ጸጉር በማስታወሻነት የሚይዙ ትንንሽ የወርቅ ሙዳዮችን አሳየኝ እኔም
ከሁሉ አብልጠሽ የምትወጂውን ሰው አንዲት ዘለላ ጸጉር ታስቀምጭበት ይሆናል
ብዬ አንዱን መርጩ ከሐብሉ ጋር እንዲያያይዝልኝ ነገኩት»

« የምን ጸጉር ? » አለች ሚሲስ ሔር "

ሚስተር ካርላይል ግድግዳዎቹም እንዳይሰሙት የፈራቸው ይመስል ዙሪያውን ካስተዋለ በኋላ ቀስ ብሎ «የሪቻርድ » አላት « አንድ ቀን ጠረጴዛዋን ስታስናዳ ሪቻርድ ታሞ የነበረ ጊዜ የተቆረጠ ነው ብላ ጸጉር አሳይታኝ ነበር »
ሚስዝ ሔር ከወንበሯ እንዶ ተቀመጠች ቁልቁል የሰጠመች መሰለች: እጥፍጥፍ አለችና ፊቷን በእጆቿ መኻል ደፍታ ንዳድ እንዶ ያዘው ተንቀጠቀጠች የሚስተር ካርላይል ቃሎች ለአንድ ከባድ ኀዘን ምክንያት የሆነ ትዝታ ቀስቀሰባት «ወይ ልጄ !ልጄ ! ያልታደልከው ልጄ ! ሚስተር ሔር ስለኔ በሽታ ይገርማል "
አየህ አርኪባልድ ..... ባርባራም ትቀልድብኛለች " ግን ይህ ሁሉ የአካልና የመንፈስ ጭንቀት የሚደርስብኝና የምሰቃየው በልጄ ምክንያት ነው ። ልጄ ሪቻርድ ልጄ ! » እያለች ትንሰቀሰቅ ጀመር

ይነጋገሩበት የነበረው ርዕስ ለምትጨነቀው እናት ተስፋም
ማጽናኛም የሚሰጥ ሳይሆን የተለየ ስለነበር ሁሉም ለጊዜው ትንሽ ጸጥ ብለው ቆዩ » « ባርባራ
ሐብልሺን አጥልቂው » አላትና ሚስተር ካርላይል ጥቂት ቆይቶ « ባንገትሽ አስረሽ ትጠግቢው ዘንድ ጤንነትን እመኝልሻለሁ ። ጤንነትና የመንፈስ ተሐድሶ ላንቺ ይሁኑ ቆንጂት »

ባርባራ የሚያምሩት ዐይኖቿን እያንከባለለች ፈገግ ብላ በሰመመን ዐይን 0ይኑን እያየች ለኮርነሊያስ ምን አመጣህላት ? » አለችው « አንድ ጥሩ ያንገት ልበስ አመጣሁላት ሻጩ እውነተኛ የፋርስ ሱፍ መሆኑን ነግሮኛል " እኔም ተራው ያገራችን የማንቸስተር ሥራ እንደማይሆን አምኜ ገዛሁት " »

« ያግር ውስጥም ቢሆን እኮ ኮርነሊያ ልዩነቱን አታውቀውም » አለችሙ ባርባራ "

« እኔ እንጃ በበኩሌ ግን የውጭ አገር ሸቀጥ ካገራችን የሚበልጥበት ምክንያት አይገባኝም " እኔ ያንገት ልብስ የምለብስ ብሆን ምርጥ ከተባለው የፈረንሳይ ሥራ ይልቅ ከራሳችን ፋብሪካዎች የተሠሩትን እመርጥ ነበር » አላት ሚስተር ካርላይል "

ሚስዝ ሔር እጆቿን ከጠወለገው ፊቷ አንሥታ ቀና አለችና«ለመሆኑ ያንገት ልብሱስ ምን ያህል ዋጋ ወሰደ? » አለችው "

« ብነግርዎ ለኮርነሊያ እንደማይነግሯት ቃል እንዲገቡልኝ እፈልጋለሁ ያወቀችው እንዴሆነ ገንዘቡን በከንቱ እንደ ጣልኩት ቆጥራ እኔንም ቁም ስቅሌን
ታሳኛለች " ልብሱንም ጠቅልላ ከሳጥን ከታ ሁሌተኛ አትነካውም " ዐሥራ ስምንት ፓውንድ ነው የከፈልኩበት " »

« አቤት ! ብዙ ነው ። በጣም ጥሩ ዕቃ መሆን አለበት እኔ ግን እስከ ዛሬ ላንገት ልብስ ከስድስት ፓውንድ በላይ ከፍዬ አላውቅም » አለች ሚስዝ ሔር ።

« ኮርነሊያ ደግሞ » አለ ሚስተር ካርላይል እየሣቀ « ከሦስት ፓውንድ በላይ ከፍላ አታውቅም " በሉ ደኅና አምሹ ከውጭ ከለንደን ተመልሼ ከቤት ሳልገባ
ይህን ያህል እዚህ መቆየቴን ካወቀች ትወርድብኛላች » አለና የእጅ ሰላምታ ሰጥቷቸው ሲወጣ ባርባራ ልትሸኘው ተከተለችው

« ብርድ እንዳይመታሽ "ባርባራ " ያንገት ልብስሽን እንኳን አልዶረ
ብሽም " »

« አይነካኝም " ግን እንዴት ቸኮልክ ዐሥር ደቂቃ እንኳን አልቆየህም»

« ከመጣሁ ከቤት አለመድረሴን ረስተሽዋል መሰለኝ»

« ወደ ቦሻም ቤት ልትሔድ አልነበረም ? ሒደህ ቢሆን ኖሮ እስከ ሁለት ሰዓት ድረስ አትመለስም ነበር ። »

« ይህ ሌላ ነገር ነው " ለሥራ ጉዳይ ከሆነ እኮ ኮርነሊያም ደስ ይላታል እንጂ አይከፋትም ። በሥራ ጉዳይ ባልሆነ ካጠገቧ ከጠፋሁ ግን መሬት አይበቃትም
አሁን እንኳን ስለ ለንደን አምስት መቶ ጥያቄ በምላሷ ጫፍ ይዛ እንዶምትጠብቀኝ አትጠራጠሪ » በነገራችን ላይ ባርባራ …….….. እናትሽ ያመማቸው ይመስላሉ »

« እሷ በትንሹ ነገር ሁሌ ራሷን እንደምትበጠብጥ ታውቃለህ። ትናንት ሌሊት ደግሞ አንድ ሕልም አየሁ ብላ እንደ ተመለከትካት እስካሁን ትንቀጠቀጣለች
እሷ እንደምትለው ሕልም አንድ መጥፎ ነገር ሊደርስ ሲል የሚታይ ማስጠንቀቂያ ነው" ስለዚህ የሚሆን ነገር አለ እያለች በሐሳብ ስትወዘወዝ ትኩሳቷ ሁሉ ተነሥቶ
እንደ ነደዶች ዋለች " ለአባባ ደግሞ ስለ ሕልሙ ደፍሮ የነገረው የለም » ሰውነቷ እንደዚህ ሆኖ የመነመነው ተጨብጣ ስለምትውል ስለሆነ ለምን አትንቀሳቀስም እያለ ይቆጣል »

« ስለ ሕልሙ ያልነገራችኋቸው ሕልሙ ስለ....»

ሚስተር ካርላይል ነገሩን አቋርጦ ዝም አለ አሁን እንደ በፊቱ ክንዱን አልሰጣትም " ባርባራ ዙሪያዋን አስተውላ ወደሱ ጠጋ አለችና «አዎን ስለ ግድያው ስለሆነ ነው " እማማ በግድያው ወንጀል ቤተልም አለበት እያለች እንደምትለፈልፍ ታውቃለህ » ለዚህ ሌላ መረጃ ባታገኝ እንኳን ሕልሟ እንዳረጋገጠላት ታምናለች "ሁልጊዜ በሕልሟ
ገባህ ? ከ....ጋር በሕልሟ እንደምታየው ትናገራለች " »

« ከሃሊዮን ? » አለ ሚስተር ካርላይል

« ከሃሊዮን ጋር » ብላ አረጋገጠችለት ባርባራ አየተንቀጠቀጠች « ሃሊዮን
ከወለሉ እንደ ተዘረረ ቤተል ከላዩ ላይ ቆሞ ታይቷታል ያቺ አፊ ደግሞ ከማድ ቤት አጠገብ ቆማ ስትመለከት ትታያታለች " »

« እሳቸው እኮ ሕልም ሰላም እንዲነሣቸው ማድረግ አይገባቸውም ቁመውም
ተቀምጠውም ስለ ግድያው ስለሚያስቡ ስለሱ ሕልም ቢያዩ አያስግርምም " ነገር ግን የሕልሙ ሐሳብ ከሌሊቱ ጋር ለቋቸው እንዲሔድ መጣር አለባቸው "

« አዬ አንተ........... የእማማን ነገር እያወቅኸው " በርግጥ እንደሱ ማድረግ ነበረባት " ነገር
ግን አልቻለችም አባባም ጧት ጧት ብሶባት ሲያይ ለምን እንደ
ሆነ እየገረመው ሲጠይቃት የማትሰጠው ምክንያት የላትም ምክንያቱም ስለ ግድያው ምንም ነገር ለሱ መተንፈስ አይቻልም »

ሚስተር ካርላይል እያዘነ ራሱን ነቀነቀ።

« እማማ ቤተልን ነው እየደጋገመች በሕልሟ የምታየው ትናንትና በበሩ ሲያልፍ አየችው " ሌሊት በሕልሟ መጣባት " እሷ የምትለው ቤተል ገደለው ሳይሆን የሱም እጅ በነገሩ አለበት ነው እና ሁልጊዜ በሕልሟ ይመጣል "

ካርላይል 'ምንም መልስ ሳይሰጥ መንገዱን ቀጠለ" የሚመልሰውም አልነበረውም ከሚስቴር ሔር ቤት እንዲህ ያለ ዳመና ማንዣበቡ አሳዛኝ ነገር ነበር ባርባራ ንግግሯን ቀጠለች "

« እማማ ይህን ሕልም ስለ አየች የሚደርስ ክፉ ነገር አለ እያለች ራሷን ይህን ያህል ማስጨነቋ ትልቅ የዋሀነት ነው » እኔ ቢቸግረኝ አኩርፊያት ዋልኩ አየህ
አርኪባልድ ባሁኑ በሥልጣኔ ዘመን ሕልሞች ወዶፊት ስለሚሆነው ነገር ይናገራሉ ብሎ ማመን ሞኝነት ነው »

« የናትሽ ችግር ከባድ ነው ሰውነታቸውም እየደከመ ሔደ» አላትና ስለዚሁ እየተወያዩ ከበር ደርሰው ሚስተር ካርላይል ሊወጣ ሲል ክንዱን ያዝ አድርጋ በማቆም ድምጿን ልስልስ አድርጋ : « አርኪባልድ ......... » አለችው

« ምነው ? »

« ለዚህ እኮ ምስጋና እንኳን አላቀረብኩልህም » አለችው ሐብሉን ከነሙዳዩ እያሳየችው «ምስጋና ቢስ አድርገህ እንዳትገምተኝ »

« ኤዲያ ለዚህ ደግሞ ምን ምስጋና ያስፈልጋል ? በይ ይልቅ ደኅና እደሪ » አለና ጐንበስ ብሎ ጉንጯን ስሞ ሲያበቃ ዞር ብሎ አይቷት ለሁለተኛ ጊዜ ደኅና
እደሪ ብሏት ሔደ
👍17🥰2😁1
እሷ ግን የሠራ አከላቷን አንድ ስሜት ሲወራት ተሰማት " የደም ሥሮቿን ነዘራት " ትርታዎ በኃይል መቱ ልቧ በደስታ ዘለለ እሷ እስከምታስታውሰው
ከልጅነቷ ጀምሮ ስሟት አያውቅም " ተመልሳ ከቤት ከባች በኋላም ደርሳ ፍንክንክ ሣቅ ቅ ነቃ...ነቃ ስትል እናቷም አይታት እንግዳ ነገር ስለሆነባት ገረማት "

« ባርባራ ... ... ደውይና ፋኖስ አስመጥተሽ ሥራሽን ቀጥይ · የመስተዋት መከለያዎችን አትዝጊያቸው በዚህ ደረስ በሚለው ሌሊት በመስኮቱ ወደ ውጭ መመልከት እፌልጋለሁ " »
ባርባራ ግን ሥራ የሚሉትን አልጀመረችም "እሷም እንደናቷ ወደውጭ መመልከት የፈለገች ትመስላለች ከመስኮቱ አጠገብ ተቀምጣ ከካርላይል ጋር ያሳለፈችው ግማሽ ሰዓት ትዝታው መጣባት " አዬ አርኪባልድ አወድሻለሁ ብሎ ልቤን ቢያሳርፍልኝ ምን ቸገረው ' ' ብላ አሰበች "

ሚስተር ካርላይልገና ከልጅነቱ ጀምሮ ከሔር ቤተሰብ ጋር በጣም የቀረበ ግንኙነት ነበረው " ያባቱ የመጀመሪያ ሚስት ጠበቃው ትልቁ ካርላይል ሁለት ጊዜ ነበር ያገባው የዳኛው ሔር የቅርብ ዘመድ ነበረች " ምክንያት ሁለቴ
ቤተሰቦች በጣም እንዲቀራረቡ አደረጋቸው " (ሁለተኛይቱ ሚስዝ ካርላይል ልጅ የሆነው ያሁኑ አርኪባልድ ካርላይል ያደገው ከሚስተር ሪቻርድ ሔር ልጆች ጋር
ነበር "

ከምሽቱ አራት ሰዓት ተደወለ ሚስዝ ሔር ደስ የማይሉ ሐሳቦችን ያጠፋል እንቅልፍ ያስወስዳል ብላ በማመን ሁል ጊዜ ማታ ማታ የለመደችውን የአንድ ብርጭቆ ሦስት ሩብ ብራንዲና ወሃ ጠጣች ባርባራ መጠጡን ለናቷ ለክታ ሰታ
ከመስኮቱ ሔዳ ቆመች ፋኖሱ ከበስተኋላዋ ይበራ ስለነበር : ከውጭ ሆኖ ለሚመለከት ቅርጹ ቁልጭ ብሉ ይታይ ነበር "

ከሕልም ዓለም መኻል ቁማ ራሷን የካርላይል ሚስት አድርጋ በመቁጠር በምኞት አየር በመንሳፈፍ ትደሰት ነበር ከድፍን ኢስት ሊን ካርላይልን ምነው ልጄን
ባገባልኝ የማትለው እናት ባጨኝ የማትል ኮረዳ አልነበረችም " በተለይ ባርባራ ደግሞ በዓለም ካለው ነገር ሁሉ አብልጣ ትወደው ነበር " በተጨማሪም በአካባቢው ከነበሩት ሁሉ የበለጠ አቻዋ ነበር እኔ እስከ ዛሬ ማታ ድረስ እርግጠኛ አልነበርኩም " አለች ያቺን የመታስቢያ መያዣ ያንገት የወርቅ ሙዳይ እየሳመች
እያቀፈች ከጉንጯ ጋር አጥብቃ እየያዘች ሁልጊዜም አንድ ነገር ይናገር ይሆናል ወይም ምንም ላይገልጽ ይችላል እያልኩ ሳስብ ነበር " ዛሬማ ይኸንን ሲሰጠኝ '
ሲስመኝ አዬ አርኪባልድ እንዲያው ምን ላርግህ ! ብላ ከሐሳቧ ጋር ስትጫወት
ቆይታ ትንሽ ዐረፍ ካለች በኋላ ዐይኖች የጨረቃ ብርሃን ከተንጠለጠለበት ምድረ ግቢ ጣል አዶረገች "

አሁን እንደሚወደኝ ብቻ ቢነግረኝና ይህን የጭንቀት ሸክሜን ከልቤ ቢያርድልኝ ነገሩማ መቸም መሆኑ አይቀር " ብቻ ያቺ ነገረኛ ኮርነሊያ እያለች "

ባርባራ ቆየት ብላ ከገባችበት የሕልም ዓለም ምልስ አለች ሐሳቧን አሰባሰበችና ወደ ደጅ ስትመለከት ከግቢው ጨፌ ወዲያኛው ጫፍ አንድ ነገር ታያት ከዚያው ቦታ ለጥቂት ደቂቃዎች ቆይቷል " በምልክት የሚጣራ የሚመስል የሰው ቅርጽ ነበር ከነበረበት ትንሽ ጠጋ አለና በግልጽ ታየ ባርኔጣውን አወዛወዘው።

ባርባራ ዶነገጠች » አሽከሮችን ለመቀስቀስም አሰበች » ኋላ ደግሞ ቤቱ ስላለበት ምስጢራዊ ችግር አገናዝባ ሐሳቧን ለወጠች ወደ መተላለፊያው ወረዶችና
በበረንዳው ተጋርዳ ቆመች አሁንም ያ ቅርጹ ብቻ የሚታየው ሰውዬ ባርጣውን በጣም አወዛወዘ

ባርባራ ሔር ተቸገረች ፈራች ደግሞም ላታውቀው ለመሸሽ አልፈለግችም " ምን ወይንም ማን መሆኑን ለማወቅ ቆረጠች የሰውየው አመጣጥ ቁርጠኛ
ነበር እሷም ብትሆን ከመሰሎቿ ወጣት ሴቶች ለየት ያለ ድፍረት ነበራት።
«እማማ » አለች በርባራ ወደ ሳሎን ተመልሳ አንድ ያንገት ልብስ ለራሷ እየደረበች « አባባ ሲመጣ ለማየት ነፋስ እየተቀበልኩ ከደጅ ልጠብቀው ወጥቻለው» ሚስዝ ሔር ግን ለራሷ ከሕልም ዓለም ገብታ ስለ ነበር አልመለሰችላትም!
ባርባራ በሩን ቀስ አድርጋ ዘግታ ወደ በረንዳው ወረዶች » ትንሽ ቆም ብላ ራሷን ለማደፋፈር ሞከረች " ያም ሰው ባርኔጣ ማወዛወዙን ቀጠለ "

ባርባራ ሔር እናቷ በሕልሟ አይታ የሚሆን አንድ ክፉ ነገር ይኖራል ያለችውን እያሰበች ፍራት ፍራት ቢላትም ወደ ሰውየው አመራች "..

