የግዜርየአደራልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ከብዙ ድካምና ልፋት በኃላ የኖብል ፋውንዴሽን አመታዊ የገቢ ማሰባበሰቢያ ቀን ደረሰ፡፡አሁን በግዙፉ እና ነፋሻማው በወላጆቿ ቤት ሁሉም አይነት ዝግጅት ተጠናቆ እንግዶችን በመጠባበቅ ላይ ናቸው‹‹እርግጠኛ ነህ ምንም ነገር የጎደለ የለም?›› ራሔል ሮቤልን ለአራተኛ ጊዜ ጠየቀችው።
በሙሉ የራስ መተማመን‹‹ሁሉ ነገር በቁጥጥር ስር ነው…አንቺ ምንም አታስቢ›› ሲል መለሰላት፡፡
ራሄል የመጀመሪያ እንግዶች በእርሻ ቦታው ላይ በሰዓቱ ሲደርሱ ስትመለከት ተደሰተች። እሷ እንደዚህ ቀደሞቹ ዝግጅቶች ሙሉ ቁጥጥር አልነበራትም። በዚህም ምክንያት በሁሉ ነገር ላይ በቀላሉ እርግጠኛ መሆን አልቻለችም፡፡
በነገራት ነገር እንዳላመነችው የተረዳው ሮቤል‹‹ ደህና ነን። ነገሮች ጥሩ ናቸው። ሁሉም ሰው በጥሩ ሁኔታ ስራውን እየሰራ ነው። ምንም አትጨናነቂ ዘና በይ … ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዘብ መሰብሰብ ሲጀመር የፋውንዴሽናችን ካዝና ሞልቶ ይፈሳል፡፡ ››አላት፡፡
ከመጠን ያለፈ በራስ መተማመኑን አልወደደችለትም፡፡ቢሆንም ማድረግ የምትችለው ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ያልታሰብ ችግር እንዳይፈጠር መፀለይ ብቻ ነው፡፡ግን ችግሩ መፀለዩም ለእሷ በቀላሉ መደረግ የሚቻል ነገር አይደለም፡፡
ቀስ በቀስ ግቢው በእንግዶች እየተሞላ መጣ…የቅርቧ ሰዎች ጓደኞቾና ዘመዶቾን ጨምሮ ከዚህ በፊት በዝግጅቷቾ ላይ ተገኝተው የማያውቁ ሚዲያ ብቻ ማታውቃቸው በርካታ ታዋቂ እና ዝነኛ ሰዎች እዚህምእዛም ስታይ በጣም ተገረመች…የሚዲያ ሰዎች በየቦታው እየተሹለከለኩ የመረጡትን ሰው ፎቶ በማነሳትና ቃለመጠየው በማድረግ ተጠምደዋል፡፡
የሚገርም ሁኔታ ቀስ በቀስ የበለጠ ነፃነት፣ እና ቀላል ያለ ስሜት እየተሰማት መጣ።ስሯ ያለችው ፀጋ እጇን ስትይዛት ወደቀልቧ ተመለሰች እና ወደታች አጎንብሳ ተመለከተቻት።
በጣቷ ወደ ግራ እየጠቆመቻት‹‹ኤሊ..ኤሊ››አለቻት፡፡ራሄል ጥቆማዋን ተከትላ እይታዋን ወደዛው አዞረች፡፡ዶ/ር ኤልያስ ወደእነሱ እየመጣ ነው፡፡ጥቁር ሙሉ ሱፍ ለብሶ ሽክ ብሏል፡፡ስራቸው ሲደርስ
‹‹ኤሊ. ኤሊ. መጣህ››ትሁት ጮኸች.
የራሄል ልብ ዘለለ፡፡ ዔሊያስ ጎንበስ ብሎ ፀጋን በእቅፉ አስገባትና ስሞ መልሷ አስቀመጣት…። በዚህ ጊዜ ሮቤል ራሄል ጀርባ ደርሶ የሁነ ነገር በሹክሹክታ እየነገራት ነበር፡፡
የኤልያስ የደመቁ ጥቁር ዓይኖቹ ወደ ሮቤል በረሩ፣ ‹‹ኤሊ ሮቤል ይባላል … ረዳቴ ነው .››ብላ አስተዋወቀችው፡፡
‹‹ሮቤል እሱ ደግሞ ዶ/ር ኤልያስ ይባላል…››በቀደም ከንፈሬን የሳመኝ እሱ ነው› የሚለውን ተጨማሪ ንግግር በውስጧ አከለችበት ,፡፡
ዔሊያስ የሮቤልን እጅ እየጨበጠው‹‹ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል።››አለው፡፡
ሮቤል በደማቅ ፈገግታ ተሞልቶ በቀልድ መልክ ››ራሔል ስራዎቾን በውክልና ለእኛ አሳላፋ መስጠት እየተማረች ነው። በተቻለህ መጠን ከእኛ አርቀህ ብትይዝልን ደግሞ ነገሮች ከዚህ በላይ እየተሻሻሉ ይሄዳሉ ››አለው
ኤልያስ የሮቤልን ንግግር እያዳመጠ ዓይኖቹ ራሔል ላይ ተከለ።
‹‹እንዳልከው አደርጋለው.››አለው ዔሊያስ…ሮቤል ተሰናብቶቸው ወደስራው ተመለሰ፡፡
ብቻቸውን ሲሆኑ ራሄል ቀሚሷን ወደታች እየጎተተች ያስቸገረቻትን ፀጋን ወደላይ አንስታ አቀፈቻት እና‹‹በመምጣትህ ደስ ብሎኛል››አለችው ።
‹‹አመሰግናለው››አላት
ፀጋ ፀጉሮሯን እየነጨችና ፊቷን እየቧጨረች አስቸገረቻት‹‹አንቺ ሞኝ ልጅ ..እረፊ… ፀጉሬን ነቀልሽው እኮ››አለቻት ራሄል ።
ፀጋ በደስታ ሳቀች ።
‹‹አውርጂኝ ›› ብላ ጠየቀች እና ዔሊያስም እንድታወርዳት ነገራት።እንዳወረደቻት ለመጫወት ከእነሱ ራቅ ብላ ወደ ሜዳው ኩስ ኩስ እያለች ሄደች፡፡
ራሄል ፀጋ የበታተነችባትን ፀጉር ለማስተካከል እየሞከረች ‹‹መጀመሪያ ወደ ቤት ሄጄ ፀጉሬን መልሼ መስራት አለብኝ›› አለችው፡፡
ዔሊያስ ከፀጉሯ ላይ ያረፈች ሳር እያነሳ ‹‹ባታስተካክይውም ቆንጆ ነሽ ››አላት፡፡
ጉንጯ በእፍረት ቀላ‹‹ አመሰግናለው..ግን እንደምታየው ልብሴንም መቀየር አለብኝ?››
ራሄል አለባበሷ ለስራ ከምትለብሰው ልብስ ጋር ሲነፃፀር የተለመደ ነው ግን ሰሞኑን እቤት ስትውል ከምትለብሳቸው ልብሰች አንፃር በጣም ያጌጠና ያመረ የሚባል ነው፡፡
የዔሊያስ ተንኮል አዘል ፈገግታ ተፈታተናት፣ እጁ ዘንበል ብሎ አገጯን እየነካካ ‹‹ጸጉርሽን እንዲህ ስትለቂው ደስ ይለኛል.››ሲላት ለአፍታ ልብን የሚያቆም ፍርሀት ወረራት፡፡
‹‹እንደገና ሊስማኝ ነው እንዴ?›› ብላ በውስጧ አሰበች። እንዲያደርገው ፈለገች።
ፍርሀቷን በሳቅ ለመሸፈን እየጣረች ‹‹ፀጋ ሳትርቅ ብንሄድ ይሻለናል››አለችው፡፡
ወደፀጋ ሄዱና እያንዳንዳቸው አንዳንድ እጃን ያዙ. ራሄል ከሩቅ ለሚያያቸው ሰው ልክ ወደ ወ.ሮ ላምሮት ቤት ሲሄድ እንደነበሩት ቀን ቤተሰብ እንደሚመስሉ አሰበች። ።ወደጎን ዞር ብላ ስታየው ዓይናቸው ተገናኘ። ቢፌ በተደረደረበት ግዙፍ ጠረጴዛ አጠገብ ሲያልፉ የ ሰላጣ ሳህኖች ባዶ ሆነው አየችና እንደመበሳጨት ብላ‹‹ይቅርታ አድርግልኝ..ይህን ማስተካከል አለብኝ.››አለችውና ተለይታቸው ልትሄድ ስትል ዔሊያስ ፈጠን አለና እጇን በእጁ ያዘ።
‹‹አይ, ይሄ የአንቺ ስራ አይደለም, ሮቤል እና አዲሷ ረዳትሽ ሁሉንም ነገር በቁጥጥራቸው ስር አድርገውታል…ለእነሱ ተይላቸው.››አላት፡፡ራሄል ፊቷን አኮሰታተረች እና ተቃውሞዋን ልታሰማ ስትል አንዲት ተለቅ ያለች ነጭ ዩኒፎርም የለበሰች ሴት በላስቲክ የተሸፈነ ሳህን ይዛ መጣችና ባዶውን የሰላጣ ሳህን ስትሞለ ተመለከተች፡፡
ኤሊያስ ቅንድቡን ከፍ አድርጎ ‹‹አየሽ…ዘና በይ ..ሁሉ ነገር አሪፍ ይሆናል?››ሲል ተናገረ።ራሄል በራሷ ችኮነት አፍራ ሳቀች።
‹‹እሺ በቃ ዘና እላለሁ ።››አለችና ረዥሙ ትንፋሽ ሳበች ፣ ዙሪያውን ተመለከተች እና ይህንን እንደምትለምድ ተገነዘበች። የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ብዙ ጊዜ የተጣደፈ ፣ የተቸኮለ ነበር፣አሁን የምታው ግን የተረጋጋ እና ዘና ያለ ሆኖ ነው ያገኘችው ፡፡አሁንም እየፈገገ ያለውን ዔሊን ተመለከተች እና ከሰዎች ጋር በቀላሉ መዋሀድ መቻል እንዴት ጥሩ እንደሆነ አሰበች። ዔሊም እያንዳንዱን እንግዳ ስታናግር ከጎኗ እንዲሆን ፈለገች።
ራሄል በሳቅ ፈገግታ ተጥለቅልቃ‹‹አስደናቂ ቀን ይሆናል ብዬ አስባለሁ››አለችው ።
ኤልያስም‹‹እንደዛ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ ።››ሲል ተጨማሪ ጥንካሬ ሰጣት።ከዚያም ራሄል ይቅርታ ጠየቀችውና አዲስ ወደገቡት እንግዶች ሄደች፡፡እሱ ፀጋን እንደያዘ በተወሰነ ርቀት ወደኃላ ቀረ፡፡ እንግዶቹን እያወራች ትኩረቷ በዔሊ ላይ ነበር።
ኤልያስ ዙሪያ ገባውን እየቃኘ የራሱን ትዝብት መውሰድ ጀመረ…አዎ እሱም እንደማንኛውም ሰው የራሱ እቅድ ነበረው፣ ነገር ግን ከዚህ ህዝብ ጋር ለመስማማት ትንሽ ከፍ ብሎ ማቀድ፣ ትንሽ መስራት፣ የአምስት አመት እቅድን ቢያንስ ወደ አስር አመት ማስፋፋት ይኖርበታል።እና የዛን ጊዜ በእንደዚህ አይነት ዝግጅት ላይ ከሚሳተፉ ከላይኛው ማህበረሰብ ሰዎች ጋር በደንብ ተቀላቅሎ ዘና ብሎ ማውራት ይችል ይሆናል..እስከዛው ግን እንደተነጠለ መቆየት መርጧል፡፡
