አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ስትባንን በመስኮቱ ሾልካ የገባችው ፀሀይ ልክ አልመው የለቀቋት ይመስል ደረቷ ላይ በጡቶቾ መካከል የአካፋዩ መጀመሪያ ላይ አርፋለች.. ከተኛችበት ቦታ ንቅንቅ ሳትል ነው የነቃችው…አንገቷን ጠምዝዛ ወደጀርባዋ ስትመለከት አልጋው ባዶ ነው…
‹‹እንዴ የት ሔደ…?››ብላ ዞር ስትል
‹‹አለሁ እዚህ ነኝ››አላት… ወደ እዛኛው ክፍል በሚወስደው በራፍ ዳፍ ላይ ፊቱን ወደእሷ ዞሮ በትኩረት እየተመለከታት ነበር፡፡
‹‹ውይ ስንት ሰዓት ሆነ?››ጠየቀችው፡፡

‹‹3፡10፡፡››

‹‹እየቀለድክ ነው?››

‹‹በፍፅም..ምነው የምትሄጅበት ቦታ ከሌለሽ ዛሬ እኮ እሁድ ነው..የእረፍት ቀን ነው?››

‹‹አይ እኔ እንኳን ስራ ፈት ነኝ ..አንተን ስራ ካስፈታሁህ ብዬ ሰግቼ ነው፡፡››

‹‹አይ በፍፁም እኔን ስራ አታስፈቺኝም…ጉዳይ ቢኖርብኝ  እኮ መልዕክት ጥዬልሽ ሄድ ነበር፡፡››

‹‹ዳግመኛማ እንደዛ አታደርግም…፡፡››

‹‹ለምን?›› አለ ግራ በገባው ፊት፡፡

‹‹እንደዛ አድርገህ እኮ በቀደም ላፕቶፕህን ይዤብህ ሄድኩ …ዛሬ ብትደግመው ጠቅላላ ቤትህን አስጭኚ ልወስደው እችላለሁ፡፡››

‹‹እሱ አያሳስበኝም..ይልቅ አሁን ታጠቢና ወደሳሎን ነይ.. የሰራሁትን ቁርስ እንዲቀዘቅዝ አታድርጊ..፡፡››አላት..ለመመፃደቅ ሳይሆን እውነቱን ነው የነገራት…

አሁን እሱ ለቁሳቁስ የሚጨነቅበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው….በቅርብ በዙርያው የኮለኮላቸውን መገልገያ ዕቃዎቹን በጠቅላላ እርግፍ አድርጎ ትቶቸው እንደሚሄድ ያውቃል..ምን አልባት እሷ እንዳለችው  ዛሬውኑ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉ ጫጭና ብትወስድ መሄጃ ቀኑን ከማፍጠኗ ውጭ ሌላ የምታደርስበት ጉዳት ወይም የኑሮ መፋለስ የለም፡፡አሁን እዚህ ቦታ እዚህ ከተማ ውስጥ አስሮ ያቆየው አንድ ጉዳይ ብቻ ነው…የፍቅረኛው ጉዳይ…የእሷን የወደፊት ህይወት መሰረት ካስያዘ በቃ ሌላ የሚቀረው ነገር የለም፡፡

  ልዩ ስለምግብ ሲያወራት በቀደም የበላችውን ምግብ አይኖቾ ላይ  ድቅን  አለ…  እናም በዛው ቅፅበት እስከአሁን ልብ ያላለችው የሚያውድ የምግብ ሽታ አፍንጫዋን ቆጠቆጣት…ቶሎ ብላ ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች…5 ደቂቃ ያህል    ነው የወሰደባት፡፡፡ሳሎን ስትገባ ቀለል ያለ ቆንጆ ቁርስ ተሰናድቶ ጠበቃት…ልክ አስደሳች ጀብዱ እንደሰራ ማራኪ ፍቅረኛ እየተፍለቀለቀች ለቁርስ ቀረበች፡፡ከፊት ለፊቷ ሆኖ እጁን ወደምግቡ ይዘረጋል ስትል  ሁለቱንም እጆቹን አንድ ላይ በማጣመር ወደግንባሩ ወሰደና ወደላይ አንጋጠጠ..፡፡ሊፀልይ መሆኑ ገባትና አብራው መፀለይ ባትችልም በዝምታ መከታተል ጀመርች‹‹….ጴንጤ ይሆን እንዴ ይሄ ልጅ;?›› በውስጧ እራሷን ጠየቀች እሱ ከንፈሩን በማነቃነቅ ሚሰሙ ቃላቶችን ከአንደበቱ እያወጣ ፀሎቱን ቀጠለ…
‹‹ለውስጣችን  የሚስፈልገንን ኃይል በትክክለኛው መንገድ እድናገኝ እርዳን….ይሄ ምግብ የተቀደሰ ይሁን…ይህ ምግብ ያለውን ኃይል አሞጦ ለእኛ እንዲሰጥ በፍቅርና በትህትና እጠይቃለሁ…ኃይሉም ለውስጣችን ጉልበት፤ ለአካላታችን ጤና እና ለመንፈሳችን ብርታትን ለአእምሮአችን ደግሞ  በጎ በጎውን  የማስብ ብቃትን እዲያጎናፅፈን ይሁን፡፡
አሜን
ጨረሰና‹‹..ብይ››አላት
ከመደነቋ ሳትወጣ‹‹..እሺ›› ብላ ለመብላት እጇን ዘረጋች..እንዲህ አይነት ፀሎት የትም በማንም ሲፀለይ ሰምታ አታውቅም‹‹….ከምን አይነቱ ተአበኛ ሰው ጋ ነው ፈጣሪ ያገናኘኝ፡፡››ስትል በውስጧ አብሰለሰለች፡፡
ማሰቧን ለሰከንድም ሳትገታ ቁርሷን ግን ጥብስቅ አድርጋ  በላች…የእሱ አበላል በጣም የተለየ ሆኖ ነው ያገኘችው ….በጣም ስርአት ያለው በፅሞና የታጀበ .ረዘም ያለ ማላመጥ ያለበት ነው፡፡
‹‹…የዚህ ልጅ ፍቅረኛ እንዴት ታድላለች?››

‹‹ምን አልሺኝ?››
ለካ ድምጻን ከፍ አድርጋ ነበር ያጉረመረመችው
በእፍረት አይኖቾን ከወዲህ ወዲያ እያቁለጨለጨች፡ ‹‹ማለት… ያው ለማድነቅ ፈልጌ ነው፡፡››አለችው..
‹‹አይ ምንም የሚደነቅ ነገር የለውም..እኔ በተቻለኝ መጠን የሚጣፍጥ ምግብ መመገብ እፈልጋለሁ…ምን አልባት መጠኑ ካልሆነ በስተቀር አንቺም ባትኖሪ ማበስለው እንደዚሁ ነው..እና ሌላ እንግዳም ቢሆን…››
‹‹እና ላንቺ ብዬ ያደረኩት ምንም የተለየ ነገር የለም ለማለት ነው?››
‹‹በትክክል፡፡››
‹‹እና እስከአሁን እኔን በተመለከተ ያደረካቸው በጎነቶችና ትእግስቶች …ለሌላም ታደርገዋለህ ማለት ነው፡፡››ስትገረምበት የሰነበተችውን ጥያቄ አጋጣሚውን ስታገኝ ጠየቀችው፡፡

ለዚህ ጥያቄ በተወሰነ መጠንም ቢሆን የተሳሳተ ወይም የተጋነነ መልስ ሊሰጣት ወሰነ.. ‹በተቻለኝ መጠን አዎ…ግን አስቤበት ለእከሌ እንዲህ ላድርግ ብዬ አይደለም…በእየእለት ገጠመኜ ፊት ለፊቴ የሚደነቀሩትን ማንኛውንም አጋጣሚዎች አእምሮዬና ልቤ ተጋግዘው በሚወስኑት ውሳኔ በመገዛት ላልፋቸው እሞክራለሁ..በዛ ሂደት ውስጥ እንግዲህ ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር በሌላው ሰው ላይ  ልሰራ እችላለሁ…..በእኔ ምክንያት ግን ሰው  ፊቱን ባያጨማድድ ደስ ይለኛል፡፡››አላት…ያለው ሁሉ እውነትነት ያለው ቢሆንም እሷ ላይ ግን የተለየ አቀራረብና ልዩ የሆነ ትኩረት አደርጓል…ይሄንን ግን ሊነግራት አልፈለገም…ለመዋሸት ፈልጎ ሳይሆን ለምን ብትለው ሚመልስላት የተዘጋጀ መልስ በውስጡ ስለሌለ ነው፡፡
‹‹አእምሮዬና ልቤ የተስማሙበትን ነው ያልከው..እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው..እስኪ ትንሽ አብራራልኝና   ከረዳኝ እኔም ልጠቀምበት፡፡››
‹‹አእምሮሽን ብቻ ስተጠቀሚ እኔነት ያጠቃሻል ….እኔነትን መሰረት አድርገሽ ምትወስኚው ውሳኔ ደግሞ ወደ ራስ ማዳላቱና ከሌላው መብት ላይ የተወሰነ ድርሻ  መስረቁ አይቀሬ ነው..ልብሽን ስትጠቀሚ ደግሞ ስሜት ያጠቃሻል ፡፡በወቅቱ በሚሰማሽ ስሜት ብቻ ሙሉ በሙሉ ተስበሽ ውሳኔ  ላይ ትደርሻለሽ….ብዙን ጊዜ ደግሞ በመጀመሪያው እይታ አይተው የሆነ ስሜት የሚቀሰቅሱ ነገሮች ጠለቅ ብለሽ ሰታጠኛቸው ሌላ ታሪክ በጀርባቸው አዝለው ይገኛሉ….ሁለቱንም ማለቴ ልብሽንና አእምሮሽን በጥምረት መጠቀም ግን ወደእውነታው የበለጠ መቅረቢያ የተሻለው መንገድ ነው፡፡ልብህ ወደሚመራህ ቦታ ተጓዝ እምሮህንም ግን ይዘህ ሂድ ያለው ማን ነበር ››አላት
‹‹ሰው ግን በምኑ ነው የሚያስበው?››ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ ሰው በአእምሮው እንደሚያስብ ነው የሚታወቀው..እኔ ግን በአእምሮችን ብቻ ሳይሆን በልባችንም እናስባለን ብዬ አምናለሁ… በኩላሊትም እንደሚያስቡ የሚያምኑ ማህበረሰቦች አሉ፡፡››
‹‹እንዴ ምን ነካህ ልብ እኮ በደም የተሞሉ የተለያዩ የደም ቱቦሆች ቅጥልጥል ነው … እንዴት ማሰብ ይችላል?››
‹‹አእምሮም ደግሞ እሱንም የለውም….አእምሮ ጭንቅላት ውስጥ ሚካሄድ የሀሳብ ስርአት ነው….ጭንቅላትም ደግሞ በቢሊዬን የሚቆጠሩ የተለያዩ ኒውሮኖች ቅጥልጥል ነው፡፡ እንዴት አድርጎ ነው የሚያስበው..ስታስቢስ በአእምሮሽ ታስብ በኩላሊትሽ፣በልብሽ ታስቢ በጉልበትሽ በርግጥ መለየት ትቺያለሽ?›› መልሶ ጠየቃት፡፡  
  
‹‹አልችልም፡፡››

ከእሱ ጋር ረዘም ያለ ጊዜ ማሳለፍ ስለፈለገች‹‹አሁን የሆነ ቦታ እንሂድ››አለችው፡፡

‹‹ደስ ይለኛል …ግን የት?››

‹‹የፈለክበት ቦታ..ሲኒማ ቤት…ትያትር ቤት.. መጠጥ ቤት…››
‹‹ካልደበረሽ እኔ አንድ ቦታ ልውሰድሽ፡፡›› አላት…
👍923👎2👏2🔥1🥰1
ደስ አላት ፡፡ምክንያቱም የሆነ ውብ ስፍራ ለመጀመሪያ ጊዜ ይዟት እንደሚሄድ ገመተች..ያ ማለት ደግሞ አንድ ከእሱ ጋር የሚያቆራኛትን ትዝታ በልብ የማስቀመጠ  አጋጣሚ ተፈጠረላት ማለት ነው፡፡አንደዛ ስላሰበች ነው በጣም የተደሰተችው፡

ይቀጥላል….
👍10311🤔9👎2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ስትባንን በመስኮቱ ሾልካ የገባችው ፀሀይ ልክ አልመው የለቀቋት ይመስል ደረቷ ላይ በጡቶቾ መካከል የአካፋዩ መጀመሪያ ላይ አርፋለች.. ከተኛችበት ቦታ ንቅንቅ ሳትል ነው የነቃችው…አንገቷን ጠምዝዛ ወደጀርባዋ ስትመለከት አልጋው ባዶ ነው… ‹‹እንዴ የት ሔደ…?››ብላ ዞር ስትል ‹‹አለሁ እዚህ ነኝ››አላት… ወደ እዛኛው ክፍል…»
ፍቅርና ጦርነት

