አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከቃል ምክር በኃላ ልዩ የሌብነት መነሻዋ ከየት ነው? የሚለውን ጥያቄ  ደጋግማ  ከመጠየቅ እራሷን መግታት አልቻለችም። ትዝ ይላታል …ኤለመንተሪ ተማሪ ሆና ነው፤ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ክፍል እያለች ጀምሮ ነው ፡፡ አያቷ  ጠጅ በጣም ይወዳሉ ….አባባ ትልቁ ነው የምትላቸው..ምክንያቱም በወቅቱ ብዙ  አባባ የሚባሉ ሰዎች ግቢያቸው ውስጥ ስለነበሩ ነው ዘበኛው ..አትክልተኛው ወዘተ)፡፡

ማታ ሞቅ ብሏቸው  ወደ ቤት ሲመጡ ጠብቃ  ተከትላቸው መኝታ ቤታቸው በመግባት  የድሮ ታሪክ ወይም ተረት ንገሩኝ ትላቸዋለች።ደስ ይላቸውና አልጋቸው ላይ ወጥተው ጋደም በማለት ማውራት ይጀምራሉ...ግን ብዙውን ጊዜ አውርተው ከመጨረሳቸው በፊት እንቅልፍ ይዟቸው ጥርግ ይላል..."እና መተኛታቸውን ስታረጋግጥ ብርድ ልብሳቸውን ሙሉ በሙሉ ወደ ላይ ስባ ሸፍና ታለብሳቸዋለች...››እንደዛ ስታደርግ የሚያያት ሰው አያቷን እየተንከባከበች መስሏቸው ይመርቋት ይሆናል…እሷ ግን  ድንገት አይናቸውን ገልጠው የምትሰራውን እንዳያዩባት ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ  ነበር...

ከዛ ኪሳቸውን መበርበር ትጀምራለች...አ10 ብርም ሆነ 50 ብርም መዛ ኪሷ ትከትና ሌላውን ትመልሳለች። የምትሰርቀውን የብር መጠን የሚወስነው ኪሳቸው በምትገባ ወቅት ባገኘችው የብር መጠን ነው።

አያቷ የእናቷ አባት….ባላንብራስ  አይተንፍሱ ይርገጤ ይባላሉ።በጣም ቆፍጣና ግትርና ወግ አጥባቂ ሰው ነበሩ።እናቷን ጨምሮ የቤቱ ሰው ሁሉ ይንቀጠቀጡላቸዋል...‹‹እኔ ፊት አውራሪ አይተንፍሱ›› ብለው ከዘራቸውን ከወዘወዙ ማንም ፊታቸው አይቆምም...እሷ ግን አትሰማቸውም.. እሳቸው እሷ ሲቆጧት እልክ ይይዘትና እጇን አጣምራ አይኖቾን አፍጥጣ ፊታቸው ትገተራለች...፡፡

ቅሬታቸውንና ኩራታቸውን ደባልቆ በሚገልፅ ስሜት"ምን ዋጋ አለው በዚህ ጀግንነትሽ ወንድ ብትሆኚ ..?."ብለው ይሉና ቁጣቸውን አብርደው ወደራሳቸው ስበው ጭንቅላቷን በመዳበስ ያሞጋግሷታል...እንደዛ ሲሆን ደግሞ የልብ ልብ ይሰማታል።እና ወደኃላ ተመልሳ  ትናንቷን ስትቆፍር የስርቆት ታሪኳ የሚጀምረው አያቷን ደጋግሞ ከመስረቅ ሆኖ ነው ያገኘችው ...ለምን እሷቸውን ብቻ ነጥላ ትሰርቃቸው እንደነበረ  አታውቅም ።ከረሜላና ቸኮሌት መግዣ ገንዘብ አስፈልጓት ነው እንዳይባል እናቷ ከመጠየቋ በፊት ነው መዥረጥ አድርጋ የምትገዛላት። ለመስረቅም ከሆነ ደግሞ ከአያቷ ይልቅ እናቷን መስረቅ ለእሷ በጣም ቀላል ነው። እናቷ መኝታ ቤት መሳቢያዎ ውስጥ ሆነ ቦርሳዎቾ   ሁሌ በብር እንደተሞሉ ነው...፡፡የፈለገችውን ያህል ብር እናቷ  እያየች  መዛ ብትወስድ ፈገግ ከማለት ያለፈ ትኩረት ሰጥታ  አትናገራትም። ይሄንን ደግሞ ከጨቅላነቷ ጀምሮ በደንብ ታውቃለች፡፡

አይገርምም በህይወታችሁ የከወናችኋቸውን አንዳንድ ነገሮች ወደኃላ መለስ ብላችሁ በትኩረት ካልመረመራችሁ እንዴትና ለምን የሚለውን ጥያቄ መልስ ሳታውቁ ዕድሜያችሁ ያከትምለታል…. እሷም  ዕድሜ ለቃል አሁን ነው  በዛን የልጅነት ወቅት አያቷን ብቻ ለይታ ትሰርቅ እንደነበር በመገረም ያስተዋለችው፤ ለምን አያቷን ብቻ?አሁንም መልሱን አታውቅም።ግን ከአያቷ ላይ ገንዘብ በሰረቀችው በእያንዳንዷ ቀን ትልቅ ደስታና የድል ስሜት ይሰማት እንደነበረ  አሁንም ድረስ ታስታውሳለች። ይሄንን ተግባሯን እስከሰባተኛ ክፍል ቀጥላበት ነበር...ከዛ አቆመች።

ያቆመችው ማቆም ፈልጋ ሳይሆን አያቷ ድንገት ስለሞቱባት ነበር። በእውነት በመሞታቸው ከእሷ እኩል የደነገጠም ያዘነም ሰው አልነበረም።ያዘነችበት ዋና ምክንያት ግን "ከአሁን በኃላ ማንን ነው የምሰርቀው ?››የሚል ስጋት ስላደረባት ነበር፡፡

ይሄንን ግራ አጋቢ ስሜቴን ማንም አያውቅም ነበር ፤እናቷን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች ሁሉ ለአያቷ ካላት የተለየ ቅርበት እና  ፍቅር የተነሳ እንደሆነ በማመን  እንድትፅናና የተቻላቸውን እንክብካቤ ሲያደርጉላት ከረሙ...በእውነት እሷም  በቀላሉ ልትፅናና አልቻለችም ነበር።በኋላ ግን ትምህርት ቤት ሄዳ ከጓደኞቾ  እስኪሪብቶና ደብተር መስረቅ ስትጀምር አያቷን  ቀስ በቀስ እየረሳቻቸው  መጣች፡፡

..ስርቆቱ ግን እያደገ እያደገ ሄዶ  አብሯት ኖሮ እንሆ እዚህ አድርሷታል…እና  ልጅነቷን እንዲህ ስትፈትሽ ሌባ እንድትሆን ያስገደዳት ምክንያት ምንድነው?በመሞላቀቅ ሰበብ በህፃንነቷ ሳንቲም ስለለመደች ይሆን?ታዲያ ስርቆቱን ሳንቲም በመስረቅ ጀመረች እንጂ  እያደረ ትርኪ ምርኪ ቁሳቁስ  ነበር ስትሰርቅ የኖረችው...ልጅ ሆና እንኳን የ50 ብር የሚያምር ብዕር ቦርሳዋ ውስጥ እያለ የአንድ ብር ተራ እስኪሪብቶ ከጓደኞቾ ትሰርቅ ነበር...ለምን..?‹‹ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል›› ተብሎ የተተረተው በትክክል የእሷን ሁኔታ ይገልፃል፡፡አይገርምም አሁን በዚህ ሰዓት እንኳን ለምን እንደሆነ አታውቅም፡፡

መኝታ ቤቷን ለቀቀችና ወደ እናቷ መኝታ ቤት ሄደች..አንኳኳች፡፡

‹‹ማነው?››

‹‹እኔ ነኝ እማ?››

‹‹ግቢ››

ከፈተችና ወደ ውስጥ ገባች

‹‹የእኔ ቆንጆ ምነው..?እስከአሁን አልተኛሽም እንዴ?›› አለቻት. ከተኛችበት ግዙፍ አልጋ ትራሷን ከፍ አድርጋ ከአንገቷ ቀና በማለት፡፡‹‹እንቅልፍ እምቢ አለኝ .ከአንቺ ጋር መተኛት ፈለጌ ነው፡፡››አለቻቸው፡፡

‹‹በሩን ዝጊውና ነይ….››ብርድልብስና አንሶላውን እየገለጡላት
እንዳሏት በራፉን ዘጋችና  ወደእናቷ አልጋ ሄዳ በተገለጠላት አንሶላ ውስጥ ገብታ ልክ እሳቸው እንዳደረጉት ትራሱን ከፋ አደረገችና ፊቷን ወደእናቷ አዞረች›

እንዲህ የማታደርገው የሆነ ነገር ከእናቷ ስትፈልግ እንደሆነ ከልምድ ይታወቃል…እና የምትለውን ለመስማት እናቷም ነቃ ብለው ተዘጋጀተዋል፡፡

‹‹እማዬ›አለቻቸው፡፡

‹‹ወዬ የእኔ ማር››

‹‹ከእዚህ በሽታዬ የእውነት እንድፈወስ ትፈልጊያለሽ"

ያልጠበቁትን ርዕስ እንዳነሳችባቸው ከፊታቸው  መለዋወጥ መረዳት ይቻላል፡

‹‹ከየትኛው በሽታሽ?››

‹‹ከሌብነቴ ነዋ››

"ምን ማለት ነው የእኔ ልጅ...?እንዴት እንዲህ አይነት ጥያቄ ትጠይቂኛለሽ..?››.