በሀሳብ ተውጦ ሳለ ድንገት ከኋላው መጣችና‹‹ሰላም ነህ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ደህና ነኝ። ትንሽ የመጨናነቅ ስሜት እየተሰማኝ ነው።›› ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ብዙ አዲስ ፊቶች ሲመጡ እያየው ነው›› አለች ራሄል ። ‹‹ግን ከጊዜ በኋላ ታውቋቸዋለህ። ››

❤60👍1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ቢንያም እና ዔሊያስ አዲሱ ቤት ውስጥ ሆነው አንዳንድ ነገሮችን እያስተካከሉ ነው፡፡
‹‹እነዚህ ክፍሎች ከተጠናቀቁ በኋላ የሚቀጥለው ፕሮጀክት የሳሎኑን ሴራሚክ ማሰራት ነው›› አለ ዔሊ፡፡
ቢኒያምም ‹‹አዎ..እኔም እንደዛ ነው ያሰብኩት ››ሲል ለሀሳቡ ድጋፍ ሰጠው፡፡
‹‹ሰሞኑን በቤቱ የፊኒሽንግ ስራ ላይ ያለህ ትኩረትና ጉጉት ጨምሮብኛል ..ምነው ?ጉዳዩ ከራሄል ጋር የሚያገናኘው ነገር አለው እንዴ?››ሲል ጠየቀው፡፡
ዔሊያስ የሚናገረው ማንኛውም ነገር በወንድሙ በተሳሳተ መንገድ እንደሚተረጎምበት ስለሚያውቅ ዝም ለማለት ወሰነ ። የቀረውን የእንጨት ፍቅፋቂ ጠራርጎ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ጣላው፡፡
ቢኒያም ወደሌላ ተያያዥ ጥያቄ ተሸጋገረ‹‹በቤተሰቧቾ ግቢ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢ አመታዊ ዝግጅት ላይ ቆንጆዎቹ ጥንዶች እናንተ እንደነበራችሁ ሰምቻለሁ።››
‹‹ስለ ቆንጆው ክፍል አላውቅም, ግን አዎ አብረን ጠቃሚ የሚባል ጊዜ አሳልፈናል.››ሲል መለሰለት፡፡
ቢኒያም መሳሪያዎቹን እየሰበሰበ ‹‹እሷ በጣም የምትስብ ሴት ነች፣ አይመስልህም?›› ሲል አከለበት።
ዔሊያስ ሳጥኑን አነሳና‹‹በአሁኑ ጊዜ ስለእሷ ምንም ላለማሰብ እሞክራለሁ…ካለበለዚያ ችግር ውስጥ ያስገባኛል.››ሲል መለሰለት ።
የሚናገረው ነገር ሙሉ በሙሉ እውነት አልነበረም። ከዝግጅቱ ቀን ጀምሮ፣ ብዙ ነገሮችን ከአእምሮው ማውጣት አልቻለም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እዛው በራሄል ቢሮ ውስጥ፣ ወደ ኋላ የተገፋ.. የተተወ ያህል ተሰምቶታል። በቀጣዮቹ ቀናት ብዙ ጊዜ፣ ወደቤቷ ተንደርድሮ ለመሄድ ስሜቱ ተፈትኗት ነበር።እሱ ግን እንደምንም ተቋቁሞት እራሱን አቅቧል። ለራሄል ልቡን ከፍቶ ነበር፣ እሷም እንዲሁ ያደረገች መስሎት ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ስለእሷ ያለውን ስሜት በትክክል ሲነግራት.. ቀዝቀዝ አድርጋዋለች።‹‹እንደዛ ማድረግ ያለብን አይመስለኝም።›› ነበር ያለችው….ታዲያ ለምን እንዲስማት ፈቀደችለት?እና ለምን አሁንም ስለ እሷ ያስባል? እሷን ከአእምሮው ለማስወጣት ወስኗል። እሱ ትኩረቱን የሚያሳርፍበት የሚሠራው ቤት ስላለው አመሰገነ። እንደ ሞኝ እሷ በቀደደችለት ቦይ ፈቃደኛ ሆኖ እንዲፈስ አድርጋዋለች።
‹‹እሷን እንደ ፍቅር ጓደኛ አድርጎ ማሰብ ከመጠን ያለፈ ነው›› አለ ፡፡
ቢንያም ‹‹ከየትኛውም ሴት ጋር ለተወሰነ ጊዜ አላሳለፍክም። ይህችኛዋ የተለየ ምን አላት?››
ዔሊያስ ሱሪው ላይ ያለውን አቧራ ጠርጎ አራገፈው። ‹‹ እርግጠኛ አይደለሁም።››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ወደሀታል?››
ኤሊያስ ቅንነት በጎደለው እንቅስቃሴ እጁን አወዛወዘ። እሱ ካልወደዳት ለምን አብዝቶ ስለእሷ ያስባል ?‹‹የሆነ ሆኖ ..ለጊዜያዊ ስሜት እንዳልፈለኳት አውቃለሁ››
ቢንያም ቀጠለ‹‹ስለዚህ ጉዳይ ማውራት ትፈልጋለህ?››
‹‹አይ ..ርዕስ ብንቀይር ደስ ይለኛል››አለው፡፡
ቢንያምን ወንድሙ ስሜት ተረዳና ርእሱን ቀየረ ‹‹በቀደም ለሆነ የስራ ጉዳይ…እኛ የነበርንበት የህፃናት የማደጎ ድርጅት ሄጄ ነበር ..አስተዳዳሪዋ ወይዘሪት ሜላት ስለአንተ ስትጠይቀኝ ነበር፡፡ሰሞኑን ፋይል ሲያደራጁ በአንተ ፋይል ላይ በፊት ካሳየችህ የተለየ ነገር እንዳገኘች ነገረችኝ፡፡››
ኤልያስ በሰማው ነገር ደነገጠ ‹‹ታዲያ ለምን አልነገርከኝም? ስለ ወላጆቼ የበለጠ ለማወቅ እንደምፈልግ ታውቃለህ።››
ቢንያም ‹‹ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደተሰማኝ ታውቃለህ.? አሳዳጊ ወላጇቼ የሚያስፈልገኝን ሁሉንም ነገር ነው የሰጡኝ … ስለ ወለደችኝ እናቴ ምንም ግድ የለኝም. አንተም ተመሳሳይ ነገር እንድታደርግ እመኛለሁ ምክንያቱም ወላጆችህ ሞተዋል..ተመልሰው አይመጡም ..በዚህ ጉዳይ ላይ አእምሮህን እንድትበጠብጥ አልፈልግም..ለዛነው ችላ ያልኩት››
ዔሊያስ በማደጎ ወንድሙ ላይ ያለው ብስጭት አደገ ‹‹የአንተ እናት ‹መቼም ቢሆን ከልጄ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ለማድረግ አልሞክርም› የሚል ስምምነት ፈርመዋል።የገዛ የስጋ እናትህ መቼም ቢሆን ከአንተ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዲኖራት አልፈለገችም…. የእኔ ግን የተለየ ነው … የወላጆቼ ትዝታዎች በልቤ ውስጥ ናቸው… ምንም እንኳን አንተም ሆንክ አሳዳጊ ወላጆቻቼ ስለ ወላጆቼ በጭራሽ እንዳውቅ ባትፈቅዱልኝም…..እኔ ግን ፍለጋዬን አላቆምም.››ሲል በቁጣ ተንዘረዘረበት፡፡
ቢኒያም በስክነት ‹‹ ብቻ እንደወንድምነቴ የተሰማኝን ነገሬሀለው….››አለው፡፡
ኤሊያስ ምንም መልስ አልሰጠውም ። እሱ እና ቢንያምን ከዚህ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ተወያይተው ነበር ግን አንድም ቀን አንድ አይነት አቋም አራምደው አያውቁም። እሱ አሳዳጊዎቹ ከማደጎ ቤት ከተቀበሉት በኋላ በእውነት የቤተሰቡ አካል እንደሆነ ለማመን ብዙ አመታት ፈጅቶበት ነበር፣ እና ከዛም የገዛ ወላጆቹ እና የእነሱ አሳዛኝ ሞት ትዝታዎች ብዙውን ጊዜ ጣልቃ በመግባት በእሱና በአሳዳጊ ወላጆቹ መካከል ክፍተት እንደፈጠረ ነበር፡፡
‹‹ስለ መዛግብት ስላልነገርኩህ ይቅርታ… አስፈላጊ ነው ብዬ አላሰብኩም ነበር. ከዚህ ሁሉ በላይ የሆንክ መስሎኝ ነበር.››
ኤልያስ በሀሳብ ነሆለለ።የሚወዳት ልጅ ራሔል ትዝ አለችው፡፡እሷ በሁለቱም በኩል ወደ ኋላ ዞራ የትውልድ ሀረጓን በኩራት መዘርዘር ትችላለች…ከዛም አልፎ በእናቷ የዘር ግንድ ሔዶ ሄዶ ከሰለሞን ዘር ይመዘዛል ብለው እናቷ ነገረውታል…. በዚህም ምክንያት እሷ በተጠየቀች ቁጥር ከየት እንደመጣች ለሰዎች በኩራት መንገር ትችላለች። እሱ ግን የዘር ግንዱ በአጭሩ ብጥስ ብሎ መጥፋቱ ከሌሎች ሰዎች ያነሰ እንደሆነ እንዲሰማው አድርጎታል።አሳዳጊ ወላጆቹን ይወዳቸዋል ። በወጣትነት ዘመናቸው ወደቤታቸው ወስደው… አመፁን እና አስቸጋሪ ፀባዩን ተቋቁመው በፍቅር አሳድገውታል..አሁንም ድረስ ስለእሱ ማሰብና እሱን ከመንከባከብ ሲደክማቸው አይቶ አያውቅም።ልክ እንደእነሱ አማኝ ሆኖ ወደ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ አለመቻሉ እንዴት እንዳሰቃያቸው ያውቃል።ግን በተመሳሳይ ስለስጋ ወላጆቹ ያለውን ቁርጥራጭ ትውስታዎቹን ማጥፋት አልቻለም. ….አልፈለገምም ነበር።
ከረጅም ዝምታ በኋላ ቢኒያም ‹‹ኤሊያስ ልነግርህ የምችለው ነገር የበለጠ ማወቅ ከፈለግክ ከወይዘሪት ሜላት ጋር ሄደህ ራስህ ብትነጋገር ጥሩ ይመስለኛል››የሚል ሀሳብ አቀረበለት፡፡
ዠቨ
‹‹እንደዚያ የማደርግ ይመስለኛል›› አለ.