💫ይቀጥላል💫
👍141🔥1
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በታደለ_አያሌው


...."“እስኪ…” አለች ዶክተር ከብዙ ዝምታ በኋላ፣ ወደ በሩ እያመለከተቻቸዉ። “እስኪ አድ አፍታ ላስቸግራችሁ፣ ዉጪ ጠብቁ ያለ ምንም ጥያቄ ሁሉም ምሰስ እያሉ ሲወጡ፣ በክፍሉ እኔና እሷ ብቻ ቀረንበት.

“ልጄን…” ስል ተቀበልኋት፣ ባልቻን የሸኙ ዓይኖቿ ወደኔ ሲመለሱልኝ፡
“ልጄ አታሳዪኝም?”

“ናፈቀችሽ አይደል?”

“ኧረ አልቻልሁም ሽዊት”

“ይገባኛል። አዉቃለሁ”

“ታዲያ አምጭልኛ”

“እያወቅሽዉ? እንደሱማ አይሆንም”

“እንዴት ናት ግን? እንደ ፈራነዉ ሆነ ወይስ እግዜር ተአምሩን አሳየሽ?” አልኋት፣ ፈራ ተባ እያልሁ።

“ኹለቱም”

የምትለዉን እንድትል ጠበቅኋት፡
“እንደ ፈራሁትም ነዉ፤ እግዚአብሔርም ተአምሩን አሳይቶኛል። ኹለቱንም”

አሁንም ጭጭ ብዬ አዳመጥኋት፡ ጠበቅኋት እያየኋት የግንባሯ ሰማይ ዳመነ፡ የዳመኑ ዓይኖቿም እንባ አዘሉ፡ ምንም ሳይቆይ ያዘለዘለ እንባዋ ቡልቅ እያለ ሲወርድ እኔም አልቻልሁም: የኔም ጉንጮች ቀዝቃዛ እንባ አለፈባቸዉ: ከመሬት ተነስቶ ብርድ አንሰፈሰፈኝ

“ቁርጤን ልስማዉ?” አልኋት፣ መጥፎ ነገር ብትነግረኝ ፍጥርቅ ብዬ ለመሞት እየተሰናዳሁ: ከመሞት በቀር ምን ምርጫ አለኝ? ምንም:: እሞታለሁ

“ግልጹል ንገርሽ: ወደ ኦፕራሲዮን ክፍሉ ስገባ፣ አንቺን ለማትረፍ
እንጂ ልጅሽ በሕይወት ትመጣለች ብዬ አልጠበቅሁም ነበር። በሆድ
ሳለች የልብ ምቷ ስናዳምጠዉ በጣም አስፈሪ ነበር። አንቺም ትናትና እንዳልሽኝ በሆድሽ ዉስጥ እየተንቀሳቀሰች አልነበረም: በዚያ ላይ ከመደበኛዉ የመወለጃ ጊዜ እጅግ ቀድማ ስለመጣች፣ ላንቺ ፈርቼልሽ ነበር: በግልጽ ልንግርሽ አይደል ዉብዬ? የልጅሽ በሕይወት መትረፍ፣ ያንቺም በጤና መገላገል የእግዚአብሔርን ሥራ በዓይኔ በብረቱ ያየሁበት
ተአምር ነዉ”
“እንግዲያዉ ምድነዉ የሚያስለቀሰሽ?”
ለመናገር ዳዳችና ተወችዉ፡፡

በጥያቄ የተጥለቀለቀ ፊቴን ስታይ ቆይታ፣ የነርሶቹን መጥሪያ ደወል ተጫነችዉ፡ ደወሉን ሳትለቀዉ ገና፣ ከቅድም ጀምራ በተለየ ሁኔታ ጠብ እርግፍ ስትልልኝ የነበረችዋ ነርስ ያለንበትን ክፍል ከፈት አድርጋ ገባች
“አቤት ዶክተር''
“እስኪ ባክሽ አንድ ነገር ላስቸግርሽ”
“ምን ልታዘዝ ዶክተር?''
“እስኪ ባክሽ ዉብርስት ወደ lCሀ ክፍል እንዉሰድና አንዳፍታ ልጇን
በዓይኗ እናሳያት”
“ኧረ?” አለች፣ ድንግጥ እያለች:
“አይዞሽ፤ አብሬሽ አለሁ: ኃላፊነቱን ራሴ እወስዳለሁ” ስትል
አደፋፈረቻት፣ ነፍሴን የያዘልኝ ግሉኮስ የተንጠለጠለበትን ዘንግ ራሷ ከፍ አድርጋ እያነሳችና መንገድ እየጀመረች:

ነርሷም ትንሽ እንደ ማቅማማት ስትል ከቆየች በኋላ መታዘዟን
አስበልጣ የተንጋለልኩበትን አልጋ
ማሽከርከር ጀመረች መኪና ማቆም ከሚያያስችለዉ የሕንጻዉ ሰፊ አሳንሰር ከነአልጋዬ ከጫኑኝ በኋላ ኹለት ፎቆች ወደ ላይ ወሰዱኝ፡ ከአሳንሠሩ ወርደን ትንሽ እንደ ሄድን፣ ጥልቀት ያለው እንክብካቤ ወደሚደረግበት (ICU) ክፍል ደረስን፡ እጅግ ሰፋ
ወዳለዉ አዳራሽ ከመግባቴ፣ የተለያየ ስምና መጠን ያላቸዉ ማሽኖች ተደርድረዉ አየሁ፡ በአብዛኛዎቹ ማሽኖች፣ በተለይም ያለ ዕድሜያቸው የተወለዱ ሕጻናት ተኝተዉባቸዋል፡ ያዉም በሆድ፣ አፍና አፍንጫቸ
ላይ በልዩ ልዩ ማስተላለፊያዎች ተተብትበዉ፡ በነዚህ ትብታቦች
አማካኝነት በዋናነት ምግብ እና አየር የሚያገኙ ሲሆን፣ ማሽኖች
የየራሳቸዉ ማሞቂያም ሆነ ማቀዝቀዣ የተሟላላቸዉ መሆናቸዉን በስማቸዉ አዉቃቸዋለሁ መሀል ለመሀል እየወሰዱኝ ሳለ፣ በግራም
በቀኝም በኩል ዓይኔ ዉስጥ የገቡትን ሕጻናት ሥራዬ ብዬ ተመለከትሁ ሁሉም እንደየአቅማቸዉ እግርና እጃቸዉን ያወራጫሉ።

ቱናትን ላያት ነዉ፡

ብዙ የተገመተላትን፣ የልጄን ዓይን በዓይኔ ላየዉ ነዉ፡፡ ልጄ ቱናት
ያለችበት ክፍል ዉስጥ መሆኔን ሳዉቅ፣ ይኼ ነዉ ብዬ መግለጽ
የማልችለዉ ሽብር ወረረኝ፡፡ ፍርሃቴም ናፍቆቴም ተደራርበዉ ልቤን ጫፍ ላይ አደረሱብኝ፡፡ ልትወጣ ምንም አልቀራትም፡፡

ፍርሃቴ ጫፉ ላይ ደርሷል፡

“ይቅርታ” አለች ዶክተር፣ ወደ ነርሷ ዘወር ብላ፡ ሲመስለኝ ቱናት
ያለችበት አጠገብ ደርሰናል በዓይኔ ባጣብራት ግን ላገኛት አልቻልሁም ጭንቅላቷ ከፍ ያለ ልጅ ፍለጋ ዓይኔን ባንከራትትም አላገኘኋትም፡ የዶክተሯ ጥቅሻ ገብቷት ነርሷ የያዘችዉን የአልጋዬን ብረት ለቀቀችና
ተመልሳ ወጣች:: ኹለት የክፍሉ ባለሙያዎች በክፍሉ ያሉ ቢሆንም፣በማሽኖች አጠገብ ግን አይደለም የቆሙት ዝም ብለዉ ብቻ እንደ ንቁ ወታደር፣ ወዲያ ወዲህ ይንጎራደዳሉ።

እኔም እሷም ወደ'ዚህ ክፍል ለመግባት፣ ቢያንስ የእነሱ ፈቃድ
እንደሚያስፈልግ እኔም ገምቻለሁ
በመሆኑም በየስማቸዉ ጠርታ ሰላም እያለቻቸዉ ወደ እነሱ ቀረበች: ምን እንደ ተባባሉ ባይሰማኝም፣ ብቻ የሆነ ነገር ብላ አሳምናቸዉ መጣች: በአንድ እጇ ግሉኮስ የተንጠለጠበትን የብረት ዘንግ፣ በሌላ እጇ ደግሞ አልጋዬን በትራስጌ በኩል እየገፋች ዉስጥ ለዉስጥ ተሂዶ ወደሚገኝ ሌላ ክፍል አደረሰችኝ፡: ጠጋ ብላ
ካነጋገረቻቸዉ ባለሙያዎች አንደኛዉ ቀደም ብሎ በመዳፉ አሻራ በሩን ከፈተልንና ገባን፡፡ እሱን በደረቅ ፈገግታም ጭምር እጅ ነስታ ከሸኘችዉ በኋላ፣ እስከ አሁን በጭራሽ አይቼባት የማላውቀዉን ፊቷን አሳየችኝ፡፡

ከተለዩትም የተለየ እክብካቤ ስለሚያስፈልጋት፣ ልጅሽ ያለችዉ
በዚህኛዉ ለይቶ ማቆያ ክፍል ነዉ: ልጅሽን የማየት መብት ቢኖርሽም፣ መንገዱ ግን አሁን የመጣንበት አይደለም: እንግዲህ ያለ ግርግር መምጣት የፈለግሁበት ምክንያት አንቺም የምታጭዉ አይመስለኝም”
ለጥያቄ አፌን እያሞጠሞጥሁ ሳለ፣ ቀልጠፍ ብላ ከአጠገባችን ያለዉን ማሽን ቁልፎች መነካካት ጀመረች ማሽኑ እጅግ ግዙፍ ሲሆን፣ ከላይ የተገለበጠ ሙኸዶ የሚመስል ክዳን አለዉ፡ ልክ መነካካት ስትጀምር፣
ቀድሞ ወደ ላይ ተስቦ የተከረፈደዉ ይኼዉ ክዳን ነዉ፡ በእርግጥ ክዳኑ ብርሃን አስተላላፊ ስለሆነ፣ ለቆመ ሰዉ እንደ ተከደነም ቢሆን ወደ ዉስጥ
ከማየት አይከለክልም፡ እኔ ግን እንደ ተንጋለልሁ ስለሆነ ተከፍቶልኝ እንኳን ልጄን ማየት አልቻልሁም እስከመጨረሻዉ ድረስ አልጋዬን ከወገብ በላይ አቃንታልኝ፣ ራሷ የመሸከም ያህል ደግፋ ቀና አደረገችኝ
እና ወደ ዉስጥ እንድመለከት አመቻቸልኝ፡

በሙሉ ዓይን ባይሆንም፣ አንገቴን ቀና አድርጋ አሳየችኝ አየኋት
ቱናትን አገኘኋት።እንደ ተፈራዉ ናት።

“ስንት ኪሎ ሆነች?” አልኋት፣ የጭንቅላቷን ግዝፈት እያስተዋልሁ፡አትሆንም እንጂ ኹለት ኪሎ እንኳን ብትሞላ ከግማሽ በላዩን የሚመዝነዉ ጭንቅላቷ እንደሚሆን ያስታዉቃል፡ ዓይኖቿ ወደ ዉስጥ
መቀበራቸዉ ሳያንስ ከተመለከቱም የሚመለከቱት ቁልቁል ብቻ ነዉ፡ እንቅስቃሴ የሚባል የላትም፡ የተኛ ሰዉ እንኳን ሲተነፍስ ሆዱ ላይ ብቅ ጥልቅ ይታይበታል፡ ልጄ ግን ጸጥ ብላለች፡ እኔን ልጄ!

“መቼስ እግዚአብሔር ምን ይሉታል?” አልሁ፣ ተአምሩን ለእኔም ያልገለጠልኝን አምላክ በመቀየም እና በማመስገን መካከል ሆኜ:

“ኧረ እንጃ። ከፊት ለፊትሽ ግን እንዲህ ነዉ የማይሉት ፈተና እንዳለ ልዋሽሽ አልፈልግም: ትእዛዝ ተቀባይ ነርቮች ብዙዎቹ በትክክል አይሠሩም: ስፓይናቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ ከጠበቅናቸዉም በላይ ሆነዉ
👍30
ነዉ የገጠሟት: ጭንቅላቷ ዉስጥ ከመጠን በላይ ፈሳሽ ተከማችቷል:: ምንም እንኳ ን ስስ ቆዳ ቢለብስም፣ የጀርባ አጥጓቷም ላይ ክፍተቱ ተፈጥሯል። ያንን ያልኩሽ nurosurgean ጨምሮ፣ በዚህ ዙሪያ የማዉቃቸዉን ባለሙያዎች እንዲያማክሩኝ ጠይቄያቸዉ ነበር።ሕክምናዉን መሞከሩ ጊዜ የሚሰጠዉ ጉዳይ ባይሆንም፣ አሁን ባለችበት ሁኔታ ደግሞ ኦፕራሲዮን ማድረግ የማይሆን ነዉ። ብቻ ግልጽ ሆኜ
ስነገርሽ፣ ከአንቺ ጥንካሬ እና ከማይነጥፈዉ የእግዚአብሔር ተአምር በቀር መፍትሔዉስ ላይ እንጃ። በጣም ፈርቻለሁ” አለችኝ፣ ጭንቅ እና ሳግ ባነቀዉ ድምፁዋ፡
“በድየህ የለ? ኃጢአቴ ዉጤት ናት?” አልሁ፣ በጣሪያዉ በኩል
ከእግዚአብሔር ጋር ለመተያየት እየፈለግሁት፡ “እስኪ በማርያም ንገሪኝ ሽዊት፤ የቱናት ነገር እንዲህ መሆኑ የማይቀር መሆኑ ካወቅሁ በኋላ በተለይ፣ ማድረግ ኖሮብኝ ያላደረግሁት ነገር ነበር እንዴ?" አልሁ እግዜርን ሳጣዉ ወደ ዶክተሯ አፍጥጬ፡ “እሺ የኔን ተዪዉ፣ አንቺስ ማድረግ እያለብሽ ያላደረግሽልኝ አለ? ግልጽነትሽን ከእኔ ከጓደኛሽ በላይ የሚያዉቀዉ አይኖ መቼስ: ንገሪኝ እስኪ በግልጽ፤ አለ?”

አንገቷን ደፍታ ጭጭ አለች፡

“የለም አይደል?”

“እኔም አንቺም ሃይማኖተኞች ነን። እግዚአብሔርን እናምናለን”
“ባናምንስ ምርጫ ነበረን?”
አሁንም ጸጥ ብላ ቱናትን ወዳስተኛዉ ማሽን ዓይኗን ተክላ ቀረች በእኔ ቤት መጠንከሬ ነዉ፡ ከሰጠኝ መቀበሉ አይቸግረኝም ማለቴ ነበር።
ከትናንት ጀምሮ እስከ አሁኗ ቅጽበት ድረስ እኔ እሷ፣ እሷ ደግሞ እኔን ነበር የምንመስለዉ፡
እግዚአብሔርን ለሚያመልኩ የሚነገር ባይሆንም፣ ካማከርኋቸዉ አንደኛዉ ያለኝን ልንገር ሽ ?»