ክፍል 5

ሰዓቶች ቀንን ሲወልዱ ቀን ቀንን ሲተካ.... ህይወት ተቀየረ ዳግም የተወለድኩኝ መሰለኝ ። ፀጋማርያም ህይወቴን አበራችው ... አዲስ አመትን አብረን ተቀበልን ሰማይም እንደኔ ህይወት ደመናውን ፅልመቱን አራግፎ ብርሀን ተጎናጽፏል 2014 በህይወቴ አዲስ ነገር ማይበት እንደሆነ ገምቻለሁ  ጤናዬም ከቀን ወደቀን እየተሻሻለ መቷል ። ፀጋም ሀዘኗን ችግሯን ረስታዋለች ከእናቴ ጓደኛ ለምለም ጋር በደንብ ተግባብተዋል በቋንቋ ስለተረዳዱ ጓደኛሞች ሆነዋል... ፀጋ አሁን ባላት ነገር ደስተኛ ናት .. ያኔ እጄን ይዘህ ባታስቀረኝ ይህ ሁሉ ያመልጠኝ ነበር ብላ ጥምጥም ብላብኝ ትስመኛለች ቅብጠቷ ተመችቶኛል                  ሰውን አታስከፉም ችግርን መከራን ሁሉን ነገር አለምን ታስረሳለች ።

ቤቱ ላይ ብዙ ነገር ጨምራበታለች ደስታ እሷን ተከትሎ ገብቷል ልቤ ላይ ተስፋ ዘርታበታለች ጤንነቴም በጣም ተሻሽሏል ማነከስ አቁሚያለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ህይወቴ የራሷን የመኖር አላማ ያዘች ከዚህ በኋላ ያለ በፀጋማሪያም ማልመው ህይወት የለኝም ። እያንዳንዷ እርምጃዎች ጎን እንድትኖር እፈልጋለሁ ካለሷ ማንም እንደሌለኝ በዚህ አጭር ጊዜ ገብቶኛል  የእሷን እርግጠኛ ባልሆንም በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ አንድም ፀጋን ብሎ የፈለጋት ሰው አለመኖሩ አስገርሞኛል እሷም ሁሉንም እንደረሳቻቸውና አሁን ያለኋት ብቸኛ ጓደኛም ዘመድም ቤተሰብም እኔ እንደሆንኩኝ ስትነግረኝ ልቤ ያዝናል። የሆነ ነገር ብሆንስ ብዬ አስባለው .... በዚች ጥቂት ጊዜ ውስጥ ካለፈው ህይወቴ ዘመን በላይ ደስታን ና ተስፉ አግኝቻለሁ አይቻለው ታዲያ ይህን ሁላ ለሰጠችኝ ለፀጋ መሰረታዊ ችግሯን ሚፈታላትን ነገር ለማድረግ አሰብኩኝ ... ያሰብኩትን ልነግራት በዛውም እራት ልጋብዛት ከቤት ተያይዘን ወጣን ። 

መንገድ ላይ ያየን ሳይገረም አልቀረም እቅፌ ውስጥ አስገብቼ በደስታ ፊታችን  አብርቶ ከእኔ ና ከእሷ ውጭ የሰው ልጅ  ሁሉን ረስተን ወደ ራስ ሆቴል ገባን ። ራስ ሆቴል በጣም ምወደው ሆቴል ነው እናት ና አባቴ የተጋቡት ራስ ሆቴል ነበር እኔን ከወለዱ በኋላም ለመዝናናት እኔን ይዘውኝ ይመጡ ነበር እኔም ይህ ስለተቀረፀብኝ ራስ ሆቴልን በጣም ነው ምወደው ።

"ዛሬ ደስ ብሎሀል " አለችኝ ፈገግታዬን አይታ
"አንቺን ካገኘሁ ቀን ጀምሮ ደስተኛ ነኝ " እጇን ጠበቅ አድርጌ ይዤዉ
" አይ የዛሬው የተለየ ነው ንገረኝ አብርሽ " ብላኝ ወደኔ ተጠጋች " ከራት በኋላ " ብያት  አስተናጋጁን ጠራሁት
ባንቺ ምርጫ አልኳት እሷም ቀለል ያለ ምግብ አዛ ምግቡን በልተን ጨረስን ። " እሺ ንገረኛ" አለችኝ ወይኑን እንደ ውሃ እየጠጣች " እነግርሻለሁ ግን እንዳትሰክሪ ቀስ ብለሽ ጠጪ " ብላትም አልሰማችኝም
"ፀጋ "
"ወዬ"     ወዬ ስትለኝ ልቤን ደስ ይለዋል
" ብቸኛ እንደሆንኩ ታቂያለሻ "
" አዋ ቤት ማንም እንደማይመጣ አይቻለው "
"የሆነ ነገር ብሆን ምን ሚፈጠር ይመስልሻል "
"እንጃ" አለችኝ ግራ መጋባቷ ፊቷ ላይ ይታያል
"ያለኝ ነገር ሁሉ ያንቺም እንዲሆን እፈልጋለሁ ቤቱም የንግድ ሱቁም ሁሉም " ተው ተው አለችኝ ንግግሬን እንኳን ሳልጨርስ "እኔ ውለታህን እንዴት እከፍልሀለው ብዬ ስጨነቅ አንተ ሌላ እዳ ትጨምርብኛለህ ተው አብርሽ አልችልም  " ብላ ተነስታ ቤት ልሂድ ብላ ጥላኝ ሄደች ላስቆማት አልፈለኩም ከሆቴሉ እስክትወጣ ባይኔ ሸኘኋት

ግራ ገባኝ ማደርገው ጠፋኝ አስተናጋጁን ጠንከር ያለ መጠጥ አምጣልኝ ብዬ መጠጣት ጀመርኩ ግን ፀጋን ሊያስረሳኝ አልቻለም ጭራሽ መጠጡ እሷን ማፍቀሬን አስረዳኝ ካሁኑ ናፈቀችኝ አይኔ ፀጋ ፀጋ አለ ናፈቃት ሂሳብ ከፍዬ ወጣው

እቤት ስገባ መብራት ጠፍቶ ሻማዎች በርተዋል ጠረቤዛው ላይ ወይን ና ጥንድ ብርጭቆ ተቀምጠዎል ምን እንደሆነ ግራ ገባኝ ፀጋ እጄን ጎትታ አስቀምጣኝ ከወይኑ ቀድታ ሰጠችኝ የቅድሟ ፀጋ አይደለችም ፊቶቿ ቀልቷ ሰውነቷ ግሏል ምን እንደተፈጠር ስጠይቃት እኔን ደስ ለማሰኘት እንዳዘጋጀችው ነገረችኝ ። ድርጊቷ ግን ግራ አጋብቶኛል የሆነ ያሳሰባት ነገር እንዳለ ያስታውቅባታል መጥፎ ነገር እንዳይሆን ብዬ ወይኑን ጨርሼ ልተኛ ብዬ ተነሳው ። ወደመኝታ ቤት ልገባ ስል አብርሽ ብላ ጠራችኝ አቤት ሳልላት ቆምኩኝ  " አብርሽ ካልደከመህ እንደንስ " ጥያቄዋ ገረመኝ ከተቀመጠችብት ተነስታ ወደኔ መጣች ....
"መደነስ አልችልምእኮ" ብላትም አልሰማችኝም እጄን ይዛ ወገቧን አሳቀፈችኝ አንገቴን ደሞ በእጇ አቀፈቻቸው ልብ ምቴ ጨመረ "አሁን እኔ ማረገውን ታረጋለህ " ብላ መደነስ ጀመርን ሰውነቷ ይነዝረኝ ጀመር ትንፋሿ አንገቴን አሞቀው ጡቶቿ ደረቴን እየታከኩ ሲንቀሳቀሱ ልቤ አልቻለም እጄም ተንሸራቶ ዳሌዋ ላይ አርፏል የሴት ገላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳበስኩ መሰለኝ ስሜቴ ተፈታተነኝ ግን እጅ አልሰጠሁም በሰውነቴ ማዘዝ አቃተኝ የህልም አለም መሰለኝ እውን መሆኑን ያወኩት ባላወኩት መንገድ መሳሳም ስንጀምር ነው ለስሜቴ ተሸነፍኩ ሁለታችንም ወደ  ማናቀው አለም ከነፍን ሁሉም ነገሬ ያንተ ነው አለችኝ ሁሉም ነገሬ ያንቺ ነው አልኳት እወድሀለው አለችኝ እወድሻለሁ አልኳት ንጉሴ ነህ አለችኝ ንግስቴ ነሽ አልኳት አንድ ነን አለችኝ አንድ ሆንን አልኳት ተያይዘን ወደኔ መኝታ ክፍል ገባን ወደ አዲስ አለም ወደ አዲስ ምዕራፍ ......


ክፍል 6 ይቀጥላል

    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
  ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍74🥰7😁51🔥1
#ባል_አስይዞ_ቁማር
:
:
#ክፍል_አስር


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

‹‹ካልደበረሽ እኔ አንድ ቦታ ልውሰድሽ፡፡›› አላት…
ደስ አላት ፡፡ምክንያቱም የሆነ ውብ ስፍራ ለመጀመሪያ ጊዜ ይዟት እንደሚሄድ ገመተች..ያ ማለት ደግሞ አንድ ከእሱ ጋር የሚያቆራኛትን ትዝታ በልብ የማስቀመጠ  አጋጣሚ ተፈጠረላት ማለት ነው፡፡አንደዛ ስላሰበች ነው በጣም የተደሰተችው፡

‹‹በጣም ደስ ይለኛል….በል ተነስ እንሂድ…››ብድግ አለች.፡፤
ቆይ ጃኬት ልልበስ አለና ወደ መኝታ ቤቱ ገብቶ ጃኬቱን ለብሶ በአንድ እጁ ብሮች ይዞ መጣና አቀበላት፡፡
‹‹ምንድነው?››ግራ ገብቷት ጠየቀችው፡፡
‹‹ያዢው ዛሬ ጋባዥ አንቺ ነሽ..››አላት፡፡
ለሊት በዛ ንዴት የመለስችለትን  ብር በዘዴና በጨዋ ደንብ መመለሱ እንደሆነ ገባት፡፡
‹‹ሌላ ብዙ ብር ይዤያለሁ እኮ..››
‹‹አሪፍ ነዋ..ብዙ እንዝናናበታለን››አላት፡፡
‹‹የማንኛውም ጥያቄ መልስ ከንፈሩ ላይ ነው፡››አለ..በውስጧ፡፡
ብዙም ክርክር ውስጥ መግባት ስላልፈለገች… ብሩን ቦርሳዋ ውስጥ ከተተች‹‹ አንዴ መኝታ ቤትህን ልጠቀም ሜካፔን ላስተካክል.. መስታወት እዛ ያለ መሰለኝ፡፡››

‹‹ይቻላል ተጠቀሚ ..ቁም ሳጥኑ ላይ አለልሽ››አላት…፡፡

‹‹እሺ ብላ ቦርሳዋን አንጠልጥላ ወደመኝታ ቤቱ ገባችና ከውስጥ ዘጋችው፡፡

ሜካፔን ለማስተካከል ፍፅም ሀሳብ የላትም….መኝታ ቤቱ የገባችው ለሌላ ቀሺም ስራ ነው…እንደለመደችው ልትሰርቅ አይደለም…ግን ደግሞ ያው ስርቆት በሉት፡፡ ቦርሳዋን በረበርችና ብይ የምታህል ዘመናዊ የመቅረጫ መሳሪያ አወጣች…እንደዚህ አይነት ዘመናዊ የመቅረጫ መሳሪያዎች በጣም ብዙ አላት..የእሷን ያህል የሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤትም ያለው አይመስልም…የዛሬ አመት አሜሪካ የሄደች ጊዜ ነው በአጋጣሚ እጇ የገባውና ከጌጣጌጦቸና ኮስሞቲኮቾ ጋር ቀላቅላ ወደሀገር ይዛ የገባችው….
እና ስለሆነ ሰው የሆነ ነገር የማወቅ ጥማት እረፍት ሲነሳት ትጠቀምባቸዋለች፡፡መኝታ ቤቱን በአይኗ ቃኘችና ቦታ ፈለገች፡፡ ከእሱ የምርቃቱ  ፎቶ ፍሬም ላይ ልታስቀምጠው ፈለገችና ወዲያው ሀሳቧን ቀየረች፡፡እሱ ልጅ ሆኖ በእናቱና በአባቱ መካከል ቆሞ የተነሳውን ፎቶ መረጠች..ወደአዛ ቀረበችና  በጥንቃቄ አስቀመጠችው፡፡ ከቦርሳዋ ለእንደዚህ አይነት ጉዳይ የምትጠቀምበትን ማጣበቂያ አውጥታ እንዳይንቀሳቀስ አድርጋ አጣበቀችው… ሞባይሏን አወጣችውና ከፈተችው ..ጢው ጡው እያለ መአት ሚሴጅ እየተግተለተለ ገባላት፡፡ ችላ አለችና ከካሜራው ጋር ሚያገናኘውን አፕ አበራችውና መቆጣጠሪያ ቁልፉን በመክፈት አገናኘችው፡፡ ከዛ በትክክል መስራቱን አረጋገጠች፡፡
አዎ ከሞላ ጎደል ከዚህቺ ሰዓት አንስቶ እዚህ ክፍል ውስጥ የሚከናወነውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ሆነ ንግግር እቤቷ ሆነ ሌላ በ200 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ባለ በማንኛውም ቦታ ሆና መከታተል ትችላለች…..ይሄም አንዱ መጥፎ ጎኗ ነው…ያው ሌብነት በሉት….
የሰውን የግል ህይወት ያለፍቃዱ ጠልፎ ማዳመጥና መቅዳት ስርቆት ካልተባለ ሌላ ምን ይባላል? እንደውም ከስርቆትም ጠንከር ያለ ወንጀል ነው….፡፡