"እንድድን ከምር የምትፈልጊ ከሆነ አሁን የምጠይቅሽን  ጥያቄዎች ትመልሺልኛለሽ?››

‹‹እንዴ… አንቺ ዳኚልኝ እንጂ የፈለግሺውን ጠይቂኝ"

"እርግጠኛ ነሽ?"

"ምን ነካሽ...አንቺን ለመፈወስ የሚያግዝ ከሆነ የማላደርገው ነገር የለም"

"እሺ ስለአባቴ ንገሪኝ?"በጣም የምትፈራውን ጥያቄ አናቷን ጠየቀቻቸው፡፡

"ምን አስደነገጠሽ?እንድትድኚ እፈልጋለሁ አላልሽም እንዴ?"

"እሱማ እፈልጋለሁ...ስለአባትሽ መጠየቅና ከችግርሽ መፈወስ ምን እንደሚያገናኛቸው ስላልገባኝ ነው።"

"በደንብ ይገናኛል..እንዴት እንደሚገናኝ በሂደት ምንደርስበት ይሆናል። አባዬ ምን አይነት ሰው ነው?።

"ያው ፎቶውን ታይው የለ፤ ሸጋ ፤መልከመልካም ሰው ነበር።›› በራሳቸው ገለፃ እንደልጃገረድነት ጊዜያቸው ተሸኮረመሙ፡

"እሱንማ አውቃለሁ...ደግሞ እኳ ያየሁት የአምስት አመት ህፃን ሳለሁ ቢሆንም ትንሽ ትንሽ እንደ ህልም  ትዝ ይለኛል።እሽኮኮ አድርጎኝ ጊቢውን ሲዞር...ኪወክስ ወስዶ ከረሜላ ሲገዛልኝ...ወድቄ ሳለቅስ ተንደርድሮ አንስቶኝ ጉያው ሸጉጦ ሲያባብለኝ...አዎ እኚን የመሳሰሉ ብጥቅጣቂ  ምስሎች  በእምሮዬ ተቀርፀው ቀርተዋል፡፡››

"እኮ ከዚህ በላይ ምን ለማወቅ ነው የፈለግሽው?"

"ምን አይነት ሰው ነበር ...?ምን አይነት ፀባይ ነበረው?"

"ያው እንዳንቺ ነው"
👍7915🔥2🥰2😁2👏1😢1🤩1
"እንዳንቺ ማለት ..እንደኔ ነጭናጫ፣ወሬ አነፍናፊና፤ ሌባ ማለትሽ ነው።" ተበሳጨችባቸው …የአባቷን ስብዕና ከእሷ ስብዕና ጋር ማመሳሰል እንደስድብ ነው የቆጠረችው፡፡

እናትዬወ ደግሞ በመልሷ አዘኑ.."በቃ ስለአንቺ ይሄንን ነው የምታውቂው.?.ደግነትሽን አታውቂም?ጫወታ አዎቂ ና ተወዳጅ ልጅ መሆንሽን አታውቂም...?ጥሩ ጭንቅላት ያለሽ ቀልጣፋ ልጅ መሆንሽን አታውቂም..?እነዚህን ባህሪዎችሽን ለማለት ፈልጌ ነው…፡፡ እርግጥ አባትሽ እንደአንቺ ሰነፍ አልነበረም…የምትለያዩት በዛ ብቻ ነው።"

"ጥሩ ነው...ታዲያ ለምን ተፋታችሁ...?ለምን ጥሎን ሄደ?  እኔን ለምን ጠላኝ"መልስ  እንዲመልሱላት  አፍጥጣ ብትጠብቅም  ዝም አሏት…እሷን እዚው ከጎናቸው አሰቀምጠው ረጅም አመት ወደኃላ መንጎዷቸውን በአይኖቻቸው መፍዘዝ መረዳት ቻለች፡፡አዎ አሷቸውም ለምን ጥሎቸው እንደሄደ ቅስም ስብርብር የሚያደርግ የአመታት ጥያቄያቸው ነው…እሳቸውም እንዲህ እሷ እንዳደረገችው አይናቸውን አፍጥጠው እየተቆጡና እያለቀሱ የሚጠይቁት እና መልስ የሚሰጣቸው ሰው ቢኖር ከምንም ነገር በላይ ሚመኙት ነገር ነው፡፡ልዩ ከዛ በላይ ልታስጨናንቃቸው አልፈለገችም፡፡

ይቀጥላል
👍7811🤔7🥰3
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ልዩ ቃል ቤት ነው ያለችው….እየሳቁና እየተጫወቱ  ሳለ ድንገት በራፍ ተንኳኳ
"ቆይ አንዴ..›› አለና ሄዶ ከፈተ::
"እንዴ ጊፍቲ ከየት ተገኘሽ?"ጎትቶ አስገባትና እቅፉ ውስጥ ሸጎጦ አወዛወዛት፡፡
በተቀመጠችበት ወንበር ወደ ውስጥ   እየሠመጠባት ያለ መስሎ ተሠማት.. ‹‹ፍቅረኛው ይህቺ ነች  ማለት ነው?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡ከአመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንጀቷ  ፀለየች.. "እባክህ አምላኬ..ምን አለ እጮኛው ከምትሆን እህቱ ሆና በሆነ..››ደግሞ በምናቧ ከሳለቻት በላይ ቆንጆ ሆና ታየቻት…‹‹ ከእሱ ጋር አንድ ላይ ሲታዩ መንታ እህቱ ነው የምትመስለው"አለች
ቃል ጊፍቲን አቅፎ ብቻ አልበቃውም ጉንጯን እያገላበጠ ሳመትና ወደእሷ ይዞት መጣ...
ከእሷ አንድ ሶስት አመት በለጥ ትላለች ..እንደእሱ ጥንቅቅ ያለች ነገር ነች።‹‹ልዩ ተዋወቂያት ..ጊፋቲ ማለት በጣሞ የምወዳት የልጅነት ጓደኛዬ ነች"..
ልዩ እጮኛዬ ነች ይላል ብላ ነበር የጠበቀችው… ጓደኛዬ ነች ስላላት ደስ አለት…ከተቀመጠችበት እንደመነሳት ብላ  እጇን ለሠላምታ ዘረጋችላት፤እሷም በተመሳሳይ  ድንግርግር ያለ ስሜት ላይ ያለች ይመስላል.. .የዘረጋችላትን እጇን በስሱ ጨበጠችና‹‹ ጊፍቲ እባላለሁ"አላቻት።
"ልዪ"
ሁለቱም ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጡ
ቃል "ሱቅ ደርሼ መጣሁ..ተጫወቱ›› ብሎቸው ወጥቶ ሄደ..ይሄንን ያደረገው ሆነ ብሎ ነው…
በራፉን አልፎ ከአይናቸው እስኪሰወር ሁለቱም አይናቸው እየተንከራተተ ነበር።ለሆኑ ደቂቃዎች  በዝምታ ከተገማገምን በኃላ ጊፍቲ ቅድሚያውን ወስደ ‹‹"ከቃልዬ ጋር እንዴት ተዋወቃችሁ...?የመስሪያ ቤት ጓደኛው ነሽ?"ስትል ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡
"ቃልዬ" ብላ ስትጠራው ቃሉ አፎ ውስጥ ሚቀልጥ ነው የሚመስለው
ልዩም ‹‹…አይ የስራ ባለደረባው  አይደለሁም ...ጓደኛው ነኝ"አለቻት ኮስተር ብላ.. ነገር አጨመላልቃለሁ ብላ ነው እንጂ ‹‹ፍቅረኛው ነኝ›› ልትላት ሁሉ ቃጥቷት ነበር፡፡
ጊፍቲ "ጓደኛው..."አለች በማሽሞጠጥ ቃና፡፡
"እ ምነው ...?ችግር አለው?"
"አረ በፍፅም የእኔ ቆንጆ...ብቻ የቃልዬ ነገር ይገርመኛል… ከልጅነታችን ጀምሮ በየጊዜው አዳዲስ ጓደኞች በማፍራት እንዳስገረመኝ ነው...ይሄው ለስራ ጉዳይ ለአንድ ወር ከስሩ ዞር ስል አንቺን የመሰለች አዲስ ጓደኛ አፍርቶ ጠበቀኝ።"
ልዩ ይህቺን ሴት ጠላቻት ‹‹..አሮጊት ነገር ነች .. እዩት በአንድ አረፍተነገር መናገር የፈለገችውን ሁሉ ስትናገር...ከልጅነት ጀምሮ እንደሚተዋወቁ...የእኔ እና የእሱ ትውውቅ ደግሞ ከአንድ ወር በላይ ዕድሜ እንደሌለው እርግጠኛ እንደሆነች አሳወቀቺኝ።›› ስትል በውስጧ ስለጊፍቲ  ንግግር የተሰማትን አብሰለሰለች፡፡
የመቆየት አፕታይቷ ተዘጋ...ቦርሳዋን ያዝችና ከመቀመጫዋ ተነሳች...፡፡
"እንዴ ምነው..?ቃልዬ ሳይመጣ ልትሄጂ ነው…ብና ወይ ሻይ ላፈላልሽ ነበር አኮ …?"አለቻት..ከፊቷ መፈገግ የሚናገረው ግን ተቃራኒውን ነው፡፡አዎ ጊፍቲ በልዩ መሄድ በጣም ደስተኛ እንደሆነች ነው፡፡
"በፊትም ልሄድ ስል ነው የመጣሺው...ቀጠሮ አለብኝ…ሻይ ደግሞ እደመጣሁ ነው ቃል አፍልቶ የጠጣነው"አለቻት…እንደዛ ስትል ቃል ቢሰማ ምን ሊያስብ እንደሚችል ታሰባትና ሽምቅቅ አለች...ምክንያቱም ከመጣች መምንም አይነት ሻይም ሆነ ቡና አልቀመሱም፡፡
"ካልሽ እሺ..አትጥፊ እዚህ ስትመጪ ታገኚኛለሽ"አለቻት…እሷስ መች የዋዛ…‹‹ለምን እዚህ ብቻ የቃል ጓደኛ ከሆንሽ የእኔም ጓደኛ ነሽ..ቁጥርሽን ስጪኝና እንደዋወል"
ቁጥሯን መስጠቷን እንዳልፈለገችው በሚያሳብቅ የድምፅ ቅላፄ "ይሻላል"አለቻት...
ልዩ  ግግም አለችባት...በውስጧ‹‹እንደው ከእዚህ ወጥቼ ባልደውልላት እንኳን እንዳበሳጨቺኝ ላበሳጫት።››ብላ ነው፡፡
ጊፍቲም እንደማትለቃት ሲገባት ቶሎ   እንድትወጣላት የፈለገች መሆኗን በሚያሳብቅ ፍጥነት ጥድፍ ጥድፍ ብላ ነገረቻት።
ጎንበስ ብላ ጉንጯን ሳመችትና ‹‹ቃልን እንዲህ ስመሽ ይቅርታ ጠይቂልኝ...ላንቺ ሰሞኑን ደውልልሻለሁ"
ጊፍቲ ምን እንደምትመልስልኝ በማሰላሠል ላይ እያለች ፈጠን ብላ እቤቱን ለቃ ወጣች።መኪናዋን ከጊቢ ውጭ ስላቆመች ቀጥታ ወደእዛ ሄዳ ለጠበቀላት ሊስትሮ ትንሽ ሳንቲም አስጨብጣ ቃል መንገድ ላይ አግኝቶ በጥያቄ እ ንዳያጣድፋት ስለፈለገች ፈጠን ብላ ሰፈሩን ለቃ ወጣች፡፡