አንገቴን በአዎንታ መታሁላት። ንገሪኝ እንደ ማለት

“ያዉ፤ የኔ ሐሳብ ግ አይደለም”

“ገብቶኛል”

“ አትቀየሚ ኝም? '

“ቆይ ለምንድነዉ የምቀየምሽ?” ኮስተር ብዬ አየኋት።

“ያዉ፤ ካማከርኋቸዉ ባለሙያዎች መካከል አንደኛዉ ወደ ማሞቂያ
ማሽን እንዳላስገባት መክሮኝ ነበር''

“እ? ምን ማለት ነዉ?”

“ቅድም ማድረግ እያለብሽ ያላደረግሽልኝ አለ ወይ ብለሸ ልጠየቅሽም ?”

“እና?”

“እኮ! እኔም ከኦፕራሲዮን እንደ ወጣሁ፣ ይኼንኑ ጥያቄ ያንን ባለሙያ ጠይቄዋለሁ: እሱ በእኔ ቦታ ቢሆን የሚ ያደር ገዉ ን ስጠይቀዉ፣ ወደ ማሞቂያ ክፍል እንዳታስገቢያት ነበር ያለኝ እንግዲህ ይኼ ሙያዊ
ዉሳኔ እንዳልሆነ እሱም የሚጠፋዉ አይመስለኝም: ግን እንዲህ ዓይነት ዉስብስብ እክል የገጠማቸዉ ሕጻናት ማለቂያ ከሌለዉ የወደፊት የዕድሜ
ዘመን ስቃይ ማትረፊያ መንገዱ ይኼ ብቻ ነዉ ብሎ ያምናል እሱ”

“እኮ ልትገድሏት?” አልኋት፣ በምን ተአምር ከአልጋዬ እንደ ተነሳሁ
ሳይታወቀኝ፡ በቂጤ ቁጭ ብያለሁ...

ይቀጥላል
👍18
#ሳቤላ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...አሮጌዉ ቤት በጨረቃ ብርሃን ሲታይ ጸጥ ቅዝቅዝ ብሎ ነበር " ያንለት ደግሞ ጨረቃዋ በጣም ደምቃለች « በብርሃንዋ ሰፊው ያታክልት ቦታም ዳር እስከ ዳር
ቁልጭ ብሎ ይታያል " በአየር ሁኔታ ማሳያው ያውራ ዶሮ ምሥል በበረንዳውና በባርባራ ላይም በማብራቷ ተለይተው ይታወቃሉ ባርባራ በረንዳውን ቀስ ብላ
አልፋ በፍርሃት ለጭንቀት እንዳፈጠጠች ከአትክልቱ ሥፍራ በታች ወደነበሩት እጅብ ያሉት ዛፎች ወረደች ያ ከዱሩ ወጥቶ እሷን በድብቅ ሲጠቅሳት የነበረው
ፍጡር ሌላ ተጨማሪ መዘዝ ይዞ የመጣ ሰው ይሆን ? ወይም †ፈጥሮው ከሰው የተለየ ልዩ ጉድ ነው ? ወይስ በውን የሌለ በሐሳብ ብቻ የተፈጠረ ባዶ ራዕይ ነው?
የሚሉ ጥያቄዎች በባርባራ አእምሮ ሲተራመሱባት አሁንም ቀረብ ብሎ ጠቀሳት ባርባራ ከፍራቷ የተነሣ እግሮቿ እየተንቀጠቀጡ ያንገት ልብሷን ጭምድድ አድርጋ ያዘች በጠራው ጨረቃ እሷ ወደሱ ስትጠጋ እሱ ደግሞ ወደ ዛፎቹ ጥላ አፈገፈገ" ባርባራ ቆም አለች

« ማነህ ? ምንድነህ ? » አለችው ድምጿን ዝቅ አድርጋ!«ምን ትፈልጋለህ ? »
« ባርባራ » ብሎ ጠራት በሹክሹክታ ድምፅ «አላወቅሽኝም ? » ገና ከመናገሩ
ድምፁ በትክክል ለየችው » ከደስታ ይልቅ ፍራት ያመዘነበት ድምፅ አሰምታ ተንደርድራ ወደሱ ሔዶች » በእርሻ ሥራ የዋለ ገበሬ የሚለብሰውን ዐይነት ልብስ
የለበሰ ሰው በክንዶቹ ዕቅፍ ሲያደርጋት ሥቅሥቅ ብላ አለቀሰች " የሥራ ካፖርት
ደርቦ የሣር ባርኔጣ ደፍቶ ሰው ሠራሽ ሪዝ አድርጎ ፍጹም ሌላ ሰው መስሎ ቢመጣም ወንድሟ መሆኑን ዐወቀችው

« ሪቻርድ ! ከየት መጣህ ? ከዚህ ምን አመጣህ ? እኔ ደግሞ ምናልባት ካንተ የተላከ ሰው እንደሆነ ብዬ ተጠራጠርኰ እንጂ እንደዚህ ሆነህ ትመጣለህ ብዬ
አላሰብኩም " አሁንም በጣም ነው ያስደነገጥኸኝ እውነት በጤናህ ነው ወይስ ዐብደህ የመጣኸው ? እዚህ ብትገኝ ሞት እንደሚጠብቅህ እያወቅህ እንዴት ደፍረሀ ትመጣለህ ? » አለችው እጆቿን እያፋተገች

«ያውም ከወንጀለኛ መስቀያ ላይ ነዋ እንደምገደል መች ጠፋኝ ባርባራ ዐውቀዋለሁ " »

« ታዲያ ለምንድን ነው ወደ መጥፈያህ ስተት ብለህ የመጣህ ? እማማ ብታይህ
በአድራጐትህና በድፍረትህ ደንግጣ ትሞታለች »

« ኑሮውን አልቻልኩትም ከወጣሁ ጀምሮ እስከ ዛሬ ለንደን ስሠራ ነበር ነገር ግን በዚሁ ዐይነት መግፋት አልቻልኩም
" ትንሽ ገንዘብ ባገኝ ግን ከዚህ የተሻለ ዕድል አለኝ " ስለዚህ አማማ ጥቂት ገንዘብ ብትሰጠኝ ለመጠየቅ ነው የመጣሁት»

« እስከ ዛፊ ምን ትሠራ ነበር ? »

« በአንድ የፈረሶች ጋጣ ውስጥ ነበር የምሠራው " »

« ምን ! በፈረሶች ጋጣ ? »
አለችው የእውነቷን ድንግጥ ብላ»
"ከዚህ የተሻለ ምን ዕድል ሊኖረኝ ይችላል ? ነጋዴ ? ባንከኛ ? መይስ የንድ ሚኒስትር ልዩ ጸሐፊ መሆን ? ነው ወይስ ንብረት ኖሮኝ በሀብቴ ልተዳደር?» አላት
የሆዱ ብሶት እየተናነቀው « አየሽ የምተዳደረው በሳምንት በማገኛት
ዐሥራ ሁለት ሽልንግ ብቻ ነው»

« አዬ ሪቻርድ ! » አለች እጁን ግጥም አድርጋ ይዛ እያለቀስች
« እንዴት ያሉ ጐደሎ ቀን ነው ? አየህ ......... እኛ የምንጽናናው ድርጊቱ በደም ፍላት እንጂ
ሆን ብለህ እንዳልፈጸምከው በማሰብ ብቻ ነው»

« ባርባራ እኔ እኮ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም »

« ምን? »

« በውነት እምልልሻለሁ ። ከደሙ ንጹሕ ነኝ እንዳያውም ሰውየው ሲገደል እኔ ከቦታወ አልነበርኩም " እስከማውቀው ድረስ በግምት ካልሆነ በቀር እገሌ ሲገድል አየሁ ብዬ በዐይን ምስክርነት መናገር እንኳ አልችልም " አላየሁም "
ግምቴ ግን ከማየት የማያንስ ትክክለኛ ነው »

ባርባራ አሁን በበላጠ አንዘረዘራት « መቸም ወንጀሉን የፈጸው ቤተል
ማለትህ እንዳልሆነ እርግኛ ነኝ »

« ቤተል ? እሱም በነገሩ የለበትም እሱ ለራሱ በድብቅ አውሬ ያድን
ነበር ፤ ወጥመዶቹን ነበር የሚከታተል »

« እማማ ግን በወንጀሉ የቤተል እጅ አለበት ያለች አላስቀምጠኝ አለች»

« ተሳስታለች እሱን እንድትጠረጥር ያዪረጋት ምንድነው ? »

« ከመጀመሪያ ይህ እምነት እንዴት እንዳደረባት ልነግርህ አልችልም እሷም ራሷ የምታውቀው አይመስለኝም " ወትሮም ቢሆን ምን ያህል ደካማ እንዶሆነችና በሐሳቧ የሚመጣባትን ሁሉ እውነት መስሎ እንደሚታያት አንተም ታስታውሳለህ አሁን ከዚያ አሠቃቂ ምሽት ጀምሮ ስለ ግድያው ሁልጊዜ ሕልም ታየኝ ትላለች በሕልሟ ውስጥ ሁሉ ቤተልም አብሮ ይታያታል " ስለዚህ ቤተል በነገሩ እንዳለበት ያለ ምንም መጠራጠር ታምናለች »

« ባርባራ እሱ በዚህ ጉዳይ አልነበረበትም »

« አንተ እንዳልነበርክበት ነው አሁን የምትነግረኝ ? »

« እኔ በዚያን ጊዜ ከሆሊጆን ቤትም አልነበርኩ " ወንጀሉን የፈጸመ ቶርን ነው»

« ቶርን ? » አለች አንገቷን ቀና አድርጋ « ቶርን ማነው ? »
« እንጃ ! ባውቀው ደስ ይለኝ ነበር ከገባበት መዝዤ ባወጣው በወደድኩ ሰውየው የአፊ ወዳጅ ነበር ። »

“ሪቻርድ !! ... ይህን ስም ስታነሣብኝ ራስህን የዘነጋህ መስልከኝ ” አልችው አንገቷን በቁጣ ወዶ ኋላ ምልስ አድርጋ

«እኔ!ኮ አንድ ጊዜ ያበላሸሁት ስለሆነ በጉዳዩ ለመነጋገር አልሻም " አሁን ስለ ንጽሕናዬ ብናገር ሪቻርድ ሔር ትንሹ በፈጸመው የግፍ ግድያ ተብሎ የተላለፈብኝን ውሳኔ ሊያስለውጥልኝ አይችልም። ግን አባባ ዛሬም እንደ ጠላኝ ነው »

«ከፊቱ ስምህን የሚያነሣ የለም " ከቤት አንድም ሰው ስምህን እንዳይጠራ ለአሽከርቹ በሙሉ ትእዛዝ ሰጥቶአል " ያቺ ኤልሳ መቸም የተነገረችውን ማስታወስ አይሆንላትም " መኝታ ቤትህን የሚስተር ሪቻርድ ክፍል " እያለች ስትናገር ሁለት ጊዜ ቢያስጠነቅቃትም እየረሳች መተው አልቻለችም " በሦስተኛው ከቤት አባረራት ። አባባኮ ምሏል ሰም†ሃል ? »

« ምን ብሎ ? እሱ ሁልጊዜ እንደማለ ነው »

« ያሁኑ ግን ከባድ መሐላ ነው ሪቻርድ።ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ከ0ሥር ዓመት በኋላ ቢገኝ እንኳን አሳልፎ እንደሚሰጥህ ከዳኞቹ ፊት ቁሞ በመማል አረጋግጦላቸዋል እሱ አንድ ጊዜ ከተናገረ እንደማይመለስ ታውቀዋለህ » ስለዚህ ያንተ ከዚህ አካባቢ መገኘት አደገኛ ነው»

« እሱኮ ዱሮውንም እንዶ ልጁ እንዳልቆጠረኝ ሊያደርግልኝ የሚገባውን እንዳላደረገልኝ ዐውቃለሁ » አለ ምርር ባለ አነጋገር « እስኪ አንቺ ስታስቢው
ጤና በማጣቴ ምስኪኗ እናቴ ስለ ተንከባከበችኝ በየደረሰበት ላገኘው ሰው ሁሉ ተሞላቀቀ እያለ ሊያሥቅብኝ ይጥር ነበር እኔ ቢቴ የደስታ ቤት ቢሆንልኝ ኖሮ ይኸ ሁሉ መቸ ይደርስብኝ ነበር ? በይ አሁን ... ...ባርባራ እናቴ ጋር ዐይን ለዐይን ተያይተን መነጋገር አለብን»

ባርባራ ከመናገሯ በፊት ትንሽ አሰበች« እንዴት እንደ ምናሳካው አላውቅም»
« ለምን አንቺ እንደ መጣሺው እሷስ ወደኔ አትመጣም? ለመሆኑ ተኝታለች ወይስ ተነሥታለች ? »

« ዛሬ ከሷ ጋር መተያየት የማይሆን ነገር ነው አባባ ሳናስበው ሊመጣ ይችላል
አሁን ያለው ከቦሻ ቤት ነው»

« ዐሥራ ስምንት ወር ሙሉ ሳንተያይ ኖረን አሁን ደግሞ ሳላገኛት ብሔድ በጣም ከባድ ነገር ነው » አለ ሪቻርድ «የገንዘቡ ነገርስ? አንድ መቶ ፓውንድ ነውየምፈልገው »
👍24😁2
« ነገ ማታ ተመልሰህ እዚ ድረስ መምጣት አለብህ ሪቻርድ " ገንዘቡን ግድ የለም ታገኛለህ ከእማማ ጋር ስለ መገናኘትህ ግን እንጃ እንዳትያዝ ነው ከፍተኛ ሥጋቴ ግን አንተ እንደምትለው ከወንጀሉ ንጹሕ ከሆንክ» አለች
ዝም ብላ ትንሽ ከቆየች በኋላ «በማስረጃ ማረጋገጥ አይቻልም?»

«ማን ያረጋግጠዋል ? የቀረበብኝ መሪጃ ከባድ ነው የቶርን ጉዳይ እንደሆነ ለኔ እንጂ ለሌላው እንቆቅልሽ ነው ስለሱ በቅጡ የሚያቅ ሰው የለም " »

« ሪቻርድ ......ሁኔታውን ግልጽልጽ አድርገህ ለአርኪባልድ ካርላይል
ብትነግረውስ ? ማንም ሰው ሊረዳህ የሚችል ከሆነ ለእሱም አያዳግተውም » ሰውየው የሰው መጨረሻ ነው»

« ምስጢሬን አምኜ ላካፍለው የምችል ከሚስተር ካርላይል በቀር ሌላ ሰው ማንም የለኝም " ለመሆኑ ባርባራ የት ነኝ እባላለሁ ? »

« ግማሹ ሙቷል ይልሃል ሌላው አውስትራሊያ ገባህ ይላል " እማማንም አስጨንቆ የያዛት ይኸ ቁርጡ ያልታወቀ ሁኔታህ ነው »

«እኔ ለንደን ግብቼ ነው የተቀመጥኩት ሌላዉ ወሬ ዝም ብሎ ነው »
« ከፈረሰ ጋጣ እየሠራህ ? »
« ከዚያ የተሻለ ሥራ ማግኘት አልቻልኩም " በምንም ሙያ አልሠለጠንኩማ » ስለ ፈረሶች ግን ጥቂት ልምድ ነበረኝ" በተለይ ደግሞ ' ፖሊሶች በየሔደበት ለሚከታተሉት ሰው እንደዚህ ያለ አልባሌ ቦታ አስተማማኝ መሸሸጊያ ነው "የትልቅ ስው ልጅ ከዚህ ገብቶ ይሠራል ብለው አይጠረጥሩም»

እነሱ ይህን ሲነጋሩ ያባታቸውና የሚስተር ስፒነር ንግግር ከወደ አጥር በሩ ተሰማቸው ወዲያው ሚስተር ሔር ዐልፎ ገባና በሩን ዘግቶ ቤት አቀና "

« በል ሪቻርድ..... እንግዲህ ነገ ማታ እዚህ ድረስ እንድትመጣ አሁን ልሒድ » አለችና ልትሮጥ ስትል ክንዷን ያዝ አደረጋት "

« ከነገሩ ንጹሕ ነኝ ስልሽ ያመንሽኝ አልመስለኝም እኔ የነገርኩሽ እወነቴን ስለሆነ ምንም አትጠራጠሪ " እኔ ምንም አላደረግሁም " ሆሊጆንን የገደለው ቶርን ነው » አላት "

ባርባራ ከጫካው ወጥታ ወደ ቤት እየሮጠች ሔዶችና አባቷ ከቤት ገብቶ በሩን ሲቀረቅር ደርሳ « ኧረ ቆይ አባባ » አለችው "

« በዚህ ሰዓት ከውጭ ምን ታደርጊያለሽ ? »

«አንተን ለማየት ወደ በሩ ሔድኩና ሳጣህ ጊዜ በቀጭኗ መንግድ ስዘዋወር ነበር አላየኸኝም ? »

ባርባራ ይኸን የመሰለ አስገዳጅ ሁኔታ ስለ ገጠማት እንጂ ውሸት አታቅም - « አመስግናለሁ
አባባ » ብላው ገባች።

« አንድ ሰዓት ቀደም ብለሽ መተኛት ነበረብሽ » አላት ቆጣ ብሎ።....

