አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከሰሀራ_በታች


#አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

የፍቅርተ ጂንስ ሱሪ ታጥቦ ከተሰጣበት የልብስ ማስጫ ገመድ ላይ ጠፋ፡፡ “የትኛው ሱሪ?”
የሚል ይኖራል፤ ፍቅርተ የነበራት አንድ ሱሪ ነበር፡፡ የጠፋውም ይሄው አንድ ለናቱ የሆነ ሱሪ ነው፡፡ የመንደሩ ሱሰኛ ጎረምሶች ለዕለት ሱሳቸው ማስታገሻ ወስደው ሸጠውት ይሁን አልያም ሞገደኛ ነፋስ እያግለበለበ ወስዶ አንዱ ቂርቂራ ሸጉጦት እግዜር ይወቅ፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ ከተገዛ ገና ስድስት ወር ብቻ የሆነው፣ ግርጌው ቀበኛ ከብት አኝኮ እንደተወው ጨርቅ
የተተፈተፈው የፍቅርተ ጥቁር ጅንስ ሱሪ ታጥቦ ከተሰጣበት ገመድ ላይ ጠፋ፡፡ ትልቅ የአገር
ቅርስ የጠፋ ያህል ነበር አንጀቴ ቁርጥ ያለው፡፡ ደምና አጥንት የተከፈለለት የአገር ድንበር
የተቆረሰ ያህል ነበር ውስጤ በቁጭት የተንገበገበው፡፡

በእርግጥ ይሄ ሱሪ መታጠብ ብዛት የልጅነት ጥቁር ቀለሙ ተገፍፎ ግራጫ መሆን ጀምሮ
ነበር፡፡ ኧረ እንደውም እንደ ሰው ፀጉር በስተርጅና ነጫጭ ጭረት ጣል ጣል ያደረገበት ሱሪ
ነበር፡፡ ቢሆንም እርጅናው ከሱሪው ህያው ዋጋ ላይ ሽራፊ ሳንቲም ሊቀንስ አይቻለውም፡፡
እርጅና የማያደበዝዘው እውነት፣ የዘመን ብዛት የማያጠፋው ሃቅ አለና፤ የዛ እውነት ማህደር
ነው የተወሰደው፡፡

የፍቅርተ ሱሪ ጠፋ ማለት የመንደራችን ባንዲራ ጠፋ እንደማለት ነው፡፡ ይሄ ሱሪ ተራ ሱሪ ብቻ አልነበረም፤ የማንነት መቋጠሪያ ጨርቅ፣ የተገፉ ድሆች እንባ ማበሻ መሃረም፣ የፍቅር
መክተቻ ከረጢት ነበር፡፡ ምን ያደርጋል ! ታጥቦ ከተሰጣበት ገመድ ላይ ጠፋ ፡፡

አንዳንዱ የደላው መንደርተኛ የፍቅርተ ሱሪ መጥፋቱን ሲሰማ “ይሄ ሁሉ ላይ ታች ማለት ለአንድ
አሮጌ ሱሪ ነው ?” እያለ ወደየ ጉዳዩ ይጣደፋል፡፡ “በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት” ቢባልም
ቅሉ እንዴት ሰው በራሱ ቁስል እንጨት ይሰድዳል? ስለፍቅርተ ሱሪ የማይመለከተው ማነው?

እኔ በበኩሌ የፍቅርተ ሱሪ ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ባይ ነኝ፡፡ ስንለው ስንጮኸው የኖርነው ቃል ነበር የፍቅርተ ሱሪ! አብሮን የኖረ ቃል ጨርቅ ለብሶ የተከሰተው በፍቅርተ ሱሪ ነበር፡፡ ድንገት የቀኝ እጄን ስመለከተው ሁለት ጣቶቼን ከቦታቸው ላይ ባጣቸው እንኳን የዚህን ያህል የምደነግጥ አይመስለኝም፡፡ እዚህ መዲናችን ውስጥ ያለው የአፍሪካ ህብረት ሕንፃ ድንገት ከስሩ ተነቅሎ የደረሰበት ጠፋ ሲባል የፍቅርተን ሱሪ ያህል አያስደነግጠኝም፤ ኧረ ፍቅርተ ራሷ ብትጠፋ የሱሪዋን ያህል
አታስደነግጠኝም፡፡ ስለዚህ ሱሪ የተዳፈነ ተስፋ፣ የተኮላሸ ፍቅር አለና ሱሪው ሱሪ ብቻ አልነበረም፡፡

ሱሪው የጠፋ ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ስምንት ሰዓት አካባቢ ከምማርበት ኮሌጅ ስመለስ እማማ አመለወርቅ በራቸው ስር ሁልጊዜ የሚቀመጡባት ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው አገኘኋቸው ዓይናቸው ቡዝዝ ብሎ በሀሳብ በመመሰጣቸው እስካናግራቸው ድረስ አጠገባቸው መድረሴንም
አላዩም ነበር፡፡ ለወትሮው እዚህች ድንጋይ መቀመጫ ላይ የሚቀመጡት እጃቸው አጠር ብላ
ለዕለት ቡና ብር ቢጤ ሲቸግራቸው ነበር፡፡ የድንጋይ ወንበሯ የመተከዣ መድረካቸው ናት::

“ማዘር ምነው ሰላም አይደሉም እንዴ?” አልኳቸው፤

ቀጥ ብለው እንባ ባኳተሩ ዐይኖቻቸው ተመለከቱኝና ሳግ ተናነቀው አሳዛኝ ድምፅ ፣ “የፍቅርን ሱሪ ወሰዱባት አብርሽ!” አሉኝ፤ ሊያናግሩኝ ቀና ሲሉ እያለቀሱ እንደቆዩ ፊታቸው ላይ ዳናውን የተወ እንባቸው ይናገራል፡፡

“እነማን ናቸው የወሰዱት?” አልኳቸው የሰማሁትን ባለማመን፤ ቅስም ከሚሰብር ዜና ኋላ
የተከሰተ የጅል የሚመስል ጥያቄ፡፡

“ምናውቄ ብለህ አብርሽ ! ከዚህ ከተሰጣበት ገመድ ላይ አንስተው ወሰዱት” አሉና እንባቸውን
ዘረገፉት፡፡ ድህነት እንደ ሸንኮራ መጥጦ ካደረቀው ሰውነት ይሄን ያህል እንባ ይወጣል ብዬ
አላሰብኩም ነበር፡፡ ሕይወት ምንጊዜም አዲስ እንባ አላት፡፡ከእንባቸው የበለጠ ፊታቸው ላይ
ያረበበው ሐዘንና ምሬት ያሳዝን ነበር፡፡አንጋጥጬ የልብስ ማስጫ ገመዱን ተመለከትኩት፡፡
ወዲህ የኤሌክትሪክ ምሰሶ ላይ ወዲያ ደግሞ የአንዲት ጎረቤት የቤት ጣራ ማገር ላይ የተወጠረው ገመድ የተወረረ ከተማ መስሏል፡፡ ባንዲራውን እንዳወረዱበት የሰንደቅ ምሰሶ ትከሻው ቀሏል፡፡ ባዶ !! ለፍቅርተ፣ ለእኔ፣ ለእማማ ዓመለ፣ ለመንደሩና ለአገሩ ባዶነትን ትቶልን የሄደው ማነው?

ይሄ ገመድ ባዶውን ውሎ አያውቅም ነበር፡፡ ቢጠፋ ቢጠፋ የጉግሳ አውራ ጣቱ የተሸነቆረ
ካልሲ ወይም አሁን የጠፋው የፍቅርተ ሱሪ ተሰጥቶበት ነበር የሚውለው፡፡ የፍቅርተ ሱሪና
የጉግሳ ካልሲ ሁልጊዜም ገመዱ ላይ ጎን ለጎን ተሰጥተው ስለማያቸው የልብ ወዳጆች ይመስሉኝ ነበር ፡፡የፍቅርተ ሱሪ ከፍ ያሉት ንቀውት ዝቅ ብሎ የካልሲ ጓደኛ የሆነ፡፡ ካልሲውም ቢጤዎቹ ንቀውት ቀን ከገፋው ሱሪ ጋር የዋለ ዓይነት፡፡

አንጋጥጬ ስመለከት ከገመዱ በላይ ጥርት ያለው ሰማይ ተዘርግቷል፡፡ የፍቅርተን ሱሪ የወሰዱት ሌቦች ለወትሮው ሰማዩ ላይ የማይጠፋውን ደመና የወሰዱት ይመስል ነበር፡፡ ሰማዩ ባዶ! የልብስ ማስጫው ገመድ ባዶ!! አይ አይ ሰማዩ እንኳን ባዶ አልነበረም፡፡ ነግቶ የረፈደባት የምትመስል ግማሽ ጨረቃ ትታያለች፡፡ የሱሪ ሌባው ግማሿን ጨረቃ ሸርፎ የወሰዳት ይመስል፡፡
ቆይ ግን ሱሪውን የወሰደው ሌባ ከሆነ ሌባውን ምን ነካው? እንዴት የፍቅርተን ሱሪ ይወስዳል? እሺ
ነፋስም ከሆነ ንፋሱን ምን ነካው ? አቧራ ያስነሳ፣ የቤት ጣራ ይገነጣጥል ቢፈልግ ! ያንን ከሰፈራችን ወደታች ያለውን የአድባር ዛፍ ከስሩ ገርስሶ ይጣለው ! ግን እንዴት የፍቅርተን አንድ ለእናቱ የሆነ ሱሪ ይወስዳል ? ምን ቁርጥ አድርጎት የመንደራችንን ባንዲራ ይደፍራል ? በሌባው ተቆጣሁ
በነፋሱ ተቆጣሁ ፡፡ በፈጣሪም ተቆጣሁ :: መምሬ ልሳኑ ታዲያ (የእማማ አመለ ንስሃ አባት)
የሱሪውን መጥፋት ሲሰሙ፣ እማማ አመለን ለማፅናናት ብለው ይሁን አልያም አምነውበት እንጃ
ብቻ ጥቅስ አጣቀሱ፤ “ላለው ይጨመርለታል፣ ከሌለው ግን ያለውም ይወሰድበታል ወለተ ኪዳን አይዞሽ” በዚህ ማፅናኛቸው በጣም ተበሳጨሁ፤ እንደውም በፈጣሪ ላይ የተሰማኝ ቅሬታ ተባባሰ፡፡

ፈጣሪ የሌባው እጅ ወደ ፍቅርተ ሱሪ ሲዘረጋ እንደ ደረቅ እንጨት ድርቅ አድርጎ ማስቀረት ይችል ነበር፡፡ ነፋስና ማዕበልን የሚገስጽ ፈጣሪ እንዴት ዝም አለ ? እሳት ከሰማይ የሚያወርድ አምላክ ከዚህ በላይ በደል፣ ከዚህ በላይ ግፍ ምን አለና ታገሰ ? የፍቅርተን ሱሪ የወሰደው ንፋስ ከሆነም መገሰጽ ይችል ነበር፣ ስለምን ዝም አለ ? እንኳን አጋጣሚውን አገኘሁ እንጂ ፈጣሪ ጋርማ በፍቅርተ ጉዳይ ብዙ ጥያቄ አለኝ! ብዙ ! ሲጀመር ፍቅርተን ስለምን እንዲህ አድርጎ ፈጠራት…እኮ ለምን !? ለእሱስ ለስሙ ጥሩ ነው ??

“የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው” ይሉት ብሂል ስጋ ለብሶ የተገለጠው እማማ አመለ ቤት ነበር፡፡እማማ አመለ በመልክ ይሁን በባህሪ የማይገናኙ፣ ከፆታቸው በቀር አንድ የሚያደርጋቸው አንድ
ነገር እንኳን ፈልጎ ማግኘት የሚከብድ ሁለት ሴት ልጆች ያሏቸው፣ እድሜያቸው የገፋ ደግ ሴት ነበሩ ፡፡ ከሁለት ክፍል ቤታቸው አንዷን ተከራይቼ ለአራት ዓመታት ቤታቸው ውስጥ ኖሬያለሁ፡፡
👍263🥰2🔥1
ለስሙ ሁለት ክፍል ተባለ እንጂ አብረን በደባልነት እንደኖርን ነበር የሚቆጠረው፡፡ እማማ አመለ
ከሁለቱ ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩበትን ከፍል ረግጬ የእኔ ክፍል ወደሆነችው ጓዳ አልፋለሁ፤
አንዳንዴ ታዲያ ወደ እኔ ክፍል ለማለፍ የተደረደሩትን እቃዎች መዝለል ይኖርብኛል፡፡ በተለይ
ቡና ከቀራረበ ረከቦቱን መራመድ ግድ ነበር፡፡ የእኔ ክፍል ከእነ እማማ አመለ ክፍል የሚለየው
በአንድ ስስ መጋረጃ ነበር :: እኔ ቤት ሆኖ የእነማማ አመለን ቤት አጠቃላይ እንቅስቃሴ
መመልከት ይቻላል ፤ ድንበራችን ስስ መጋረጃ ነበርና፡፡

ፍቅርተ የእማማ አመለ ሁለተኛ ልጅ ናት፡፡ ፍቅርን ጨምሮ ሁሉንም ነገር የነሳት፣ የአርባ ቀን እድሏ በየቀኑ አርባ የሰቆቃ ጅራፍ የሚያሳርፍባት መልከጥፉ ወጣት ናት፡፡ ልቅም ያለች መልከ
ጥፉ ነበረች፡፡ ቁንጅና እንደተመልካቹ ነው ቢባልም ፍቅርተን “ቆንጆ” የሚል ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም፤ ራሷን ፍቅርተን ጨምሮ፡፡

ፍቅርተን ድንገት የተመለከታት ሰው ድንገት የተከሰተ ሰይጣን ፊት የቆመ ሊመስለው ይችላል፡፡
መጀመሪያ ግማሽ ፊቷን የሞላ የሚመስለው ትልልቅ እና የተፍረከረከ ከንፈሯ ድራማ ለመስራት የተጠለቀ ጭምብል እንጂ በእርግጥም የአንዲት የአስራ ስምንት ዓመት ወጣት ከንፈር አይመስልም፣ከላይኛው ከንፈሯ የተረፈው ቦታ ላይ ለምልከት የተቀመጠው አፍንጫዋ ወደላይ ቀና ብሎ
ሰፋፊ ሸንቁሮቹ ፊት ለፊት የቆመ ተመልካች ላይ የተደገኑ መንታ የከባድ መሳሪያ አፈሙዞች .
ይመስላሉ፡፡የመርፌ ቀዳዳ የሚያካክሉ ዓይኖቿ ሁሌም ጉሽርጥ መስለው እንደቀሉ ናቸው፡፡ የፀጉሯ ነገር አይነሳ ! የፍቅርተ ፀጉር ቀለም የለውም ፤ የማለዳ ጠል የሰፈረበት የሜዳ ላይ ችፍርግ ! ስታበጥረው አሰቃቂ ፉጨት የመሰለ ድምፅ ይወጣል፡፡

ይህን ሁሉ ተፈጥሯዊ በደል የተሸከመችው ፍቅርተ በዚህ በቃሽ ቢላት ጥሩ ነበር፤ ከቁመቷም ክፉኛ በድሏታል፡፡ በእጥረቷ ላይ ሲበዛ ትልልቅ ጡቶቿና አጠቃላይ የሰውነቷ ውፍረት ተዳምሮ በሰቆቃ እንድትኖር ፈርዶባታል፡፡ በእርግጥ ሰዎች እግዜር የሰጣትን በፀጋ መቀበልና መኖር ነው ለምን ትሳቀቃለች?” የሚል ጉንጭ አልፋ ንግግር ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ግን እንደባለቤቷ ሰቆቃው ሊገባቸው አይችልም፡፡ “ምክርና ቡጢ ለሰጪው ቀላል ነው” እንዲሉ ፡፡ የልብሳቸው መዛነፍ፣ የከንፈር ቀለማቸው አለመስተካከል የሚያስጨንቃቸው ቆነጃጅት “እግዜር የሰጠውን ይሏታል፤ ይሄን ሁሉ ነገር የተሸከመችውን ፍቅርተን !

እንግዲህ የእናት ሆድ ሲዥጎረጎር ፋና ተወለደች ፤ “ያየሽ ይውደድሽ?” የሚል ምርቃት አብሯት የተወለደ፡፡ ከባህሪውም ከቁንጅናውም አትረፍርፎ የሰጣት ውብ የአስራ ዘጠኝ ዓመት ወጣት
ነበረች መልዓክ ! ፋናን ዓይኗን ትክ ብዬ ማየት አልችልም፡፡ ርዳለሁ እፈራታለሁ፡፡ቁንጅናዋ ከተለመደው የሴት ልጅ ቁንጅና ያልፋል፡፡

በዕድሜ ከእኔ ብታንስም ሁልጊዜም አጠገቧ ስቆም ትገዝፍብኛለች፡፡ ፋና ለእኔ ቆንጆ ብቻ አልነበረችም፤ የቁንጅና ማነፃፀሪያ ሚዛን የለም እንጂ፡፡ ልክ የሌለው ቁንጅና፣ ቃል የማይገልፀው መስህብ ነበራት፡፡ የፊቷ ቆዳ ነፋስ እንደቆለለው የምድረበዳ አሸዋ ለስላሳ ነበር፡፡ እንዲሁ በዓይን ሊመለከቷት በእጅ የዳሰሷት ያህል ልስላሴዋ ይሰማል፡፡ ዓይኖቿ ልብን የሚያስጨንቁ ነገሮች ናቸው፡፡ ፋና በልብ ውስጥ ለዘላለሙ የሚታተም ግን ቃል አውጥተው የማይናገሩት ቁንጅና የነበራት ልጅ ነበረች፤ ህያው ፈተና !

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ (ኮሜርስ) ተማሪ ነበርኩ፡፡ ለአንድ የክፍለ ሐገር
ልጅ ይቅርና አዲስ አበባ ተወልደው ላደጉ ልጆችም ቢሆን ንግድ ስራ ኮሌጅ መማር ከባድ
ነበር፤ የመጀመሪያው ችግር ኮሌጁ ለተመደቡ ተማሪዎች የመኝታም ይሁን የምግብ አገልግሎት ስለማይሰጥ በየወሩ ለተማሪዎች እዚህ ግባ የማይባል የኪስ ገንዘብ እየከፈለ ከግቢ ውጭ እየኖሩ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ያደርጋል፡፡ ተማሪው በአካባቢው ቤት አፈላልጎ በመከራየት ትምህርቱን ይቀጥላል፡፡

ገና ከጅምሩ እዚህ ኮሌጅ መመደቤን ስሰማ አልቅስ አልቅስ እያለኝ ነበር ከክፍለ ሐገር ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት፡፡ የኮሌጁን ተማሪዎች የማሰቃየት ጀብዱ በሩቁ ሰምቻለሁ፡፡ በዛ ላይ አዲስ አበባ የመጣሁት፡፡
አዲስ ስለነበርኩና የማውቀው ሰው ስላልነበረኝ እንኳን እየዞርኩ ቤት መፈለግ ቀርቶ አምስት ርምጃ
ብራመድ ተመልሼ አልጋ የያዝኩበትን ሆቴል የማገኘው አይመስለኝም ነበር፡፡ በዚህ ግራ በተጋባሁበት ወቅት ነበር ባረፍኩበት ሆቴል አልጋ አንጣፊ በኩል የእማማ አመለን ቤት ለመከራየት የበቃሁት ::
“እንደው መንደሩም ቤቱም ይሆንህ አይመስለኝም እንጂ የሚሆንህ ከሆነ አንዲት ጎረቤታችን አንዲት ክፍል ቤት አለቻቸው” አለችኝ የሆቴሉ አልጋ አንጣፊ፡፡ ቤቱን ልናይ ጎተራ አሁን ቀለበት መንገዱ የተሰራበትን ወደቀኝ ትተን ወሎ ሰፈር የሚባለው አካባቢ ሄድን፤ በመንገዱ ግራና ቀኝ የተሰደሩት ትላልቅና ውብ ሕንፃዎች ጀርባ ውስጥ ለውስጥ ሂደን እዚህ አካባቢ ይኖራል ተብሎ የማይታሰብ ጭርንቁስ መንደር ውስጥ ገባን፡፡ እርስ በርስ ተደጋግፈው የቆሙት ቤቶች
ግድግዳ ላይ ተለጥፈው የተሰሩ የውሻ ቤቶች እንጂ የሰው ቤት አይመስሉም፡፡ “ጨረቃ ቤት”
እንደሚባሉ በኋላ ሰማሁ፡፡ አፈር አፈር የመሰሉ ሕፃናት መንደሩ ውስጥ ውር ውር ይላሉ፡፡
ትንሽ ተጉዘን ካገኘናቸው መደዳ ቤቶች ያሉበት ቦታ ስንደርስ በአንዱ በር ላይ ቆምን፡፡ ፍቅርተ
እና እናቷ እማማ አመለ ነበሩ ያናገሩኝ፡፡

እውነቱን ለመናገር ፍቅርተን ሳያት ላማትብ ቃጥቶኝ ነበር፡፡ በስመአብ በ…፡፡ ድንገት ፍቅርተን
የተመለከተ ሰው ሊሰማው የሚችለው ነገር ቢኖር ይሄው ነው፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አዲስ አበባ ውስጥ የዚህ ዓይነት ቤትም፣ የዚህች ዓይነት ልጅም ይኖራሉ ብዬ አስቤውም አልሜውም አላውቅም፡፡እንደውም ያመጣኝ አውቶብስ በትክክል አዲስ አበባ እንደጣለኝ ተጠራጠርኩ፡፡የእኔ ቤተሰቦች መካከለኛ ኑሮ የሚኖሩ የክፍለ ሐገር ሰዎች ናቸው፡፡ ያደግኩበት ቤትና ግቢ ግን በስፋትም በንፅህናም ከዚህ “ቤት” ጋር ሲወዳደር…ኧረ አይወዳደርም፡፡ ወይ አዲስ አበባ !!