በዛን ደቂቃ ግን ቃል ኪስ ውስጥ ያለው ሞባይል ቅጭልጭልታ ድምፅ አሰማ…ግራ ገባው.. አውጥቶ አየው…በጣም ተገረመ..ምን እየተፈጠረ ነው….?እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ?›እራሱን በሚገርም ጥያቄ አጨናነቀ፡፡
ሁሉን ነገር አጠናቅቃ ስትወጣ ቀልም ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል የፊትለፊቱ በራፍ ጋር ቆሞ ሲጠብቀት ነበር፡፡እቤቱን  ለቆ ወጣ ፡፡ተከተለችው፡፡ በራፉን ቆለፈና ወጡ.. ቀጥታ ወደበሩ ስያመራ የውጩን በራፍ ሊከፍትላት መስሏት ነበር፡፡ እሱ ግን ትንሿን በራፍ ከፈተና ወደኃላ ዞረ…‹‹ምነው ቆምሽ  …አትመጪም  እንዴ?››አላት፡፡
‹‹በራፍን ክፈትልኝ እንጂ መኪናዬን ላስወጣ..፡፡››
‹‹መኪናዋ ያንቺ ነች እንዴ… ?እማማ ጋር የመጣ እንግዳ መስሎኝ ነበር እኮ›› አለና ትልቁን በራፍ ለመክፈት መታገል ጀመረ…እሷም ወደመኪናዋ ገባችና ሞተሩ አስነሳች…መኪና ይዛ እስከ ግቢው መምጣቷ ያልጠበቀው እንደሆነ ቢያስታውቅበትም የገመተችውን ያህል ግን መደነቅ አላየችበትም
‹‹…ሌላ ወንድ ቢሆን በአድናቆት አፍን ከፍቶ ለሀጪን ያዝረከርክ ነበር..ይሄ እንደው ሲሞቅም ሲቀዘቅዝ አንድ ጌጅ ያህል ብቻ ነው ከፍ ዝቅ የሚለው….ሰው እንዴት በዚህ ልክ ስሜቱን መግራት ይችላል?፡፡››ስትል አጉተመተመች፡፡
በራፉን ከፍቶ ሲጨርስ መኪናዋን አንቀሰቀስችና ከግቢው እስወጣቻት..እሱም የከፈተውን በራፍ መልሶ ዘግቶ ሄዶ ተቀላቀላት፡፡
‹‹ ወደየት ልንዳው?››ጠየቀችው፡፡
‹‹ወደሜቅዶኒያ››
‹‹እርግጠኛ ነህ››ያልጠበቀችውን ስም ስለጠራላት ግራ ተጋባች..እሷ እንጦጦ ወይ አንድነት፤ካልሆም እስካይ ላይት እንደው ካነሰ ካነስ የሆነ ሲኒማ ወይም ቲያትር ቤት አንሂድ ይለኛል ብላ ነበር የጠበቀችው፡፡
..እንሂድ ወዳላት ቦታ ለመሄድ ብዙም ደስተኛ እንዳልሆነች በመገመት‹‹አዎ ምነው…?አባቴ እዛ ነው የሚኖረው ..በየሳምንቱ በዚህን ሰአት ይጠብቀኛል..ባይሆን ከዛ መልስ አንቺ የፈለግሽው ቦታ እንሄዳለን፡፡›አላት፡፡
‹‹አረ ችግር የለውም..እንዲሁ ያልጠበቅኩት ቦታ ስለሆነ ነው››ብላ በምትሄድበት ቦታ እንዳልተከፋች ተናገረች…እውነታው ግን እንደዛ አልነበረም፡፡

ይቀጥላል
👍9418🤩4🔥1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር : : #ክፍል_አስር ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ‹‹ካልደበረሽ እኔ አንድ ቦታ ልውሰድሽ፡፡›› አላት… ደስ አላት ፡፡ምክንያቱም የሆነ ውብ ስፍራ ለመጀመሪያ ጊዜ ይዟት እንደሚሄድ ገመተች..ያ ማለት ደግሞ አንድ ከእሱ ጋር የሚያቆራኛትን ትዝታ በልብ የማስቀመጠ  አጋጣሚ ተፈጠረላት ማለት ነው፡፡አንደዛ ስላሰበች ነው በጣም የተደሰተችው፡ ‹‹በጣም ደስ ይለኛል….በል ተነስ…»
ፍቅርና ጦርነት

ክፍል 6

ደስ ይላል ያሰብኩት ተሳክቷል
ዝንፉም ተቃንቶ የጎደለው ሞልቷል
ድፍርሱ ጠራ ህልሜም ተፈታ
የተመኘኋት እጄ ገብታ

ይህን ዘፈን ወንድሙ ጅራ ለኔ የዘፈነው መሰለኝ ... በዚህ ስዓት እንደኔ እድለኛ የለም ህይወቴ አበራ ደስታ ቤቴን አንኳኩቶ ገባ ፍቅር አሰከረኝ በፀጋማሪያም ተሸነፍኩኝ እጄን ሰጠው ሁሉም ነገር ተቀየረ እናት ና አባቴ ከሞቱ በኋላ ደስታ ርቆት ተስፉ ጠፍቶት የነበረው ህይወቴ አዲስ ምዕራፍ ጀመረ የእያንዳንዱ ቀኖች ትርጉም ገባኝ ወራት ሳምንታት ሆኑ ሳምንታት ቀናት ሆኑ ቀናት ስዓታት ሆኑ ።

ከፀጋ ጋር ቀጣይ የህይወታችንን እቅድ ማውጣት ጀምረናል .... "ፀጋዬ መቼ ነው ባልሽ ምሆነው " ድምፄን ከፍ አድርጌ ጠየኳት መኝታ ቤት ሆና ስትስቅ ሰማኋት
" ምን ያስቅሻል "
" ባሌ ለመሆን ማሰብህ ገርሞኝ ነው " አጠገቤ መታ ቁጭ አለች
" አይ ከዚህ በኋላ ወንድምና እህት ነን " ብዬ አንገቷን ሳምኳት
"እረፍ አብርሽ እሺ ባሌ ነህ " እንደ ህፃን ልጅ ሳቋን ለቀቀችው
"ለዚች አቅምሽ ነው " ለቀኳት ሮጣ ወደ መኝታ ቤት ገብታ ጮክ ብላ " ሲያምርህ ይቅር " አለችኝ ቆይ መጣሁልሽ ብዬ ከተቀመጥኩበት ስነሳ ለምለም በሩን በርግዳ ገባች ትንፋሿ ይቆራረጣል ምታዋራኝ ነገር እንዳለ ነግራኝ ወደውጭ ወጣን ።

"ምነው" አልኳት ሁኔታዋ ገርሞኝ
" አሸብርን ታቀዋለህ "
"አዋ ፖሊሱ "
" ደውሎልኝ ነበር ፀጋን ለማሰር ፖሊሶች እየመጡ እንደሆነ ነገሮኝ ነው " አለችኝ ንግግራችንን ፀጋ እየሰማች ነበር ምንም እንደማይፈጠር እያስረዳኋቸው የጊቢው በር ተንኳኳ ፀጋ ፍራቷ አይኗ ላይ ይታወቃል እጇን ጠበቅ አድርጌ ይዤ ሄጄ በሩን ከፈትኩት ።

" ፀጋማርያም ኪዳኔ ትኖራለች " የኳንስታብል ማዕረግ ትከሻው ላይ ያረገው ፖሊስ ድምፁን ጎርነን አርጎ
"ትኖራለች "
"ልናናግራት ፈልገን ነበር "
"እኔን አናግሩኝ " ብያቸው ወደነሱ ተጠጋው በዚህ አካባቢ የፀጉረ ልውጥ ሰው እንቅስቃሴ እንደበዛ እና የፀጋን ማንነት ለማረጋገጥ እንደመጡ ነገሩኝ ፤ እየተገረምኩ ከኪሴ መታወቅያ አውጥቼ ሰጠሁት መታወቅያውን አይቶ መልሶ ፀጋን አያት " ላንተ ምንህ ናት " ብሎ ጠየቀኝ ትከሻው ላይ ምንም ማዕረግ ያላረገው ፓሊስ ፀጋን ፀጋን እያየ " የሰማንያ ሚስቴ ናታ " ገርሟቸው እርስ በራሳቸው እየተያዩ "ያንተን መታወቅያ ማየት እንችላላን " ሳሳያቸው ሁለቱም ግራ ተጋቡ ወታደራዊ ሰላምታ ሰተውኝ ላደረጉት ነገር ይቅርታ ጠይቀው ሄዱ ።

ፀጋ የፖሊሶቹ መደናገጥ አይታ እንዳስረዳት ጠየቀችኝ ምን እንደምላት ግራ ቢገባኝ መታወቂያዬን አሳየኋት ወታደር ነህ አለችኝ ነበርኩ አሁንማ ያንቺ ባል ነኝ አልኳት ፤ እንባ ካይኗ ሲፈስ አየሁ ላባብላት ብሞክርም አልቻልኩም ጥምጥም ብላ አቅፋኝ " ትተከኝ ትሄዳለህ "አለችኝ ከንፈሬን እየሳመች የእንባዋን ጣአም ከከንፈሯ ላይ ቀመስኩት ሀዘኗ ጥልቅ እንደሆነ ተረዳሁ ብታጣኝ ምን እንደምትሆን ገባኝ
" የትም ጥዬሽ አልሄድም በህይወት እስካለሁ ያንቺ ነኝ እንዳንገትሽ ማእተብ ካንቺ አልለይም ፀጊ እሺ " ደግማ ሳመችኝ አይ መጣፈጡ " እኔ ብቻ አይደለሁም ምፈልግህ " ብላ እጄን ሆዷ ላይ ጫነችው እርጉዝ እንደሆነች ነገረችኝ ማመን አቃተኝ እኔ አባት ልሆን ከዛ ሁላ እሳት መአት አውቶ እኔን አባት አረገኝ ሰው እንደ ቅጠል ከሚረግፍበት አባቶች ልጄ ልጄ እንዳሉ በሚሞቱበት ያልወለዱ ልጅ ልጅ እያሉ ከሚረግፉበት አውቶ ለዚህ አበቃኝ ለማረጋገጥ አንዴ ደግሜ ጠየኳት አረጋገጠችልኝ ለምለም ጥግ ላይ ሆና እውነት እንደሆነ ማረጋገጫ ሰጠችኝ የዛሬውን ቀን ልደቴ መሰለኝ የተወለድኩበት ህዳር 21 ደስ አለኝ አነባሁ ለኔም ለጓደኞቼም ፀጋን ምን እንደምትፈልግ ጠየኳት አግባኝ አለችኝ እሺ ተባብለን ተያይዘን ወደ ቤት ገባን ወደ ጎጃችን ወደ አለማችን

