የማሪየስ አክስት መጽሐፍ ነው ያለችው የተጠቀለለውን ነገር ዣን
ቫልዣ ወደ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው:: የታሠረበትን ገመድና የተጠቀለለበትን ወረቀት ፈታው:: ባለከፍተኛ የገንዘብ ኖታ ብቻ ነበር፡፡ ገንዘቡ ተቆጠረ:: 500 ባለ አንድ ሺህ፤ 168 ባለ አምስት መቶ ፤ በድምሩ 584ዐዐዐ ፍራንክ ሆነ፡፡
«ጥሩ መጽሐፍ ነው» አለች የማሪየስ አክስት:: በዚህ ጊዜ ማሪየስና ኮዜት ዓይን ለዓይን ተያዩ:: ብዙም በገንዘቡ አልተሳቡም::
ለጋብቻው በዓል የሚያስፈልገው ዝግጅት ሁሉ ተደረገ፡፡ ቀኑን
ለመወሰን ሐኪሙ ሲጠየቅ ከአንድ ወር በኋላ በጥር ወር መጨረሻ ለማድረግ እንደሚቻል
አበሰረ:: በደስታ ጊዜ ሰዓቱ ሳይታወቅ ስለሚያልፍ ቀኑ ቶሎ
ደረሰ፡: ኮዜትና ማሪየስ በድንገት ከመቃብር ወደ ገነት ገቡ:: አንዳንዴ የማሪየስ አባት ኮዜት ላይ አፍጥጠው ለረጅም ጊዜ ይቆያሎ:: ኮዚትም በውበትዋ ተማርከው እንደሆነ በመገመት በዚህ አትከፋም::
«ነገሩ ሁሉ እንዴት እንደተለወጠ ይገባሻል?» ሲል ማሪየስ ኮዜትን
ጠየቃት::
«እኔ አይገባኝም፧ ብቻ ሀያሉ አምላክ ፊቱን ወደ እኛ እንዳዞረ
አውቃለሁ» ስትል መለሰችለት::
ዣን ቫልዣ ሁሉንም አስተካከለው:: ነገሩ ሁሉ ትክክል እንዲሆን
አደረገ፡፡ ከባድ ነገር ቀላል እንዲሆን አመቻቸው:: ኮዜት ደስ እንዲላት ብቻ የሚችለውን ሁሉ ፈጸመ:: የኮዜኔትም ደስታ እጥፍ በእጥፍ እየሆነ ሄደ፡፡
ማሪየስን አገኘች:: የደጉ ሰው ፍቅር ቀስ በቀስ በወጣቱ ፍቅር እየተተካ ሄደ፡፡ ይህ ደግሞ አያስገርምም፤ የሕይወት እውነታ ይኸው ነውና!
ነገር ግን ዣን ቫልዣን «አባባ» ከማለት አልተቆጠበችም::
ከጋብቻው በኋላ ማሪየስና ኮዜት ከማሪየስ አያት ጋር እንዲኖሩ
ተደረገ፡፡ ዣን ቫልዣ ደግሞ ከቤታቸው አልጠፋም::
ታሪክ ውስጥ የተከታተልናት ሚስስ ቴናድዬ ከእስር ቤት ውስጥ
ሞተች፡፡ ከእነዚያ አሰቃቂ ቤተሰቦች በሕይወት የቀሩ ሚስተር ቴናድዬና አንደኛዋ ልጅ አዜልማ ነበሩ፡፡ ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ የት እንደገቡና መጨረሻቸው ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ተሸፋፍኖ ቀረ:: ተሸፋፍኖ የቀረ ታሪክ ይህ ብቻ አልነበረም::
ማሪየስ ከጦርነቱ መካከል ከተመታ በኋላ ማን ከዚያ አንስቶ ከአያቱ ቤት እንዳመጣው እንዲሁ ሳይታወቅ ቀረ፡፡ ምሥጢሩን ለማወቅ ብዙ ሙከራ ተደርጎ ነበር፡፡ ሆኖም ጥረቱና ልፋቱ መና ሆነ፡፡
አንድ ቀን ጨዋታ ደርቶ ሲጫወቱ ማሪየስ በቁጣ ስለዚያ ሰው
ያነሳል፡፡
«አዎ! ያ ሰውዬ፤ ማንም ይሁን ማን፣ ለእኔ ብሎ እንደዚያ የተሰቃየ
ሰው እንደ ጉም ተንኖ ቀረ፡፡ የኮዜት ስድስት መቶ ሺህ ፍራንክ የእኔ በሆነና» ብሎ ሲናገር ዣን ቫልዣ ጣልቃ ይገባል፡፡
«ገንዘቡ የአንተ ነው፡፡»
እንግዲያውማ ያ ሰው ማን እንደሆነ ለሚነግረኝ እከፍለው ነበር። አለ ማሪየስ ለዣን ቫልዣ ሲመልስለት::
ዣን ቫልዣ ዝም አለ፡፡
የሠርጉ እለት ዣን ቫልዣ ከበር አጠገብ ተቀምጦ መተከዙን ኮዜት
ተመለከታለች፡፡ ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ወደ እርሱ ሄደች፡፡
«እባዬ ደስ ብሉሃል?» ብላ ጠየቀችው::
“አዎን አለ ዣን ቫልዣ ፧ “ለምን ደስ አይለኝም ፤ ደስ ብሎኛል
እንጂ::"
እንግዲያውማ ሳቅ ሳቅ በላ ስትለው ከት ከት ብሎ ሳቀ፡፡
በእራት ሰዓት ግን ዣን ቫልዣ ከሠርጉ ቤት አልነበረም፡፡ ትንሽ
ስላመመው በጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ የእርሱ ከዚያ አለመገኘት ኮዜትን ቅር አሰኛት:: ሆኖም የእርሱን ቦታ ማሪየስ በመውሰዱ ሀዘንዋ እየተቃለለ ሄደ፡፡ በመጨረሻ ዣን ቫልዣን እስከ መርሳት ደረሰች::...
💫ይቀጥላል💫

👍21❤2
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሶስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....በእራት ሰዓት ግን ዣን ቫልዣ ከሠርጉ ቤት አልነበረም፡፡ ትንሽ

ዣን ቫልዣ ከቤቱ ሲደርስ ቤቱ ውስጥ ማንም አልነበረም፡፡ ወደ
ኮዜት ክፍል ሲሄድ አልጋዋ አለመነጠፉን ተገነዘበ፡፡ አንሶላዎቹና የትራስ ልብሶች ተነስተዋል፡፡ አንዳንድ የኮዜት የግል እቃዎችም ከዚያ ተወስደዋል፡፡ከዚያ የቀሩት ከባድ የቤት እቃና አራቱ ግድግዳዎች ብቻ ናቸው፡፡ ዣን ቫልዣ ክፍት የነበረውን ሣጥን ዘጋግቶ ከክፍሉ ወጣ፡፡ ክፍሎቹን ሁሉ እየተዘዋወረ ጎበኘ፡፡ ከራሱ መኝታ ቤት ደረሰ፡፡ ወደ አልጋው ሲሄድ ዓይኑ
ከአንድ ነገር ላይ አረፈ፡፡ ዘወትር ከዓይኑ የማይለየው አነስተኛ ሣጥን ከዚያ ተቀምጧል፡፡ ከአጠገቡ ስለማይለየውና በጣም ስለሚንከባከበው ኮዜት
ትቀናበት ነበር፡፡ ከኪሱ ቁልፍ አውጥቶ ትንሹን ሻንጣ ከፈተው::
ከውስጡ የነበሩትን ልብሶች አወጣ፡፡ በመጀመሪያ ጥቁር ቀሚስ፤ ቀጥሎ ጥቁር እስካርፍ፤ ከዚያም ዛሬም ቢሆን ኮዜት ልታደርገው የምትችል ትልቅ የልጅ ጫማ፤ በመጨረሻ ባለኪስ ሽርጥና የተቀደደ የእግር ሹራቦችን
አወጣ፡፡ ኮዜት ከአሥር ዓመት በፊት ሞንትፌርሜን ለቅቃ ስትወጣ የተቀመጠና እናትዋ ከሞተች በኋላ ኮዜትን ፍለጋ ሲሄድ ዣን ቫልዣ የወሰደላት ጥቁር ልብሶች ናቸው:: ልብሶቹን ከአልጋው ላይ ዘርግቶ
እንዳስቀመጣቸው የኮዜት እናት ትዝ አለችው:: በዚያን ጊዜ ኮዜትም ምን ትመስል እንደነበረና እንዴት ከእዚያ አስከፊ ቤት አስወጥቶ ለእናትዋ ሀዘን
ያመጣላትን ጥቁር ልብስ ለብሳ ምን ትመስል እንደነበረ አስታወሰ፡፡ በእናትዋ ሞት ምክንያት ከል ለብሳ እናትዋ በመንፈስ ስታያት ሳትደሰት አልቀረችም ሲል አሰበ፡፡
ኮዜት ከዣን ቫልዣ ጋር ጥቅጥቅ ባለው ጨለማ ያቋረጠችውንም
ጫካ አስታወሰ፡፡ ኮዜት ደስ ብሎአት ያንን የገዛላትን ትልቅ አሻንጉሊት ተሸክማና የሀዘን ልብስ ለብሳ ከማታውቀው ሰው ጋር በደስታ ስትጓዝ ምን ትመስል እንደነበር ትዝ አለው:: ሆዱን ባር ባር አለው፡፡ ከአልጋው ላይ
ከዘረጋው የኮዜት ልብስ ላይ ተደፍቶ ማልቀስ ጀመረ::
ያን እለት ማታ የሕይወቱን የመጨረሻ ትግል፣ የመጨረሻ ፈተና እንደሆነ ዣን ቫልዣ ተገነዘበ፡፡ እንደ ልማዱ ዣን ቫልዣ ከሌላ ፈተና ውስጥ ገባ፡፡
እንዴት አድርጎ ነው የማሪየስንና የኮዜትን ፍቅር ሳያበላሽ አብሮ
የሚኖረው? ለግል ጥቅሙ ሲል ደንቃራ ይሁን ወይስ ብቻውን ውስጥ ውስጡን ይሰቃይ? ይህ ሁልጊዜም ቤተሰቦችን ያስጨነቀና የብዙ ፍቅረኞችን ሕይወት ያበላሸ ጥያቄ ነው::
በሥጋ ፈቃድ ተመርቶ እርምጃ መውሰድ ውጤቱ ግጭት ነው::
ታዲያ እስከመቼ ነው የነፍስ ተገኝዎች ሆነን የምንቀረው? ዣን ቫልዣ ለሥጋው አድሮ ኮዜትን አልለቅም ይበል ወይስ ለነፍሱ አድሮ ሙሉ በሙሉ ለማሪየስ አሳልፎ ይስጣት?
ግን እኮ ቀላል አይደለም:: እርሱስ ምን ይሁን? ከትቢያ አንስቶ ለዚህ
አደረሳት:: የመንፈስ ልጁ ናት:: በዓለም ላይ ያለ እርስዋ ሌላ ሀብት የለውም:: ወንድሙም፣ እህቱም፣ እናቱም፣ አባቱም፣ ጎረቤቱም፣ ምኑም ምኑም ኮዜት ናት:: ኮዜት ትሂድና ሙልጭ ይውጣ? ታዲያ ምን ይሁን?
ታዲያ ለዣን ቫልዣ ሲባል የኮዚት ሕይወት ይበላሽ?
እንዴ፣ ሕይወትዋ የማን ሆነና?
መስዋዕትነት መትነን ነው፣ ለመደሰት መሰቃየት አለ፤ ይህን መፈጸም ማለት ደግሞ ከጋለ ብረት ላይ መቀመጥ ነው:: ግን ካጋለ ብረት ላይ መቀመጥ ከቻለ ዓለምን ከቁጥጥር ስር ማድረግ ይሆናላ!
ዣን ቫልዣ ፍልስፍናውን ትቶ ተስፋ በመቁረጥ ጋደም አለ፡፡ ነገሩን
ሁሉ ለካው፣ መዘነው:: ከዉሳኔ አሳብ ላይ ደረሰ፡፡ እርሱና ጨለማ
ብቻቸውን ቀሩ፡፡
በሠርግ ማግሥት ሁሉም ነገር ጭር ይላል:: ለፍቅረኞች እድል
ለመስጠት ታስቦ ይመስል ሁሉም አርፍዶ ነው ከመኝታው የሚነሳው::ዣን ቫልዣ ግን በጠዋት ተነስቶ ወደ ማሪየስና ኮዜት ቤት ሄደ::
«እርስዎ ነዎት አባባ!» አለ ማሪየስ ዣን ቫልዣ ከነበረበት መጥቶ::
ማሪየስ ብዙም ስላልተኛ በጣም ከብዶታል፡፡
«ምነው በጠዋቱ? ኮዜት ገና አልተነሳችም፡፡ ማታ ቶሎ በመሄድዎ በጣም ቅር አለን፡፡ ስለእርስዎ ብዙ ተጫወትን፡፡ ኮዜት በጣም ትወድዎታለች:
ከዚሁ ጥሩ ክፍል እንደተዘጋጀልዎት ቀደም ብዩ ነግራዎት ነበር፡፡ ከእኛ ጋር መቀመጥ አለብዎት:: ከዚያ ብቻዎን ምን ያደርጋለ? እንዲያውም ከዛሬ ጀምሮ ከዚሁ ነው የሚሆነት:: አባባንም እንደሆነ በመንፈስ ገዝተወታል፡፡ እርሱ የእርስዎ ነገር አይሆንለትም:: በጣም ነው
የሚያከብርዎትና የሚወድዎት፡፡ አብረን የኖርን ተደስተን ነው የምንኖረው።
እርስዎ ደግሞ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው:: አሁን እንሂድ ቁርስ ቀርቦአል» አለ፡፡
«ሰማሀ ማሪየስ» አለ ዣን ቫልዣ ፤ «አንድ የምነግርህ ነገር አለ፡፡ እኔ
እንደሆንኩ አሮጌና ሽማግሌ ወንጀለኛ ነኝ::»
አንዳንድ ጊዜ ጆሮ ለመስማት የማይፈልገውን አይሰማም፡፡ በተለይም ካልተጠበቀ ምንጭ የሚወጣ የማይሆን ወሬ ጆሮ ያልፈዋል፡፡ “ወንጀለኛ ነኝ" የሚለውን ዜና ከ መሴይ ፎሽለማ የሚጠበቅ ስላልሆነ የማሪየስ ጆሮ ሊሰማው አልፈቀደም አንድ ነገር ግን እንደሰማ ስለሚያውቅ ፈዝዞ ቀረ።
ምን ማለትዎ ነው?» ሲል በማጉረምረም ይጠይቃል፡፡
«ይህም ማለት» አለ ዣን ቫልዣ ፣ «ወህኒ ቤት ነበርኩ ማለት ነው፡፡»
ምነው እኔን ለማሞኘት ነው?» ሲል ማሪየስ ቅሬታውን ገለጸ፡፡
«ማሪየስ» አለ ዣን ቫልዣ፣ «ከወህኒ ቤት አሥራ ዘጠኝ ዓመት
ኖሬአለሁ:: በሌብነት ወንጀል ተከስሼ ነው የታሰርኩት:: በመጨረሻ ላደረስኩት ጥፋት የእድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶብኝ ነበር፡፡ ሆኖም አምልጬ
በመውጣቴ አሁንም ወንጀለኛ ነኝ::
ማሪየስ አሁን መከራከሩ ዋጋ እንደሌለው ስላመነ ዝም ብሎ ይሰማ ጀመር፡፡ ነገሩ እየገባው ሄደ፡፡ እንዲያውም ከነአካቴው ራሱም ፈራ፡፡
«ይቀጥሉ፤ ይቀጥሉ፤ ሁሉንም ይንገሩኝ» ሲል ተናገረ፡፡ «እርስዎ
የኮዜት አባት ነዎት!»
ፍርሃቱን ለመግለጽ ሁለት እርምጃ ወደኋላ ተራመደ፡፡
ዣን ቫልዣ በኩራት መንፈስ ጭንቅላቱን ወደ ጣራ አቅንቶ ያለምንም ማፈር ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«ምንም እንኳን የምለው ነገር የሚዋጥና የሚጥም ባይሆንም
እንድታምነኝ ያስፈልጋል::)
እዚህ ላይ ዣን ቫልገዥ ጥቂት ቆም ብሎ ንግግሩን በዝግታና ግርማ ሞገስ በተሞላበት አንደበት ቀጠለ፡፡
«ታምነኛለህ ፧ እኔ የኮዜት አባት ነኝ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ግን
አባትዋ አይደለሁም:: ፌቨሮል ከሚባል ሥፍራ ገበሬ ነበርኩ፡፡ ሥራዬ አትክልት መከርከም ነበር:: ስሜ ፎሽለማ ሳይሆን ዣን ቫልዣ ነው:: ከኮዜት ጋር ዝምድና የለንም:: ኣእምርህን ሰብሰብ አድርግ፡፡»
ለማሪየስ እድል ለመስጠት ንግግሩን ካቋረጠ በኋላ እንደገና ጀመረ፡፡
«ታዲያ ለኮዜት ምንዋ ነኝ?አዛኝ! ከአሥር ዓመት በፊት በሕይወት
መኖርዋን እንኳን አላውቅም ነበር፡፡ በእርግጥ እወዳታለሁ፡፡ የሙት ልጅ ስለሆነች አባትና እናት የላትም:: የዛሬ አሥር ዓመት ገደማ የእኔን እርዳታ በጣም ያስፈልጋት ስለነበር እርስዋን ማፍቀር ጀመርኩ፡፡ ልጆች ደካሞች