💫ይቀጥላል💫
👍223👏1🎉1
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና መልኳ ልውጥውጥ ብሏል። ከቤት እንደደረሰች የበሩን ቁልፍ ከፍታ ገባችና በረጅሙ የእግር ጉዞ የዛለ ሰውነቷንና በደረሰባት የሕይወት ፈተና የደከመ አእምሮዋን ለማሳረፍ ከሆስፒታል ይዛ የመጣችውን የምግብ ሣህን ወደዚያ ጣል ካደረገች በኋላ፤ ከአሮጌው ሶፋ ወንበር ላይ መቀመጥ ሳይሆን ሄዳ ስትወድቅበት ተንቋቋ፡፡ በቤቱ ውስጥ የቀረው ጥሪት…»
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በታደለ_አያሌው

...“እኮ ልትገድሏት?” አልኋት፣ በምን ተአምር ከአልጋዬ እንደ ተነሳሁ ሳይታወቀኝ፡ በቂጤ ቁጭ ብያለሁ

“ሽዊት? ለካ እስከዚህ ድረስ ጨካኝ ሆነሻል?”

“መቼም እኔን ታዉቂኛለሽ:: እኔ በሙያም በእምነትም ዓይን ስለማየዉ፣ እንደማልስማማበት ታዉቂያለሽ: ግን በእሱ እምነት ይኼ መግደል ሳይሆን ማዳን ነዉ”

“ቆይ ቆይ! ለምንድነዉ ይኼን ለኔ የምትነግሪኝ አሁን?”

“እኔ እንጃ: ምናልባት እንዲህ ያለ እምነት ያለዉ ሐኪም መኖሩንም
ማወቅ ከፈለግሽ ብዬ እደሆነ”

“አወቅሁ: ከዚያስ?”

“እመኚኝ ዉቤ፣ እኔም አልተስማማሁበትም…”

“በቃሽ!”

ንዴት አቅሌን አሳተኝ፡፡

ክፉና ደጉን የተጋራኋት የቀድሞ ጓደኛዬ አስጠላችኝ፡ ብዙ የተፈተንሁባትን ልጄን መግደል እንደ ማዳን የሚቆጥር ወዳጅ እንዳላት ከነገረችኝ በኋላ፣ ፈጽሞ ዓይኗን አያሳየኝ አልሁ: ዉዬ አድሬ ሳብሰለስለዉ እንዲያዉም፣ ሐሳቡ የወዳጇ ብቻ ሳይሆን የእሷም ጭምር መሆኑን ስለጠረጠርሁ ለሆስፒታሉ አስተዳደር ሳይቀር ከሰስኋት። እሷ የነገረችኝ ለብቻዬ ቢሆንም፣ እኔ ግን ያላዳረስሁባት ሰዉ የለም፡፡

ጨርሼ፣ እንደ ቀዉስ ሆኜ ሰነበትሁ።

ቱናትን ከተገላገልሁ ዛሬ ኹለት ወር ስለ ሞላኝ ቱናትን ይዤ
ከሆስፒታል የምወጣበት ቀን መሆኑን ሰምቻለሁ ዛሬ፣ በጥልቀት
እንክብካቤ ይደረግላት ከነበረችበት ክፍል ወጥታ በእቅፌ ትገባለች ጡቶቼን አጉርሻት በእናት ስስት እያየኋት፣ እስከማጠባት ጓጉቻለሁ።በዚ ላያ ላይ የሆስፒታል ቆይታዬም ጉሮሮዬ ላይ ደርሷል፡ ከዚህ በላይ
እንደ እስረኛ በአንዲት ጠባብ ክፍል ተከልክዬ ለመሰንበት ቀርቶ
ለአንዲትም አዳር የሚበቃ ትዕግሥት የለኝም፡ ሙጥጥ ብሎ አልቋል።

“በሉ ልጄን አምጡልኛ፣ ልዉጣበት” አልኋት ነርሷን፣ መጥሪያዉን ደዉዬ እንደ መጣችልኝ፡

“ሂሳብ ክፍል ያለዉን ነገር ጨረስሽ? ከጨረስሽ መዉጣት ትችያለሽ''

ልክ ይኼን ብላኝ ስትጨርስና ባልቻ በሩን ከፍቶ ሲገባ አንድ ሆነ፡
ከሆስፒታሉ ያለብን ቀሪ ሂሳብ ቀድሞም ተነግሮን ስለነበር፣ ገንዘቡን ይዞልኝ መምጣቱ ነዉ፡ የሚከፈለዉን ከፍለን፣ የሚፈረመዉንም ሁሉ
ፈርመን ስናበቃ፣ ቱናት ኹለት ወር ሙሉ ጥልቅ እንክብካቤ ስታገኝበት ከነበረዉ ልዩ ክፍል በነጭ ፎጣ ተጠቅልላ መጣችልን፡፡ ያመጣችልንን
ነርስ ደህና አድርገን አመሰገንናት፡ ልጄን ተቀብዬ ላቅፋት እጄን ስዘረጋ ሁሉ፣ ቅር ብሏታል ነርሶች ግን ታድለዉ! ልበ ጥሩዋ ነርስ፣ ቱናትን የሰዉ ሰዉ ሳትል እንዴት እንደምትሳሳላት ሳይ እንደገና አመሰግንኋትአስከትላም ልናደርግላት የሚገባዉን ጥንቃቄ
አስረዳችን: ቱናት ራሷን ችላ ካካ ማድረግ ስለማትችል ትንሿን ጣታችንን እየተጠቀምን እንዴት ማጸዳዳት እንዳለብን አደራ አለችን በተጨማሪም ሌሎች ማስታወሻዎች በሥዕላዊ መንገድ የተገለጹበትን መጽሔት
ሰጠችንና፣ አስታቀፈችኝ፡፡
ልጄ ቱናትን ለመጀመሪያ አቀፍኋት፡

ከወለድኋት ከኹለት ረዣዥም ወራት በኋላ፣ ከቱናት ጋር ትንፋሽ
ለትንፋሽ ተገናኘን፡ ወደ ታች ተቀብሮ ግራና ቀኝ እንደ ነገሩ ከሚቃብዘዉ ዓይኗ እና ሲር ሲር ከሚለዉ የጭንቅ ትንፋሿ በቀር እንዲህ ነዉ የሚባል
እንቅስቃሴ የላትም፡ እግሯ አይላወስም፡ ጡቴን ዳብሳ ታገኘዋለች ብጠብቅም፣ አፏ ላይ አድርሼላት እንኳን ጎርሶ መጥባቱ አልሆንልሽ አላት፡ ዝም ብዬ ጭምጭም እያደረግሁ ሳምኋት
ትንፋሿን አሸተትሁት ደስ ይላል
“ወደ እመዋ ቤት አይደል?” አለኝ ባልቻ፣ መኪናዉ ዉስጥ እንደ ገባን የወንበሩን ቀበቶ በትካሻዉ ላይ እያዋለ፡፡ ቁልፉን ወደ ቀኝ ጠምዝዞ ሞተሩን አስነሳና፣ በፊተኛዉ መስታዎት ወደ ኋላ እያየኝ መልሴን
ተጠባበቀ

“አይ እኔ እንኳን ቤቴ ነበር መሄድ የፈለግሁት” አልሁት፣ ሲራክ ፯ ወደ ተከራየልኝ ምስጢራዊዋ የግሌ ቤት ለመሄድ በመምረጥ፡ “ለእመዋም ተጨማሪ ጫና ከምሆንባት፣ ፈተናዬ ራሴ ብወጣዉ ነበር የሚሻለኝ።
እሷን ለማሳመን የሚሆነዉን ምክንያት ግን ከየት ልዉለደዉ?”

“አለማፈርሽ!” አለ፣ ባልቻ “ሆ!”

“የአራስ ወጉ እዳይቀርብኝ ብለህ ነዉ?”

“ኧረ ተዪ አቺ! እናቷን አስቀምጣ ለብቻዬ ካልታረስሁ ያለችዋ
የመጀመሪያዋ እናት ልትሆኚነዉ እንዴ? ሆ! በይ ተይ፤ ዕድልሽንማ
አትቀልጅበት!''

“በል እሺ እንሂድ”

“ወደ እመዋ ቤት?”

“ይሁን”

ወደ እመዋ ቤት ሄድን፡፡ ልክ ከግቢዋ በር ስንደርስ በሕልሜም በዉኔም ያለልጠበቅሁት እልልታ መንደሩን አቀለጠዉ፡ መነሻዉን ለማወቅ ዞር ዞር ስል ያደገደጉ ቆንጆዎች እና ጎበዞች እርጥብ ጨፌ እየጎዘጎዙ ተቀበሉን፡፡ በአቀባበሉ እየተደነቅሁ ወደ ዉስጥ ብቅ ስል፣ የእመዋ ግቢ
ጭራሽ የጥምቀት አደባባይ መስሏል: ከግቢዉ ጫፍ እስከ ጫፍ የሚደርስ ዳስ ተጥሎበት፣ የንፋስ ማለፊያ እስኪጠፋ ድረስ በሰዉ ጢቅ ብሏል፡ ያልመጣ የአዲስ አበባ ሰዉ መኖሩን ሁሉ እንጃ፡፡ የእመዋ ጎረቤቶች፣ በቀጥታ እኔን የሚተዋወዉቁኝ፣ በባልቻ በኩል የሚያዉቁኝ፣
የእሸቴ ዘመዶች፣ በእህቶቼ በኩል የሚያዉቁኝ ሁሉም እዚህ አሉ፡
የንስሐ አባቴን ጨምሮ፣ በዛ ያሉ ካህናት ሁሉ ተገኝተዋል። ከሁሉም
ከሁሉም በላይ የገረመኝ ግን የተጣላኋት አዋላጅ ሐኪሜን፣ ሸዊትን እዚህ ማግኘቴ ነዉ፡ ተጣልቻት ንግግርም ከልክያት እንዳልነበር፣ ሚያሸንፍ ፈገግታዋ እንደዚህ ስታየኝ ግን አልቻልሁም: እኔም ፈገግ አልሁላት ወደ ዉስጥ በዘለቅሁ ቁጥር፣ ልክ ለንግሥ የወጣ ታቦት በአጠገባቸዉ የሚያልፍ ይመስል፣ጎንበስ ቀና እያሉ እልልታዉን አደበላለቁት “እንኳን ማርያም ማረችሽ” የሚል ምርቃት እንደ ጉድ ተዥጎደጎደ፡ እንደ ታቦትም፣ እንደ ሙሽራም፣ እንደ አራስም ነዉ የተከበርሁ፡ እመዋ በተለይ፣ አይቼባት የማላዉቀዉ ዓይነት ደስታ
ፈልቆባታል ልክ እንደ ልጅ አድርጓታል፡

ቱናትን ስታቅፋትማ ደስታ የሚያደርጋትን ነዉ ያሳጣት፡ ያዉም እኮ እንደ ተሸፋፈነች አቀፈቻት እንጂ ገና ገልጣ እንኳን አላየቻትም እንቅልፍ ወስዷት ስለነበር፣ ፀሐይም ላይ ላለመግለጥ ብላ እንደ
ተሸፋፈነች ከልቧ አጠገብ ደረቷ ላይ ልጥፍ አደረገቻት እና እኔን ወደ ዋናዉ ቤት ጎተተችኝ፡፡

ደስታ በደስታ ሆናለች ፍልቅልቅ ብላለች

“እመዋ”

“አቤት የኔ ልጅ”

“ምንድነዉ ጉዱ?”

“የምን ጉድ? ደስታ ነዉ ጂ! ሰርግሽም አይደል?''

“እ?” አልኋት፣ ከተናገረችዉ ያልስማሁት ቃል ያለ ይመስል
“ዓለሜን አሳየሽኝ ልጄ: ድሮዉንም ቢሆን ከአባትሽ ጋ እንጨቃጨቅ
የነበረዉ በአንቺ የሕይወት መንገድ የተነሳ አልነበር? እኔ ወትሮዉንም ዓለምሽን ማየት ነበር ምኞቴ: ይኼዉ ደራርበሽ አሳየሽኝ። ክብር አለበስሽኝ። ደግ አደረግሽ የኔ ልጅ! እልልልልል!”
ደስታዋ መረጋጋቷን ነጥቋታል: እያቻኮለች ወደ ዋናዉ ቤት አስከትላኝ ገብታ፣ ቱናትን ልታስተኛልኝ ክፍት ካሉት መኝታ ክፍሎች ያደረሳትን
መረጠች: እንዳደረሳት የመረጠችዉ ክፍል ግን የጃሪም መሆኑ የኔን ያህል ቀርቶ ምንም ያሰጋት አልመሰለኝም: በእርግጥ ይኼኛዉ ክፍል ለሳሎኑ ቅርብ በመሆኑ ቱናትን አስተኝቻት ብወጣ እንኳን ቶሎ ቶሎ እየመጣሁና እየሄድሁ በደህና መተኛቷን ለማየት ያመቸኛል: ችግሩ ግን
የጃሪም ክፍል ነዉ፡ ይኼን ጭንቄን ያላወቀችልኝ እመዋ፣ ዝም ብላ ቱናትን በጥንቃቄ አስተኛችልኝ፡ ከዚያ ቀዝቀዝ የምትልበት ትንሽ አፍታ
ከታገሰቻት በኋላ፣ ገለጥ አድርጋ አየቻት፡ እንደገና ሳመቻትና በንጹሕ
አዲስ ጋቢ ጥቅልል አድርጋ መልሳ አስተኛቻት፡፡ ቅሬታዬን እንኳን ለመግለጽ ፋታ ሳትሰጠኝ፣ ወዲያዉኑ እጄን ይዛ እንግዶች ወደ ሞሉት ዳስ ጎተተችኝ፡፡

“አንዴ? ልጄን ትቼ!?”