ተፈፀመ




"    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ   
  ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍7415👎4🔥2
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
.እንሂድ ወዳላት ቦታ ለመሄድ ብዙም ደስተኛ እንዳልሆነች በመገመት‹‹አዎ ምነው…?አባቴ እዛ ነው የሚኖረው ..በየሳምንቱ በዚህን ሰአት ይጠብቀኛል..ባይሆን ከዛ መልስ አንቺ የፈለግሽው ቦታ እንሄዳለን፡፡›አላት፡፡
‹‹አረ ችግር የለውም..እንዲሁ ያልጠበቅኩት ቦታ ስለሆነ ነው››ብላ በምትሄድበት ቦታ እንዳልተከፋች ተናገረች…እውነታው ግን እንደዛ አልነበረም፡፡
ከዛ በመሀላቸው ዝምታ ሰፈነ›…የሆነ ነገር ይናገራል ብላ ብትጠብቅም ለረጂም ደቂቃ ዝም አለ፡፡እሱ በጥልቀት ስለእሷ እያሰበ ነው…እሷ ከጠበቀችውና ከምታውቃቸው ወንዶች ሁሉ የተለየ ሆኖ እንዳገኘችውና በዛም እየተደመመችበት ሁሉ አሱም እጅግ ገራሚ ሴት ሆና አግቷታል…..የሌብነት ታሪኳ ግራ አጋብቶት ሳያበቃ አሁን መኝታ ቤቱ ገብታ የሰራችው ስራ ከግምቱ ውጭ ነው የሆነበት ‹‹ይህቺ ልጅ በህይወቴ የተከሰተችው በድንገgትና በአጋጣሚ ነው ወይስ ሆነ ተልዕኮ ኖራት አቅዳና አልማ?››ሲል እራሱን ጠየቀ..ቃል የተመረቀው በኮምፒተር ኢንጂነሪንግ ነው፡፡በስራው በጣም የተመሰገነ እና ፕሮፌሽናል ባለሞያ ነው፡፡ስልኩ ላይ አንድ እራሱ የሰራው አፕ አለ..ባለበት በ10 ሜትር ያለ ካሜራ መኖሩን ምልክት የሚሰጥ አፕ ነው…ለረጅም ጊዜ የለፋበትና ሚኮራበት ስራው ነው…ከስድስት ወራ በላይ ሙከራ ላይ የቆየና መቶ ፐርሰንት ሙከራውን አልፎ አሁን ለሽያጭ ሊያቀርበው ድርድር ላይ ይገኛል፡፡እና ልዩ መኝታ ቤቱ ከገባችበት ከደቂቃዎች በኃላ ይሄ አፕ ካንቀላፋበት ነቅቶ ድምፅ ሲያሰማው ማመን አቅቶት ክፉኛ የደነገጠው ለዛ ነው፡እዛ እሱ ቤትም ሆነ በጊቢው ምንም አይነት የካሜራ ዘር አንደሌለ እና ኖሮም እንደማያውቅ እርግጠኛ ነው፡፡ለማንኛውም ወደቤቱ ሲመለስ ያረጋግጣል .ለምን አለማ እንዳስቀመጠችውና እሱስ ምን እንደሚያደረግ ያስብበታል.
‹‹ምነው ዝም አልክ ፈራህ እንዴ ?››ስትለው ነበር ከሀሳቡ የባነነው፡
‹‹ለምንድነው የምፈራው?››
‹‹አይ…ምን አልባት የተሰረቀ  መኪና ውስጥ ያስገባሁህ መስሎህ …እንዳልታሰር ብለህ ፈርተህ እንደይሆን ?››
የማሪያምን ብቅል የበላ ይለፈልፋል ነው የሚባለው አይደል..የራሷ ክፉ ስራ ደጋግሞ ያስለፈልፋት ጀመር.
‹‹በፍፅም እንደዛ አላሰብኩም….››አለ ፍርጥም ብሎ፡
‹‹ብታስብም እኮ በቂ ምክንያት አለህ..ግን ማረጋግጥልህ መኪናዋ የራሴው ነች .. ማለቴ የእኔ እንኳን አይደለችም የእናቴ ነች፡፡››
‹‹ገባኝ….››
‹‹ግን ትገርማለህ…እንዴት ነው ስሜትህን እንደዚህ ማመቅ የምትችለው?›› አለችው፡፡
‹‹እኔ ስሜቴን ማመቅ..?እንዴት እንዳዛ ልትይ ቻልሽ…?››አላት በውስጡ‹‹እኔም በአንቺ ሚስጥራዊ ደርጊቶች ተገርሜያለሁ››ሲል አሰበ
‹‹እኔን በተመለከተ እስከአሁን ያየሀቸው ነገሮች ድርጊቶቼ  የተለመዱ እና ዝም ብለህ የምታልፋቸው ናቸው ማለት  ነው…? ምንም አያስደንቁህም…? የማወቅ ጉጉትህን አይቀሰቅሱም..? እና ምንም ጥያቄ የለህም….?››
‹‹ስለአንቺ  በጥልቀት  ለማወቅ ሁኔታዎችን እየገመገምኩ ነው..ማለት እንዳልሽው ከድርጊቶችሸ በፍቃድሽ ከምታደረጊያቸው ነገሮች በመነሳትና   እነሱን በመገጣጠም…ግን ጥያቄ ልጠይቅሸ አለሰብኩም.. ማለት ምንም ጥያቄ የለኝም››እውነቱን ነገራት፡፡
‹‹ማለት ጥያቄ ካልጠየቅከኝ እንዴት ታውቀኛለህ?››
‹‹ጥያቄ በመጠየቅ የሆነ ስውን በጥልቀት መረዳት እኮ አድከሚው መንገድ ነው…አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽ ለዛ መልስ ትሰጪኛለሽ…ግን ደግሞ መልስሽ ውስጥ ተደብቀው የሚወለዱ ሌሎች ጥያቄዎች ይፈልቃሉ…. መልስ ጥያቄ ..መልስ… ነገሩ ሁሉ  አዙሪት ነው የሚሆነው…..››አለ….ወደቤቱ ሲመለስ ሰለሚጠብቀው እሱን ለመሰል ስለተደበቀ ካሜራ እያሰበ፡፡
‹‹እሺ እራሴ እየጠቅኩ እራሴ ልመልስ..?›››
ዝም አላት.እሷ ማውራቷን ቀጠለች፡፡
‹‹ለምን ሌባ ሆንኩ…?መስረቅ ስለሚያስደስተኝ  ወይ  የመስረቅ በሽታ ስላለብኝ…መልሱ ሁለተኛው ነው፡፡የስርቆት በሽታ አለብኝ፡፡አስቂኝ ነው አይደል?፡፡ግን በሚገርም ሁኔታ  ይሄን በሽታ ደበሪ ነው፡ አወቃላሁ ደባሪነቱ የሚገለፅልኝ ግን  ካደረኩት በኃላ ነው ፤እንደ መጠጥ ወይም ሲጋራ ሱስ በለው..አንድ የሀሺሽ ሱሰኛ ፊት ለፊቱ ሀሺሽ ሲያይ እንደሚያቅበጠብጠው ሁሉ እኔም የሚሰረቅ ነገር በአቅራቢያዬ ካለ እንደዛ ነው ሚያደርገኝ፡፡ ምንም ያህል ብጥር እራሴን ወደኃላ መግታት አልችልም፡ ሆን ብዬ እኮ አይደለም ማለቴ እቅድ ወጥቼ ልስረቅ ብዬ በፍፅም ሰርቄ አላውቅም፡፡ የማደርጋቸው ነገሮች በሁኔታዎች ውስጥ ነው የሚከሰቱት፡፡ለምሳሌ ፀጉር ቤት ፀጉሬን ለመሰራት ሄጄ ተሰርቼ ከጨረስኩ በኃላ  ሂሳብ 200 ብር ከሆነ ሀምሳ ብር ጨምሬበት 250 ብር ከፍልን ባለሞያዎ ስትፍነከነክ አዘናግቼ የ25 ብር ማበጠሪያ ሰርቄ ቦርሳዬ ውስጥ ደብቄ ወጣለሁ፡፡››
‹‹እንደዛ ካደረግሽ በኃላ ምን ይሰማሻል?›ሲል የትዝብት ሳይሆን የሀዘኔታ በሆነ ድምፅ ጠየቃት፡፡ንግግሯን ከስሜቷ ጋር አንድ ላይ አጣምሮ ሲመዝነው ምንም አይነት ውሸት የሚመስል ነገር ሊያገኝበት አልቻለም…
እሷ ቀጠለች‹‹በወቅቱማ  አሷ ዞር እስክትል መጠበቁ…. .ማዘናጋቱ …ሌሎች ተስተናጋጆች እንዳያዩኝ መጠንቁ ከዛ ፐርፌክት በሆነ ታይሚንግ ማበጠሪያውን ባርሳዬ ውሰጥ ከትቼ ምንም እንዳልተፈጠረ በፈገግታ ሁሉንም ተሰናብቼ መውጣቱ በጣም ደስ የሚል እርከታ ነው የሚሰጠኝ..ችግሩ አካባቢውን ለቅቄ ትንሽ ራቅ ካልኩ በኃላ ነው.፡፡
ስሜቴ ሁኑ በአንዴ ዘጭ ይላል፡፡.ለምንድነው እንዲህ ያደረኩት.?አሁን ይሄ ማበጠሪያ ምን ይረባኛል..?ብያዝስ ምንድነበር የምለው.?እኚህንና ሌሎች መሰል ጥቄዎችን እየጠየቅኩ በጣም አዝናለሁ፡፡ አንዳንዴም ስቀስቅ ብዬ አለቅሳለሁ፡፡ .እራሴን እጠየፋለሁ፡፡ ለምሳሌ እንዳልኩህ የሰረቅኩት ማበጠሪያ ከሆነ ፀጉሯ የተንጨፈረረ የጎዳና ለማኝ ፈልግና የመኪናዬን መሰኮት ዝቅ አድርጌ ወረውርላታለሁ….ካልሆነም ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ እጥለዋለሁ…ስልክ ከሆነ ደግሞ  ብዙውን ጊዜ መልሰው ስለሚደውሉ የሆነ ቦታ አስቀምጥላቸዋለሁ.ሄደው ይወስዳሉ.. አንዳንዱ ደግሞ  ሊሳደብ ሲፎክር እልክ ይይዘኝና ዝም ብዬ ለአንዱ የሰፈር ጎረመሳ ሸልመዋለሁ...ብቻ አንድም ቀን የሰረቅኩት ነገር ትንሽ እንኳን አጓጉቶኝ ተጠቅሜበት አላውቅም…. ምክንያም ምሰርቃቸው ነገሮች ሁለ ቤቴን ያጨናንቁ ተራ ቁሶች ናቸው.ቢሆንም ግን እቃዎቹን አለመጠቀሜ እኔን ንፁህና ስራዬንም ልክ አያደርገውም፡፡...ያው ሰርቃለሁ ማለት ሌባ ነኝ..ሌላ ምንም ማስተባበያ ሊሰጥበት የሚችል ጉዳይ አይደለም…፡፡
‹‹ግን ተይዘሽ አታውቂም.?››
‹‹አንድ አራቴ››
‹‹ታዲያ እንዴት ተወጣሽው.?››
‹‹ሶስቱን ከተሰራቂዎቹ ጋር ተደራድሬ ብር ሰጥቼያቸው ለቁኝ፣አንዱ ግን ፖሊስ ጣቢያ ወስዶ አንድ ቀን አሳደረኝ፡፡›
‹‹እንዴት ?ልትደራደሪው አልቻልሽም ነበር?››
‹‹እንደውም መስረቄ ሳይሆን ለመደራደር ሞከሬ ነበር ይበልጥ ያበሳጨው... ሰውዬው ለካ ፖሊስ ነበር››
‹‹‹በተሰቀለው..ታዲያ በመጨረሻ እንዴት ሆንሸ?›
👍10711🔥2🥰2👏2👎1😱1
‹‹ያው እናቴ በየቦታው ዘመዶች አሏት..ለፖሊሱ ከሀለቆቹ ተደውሎለት ችግሬ ተነግሮት ተለቀቅኩ፡፡››
‹‹ግን እኮ ይሄ የስነልቦና ችግር እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡››
‹‹እሱማ ኪልፕቶሚያ የሚል ስያሜ ሰጥተው ከስነልቦና በሽታ ዝርዝሮች ውስጥ በመዝገብ እውቅና ሰጥተውታል ፡፡››
‹‹እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?››
‹‹ትርጉሙ ጤናማ ባልሆነ ውስጣዊ የስሜት  መነሳሳት ተገፋፍቶ  ያልሆነ አደጋ ውስጥ እራስን ከቶ ከዛ በመዳን የሚገኝ እራካታ ማለት ነው፡፡እኔና መሰሎቼ የዚህ ስነልቦናዊ ችግር ተጠቂዎች ነን..እኛን ከዋናዎቹ ሌቦች ሚለየን  ሰርቆቱን ምንፈፅመው አልመንና አቅደነው አለመሆኑና ለጥቅም ስንልል  አለማድረጋችን  ነው››
‹‹ታዲያ ህክምና የለውም? ››
‹‹እኔ እንግዲህ እዚህም አሜሪካም ሂጄ ተክሜያለሁ...ግን ውጤቱን ይሄው እንደምታየው ነው...ያ ማለት እነሱ እንደሚሉት ጉዳዩ የስነልቦና ችግር ሳይሆን ..ያው ክፉ አመል በለው፡፡›
‹‹አይመስለኝም..መጀመሪያ የስነልቦና ችግር መሆኑን ሳታምኚ አንዴት ታክመሽ መዳን ትቺያለሽ? ››ሲል የሰለቻትን አዕምሮ የሚፈትን ጥያቄ ጠየቃት ፡፡
‹እነሱም እንደዚህ ነው የሚሉኝ..ይሄ የበሽታው ባህሪ ነው፤ ተጠቂዎቹ የስነልቦና ተጠቂ ናችሁ ከሚባሉ ሌቦች ቢባሉ ይመርጣሉ አሉ፡፡››
‹‹እና ትክክል አይመስሉሽም?››
‹‹ሊሆን ይችላል ፤እኔ እንጃ ››
‹‹እንዳልኩት ህክምናወም ያልተሳካው ለዚህ ይመስለኛል እኔ እንደማስበው በተለይ ከስነልቦና ጋር ንክኪነት ያላቸው በሽታዎች  መድሀኒታቸው የሚገኘው በቅድሚያ በሽታው መኖሩን አምኖ ከመቀበል ላይ ነው…መድሀኒቱ የሚገኘው እዛው በሽታው ውስጥ ነው ይባላል?››
‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ .እስኪ ተመልሼ እሞክራለሁ››በዚህ ጊዜ መዳረሻችን የሆነው መቄዶኒያ ደረሰን ነበር.መኪናዋን አቁማ ሞተር አጥፍታ ወረደች…. ቀድሟት ወርዶ ስለነበረ ወደእሱ ተጠጋችና ጎን ጎኑ መሄድ ጀመረች፡፡
‹‹አዎ እንዳልሽው ህክምናውን መሞከር አለብሽ፡፡ ደግሞም አይዞሽ እኔም ከጎንሽ ነኝ››አለትና ወደራሱ ጎትቶ ጉያው ውስጥ ሸጎጣት… .ልጥፍ አለችበት...፡፡
ጠረኑን ወደውስጧ በጥልቀት ማገች..ውስጧን በልዩ ሁኔታ ተነቃቃ…፡፡