👍19
ስለሆኑ የማንንም ፤ እንደ እኔ ያለውን እንኳን፣ እርዳታ ይሻሉ፡፡ ይህን ግዴታዬን ለመወጣት ነበር ያስጠጋኋትና የሕይወቴ ቁራጭ ልትሆን የቻለችው:: ዛሬ ኮዚት የሰጠችኝን ሕይወት: ከእኔ ትታ እየሄደች ነው::መንገዶቻችን ተለያይተዋል:: ከአሁን በኋላ ምንም ላደርጋት አልችልም::
ዛሬ ጠባቂዋ ሌላ ሰው ነው:: ጠባቂዋ በመቀየሩ ደግሞ ተጠቅማለች እንጂ አልተጓዳችም
መጠቀሟ ደግሞ መልካም ነው።
ዣን ቫልዣ የማሪየስን ፊት ተመለከተ፡፡ ነገሩን እየረገጠ አሁንም ንግግሩን ቀጠለ።
«ማሪየስ ይህ ግምታዊ አነጋገር ሳይሆን እውነት ነው:: እኔ ትክክለኛና ቅን ሰው ነኝ:: በአንተ አመለካካት ራሴን ዝቅ በማድረጌ እርሱነቱን ከፍ ያደርጋል ብለህ ትገምት ይሆናል አሁን የምነግርህ
አሁን የምነግርህ ነገር ቀደም ሲል የደረሰብኝ ሲሆን በዚያን ጊዜ እንዳሁኑ የሚያሳዝን ጉዳይ አልነበረም::አዎን ትክክለኛና ቅን ሰው! በራሴው ጥፋት ሊሆን ይችላል፤ ስለእኔ ያለህ
ግምት ዝቅተኛ ይሆን ይሆናል:: አንተ የፈለግኸውን ግምት ልትወስድ ትችላለህ፡፡ እኔ ግን ቀና ሰው ነኝ፡፡ ከወህኒ ቤት አምልጬ ስለጠፋሁ ሕገ ወጥ ብሆንም ሕይወቴን የምመራው በሕሊና ዳኝነት ነው፡፡ ቃሌን አከብራለሁ:: መጥፎ አጋጣሚ የሙጥኝ ከሚል ወጥመድ ሲጨምረን
መጥፎ እድል ደግሞ ታላቅ ኃላፊነትን ከሚጠይቅ ሥራ ውስጥ ይከትተናል።
አየህ ማሪየስ፣ በሕይወቴ ዘመን ብዙ ነገር አይቻለሁ፡፡
ዣን ቫልዣ አሁንም ንግግሩን ለጊዜው ቆም አደረገ፡፡ ቃል መርሮት ምራቁን ለመዋጥ እንደሚታገል ሰው እርሱም ተቸገረ:: ሆነም ቀረም
ንግግሩን ቀጠለ፡፡
በኣንድ ወቅት ለመኖር ስል ዳቦ ሰረቅሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ ለመኖር ስል
ስም አልሠርቅም::
«ለመኖር!» አለ ማሪየስ ጣልቃ ገብቶ ፤ ለመኖር አዲስ ስም
አያስፈልጎትም እኮ!
«ይገባኛል» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰ፡፡ አንገቱን ወደ ላይና ወደ ታች ደጋግሞ እየነቀነቀ::
ማሪየስ ወደ ዣን ቫልዣ ጠጋ ብሎ እጁን ዘረጋለት:: ዣን ቫልዣም
የማሪየስን እጅ ጨበጠ፡፡ «ምስኪን ኮዜት!» ሲል አጉረመረመ፡፡ «ይህን
ስትሰማ ምን ትላለች?››
«ኮዜት! አዎን፤ እውነት ነው:: የነገርኩህን ሁሉ ንገራት:: ይህም
ትክክለኛ አሠራር ይሆናል፡፡ ይህን አላሰብኩም ነበር፡፡ የለም! የለም አሳቤን ለውጫለሁ:: ላትነግራት አሁኑኑ ቃል ግባልኝ:: አንተ ካወቅህ ይበቃል።»
«ረጋ ይበሉ አባባ» አለ ማሪየስ ፤ «አትናገር ካሉኝ አልናገርም።
ምሥጢር ሆኖ ይቅር ካሉ ይሆናል::
«ይብቃን መሰለኝ» አለ ዣን ቫልዣ «ግን እኮ አንድ ነገር ቀርቷል፡፡»
ምን?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ::
«አሁን ማን እንደሆንክ ካወቅህ በኋላ የኮዜት አሳዳሪ እንደመሆንህ መጠን ሁለተኛ አያታለሁ ወይስ ባልገናኛት ይሻላል?»
ባይገናኝዋት የሚሻል ይመስለኛል» አለ ማሪየስ፡፡
«ሁለተኛ ዓይንዋን አላይም» ሲል ዣን ቫልዣ በማጉረምረም ተናገረ፡፡
ይህን እንዳለ ወደ በሩ አመራ፡፡ ለመውጣት በሩን እንደከፈተ እንደገና ቆም አለ፡፡ በሩን መልሶ ዘጋው::
«ግን» አለ፤ «ፈቃድህ ከሆነ፤ መጥቼ አያታለሁ:: እርስዋን ለማየት በጣም እፈልጋለሁ፡፡ ለእርስዋ ያለኝ ፍቅር ብርቱ ባይሆን «ከመካከላቸው ልግባና ልበጥብጥ» የሚል ሥጋዊ ፍላጎት አያድርብኝም ነበር፡፡ የዚህ
ዓይነት ብርቱ ፍላጎት ባይኖር ኖሮ ደግሞ አሁን የነገርኩህን ባልነገርኩህ፡፡ባልነግረህ ኖሮ ደግሞ አሁን እንደቀለለኝ አይቀለኝም ነበር፡፡ ስለዚህ ይህን
ሁሉ ያመጣው የኮዜት ፍቅርና እርስዋን የማየት ፍላጎት ስለሆነ አያታለሁ፡፡ነገር ግን እኔ ለእርስዋ ያለኝን ፍቅር ለማርካት ስል «አብሬያቸው በመኖር ከፍቅራችሁ መካከል አልገባም:: እንዲያውም ሁለተኛ ከአጠገባቸው አልደርስም» በሚል ውሳኔ ነው ያን ሁሉ ታሪክ የነገርኩህ፡፡ አሁን ሳስበው ደግሞ አብሮ መኖርና መተያየት ለየቅል መሆናቸውን ስለተገነዘብኩ ልያት ብዬ ጠየቅኩህ:: ለመሆኑ ለማለት የፈለግሁት ምን እንደሆነ በትክክል ገብቶሃል? አየህ! ኮዜት ካጠገቤ ሳትለይ ከዘጠኝ ዓመት በላይ ኖራለች::ስለዚህ አንተን ቅር ካላለህ ኮዜትን በየጊዜው እየመጣሁ አያታለሁ:: እግር
ግን አላበዛም:: ስመጣም ለብዙ ጊዜ አልቆይም:: እልም ብዬ ብጠፋ ደግሞ ደግ አይሆንም::»
«ከፈለጉ ለምን በየቀኑ አይመጡም» አለ ማሪየስ፤ «ኮዜት ደግሞ ደስ ይላታል እንጂ አይከፋትም::»
«እርሱማ እኔንም ደስ ይለኛል፤ እንዳላስቀይማችሁ፤ ደግሞም
በፍቅራችሁ መካከል እንዳልገባ ብዬ ነው እንጂ፡፡ ለማንኛውም ምስጋናዬ የላቀ ነው፤ ደግ ሰው ነህ ማለት ነው» አለ ዣን ቫልዣ፡፡
ማሪየስ ዣን ቫልዣን ለጥ ብሎ እጅ ነሳው:: ደስታና ተስፋ መቁረጥ ተሳክረውባቸው ነው ሁለቱ ሰዎች የተለያዩት::....
ማሪየስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ዣን ቫልዣን ይጠራጠረው ነበር፡፡
ቀንቶ ይሁን ወይም በምን ምክንያት እንደሆነ አይታወቅም ብቻ ግን ዣን ቫልዣን ይጠላዋል፡፡ የዣን ቫልዣም ስሜት ከዚህ የተለየ አልነበረም::አሁን ግን ለማሪየስ ግልጽ ሆነለት፡፡ ይህም በመሆኑ ለሰውየው አዘነለት::
ይህ ለካ የሁለት ጊዜ ወንጀለኛ ቢሆንም የተናገረው ነገር እውነትነት እንዳለው ማሪየስ አምኖ ተቀብሎታል፡፡
እንዴት ያለ እምነት? ስድስት መቶ ሺህ ፍራንክ በገዛ ፈቃዱ ከእጁ
አውጥቶ መስጠቱ ቀላል አልነበረም:: ገንዘቡ ከየትም መጣ፣ ምስክር ሳይኖር በሕሊና ዳኝነት ብቻ ያን ሁሉ ገንዘብ ሰጥቶታል፡፡ ለምን? ይህ ሰው
ምንድነው የሚፈልገው? ሰውዬው የፈለገው ወንጀለኛ ቢሆንም በሕሊናው ዳኝነት የሚኖር ንጹህ ሰው እንደሆነ ማሪየስ እንዲያውቅለት ነበር፡፡ በሕሊና
ዳኝነት ሕይወቱን የሚመራ ሰው ደግሞ ታላቅ ነፍስ ያለው ነው::
ማሪየስ የዣን ቫልዣን ማንነት በትክክል ለማወቅ ሌሎች ጥያቄዎችን አነሳ::
ለምንድነው ይህ ሰው ጦርነቱ ቦታ የመጣው? ጠመንጃ አንስቶ
አልተዋጋም፡፡ ዣቬርን ለመበቀል ሲል ይሆናል በማለት ደመደመ፡፡ ዣቬር ታስሮ ዣን ቫልዣ እየጐተተ ወደ ጓሮ መውሰዱንና በኋላ በጥይት መተኮሱ ለበቀል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ምናልባት በሁለቱ መካከል ከባድ ጥላቻ ኖሮ
ይሆናል ሲል አሰበ፡፡ ያም ሆነ ይህ፣ ዣቬር በዣን ቫልዣእጅ ነው
የሞተወ::
ከዚያም ማሪየስ መልስ የሌለው ጥያቄ ይጠይቃል:: ይህም ጥያቄ
እንደ መርፌ ወጋው:: የኮዜትና የዣን ቫልዣ ሕይወት ይህን ያህል ምን አቀራረበው? ምን ዓይነት ተአምር፣ ምን ዓይነት ኃይል ነው ያቺን ምስኪን ከዚህ ሰው እጅ ላይ እንድትወድቅ ያደረገው? ይህቺን ድንግል ልጅ ክብረ
ንጽህናዋን ጠብቃ እንድትኖርና ራሱ ንጹህ ሳይሆን እርስዋን በንጽህና እንዲጠብቃት፧ እንዲንከባከባት ያደረገው የትኛው ሃይማኖቱ፡ ነው? በትምህርት እስክትበስል ድረስ ለምን አስተማራት? የመጨረሻው ፍላጎቱ ምን ሆኖ ነው እስከዚህ ተጨንቆና ተጠብቦ ያሳደጋት?
የዣን ቫልዥ ምሥጢር ማለት ይህ ሲሆን የፈጣሪም ምሥጢር ይህ
ነው:: ምሥጢር መሆኑም ማሪየስ በይበልጥ ግራ ተጋባ እንጂ ለጥያቄዎቹ መልስ አላገኘም::
ዣን ቫልዣ አላፊ ሰው ሲሆን ይህን ራሱም ተናግሮታል:: ሰውዬው
ማንም ይሁን ማን የበኩሉን ተወጥቶ አልፎአል:: ከአሁን በኋላ ስለኮዜት ሃላፊነት ያለበት ማሪየስ ነው፡፡ ኮዜት በአጋጣሚ የኑሮ ጓደኛዋን ፍቅረኛዋን፣ ባልዋን፣ በአሳብ የሳለችውን ወንድ አግኝታለች:: ኮዜት ክንፍ
አውጥታና ራስዋን ለውጣ ከአንዱ ዓለም ወደ ሌላው ስትሄድ ጠባቂዋን ብቻ ሳይሆን ሁለተኛ ፈጣሪዋን ዣን ቫልዣን ጥላ ነው የሄደች::

👍21
ማሪየስ በዚህ ዓይነት ያስብ፣ ያስብና ዞሮ ተመልሶ ከነበረበት
ይመለሳል፡፡ የዣን ቫልዣ ፍራቻ ከፊቱ፡ ድቅን ይልበታል:: ማሪየስ ምንም እንኳን የሕግ ሰው ቢሆንና ብዙ ቢያውቅም በሰዎች በተደነገገው ሕግና
በእግዚአብሔር ሕግ መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ አያውቅም::ስለአጠቃላይ ሕግና ትክክል ሥራም ልዩነት የነበረው እውቀት ግልጽ አልነበረም፡፡ በእርሱ አመለካከት ሰው ሕግ ከጣስ በሕጉ መሠረት መቀጣት
አለበት::
ዣን ቫልዣ ስለራሱ በሚናገርበት ጊዜ ቅን ሰው እንደሆነ ነው
የተናገረው:: ቢሆንም በማሪየስ ዓይን ዣን ቫልዣ ከኅብረተሰሱ መገለል ያለበት ወንጀለኛ ነው:: ለዚህ ነበር ዣን ቫልዣና ኮዜት ከአሁን በኋላ ግንኙነት እንዳይኖራቸው ማሪየስ የፈለገው:: ቢሆንም ይህ ሰው ራሱን እንደ
ንጹህና ትክክለኛ ሰው ወይም ደግሞ እንበል ራሱን እንደ ደካማ ሰው አድርጎ ቆጥሮአል፡፡ ያ ድክመቱ ነው ከስህተት ላይ እንዲወድቅ ያደረገው::ታዲያ ዣን ቫልዣን ከእርሱ ማራቅ እንጂ ወንጀለኛ ነው ብሎ መደምደም
ትክክል ነው?»
የዣን ቫልዣ ከቤቱ መምጣት ማሪየስን ያበሳጨዋል:: የዚህ ሰው
ከቤቴ መምጣት ምን ይጠቅማል? እንዳይመጣ ምን ማድረግ አለብኝ?» እያለ የተለያየ አሳብ መጣበት:: አንዱ አሳብ ሲሄድ ሌላው ይተካል:: አዲስ
አሳብ በመጣ ቁጥር መፍትሔውን ያገኘ እየመሰለው ይጎመጃል:: ይህን ስሜት ከኮዜት መደበቅ ቀላል አልነበረም:: ነገር ግን ፍቅር ማለት ችሎታና በቀላሉ ራስን ማታለል ማለት ስለሆነ በቀላሉ ሊወጣው ቻለ፡፡ አንዳንድ
ጥያቄዎችን በዘዴ በሚያነሳበት ጊዜ ልብዋ እንደ ነጭ ርግብ የነጣ በመሆነ ምንም አልጠረጠረችም:: ሆኖም ስለሕፃንነትና ስለወጣትነት ዘመንዋ እያነሱ ሲጫወቱ ይህ ምሥጢረኛና ወንጀለኛ ክብር የሚገባው ጥሩ ሰው እንደሆነና
ኮዜትንም ማንም ሰው ከሚያደርገው በላይ መንከባከቡንና ከልብ ማፍቀሩን
አልካደም::....

👍18❤5
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አራት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
ደክሞ የጨለመው ውጋጋን ሲፈካ
በሚቀጥለው ቀን ዣን ቫልዣ ከነኮዜት ቤት ሲሄድ ዘበኛው ትእዛዝ የተሰጠው ይመስል ከበራፍ ቆሞ ጠብቆት ወደ ምድር ቤት ይዞት ሄደ:: ዣን ቫልዣ በጣም ደክሞታል ባለፉት ጥቂት ቀናት እህል አልቀመሰም፤ብዙም እንቅልፍ አልተኛም:
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኮዜት መጥታ ‹ሰላምታ» ስትሰጠው ዞር ብሎ
በማፍጠጥ አያት
‹‹ምነው አባባ፣ ሰሞኑን ደስ አላለህም? ምነው ይህን ጨለማ ቤት መረጥክ! ከዚህ ለመሆን እንደፈለግህ ማሪየስ ነግሮኛል »
«አዎን፣ ነግሬዋለሁ፡፡››
«ትስመኛለህ ብዬ ጉንጬን ሳቀርብ ፊትህን አዞርክብኝሳ? እስቲ አሁን
ሳመኝ:»
እንደመጀመሪያው አሁንም ፊቱን አዞረባት እንጂ አልሳማትም::
«አሁን የከበደው መጣ» አለች ኮዜት እንደመቀለድ ብላ:፡ «ምን አደረግሁ? ግራ ነው የገባኝ፡ ለዚህ ማካካሻ እራት ከእኛ ጋር መብላት አለብህ::››
«በልቼአለሁ:»
«ውሸት ነው፡፡ ና እባክህ፤ አሁኑኑ ወደ ምግብ ቤት እንሂድ»
«አልችልም »
ኮዜት ጨነቃትና በትእዛዝ መልክ ከማናገር ቆጠብ አለች
ለምንግን? እንድንገናኝበት የመረጥከው ክፍል አስቀያሚ ክፍል
ስለሆነ አስጠላህ?»
«ሰማሽ እመቤቴ፧ ታውቂኛለሽ‥ ጠባዬ ከሰው አይገጥምም::›
«እመቤቴ! ይሁና!»
«እመቤቴ መባልን ፈለግሽ: ይኸው አገኘሽው:»
«እመቤትነቴ ለአንተ አይደለማ!»
«ከአሁን በኋላ አባባ እያልሽ ባትጠሪኝ መልካም ነው»
«ምን?»
«መሴይ ዣን ቫልዣ ብለሽ ጥሪኝ፤ ከፈለግሽ ዣንም ይበቃል»
«በቃ ከአሁን በኋላ አባቴ አይደለህም ማለት ነው? እኔም ከአሁን
ወዲያ ልጅህ ኮዜት አይደለሁም ማለት ነው? ይህ ምን ማለት ነው? ምነው
ጠላኸኝ? መከራ ውስጥ ነው የዘፈቅኸኝ:»
በድንገት ኮስተርተር ብላ ዣን ቫልዣ ላይ አፈጠጠችበት:
እያፈጠጠችም የሚከተለውን ቀጥላ ጠየቀችው::
«እኔን ደስ ሲለኝ አትወድም ማለት ነው?»
አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው የአነጋገር ዘይቤ ሳያውቅ ቀርቶ እንዳመጣለት ሲናገር ንግግሩ አጥንት ሰብሮ ይገባል፡ ይህ ጥያቄ ለኮዜት ቀላል ቢመስልም
ለዣን ቫልዣ ከአሜከላ የበለጠ የሚዋጋ ነበር፡ ኮዜት እሰፋለሁ ብላ ተረተረች:: የዣን ቫልዣ ፊት በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ለጥቂት ጊዜ ለጥያቄው መልሰ ሳይሰጥ ዝም አለ፡፡ በመጨረሻ በቃላት ሊገልጽ በማይቻል የአነጋገር ስልት በጣም ዝግ ብሎ እርሱ በራሱ ይነጋገር ይመስል
በማጉረምረም ተናገረ::
«የእርስዋ ደስታ የሕይወቴ ግብ ነበር፡ አሁንስ እግዜር ቢወስደኝ ይሻላል፡ ኮዜት ደስ ብሎሻል፡ ከአሁን በኋላ በቃኝ»
«ጎሽ 'ኮዜት ብለህ ነው እኮ የጠራኸኝ: 'እመቤት አላልክም» ስትል ጮኸች:: ዘልላ ከአንገቱ ላይ ተጠመጠመች::
ዣን ቫልዣ የሚያደርገውን ቢያጣ ጭምቅ አድርጎ አቀፋት፡፡ ወደ ቤቱ መልሶ የሚወስዳት መሰለው
«እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣ አባዬ» አለችው፡፡
ዣን ቫልዣ ቀስ ብሎ ራሱን ካላቀቀ በኋላ ቆቡን አነሳ፡
«እና!» አለች ኮዜት
«ልሂድ» አለ ዣን ቫልዣ ፧ «ይጠብቁሻል ኮዜት» በሩ አጠገብ ሲደርስ መለስ ብሎ ኮዜት ብዬ ጠራሁሽ እኮ ሁለተኛ እንደማይደገምና ይቅርታም እንደጠየቅሁ ለባልሽ ንገሪው፡፡›
ዣን ቫልዣ ወጥቶ ሄደ ኮዜት ከቆመችበት ፈዝዛ ቀረች በሚቀጥለው ቀን በዚያቹ ሰዓት ዣን ቫልዣ ተመልሶ መጣ: ኮዜት
ግን ነገር አላበዛችበትም: መሴይ ዣን» ወይም «አባባ» ብላ ላለመጥራት
ጥንቃቄ አደረገች የፈለገውን እንዲናገር እድል ሰጠችው፡ ማዘንዋንም ላለማሳየት ሞከረች
ምናልባት ከማሪየስ ጋር ስለ ዣንቫልዣ ተነጋግረ ይሆናል:: ሆኖም የሚወዱት ወንድ ቢቀባጥርና ያፈቀደውን ቢናገር ብልጫና ፍሬ ያለው ንግግር እንደተናገረ በመቁጠር በቀላሉ እንደሚረኩበት ሁሉ ያፈቀረችውም ሴት እንዲሁ በቀላሉ ስለምትታለል እርስ በርስ በመተማመን በንግግራቸው ብዙም አልተጨቃጨቁ ይሆናል የፍቅረኞች የማወቅ ጉጉት ከፍቅራቸው አያልፍምና::
በዚህ ዓይነት ብዙ ሳምንቶች አለፉ ዣን ቫልዣ በየቀኑ እየመጣ ዓይንዋን ብቻ አይቶ ይሄዳል: ኮዜት ግን ሀዘንዋ እየቀለላት መጣ እንጂ
ለዣን ቫል የነበራት ፍቅር አልተቀነሶም ዓይንዋን ማየት ዣን ቫልዣን
ያረካዋል አንድ ቀን እንደለመደው ከነኮዜት ቤት ሲመጣ ኮዜት በመርሳት
«አባባ» ስትል ጠራችው:: እርሱ መልሶ «ዣን ይላታል፡ «ይቅርታ፣
መሴይዣን» ትለዋለች እየሳቀች: «ልክ ነሽ» ብሎ ከመለሰላት በኋላ
እንባው ሲወርድ እንዳታየው ፊቱን ወደ መስኮት አዙሮ እንደመናፈጥ
በማለት እንባውን ይጠራርጋል
ዣን ቫልዣ በመጣ ቁጥር ዘወትር ከሚገባበት ክፍል እሳት ተቀጣጥሎ
ነበር የሚጠብቀው: አንድ ቀን ሲመጣ እሳቱ ሳይቀጣጠል ይቀራል: ቆይቶ
ደግሞ በሌላ ቀን ሲመጣ ይቀመጥበት የነበረው ወንበር ከቦታው ይነሳል
በሌላ ቀን ከክፍሉ ውስጥ ጨርሶ ወንበር አይቀመጥም፡ በዚህ ጊዜ
እንዳልተፈለገ ገባው፡ ኮዜት «ለምን እሳቱ አልተያያዘም? ወንበሮቹስ የት ሄዱ? ብላ ስትጠይቅ ዣን ቫልዣ እኔ አዝዤ ነው» ይላታል በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ከነኮዜት ቤት ሳይመጣ ቀረ፡ ኮዜት ሰው
ከቤቱ ላከች::
‹‹ምነው ትናንት ሳትመጣ ቀረህ?» ብለዋል እመቤቴ
«ከትናንት ወዲያም አልመጣሁም» አለ ሳቅ እያለ ሠራተኛዋ አልገባትም፡ ስትመለስ ከ ዣን ቫልዣ ደኅንነት በስተቀር
ለኮዜት ሌላ ነገር አልነገረቻትም
በ1833 ዓ.ም መጀመሪያ አጋማሽ ፓሪስ ከተማ ውስጥ ማሬይ ከተባለ ቀበሌ አካባቢ የሚኖሩ ባለሱቆችና ቦዘኔዎች አንድ ነገር ያያለዘሉ:: አንድ ከወገቡ የጎበጠ፣ ከፀጉሩ የሸበተ ሽማግሌ በየቀኑ በተወሰነ ሰዓት ሽርሽር ይወጣል:: የሚሄድበት መንገድ አንድ ሆኖ ሳለ የሚሸፍነው ርቀት ግን በየቀኑ በትንሽ በትንሹ ይቀንሳል የሚራመደው በጣም ዝግ ብሉ ሲሆን አንድም ቀን ግራና ቀኝ ሳያይ እንዳቀረቀረ ወደፊት ነው የሚጓዘው
አንድ ከተወሰነ ስፍራ ሲደርስ ፊቱ ወገግ ይልና እርስ በራሱ ብቻውን ያወራል ማውራቱን ለማወቅ የሚቻለው ከንፈሮቹ ሲነቃነቁ ነው: ካልቬር ከተባለ ጎዳና ላይ ከሚገኝ አደባባይ ሲደርስ ቆም ይልና አካባቢውን ይቃኛል
" አካባቢውን ቃኝቶ ከጨረሰ በኋላ በአሳብ ተውጦ ዓይኑ እንባ ያቀርራል:
ጥቂት ካለቀሰ በኋላ በመጣበት መንገድ ይመለሳል
ቀን እያለፈ ሲሄድ አደባባዩን በሩቁ ማየት እንጂ ከእዚያ ለመድረስ አልቻለም፡ ሰውነቱ እየደከመ ሄደ:፡ ወደኋላማ ወደ አደባባዩ መጠምዘዣ መድረስ እንኳን ተሳነው፡፡ በየቀኑ በዚህ ዓይነት በተወሰነ ሰዓት ከቤቱ እየወጣ ጉልበቱ እስከፈቀደለት ድረስ ተጉዞ ይመለሳል፡፡ ዝናብ ሲሆን ጥላ ይይዛል፡ ብርድ ሲሆን ካፖርት ይለብሳል፡ የሚሸፍነው ርቀት ባጠረ ቁጥር ከደረሰበት ቆም ይልና አንገቱን ከነቀነቀ በኋላ ግራ ቀኙን ተመልክቶ ይመለሳል፡፡ ከጊዜ በኋላ የተቀነሰው መንገዱ ብቻ አልነበረም፤ የእንባውም ዘለላ ተቀነሰ፡ በመጨረሻ እስከነአካቴው ዓይኑ ደርቆ ለማልቀስ ቢፈልግም እምባ አይወጣውም:፡ በየእለቱ ሽማግሌው ብቅ ሲል አንዲት አሮጊት «የሚገርም ነው‥ ሰዓቱን ጠብቆ ይመጣል፣ አይቀራትም መቼም» ይላሉ፡
ከተወሰነ ነጥብ ሲደርስ ደግሞ ልጆች እየሳቁ ይከተሉታል
አንድ ቀን ዣን ቫልዣ ከቤቱ ወጥቶ ከዋናው ጎዳና ሲደርስ ሦስት
እርምጃ ወደፊት ከተራመደ በኋላ ከድንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡ ሰኔ 5 ቀን
ከዚህች ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ነው ጋቭሮችን ያነጋገረው:፡ ጥቂት አወጣ፣
አወረደና ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ከዚያ በኋላ ለሽርሽር መውጣት አልቻለም::
በሚቀጥለው ቀን ከክፍሉም አልወጣም:: አሁንም በሚቀጥለው ቀን ከአልጋው አልተነሳም::