ዶ/ር ኤልያስ በማግስቱ አስረአንድ ሰዓት ላይ በህፃናት ማሳደጊያ በጎ አድርጎት ድርጅት ቢሮ ውስጥ ከመዘጋቱ በፊት ተገኘው። ምሳ ሰዓት ላይ ስልክ ደውሎ ቀጠሮ ይዞ ነበር ። ወ.ሪት ሜሮን ተከትሎ ወደ ቢሮዋ ሲገባ ልቡ ከተገቢው በላይ እየመታ ነበር።
የራሄል ምስል በአእምሮው ውስጥ ድቅን አለና ለስለስ ያለ ህመም ተሰማው። ‹‹ ዶ/ር ኤልያስ…እንኳን በሰላም መጣህ…ምን እንድረዳህ ትፈልጋለህ?›› ስትል ጠየቀችው ፡፡
‹‹ስለ ስጋ ወላጆቼ አንዳንድ ነገሮች ሚያስረዳ ፋይል እንዳለሽ ተረድቻለሁ›› አለ ።ወ.ሪት ሜላት ጭንቅላቷን በአውንታ ነቀነቀች። ‹‹ብዙ መረጃ አልያዘም ነገር ግን ጥቂትም ቢሆን ምን አልባት የምትፈልገውን ነገር ልታገኝበት ትችል ይሆናል::››
‹‹እና አሁን ማየት ብችል ደስ ይለኛል?››
‹‹እላይ ፎቅ ላይ በሚገኝ መዝገብ ቤት ውስጥ ነው ያለው…ትንሽ ታገሰኝ ይዤ ልምጣ ›› ብላ እዛው የተቀመጠበት ትታው ወጥታ ሄደች፡፡

❤48👍5
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ራሄል ዶ/ር ኤልያስን ማግኘት ስለፈለገች ስልኳን አንስታ መጀመሪያ ሞባዩሉ ላይ ደወለች….ዝግ ነው፡፡ከዛ ሆስፒታል ደወለች፡፡ከተወሰነ ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ እባኮት ዶ/ር ኤልስን ማግኘት እችላለው?››
‹‹ይቅርታ የእኔ እመቤት ዶ/ሩ ዛሬ ስራ ››
‹‹ነገር ግን ዶክተር ኤልያስ የግድ ማግኘት አለብኝ››አለች ኮስተር ብላ፡፡… ራሄል የረጠበ ጨርቅ በፀጋ ፊት ላይ እያስቀመጠች የሰውነቷን ሙቀት ለማስተካከል በመጣር ስልኩን እያወራች ነው። ከሁለት ቀናት በፊት ከቤታቸው ከተከናወናው የበጎ አድራጎት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ጀምሮ፣ ፀጋ ተለዋዋጭ በሆነ የጤና ችግር እየተሰቃየች ነው፡፡
በዛን ቀን ከሌንሳ መንታ ልጆች ጋር አብራ ስትጫወት ነበር ፡፡ምን አልባት ከእነሱ የሆነ ጉንፋን አይነት በሽታ ወስዳ ሊሆን እንደሚችል ጠረጠረች። ሌንሳ ትናንት ለራሄል ደውላ አንደኛዋ ልጇ ትንሽ ንፍጥ እና ትኩሳት እንዳለባት ነግራት ነበር። ለፀጋ በጣም ተጨነቀች፣ እና አሁን ጭንቀቷ ትክክል የሆነ ይመስላል።
በስልክ መስመር ላይ ያለችው የዶክተሩ ፀሐፊ ‹‹ይህን ተረድቻለሁ ግን የሱን ቀጠሮዎች በሙሉ ወደሌላ ቀን ለማዘዋወር በሂደት ላይ ነኝ። ይቅርታ፣…. በቤተሰብ ላይ ባጋጠመው ድንገተኛ ችግር ምክንያት ለአንድ ሳምንት ያህል ወደስራ መግባት አይችልም፡፡››
ራሄል ሴትዮዋን አመሰገነች እና ስልኩን ዘጋችው‹‹ ዔሊ ምን አይነት የቤተሰብ ችግር ነው ያጋጠመው?››ፍርሀት ሰውነቷን ወረራት፡፡ባለፈው ምርጥ ጊዜ አሳልፈው በመጥፎ ሁኔታ እንደተለያዩ አሰበችና እራሷን ወቀሰች፡፡ስለ ፀጋ ምን ማድረግ እንዳለባት መወሰን አልቻለችም፡፡
ፀጋ አይኖቿን በእጆቿ እያሻሸች‹‹መጠጣት እፈልጋለሁ›› አለቻት ።ራሄል አንድ ብርጭቆ ጭማቂ ሰጠቻት፣ከዚያም አብራት በኩሽና ወንበር ላይ ተቀምጣ አቀፈቻት ።ራሄል ብርጭቆውን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች እና ፀጋን በእርጋታ እያወዛወዘች ለስለስ ያለ ዘፈን ትዘፍንላት ጀመር። ሌላ ምን ማድረግ እንዳለባት አላወቀችም።ፀጋ ጧዋት ሙሉውን ጊዜ ስትበሳጭ ነው ያረፈደችው፣ እና የሙቀት መጠኑ በጣም ከፍተኛ ባይሆንም ራሄል መጨነቋን ማቆም አልቻለችም ።ራሄል የእህቷን ጭንቅላት በስሱ ሳመቻት፡፡
‹‹ኤሊ የት ነው ያለኸው?›› ብላ በሹክሹክታ ተናገረች፡፡
ነገሮች እንዴት በፍጥነት እንደተቀየሩ አስቂኝ ሆነውባታል። እሷ በዚህ መጠን እሱን ማነጋገር መፈለጓ በጣም የሚገርም ነው…. የዚያን የዝግጅት ቀን ምን እንደተሰማት ለማስረዳት ፈልጋለች። በሁለቱ መካከል ስላለው ነገር በጥንቃቄ ማስረዳት ፈልጋለች፣ ግን ይህን ማድረግ በእሱ እይታ ምን ያህል የተጋለጠች እንደሚያደርጋት ፍራቻ አድሮባታል። ፀጋን መልሳ ወደ አልጋው ወስዳ አስተኛቻት… ፀጋ አልተቃወመችም… ይህም ለራሄል ልጅቷ ምን ያህል እንደታመመች እንድትረዳ አደረጋት። ከሰአታት ስቃይ በኋላ ተኛች። እሷን ሊያሳስብ በሚችል ጸጥ ባለ ጽናት ነው የተኛችው።ትንሽ ተጨማሪ ጉልበት እንድታሳይ ፈለገች። ለብዙ ደቃቂ ስሯ ከተቀመጠች በኃላ በጸጥታ ክፍሉን ለቃ ወደ ቢሮዋ ሄደች። ከፋውንዴሽኑ የፋይናንስ ክፍል የቀረበውን ዘገባ አነበበች፣ ሮቤል እንዲከታተል የሚያሳስብ ጥቂት ማስታወሻዎችን አዘጋጅታ ጥቂት የስልክ ጥሪዎችን አደረገች።ከዛ ለዔሊያስ ለመደወል ሞከረች… ነገር ግን ያገኘችው የመልስ ማዳመጫ ማሽኑን ድምፅ ብቻ ነው.፡፡
ራሄል ብቸኝነት ተሰማት።ወደ ፀጋ ክፍል ስትመለስ ኮሪደር ላይ አለምን አገኘቻት።
‹‹ራሄል የደከመሽ ትመስያለሽ…ለምን ለትንሽ ጊዜ ወጣ ብለሽ አትመለሺም?ጸጋን እኔ ልከታተልሽ። ››አለቻት፡፡
‹‹ፀጋ አሁንም መተኛቷን ለማረጋገጥ ወደክፍሏ ዘልቃ ገባችና ተመለከተቻት።ተኝታለች ፣ተመልሳ ወጣችና በራፍ ላይ ካለችው አለም ጋር ማውራቷን ቀጠለች፡፡
‹‹ በጣም ፈታኝ ይመስላል…አለም››
‹‹ግድየለሽም …ሞባይልሽን ይዘሽ መውጣት አለብሽ… ፀጋ ተኝታለች፣ ደህና ትሆናለች..ችግር ካለ ወዲያው ደውልልሻለው።››የሚል ሀሳብ አቀረበችላት፡፡
‹‹ራሄል አለም ትክክል እንደሆነች ታውቃለች። ከገቢ ማሰባሳቢያው ቀን ጀምሮ፣ ስለ ዔሊያስ መርሳት አልቻለችም። በምትኩ እራሷን ወደ ስራ እና ፀጋን በመንከባከብ ውስጥ አስገብታ ነበር። ዓይኖቿ እስኪቃጠሉ ድረስ የቢሮዋን ስራ በቤቷ ውስጥ ሠርታለች፣ ነገር ግን እራሷን ስለእሱ እንዳታስብ ለማድረግ የወሰደችው እርምጃ ሙሉ በሙሉ አልሰራላትም። ከሁሉም በላይ ዔሊያስን የሳመችበት ክፍል ውስጥ መገኘቱ ትዝታውን ደጋግሞ እንዲቀሰቀስባት አድርጎታል። በአእምሮዋ ውስጥ ሌሎች ሀሳቦችን ለማስቀመጥ ፤ለጊዜውም ቢሆን ያንን ክፍል ለቃ መውጣት አለባት።ሞባይሎን እና የመኪናዋን ቁልፍ ይዛ ‹‹እሺ ከአንድ ሰአት በኋላ እመለሳለሁ››ብላ ወጣች…. መኪናዋን አስነሳችና ተንቀሳቀሰች፡፡
ከአርባ ደቂቃ ጉዞ በኃላ ራሔል በድንገት የ ዔሊያስ አዲሱ ቤት በሚገኝበት ጎዳና ላይ እራሷን አገኘችው፡፡ የመኪናውን ፍጥነቱን አቀዘቀዘች። እሷ በዚህ መንገድ ለመምጣት አላሰበችም ነበር፡ በእውነቱ የጉዞው ምክንያት ስለ ዔሊ ለመርሳት ነበር። ሳታስበው ግን እሱ ቤት ፊት ለፊት ተገኝታለች፡፡ፀሐፊው የቤተሰብ ችግር አጋጥሞት ከከተማ እንደወጣ ነበር የነገረቻት ነገር ግን የዔሊ ሞተር ሳይክል ከቤቱ ፊት ለፊት ዛፍ ጥላ ስር ቆሞ ነበር።
‹‹ርቆ ቢሄድ ኖሮ ሞተር ሳይክሉን ከእሱ ውጭ ሌላ ሰው መኖር ባልጀመረበት ቤት በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ጥሎ አይሄድም ነበር..››ስትል አሰበች
በውስጧ ሲጉላላ የከረመውን በእሱና በእሷ መካከል ስላለው ነገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስተካከል አለባት።እሷ ዔሊን መንከባከብ ትፈልጋለች, እሱ እንደሚያስብላት ታውቃለች…እሷም በጣም ታስብለታለች…ትጨነቅለታለች፡፡ግን ደግሞ በልቧ ውስጥ ፍራቻ ሚረጭባትን ስሜት ለእሱ መንገር እንዳለባት ታውቃለች፡፡ወደእሱ ለመቅረብ ታመነታ ነበር …አዎ፣ ወደ ሌላ ግንኙነት ለመግባት ፈርታለች። ቀድሞውንም ይሄንን ብታብራራለት ይረዳት ነበር። ሁለቱም ትልልቅ ሰዎች ናቸው። በመሀከላቸው ያለው ነገር ቀላል መሆን አለበት…. መኪናዋን ከሞተር ሞተሩ አጠገብ አቆመችና የቤቱን ደረጃ ወጣች ። የቤቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ገጽታ ውስጡን ለማየት እንድትጓጓ አድርጓታል። የቤቱ ውጫዊ ክፍል በቅርብ ጊዜ የሚጠናቀቅ አይነት ቢሆንም ግቢው ተጨማሪ ሥራ እንደሚያስፈልገው አስተዋለች። ጠርዝ ላይ ባለው የአበባ አልጋ ላይ ምን ዓይነት ተክሎች መቀመጥ እንዳለባቸው በምናቧ እየቀረጸች አሰላሰለች, በሩ ተከፈተ። ዔሊ ከፊት ለፊቷ ቆመ፣ ያልተላጨ ፂሙ፣ ክፍት ሸሚዙ፣ መላ ቁመናውን በሰከንድ ሽርፍራፊ አስተዋለች።
‹‹ሄይ… ራሄል ምን አመጣሽ?››
ፊቱ ላይ ምንም አይነት የተለየ ስሜት ማንበብ አልቻለችም ፡፡ ‹‹ትንሽ አየር ልውስድ ብዬ በመኪና ወጥቼ ነበር፣ድንገት በዚህ ሳልፍ የሞተር ሳይክልህን አየሁና ፣ እናም...››
በእጁ አንድ ወረቀት ይዟል..እጇቹ እየተንቀጠቀጡ መስሎ ተሰማት፡፡ ፎቶ መሆኑን ለየች ፣ወዲያው ከእጁ አመለጠውና ወደቀበት… ራሄል ልታነሳለት ጎንበስ ስትል ኤሊያስ እጁን በፍጥነት ዘረጋና ለቀም አደረጋት።አስደነገጣት፡፡
በሻከረ ድምጹ‹‹ተይው እኔ አነሳዋለው፣ቆሻሻ ነው ›› አላት ፡፡

❤47🔥1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
//////
ራሄል ፀጋን ስታበረታታ‹‹ነይ የኔ ማር ..አንድ ነገር መጠጣት አለብሽ››አለች ። እሷ ግን ከራሔል ደረት ጋር እንደተለጠፈች ጭንቅላቷን ወደ ጎን አዞረች። ራሄል ትንሿን ህፃን በምቾት መያዝ አልቻለችም ሰውነቷ በጣም ሞቃት እና የሚፋጅ ነበረ….ራሄል ዔሊያስ ባሳየት ዘዴ በመጠቀም የሙቀት መጠኑን ለመቀነስ ሞክራ ነበር፣ነገር ግን ለልጁቷ ጊዜያዊ እፎይታ ቢያስገኝላትም፣ የሙቀት መጠኑ ብዙም ሳይቆይ ከደቂቃዎች በኃላ እንደገና ይጨምሯል። ራሄል ደፍራ ለዔሊያስ ደውላ ሁኔታውን ልትነግረው አሰበችና ስልኩን ተመለከተች። ወዲያው ግን ትላንት ቤቱ በሄደች ጊዜ እንዴት እንዳስተናገዳትና ከህይወቱ ጭምር አሽቀንጥሮ እንዳስወገዳት ትዝ ሲላት እጇን ሰበሰበች፡፡ እንደገና መዋረድ ስላልፈለገች ከዔሊያስ ለመራቅ ወሰነች ። ከዛ ምንም ምርጫ ስለሌላት.. የሚሆነውን መጠበቅ ጀመረች፡፡