ይቀጥላል
👍109🥰138👏1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// .እንሂድ ወዳላት ቦታ ለመሄድ ብዙም ደስተኛ እንዳልሆነች በመገመት‹‹አዎ ምነው…?አባቴ እዛ ነው የሚኖረው ..በየሳምንቱ በዚህን ሰአት ይጠብቀኛል..ባይሆን ከዛ መልስ አንቺ የፈለግሽው ቦታ እንሄዳለን፡፡›አላት፡፡ ‹‹አረ ችግር የለውም..እንዲሁ ያልጠበቅኩት ቦታ ስለሆነ ነው››ብላ በምትሄድበት ቦታ እንዳልተከፋች ተናገረች…እውነታው…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

በፊት ፍቅር ማለት....?ብለው ሲጠይቋት በመራቀቅ እና በልበ ሙሉነት ትዘረዝር ነበር::አሁን ከዚህ ልጅ ጋር በአጋጣሚ ከተላተመች በኃላ ግን...ፍቅር ማለት ...?ብለው ሲጠይቋት መልሷ  ረጅም ዝምታ  ነው።እንደዛ ማድረጓ ፈልጋ አይደለም  …ከእሱ ጋር ከተጋራችው ስሜት አንፃር ፍቅርን ለመተንተን ብቁ የሆነ ሀሳቧን የሚመጥን ቃል  በከንፈራ ላይ ስለሌለ ነው።

በቀደም ሜቅዶኒያ በሄድ ቀን በጣም አሪፍ ሚባል ጊዜ ነበር ያሳለፉት…ከአባቱ ጋር አስተዋወቃት…አብረው ከሁለት ሰዓት በላይ አዛውንቶቸን በመንከባከብ የሚሰሩ የበጎ ስራ አገልግሎት ሰራዎችን  ሰሩ፡፡
ይሄ ተግባር  ለቃል  የዘወትር የእለተ እሁድ የግማሽ ቀን ተግባሩ ነው…ለልዩ ግን የመጀመሪያ ኤክስፒሪያንሶ ነበር..እና ከጠበቀችው በተቃራኒ እጅግ አስደሳችና ጭፈራ ቤት አምሽቶ ከመዝናናት በላይ በተሻለ ጥልቅ የሆነ ደስታ የሚሰጥ ተግባር ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡
ስራቸውን ጨርሰው በአባቱ ተመርቀው እና ተሰናብተው ከወጡ በኃላ መንገድ ላይ‹‹ምንም ነገረ ሳይከፈል ምንም ነገር ጥቅም ሳይገኝበት እንዲህ አይነት ፈታኝ ስራዎችን  መስራት የሚገርም ስብዕናን የሚጠይቅ  ነው››አለችው፡፡
‹‹ አይ በነፃ ይመስልሸል እንጄ በነፃ አይደለም…በዚህ ምድር ላይ ያደረግሽው ሁሉ ይመለሰልሻል.አሁን እነዚሀ የአረጋዊያንን ልብስ አጥበሽ በምርቃት ብቻ ተቀብለሽ ስትሄጂ በነፃ ያገለገልሽ መስሎሽ ይሆናል..ግን በሌላ መንገድ ታገኚዋለሽ…ለምሳሌ አሁን አይበለውና መኪናሽ ከሆነ መኪና ጋር ተጋጭታ አደጋ ደርሶብን ሆስፒታል ብንገባ   አንድ የማናውቀው ሰው ለሁለታችንም በናፃ ደም ለግሶን ከሞት ሊያተርፈን ይችላል፡፡ …ያደረግሽው በጎ ነገር ሁሉ ይፍጠንም ይዘግይም ይመለስልሻል…መጥፎውም ነገር እንደዛው›› እንደዛ ነበር ያላት፡፡
ያው እሷ በሰዓቱ ምንም እንኳን በንግግሩ ብትደመምም በትክክለኝነቱ ግን ሙሉ በሙሉ አላመነችበትም..ቢሆንም የሰማችው ግን በፅሞናና በመመሰጥ ነበር…ባለው ነገር ሙሉ እምነት ያልተሰማት ምክንያት ዕድሜያቸውን ሁሉ ክፍ ስራ እየሰሩ ግን ደግሞ በሰላም የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በዙሪያዋ ስለምታውቅ ነው፡፡ለቃል ግን እንዳዛ አላለችውም…፡፡ምን አልባት እንደዛ ብላው ቢሆን ‹‹በሰላም እየኖሩ መሆናቸውን በምን አወቅሽ…? ሰላም ማለት እኮ ትርጉሙ ሰፊ ነው..በህይወታቸው ደስተኛ ናቸው…?ጥሩና ሰላማዊ እንቅልፍ እየተኙ ነው…? አይነት ጥያቄዎችን በመጠየቅ በእጅ አዙር ይመልስላት እንደነበር እርግጠኛ ነበረች፡፡
ከዛን ከሰአት እንጦጦ ሄድ.. በየካፌውና ሬስቶራንቶቹ እየቀያየሩ ድንቁና አረንጓዴ  የሆነውን ወጣ ገባ መልካ ምድር እየጎበኙ ንፅህንና ነፋሻማውን አየር እየማጉ በደስታ ሲፈነጥዙ ዋሉና ማታ አንድ ሰዓት እቤቱ በራፍ ድረስ አድርሳው  ቅር እያላት ወደቤቷ ሄደች…፡፡
ከዛን ወዲህ ሁለት ቀን ተገናኝተው ሻይ ቡና ብለዋል…አሁን ግን ካየችው ሌላ ሁለት ቀን አለፋት ፡፡ናፍቆታል፡፡‹‹
‹‹አይገርምም ..አሁን ናፍቆኛል ስል መድህኔ ቢሰማ ምን ያህል ልቡ ይሰበራል?››ሳታስበው እራሱ ዝግንን አላት…፡፡ቢሆንም  ግን መናፈቋ የማይካድ ሀቅ ነው: አሁን በዚህ ምሽት እያደረገች ያለችው አልጋዋ ላይ እየተገላበጠች ስለእሱ ማሰላሰል ነው..ስለመድህኔ አይደለም…ስለቃል እንጂ ፡፡
‹‹አዎ እስኪ አይኑን ልየው›› አለችና ከመኝታዋ ተነስታ ላፕቶፖን ከተቀመጠበት አመጣች፡፡ ወደቦታዋ ተመልሳ ከፈትችው፡፡
እንዲህ አይነት ስራዎችን በተለያዩ ሰዎች ላይ እንደምትሰራ  የምታውቅ አንድ የትምህር ቤት ጓደኛዋ‹‹ ለምን ግን ደህንነት መስሪያ ቤት ሲርቪስን አታስገቢም፤አንቺ እኮ የተፈጠርሽው ሰላይ ለመሆን ነው፡፡ ብልሀቱንም፤ተንኮሉንም ማስመሰሉንም ተክነሽበታል››ትላት ነበር…፡፡በወቅቱ አስተያየቷን ብትቃወማትም አሁን ሳታስበው ግን እውነቷን ነው ብላ ማመን ጀምራለች፡፡
..ከእሱ መኝታ ቤት የቀበረችው ካሜራ ጋር የሚያገናኘውን ቁልፍ ተጭና እሱ ወደ መኝታ ቤቱ እስኪገባ መጠበቅ ጀመረች፡፡የፊት ለፊቱ ክፍል እንዳለ አውቃለች፡፡ ሙዚቃና አንዳንድ የሚንጋጉ ድምፅች  ከሚቀጠልው ክፍል ውስጥ መኖሩን ያሳብቃሉ…፡፡
መኝታ  ቤቱ ተከፈተ…ቃል ገባና በራፉን ዘጋው…፡፡ትኩረቷን ሰብስባ መከታተል ጀመረች፡፡ወደ ቁም ሳጥኑ ቀረበ፡፡ከፈተ.. ፡፡ቢጃማ አወጣ..፡፡
‹‹ውይ ልብሱን  ሊቀይር  ነው…፡፡››አለች..ግራገባት…ምን ታድርግ..?፡፡
‹‹ለጊዜው ቀይሮ እስኪጨርስ ላፕቶፑን ልዝጋው..ወይስ እኔ ከስሩ ዞር ልበል..?፡፡›› ውሳኔ ላይ ሳትደርስ ከላይ የለበሰውን ሸሚዝ አወለቀና በስነስርአት አጣጥፎ ጥግ ላይ ካለች ጠረጴዛ  ላይ አስቀመጠ..ሲሊፐሩን አወለቀና ባዶ እግሩ ምንጣፍ ላይ ቆመ፡፡ ሱሪውን መዥርጦ አወለቀ…ሰማያዊ ፓንት እየታያት ነው፡፡
‹‹..ወይ ምን እየሰራሁ ነው….?.ሱሪውን በተመሳሳይ አጣጥፎ  አስቀመጠ…፡፡
‹‹እንዴ ሌላ ነገር ሊያወልቅነው እንዴ?›› ስትል እግዜር ይስጠው አልጋው ጠርዝ ላይ አስቀምጦት የነበረውን ፒጀማ አነሳና በየተራ ለበሰ…፡፡መሀል ወለል ምንጣፍ ላይ በጉልበቱ ተንበረከከ… …፡፡
‹‹እንዴ ምን እየሰራ ነው..?ስትል እጁን ወደፊቱ ዘረጋ….ከዛ ድምፅ አውጥቶ ከዚህ በፊት ሰምታው የማታውቀው አይነት አዲስ ፀሎት መፀለይ ጀመረ..‹‹ታድሎ የየትኛው ሀይማኖት ፀሎት ይሆን ..?ምን አልባት አንድ ቀን በደንብ ስንግባባ ጠይቀው ይሆናል..እናም አብሬውም ከጎኑ ተንበርክኬ እጆቹን በእጆቼ ይዤ እፀልይ ይሆናል፡፡››ስትል ተመኘችና ፀሎቱን በጥሞና መከታተል ጀመረች፡፡
///
የውበቶች ሁሉ ድምር ውበት...የሙዚቃዎች ሁሉ ጥቅል ዜማ....የብርሀን ሁሉ  ብርሀን ...የሠው ልጆች ሁሉ ጥምር እስትንፍስ ...እሱ እግዚያብሄር ነው።መላእክቶች ቅርንጫፍ ላይ የበቀሉ ወረቃማ ቅጠሎች ናቸው። ፀሀይ ከልብ አንድ ጥግ መንጭታ  ለአጥናፍ አለሙ ብርሀንና ሙቀት የምትለግስ  የህይወት ምንጭ ነች።  ጨረቃ ከአይኖቹ ብሌን ጫፍ የምትገኝ  የውበት ፈርጥ ነች..ከዋክብቱ ግንባሩ ላይ ልክ እንደፀጉር የተበተኑ  ድንቆች ናቸው ....እኛ የሰው ልጆች  የአእምሮው ህብረሰረሰር ቅንጣት ህዋስ ነን።የእኛ ኢምንት ሀሳቦቻች  ከሱ  እልቆ መሳፍርት ሀሳብ  እየተሸረፍ ሚበተኑ ህልሞቻችን ናቸው። አፅናፍ አለም በእጅ መዳፍ ላይ የተበተኑ የሚነበብና የሚተነተኑ  መስመሮች ናቸው። የምድር ደኖችና ተክሎች  እግሮቹ ላይ የበቀሉ ፀጉሮች ናቸው።  የፍጥረታት ነፍስ ከትንፍሹ የተሸረፈች  የህይወት እርግብግቢት ነች።እግዚያብሄር ሁሉም እና አጠቃላዪ ማለት ነው። ጥልቀቱ ወሰን አልባ ርዝመት የማይደረስበት ...ልኩ ይሄን ያህል ነው የማይባል ...  የነገሮች ሁሉ የመጨረሻው ቅንጣት ኢነርጂ ... በጊዜ የማይገመት በቦታ የማይታጠር   ኤልሻዳይ አምላክ ነው።
/
ከዛ ፀሎቱን እንደጨረሰ ትንፋሽ በጥልቀት ወደውስጥ እየሳበ ከዛ አምቆ ይቆይና ወደውጭ ይለቀዋል…መልሶ ወደውስጥ ይስብና ወደውጭ ይለቀዋል.. ያለመታከትና መሰልቸት ለአስር ያህል ደቂቃ እንደዛ ካደረገ በኃላ...ባለበት ያለምንም እንቅስቃሴ አይኖቹን ጨፍኖ ፀጥ አለ…፡
👍794🔥1
‹‹ወይኔ ይሄ ልጅ መንፈሳም ነገር ነው እንዴ?››ስትል አጉረመረመች፡፡ ከአስር ደቂቃ በኃላ ቀስ ብሎ ተነሳና በዝግታ ወደአልጋው ወጥቶ ከውስጥ በመግባት መብራቱን በእጁ ተንጠራርቶ አጥፍቶ  ተኛ ፡፡እሷም ላፕቶፖን ከእሱ ቤት ጋር ያለውን ግንኙነት አቆረጠችና ወደራሷ ሀሰባ  ተመለሰች….
‹‹እስከመቼ ነው ይሄን ልጅ መሰለል የምቀጥለው..?ጥቅሙስ ምንድ ነው….?ባለብኝ ሁለት ሱስ ላይ ሌላ ሶስተኛ ሱስ….››
ከዚህ ልጅ ጋር  በጠነከረና ከዚህ በባሰ ሁኔታ ፍቅር ሳይዛት ሾልካ ማምለጥና እራሷን ማዳን እንዳለባት ወሰነች፤ከዛ ስልኳን አነሳችና ደወለች…መድህኔ ጋር ነው፡፡