👍16
ሠራተኛዋ በሚቀጥለው ቀን ወደ ክፍሉ ስትገባ ያቀረበችለትን ምግብ
አለመነካቱን ስታይ «ምነው አንድ ጉርሻ እንኳን!» ስትል ጮኸች፡፡
ዣን ቫልዣ የአሮጊትዋን እጅ ነካ ነካ በማድረግ «ዛሬ ለመብላት እሞክራለሁ» ሲል ቃል ይገባላታል፡፡
«አሁንስ አበዙት፤ ምነው ሠርቼ ሠርቼ ለፍቶ መና ያደርጉኛል?»
ዣን ቫልዣ ከዚህች ደግ አሮጊት ሌላ የሚያየው ወይም የሚያነጋግረው
ሰው አልነበረም: የዣን ቫልዣ ሰፈርም ሆነ ቤት ጭር ያለ ነበር አሮጊትዋ ሥራዋን ሠርታ ከቤትዋ ስትመለስ አሁንስ አልሆነላቸውም ፧ ከአልጋቸው እንኳን ተነስተው አያውቁም፧ ብዙም የሚቆዩ አይመስሉም፡ ምነው ልጃቸው ረሳቻቸው» እያለች ከባልዋ ጋር ትጫወታለች፡
አንድ ቀን የሰፈር ሐኪም በዚያ ሲያልፉ አይታ ከዣን ቫልዣ ዘንድ ይዛቸው ሄደች: ዣን ቫልዣን መረመሩት በጠና መታመሙን ሐኪሙ ገለጹ
«ምን ሆኑ?»
‹‹በአንድ በኩል ምንም፧ በሌላ በኩል ሁሉም ነገር ሆኖአል» ሲሉ
ከመለሱ በኋላ «ምናልባት የፈለገውን አጣ መስለኝ አንዳንድ ሰዎች የፈለጉትን ሲያጡ ከመታመም አልፈው እስከ መሞት ይደርሳሎ» ሲሉ ተናገሩ፡፡
‹‹ምን ነገርዎት?» ስትል ሠራተኛዋ ጠየቀች:
«ደህንነቱን ገልጾልኛል» አለ ሐኪሙ ሲመልስ
«ይመለሳሉ ዶክተር?»
«አዎን እመለሳለሁ» አሉ፤ «ግን ከእኔ ይልቅ ሌላ ሰው ቢመጣ
ይሻል ነበር፡፡»
አንድ ቀን ዣን ቫልዣ ከአልጋ መነሳት አቃተው፤ ትንፋሽም አጠረው::
እየደከመ መሄዱን አወቀ እንደምንም ታግሎ ከአልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ
አለ፡፡ ጥቂት እረፍት ካደረገ በኋላ ከአልጋው ተነስቶ ልብሱን ለበሰ::
ልብሱን ለብሶ ሳይጨርስ በመካከሉ ለማረፍ ተገደደ ልብሱን ለመልበስ
ጥረት በማድረጉ ብቻ ላብ አሰመጠው::
ያቺን ትንሽ ሻንጣ ከፍቶ የኮዜትን ልብስ አወጣ፡ ከአልጋው ላይ ዘርግቶ አስቀመጣቸው:: ጳጳሱ የሰጡትንም የሻማ ማንደጃ አውጥቶ ከጠረጴዛ ላይ አስቀመጠ፡፡ ከመሳቢያ ውስጥ ሁለት ሻማ አወጣና ከሻማ ማቀጣጠያው
ላይ ካስቀመጣቸው በኋላ ለኰሳቸው: ግን ቀን ነበር በፈረንጅ ባህል ሰው
ሞቶ አስከሬኑ ከተቀመጠበት ሥፍራ ቀንም ቢሆን ሻማ ይበራል::
ከወዲህ ወዲያ በማለቱ ሰውነቱ ዛለ፡፡ ለመቀመጥ ተገደደ ከፊት
ለፊት በነበረው መስታወት ፊቱን ተመለከተ: የእርሱ ፊት መሆኑን
ማወቅ ተሳነው፡ በጣም ተለዋውጧል፡፡ እድሜው ሰማንያ ዓመት ነው:: ከግምባሩ ላይ የሞት ጥላ አንዣብቧል አፉ ደርቋል፤ ጉንጩ ሰርጉዷል፧ ግምባሩ ተጨማድዷል፤ ዓይኑ በርሯል ነፍሱ በተስፋ መቁረጥ ጓጉሎአል
በድንገት አንቀጠቀጠው፡፡
«ወይኔ!» ሲል ጮኸ:፡ ከእግዚአብሔር በስተቀር የሰማው አልነበረም
«አልቋል፤ ከአሁን በኋላ ሁለተኛ ኮዜትን አላያትም: ወደሚቀጥለው ዓለም
መጓዜ ነው፡፡ ምነው ነፍሴ ሳትወጣ አንድ ጊዜ ባየኋት‥ ቀሚስዋን በነካሁ
ያቺን መልአክ ለመጨረሻ ጊዜ ትኩር ብዬ ባየኋት! ከዚያ በኋላ በሞትኩ
መሞት እኮ ምንም አይደለም ግን ሳላያት መሞቴ ነው የሚያስቆጨኝና
የሚያንገበግበኝ:፡ አሁን መጥታ ፈገግ ብላ ባናገረችኝ: ይህ ማንን ይጎዳል?
ብቻ... የለም... አልሆነም: ይኸው እዚ እኔ ብቻዬን ጣዕር ይዞ ያጣድፈኛል
ብቻዬን! ወይ አምላኬ፣ ወይ አምላኬ ስማኝ፡ ሁለተኛ አላያትም?
ልክ ይህን ሲያሰላስል በር ተንኳኳ፡....

👍24❤3
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
ዉሃ ሆንሁ፣ የመጨረሻዉን ድንጋጤ ደነገጥሁ።
ከነበርሁበት የምድር በታቹ የሲራክ ፯ ማዕከል ወጥቼ በቅርበት ወደሚገኘዉ የድንግል ማርያም ገዳም ለጸሎት ገባሁ አንድ ያለኝ አቅም ጸሎት ነዉና፣ አሳፍሮኝ የማያዉቀዉን አምላክ በእናትህ እርዳኝ አልሁት ተንበርክኬ ከተንበረከክሁበት ተነስቼ በምሥራቅ በኩል ባለዉ የቅጽሩ
በር ልወጣ እየተራመድሁ ልክ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ ላይ ስደርስ፣ ደስ የሚያሰኝ የሕጻናት መዝሙር በጆሮዬ ጥልቅ አለ በክፍቱ መስኮት አስግጌ ወደ ዉስጥ ስመለከት፣ ሰልፍና ልብሳቸዉን ያሳመሩ ሕጻናት “ሀገሪትነ” የሚለዉን ነባር ዝማሬ በኅብረት ያጠናሉ። ለአጭር
አፍታ ከዝማሬያቸዉ ቀምሼ መንገዴን ልቀጥል እግሬን ሳነሳ አንድ በየት
በኩል እንደ መጣ ያላየሁት፤ 'ቤ መ' የሚል ኮድ ያለዉ ታርጋ የለጠፈ
መኪና ከሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ በር ጥሩንባዉን ነፋና ሲጢጥ ብሎ ቆመ። የታርጋዉ ኮድ ትኩረቴን ስለ ሳበዉ፣ በአዳራሹ እና በግቢዉ አጥር መካከል ወዳለዉ ሰዋራ ሥፍራ ተሰዉሬ የሚሆነዉን ሁሉ በሥርቆሽ መከታተሌን ጀመርሁ: አፍታም ሳትቆይ፣ ሕጻናቱን
እያስጠናች የነበረችዋ ወጣት ወደ በሩ ብቅ ብላ አየችዉና ልጆቹን
እንዲወጡ ጠራቻቸዉ። ሕጻናቱም በደስታ እየፈነደቁ ተሯሩጠዉ ወጥተዉ የመኪናዉ በር እስከሚከፈትላቸዉ ድረስ ተቁነጠነጡ።
“ኧረ ክፈቱልን” ይላል አንደኛዉ ሕጻን፣ አላዳርስ ብሎት በሩን ራሱ
ለመክፈት እየታገለ
“ስሚ ለማን እንደምዘምር አዉቀሻል ግን? ለመንግሥት እኮ ነዉ” ትላለች ሌላኘዋ ጓደኛዋን ለማስቀናት በሚመስል አኳኋን አንገቷን እየወዘወዘች።
“ለመግሥት? ኧረ አይባልም!” ብላ አረመቻት ያቺኛዋ፣ በሳቅ ቡፍ
እያለችባት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስም ጠርታ፣ መንግሥት ያለችዋን ልጅ አላገጠችባት።
አሁን ነዉ እንግዲህ መፍጠን አልሁት ለራሴ፡ ዕድሎች ከስንት አንድ
ከላይ ይወርዱልናል፣ አብዛኞቻችን ግን ራሳችን ነን የፈጠርናቸዉ› ሲባል
ሰምቼ ነበር በማዕከላችን በሲራክ ፯ ከስንት አንድ ከሚወርዱት ዕድሎች
አንደኛዉ ይኼዉ የዓይኔ ብረቱ ሥር ወርዶልኛል።
እንዴት ብጠቀመዉ ይሻላል?
ሁሉም ሕጻናት ከወጡ በኋላ መዝሙሩን ያስጠናችዋ ወጣት መብራቱን
አጠፋፍታ ነጠላዋንም በቅጡ እያጣፋች መጣች፡ ይኼ ሁሉ ሲሆን ሾፌሩ
አልወረደም አለመዉረዱ ሲገርመኝ፤ በሩንም ራሷ እንድትከፍትላቸዉ
ጠበቃት እሷ ደርሳ ስትከፍትላቸዉ ልጆቹ እሽቅድምድም ፈጥረዉ አይገቡ የለም እርስ በእርስ እየተጣጣሉ ገቡ፡ አሁን መኪናዉ ፊቱን አዙሮ ይሄዳል ብዬ ስጠባበቅ፣ ምን እንደ ረሳች እንጃላት፣ አስጠኛቸዉ ወረደችና ተመልሳ ወደ አዳራሹ ሮጣ ገባች። ይኸኔ ጥግ ለጥግ
ተሹለኩልኬ የአዳራሹን የኋላ በር በኃይል አንኳኳሁባት። ያለ ምንም ፋታ ደጋግሜ ሳንጓጓባት ብልጭ ብሎባት በእልህ ከፈተችልኝ።
“እ! ምንድነዉ?” አለች፣ በሩን በጥድፊያ ስትከፍተዉ እኔ በድንግዝግዙ
ዉስጥ ብቁለጨለጭባት የተመለሰችዉ ከበሮዉን ረስታዉ ኖሯል ለካ፣
በቀኝ ትከሻዋ አንግታዋለች ለኹለት ሰዓታት ሰመመን ዉስጥ የሚከተዉን ቅባት የረጨሁባቸዉ መዳፎቼን እያፋተግሁ ትንሽ የመዘናጊያ ፋታ ከሰጠኋት በኋላ ዘልዬ አፏን አፈንሁት፡ በቅጽበት መዝለፍለፍ ስትጀመርልኝ፤ ከበሮዉን በአንድ እጄ፣ እሷን ደግሞ
በሌላኛዉ እጄ ለመደገፍ ሞከርሁ፡ ሽርተት ብላ መሬት ያዘችልኝ፡ ዝቅ ብዬ እጄን በመሬቱ አሽቼ ቅባቱን ካረከስሁት በኋላ፣ ነጠላዋን ልክ እሷ ተከናንባዉ እንደነበር አድርጌ አጣፋሁትና ከበሮዉን አንስቼ አነገትሁት ክራሬንም በግራ እጄ አንጠለጠልሁትና መብራቱን አጠፋፋሁ፡፡
መኪናዉም ፊቱን አዙሮ ለመሄድ ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቀኝ፡ ከሾፌሩ ይልቅ ሕጻናቱ እንዳይለዩኝ የባሰ ስለ ሰጋሁ፣ ከበሮዉን ከኋላ ጭኜ፣ ጋቢና ገባሁ ብቻ የፈራሁትን ያህል ሳልቸገር፣ ወደ ታላቁ ቤተ መንግሥት ገባሁ የመኪና ማቆሚያዉ ላይ ስንደርስ፣ ሌላ ሰዉ ተቀብሎን ወደ
ግብዣዉ አዳራሽ ወሰደን በዚያ ስንደርስ ደግሞ አንዲት ባህላዊ ቀሚስ
የለበስች ሴት ተቀብላ ከመድረኩ ጀርባ ካሉት ክፍሎች ወደ አንደኛዉ
አስገባችን ክፍሉን ሳየዉ ጠበብ ያለ ቢመስለኝም፣ ስንገባበት ግን ጠብ
እንኳን አላልንበትም ሌላ ብዙ ሰዉ ቢጨመር ሁሉ አይጠብም፡ በዚያም
ላይ የመድረኩን ትዕይንት በቀጥታ የሚያስተላልፍልን ዘመናዊ
ቴሌቪዥን ግድግዳዉ ላይ ተሰቅሎበታል
አሁን ነዉ ጉዱ ከሕጻናቱ ጋር በደማቅ ብርሃን ልፋጠጥ ነዉ፡ መቼም ጥያቄ
መጠየቃቸዉ አይቀር፣ ወይ ደግሞ እንድናገር የሚያደርጉበት አንድ ነገር
አያጡም: ያስጠናቻቸዉ ወጣት እንዳልሆንሁ ሲያዉቁ ምን ያደርጉ
ይሆን? በተቻለኝ መጠን አንገቴን አቀርቅሬ ወዲያ ወዲህ እያልሁ ራሴን ባተሌ አደረግሁባቸዉ። ዓይናቸዉ ዉስጥ ላለመግባት ብዙ ተፍተለተልሁ መቆያ ክፍል የሰጠችን ደርባባ ሴት ተመልሳ መጣችና የመርሐ ግብሩ ቅደም ተከተል የሰፈረበት ወረቀት ሰጠችኝ፡ አስከትላም፣
የኛ ተራ እስከሚደርስ ድረስ የመጨረሻ ልምምድ ማድረግ ከፈለግን፣
ያለንበት ክፍል ድምፅ ወደ ዉጪ ስለማያስወጣ እዚሁ መለማመድ
እንደምንችል አሳወቀችኝ፡ ስለዚያ ገና ሳላመሰግናት፣ መቆያ ምግብ
እንድናዝዝ ጎንበስ ብላ ጠየቀችን፡ እንዲህ ያለችዋ ሽቁጥቁጥ ሴት ለሕጻናቱ ከተመደበች፣ ለዋናዎቹ እንግዶችማ እንዴት ያለ ሰዉ ሊመደብ እንደሚችል ገመትሁ። መቼም ትሕትናዋ ወደር አይገኝለትም: ምንም እንኳን ሕጻናቱ ምርጫቸዉን እየለዋወጡ ረዥም ሰዓት ቢወስዱባትም፣ከበሬታዋ ግን አልቀነስም፡ እኔም እንዲሁ ወዳፌ የመጣልኝን የባቄላ
ሾርባ አዘዝሁ።
የሕጻናቱን መዝሙር ተከትሎ መንዙማ የሚያቀርቡ ሙስሊም ሕጻናትም መኖራቸዉን ያወቅሁት ወረቀቱ ላይ የሰፈረዉን ዝርዝር መርሐ ግብር ከተመለከትሁ በኋላ ነበር ሰዓቴን ስመለhት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ይላል። በዕቅዱ መሠረት መዝሙር ለሚቀርብበት ተራ፣ ሃያ ደቂቃዎች ይቀራሉ ማለት ነዉ: ከፊቴ የተሰቀለዉ ቴሌቪዥን፣
የአዳራሹን ትዕይንት ቀጥታ እያመጣ ስለሚያሳየኝ፣ የተጠቀሱት መርሐ
ግብራት ያለ ምንም መጓተት በየተራቸዉ እየቀረቡ መሆኑን አዉቄያለሁ:
ሲንሾካሾኩ ሰምቼ በቀስታ ዞር ብል ሁሉም ሕጻናት አፍጥጠዉብኛል ዝምታየ ሽሽቴ፣ አድራጎቴ ሁሉ ገርሟቸዉ! ወዲያ ስልም ወዲህም ስል በዓይናቸዉ ይከታተሉኛል። የመጣዉ ይምጣ ብዬ ክንብንቤን ገለጥ
አደረግሁና፤ ማንነቴን በከፊል ነገርኋቸዉ።
“እንዴ?” ተባባሉ
“አላልኋችሁም? እግዚሐርያ አይደለችም” አለ አንደኛዉ ሕጻን፣ዉርርዱን በማሸነፍ።
“እሷስ?”
“እግዚሐርያስ?”
"በጥያቄ አካለቡኝ"
“እግዚሐርያ እኮ ድገት አሟት ተተኪልኝ ብላኝ ነዉ” አልኋቸዉ፣ መዝሙሩን ያስጠናቻቸዉ ልጅ እግዚሐርያ መባሏን ከራሳቸዉ አፍ ስላወቅሁ ስሟን መጥራቴ ለአመኔታ እንደሚያግዘኝ በማሰብ
“ኧረ ቅድም ደህና አልነበረች? ከምኔዉ አመማት?” አለ፣ ከመካከላቸዉ
ቅድም ጀምሮ ቀደም ቀደም የሚለዉ ልጅ።
“ግድየለምቆይ፤ በኋላ በስልክ አገናኛችኋለሁ: አሁን መዝሙሩን
ለመጨረሻ ጊዜ እንለማመደዉ? የማቅረቢያ ሰዓታችን እየደረሰ ነዉ። በሉ
ተነሱ። ተነሷ” አልሁ በመለማመጥም በማጣደፍም ጭምር፣ ከዚህ በላይ
እንዳይከራከሩኝ በልቤ እየጸልይሁ፡ ክራሬን እየቃኘሁ “በሉ እሺ፤
መዝሙሩን ለመዘመር፣ በአብ በወልድ በመፈስ ቅዱስ ስም…”አልኋቸዉ፣ ፋታ ላለመስጠት እዉነትም አላሳፈሩኝም፤ ብድግ ብድግ አሉልኝ፡ ከመካከላቸዉ ትንሽ ከፍ የምትለዋ ልጅ ከበሮዉን አነሳች፡ እኔም መዝሙሩን በቅጡ የምችለዉ ስለሆነ፣ እምብዛም
ሳልደነቃቀፍባቸዉ ጥሩ አድርገን አብረን ወጣነዉ