“ተኝታ የለ፤ ምንም አትሆንም”

“ብቻዋን?”
👍374👎1🔥1
“ወይ ብቻዋን! ይኼ ሁሉ ሰዉ እየወጣ እየገባ? እኔስ ምን ሥራ አለኝ ብለሽ ነዉ? እየመጣሁ አያታለሁ: እህቶችሽም አሉ፣ ወጣ ገባ እያሉ ያይዋታል: ነይ በይ ይልቅ ወደ ቦታሽ ነይ የኔ ሙሽራ”

ደስ እንዳለኝ እና እንዳላለኝ እንኳን የማስተዉልበት ፋታ አላገኘሁም
ቢሆንም ግን ለእሷ ስል ተሸነፍሁና፣ ተከተልኋት

ጎትታ ወስዳ ከእሸቴ አጠገብ አስቀመጠችኝ የመቀመጫዉ ከፍታ እዉነትም የሙሽራ ነዉ የሚመስለዉ፡ በዚያ ላይ የሁሉም ሰዉ ዓይን እኔ ላይ እንደሆነ ሳዉቅ፣ ለዓይኔ ማረፊያ አጣሁለት፡ እንደ ምንም ትንፋሼን ሰብስቤ፣ ትንሽ ቀለል ሲልልኝ ከመሀል ጀምሬ እይታዬ ዉስጥ
የገቡትን እንግዶች ሁሉ አንድ በአንድ በአንገት ሰላም መባባል ጀመርሁ፡ ሁሉም የየአቅሙን ስጦታ በየእጁ አንጠልጥሏል፡፡ እዉነትም እንግዳዉ የተጠራዉ ‹ሙሽራዋን ዉብርስትን እና የዉብርስትን ልጅ መርቁልኝ
ተብሎ ሳይሆን አይቀርም፣ ስጦታዎቹ ለእኔም ለቱናትም የመጡ ናቸዉ።በአንደኛዉ ጠርዝ በኩል ደግሞ፣ ሴቶች ከገረወይና ትንሽ ዝቅ የሚል ድስታቸዉን የሚንቀለቀል እሳት ላይ ጥደዉ ገንፎ ያገነፋሉ፡ ገንፎዉ
እየበሰለ ሲመጣ፣ አስተናጋጆች በቅልጥፍና ሽዉ ሽዉ እያሉ ሳህን ማደል ጀመሩ። እመዋም የቅቤ ቅሏን ይዛ ወጣች:: ገንፎ እና ቅቤዉ በየሳህኑ ሲጨመር፣ አንዳንዶች በነጠላቸዉ ሌሎች ደግሞ ባይበሉባቸዉ አፋቸዉን
ጋረዱ ምራቃቸዉን መዋጥ ጀምረዋል ለነገሩ የእኔም ምራቅ በአፌ ጢም ብሏል

ሳህን ታድሎ እንዳለቀ፣ ካህናቱ ለጸሎት ተነሱ፡ እድምተኛዉም
ተከትሏቸዉ ብድግ ብድግ አለ ካህናቱ በሚታወቀዉ ትሕትናቸዉ
"እርስዎ ይበሉ” “ኧረ እርስዎ ይበሉ” እየተባባሉ ትንሽ ከተለማመኑ በኋላ፣ የራሴ የንሥሐ አባት እንደ መሸነፍ አሉ፡ ለነገሩ በዚህ ካሉት ሁሉ በዕድሜ እሳቸዉ ጠና ሳይሉ አይቀሩም: ያም ብቻ ሳይሆን እሳቸዉ ያላቸዉም ብቻ
እንደማየዉ፣ ቁምስና
ከአለባበሳቸዉ ይመስሉኛል እንደዚያ ቢሆን እንኳን፣ ምናልባት ከዳር እስከ ዳር ግጥም
ካለዉ ከዚህ ሁሉ እድምተኛ ከፍ ያለ ባለ ማዕረግ መኖሩ አይቀርም
ብለዉ ተጠራጥረዉ ካልሆነ በቀር፣ ማዕረጋቸዉም ከሌሎች ይልቅ እሳቸዉ ጸሎቱን ቢመሩት አያከራክርም ነበር፡

“በስመ ኣብ” ብለዉ፣ ጸሎቱን ጀመሩልን፡ ጸሎት አልሁት እንጂ
ምርቃትና ትምህርትም ጨምረዉበታል፡

መቼም ከንስሐ አባቴ በላይ የሚያዉቀኝ አይኖርም፡ በተለይ በመንፈሳዊ ሕይወቴ በኩል ያለዉን ገመናዬን ልቅም አድርገዉ ስለሚያዉቁት ገባ ገባ ያሉ ገመናዬን አወጡብኝ፡ አልፎ አልፎ ለአንዳንዱ ፈቃዴን እየጠየቁ በሚመስል መልኩ እየተመለከቱኝ ቀጠሉ፡ ንግግራቸዉ

“ልጄ ፍቅርተ ማርያም” ብለዉ፣ በክርስትና ስሜ ጀመሩ፡ “በእኔ
በደካማዉ ሐሳብ የፍቅርተ ማርያም መንገድ በዚህኛዉ በኩል
አይመስለኝም ነበር: እኔም ብቻ ሳልሆን፣ እሷም ምኞቷ እንደዚ
አልነበረም: ከጀመርሁት አይቀር እንዲያዉም፣ ይኼን በመሰለ የደስታ ቀናችን ምስጢር ባወጣባት የምትከፋብኝ አይመስለኝም: መመንኮስ
ነበር የምትፈልገዉ እሷ: ግን እሱ የማይሳሳተዉ አምላክ በወደደና
በፈቀደዉ፣ ይኼዉ የልጅ እናት አድርት ቁጭ: እግዚአብሔር
ይመስገን''

“አሜ ን”

“ ንዲህ ነዉ እንዲህ ነዉ የማይሉት አምላክ ይክበር ይመስገን''

“አሜን”

“ልብ ያለማድረግ ካልሆነ በቀር፣ በመጽሐፉም እኮ ተጽፎልናል::
አይተርፉም የተባሉት ሲተርፉ፣ ይኮነናሉ የተባሉት ሲጸድቁ፣ አባራሪ የነበሩት ሲባረሩ አይተናል: ለእረኝነት ሲጠበቁ ንግሥና፣ ለንግሥ ሲጠበቁ ደግሞ በሰማእትነት የሚወስድ አምላክ ተሳስቶ ነወይ? በፍጹም! ሰማእቱ ጊዮርጊስ እኮ ከልጅነቱ ጀምሮ ሲለማመድ የኖረዉ ለምድራዊ
ሹመት ነበር። ፈረስ ግልቢያ እና ጦር ምከታ ለምድራዊ ንግሥና የሚ ደረግ ልምምድ አልነበረም ወይ? ነበረ እንጂ። ነገር ግን መጨረሻዉ ምንድነዉ
የሆነዉ? ሌላ ነዉ። ለሹመት በገባበት መንገድ ይደርስበታል ተብሎ ሲጠበቅ፣ የሰማእትነቱን መንገድ ታደለ። ፈቃደኛዉ አምላክ
ከሚመርጥልን መንገድ አንጻር ፣ የእኛ ምርጫ ከንቱ ነዉ። ፍቅርተ
ማር ያም? ''

“አቤት” አልሁ ድንግጥ ብዬ፣ መልሼ ደግሞ ሰበር እያልሁ

“እንኳን ለዚህ አበቃሽ”
የባሰ መሬት ገባሁ 'ባምላክዎ' የማለት ያህል።

“ዳርቻሽን ያሳምርልን''

“አሜን”

“ኡዎ፣ ዳርቻሽን ያሳምርል : አየሽ አይደል? በዚያም ላይ እኮ፣
የለመኑትን ከልክሎ የሚከለክል አምላክ አይደለም የምናመልከዉ
እናትሽ በአንድ በኩል ዓይኗን በዓይኗ አሳዪልኝ እያሉ ይለምኑታል፣ አንቺ ደግሞ በሌላ በኩል ለምኩስና አብቃኝ እያልሽ ለመሽዉ: ስለዚህ የሁለታችሁንም ልመና አይደለም የተሰማላችሁ? ለእናትሽ ሲል ልጅ፣ ለአንቺ ሲል ደግሞ ልጅሽ ልዩ አድርጎ ሰጠሽ: መቼስ መመንኮስ የተመኘሽዉ በገዳም ድሎት ያለ መስሎሽ አይሆም። ያለ ጽናት የሚገኝ።
ነገር የለም: መነኮሳት ራሳቸዉን ገስጸዉ፣ አፈር ላይ ተኝተዉ እና ያን ሁሉ ፈተና ሁሉ ተቋቁመዉ የሚ ያመሰግኑት ለምንድነዉ? እግዚአብሔር ይሄንን ነዉ የሰጠሽ እንግዲህ። የመነኮሳቱ መኖሪያ ሰጥቶሻል። ልጅሽ ናት ያንቺ ገዳም። ከጨቅላነትሽ ጀምሮ የጓጓሽለት ምንኩስና ይኸዉ
ገብተሸበታል እንግዲህ። እግዚአብሔር ለድል ያብቃሽ: የሰጠሽን ክብር አይዉሰድብሽ: ገዳምሽን ያሳድግልሽ። በገዳምሽ ያጽናሽ”

ጨመር አድርገዉ መረቁኝ፡ ምርቃቱን አስከትለዉ፣ ለእኔ ብቻም ሳይሆን ለሁላችንም ጸሎቱን አደረሱልን፡፡ እኔም ልክ እንደ እንግዶቹ እሳቸዉን እየተከተልሁ አሜን አሜን ስል
ቆየሁና፣ አቡነ ዘበሰማያትን አድርሼ፣ በጸሎትም መሀል ምራቅ
ሲያስዉጠኝ ከነበረዉ ገንፎ በጣቶቼ ዝቄ ሰለቀጥሁ ከቅቤዉ እያጣቀስሁ ኹለት ጊዜ በስስት እንደ ጎረስሁ ለሦስተኛ ጊዜ እጄን ስሰድ፣ የአንዳች ነገር ጥላ ትከሻዬ ላይ ወደቀብኝ፡፡

ክብድ አለኝ፡፡

እየቀፈፈኝ በዝግታ ቀና ብል የጃሪምን ጫማ አየሁት ጫማዉን አልፌ በጉልበቱ በኩል ወገቡ አካባቢ ስደርስ ጥለቱ ዘርፈፍ ያለ ባዶ ጋቢ አየሁ ሰዉነቴ ስንጥቅ አለብኝ የገዛ ምራቄ ሳይቀር ደም ደም አለኝ፡፡ምክንያቱም፣ ጋቢዉ ልጄ ቱናት ጥቅልል ብላ ተኝታበት የነበረዉ ጋቢ ነዉ፡ እመዋ ያለበሰቻት ከዚህ በላይ ቀና ማለት እንደ ሞት አስፈራኝ፡ እንዳይደርሱት የለም፣ እንደ ምንም ጥርሴን ነክሼ ቀና እያልሁ
እቅፉ ላይ ደረስሁ ባዶዉን ጋቢ በኹለት እጆቹ አቅፎ ጃሪም
አግጥጦብኛል ባዶዉን ጋቢ እያባበለ አላገጠብኝ፡፡ እኔን እና በእቅፉ ያለዉን የቱናትን ጋቢ እያስተያየ፣ ተሳለቀብኝ፡
ጋቢ፡

“ማን አልሻት በይ ስሟን?” አለኝ፣ በሳቅ ቡፍ ለማለት እያሞጠሞጠ፡
ብመልስለት የባሰ ለመገልፈጥ እንደቋመጠ ስላወቅሁ፣ የሚተናነቀኝን ስሜት ችዬ ጭጭ አልሁበት

“ መልክ ከሆድ፣ ጤና ከነፍስ ይወጣል» ይል ነበር ተረተኛ አባትሽ። ምነዉ ታዲያ ልጅሽ እንዲያ ጎጎለች ባክሽ? መቼም የተመጻዳቂነትሽ ዉጤት
መሆን አለባት እሷ። ናት አይደል?”

እስኪበቃዉ ድረስ አሽሙሩን ሲያጠጣኝ ቆየ።

አሁን ያለሁበት ስሜት የደስታም ይሁን የሌላ፣ እንደ ወንድም የሚጋራኝ አለመሆኑን በግላጭ ማወጅ ፈልጓል ከቤተሰብም አልፎ፣ ወዳጅም ጠላትም ጭምር በተሰበሰበበት የጥላቻዉን ልክ አሳየኝ፡ የፍላጎቱ የልቡ
ሞልቶለት፣እኔንም እናቴንም አንገት ማስደፋት ቻለ
እስኪወጣለት ድረስ በሰዉ ፊት አሳጣኝ፡፡ እኔም ስብር ብዬ አዳመጥሁት:: ዓይኑን ጎልጉሎብኝ ቆየና ጋቢዉን እግሬ ሥር ወርዉሮልኝ፣ በመንገዱ
ያሉትን ሰዎች ሁሉ እየረጋገጠ ከግቢዉ ወጥቶ ሄደ፡ ትርጉሙ ግን ምንም አልገባኝም ኧረ አሁንስ ለስንቱ ልሁን? ለስንቱ ነዉ የዳረገኝ? ልጄን ምን አድርጓት ይሆን ብዬ ልጨነቅ? ወይስ በሰዉ ፊት ስለሆነዉ ነገር ልሳቀቅ?

ግራዉ ነዉ ግብት ያለኝ፡፡
👍293
የዋናዉን ቤት በር በአንድ ዓይኔ አየሁት ልክ የቀትር ፀሐይ የወጋችዉ ይመስል፣ ዓይኔ ያለቅጥ ተጥበረበረብኝ፡ ወደ ዉስጥ መግባቱን ሳስበዉ
ደግሞ የባሰ ባባት ለቀቀብኝ፡ በቅዠት ዓለም ጠልቆ እንደሚሮጥ ሰዉ እየወደቅሁ እየተነሳሁ እመዋ ቱናትን ወዳስተኛችበት የጃሪም መኝታ ክፍል ስደርስ፣ ልብሷን ተገፍፋ በሆዷ ተደፍታ አገኘኋት፡፡ በዚያችዉ አቅሟ ቁና ቁና ትተነፍሳለች፡ እንዲያዉም ሲፈጥራት ዋነኛዉ ጉዳቷ
እንደ ልብ አለመተንፈሷ ነዉ፡፡ ሲር ሲር የሚለዉ ትንፋሿ የባሰ ፈጥኖ
ደክሞባታል፡ ይኼ ሳያንስ፣ የነርቯን ክፍተት የሚያመለክተዉ የጀርባዋ እባጭ፣ ዙሪያዉን ፈሳሽ ነገር ፍጭጭ ብሎበት ሳይ የምሆነዉን አጣሁ እንደ መጨፍለቅ ብሏል ጃሪም በጭካኔ ነክቶባታል ማለት ነዉ፡
ጃሪም ግን እዚህ ሁሉ ጭካኔ ከምኔዉ ደረሰ? የኔስ ይሁን ግድየለም፣ ቢጨከን ቢጨከን በቱናት ይጨከናል ወይ? በእርጥብ ገላዋ ላይ ይኼን
ሁሉ ጉዳት ተሸክማ እያያት፣ በሷ የሚጨክን ልቡን ከወዴት አገኘዉ
በማርያም?

እንዲህም ሆኖ ደግሞ እኮ ያሳዝነኛል፡ ወንድምነቱ ይመጣብኛል፡

ለጃሪም እያዘንሁለት፣ ለቱናት ደግሞ እየተንሰፈሰፍሁላት፣
ቅድም እንደ ፡ ነበረችዉ ሽፍንፍን አደረግኋት በጥንቃቄ እቅፍ አድርጌ ጨመጨምኋት፡ ከዚያ አንገቴ ሥር ሰግስጌ ካረጋጋኋት በኋላ፣ ነፍሷ እንደ ምንም መለስ አለችልኝ: አይሆንም እንጂ ብችልማ እንዲያዉም
ከዚህ በኋላ ማንም በነዉረኛ ዓይኑ እንዳያይብኝ መልሼ ባረግዛት፣ በሆዴ ትሸሸግልኝ ነበር፡፡ እንኳንስ ከጃሪም፣ ከገዛ እናቴ ሳይቀር መሸሸግ አለብኝ፡፡
ከዚህ ሌላ ምንም ምርጫ አይታየኝም ስለዚህ ብችል ሀገር፣ ቢያንስ ግን ከተማ መለወጥ አለብኝ፡ የሚያዉቀኝ ሰዉ ወደ ሌለበት ልጠፋ፣ ልጄን ጠቀለልሁ...