ከአንድ ሰዓት በኃላ ፀጋ ለውጥ እያሳየች መጣች…ከዛም በላይ እራሷን ችላ መቀመጥና በአሻንጉሊቶች መጫወት ጀመረች…ራሄል በጣም ደስ አላት..ከእሷ እቅፍ ላይ ወረደቻና ግዙፉ ሶፋ ላይ ሆና መጫወት ጀመረች…ራሄልም በተወሰነ መንገድ ስለተረጋጋችላት ተደስታ እዛው አጠገቧ ቁጭ ብላ አንዳንድ ሰነዶችን ማየት ጀመረች…ግን ብዙም ሳይቆይ አስጠሊታ ነገር ተከሰተ ፡፡ፀጋ ከተቀመጠችበት ተነስታ ከእሷ የሸሸውን አሻንጉሊት ለመያዝ እግሯን ስታነሳ የሶፋው ቆዳ አዳለጣትና ወደኃላዋ ወደቀች…ወደኃላዋ ስትወድቅ የሶፋው እጄታ ጭንቅላቷን መታት…ለሌላ ልጅ ቢሆን ምንም አይነት ጉዳት የሚያስከትል አይነት አልነበረም…ፀጋ ግን ልትቋቋመው አልቻለችም፡፡
ራሄል እዛው አጠገቧ ስለነበረች በእጇ የያዘችውን ወረቀት በትና ተንደርድራ ሄዳ አነሳቻት…ክንዷ ላይ ዝልፍልፍ ብላ ዝርግትግት አለች..አይነቾ ግልብጥብጥ አሉ….ራሄል እሪታዋን ስታቀልጠው..ከኪችን አለምና ረዳቷ ከውጭ አትክልተኛውና ዘበኛው እያለከለኩ መጥተው ከበቧት..አለም ፀጋን ከራሄል እጅ ላይ ተቀበለች…‹‹ቶሎ በሉ አምፑላንስ ደውሉ..አንፑላንስ ደውሉ….››ተንጫጩ..ራሄል ራሷን መቆጣጠር አቃታት…ልቧ መጥታ ጉሮሮዋ ላይ እንደተወተፈች እርግጠኛ ነች…መተንፈስ ሁሉ አቃታት..በእንብርክክ ሳሎኑና ታስሰው ጀመር ..…ከ30 ደቂቃ በኃላ አምፑላንሷ ቀፋፊ የሆነ ሳይረኗን እያስጮሐች ደረሰች…ባለሞያዎቹ ከአለም እጅ ጸጋን ተቀብለው በጥንቃቄ ወደውስጥ አስገብተው አልጋው ላይ አስተኞት..ከዛ ወዲያው የመተንፈሻ መሳሪያዎቹን ይሰካኩላት ጀመር… ራሄል በደመነፍስ ተከትላ ገባች…የአምፑላንሱ በራፍ ተዘጋና ተንቀሰቀቀሱ ፡፡
ሆስፒታል ከደረሰችና ፀጋን ለሀኪሞቹ ካስረከበች ከአንድ ሰዓት በኃላ ግን ነገሮች በብዙ እጥፍ እየተባባሱ እንደመጡ መታዘብ ቻለች፡፡ወደ ውስጥ ገብታ ከሚስኪን እህቷ ጎን መሆን ፈለገች…እግሯን ስታንቀሳቅስ ግን ‹‹እመቤት ፣ ወደእዛ መሄድ አትችይም።››ስትን ነርሷ አገደቻት ፡፡
መሄድ አለባት፣ ከፀጋ ጋር መሆን ነበረባት።ነርሷ ‹‹ሀኪሞቹ ሰራቸውን መስራት አለባቸው ልጅሽ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነች››አለቻት፡፡
ልጅሽ የሚለው ቃል አእምሮዋን በጦር ወጋት‹‹..አዎ የአደራ ልጄ ነች››ስትል አሰበች….‹‹ግን አንድ እናት ከማህፀኗ የወጣ ልጅ ሊሞትባት ሲያጣጥር ስታይ ምን አይነት ስሜት ይሰማት ይሆን …?እንዴትስ መቋቋም ትችላለች?››እራሷን ጠየቀች…መልሱን ማሰብ እንኳን ዘገነናት፡፡ ቃላቱ በራሔል አእምሮ ውስጥ ከላይ እንደተወረወሩ ጠጠሮች ወደቁ።ነርሷ ያለችው ገብቷታል.. ግን አልተዋጠላትም።
‹‹ለምን ዶክተሩ ራሱ መጥቶ ምን እየተፈጠረ እንዳለ አያሳውቀኝም ?።››
ነርሷን ስታያት ወጣት እና ከእሷ በላይ አጭር ነች፣ ነገር ግን ክንዷን የጨበጠው እጇ በሚገርም ሁኔታ ጠንካራ ነው።ራሄል ፀጋን ወደ ወሰዱበት ቦታ በጨረፍታ ተመለከተች፣ በተጨናነቀው ክፍል ዞር ብላ ስትመለከት በድንገት የጠፋች አይነት ስሜት ተሰማት። እንዴት እዚህ ደረጃ እንደደረሰች አታውቅም። የሚወዛወዘውን አምቡላንስ በድንጋጤ አስታወሰች፣ ሁለቱ ሰዎች በፀጋ ላይ ሲያንዣብቡ፣ ወደ ኋላ እና ወደ ፊት መመሪያ ሲሰጡ ድምፃቸው ጥርት ብሎ ይሰማት ነበር። መመሪያው በግልፅ ምትረዳቸው አልነበሩም ፡፡ከቤት ተነስተው ሆስፒታል እስኪደርሱ ነገሮች ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ አይነት ነበር…
ነርሷ በእርጋታ እየመራች ወደአንድ ክፍል ይዛት ገባችና ወንበር ስባ አስቀመጠቻት ..እሷ ከኮምፒዩተር ባሻገር ባለው ሌላ ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡ ከዛ ራሄል በጥያቄዎች ዝርዝር ታጣድፋት ጀመር ። አለርጂዎች የለባትም?ምን ምን መድሃኒቶች ነው የምትወስደው?. የሚከታተላት ዶክተር ማን ነው?።እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን ጠየቀቻት፡፡ቢያንስ ለነርሷ አስፈላጊውን መረጃዎች መስጠት ፀጋን በተወሰነ መጠንም ቢሆን መርዳት እንደሆነ በማሰብ በተቻላት መጠን በትኩረትና በትዕግስት መለሰችላት፡፡ በመጨረሻ ተጠናቀቀ ።
ራሄል ከነርሷ የቀረበላትን ውሃ አልተቀበለችም። ‹‹እህቴን መቼ ማየት እችላለሁ?›› ስትል ጠየቀች።
ነርሷ ተነሳች እና በፍጥነት ወደ ክፍሉ ሄደች፣ ራሄል በቁጣ እና በንዴት ተከተለቻት ። ብዛት ያላቸው የማታውቋቸው ዶክተሮች ፀጋ ህክምና ላይ እየሰሩ ነበር፣ ቢሆንም የገዛ እህቷን ፣የአደራ ልጇን እንዳታይ ተከልክላለች..ያ ደግሞ በጣም ያበሳጫል።ዓይኖቿን በመጠባበቂያ ክፍል ውስጥ ካሉት ሌሎች ሰዎች ራቅ አድርጋለች። አእምሮዋም ስቃያቸውንና ጭንቀታቸውን ሊቀበል አልቻለም።በመጨረሻ ነርሷ ተመለሰች።
‹‹አሁን የተረጋጋች ነች። ወደ ህፃናት ህክምና አይሲዩ አስተላልፈዋታል።››ራሄል ደረቷ ላይ ቀዝቃዛ ክብደት ያለው ብረት የተቀመጠባት መስሎ ተሰማት ።
‹‹ተረጋጊ ያልሽኝ መስሎኝ ነበር?።››ስትል ነርሷ ላይ አፈጠጠችባት።
‹‹ትክክል ነሽ ተረጋጊ ብዬሻለው…ግን ጥብቅ ክትትል ሊደረግላት ይገባል።›› ነርሷ ጥንቃቄ የታከለበት ፈገግታ ፈገግ አለችላትና ። ‹‹ለአሁን… ደህና ነች ።››የሚል ንግግር አከለችበት፡፡
‹‹ለአሁኑ?››
‹‹ከፈለግሽ ወደ እሷ ልወስድሽ እችላለሁ።››
‹‹በጣም እፈልጋለው።››ራሄል ነርሷን ተከትላ ተራመደች።ሰውነቷ ኤሌክትሪክ እንደጨበጠ ሰው እየተንዘረዘረ ነው፡፡ ሰዎች ወደ ሞሉበት ኤሊቬተር ውስጥ ገቡ፣ እና ራሄል እጆቿን ተመለከተች…በቀደም በወላጆቾ ቤት ለተዘጋጀው ዝግጅት ብላ የተቀባችው የጥፍር ቀለም ተፋፍቆ ነበር።…አለባበሷን ስታይ የበለጠ ገረማት…ለቀናት ከላዮ ላይ ያልወለቀ የቆሸሸ እና የተጨማደደ ቲሸርት የሆነ እንዴት እንደለበሰችው እንኳን ማታውቀው አመድማ የነተበ ጅንስ ለብሳለች።በህይወቷ እንደዚህ እራሷን ጥላ እና ሙሉ በሙሉ ዘንግታ እንዳማታውቅ እርግጠኛ ነች፡፡ከመቼ ወዲህ ነው ይህቺን ልጅ እደዚህ የወደደቻት….?
ሊፍቱ ቆመና ፣ በሮቹ ተንሸራተው ተከፍቱ.. ራሄል ነርሷን ተከትላ ወደ አንድ ክፍል ገባች
… ወደ ማጠቢያ ገንዳ ተወሰደች እና እጇን እንድትታጠብ ታዘዘች። እጆቿን በማድረቅ ነርሷ አገዘቻት ‹‹ጋውን እና ጭንብል ማድረግ አለብሽ››አለችና አቀበለቻት ።ከዛ ነርሷ በተቆጣጣሪዎች የተከበበ አራት ትናንሽ አልጋዎችን ወደያዘ ክፍት ክፍል መርታ ወሰደቻት።

❤51
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ተደግፋ በተቀመጠችበት ወንበር ላይ ተኮራምታ ነው ያደረችው፡፡በጥዋቱ ተረኛ ዶክተሮች መጥተው እህቷን ቢመለከቷትም ምንም የተቀየረ ነገር አላገኙም…..ይህ መሆኑ ደግሞ ራሄልን ይበልጥ ተስፋ ቢስና ረዳት አልባ ስሜት እንዲሰማት አደረጋት፡፡መፅሀፍ ቅዱሷን አነሳችና …አነስተኛ ወንበር እህቷ አልጋ አጠገብ በማድረግ የፀጋን ትንሽዬ ጣት ይዛ መፀለይ ጀመረች…አምላክ ለሁለተኛ ጊዜ ልቧን እንደማይሰብራት ተስፋ አድርጋለች፡፡ ድንገት ቀና ስትል ዔሊያስ የሕፃናት ሕክምና አይሲዩ በር ላይ ቆሞ ተመለከተችው፣ ልቡ ከብዷል። ስለ ፀጋ እንዳወቀ ወደ ሆስፒታል በፍጥነት ነው የመጣው።
ኤልያስ ወደ ክፍሉ ከመምጣቱ በፊት የህክምና ቻርቱን አንብቦ መድሃኒቱን ሁለት ጊዜ ፈትሾ ነበር ….የፀጋን አሁናዊ ሁኔታ እና እየተደረገላት ያለውን እንክብካቤ ከህፃናት ሐኪም ጋር ተወያይቷል. ሁሉም ምርመራዎች ታዝዘዋል እና ረፋድ ላይ ሌላ ሲቲ ስካን ማድረግ እንደሚያስፈልጋት ተወስኗል።ፀጋ ለጊዜው ራሷን ስታለች ግን የተረጋጋች ነበረች።በአሁኑ ጊዜ ኤልያስን በጣም ያሳሰበው ከፀጋ እጅ ጋር የተጣበቀችው እና የገረጣችው ሴት ሁኔታ ነው፣ በመጋረጃዎቹ ክፍተት መሀል አልፎ የሚመጣው የጠዋት ብርሃን ጭንቅላቷ ላይ አርፎ ይታያል .. መጽሃፍ ላይ አቀርቅራ እያነበነበች ነው ። ራሔል አንድ ጊዜ ስልክ ለመደወል ከፀጋ ጎን ከመነሳቷ ውጭ ሌሊቱን ሙሉ ከጎኗ ሳትንቀሳቀስ እንዳሳለፈች ነርሷ ነግራዋለች፡፡
ለመጨረሻ ጊዜ እሱ ቤት መጥታ በመጥፎ ሁኔታ ካስተናገዳት በኋላ ከእርሷ ጋር የመነጋገር መብት እንደሌለው ተሰማው። በወቅቱ ባለበት ንዴት ተነስቶ በሰራው ስህተት በጣም ተቆጭቶ ስህተቱን ለማረም በመፈለግ ለእሷን ለመደወል ፈልጎ ነበር ..እሷን ማስቀየሙ እንዴት ህይወቱን እንዳመረረበት ሊነግራት ፈልጎ ነበር ። ለምን በእሷ ላይ እንደዛ እንደሆነ እና ስለወላጆቹ ማንነት ያወቀው አዲስ መረጃ ውስጡን እንዴት እንደሰባበረው ሊያስረዳትና አዝናለት ይቅር እንድትለው ለመጠየቅ ፈልጎ ነበር…ግን አንዱንም ማድረግ ሳይችል ነው.. ቆይ በኋላ ..ቆይ ትንሽ ልቆይ ሲል ድንገት ዛሬ ጥዋት ከሆስፒታል ተደውሎለት ስለፀጋ በአደገኛ ሁኔታ መታመም እና ለሊቱን ሙሉ ሆስፒታል እንዳደረች የተነገረውና ሲሮጥ የመጣው፡፡
አዎ አሁን ትልቅ ሰው ነው… አዎ እሱ የበለጠ ጥበበኛ ነው። አዎን፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ጠንካራ ቦታ አለው።ያ ሁሉ ቢሆንም ግን ከወላጆቹ የተቀዳ ተመሳሳይ ድክመት በደም ሥሩ ውስጥ ሊፈስ እንደሚችል መገመቱ አልቀረም ። ብዙውን ጊዜ አንድ ልጅ ከወላጆቹ የሚወርሳቸው ጥሩም ሆነ መጥፎ የባህሪ ውርሶች እንደሚኖሩ ለማወቅ በቂ የታካሚ ታሪኮችን አንብቧል.፡፡ራሄል በቤቱ ልትጠይቀው ስትመጣ መረጃውን ለመቀበል እየሞከረ ነበር…በህይወቱ ውስጥም የት ቦታ ሊያስቀምጠው እንደሚችል ለማወቅ በመጣር ላይ ነበር…. በዛ ምክንያት ነበር እሷን ሊያስቀይማት የቻለው፡፡