“ለጊዜው እዚህ ቤት አረፍ ብዬ አገሩንና ሰዉን ስለምደው የተሻለ ቤት እፈልጋለሁ” ብዬ የአዲስ
አበባ የቤት ችግር መፈናፈኛ ያሳጣኝ እኔ ጓዳዋን በሶስት መቶ ብር ለመከራየት ተስማማሁ፡፡

ከሰዓት በኋላ አንዲት የስፖንጅ ፍራሽ ገዝቼ ካረፍኩበት ሆቴል ሻንጣዬን በመያዝ ወደተከራየሁት
“ቤት” ስመለስ ያጋጠመኝ ነገር ባንድ ራስ ሁለት አስወራኝ፡፡ “ያመጣኝ አውቶብስ አዲስ አበባ
ነው ወይስ ገነት ያወረደኝ?!”፤ ፋና በር ላይ ቆማ ነበር፡፡ ፋና የእኔ የማለዳ ጀምበር…! ፋና
የእኔ ደግ ፊት ! ሩህሩህ ፊት፣ የተከሰተች መልአክ…!
ሻንጣዬን ልትቀበለኝ እጇን ዘረጋች፡፡ ለስላሳ ጣቶቿ የእጄን መዳፍ ነኩኝ! የከተማው የኤሌክትሪክ ኃይል ሁሉ በፋና እጅ በኩል አድርጎ ልቤን ቀጥ እስኪያደርገው ነዘረኝ፡፡ አዲስ አበባ በጨለማ ተውጣ በጥቁር አዲስ አበባ ላይ ፋና የምትባል ፀሐይ ፍንትው ብላ ወጣች ! እነሆ ይህቻትና አዲስ አበባ የልዩነት አገር… ሁሉን ቻይ አዲስ አበባ! የሁሉ መኖሪያ አዲስ አበባ! ከትላልቆቹ ሕንፃዎች ኋላ ሲኦልና ገነት በፍቅር በመተሳሰብና በአንድነት ተቃቅፈው የሚኖሩባት አዲስአበባ! የአዲስ አበባ ልጅ የሆንኩ መሰለኝ፤ አዲስ አበባ ተወልጄ ያደግኩ መሰለኝ፡፡
👍20
ፋና ፋና ፋና ፋና ያለችበት ቤት ውስጥ ልኖር ነው፡፡....
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ እግዜር ይስጠው፤ አካውንቲንግ ላስተምርህ ብሎ
ጠርቶ፣ ከቁጥሮች ክምር ውስጥ እውነትን ማውጣት ላስተምርህ ብሎ ጠርቶ፣ ድህነት ከቀበረው
መንደር ውስጥ የወርቅ ፍልቃቂ የመሰለች ልጅ እንዳወጣ የተላክኩ መልአክ አደረገኝ፡፡ እኔኮ ቆንጆ ሴት ሲያዩ የሚደነግጡት የፊልም አክተሮች ብቻ ይመስሉኝ ነበር፡፡ ፈዘዝኩ ! ፋናን ስመለከት ፈዘዝኩ፡፡
ከዚች ቤት እንኳን ራሴ ልወጣ ውጣም ቢሉኝ እግሬን እንደማላነሳ የገባኝ ገና ፋናን እንዳየኋት ነበር፡፡ “ለልማት መንደሩ ሊፈርስ ነው መድረሻህን ፈልግ” ቢሉኝም “አብራችሁ አፍርሱኝ ከማለት ወደኋላ እንደማልል የገባኝ የፋና ጣቶች ሲነኩኝ ነው ፡፡ማን አለ ለርስቱ የማይሞት!
ፋና እኮ ርስት ናት፤ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ የተዘረጋች
እግዚዮ ! ፋናን እዚህ መንደር ውስጥ ምን እግር ጣላት ?! መቼም ከዚህ ቤት በሆነ መንገድ
አውጥተው ቢጥሉኝ አርቀው እንደጣሉት ውሻ፣ ጫካ ወስደው እንደወረወሩት ድመት የፋናን
ኮቴ እያነፈነፍኩ ተመልሼ እዚሁ መገኘቴ አይቀርም፡፡

ማንም ችኩል ቢለኝ ግድ አይሰጠኝም፡፡ ፋናን ገና ስመለከታት ልቤ ውስጥ የማይናወጥ የፍቅር ሐውልት ቆሟል፡፡ ማንም ብትሆን ግድ አይሰጠኝም፤ ቤት ውስጥ ምንሽር የታጠቀ፣ ጓንዴ ትራሱ ስር
ያስተኛ ባሏ ቢቀመጥ፣ ሰባት ልጆቿ “እማ እማ!” እያሉ የሚንጫጩ ሴት ብትሆንም ግድ የለኝም፡፡ፋናን አየኋት፣ ወደድኳት በቃ!! ይሄ ሁሉ ነገር የሆነው አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ እና ይሄን ሁሉ ሴኮንድ፣ ዘላለም የሚያህል ደቂቃ ፋናን አይቼ ባፈቅራት “ቸኮልክ” የሚለኝ ማነው?!......

ይቀጥላል
👍18
ማንኛውንም አይነት ከ 3 k (3000) ተከታይ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ድረስ ያላችሁን ቻናል ለመሸጥ ካሰባችሁ በ @buchula36 ላይ አውሩኝ አመሰግናለው።
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ጥሪ
የሳጥናኤል ኮከብ

የሴሰኝነት ጥሪ
ሲልቪ

እኔና ሲልቪ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ፓሪስ ተጓዝን። በሷ መሪነት
ከፓሪስ ጋር ይበልጥ ተዋወቅኩ። በሲልቪ አስተማሪነት ከቅናት ጋር
ይበልጥ ተዋወቅኩ፡፡ ራሴንም ይበልጥ አወቅኩ ፓሪስ በገባን በሁለት ቀናችን፣ እንደ ልማዷ አንድ ደስ የሚላት ጎረምሳ አየችና አጣድፋ ወደ ሆቴላችን ወሰደችኝ፡፡ መብራቱን አጠፋች፡፡ እንደ “ልማዷ በኔ ገላ ጎረምሳውን ተደሰተችበት፣
አቃሰተች፣ ነገሩ ሊያልቅ ሲል ጮኸች። ተኛን፡፡ ያን ጊዜ እኔም
እሷም አላወቅነውም እንጂ፣ ከኔ ጋር እንዲህ ስትሆንና ስታደርግ
የመጨረሻ ጊዜዋ ነበር ነቃሁ። ጭለማ ውስጥ ነኝ። ምን እንደቀሰቀሰኝ እንጃ:: ከጎኔ
ተንቀሳቀሰች፡፡ በእንቅልፍ ልቧ «“Non! Non! Non!" እያለች
እየተጨነቀች ተፈራገጠች። በጣም የሚያስፈራ ህልም መሆን
አለበት። እየቀሰቀስኳት
«አይዞሽ አይዞሽ፣ ከኔ ጋር ነሽ» አልኳት ራሷን እየደባበስኩ።
በሀይል እየተነፈሰች ተጠጋችኝና
«አንድ ነገር አስደነገጠኝ፡፡ መብራቱን አብራልኝ አለችኝ
አበራሁት። አይኔ ብርሀኑን ከለመደው በኋላ ታየችኝ፡፡ ጥቁር
ረዣዥም ፀጉሯ ጉንጭና አንገቷ ላይ ተጠምጥሟል፣ተለጣጥፏል። ግምባሯ ላይ ላቡ ያብለጨልጫል፡ ጠረግኩላት፣
ፀጉሯን ወደ ኋላዋ ሰበሰብኩሳት
ውሀ» አለችኝ፡፡ ራስጌ ካለው ጠርሙስ አጠጣሁዋት
«ደህና ነሽ?» ስላት፣ ሳቅ ብላ
«አጥፋው» አለችኝ። አጠፋሁት፣ አቀፍኳት
«ቅዠት ነበር፡፡ ኮሙኒስቶች የኢራንን ሻህ መንገድ ላይ
አግኝተውት በጩቤ ሲገድሉት አየሁ፡፡ በኋላ ግን ባህራም ሆነ።
«አይዞሽ ነቅተሻል፡ አይዞሽ» እያልኩ እጄን ጀርባዋ ላይ
ሳንሸራትት ትንሽ ከቆየሁ በኋላ
Tu es plutôt une mére Française qu' un sauvage Africain"
አለችኝ («ፈረንሳዊት እናት ነህ እንጂ አፍሪካዊ አረመኔ
አይደለህም ኮ») ሁለታችንም በሳቅ መንፈርፈር ጀመርን። ታድያ'ኮ ያን ያህል የሚያስቅ አልነበረም፤ ያን ጊዜ መሳቅ ስላስፈለገን ነው
እንጂ፡፡ እየተጠመጠመችብኝ፣ ደስታ ባፈነው ድምፅ
«መኖር እንዴት ጥሩ ነው!» አለችኝ
ካንቺ ጋር ሲሆኑማ!»
የኔ ካስትሮ፣ ይልቅ ካንተ ጋር ሲሆኑ ነው እንጂ፡፡»
እቅፍ አድርጌ ጉንጯን ሳምኳት። በጭለማው ላዬ ላይ ወጣች፡
እንደምትወደው ጀርባዋንና አንገቷን እያሻሸሁ
«ምን ይሰማሻል?» አልኳት
እንደምትወደኝ ይሰማኛል»
«አውቀሻል»
«የተለየ ስጦታህ ምን እንደሆነ ልንገርህ?»
«ምንድነው?»
«የሰላም
ተሰጥዎ ነው ያለህ፡፡ ካንተ ጋር ስሆን ሰላም ይሰማኛል። ካንተ ጋር ስሆን ፀፀትና ንስሀ አያስፈልገኝም፡፡»
«ፀፀትና ንስሀ?»
በተለወጠ ድምፅ
«ቅድም ስለበደልኩህ ገላህን ለጋራ ጥቅማችን ሳይሆን ለግል
ደስታዬ ስላዋልኩት»
ፀፀት ሊጀምራት እንደሆነ ገባኝ፡ አሳዘነችኝ
«የኔ ቆንጆ፡ ቂል አትሁኚ። አንቺ ገላሽን እንድደሰትበት
ትሰጪኝ የለ?» አልኳት
«አዎን»
«ታድያ እኔ ገላዬን እንድትደሰቺበት ብሰጥሽ ምናለበት?»
«ከዚያ ይለያላ»
«አስር ጊዜ ልዩ ይሁን። በናንተ አገር ፍቅር ማለት ምንድነው?
መስጠትና መቀበል አይደለም?»
«ነው»
«ታድያ ገላዬን ብሰጥሽና ተቀብለሽ ብትደሰቺበት ምን ፀፀት
ያስፈልገዋል? እኛ አገር መስጠት ማለት መስጠት ነው። ገላዬን
ከሰጠሁሽ የራስሽ ሆነ ማለት ነው፡፡ የራስሽ ከሆነ ደሞ የፈለግሽውን ልታረጊበት ትችያለሽ ማለት ነው።
«እንደሱ ሆኖ ነው እሚታይህ?»
«ነው እንጂ»
«እንዴት ጥሩ ነህ! እኔ ግን እንዴት መጥፎ ነኝ!»
እንዴት?
«ውሸታም ነኛ!»
«ውሸታም?»
«አዎን፡፡ ለምሳሌ፣ ያን ጊዜ ስትጠይቀኝ የሌላ ሰው ገላ
እያቀፍሽ በሰውየው ገላ ከኔ ጋር ተኝተሽ ታውቂያለሽ ወይ?”
አላልከኝም? እኔ ምን አልኩህ? »
«በጭራሽ አድርጌው አላውቅም አልሽኝ»
«አዎን። ግን ውሽቴን ነበር። ላንተ
መዋሸቴ በጣም ይቆጨኛል፡፡ ስለዚህ አሁን አንድ ውል እንግባ። አንተ ላለፈው ውሸቴ ይቅርታ አድርግልኝ። እኔ ደሞ ለወደፊቱ ሁልጊዜ እውነቱን እነግርሀለሁ፡፡»
«ስሚኝ የኔ ቆንጆ:: ለኔ ምንም ነገር መንገር የለብሽም፡፡»
“አውቃለሁ። ለዚህ ነው ልነግርህ የምፈልገው:: ከዚያም በላይ፣
አንተ ልትረዳኝ ትችል ይሆናል፡፡ እውነቱን ልንገርህ?»
«እሺ»
«አትጠላኝም?»
«በጭራሽ አልጠላሽም»
እሺ፡፡ ያኔ ታስታውሳለህ?»
የኔ ሻህራዝድ የኔ ቆንጆ፣ እንዴት ልረሳው እችላለሁ?»
“ተመስገንን ፍለጋ የምመጣ ይመስልህ ነበር፡፡ እኔ ግን አንተን
ለማግኘት ነበር የምመጣው፡፡ ሳይህ በጣም ደስ ትለኝ ነበር።
ካስትሮን ትመስለኝ ነበር። ስንቀልድ ስንስቅ ጥርስህን አፍህን ሳየው
አንቀህ እንድትስመኝ እመኝ ነበር፡፡ ታድያ አንተ እምቢ አልክ።
ስለዚህ ካንተ ስለይ፡ ተመስገን ጋ እሄድና አይኔን ጨፍኜ አንተን
እያሰብኩ አቅፈው ነበር፡፡»
«ያውቅ ነበር?»
«ምስኪን ተመስገን! እንዴት አርጎ ይወቅ?»
እንጃ፣ ነግረሽው ሊያውቅ ይችላል ምናልባት?»
«እንዲህ አይነት ነገር እንዴት ሊገባው ይችላል?»
»እሺ ቀጥዪ»
«ትጠላኛለህ»
«እንግዲህ ቂል አትሁኚ፡፡ በኔ የመጣ ስለምንም አለመግባባት
አትስጊ። ንገሪኝ፡፡»
«እንዴት አርጌ ልንገርህ?»
«እንደመጣልሽ»
ከነገርኩህ በኋላ ምን እንደሚመስልህ ትነግረኝ እንደሆን»
“Parole d'honneur?'' (የከበሬታ ቃልህን ሰጥተሃል?»)
“Parole d'honneur” («የከበሬታ ቃሌን ሰጥቻለሁ»)
«እሺ። እንዲህ ነው:: አየህ፣ ካንተ ጋር ግብረ ስጋ በጣም
ደስ ይለኛል። ደጋግሜ ነግሬሀለሁ፡፡ ያንተን ግማሽ እንኳ ያህል እኔን ማስደሰት የቻለበት የለም፡፡ ብቻ ምን ልበልህ፣ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን
በሽታዬ ይመጣል። ሲመጣ ደሞ መከላከያ የለኝም። ገባህ?»
«ገና አልገባኝም
«እንዳልኩህ፤ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን በሽታዬ ይመጣል፡፡ በጣም
ታምረኛለህ፣ በሀይል እመኝሀለሁ
«ታድያ አለሁልሽ አይደለም?»
“እንደሱ አይደለማ የምታምረኝ»
ልቤ መምታት እየጀመረ
“ታድያ እንዴት ነው?» አልኳት፣ ጐሮሮዬም መድረቅ ጀምሯል
በሀይል ታምረኛለህ፣ ምኞቱ ያንገበግበኛል። ግን ስትተኛኝ
በገዛ ገላህ እንዳይሆን ያስፈልጋል። የሌላ ወንድ ገላ ተውሰህ፣ በሱ ገላ አንተ እንድትተኛኝ ፈልጋለሁ። እንደዚህ ያማርከኝ ጊዜ፣ ካንተ
ተለይቼ መሄድ ይኖርብኛል።»
«ወዴት?» ጉሮሮዬ ጨርሶ ደርቋል
“አንተን ፍለጋ፣ ሌላ ወንድ ፍለጋ»
«ታገኚዋለሽ?»
«ምን ይመስልሀል?» ጉሮሮዋ ውስጥ ወፍራም ተንኮለኛ ሳቅ
ተሰማኝ ቅናት ማለት ይሄ ይሆን እንዴ? ታድያ ንዴቱና ብስጭቱ
የታለ? እኔን የሚሰማኝ ጥልቅ የሆነ እሳት የሆነ የሚያቃጥል
ቅንዝር! እንደ ዛሬም አንገብግቦኝ አያውቅ! ተለይታኝ ስትሄድ፣
ወፍራም ዳሌዋን እያወዛወዘች፣ ውብ ኣይኖቿን ክፍት ክድን
እያረገች፣ በፍትወተ ስጋ እስኪፈነዱ ብልታቸውን በሚያሳብጠው ፈገግታዋ የመረጠችውን እድለኛ ወንድ ስትጣራ ታየችኝ። ስጋዬ
አላስታግስ አላስችል አለኝ፣ እላዬ ላይ እንደተጋደመች በጥድፊያ
ገለበጥኳትና ጭኖቿን ፈልቅቄ ስገባ፣ በሙዚቃዊ ፈረንሳይኛዋ፣
በቅንዝር ድምፅዋ
“Ah. cheri, comme tu es sauvage! C'est delicieux"
👍20
አቀፈችኝ፡፡ (አንተዬ፣ እንዴት አውሬ ሆነሀል! ደስ ሲል!)
ዝም ጭጭ አልኩ፣ እውነትም አውሬ ሆኜ ነበር
አይ ሲልቪ! ለኔ እንዴት ደግ ነበረች! ስታባብለኝና ስታፅናናኝ
እንደ ህልም መስሎ ይታወቀኝ ነበር፡፡ ጭንቅላቴንና ትከሻዪን
እያሻሽች፣ በልዝብ ፈረንሳይኛዋ፣ በልስልስ ድምፅዋ እየደጋገመችልኝ
«አይዞህ የኔ ቆንጆ፡ ከኔ ጋር ነህ የኔ ፍቅር፤ አንተን ነው የምወደው
የኔ አበባ፣ አይዞህ ውደደኝ» ስትለኝ ይሰማኝ ነበር ..
በኋላ፣ እግሮቿ መሀል እንዳለሁ፣ ትንሽ ወደታች ገፋ አድርጋ ሆዶን አንተራሰችኝ፡፡ እጇ ጭንቅላቴን ሲያሻሽኝና የተንተራስኩት
ሆዷ ከትንፋሿ ጋር ከፍ ዝቅ ሲል፤ እሹሩሩ እንደምትለኝ የሚያጎናፅፍ፣ ሰፊ ጥልቅ የሆነ ሰላም እየተሰማኝ እንቅልፍ እያንሳፈፈ ወሰደኝ
ስነቃ ሲልቪ በውብ አይኖቿ ታየኛለች፤ አልጋው ጎን ተምበርክካ እጇን ከጉንጫ ጋር ታሻሻለች፡፡ መስኮቱ ተከፍቶ የፀደይ
ብርሀንና ነፋስ ይገባል። ውስጥ ውስጥ ውስጥ፣ ልቤ ልብ ውስጥ
ደስታው ሲመነጭ ተሰማኝ፡፡ እንደተምበረከከች እጄን ከጉንጫ ጋር እያተሻሽች
የመሄጃችን ሰአት ደርሷል ብዬ ነው የቀሰቀስኩህ፡፡ ቁርስ ይምጣልህ?» አለችኝ
«ይምጣልኝ፡፡ ለምንድነው የተምበረከክሽው?»
እኔ እንጃ። ተኝተህ ሳይህ እንዴት ታምራለህ! ፂምህን
ስትላጭ ለካ በጣም ቆንጆ ነህ!»
ተነስቼ ፊቴን ስታጠብ ፎጣውን አቀበለችኝ። ቁርስ መጥቶልን
ስንበላ ወተትና ቡናውን እሷ ቀዳችልኝ፤ ዳቦውን እሷ ቀባችልኝ።
ልብሴን ስለብስ አገዘችኝ፡፡ አይኖቿ ሲያዩኝ፣ የለመድኩት ብርሀናቸው ውስጥ አይቼው የማላውቅ ልስልስ ያለ አስተያየት ሆነብኝ
ልንወጣ ስንል፣ ጉንጯን ይዤ ወደ ታች እያየኋት
«ዛሬ ምን ሆነሻል?» አልኳት
«ምን ሆኛለሁ?»
«ለኔ ያደረብሽ ፍቅር ያደገብሽ የሰፋብሽ ይመስላል። ያለ
ልማዳችን ትንከባከቢኛለሽ።»
«ዛሬ በጭራሽ እንዳትለየኝ አደራህን። እሺ?»
«ምነው? ምን ሆነሻል?»
ቀና ብላ እያየች፣ እጆቿን ወገቤ ላይ እያሳረፈች
«ምንም አልሆንኩም፡፡ በጣም ወድጄሀለሁ። ካይኔ እንድትርቅ
አልፈልግም።»
“ምነው? ምንድነው?»
“ምንም፡፡ ወደድኩህ፡፡ ዛሬ ገና ነው ሰው መሆንህ የገባኝ»
«ከዛሬ በፊትስ?»
“እስከዛሬ ሰው ሆነህ ታይተኸኝ አታውቅም፡፡ ስለትምህርት ግድ
ያለህ፣ ስለገንዘብ ግድ የለህ፣ ጓደኛ የለህ፣ አትፈራ፣ አትበሳጭ
ብቻ ምን ልበልህ፡ ስለምንም ግድ የለህም፡፡ «La vie tu t'en fouts
perdament» («ስለ ኑሮ በጭራሽ ደንታ የለህም») ሁሉንም ሰው፣ሁሉንም ነገር፣ ከላይ ሆነህ ወደታች ነው የምታየው:: ምንም ነገር ሊያምበረከክህ አይችልም፡፡ ብቸኛ ከመሆንህ የተነሳ፣ የብረት ሰው ሊያሸንፍህ አይችልም፣ ማንም ሰው እጅ ሊያስነሳህ፣ ሊያለማምጥህ፣ሊያንበረክህ አይችልም ብቸኛ ከመሆንክ የተነሳ የብረት ሰው ነህ ማለት እስከዛሬ እንዲህ ሆነህ ነበር የምትታየኝ።
እንደምመስልሽ የብረት ሰው አይደለሁም፡ ተራ ደካማ ሰው
ነኝ፡ ፊሪ ነኝ፡ ልላት ፈለግኩ። ግን ጊዜው የመናገር ጊዜ
አልነበረም፣ የማዳመጥ ጊዜ ነበር፡፡ ንግግሯን እንድትቀጥል፣
ከሆነላትም የልቧን
እንዲወጣላት፣ ለራሴም
ምን እንደሚሰማት ለማወቅ እንድችል
«ዛሬስ እንዴት ሆኜ ታየሁሽ?» አልኳት
ትላንት ሌሊት ስታቅፈኝ ሰው ሆንክ፡ ለመጀመርያ ጊዜ ሰው
«ራስህን ረሳህ:: እኔን አምነኸኝ፣ ከኔ ጋር በመሆንህ ራስህን
መጠበቅ ስላላስፈለገህ፣ ራስህን ረሳኸው፡፡ ራስህን እጄ ውስጥ
አስገባህ፡፡ ማለቴ በላዬ መሆን ትተህ፣ ወደታች መጥተህ ከኔ እኩል ሆንክ፡ ከዚያም አልፈህ የባሰውን ወርደህ እኔ ካንተ በላይ እንድሆን ፈቀድክልኝ አመንከኝ፡፡ በናንተ አገር ቋንቋ እወድሻለሁ አልከኝ ባማርኛ አወራሁልሽ?» አልኳት፡ በጭራሽ አልታወቀኝም ነበር አዎን። ሳታውቅ ነው።
እወድሻለሁ ማለቴን እንዴት እወቅሽ?»
በድምፅህ፡፡ እንደዚያ ወደኸኝ አታውቅም፡፡ በቋንቋህ ሲሆን
ጊዜ፣ ሳታውቅ መሆኑ ሲታየኝ ጊዜ፣ በጣም ሰው ሆነህ አገኘሁህ።
ለመጀመርያ ጊዜ ፣ ፈፅመህ የኔ ሆንክ፡፡ እስካሁን የማንም ሆነህ
ስለማታውቅ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የኔ ስለሆንክ፣ ሀሴት ተሰማኝ።
በልቤ የኔ ነው! የኔ ነው! የራሴ ነው!' አልኩ፡፡ ዛሬ ጧት ደሞ
ዛሬ ጧት ደሞ?»
ተኝተህ ሳይህ እንዴት ታምራለህ! እንዴት ወጣት ነህ!
እንዴት ንፁህ ነህ! ያ ፊትህን የሚሸፍነው ፂምህ ተላጭቶ፡ እነዚያ ሁሉን ወደታች የሚያዩት አይኖችህ ተከድነው፣ ያ ሁሉን የሚንቅ አንጎልህ ተኝቶ ሳይህ፣ ጀግናው ጦረኛ አኪሌስ የጦር ትጥቁን አውልቆ ያለ አንዳች መከላከያ ተኝቶ እንደማየት ነበር፣ በፍቅር አይን ለምታይህ ሲልቪ፡፡ እና ታድያ፣ ሳይህ፣ እርጅና እያረሳሳዐእንደሚወስድህ፣ ሞት አድፍጦ አንድ ቀን ጉብ እንደሚልብህ አፈጠጠብኝ