ይቀጥላል
👍6113
#ኑ_አብረን_እንበድ
.
.
የቀን ጅብ ሲሔድ
የተራበ ጅብ ፣ እያሳደደኝ
ኑሮ እንደ ዱካክ ፣ እየከበደኝ
የበቀል  ውሃ
እያሳሳቀ ፣ ለሞት ሲወስደኝ
በላዬ ሲወርድ
የምድር መርገም ፣ የሰማይ ቁጣ
እንኳን መቆሚያ ፣ መውደቂያ ሳጣ
ርሃብ ጥማቴ ፣ ሞት እያስመኘኝ
መንግስት ደርሶ ፣ ማሳ አስጎበኘኝ
ከማሳም ማሳ ፣ የሚላክ  ስንዴ
ይሄን ሁሉ ግፍ
ከሀገር በሰፋ ፣ በአንድ ሆዴ
ይዤ እየኖርኩኝ
የጤና አይደለም ፣ አለማበዴ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍8821😁4🥰3👏3
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከአስር ጊዜ በላይ ደውሎላት ነበር ቀልቧ ቃል ላይ ተለጥፎ ስለነበረ አላነሳችለትም ..እና አሁን ለዛ ነው እየደወለችለት ያለችው፡፡
አነሳላት‹‹‹ምነው አንቺ ይሄን ሁሉ ስደውል?››
‹‹አላየሁትም ነበር..ስልኬን መኝታ ቤት ጥዬ ሳሎን ነበርኩ….››
‹‹ምን አስዋሸሽ ማሚ ጋር ደውዬ መኝታ ቤትሽ እንደሆንሽ ነግራኛለች፡፡››
‹‹አይ አንተ ሰው..ስለእኔ ዘበኞችንም ቤት ሰራተኞችንም እናቴንም መጠየቅ አይደክምህም?››
‹‹እንደዛ እንዳላደርግ ከፈለግሽ ስፈልግሽ ተገኚያ››
‹‹እሺ……››
‹‹በቃ ለንቦጭሽን አትጣይ..ንፍቅ ብለሺኝ እኮ ነው፡፡››
‹‹እንዴ ጥዋት እኮ አብረን ነበርን››አለችው…ስልክ ስላላነሳችለት ብቻ እንዲህ መንጨርጨሩ አስገርሞታል…ምን ስታደርግና ምን ስታስብ የእሱን ስልክ እንዳላነሳች እውነቱን ቢያውቅማ ጨርቁን እንደሚጥል እርግጠኛ ነች፡፡
‹‹እኔ እኮ እንደአንቺ ደንዳና ልብ የለኝም…ለሰከንድም ባትለይኝ ደስ ይለኛል… በጣም እኮ ነው የማፈቅርሽ››
‹‹እኔም አፈቅርሀለሁ››ለምን እንደሆን ባታውቅም ይሄን ቃል ምን አልባት ከሺ ጊዜ በላይ ለእሱ ተጠቅማለች፡፡ከልቧ ደስ ብሏትና የእውነቷን ነበር ቃሉን ከአንደበቷ የምታወጣው….፡፡ዛሬ ግን ከበዳት ….እየሻከረት ነው የተናገረችው፡፡
‹‹…ፍቅርን እያቆሸሽኩት ይሆን እንዴ?…..ቺት እያደረኩብት ይሆን እንዴ…?ምን ያደረኩት ነገር አለ….? ተጀናጀንኩ.. ተሳሳምኩ..ምን ፈፀምኩ….?›› ብላ እራሷን ለማፅናናት ብትሞክርም ልቧ ግን ለሆነ ሌላ ሰው መቅለጥ መጀመሯን መዋሸት አልቻለችም…፡፡
ከእዚህ ጉድ ለመውጣት ቶሎ ይሄን ሰው ማግባት እንዳለባት ቅፅበታዊ ውሳኔ ወሰነች ‹‹…ልዩ ሳትወራጂ ይሄን ነገር አድርጊው››እራሷን መከረች…እና ወዲያውኑ ወደተግባር ተሸጋገረች፡፡
‹‹ስማ…›
‹‹ወዬ የእኔ ፍቅር…››
‹‹ደግሞ ሸጉጠሀኝ ውለህ ሸጉጠኸኝ ማደር ከፈለክ ጠቅልሎ ማግባት ነዋ…››
‹‹ምን?››
‹‹አዎ ሰምተሀል…››
‹‹መለመን ከጀመሪኩ እኮ አመት ሊያልፈኝ ነው…አንቺ ነሽ ሰበብ እየፈጠርሽ ስታዘገይው የነበረ፡፡››
‹‹ለትምህርቴ ብዬ ነዋ..አሁን ደግሞ ለምርቃት ሶስት ወር ነው የቀረኝ፡፡››
‹‹አንቺ የሆነ ሀሳብ መጣልኝ..፡፡››
‹‹ምንድነው ?ልስማው…››
‹‹ለምን አንድ ቀን አናረገውም…?ማለቴ አንድ ቀን እንኳን ባይሆን ተከታታይ ቀን ይሁን..፡፡ ››
‹‹አይ አንደዛ አይሆንም.. ሁለቱንም ለየብቻ ነው ማጣጣም የምፈልገው… ግን ምርቃቴንና ቀለበቴን በአንድ ቀን ማድረግ እንችላለን፡፡
‹‹አሪፍ ነው…ግን ቀለበት አስሮ ብቻ አንድ ቤት መግባት ይቻላል እንዴ?››
‹‹አዝናለሁ እንደዛ አይቻልም፡፡››
‹‹ወይ ታዲያ ምንድነው ትርፌ?››
‹‹በወሩ ደግሞ ሰርግ ይሆናላ…››
‹‹ምሽቱን ሙሉ ስታበሳጪኝ ያመሸሽው እንዲህ አይነት የሚያስፈነጥዝ ዜና ልታሰሚኝ ነው…..በስመአብ ….በጣም ነው የማፈቅርሽ..››
‹‹እኔም አፈቅርሀለሁ..በል ደህና እደር..፡፡››
‹‹ደህና እደሪ …ደግሞ ነገ አላልኩም እንዳትይ….ንግግራችንን ቀድቼዋለሁ››
‹‹የሰው ድምፅ ያለፍቃድ መቅዳት ወንጀል እኮ ነው፡፡››
‹‹የሰው ድምፅ አልቀዳሁም ፤የሚስቴን ነው…የሚስቴ ድምፅ ማለት ደግሞ የራሴ ነው፡፡››
‹‹በል ይሁንልህ… ቻው፡፡›
‹‹ቻው››
ስልኩን ዘጋችና በድንጋጤ ጭንቅላቷን ያዘች‹‹…ልዩ ምድነው የሰራሽው…? አሁን ከአራት ወር በኋላ ሚስትና የቤት አስተዳዳሪ ለመሆን ዝግጁ ነሽ……?ልጅ ወልደሽስ ማሳደግ ትችያለሽ…?.›› እራሷን አምርራ ብትወቅስም አንዴ ከአንደበቷ ያወጣችውን ቃላት ሰብስባ መልሳ ልትወጣቸው አልችለችም፡፡
‹‹….እስኪ ገና ለገና ፍቅር ከሌላ ሰው እንዳይዘኝ ተብሎ ያልሆነ መክለፍለፍ ውስጥ ይገባል…?››እራሷን አምርራ ወቀሰች፡፡
ከልጁ ፍቅር እንዳይዛት ቀላል ዘዴዎች ነበሩላት..ለምሳሌ እቤቱ አለመሄድ… መኝታ ቤቱ የቀበረችውን መከታተያ እንዳይሰራ ማበላሸት…ስልኩን ከስልኳ ላይ ማጥፋት…በቃ ካልደወለችለት እንደማይደውልላት እርግጠኛ ነች..እቤቱ ካልሄደች እሱ እቤቷ አይመጣም…ጭራሽ አድራሻውንም አያውቀውም…ታዲያ ከእሱ ፍቅር እንዳይዛት ልትወስድ ያሰበችው እርምጃ ምን የሚሉት ነው .. በቅፅበታዊ ውሳኔዋ እራሷን ጠላች …
ግን ፍቅር እንዳይዘኝ እንዳይዘኝ የምትለው እስከአሁን አልያዘትም ማለት ነው…..?ፍቅር ያዘት ተብሎ በእርግጠኝነት የሚወራው የፍቅሩ መጠን ምን ያህል ሲሆን ነው? መለኪያውስ ምንድነው?ይህንን እሷስ ታውቀዋለች?
እና ደግሞ አሁን በዚህ ሰአት ቃል ከተኛበት ተነስቶ ከራሷ ኮሚፒተር እሱ ቤት በደበቀችውን ካሜራ ሀክ አድርጎ እሱን መኝታ ቤቱ የሚያደርገውን እያየች እያሳየች የነበረውን ስሜት መድሀኔ ጋር ደውላ ስለመጋባት የተነጋገረችውን ስልኩን ከዘጋች በኃላ በተናገረችው ተፀፅታ ስትቆጭ ጠቅላላ ቆይታዋን ሰምቶ ተገርሞ መልሶ እንደተኛ ብታውቅ ምን ትል ይሆን?