ይቀጥላል
👍9916🤔6😢3🔥2👏2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ልዩ ቃል ቤት ነው ያለችው….እየሳቁና እየተጫወቱ  ሳለ ድንገት በራፍ ተንኳኳ "ቆይ አንዴ..›› አለና ሄዶ ከፈተ:: "እንዴ ጊፍቲ ከየት ተገኘሽ?"ጎትቶ አስገባትና እቅፉ ውስጥ ሸጎጦ አወዛወዛት፡፡ በተቀመጠችበት ወንበር ወደ ውስጥ   እየሠመጠባት ያለ መስሎ ተሠማት.. ‹‹ፍቅረኛው ይህቺ ነች  ማለት ነው?››ስትል…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በማግስቱ  ከስራ መመለሻ ሰዓቱን ጠብቃ ደወለችለት .ተገናኙ መክሰስ ጋበዘችው.ከዛ ቡዙ ብዙ ነገር አወሩና በድንገት በየራሳቸው ሀሳብ ውስጥ በመግባት በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ..ልዩ እንዲህ እርቃና ጠልቃ የምታስበው ፊት ለፊቷ ሰለተቀመጠው ሰው መሆኑ ደግሞ አስገራሚ  ነው‹‹ዛሬም ያለሁት እዛው የተገናኘንበት ቦታ ላይ ነኝ። አንዳንድ አጋጣሚዎች በቅፅበት ቢገባደድም  በአዕምሮችን ውስጥ ግን መሽከርከራቸውንና መንቀሳቀሳቸውን ይቀጥላሉ...አዎ ዛሬም እነዛ የተረገሙ ጣቶቼን ኪስህ ውስጥ ከትቼ ሞባይልህን እየመዘዝኩ ነው...አሁን በዚህች ሰአት"ተዋት ልጅቷን ገደላችኋት እያልክ  እየጮህክ ነው...አዎ የተረገሙ እጆቼን በቅድስ እጇችህ አጥብቀህ ይዘህ ከረጋሚዎችህና ከደብዳቢዎችህ መካከል  ጎትተህ እያወጣኸኝ ነው... ፡፡
እንዴት ከዚህ ቦታ ተንቀሳቅሼ ወደፊት መጓዝ እንደምችል አላውቅም...በምን አይነት ተአምር እየሠማዎቸው ያለሁትን ልስልስ ድምፅህን ወደ አእምሮዬ ውስጠኛ ማከማቻ ገፍቼ ጨምሬ ፊት ፊቱን ባዶና ንፁህ እንደማደርገው አምላክ ነው የሚያውቀው...ምን አልባት ከተጣበቅኩበት ቅፁበት መላቀቅ አልችል ይሆናል።አዎ ይሄም ሌላው ተጨማሪው በሽታ ሆኖ ተጣብቶኝ ሊሆን ይችላል...እንግዲህ መድሀኒት የማይቀበለው ሰውነት እንዴት አድርጎ በምንስ ተአምር ይፈወስ ይሆን? የምረግጠው ቦታ ሁሉ እየከዳኝ ነው...ደረቅ መሬት መስሎኝ በሙሉ ክብደቴ ስጫነው  ያዳልጠኝና ሰማይ ደርሼ መሬት እፈርጣለሁ።መሬት ሳርፍ የእጆቼን ቆዳ ጠጠርና አሸዋው ገሽልጦ ያቆሳስላቸዋል።ወገቤ ለሁለት ይከፈላል።ቢሆንም በወደቅኩበት እየተንከባለልኩ ማላዘን አይሆንልኝም። እንደምንም እራሴን አበርትቼ እነሳለሁ ።የጀርባዬ ህመም ጥዝጣዜው እስኪያቅለሸልሸኝ ድረስ ቢያመኝም ከአቋቋሜ ሽብርክ አልልም ..ፊቴንም አልቋጥርም.... ወደፊትም ከመራመድ አልሰንፍም። የራሴን ህመም ለራሴው በሚስጥር ይዘዋለሁ።እኔ እንዲህ ነኝ።››
ከረጅም ዝምታና ማሰላሰል በኃላ እሱ ቀድሞ ዝምታውን ሰበረና መናገር ጀመረ

‹‹እስኪ ይጠቅምሽ ከሆነ አንድ ታሪክ ልንገርሽ››አላትና እሷን  ከሀሳብ ባህር ውስጥ መዞ አወጣት፡፡

እሷም በፍጥነት ከገባችበት መደበት በመውጣት እራሷን አንቅታ‹‹በናትህ ንገረኝ››ስትል ልክ  እድሜዋን እንደጨረሰች ወሬ አሳዳጅ አሮጊት የሚነግራትን ለመስማት ተስገበገበች…ስለሆነ ነገር እንዲነግራት ፈልጋ አይደለም..በቃ ስለምንም ይሁን ስለምንም ዘለግ ያለ ወሬ እንዲያወራትና ምስጥ ብላ ከአንደበቱ የሚወጡትን ቃላቶች ለማድመጥ አይኖቹን ሲያንከባልላቸውና  ፊቱ ቆጠረ ፈታ ሲያደርግ ለማየት ነው፡፡

ሊነግራት የፈለገውን ታሪክ መተረክ ጀመረ

‹‹አንድ ወቅት ነው ሀዋሳ ነበርኩ፡፡እና በእለቱ ጭፍግግ ብሎኛል... እራሴን  ዘና ለማድረግ ወደባህር ዳርቻ ሄድኩ...ጠፍጣፋ እና ምቹ ድንጋይ ላይ ተቀምጬ የሀይቁን ዳር አርቄ በማየት እየተደመምኩ ሳለ አንድ  ያጎበደድና ዕድሜ የተጫናቸው አዛውንት ከዘራቸውን እያንቋቁ መጥተው  በግማሽ ሜትር  ርቀው ከጎኔ ተቀመጡና "ልጄ ምነዋ ተክዘሀልሳ?"ሲሉ ጠየቁኝ…እኔም ቀና በማለት በትኩረት ካየኋቸው በኃላ ለጥያቄያቸው መልስ በመመለስ ፋንታ ሌላ ጥያቄ ጠየቅኳቸው?

‹‹እኔ በ35 ዓመቴ  መኖር እንዲህ የከበደኝ እርሷ  ይሄን ሁሉ ጊዜ እንዴት ቻሉት?"