«አንተ ይህን ሁሉ ሳትጠረጥር፣ ቆንጆ ራስህን ትራሱ ላይ
አሳርፈህ፣ ንፁህ እንቅልፍህን ትለጥጣለህ፡፡ በጭራሽ መከላከያ የሌለሀ ሆነህ ታየኸኝ። አሳዘንከኝ፡፡ አዘንኩልህና እምባዬ መጣ፡፡» ራሷን ደረቴ ላይ አንተራሰች፡፡ ጭንቅላቷን አቅፍ አደረግኩት። እንደዚህ
ቆመን ረዥም ጊዜ ቆየን፡፡ በኋላ፣ በቀስታ ቀና አድርጌ ሳያት፣
እምባዋ ይወርዳል። እየተጠጋችኝ፣
«ዛሬ እንዳትለየኝ አለችኝ
እቅፍ አደረግኳት። ብዙ ነገር ልነግራት ፈለግኩ። ግን የመናገር
ጊዜ አልነበረም፡፡ እንደተቃቀፍን እንቅልፍ አቀፈን ..

💫ይቀጥላል💫
👍26
#ከሰሀራ_በታች


#ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም


ማንም ችኩል ቢለኝ ግድ አይሰጠኝም፡፡ ፋናን ገና ስመለከታት ልቤ ውስጥ የማይናወጥ የፍቅር ሐውልት ቆሟል፡፡ ማንም ብትሆን ግድ አይሰጠኝም፤ ቤት ውስጥ ምንሽር የታጠቀ፣ ጓንዴ ትራሱ ስር
ያስተኛ ባሏ ቢቀመጥ፣ ሰባት ልጆቿ “እማ እማ!” እያሉ የሚንጫጩ ሴት ብትሆንም ግድ የለኝም፡፡ፋናን አየኋት፣ ወደድኳት በቃ!! ይሄ ሁሉ ነገር የሆነው አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ እና ይሄን ሁሉ ሴኮንድ፣ ዘላለም የሚያህል ደቂቃ ፋናን አይቼ ባፈቅራት “ቸኮልክ” የሚለኝ ማነው?!.


ቤተሰቦቼ በየወሩ የሚልኩልኝ ብር ከዚህ የተሻለ ቤት እንድከራይ የሚያስችለኝ ቢሆንም ፋና
የምትባል የእግር ብረት ተጠናውታኝ በየት በኩል ! ቤቱ ለአንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ምኑም
የሚመች አልነበረም፡፡ ከእኔ ክፍል ኋላ የታወቀ ጠላ ቤት ነበር፤ ጫጫታው፣ ሁካታው፣ ዘፈኑ፡
ፀቡ ሁሉ ይረብሸኛል ፡፡ በሳምንት ሦስት ቀን !!

የጠላ ቤቱ ጩኸት ጋብ ሲል ኳስ የሚጫወቱ ልጆች ይተካሉ፡፡ ግድግዳየን በኳስ ሲነርቱት
የቤቴ ምርጊት አፈሩ በለጠፍኩት የግድግዳ መሸፈኛ ወረቀት ስር እየተንኮሻኮሻ ሲፈርስ
ይሰማኛል፡፡ ይህን ሁሉ ስችለው ደግሞ የጠላ ቤቱ አሻሮ ሲታመስ ፣ የጠላ ቂጣው ሲጋራ አአአሻሮ አሻሮ የሚሸትት እንኩሮ እንኩሮ የሚተነፍግ ጭስ ጠባብ ክፍሌን ይሞላታል፡፡

ይህ ሁሉ ችግር ግን ቤቱን እንድጠላው አላደረገኝም፡፡ ፋናን ስመለከት ጫጫታው የፍቅር
ሙዚቃ፣ ጭሱ ፍቅርን የሚያጥን
የገነት ከርቤ እስኪመስለኝ ይስማማኛል፡፡

እዚህ ቤት ውስጥ ለስድስት ወራት ስኖር ከፍቅርተ ጋር ተግባባን፤ እማማ አመለ ጋር የእናትና የልጅ ያህል ተቀራረብን፤ ከፋና ጋር ግን ከሰላምታ ውጭ አንዲት ቃል ተለዋውጠን አናውቅም። ፋና እዛው ተቀምጣ አንድ ቤት እየኖርን ትናፍቀኛለች ፤ አትናገር አትጋገር ! ዝም፡፡ ፋና
ቤት ውስጥ አለች ማለት ማንም ቤት ውስጥ የለም እንደማለት ነው፤ ዝምታ ይነግሳል፡፡ የፋናን
ድምፅ አንዳንዴ ለአራት ለአምስት ቀናት አልሰማውም፤ እዛው እያለች፡፡ አይገርምም ? እኔም
በቤተሰቦቼ “እሱ አይናገር አይጋገር ዝም ነው!” እየተባልኩ እሞካሽ ነበር፡፡ ጉዳቸውን ባዩ !
እዚህ ሞት የሚያስንቅ ዝምታ የሰፈረባት ጋግርታም ጋር በፍቅር ወድቄ አንድ ቃል ሲናፍቀኝ፡፡

የፋና ዝምተኝነት የጤና አልመስል ብሎኝ ነበር፡፡ እንጀራ እየበሉ ወጥ ሲያልቅባት እንኳን ወጥ
ጨምሩልኝ አትልም፡፡ ደግነቱ እናቷ እማማ አመለ ዓይናቸው ከፋና ላይ ስለማይነቀል ገና ወጡ
ሲያልቅባት በላይ በላዩ ይጨምሩላታል፡፡ ፋና በቀን ውስጥ የምትናገራቸው ቃላት ሲደመሩ
እህቷ ፍቅርተ በግማሽ ደቂቃ ከምታዘንበው ንግግር እሚበልጡ አይመስለኝም፡፡ ፍቅርተ ሙሉ
ቀን ስታወራ፣ ስትስቅ፣ ስትጫወት ነው የምትውለው፡፡ አንዳንዴ ፈገግታ የሚያጭርብኝ ነገር
ፋናና ፍቅርተ ሲያወሩ መስማት ነበር፡፡ ፍቅርተ ብቻዋን የምታወራ ነው የምትመስለው።ፋና አንድ ቃል አትመልስም፤ ፍቅርተም ብትሆን የእህቷን አመል ያወቀች ይመስል መልስ አትጠብቅም፤ ዝም ብላ ታወራለች ::

የፍቅርተን ወሬ መስማት አይሰለችም፡፡ እንደው ፍቅርተን መልኳን ሳይመለከት ድምጿን ብቻ
ያደመጠ ሰው በዓለም አንደኛዋ ቆንጆ ሴት እየተናገረች ሊመስለው ይችላል፡፡ በተለይ ሳቋ ! የፍቅርተ ውበት ግን ድምጿ ብቻ ነው:: “ስምን መልአክ ያወጣዋል” የሚባለው ብሂል እውነት
ከሆነ የፍቅርተን ስም ያወጣው መልዓክ ድምጿን ብቻ በሆነ መንገድ አድምጦ “ፍቅርተ” ብሎ
ሳይሰይማት አልቀረም፡፡

እማማ አመለወርቅ ብርቱ እናት ነበሩ፡፡ ሁለቱን ሴት ልጆቻቸውን ያሳደጉት ካለ አባት ነው፡፡
ዛፍ ቆራጭ የነበሩ ባለቤታቸው አንድ ቀን ዛፍ ሲቆርጡ የዛፉ ቅርንጫፍ የተላጠ ኤሌክትሪክ
መስመር ጋር የተነካካ ሆኖ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው አለፈ፡፡ ያኔ ፋና የሶስት፣ ፍቅርተ
የሁለት ዓመት ሕፃናት ነበሩ፡፡ እነዚህን ሁለት ልጆች ለማሳደግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡
ያለፉበትን አሰቃቂ የድህነት መንገድ ተመልሰው ሲያስቡት ያንገሸግሻቸዋል፡፡ ታዲያ ከተቀራረብንና እኔም ከቤተሰቡ አባል እንደ አንድ ተቆጥሬ ገመናቸውን ተካፋይ ስሆን ማታ ማታ ቡና ተፈልቶ ታሪካቸውን ያወሩልኝ ነበር፡፡ እማማ አመለ ወሬ ይችላሉ፤ አሁን በሐዘን ዐይናችንን በእንባ ሞልተውት ድንገት ጣል በሚያደርጉት ቀልድ ለሐዘን የኳተረ እንባችን በሳቅ ይፈሳል፡፡

የማታ ቡና አብሬያቸው መጠጣት የጀመርኩበት ቀን ትዝ ይለኛል፡፡ በፊት ቡና ሲያፈሉ ፍቅርተ
መጋረጃዬን ገለጥ አድርጋ አንድ ስኒ ታቀብለኝና እጠጣለሁ፤ እጣኑም ቢሆን እየተጥመለመለ
መጋረጃዬን አልፎ ክፍሌ ይደርሳል ፡
“አብዬ” ይሉኛል እማማ አመለ ሲጠሩኝ እንዲህ ነው፤
“አቤት ማዘር !”
"ሁለተኛ ትጠጣለህ?”
“አይ ይበቃኛል ማዘር” እላለሁ፡፡ እየፈራሁ እንጂ ብጠጣ ደስ ይለኝ ነበር፡፡
አንድ ቀን ታዲያ ቡናው ተፈልቶ፣ እጣኑ ቤቱን ሞልቶት፣ እኔም ነቃ ብዬ ፍቅርተ መጋረጃዬን
ገለጥ አድርጋ ቡናዬን እስክታቀብለኝ ስጠብቅ እማማ አመለ ጠሩኝ፡፡
“አብዬ !”
“አቤት ማዘር”
“እንደው ከሰውም አልተፈጠርክ ? ምናለ ወዲህ ወጣ ብለህ ብትጫወት፣…ጀበናውንም እያየህ ቡና ብትጠጣ፣ እኔም እናትህ ነኝ፣ እነፍቅርዬም እህቶችህ ናቸው” አሉኝ፡፡ ይሄ የመለአክት ጥሪ ነው !
ልብሴን ቀየርኩ፤ (ምርጥ የምላትን ልብስ ነው የለበስኩት፣ ከዚህች እዚች የመጋረጃ ድንበር ለማለፍ
ሽክ!!)፡፡ እናም መጋረጃዬን ገለጥ አድርጌ ብቅ አልኩ፤ ሁሉም በአክብሮት ተቀበሉኝ፡፡ የተዘጋጀችልኝ ኩርሲ ላይ ተቀመጥኩ ፡፡ እዩት እንግዲህ እግዜር ጨዋታውን ሲያሳምረው! ፋና ፊት ለፊቴ ነው የተቀመጠችው፡፡ ከዚህ በፊት ፊት ለፊቴ ተቀምጦ የሚያውቅ ውብ ነገር ምን ነበር?…ምንም !!

በእኔና በፋና መሃል የሲኒ ረከቦት፣ ሲኒዎቹ ስድስት ጨረቃ መስለው፣ ከረከቦቱ ጎን ማጨሻው
እንደ ደመና በቀስታ ሽቅብ ወደ ጠቆረው ጣራ፣ ከሚሳብ የእጣን ጭሱ ጋር፡፡ ከስሱ የእጣን
መጋረጃ ባሻገር ፋና አንገቷን ደፍታ መሬት መሬት እየተመለከተች ተቀምጣለች፡፡ አዲስ ሰው
ስለተቀላቀልኩ ጨንቋታል፡፡ አቤት እንዲህ ፊቷ ተቀምጠው በእጣኑ ጭስ ውስጥ ሲመለከቷት
“ምነው ባልነቃሁ” በሚባልበት እንቅልፍ ውስጥ የተከሰተች ጣፋጭ ህልም ነው የምትመስለው ፋና የኔ ውብ፡፡

ድህነትን አፈር ድሜ ያስጋጠ ውበት በዚህ ጭርንቁስ ቤት ውስጥ ፊት ለፊቴ በእጣን ደመና
ተከብቦ ተቀምጧል፤ እኔም ከእግር ጥፍር እስከራስ ፀጉር በሚነዝር በሚያስረቀርቅ ደስታ
ውስጥ ህያውና ዘላለማዊ ሥዕል ላደርጋት እያጠናኋት ነው ፡፡ነፍሱ በፍቅር ፍላፃ እንደተወጋች
አይደለም የሚያሳምረው፤ የተፈቃሪውን ነፍስ ይመለከታል፤ ነገን ይመለከታል፤ በዝምታ ውስጥ ያለ ሰላምን የሚቃኙ ዐይኖች ይታደላል፡፡ ከተከዘ ፊት ፈገግታን ያወጣል፡፡ እውነትን በዓይነ ህሊናው ይቃኛል! አፍቃሪ ሠዓሊ ነው!