👍39
ተራችን ደርሶ ወደ መድረኩ ገባን፡
ሕጻናቱ የዝማሬ ባለጸጎች ናቸዉ። ቁጥራቸዉ ምን ትንሽ ቢሆንም፣ ከዚያ
ሰፊ መድረክ ግን የተረፈ ቦታ አይታይም። ሰልፍ ማሳመሩን አወቁበት ምነዉ እግዚሐርያ የልፋቷን ዉጤት ባየች ኖሮ! በዚያም ላይ በመዝሙሩ የተጠራችዉ ሀገሩ ስለሆነች፣ ሰረቅ አድርጌ ስመለከት በአግራሞት እጁን አፉ ላይ ያልጫነ ታዳሚ አጣሁ: ሽብሻቧቸዉ፣ የድምፅ ምጣኔያቸዉ፣ ነገረ ሥራቸዉ ሁሉ፣ ከእነሱ ዕድሜ ከእኔም አእምሮ በላይ ነዉ ሰአሊ ለነ!
ልክ እንደ ጣፈጠ፣ እልቅ አለ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀር ማልለዋል እየተቁለጨለጩ ወደ እኛ
ሲመለከቱ፣ ሌላ መዝሙር ብንጨምርላቸዉ የበለጠ እንደሚወዱ
ከግንባራቸዉ ላይ ያነበብሁ መሰለኝ። ከእኛ በኋላ መንዙማ የሚያቀርቡትን ሕጻናት ሰዓት እንዳንወስድ እየፈራሁም ቢሆን፣ ክራሬን ገረፍሁት፡ ሕጻናቱ፤ በዓይኔ እንኳን እንዲህ ነዉ እንዲህ ነዉ ሳልላቸዉ
የክራሩን ዜማ ብቻ ተhትለዉ ማሸብሽቡን ቀጠሉበት በተለያየ ምክንያት ዕለት በዕለት የማይቋረጠዉን ሐዘን ሳስብ ቀድሞ የመጣልኝ “ሐዘነ ልቡና” የሚለዉ መዝሙር ስለነበር፤ በእንባ ጭምር እያጀቡኝ ዘምረነዉ እንዳማረብን ጨረስን፡፡ አዳራሹ እንደገና በጭብጨባ ቀለጠ። ሼሆቹ ሳይቀር ብድግ ብለዉ ከበሬታ አሳዩን፡ ጳጳሳቱም በልጆቻቸዉ ኩራት
ኩራት ሳይላቸዉ አልቀረም: ከታዳሚዉ ሁሉ ያልቆመ አይታየኝም፡ ልዩ ሆነ፡፡
ልክ ከመድረኩ ስንወርድ፣ ልጆቹ ወደ ልጅነታቸዉ ተመለሱ እንደ አባቶቻቸዉ ዘምረዉ ሲያበቁ፣ እንደ ልጅነታቸዉ በመንገዳቸዉ ያገኙትን ሁሉ ማንሳት መጣል ጀመሩ። ለጨዋታ መጎነታተላቸዉን እንደገና አመጡት፡ በኋለኛዉ በር ወጥተን ወደ ክፍላችን እየሄድን ሳለንም፣ አበባ ካልቀጠፍን እና ያየነዉን ሁሉ ካልነካን እያሉ አስቸገሩ፡
“ደስ ስትሉ!” አልሁኝ ሁኔታቸዉ ሁሉ ደስ ቢለኝ፡
“ካንቺ ይበልጥ?” አለኝ፣ ከኋላዬ ድንገት ከተፍ ያለ ሰዉዬ፡፡ ዞር ስል፣ ቡዝዝ ብሎ ሲያየኝ ደረስሁበት መፍዘዙ ሳያንስ በፈገግታዉም ላይ መሽኮርመም አለዉ፡ “ለካ ክራርም ጉሮሮ ኖሮታል እንዲህ? የሚደንቅ ነዉ ችሎታሽ!” ሲል ጨመረልኝ፡
“ክራር ትወዳለህ ማለት ነዉ?”
“ኧረ በጭራሽ! ቀድሞ ነገር ክራርና ሰዉ እንዲህ አፍ ለአፍ ሲነጋገሩ
ገጥሞኝ የት ያዉቅና!”
ወሬያችንን እንዴት ማስቀጠል እንዳለብኝ ሳወጣ ሳወርድ፣ ጆሮዬ ላይ በሰካሁት ረቂቅ ስልክ፣ ፈጣን ጺዉጺዉታ ሰማሁ። ከሲራክ፯ እንደሆነ ስለገባኝ ለሰዉዬዉ ንግግር የተሸኮረመምሁ አስመስዬ መሬት መሬት እያየሁ፣ ሳላስነቃ ከወዲያ በኩል የሚተላለፍልኝን መልእክት
አዳመጥሁት፡ “በጥቃቄ፤ አሁኑኑ!” ተባልሁ።
“ክራሩን ካልሆነ እንግዲያዉ መዝሙሩን ነዋ የወደድኸዉ” አልሁት፣ለመቀራረብ የፈለግሁ በሚመስል እርጋታ
“መዝሙር? ባይገርምሽ እንደ መዝሙር የሚያስጨ ንቀኝ ነገር የለም”
“ይቅርታ: እኔ እኮ ደስ አለኝ ያለኸኝ የልብህን መስሎኝ ነበር''
“ደስታ ቢሉሽ ደስታ መሰለሽ?”
“መዝሙሩንም ክራሩም ልሆ እንግዲያዉ ምኑ ነዉ የወደድኸዉ?”
“አንቺን”
“አቤት?”
“እንዳንቺ ደስ ያሰኘኝ የለም ምነዉ ክራሩን ባደረገኝ የምታሰኝ ዓይነት
ሴት ነሽ: ግዑዙን ያናገርሽ እኔንማ…”
“ማለት!?” አልሁት፣ ቆጣ ብዬ። ለቁጣዬ መልስ መስጠቱን ቸል ያለበት
መስሎ ቅድም የነበርንበትን ክፍል በር ወለል አድርጎ ከፈተዉ። እኔ ላይ
መንገድ ዘግቶብኝ፣ ልጆቹን እንዲገቡ ነገራቸዉ፡ ሕጻናቱም ግር ብለዉ
ገቡለት “ልጆች፣ አሁን እራት እየደረሰላችሁ ነዉ እሺ? በሉ የምትፈልጉትን ምረጡና ጠብቁ፣ ይመጣላችኋል” አላቸዉ፣ በሩን ሊዘጋባቸዉ እየቸኮለ፡ በእሱ ቤት እኔ
እልም ያልሁ ጅል፣ እሱ ደግሞ እልል ያለ ብልጥ መሆኑ ነዉ። ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ሃይማኖተኛ የሚመስሉ ሰዎች ሁሉ እንደ ሞኛሞኝ ሲገመቱ አያለሁ: መስሎታል!
“ አንድ ቦታ ልዉሰድሽ?”ፈ
“የት?”
"እዚሁ ቤተ መንግሥቱ ግቢ ዉስጥ: እርግጠኛ ነኝ ትወጂዋለሽ: ተከተዪኝ” ብሎ፣ እጄን ያዝ አደረገኝ
“አይ…” አልሁት እጄን መንጭቄዉ፣ አንዴ ከተዘጋ ያለ ካርድ እንደማይከፈት ባዉቅም በሩን ለመክፈት እየታገልሁ
“ስታይ ክፉ ሰዉ ነዉንዴ ምመስለዉ? ምን ማደርግሽ መስሎሻል?”
"ኧረ እንደዛ አስቤ አይደለም” አልሁት የበለጠ ገራገር
እየመሰልሁለት፣ በልቤ ግን ባልቻ ባስጠናኝ የቤተ መንግሥቱ ካርታ
መሠረት አሁን የት እንዳለሁ እያገናዘብሁ። የተቋረጠዉ ካሜራ አሁን ከቆምሁበት ሥፍራ ከሦስት መቶ ሜትር በላይ ባይርቅም፣ የተቋረጠበትን ምክንያት ለማወቅ ግን በሚንቀለቀል እሳት መካከል
ይጠበቅብኛል ምክንያቱም ካሜራዉ ተሠዉሮ የነበረበት ቦታ፣ በዋናዉ አዳራሽ እና ጠቅላይ ሚንስትሩ ከካቢኔያቸዉ ጋር አዘዉትረዉ ስብሰባ በሚያደርጉበት ልዩ ክፍል መካከል ነዉ በአካባቢዉም ታላላቅ የቤተ መንግሥቱ እንግዶች የሚያርፉባቸዉ ክፍሎች ስለሚገኙበት፣ መንገዱ
ሁሉ ባነጣጠሩ ወታደሮች የተሞላ ነዉ
“አየሻት ኣ ጨረቃ ዝም ስትል?” ዓይን ዓይኔ ላይ እየተቁለጨለጨ፡ እርፍ! እኔ ተልእኮ ተልእኮዬን ሳዉጠነጥን፣ አጅሬ ጭራሽ ያን ግንዲላ እጁን ትከሻዬ ላይ ጭኖብኛል? ደግሞ የእጁ ክብደት!
“አሸማቀቅሻት”
“ማንን?”
“ጨረቃን”
“እ?”
“የምሬን እኮ ነዉ፤ ልዩ! ነሽ በጣም: ወታደሮች እያቸዉ እስኪ
ሥራቸዉን ትተዉ አንቺን እኮ ነዉ የሚያዩት” አለ፣ የምሩን በሚመስል ፈዘዝታ። እዉነትም ግን እዚህም እዚያም በየሥርቻዉ
በንቃት ከቆሙት ወታደሮች፣ በአጠገባቸዉ ስናልፍ ሁሉ የከለከለን አልነበረም ምናልባትም ባልደረባቸዉ እኔን የመሰለች ቆንጆ አቅፎ ስላዩት ኮርተዉበት፣ ወይ ደግሞ አለቃቸዉ ቢሆን ይሆናል ስል አሰብሁ።
የሆነዉ ሆኖ፣ ማናቸዉም ወዴት ነዉ፣ ይቺ ደግሞ ማናት አላሉም።
“ኧረ የት እየወሰድኸኝ ያለኸዉ?” አልሁት፣ ባጠናሁት ካርታ መሠረት
ወደ ካሜራዉ የሚወስደኝ መታጠፊያ ላይ ስንደርስ ድንገት ቀጥ ብዬ ቆሜ፡
“ትንሽ እኮ ነዉ የቀረ” አለኝ የመለማመጥ ያህል።
“እኮ የት ለመድረስ? ቆይ የት ነዉ እየወሰድከኝ ያለኸዉ?” አልሁት
ለስንተኛ ጊዜ እንደሆነ እንጃ፣ ከዚያች ልብ ከምትሰርቅ ፈገግታዬ ጠብ አድርጌ እያቀመስሁት።
“ልክ በዚያኛዉ ቅያስ ትንሽ እንደሄድን የቤተ መንግሥታችንን ቁጥር አንድ ሬስቶራት እናገኛለን: ለስላሳ ምናም ብጋብዝሽ ችግር አለዉ? ደግሞ ለስላሳ ቢሉሽ ለስላሳ እዳይመስልሽ! ጣፋጭ የሲንጋፖር ለስላሳ ነዉ የምጋብዝሽ: ቀምሰሽ ታዉቂያለሽ?” አለኝ፣ የኮቱን ቁልፍ መላልሶ ከፍቶ እየቆለፈ
“ኧረ እኔ ሲባልም ሰምቼ አላዉቅ”
“ግድ የለሽም ትወጅዋለሽ "
ባይገርምሽ እኔም የሲጋፖር ለስላሳ ሥጋብዝ አንቺ ሦስተኛዬ ነሽ: መጀመሪያ እኔ ለራሴ፣ ቀጥዬ ለእናቴ፣ አሁን ደግሞ ላንቺ: ምናለ በዪኝ ትወጂዋለሽ''
ትንሽ ተግደረደርሁበት በእርግጥ መግደርደር ፈልጌ ሳይሆን የማደርገዉ ቸግሮኛል። እሺ ብዬ እንዳልጋበዝለት፣ ሰዓቱ እየነጎደብኝ ነዉ። በዚያም ላይ የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ጆሮዬ ላይ በደበቅሁት ረቂቅ ማዳመጫ በኩል እየመጣ እንድፈጥን ይወተዉተኛል፡ ግብዣዉን እምቢ እንዳልለዉ ደግሞ፣ አመኔታዉ እንዳይቀንስብኝ ሰጋሁ፡ ቸኩዬ ዕድሌን እንዳላበላሸዉ

👍21❤1👏1
ፈራሁ። ለአፍታ ከራሴ ጋር አወጣሁ አወረድሁና፣ ግብዣዉን
ተቀበልሁለት ራመድ ራመድ ብሎ ወደ አንድ በደብዛዛ ብርሃን ወደ
ተሞላ ቤት መራኝ፡ ልክ ወደ በራፉ ስንጠጋ፣ በሩ በራሱ ጊዜ ወለል
ብሎ ተከፈተልን ወደ ዉስጥ እንደ ዘለቅን ኹለት አማራጮች ብቻ
ቀሩን፣ ወደ ግራ ወይ ደግሞ ወደ ቀኝ መታጠፍ ብቻ: በኹለቱም በኩል ግን ምንም ሬስቶራንት የሚመስል ነገር አይታየኝም፡ ድንገት ቅፍፍ አለኝ ቢሆንም ግን ተከተልሁት። ወደ ግራ ታጥፎ፣ አንድ በር ከፈተና ፈገግ ብሎ ወደ እኔ መለስ አለ፡ እንደ ደህና ወዳጅ ጭምድድ አድርጎ አቅፎ
ወደ ዉስጥ ወረወረኝ።
ወ ይ ኔ!
ቡጭቅ አድርጎ ተጫዉቶብኛል!
ሬስቶራንት ብሎ ነገር የለም፡ እንኳንስ የሲንጋፖር ለስላሳ ይቅርና፣የወንጂ ስኳር መጠቅለያ ወረቀት እንኳን በቤቱ የለበትም: ተወልዉሎ በታጠበ ወለል ላይ አንዲት የእንጨት ወንበር ተገልብጣ ወድቃበታለች
ቀና ብዬ ሳይ ግድግዳዉ ዙሪያዉን በአመድ መሳይ ልሙጥ ቀለም
ተለቅልቋል፡ እንዲያዉ ለማስመሰል እንኳን ጥርሶቼን መግለጥ አቃተኝ፡
“አሥር ደቂቃ ሰጥቼሻለሁ!”
እንደ ምንም ዞር ብዬ አየሁትና፣ “0ሥር ደቂቃ ሁሉ?” አልሁት ቀለል አድርጌ: ዉስጥ ዉስጤን ያልተበለጥሁ ለመምሰል ከራሴ ጋር እዋደቃለሁ። “ኧረ ዐሥር ደቂቃ ብዙ ነዉ: አይበዛም?”
“ደህና” አለኝ፣ በአንድ እጁ ጆሮዬ ላይ የተኛዉን ጸጉሬን እየገላለጠ፣
የሌላ እጁን አይበሉባ ደግሞ ጉንጮቼ ላይ እያመላለሰ፡ ቀጥሎ ሌባ ጣቱን ወደ ግራ ጆሮዬ አስገባ: ረቂቋን የጆሮ ማዳመጫ አዉቆብኝ ኖሯል፤ መንጭቆ አወጣብኝ፡፡......
✨ይቀጥላል✨

👍16❤3
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አምስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
ብቻ... የለም... አልሆነም: ይኸው እዚ እኔ ብቻዬን ጣዕር ይዞ ያጣድፈኛል
ብቻዬን! ወይ አምላኬ፣ ወይ አምላኬ ስማኝ፡ ሁለተኛ አላያትም?
ልክ ይህን ሲያሰላስል በር ተንኳኳ፡
ያን እለት፤ ሰዓቱ ግን ትንሽ ቀደም ይላል፤ ዣን ቫልዣ እንደዚያ ጣዕር ይዞት ሲታገል አሽከር ለማሪየስ ደብዳቤ ያመጣለታል፡ ደብዳቤው ሲሰጠው ማስታወሻውን የሰጠው ሰው ከሳሎን ቤት እንደሚጠብቅ
ይገለጽለታል፡ ደብዳቤውን ከፍቶ አነበበው::
«ጌታዬ፣ እኔም ፈጣሪ ቢልልኝ ኖሮ ባሮን ቴናድዬ በመባል ጌታ የጌታ ልጅ ተብዬ በታወቅሁ ነበር ግን አላለልኝም፡፡ ያም ሆነ ይህ አሁን ለምትውልልኝ ውለታ ወይም ለምታደርግልኝ እርዳታ አጸፋ እመልሳለሁ፡፡»
«ስለአንድ ሰው ምሥጢር አውቃለሁ፡፡ ግለሰቡ ከሕይወትህ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ምሥጢሩን ማወቅ ይጠቅምሃል:: እኔ ደግሞ ምሥጢሩን
ለማካፈል ፈቃደኛ ነኝ፡፡ ይህ ሰው የተከበረ ቤተሰብህን ስም የሚያጐድፍ ነው፡: ከክብርት እመቤቴም ጋር ግንኙነት ስለሌለው ከእናንተ መራቅ አለበት: ወንጀለኛው ወንጀሉ ሳይገለጥበት እንዲኖር መፍቀድ የትክክለኛ
ፍርድ ገጽታ አይደለም... ከታላቅ አክብሮት ጋር!››
ደብዳቤው ቴናድ በሚል ስም ተፈርሞአል፡
ማሪየስ በጣም ተረበሸ:: በአንድ በኩል ሲደሰት በሌላ በኩል ተከፋ፡፡ እንደ ሌሎቹ ጠቋሚዎች ሕይወቱን ያዳነለት የውሸት ስው ይዞለት የመጣ መሰለው፡፡ ለማንኛውም ከኪሱ ገንዘብ መኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ተጣራ:
አሽከር ገባ::
«ሰውዬውን ይዘኸው ና።»
ደብዳቤውን የላከው ለው ገባ: ማሪየስ እንደ መደነቅ አለ፡፡
አሁን የገባው ሰው «ሕይወትህን ያዳነልህ ሰው ይዤ መጣሁ»
በማለት ቀደም ሲል የመጣ ሳይሆን እንግዳ ሰው ነው።
ጥቁር በጥቁር ነው የለበሰወ ጥቁር መነጽርም አድርጎአል: ከአፍንጫው ደፍጠጥ፣ ከአገጩ ረዘም ያለ ሲሆን በእጁ ባርኔጣ ይዟል።
ማሪየስ የጠበቀውን ሳይሆን ሌላ ሰው ከክፍሉ ውስጥ በመግባቱ
ከፊቱ ላይ ተስፋ የመቁረጥ ምልክት ታየበት እርሱን ያስጨነቀው ሕይወቴን ያዳነው ማን ነው የሚል ፕያቄ ሲሆን ጠብቆት የነበረው ሰው ይህን ዜና ይዞልኝ ይመጣል» ብሎ የገመተው ነበር ሰውዬውን ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ፀጉር አጤነው::
«ምን ትፈልጋለህ?» ሲል በመኮሳተር ጠየቀው
እንግዳወ በተራው ማሪየስን አጤነው የመረበሽ መልክ አልታየበትም፡: እንዲያውም እጁን ሱሪ ኪስ ውስጥ ጨምሮ ወገቡን ሳያቀና ግምባሩን ብቻ አቅንቶ ነው ማሪየስን ያየው «ጌታዬ፣ የመጣሁበትን አስረዳለሁ:: የምሸጥልህ ምሥጢር አለኝ፡»
«ምሥጢር?»
«አዎን፣ ምስጢር»
«ቀጥል፡››
«ጌታዬ ከቤትህ ውስጥ ሌባና ነፍሰ ገዳይ አለ፡፡»
ማሪየስ ክው አለ
«እኔ ቤት ውስጥ? የለም» ሲል ጮክ ብሎ ተናገረ ነቅነቅ የማይለው ደፋሩ እንግዳ ባርኔጣውን በእጁ ጠረግ ጠረግ
አድርጎ ንግግሩን ቀጠለ፡
«እውነተኛ ስሙን ልነግርህ ነው፡፡ ስሙን በነፃ ያለ ክፍያ ነው የምገልጽልህ፡»
‹‹እየሰማሁ ነው»
«ስሙ ዣን ቫልዣ ይባላል፡፡»
«አውቀዋለሁ »
«አሁን ስነግርህ ነው ያወቅከው::»
«አይደለም፧ከዚያ በፊት አውቀዋለሁ::
እንግዳው በፈገግታ ቀጠለ፡፡
‹‹ጌታዬን መቃወም አልፈልግም፡ ለማንኛውም ብዙ ነገር ማወቄን
መገንዘብ አለብህ አሁን የምነግርህ ጉዳይ ግን እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው»
ማሪየስ እንግዳውን ትኩር ብሎ አየው::
«ዣን ቫልዣን የምሥጢር ስም ብቻ ሳይሆን የአንተንም የምሥጢር
ስም አውቃለሁ፡፡ እንዲሁም ትልቁን ምሥጢር አውቀዋለሁ
«ያንተን ስም»
«የእኔን ስም?»
«አዎን፣ ያንተን ስም:»
«ይህ እኮ አስቸጋሪ አይደለም ጌታዬ ከጻፍኩልህ ደብዳቤ ላይ ስሜን
ጽፌ የለም እንዴ?»
"
«'ዬን' አስቀርተሃል»
«እህ?»
«ቴናድዬ::»
«ማነው እሱ?»
አደጋ ሲመጣ ከሰው ጀምሮ እስከ ትንኝ ሁሉም መከላከያውን ያበጃል፡፡"
ዘበኞች ጥግ ይይዛሉ፡ ይህ ሰው ግን መሳቅ ጀመረ።
ማሪየስ ከኪሱ ገንዘብ አውጥቶ ወረወረለት:
«አመሰግናለሁ ጌታዬ! አምስት መቶ ፍራንክ!» አለ ቴናድዬ።
ቴናድዬ በመገረም ገንዘቡን አየው፧ ደባበሰው፤ መረመረው: በድጋሚ
«አምስት መቶ ፍራንክ» አለ በመደነቅ:: ቀጥሎ «ይቺ...ቺ ጥሩ ናት» አለ
በማጉረምረም:: ከዚያም በድፍረት «አሁን መነጋገር እንችላለን›› ካለ በኋላ
በጉሬሣ ፍጥነት መነጽሩን አወለቀ አንገቱ ላይ የጠመጠመውንም እስካርፍ
ፈታ፡፡ ዓይኑ በራ፤ ፊቱ አንፀባረቀ:: አፍንጫው ቀጥ አለ፡፡ ያ አስከፊ ፊቱ
ጥምብ ያየ አሞራ ይመስል ቶሎ ተቀያየረ ልክ እንደ ጥምብ አንሳ አሞራ
እርሱም ጥምብ ያገኘ መሰለው፡
«ጌታዬ መቼም አትሳሳትም» አለ ጥርት ባለ ድምፅ፤ «በእርግጥ እኔ ቴናድዬ ነኝ::»
አሁን ገና ከወገቡ ቀና አለ፡፡ በቴናድዬ አመለካከት በማሪየስና በእርሱ መካከል ገና ንግግሩ አልተጀመረም:: አካሄዱን ለውጦ አዲስ ስልት መቀየስ እንዳለበት አምኖአል፡ ጉዳዩ ብዙም አልተበላሸም:: አምስት መቶ ፍራንክ እንደሆነ ተገኝቷል
«እኔ ቴናድዬ ነኝ» ለ በኋላ ዝም ስላለ ማሪየስ ጣልቃ ይገባል፡
«ቴናድዬ፧ ስምህን ነግሬሃለሁ: አሁን አንተ በተራህ ምሥጢርህን ንገረኝ፡፡ ልትነግረኝ የመጣህበትን እኔ እንድነግርህ ትጠብቃለህ: እኔም እንዳንተው ወሬ የምሰበስብበት መንገድ አለኝ፡፡ ከአንተ ይበልጥ እንደማውቅ አሁን ትገነባለህ እንዳልከው ዣን ቫልዣ ሌባ፤ ቀማኛና ነፍሰ ገዳይ እንደሆነ አውቃለሁ መሴይ ማንደላይን የተባለውን ሁብታም ባለፋብሪካ በመዝረፉና በማክሰሩ ቀማኛ ነው የፖሊስ አዛዥ የዣቬርን ሕይወት
በማጥፋቱ ገዳይ ነው»
ቴናድዬ በተሸፈነ ሰው ዓይን ማሪየስን አየው: ነገር ግን ወዲያው አንድ መላ ስለታየው በኩራት መንፈስ አሁንም ፈገግ እያለ ተናገረ::
«ጌታዬ የተሳሳትን መሰለኝ
‹ምን!» ሲል ማሪየስ መለስ፡ «ይህን ትክዳለህ? ቃሌ እውነትን ያዘለ
ነው፡፡»
«ጌታዬ በማረጋገጥ ነው የምትናገረው፡፡ ለዚህም ስለአንተ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ሆኖም እውነትና ትክክለኛ ፍርድ መውጣት አለባቸው:: ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ሲወነጀሉ መስማት አልፈልግም ጌታዬ፣ ዣን ቫልዣ መሱይ ማንደላይንን አልዘረፈም: ዣን ቫልዣ ዣቬርን አልገደለም»
«እንዴት ነው? ስትናገር አረጋግጠህ ነው!»
«በሁለት ምክንያት»
«በምንና በምን?»
«የመጀ…ሪያው ይኸውልህ፡ ዣን ቫልዣ መሴይ ማንደላይንን አልዘረፈም፤ ምክንያቱም ዣንቫልዣና መሴይ ማንደላይን አንድ ሰው ናቸው:፡›
‹‹ምንድነው የምትነግረኝ?»
‹‹ሁለተኛውን ምክንያት ደግሞ ስማ:: ዣቬርን አልገደለም ምክንያቱም
ዣቬርን የገደለው ራሱ ዣቬር ነው፡
«ምን ማለትህ ነው?»
«ዣቬር ራሱን ነው ያጠፋው፡»
‹ማረጋገጫ፣ ማረጋገጫ አምጣ» ሲል ማሪየስ በኃይል ጮኸ::
ቴናድዬ ቀጠለ፡፡ የሚናገረውን በማራዘም ጫን እያለ ተናገረ:
«የፖ.ሊሱ.... አዛዥ.... ዣ....ቬ...ር …ስም…ጦ ...ከጀ....ልባ .ሥር…ነው...የተገኘው...::»
«አሁንም ማስረጃ አምጣ
ነው የምልህ»
ቴናድዬ ከኪሱ ውስ ኦንድ ፖስታ አወጣ በፖስታው ውስጥ ቀለማቸው የተለያየ የተጣጠፉ ወረቀቶች ነበሩበት።
መረጃዎቼ እኮ ከእጄ ውስጥ ነው ያሉት አለ በዝግታ ስናገር ያለማስሪጃ አልናገርም ደግሞም ስለእጅ ጽሑፍ ማስረጃ አይደለም የማወራው
«እና ማስረጃዎቹ የታተሙ ናቸው።» "
ቴናዲዬ እየተናገረ ከፓስታው ውስጥ
የጋዜጣ ቁራጮችን አውጥቶ
ዘረጋ ወረቀቶቹ ፀሓይ ስለመታቸው ወደ ቢጫነት ተቀይረዋል፡ ከሁለቱ አንደኛው ቁራጭ ጫፍ ጫፉ በመበላቱና በመቀደዱ የቆየ ለመሆኑ በግልጽ
ይታወቃል::