ይቀጥላል
👍226
#ሳቤላ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ዌስትሊን መኻል ተጠጋግተው የተሠሩ ሁለት ቤቶች ይታያሉ " አንዱ ትልቅ ሌላው አነስ ያለ ሲሆን ትልቁ የካርላይል መኖሪያ ትንሹ ደግሞ ቤሮው ነው ካርላይል የሚለው ስም በዚያ አካባቢ በጣም የታወቀ ነው " ካርላይልና ዴቪድስን በአንደኛው ደረጃ የሚቀጠሩ ጠበቆች ነበሩ " ዱሮ ካርላይልና ዴቪድሰን በጋራ
ይዘውት የነበረ ድርጅት ዛሬ አርኪባልድ ካርላይል የብቻው አድርጐታል እነዚ የሥራ ሸሪኮች አምቻዎችም ነበሩ " የጀመሪያይቱ ሚሲዝ ካርላይል የሚስተር
ዴቪድሰን እኅት ነበረች እሷም ኮርኒሊያን ብቻ ከወለደችለት በኋላ ሞተች ኮርኒሊያ ትልቅ ልጅ ከሆነች በኋላ ሚስተር ካርላይል ሁለተኛ ሚስቱን አገባ " ሁላተኛይቱ ሚሲዝ ካርላይል ደግሞ የመጀመሪያ ልጅዋን አርኪባልድ ካርላይልን ወልዳለት ሞተችና እኀቱ ኮርነሊያ ተንከባክባ እንደ እናት ተጨንቃ እሷ በምትፈልገው ዐይነት መርታ አሳደገችው " ልጁም ሌላ እናት አያውቅም ነበርና እማማ ኮርኒ” ይላት ነበር እማማ ኮርኒ ለሱ ማድረግ የነበረባትን ሁሎ ፈጽማለታለች
ነገር ግን ዛሬም ትልቅ ከሆነ በኋላ ልክ እንደ ልጅነቱ በሷ እንዲመራ ትፈልጋለች
ከልማድ መላቀቅ በጣም ከባድ በመሆኑ አርኪባልድም ቢሆን ብዙውን ጊዜ እንዳለችው ይታዘዛታል » በአንዳንድ ነገሮች ደካማ አስተያት ይኑራት እንጂ ባጠቃላይ ግን ብርቱ ሴት ነበረች " ያለ የሌለ ሐሳቧ የአርኪባልድና የንዘብ ማስቀመጥ ፍቅር ብቻ ነበር " ሚስተር ዴቪድሰን ትዳር የሚባል ሳይሞክር ከሥራ ሸሪኩ ከሚስተር ካርላይል ቀደም ብሎ ሲሞት 'ሀብቱን ለኮርነሊያና ለአርኪባልድ እኩል አወረሳቸው " አርኪባልድን ባይዛመደውም በጥሩ ምግባሩ ይወደው ነበር ሚስተር ካርላይል ብዙ ሀብት ሊያከማች የቻለው ሁለተኛዋ ሚስቱ ባመጣችው ኻያ ሺህ ፖውንድ በመሆኑ ይሆናል ለሴት ልጁ ለኮርነሊያ ጥቂት ሰጥቶ አብዛኛውን አርኪባልድ አውርሶት የሞተው "

ሚስ ካርላይል ወይም በከተማው እንደምትጠራው ሚስ ኮርኒ ባል አላገባችም ሰዎች ለትንሽ ወንድሟ የነበራት ፍቅር ሳታገባ ብቸኛ ሆና እንድትቀር ያደረጋት ይመስላቸው ነበር ነገር ግን የባለጸጋው የሚስተር ካርላይል ልጅ ከነጭራሹ ባል የምትፈልግ አትመስልም ነበር " የፍቅር ነገር ይዘው የቀረቧትን ሁሉ አፋቸውን እያስያዘች መልሳቸዋለች የመጨረሻውን ሙከራ ያደረገው አንድ አዲስ የመጣ ቄስ ነበር " የዚያን ጊዜ ዐርባኛ ዐመቷን ይዛ ነበር አንድ ቀን ነጭ ክራባት አስሮ ወይን ጠጅ ቀለም የእጅ ሹራብ አጥልቆ አሸብርቆ ከጧቱ ቀዶም ብሎ ከቤቷ መጣ

ሚስ ኮሮኒ ከልክ ያለ የቤት አያያዝ ዐዋቂ ገረዶቿ ሊፈጽሙት ከሚፈልጉት የበለጠች ጠንቃቃ ነበረች " ለምሳ የሚዘጋጅ ሥጋ የሚጋገር ሊጥ እየመጠነች ስትሰጥና ስለ ዝግጅቱም እያስረዳች ሳለች የምግብ ቤቱ በር ተከፈተ ወዲያው ቄሱ ገባ " የዩልኝታን ነገር እርግፍ አድርጋ የተወችው ሚስ ካርላይል እንግዳ በመምጣቱ ልታጠብ ልለቃለቅ አላለችም- ሊጥ ስትከፋፍልበት የነበረ አንድ ሳህን እንድ ያዘች እንግዳው ዐረፍ ከሚልበት ምግብ ቤት ገባች "

በዐሥራ ሁለት ዓመት በዕድሜ የምትበልጠው መንፈሳዊ ሰው የሚላትን እስክትሰማ ሰሐኑን ጉኗ በነበረው ጠረጴዛ ላይ አሳረፈችው ኮርነሊያ የያዘችውን ሥራ እንዳደበላሽባት ሰውየው ሳይንተባተብባትና ሳይዘበዝብ ቶሎ እንዲወጣላት መፈለጓን
በተዘዋዋሪ መንገድ ስትጠቁመው አልገባው ሲል ቀጥውን በመንገር አጣደፈሻው » እሱ ለአንድ በጎ አድራጐት ድርጅት በረጂ አባልነት እንድትመዘገብ ሊጠይቃት መሰላት » ከሷ በሁለት ስንዝር ያህል አጠር ይል ስለነበር እሁንም ነገር አልቆርጥ በማለቱ ትግሥቷን ጨርሳ ቁልቁል ትመለከተው ጀመር" በመጨረሻ እሷን እንጂ ገንዘቧን ፈልጎ እንዳልመጣ ነገሩን ገልጾ ሲነግራት እሳት ሆነችበት " እሱን የመሰለ ውርጋጥ እሷን ለዚህ ነገር ደፍሮ ሲያስባት ኣለማፈሩን እየነገረች የቁጣ
መዓቷን አወረዶችበትና ያን ከጠረጴዛው ላይ በሰሐን አኑራው የነበረውን ሊጥ ብድግ አድርጋ በረዶ ከመሰለው ነጭ ሸሚዙ ላይ ለደፈችበት » ኃፍረትና ድንጋጤ ኩምሽሽ ያደረገው ካህን እንዴት አድርጎ ከቤት ወጥቶ በዌስት ሊን ቁልቁል ወርዶ ቤቱ እንዶ ደረሰ ለማስታወስ እንኳን አይፈልግም ነበር " ወሬው ግን ባንድ ጊዜ ዳር እስከ ዳር ተዳረሰና ከዚያ ወዲህ ሚስ ኮርኒን ለጋብቻ በመጠየቅ ረገድ ማንም ስው አስቸግሯት አያውቅም "

ሚስተር ካርላይል ከለንደን በተመለሰ ማግሥት ጧቱን ከቢሮው ገብቶ ተቀምጧል " አብዛኛውን ጊዜ ሥራውን የሚያካሒድለት ታማኝ ጸሐፊውና ሥራ አስኪያጁ የሆነው ሚስተር ዲል ከአጠገቡ ቆሟል " ሚስተር ዲል ዐይን አፋር ቢጤ አጭር ' ቀጭንና ራስ መላጣ ነበር " ድሮ በትልቁ ካርላይልና በዴቪድስን ጊዜ ቀጥሮ ገባ ጀምሮ ችሎታውና የሥራ ልምዱ ሳያንሰው ራሱን ችሎ ከመሥራት ይልቅ ሥራ አስኪያጅ እየተባለ በሰው ሥር ሆኖ ደኅና ደመወዝ እያገኘ መኖሩ ምኞቱን ያረካለት ይመስላል " ለመለየት አሳብ አልነበረውም » በዚያው አካባቢ በአንድ
ጥሩ ቤት ሲኖር እሱም እንደ ኮርነሊያ አላገባም ነበር " የሚስ ካርላይል ልባዊ ወዳጅ ስለመሆኑ ይነገር የነበረው ሐሜት በዌስት ሊን ክብደት እያገኘ መጥቶ ነበር
በሩቁ ግን የማምለክ ያህል ነበር የሚያከብራት " ግምቱ እውነት ቢሆንም ባይሆንም ሚስተስ
አርኪባልድ እያለ የሚጠራውን ያሁኑን ጌታውን ይወደው እንደነበር
ግን እርግጥ ነው አሁን ለንደን ሒዶ በሰነበተባቸው ቀኖች ውስጥ በቢሮ አካባቢ የተፈጸሙትን ነገሮች ሲያስረዳው ቆየና ወጣ"መጨረሻው ሲዶርስ «ጆንስና ራሽዎርዝ ተካረዋል " ሁለቱም በየራሳቸው እንድትቆምላቸው ፈልገውህ ትናንት መጥተው ነበር " ዛሬ የምትሰጣቸውን መልስ ለመስማት ይመጣሉ » አለው "

« ለአንዳቸውም አልቆምም " ከነሱ ጋር ምንም ግንኙነት እንዲኖረኝ አልፈልግም እነሱ መጥፎዎች ናቸው " ሀብታቸውም ሁሉ በግፍ የተለበሰበ ስለሆነ
ሰዎች አይደሉም ስለዚህ እኔ ፈቃደኛ አይደለሁምና ሌላ ሰው ይፈልጉ »

« በጣም ጥሩ እሺ» አለው ዲል

« ኰሎኔል ቤተል መጥተዋል
ጌታዬ » አለ አንዱ ጸሐፊ በሩን ከፈት አድርጎ ወዶ ሚስተር ካርላይል እያየ
«ሊያነጋግሯቸው ይችላሉ ? »

ሚስተር ዲል ወደ ተላከው ጸሐፊ ዞር ብሎ' «ኮሎኔሉን እንዲጠብቁ ንገራቸው» አለውና • ሰውየው መልሱን ሰምቶ ሲወጣ አይቶ ወደ ጌታው ምልስ ብሎ «እንግዲህ ይኸው ብቻ መሰለኝ » አለው
« ጥሩ ነው ስማ ዲል ... ሰሞኑን ስለ ኢስት ሊን የባለቤትነት ይዞታ
ስለ ወለድ አግድ ሁኔታ የሚያስረዱ ሰነዶች ከነሙሉ ማስረጃቸው ይቀርቡልሃል "
ለማንም ሳታሳይና ሳትናግር በደንብ አድርገህ እንድታያቸው እፈልጋለሁ ኢስትሊን ባለቤት ሊለወጥ ነው እንደ ሎርድ ማውንት እስቨርን ከመሰለ በችግር ከተወጠሩ ሰዎች ቦታ ሲገዙ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል ስለዚህ ማንም አንዳይሰማ ሆኖ ተጠንቅቀህ እንድትመረምረው በል አሁን ቤቴልን አስገባልኝ »

በሚስተር ካርላይልና በጸሐፊዎቹ ክፍሎች መካከል አንድ አራት ጎኑ እኩል የሆነና ወዶ ዋናው መተላለፌያ የሚያስገባ ሁለተኛ በር የነበረሙ አንድ ትንሽ መተላለፍያ ነበር » በዚያ መተላለፊ በኩል አንድ ጠባብ ክፍል ነበር » ክፍሉ ሚስተር ካርይል በማይኖርበት ወይም እንግዶችን ማያስችል ከባድ ጉዳይ ሲኖርበት ሚስተር ዲል እሱን ተክቶ የሚሸኝበት ልዩ ቢሮው ነበር " ይህ ክፍል የጸሐፊዎቹን ቢሮ የምታሳይ አንዲት ጠባብ መስኮት ነበረችው " ሚስቴር ዲል አንዳንድ ጊዜ በዚያች መስኮት አሹልኮ እየተመለከተ ስላሠቀቃቸው
👍21
ሠራተኞቹ ያቺን መስት «የሺሜው ዲል ጮለቂያ» ይሏት ነበር " መስኮቲቱ ከዚያ ቦታ ብትጠፋለት የማይመኝ ሠራተኛ አልነበረም " ሽማግሌው ከጸሐፊዎቹ ቢሮ ውስጥም ሌላ ጠረጴዛ ስለነበረው ከዚያም ብዙ ጊዜ ይቀመጥ ነበር" የዚያን ቀን ጧትም ከጠረጴዛው ተሠይሞ ዙሪያውን ኢያስተዋለ ሲቃኝ በሩ ቀስ ብሉ ተከፈተ " ባርባራ የሚያምረው ፊቷ በፍርሃት ፍም እንዶ መስለ ብቅ
አለች

« ሚስተር ካርይልን ማነጋገር እችላለሁ ? » አለች "

ሚስተር ዲል ከተቀመጠበት ተነሥቶ ጨበጣትና ወደ ኮሪዶሩ ይዟት መጣ በሩን ከበስተኋላው ዘጋው እንደሷ ያሉ ያላገቡ ቆነጃጅት ሚስተር ካርላይል ዘንድ
ሲመጡ አይቶ ስለማያውቅ ነገሩ የገረመው ይመስል ነበር "

« ሚስ ባርባራ አሁን እንግዶች አሉበት ዳኞቹ ገብተዋል " »

« ዳኞቹ ! አባባም አብሮ አለ ? ምን ይሻለኛል ሚስተር ዲል? እዚህ ግድም እንዲያየኝ በጭራሽ አልፈልግም ! »

ወዲያው ዳኞቹ የመጡበትን ጨርሰው የመነሣታቸው ድምፅ ተሰማ ዲል ቶሎ ብሎ የፀሐፊዎችን ቢሮ ከፈተና ባርባራን በዚያ በኩል አሳልፎ ከራሱ ልዩ
ጽሕፈት ቤት አስገብቶ ዘጋባት "

ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ተመልሶ ከፈተላት » «ሁሉም ሔደዋል ሚስ ባርባራ' አሁን ማንም የለም » አላት "

ሚስተር ዲል እዚህ ሲያዩኝ ምን ሐሳብ እንደሚደቀንብዎ አላውቅም ጉዳዩን በምስጢር ልግለጽልዎ " እናቴ ከሚስተር ካርላይል ዘንድ የግል ጉዳይ አላት
ነገር ግን በጤንነቷ ምክንያት ራሷ ልትመጣ ስለ አልቻለች እኔ ስለሏ .
እዳነጋረውና መልሱን እንድነራት ልካኝ ነው የመጣሁት " አባቴ እዚ እንዳያየኝ የፈለግሁትም ጉዳዩ ብርቱ ምስጢር ስለሆነ ነው "

« ሰማሽ ልጄ…… አንድ ጠበቃ ብዙ የተለያዩ ባለጉዳዮችን ይቀበላል " ስለዚህ የሥራ ረዳቶችም ልዩ ትርጉም የሚሰጡበት ቦታ አይደለም » አለና የሚስተር ካርሳይልን በር ከፍቶ አስገባት እሱም ድንግጥ ብሎ ተነሥቶ ተቀበላት "

« እንደማንም ባለጉዳይ እየኝ በማስቸገሬ ይቅርታ አድርግልኝ » አለችው ባርባራ ፍርቷን ለመደበቅ እንደ መሣቅ ብላ « ከአባባ ጋር ከመተላለፊያ ላይ ልንገናኝ ስንል ሚስተር ዲል ከቢሮው ዘግቶብኝ ለጥቂት አመለጥኩት " በድን
ጋጤ ነፍሴ ልትወጣ ነበር " »

ሚስተር ካርይል እንድትቀመጥ በጁ አመለከታትኔ እሱም ቦታውን ያዘ "የቢሮ ጠባዩ ከሥራ ውጭ ከምታውቀው የተለየ ሆነባት " ከቢሮው ውጥ በጣም የረጋ ጸጥ ያለና ከባድ ሰው ሆኖ ታያት "

« አንድ የምነግርህ እንግዳ ነግር አለኝ » አለችው በጆሮው ግን ሰውሊሰማን ይችል ይሆን ? ከሆነ ውጤቱ ሞት ነው »

« ፈጽሞ ሊሰማ አይችልም
ስትግቢ ልብ አላልሽው እንዶሆነ ነው እንጂ መዝጊያዎቹኮ ድርብ ናቸው»

ቢሆንም ወንበሯን ትታ ወደ ሚስተር ካርላይል ጠጋ ብላ እጅዋን ከጠረጴዛው ላይ አስደግፋ ስትቆም እሱም ብድግ አለ "

« ሪቻርድ እኮ መጣ »

« ሪቻርድ ? እዚህ ዌስት ሊን ? »

« አዎን እዚህ ትናንት ማታ ሌላ ሰው መስሎ በዐጸዱ በኰል ወደ ቤት ጠጋ አለና በምልክት ጠራኝ - እየውልህ እስከዛሬ - የሥራው ነገርስ ላንተም ልነግርህ ያሳፍረኛል " ለካ ከፈረሶች ጋጣ እየሠራ አንዳንዴ ጾም ውሎ እያዶረ ለንድን ውስጥ ኖሯል የተቀመጠው እና ደግሞ አየህ
አርኪባልድ ከወንጀሉ ንጹሕ
ነኝ ይላል " » ሚስተር ካርላይል ሰምቶ ምላሽ ሳይሰጣት ዝም ብሎ ቆየና« ተቀመጭ ባርባራ » አላት ወንበሩን ጠጋ አድርጎ " ባርባራ ተቀመጠች ነገር ግን ጥድፊያና ጭንቀት ይታይባት ነበር « አየህ አሁን ሰው ሲመጣ የኔ እዚህ መገኘት እንግዳ ነገር ሆኖ ነው የሚታየው እማማን ስለ አመማትና አባባም ያያት እንደሆነ ብላ ባትፈራ ኖሮ ራሷ ትመጣ ነበር ።

« አይዞሽ ይህ ክፍል ማንም እንዳሻው ሰተት ብሎ የሚገባበት አይዴለም ስለ ሪቻርድ እስቲ ንገሪኝ " »

« እሱማ ግድያው በተፈጸመበት ጊዜ ከዚያ ቤት እንዳልነበረና ሃሊዮንን ገደለው ቶርን የሚባል ሰው መሆኑን ነገረኝ " »

« የምን ቶርን ? » አላት ሚስተር ካርላይል አለማመኑን በደበቅ "

« እኔ እንጃ የአፊ ወዳጅ የነበረ ነው አለኝ ዛሬ ማታም ትናንት ከተገናኘንበት ቦታ ድረስ እንዲመጣ ስለ ቀጠርኩት የሚቻልህ ከሆነ እንድታነጋግረው
ፈልጌ ነበር " የራሱን ታሪክ ቢነግርህ ካንተ ብልህነት የሚያመልጥ ዘዴ ስለሌለ
ንጽሕናው ይፋ የሚወጣበትን መላ ልትፈልግለት ትችል ይሆናል »

ሚስተር ካርላይል ፈግግ አለና ' «እሱ እንኳን የሚሆን አይመስለኝም ግን ይኸን ሊነግርሽ ነበር የመጣው ? » አላት

« አይደለም ነገሩን አነሣው እንጂ ማንም ሊያምነው እንደማይችል በትክአክል ያውቃል " የመጣበት ጉዳይ ችግር ስለ ጠናበት፡እማማ አንድ መቶ ፓውንድ
ያህል ብትሰጠው የተሻለ ሥራ ለማግኘት እንደሚችል ሊጠይቅ ነው" እሷ ደግሞ በእጇ ምንም ስለሌላትና አባባንም ለመጠየቅ ስለማትችል የጠቀውን ገንዘ በ
እንተ ብትሰጥላት ስለ አከፋፈሉ ራሷ ከአንተ ጋር የምትመካከርበት መሆኑን እንድነግርህ ልካኝ ነው የመጣሁት»

« እኔ በማልኖርበት ጊዜ ዲል ብዙ ገንዘብ ከቤት ስለማያስቀምጥ አሁን ትፈልጊው እንደሆን ከባንክ ላስወጣ"

« እኔ የምፈልገው ለማታ ነው" ግን ሪቻርድን ልታነጋግረው ትችላለህ ?