ከዛን ቀን ጀምሮ ፋና ጋር በእጣን ጭስ መሃል መተያየት የዘወትር ተግባራችን ነበር፡፡ የእማማ
አመለ ጣፋጭ ወግ፣ የፍቅርተ የማያባራ ሳቅና ጨዋታ፣ የፋና የማይገሰስ ዝምታና የዝምታዋ
ውበት፣ የውበቷ ግዝፈት እንደ መንፊስ በቤቱ ውስጥ ያረብብ ነበር፡፡ ያችን የድህነት ጎጆ ሙሉ
ያደረገ መልካም ቤተሰባዊ ፍቅራችን ለአራት አመታት አብሮን ኑሯል፡፡
👍274🥰4👎1
ድህነት ክፉ ነው፡፡ ድህነት ምኑም አያኮራም፤ ድህነት ያስጠላኛል፡፡ አንድ ቀን ትንሽ ራሴን
ስላመመኝ በጊዜ ወደቤት ተመለስኩ፤ ማንም አልነበረም፤ የት እንደሄዱ እኔንጃ፡፡ ወደ ክፍሌ
ገብቼ ፍራሽ ላይ በደረቴ ተደፍቼ ተኛሁ፡፡ ብዙ ሳልቆይ ፍቅርተ ከውጭ አየተጣደፈች ገባች፤
መኖሬን አላወቀችም፡፡ እኔም ካለወትሮዬ ዝም ብዬ በመጋረጃው አሻግሬ እመለከታታለሁ፡፡ አለ አይደል አንዳንዴ መናገር የሚታከትብን ጊዜ…

ፍቅርተ የሆነ ቦታ ልትሄድ በጥድፊያ ላይ እንደሆነች ታስታውቃለች፡፡ ከአሮጌው አልጋ ስር ዚፑ የተበላሸ አንድ የልብስ ማስቀመጫ ሻንጣ ጎትታ አወጣች፡፡ ይህ ሻንጣ የቤተሰቡ ብቸኛ የልብስ ማስቀመጫ ነበር፡፡ ከፈተችውና ልብስ መምረጥ ጀመረች፤ ትእይንቱ አሳዛኝ ነበር፡፡
አንዱን ታነሳና በሁለት እጆቿ ራቅ አድርጋ ይዛ እያገላበጠች ትመለከተዋለች፣ አልጋው ላይ
ትጥላለች፤ ሌላውን ታነሳለች ትጥላለች፡፡ የእማማ አመለ የክት ቀሚስና ነጠላ፣ የፋና አንድ
ሁለት ተራ ቀሚሶች እናም የፍቅርተ በርካታ ነጫጭ ቲሸርቶች…ሻንጣው ውስጥ የነበረው ልብስ በሙሉ አለቀ፡፡ ፍቅርተ ልትሄድ ላሰበችበት ቦታ የሚመጥን አንድም የረባ ልብስ
አላገኘችም፡፡ በረዥሙ ተነፈሰችና በአንድ እጁ ወገቧን ይዛ በሌላ እጁ ጠጉሯን እያከከች ግራ
ተጋብታ ለብዙ ደቂቃዎች በትካዜ ቆመች፡፡ ከዛም በቁጣ ልብሱን ከአልጋው ላይ ገፍቶ ወደ
ሻንጣው ወረወረችውና ሻንጣውን ዘግታ በእርግጫ ወደ አልጋው ስር ገፋችው፡፡ በዚህች ቅፅበት ጓደኞቿ ከውጭ ጠሯት፤

“…ፍቅር ቶሎ በይ እንጂ…ረፈደ
እኮ!”

እናንተ ሂዱ ኤልሲ ! ሌላ ቀጠሮ አለኝ ረስቼው ነበር” አለቻቸው፤ ጓደኞቿ ሄዱ፡፡ ፍቅርተ
አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች፡፡

“ኤጭ! ወይ መልክ የለኝ፣ ወይ ደህና ቤተሰብ የለኝ፣ ሰው ጋር መቀላቀያ እንኳን አንዲት ልብስ
ያጣል ሰው ?…አንዲት ልብስ..እግዚአብሄር አሁንስ ብትገለኝ ምናለበት ! በስንት ነገር ከሰው በታች ታደርገኛለህ?” አለች በምሬት፡፡ አልቅሳ ሲወጣላት እንባዋን ጠራርጋ አንዲት ትንሽ
መስተዋት ወደተሰቀለችበት ጥግ ሄደችና መስተዋቷን አውርዳ አንዴ ከንፈሯን ሰብሰብ አንዴ
ለቀቅ እያደረገች መልኳን ስትመለከት ቆየችና መስተዋቱን ወደ ቦታው እየመለሰች “አስቀያሚ”
ብላ በምሬት ተናገረች፡፡ ማታ የተለመደው ቡናችን ላይ ግን ፍቅርተ በሳቅ ስትፍለቀለቅና
ምንም ነገር ያልተሰማት ልጅ መስላ አመሸች፡፡ “ሳቅ የደስታ ምልክት ነው” የሚሉ የዋሆችን
ታዘብኳቸው፡፡

ከዛን ቀን ጀምሮ የፍቅርተን ልብሶች ማስተዋል ጀመርኩ፡፡ የፍቅርተ የሚበዙት ልብሶቿ ነጫጭ ቲሸርቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ ቲሸርቶች ከተለያዩ ድርጅቶች በነፃ የሚታደሉ የተለያዩ መፈክሮች
ደረታቸው እና ጀርባቸው ላይ በተለያዩ ቀለማት የታተሙባቸው ሲሆኑ ብዙዎቹ ለአንድ በዓል
ወይም ለሆነ ቀን መታሰቢያነት የተዘጋጁ ናቸው፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ፍቅርተ ልብስ አጥባ
ቲሸርቶቹ የተሰጡበት ቆሜ ስመለከት ገረመኝ፡፡ የፍቅርተ ቲሸርቶች ታጥበው ሲሰጡ የኢትዮጵያ ችግሮች በሙሉ ታጥበው የተሰጡ ነበር የሚመስሉት፡፡

“የእናቶች እና ህፃናት ሞት ይቁም” በቀይ ቀለም ደረቱ ላይ የተፃፈበት ቲሸርት፤

“ከ ኤች አይ ቪ ኤድስ ራሳችንን እና ቤተሰባችንን እንጠብቅ” በሰማያዊ፤

“ፖሊዮን ከኢትዮጵያ እናጠፋለን” በጥቁር፤

“መስኮት በመክፈት የቲቢ በሽታን እንከላከል” በቀይ፤

“ችግኝ በመትከል አካባቢያችንን ውብና ፅዱ እናድርግ” በአረንጓዴ፤

ከነጫጮቹ ቲሸርቶቹ ለየት ያሉት ደማቅ ቀይና ቢጫ ቲሸርቶች ደግሞ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ
አርማ የታተመባቸው ነበሩ፡፡ ፍቅርተ ብትበሳጭ እውነት አላት፡፡የዘመኗን ወጣቶች፣ የአዲስ
አበባን ቆነጃጅት በእነዚህ ቲሸርቶች መወዳደር ዘበት ነው፡፡ እያንዳንዷ ወጣት ሴት ውስጥ
እድሜ የሚያመጣው የቁንጅና ውድድር አለ፡፡ መልክ ያለው በመልኩ፣ የሌለው በዘመናዊና
ውብ ልብሶች ውድድሩ ውስጥ አለበት፡፡ በዚህ የታይታ ዘመን ግባቸው መታየት የሆነ እልፍ
አእላፍ ወጣቶች የማይታዩ መስዋዕትነቶችን የሚከፍሉት ወደው አይደለም፤ መታየት መኖርን ማረጋገጫ አንድ ምስክርነት ስለሆነባቸው እንጂ፡፡ እናም ለመታየት፣ ዕይታ ውስጥ የሚገባ አልባሳት አንዱ መስፈርት ነው፡፡ በዚህ ውድድር ላለመውደቅ የከፋ አዘቅት ውስጥ የሚወድቁትንም ቤት ይቁጠራቸው፡፡....

ይቀጥላል
👍157🥰1
አትሮኖስ pinned «#ከሰሀራ_በታች ፡ ፡ #ሁለት ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ማንም ችኩል ቢለኝ ግድ አይሰጠኝም፡፡ ፋናን ገና ስመለከታት ልቤ ውስጥ የማይናወጥ የፍቅር ሐውልት ቆሟል፡፡ ማንም ብትሆን ግድ አይሰጠኝም፤ ቤት ውስጥ ምንሽር የታጠቀ፣ ጓንዴ ትራሱ ስር ያስተኛ ባሏ ቢቀመጥ፣ ሰባት ልጆቿ “እማ እማ!” እያሉ የሚንጫጩ ሴት ብትሆንም ግድ የለኝም፡፡ፋናን አየኋት፣ ወደድኳት በቃ!! ይሄ ሁሉ ነገር የሆነው አንድ…»
#ከሰሀራ_በታች


#ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም

....ፋና ጋር መቀራረብ በጣም ከባድ ነበረ፡፡ አንዳንዴ ባህሪዋ ያበሳጨኛል፡፡ “ምናይነት የደነዘዘች ልጅ ናት” እልና ለራሴ ቁጣ ቁጣ ይለኛል፡፡ ለምን እንደ ፍቅርተ አታናግረኝም ? ሌላው ቢቀር አንድ ዓመት ሙሉ እዚህ ቤት ስኖር ቤቴን እንኳን ተሳስታ ረግጣው አታውቅም፡፡ ፍቅርተ እኮ
እናት ማለት ናት፡፡ ረፍዶብኝ ፍራሼን ሳላነጣጥፍ ከወጣሁ ፍራሼን አነጣጥፋ፣ ያዝረከረኩትን
ወረቀት አስተካክላ የሚጠጣ ውሃ ቀድታ አስቀምጣልኝ ነው የማገኘው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
ደግሞ ምግቤንም የምትሰራልኝ ፍቅርተ ናት፡፡ እች ፋና የሚሏት ዝግ ግን…ዝምታዋ ሰልችቶኝ
ነበር፡፡

የሆነ ጊዜ ታዲያ ድንገት ታመምኩ፡፡ ለሳምንት ትምህርት ቤት አልሄድኩም፤ ፍቅርተና እማማ
አመለ ተጨንቀው ሲሯሯጡ ሰነበቱ፡፡ ፋና ዝርም ብላ አታውቅም፡፡ ከዛን ጊዜ በኋላ የፉና ነገር በቃኝ፡፡ “እግዜር ይግደልህ !” ማንን ገደለ? አንድ ቀን ሳትጠይቀኝ በቃ ድኜ ተነሳሁ፡፡
ፋና የምትባል ልጅ በቃ በቃችኝ፡፡ ሳልፍ ሳገድም እወረውርላት የነበረውን ሰላምታዬን እኔም
አቆምኩ፡፡ ስገባ ብቻዋን ተቀምጣ ባገኛት እንኳን ሰላም አልላትም፡፡ እንደውም ከብስጭቴ
ብዛት ቤት ለመቀየር አሰብኩ፡፡ ግን ለእማማ አመለ ምን ሰበብ እንደማቀርብ ጨነቀኝ፡፡ ከእኔ
ከሚያገኟት የኪራይ ብር በላይ ለእኔ ያላቸው ቤተሰባዊ ፍቅር ቦታ አለው፤ ለእርሳቸው::ደግሞም ብቸኛ መተዳደሪያቸው ከእኔ የሚያገኟት የኪራይ ብር ነበረች፡፡ ምን ሆንኩ ብዬ ቤት ልውጣአ ? እች ጉልት ስወጣ ስገባ እንደ ግኡዝ ነገር ተጎልታ ማየቴ ያበሳጨኛል፡፡ ማታ ማታ ቡና ሲጠሩኝ በህመሜ አሳብቤ ልቀር ብሞክርም አልተሳካም፡፡
“ቡና ባትጠጣ እንኳን ና እና ተጫወት፤ በሽታውም ለብቻ ሲሆኑ ነው የሚጠናው” አሉኝ
እማማ አመለ፡፡ ጨዋታው እንደወትሮው አልጥምህ አለኝ፤ እጣኑ ከነከነኝ፤ ከእጣኑ ወዲያ
አቀርቅራ የምትቀመጠው ፋና ሰለቸችኝ፡፡ እወዳታለሁ፤ ግን ግኡዝ ናት በቃ ! ወይስ ከራሷ
ውበት ጋር በፍቅር ወድቃ ዓለምን ረስታለች ? ምናይነት ድንዛዜ ነው ይሄ ?
!
ፍቅርተ ጋር ቅርርባችን ተጠናክሮ ነበር፡፡ ማታ ማታ ቡናው እስከሚፈላ ደብተሯን ይዛ
ወደ ክፍሌ ትመጣለች፡፡ ግን አታጠናም፤ ቤታቸው ውስጥ ቴፕ ስለሌለ ሁልጊዜ የደብተሯ
ቦርሳ ውስጥ የምታኖረውን የአስቴርን ካሴት ይዛ ትመጣና በእኔ ቴፕ ታዳምጣለች፡፡ ግጥሙን
ሸምድዳዋለች፤ ጀምሮ እስኪጨርስ በቃሏ ትወጣዋለች፡፡ ሙዚቃውን እንደ ሙዚቃ ሳይሆን
እንደ መርዶ ነበር ፊቷን አጨፍግጋ የምታዳምጠው፡፡ አንድ ቀን ሙዚቃውን እያዳመጠች
እንባዋ በጉንጫ ላይ ኮለል ብሎ ወረደ፤

“ምን ሆንሽ ፍቅርተ” አልኳት ደንግጬ፤

“ምንም” ብላ ተነስታ ከክፍሌ ወጣች፡፡ከዛን ቀን ጀምሮ ፍቅርተ የወትሮዋ አልነበረችም፤ የሌላትን
አመል መነጫነጭ ጀመረች፡፡ ከመሬት ተነስታ ታለቅሳለች፤ በትንሽ ነገር ይከፋታል፡፡ ከወራት
ልመና በኋላ ጭንቋን ተነፈሰችው፤ ፍቅርተ ፍቅር ይዟት ነበር፡፡ ፍቅር እንደያዛት ስትነግረኝ
“እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፣ የነገስታት ንጉስ፣ የዓለም ሁሉ ፈጣሪ ኃያል! እባክህ ይህች ልጅ
ፍቅር የያዛት ከእኔ እንዳይሆን እርዳኝ” ብዬ ፀለይኩ፡፡

“ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ አብረን አንድ ክፍል ነው የተማርነው፤ ቶማስ ይባላል” ስትለኝ ሃሌሉያ!”
ብዬ ልጮኽ ቃጥቶኝ ነበር፡፡ ኡፍፍፍፍፍፍ ! አሁን እዳው ገብስ ነው ! ተረጋግቼ አዳምጣት
ጀመር፡፡ የከፍሎቿ ልጆች ተሰባስበው የተነሱትን አንድ ፎቶ እየሰጠችኝ ልጁን ጠቆመችኝ፤
ሲበዛ ቆንጆ ልጅ ነበር፡፡ ከግራና ቀኙ ሁለት ቆነጃጅት እንደ መዥገር ተጣብቀውበታል፡፡

“አንቺ የታለሽ ታዲያ!” አልኳት፤

“እኔ ፎቶ መነሳት አልወድም” አለችኝ ትክዝ ብላ፡፡ ለምን ብዬ አልጠየቅኳትም፡፡

“ከወደድሽው ስንት ጊዜ ሆነሽ?” አልኳት ፎቶውን እያየሁ፤
“እኔንጃ ግን ቆይቷል ፤ ሶስት አመት”
“እና ሦሰት ዓመት ሙሉ ስታፈቅሪው እርሱ ምን አለ ?”
“አያውቅም፡፡”
“ተነጋግራችሁ አታውቁም”
“አንድ ቀን አናግሮኛል…”
“እና ምን አለሽ?” አልኳት በጉጉት፡፡
“እርሳስ አጥቼ ስጠይቅ ሰጠኝ…ስመልስለት 'ውሰጂው! አለኝ” አለችና እዛኛው ክፍል ሄዳ አንድ
ቢጫ እርሳስ ይዛ ተመለሰች፡፡ እንደ ትልቅ ቅርስ በፍቅር እርሳሱን እየተመለከተች…፣ “አየኸው
የእሱ ነው” አለችኝ፡፡ ፊቷ ላይ የነበረው ደስታ… ናፍቆት…ፍቅር ያሳዝን ነበር፡፡ ትቀጥላለች
ብዬ ጠበቅኳት፡፡ የተነጋገሩት ግን እችኑ ነበር፡፡ አንድ ቃል “ውሰጅው” አላት፤ በቃ፡፡ ይሄ ቃል ለፍቅርተ “ንግግር” ነበር፡፡

“ለምን አታናግሪውም ታዲያ ? በቀጥታ መናገር እንኳን ባትችይ በሆነ መንገድ እንደወደድሽው
አሳውቂው፡፡ እሱም ሊወድሽ ይችላል” አልኳት እንደው ለማፅናናት እንጂ ያልኩትን ለራሴም አላመንኩበትም፡፡ ይሄ ልጅ ፍቅርተን ቢወዳት በሺ ዓመት አንድ ጊዜ የሚከሰት አጋጣሚ
አድርጌ ላየው ሁሉ እችላለሁ፡፡

በድንጋጤ አፍጥጣ እያየችኝ፣ “ትቀልዳለህ ?” አለችኝና አፏን በሁለት እጆቿ አፍና እንደዘገነነው
ሰው ሰውነቷ ተንዘረዘረ፤

“በጣም የሃብታም ልጅ ነው፤ በዛ ላይ ክላሳችን ውስጥ ካሉ ሰላሳ ሴቶች ግማሹ በሱ ፍቅር ያበዱ
ናቸው፡፡ በእረፍት ሰዓት ጎታቹ ብዙ ነው፤ በዚያ ላይ ጎበዝ ተማሪ፤ ኤጭ” ብላ በምሬት ፊቷ
አጨፈገገች፡፡ ዝም ብዬ አየኋት፤ ፍቅርተ ይበልጥ በቀረቧት ቁጥር ይበልጥ መልከጥፉ የምትሆን
ሚስኪን ነበረች፡፡ በቦዙ አይኖቿ ባዶውን እየተመለከተች ምሬቷን አምበለበለችው፡፡ የሆነ ነገር
ያስፈልግሃል፡ ለመፈቀር አንድ የሆነ ነገር ያስፈልግሃል፣ መልክ ወይም ሃብት…ብቻ የሆነ ነገር
እኔ ደግሞ ምንም የለኝም፤ መልክ የለኝ፣ ሃብት የለኝ፣ በትምህርት እንኳን እንዳላካክሰው እንደ ትምህርት የሚያስጠላኝ ነገር የለም እማማ እንዳይከፋት ነው የምማረው ቸኮኛል ከቤት
ባልወጣ ደስታዬ ነው፡ ማንንም ባላይ፡ ማንም ሳያየኝ ደስታዬ ነው አለችና እንባዋ ይፈስ ጀመር

“ፍቅርተ ለፍቅር ሃብት ፣ መልከ ምናምን ሲያስፈልግ ኖሮ እኮ አታፈቅሪም ነበር” አልኳት፡፡

ከአፌ ነጥቃ በቁጣ መናገር ጀመረች፡፡ንግግሯ በምሬት የተሞላ ነበር፡፡ “እንኳን ለፍቅር ለተራ
ሰላምታም ሀብት ያስፈልጋል ፡፡መልክ ያስፈልጋል ፡፡ አንተ አስቀያሚ ወጣት ሆነህ ታውቃለህ ? አስቀያሚ ሴት ሆነህስ ታውቃለህ ? ህመሙ አይገባህም፡፡አብርሽ መገፋቱ ስሜት አይሰጥህም….እየውልህ እንኳን አሁን ሕፃን ሆነን እኔና ፋና መንገድ ላይ ስንሄድ ያገኘን ሁሉ ፋናን አገላብጦ ጉንጯን ይስምና እኔን…” መጨረስ አልቻለችም እንባዋ ቀደማት፡፡

“አስራ ስምንት ዓመት አልፎኛል፡፡ እስካሁን አንድ ወንድ እንኳን ጠይቆኝ አያውቅም፡፡አንዳንዴ እንዴት እንደተፋቀሩ ይቅርና ያፈቀሩት ጋር እንዴት እንደተጣሉ ሴቶች ሲያወሩ እቀናለሁ..ከፍቅረኛ ጋር መጣላት በራሱ ያስቀናል፤ ይናፍቅሃል፤ ሰው ሆነህ በፍቅር መጋጨትህ ለራሱ ከሰው እኩል ያደርግሃል፡፡ የሚጣላህም የሚወድህም በሌለበት ዓለም መኖር ካለመኖር እኩል ነው” ፍቅርተ ባንዴ ተቀየረችብኝ፤ አስፈሪ ሆነችብኝ፡፡ ንፍጧ በአፍንጫዋ ተዝረከረከ፤
እንባዋ ፊቷን አጨቀየው፤ አስቀያሚነቷ ሙሉ ሆነ፡፡ ስታሳዝን!