👍18
ሁለት መረጃ፣ ሁለት ማረጋገጫ» አለ ቴናድዬ በእጁ የያዛቸውን የጋዜጣ ቁራጮች ለማሪየስ እየሰጠ፡፡
አሮጌው ሐምሌ 25 ቀን 1823 ዓ.ም የወጣ ሲሆን መሴ ማንደላይንና
ዣን ቫልዣ አንድ ሰው ለመሆናቸው ያረጋግጣል: ሁለተኛው ሰኔ 15 ቀን
1832 ዓ.ም የወጣ ሲሆን ዣቬር ራሱን ለመግደሉ ይናገራል፡ ሌላው ቀርቶ
ጦርነቱ ቦታ ተይዞ ከአድመኞች መካከል አንዱ ሊገድለው ሲችል ሳይገድለው
የገደለው ለማስመሰል ሽጉጥ ወደ ሰማይ መተኰሱንና ይህንንም ታሪክ በቃሉ ለአለቃው ቀደም ሲል የነገራቸው ለመሆኑ ተጽፎአል፡፡
ማሪየስ የጋዜጣ ቁራጮችን አነበበ፡፡ ትክክለኛ ማስረጃና ማረጋገጫ
ነበሩ፡፡ የተጻፈበት ቀን እንኳን ሳይቀር አለበት የዣን ቫልዣ ትልቅነት በአንድ ጊዜ መጠቀ፡፡ ማሪየስ የደስታ ለቅሶ ከማልቀሱ መቆጠብ ተሳነው፡፡
«እንግዲያውማ ይህ የተከፋ ሰው ወደር የማይገኝለት ሰው ነው፡፡ ያ ሁሉ ሀብት ለካስ የራሱ ኖሮአል:: ማንደላይን ነው:: እርሱ ከነበረበት አካባቢ ያለ ሰው ሁሉ እንደ አምላክ ያየዋል ዣቬርን ያዳነው ዣን ቫልዣ ነው! ጀግና ነው! ቅዱስ ነው!››
«ቅዱስም፣ ጀግናም አይደለም» አለ ቴናድዬ:: «ነፍሰ ገዳይና ሌባ
ነው:፡» ሲናገር እንደ ባለሥልጣን በትምክህት ነበር:
«እስቲ ረጋ እንበል አለ ቴናድዬ ቀጥሎ፡»
ሌባ፤ ነፍሰ ገዳይ የሚባሉ ቃላት የበቃቸው መስሎት ሳለ እንደገና
በመነገራቸው እንደ በረዶ ጀርባውን ቀዘቀዘው::
«እንደገና!» ሲል ተናገረ::
«ጌታዬ ሰኔ 6 ቀን 1832 ዓ.ም. በግምት ከአንድ ዓመት በፊት መሆኑ ነው፣ አንድ ሰው ከተፈጠረው ረብሻ ለማምለጥ ሲል ከዋናው የቆሻሻ መውረጃ ቱቦ ውስጥ ገብቶ ነበር ይህ ሰው የገባው ከሳይን ወንዝ መፋሰሻ አካባቢ መሆን አለበት
ማሪየስ ወንበሩን ጎትቶ ወደ ቴናድዬ ጠጋ አለ ከማሪየስ ፊት ላይ ለውጥ መታየቱን ቴናድዬ ይገነዘባል እንደ ጎበዝ ወይም ተንኮለኛ ተናጋሪ የመጓጓት ስሜቱን ለማናከር ጥቂት ዝም ካለ በኋላ ንግግሩን ቀጠለ፡
«ይህ ሰው ራሱን ለመደበቅ ተገድዶ
ነበር:: ሰውዬው ከፖለተካ ውጭ በሆነ ምክንያት ለመሰወር ፈልጎ ወደ ቱቦ የሚያስገባውን ቀዳዳ ቁልፍ ይዞ ከዚያ ውስጥ እንደገባ አንድ የሆነ ድምፅ ይሰማል ቀኑን ልድገመውና ሰኔ 6 ቀን ሲሆን ሰዓቱ ወደ ሁለት ሰዓት ገደማ ይሆናል ድምፅ ከየት መጣ ብሎ ሰውዬው ይደነቃል ይህ ሰው ለጊዜው ይሸሽጋል
ሰው ወደ እርሱ ሲመጣ በሩቁ ያያል የሚገርመው ከዚህ ሰው
ጋር ሌላም ሰው ነበር፡፡ ከቱቦው ወደ ውጭ የመውጫ ቀዳዳ ሰዎቹ ከነበሩበት ሩቅ አልነበረም: በቀዳዳው የሚገባ መብራት ሰውዬውን የማየትና ይህ
በጀርባው አንድ ነገር መሸከሙን ለመለየት ያስችለዋል: ሲራመድ ከወገቡ
ጎብጦ ነው:፡ ያ አቀርቅሮና ሌላ ሰው በጀርባው ተሸክሞ ይመጣ የነበረው
ሰው ሽማግሌው ወንጀለኛ ነው: የሚያሳዝነው የተሸከመው ሰው
የሰው ሬሣ ነበር፡ …የገደለው ሰው ሬሣ መቼስ አንድ ሰው ሌላውን ያለ ምክንያት አይገድልም: ይህ ወንጀለኛ ሬሣ ተሸክሞ የመጣው ሬሣውን ውሃ ውስጥ ለመጨመር ነበር:»
አሁንም ማሪየስ ወደ ቴናድዬ ወንበሩን በማንፏቀቅ ጠጋ አለ:: ቴናድዬ ትንፋሹን ለመሰብሰብ እድል አገኘ::
«ጌታዬ፣ መቼስ የቆሻሻ መውረጃ ቱቦ ውስጥ እስከዚህም ሰፊ ቦታ ስለሌለ ሁለት ሰዎች ከዚያ ቢገቡ መገናኘታቸው የግድ ነው:: ይኸው ነው የሆነው:: ከዚህ ውስጥ የማኖረው ሌላ ግለሰብና መንገደኛው ሲፋጠጡ የእግዜር ሰላምታ ተለዋወጡ ነዋሪውን አናገረው»
«በጀርባዬ የተሸከምኩትን ታያለህ
የመውጫውን ቁልፍ ይዘሃልና ስጠኝ::
ከዚህ መውጣት አለብኝ:: የመውጪያውን ቁልፍ ይዘሃልና ስጠኝ።»
ወንጀለኛው የነበረው ጉልበት መቼም ለጉድ ስለሆነ መከልከል ዋጋ
አልነበረውም:: ቁልፉን የያዘው ሰው ከሰውዬው ጋር ለማውጋት የተገደደው
ጊዜ ለማግኘት ነበር የሞተውን ሰው በጥሞና ቢመለከተው ምንም ነገር
ለማግኘት አልቻለም:: ሰውዬው ወጣት ለመሆኑና ሽክ ብሎ መልበሱን
ለመገንዘብ ችሎአል ሀብታም ሰው መሆን አለበት:: ሰውነቱ በደም ተጨማልቋል ነዋሪው ከሰውዬው ጋር ሲያወራ ሳይታይ ከሟች ኮት ቁራጭ ጨርቅ ቀድዶ ይወስዳል ወደፊት ወንጀለኛውን አሳድዶ ለመያዝና ለፍርድ እንዲቀርብ ለማድረግ: ቁራጩን ጨርቅ በማስረጃነት
እንዲጠቀምበት ከኪሱ ውስጥ ይጨምራል ከዚያም ሲሄድ ነዋሪው በሩን
ይከፍተለትና ሰውዬው ከነሸክሙ ወጥቶ ሲሄድ ነዋሪው በሩን ዘግቶ ወደ
ሥፍራው ቶሎ ይመለሳል፡፡ ቶሎ የተመለሰው ሬሣውን ከወንዝ ውስጥ
ሲጨምር ላለማየት ፈልጎ ነበር አሁን ገብቶሃል ሬሣውን ተሸክሞ የወጣው ዣን ቫልዣ ነው ቁልፉን የያዘው ሰው አሁን የሚያናግርህ ሰው ነው: እና የኮቱን ቁራጭ.. ቴናድዬ ንግግሩን የጨረሰው ቁራጩን እራፊ ከኪሱ በማውጣት
ነበር...

👍18❤6
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...ረቂቋን የጆሮ ማዳመጫ አዉቆብኝ ኖሯል፤ መንጭቆ አወጣብኝ፡፡
ማደመጫዉን የያዘበትን እጁን ሳይ ተገለጠልኝ ባልቻ በአንድ ወቅት
ከፍተኛ የመንግሥት ደኅንነት ሹሞችን አጠቃላይ መገለጫቸዉን ለጥቂት
የሲራክ፯ አባላት በገለጸልን ጊዜ፣ ስለዚህ ሰዉ ልዩ ምልክት የነገረን አስታዉሼ ይኼን ሰዉ ገመትሁት አወቅሁት የቀለበት ጣቱ ከስሯ ጀምራ የለችም: በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ሰው
እጅ መግባቴን፣ አሁን አወቅሁ ሰዉዬዉ የሀገር ዉስጥ ደንነት ዋና መምሪያ ሹም መሆኑን አሁን ገና፣ ነገሮች ሁሉ ከተጨመላለቀ በኋላ ተረዳሁ። አጠመድሁ ስል እንደ ተጠመድሁ ያወቅሁት፣ አሁን ገና ሁለት እጆቹ ካነቁኝ፣ ድፍርስ ዓይኑ ካፈጠጠብኝ፣ ድርብርብ ጥርሱ ካገጠጠብኝ በኋላ ነበር። መጠርጠር አልነበረብኝም? ነበረብኝ።
«ላም ሆይ ላም ሆይ ሞኟ ላም ሆይ
ሣሩን አየሽና ገደሉን ሳታይ
እልም ካለው ገደል ወደቅሽብን ወይ
እያልሁ፣ መስኮት ቀርቶ ስንጥቅ እንኳን በሌለዉ አመዳም ግድግዳ ላይ
አፍጥጬ በራሴ አላገጥሁበት።
“ጥሩ” አለ የተገለበጠችዋን ወንበር አቃንቶ ራሱ እየተቀመጠባት
“እንተዋወቃ… ማን ብዬ ልጥራሽ?”
ባፍንጫዬ አናፍቼ ብቻ ጭጭ አልሁበት።
“ኦ..ይቅርታ፤ መጀመሪያ ራሴን ማስተዋወቅ ይገባኛል ለካ። ኮሎኔል…"
ብሎ ስለራሱ ሊነግረኝ ሲጀምር ጆሮዬን ያዝሁበት ስሙን እንዲጠራብኝ
አልፈለግሁም አዉቄዋለኋ!
“ማ..ነ..ሽ?” አለኝ በዝግታ፣ በዚያች ኦና ቤት ዉስጥ ብቻ ለብቻ ሲከበኝ
ቆይቶ በዓይኔ እንኳን እንዳልላወስ ከግድግዳዉ ጋር እያጣበቀኝ
ወዲያዉኑ ጆሮዉን ወደ ከንፈሮቼ አምጥቶ ለረዥም አፍታ መልሴን መጠባበቅ ቢጀምርም፣ ትንፋሼን ሳይቀር ዋጥሁበት እንኳንስ ለኮሎኔ ይቅርና፣ ለገዛ እናቴ እንኳን እንዲህ ነዉ ብዬ የማፍረጠርጠዉ ማንነት የለኝ እኔ፡ ዉብርስት እባላለሁ የሲራክ አባል ነኝ የምል መስሎታል? አያዉቀኝማ! አ ያ ዉ ቀ ን ም! ሲራክ.፯ን ጨርሶ አያዉቀንም ማለት ነዉ። የሆነዉ ሁሉ ሆኖም፣ ኮሎኔሉ ከዚህ በላይ
ትዕግሥት የሚኖረዉ አይመስለኝም: ቀጣዩን ጥያቄዉንም እንደዚሁ
ተለሳልሶ እንደማይጠይቀኝ ቁልጭ ብሎ ታይቶኛል።
ስለዚህ አእምሮዬን ማሠራት አለብኝ፡
እኔ ስለማደርገዉ ሳወጣ ሳወርድ፤ እሱ ቀድሞኝ ጆሮዉን ከከንፈሮቼ አንስቶ ከንፈሮቹን ወደ ጆሮዬ አመጣብኝ፡ ይህም ሳያንስ የጥምቀትን ዉርጭ የሚያስመሰግን ቀዝቃዛ ትንፋሹን ለቀቀብኝ ፡ ከዚያ ምላሱን እና
የላይኛዉን ትናጋዉን በማጋጨት መሰለኝ፣ ሦስት ሰቅጣጭ ድምፆች
አከታትሎ አጮኸብኝ በምላስም ማጨብጨብ ይቻላል እንዴ?
“ጣ! ጣ! ጣ!”
ጣዉላ እና ጣዉላ ቢጋጭ ራሱ እንደዚህ መጮሁን እኔ እንጃ በቅጽበት አንድ ጎረምሳ እንደ ሳምሶናይት ያለ ትልቅ ቦርሳ ተሸክሞ ከተፍ አለለት የመጨረሻ ዕድል ሰጥቼሻለሁ፣ የምትነግሪኝ አለ? ማነሽ ለማለት በሚመስል ሁኔታ በጥልቀት ሲያስተዉለኝ ቆይቶ ወደ በሩ አመራ።
በሩን ከፍቶ እንደ መዉጣት ካለ በኋላ፦
“ቶሎ!” የሚል ትእዛዝ ሰጠዉ
“እሺ፤ እንደ ተለመደዉ” ሲል መለሰለት፣ ባለ ሳምሶናይቱ አናዛዥ። እኔና አናዛዡ ብቻ ቀረን፡ በሩን ቀጭ አድርጎ ቆለፈና መክፈቻዉን በኪሱ ወሽቆ ሳምሶናይቱን እዚያች ደረቅ ወንበር ላይ አስቀመጠ። እስኪከፍተዉ ድረስ እሱም ዓይኑን ከዓይኔ፣ እኔም ዓይኔን ከእጁ ላይ አልነቀልንም አንደኛዉን ኪስ ከፍቶ ዘረገፈዉ፡ ሰአሊ ለነ! ያላመጣዉ ምንም የስለት መሣሪያ የለም፡ ትንሿ የብረት መጋዝ ሳትቀር መጥታለች፡ ከሳምሶናይቱ
ሌላኛዉ ኪስም እንዲሁ መርፌዎች እና መርዝ የተሞሉ አራት ብልቃጦች ዘረገፈ፡ ይኼ ሁሉ ለኔ እንዳይሆን ብቻ! ነዉ?
“ቶሎ ምረጭ፣ የቱ ላስቀድምልሽ?”
“እ?” አልሁት፣ ድምፄን ቢከዳኝ በቅንድብ ምልክት፡
“‹ለሞኝ ጉድኋድ አያሳዩትም፣ ቤት ነው ብሎ ራሱ ይገባበታል› ተብሎ ሲተረት ብሰማም፤ የቆንጆም ሞኝ እንዳለዉ ግን አቺን አሁን ገና አየሁ ገና በገዛ'ጅሽ ሰተት ብለሽ እንጦሮጦስ ትወርጃለሽ? ጅል!”
ደም የጠማዉ ነፍሱን በጥርሱ በኩል አሳየኝ፡፡ በኹለቱም ጎኗ ስለት ያላትን ቢለዋ እና ፒንሳ እያጋጨ ወደኔ መጣ፡ ሥራዉ የሰዎችን አካል እያፈረሰ የሚያናዝዝ ሰዉ መሆኑ ያስታዉቃል ለእንደ'ሱ ዓይነት ሰዎች ደግሞ ጥፍር መንቀል፣ የዉሃ ጥም እንደ መቁረጥ ያለ እርካታ ያመጣላቸዋል እንጂ እንዲች ብሎ አይስቀጥጣቸዉም፡ ለምደዉታል:
ርኅራኄ የሚባለዉን ነገር ከዉስጣቸዉ ጨልጠዉ ደፍተዉታል እንዲያዉም ብዙ ጊዜ የሚመረመረዉ ሰዉ ለሐቅም ሆነ ራሱን ለማትረፍ ሲል፣ ገና ሳይነኩት ቶሎ የተናዘዘ እንደሆነ በኃይል ይናደዳሉ ይባላል።
“ጅል ነሽ እንዴ ? ”
እንደ ቅድሙ ባፍንጫዬ አናፍቼ ብቻ ጸጥ አልሁት።
ቁልቁል እያየኝ ከአጠገቤ ቆሞ ነበር። ወደ ኋላ የሚመለስ መስሎ፣ ከመሬቱ ጋር ደባለቀኝ፡ ምኔን በምኑ እንደ መታኝ እንኳን አላየሁትም። ብቻ ብዥ ጭልም ብሎብኝ ቆየሁ።
ነፍሴ ስትመለስ ብልቃጧን ሲያነሳ አየሁት በብልቃጧ ላይ የሰፈረዉን
ስም አሻግሬ ሳነበዉ ሪማሾ-ሚር (Himacio-mir) የሚባለዉ የሰመመን
መርዝ መሆኑን አወቅሁ። ከሚያስቃዠዉ ሰመመን በፊት ጡንቻ የሚያኮማትር እና ሽቅብ ሽቅብ የሚያስብል ንጥረ ነገሮችም አብረዉ እንደ ተቀበመሙበት አዉቃለሁ እሱን የተወጋ ሰዉ ታዲያ እንባ እንደ ዝናብ
እስኪወርደዉ ድረስ ያምጣል እንጂ ወጥቶለት የሚገላገለዉ ነገር
አይኖረዉም፡ ለማስመለስ ጫፍ ይደርስና ይመለሳል። ስለሆነም ጭንቁ አያድርስ ነዉ በጠባብ ጫማ ከመዋልም፣ ሽንት አቋርጦ ከመቋጠርም፣ ሚስማር ላይ ከመቀመጥም ሁሉ ይብሳል
መርፌዉን ተክሎ ሲሪንጁ እስኪሞላ ድረስ ብልቃጧን ምጥጥ አደረጋት።
ሲሪንጁ ጢቅ አለለት: ይኸኔ ጡንቻዎቼን ማነቃቃት ጀመርሁ። ከቀደመኝ አበቃልኝ፡ ልክ እጁን አንከርፍፎ ሲመጣ፣ የፈራሁ መስዬ አንድ ዓይኔን በእጆቼ ጨፈንሁ: ወደ ማጅራቴ መርፌዉን ሲሰድ እጁን
ለቀም አድርጌ ያዝሁትና፣ ፋታ ሳልሰጠዉ ጠምዝዤ ደረቱ ላይ ስካሁለት ዓይኔን እንኳን እስከማርገበግብ አልዘገየም፣ ትዉኪያ ሲያጣድፈዉ ልክ የገማ ጣት እንደ ጎረሰ ሰዉ፣ እንባዉ ዱብ እስኪል ድረስ ሽቅብ ቢለዉም ምንም አይወጣዉ። “ህእእእ!” ይላል በየቅጽበቱ፣ ስቃይ ብቻ! በዚያ ላይ የሠራ አካላቱ እየዛለበት መጣና፣ እንደ አሮጌ ጨርቅ እጥፍጥፍ ብሏል ጊዜ ኖሮኝ ባዘንሁለትማ ደስታዬ ነበረ ግን ለሐዘኔታ የሚሆነዉን ጊዜ የት ልዉለድለት? ይልቅ አሁኑኑ ማምለጥ አለብኝ፡፡ ባይሆን
እያመለጥሁ አዝንለታሁ
ያዉም ከቻልሁ ከኪሱ ባወጣሁት ቁልፍ በሩን ቀስ አድርጌ ከፍቼ አንገቴን ሳሰግግ
በአካባቢዉ ማንም የለም:: ቢሆንም ግን እርግጠኛ መሆን አልቻልሁም:
ያለሁት ዋነኛዉ ቤተ መንግሥት ዉስጥ ነዉ፡ ቤተ መንግሥትን ያህል ግቢ፣ በሚታዩና በሚዳሰሱ ወታደሮች ብቻ ይጠበቃል ማለት ጅልነት
ነዉ። በየሥርቻዉ ካሜራ፣ በየቦታዉ ረቂቅ ዳሳሾች መኖራቸዉ አያጠራጥርም።
“ህእእእ. አህክ እትፍ! ህእእእ አህክ እትፍ!” ይላል አሁንም፣አንጀቱ ከጉሮሮዉ ጫፍ እስኪደርስበት እየሳበዉ፡ ደም ከሚያስንቅ እንባ በቀር ሌላ ምንም ጠብ አይለዉም: መጨከን አለብኝ እንጂ፣ ሁኔታዉ አንጀት ይበላል ያሳዝናል። የሐፍረተ ሥጋዉን መሸፈኛ ብቻ ትቼለት