በጸጥታ ወደ ክፍሉ ገባ፣ አይኑ ወደ ተቆጣጣሪ ማሽኖቹ ተመለከተ፣ እየፈተሸ፣ እየለካ። ወደ አልጋው አጠገብ ሲደርስ ራሄል .ተስፋ ቆርጣ ታነብ ከነበረው መጽሐፍ ቀና ብላ ተመለከተችው። ፊቷ እርብሽብሽ ብሏል እና ስታለቅስ ተመለከተ።
ፊቷ ላይ ያለው ህመም በግልፅ ይነበባል። ለሌሎች ታካሚ ወላጆች እንደሚያደርገው አይነት በርህራሄ የተሞላ እንክብካቤ ሊያደርግላት ከጎኗ ቆመ። ማድረግ የፈለገው ግን ወደ እቅፉ ጎትቶ ደረቱ ላይ ለጥፎ ግንባሯን ደጋግሞ ለመሳም ነበር፡፡ ሊያበረታታት እና ሊያፅናናት ነበር ሚፈልገው ።
‹‹ደህና ትሆናለች?››አላት፡፡
ራሔል ቀና ብላ ተመለከተችው፣
‹‹ለአሁን የተረጋጋች ናት›› ሲል አከለበት፡፡
በዝምታ እያዳመጠችው ነው፡፡
‹‹ሲቲ ስካን ሰርተንላታል እና ስለ ደም ዝውውሯ ከላቦራቶሪ ውጤት በኋላ እናውቃለን ።››
የራሄል እንባ ዝርግፍ አለ…ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቆመች ፡፡በእጇ ይዛ ነበረውን መፅሀፍ አጠፈችውና ማውራት ጀመረች
‹‹ጉንፋን ብቻ ነበር ያመማት..ድንገት በዚህ ደረጃ እንዴት አቅም ልታጣና እራሷን ልትስት ቻለች?››ስትል ጠየቀችው፡፡
ዔሊያስ ራሱን ነቀነቀ።
‹‹አናውቅም… ከዚህ በፊት እንደነገርኩሽ የፀጋ የጤና ችግር ተደራራቢና የተወሳሰበ ነው….. አንዱ በሽታ ሲጀምር ሌላውም ይከተላል…አሁን በጣም አደገኛ የሆነው በአእምሮዋ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ነው፡፡
‹‹ከዚህ ስቃይ ትወጣለች?››
‹‹በአጠቃላይ ያቺ ትንሽ ልጅ ሳንባዋ ጥሩ ነው፤ልቧ ጠንካራ ነው። ከዚህ በሽታ እንደምታገግም አምናለሁ።››
ራሄል በሚናገርው ነገር ላይ እርግጠኛ እንዳልሆነ ተረዳች፡፡ ‹‹እግዚአብሔር በእርሱ እንድንታመን እንዴት እንደሚነግረን እና የልባችንን መሻት እንዴት እንደሚሰጠን እያነበብኩ ነበር…ይህን ታምናለህ?››ዔሊ ወደ ፀጋ ከዚያም ደግሞ ወደ ራሄል እያፈራረቀ ተመለከተ፡፡
‹‹እኔ በዚህ ወቅት ምን ማመን እንዳለብኝ አላውቅም። ለፀጋ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን እንደሆነ አውቃለሁ። እና እሷን በሕይወት ለማቆየት ባለን ቴክኖሎጂ ላይ እምነቴን ማሳረፍ እመርጣለው።››
ራሄል የደከመ ፈገግታ ፈገግ አለችለት‹‹ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ እግዚያብሄርን አመንኩኝ እና አሳዘነኝ. ..ማለቴ ስለ ኪሩቤል እያወራሁ ነው?››ራሷን ነቀነቀች፣ ከዚያም ቀና ብላ ተመለከተችው…በዛ ቅፅበት ነርሷ ወደ ፀጋ አልጋ መጣች።
‹‹ነርሷ ለሰዓታት እዚህ እንደተቀመጥሽ ነገረችኝ…ሄደን ቡና ብንጠጣ ምን ይመስልሻል? እስክንመጣ እዚህ ያለውን ነገር ነርሷ ትከታተለዋለች?›› አለና በቀስታ እጇን ጎተታት።
‹‹እኛ ስንሄድ ፀጋ ደህና ትሆናለች?።››ስትል ጠየቀች፡፡
ነርሷ እያስተካከለችው ያለውን መቆጣጣሪውን ቀና ብላ ተመለከተች..ወደ ዶ/ር ኤልያስ ተመለከተችና ‹‹አንድ ነገር ከተቀየረ ወዲያውኑ አሳውቅሃለሁ››አለችው ።
‹‹ለአሁን ነገሮች ደህና ሆነው ይታያሉ።››ራሄል ወደ ፀጋ ተመለከተች፣ ፡፡ጥላት መውጣቷ ብዙም ምቾት አልሰጣትም፡፡
በለሆሳሳ‹‹እሺ ..እንዳልክ እንሂድ››አለች ።ኤሊያስ መጽሐፍ ቅዱስን ከእጇ ወስዶ ከፀጋ አልጋ አጠገብ ባለው ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው። ከዚያም ከክፍሉ ይዟት ወደ ካፍቴሪያ ሄደ፡፡ወንበር ስበው ፊት ለፊት እየተዩ ተቀመጡ፡፡የሚፈልጉትን አዘዙ፡፡
አሁንም ከፀጋ ውጭ ምንም ነገር በአእምሮዋ የለም..‹‹ትናንት ከሰዓት ነው፡፡ትንሽ እንደመሻል ብሏት ነበር… ከእኔ በቅርብ ርቀት ሶፋው ላይ ሆና ስትጫወት ነበር…ድንገት አንሸራተታት እና ለስላሳ የቆዳ ሶፋ ላይ ወደቀች እና በጭንቅላቷን ወደኋላ ተኛች… ከዛ ተዝለፍለፈችብኝ..ጮህኩ..ወዲያው አምቡላንስ ተጠራ…ወደዚህ ይዘውን መጡ…..ይሄው እየባሰ ከመሄድ ውጭ ምንም መሻሻል አላየሁም፡፡››
‹‹አይዞሽ……ሁሉም ነገር ሰላም ይሆናል››
ያዘዙት ነገር መጣላቸው…..እሷ ጥቁር ቡና ብቻ ነበር ያዘዘችው፡፡
ትኩር ብሎ ሲያያት ያዘችው….ፀጉሯን ከፊቷ ላይ ገፋች እና ‹‹የባቡር አደጋ የደረሰብኝ መስያለው አይደል?››
ከዚህ በፊት አይቷት ከነበረው በተለየ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ እየተመለከታት ነው ፡፡የለበሰችው ልብስ የተዘበራረቀ እና የተዝረከረከ አይነት ነው… ምንም አይነት ሜካፕ አልተጠቀመችም እና ፊቷ ተጎሳቅሏል እና ደክሟታልል።

❤45👍1🥰1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ዋ
//////
ዔሊያስ በፀጋ አልጋ ጥግ ላይ ቆሟል፡፡ማንኛውም ሕፃን ከማሽን ጋር ተጣብቆ ማየት ሁል ጊዜ ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ይጨምረዋል ፡፡እንደፀጋ አይነት የሚያውቃትና የሚቀርባት ልጅ ስትሆን ደግሞ ነገሩ ከባድ ነው የሆነበት ..በዛም ምክንያት እሱ ዛሬ ጠፍቷል፣ ግን ለማንኛውም ከልምዱ ወጥቶ ወደ ተቆጣጣሪ ማሽኖቹ ተመለከተ። ምንም ለውጥ የለም።በአንድ በኩል ማመስገን ያለበት ነገር ነበር።በሌላ በኩል፣ አሁን ለሃያ አራት ሰአታት ራሷን ስታ ቆየች ማለት ነው። እና ለምን እንደሆነ አላወቀም. ተአምር እስኪፈጠር ድረስ ከመጠበቅ ውጭ ምን ማድረግ እንደሚችል ምንም ሀሳብ አልነበረውም።
ከዚያን ቀደም ብዙ ነገር ሲከሰት አይቷል። ልክ እንደ ራሄል በልጁ አልጋ አጠገብ ሲያንዣብቡ ለነበረሩ ወላጆች አሳዛኝ ዜና አቅራቢ ሆኖ ያውቃል ።የወንድሙ ሚስት በካንሰር ስትሞት በዛ ምክንያት ወንድሙ ሲሰቃይ ተመልክቶ ነበር።
የፀጋ ወላጅ እናት ትዝ አለችው፡፡ጽጌረዳ፡፡አሁን በዚህች ደቂቃ ልጇ ያለችበትን ሁኔታ ሰምታ ብትመጣና ለመጨረሻ ጊዜ ብትሰናበታት ደስ ይለው ነበር፡፡ግን አድራሻዋን ካልታወቀ ምን ማድረግ ይቻላል?፡፡አንድ ቀን ከአመት ወይም ከአስር አመት በኋላ ካለችበት መጥታ‹‹ ልጄስ የት ነው ያለችው? ››ብላ ስትጠይቀው…መቃብር ቦታ ወስዶ ሲያሳያት በአእምሮው ሳለና ዝግንን አለው፡፡‹‹እግዚያብሄር ሆይ እባክህ እርዳኝ››ሲል ለአምላኩ ተማፅኖ አቀረበ፡፡
‹‹እንዴት ነች?›› የራሄል ድምፅ ነበር ከሀሳቡ የመለሰው።
‹‹ ..ምንም ለውጥ የለም …ነገሮች ባሉበት እየሄዱ ነው.›› ወደ እሷ ዞረ፣ በዓይኖቿ ውስጥ ፍርሀት ይነበባል፡፡
‹‹ተኝተሻል?››
‹‹ትንሽ ›› ራሄል ፈገግ አለችለት፣
ከዚያም አንገቷን በቀስታ ዞረች፣
‹‹ሴቶቹ ሄዱ?››ሴት ጓደኞቾ ሊጎበኟቸው መጥተው ነበር፣ እና በእሱ እርዳታ ራሄልን ለጥቂት ጊዜ መተኛት ችላለች ። እሷ በተኛችበት ጊዜ ጓደኞቾ በፀጋ አልጋ አጠገብ ተንበርክከው ሲፀልዩላት አይቶ ነበር።
‹‹አዎ ሄደዋል…ብዙ ቆዩ እኮ››
‹‹ደህና …በመምጣታቸው በጣም ደስ ብሎኛል….እንደዚህ አይነት ጥሩ ጓደኞች ስላለሽ እድለኛ ነሽ››የሚል አስተያየት ሰጣት ፡፡
ራሄል በቀስታ ጉንጯን እየዳበሰች ‹‹አዎ ልክ ነህ…ለጸሎታቸው በጣም አመስጋኝ ነኝ።››አለችና ወደ ፀጋ ሄደች።
በቀስታ መዳፏን ግንባሯ ላይ አሳረፈች ‹‹ስነካት ይታወቃታል እንዴ?›› ብላ ጠየቀችው፡
‹‹አንዳንድ የአካላቷ ክፍል ሴንስ ሊያደርግ ይችላል ። ግን ያንን የምንለካበት ምንም መንገድ የለንም።››
‹‹ግን ከዚህ ኮማ ትነቃለች አይደል? ስትነሳ እንደበፊቱ እራሷን ትሆናለች አይደል?››ጥያቄዎቾ ሁሉ ጭንቀት የወለዳቸው ናቸው፡፡
እሱም ከእሷ ባልተናነሰ በመጨነቅ‹‹ሁሉም ነገር ደህና መሆኑን ብነግርሽ ደስ ይለኝ ነበር››አላት፡፡
በዚህ ሆስፒታል ውስጥ በህፃናት ሀኪምነት ካሳለፈው ከማንኛውም ጊዜ በላይ አቅመ ቢስነት ተሰማው።‹‹ፀጋ የራሷ የሆነ ችግር አለባት ፤ ነገር ግን የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው።››አለና ወደራሄል ተጠግቶ እጇን በእጁ ያዘው።
‹‹ዶክተሯ ስለሆንክ ደስ ብሎኛል››አለችው።
‹‹እዚህ በመሆናችሁ ደስ ብሎኛል.››እጇን ጨመቀ ፣ -ጸጋ በእሱ እጅ ፈውስ ታገኝ ዘንድ ተመኘ። እሷን ከኮማ እንድትወጣ ለማድረግ ትክክለኛውን መድሃኒት በፀጋ ደም ስር ማስገባት ይችል ዘንድ ተመኘ። በራሔል ፊት ላይ ፈገግታ መመለስ ይችል ዘንድ ተመኘ… ያን ሁሉ ነገር ማድረግ ቢችል ተመኘ።ስለ ወላጆቹ ሊነግራት ፈለገ, ለምን እንደገፋት ሊያስረዳት ፈለገ. ነገር ግን ከመናገሩ በፊት አንዲት ነርስ ወደ በሩ መጣች።
‹‹ራሄል ቸርነት? ወላጆችሽ እዚህ ናቸው።››አለቻት፡፡
ድንጋጤ የተቀላቀለበት ብስጭት በእሱ ውስጥ ፈሰሰ።.ራሄል እጁን የበለጠ ጨመቀች፡፡
ነርሷ ራሔልን ‹‹በአንድ ጊዜ ሁለት ጎብኝዎች ብቻ ናቸው ወደ ውስጥ መግባት የሚችሉት …ስለዚህ እነሱ ከገቡ መውጣት አለብሽ።››ስትል አስጠነቀቀች።
ወደ ፀጋ ዞር ብላ ተመለከተች እና ‹‹ገባኝ።››አለቻት።
ደ/ር ኤልያስ የአቶ ቸርነት እና የትርሀስ ጸጥ ያሉ ድምጾችን እና የራሄልን ዝቅተኛ ምላሽ እስኪሰማ ድረስ በአልጋዋ አጠገብ ቆየ።የራሄል እናት አቶ ቸርነት እየገፏቸው በዊልቸር ላይ ነበሩ፣ ። ሀኪሞቹ ለልጃቸው ምን እየሰሩ እንደሆነ በአጭሩ አስረዳቸው እና… የተሻለ ዜና ሊነግራቸው ቢችል ደስተኛ ይሆን እንደነበረ በፀፀት ስሜት ነገራቸው፡፡