“አስራ ስምንት ዓመት እኮ ትንሽ እድሜ ነው…ገና ነሽ ወደፊት የሚያፈቅርሽ የራስሽ ሰው
ይመጣል” አልኳት ልክ የሚያፈቅራትን ሰው የቀጠርኩት ይመስል በእርግጠኝነት፡፡ ግን ውስጤ መቼም ቢሆን ፍቅርተን የሚያፈቅር ሰው በምድር ላይ የሚፈጠር አይመስለውም፤ እናገራለሁ፤ግን የምለውን እኔም አላምንበትም፡፡
👍28
በቅሬታ ፈገግ ብላ ልትሄድ ተነሳች፡፡ እስካሁን በስሜት ባወራችኝ ነገር ሃፍረት ተሰምቷት
ነበር.…ማታ ቡና ላይ ግን ስትስቅ ስትጫወት ዓለም የሞላላት ደስተኛ ወጣት ትመስል ነበር፡፡
ስቃይን አፍኖ እንደፍቅርተ መሳቅ ትልቅ ብቃት ሳይጠይቅ አይቀርም፡፡

ፋናን እንዳኮረፍኳት አስራ አምስት ቀናት አለፉ፡፡ አስራ አምስት የሚያንገሸግሹ ቀናት፡፡ ወደ
ጓዳዬ ስገባ ፋና ያለችበትን ክፍል ማለፍ በሲኦል ውስጥ እንደማለፍ ነበር ለእኔ፡፡የመገፋት ሥሜት ይሰማኝ ነበር ፣ የመናቅ ስሜት ይሰማኝ ነበር፡፡ ልክ በአስራ አምስተኛው ቀን ከትምህርት
ቤት ስመለስ ፋና ብቻዋን ቤት ውስጥ ተቀምጣ ነበር፡፡ ሰላም ሳልላት አልፌ ወደ ክፍሌ ገባሁና
ደብተሬን ፍራሼ ላይ ወርውሬ እኔም ፍራሼ ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ ተኛሁ፡፡ለምን እንደሆነ እንጃ ፋናና እኔ ብቻችንን ቤት ስንሆን ይጨንቀኛል፣ የማደርገው ሁሉ ግራ ይገባኛል፡፡ እንዳናግራት
የሚገፋፋኝ ነገር አለ ግን አፌ አይከፈትም፣ እግሬም ወደ ርሷ ስንዝር መራመድ አይችልም፡፡
ለራሷ ደንዝዛ እኔንም አደንዝዛኛለች፡፡

በጀርባዬ ተኝቼ እያሰብኩ እያለ የበር መጋረጃዬ በቀስታ ሲገለጥ እና የውጪው ብርሃን ያሳደደው
የሰው ጥላ ሲያርፍብኝ ታየኝ፡፡ መጀመሪያ ፍቅርተ መስላኝ ነበር፡፡ ቀጥ ብዬ ተመለከትኩ
የተሰበሰበውን መጋረጃ በእጇ እንደያዘች ፋና በሬ ላይ ቃፊር መስላ ቆማለች…መንፈስ !!
ዝም ብዬ አየኋት፡፡

“ተሻለህ ?” አለችኝ፡፡ እውነቱን ለመናገር ሳቄ ነበር መጀመሪያ የመጣው::

“አዎ ደህና ነኝ” አልኳት መጋረጃውን ለቅቃ ተመልሳ ሄደች፡: ውስጤ ሊዳፈን ዳር ዳር ሲል የነበረውን ፍቅር ቆስቁሳው ሄደች፡፡ የተዳፈነ ፍላጎቴ በአንዲት ቃል እንደገና ነበልባል ሆኖ
ፋናን በመሻት ያንገበግበኝ ጀመረ፡፡ ለሌላ ዘላለም እዚሁ ቤት እንደምኖር እያሰብኩ ነበር፡፡
ምን ጉድ ናት ይህቺ ፋና !! ሲቆይ የገባኝ አንድ ነገር ቢኖር ፋና እንኳን ሌላ ሰው ጋር ራሷም ጋር ለማውራት የምታፍር አይነት ልጅ መሆኗ ነበር፡፡

የተቋረጠ ሰላምታዬን ቀጠልኩ፡፡ ፋናም ከወትሮው ትንሽ፣ በጣም ትንሽ ቀረብ ያለችኝ መሰለኝ:
ይህን ቀረቤታ በሌላ መንገድ ለመግለፅ ካስፈለገ በዓይን የማይታይ በጣም ደቂቅ የሆነ የመቀራረብ ለውጥ ልንለው እንችላለን፡፡ ከተለመደው መቀራራብ በመቶ ሚሊየን እጅ ያነሰ ረቂቅ የነፍስ መቀራረብ፡፡ ለእኔ ግን ይታየኛል ፍቅር የሚሉት አጉሊ መነፅር ዓይኖቼ ላይ ተደንቅሮ ነበርና የማያሳየኝ ነገር አልነበረም ፡፡

የማይታዩ መቀራረቦች ተደማምረው ወደሚታይ መቀራረብ ለመቀየር ዓመት ወስደዋል፡፡ ይሄ ቀስ እያለ የተገነባ ፅኑ የመቀራረብ ግንብ የወሬ ዛዛታ፣ አስር ጊዜ የመማማል ስሚንቶ አልነበረም ፀንቶ እንዲቆም ያደረገው መሰረቱ ዝምታ ነበር፡፡ በእኔና በፋና ውስጥ ዝምታ ነበር፡፡ በዛች ውድና ዘላለማዊ በምትመስል የቡና ሰዓት በእጣን መጋረጃችን ውስጥ ሁለታችንም ዓይኖቻችን
ሲገጣጠሙ ነፍሶቻችን የሚያወሩት ነገር ነበር፡፡ ፍቅርተና እማማ አመለ በሚያወሩን ነገሮች
የጋራ ሳቅ ስቀናል፣ ፋና ስትስቅ ሳቋን አጅቤ እስቅ ነበር ምንም ይሁን ጉዳዩ፤ እኔም ሳወራ
ፋና ትስቅ ነበር ድጋፍ ነው፡፡ ሳቋ ውስጥ “ለዘላለሙ ሳቅ አይለይህ” የሚል ምርቃት ነበር፡፡

ፋናን በየቀኑ አፈቅራት ነበር፡፡ አዳዲስ አይነት ፍቅር፣ ሰርክ አዲስ ፍቅር፡፡ እንተያያለን፡፡
ዓይኖቻችን ውስጥ ከብረት የጠነከረ መሻት ነበር፡፡ ቃል ሳንተነፍስ ነገሩን ጨርሰነው ነበር……
“ፋኒ የኔ መልአክ እንዴት ነሽ”

“አብርሽዬ የኔ ጌታ ዛሬ ናፍቀኸኝ ነበር የት አምሽተህ ነው”

“ምን አንድ ሞዛዛ አስተማሪ ሲሟዘዝብን አመሸ ፋኒዬ የኔ ውብ…” በቃ እንደዚህ የምናወራ
ይመስለኛል፡፡ ራሴ በፈጠርኩት የሀሳብ ንግግር በደስታ አብዳለሁ፡፡ እኔና ፋኒ ተግባብተናል፡፡ እማማ አመለ እና ፍቅርተ እዚህ ቤት ውስጥ የታፈነ ገሞራ ሊፈነዳ እየተብላላ መሆኑ በጭራሽ አልገባቸውም፡፡ ፍቅር ወሬ አያስፈልገውም፣ አዳሜ ጉድ የሆነው የስጋም የነፍስም ዓይኖቹን ዘግቶ ስለፍቅር እየደሰኮረ ነው፡፡ እኔና ፋኒ ዓይኖቻችንን ከፍተናቸው ነበር፡፡ እናም በዓይኖቼ የፋናን
ልብ እየተመለከትኩት ነበር ወዶኛል ! የፋናም ዓይኖች ልቤ ላይ ከተደገሰላቸው የፍቅር ድግስ
ድርሻቸውን አንስተው ሲመለሱ ይታወቀኛል፡፡ የሰው ልጅ እድሜ በወራት ቢሰየም ያ ጊዜ ለእኔና
ለፋና መስከረም ነበር፡፡ የህይወታችን መስክ በአደይ አበባ የተሸቆጠቆጠበት የመኖር ጅማሬ።

ቀስ በቀስ ፋና ወደክፍሌ ጎራ ማለት ጀመረች፣ ፍራሽ ጫፍ ላይ ትቀመጥና እናወራለን፡፡ ስለምን
እንደምናወራ አላውቅም፡፡ ብቻ ፋና ካለች አውራ አውራ ይለኛል፡፡ ለፍላፊ እሆናለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ፍቅርተም አብራን ስለምትሆን ነፃ ሆነን አናወራም ::

አንድ ቅዳሜ ቀን ከሰዓት በኋላ ፍቅርተ የት እንደሄደች እንጃ ቤት አልነበረችም፡ እማማ አመለም ለቅሶ ቤት ሄደው ነበር፡፡ ፋና መጣችና መጋረጃዋን ገለጥ አድርጋ በር ላይ ቆመች፣ ፋና ግቢ ካላልኳት አትገባም፡፡

“ፋኒ ግቢ!” እልኳት ገባችና ፍራሹ ጫፍ ላይ ተቀመጠች፡፡ እኔም ፍራሽ ላይ ተቀምጫለሁ ጎን ለጎን ነን፡፡ ፋና አንደ እንግዳ መሬት መሬት እያየኝ ተቀምጣለች፡፡ ውስጤ በሐሴት ይጨፍራል፡፡ በዓለም ላይ ካሉ እፁብ ድንቅ ነገሮች ሁሉ ትልቁ ነገር ጎኔ ተቀምጧል ፍቅር!!
ከብዙ ዝምታ በኋላ፣ “ታምሜ ያልጠየቅሽኝ ለምንድን ነው?" አልኳት ጥያቄዬ ድንገተኛ ነበር፡፡ደግሞ የመቼውን ህመም አንስቼ እንደወቀስኳት ለራሴም ገርሞኛል፡፡

“ቤተክርስቲያን ስሄድ እንዲሻልህ ስፀልያልህ ነበር፡፡ በጣም ነበር የተጨነቅኩት ..ደግሞ እንዲሻልህ
ተስዬልህ ነበር” አለችኝ፡፡ ውስጤ አዘነ፡፡

“እና ስእለትሽን እስገባሽ?” አልኳት እንደ ቀልድ ነበር የጠየቅኳት፡፡ ፋና አቀርቅራ ዝም አለች፡፡
ፋና የተሳለችው አንድ ፓኮ ሻማ ነበር፡፡ብር ስላጣች ስእለቷን አላስገባችም፡፡ ስትነግረኝ አንጀቴ
ነው የተላወሰው፡፡ እጇን በእጄ ያዝኩት፤ ደነገጠች፡፡ ቀስ አድርጋ እጇን ወደ ኋላዋ ለመሳብ
ሞከረች፤ እኔ ግን እጇን ይዤ ወደ እኔ ሳብኳት ፤ ሰውነቷ ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ቀና ብላ
አየችኝ ፤ ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው ነበር፡፡ ከንፈሮቻችን ሲገናኙ የፋና ጉንጮች ላይ እንባዋ ተዘረገፈ፡፡ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳት ፤ ደረቴ ላይ ተለጥፋ በእጆቿ የወገቤን ዙሪያ አቀፈችኝ፡፡

ይቀጥላል
👍1712
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...«ዛሬ እንዳትለየኝ አለችኝ
እቅፍ አደረግኳት። ብዙ ነገር ልነግራት ፈለግኩ። ግን የመናገር
ጊዜ አልነበረም፡፡ እንደተቃቀፍን እንቅልፍ አቀፈን .

ቀኑን በብዙ ስትስቅና «ዥማንፉ» የሚለውን ፈረንሳይኛዋን
ስትደጋግም ዋለች፡፡ እኔ አንድ የሆነ ነገር በምመለከትበት ጊዜ እሷ ያላወቅኩባት መስሏት ስትመለከተኝ ብዙ ጊዜ ተሰማኝ፡፡ እንደዚህ ስትመለከተኝ፣ አንድ ሁለት ጊዜ ድንገት ዘወር ብዬ አየኋት ያዘነና የናፈቀ ገፅታ አየሁባት፡ በአይኗ እንደምትጠጣኝ ይመስል ነበር፡፡ የማላውቀው እፍረት ተሰማኝ። ይህን ያህል የሚወደድ ምን አለኝና ነው?

ማታ ከእራት በኋላ «ለቫር ሳን ሚሼልኦ ወሰድኳትና አንድ
ሁካታ ያነሰበት ካፌ ገብተን ቢራ ካዘዝን በኋላ፣ እጄን ዘርግቼ
ጉንጫን አየዳሰስኩ
«ዛሬ ምን ሆነሻል?» አልኳት
«እኔ እንጃ፡ አዝኛለሁ። እዝን ብያለሁ» አለችና፣ እጄን በሁለት
እጇ ይዛ ሳመችው:: አሁንም እፍረት ተሰማኝ። እጄን መሳሟ
ሳይሆን አሳሳሟ
«አውራልኝ አለችኝ
«ስለምን ላውራልሽ?»
«ስላንተ። ዛሬ ውስጤ አንድ ትልቅ ቀፎ ተከፍቷል፡ ባዶውን
ነው፡፡ ባንተ ልሞላው እፈልጋለው:: ከልጅነት ጀምሮ አውራልኝ።
ምንም ሳታስቀር በሙሉ ንገረኝ፡፡»
ጧት ልነግራት ፈልጌ የነበረውን ነገርኳት። ፍርሀቴን፣ ስጋቲን፣
ጭንቀቴን ዘረዘርኩላት። ስጨርስ አንድ እጄን እያሻሽች
«ውይ የኔ ካስትሮ! ሰው ነህ ለካ!» አለችኝ፡፡ በሊላው እጄ ፀጉሯን እየደባበስኩ
«ምን መስዬሽ ኖሯል?» አልኳት
«የማትፈራ፣ የማትጨነቅ፣ የማትታመም፣ የማትሞት መስለህ
ነበር ምትታየኝ፡፡ አትሳቅብኝ! ሰው እንደመሆንህ፣ ሟች መሆንህን
አውቅ ነበር። ግን እውቀት ዋጋ የለውም፡፡ ስሜት ነው ዋናው፡፡
ስሜቴ ደሞ ስላንተ ሌላ ነገር ነበር የሚነግረኝ፡፡ ተው አትሳቅ
እየው፤ እንዲህ አስበው እስቲ።
ጊ ደ ሞፓሳን የደረሰውን
«ቤል አሚ» የተባለውን ልብወለድ ታሪክ አንብበህ የለ? ቤል አሚ
እጅግ የተዋበ፣ ሽንቅጥ የሆነ ጎረምሳ ነው። ታስታውስ የለ፣ መፅሀፉ የሚያልቀው፥ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሄ አይናማ ጎበዝ በብዙ ሰው እየተደነቀ፣ ሀብታሟን ልጅ ሲያገባ ቄሱ ወዳሉበት ሲራመድ ነው።
ታድያ ቤል አሚን ባስታወስከው ጊዜ፤ ሲያረጅ ወይ ሲታመም ወይ
ሲሞት አስበኸው ታውቃለህ? ሁልጊዜ ወጣት እንደሆነ አይደለም የሚታይህ? . . እንደሱ ነው አየህ፡፡ ሳስብህ፣ ዘለኣለም ወጣት፣ ዘለአለም ጤነኛ ዘለአለም ኩሩ ሆነህ ነበር የምትታየኝ»

«አሁን ግን ሰው ሆነህ ትታየኝ ጀመር፡፡ ጧት እንደነገርኩህ!
ማንም ሰው፣ ምንም ነገር ሊያሸንፍህ የማይችል ይመስለኝ ነበር፡፡ የብረት ሰው ትመስለኝ ነበር። አሁን ግን እንደ ቢራቢሮ ሆነህ ነው የምትታየኝ። በጣም ቆንጆ ነህ፣ ነጭ ፈገግታህ ጥቁር ፊትህ ላይ ሲያበራ፣ አልማዝ መሳይ አይኖችህ በሳቅ ብልጭ ብልጭ ሲሉ ወይም በምኞት ሲግሉ፣ በወጣትነት ፀሀይ ውስጥ የሚበር ውብ ቢራቢሮ ነህ። እንደ ቢራቢሮ በቀላሉ የምትጠፋ ነህ። ከዚህ ወጥተን መንገድ ስንሻገር መኪና ቢገጭህ ትሞታለህ፣ በባቡር ስንሄድ ከሌላ ባቡር ጋር ብንጋጭ ትሰባበራለህ፣ በኤሮፕላን ብትበር፣ እና
ኤሮፕላኑ አንድ ነገር ቢሆን፣ እንደ ወረቀት ትቦጫጨቃለህ፡፡
አንዲት ጥይት ብትመታሀ ትሞታለህ፡፡ ...»
«አይዞሽ አይዞሽ»

«ምን አይዞሽ ትለኛለህ? መሞትህ ነው ። አይታይህም?»
ሌላውም ይሞታል ኮ፡፡ አንቺም ጭምር»

ሌላውን የት አውቀዋለሁ? ምኔ ነው? አንተ ግን አንተ ነህ፡፡
ማንንም አትፈራም፡፡ እንደ ሲራኖ ደ ቤርዤራክ ነህ፡፡ ጀግና ነህ።
ወንድ ነህ። የኔ ነህ። እወድሀለሁ፡፡ የኔን የራሴን ማርጀትና መሞት
በሀሳቤ ልቀበለው እችላለሁ፡፡ አንተ ታረጃለሀ ትሞታለህ ቢሉኝ ግን አልቀበልም፡፡ ይሄ አንፀባራቂ ፈገግታህ ሲጨልም፣ እነዚህ ብሩህ አይኖችህ ሲፈዙ ለማየት አልፈልግም፡፡ አልቀበልም፡፡ እምቢዮ! ኤክስ ውስጥ ፀሀይ እየሞቁ በባዶ ብርጭቆ አይን ሞታቸውን ከሚመለከቱት ሽማግሌዎች አንዱ እንድትሆን እልፈቅድልህም፡፡
አልፈቅድልህም! ይገባሀል? አልፈቅድልህም! ወጣት መአዛህን
ወስደው የእርጅና ሽታ ሲለጥፉብህ እንዳትቀበል!»