« አደገኛ ነግር ነው ማለቴ ለሱ ሆኖም ዛሬ ማታ ወደ 0ፅዱ የሚመጣ ከሆነ እዛው ድረስ መጥቼ አነጋግረዋለሁ።

« ሌላው ችግሬ ደግሞ ለእማማ ሰው መላኩን እንጂ እሱ ራሱ መምጣቱ አልነግርኳትም " ስለዚህ እውነቱን ብገልጽላት ምን ይመስልሃል?»

« ለምን አትነግሪያቸውም ? መንገር ያለብሽ ይመስለኛል»

« ብነግራት ልየው ብላ እንዳታስቸግረኝ ፈራሁ እሱም እናቱን ለማየት በጣም ፈልጓል»

« ይኸ ደግሞ ምኑ ያስፈራል ? ሚሲዝ ሔር የልጃቸውን ደኅንነት ከራሱ ቢሰሙት በጣም ደስ ይላቸዋል " ስለዚህ ቢገናኙ ጥሩ ነው »

« ታዲያ ይህን ለማድረግ አባባ ከውጭ አንደሚያመሽ ማረጋገጥ አለብን ግን እንዴት አድርገን ? »

« እስኪ ምን ማድረግ እንደሚቻል ላስብበትና»

« እኔ ካሁን በኋላ ወደዚህ መምጣቴ ደስ አይለኝም » አለችው ንግግሩን አቋርጣ «ጥርጣሬ ሊያስነሣ ይችላል ወይም አንድ ሰው ያየኝ እንደሆነ ላባባ ሊነግርብኝ ይችላል »

« በይ እንግዲያው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ዐሥር ሰዓት ሲሆን ወደ መንገዱ ዝለቂ...0ቆይ እስቲ ለካ ዐሥር ሰዓት የራት ሰዓትሽ ነው ። በይ ልክ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን
ከመንገዱ ድረስ እመጣለሁ " እዚያ ቀስ እያልሽ እየሔድሽ ጠብቂኝ » አላትና እስከ ዋናው በር ድረስ ሸኝቶ የእጅም ሰላምታ ሰጥቷት ተመለሰ ሚስተር ካርላይል እንደዚያ ያለ ትሕትናና ከበሬታ ለማንም ሰው አሳይቶ አያውቅም " ባርባራ ወጥታ
በሩ ተዘግቶ ገና አንድ እርምጃ እንደ ተራመደች ከሚስ ካርላይል ጋር ፊት ለፊት ግጥም አሉ » ሚስ ካርላይል ከዓለም ሴቶች ሁሉ በቁመት ሳትበልጥ አትቀርም "
በቁንጅናዋ ዘመን መልኳ ደኅና እንደ ነበረች የሚመሰክሩ ምልክቶች ገና አልጠፉም አሁንም ምንም እንኳ ሥጋዋ አልቆ አጥንቷ ብቻ የቀረ ብትመስልም መልኳ ደርባባነት አልተለየውም።

« ምንድነው አንቺ ? እንዴት እንዴት !» ብላ ጀመረቻት « ከአርኪባልድ ጋር የነበርሽው አንቺ ነሽ ? »

ባርባራ • ለሚስተር ዲል የነገረችውን ምክንያት ልትነግራት ተንተባተበች

«እናትሽ ለጉዳይ ልካሽ ነው?እኔ እንደዚህ ያለ ነገር ሰምቼም አላውቅ አርኪባልድን ለማነጋገር ሁለት ጊዜ መጣሁ" ሥራ ይዟል ' ሰው አይገባም ብሎ ዲል ሁለት
ጊዜ መለሰኝ » ለምን ምስጢር አድርጐ እንዶ ያዘው ዲልን ሳላስለፈልፈው ብቀር
👍161
« ኧረ ምስጢር የለበትም » አለች ባርባራ ነገሩ እየተዛመተ አባቷ ዘንድ እንዳይደርስ እተጨነቀች » «እማማ ስለ አንድ የግል ጉዳይ የሚስተር ካርላይልን ምክር
ፈለገችና እሷ መምጣት ስላልቻለች እኔን ልካኝ ነው " »

ሚስ ካርላይል የባርባራን ነገር አላመነችም « የምን ጉዳይ ? » አለቻት "

« ላንቺ የሚጠቅም ቁም ነገር ያለው ጉዳይ አይደለም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ትንሽ ጉዳይ ነው»

« ታዲያ ቁም ነገር ከሌለው ይህን ያል ጊዜ ከአርኪባልድ ጋር በር ዘግቶ ያዋለሽ ምንድነው ? »

« ስለጉዳዩ ዝርዝር ነገር ሲጠይቀኝ ነበር » አለቻት ከድንጋጤዋ እየተላቀቀች
ሚስ ካርላይል አንድ ሐሳብ ባልተስማማት ጊዜ እንደምታደርገው አነፈነፈች "
አንድ ምስጢር መኖሩ ተሰማት ስለዚህ አዘናግታ ነገር ለማዋጣት ስትል ተመለሰችና ከባርባራ ጋር እያወራች ብዙ መንገድ ሔዶች " ነገር ግን ከሷ ምንም ፍንጭ
ማግኘት አልቻለችም "

ሚስተር ካርላይል ' ባርባራን ሸኝቶ ወደ ቢሮው ተመልሶ ከገባ በኋላ መጥሪያውን ደወለና አንድ ጸሐፊ ገባ።

«ባክስ ሔድ ሒድና ሚስተር ሔርና ሌሎችንም ዳኞች ካገኘኻቸው ወዶዚሀ እንዲመጡ ንገራቸው »

ዳኞቹ ቀደም ሲል አንድ ያሠራር ስሕተት ፈጽመው ነበር በዚህ ስሕተታቸው በሕግ ከመጠየቃቸው ሊያወጣቸው የሚችል ሚስተር ካርላይል መሆኑን ስላመኑ ጥሪውን በመቀበል በአንድ ጊዜ ተግተልትለው ደረሱ "

« ብዙ ስለማላቆያችሁ ተቀመጡ አልላችሁም " እንድትመጡልኝ የጠየቅኋችሁ የዚያ ሰውዬ መታሰር በጣም እያሳሰበኝ ስለመጣ ዛሬ ማታ አምስታችሁም
ከኔ ቤት ብንገናኝና ትምባሆአችሁን እያጤሳችሁ ምን መደረግ እንዳለበት በሰፊው
ብንነጋገርበት ብዬ ነው " ልክ በአንድ ሰዓት ድረሱ እኔ ደግሞ ትምባሆውን ባባቴ የጋያ ገምቦ ሞልቼ ግማሽ ዶርዘን የሚሆኑ መማጊያ ውዥሞዎችን አዘጋጅቼ እጠብ ቃችኋለሁ " ምን ይመስላችኋል ? »

አምስቱም ጥሪውን በደስታ ተቀበሉት " ሁሉም ሊወጡ ሲደረዶሩ ሚስተር ካርላይል የዳኛው ሔርን ክንድ ያዝ አድርጎእርስዎም እንደሚጡ እርግጠኛ ነዎት . . . ሚስተር ሔር » አለውና ወደ ጆሮው ጠጋ ብሎእርስዎ ካልተገኙ የሚ
ሆን ነገር የለም የሰው ሁሉ ጭንቅላት እንደ እርስዎ በጥራትና በጥልቀት ተመልክቶ የማፍታታት ተሰጥዎ አልታደለም » አለው "

« እንዴ ! እመጣለሁ እንጂ ለምን እቀራለሁ » አለ በሚስተር ካርላይል ሙገሳ ተደስቶ "

ሚስተር ካርላይል ዳኞቹን አሰናብቶ ብቻውን ሲሆን አንድ አሽከር ገባና'
« ሚስ ካርላይል ሊያነጋግሩዎ ይፈልጋሉ ኰሎኔል ቤቴልም ተመልሰ መጥተዋል » አለው "

« መጀመሪያ ሚስ ካርላይልን አስገባልኝ» አለውና ወዲያው እንደ ገባች « ምንድነው : ኮርኒሊያ ? » ብሎ ጠየቃት

«አንተማ ምን አለብህ ምንድነው እያልክ ጠይቅ እንጂ !እንደ ወትሮህ በሥራ ሁለት ሰዓት ራት እንደማትበላ ከተናገርክ በኋላ የምትፈልግበትን ሰው
አናግረህ ሾልከህ እልም ትላለሀ ? ታዲያ እኔ ምን ብዬ ትእዛዝ ልስጥ ? »

በሥራ ጉዳይ ወደ ውጭ ለመሔድ አስቤ ነበር ቀረሁ ስለዚህ ዛሬ ትንሽ ቀደም ብለን ወደ ሩብ ጉዳይ አካባቢ ቢሆን ይሻላል " ምክንያቱም አብረውኝ ከቤት የሚያመሹ ሰዎች ጠርቻለሁ " »

« ምን የሆነ ነገር አለ አርኪባልድ ?» አለችው የራሱን ሳይጨርስ።

« እንጃ እኔ የማውቀው ነገር የለም አሁን ሥራ በዝተብኛል ... ኮርኒ . .
ኰሎኔል ቤቴል ደግሞ ከውጭ እየጠበቀኝ ነው እኔና አንቺ በራት ጊዜ እንጨዋወታለን

ኮርነሊያ ለዚህ ግልጽ ለሆነ ንግግሩ ምላሽ እግሯን አነባብራ ከባለ ጉዳይ ወንበር ላይ ተደላድላ ቁጭ አለች " ያደረገቻቸው ነጭ የእግር ሹራቧና ጫማዋ ሙሉ በሙሉ ይታዩ ጀመር ሚስ ካርላይ ረጅም ቀሚስ የሚባል ነገር አትወድም - « እኔ የምልህ ያቺ ባርባራ እዚህ ድረስ መጥታ የቢሮህን በር አስዘግታህ የነበረችው ከሚስተር ሔር ቤት ምን የደረሰ ነገር አለ ? ስለ እናቴ ጉዳይ ነው የምትለው ቋንቋ አላት እናቷ ምን ሆናለች ? »

«ምነው...ሚስተር ሔርና ሌሎቹም ዳኞች የገቡበትን ጣጣ ሰምተሻል? ያን ምስኪን ሰውዬ በእሑድ ከጓሮው አረም ነቀለ ብለው ወህኒ ቤት አስገቡት "
አሁን»

« ደደብ አሮጌ መጋዣ ሁላ!» ብላ ጮኸች ነገሩን ሳይጨርስ «ሁሉም ቢጠራቀሙ ቅንጣት ልብ የላቸውም "

“ አሁን ይኸውልሽ ... ሰውዬው ለአገር አስተዳደር ሚኒስትሩ ስላመለከተ ሚስዝ ሔር በጣም ሠጉና ምን ማድረግ እንደ ሚሻል ምክር ለመጠየቅ ባርባራን
ወደኔ ላኳት ራሳቸው እንዳይመጡ ባርባራ እንደ ነገረችኝ ታመዋል » ኮርነሊያ ዳኞቹን ዛሬ ማታ ከቤት እንዲመጡ ጠርቻቸዋለሁ አንድ አምስቱ ያል ጋያ ለማጨስ ይመጣሉ " ስለዚህ ያን ከእርሳስ የተሠራውን ያባቴን የትንባሆ ሳጥን እንድታጪውና

“ ከዚች አይመጧትም " ከአንድ ደርዘን የትንባሆ ውዥሞዎች በሚወጣ ጢስ መርዝ የምታጠንልህ ይመስልሃል ?

አንቺ ካልፈለግሽ እኮ እኛ ከምዓቀመጥበት ክፍል ላትቀመጭ ትችያለሽ " "

“ እነሱም ቢሆኑ በክፍሉ አይቀመጡበትም ሁሉም መስኮቶች ንጹሕ መጋ ረጃዎችን ያደረግሁ ስለሆነ በአስቀያሚ የትንባሆ ጢስ ሲያጠቁሩዋቸው ማየት አልችልም "

ኮርነሊያ ... ”አላት ሚስተር ካርላይል ቁርጥ ባለ ወሳኝ ድምፅ “ እነዚህን ስዎች ለሥራ ጉዳይ ጠርቻቸዋለሁ ገባሽ ? ለሥራ ጉዳይ ስለዚህ መምጣታቸው የማይቀር ነገር ነው ከሳሎን እንዲቀመጡ አንቺ የማትፈጊ ከሆነ መኝታ ቤት ያመሻሉ "

ሥራ የሚለው ቃል ለሚስ ካርላይል አንድ ትርገም ብቻ ነበረው "ገንዘብ ማለት ነበር " ወንድሟ ይህን ደካማ ጐኗን ስለሚያውቅ ሌላ ዘዴ ሲያጣ
ለስራ ጉዳይ ይላት ነበር።
" ከፍተኛ የገንዘብ ፍቅር ስለነበራት ገንዘብ ስታገኝ ወይም ሚስተር ካርላይል ገንዘብ አገኘ ማለትን ከሰማች ልዩ ደስታ ይሰማት ነበር እሱ ደግሞ በንዘብ ፍቅር የሚጠራ ሰው አልነበረም እንዳመጣጣቸው እየተቀበለ ቢከራከርላቸው ብዙ ገንዘብ ሊያገኝባቸው የሚችሉ አያሌ ባለጉዳች አዳምጦ አብርዶ አስማምቶና ግልጽ የሆነ ምክሩን ስጥቶ በነጻ ያሰኖብታቸው ነበር
« ኮርኒሊያ እነዚሀን አንቺ እንደምትሠጊው የትምባሆ ጢስ ካበላሻቸ አዲስ መጋረጃዎችን እገዛሁ " ስለዚህ ሳልታወክ እንድሠራ ተይኝ " »

« የባርባራ ሔርን ጉዳይ ሥረ ነገር ላገኝብህ ስል ነው ተይኝ የምትለኝ ! » አለችው የትምባሆውን ጉዳይ እርግፍ አድርጋ ትታ " « አንተማ ብልጥ አይደለህ
አርኪባልድ " እኔን ማታለል ግን አትችልም " ባርባራን ለምን እንዶ መጣች ጠይቂአት ስለአንድ የገንዘብ ጉዳይ እናቷ እንደ ላከቻት ነግራኛለች አንተ ደግሞ ዳኞቹ ስለ ፈጸሙት የሥራ ስሕተት ነው ትለኛለህ " ሁለቱም አውነተኛ መልሶች አይደሉም ይልቁንስ ባንተና በባርባራ መካከል ስላለው ምስጢር ንገረኝ ሳልሰማው የምቀር አይምሰልህ " »

ከወንበሯ ቀጥ ብላ †ቀመጠችና ትክ ብላ አየችው " ሁለቱም በጸጉራቸ አበቃቀልና በግንባራቸው ስፋት ጥቂት ከመቀራረባቸው በቀር በመልክ አይመሳሰሉም የወንድሟን ያህል መልከ መልካም አልነበረችም » ቢሆንም ከብዙዎቹ የዌስት ሊን ሴቶች ትበልጥ ነበር ።

ሚስተር ካርላይል የእኅቱን
ጠባይና ቆራጥ አመለካከት በዶንብ ስለሚያውቅ
ሐቁን ፍርጥ አድርጐ ሊነግራት ወሰነ እሷ መቸም ምስጢር ተብሎ የተነገራትን ታወጣለች ማለት ዘበት ነው በሌላ በኩል ከሷ የተደበቀ ምስጢር መኖሩን ከጠረ
ጠረች እስክታውቀው ድረስ እንደ ፋሮ ቁፋር ትጀምራለች እንጂ ምን እንዶሆነ ሳትዶርስበት አትለቅም ።
👍16
ሚስተር ካርላይል ወደሷ ጐንበስ ብሎድምፁን ዝቅ በማድረግ « ነገሩ መሰማቱ ደስ አይልም እንጂ ከፈለግሽ እነግርሻለሁ ሪቻርድ ሔር ተመልሶ መጥቷል» አላት