👍33🥰2
ልብሱን ከላዩ ላይ አወላልቄ ለራሴ ለበስሁት ኮፍያዉንም አዉልቄ ራሴ
ላይ ደፋሁት። ረዥሙ ጸጉሬ ግን ከኮፍያዉ እየተረፈ አስቸገረኝ፡ ምን
አማራጭ ነበረኝ? የኔን ሆድ እቃ ለመዘክዘክ አምጥቷቸዉ hሳምሶናይቱ
ከዘረገፋቸዉ ስለቶች አንዱን እንስቼ ሸለትሁት አሁን የሚቀረኝ ነገር
ጺም እና የፊት ገጽታ ብቻ ነዉንጂ፣ በአለባበስ በኩል ሰዉዬዉን ከላይ
ስከታች ገፍፌ ቁጭ ራሱን መስያለሁ፡ ለጺም ንቅለ ተከላ የሚሆን ጊዜ
ስለሌለኝ፣ እንዲሁ ወለሉን በእጄ እየጠቀስሁ ለስላሳ ቀይ ፊቴን አመዳም
አደረግሁት።
ልክ ልወጣ ስል የአንድ ሰዉ ኮቴ ወዳለሁበት ክፍል እየቀረበ መጣ።
እንዲች ብዬ እንኳን አልፈራሁም፡ ብቻ፣ ትራፊዋን መርዝ ከነመርፌዋ ጨበጥሁና በሩ ሥር ቆሜ ጠበቅሁት: የሚመጣዉ ማንም ቢሆን መርፌዋን ምኑ ላይ እንደምሰካለት እያዉጠነጠንሁ ሳለ፣ “አንድ ደቂቃ ጨምሬልሃለሁ፣ ጨርስ!” ብሎ ብቻ ከበሩ ተመለሰ፡ ኮሎኔሉ እንደሆ
በድምፁ ገምቼዋለሁ ጭራሽ የቅድሟ አልባሌ የቃል ልዉዉጣቸዉ
በዉስጧ የደቂቃ ገደብም ኖሮበታል ለካ? ጉድ እኮ ነዉ ሌላስ ምን ኮድ ይኖራት ይሆን? ኮሎኔሉ ቶሎ ሲል ስንት ደቂቃ ማለቱ ኖሯል?
አናዛዡስ እንደ ተለመደዉ ሲል ምን ማለቱ ነበር?
ምንም ይሁን ምን፣ የማምለጫ ጊዜዬ አሁን ናት።በሩን ቀስ አድርጌ ከርፈድ አደረግሁና፣ ግራ ቀኙን ቃኘሁት። ምንም
የለም፡ መሰስ ብዬ ስወጣ ግን፣ የሆነ ነገር ዉልብ አለብኝ፡ እንደገና ዙሪያዬን ሳስተዉል ደግሞ ማንም የለም ወደ መንገዱ እስከምገባ ድረስ ማንም አልገጠመኝም። እንዲህ ጭር ማለቱ ራሱ ልቤን ገምሶብኛል። ሣር ቅጠሉን አላምነዉም ያለሁት ቤተ መንግሥት አይደል?
ቢሆንም ግን ቀልጠፍ ማለት አለብኝ። ራመድ ራመድ ብዬ ወደ ቀጣዩ
ቅያስ ልገባ እግሬን ሳነሳ ሌላ ዳና ከኋላዬ ሰማሁ። እንዳልቆም ራሴን ማጋለጥ መሰለኝ፣ እንዳልቀጥል ደግሞ የሚተኮስብኝ መሰለኝ፡ እንዲሁ
ኹለት ርምጃ እንደ ሄድሁ hኋላዬ የሚከተለኝ ሰዉ ፈጠን ብሎ ደርሶ
ትከሻዬን ቸብ ቸብ አደረገኝ።
“ያቺን ነገር እኮ አስለምደኸኝ፤ ከአሁን አሁን መጣህ እያልሁ እኮ መንገድ መንገዱን ሳይ. አመጣህልኝ አይደል?” አለኝ፣ በድምፁ እየተቅለሰለሰ። እዉነትም በአለባበሴ መርማሪዉን መስየዋለሁ በማለት የልብ ልብ ተሰማኝ፡ በእሱ ቤት እኔ ያ አናዛዥ መርማሪ ነኝ። ጅሎ! ያቺ
ነገር የተባለችዋ ግን ምን ትሆን? ምናልባት መጠጥ ወይ ደግሞ ሲጋራ
ማለቱ ሳይሆን አይቀርም ስል አሰብሁ።
“ስመለስ” አልሁት፣ ወደ ጨለማዉ ዞሬ እንዳቀረቀርሁ። ድምፄን ጎርነን
አድርጌ የመርማሪዉን ለማስመሰል ሞክሪያለሁ።
“እህ ምን ማለት ነዉ ስመለስ! ከየት ነዉ የምትመለሰዉ?” መቼም ከዚህ በላይ ከመለስሁለት መዋረዴ ነዉ። ስለዚህ ሌላ መላ መፍጠር አለብኝ፡ የለበስሁት ሱሪ ኪስ ዉስጥ በእጄ ገባሁና ለማንኛዉም
ብዬ የያዝኋትን የቅድሟን መርፌ ጨበጥኋት። ከዚያም፣ ለማዘናጋት
ያህል ትንሽ እንደ መራመድ ካልሁ በኋላ በልምምጥ ሲከተለኝ ዞር ብዬ
ጎኑ ላይ ተከልሁበት ከመቅጽበት ጨርቅ ሆነ የቤተ መንግሥቱን ካርታ በልቤ እያሰብሁ፣ በቅርበት ወደሚገኘዉ
የዉጪ አጥር ሸመጠጥሁ። ጨለማ ጨለማዉን ተሽሎክሉኬ ወደ አጥሩ
ብቃረብም፣ ዘሎ መዉጣት ግን የሚሞከር አልሆነልኝም: በየመቶ ሜትር
ልዩነት እዚህም እዚያም መሣሪያ የወደሩ ወታደሮች ተገድግደዉበታል።እንኳንስ በአጥር የሚዘል ሰዉ አግኝተዉ ይቅርና፣ በአቅራቢያ ዝቅ ብላ ለምትበር ወፍ ጭምር ከመተኮስ የሚመለሱ አይመስሉም:
በግራ በኩል አሻግሬ ስመለከት፣ መጀመሪያ ወደ ግቢዉ እንደ ገባን
የወረድንበት የመኪና ማቆሚያዉ ታየኝ
አሁን ማምለጫ መንገዱ ወለል አለልኝ፡ አዎ ከዚያ ሁሉ መዐት መኪና የአንዷን መስታዎት አረግፍና እገባለሁ ከዚያ ሞተሩን እንደ ምንም መንጭቄ አስነሳለሁ
ከዚያ እሱን እየነዳሁ ወደ ዋናዉ የግቢ በር እነዳለሁ ግፋ ቢል ከበሩ ላይ ስደርስ፣ በዚያ ያሉ ወታደሮች የመዉጫ
ወረቀት ቢጠይቁኝ ነዉ: ያን ጊዜ ማንኛዉንም እጄ ላይ ያገኘሁትን
ወረቀት እሰጣቸዋለሁ። እሱን ለማስተዋል ለአንድ አፍታም ቢሆን መዘናጋታቸዉ አይቀርም: ያን ጊዜ ነዳጁን በኃይል መርገጥ ነዉ በእርግጥ ከኋላ መተኮሳቸዉ አይቀርም:: ቢሆንም ግን የምመርጠዉ መኪና ከኋላ የማያስመታ ስለሚሆን፣ ጎማዉን ያፈነዱብኝ እንደሆነ እንጂ እኔን አያገኙኝም በዚህ መልኩ አመለጥሁ ማለት አይደል? ለተገለጠልኝ
ብልሃት ራሴን አድንቄ ሳልጨርስ፣ ኮሽታ ሰማሁ። በየት በኩል እንደሆነ
በዓይኔ እየቃበዝሁ ሳለ ከየት መጣ ያላልሁት መዳፍ አፌ ላይ አረፈ።
ሽሽሽሽሽ!” አለኝ፣ ወደ ጆሮዬ ቀርቦ አባትዮ ነዉ? አዎ ባልቻ ነዉ።
“ጀግና!” አለኝ ለጥያቄ ፋታ ሳይስጠኝ፣ እንዳወቅሁት ሲያዉቅ እጁን
አንስቶልኝ፡፡ ቆይ እንዴት መጣህ?” አልሁት፣ ለተልእኮዉ ከእኔ ይልቅ እሱ
እንዲመጣ ያን ያህል ስማጸነዉ እምቢ ብሎኝ እንዳልነበር ሁሉ አሁን
እዚህ ባገኘዉ ደንቆኝ። “ለምን መጣህ ቆይ? አየህ አይደል፤ በእኔ
አትተማመኑም: ድሮዉንም
አልተዋጠልኝም ነበር” አልሁት፣ በመጠኑ እንደ መናደድ ብዬ።
“ብቻ ግን አኩርተሽኛል!”
“ኧረ ባክህ፣ አልተሳካልኝም” አልሁት፣ አንገቴን ሰብሬ፡ ተልእኮዬን
የተወጣሁ መስሎታል? በንዴቴ ላይ ሐፍረት ጨመርሁበት
“እንዲች ነሽ የኔ ልጅ!”
“ህእ ወደ ተቋረጠዉ ካሜራ እኮ አልደረስሁም እኮ ነዉ የምልህ:
አልሆነልኝም”
“ሆኖልሻል። በጣም ተሳክቶልሻል”
“እንዴት?”
“እስከ አሁን የሠራሽዉ ሥራ ቀላል መስሎሻል? ተአምር ነዉ የሠራሽዉ!”
“ዞሮ ዞሮ ዉጤት አልነበር ዳሩ?”
“እኔስ ምን አልሁ? እሱን እኮ ነዉ የምልሽ:: ዋናዉ ነገር ዉጤቱ እና ወደ
ዉጤቱ መድረሻዉ ነዉ። ለዚያም ነዉ ተሳክቶልሻል ያልሁሽ: ነይ እቀፊኝ”
“እንዴት?”
“ካሜራዉም እንደገና መሥራት ጀምሯል፡ ተልእኮሽም ጨብጦልሻል።በይ ነይ ተከተዪኝ” ብሎ ወደ መኪና ማቆሚያዉ መራኝ። ቀጥሎ፣ ቅድም ከሕጻናቱ ጋር ከማርያም ገዳም ጭኖ ወዳመጣን መኪና ወሰደኝ።ልክ ወደ መኪናዉ ገብቶ መሪዉን ሲጨብጥ፣ አንድ ነገር ገባኝ።
“ባዛጞቷ! አንተ ነህ ማለት ነዋ ቅድምም ከማርያም ያመጣኸን? ሹፌሩ
አን† ነበርህ?
ፍርፍር ብሎ ሳቀብኝ አስተዋይ ባለመሆኔ መሰለኝ እንዲህ የተፍነከነከብኝ፡
“ራስህ ነህ፤ አዎ: ግን እንዴት?” አልሁት መኪናዉን የቤተመንግሥት ታርጋ እንዳየሁበት አስታዉሼ። ለነገሩ ባልቻ የማያልፍበት ምን የመርፌ ቀዳዳ አለና ነዉ? ልክ ወደ መዉጫዉ በር ስንቃረብ፣
መኪናዉን ድንገት ሲጢጥ አድርጎ አቆመዉ።.....

👍44🔥3
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
ቴናድዬ ንግግሩን የጨረሰው ቁራጩን እራፊ ከኪሱ በማውጣት ነበር ጨርቁ በደረቀ ደምና በቆሻሻ ተጨማልቋል ቀለሙ ጥቁር ሲሆን ማሪየስ እንዲያየው ወደ ዓይኑ አስጠጋለት።
ማሪየስ ብድግ አለ:: ፊቱ በአንድ ጊዜ አመድ መሰለ፡፡ መተንፈስ አቃተው፡ ዓይኑ ከጨርቁ ላይ ተተከለ: መናገር አልቻለም: ዓይኑን ከጨርቁ ሳያነሳ ወደኋላ ሸሸ፡፡ ቀኝ እጁን ከኪሱ አስገብቶ ቁልፍ አወጣ
በቁልፉ ከዚያ የነበረ አነስተኛ ቁምሣጥን ከፈተ አሁንም ዓይኑን ከቁራጩ ጨርቅ ላይ አላነሳም፡ በዚህ ጊዜ ቴናድዬ ቀጠለ።
«ጌታዬ፣ ሟቹ ወጣት በኪሱ ብዙ ገንዘብ ይዞ እንደነበረና ዣን ቫልዣ በጥበቡ አጥምዶ እንደ ገደለው ብርቱ የሆነ እምነት አለኝ፡»
«ወጣቱ የምትለው እኔው ራሴ ነኝ፤ ኮቱም ያውልህ! ሲል ማሪየስ ጩኸቱን ለቀቀው:: በደም የተጨማለቀውን ኮት ከምንጣፍ ላይ ጣለው»
ከዚያም ቁራጩን ጨርቅ ከቴናድዬ እጅ ነጠቀ:: ጎንበስ ብሎ ቁራጩን
ጨርቅና የኮቱ ቀዳዳ ይገጥሙ እንደሆነ ለካ፡፡ ጨርቁ ከቀዳዳው ልክክ በማለቱ የኮቱን ቀዳዳ በትክክል ደፈነው::
ቴናድዬ አመዱ ቡን አለ፡፡ ‹‹ተበላሁ» ሲል አሰበ፡፡
ማሪየስ ከተቀመጠበት ገንፍሎ ተነሳ:: በአሳብ ረመጥ ተቃጠለ፡፡
ቶሎ ብሎ ከኪሱ ውስጥ ገባ እጁን ከኪሱ ሳያወጣ መንቆራጠጥ ጀመረ: ግሥላ መስሎ በቀጥታ ወደ ቴናድዬ ሄደ: ከኪሱ ውስጥ ያወጣን አንድ ሺህ አምስት መቶ ፍራንክ የቴናድዬን እጅ በማስነካት አሳየው
«ርኩስ ነህ! ውሸታም ነህ! ስም አጥፊ ነህ! ተንኮለኛ ነህ ምቀኛ ነህ! ይህን ሰው ለመክሰስ ነው የመጣኸው፤ ግን ትክክለኛና እውነተኛ ሰው
መሆኑን ነው የመሰከርክለት፡፡ ልታጠፋውና ስሙን ልታጕድፈው ፈልገህ
ነበር፤ ግን ክብር ነው ያጕናጸፍከው:: አንተ ነህ ሌባ! አንተ ነህ ነፍሰ ገዳይ
አንተ ነህ እንጂ እርሱ አይደለም ወደ ሆስፒታሉ ከሚወስደው ጎዳና አጠገብ ከሚገኘው ትኖርበት ከነበረው ዋሻ ውስጥ ጣራ ላይ ተንጠልጥዬ የሠራኸውን ሁሉ አይቼሃለሁ፣ ዦንድሬ! ቴናድዬ: ብፈልግ አንተን ለማሳሰር
የሚያስችል በቂ ማስረጃ አለኝ ግን
ምን ያደርግልኛል! አሁን ብቻ ከዚህ
ጥፋልኝ:፡ እንካ ለማኝ ስለሆንክ ይህን አንድ ሺህ ፍራንክ ጨምረህ ውሰድና
ውጣልኝ፡»
ገንዘቡን ወረወረለት
«ስማ ዦንድሬ! ቴናድዬ፣ አንተ እቡይ! ይህ ትምህት ሊሆንህ ይገባል የእኛ ምሥጢረኛ፣ የእኛ የጨለማ ነጋዴ፣ አንተ የተረገምክ ይህንንም አምስት መቶ ፍራንክ ወሰድና ብቻ ከዚህ ውጣልኝ ሂድ፣ ሂድ ከዚህ ቤት ውጣ ከዓይኔ ብቻ ተሰወር ደስ ይበልህ ይህን ብቻ ነው የምፈልገው ውይ ርኩስ! እንዲያውም ሦስት ሺህ ፍራንክ በተጨማሪ እንካ! ውሰዳቸው፡ አንተ ሽፍታ! ነገ ወደ አሜሪካ ትሄዳለህ እኔ ደግሞ አገር ጥለህ መሄድህን እከታተላለሁ: አገር ጥለህ ከወጣህ ሌላ ሃያ ሺ ፍራንክ እሰጥሃለሁ ሂድና እዚያው ተጨማለቅ!»
«ክቡር ጌታዬ» ሲል ቴናድዬ ግራ እንደተጋባና እንደተከዘ ምንም ነገር
ሳይገባው ገንዘቡን ተሸክሞ ሄደ
በጣም ክው ነው ያለው፤ ሆኖም ደስ ብሎታል ከአሁን በኋላ ስለዚህ
ሰው በአጭሩ ተናግረን ብናቆም ይሻላል በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በማሪየስ እርዳታ ልጁን አዜልማን ይዞና ስሙን ቀይሮ ወደ አሜሪካ ሄደ:ማሪየስ ቃል የገባለትን ገንዘብ ሰጠው: አሜሪካም ከገባ በኋላ ያ ርኩስ ጠባዩ አልለቀቀውም፡፡ ብዙ ጊዜ የደካማና የክፉ ሰው ድርጊት የደህናውን ሰው በጎ ተግባር ስለሚያበላሽና ይህም ከመጥፎ ውጤት ላይ ስለሚያደርሰው ማሪየስ በሰጠው ገንዘብ ቴናድዬ አሜሪካ ውስጥ የባሪያ ንግድ አጧጧፈበት᎓
ማሪየስ ወዲያው ቴናድዬን እንደሸኘ ኮዜት ከነበረችበት የአትክልት ቦታ እየተጣደፈ ሄደ።
«ኮዜት! ኮዜት!» ሲል ተጣራ፡ «ነይ ቶሎ በይ፤ ፍጠኝ! እንሂድ:: ባስክ ቶሎ በል ሠረገላ አስመጣ፧ ፈጠን በል! ያንተ ያለህ! ለካስ እሱ ነው ሕይወቴን ያዳናት ደቂቃ አናጥፋ፤ ቶሎ ብለሽ ነጠላ ነገር ከላይሽ ላይ ጣል አድርጊ፡፡»
ኮዜት፣ ማሪየስ ያበደ መሰላት፡ ሆኖም ትእዛዙን ተቀብላ ራስዋን በቶሎ አዘጋጀት፡
ማሪየስ መተንፈስ አቃተው የሚዘልለውን ልቡ ለማብረድ እጁን ደረቱ ላይ አኖረ: ከወዲህ ወዲያ ተንቆራጠጠ ኮዜትን ዘልሎ አቀፋት «እንጃልኝ ኮዜት! ከአሁን በኋላ የተከፋሁ ሰው ነው የምሆነው» ሲል ተናገረ::
የዣን ቫልዣን ትልቅነት፣ የዣን ቫልዣን ክቡርነት የዣን ቫልዣን ስቃይ በጉልህ ስላየ ማሪየስ ፈዘዘ ወንጀለኛው ከርኩስነት ወደ ቅዱስነት ተቀየረበት ይህም በጣም አስደነቀው:: ከሕሊናው ውስጥ የሚተራመሰው ነገር ግልጽ ሊሆንለት አልቻለም ሆኖም የዣን ቫልዣን ክቡርነት
አልተጠራጠረም
ብዙም ሳይቆይ ሠረገው መጣ ኮዜትን በመደገፍ ካሳፈራት በኋላ ራሱም ዘልሎ ከሠረገላው ላይ ወጣ
«ቶሎ በል፤ ፍጠን» ሲል ባለ ሠረገላውን አዘዘው፡፡ «የምንሄደው
አርሜ ጎዳና የቤት ቁጥር 7 ነው»
ባለሠረገላው መንገዱን ቀጠለ፡፡...
በሩ ሲንኳ ሲሰማ ዣን ቫልዣ ፊቱን አዞረ: በደከመ ድምፁ ‹‹ግቡ» አለ፡፡
በሩ ተከፈተ:፡ ኮዜትና ማሪየስ ብቅ አሉ ኮዜት ቀደም ቀደም ብላ በችኮላ በመራመድ ከክፍሉ ውስጥ ገባች ማሪየስ ግን የበሩን እጄታ ይዞ ከበሩ ላይ ቀረ
«ኮዜት!» አለ ዣን ቫልዣ ብድግ ብሎ እጆቹን ሲዘረጋቸው ተንቀጠቀጡ፡፡ እጅግ በጣም ቢዳከምም ዓይኖቹ ውስጥ የደስታ ምልክት ታየው ኮዜት በስሜት ተውጣ ከደረቱ ላይ ሄዳ ዘፍ አለች ከዚያም «አባዬ» በማለት ስትናገር ዝግ ብሎ መለሰላት፡
«ኮዜት! እውነትም እርስዋ ናት? አንቺ ነሽ እመቤቴ! አንቺው ነሽ ኮዜት? ያንተ አለህ!» ብሎ እጆችዋን ጥርቅም አድርጎ ያዘ: ቀጥሎም ያንኑ ጥያቄ በመድገም «አንቺ ነሽ ኮዜት? መጣሽ» ይቅርታ አድርገሽልኛላ!›› ሲል ተናገረ::
ማሪየስ ከዓይኑ ላይ ያቀረረው እምባ ዱብ እንዳይል በርግብግቢቱ ዓይኑን ከጨመቀ በኋላ ወደፊት ተራመደ፡፡ እንዳያለቅስ ስሜቱን በኃይል እየተቆጣጠረ በጣም በደከመ ድምፅ አባባ» አለ
«አንተም ይቅር ብለኸኛል!» አለ ዣን ቫልዣ:
ማሪየስ ቃል ለመናገር አልቻለም፡ ዣን ቫልዣ በመቀጠል አመሰግናለሁ» ሲል ተናገረ
ኮዜት ነጠላዋን ጣል አደረገች: ከዚያም የዣን ቫልዣን ሽበት ማሻሸት ጀመረች ቀጥሎም ግምባሩን ሳመችው፡ እሱም ዝም አላት እርስዋም የማሪየስን እዳ የምትከፍል እየመሰላት ማሻሸቱን ቀጠለች::
መጣሃ፣ መሴይ ፓንትመርሲ፤ ይቅር ብለኸኛላ! ሲል ዣን ቫልዣ ቀደም ሲል የተናገረውን ደገመ:፡
ዣን ቫልዣ ያለውን ደግሞ ሲናገር ማሪየስ አልቻለም፤ ፈነዳ
«ኮዜት ትሰሚያለሽ? ይሄ ነው የእርሳቸው ጠባይ! እኔን ይቅርታ ይጠይቃሉ፡፡ ኮዜት
ያደረጉልኝን ታውቂያለሽ? ሕይወቴን ያዳንዋት እኮ እርሳቸው ናቸው፡: ከዚህም
ይበልጥ ነው ያደረጉት አንቺን ለእኔ አሳልፈው ሰጥተውኛል፡ የእኔን ሕይወት ካዳኑና አንቺን ለእኔ አሳልፈው ከሰጡ
በኋላሳ ምን አደረጉ! ራሳቸውን በደሉ:: ይሄ ነው ሰው ማለት፡፡ እና ለእኔ
ለውለታቢሱ፤ ለእኔ ለረሺው፤ ለእኔ ለማይታዘንለት፤ ለእኔ ለወንጀለኛ
ምስጋና ያቀርባሉ፡ ሰማሽ ሕይወቴ ከእኚህ ሰው ጫማ ስር ተደፍታ ብትቀር እንኳን በቂ አይሆንም ያ ምሽግ፣ ያ የቆሻሻ መውረጃ፣ ጨለማ፣ ያ ስቃይ! ያ ሁሉ መከራ የተቀበሉት ለእኔ ሲሉ ነው፡፡ ሕይወቴን በሕይወታቸው ነው የዋጁት ጀግንነት፣ ደግነት፣ ድፍረትና ቅድስና ሁሉ
የእርሳቸው ቢሆን አይበዛባቸውም፡፡ ኮዜት እኚህ ፍጡር መልአክ እንጂ ሰው አይደሉም»