«እሺ የኔ ቆንጆ፣ እሺ ይቅር፣ ረጋ በይ አይዞሽ። አሁን
ወጣት ነኝ፣ ካንቺ ጋር ነኝ»
«አሁን ብቻ ነዋ!»
«አሁን ብቻ አይደለም፡፡ አይዞሽ አይዞሽ»
«ከዚህ ውሰድኝ»
«እሺ»
«ውሰደኝና ልብሴን አውልቀህ እቅፍ አርገኝ። ከድሮ ይበልጥ
እቀፈኝ፡፡ ፍርሀት ይዞኛል፣ ሀዘን ተጫጭኖኛል፡፡ መወደድ መታቀፍ
እፈልጋለሁ፡፡»
«እሺ የኔ ሲልቪ»
«እንሂዱ»
«እሺ»
«በል እንሂድ»
«እሺ የኔ ፍቅር፣ ይኸው መሄዳችን ነው።»
ሆቴላችን እንደደረስን፣ ቶሎ ልብሷን አውልቄ እቅፍ አረግኳት
«እወድሻለሁ የኔ ፍቅር፣ ከልቤ እወድሻለሁ» አልኳት
«በላ አሳየኝ፣ በስጋህ አሳየኝ፣ በነብስህ አሳየኝ
«ይኸው የኔ ፍቅር፣ ይኸው»
በጭለማው፣ በሹክሹክታ
«አማልክቱ ሁሉ ሞተዋል፡፡ እኛ ብቻ ነን የቀረነው:: አንተ ለኔ
አምላኬ ነህ። እኔስ አምላክህ ነኝ?»
«አዎን አምላኬ ነሽ»
«ድገምልኝ»
«አምላኬ ነሽ፡፡ አምላኬ ነሽ፡ የኔ አምላክ ነሽ»
አፌ ውስጥ እየተነፈሰች «በላ መስዋእት አቅርብልኝ»
«እሺ። ምን መስዋእት ትፈልጊያለሽ?»
«ሁልጊዜ ከላይ ሆነህ ወደታች ታየኛለህ፡፡ ዛሬ ታች ውረድና
እኔ አዘቅዝቄ ልመልከትህ ክብርህን ሰዋልኝ»
«እሺ፡፡ ክብሬን ውሰጂው:: ላንቺ ክብሬን ብሰዋ ደስ ይለኛል።
በጭለማው በሹክሹክታ
«በላ»
«እዘዢኝ»
«እንዳታመነታ ልባርግ»
«ዝግጁ ነኝ፡፡ ንገሪኝ፡፡ ምን ላርግሽ? ምን ልሁንልሽ?»
«ወደታች ውረድና ከእግሬ ጥፍር ጀምረህ እየሳምከኝ አየላስከኝ
ወደላይ ና፡፡»
«እሺ የኔ መቤት»
ከእግሯ ጥፍር ጀምሬ እስከ አፏ ሳምኳት ላስኳት። በአፉ
ተቀበለችኝና እየሳመችኝ፣ በጭለማው በሹክሹክታ
«ጥሩ ነበር፣ ግሩም ነበር፡፡ ግን አይበቃም። በጭራሽ
አይበቃኝም» አለችኝ
«የፈለግሽውን ንገሪኝ። አደርገዋለሁ፡፡ አምላኬ ነሽ»
«እንዴት ነው ጭኖቼ መሀል ስመኘኝ የማታውቀው?»
«አድርጌው አላውቅማ»
«በጭራሽ አርገኸው አታውቅም?»
«በጭራሽ»
«በጭለማው፣ በሹክሹክታ
ውረድና ጭኖቼ
ሳመኝ። ልክ አፌን
እንደምትስመኝ አርገህ ሳመኝ፤ በከንፈርህ፣ በጥርስህ፣ በምላስህ
ሳመኝ፡፡ አምላክህ ነኝ፡፡ ካንተ ምፈልገው መስዋእት እሱ ነው::»
«እሺ»
ሳረገው አልቀፈፈኝም፡፡ በጭራሽ አልቀፈፈኝም፡፡ እንዲያውም
በጣም ነው ደስ ያለኝ። ስስማት፣ በማክበርና በማምለክ ስስማት፣
እያቃሰተች ራሴን ስታሻሽ ቆይታ ቆይታ፣ በጭንቅላቴ ስባ ወደ ላይ
ወሰደችኝና
«ትወደኛለህ፡፡ በእውነት ትወደኛለህ፡፡ እንዴት ግሩም ነው!
ትወደኛለህ፡፡ አንተ እኔን ትወደኛለህ!» አያለች ስታቃስት
«አይዞሽ አይዞሽ፣ ያንቺው ነኝ» እያልኩ አባበልኳት
«እንዴት እድለኛ ነኝ! እንደ ዛሬ ደስ ብሎኝ ኣያውቅም»
«ገዝተሽኛል»
«ገዝቼሀለሁ። እወድሀለሁ፡፡ አንተም ገዝተኸኛል። እንዴት ጥሩ
«አሁን ተኚ። ደክሞሻል፡፡»
«እሺ፣ አቅፈህ አስተኛኝ።»
ከትንሽ ዝምታ በኋላ
«እንደዚህ ጥሩ ልጅ ሆነህ ሽርሙጣ መውደድህ አያሳዝንም?»
👍21😁1
አለችኝ
የምን ሽርሙጣ?»
«እኔ ራሴ»
ኦ ! እንግዲህ እረፊ!»
«እውነቴን 'ኮ ነው:: የወጣልኝ ሽርሙጣ ነኝ»
“ምን እንደዚህ ያሰኝሻል? ዛሬ ምን ሆነሻል?»
«ወድጄሀለኋ!
አንተም ወደኸኛል። ስለዚህ ሴሰኛ መሆኔ ይቆጨኛል፡፡ ስለዚህ ላንተ ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡ ምን አይነት ውሻ እንደሆንኩ እንድታውቅልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ንስሀ መግባት እፈልጋለሁ።ከቻልክ ታድነኛለህ፡፡ ማዳን ካልቻልክ ይቅርታህን ታለብሰኛለህ::እሱንም ካልቻልክ ደሞ፣ እንደ ሽርሙጣ ትጠቀምብኛለህ»
እየሳቅኩ
«እሱንም ካልቻልኩስ?»
«ወደህም ባይሆን በግድህ ትችላለህ፡፡ እኔ ከፈለግኩ እምቢ
ሊለኝ የሚችል ወንድ አለ ይመስልሀል? ይሀን ንካ እስቲ
እምቢ ልትለኝ ምትችል ይመስልሀል?»

«አቤት ትእቢት እሺ ቀጥዪው»

ከልጅነቴ ልጀምር መሰለኝ፡፡ በሽታው የጀመረኝ ያን ጊዜ
ይመስለኛል፡፡ አየህ፣ እባቴን በሀይል እወደው ነበር። ሀብታም ነው፣ስራ ካላሰኘው አይሰራም፣ እኔ ከሱ ጋር ነው የምውለው፣ ስንስቅ ስንጫወት ነው የሚመሸው። ታድያ አምስት አመት ሲሆነኝ፣ በአሮፕላን አደጋ ሞተ። እንግዲህ እኔ ያን ጊዜ አልገባኝም እንጂ፣ እናቴ ኣንድ ውሽማ ነበራት

አባቴ እንደሞተ፣ ይሄ ሰውዬ እኛ ቤት ይመላለስ ጀመር።እናቴ በሌለችበት ያጫውተኛል፣ ይላፋኛል፣ ያቃቅፈኛል፡፡ አንዳንዴ
ሶፋ ላይ ተቀምጦ፣ ላዩ ላይ ያስቀምጠኝና ያሻሽኛል። አባቴ በሀይል ይናፍቀኝ ስለነበረ፣ አይኔን እጨፍንና፣ በሀሳቤ አባባ ነው አሉ
እቅፎኝ ያለው » እላለሁ። ሰውዬው ያሻሽኛል፣ እኔ አይኔን ጨፍኜ
አባባን አስባለሁ፡፡ እሱ እጁን ቂጤ ላይ፣ ጭኔ ላይ ያንሸራሽራል፣
ጉንጩንና አንገቴን ይስመኛል እኔ በሀይል ደስ ይለኛል
«አሁን ሳስበው እንደሚመስለኝ፣ እናቴ 'ሲልቪ እንድትወድህ
ካረግክ አገባሀለሁ' ብላዋለች። ምክንያቱም፣ እሷ እየፈቀደችለት
ሀሙስ ሀሙስ ለብቻው ሽርሽር ይወስደኝ ነበር። በወሰደኝ ቁጥር
ለአንድ ሰአት ያህል ቤቱ እንሄዳለን። ብቻችንን ነን። መጋረጃውን ይዘጋና ቤቱን ግማሽ ጭለማ ያረገዋል። ሶፋ ላይ ወይም ድንክ አልጋ ላይ ይጋደምና ላዩ ላይ ያስቀምጠኛል። ወይም ያጋድመኛል። ይሄ ሁሉ በፀጥታ ነው። እኔ አይኔን ጨፍኜ ከአባባ ጋር ነኝ እላለሁ፣ እሱ ያሻሽኛል። አያሻሸ እየሳመ ሙታንቲዬን ያወልቃል አስታውሳለሁ፣ እጁ ላብ በላብ ይሆን ነበር፡፡ ያሻሽኛል። ጭኔን፡ቂጤን፣ ብልቴን ቀስ እያረገ ይዳሰሰኛል። አንድ ሰአት ያህል
እንዲህ ካረግን በኋላ፣ ወጥተን ሽርሽር እንሄዳለን። የፈለግኩትን
ይገዛልኛል፡፡»

«በኋላስ?»

«አንድ ቀን እንዲህ እንደሆንን እማሚ ደረሰችብን፡፡ እማማ
ከሰውየው ነጠቀችኝና አቅፋኝ አለቀሰች። ሰውየው ከዚያ በኋላ
ቤታችን መጥቶ አያውቅም
ቀጥሎ እንግዲህ አደግኩ፡፡ አስራ አምስት አመት ሆነኝ።
ከፖል ጋር ፍቅር ያዘኝ። አንድ ኣመት ያህል ከተዋደድን በኋላ
እነካስትሮን ለማገዝ ወደ ኩባ ሄደ። ሁለት ወር ያህል አለቀስኩ።
ከዚያ አንድ ቀን አንዱ ልጅ ናይት ክለብ ወሰደኝ፣ አይኔን
ጨፈንኩና፣ “Paul, Paul mon amour! (ፖል፣ የኔ ፍቅር») እያልኩ እያሰብኩ ከልጁ ጋር ጥብቅ ብዬ ደነስኩ፡፡ እሱ በምኞት አብጦ በሀይል ይታከከኛል፡፡ እየሳመኝ «እቤት እንሂድ?» አለኝ። እሺ አልኩት። ወሰደኝ። ሲተኛኝ አይኔን ጨፍኜ ፖልን ነበር የማስበው፡፡ በጣም ተደሰትኩ፡፡ ግን ነገሩ ካለቀ በኋላ፣ አንድ አይነት ሀዘንና ፀፀት ልቤን ሞላው:: እለቀስኩ

ከዚያ ንግዲህ አንድ ነገር በግልፅ ታየኝ። ይኸውም፣ ወንድ
በጣም እወዳለሁ። ቢያንስ በሳምንት ሁለት ሌሊት ከወንድ ጋር ማደር አለብኝ፡፡ ታድያ ወንዶቹ ይሰለቹኛል

«አይ ሲሰለቹ! እንደ ፖል አይደሉም፡ ውስጣታቸው እንደ
እሳት የሚነድ፣ የህይወታቸው መሪ የሆነ ቋሚ እምነት የላቸውም፡፡ ባዶ ናቸው፣ በህይወታቸው የሚፈልጉት ምንድነው? ገንዘብና ሴት፣
ግፋ ቢል ስልጣን። በቃ። ይሰለቹኛል። መጀመርያ ሳያቸው
አቋቋማቸው፣ አስተያየታቸው ወንዳ ወንድ ነው። ያምሩኛል።
ኣይዛቸዋለሁ። የመጀመሪያ ጊዜው በጣም ጥሩ ነው። ስለፖል ማሰብ የለብኝም፣ እነሱኑ እደሰትባቸዋለሁ። ከአንድ ሶስት አራት ሳምንት በኋላ ይሰለቹኛል፣ ባዶ ናቸው። ለኔ የሚሆን ምንም የላቸው። ገላቸውን እንደሆነ ቀምሼው ጠግቤዋለሁ። ስለዚህ እያቀፍኳቸው ፖልን አስባለው ጊዜ እያለፈ እየተረሳኝ ሲሄድ ግን ፖልን ሳይሆን ሌላ ወንድ ማሰብ ጀመርኩ። ማንም ወንድ ሊሆን ይችላል። ማርለን ብራንዶ ያለበት ፊልም አይቼ ንደሆነ፣ እነሱን አያቀፍኩ እሱን አስበዋለሁ። ብቻ ምን ልበልህ፣ ተበላሸሁ። ክፉኛ ተበላሽ
«ይህን ሁሉ ያባባሰው ምንድነው ብትል፣ ትምህርት በጣም
መቅለሉ። ሳነብ በጣም ፈጣን ነኝ፣ ያነበብኩትን ደሞ አልረሳም::
ብዙውን ጊዜ በማስታወሻ ደብተርም መፃፍ ኣያስፈልገኝ። ፈተና ሲሆን በፍፁም አልደናገጥም፣ ስለዚህ ሀሳብ በቀላሉ ይመጣልኛል፡
የሌሎቹን ተማሪዎች አንድ አራተኛ ያህል ብስራ ፈተናውን ኮርቼ
አልፋለሁ በስጋዬ ለመደሰት ብዙ ጊዜ አለኝ። በዚህ ላይ እንግዲህ ስጋዊ ፍትወት ከድርሻዬ በላይ ተሰጥቶኛል፤ ወንዱ ራሱ ሰልችቶኝ ካላስጠላኝ ወይም እሱን ካልደከመው ሌሊቱን ሙሉ ላድርበት እችላለሁ፡፡
ወንድ ማግኘቱ እንዳይቸግረኝ ደሞ ቀን እደምታየው ነው:: ጠባብ ቀሚስ ወይም ሱሪ ለብሼ ወጣና፣ አይኔን ትንሽ ጣል ሳረግባቸው እየተንገበገቡ እንደ ውሻ ይከተሉኛል። መጥተው ይታከኩኛል፣ምኞት ባሳበጠው ትኩስ ገላቸው ይተሻሹኛል፡፡ ሴት መሆን እንዴት
ጥሩ ነው!

“ስንት ቆንጆ ወንድ እለ ጡንቸኛ፣ ጠንካራ፣ ወጣት፣ መልከ መልካም የሆነ ስንት ወንድ አለ! ታድያ ሁሉም የኔ ነው፣
ከፈለግኩ በአይኔ እጠራዋለሁ፡ ይመጣል፡፡ ግሩም የተገማመደበትን ውብ ገላውን ለኔ ለግል መደሰቻዬ ያበረክትልኛል፤
እደሰትበታለሁ። ሲበቃኝ አሽኘዋለሁ። ባማረኝ ጊዜ እንደገና እጠራዋለሁ .. ደስ ሲለኝ የወንዶች ጠረን! እኔ ከስራቸው ተመቻችቼ፣
በእጄ የገላቸውን ጠንካራ ጡንቻ ስዳስስ፣ እነሱ ከላዬ ሆነው እያዩኝ፣ አየወደዱኝ፣ እየሳሙኝ፣ እየላሱኝ፣ ያለ የሌለ
አሳብጠው ለኔ ደስታ ከፍ ዝቅ ሲሉ፣ ድካሙና ስሜቱ ላብ በሳብ
ሲያረጋቸው፣ ያን ጊዜ የላባቸው መአዛ አቤት ደስ ማለቱ! ሴት
መሆን ምንኛ ገነት ነው!»

ሲልቪ ይህን ሁሉ በጭለማው
ስትነግረኝ፡ ፈረንሳይኛዋና በቅንዝረኛ ድምፅዋ ስሰማው፣ ቃላቷ ምናቤ ውስጥ ግልጥ ያለ ትርኢት ይቀርፃሉ ጥብቅ ያለ ሱሪ ለብሳ፣ ወፍራም ዳሌዋን እያወዛወዘች ስትራመድ፣ በሚያባብሉ አይኖቿ ቆንጆዎቹን
ወንዶች ስትጠራቸው ትታየኛለች። ራቁቷን አልጋ ላይ ተጋድማ፡
ወተት መሳይ ጭኖቿን ክፍት አርጋ፣ ልዩ ልዩ ወንድ ስታስገባ፣
እነሱ ሲደሰቱባትና ሲስሟት ይታየኛል። ኃይለኛ ቅናት እንቅ
ግን ኣቤት ማስደሰቱ! እሷንም ሆነ ወንዶቹን ኣልጠላኋቸውም፣ ይልቅስ እኔም ከነሱ ኣንዱ መሆን አማረኝ፤ እንደነሱ ከላይዋ ሆኜ ጭኖቿ መሀል ገብቼ፣ እየሳምኳት እየላስኳት «ሲልቪ!
ሲልቪ!» ልላት ፈለግኩ። በጭለማው እላይዋ ላይ ወጣሁ

«ምን ሆነሀል የኔ ቢራቢሮ?» አለችኝ እግሯን እየከፈተችልኝ፣
እያቀፈችኝ፣ እጆቿን ገላዬ ላይ እያንሸራሽረች፡ አፌን በሰፊ አፏ
👍231
እየሳመች
«ስንት ናቸው? ስንት ይሆናሉ?» አልኳት እየተንገበገብኩ፣
በጭለማው እርጥብ አፏን እየሳምኩ
«ምኖቹ?» አለችኝ
«ወንዶቹ። የተኙሽ ወንዶች ስንት ናቸው? ብዙ ናቸው?»
ማሰብያዬ የለም፣ ተኝቷል፤ የምናገረው ቅዠት ነው፤ ግን ያለሁት ገነት ውስጥ ነው የቅናት ገነት፣ በደስታ የሚያቃጥል
የሚያንገበግብ ገነት፤ ራስ የሚያዞር፣ ክብር የሚያስረሳ ገነት፣እፍረት የማያውቅ ገነት። የጉርምስና ትኩሳታም ገነት
«ንገሪኝ እንጂ። ብዙ ናቸው?» አልኳት
«ብዙ እንዲሆኑ ትፈልጋለህ?»
«በጣም ብዙ : ንዲሆኑ ትፈልጋለህ?
«አዎን»
ነግሬህ የለ? ሴሰኛ ነኝ፡ የተነሳብኝ ጊዜ ከወገቤ በላይ ሳቅና
ደስታ፣ ከወገቤ በታች ቅንዝር ነኝ። ስለዚህ ወንድ ሁሉ ይፈልገኛል።
ቆንጆ ከሆነ ደግሞ ያገናኛል፡ ' “ብዙ ናቸው የተኙኝ ወንዶች።
በጣም ብዙ ናቸው። ቁጥራቸውን በግምት እንኳ ላውቀው
አልችልም፡፡ ... ደስ አለህ? ደስ አለህ የኔ ቢራቢሮ?»
«እስክቃጠል ደስ አለኝ. . . እንደዛሬ ጥመሽኝ አታውቂም፡፡»
«መቅናት ደስ ይልሀል?»
«አዎን! አዎን! አዎን!»
«እንግዲያው ስማኝ፡፡ በበጋ ከኢጣልያ እንደተመለስን ኣንተ ወደ ኤክስ ስትሄድ፣ እኔ ቤቶቼን ለማየት ወደዚህ አልመጣሁም?»
«አዎን»
«ቤቶቼን አንድ ቀን ብቻ ነው ያየሁዋቸው። ሌላውን ቀን
ከወንዶች ጋር ነበር ማድረውና ' ምውለው። ስድስት ቀንና ሌሊት
ሙሉ፣ ያለማቋረጥ ወንድ እያቀያየርኩ ስደሰት ሰነበትኩ፡፡ ለዚህ ነው ወደ ኤክስ ስመለስ አሞኝ የነበረውና ልትተኛኝ ያልቻልከው።አብዝቼ ነው:: አስበው እስቲ፣ ማታ አንድ ሶስት ኣራት ወንድ ሳቀያይር አመሽና፣ ሌሊት ካንዱ ጋር ስንታገል እናድራለን። ከሰአት
በኋላ አንድ ወይም ሁለት ማግኘት አለብኝ፡፡ ማታ እንደገና ሶስት
አራት. . . ይታይሀል?»
«አዎን ይታየኛል»
«ምን ይታይሀል?»
«በተራ ሲተኙሽ ሲልሱሽ ይታየኛል . . ብዙ ብዙ ናቸው።
ታድያ'ኮ እነሱ ሁሉ እኔ ነኝ። ቁጥሬ በዛ እንጂ እኔው ነኝ፡፡ ልዩ
ልዩ ገላ : የለበስኩ ነው እንጂ፣ እኔ ነኝ። እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ .. እኔ
.
«አውቃለሁ የኔ ቆንጆ፡፡ አንተ ነህ። ሁሉም አንተ ነህ። . .
የብቻህ ነኝ. . . አይዞህ እዚሁ ነኝ፣ ካንተ ጋር ነኝ፣ አቅፌሀለሁ.
አይዞህ ተኛ .. እኔ 'ጠብቅሀለሁ. .. ተኛ የኔ ቆንጆ ቢራቢሮ
ከእራት በኋላ «ቡለቫር ሳን ሚሼል» ሄደን እዚያው ፀጥታ
የሰፈነበት ካፌ ገብተን፣ እዚያችው ጠረጴዛ ጋ ተቀመጥን፣ ቢራ
እየጠጣን ማውራት ጀመርን። ዛሬ ግን ሲልቪ አላዘነችም፡
የተለመደው ሳቋ አይኖቿን እየደጋገመ ያበራቸዋል፣ ከንፈሮቿን
ያለማቋረጥ ይከፋፍታቸዋል። እራት ላይ ሁለት ጠርሙስ ወይን
ጠጥተን ነበር፣ አሁን ሁለት ጠርሙስ ቢራ ስንቀላቅልበት ጊዜ ወሬአችን ሞቀ....