ሚስ ካርላይል ክው ብላ ደነገጠች " « ሪቻርድ ሔር ? ዐበደ እንዴ ? »

« በርግጥ አድራጐቱ የዕብደት ያህል ነው ! እናቱ ገንዘብ እንዲሰጡት ይፈልጋል ሚስዝ ሔር ደግሞ በእጃቸው ገንዘብ ስለሌላቸው እኔ እንድሰጣቸው ለመጠየቅ ባርባራን ወደኔ ላኳት እሷም በአደጋ ስለ ተከበበች መደንገጧና መርበድበዷ
አያስዶንቅም »

« እና አሁን ከቤት ገብቷል ? »

« አባቱ ከቤት እያሉ እንዴት ሊገባ ይችላል ? አንድ አልባሌ ሰው መስሎ ሦስት ምዕራፍ ያህል ወጣ ብሎ ከሚገኝ መንደር ውስጥ ተደብቋል » የጠየቀውን ገንዘብ ለመቀበል ዛሬ ማታ ከወላጆቹ ግቢ ድረስ ይመጣል " ሚስተር ሔር በዚያ ሰዓት ከቤታቸው እንዳይኖሩ ስለ ፈለግሁ ዳኞቹን እዚህ ከኛ ቤት እንዲያመሹ
ጠራኋቸው ሪቻርድን ካገኙት ላንቺም ሆነ ለኔ ስም ጥሩ አይሆንም እሳቸው ለፍርድ ያቀርቡታል " አንድ የቤተ ዘመድ አባል በነፍስ ግዳይ ተፈርዶበት ከተሰቀለ በካርላይል ቤት ለትውልድ የሚተላለፍ ነጥብ እንደሚጥል አንቺም የምታውቂው ነው»

ሚስ ካርላይል ስለ ሰማችው ነገር እያሰበች ሰፊውን ግንባሯን ቋጥራ ጸጥ ብላ ተቀመጠች "

« አሁን እንግዲህ ኮርኒሊያ ... ሁሉን ነገር ዐውቀሻል " ስለዚህ ብዙ ሥራ ስለ አለብኝ ተይኝና ልሥራ እባክሽን »

አንድም ቃል ሳትናገር ብድግ ብላ ወታ ሔዶች » እሱም ከፊቱ ከነበረው ማስታወሻ ደብተር አንድ ቅጠል ነጠለና በአንቬሎፕ ከቶ ካሽገው በኋላ አድራሻውን
ለራሱ አድርጎ ጽፎ እንዳበቃ ዲልን ጠርቶ ሰጠው "

ሚስተር ዲል ተቀበለና አድራሻውን ሲያይ የገረመው መሰለ ።

« ዛሬ ማታ በሁለት ሰዓት » አለው ሚስተሮ ካርላይል «ይህን ፖስታ ይዘኸልኝ ከቤቴ ትመጣለህ ።»

ሽማግሌው እሺታውን ባንገቱ ገልጾ ፖስታውን ከኪሱ ከቶ ወጣ»

ሚስተር ካርላይል ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት መንገዱን ይዞ ቀስ እያለ በእግሩ ሲሔድ ከባርባራ ጋር ተገናኙ " ዳኞቹን አባቷንም ጭምር ለትንባሆና ለመጠጥ እንደ ጋበዛቸው ነገራት።

ባርባራ በጥርጣሬ ዐይን ቀና ብላ አይታው «ታዲያ እንግዶች ካሉብህማ ወደኛ ላትመጣና ሬቻርድንም ላታየው ነው ማለት ነው ? » አለችው።

« እመኝኝ» ብሏት እየገሠገሠ ሔደ...

💫ይቀጥላል💫
👍114
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ


#በታደለ_አያሌው


ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያለሁበት ክፍል ተንኳኳ።

“ጎሽ! ደረስሽልኝ ሸዊት?” አልሁ፣ እንባ ሲጠምቁ የቆዩ ዓይኖቼን በቱናት ጋቢ እያደራረቅሁ። ቱናት ደክሟት ይሁን እንጃ፣ ብቻ እየሰለለ መጥቶ የነበረዉ ለቅሶዋን ጨርሳ ትታዋለች: እንዲያዉም ያንን ሲር የሚል ትንፋሿን እንደገና መስማት ጀምሬያለሁ፡ ቢሆንም ግን
አላመንኋትም እነዚያ ቁልቁል ሰርገዉ እንደ ነገሩ ግራ ቀኝ የሚባክኑት
ዓይኖቿን ድንገት የምትከደንብኝ መሰለኝ፡፡ ይቺኑ ትንፋሿንም የማጣት መሰለኝ፡ ፍርሃት ፍርሃት ብሎኛል።

እሷን እሷን እያየሁ የጎድን ሄጄ፣ የበሩን ቁልፍ ጠምዝዤ ከፈትሁት

“አገኘሽ? አመጣሽልኝ?” አልሁ ቀና ብዬ እንኳን ሳላይ፣ መልሼ ጣቶቼን የቱናት ልብ ላይ እያስቀመጥሁ የልብ ምቷ አንጻራዊ መሻሻል እንዳለዉ ሳዉቅ፣ ተመስገን› ብዬ ሙሉ ቀልቤን ወደ ሸዊት ሳዞር
አጣኋት: እሷን በጠብቅሁበት ቦታ፣ ጃሪም ድፍርስ ዓይኑን ልጄ ላይ ተክሎ ቆሞበታል ለካ ለእሱ ነዉ በሩን የከፈትሁለት?

“የልጅሽ አባት…” አለኝ፣ ዓይኖቹን ከቱናት ላይ ሳይነቅል።

ደንግጫለሁ። ደረቅ ሊሾ ላይ እንደ ወደቀ ሸክላ ነዉ ድቅቅ ያልሁት።

እዚህ መሆኔን እንዴት አወቀ? ምን ቀረዉና መጣ ደግሞ? ምን ሊያደርገኝ? ልጄን ሊገድልብኝ? እንዲያዉም ፍርሃት ላይ ነበርሁ፣ ጨረሰኝ: በዓይኑ እና በቱናት መካከል ቆሜ አንዴ እሱን፣ አንዴ ደግሞ
ቱናትን በማየት ተወጠርሁ ከአሁን አሁን እጁን አነሳባት እያልሁ፣
ለመከላከል እንደ ምንም ጡንቻዎቼን አነቃቅቻለሁ።
“የልጅሽ አባት ግን ማነዉ? ማነዉ ያ ደብተራ ሰዉዬ፣ ባልቻ ነዉ ማን
የምትዪዉ ?»
መልስ አልሰጠሁትም አሁን እዉነት ባልቻ ጠፍቶት ነዉ "ያ" ብሎ የማያዉቀዉ የሚመስለዉ? ካላወቀም ሲራክ ፯ን እና ባልቻ የሲራክ፯ ዋና ኃላፊ መሆኑን አይወቅ እንጂ፣ ቢያንስ በአነጋጋሪ ድርሰቶቹ የተነሳ ባልቻን የማያዉቅ ሐበሻ የለም አለማድነቅ ሌላ፣ አለማወቅ ግን ሌላ ዉሸት፡

“ከእሱ ነዉ የወለድሻት ኣ? ብቻ ከማንም ዉለጃት፤ እሱ አይመለከተም ነበር ! ግ ን እሱ ሰዉዬ፣ ያለሁበት ድረስ ትናትና መጥቶ ሲመክረኝ ሲመክተኝ.” አለ፣ በማላገጥ በዙሪያዬ እየተንጎራደደብኝ፡ “ባይገርምሽ በንግግሩ ከመነካቴ የተነሳ፣ እራቴን እንኳ ን ሳልጠጣ ነዉ ያደርሁት
ብታይ። በጣም ነዉ የተሰማኝ"
ልጄን ለመከለል በእሱ እንቅስቃሴ ትይዩ እየተንቀሳቀስሁ፣ ስላቁን
አዳመጥሁለት “እናትሽ እናቴ አይደለችም, አልሁ እንጂ እናቴ አትወደኝም ያልሁት ይመስል፣ ‹እናትህ ትወድሃለች እያለ ሊሰብከኝ አማረዉ። ሱራሎ፣
እናትህ፣ አባትህ፣ ወደዚህ፣ ወደዚያ እያለ ሲዘበዝብብኝ አመሸ''
አለኝ፣ ስላቁን ለዘብ አድርጎ፡
“ትዝ አይልህም ግን?''
“ምኑ?”
“የሱራሎዉ ጊዜ ጎርፍ: ያ ጊዜ ረሳኸዉ? እመዋን ለማትረፍ ዘለህ የገባኸዉን? ሁላችንም የተሟሟትነዉ ? ''
ጀርባዉን ሰጥቶኝ ቆመ፡

“ረሳኸዉ?”

“አለማፈርሽ!” አለ የደም ሥሮቹ እየተገታተሩ። “አፍሽን ሞልተሽ
ሱራሎ ስትይ አለማፈርሽ! ቆይ ቀድሞ ነገር በምን ሆነና እናትሽ እናቴ አለመሆኗ ፣አንቺም እህቴ አለመሆሽ የተገለጠዉ? መቴ መሰለሽ? !! እ'
ከዚያ በኋላ እኮ ነዉ”

ዓይኖቼን በልጥጬ፣ አፍ አፉን አየሁ
“እንደዚያ ነፍሴን ለአደጋ ሰጥቼ ከዉሀ ሙላት ያተረፍኋት እናትሽ በቡናዉ እና በየእድሩ የምታወድሰዉ አንቺን ብቻ ሆነ። (ዉዷ ልጄ የምትለዉ፣ (መመኪያ የምትለዉ፣ (አተረፈችኝ የምትለዉ አንቺን ብቻ ነዉ። እኔስ? ሌሎቹስ? ጭራሽ በቦታዉ እንኳን የነበርን አታስመስይዉ
ነበር እኮ: አሁን ምን ተገኝቶ ነዉ ታዲያ፣ ሱራሎ ሱራሎ አልሽኝ በይ? እ!?”

“ኧረ እኔ የተለየ አፍ ኖሮኝ አያዉቅም: ሱራሎ አስቤ አንተ ረስቹ
አላዉቅም: የሱራሎን ነገር ለሰዉ ስነግርም፣ በዚያ ጊዜ ወንድሞቼ እና
እህቶቼ የፈጸማችሁትን ሁሉ በጭራሽ ረስቼዉ አላዉቅም”

“ተዪ እንጂi” አለኝ፣ ቢያሳየኝ ቢያሳየኝ የማያልቅበትን የሽሙጥ ሳቁን
መልሶ እያመጣብኝ፡፡ “እሱን ተዪዉና፣ ባልቻ ተብዮሽ፣ ምን ብሎ እንደ
ጠየቀኝ ነገረሽ? ‹ቤተሰብህን ለምን ማፍረስ ፈለግU? ብሎኝ አረፈዋ!
እንዴት ነርቬን እንደ ነካኝi” አለኝ፣ ወዲያ ወዲህ መንጎራደዱን ትቶ ፍጭጭ ያለ ሳቅ እየሳቀብኝ፡ “ግን እኮ እዴት እኔ ማፍረስ እችላለሁ? ነዉ ወይስ መጀመሪያዉኑም፣ ቤተሰባችን የዉሸት ቤተሰብ ነበር?”

“የዉሸት?” አልሁት፣ አላስችል ቢለኝ በቆየሁ ቁጥር ለእሱ የነበረ ፍርሃት ለቀቅ እያደረገኝ መጥቷል። ልጄ ግን በረኀብ እንዳትሞትብኝ አሁንም እፈራላታለሁ

“እህስ!”

“እንዴት ነዉ የዉሸት?''

“ሌላዉ ይቅር እሺ። ግን… ኹለት ልጆች፣ መንታ ሳይሆኑ ግን ደግሞ ከአንድ እናት ተወልደዉ ዕድሜያቸዉ እኩል መሆኑ አይደንቅም ነዉ የምትዪኝ? ''

“እንዴት?” እንዴት አልሁኝ፣ እዉነትም አሁን አሁን ስናድግ እየተዉነዉ መጣን እንጂ፣ የእኔና የእሱ ልደት ይከበርልን የነበረዉ በአንድ ቀን መሆኑ ትዝ ብሎኝ፡፡

“ኅዳር 14 አይደል?”

“ልደታችን?”

“እ”

“አዎ” አልሁት፣ ምን እየጠቀለለብኝ እንደሆነ እንኳን ሳይገባኝ።

“እና ኹለታችንም ኅዳር 14 ተወልደን ነዉ የምትዪኝ?''

“ሌላ ምን ይሆናል?”

“መንታ ነን እንዴ ? ''

“አይ፣ እንደዚያ እንኳን አይመስለኝም”
“እሺ በተለያየ ዓመት ግን በአንድ ዓይነት ቀን ተወልደን ነዉ?”

“እንደሱም አይመስለኝም” አልሁት፣ በዕድሜ እንደማንበላለጥ
አስታዉሼ፡ የኹለታችንም ዕድሜ እኩል ከሆነ በተለያየ ዓመት ልንወለድ
አንችልም።

“አየሽ ጅልነታችሁን? ስትሸዉዱ እንኳን ብልሃቱን እታዉቁበትም: ኅዳር
14፣ አባትሽ አባቴን በመተት ገድሎ ርስቱን የቀማበት ቀን ነዉ። እንደዚህ
ነዉ የተሳለቃችሁብኝ! የእኔ የሐዘን ቀን ለእናንተ በዓል ነዉ! በእናቴ ቤት
ነዉ እናትሽ እንኳን እናት የመሰለችዉ!”

“ኧረ በማርያም! በማርያም ተዉ። እንዴት እዴት ነዉ የምታወራዉ?”

“ገብቶሻል። ግጥም አድርጎ ገብቶሻል”

“አንዴ” ሳቄን መያዝ አልቻልሁም: ለቀቅሁት። “ቆይ ምኑ ነዉ
የሚገባኝ? ''

እሱ ግን ብልጭ አለበት፡ እንደ ምንም ለመረጋጋት ወደ ግድግዳዉ ዞሮ
ከቆየ በኋላ፣ በዚያ ድፍርስ ዓይኑ መልሶ ጥብስቅ አድርጎ ያዘኝ፡፡ ያዉም
በኃይል እስከሚያመኝ ድረስ!
“ሲራክ ማነዉ?” አለኝ፣ ከዓይኑ ማምለጫ እየፈለግሁ ሳለ፡ እርፍ! ጭራሽ ሲራክ ፯ን ያዉቀዋል? መንግሥት እንኳን እስካሁን ያልደረሰበትን ሲራክ ፯ን ጃሪም ያዉቀወዋል? የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት
አገልግሎት እኮ ማኅበራችንን በፖለቲካ ከመጠርጠር ባለፈ፣ እስከዚህ
አያዉቀዉም: ተአምር ነዉ!

“ሲራክ ምንድነዉ?” አለኝ፣ የባሰ ፍጥጥ ብሎ

“እ?”

“አቺና እናትሽ እዚያ ምን ትሠራላችሁ?”
ትንሽ ተንተባተብሁ፡ ሙልጭ አድርጌ መካድ ቢኖርብኝም፣ አልቻልሁም: አመነታሁ። ነገር ግን መላወሻ የሚባል አልሰጠኝም።

ስለዚህ የታየኝ አማራጭ እዉነቱን ማፍረጥረጥ ብቻ ነዉ፡ በእርግጥ
በሲራክ ፯ ሥነ ምግባር መሠረት፣ ቁጥር አንድ የሚባለዉ ወንጀል፣
አሁን እኔ ቀጥዬ የማደርገዉ ድርጊት ነዉ፡፡ እንደ ሕጋችንማ፣ ከቅርብ ኃላፊዬ ግልጽ ይሁንታ ካልተሰጠኝ በቀር፣ ማንም ቢያስፈራራኝም ሆነ
ቢያዉጣጣኝ፣ እንኳንስ በማኅበራችን ሥር ስላለዉ ሲራክ፯ ህልዉና ይቅርና፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱሱ መጽሐፈ ሲራክ ቢሆንም ማዉራት አልችልም፡ ይኼ በማንኛዉም አባል የሚጠበቅ ሕግ ነዉ

አሁን ግን ይኼን ሕግ በመተላለፌ የጃሪምን ልብ የማለሰልሰዉ
ስለመሰለኝ፣ ልሽረዉ ነዉ፡
👍35👎1🔥1🥰1