‹‹በሰው የሚቻለውን ሁሉ እንደምታደርጉ እናምናለን›› አሉ አቶ ቸርነት፡፡የሚያጽናና እጃቸውን በዔሊያስ ትከሻ ላይ ዘረጉና።
‹‹እኛ ከትንሿ ልጃችን ጋር ስለምንቆይ ለምን ራሄልን ለጥቂት ሳዕታት ማረፍ ወደምትችልበት ቦታ አትወስዳትም.››አሉት
እሱም መስማማቱን ጭንቅላቱን በመነቅነቅ አረጋገጠላቸው፡፡
‹‹ይቅርታ እማዬ…አደራችሁን መወጣት እልቻልኩም››አለች እና እንባዋ እርግፍ አለ!! ከዛ እናቷን ለመሳም ጎንበስ አለች፡፡
እናትዬው የልጇን ፊት በእጆቿ አሻሸች‹‹ልጄ እህትሽን በአደራ አልሰጠሁሽም..እሷ ለሁላችንም የእግዚያብሄር አደራ ነች…የተቀበልናት ከእግዚያብሄር ነው….አይ እፍልጋታለው ብሎ መልሶ ከወሰደብንም ከእሷ ጋር ስላሳለፍናቸው ጣፋጭ ወራቶች ከማመስገን ውጭ ምንም ማለት አንችል ..ብቻ በዚህ አይነት ጉዳይ ዳግመኛ ወደዚህ ሆስፒታል እንድትመጪ ስላደረኩሽ አዝናለሁ።››
ራሄል እንባዋን ዘረገፈችው‹‹እማዬ እኔ እኮ እምነቴ እንደእናንተ ጠንካራ ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር..ግን አልችልም››
ወ.ሮ ትርሀስ‹‹ልጄ፣ትቺያለሽ ልብሽን ብቻ አለስልሺው… ይሄ የእኔ ስህተት ነው ብለሽ ለአንድ ደቂቃ እንኳን እንዳታስቢ…እሷን ለመርዳት በአቅራቢያዋ ስለነበርሽ ደስ ብሎኛል. እግዚያብሄር ይሁን ያለው ነገር ማንም ከመሆን ሊያግደው አይችልም.››በማለት የራሔልን ጭንቅላት ወደ ታች ጎትተው ግንባሯ ላይ ሳሟት።
ቀጥለው የተናገሩት አቶ ቸርነት ናቸው‹‹ አሁን ሄደሽ ቡና ጠጪ። ትንሽ እርፍት ውሰጂ እኛም ከናፈቀችን ልጃችን ጋር ትንሽ እንቆይ ።››ራሄል ደካማ ፈገግታ ሰጠቻቸውና, ክፍሉን ለቃ ስትቀወጣ ኤልያስ ከኋላዋ ተከተላት፡፡
‹‹ከእኔ ጋር መምጣት የለብህም››
‹‹አይ መምጣት ስለምፈልግ ነው፣…እንደውም ተከተይኝ ቆንጆ እርፍት የምታደርጊበት ያልተያዘ ክፍል አውቃለው፡፡››አለና ክንዷን ይዞ እየመራ ወሰዳት…ክፍሉን ከፍተው ሲገቡ ግን እንደጠበቁት ባዶ አልነበረም ፡፡ ሲገቡ አንድ ወጣት ባልና ሚስት ከአልጋው ተነሱ..እና ለመውጣት ወደበሩ ተንቀሳቀሱ።
‹‹እባካችሁ በእኔ ምክንያት አትውጣ››አለችው ራሄል።
ሴትየዋ በከፍተኛ ፈገግታ ‹‹እኔና ባለቤቴ እየሄድን ነበር፣እዚህ ያለንን ቆይታ ጨርሰን ወደቤታችን እየሄድን ነው…››አለች
‹‹ለዚያ አመሰግናለሁ.››ወጣቱ እጁን በሚስቱ ትከሻ ላይ አድርጎ አቀፋት፡፡ እሷን ዘና ብላ ራሷን በትከሻው ላይ አስተኛች።ዔሊያስ የቅናት ስሜት ተሰማው። ደስተኛ ሆነው ይታዩ ነበር። እሱ እና ራሄል እንዲኖራቸው የሚፈልገው እንዲህ አይነት ፍቅር እና መፈቃቀድ ነው ።በሩ ከኋላቸው ተዘግቶ ሳለ፣ ፊቷ የናፍቆት መልክ ይዞ ራሄልን እያያቸው ያዘ።
‹‹ወደ ቤታቸው መሄድ በመቻላቸው ደስ ብሎኛል››አለች በለስላሳ።
ክፍሉ ውስጥ ግድግዳ ተጠግቶ ካለ ሶፋ ላይ ተቀመጠና በረጅሙ የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰች፡፡

❤45👍3
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
//
ራሄል የእናቷ የቀዘቀዙ እጆቿን ይዛ በሆስፒታሉ የእንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ባለው የሶፋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣለች። ቄሱ በአጠገባቸው ተቀምጦ፣ መዝሙር 46ን ሲያነብ አቶ ቸርነት ከመግቢያው በራፍ ጋር ቆመው በትካዜ ጎብጠው ይታያሉ፡፡
‹‹ እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው፥ ስለዚህ ምድር ብትናወጥ ተራሮቸም ወደምድር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም፡፡
።››ራሄል ቃላቷ በተዳከመ እና በዛለ አእምሮዋ ላይ እንዲያርፍ እየሞከረች ነው፡፡
"ቸርነት ከእኛ ጋር ትቀላቀላለህ?" ቄሱ ጠየቁ።
አቶ ቸርነት እንደመባነን አሉና ጭንቅላታቸውን በአውንታ በመነቅነው ወደእነሱ ተንቀሳቀሱ…ከራሔል አጠገብ ተቀመጡ።ቄሱ የአቶ ቸርነትን እና የወ.ሮ ትርሀስን እጅ ያዙ፣ ቸርነት ደግሞ የራሄልንን፣ ራሄል የእናቷን ያዘች፣ ክቡኑ ዘጉት ።ቄስ መጸለይ ጀመሩ። እሱ ፈቃዱ ከሆነ ፀጋን እንዲወስድ ሲጸልይ፣ ራሄል ተቃውሞዋን በጮኸች አሰማች።ግን የእናቷ እና የአባቷ እጆች እጆቿን ሲጨምቋት የተከፈተ አፏን መልሳ ዘጋች፡፡ እግዚያብሄር የሚፈልገው ያንን ከሆነ ፀጋን መልቀቅ እንዳለባት አወቀች፣ሲጨርሱ፣ ወደ ቄሱ ቀና ብላ ተመለከተች።
‹‹ አመሰግናለሁ…እዚህ መገኘትዎ በጣም አስፈላጊ ነበር.››አለች፡፡
ቄሱ ፈገግ አሉላት እና‹‹እኛ ቤተሰብ ነን ራሄል ..እርስ በርሳችን እንረዳዳለን።››
‹‹አውቃለሁ እናም ለዚህም አመሰግናለሁ.››
ከሶፋው ተነሳች፣ ድንገት እረፍት ማጣት ተሰማት።እህቷን ማየትም ፈልጋለች። ነገር ግን ኤሊያስና እና ነርሶቹ ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች አያስፈልጋቸውም። የአይሲዩ ተከፋች በሮች መስኮቱን እየተመለከተች በሩ አጠገብ ቆመች። ከእነሱ ቀጥሎ አንድ ነርስ በችኮላ ጋሪ እየገፋች ወደ ፀጋ ክፍል ስትሮጥ ተመለከተች፣ እና ልቧ ወርዶ የጎድን አጥንቷ ውስጥ የተሰነቀረ መሰላት፡፡ …
‹‹ምን እየሆነ ነው?ጌታ ሆይ እባክህ እሷን ከእኛ ጋር አቆይ… እባክህ…ትንሽ እንንከባከባት። ›› ፀሎቷን ሳታቆርጥ ወደበሩ ቀረበች ።አንገቷን አስግጋ እና አይኖቾን አጨንቁራ በመስኮቱ ወደውስጥ ለማየት ሞከረች..ነገሮች ጥሩ እየሄዱ እንዳልሆነ ያስታውቃል..ሁሉም ከወዲህ ወዳያ ይሯረሯጣሉ….ሚስኪኗን ፀጋን ከበዋታል…
‹‹ቢ.ፒ. እየወረደ ነው›› አለ ‹‹ፈሳሽ ቦልስ ስጧት.›› ሌላ ማሽን ጠፋ።ሌላ ነርስ ‹‹የኦክስጅን መጠን እየቀነሰ ነው›› .ከማሽነቹ የሚወጣው ሲጥሲጥታ ይሰቀጥጣል….ሁሉም ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሆነ ነው የሚያወራው…ራሄል በምታየውና በምትሰማው ነገር እራሷን መቆጣጠር አቅቷት ጩኃቷን ስትለቀው በኮሪደሩ አካባቢው የነበሩ ሰዎች ሁሉ ትኩረት ወደእሷ ዞረ…ሁኔታውን የተረዳች አንድ ነርስ ፈጠን ብላ መጣችና የመስታወቱን መጋረጃ ከውስጥ በመሳብ ዘጋችው፡፡
…በሁሉም ፊት ላይ ድንጋጤ እና ተስፋ መቁረጥ ነው የሚነበበው…ከኤልያስ በስተቀር ሌሎች ያከተመ ነገር አድርገው በመውሰድ እጃቸውን ሰብስበዋል…እሱ ወደጆሮዋ ጎንበስ አለና ‹‹የእኔ ቆንጆ መልአክ …ከእኛ ጋር ቆይ። ራሄል ትፈልግሻለች። ሁላችንም እንፈልጋግሻለን።››አላት..እሱ ሊደርግ ሲገባው ያላደረገው ምንም ነገር ስለሌለ ..አምላክ ጥንካሬ እንዲሰጠው ጸለየ፣ ጥበብ ለማግኘት ጸለየ እና ይህች ትንሽ ልጅ እንድትቆይ እንዲፈቀድላት ተማጸነ።ከዛም ወደፀጋ ተመለሰና በደመነፍስ ሚችለውን ነገር ሁሉ መሞከር ጀመረ…ከ10ደቂቃ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ትግል በኃላ መቆጣጠሪያ ማሽኖቹ ድንገት የምስራች ማሰማት ጀመሩ….ሁሉም ማመን አልቻሉም…
አንድ ነርስ ‹‹ቢ.ፒ. እየወጣ ነው›› አለች.፣ኤሊያስ ቀና ብሎ ማሽኑን ተመለከተ፣ ትንሽም ቢሆን ምላሽ የመስጠት ምልክት ማሳየቷ የተስፋ ጭላንጭል በልቡ ፈነጠቀ፡፡
በመቀጠልም ‹‹ የኦክስጅን መጠን እየጨመረ ነው››አለች ነርሷ ።
ሁሉም በደስታ ተሳሳቁ…ፀጋ አምልጣ እንደነበር ሁሉም ባለሞያዎች ተቀብለው ነበር…ተአምሩን በደስታ በመተቃቀፍ ተቀበሉት… እናም እሷን ቀስ በቀስ ለማረጋጋት አስፈላጊውን ሁሉ አደረጉ፡፡ዔሊያስ የተረጋጋች መሆኗን በደንብ እስኪያረጋግጥ ጥቂት ጊዜ ቆየ። ከዚያም ለራሔልና ወላጆቿ ሊነግራቸው ወጣ።
ፍፅም በድካም ዝሎ እና መላ ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ ነበር…የዛሬው ህክምና በእሱ እውቀት ሳይሆን በአምላክ ጥበብ ነው የተሳካው።ምን ተጠቅሞ ምን አድርጎ ከሞት ወደህይወት እንደመለሳት የሪፖርት መዝገቡ ላይ አስታውሶ መፃፍ አይችልም….ብቻ በመጨረሻ ተቆጣጣሪው እግዚአብሔር ነበር።ለእሱ ብሎ ሳይሆን ያቺን ሚስኪን ልጅ ተጨማሪ ጊዜ በምድር እንድትኖር ስለፈለገና ለእሷ ሚሆን እቅድ ስላለው ነው..አዎ እንደዛ ነው የገባው፡፡ በኮሪደሩ ላይ ወደ ቤተሰቧ ሲሄድ እያሰበ የነበረው ይሄን ነበር ፡፡
ራሔል ሲመጣ አይታ ወደእሱ ተንደረደረች… እሱም ወደ እሷ ሮጠ፣
‹‹ደህና ትሆናለች?››
‹‹ጌታ ይመስገን..አስቸጋሪውን ጊዜ አልፈነዋል››
ራሄል ተነፈሰች። ተጠምጥማ አቀፈችው…ከዚያም እንባ አፈሰሰች።ከዛ እህቷን እንድታያት ወደውስጥ ይዞት ገባ ፡፡
የፀጋ አልጋ ጋር ቆማ ቁልቁል በስስት እያየቻት‹‹ጥሩ ትመስላለች››ስትል በሹክሹክታ ተናገረች። ወላጆቿ ከአንድ ሰአት በፊት ነበር ፀጋ እየተዳከመች ስትሄድ ሞቷን ቁጭ ብለው ላለማየት ወደቤተክርስቲያን ለመፀለይ ተያይዘው የሄዱት፡፡
ራሄል ጸጋ ከኮማዋ እስክትነቃ ድረስ ከአልጋዋ ጎን መነጠል እንደማትፈልግ ተናገረችው..እሱ ግን እንደዛ ማድረግ እንዳማትችልና ለ5 ደቂቃ አይኗን አይታ እንድትረጋጋ ብቻ አስቦ እንደፈቀደላት በትህትና አስረዳት፡፡
ኤሊያስ ከ ጀርባ ቆሞ እጆቹን ትከሻዋ ላይ አደረገ እና ‹‹አሁን ደህና ትሆናለች..አታስቢ ››አለ
‹‹አመሰግናለሁ…አንተ ድንቅ ዶክተር ነህ.››አለችው
‹‹እኔ ዶክተር ብቻ ነኝ…የዳነችው በተአምር ነው›› አለ.