💫ይቀጥላል 💫
👍18
አትሮኖስ pinned «#ከሰሀራ_በታች ፡ ፡ #ሶስት ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ....ፋና ጋር መቀራረብ በጣም ከባድ ነበረ፡፡ አንዳንዴ ባህሪዋ ያበሳጨኛል፡፡ “ምናይነት የደነዘዘች ልጅ ናት” እልና ለራሴ ቁጣ ቁጣ ይለኛል፡፡ ለምን እንደ ፍቅርተ አታናግረኝም ? ሌላው ቢቀር አንድ ዓመት ሙሉ እዚህ ቤት ስኖር ቤቴን እንኳን ተሳስታ ረግጣው አታውቅም፡፡ ፍቅርተ እኮ እናት ማለት ናት፡፡ ረፍዶብኝ ፍራሼን ሳላነጣጥፍ ከወጣሁ…»
#ከሰሀራ_በታች


#አራት(መጨረሻ)


#በአሌክስ_አብርሃም



...ከፋና ጋር ከተሳሳምንባት ቅዳሜ በኋላ ዋና ስራችን የእማማ አመለ እና የፍቅርተ እግር
ሲወጣ መጠበቅ ሆነ..በቃ ወጣ ሲሉ ፋና ወደ ክፍሌ ሮጣ ትመጣና እቅፌ ላይ ናት፣ከንፈሮቻችን እንዳይገናኙ ማድረግ ከሁለታችንም አቅም በላይ ነበር፡፡ በፍቅር ሰከርን፤አንዳንዴ እማማ አመለ ቤት ውስጥ ሆነውም ፋና ተነስታ ወደ ክፍሌ ትገባለች፣“አብርሽ ስራ ይዘሃል እንዴ?” ትላለች፡፡እማማ አመለ ከትምህርት ጋር የተያያዘ ነገር አድርገው ስለሚያስቡት በጭራሽ አይጠራጠሩም፡፡ፋኒ ወደ ክፍሌ ትገባና እንደ እብድ ትስመኛለች!
ከሚፈታተነኝ ስሜት ጋር እየታገልኩ እማማ አመለ እንዳይሰሙ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ፤ ፋኒ ግን መሳሳም ከጀመርን ነፍሷን አታውቅም፤ ማንም ቢመጣ ግድ አይሰጣትም፡፡

ማታ ማታ ቡናችን ላይ ስንቀመጥ ፋኒ ዓይኖቿን ከእኔ ላይ መንቀል አትችልም፤ በቃ ዓይኗ ቡዝዝ ብሎ ታየኛለች፡፡ አስተያየቷ ይጨንቀኛል፡፡ ፍቅርተ ድንገት ብትጠራጠር ብዬ እፈራለሁ፡፡
ደግነቱ ፍቅርተ ሳታቋርጥ ስለምታወራ ሁለታችንንም አትመለከተንም፡: ፋና ትምህርት ማጥናቷ ሁሉ እርግፍ አድርጋ ተወችው፡፡ በየምክንያቱ እኔ ክፍል መመላለስ ሆነ ስራዋ፡፡ መቸም እኔና ፋና ከዚህ በፊት እማማ አመለ አዕምሮ ውስጥ የፈጠርነው እምነት ረዳን እንጂ የፋና ባህሪ መቀየር፣ የሁለታችንን የፍቅር ግንኙነታችንን አፍ አውጥቶ የሚናገር ነበር፡፡ አንዳንድ ሰው አለ
መሃል ላይ መቆም የማይችል፣ ወይ ጥቅልል አድርጎ ራሱን ይሰጣል፣ አልያም ገና ከሩቁ ከሰው ይሸሻል ፋና እንደዛ ነበረች፡፡ ሙሉ እሷነቷን ለእኔ ስለሰጠችኝ ለምትሰራው ነገር ሁሉ ሌላ ሰው አልታይ አላት፡፡

የነፋና ኑሮ ሊገልፁት በማይችሉት ድህነት ውስጥ የተዘፈቀ ነበር፡፡ ባጭሩ ቤት ያላቸው የጎዳና
ተዳዳሪዎች ይመስሉኛል፡፡ አንዳንዴ እማማ አመለ የከሰል መግዣ ብር ያጡ ስለነበረ ከቤቷ
ጋር ተያይዛ የተሰራች በላስቲክ የተጋረደች ኩሽና ውስጥ ምናምኑን ጓድፈው ይማግዱና ቡና ያፈላሉ፡፡ ቡናው ታዲያ ጣዕሙ ጭስ ጭስ ይላል፡፡ እኔ ያን ያህል ብር ባይተርፈኝም አንዳንዴ ከቤተሰብ ሲላክልኝ ለፋና አልያም ለፍቅርተ ትንሽ ብር ልሰጣቸው እሞክራለሁ፡፡ ሁለቱም ቢሞቱ ብር ከእኔ አይቀበሉም፡፡ ብዙ ጊዜ ሞክሬ ሲቸከኝ መጠየቁንም ትቼዋለሁ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ፋና ወደ ክፍሌ ገባችና እየፈራች “አብርሽ ሰላሳ ብር አለህ ?” አለችኝ ፊቷ ላይ የነበረው ሀፍረት ያሳዝን ነበር፡፡ ደስ ብሎኝ ለፋና ድፍን ሃምሳ ብር ሰጠኋት፣ ደስ ብሏት እየተጣደፈች ወጣች፡፡
ፋና ወደ ማታ አንድ የተጠቀለለ ነገር ይዛ ወደ ክፍሌ ገባች፡፡ ፊቷ በደስታ ፈገግታ ተጥለቅልቋል፡
፡ ጥቅልሉን ፈታታችና አንድ ጥቁር የሴት ጅንስ ሱሪ አወጣች፣ “ለፍቅርዬ ገዛሁላት” አለችኝ፡፡
ሱሪውን ሳይሆን ፋና ፊት ላይ የነበረውን ፈገግታና ደስታ አይቼ መጥገብ አልቻልኩም፡፡ ፋና
እንደዚህ በደስታ ስትሰክር አይቻት አላውቅም፡፡

ትምህርት ቤታቸው ውስጥ በነበረ የስነተዋልዶ ስልጠና ላይ ተሳትፋ በተሰጣት አበል ከእኔ ሰላሳ
ብር ጨምራ ለፍቅርተ ይህን ሱሪ ገዛች፡፡ ፋና እንዲህ አይነት ልጅ ነበረች፡፡ ቁንጅናዋ የልብሷን
ተራነት ይሸፍነዋል እንጂ ለራሷ አንድም የረባ ልብስ የላትም፡፡ አዲሱን ሱሪ ይዛ ፍራሽ ጫፍ
ላይ ተቀመጠችና በጀርባዋ ተደገፈችኝ፡፡ የሆነ ርካታ ይነበብባት ነበር፡፡
“ፍቅርዬን እወዳታለሁ ከህፃንነታችን ጀምሮ ሁሉም ሰው እንደገፋት ነው የኖረችው፡፡ ሁልጊዜም ስለሷ እያሰብኩ እሰቃያለሁ፡፡“ አብርሽ ፍቅር እኮ እንደ መልኳ አይደለችም ደግ ነች፣ ጥሩ እህት፣ ጥሩ ጓደኛ ናት፡፡ ሁሉም ሰው ግን ይርቃታል” አለችና ማልቀስ ጀመረች፡፡ እንባዎቿን ጠረግኩላት፡፡ እንባዋ በንፁህ ጉንጮቿ ላይ ሲንኳለል መስተዋት ላይ የፈሰሰ ውሃ ይመስል ነበር፤ ጉንጯን ሳምኳት ፤ ወዲያው ግን በየት በኩል እንደተንሸራተትኩ እንጃ ከንፈራችን ተገናኘ፡፡ቅልጥ ያለ መሳሳም ውስጥ ገብተን ይሄን የዘቀጠ ኑሮ የጠቆረ ድህነት ለደቂቃዎች ተሰናበትነው።

ሱሪው ፍቅርተን ቀየራት፡፡ ስትለብሰው ዳሌዋን ሰፋ ኣድርጎ ወገቧን ሸንቀጥ ስላደረገው የፍቅርተ ቁንጅና መቃብሩን ፈንቅሎ ወጣ፡፡ ሱሪውን ስትለብስ አንድ የጥንካሬ መንፈስ የለበሰች ይመስል አስገራሚ በራስ መተማመን ይታይባታል፡፡ ጓደኞቿ ጋር መወጣት፣ አመሻሹ ላይ ከጎረቤት እኩዮቿ ጋር ተያይዛ መዞር ጀመረች፡፡ በዕርግጥም ሱሪው የሰውነቷን ቅርፅ ጎላ አድርጎ አሳምሯት ነበር፡፡ ይህንን አድናቆት ከአንዳንድ ወንዶች ጭምር እንደተቸራትም ፍቅርተ ራሷ በደስታ ለእኔና ለፉና እየነገረችን ስታስቀን ነበር፡፡ ልብስ መንፈስ ነው፡፡ ስጋን ሸፍኖ የስጋን ውበት የሚያጎላ መንፈስ፡፡ ይሄ መንፈስ ሱሪ ተመስሎ ፍቅርተ ላይ አርፎ ነበር ፡፡

የእነፉና ህይወት ከቀን ወደቀን ወደባሰ ድህነት እየተዘፈቀ ነበር የሚሄደው፡፡ እማማ አመለ አልፎ
አልፎ ልብስ ያጥቡላቸው የነበሩ የመንገድ ስራ ሙያተኞች ነበሩ፡፡ ከዛች የሚያገኟት ገቢ እኔ
በየወሩ ከምሰጣቸው የኪራይ ብር ጋር ተዳምራ ኑሯቸውን ስትደጉም ኖራለች፡፡ ታዲያ የመንገድ
ስራ ባለሙያዎቹ መንገዱን ሰርተው ስለጨረሱ የእማማ አመለም ገቢ ተቋረጠና ቤተሰቡ የባሰ ችግር ላይ ወደቀ፡፡ አንዳንድ ቀን የወትሮውን ቡና ማፍሊያ ብር ስለሚያጡ ሁላችንም በጊዜ
እንተኛለን፡፡ ቤቱ እንደ መቃብር ቤት ፀጥ ይላል፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በሰፈሩ
ለሚያልፈው መንገድ ግንባታ ቤታቸው በቅርቡ እንደሚፈርስ ለእማማ አመለ ተነገራቸው፡፡
እማማ አመለ ይህን መርዶ እንደሰሙ ሙሉ ቀን ታምመው ከአልጋቸው ሳይነሱ ዋሉ፡፡

አንድ ቀን ታዲያ ፍቅርተ ትምህርቷን አቋርጣ ካፍቴሪያ በእቃ አጣቢነት ለመቀጠር መወሰኗን ለቤተሰቡ አሳወቀች፤ መርዶ ነበረ፡፡ እማማ አመለ እያለቀሱ እግሯ ላይ ወድቀው ለመኗት፡፡ ፋና ፊቷ ገርጥቶ እና አይኖቿ በእንባ ተሞልተው ዝም ብላ ፍቅርተን እና እናቷን ትመለከታለች፡፡በብዙ ልመና ፍቅርተ የዛን ቀን ትምህርት ቤት ሄደች፡፡ ፋና ፊቷ በሐዘን ድባብ ተውጦ ከወትሮ ዝምታዋ ሺ ጊዜ የገዘፈ ዝማታ ውስጥ ሰጥማ ዋለች፡፡ የዛን ጊዜ ፋና የአስራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና ወስዳ ውጤት እየተጠባበቀች ነበር፡፡

በቀጣዩ ቀን ወደ ማታ ላይ ፋና ወደ ክፍሌ መጣች፡፡ አልሳመችኝም፣ ትክዝ ብላ ፍራሽ ጫፍ ላይ ተቀመጠችና “አብርሽ አረብ አገር ልላክሽ የሚለኝ የሆነ ጎረቤታችን አለ፣ ብዙ ልጆች ልኳል
እዚሁ እኛ ሰፈር ነው ተፈሪ የሚባለው ታውቀው የለ ?” አለችኝ፡፡

“እና…” አልኳት አሁኑኑ ብርር ብላ ትሄድብኝ ይመስል ስጋት ሁለመናዬን ወርሮት እጆቿን
በእጆቼ እየያዝኩ፡፡ ደንግጬ ነበር፣ መተንፈስ ሁሉ አቅቶኝ ነበር፡፡
“አይ ቢያንስ ፍቅር ትምህርቷን እስክትጨርስ ለሁለት ዓመት ሰርቼ ብመለስ ብዬ አሰብኩ፤
በዛ ላይ ይሄ ቤት ከፈረሰ የት እንወድቃለን ዘመድ የለን መጠጊያ” አለችኝ፡፡ ድንጋጤዬ
አስደንግጧት ሳይሆን አይቀርም ስትናገር ፈርታ ነበር፡፡

“አብደሻል ፋኒ…ምን ሰይጣን ነው ይሄን ያሳሰበሺ..እንዴት እንደዚህ አይነት መጥፎ ነገር ታስቢያለሽ” ጮህኩባት ::

“ኧረ እብርሽ ቀስ እማማ እንዳትሰማ አለችኝ በጭንቀት በአገጯ ወደዛንኛው ክፍል እየጠቆመች።
👍26
ስሚኝ ፋኒ ! ትምህርቴን ልጨርስ፡ አንድ ዓመት የማትሞላ ጊዜ ናት የቀረችኝ፡፡ እንደጨረስኩ
እንጋባለን፡ ስራ እይዛለሁ፡፡ ከዛ በኋላ አንቸገርም እባክሽ ለዚህች
አጭር ጊዚ ብለሽ መጥፎ
ነገር አታስቢ ፋናን ጨምድጄ ይዤ የምናገረው ከልቤ ነበር እንደ እብድ ለፈለፍኩ፡፡ የምናገረው ከልቤ ነበር፡፡ ፋናን ማግባት በምድር ላይ ካሉ ጉዳዮች ሁሉ ቅድሚያ የምሰጠው ጉዳይ ነበር፡፡ ፊቷ ላይ የነበረው ባዶነት ፣ ዓይኖቿ ውስጥ የነበረው ተስፋ መቁረጥ የነገረኝ ነገር ነበር፡፡ ፋና ስጋዋን አስቀምጣ ቀድማ ወደማታውቀው ዓለም ሄዳለች፡፡ በቃ የለችም ፡፡ ሳምኳት ምንም አልተሰማትም ! ፋና የኔ ውብ የእኔ መለአክ እንኳን ስሚያት ዓይኖቻችን ሲተያዩ ፊቷ በፍቅር ስሜት የሚቀላው ፋና አይኔ እያየ ከስማለች፡፡ እንደ ግዑዝ ተራራ ከስሩ ውሃ እንደሚያመነጭ ግዑዝ ስጋዋ ብቻ እንባ እያፈለቀ አጠገቤ ተቀምጧል፡፡

“ምናባቴ ላድርግ አብርሽ ጨነቀኝኮ..ለስሙ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ…ትልቅ እህት ነኝ፡፡ ቤተሰቦቼ በችግር ሲያልቁ እጄን አነባብሬ ማየት ብቻ ሆነ ስራዬ፡፡ እህቴ በብስጭት አንድ ነገር ብትሆንብኝ ዘላለም ሲፀፅተኝ ይኖራል፡፡ ማነው የዚህ ቤተሰብ ታዳጊ፡፡ ዘመድ የለንም፣ ማን መጥቶ ከዚህ መከራ ያውጣን ? ..መሃል አዲስ አበባ ላይ ቤተሰቦቼ በረሃብ ሲሞቱ ዝም ልበል ?…መሃል አዲስ አበባ ቤተሰቦቼ በድርቅ ይለቁ ? …ጎረቤት የሚሰራ ወጥ እየሸተታቸው አንጀታቸው ታጥፎ
ሲተኙ ዝም ልበል ? ንገረኛ አብርሽ ! እሺ ምን ልሁን፣ ሴተኛ አዳሪ ልሁን? እናቴ የቡና ሱስ
እያሰቃያት አይኗ እንባ እያጎረፈ ጎረቤት የሚወቀጥ ቡና ድምፅ እያዳመጠች “ቡና በጠሩኝ”
እያለች ስትመኝ እያየሁ ስንት ዓመት በዝምታ ልኑር?…አንዲት ልጆቿን ለማሳደግ እድሜ ልኳን
የተራበች የተንከራተተች ባልቴት ልጆቿም ደርሰው በርሃብ ስትሰቃይ እያየች ዝም የምትል ልጅ
ልጅ ትባላለች ? እሄዳለሁ ! የትም ቢሆን እሄዳለሁ” ብላኝ እንባዋን ጠራርጋ ከከፍሌ ወጣች፡፡
አፈር ለብሶ በዝምታ የኖረ ፈንጅ የድህነት ጨካኝ እግር ረግጦት ፈነዳ ፤ ውስጤ በፍንዳታው
ሲናጥ ይሰማኛል፤ የአብሮነት ከተማ ሲፈራርስ፣ የፍቅር ቅርስ ሲወድም ይታየኛል፡፡

ማታ ላይ ፍቅርተ ፊቷ ሳቅ ለብሶ ሳቅ ጎርሶ መጋረጃዬን እስኪገነጠል በርግዳው ገባች፡፡ ተጠምጥማ ጉንጬን ሳመችኝ ፡፡ እውነቱን ለመናገር በዛ ከንፈር አፈሰችኝ ማለት ይሻላል ! ከዛም ድምጿን ቀንሳ፣ “ቀጠረኝ” አለችኝ፡፡ ለሶስት ዓመት ያፈቀረችው ልጅ ቅዳሜ ሊያገኛት ቀጥሯት ነበር፡፡
“ለምን?….እንዴት?” አላልኳትም የፋና ጉዳይ እያብሰለሰለኝ ነበር፡፡ ብቻ ለማስመሰልና አብሬያት
ለመደሰት ሞከርኩ፡፡ ፍቅር ግን እንዴት ኃያል ነው በእግዚአብሔር ችግር አያግደው ድህነት
በቃ በመከራ የተከበበን ሰው ከመሬት አስነስቶ ያስፈነድቀዋል ወይንስ ያፈቀረ ሰው ለሌላው
የማይታይ ላፍቃሪው ብቻ የሚገለጥ ከችግር፣ ከድህነት፣ ከመከራ የሚታደግ የመላእክት፣ የእሳት ሰረገላ አገሩን ከብቦ ይታየዋል ?

ለፍቅርተ ቀጠሮ በነገረችኝ ሰዓት ቸልተኛ ልሁን እንጂ እርሷ ደስታ የፋና የስደት ሐሳብ
ይጨነግፋል ብዬ ስላሰብኩ በሚያስፈልጋት ሁሉ ከጎኗ ሆኜ ድጋፍ ለመስጠት ወሰንኩ፡፡ ቅዳሜ ጠዋት ሀምሳ ብር ሰጠኋት ላለመቀበል አንገራግራ ነበር ፀጉርሽን ተሰሪ ጀግሞ ቀጠሮ ቦታ
ባዶ እጅ አይኬድም” ብዬ አሳመንኳት፡፡ ብሩን ተቀበለችኝ፡፡

ጥቁር ሱሪዋን ከአሮጌው ሻንጣ አወጣችና ማጠብ ጀመረች፣ “ይሄ ሱሪ እዳውን አየ እስቲ አሁን መች
ለበሽውና የምታጥቢው” አሉ እማማ አመለ፡፡ ፍቅርተ እያንጎራጎረች አጠባዋን ቀጠለች፡፡ በዚህ ሰዓት እግዜር ወርዶ ቢናገራትም መስማቷን እንጃ ! ሱሪውን አጥባ ስትጨርስ አስተካክላ ገመድ ላይ አሰጣችና ወደ ፀጉር ቤት በደስታ እየተንሳፈፈች ሄደች፡፡ እኔም “ክላስ” ስለነበረኝ ወደ ግቢ ሄድኩ፡፡

ከሰዓት በኋላ ወደ ስምንት ሰዓት አካባቢ ከምማርበት ኮሌጅ ስመለስ እማማ አመለወርቅ
በራቸው ስር ሁልጊዜ የሚቀመጡባት ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው አገኘኋቸው፡፡አይናቸው ቡዝዝ ብሎ በሀሳብ በመመሰጣቸው እስካናግራቸው ድረስ አጠገባቸው መድረሴንም አላዩም ነበር፡፡ ለወትሮው እዚህች ድንጋይ መቀመጫ ላይ የሚቀመጡት እጃቸው አጠር ሲል ለእለት ቡና ብር ቢጤ ሲቸግራቸው ነበር፡፡ የድንጋይ ወንበሯ የመተከዣ መድረካቸው ናት፡፡

“ማዘር ምነው ሰላም አይደሉም እንዴ ?” አልኳቸው፡፡

ቀጥ ብለው እንባ በቋጠሩ ዓይኖቻቸው ተመለከቱኝና ሳግ ተናነቀው አሳዛኝ ድምፅ ! “የፍቅርዬን ሱሪ ወሰዱባት አብርሽ” አሉኝ ሌባ ቁሳቁስ ብቻ ሳይሆን ተስፋ ጭምር እንደሚሰርቅ የገባኝ ያኔ ነው፡፡ ፍቅርተ ለዓመታት ስትመኘው ከኖረችው ፍቅር፣ በተዓምር ከተሳካ ቀጠሮ በአንድ
ሱሪ ምክንያት መቅረት አልፈለገችም፡፡ የሆዷን በሆዷ አድርጋ ሰፈር ውስጥ ወዳሉ እኩዮቿ ሁሉ እየሄደች ልብስ እንዲያውሷት ጠየቀች አልተሳካላትም፡፡ ሁሉም ልብስ አላቸው፣ ሁሉም ልብሳቸውን የማያውሱበት ምክንያትም አላቸው፡፡ ሁሉም ግን አንድ ተራ ልብስ በዚያች ቀን ለፍቅርተ ከንጉስ ካባ የበለጠ ዋጋ እንደነበረው አያውቁም ነበር፡፡