"በእኔ የደረሰ አይድረስብህ?"አሉኝ፡፡

"እንዴት አባቴ"

"አንድ ህይወት  መኖር ፋፅሞ ሊከብድህ አይገባም.....ተወልደህ ፤አድገህ፤ ተምረህ፤ ስራ ይዘህ፤አግብተህ ወልደህ  ፤የልጅ ልጅ ስትል የተሰጠህ ህይወት እልቅ ትልና ሾልከህ እንደመጣህ ሾልከህ በመሄድ ትገላገላለህ፡፡"

"እና እርሶ በእኔ የደረሰ አይድረስብህ ያሉኝ ለምንድነው? አልገባኝም እርሷም እኮ በአንድ ህይወት እንደተንገሸገሹ ያስታወቅቦታል።››

‹‹ልጄ የእኔ ነገርስ ግራ ነው።››

‹‹እስኪ ልስማዋ።››

‹‹ድሮ ነው በጣም ድሮ…ጌታ ሆይ አንድ ነገር እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ "ስል ለአመታት ፀለይኩ።..እግዚያብሄርም ...የፀሎትህ  ድምፅ በጆሮዬ አንቃጭሏል:: አሁን አንድ ነገር ያልከኸውን ጠይቀኝ...ወዲያው ሰጥሀለሁ..አንድ  ማስጠንቀቂያ ግን አለኝ.."አለኝ አለ

።"አምላኬ   ምንድነው?"ስል በከባድ ትህትና ጠየቅኩት።

"የጠየከኝን አንዴ ከሰጠውህ በኃላ  መልሰህ ውሰደልኝ ብትል የሚሆን ጉዳይ አይደለም፤ስለዚህ የምትጠይቀውን ደግመህ አስብበት።" ብሎ አስጠነቀቀኝ፡፡

"ግድየለም  ለአመታት ያሰብኩበት ጉዳይ ነውና ምንም የሚያፀፅት ነገር   አይኖርም"አልኩት

"እንግዲያው ጠይቅ"ሲል ፈቀደልኝ።

"አንድ ነፍስ ብቻ አይበቃኝም...ስድስት ነፍስ አድርግልኝ...ይሄ ነው ልመናዬ ።"አልኩት
"ጥያቄህ ቀላል ነው… .ግን ስድስት ይበቃሀል?"አለኝ።

"ካላስቸገርኩህማ ዘጠኝ ብታደርግልኝ ምስጋናዬ የዘላለም ነው።"አልኩት"

ያው እንግዲያው ከዚህች ደቂቃ በኃላ ባለዘጠኝ ነፍስ ነህ"አለኝና ተሠወረ...የሆነ ኃይል በሰውነቴ ሞገድን ሲረጭና ሲያንዘረዝረኝ ተሰማኝ። ወዲያው ነበር የፀፀተኝ"እንዲህ ቀላል ከሆነ ምነው አስራስምንት ነፍስ ጠይቄው በሆነ"የሚል የስስት መንፈስ እንደቅንቅን መላ ሰውነቴን በላኝ።

" ውለው ሲያድርስ ?እንዳልተፀፀቱ ተስፋ አደርጋለሁ"አልኳቸው

"ፀፀት ብቻ አይገልፀውም።"

‹‹አልገባኝም… ዘጠኝ ነፍስ ማለት እኮ   ዘጠኝ ተከታታይነት ያለው የተለያየ ህይወት የመኖር እድል ማለት ነው።››

"አዎ ትክክል ነህ...ዘጠኝ የመሞት እድልም አብሮት እንዳለ አትዘንጋ...በራስህ እየው በአንድ ህይወት ውስጥ ያለው ስቃይ፤ ህመም ፤ስጋትና መረበሽ፤ተስፋ መቁረጥና ቁዘማ  ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እየው...እና ይሄንን በተለያየ ዘመን ውስጥ ዘጠኜ ለዛውም ያለማቋረጥ ስትደጋግመው ምን ያህል    እንደሚከብድ?
"እና ዘጠኝ ነፍስ ነበረኝ እያሉ ነው?››ስል ጠየቅኳቸው፡፡

አይ አሁን እንኳን የቀረኝ ሶስት ነፍስ ነው...ስድስቱን ኖሬ አልፌዋለሁ፤የስድስት ህይወት ደስታ ተደስቼ የስድስት ህይወት መከራ አሳልፌያለሁ፤መኖር ብቻ ሳይሆን ስድስቴ ሞቼያለሁ ማለት ነው..እና አሁን ምንም ነገር ትርጉም አልባ ሆኖብኛል፤መጠጣት መዳራት፤ቤት መስራት ፤ሀብታም መሆን፤ዝነኛ መሆን..ሁሉንም በየተራ አይቻቸዋለው..አሁን  አየር ስተነፍስ እንኳን ከመሰላቸቴ የተነሳ  እየደከመኝ ነው፡፡ "አሉኝ

‹‹እና እውነታቸውን ዘጠኝ ነፍስ ኖሮቸው ስድስቱን የኖሩ ይመስልሀል? አምነሀቸዋል…?››ስትል በነገራት ግራ አጋቢ ታሪክ ገራ ተጋብታ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹ማመን አለማመኑ አይደለም ዋናው ጉዳይ… ሰውዬው በታሪኩ ውስጥ ሊያስተላልፉልኝ የፈለጉትን ነገር ነው ላካፍልሽ የፈለኩት››አላት

‹‹ማለት?››

‹‹ማለትማ..ህይወት ልሙጥ ሆና አትከሰትም፤ደስታውም ሀዘኑም የእኛው ነው፤በሽታውም ጤንነቱም እንደዛው……መኖር እንደተሰጠንም ሁሉ ሞትም ስጦታችን ነው፡፡እና ህይወትን ሙሉ ፓኬጆን ነው መቀበል ያለብን፡የዛን ጊዜ በህይወት የሚለገሰን  ደስታው ፈንጠዝያ፤በኑሮ የሚያጋጥመንም መከራ  ደግሞ ችግርና ስቃይ  ብቻ አይደለም ፤ይልቅስ በንቃት ተቀብለን የሁለቱንም ባላንስ በመጠበቅ ከተጠቀምንባቸው ባላሰብነው መንገድ  ስብዕናችንን ይሞርድልናል፤ የአእምሮችን የተለያዩ የማሰላሰያና የሀሳብ ማብላያ ሞተሮችን በተገቢው መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ልክ እንደዘይት ሆኖ ያለሰልሱልናል።››

‹‹እና ምን እያልከኝ ነው?››

ይቀጥላል
👍1218🥰4🤔3👏2🔥1😁1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስምንት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ በማግስቱ  ከስራ መመለሻ ሰዓቱን ጠብቃ ደወለችለት .ተገናኙ መክሰስ ጋበዘችው.ከዛ ቡዙ ብዙ ነገር አወሩና በድንገት በየራሳቸው ሀሳብ ውስጥ በመግባት በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ..ልዩ እንዲህ እርቃና ጠልቃ የምታስበው ፊት ለፊቷ ሰለተቀመጠው ሰው መሆኑ ደግሞ አስገራሚ  ነው‹‹ዛሬም ያለሁት እዛው የተገናኘንበት ቦታ ላይ ነኝ።…»
#የታከተው_ወንፊት

ማኛ ነኝ እያለ ገለባና ገልቱ
ቢፈተግ ቢነፋ ጠብ ላይል ከቋቱ
በከንቱ መዳከር ለፋን ብዙ ለፋን
ስንዴ እየመሰለን ገለባ እየነፋን።

🔘ኢዛና መስፍን🔘
👍6413
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


‹‹እና ምን እያልከኝ ነው››

‹‹አንቺም የተሰጠሸን ህይወት ሙሉ በሙሉ ተቀበይው፤ገዳይ ሆንሽ አስገዳይ….ፃድቅ ሆንሽ ሀጥያተኛ….መጀመሪያ ባለሽበት ሁኔታ እራስሽን ተቀበይ፡እናም ደግሞ ሁሉም ሰው ከውጭ እንደምትመለከቺው እንዳልሆነም እወቂ..ስለዚህ አንቺም እራስሽን እንደምታይው ብቻ አይደለሽም፡፡ ልዩ ማለት ከሺ በላይ በጣም ድንቅ የሆኑ መልካም ምግባሮችና ፀባዬች ያሏት እንዲሁም በመቶ የሚቆጠሩ ትንሽ ሚጎረብጡና መስተካከል ያለባቸው እንቅፋቶች የተጋረጡባት ወኔ ሙሉ እና በኃይል የተሞላች ወጣት ነች፡፡ይሄንን ካወቅሽ ከነዛ መቶ እንቅፋቶች ላይ በየጊዜው የተወሰኑትን እየቀረፍሺ ሺዎች ላይ እየጨመርሽ መሄድ ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ፡፡

እወቂ መቼም መቶውንም እንቅፋት በአንዴ ማስወገድ አትችይም፡፡ በአመት 10ሩን እንኳን ካስወገድሽ በቂና ድንቅ ነዋ.. ዋናው ከአምናው በሆነ ነገር የተሻልሽ ሰው መሆንሽ ነው፡፡ ..እወቂ ሰው እስከሆንሽና በዚህ ምድር ላይ መኖር እስከቀጠልሽ ድረስ ፍፅም ሰው መሆን አትቺይም …ማንም ደግሞ እንደዛ እንድትሆኚ አንቺን የመጠየቅ ሞራል የለውም፡፡እሱም እንደዛው በመቶዎች የሚቆጠሩ የህይወት እንቅፋቶች በውስጡ ተሸክሞ ስለሚዞር ማለቴ ነው፡፡እና እራስሽን የተለየ ችግር እንዳለብሽ አድርገሽ በማሰብ ነፍስሽን ማሰቃየት አቁሚ…..››

በተመስጦ ቀል በባል ካዳመጠችው በኃላ‹‹አመሰግናለሁ..አንተ በጣም ጥሩ ሰው ነህ፡፡››አለችው

"እኔ ደጓች ስላሰደጉኝ ደግ ከመሆን ውጭ ምርጫ የለኝም። ››
"ልክ ለእኔ ደግ እንደሆንከው ማለትነው"
"ማለት?"