ራሔል ከዔሊ አጠገብ ተነስታ ወደ እኅቷ ቀረበችና ጎንበስ ብላ ጭንቅላቷን በስሱ ሳመቻት ።‹‹ጥሩ እንቅልፍ ተኚ የእኔ ውድ ››አለች። ከዚያም ወደ ዔሊ ዞረች።
‹‹እዚህ መቆየት አይቻልም ካልክ… አሁን ለመሄድ ዝግጁ ነኝ.››አለችው…ራሄልን አልፎ ሄዶ የፀጋን ጉንጭ በአንድ ጣቱ ነካ።
‹‹ጌታሆይ አመሰግናለሁ››ብሎ በሹክሹክታ አመሰገነ። ከዚያም አብረው ከክፍሉ ወጡ በኮሪደሩ ላይ ወደ አሳንሰሮች ሄዱ። ሲከፈት ተያይዘው ገቡ፡፡ ድክምክም ብሏታል…ደረቱ ላይ ደገፍ አለችበት፡፡
እጆቹን በደረቷ ዘርግቶ አቀፋትና ወደታች ተመለከታት እና ቀስ ብሎ ወደታች ጎንበስ በማለት ከንፈሯን ሳመ።‹‹ሁሉንም የታካሚዎችህን ዘመዶች እንደዚህ ነው የምትስመው?›› ብላ በፈገግታ ጠየቀችው።
‹‹በጣም የሚያስጨንቁኝን እና የምወዳቸውን ብቻ ነው የምስመው››
ራሄል የሚንቀጠቀጡ ጣቶቿን አነሳችና ጉንጯ ነካች፣ እይታዋ አሁንም በሱ ተጋርዷል።
‹‹እና እነዚያ ስንት ናቸው?››
‹‹አንድ ብቻ›› አገጮን ቀና አድርጎ በድጋሜ ሳማት።መልሳ ሳመችው፡፡
‹‹እወድሀለው ዶ/ር ኤሊ ። ››
‹‹መቼም ቢሆን እነዚህን ጣፋጭ ቃላት ከአንደበትሽ ታወጪያለሽ ብዬ አስቤ አልውቅም ነበር››በማለት ፈገግ አለና እንደገና ሳማት… እና እንደገና።

❤41👍7
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
//
ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡
ፀጋ ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡
ራሄል ከተቀመጠችበት ተነሳችና የፀሐይ መነፅሯን ወደ ጭንቅላቷ ገፋ በማድረግ እህቷ የፈለገችውን አበባ ቀነጠሰችና በትናንሽ እጆቾ ውስጥ አስቀመጠችላት…ፀጋ በደስታ ፈነጠዘች፡፡
ሮቤል እና አዲሷ ረዳት የፋውንዴሽኑን ስራ ከአሰበችው በላይ በጥሩ ብቃት እየመሩላት እንደሆነ ለሁለት ቀን ወደቢሮ ተመልሳ ባደረገችው የስራ ግምገማ መረዳት ችላለች፡፡
…እህቷን ለማስታመም በሆስፒታል ባሳለፈቻቸው አስር ቀናት ውስጥ ምንም የጎደለ እና ሳይሰራ የተወዘፈ ስራ አልነበረም…እና አሁንም ለሌላ አንድ ሰምንት ታናሽ እህቷ በደንብ እስክታገግም አብራት እንድትሆንና ቀለል ያሉ ስራዎችን እዛው እቤት ሆና እንድትሰራ ፈቅደውላት እሷም ተስማምታ ወላጇቾ ቤት ነው ያለችው፡፡
‹‹ኤሊ እመጣለሁ ያለው መቼ ነው?››ወ.ሮ ትርሀስ መጽሃፏቸውን ከጎኗቸው ባለ የመስታወት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ራሄልን ጠየቋት።
‹‹ከሶስት እስከ አራት ሰዓት እመጣለሁ ነበር ያለው ፡፡ ››መለሰች…ጸጋ ራሷ ቀጥፋ የሰጠቻትን አበባ ፀጉሯ መካከል ሻጠችላት…ራሄል በፈገግታ እህቷን ወደራሷ ሳበችና ጉንጮን በመሳም‹‹ትንሿ እህቴ ..እንዲህ ስላሳመርሺኝ አመሰግናለው››አለቻት፡፡
በዛው ቅፅበት ወደግዙፉ ግቢ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ተሰማ ፡፡
‹‹የምትጠብቂው ጓደኛሽ አለ እንዴ?››አቶ ቸርነት ጠየቁ፡፡
‹‹ አይ አይመስለኝም?››ራሄል እርግጠኛ ባለመሆን ጠየቀች፡፡
‹‹እንግዲያው አለም መጥታ ማንነቱን እስክታሳውቀን እንጠብቅ ?››በማለት እናቷ ሳቁ።
አለም ወዲያው እየተፍለቀለቀች መጣች…‹‹ራሄል ነይ እንግዳሽን ተቀበይ››
‹‹ማን ነው?››
‹‹አትንገሪያት ተብያለው…እራስሽ መጥተሸ እይው››አለችና ወደኪችኗ ተመለሰች፡፡
ራሄል.‹‹ማነው በወላጆቼ ቤት ከእኔ ጋር እንዲህ አይነት ጫወታ ለመጫወት የደፈረው?››በማለት ተነስታ ፀጋን ይዛ ሄደች።ራሄል እና ፀጋ ወደ ግቢው የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ሲሄዴ ኤሊ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት ።ራሄል እንዳየችው በውስጧ የደስታ ማዕበል አጥለቀለቃት።
ባለመኪና ስትጠብቅ ባለሞተር ሰው በማየቷ ተደንቃ ‹‹ሄይ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ? የሞተር ሳይክልህን ድምፅ አልሰማሁም።››አለችው…
ዔሊ ጎንበስ ብሎ በቀስታ ሳማት እና ፀጋን አንስቶ ካቀፋት በኃላ‹‹ሌላ አይነት የመጓጓዣ ዘዴ ነው የተጠቀምኩት.››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ሞተርህ ተበላሸች እንዴ ?›› አለችና አይኖቾን ወደመኪና ማቆሚያ አዞረች ከእሷ ቀይ መኪና አጠገብ የቆመ ባለ ሰማያዊ ቀለም መኪና እያየች ግራ ተገባች።
‹‹ ያን መኪና ከማን ነው የተዋሰከው? ወንድምህ እንደዚህ አይነት መኪና የለውም።››
ዔሊ ተነፈሰ። ‹‹እነሆ፣ ወ.ሮ ራሄል ሞተሬን ሸጥኩት።››
ራሄል መኪናዋን በድጋሜ ተመለከተች፣ ‹‹ሞተር ሳይክልህን አስወገድከው !አየህ እኔ ስለ አንተ የምወደው ያን ነው ። ቆንጆ እና ፈጣን ተማሪ ነህ….ግን ለምን?››
…‹‹ደህና፣ በአንድ ወቅት አንድ ሰው እንዴት አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ለዛውም የህፃናት ሀኪም የሆነ ሰው ሞተር ሳይክል ይነዳል ? የሚል ጥያቄ ጠየቀኝ። እና ለእሱ መልስ ለመስጠት ብዬ ነው መኪና የገዛሁት፡፡››
ራሄል ወደ መኪናው ሄዳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ትንሽ ነካችው፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለሰች፣ ››
‹‹አስደንቀኸኛል ››አለችው
‹‹ስለሞተር ሳይክሎች ያለሽን ስሜት ስለማውቅ እናም የፍራቻሽም ምክንያት በከፊል ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት ነው...››
እዛው የሳሎኑ በረንዳ ላይ ካሉ ወንበሮች አንዱን እንዲቀመጥ ሳበችለት ፀጋን በክንዱ እንዳቀፈ ተቀመጠ….ከጎኑ ሌላ ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡
ከዛ ሳታስበውና ምንም ሳትዘጋጅበት ትልቅ ቁም ነገር ከአንደበቱ አፈትልኮ ወጣ ‹‹ይህን ሁሉ በትክክለኛው መንገድ ይፋ ማድረግ ፈልጌ ነው …ራሄል፣ ላገባሽ እፈልጋለሁ።››አላት፡፡
ጆሮዎቾን ማመን አልቻለችም…ልቧን ደረቷን ሰንጥቆ እንዳይወጣ የፈራች ይመስል ደግፋ ያዘችው ። በውስጧ የሚንተከተከው ደስታ እና ፍቅር እና ምስጋና መውጫ ለማግኘት እየሞከሩ በአንደበቷ ላይ ተንገዋለሉ….ማልቀስ ብቻ ነው የቻለችው፡፡
‹‹ሄይ እኔ ያን ያህል መጥፎ ነገር አልተናገርኩም….ለምን ታለቅሻለሽ?››
‹‹በጣም ደስ ብሎኝ ነው…..››ስትል በለሆሳሳ መለሰችለት፡፡‹‹እወድሀለሁ ኤሊ›› ወደ እሱ ተሳበችና ጉንጩን ሳመችው..ታፋው ላይ የተቀመጠችው ፀጋ በደስታ እጆቿን እያጨበጨበች በሳቅ ተንከተከተች። የእሷ ሳቅና ደስታ ወደ እነሱም ተጋባ፡፡
‹‹መጀመሪያ ዝም ብዬ ለአንቺ ምንም ሳልነገርሽ ወደቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ለመላክ አቅጄነበር …››
‹‹እንዴ የእኔን ሀሳብ ሳታውቅ ሽማግሌ ልከህ እምቢ ብልህስ?››
‹‹ያው ምን አደርጋለው የተሰበረ ልቤን ይዤ የብቸኝነት ኑሮዬን ቀጥላለዋ !!››ብሎ ትከሻውን ነቀነቀ።ራሄል ጣቷን ከንፈሩ ላይ አድርጋ ሳቀች።
‹‹ ስለነርከኝ ደስ ብሎኛል፣ደግሞ ስትነግረኝ ፀጋ በመሀከላችን መገኘት በመቻሏ ደስታዋ ድርብ ሆኗል … ለነገሩ እኛን አንድ ያደረገች እሷ ነበረች.››
‹‹እሺ ስላልሽኝ ደስ ብሎኛል…:በዚህ ምክንያት በህይወቴ ለሆነው ነገር እግዚአብሔርን በየቀኑ አመሰግነዋለሁ:: በአንቺ ምክንያት ህይወቴ መሉ ሆኗል››
‹‹አንተ ስጦታዬ ነህ ኤሊ ›› አለችና አቀፈችው።
‹‹አሁን እናትና አባትሽን እንፈልግ።››