ይቀጥላል
👍95🥰306😁6😱2🔥1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ከአስር ጊዜ በላይ ደውሎላት ነበር ቀልቧ ቃል ላይ ተለጥፎ ስለነበረ አላነሳችለትም ..እና አሁን ለዛ ነው እየደወለችለት ያለችው፡፡ አነሳላት‹‹‹ምነው አንቺ ይሄን ሁሉ ስደውል?›› ‹‹አላየሁትም ነበር..ስልኬን መኝታ ቤት ጥዬ ሳሎን ነበርኩ….›› ‹‹ምን አስዋሸሽ ማሚ ጋር ደውዬ መኝታ ቤትሽ እንደሆንሽ ነግራኛለች፡፡››…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በተለያየ ጊዜ ከሶስት ከሚበልጡ ወንዶች ጋር የመተሻሸት እና የመሳሳም አጋጣሚዎች አሳልፋለች። ከእነሱም መካከል አንድ መድህኔ ነው። ግን ከቃል ጋር ቁጭ ብሎ ማውራትን ያህል ንዝረቱ ለነፍሷ ተሰምቷት አያውቅም።ቃል አፈቅርሻለሁ ብሏት አያውቅም...እሷም እንደምታፈቅረው ነግራው አታውቅም። ሲገናኙ ፍቅር የወሬያቸው ዋና ማጠንጠኛ ሆኖ አያውቅም።
ግን ቃል ስለምንም ያውራ ስለምንም ወደእሷ አነጣጥሮ የሚረጨው ስውር ኃይል አለ..ሳታስበው ሙላት ይሰማታል... በሰውነቷ የሚለቀው ንዝረት ተርገብግቦ ተርገብግቦ ሲሰክን ከወሲብ እርካታ እጥፍ የሆነ ደስታን ይረጫል...ይሄ ልምድ ለእሷ ገራሚ ነው ።እናም ደግሞ ሱስ አስይዟታል።
….ብዙውን ጊዜ ከስራ ሲመለስ በራፍ ላይ መኪናዋን አቁማ ትጠብቀዋለች..ተከትላው ወደቤት ትገባና ሲጫወትና የባጥ የቆጡን ሲያወሩ ቆይተው ከምሽቱ አንድ ወይም ሁለት ሰዓት ላይ ወደቤቷ ትሄዳለች… አልያም መኪናዋ ውስጥ ታስገባውና ይዛው ወደ መሰላት ቦታ ወስደው እስከተቻላት ሰዓት ድረስ አብራው ትቆያለች.››
አሁን ያሉት ኢትዬጵያ ሆቴል ነው…ሰዓቱ 12፤40 ሆኗል ..መክሰስ ከበሉ በኃላ…ለስላሳ ነገር እየጠጡ ጫወታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ከብዙ ጫወታ በኃላ ድንገት አዲስ ርዕስ ከፈተች‹‹እና ጓደኛህን መች ነው ምታስተዋውቀኝ?››ፍቅረኛህን ለማለት ፈልጋ ነበር ግን ደግሞ ተናነቃት፡፡
‹‹እነግራትና የሚመቻትን ጊዜ ጠይቄ እነግርሻለሁ››አላት፡
‹‹አዎ አስተዋውቀን..እሷም መቼስ እንደአንተ አይነት ከሆነች የዕድሜ ልክ ጓደኛ ነው የማደርጋት››አለችው…በውስጧ ፍራቻና ንዴት እየተቀጣጠለ፡፡
‹‹እንደእኔማ እንዴት ልትሆን ትችላለች….?ደግሞ እንደእኔ አይነት ሌላ ምን ያደርግልሻል.. እኔው አለሁ አይደል?››አለት፡፡
‹‹እና አንተን የዕድሜ ልክ ጓደኛዬ እንዳደርግ እየመከርከኝ ነው››አለችው በውስጧ ሌላ ምቀኝነት ተንኮል እያብሰለሰለች…፡፡
‹‹እንደእሱ ነገር..እሷን ደግሞ በራሷዋ ማንነት ትቀበያታለሽ ማለት ነው፡፡››
‹‹ግን ምንድነው የምትሰራው ..?ተማሪ ነች?››
‹‹አይ የመንግስት ሰራተኛ ነች….ውጭ ጉዳይ ውስጥ በፀሀፊነት ነው የምትሰራው››ደስ አለት….ለምን እንደሆነ ግን አታውቅም፡፡
‹‹አይ ጥሩ ነው..ታዲያ ስራ ካላት አኮ እስከአሁን መጋባት ነበረባችሁ…የዘመኑ ወንዶች መቼስ ጋብቻን እንደመቅሰፍት ነው የምትፈሩት..››
‹‹አይ እኔ አልፈራም..መጋባትም እፈልጋለሁ…እሷ ግን ?››ንግግሩን አንጠልጥሎ ተወው፡
‹‹እሷ ምን….?››መልሱን ለመስማት ተስገበበች፡
‹‹እሷ የልጅነት እቅድ ነበራት ..ገና ልጆች እያለን ምን አልባት እሷ የ13 እኔ ደግሞ የ14 አመት ታዳጊዎች ሳለን እንደማፈቅራት ነግሬያት ወደፊት እሷን አግብቼ መኖር እንደምፈልግ ነግሬያት ነበር››
‹‹ታዲያ እሷ ምን አለችህ…?እርግጠኛ ነኝ እሺ ነው የምትልህ›› አለችው..በምን ስሌት ነው እሺ እንደምትለው እርግጠኛ መሆን የቻለችው...?ልጅቷ ቀይ ትሁን ጥቁር….ቆንጆ ትሁን አስቀያሚ አታውቃትም፡፡ብቻ እኔ ብሆን በሚል እሳቤ መዝና ነው ሀሳቧን የሰነዘረችው፡፡ እሱም ለምን እንደዛ እንዳለች ገብቶታል፡፡
‹አዎ ግን በተለየ መልኩ ነው እሺ ያለቺኝ?››ሲል መለሰላት፡፡
‹እንዴት?››
ብዙ አመት ወደኃላ ተመልሶ ትዝታውን ይተርክላት ጀመረ‹‹ያንን ጥያቄ ስጠይቃት ነገ መልስልሀለሁ ብላ ነበር በእለቱ የተለያየነው...በማግስቱ ወደቤተክርስቲያን ይዛኝ ሄደች.. ከዛ የእናቷ መቃብር ጋር ወሰደችኝ፡፡በጣም ነበር የደነገጥኩት.ይታይሽ በ14 አመት ከምትወጂያት ልጅ ጋር እናቷ መቃብር ስር ቁጭ ብለሽ ስለፍቅር ስታወሪ..…ግን ፍራቻዬን በውስጤ አፍኜ ያስቀመጠቺኝ ቦታ ቁጨ በማለት የምትለኝን በፅሞና መስማቴን ቀጠልኩ፡፡እና በወቅቱ እንዲህ ነበር ያለቺኝ፡፡‹‹….ይሄውልህ ቃል አኔም በጣም ነው የምወድህ ፤ማግባትም የምፈልገው አንተንና አንተን ብቻ ነው.. ግን ለእናቴ ቃል ገብቼላታለሁ…የእራሴ አሪፍ ቤት ሳይኖረኝ ባል ባገባ የአንቺን እናትነት እንደካድኩ ይቆጠርና እጥንትሽም ይውቀሰኝ ብዬ …ይሄንን ቃል ያስገባቺኝ ልትሞት በጣር ላይ በነበረቺበት በመጨረሻው ቀን ነው…እናም ከዛሬ ጀምሮ አንተም እንደምታፈቅረኝ እኔም እንደማፈቅርህ አውቀናል.. ዳግመኛ ሰለእዚህ ጉዳይ አንስተን የምናወራው ግን ከሁለት አንዳችን የግላችን የሆነ ቤት መስራት ወይም መግዛት የቻልን ጊዜ ብቻ ነው፡፡›አለችኝ፡፡
‹‹ካልቻላችሁስ?››
‹‹እኔም ይሄን ጥያቄ የዛኑ ቀን ነበር የጠየቅኳት.እሷ ግን ቆፍጠን ብላ ካልቻልን ምንም ማደረግ አንችልም… እንደተፋቀርን እንለያያለን ማለት ነው….ግን የግድ መቻል አለብን .እግዚያብሄርም ይረዳናል፡፡›› አለችኝ.፡፡
‹‹እና አንተም ተስማማህ?››
‹‹ይሄ እኮ የእሷ የማይሻር ውሳኔ ነው…የእኔ መስማማትና አለመስማማት ቦታ የለውም››
‹‹ቆይ ያልገባኝ እናተዬው እንደዛ አይነት ግራ የተጋባው ቃል ለምንድነው ያስገባቻት….ለዛውም ገና ለአቅመሄዋን እንኳን ባልደረሰችበት ዕድሜ ላይ›››
‹‹እናትዬውማ እንደዛ ያደረጉት እራሳቸው ከገጠማቸው የህይወት ገጠመኝ በመነሳት ይመስለኛል፡፡ የእሳቸው እጣ በልጃቸውም እንዳይደገም ከመፍራት የተነሳ…እናትዬው ከአባቷ ጋር ተፋቃቅረው በኪራይ ቤት ነበር የተጋቡት…ከዛ ቃል እና አንድ ታናሽ ወንድሟ ተወለዱ፤ቃል የአምስት አመት ወንድሟ የሁለት አመት እያሉ አባትዬው ድንገት ታሞ ይሞታል…ቤተሰቡ ሙሉ በሙሉ የሚተዳደሩት በአባትዬው ገቢ ስለነበር ከፍተኛ ችግር ላይ ይወድቃሉ.መጀመሪያ ተከራይተው ከሚኖሩበት ሶስት ክፍል ቤት ወደሁለት ክፍል፤ ከዛ ወደአንድ ክፍል እያሉ መጨረሻ በረንዳ እስከመውጣት ሁሉ ደርሰዋል ፡፡በዛ ስቃይ መካከል ነው ወንድሟና እናቷ በተከታታይ የሞቱት..እና እናትየው እንደሚያምኑት ቢያንስ አንደ ክፍል የራሳችን ቤት ቢኖራቸው ኖሮ ልጆቻቸውን የጉልበት ስራም ቢሆን በመስራት ማሳደግ የችሉ እንደነበረ ነው….እና ለዛ ነው ልጅቷንም በእሷቸው የደረሰ የልጆችን ስቃይ የማየት መከራ በእሷ እንዳይደርስ ከመፈለጋቸው የተነሳ በእንደዚህ አይነት ቃል ኪዳን ያሰሯት፡፡››
‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው?›፡ያለበትን አጣብቂኝ አሰበችና አሳዘናት፡፡ቢሆንም ግን ይሄንን ክፍተት ልትጠቀምበት እንደምትችል አሰበችና ፈገግ አለች፡