👍15
«ተው፣ ተው፣ በቃህ» አለ ዣን ቫልዣ በዝግታ፤ «ይህ ሁሉ ምን
ያስፈልጋል?»
«የፈጠርከኝ ጌታ!» ሲል ማሪየስ ተናገረ ይህን ሁሉ ያወቅሁት በአጋጣሚ ነው፡ አሁኑኑ ወደ ቤት ተሸክመን ልንወስዶት ነው፡፡ እርስዎ የአካላችን ቁራጭ ነዎት፡ የእኔም የእርስዋም አባት ነዎት ከዚህች ቀፋፊና ብቸኛ ቤት አንድ ቀን እንኳን አያድሩም:: ነገ ከዚህ እሆናለሁ ብለው
አያስቡ፡፡››
«ነገ» አሉ ዣን ቫልዣ፤ ከዚህ አልኖርም፤ ግን እናንተም ቤት ውስጥ አልሆንም»
‹‹ምን ማለትዎ ነው?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ፡ «አይ፣ ከአሁን በኋላ
ከቦታ ቦታ በመሄድ እንዲንከራተቱ አንፈቅድም:: ሁለተኛ ከእኛ አይለዩም:
ከእንግዲህ የእኛ ብቻ ስለሚሆኑ ልሂድም ቢሉ አንፈቅድልዎትም፡፡»
«አሁን የመጨረሻው ነው» ስትል ኮዜት ጨመረችበት «ከታች ሠረገላ ይጠብቀናል:: እኔ አሁን ወደዚያው ልሂድ 'አብሬ አልሄድም' ብትል
እንኳን እናስገድድሃለን፡፡››
ኮዜት እየሳቀች ዣን ቫልዣን ተሸክማ ለማንሳት እንደ መሞከር
አለች::
«ለአንተ የሚሆን ክፍል በሚገባ ተዘጋጅቷል» በማለት ቀጥላ
ተናገረች: «ግቢያችንን እንዴት እንዳሳመርነው ብታይ ሌላ ሆኖአል፡
አትክልቱን ውሃ የማጠጣው ራሴ ነኝ: ከአሁን በኋላ 'እመቤቴ' ወይም
መሴይ ዣን የሚባሉ ቃላት ከከንፈራችን ውስጥ አይገቡም፡ አይደለም
ማሪየስ?»
ዣን ቫልዣ ሳያዳምጡ ሰምዋት፡ ድምፅዋ እንደ ሙዚቃ ጣማቸው፡ ከነፍስ ተጨምቀው የሚወጡ የሚመስሉ እነዚያ ትላልቅ የእምባ ዘለላዎች ዓይናቸው ውስጥ አቀረሩ:፡ ከዚያም በማጉረምረም ተናገሩ፡፡
«አምላክ ደግ ለመሆኑ የእርስዋ መምጣት ምስክር ነው፡፡»
«አባዬ!» አለች ኮዜት፡፡
ዣን ቫልዣ ቀጠሉ፡፡
«እውነት ነው፤ አብረን ብንኖር በጣም ደስ ይል ነበር ግቢያችሁ ውስጥ ብዙ ዛፎች ስላሉ የወፎች ዝማሬ እንሰማለን፡፡ ከኮዜት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ከአበባው መካከል እንሸራሽራለን፡: ከሚያፈቅሩትና ከሚያፈቅር ሰው ጋር መኖር እንዴት ውብ ነው:: አብረን ብንኖር በየቀኑ እንተያያለን::
ከግቢው ውስጥ ከሚበቅሉ ፍራፍሬ እየለቀምን እንበላለን:: አበባ እየቀጠፈች
ትሰጠኛለች፡፡ እንዴት ደስ ይላል፡፡ ግን...»
ቃላቸውን ሳይጨርሱ ቆም አሉ፡፡ ከዚያም «ያሳዝናል!» ሲሉ ተናገሩ፡፡ እምባቸው ዱብ አላለም፡፡ እምባዎቹ ቀስ ብለው ከነበሩበት ጠፉ፡፡
ዣን ቫልዣ በፈገግታ ተክዋቸው፡፡
ኮዜት የሽማግሌውን ሁለት እጆች ያዘች::
«ወይኔ» አለች ኮዜት፣ «እጆችህ እንዴት ይቀዘቅዛሉ! በጣም አሞሃል
እንዴ!»
«የለም» ሲሉ ዣን ቫልዣ መለሱ፡፡ «ተሽሎኛል፤ ብቻ... አሁንም ንግግራቸውን አቆሙ::
«ብቻ ምን?»
«ቶሎ እሞታለሁ፡፡»
ኮዜትና ማሪየስ በጥፊ እንደተመታ ሰው ክው አሉ፡፡
«እሞታለሁ!» ሲል ማሪየስ በማቃሰት ተናገረ:፡
«አዎን፣ ግን ምንም አይደለም» ሲሉ ዣን ቫልዣ መለሱ፡፡
ማሪየስ ፈዝዞ ቀረ፡: ዓይኑን ከሽማግሌው ዓይን አላነሳም፡፡ ኮዜት ልቅሶዋን ለቀቀችው፡፡
ዣን ቫልዣ በመደነቅ ከአንገታቸው ቀና ብለው አይዋት፡፡
«አባባ! አባዬ አትሞትም፤ ትኖራለህ፤ሰማህ፤ እኔ ነኝ ሕይወት
የምሰጥህ»
«አዎን፣ ማን ያውቃል፣ ከመሞት ታግዱኝ ይሆናላ! እኔም ትእዛዝሽን እቀበል ይሆናል ከዚህች ክፍል ውስጥ ስትገቢ ለመሞት ሳጣጥር ነበር የአንቺ መምጣት ሞቴን አዘገየው፡ እኔም እንደገና የተወለድኩ መሰለኝ
«ገና ሕይወት ያልተለየው ጎበዝ ነዎት» አለ ማሪየስ፡ «ሰው እንዲህ እንደ ቀልድ በቀላሉ የሚሞት መሰሎት? በሕይወት "ዘመንዎ ብዙ ተሰቃይተዋል፡፡ ከአሁን ወዲያ ግን ስቃይ የሚሉት ነገር ከጫፍዎ
አይደርስም:፡ እስከዛሬ ለሆነው ከጉልበትዎ ስር ተደፍቼ ይቅርታ እጠይቃለሁ ለረጅም ዘመን ይኖራሉ እንጂ አይሞቱም የሚኖሩት ደግሞ ከእኛ ጋር
ነው:፡ አሁኑኑ ነው አብረን ከቤታችን የምንሄደው:: ከአሁን ጀምሮ እኔም
ሆንኩ ኮዜት ከእርስዎ ደስታ በስተቀር የምንፈልገው ነገር አይኖርም»
«አየህ» አለች ኮዜት እምባ እየተናነቃት፧
ማሪየስም አትሞትም ነው ያለው፡፡»
ዣን ቫልዣ ፈገግ አሉ፡፡
«መሴይ ፓንትመርሲ፣ ከቤታችሁ ብትወስደኝ ከአሁን በኋላ ለውጥ
የሚያመጣ ይመስልሃል? የለም፣ እንዳንተና እንደ እኔ እግዚአብሔር አሳቡን
አልለወጠም፡፡ ብሰናበት ነው የሚሻለው፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ ይበልጣል::
ከእኛ ይበልጥ አምላክ የምንፈልገውን ያውቃል፡»
ከበር ውጭ ጫጫታ ተሰማ፡፡ ሐኪሙ ነበሩ የመጡት፡ ከክፍሉ ውስጥ ገቡ፡፡
«እንደምን አደሩ፧ ደህና ይዋሉ» አሉ ዣን ቫልዣ ወደ ሐኪሙ እያዩ፡፡ ‹‹ምስኪን ልጆቼ ናቸው:፡›
ማሪየስ ወደ ሐኪሙ ጠጋ አለ፡፡ «ጌታዬ» ሲል አናገራቸው፡፡
የተናገረው አንድ ቃል ቢሆንም በአባባሉ ምን ለማወቅ እንደፈለገ ያስታውቃል::
ሐኪሙ በዓይን ጥቅሻ መልሱን ሰጡት
«ነገሩ ደስ ስለማይል» አሉ ዣን ቫልዣ፧ ‹‹እግዚአብሔርን ማስቸገር ትክክል አይሆንም:፡»
ዝምታ ሰፈነ፡፡ የሁሉም ልብ ተጨንቋል
ዣን ቫልዣ ወደ ኮዜት ፊታቸውን አዞሩ
አመለካከታቸው ከኮዜት አካል ውስጥ ገብቶ ለዘላለም እንዲኖር የፈለጉ ይመስል አፍጥጠው ቀሩ፡፡
ሐኪሙ የልብ ትርታቸውን ለኩ፡:
«ለካስ እናንተን ነበር የፈለገው» ሲሉ ሐኪሙ ወደ ማሪየስና ኮዜት
እያዩ ዝቅ ባለ ድምፅ ተናገሩ፡፡ ከዚያም ወደ ማሪየስ ጆሮ ጠጋ ብለው
«አልሆነም» አሉት፡፡
ዣን ቫልዣ ከኮዜት ላይ ዓይናቸውን ሳያነሱ ማሪየስንና ሐኪሙን አይዋቸው::
«መሞት ምንም አይደለም፧ አለመኖር ግን ያስፈራል፡፡»
በድንገት ብድግ ብለው ተነሱ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የዚህ ዓይነቱ ድንገተኛ የሆነ ጉልበት የጣዕር ምልክት ነው ይባላል:፡ ማሪየስንና ሐኪሙን ገፍትረው ወደ ግድግዳው ሄዱ ሁለቱም እንዲደግፏቸው ቀረብ ብለው ነበር፡፡ ከግድግዳው ላይ ተሰቅሎ የነበረውን መስቀል አወረዱ፡፡ ከወንበር ላይ ቁጭ ብለው መስቀሉን ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጡት
‹‹ሰማዕቱን ተመልከተው፡፡»
ይህን እንዳሉ መላ ሰውነታቸው ተዝለፈለፈ:፡ ሁለት እጆቻቸውን
ከጉልበታቸው ላይ በማሳረፍ ደገፍ አሉ፡ ኮዜት ጀርባቸውን ያዘች፡፡ አሁንም
እያለቀሰች ነው፡፡ አባትዋን ለማናገር ፈልጋ አቃታት፡፡
«አባዬ፣ ምነው ጥለኸኝ አትሂድ፡ ምነው ተስማምተን አሁን በመጨረሻ
ልትለየን» ብላ ለመናገር እንደፈለገች ዓይንዋ ያስታውቃል፡፡
ጣዕር ሲይዝ ሕመም መለስ ይላል በሽተኛው ደህና ይሆንና ወዲያው
ደግሞ ዝልፍልፍ ነው የሚለው:
ሠራተኛዋ ከሐኪሙ ጋር መጥታ ነበር፡ ገርበብ ብሎ በተከፈተው በር ስታይ ሐኪሙ መለስዋት፡ እምባዋን ግን ሊያስቀሩ አልቻሉም:
«ቄስ ልጥራ?» ስትል ጠየቀች::
«እኔ አለኝ» ሲል ዣን ቫልዣ መለሱላት
ይህን እንዳለ አንገታቸውን ቀና አድርገው ተመለከቱ:: እኚያን የተቀደሱ ጳጳስን ማየታቸው ይሆናል
ኮዜት ትራስ ከጀርባቸው ስር አደረገችላቸው::
«መሴይ ፓንትመርሲ አትፍራ፡ ያገንዘብ በእርግጥ የኮዜት ሀብት ነው
ደቂቃ ባለፈ ቁጥር የዣን ቫልዦም ጉልበት እየቀነሰ ሄደ ጉልበታቸው ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነታቸው ደከመ: ዓይናቸው ፈዘወ
ሐሞታቸው ፈሰሰ፡፡ እውነትም ሞት እንደቀረባቸው አስታወቀ፡፡ ወደኋላማ
ሰውነታቸውን ማንቀሳቀስ አቃታቸው፡፡ የማይታወቀው ዓለም ጥላ
አንዣበበባቸው፡፡ የሕይወት የመጨረሻ ደቂቃ እየተቃረበች መጣች፡

👍23
«ሁለታችሁም ጠጋ በሉ» ሲሉ በራቀ ድምፅ ጠርዋቸው:፡ ብጣም
እወዳችኋለሁ እናንተም ትወዱኛላችሁ: ትንሽ ታለቅሺልኝ የለም? ግን
እንዳታበዢው፡፡ እዚያጋ ያለውን ትንሽ ቀሚስ ታይዋለሽ? የአንቺ ልብስ
ነው ከአሥር ዓመት በፊት የተገዛው: ጊዜ እንዴት ያልፋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ደስ ብሎን ነበር የኖርነው: አሁንስ በቃ ልጆቼ አትዘኑ! አታልቅሱ ብዙ ርቄ አልሄድም ከዚያ ሆኜ አያችኋለሁ ማታ ማታ እኔን ለማየት ሞክሩ፡ ኮዜት ውሃ ልትቀጂ የሄድሽበት ጫካ ትዝ ይልሻል? እነ ቴናድዬስ? አሁን መንገር አለብኝ! እናትሽ ፋንቲን ነበር የምትባለው ስምዋን
እንዳትረሺው... ፋንቲን፡፡ እናትሽ በጣም ትወድሽ ነበር ስለንቺ ብዙ ተሰቃይታለች ልጆቼ እኔ አሁን መሄዴ ነው እርስ በእርስ ተፋቀሩ: ከፍቅር የሚበልጥ ነገር የለም፡ ከዚህ የሞተው ምስኪን ሽማግሌ እያላችሁ አስታውሱኝ አንድ ነገር እየጋረደኝ ነው: በደምብ አላያችሁም ጠጋ በሉ
እስቲ ደስ ብሎኝ ልሙት: እጆቼ ከእናንተ ላይ ይረፉ »
ኮዜትና ማሪየስ እምባ በእምባ ሆነው ከዣን ቫልዣ አልጋ አጠገብ
ተንበረከኩ፡፡ እያንዳንዳቸው አንዳንድ እጃቸውን ያዙ እጆቹ ቀዝቅዘዋል
ከዚያ በኋላ እነዚያ እጆች አልተነቃነቁም: ዣን ቫልዣ ወደ ሰማይ ተመለከቱ
ማሪየስና ኮዜት የያዙትን እጅ ስመው መልሰጡ አስቀመጥዋቸው ዣን ቫልዣ ነፍስ ከሥጋቸው ተለየች
ክረምት፣ ክረምት ሳር በሀይል ስለሚበቅልት ጤዛ ሱሪዬንና ጫማዬን
ያርስብኛል! በጋ ደግሞ ፀሐይ ለመሞቅ የሚወጣው እንሽላሊት የመቃብሩን
አካባቢ ስለሚወርረው በዚያ ማለፍ ያስጠላኛል በሚል ሰበብ ሰው
ከማያልፍበት የመቃብር ሥፍሪ ዣን ቫልዣ ተቀበሩ። ከመቃብራቸው በላይ
ከተተከለ ድንጋይ ላይ የሚከተለው ቃል ተፅፎ ነበር
«አንቀላፍቶአል የዚህ ሰው እጣ ፈንታ እንግዳ ቢሆንም በሕይወት ኖሯል ቀንና ማታ ሳይዛባ እንደሚፈራረቅ ሁሉ ሁለም ነገር ጊዜውን ጠብቆ ሆነ
💫ተፈጸመ💫
አምናለው ብዙዎቻችሁን ወደ ኋላ መልስ እንዳረኳችሁ ምክንያቱም እኔ እራሴ እንዳዲስ እያነበብኩ ነው ያስተላልፍኩላችሁ እስቲ አስተያየታችሁን እጠብቃለሁ በ @atronosebot አድርሱኝ እንዲቀርብ የምትፈልጉትንም መፅሀፍ መጠቆም ትችላላችሁ መልካም ጊዜ።

👍30👏2👎1
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
....“ራስህ ነህ፤ አዎ: ግን እንዴት?” አልሁት መኪናዉን የቤተመንግሥት ታርጋ እንዳየሁበት አስታዉሼ። ለነገሩ ባልቻ የማያልፍበት ምን የመርፌ ቀዳዳ አለና ነዉ? ልክ ወደ መዉጫዉ በር ስንቃረብ፣
መኪናዉን ድንገት ሲጢጥ አድርጎ አቆመዉ።
"አይሆንም በዚህ መልኩ መዉጣት አንችልም። ይኸኔእኮ በሩ ተከርችሞ ወታደሮችም በጥፍሮቻቸዉ ቆመዉ እየጠበቁሽ ይሆናል: ኮሎኔሉ ሳይቀር መሬቱን እየጠለዘ በመንቆራጠጥ ላይ ነዉ የሚሆነዉ።ምክንያቱም ከግብጽ ትሆኚ ከኤርትራ፣ አሸባሪ ትሆኚ ተገዳዳሪ፤ ምንነትሽን እንኳ ን በቅጡ ያላወቁሽ አንቺ ከእጃቸዉ ስላመለጥሽባቸዉ እታሰስሽ ነዉ የምትሆኝዉ: ስለዚህ በየትኛዉም በር መዉጣት አንችልም ደኅነት እና ወታደር ሁሉ ተነስንሶ እያፈላለገሽ ከሆነ ደግሞ አስቢዉ፣ግቢም ደግሞ መቆየት አንችልም: አጣብቂኝ ዉስጥ ነን”
አለኝ፣ እንደ መረታት ብሎ።
“እንዲህ ብናደርግስ?” አልሁት፣ ሰዓቱን እንዲመለከት እየጠቆምሁት።
“በመርሐ ግብሩ መሠረት፣ በአዳራሽ የነበሩት እንግዶች መዉጫቸዉ ነዉ: በእርግጥ አልፏል: የፈለገ በየሰበቡ አንዛዝተዉ ቢያቆዩአቸዉ
እንኳን፣ መዉጣታቸዉ ግን አይቀርም: መቼሰ እዚሁ አያሳድሯቸዉ።ይወጣሉ። እነሱ እስከሚወጡ ድረስ ጠብቀን በየመኪናቸዉ ተከታትለዉ
ሲወጡ እኛም ተደባልቀን መዉጣት እንችላለ”
“ፍተሻዉ ቀላል ይሆናል ብለሽ ነዉ?” አለ የመኪናዉን መብራቶች
አጠፋፍቶ በዝግታ ወደ ተነሳንበት ቦታ ወደ ኋላ እያሽከረከረ ወደ ሰፊዉ የመኪና ማቆሚያ ተመልሰን ልክ ከመቆማችን፣ የጋቢናዉ በር ተንኳኳ።
ስአሊ ለነ! መኪና ማቆሚያዉ ጠባቂ እንዳለዉ እንዴት አልገመትንም?እንኳንስ የቤተ መንግሥቱ ተራ የመንገድ ዳር መኪኖችስ ጠባቂ አላቸዉ
አይደል እንዴ? ቀሽሞች ነን! የኔስ እሺ፣ ባልቻ እንዴት ልብ አላለዉም
ይኼን?
ጋቢናዉ በድጋሚ ተንኳኳ
“አቤት?” አለ ባልቻ እኔን ወንበር ሥር እንድደበቅ በዳበሳ ምልክት
ከሰጠኝ በኋላ፣ መስታዎቱን ዝቅ አድርጎ፡
“ችግር አለ?” አለ ጠባቂዉ፣ በትሕትና
“እህህ” ብሎ የማስመሰል ሳቅ አስቀደመ፣ ባልቻ። “እህህ… ያዉ
ታዉቀዉ የለ የኛን ሥራ? አለቆቼ አድ ቦታ ላኩኝና እየወጣሁ ሳለ ደግሞ እንደገና እንድተወዉ ደዉለዉልኝ ነዉ እንጂ ችግር የለም: የማደርሳቸዉ እንግዶች ሳይኖሩ አይቀርም”
“አይደል? ተደዉሎልህ?” አለ ሰዉዬዉ ልብ በሚወጋ ስላቅ።
ወዲያዉኑ በአቅራቢያ የሚያልፉ ኹለት ወታደሮችን አፏጨላቸዉ።
እየበረሩ እንደ መጡ ኮቴያቸዉ ነግሮኛል።
“ይቅርታ ጌቶቼ፣ የሚያጠራጥር ነገር ካለ አሳዉቅ ተብዬ ነበር። መቼም ሰዉ ያለ ምክንያት መብራት አጥፍቶ ወደ ኋላ አይነዳም: ምናልባት
የምትፈልጉት ዓይነት ሰዉ እንደሆነ ብዬ ነዉ” አላቸዉ፣ ወደ ባልቻ እየጠቆመ። መሣሪያቸዉን አነጣጥረዉ ከመኪናዉ በቀስታ እንዲወርድ አዘዙት።
“እንዳትሳሳቱ፣ እኔ ተራ ሹፌር ነኝ: ከዚህ ሁሉ ለምን ጉቦዳን
አትጠይቁትም?”
ምን አስቦ እንደሆነ ባይገባኝም፣ አመላለሱ ግን ሆነ ብሎ ጥርጣሬያቸዉን የሚያጎላ ነዉ ምክንያቱም ገና አንድ ጥያቄ እንኳን ሳይጠይቁት፣
በዉስብስብ ጥያቄዎች እንዳስመረሩት ሁሉ መቀለማመዱ ከባልቻ የሚጠበቅ አይደለም: እንዲያዉም እሱ ራሱ “ጅል ለስለላ ሄዶ ምግብ
ቢያቀርቡለት ስለላ ላይ ነኝ ብሎአረፈዉ” ብሎ በተልካሻ የመረጃ አነፍናፊዎች ሲስቅ ሰምቼዋለሁ። የእሱ የተቻኮለ መልስ ግን ከጅሉ በላይ
ቢብስ እንጂ አይተናነስም
“ጉቦዳን ጠይቁት”
“ማነዉ ደግሞ ጉቦዳ?”
“ጉቦዳ የመኪና ስምሪት ኃላፊዉ ነዋ: አታዉቁትም? ጉቦዳ ?”
“ና ቅደም እስኪ ለማንኛዉም” ብለዉ ወሰዱት እርስ በእርስ ትንሽ
ከተመካከሩ በኋላ።
እኔን ማንም ሳያየኝ መኪና ዉስጥ ቀረሁ አሁን ሐሳቡ የገባኝ መሰለኝ፡ ኹለታችንም ከምንያዝ፣ እኔን አትርፎ ራሱን ማጋለጡ ነዉ። ባልቻ አይደል ሰዉዬዉ? መhራዬን መዉሰድ ያዉቅበት የለ? መንገድ አብረን እየሄድን ድንገት ጋሬጣ ሲያደናቅፈኝ ‹እኔን ባዩ ሰዉ! ለማለቱማ ማንም ሰዉ ይለኝ ይሆናል፣ ከልቡ መሆኑን ግን ከእሱ በቀር የማምነዉ ማን
አለኝ? ከእናቴ ቀጥሎ ከሰዉ ማንም እንደሱ የለም ባልቻ ብቻ!
ባልቻን በወሰዱበት መንገድ አፍጥጬ እንባ እያፈሰስሁ ለደቂቃዎች በድንዛዜ ቆየሁ ከዚያ እንደ ምንም እንባዬን ጠራርጌ ዓይነ ልቡናዬን እንዲያበራልኝ አጭር ጸሎት ማድረስ ስጀምር፣ በርከት ያለ ድምፅ ሰማሁ። እንግዶች መዉጣት ጀምረዋል። አሁን የዕቅድ ለዉጥ አድርጌም
ቢሆን ከዚህ ግቢ ቶሎ ማምለጥ አለብኝ፡ እንዴት? መቼም እንግዶቹ
ሲወጡ በር ላይ ጠበቅ ያለ ፍተሻ መኖሩ የማይቀር ነዉ። ያን ጊዜ
ትኩረቱ ሁሉ ወደ በሩ ይሆናል ማለት ነዉ፡ እንደዚያ ከሆነ ደግሞ እኔ በአጥር መዝለል እችላለሁ፡ በእርግጥ እንኳንስ በአጥሩ መዝለል ይቅርና፣ አጥሩ አጠገብ መድረሱ በራሱ ዋዛ እንደማይሆንልኝ አልጠፋኝም: ነገር ግን ከጥበቃ ማማዎች ወደሚቀርበኝ ቃኚ ወታደር መስዬ እያዘናጋሁ እቀርበዉና ያቺን የሰመመን መርዝ ጠቅ አደርግበታለሁ። ይወድቅልኝ
የለ? ያን ጊዜ ከራሱ ማማ እመር ብዬ ወደ ዉጪ እዘላለሁ፡ ምናልባት በግራና በቀኝ በኩል ባሉ ማማዎች ያሉ ወታደሮች ቢተኩሱብኝ ነዉ ቢሆንም ግን የመጨረሻዉ ቀላል ማምለጫ ይኼ ብቻ ነዉ ሌላ አልታየኝም:
ያቀድሁት ሁሉ ሰምሮልኝ ዘልዬ ወደ ዉጪ ከመዉደቄ እንደ ጠበቅሁት የተኩስ እሩምታ ይዘንብብኝ ጀመር። እየተንከባለልሁ ወደ ዋናዉ ጎዳና
ስወርድ፣ ማንነቱ የማይታይ ሰዉ አንዲት ሚኒባስ ታክሲ እያበረረ
አጠገቤ አድርሶ በሯን ከፈተልኝ፡ የሲራክ፯ አባላትን የምታግባባዋን
የመኪና ጥሩምባ ቀድሞ ስለነፋልኝ፣ ለእኔ የመጣ መሆኑን አወቅሁና ሳላቅማማ ተወርዉሬ ገባሁባት ነዳጁን ረግጦ ከግቢ ገብርኤል በታች ወዳለዉ የመንደር መንገድ ወሰደኝ።
አመለጥሁ።
ከቤተ መንግሥቱ መራቃችንን ሲያዉቅ፣ ሹፌሩ የመኪናዉን የዉስጥ መብራት አብርቶ በድል አድራጊነት አየኝ፡ አየሁት።
“አ-ባ-ቴ?!” ብዬ በጩኸት አቀለጥሁት ባልቻ ነዉ። በምን ተአምር እንዳመለጠ ልጠይቀዉ ወይስ ዝም ብዬ ከአንበሳ ጉሮሮም ቢሆን የሚያተርፈንን አምላክ ላመስግን? ቸገረኝ እኮ፡ ሰአሊ ለነ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ባልቻ ነዋ ሰዉዬዉ! እንዴት አያመልጥ?” ሲል አቋረጠኝ፣ ቢራራ እኔም ልክ አሁን የሆነ ያህል ነበር በስሜት ያጫወትሁት።
በዚህ እና ከዚህ በባሱ መዐት ሞቶች መካከል አልፌ የማዉቀዋ እኔ፣ ዛሬ ግን ፈራሁ። እዉነትስ ፈተና ባይኖር ሁሉ ተማሪ፣ ጠያቂ ባይኖር ሁሉ አስተማሪ የሚለዉ አባባል ይመለከተኛል? በጭራሽ! በጅቦች መካከል፣ በጨለማ አካፋይ ሞትን ተፋጥጬዉ አልፏል።
“እንግዲያዉ ለምን ፈራሁ አሁን? አንተ እስክትሳለቅብኝ ድረስ ለምን
ተንቀጠቀጥሁ?”
“ይኼን ስትነግሪኝ ምን እንደመጣብኝ ታዉቂያለሽ?ስለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጴጥሮስ ያነበብሁት አንድ ምዕራፍ” አለ፣ በሞባይሉ መጽሐፍ ቅዱስ እየከፈተ። የሚፈልገዉን ምዕራፍ ሲያገኘዉ፤ “ከዚህ ጀምረሽ
አንብቢዉማ” ብሎ ሞባይሉን አቀበለኝ። ታሪኩ ጌታችን ኹለት ዓሣ እና አምስት እንጀራ አበርክቶ ሕጻናቱንና ሴቶቹን ሳይጨምር አምስት ሺ ወንዶችን ያጠገበ ዕለት፤ ሌሊቱን የሆነ ነዉ።