‹‹እንዴት ማለት አለ ስሰርቅህ ያዝከኝ ግን አብረኸኝ ተደበደብክ"
"አዎ ጥሩ ምሳሌ አመጣሽ ..ለአንቺ መስረቅ እኔም ከጥፋተኝነት እራሴን ንፁህ ማድረግ አልችልም፡፡ስልክ አያያዜ በጣም እንዝላልና ግዴለሽነቴን የሚያሳብቅ ነበር..አንቺ ለመስረቅ ስትመጪ እኔም ለመሠረቅ ዝግጅ ሆኜ ነበር እየጠበቅኩሽ ያለሁት፡፡ስለዚህ ከደሙ ንፁህ ነኝ ማለት አልችልም...ብደበደብም በገዛ ጥፉቴ ነው።››
‹‹አንተ መንፈሳዊና መልካም ሰው ከሆንክ ክፍትንና ክፉዎችን፤ ሀጥያትንና ሀጥያተኞችን አጥብቀህ ማውገዝና መኮነን አለብህ..አሁን ግን እንደማየው እየተከላከልክላቸው ነው"
"አደበላለቅሽው….እንዳልሽው ክፍትንና ፤ሀጥያትን አጥብቄ አወግዛለሁ። ክፍዎችንና ሀጥያተኞችን ላልሽው ግን አላደርገውም።እነዚህ ክፉና ሀጥያተኛ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው መወገዝና መወቀስ አይደለም፡፡ መፈቀርና መደመጥ ነው የሚፈልጉት። ከልክፍታቸው ለመፈወስ ህክምናው ፍቅር ነው። ውግዘትና ስድብማ እሳት የሆነ ተግባራቸው ላይ ቤንዚል ጨምሮ ማቀጣጠል ማለት ነው።ደግሞ ማንም ከመሬት ተነስቶ በፍቃድ ገዳይም ዘራፊም አይሆንም...ትናንትናውን ያበላሸበት አንድ ሰው ወይም አንድ አጋጣሚ ይኖራል። እያንዳንድ ወንጀለኛ ሰው በግለሠብ ደረጃ ኃላፊነት ቢኖርበትም በየደረጃው ያሳደጉት ወላጆች፤ ያስተማሩት መምህራን ፤አብረውት ያደጉት ጓደኞቹ ፤በውስጡ አቅፎ ያሳደገው ማህበረሰብ..እየተመላለሰ ሲያመልክበት የነበረው የሀይማኖት ተቋም፤ሲያስተዳድረው የነበረ መንግስት እነዚ ሁሉ የየድርሻቸውን ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው።ለአንድ ገዳይ ተገዳዩን ጨምሮ ከላይ የዘረዘርኳቸው በሙሉ ንፁህ አይሉም።›
‹‹እንዴ ተገዳዩ ደግሞ በመገደሉ የተሠራበት ግፍ ሳያንስ የምን ተጠያቂነት መሆን ነው?።
"ታሪኩን ስትመረምሪ በግልፅ ታገኚዎለሽ...የሆነ ነገር አድርጎ ገዳዩን አነሳስቶታል..ወይ ከሚስቱ ጋር ያልሆነ ቀረቤታ ፈጥሯል..ወይ በእምነት ያበደረውን ገንዘብ ክዶታል..ወይ እሱ ቸግሮት ባለበት ወቅት የበሬ ማሰሪያ የሚያህል ሀብል አድርጎ ተፈታትኖታል፡፡
"እንደዚህ እኮ ምታስበው አንተ ብቻ ነህ...››
"አይ ጥቂትም ቢሆኑ ሌሎቹም አሉ...ደግሞም አንቺም ብትሆኚ ከአሁን በኃላ እንደዚህ ከሚያስብት መካከል አንዷ የምትሆኚ ይመስለኛል፡፡"
"አይ አንተ ..እስኪ መጀመሪያ ከተፀናወተኝ ከዚህ ሌብነት ልፈወስ"
"ትፈወሻለሽ አይዞኝ"
"አይ አንተ እንዲህ ቀልድ መሠለህ ..እናቴ ከየአድባራቱ አስመጥታ ያረጨችኝ ፀበል የለም..ህክምናም በጣም ብዙ ሳይካታሪስቶች ሊያክሙኝ ሞክረዋል ..የመስረቅ ረሀቤ ትንሽ ጋብ እንዲልና ፋታ እየወሰድኩ እንዳደርገው ማድረግ ቻሉ እንጂ ከስሩ መንግለው ሊገላግሉኝ አልተቻላቸውም"
"ስለዚህ እራስሽን በራስሽ አክሚያ"
‹‹እሺ እንግዲህ እንዳልክ››
ልዩ ለጊፍቲ ቃል ቤት ከተገናኙ ከሳምንት በኃላ ደወለችላት
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ ማን ልበል?››አለቻት ግራ በተጋባ ድምፅ
‹‹አዲሷ ጓደኛሽ ነኝ፡፡ ››
‹‹ይቅርታ አላወቅኩሽም፡፡››
‹‹በቀደም ቃል ቤት እራሱ ቃል አስተዋውቆን ነበር፡፡››
‹እእእእእ…››የጊፍቲ የንግግር ቃና ደቂቃዎች ውስጥ ተቀየረ
‹‹አወቅሺኝ?››
‹‹አዎ…እሺ ምን ልታዘዝ?››
‹‹አረ አይባልም.. መጀመሪያ ሰላም ነሽ ወይ አይቀድምም?›
‹‹ይቅርታ ሰላም ነሽ?››
‹አለሁልሽ..እንደው ጊዜ ካለሽ ላስቸግርሽ ነበር፡፡››
‹ምንድነው .?ግን አሁን ስራ ቦታ ነኝ፡፡››
‹‹እኮ አውቀያለሁ መስሪያ ቤትሽ አካባቢ ነው ያለሁት.. ከ30 ደቂቃ በኃላ ስትወጪ እንድንገናኝ ፈልጌ ነው፡፡›
ልታገኛት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት በሚያሳብቅ ንግግር‹‹እሺ..ግን ለምን ጉዳይ ነው…?ከስራ በኃላም ሚመቸኝ አይመስለኝም…ሌላ ቀጠሮ ነበረኝ›› አለቻት…፡፡
ይህቺ ሴት እራሷን እያዋደደች ስለሆነ ቀልቧን ልግፈፈው ብላ ስሌት ሰራች‹‹የቃልዬን ምርጫ እኮ ከእኔ በተሻለ አንቺ ስለምታውቂው ብዬ ነው››አለቻት፡፡
‹‹የምን ምርጫ….ምን ማለት ነው››እንደገመተችው ጊፍቲ በደንብ ተነቃቃች….
ልዩም ሙሉ ትኩረቷን እንዳገኘች እርግጠኛ ስትሆን ንግግሯን አራዘመች‹‹አስራ ሁለት ሰዓት ላይ እራት ልጋብዘው ቀጥሬዋለሁ..እና ዝም ብሎ እራት ብቻ ከሚሆን የሆነ ስጦታ ልገዛለት ፈልጌ ነበር…ግራ ስለተጋባሁ በምርጫው ብታግዢኝ ብዬ ነው፡፡››
‹‹አሁን መጣሁ. 5 ደቂቃ ጠብቂኝ››ብላ ስልኩን ጆሮዋ ላይ ጠረቀመችው፡
እንዳለችውም 5 ደቂቃ እንኳን ሳይሞላ መጠች…ልዩ የመኪናዋን መስታወት ወደታች በማውረድ እጇን ወደላይ በመቀሰር እንድታየት ምልክት ሰጠቻት ..የጨለመ ፊት ይዛ እየተውረገረገች ወደእሷ መጣች..ፈጠን ብላ የገቢናውን በራፍ ከፈተችላት… ገባቸ ና ዘጋችው፡፡
ለሆኑ ደቂቃዎች ዝም እንደተባባልን ተጓዙ.. በመሀል ጊፍቲ እንዳኮረፈች መናገር ጀመረች‹‹ ምን አይነት ዕቃ መግዛት ነው ምትፈልጊው?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ውይ ሳልነግርሽ ተውኩት እኮ››
‹‹ምኑን?›
‹‹ስጦታ ልገዛ ነው ያልኩሽን ነዋ›
‹እየቀለድሺብኝ ነው እንዴ?›