ይቀጥላል
👍13115🔥5🤔4👎1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ በተለያየ ጊዜ ከሶስት ከሚበልጡ ወንዶች ጋር የመተሻሸት እና የመሳሳም አጋጣሚዎች አሳልፋለች። ከእነሱም መካከል አንድ መድህኔ ነው። ግን ከቃል ጋር ቁጭ ብሎ ማውራትን ያህል ንዝረቱ ለነፍሷ ተሰምቷት አያውቅም።ቃል አፈቅርሻለሁ ብሏት አያውቅም...እሷም እንደምታፈቅረው ነግራው አታውቅም። ሲገናኙ ፍቅር የወሬያቸው ዋና ማጠንጠኛ…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው?›፡ያለበትን አጣብቂኝ አሰበችና አሳዘናት፡፡ቢሆንም ግን ይሄንን ክፍተት ልትጠቀምበት እንደምትችል አሰበችና ፈገግ አለች፡
‹‹አሁንም ምን አደርጋለሁ ሎቶሪ እንዲወጣልኝ እየፀለይኩ ነው ልበልሽ.?እንደማንኛውም የአዲስ አበባ ኑዋሪ ኮንደሚኒዬም ተመዝግቤ  በመቆጠብ እድሌን እየጠበቅኩ ነው…በስንተኛው ዙር በየትኛው አመት ነው የሚደረርሰኝ? የሚለውን ለመገመት ምን ይህል አስቸጋሪ እንደሆነ ታውቂያለሽ…ሌላ አማራጭ ለመፈለግ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ እንኳን ቤት ለመስራት 75 ካሬ መሬት ለመግዛት እራሱ ስንት ብር እንደሚያስፈልግ ...ብቻ ተይው…ለማኛውም ቃል የተጋባባነውን ነገር ማሟላት ስንችል ነበር እንጋባለን ያልነው..እስከአሁን ማድረግ አልቻልንም..በተለይ እኔ ኃላፊነቴን መወጣት አልቻልኩም…››አላት.በዝርዝር የነገራት ታሪኩ በሙሉ እውነት ቢሆንም መደምደመያው ላይ ግን ዋሽቷታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቃል ባንክ ደብተሩ ውስጥ ቢላ ቤት ባያስገዛም ቢያንስ ሶስት ክፍል ሰርቢስ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ የሚያስገዛ ብር ባንክ ደብተሩ ላይ አለ..እርግጥ ይሄ ብር እጁ የገባው ከብዙ ዓመት ልፋትና ጥረት በኃላ ከስድስት ወር በፊት ነው..ችግሩ ብሩን ሲያገኝ ብሩን ተጠቅሞ እቤቱን መግዛት ትርጉመቢስ የሚያደርግ ጉዳይ ውስጥ ገብቶ ነበር…እቤቱን የሚፈልገው ጊፍቲን ለማግባት ነበር፡፡በድንገት በህይወቱ በተሰነቀረው ግዳጅም ውዴታም በታከለበት ትልቅ የህይወት አላማ ምክንያት ደግሞ ጋብቻ መስርቶ ባለቤት እና የልጆች አባት የመሆን እድል የለውም.. ቢያንስ ለሚቀጥሉት15 እና ሀያ አመት ያንን ማድረግ አይችልም፡፡
አሁን ከዚህ ከተማ ከመሰወሩ በፊት መከወን የሚፈልገው አንድ ብቸኛ ጉዳይ ቢኖር  ጊፍቲ በእሱ ተስፋ ቆርጣ የራሷን ህይወት መስመር መፈለግ እንደትችል ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ..በዛም ምክንያት ስላለው ብር እንድታውቅ አላደረገም… ያንን ካወቀች እንጋባ ምን እየጠበቅክ ነው ብላ ጉሮሮውን እንደምታንቀው ያውቃል…እሱ ደግሞ በዚህ ምክንያት ላገባሽ አልችልም ብሎ ምክንያት ደርድሮ  ሊያስረዳት አይችልም፡፡..በዚህም ምክንያት ግራ በተጋባበት ጊዜ ነው… ልዩ በተአምራዊ አጋጣሚ ወደ ህይወቱ የገባችው..እና የእሷ መግባት በጊዜው የሚያደነጋግርና ግራ ሚያጋባ ስሜት የፈጠረበት ቢሆንም እያደር ግን ምን አልባት በምክንያት ነው በሚል ስሌት ውስጥ በመግባት በደስታ ተቀብሎታል…፡፡
ጊፍቲን ከአሱ ህይወት ነጥሎ ቦታ በማስያዙ ጉዳይ ላይ በሆነ መንገድ ትረዳኝ ይሆናል የሚል ተስፋ ስንቆባታል..ለምን እንደዛ እንዳሰበ ግን ለራሱም ግልፅ አልሆነለትም…ምን አልባት ከተገናኙበት ቀን አንስቶ እሱ ላይ በሚታሳየው መቅላብለብና የጋለ ስሜት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡  ደግሞም ሰሞኑን እየተሰማውና እያሰበበት ያለ ሌላ ጉዳይ አለ.፡፡የራሷ ልዩ ጉዳይ…ከተቻለው ባለችው ጊዜ እሷንም ከተጠናወታት የሌብነት ልክፍት እንድትፈወስ ቢያግዛት ደስ ይለዋል…አዎ በተቀሩት ጥቂት ወራቶች እሷ እረድታው የጊፍቲን ጉዳይ ከደር ቢያደርስና ለዛ ውለታዋ ምላሽ ደግሞ እሷን ከሌብነት አመሏ እንድትላቅ ማድረግ ቢችል በደስታ ወደአዲሱ የህይወት ጥሪው ያለምንም ቅሬታ ይጓዛል፡፡
ልዩ ግን በነገራት ነገር  በጣም አሳዘናት…
‹‹እና በቅርበ የሚስተካከል ይመስልሀል?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አላውቅም..እንዲስተካከሉ ከልቤ ጥራለሁ….››ነበር መልሱ፡፡
‹‹አሁን እኮ ነገሮች ተቀይረዋል..ማለት እሷም ሀሳቧን ቀይራ ሊሆን ይችላል ለምን አታናግራትም››
‹‹አይ እንደዛማ አላደርግም...ቀይራ ከሆነ እራሷ ነች ልትነግረኝ ሚገባ…እኔ ለሙት እናትሽ  የገባሽውን ቃል ለእኔ ስትይ እንዲህ አድርጊ እንዳዛ አድርጊ  ልላት አልችልም…እንደዚህ አይነት ነገር በጣም ሴንሴቲቭ ስለሆኑ የሰውን ስሜት እንዴት እንደሚረብሹ መገመት ከባድ ነው››
‹‹እኔ ብሆን ግን ገና ለገና መቼ ሊሳካ እንደሚችል ለማላውቀውን ነገር በጥበቃ ጊዜዬን  አላባክንም… .የምወደውን ሰውም አላሳቅቅም..እንደው ዘልዬ ነበር የኪራይ ቤትህ ውስጥ ቢሆንም የምገባው፡፡›አለችው .እንደዛ ያለችው ከምሯን ነው..እናቷ ምን ነካቸው…
‹‹ሊሆን ይችላል…..አንዳንድ ነገሮች ማለት ጥያቄዎቻችን የእኛ ብቻ አይደሉም አብረውን ያደጉ ናቸው..ምን አልባት የእሷ የራሴ መኖሪያ ቤት ሳይኖረኝ አላገባም የሚለው ውሳኔ ከእናቷ ይመንጭ እንጂ እሷም ደጋግማ በማሰላሰል የራሷ የህይወት ዋና ግብ አድርገዋለች ፡፡ ከእናቷ ጋር ከኪራይ ቤት ሲባረሩና እናትዬው እነሱን  ሚያሳድሩበት አጥተው ሲያለቅሱ በጮርቃ ዕድሜዋ ስትታዘብ ስለነበረ ያን በከፊል ንቁ በሆነው አዕምሮዋ ተቀብሮ ዳብሮ በቃ አሁን የሀሳቧን ግማሽ ተቆጣጥሮታል  ….አዎ.ግምቴ እንደዛ ነው፡፡.››አላት…እዚህ ላይ የእውነት ሚያምንበትን ነገር ነው የተናገረው….ለብዙ አመት ጊፍቲ ‹‹በቃ የቤቱን ሀሳብ ትቼዋለሁ፤እንጋባና አንድ ላይ ሆን ቀስ ብለን እንሰራዋለን ወይም እንገዛዋለን ››ትለኛለች ብሎ ሲጠብቅና ሲጎጎ ኖሯል…በወቅቱ እንደጉጉቱ እንደዛ ብላው ቢሆን ኖሮ በአንድ አፍ ብሎ ዘሎ ወደጋብቻው እንደሚገባ እርግጠኛ ነበር.እንደዛ ቢሆን ደግሞ ዛሬ የአንድ ወይም የሁለት ልጆች አባት ሆኖ እቤቱም ተገዝቶ የሁለቱም የልጅንነት ምኞት እውን ሆኖ ነበር….እሱም አሁን ሊጓዝበት ወደተሰናዳው አዲስ የህይወት ተልዕኮ የሚታጭበትም የሚገባበትም ምንም አይነት እድል አይኖርም ነበረ.እንግዲህ ህይወት እንዲች ነች፡፡ ጊዜ ቦታና አጋጣሚዎችን አንዴ ከተላለፉ በቀጣይ ሚገጥመን ሌላ ታሪክና ሌላ መንገድ ነው፡፡
ልዩ‹‹ታድለሀል››ስትል ጫወታውን አስቀጠለች፡፡
‹‹እንዴት?››
‹‹ነገሮችን የምትረዳበት መንገድና ለሰው ስህተት ይቅር ለማለት ምትጓዝበት ርቀት እስከምን ድረስ እንደሆነ ሳስብ በጣም ድንቅ ይለኛል፡፡››
‹‹አዎ ምን አምናለሁ መሰለሽ..  እንደነገርኩሽ ማናችንም የምንሰራው መርጠን ካልተወለድንባቸው እናትና አባቶቻቸን ነው..እናዛ ሁለት ሰዎች በእኛ ሙሉ ህይወት ላይ ሚያሳርፍት ጫና ቀላል አይደለም..ግማሹን ባሀሪያቸውን በዲኤን ኤ አቸው አማካይነት አዋጥተው ይሸልሙናል..ከዛ ከተወለድን በኃላ ሲያሳድጉን ደግሞ እነሱም ከእናት አባታቸው የወረሱትን ፀባይ ጨምረው ለእኛ ያስረክቡናል..አየሸ  ብዙን ጊዜ    ችግር ላይ ስንወድቅ እዚሁ ዙሪችን ነው መፍትሄውንም ምክንያቱንም የምንፈልገው…መነሻው ግን ያለው ልጅነታችን ላይ ነው፡፡ ገና በምንሰራበት ወቅት ነው ነገሮች የሚበላሹት ወይም ቀና ጓደና የሚይዙት….ይሄንን ሀቅ ከተረዳሽ ማንኛውም ሰው ለሚሰራቸው ጥፋቶች ለመፍረድና እጣት ለመጠቆም አትቸኩይም እሱን ሆኖ ከተፈጠሩ እሱ የሰራውን ጥፋት ላለመስራት መቻል ከባድ ነው፡፡››
የሰጣት ትንታኔ ውስጧ ነው የገባው…ነገሩን ከራሷ ጋር አገናኘችው‹‹እና እኔም ሌባ የሆንኩት ከልጅነቴ በተያያዘ ምክንያት ነው ማለት ነው?››
‹‹ብዬ እስባለሁ..አሁን ላይ ዞረሽና ተሸከርክረሽ መልስ ካላገኘሽ ማድረግ ያለብሽ  ወደ ልጅነትሽ ተሰደሽ የቤተሰብ ታሪክሽን …ከአባታሽ ጋር የነበረሽን ግንነኙነት..ከእናትሽ ጋር የነበረሽን..ከጠቅላላ ቤተሰብሽና ከሰፈር ሰዎችም ጭምር  መመርመሩ ከደዌ ለመዳን ብዙውን ጊዜ ትክክለኛ ስፋራ ነው…፡፡››
👍8610🔥4😱3🤔1
ውስጧን እየቆጠቆጣት‹‹እስቲ እሞክራለሁ››እለችው.. ….ምክንያቱም የተናረው ነገር ለእሷ በደንብ ስሜት ሰጥቷታል..አዎ አባቷን የህልም ያህል ነው ተዝ የሚላት ለዛውም አስጠሊታና የሚያም ትዝታ…..እና ደግሞ በጣም ጥያቄዎች አሏት‹‹….አሁን የት የሆን ያለው…?.በህይወት ካለስ እንዴት እስካዛሬ ሊፈልገኝ ሳይመጣ..?ሞቶስ ከሆነ እንዴት በእርግጠኝነት መርዶውን መስማት አቃተን….?.ሌላ ቤተሰብ መስርቶ ይሆን..?ሌሎች ወንድሞችና እህቶችስ ይኖሩኝ ይሆን…››ይሄ በከፋትና ድብርት ውስጥ በገባችበት ጊዜ ሁሉ የምታብሰለስለው የጥያቄ ቢፌዎች ናቸው፡፡አሁን ቃል ሲናገር ግን እሷም ዝም ብላ በሀሳብ ከማብሰልሰል አለፍ ብላ ለጥያቄዎቾ መልስ ለማግኘት እስከዛሬ ከጣረችው ጥረት በላይ መጣር እንዳለባት ገብቷታል፡፡
‹‹ሞክሪ…ባይሳካ እንኳን በመሞከርሽ ምንም አታጪም…”
‹‹ግን የየት ሀገር ልጅ ነህ››
‹‹የኢትዬጵያ…››
‹‹እውነቴን እኮ ነው ትውልድ አካባቢህ…››
‹‹እዚሁ ነኝ.ኮልፌ…የድሮ ሰፈሬን አንድ ቀን አስጎበኝሽ ይሆናል››
‹‹በአንድ አፍ ..ቃል ገብተሀል፡፡››
መቼም እንደማያደርገው በልቡ እያወቀ‹‹አዎ ቃል ገብቻለሁ…የዕድሜ ልክ ጓደኛሞች ሆንን አይደል..ምን አልበት ሳገባም መጀመሪያ ሚዚዬ ትሆኚ ይሆናል..››
‹‹ለእሷ ነው ለአንተ ሚዜ የምሆነው?››.
‹‹ለጊዜው የእኔ  ጓደኛ ኮ ነሽ..ስለዚህ ለእኔ ነው፡፡››
‹‹ይሁንልህ…››ተሳሳቁን,..የእሷ ሳቅ ግን የቅናት ሳቅ መሆኑ ቢገባው እንዴት ይታዘበት እንደነበር አሰበችና ሽምቅቅ አለች?

ይቀጥላል
👍6410🥰6
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው?›፡ያለበትን አጣብቂኝ አሰበችና አሳዘናት፡፡ቢሆንም ግን ይሄንን ክፍተት ልትጠቀምበት እንደምትችል አሰበችና ፈገግ አለች፡ ‹‹አሁንም ምን አደርጋለሁ ሎቶሪ እንዲወጣልኝ እየፀለይኩ ነው ልበልሽ.?እንደማንኛውም የአዲስ አበባ ኑዋሪ ኮንደሚኒዬም ተመዝግቤ  በመቆጠብ እድሌን እየጠበቅኩ ነው…በስንተኛው…»