ተስማሙና …ተያይዘው በአረንጓዴ ተክሎች ወደተሸፈነው ግዙፉ ጊቢ ተያይዘው እየተሳሰቁ ሄዱ፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

❤74👍18
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ዶ/ር ኤልያስ ዛሬ ምን አልባትም በህይወቱ ፍፁም የሆነ ደስታ የተሰደሰተበት ቀን ስለሆነ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቷት ጥንቅቅ ብሎ ባለቀ ውብ ቤቱ ውስጥ ከክፍል ክፍል እየተመላለሰ እንደህፃን እየቧረቀ ነው፡፡ስልኩን አነሳና ደወለ…፡፡ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ውድ ባለቤቴ እንዴት አለሽልኝ››
‹‹አንተ ያንን ቃል መጠቀም የምትችለው እኮ ሰማንያ ፈርመህ ቤትህ ስታስገባኝ ነው››አለችው እየሳቀች፡፡፡
‹‹ያው በይው..ዜናውን አልሰማሽም እንዴ…..?ሽማግሌዎቼ እኮ ወላጆችሽ ልጃቸውን ሊሰጡኝ በደስታ መስማማታቸውን አሁን ነግረውኝ በደስታ እያበድኩ ነው፡፡››
‹‹ከአንተ ቀድሜ ሰማሁ…ምነው ይከለክሉኛል ብለህ አስበህ ነበር እንዴ?››
‹‹እንዴ ምን ይታወቃል…..ምን አልባት ቅድሞ እደጅ እየጠና ያለ ብረት መዝጊያ አማች ኖሮ ሀሳባቸው ወደእሱ ቢያጋድልስ?››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው …ለአሁኑ ግን ተርፈሀል››
‹‹እኔም መትረፍ የምፈልገው ለአሁኑ ብቻ ነው…የማገባው አንዴ ብቻ እኮ ነው…››ተሳሳቁ፡፡
‹‹እና ይሄንን ደስታ አብረን ማክበር የለብንም ትያለሽ…?››
‹‹አንተ ..ከአሁን ወዲህ እኮ እስከሰርጌ ቀን ድረስ ልታየኝ አይገባም…››
‹‹እንደዛ ከሆነማ ሰርጉን ነገውኑ ደግስ በይኛ››
‹‹አዎ ..ያን ያህል ከቸኮልክ አድርገው››
‹‹እሺ..አስበብበታለው..እውነት ግን በጣም ላገኝሽ ፈልጌለሁ…››
እሷም ከአንደበቷ አውጥታ አትናረው እንጂ በጣም ልታገኘው ፈልጋለች፡፡‹‹ ይቻላል..የትና መቼ?፡፡››
‹‹ምሳ ልጋብዝሽ …ሰባት ሰዓት ስካይ ላይት እንገናኝ፡፡››
‹‹ሰባት ሰዓት ..አሁን እኮ አራት ተኩል ሆኖል…..ለመዘጋጃጀት በቂ ጊዜ አይኖረኝም፡፡››
‹‹አንቺ ደግሞ..እንደውም ምንም መዘገጃጀት አያስፈልግሽም… እዛ ሆስፒታል በነበርሽበት ጊዜ ያለምንም ዝግጅት ምን እንደምትመስዬ እኮ አውቃለው…ለእኔ ብለሽ ለመቆነጃጀት ከሁለት ሰዓት በላይ ማጥፋት የለብሽም…ከዛሬ ወዲህ ባልሽ ነኝ፡፡ማለቴ ለጊዜው እጮኛሽ ነኝ..ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡››
‹‹‹ይሁንልህ እሺ…..ግን ቅር ካላለህ አንድነገር ልጠይቅህ ››
‹‹ምን ጠይቂኝ››
‹‹ጸጋን ይዣት ብመጣ ቅር ይልሀል?››
‹‹አረ በፍፅም ..እንደውም በተቃራኒው ደስ ነው የሚለኝ …እሷ ከመጀመሪያው ጀምሮ የፍቅራችን ብቸኛ ምስክር ነበረች..ዛሬ መገኘት ይገባታል….ጫጉላ ቀናችን ላይ አብራን ወደመኝታ ትግባ እንዳትይ እንጂ ለዛሬው ደስ ይለኛል››
ስለጫጉላ ሲያወራ እፍረትም ሙቀትም ተሰማት‹‹አንተ ምን እያልክ ነው..?በል ቸው››ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡
እሱም ወዲያው ወደሻወር ቤት ገባና ሰውነቱን በፍጥነት ተለቃለቀ…ከዛ ፂሙን ላጨ…ሙሉ ሱፍ ለበሰና ዝንጥ አለ…፡፡ለመውጣት ዝግጁ ሆነ…፡፡ሰዓቱን ሲያይ 5 .ከሩብ ይላል….ከራሄልና ከፀጋ ጋር ወደሚገናኝበት ቀጠሮ ከመሄዱ በፊት ማግኘት የሚገባው አንድ ሰው አለ…ከአመት በፊት በሆስፒታል አብራው ትሰራ የነበረች የህጻናት ሀኪም ነች ትናንትና ደውላ ላገኝህ እፍልጋለው ያለችው፡፡ለዚህች ዶ/ር የስራ ባለደረባው ነበር…ያለፈውን አንድ አመት ተጨማሪ ትምህርት እድል አግኝታ ኖሩዌይ ነበር ያሳለፈችው፡፡አሁንም ለሁለት ሰምንት ረፍት እንደመጣች እና መመለሻዋ እንደደረሰ እናም ከመሄዶ በፊት አንድ እቃ ልትሰጠው እንደምትፈልግ ነግራው ነው እግረመንገዱን ሊያገኛት የወሰነው፡፡
ሀያ ሁለት ነበር ቀጠሮቸው…እሷም ቸኩላ ስነበረ ቀጥታ ወደጉዳዩ ነበር የገባችው፡፡አንድ የታጠፈ ነጭ ፖስታ አውጥታ እጁ ላይ አደረገች፡፡ግራ ገብቶትም ደንግጦም‹‹ምንድነው ሲል?››ጠየቃት፡፡
‹‹ትዝ ይልሀል ከመሄዴ በፊት አብረን የምንከታተላት አንድ ታማሚ ልጅ ነበረች…እናቷ ከአንተ ጋር ትግባባለች…እንደውም የልጅነት ጓደኛዬ ነበረች ብለሀኛል››
‹‹ኦኬ ትክክል ነሽ..ስለፀጋ ነው…ማለቴ የዛን ጊዜ ስሟ ትሁት ነበር..ስለእሷ ነው የምታወሪው››
‹‹አዎ ስለእሷ ነው…ለመሆኑ እንዴት ነች…?አሁንም በህይወት አለች?››
‹‹አዎ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ነች…ግን ፖስታው ምን እንደሆነ አልገባኝም››
‹‹ፖስታውማ እናትዬው እዛ ሆስፒታል ውስጥ ህጻኗን ጥላ ከመሄዶ በፊት ይህንን ፖስታ ለአንተ እንድሰጥ አደራ ብላ ሰጥታኝ ..ነበር….እርግጥ በወቅቱ ልጇን ጥላ እንደምትሄድ አልገመትኩም እና እሺ ብዬ ተቀበልኮት….ግን በዛው ሰሞን አንተም ለሆነ ስራ ወደክፍለሀገር ወጥተህ ነበር..እኔም ውጭ ለመሄድ በጣም እየተዋከብኩ ስለነበረ እቤቴ ወስጄ እንደቀልድ እንዳስቀመጥኩት እረሳሁት እና ሳልሰጥህ ሄድኩ ..በቀደም ነው የድሮ ወረቀቶቼን ሳስተካክል ድንገት አገኘሁት..አድራሻውን ሳነብ ትዝ አለኝ….መጀመሪያ አፍሬ እንደተረሳ ልተወው ነበር›..በኃላ ሳስበው ግን ምን አልባት በጣም አስፈላጊ ነገር ቢሆንስ ብዬ…አይኔን በጨው አጥቤ አግኝቼ ልሰጥህ ወሰንኩ….ይቅርታ እሺ››
‹‹አረ ችግር ለውም…ያው ልጄን አደራ..ተከታተላት ምናምን የሚል መልዕክት ነው የሚሆነው….ያንን ደግሞ እሷ ባትለኝም አደርገዋለው››በማለት ፖስታውን ኪሱ ውስጥ ከተተና ከእሷ ተሰናብቶ መኪናው ወደ እስካይ ላይት አዞረ፡፡
ከቀጠሯቸው 10 ደቂቃ ቀድሞ ነበር የደረሰው፡፡ ወንበር ይዞ በጉጉት ይጠብቃቸው ጀመር..፡፡ድንገት ፖስታው ትዝ አለው፡፡ አወጣና አየው…፡፡ከጀርባው ለማከበርህ ደ/ር ኤልያስ ከፅጌረዳ ይላል፡፡
እነ ራሄል እስኪመጡ ቀዶ ሊያነበው ፈለገ…መቅደድ ከመጀመሩ በፊት ፖስታውን ጠራጴዛው ላይ አስቀምጦ ስልኩን ከኪሱ አወጣና ተመለከተው…ራሄል ነች፡፡አነሳው፡፡
‹‹እሺ የእኔ ፍቅር››
‹‹ቀድመንህ ደርሰናል መሰለኝ››
‹‹አረ እንዴት ተደርጎ…››አለና ያለበትን ቦታ ነገራቸውና እስኪያዩት ቆሞ ጠበቃቸው…. ራሄልን ሲያያት ልቡ ትርክክ አለ….ወደፊት ተራምዶ ፀጋን ከእቅፏ ተቀበለና..ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ…. ወደ ጠረጴዛቸው ሄደው ተቀመጡ….ምሳ ታዘዘ እና እስኪመጣ ሞቅ ያለጫወታ ጀመሩ…..ራሄል ድንገት ፊት ለፊቷ የተቀመጠ ፖስታ አየችና በመገረም አነሳችና አየችው…፡፡
‹‹ፅጌረዳ ማን ነች?››ኮስተርተር አለች፡፡
‹‹ቀናሽ እንዴ?››
‹‹በኢንተርኔት ዘመን ፖስታ በምትልክልህ ሴት እንዴት ብዬ ነው የምቀናው?››
‹‹በፖስታው አድራሻ ላይ የተጠቀሰችው ፅጌረዳ ማለት የፀጋ እናት እንደሆነችና ፖስታው ከተፃፈ ከአመት በኃላ እንዴት እንዳገኘው… በእንግሊዘኛ ነገራት››ይሄንን ያደረገው ፀጋ ፊት ስለእናቷ በምትሰማው ቋንቋ ለማውራት ስላልደፈረ ነው፡፡
‹‹እና..አልተከፈተም እኮ››
‹‹አዎ…አሁን ስለፀጋ እኔን ብቻ ሳይሆን አንቺንም ስለሚመለከት አብረን እናነበዋለን››
‹‹እርግጠኛ ነህ?››
‹‹ አዎ እርግጠኛ ነኝ››
‹‹እና እናንብበዋ››ብላ ልትቀደው ስትዘጋጅ፡፡
‹‹አይ …ይሄንን ጊዜያችንማ ለሌላ ጉዳይ አንጠቀምበትም…››ብሎ ፖስታውን ከእጇ ተቀበለና ከጎኗ ካለው ወንበር ላይ የተቀመጠው የራሷ ቦርሳ ውስጥ ከተተው፡፡
‹‹በቃ አንቺ ጋር ይሁንና ..ሰሞኑን አንድ ላይ ሆነን እናነበዋለን፡፡››ተስማማች…ምሳ ቀረበላቸው በሉ…ከዛ ወጥተው ወደአለም ሲኒማ ጎራ አሉና ፊልም አዩ….አሪፍና ጣፋጭ ቀን አሳለፉ….

❤34👍3👏1