ይቀጥላል
👍10416🥰6😁2🔥1🤔1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ ፡ ‹‹እና ምን እያልከኝ ነው›› ‹‹አንቺም የተሰጠሸን ህይወት ሙሉ በሙሉ ተቀበይው፤ገዳይ ሆንሽ አስገዳይ….ፃድቅ ሆንሽ ሀጥያተኛ….መጀመሪያ ባለሽበት ሁኔታ እራስሽን ተቀበይ፡እናም ደግሞ ሁሉም ሰው ከውጭ እንደምትመለከቺው እንዳልሆነም እወቂ..ስለዚህ አንቺም እራስሽን እንደምታይው ብቻ አይደለሽም፡፡ ልዩ ማለት ከሺ በላይ…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
‹‹እና ምን እያልከኝ ነው››
‹‹እንዴ!! እንዴት እንዲህ ትያለሽ.?መጀመሪያ ከቃል ጋር እራት ቀጠሮ ነበረን..አሁን ለአንቺ ከደወልኩልሽ በኃላ ደውሎ ድንገተኛ ጉዳይ ስላጋጠመው ዛሬ እንደማይችል ነግሮኝ ይቅርታ ጠየቀኝ...የእራት ግብዣው አሌለ ደግሞ ስጦታው አያስፈልግም ››የመዋሸት ብቃቷ  ለእሷው ለራሷ አስደነቃት፡፡

‹‹እና መኪናሽ ወስጥ ሳልገባ ለምን እዛው አልነገርሺኝም፡፡››

‹‹ውዴ አረ ዘና በይ..መምጣትሽ ካልቀረ ሻይ ቡና እንባባል ብዬ እኮ ነው ..ያው የቃል ጓደኛ ነሽ ማለት የእኔም ጓደኛ ነሽ፡፡››

ጊፍቲ በጣም ከመናደዶ የተነሳ መከራከሩንም ስላልቻለች ዝም አለች፡፡ቦሌ ካልዲስ ገቡና የሚፈልጉትን አዘው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጡ፡፡

‹‹ከቃል ጋር የረጂም ጊዜ ጓደኛሞች ናችሁ?››ልዩ ነች የጠየቀችው፡፡
‹‹ከልጅነት ጀምሮ አብረን ነበርን…አንድ ጊቢ ውስጥ ነው ያደግነው፡፡››

ልክ ምንም እንደማያውቅ ሰው ‹‹እና ያው ጓደኛ ብቻ ናችሁ አይደል?.››ብላ የሚያበሰጭ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡

.ለተወሰኑ ደቂቃዎች ፀጥ አለች‹‹እንዴት እንደህ ልትይ ቻልሽ? ቃል ነው እንዲህ ብሎ የነገረሽ?››
‹‹አረ በፍፅም›አለቻት ደንግጣ…የደነገጠችው ሄዳ ቃልን ብትጠይቀውስ.?ብላ በመስጋት ነው…በዚህ ጉዳይ ከቃል ጋር ብትጣላ  ለእሷ ትልቅ ኪሳራና እፍረት ነው፡፡
‹‹ቃል ጓደኛዬም፤ወንደሜም፤ፍቅረኛዬም ሁለነገሬ ነው››በማለት አንጀቷን ለመበጠስ ሞከረች፡፡

‹‹ምን ያህል ነው የምትፈልጊው?››የሚል ፍጥጥ ያለ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡

ጊፍቲ መመለስ ጀመረች‹ቃልን የምፈልገው …እራሴን ከምፈልገው በላይ ነው…ቃል ህልሜ ነው፡፡የልጅነት ህልሜ…ሁለታችንም አንዳችን ከአንዳችን ለረጅም አመት ማለት ከልጅነታችን ጀምሮ ስንደጋገፍና የህይወትን ጨለማ ጎኗንም በመረዳዳት በብርሀኗም አንድ ላይ በመድመቅ ነው እዚህ የደረስነው….፡፡››

ይህቺ ልጅ የዋዛ አይደለችም ››አለች ልዩ..ጥያቄዋን አራዘመች‹‹እና ታገቢዋለሽ ማለት ነዋ?››

‹‹ይሄ ምን ጥርጥር አለው?››

‹‹እሱስ?››

‹‹ነገርኩሽ እኮ…እኛ እስከአሁን የመጣንበትን የሕይወት መንገድ  አብረን ነው የተጓዝነው...ከአሁን በኃላ ያለውን ህይወታችንንም አብረን ከመዝለቅ ውጭ ምንም ምርጫ የለንም፡፡››

‹‹ቃልና አንቺ ግን መች ነው የምትጋቡት?››

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹እኔ እንጃ ማለት.አልተነጋገረችሁበትም..?›
‹‹አይ ተነጋረንበታል…እናማ ሁኔታዎች ሲስተካከሉ እንጋባለን..ደግሞ ምን የሚያጣድፍ ነገር አለ?››

‹‹ቃልን ትወደጂዋለሽ አይደል?.›በሁኔተዋ ተጠራጥራ ጠየቀቻት..

‹‹በጣም እወዳዋለሁ…ባለወደው ከእሱ ጋር ምን አንዘለዘለኝ…. አፈቅረዋለሁ ማለት ታዲያ በኪራይ ቤት እሱን ለማግባት ፍቃደኛ ነኝ እያልኩሽ አይደለም.. በፍፅም እንደዛ አላደርግም….ግን ደግሞ ሌላ ወንድም ማግባት አልፈልግም እስከ ስልሳ አመትም ቢሆን እጠብቀዋለሁ…ምክንያቱም  ቃልን የመሰለ ባል የትም አይገኝም…..አምስት ወንድ እንድ ላይ ተደርበው ቢታሰሩ እሱን አይደርሱበትም፡፡››ብላ አንጀት ሚበጥስ ከረር ያለ መልስ ሰጠቻት፡
‹‹እኮ እኔም  እሱ ነው የገረመኝ….በጎዳና ላይ በተጣለ ዱንኳን ቤትም ቢያገቡት ያዋጣል ብዬ እኮ ነው››ሳታስበው የውስጧን ቀባጠረች፡፡
‹‹ተይ ተይ ህይወት እቃቃ ጫወታ  አይደለችም…ፍቅር እንጀራና ዳቦ መሆን አይችልም…እናንተ የሀብታም ልጆች ፊልምና ህይወት ይምታታባችኋል፡፡አንቺ አሁን ፍቅረኛ አለሽ አይደል?ሰትል እራሷን ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዎ›› አለቻት፡፡
‹‹ማለት?››
‹‹እሺ አለኝ››
‹‹መች ታገቢዋለሽ..››
‹‹በቅርብ…ከሶስት ወር በኃላ፡፡;;
‹‹ቤት አለው…?››
‹‹አዎ አዲስአባባ እና ሰንዳፋ ላይ መኖሪያ ቤት አለው›
‹‹ሁለት ቤት ማለት ነው?››
‹‹አዎ….››
‹‹እሺ መኪናስ?››
‹‹ምን የቤት ነው የንግድ ?ማለት የካማፓኒያችን ከሆነ ቁጥራቸውን አላውቅም››
‹እሺ የቤትስ?››
‹‹ሶስት መኪኖች አሉት››
‹‹አየሽ ለምን እንደምታገቢው?››
ልዩ ተበሳጨች‹‹እና ለብር ብዬ የማገባው ነው ሚመስልሽ..?››
‹‹እና በጣም ስለምታፈቅሪው ነው…አይመስለኝም? ስለእሱ ስታወሪ አይኖችሽ ላይ የሚነድ የፍቅር እሳት አይታየኝም፡››
‹‹እርግጥ ምን ያህል እንደማፈቅረው አላውቅም….ግን ያ ማለት የማገባው ለገንዘብ ነው ማለት አይደለም…እኔ ከቤተሰቤ በውርስ ማገኘው ሀብት ምን አልባት ከእሱ ይበልጥ እንደሆነ እንጂ አያንስም፡፡››
‹‹አይ ይህቺ አለም…አየሽ ዲታውን ከዲታ ከምታጣብቅ ምን አለበት .ያለውን ከሌለው ብታፋቅር….ለፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልም አሪፍ ነበር.››ስትል ቁምነገሩን ከቀልድ ጋር ደባልቃ ተናገረች፡
‹‹ታዲያ ምን ችግር አለው? ባል አንቀያየራ››አለቻት ልዩ
‹‹አይ አንቺ ምን አለብሽ ?ቀልጂ….››
ልዩ ለመቀለድ ብላ አልነበረም የተናገረችው…ሰው አስቦ ይናገራል ፣እሷ ግን ተናግራ ማሰብ ጀመረች..‹ባል እንቀያየር››ደጋግማ ደጋግማ በእምሮዋ አሰላሰለች… ድንቅ ሀሳብ ነው፡፡
በንግግሯ ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ አልፈለገችም..አዎ ስልሳ አመትም ቢሆን ጠብቃው እንድታገባው ፈፅሞ ልትፈቅድላት አልፈለገችም ፡፡ እልክ ውስጥ ገባች፡፡ጊዜ አንፃራዊ ነው..‹‹እሷ ዕድሜ ልክ አብራው ቆይታለች ማለት ከእኔ በላይ ታፈቅረዋለች ወይም ከእኔ በተሻለ እሱ ላይ መብት አላት ማለት አይደለም …ፍፁም፡፡››ስትል የራሷን ድምዳሜ ሰጠች፡፡
ልክ ጊፍቲ  የህይወት ታሪኳን ለሌላ ሰው ስታወራ በጉልህ የምትጠቅሰውና አይኗ እየበራ ምታወራው ስለቃል እንደሆነ ሁሉ የልዩም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው…
‹‹.ምን አልባት በጣም ወደአካላቱ ለጥፎ አቅፎ ከንፈሮቾን ለሺ ምናምን ጊዜ ስሟቸው ሊሆን ይችላል…ጭኖቾንም ፈልቅቆ ለበርካታ ቀናትና አመታት የሚያቃትት አይነት ወሲብ ፈፅመውና እረክተው ሊሆን ይችላል…ይሄም ቢሆን ግን ከእኔ በላይ ቀርባዋለች ብዬ እንዳስብና እንዳምን አያደርገኝም…፡፡አዎ ..እሱን ማግባት ያለብኝ እኔ ነኝ ፡፡ይሄ የህይወቴ ዋናው ግብ ነው፡፡እኔ እሱን ነጥቃታለሁ፡፡ከዚህች  ልጅ ጋ በዘዴና በጥበብ መደራደር አለብኝ›› ስትል  ወሰነች፡፡
‹‹አዎ ባሌን ወስዳ ባሏን ብትሰጠኝ ሁለታችንም በጣም ደስተኞች እንሆናለን፡፡ አዎ ወንዶቹም የሚከፋቸው አይመስለኝም..አዎ ከዛሬ ጀምሮ ይሄንን ትልቅ አላማ አንግቤያለሁ ማለት ነው.ይሄን ሳላሳካ እንቅልፍ በአይኔ አይዞርም››ብላ በውስጧ ፎከረች፡፡
አዎ ቃልን ለማግኘት ስትል መድህኔን ልትሰጣት ወስናለች… ቃል የጊፍቲ ልጅነት ጓደኛዋና ወደፊት ልታገባው ያሰበችው ቃል ኪዳን የገባላት ፍቅረኛዋ እንደሆነ ሁሉ መድህኔም ለእሷ የልጅነት ጓደኛዋ እና እጮኛዋ ነው…..ነገር ግን አሁን እሷም በማታውቀው ምክንያት ቃልን አምርራ ትፈልገዋለች.... ጊፍቲ ደግሞ  መድሀኔን ባትፈልግም ተዋውቀው ሲለማመዱ ግን ልትፈልገው ትችላለች ብላ አሰበች …በእዛ ላይ ጭማሪ ሀብት ትፈልጋለች ብላ አሰበች…ያንን ደግሞ  ቃል ሊሰጣት አይችልም ..ቢያንስ በቅርብ አመት እንደዛ ማድረግ እንደማይችል በማያሻማ ቃል በራሱ አንደበት ነግሯታል.‹‹.ብንቀያየርስ..?ሁሉ ነገር ፐርፌክት ይሆናል፡፡›› ደመደመች፡፡
👍7210🎉4😁3👏2
አንድ ሊኖር የሚችል ጉድለት ቢኖር ጊፍቲ መድህኔን እንዴት ታፈቅረዋለች የሚለው ነው…?ስለዚህ ከዛሬ ጀመሮ የእኔ ፕሮጀክት መድሀኔንና ጊፍቲን እንዲቀራረቡ ማድረግ ነው..እኔ እራሴን ከመድህኔ እያላቀቅኩ ወደቃልዬ ማጣበቅ…፡፡
በተቻለኝ መጠን ሁኔታዎችን እያመቻቸች መደህኔና ጊፍቲን ቀድመው እንዲሳሳቱ እና ወደ ፍቅር መስመር ውስጥ እንዲገቡ በተቻለኝ መጠን ስውር ጥረት ማድረግ እንዳለባት ውስጧን አሳመነች …ከዛ ጥረቷ ተሳክቶ እንዳሰብበችው ካደረገች እሷ ቀድማ እጮኛዋን በመነጠቆ ማእበል ታስነሳለች....ከዛ በድፍረት ሄዳ ባሌን ወስደሻልና ባልሽን ተይልኝ ትላታለች… ባል አንዲቀያየሩ ታስገድዳታለች....ከፈለገች የፈለገችውን ያህል ብርም ልትጨምርላት ትችላለች፤ይሄንን ዕቅድ  በአእምሮዋ አብሰልስላ ከወሰነች በኃላ በውስጧ የተሰማት የደስታ ስሜት ለማስረዳት ይከብዳል፡፡