ፍቅርተ አንገቷን ደፍታ ወደ ቤት ገባችና ሁልጊዜ ፋና ትቀመጥበት የነበረው ኩርሲ ላይ ተቀመጠች ፡፡ የፋናን ወንበር ብቻ ሳይሆን የፋናን ዝምታ ወረሰች፡፡ ከዛን ቀን ጀምሮ ፋናም ዝም፣ ፍቅርተም ዝም ! እማማ አመለ ብቻ እንዲሁ የልጆቻቸውን ዝምታ ለመስበር የባጥ የቆጡን ያወራሉ፡፡ የማታ ማታ ቡናችን እንደወትሮው አይደምቅም ነበር፡፡ የፍቅርተን ሱሪ የወሰደው ሌባ የፍቅርተን ምላስ የወሰደው እስኪመስለኝ ፍቅርተ ከዛ በኋላ እንደበፊቱ ስታወራ ሰምቻት አላውቅም፡፡

“አብርሽ ሰላም ነው” በቃ የምታናግረኝ እችን ብቻ ነበር፡፡ እንደ በፊቱም እቤቴ አትመጣም፡፡
ከትምህርት ቤት ስትመለስ የእማማ አመለን ነጠላ በደንብ ልብሷ ላይ ጣል ታደርግና ቤተከርስቲያን ትሄዳለች፡፡ አንዳንዴ በጣም አምሽታ ስለምትመለስ እና ጧት ስለምትወጣ ለሁለት ለሶስት
ቀን አንነጋገርም፡፡ በስሱ መጋረጃ ዓይኖቼን ልኬ በደበዘዘው ብርሃን የሰለቸውና ከወትሮው
የባሰ አስፈሪ የሆነ ፊቷን አያለሁ፡፡

ፋና ጋር የነበረን ግንኙነት ግን ቀስ በቀስ እንደነበረው ተመለሰ ፤እንደውም ከበፊቱ የበለጠ
አብረን መዋል ጀመርን፡፡ ፋናም የበፊቷ አፍቃሪ ፋና ሆነች፡፡ ዓለምን ረስተን በዛች ደሳሳ ጓዳ
ውስጥ የራሳችን ፀሐይ፣ የራሳችን ጨረቃ፣ የራሳችን ከዋክብት ያሉባት ዓለም ፈጠርን ፣ ፋናን
ያፈቀርኳት ሳይሆን እኔን ራሴን የሆነች እስኪመስለኝ ሁሉ ነገሬ ሆነች፡፡

የሶስተኛ ዓመት ትምህርት እንዳለቀ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቼ ለመሄድ ምን ያህል እንደተጨነቅኩ መግለፅ አልችልም፡፡ ፋናን ትቼ መሄድ ራሴን ትቼ ከመሄድ በምንም አይተናነስም፡፡ ግን የግድ
መሄድ ነበረብኝና ወደ ቤተሰቦቼ ጋር ክፍለ ሐገር ለሁለት ወር እረፍት ሄድኩ፡፡ ለተከታታይ
ሁለት ሳምንታት ፋና በህዝብ ስልክ እየደወለችልኝ እናወራ ነበረ፣ ከዛ በኋላ ግን ድምፅዋ ጠፋ፤
ለእስራ አምስት ቀናት ጠበቅኩ ፤ ፋና አልደወለችም፡፡ የማውቀው ስልክ አልነበረኝም፣ ፋናም
👍17
ስልክ አልነበራትም ናፍቆቷን መቋቋም ለእኔ ስቃይ ነበር ፡፡
በመጨረሻ ወሰንኩ፡፡ ቤተሰቦቼን የምማርበት ኮሌጅ እንደጠራኝ በመንገር ማቄን ጨርቄን
ሳልል በአንድ ወሬ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ፡፡ አዲስ አበባ ስደርስ ልቤ ፈርቶ ነበር፡፡ እቤት
ስደርስ እማማ አመለ አንገቴ ላይ ተጠምጥመው ሳሙኝ፡፡ እንባቸው አንገቴ ስር ሲረጥበኝ ነበር
እያለቀሱ መሆኑን ያወቅኩት፡፡
ወደ ቤት ስገባ ቤቱ ካለወትሮው ጭር ብሏል፡፡ እማማ አመለ ጉድ ጉድ ብለው ቡና አፈሉ፣
“ድንገት መጣህብኝ” ብለው ቁራሽ እንጀራ በበርበሬ አቀረቡልኝ እና የመጀመሪያውን ቡና
ቀድተው ሲያቀብሉኝ እጃቸው ሲንቀጠቀጥና ሲኒው ከማስቀመጫው ጋር በእጃቸው እንቅጥቃጤ ምክንያት ሲንቀጫቀጭ ተመለከትኩ፡፡ ልቤ የባሰ ፈራ፡፡

“እቡዬ ይሄውልህ ፋኒዬ ድንገት ሳላስበው ብድግ ብላ አረብ አገር ሄደችብኝ” አሉና እንባቸውን
ዘረገፉት ! የያዝኩት ቡና ሳላስበው ከእጄ ላይ ወድቆ ተከነበለ፡፡

እንዴት ማዘር?…ማን ወሰዳት?…እርስዎ እንዴት ዝም ይላሉ?…” የጥያቄ መዓት ዘረገፍኩባቸው፤
ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም ፤ እማማ አመለ ግን አንገታቸውን ደፍተው አንዲት የቄጤማ ዘለላ
እያፍተለተሉ ስቅስቅ ብለው ከማልቀስ ውጭ ቃል አልተነፈሱም፡፡ ሽበት የወረረው ፀጉራቸው፡ቆዳቸው፣ በእርጅና ብዛት የተጨማደዱ እጆቻቸውና አስር ቦታ ላይ በከር የተሰፋ ኮንጎ ጫማ ያጠለቀ እግራቸውን ስመለከት ከፋና ናፍቆት ጋር ተደማምሮ እንባዬ ከውስጤ ገነፈለ ፡፡እማማ አመለ ማልቀሴ አስደንግጧቸው ከፍራሻቸው ተነስተው መጥተው ጎኔ ተቀመጡና እንደ ልጅ አጥንታም ደረታቸው ላይ ራሴን አስጠግተው አቀፉኝ፡፡ ሁለታችንም በዛች ልትፈርስ አንድ ሃሙስ በቀራት ደሳሳ ጎጆ ስቅስቅ ብለን ተላቀስን፡፡
ወደ ማታ ላይ ፍቅርተ መጣች፡፡ ገና ስታየኝ አቅፋኝ መነፋረቅ ጀመረች፡፡ በቀጣዩ ቀን የማደርገው ነገር ግራ ገብቶኝ ፍራሽ ላይ ተቀምጬ ስቆዝም ፍቅርተ ወደ ከፍሌ ገብታ የተጣጠፈ ወረቀት
ሰጠችኝ እና ወደ ክፍሏ ተመለሰች፡፡ ፋና የፃፈችልኝ ደብዳቤ ነበር ፤ የፋኒ ትንንሽና ቁልጭ ያሉ ፅሁፎች፡-…

አብርሽዬ መቼም እንደምታዝንብኝ አውቃለሁ፡፡ ጨካኝ ትለኛለህ አውቃለሁ፡፡ ግን….የሌለህበት
እዚህች ብዙ ነገር ያሳለፍንባት ጓዳ እየገባሁ ስንት ቀን አለቀስኩ መሰለህ…ችግራችን ገፋኝ….
በየቀኑ የማየው ነገር እንገሸገሸኝ፡፡ ከአንተ በላይ የቤታችንን ችግር የሚያውቅ ማን አለ አብርሽ? በእርግጥ የዛን ጊዜ ለመሄድ ማሰቤን ስነግርህ የሆንከውን ነገር አይቼ ሐሳቤን ቀይሬ ነበር፤ ግን የፍቅርዬ ሱሪ የጠፋ ቀን በቃ ወሰንኩ፡፡ እንዳትቆጣኝ ሃሳቤንም እንዳታስቀይረኝ ፈርቼ ተደብቄ ደላላው ሰውዬ ጋር አስፈላጊውን ሁሉ ጨረስኩ፣ አንተ ለእረፍት እስከምትሄድ ነበር የምጠብቀው፡፡ ፍቅርዬ በውስጧ የሞተውን ፍቅር፣ የከሰመውን ተስፋ ማዳን የምችልበት ሌላ ነገር የለኝም፡፡
አፈቅርሃለሁ አብርሽ አከብርሃለሁ እና እመለሳለሁ፡፡እግዚአብሄር እንዲረዳኝ ፀልይልኝ፡፡
ስለምታፈቅረኝ ከልብህ እግዚአብሄርን እንደምትለምንልኝ አውቃለሁ፡፡ አብርሽ እዛ ትልቁ
ዲክሽነሪ ውስጥ የነበረውን ጉርድ ፎቶግራፍህን ሳላስፈቅድህ ወስጄዋለሁ፡፡ ሁልጊዜም ላይህ
እፈልጋለሁ ሁልጊዜም አብርሽዬ…ግን እንዳትረሳኝ ሁልጊዜም አፍቅረኝ፡፡

አብርሽ ትወደኝ የለ ? እማማን ትወዳት የለ ? ፍቅርን ትወዳት የለ ? እኔ እና አንተ በፍቅር
ልናሳልፋቸው ከምንችላቸው ውድ የፍቅር ጊዜያት ሁለት ዓመት ለምንወዳቸው ሰዎች ብንሰጥ
ሁሉንም ነገር ታውቀዋለህና ይቅር ትለኛለህ ብዬ አስቤ ነው፡፡ እንኳን እንዲህ ርቄህ መሄድ ከዚህች መጋረጃ አልፌ ከክፍልህ ስወጣ አልቅሽ አልቅሽ እኮ ነው የሚለኝ፡፡ አብርሽ እፈራለሁ፤ ከፊቴ ምን እንደሚጠብቀኝ አላውቅም ግን ምናባቴ ላድርግ…እመብረሃን ትርዳኝ ”

ደብዳቤውን አንብቤ ስጨርስ አቅመቢስነት ተሰማኝ፡፡ በቃ ! ከአሁን በኋላ እድሜ ልኬን
ለማንም ለምንም የማልጠቅም ከንቱ መሆኔ ገዘፈብኝ፡፡ ፍራሽ ላይ በደረቴ ተኝቼ ወደ ዛኛው
ክፍል በትካዜ መመልከት ጀመርኩ፡፡

ከመጋረጃዬ ባሻገር ድህነት የነገሰበት ዓለም ይታየኛል የተራቡ ባልቴቶች ቅንጦት ባሰከራት
ከተማ ስር ተቀብረው ይታዩኛል፡፡ ሊሰደዱ የሚያኮበኩቡ ወጣቶች ታዳጊ አጥተው ይታዩኛል
ትምህርታቸውን ትተው ለጉልበት ስራ የተሰለፉ ወጣቶች ይታዩኛል፡፡ ለእለት ጉርስ ለዓመት ጉርስ
የተቸገረ ቤተሰብ ይታየኛል፡፡ ከመጋረጃው ወዲህ ክፍሌ ውስጥ ሬዲዮው ያወራል ስለ ሙዚቃ ያወራል፣ ስለ ልብስ ያወራል፣ ስለ ፅዳት ያወራል፣ ስለ እድገት ያወራል፣ ስለ ፖለቲከኞች ምርጫ ያወራል፣ የአገር መሪዎችን ያሞካሻል፡፡ ሬዲዮው አጠገብ በልቼ የተረፈኝ ዳቦ በወረቀት ተጠቅልሎ
ተቀምጧል፡፡ ከጎኑ እንቁላል የተጠበሰበት መጥበሻ ከነተረፈ የእንቁላል ጥብሱ ይታየኛል፡፡
እኔ ያለሁበት ሆነው የእማማ አመለን ቤተሰብ ሲመለከቱት ይህ ቤት “ከሰሃራ በታች” ነው፡፡
ችግሩ ፣ተስፋ ማጣቱ ፣ስደቱ የተጧጧፈበት፣ ሰው በአይነውሃው የሚጠላበት፣ በተፈጥሮ መልኩ ደረጃው ከፍና ዝቅ የሚልበት፣ ይሄ ቤት “ከሰሃራ በታች” ነው ! እኔ ቤታቸውን ተከራይቼ የምኖረው ስደተኛ ባለቤቶቹ ተወልደው ባደጉበት ጓዳ በችግር ሲሰቃዩ እየታዘብኩ ነውና ይሄ ቤት “ከሰሃራ በታች” ነው፡፡ አዲሳባ እንዲህ ናት ! አገሬ ከነጭ ልብሷ፣ አገሬ ከጠጅና ጮማ ግርጌ እቻትና፡፡ በስስ መጋረጃ ድንበር የተከለሉ ጎረቤቶች አንዱ ብሩን መጣያ አጥቶ በጥጋብ ሽቅብ ሲሸና ከመጋረጃው ጀርባ በረሀብ ከንብል የሚሉ እልፎች የሚኖሩባት አገሬ እቻትና |

ከተመረቅኩ በኋላ አዲስ አበባን ለቅቄ ወደ ቤተሰቦቼ ሄድኩ፡፡ እዛው ስራ ስላገኘሁ አዲስ አበባን
ለአራት ዓመታት ተመልሼ አላየኋትም፡፡ ፋናም በውስጤ ደበዘዘች፡፡ቀስ በቀስ ያች የፍቅር
ጀምበር በመለያየት አድማስ ጠለቀች፡፡ ሌላ ህይወት፣ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገባሁ ፡፡ ከአራት
ዓመት በኋላ የማስተርስ ትምህርቴን ለመቀጠል ወደ አዲስ አበባ መጣሁ ፡፡
ሂድ! ሂድ!” እያለኝ ከስድስት ወራት በላይ እነ እማማ አመለ ሰፈር ሳልደርስ ቆየሁ፡፡ ምን
እንዳስፈራኝ ባላውቅም ውስጤ በፍርሃት ይታመስ ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን ወሰንኩ፡፡ ታክሲ ይዤ ወደ ወሎ ሰፈር ሄድኩ፡፡ ከታክሲ ስወርድ የገጠመኝ ነገር አስደንጋጭ ነበር፡፡ የእነፋና
ቤት ይቅርና ሰፈሩ ራሱ ምልክቱ ጠፍቷል፡፡ ሰፈሩ የለም መንገድ ሆኗል ቀለበት መንገድ
ሆኗል በረሀ ሆኗል፡፡ ወገቤን ይዤ ቆምኩ፤ ግራ ገባኝ፤ እንደ አዲስ ፋና ናፈቀችኝ፡፡ እማማ አመለን ማየት ፈለግኩ ! ሁሉም የሉም፡፡ ተስፋ ቆርጬ ተመለስኩ፡፡
ከብዙ ጊዜ በኋላ የማስተርስ ትምህርቴን አጠናቅቄ በምርቃቴ ማግስት ለምርቃት የተነሳሁትን
ፎቶዬን ለመውሰድ ካዛንችስ ወዳለ አንድ ፎቶ ቤት ሄድኩ፡፡ ሮዳስ የምትባል ልጅ አብራኝ
ነበረች፡፡ ሮዳስ ፍቅረኛዬ ናት፡፡ ፍቅር ከጀመርን ዓመት አልፎናል፡፡ እርሷም እንደኔው አዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ ማስተርሷን ስትሰራ ነው የተገናኘነው፡፡ ፎቶ ቤቱ እንደደረስን ፎቶ ያነሳንን
ልጅ አገኘነው፡፡ የምርቃት ኮሚቴ ሆኜ ስሰራ ፎቶ የሚያነሳው ልጅ ጋር በደንብ ተግባብተናል፡፡
👍21
ፎቷችንን እስኪሰጠን ለእኔና ለሮዳስ ሻይ አስመጥቶልን ስለምርቃት ፎቷችን የባጥ የቆጡን
እያወራልን ስንጠብቅ፣ ድንገት ፎቶ ቤቱ መስተዋት ላይ የተለጠፈ አንድ ሰላሳ በአርባ ሴንቲሜትር
ስፋት ያለው ፎቶ ተመለከትኩ፡፡ ምን አስፈንጥሮ እንዳስነሳኝ አላውቅም፡፡ ወደ መስተዋቱ
ተንደርድሬ ሄድኩና ቆምኩ ፋና ! ራሷ ናት…የራሷ የፋና ፎቶ ነው፡፡
የለበሰችው አጭር ቀሚስ ፍም የመሰለ ቀይ ታፋዋን አጋልጧታል ቢሆንም ፋና ናት ! ዓይኖቿን ጨፍና ወደ ሰማይ አንጋጥጣለች፡፡ ቀይ የከንፈር ቀለም የተቀቡ ከንፈሮቿ በመጠኑ ከፈት ብለዋል፡፡ ፀጉሯ ባጭር ተቆርጦ ወርቃማ ቀለም ተቀብቷል፡፡ ቢሆንም ፋና ራሷ ናት! አፍንጫዋ ተበስቶ ቀለበት ተንጠልጥሎበታል፡፡ ጡቶቿ ደረቷ ላይ በሰፊው እስከ ሆዷ ድረስ ቅድ ባለው ቀሚሷ ምከንያት ግራና ቀኝ በግማሽ ብቅ ብለው ይታያሉ፡፡ ራቁቷን ናት ማለት
ይቀላል፡፡ ተረበሽኩ፡፡ ጩህ..ጩህ አለኝ፡፡

ጓደኛዬን ሮዳስን ረስቻት ጉርድ ፎቶ በመቀስ እየቆራረጠ ከመደርደሪያው ኋላ ወደ ቆመው ፎቶ አንሺ ተመለስኩና ወደ ፋና ፎቶ በእጄ እየጠቆምኩ፣

“ይህችን ልጅ ታውቃታለህ?” ብዬ ጠየቅኩት፡፡

ለአመል ያህል ወዳመለከትኩት ፎቶ ዓይኑን ላከና በፍጥነት መለሰልኝ፣ “ከዚህ ቀጥሎ፣ ቀጥሎ ያለው ሶስተኛው ቤት ውስጥ ትሰራለች፡፡ ከአረብ አገር ነው የመጣችው፣ አዕምሮዋ ትንሽ ትንሽ ችግር አለበት፡፡ ተጠፍራ ነው የመጣችው፡፡ ደግሞ አረቦች ደፍረዋት የወለደቻት አንዲት ልጅ
አለቻት” አለኝ፡፡

“ምንድን ነው ቤቱ ?ማለቴ የምትሰራበት…"

“ቡና ቤት ብሎኝ ወደ ስራው ተመለሰ !

«እና ቡና ቤቱ ውስጥ ምንድን ነው የምትሰራው” አልኩት ባለማመን፡፡
ቀና ብሎ በመገረም ተመለከተኝና፣ “ሴት ልጅ ቡና ቤት ውስጥ ምን ልትሰራ ትችላለች አብርሽ?” ብሎኝ ጥያቄዬን በጥያቄ መለሰልኝ፡፡ ቀስ ብዬ ስዞር ሮዳስ ጎኔ ቆማ ልጁ የተናገረውን ሁሉ ስታዳምጥ አገኘኋት፡፡ ፎቷችንን ተቀብለን ስንወጣ ሮዳስ እንደ ቀልድ እንዲህ አለችኝ፣

“ደግሞ ብለህ ብለህ የሴተኛ አዳሪ አድራሻ መጠየቅ ጀመርክልኝ ?” አልመለስኩላትም፡፡ ሮዳስ ዛሬ ካለችበት የትምህርት እና የኑሮ ደረጃ ላይ ቆመው ቁልቁል ወደፋና ከተመለከቱ፣ ፋና…ከሰሃራ በታች ናት፡፡

አለቀ
11👍4😢2🎉1
አትሮኖስ pinned «#ከሰሀራ_በታች ፡ ፡ #አራት(መጨረሻ) ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ...ከፋና ጋር ከተሳሳምንባት ቅዳሜ በኋላ ዋና ስራችን የእማማ አመለ እና የፍቅርተ እግር ሲወጣ መጠበቅ ሆነ..በቃ ወጣ ሲሉ ፋና ወደ ክፍሌ ሮጣ ትመጣና እቅፌ ላይ ናት፣ከንፈሮቻችን እንዳይገናኙ ማድረግ ከሁለታችንም አቅም በላይ ነበር፡፡ በፍቅር ሰከርን፤አንዳንዴ እማማ አመለ ቤት ውስጥ ሆነውም ፋና ተነስታ ወደ ክፍሌ ትገባለች፣“አብርሽ…»