👍30😁2🔥1👏1
“…ታንኳይቱም በባሕር መካከል ሳለች፥ ነፋስ ከወደ ፊት ነበርና
በማዕበል ትጨነቅ ነበር። ከሌሊቱም በአራተኛው ክፍል ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፡ ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ፤ ምትሐት ነው ብለው ታወኩ በፍርሃትም ጮኹ: ወዲያውም ኢየሱስ ተናገራቸውና አይዞእችሁ፥ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ አላቸው: ጴጥሮስም መልሶ ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አን† እንድመጣ አዝዘኝ አለው:
ኢየሱስም "ና" አለው: ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ
ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ:: ነገር ግ3 የነፋሱ ኃይል
አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ
ጮኸ: ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና ‹አንተ
እምነት የኅደለህ፥ ስለ ምን ተጠራጠርህ? አለው…”
እኔስ?
ምናልባት፣ እንደ ሐዋርያዉ በባሕር ላይ ያረማመደኝን እምነት አጉል አድርጌዉ ይሆን? አምላኬን ተጠራጥሬዉ ነዉ?እኔ አላውቅም
“ኧረ ጌታ ሆይ፤ አድነኝ!”
እግዚአብሔር ላይ የነበረኝን እምነት አጉድያለሁ አላጎደልሁም
እያልሁ ራሴን ስነታረከዉ፣ ሌላ ሌላዉንም ጨምሬበት እያብሰለሰልሁ ተበጥብጬ ሰነበትሁ። የትኛዉ ነዉ ግን ወደ የትኛዉ ያደረሰኝ? በፈጣሪ
የነበረኝ መተማመን መሸርሸሩ ነዉ ልክ ያልሆነዉን ፅንስ ያመጣብኝ?
ወይስ ልክ ያልሆነዉ ፅንስ ነዉ ፈጣሪን እንዳልተማመን የዳረገኝ? የፅንሱ አባት እሸቴ መሆኑ ነዉ ጉዴን ያፈላዉ? ወይስ ወንድምነቱን የተጠራጠረዉ ጃሪም ነዉ? ወይስ የተልእኮ ምንጬ ሲራክ ፯? ወይስ ሌላ
ምንድነዉ?
ልክ የሆነዉን እና ያልሆነዉን የምለይ መስሎኝ እንዲችዉ ስብከነከን ሰነበትኋት። አልፎ አልፎ ከሲራክ ፯ ለሚሰጡኝ ቀለል ላሉ ተልእኮዎች ካልሆነ በቀር፣ በእመዋ ቤት ካለኝ ክፍል እምብዛም ሳልወጣ ሳምንታት
ከሰሙ።
“ዉዉዉ..ዉብዬ” አለኝ በተብታባ ድምፁ፣ ያለሁበትን በር እያንኳኳ።
እሸቴ።
“ክፍት ነዉ፤ ግባ”
በሩን ገፋ አድርጎ ገባና፣ እቅፍ አድርጎ በቀዝቃዛ ከንፈሩ ጉንጬ ላይ ሳመኝ፡
“እእእ..እስከ አሁን ተኝተሽ?”
ረፍዷል አይደል? ጭራሽ መንጋቱም ልብ አላልሁት እኔስ''
ምሳ ሰዓት ሊደርስ እኮ ነዉ።
በበበ..በበይ ተነሽ፣ እንሂድ''
“ኧረ እኔ የትም ንቅንቅ አልልም: አላሰኘኝም”
“እህእ”
“እሽቴ ሙት፣ ብሞት ከዚህ አልወጣም”
“የት እንደሆነ ሳሳሳሳሳሳ..ሳሳ.ሳትጠይቂኝ?”
“የትም ቢሆ፤ አልወጣም አልሁህ አልወጣም: ስልችት ብሎኛል ሁሉም ነገር'
“ዛሬ እኮ ነዉ የክትትል ቀጠሮሽ: ረስተሽዋል?”
“ሰባት ወር ሞላኝ ማለት ነዉ?” አልሁኝ ለራሴ፣ አልቅሽ አልቅሽ
እያለኝ።
“እንሂድ?” አለኝ፣ የገፋ ሆዴ ላይ ኹለት እጄን ጭኜ ፍጥጥ ብዬ
ብቀርበት
“ታዲያ አሁን ምሳ ሰዓት ደርሷል አላልከኝም? ከሄድጓም ከሰዓት በኋላ እንሄዳለና”
“አዎ። እስከዚያ ደግሞ ቆቆቆቆቆቆቆቆ..ንጆ ምሳ እጋብዝሻለሁ”
“ምሳ?”
“ምን የመሰለ ቤት መርጬልሻለሁ”
“አይ ተወኝ፤ ይቅርብኝ” አልሁት፣ ሳስበዉ ገና እየታከተኝ።
“ምናለበት ወግ ደርሶኝ ብጋብዝሽ? በናትሽ። እ ዉቤ? እንዉጣ አይደል? እሺ አልሽኝ አይደል በእጅ በእግሬ እየገባ ሲለማመጠኝ አንጀቴን
በላዉ ምን ቸገረኝ ብዬ ተለሳለስሁለት፡
“ሰዉ አይበዛበትም ግን?”
“የጸጥታ ቤት ነዉ ኧረ! ሙዚቃ የለ፣ ጩኸት የለ፣ ሲጋራ የለ። ምንለ ብዪኝ ትወጅዋለሽ እንሂድ አይደል? እ? እሺ ብለሽኛል?”
እሺም እምቢም ሳልለዉ፣ እንዲሁ እግሬን እየጎተትሁ ወጣሁ ለእኔ
የተከተለኝ መስሎኛል፣ ለእሱ ደግሞ ተጣጥቤ የምመለስ መስሎታል።
“እህእ፣ ና እንሂዳ!” አልሁት፣ እንደገና ገባ ብዬ፡
“እእእእ..እንደዚህ ሆነሽ? ፊትሽን እንኳን አትታጠቢም? ኧረ ባይሆን
ያደርሽበትን ልብስ እንኳን ለዉጪዉ?”
ግድ የሌለኝ ከሆንሁማ ቆየሁ። አልመለስበትም ወዳልሁት ስሜት ሁሉ በትንሽ በትልቁ ሰበብ እየተንሽራተትሁ ጥልቅ ማለቱንማ ለምጄዋለሁ። እንደገና ተመልስሁና ያገኘሁትን ልብስ በዘፈቀደ ለባብሼ እና እንደ ነገሩ
ፊቴን ተጣጥቤ ወጣሁ ከዚያ ለምሳ መርጬልሻለሁ ወዳለኝ ሆቴል ተያይዘን ሄድን መኪና ማሽከርhር ሁሉ ስላስጠላኝ፣ ረዥሙን መንገድ በእግር ነበር የጨረስነዉ። እየቆየ ትንሽም ቢሆን ቀለል እያለኝ መምጣቱን
ኹለታችንም ያስተዋልነዉ፣ ልክ ወደ ሆቴሉ መግቢያ ግድም ስንደርስ ሸንኮራ አገዳ ሲያምረኝ ነዉ: ድንገት በዓይን በዓይኔ ዞረብኝ፡ ከመሬት ተነስቶ በኃይል አማረኝ።
የእርጉዝ ወግ ደረሰኝ ማለት ነዉ?
ተመስገን፡ ምንም ነገር አምሮኝ አያዉቅም ነበር። እሸቴ ደግሞ ሸንኮራ አገዳ ፍለጋ እንዴት እንደ ወደቀ እንደ ተነሳ በስመ አብ! ወደ ላይ ወጥቶ ሳያገኝ ተመለሰ፡፡ እንደገና ወደ ታችም ወርዶ አላገኘም: ባንፈልገዉ ይኸኔ፣ በሚገፋ ጋሪ ጭነዉ አገዳ የሚያዞሩት በመንገዱ አያሳልፉን
ነበር፡ ያልጠየቀዉ መንገደኛ እና ባለሱቅ የለም ግን ሸንኮራዉ ከየት
ይገኝ? ቢያንስ ለሃያ ደቂቃ ያህል ተንጓሎ ተንጓሎ ቢያጣም አላዉቅልህ አልሁት፡ ከየትም ቢሆን መዉለድ አለበት እኔ ለራሴ ምራቄ በአፊ እየሞላ ተቸግሪያለሁ፡ አምሮት እንዲህ ያቅበጠብጣል ለካ! ሽንት መቋጠር ቀላል ነዉ ከዚህስ፡ ምንም አልቻልሁም ያለ ቅጥ ተነጫነጭሁበት
“እናንተ?” አለችን እመዋ፣ ድንገት ከኋላችን ድርስ ብላ። ገና ሆቴሉ
ዉስጥ ገብተን፣ ዞር ባለ ቦታ ወንበር መያዛችን ነዉ። እሷን ሳይ ድርቅ ብዬ ቀረሁ፡
“ሰእሊ ለነ! እመዋ?”
“እዚህ ደግሞ ምን ትሠራላችሁ?”
“እኛማ… ይኼ እሸቴ ምሳ ካልበላን ብሎኝ ነዉ እንጂ። አንቺ ግን ከየት መጣሽ?”
ግርም ብሎኝ ልሞት በተለይ አሁን አሁን፣ እመዋን ወይ ከሥዕል ቤት
ወይ ከግቢ ገብርኤል ወይ ከታዕካ ነገሥት ገዳም ዉጪ አገኘኋት ማለት፣ እኔም እሷም በቤቷ ዉስጥ ነን ማለት ነዉ። ከዚያ ዉጪ በአጋጣሚም ቢሆን፣ ከቤት እስከ ገዳም ባለዉ መንገድ እንኳን ተገናኝተን አናዉቅም፡
ከገዳም እና ከቤቷ ዉጪ ካየኋት ስንት ጊዜዬ። ድሮም ቢሆን ለነገሩ
ከስንት አንድ ወደ ገበያ ትወስደኝ እንደሆነ እንጂ፣ ሆቴል ዉስጥ እሷን አስቢያት አላዉቅም ኧረ በፍጹም፡ ብርቅ ድንቅ ሆነብኝ፡ ተአምር! ወይ እሷ ወይ እኔ ከሌላ ሀገር መጥተን ከዓመታት በኋላ የተገናኘን ይመስል፣ ጥምጥም ብዬ አቀፍኋት ለሚያየን ስዉ የተነፋፈቅን ብንመስለዉም፣
ያደርነዉ ግን በአንድ ቤት ነዉ። በእርግጥ በአንድ ቤት ብንሰነብትም፣ በዐዚሜ የተነሳ፣ አብሪያት ነበርሁ ማለት ግን አልችልም እንደገና አንገቷ ዉስጥ አስርጋ አቆየችኝ
ሆዴንም ፊቴንም በእናት እጇ እየደባበሰችኝ ሳለ፣ እሷ ከመምጣቷ በፊት ተቀምጬበት የነበረዉ ወንበር ፊት ለፊት አንዲት ለግላጋ አስተናጋጅ የተሸፋፈነ ነገር ጠረጴዛዉ ላይ አስቀመጠች፡ ገና ቁጭ ከማለቴ እንድገልጠዉ ምልክት ሰጠችኝ፡፡ እንደ ዋዛ ነጩን ዳንቴል መሳይ ጨርቅ
ስገልጠዉ፣ ነገርዮዉ፣ ያ በአምሮት የተቅበጠበጥሁለት ሸንኮራ አገዳ ሆኖ እርፍ!
“በስመአብ! ያዓቺ ሥራ ነዉ እመዋ? መቼም ሆቴል ዉስጥ አገዳዉም እንዲህ ተከትክቶ ይቨጣል አትሉኝም ! አይቼም ስምቼም አላዉቅም። አንቺ ነሽ እ እመ?”
የእናት ሳቋን አሳየችኝ አዎ በማለት ጭምር
“እንዴት?” አልኋት፣ ድንገት ፊቴን ቅጭም አድርጌ። አገዳ እንዳማረኝ እንዴት አወቀች?
“እናትሽም አይደለሁ? ዐመልሽ አዉቃት የለ? ምን እንደሚያምርሽ እኮ አይጠፋኝም”
“ኼኼኼ፣ እሱንስ ተይዉ: ባይሆን ይኼ ነግሮኝ ነዉ ካልሽኝ አምንሽ
እንደሆነ እንጂ” አልሁኝ፣ ወደ እሸቴ እየተፍለቀለቅሁ፡ “ከአሁን ቀደም ለሸንኮራ እንዲህ ስሆን አይታኝ አታዉቅ እሷ፤ አንተ ነግረሃት ነዉ ኣ?”

👍26😁2
እርስ በእርስ ተያዩና፣ አንገቱን በአዎንታ ነቅንቆ ፈገግ አለ።
“እንዴት?” አልኋቸዉ በሁሉም ነገር በመደነቅ፣ አንደኛዉን የአገዳ
ክፋይ አንስቼ እየላጥሁ። እመዋ እኮ ስልክ ኖሯት አያዉቅም ታዲያ
በምን አስማት ተገናኝተዉ ሊነግራት ቻለ? መቼስ አጋጣሚ ነዉ አይሉኝ።
“እኔ ምናችሁም አልተዋጠልኝም…” አልሁኝ የአገዳዉ አምሮት በመጀመሪያዉ ጉርሻ ወጥቶልኝ ከፊቴ እየገፋሁት። “እመ?”
“እመት ዓለሜ”
“ከገዳም ነዉ አይደል አመጣጥሽ?”
“ነዉና”
“እኮ እሸቴ እንዴት አግኝቶ ነገረሽ? ባስበዉ ባስበዉ የሚመስል ነገር
አጣሁበት”
“ማነሽ አስተናባሪ?” አለች ድንገት ፊቷን ለወጥ አድርጋ፡ “እስኪ ምሳ
አቀራርቢልን እንጂ: እሸቴ? ዉቤ?በሉ የምትጋብዙኝን ተነጋገሯት
እንጂ”
ጥያቄዬን አልወደደችዉም ማለት ነዉ። ያልወደደችዉ ደግሞ ከጀርባ አንድ ነገር ቢኖር ይሆናል፡ በዚያ ላይ ያለ ዐመሏ ችኩል ችኩል አለችብኝ፡ ቋንቋዋ ሁሉ ልዉጥዉጥ አለብኝ፡ ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ብቻ የባሰ ከነከነኝ ግን ምን ይኖራል? በሐሳብ ጭልጥ ብዬ የትና የት
ደርሻለሁ። ይኸኔ እኮ ዝም ብዬ ይሆናል ያጋነንሁት፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እኔ ከቀልቤ አይደለሁም: ራሴን አላዉቀዉም፡ ወፈፍ ማድረጉ ሳይጀማምረኝ አልቀረም: ኧረ ያዉም ከመጀማመር የባሰ ባይሆን ነዉ፡
ምግብ በልተን እንደ ጨረስን፣ አስተናጋጇ መሶቡን ከፍ አደረገችዉና እንደገና ከሌላ አስተናጋጅ ጋር ተከታትለዉ ተመልሰዉ እጃችንን በተቀመጥንበት አስታጠቡን በቀረበልን ፎጣ እጃችንን ካደረቅን በኋላ ለእግዚአብሔር የአንድነት ምስጋና አደረስን፡ ከዚያ የከነከነኝን ነገር እንደገና ላነሳባቸዉ ስል፣ እሸቴ ስልክ የተደወለለት አስመስሎ ሹልክ አለ ማንም እንዳልደወለለት ግን እርግጠኛ ነኝ። እንዲያዉም ሊወጣ ሲል፣ ከእመዋ ጋር ተጠቃቅሰዉብኛል፡ አረሳስቶ ይመጣል ብዬ
ብጠብቅም፣ በዚያዉ ጠልቆ ቀረ።
"አንቺ ይኼን ልጅ ምን በላዉ? ቀልጦ ቀረ እኮ” አለች እመዋ፣
ሲጠቃቀሱ ያላየኋቸዉ መስሏት እሷም ከየት እንደምትጀምርልኝ
ጨንቋት ይሆናል እንጂ
ታስታዉቃስች። ልትነግረኝ የፈለገችዉ ነገር እንዳለ ታስታውቃለች።
“ንገሪኝ” አልኋት፣ በሚያደፋፍር ሁኔታ።
“አይ፣ የሚነገር አይደለም”
“ምናለበት፣ ልጅሽ አይደለሁም? ምንም ሆነ ምን እኮ ልትነግሪኝ
ትችያለሽ:: ግድ የለሽም ንገሪኝ” አልኋት፣ ልክ እሷ ሁልጊዜም ለእኔ
እንደምታደርገዉ ሁሉ እኔም ፊቷን እየዳበስሁላት።
“አመጣጤስ ልነግርሽ አይደል እሱማ: ግን ከምነግርሽና ከማሳይሽ?”
“እ?”
“ምረጭ፤ ብነግርሽ ይሻልሻል ወይስ ባሳይሽ?”
“እህእ፣ ምንድነዉ ጉዱ? ንገሪኝም አሳዪኝም እንጂ”
“ እንግዲያዉ ተነሺ፣ እንሂድ”
"ሳትነግሪኝ?”
“እኮ እዚህ አይደለማ። እያሳየሁ የምነግር ሽ ነገር አለ፣ ነይ ተነሺ”
ተነስቼ ተከተልኋት ከነበርንበት ሆቴል ወጥተን በግቢ ገብርኤል ገዳም በኩል ዉስጥ ለዉስጥ በእግራችን አቆራርጠን፣ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ዋና በር ደረስን፡
“አንድ ጊዜ ከባልቻ ጋር እዚህ መጥታችሁ ነበር አይደል?” አለችኝ እንደ ዋዛ፣ ወደ ታላቁ ቤተ መንግሥት በቅንድቧ እየጠቆመችኝ፡
“አዎ” አልኋት፣ እኔም እንደ ዋዛ፡ “እ?” አልኋት ወዲያዉ፣ ዉሃ ሆኜ ምን ምን? ያለችዉን ነገር እኮ ገና አሁን ነዉ ልብ ያደረግሁበት::
ከማን ጋር ምንድነዉ ያለችኝ? ባልቻ? እርፍ! እንዴት እንዴት ነዉ ነገሩ?......

👍22❤8