ይቀጥላል
👍67🤔42
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ //// ‹‹እና ምን እያልከኝ ነው›› ‹‹እንዴ!! እንዴት እንዲህ ትያለሽ.?መጀመሪያ ከቃል ጋር እራት ቀጠሮ ነበረን..አሁን ለአንቺ ከደወልኩልሽ በኃላ ደውሎ ድንገተኛ ጉዳይ ስላጋጠመው ዛሬ እንደማይችል ነግሮኝ ይቅርታ ጠየቀኝ...የእራት ግብዣው አሌለ ደግሞ ስጦታው አያስፈልግም ››የመዋሸት ብቃቷ  ለእሷው ለራሷ አስደነቃት፡፡ ‹‹እና…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ሰዓቱ 11.10 ነው።22 አንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብላለች።ብቻዋን ነው ያለችው...ስልኳን አወጣችና ደወለች።
‹‹ሀይ ቃልዬ እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁ ልዩ ደህና ነሽ?››
‹‹አለሁ ...ከስራ አልወጣህም እንዴ?››
‹‹ወጥቼያለሁ ..መገናኛ ነኝ።››
"ለምን መክሰስ አልጋብዝህም 22 ነው ያለሁት"
"ደስ ይለኝ ነበር.. ግን አሁን ጊፍቲ ደውላ  ሰፈር እየጠበቅኩህ ነው ስላለቺኝ ወደእዛው ልሄድ ነው"እንደዛ ያላት አውቆ ነው…ልዩ እንገናኝ ካለችው ጊፍቲንም ይዟት ሊሄድ ስለፈለገ ነው…
"ሰፈር ማለት አንተ ቤት ?"
‹‹አዎ"
‹‹ለምን ይዘሀት አትመጣም..እንደውም አሪፍ ነው?"
አንዳሰበው ስለሆነለት ፈገግ አለ"ልጠይቃትና መልሼ ልደውልልሽ"

"እሺ ቃልዬ...እዛው ቁጭ ብዬ ጠብቃለሁ"አለችውና ስልኩ ተዘጋ። ከጨጓራዋ አካባቢ የተነሳ ቃጠሎ  ጉሮሮዋ ድረስ ሲሰማት ታወቀት፡፡

ቃል የልዩን ስልክ እንደዘጋ ወደ ጊፍቲ ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ ቃለዬ..፡፡››
‹‹አለሁልሽ ጊፍቲ.ላግኝሽ?››
‹‹ደስ ይለኛል..መክሰስ ልትጋብዘኝ ነው ወይስ እራት?››
‹‹አይ መክስ ነው.. ግን ጋባዡ እኔ አይደለሁም.›
‹‹ችግር የለውም እኔ ጋብዝሀለው››
‹‹አይ ጋባዥ አለን›
‹‹ማን?››
ልዩ ደውላልኝ ነበረ ..ልጋብዛችሁ ስላልች ነው የደወልኩልሽ››
ቅሬታዋን መደበቅ አልቻለችም‹‹ቃል ግን እሷ ልጅ…››አንጠልጥላ ተወችው፡፡
‹‹እሷ ልጅ ምን…?››
‹‹እኔ እንጃ ነገረ ስራዋ አያምረኝም…ሌላ አላማ ያላት ይመስለኛል››
እንዳልገባው ሆነ‹ሌላ አላማ ስትይ..?››
‹‹ያው ማለቴ ምትወድህ ይመስለኛል..››
ደስ አለው…..አዎ ቅናት እየጀመራት ነው ሲል አሰበ..‹‹ብትወደኝ ምን ችግር አለው? ጓደኛዬ አይደለች..››
‹‹ቃል ደግሞ… እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም.ምታፈቅርህ ይመስለኛል.ደግሞ ይመስለኛል አይደለም እርግጠኛ ነኝ…››

‹‹አረ ተይ .እኔ ምንም እንደዛ አይነት ስሜት አላየሁባትም.ደግሞ ፍቅረኛዬ እንደሆንሽ ነግሬታለሁ እኮ››
ቢሆንም ተጠንቀቃት.ለማንኛውም የት ነህ ልምጣ.››ያለበትን ቦታ ነገራትና በፈግታ ስልኩን ዘግቶ ለልዩ እንደሚመጡ ለመናገር ደወለላት፡፡

"ይህቺ ጊፋቲ የምትባል ሴት እንዴት ላስወግዳት?"ልዩ እራሷን ጠየቀች... ...ስልኳ ተንጫረረ ..ቃል ነው.. ቀና መልስ እንዲመልስላት በውስጧ እየፀለየች አነሳችው፡፡
"እሺ ቃል?"
"15 20 ደቂቃ እናስጠብቅሻለን።
"ችግር የለውም አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቃችኋለው"አለችና በደስታ ያለችበትን ካፌ ስም ነግራቸው ስልኳን ዘጋችው፡፡

በራሷ ሁኔታ  መገረም ጀመረች"ወይ ጉዴ.. አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቃችኃለው"ስል አሁን መድህኔ ቢሰማ ጭንቅላቱን ይዞ ነው የሚጮኸው...›አለች እንዲህ ልትል የቻለችበት ምክንያት  5 ደቂቃ አረፈድክ ብላ ብዙ ቀን ጮኸበታለች...አስር ደቂቃ አርፍዶ ቀጠሮውን ሰርዛ ጥላው የሄደችበትም ቀናቶች ጥቂት አይደሉም።  

እንዳሉትም ከ20 ደቂቃ በኃላ እጅ ለእጅ ተያይዘው ፊቷ ተከሰቱ፡..መጀመሪያ ልክ እንደረጅም ጊዜ የልብ ጓደኛዋ እሷ ላይ ተጠመጠመችባት ..አገላብጣ ጉንጮቾን ሳመቻት...ጊፍቲ ያልጠበቀችው አይነት አቀባበል ስለሆነ  ግር እንዳላት    ከሁኔታዎ ያስታውቃል...እሷ እራሷ ለምን እንደዛ ኦቨር አክት እንዳደረገች አልገባትም ‹‹...ምን አልባት የይሁዳን መሳም ይሆናል የሳምኳት..››ስትል እራሷን ታዘበች፡፡.ቃልን ከእሷ መለስ ባለ  ሰላምታ  ሰላም አለችውና ሁለቱም ከፊት ለፊቷ ወንበር ስበው ሊቀመጡ ሲሉ‹‹..አይ ቆይ እንውጣ"አለቻቸው፡፡

"ምነው ታሳፍሪኛለሽ ..መክሰስ ትጋብዘናለች ብዬ እኮ ነው ይዤት የመጣሁት..መክሰሱ ቢቀር ቢያንስ ሻይ ጋብዢን እንጂ"ሲል ቀለደ

"አይ የመክሰሱን ሰዓትማ አሳለፍችሁት  አሁን የእራት ሰዓት ነው...እራት የሚገኝበት ቤት እንሂድ.."

‹‹እሱ የተሻለና የተቀደሰ ሀሳብ ነው"አለች ጊፍቲ ...

ተያይዘው ወጡና  መኪናዋ ውስጥ ገቡ… ወደ ዪሆሚያ ክትፎ ቤት ይዛቸው ሄደች ...እዛ ገብተው እስፔሻል ክትፎቸውን አዘው ቀላል ጫወታዎችን እየተጫወቱ ..በልተው ሲያጠናቅቁ አንድ ሰዓት ከሩብ  ሆኖ ነበር። ሂሳብ ልትከፍል ስትጠይቅ ተከፍሏል አሏት...ልቆጣጠረው የማትችለው ንዴት ተናነቃት፡፡..

‹‹ማን ነው የከፈለው ...?››ፊት ለፊቷ ያሉት ቃልና ጊፍቲ ላይ አፈጠጠችባቸው።ሁለቱም ደንግጠው እርስ በርስ ተያዩ   ..."አረ ተረጋጊ እኛ አልከፈልንም"አለት ቃል።
"ማን ነው የከፈለው?"አስተናጋጅን ጠርታ  ጠየቀችው፡፡

"ጋሽ መድህኔ ነው"

ተረጋጋች"እሱ ደግሞ ከእዚህ ቤት አይጠፍም" ስትል በውስጧ አልጎመጎመች፡

"መድህኔ ማን ነው?"ብላ ጠየቀቻት

‹‹ እስቲ አሁን ሆነ ብላ እኔን ለማሳቀቅ ካልሆነ የመድህኔ ማንነት ምን ይረባታል..? በውስጧ ነው ምታወራው…ቀና ብላ ቃልን ስታየው እሱም የመድህኔን ማንነት ለማወቅ የጓጓ መሆኑን በሚያሳብቅ  አስተያየት ነው እያየት ያለው..ለተጠየቀችው ጥያቄ መልስ ከመመለስ ውጭ ሌላ ምርጫ እንደሌላት ግልፅ ሆነላት፡፡ምን ብላ ትመልስ…ግራ ገባት" መድህኔ ጓደኛዬ...ማለቴ ፍቅረኛዬ ነው"አለች፡፡

‹‹የት አለ አስተዋውቂና አረ ጥሪው"ጊፍቲ አሽቃበጠች….፡፡

ልዩ አሁንም የሆነ ነገር ለማድረግ ከአባቱ ፍቃድ እንደሚፈልግ ህፃን በቆረጣ ቃልን አየችው፡፡

ቃልም ልክ ከዚህ በፊት መድሀኒ የተባለወን ስም እንዳልሰማ በማስመሰል "አዎ ጥሪውና እናመስግነው...በዛውም እንተዋወቀዋለን"አላት

"ደወለችለት"

"አንተ የት ነህ?"

"ውስጥ ነኝ ..እጄን እየታጠብኩ"

‹‹ታዲያ ሰላም አትለንም እንዴ?"

‹‹መጣሁ"ከ3 ደቂቃ በኃላ መድህኔ እንደወትሮ ዝንጥ ብሎ በሱፍ እንደታነቀ ፊት ለፊታችን ገጭ አለ...

‹‹ተዋወቁት መድህኔ ማለት እሱ ነው"በየተራ እየጨበጠ ተዋወቃቸው..

"ስለተዋወቅኩህ ደስ ብሎኛል...ልዩ ግን ይሄን የመሰለ ሸበላ ባል እንዳለሽ ለምን እስከዛሬ ደበቅሽኝ?"አለቻት ልዩ ተሸማቀች፡፡ የጊፍቲን ንግግር ለሚሰማ ሰው የሁለቱ ትውውቅና የጓደኝነት ታሪክ አመታትን ያስቆጠረ  ነው ሚመስለው? ልዩ ከውስጧ እየታገለች ዝም አለች

..ቃል ‹‹ቁጭ በላ›› አለው ቦታ እያመቻቸለት

"ቆይ ጓደኞቼን ተሠናብቼ ልምጣ ››አለ

ልዩ ግን መድሀኔ ተመልሶ እንዲመጣና እንዲቀላቀላቸው  ስላልፈለገች..."አይ ለምን እኛም እኮ ልንወጣ ነው"አለችው፡

"እኮ 2 ደቂቃ ብቻ ጠብቁኝና አብረን እንወጣለን ..እንዴ ክትፎ በልቶ ደግሞ አንድ ሁለት ሳይባል ቢገባ ጥሩ አይደለም...እራት እኔ አይደል የጋበዝኮችሁ አንቺና ጓደኞችሽ ደግሞ መጠጥ ትጋብዙኛላችሁ ...››ብሎ መልስ ሳይጠብቅ  ዞሮ ሄደ...ሳታስበው እንደውም ጥሩ ሀሳብ ነው..

ወደእነ ቃል ዞራ "ሰዎች እንግዲህ ቻሉት.. መድህኔ ካለ አለ ነው "አለች

ጊፍቲ"እንዲህ አይነት ድንገተኛ ግብዣ ተገኝቶ ነው...ጭፈራ ቤት ብንሄድ ደግሞ እንዴት ደስ ይለኛል መሰለሽ" ስትል ተቅለብልባ መለሰችላት..ቃል ዞር ብሎ አያትና"በቃ አንቺና ጭፈራ መች ነው የምትለያዩት"አለ፡፡

"ጭፈራ ትወጂያለሽ እንዴ?"ልዩ ነች ጠያቂዋ፡

"አትጠይቂኝ… ጭፈራ ከመውደዴ የተነሳ አንድ አመት ዲጄ ሆኜ ሰርቼያለሁ... "

‹‹አንግዲያው ከመድህኔ ጋር በጠም ትጣጣማለችሁ ማለት ነው›ሥትል ከኃላዋ መድህኔ መጣና በምንድነው የምንጣጣመው? ››ሲል ያልተዘጋጀችበትን ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡…

‹‹ በቅርቡ ልታየው አይደል ››በማለት ድፍን ያለ መልስ መለስችለትና  ተያይዘን ወጡ ...

ይቀጥላል
👍142🥰145🤔3😱2👏1😁1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ሰዓቱ 11.10 ነው።22 አንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብላለች።ብቻዋን ነው ያለችው...ስልኳን አወጣችና ደወለች። ‹‹ሀይ ቃልዬ እንዴት ነህ?›› ‹‹አለሁ ልዩ ደህና ነሽ?›› ‹‹አለሁ ...ከስራ አልወጣህም እንዴ?›› ‹‹ወጥቼያለሁ ..መገናኛ ነኝ።›› "ለምን መክሰስ አልጋብዝህም 22 ነው ያለሁት" "ደስ ይለኝ ነበር.. ግን…»
ሰጠሁኝ ለማለት
ካሜራ ደቅኖ ድሀን የሚያጎርሰው
እናቱን ድህነት እናቱን "በጎ" ሰው።
😢87👍92👎1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹ በቅርቡ ልታየው አይደል ››በማለት ድፍን ያለ መልስ መለስችለትና ተያይዘን ወጡ ...

‹‹እሺ ቦታ ትመርጣላችሁ ወይስ እኔ ልምረጥ?››መድህኔ ነው ወደ መኪና ከመግባታቸው በፊት የጠየቀው፡፡

"ቦታውን አንተ ምረጥ ..ግን ጭፈራ ቤት መሆን አለበት"አለችው ልዩ፡

"አሪፍ ነዋ"አለ ፊቱ በርቶ..ከዛ ወደ መኪናው መራመድ ጀመረ...ተከተሉኝ፡፡

እስከ ለሊቱ ሰባት ሰዓት ቀወጡት ..በዋነኝነት ተዋናዬቹ ሶስቱ ነበሩ፡፡ ከመሀከላቸው ቃል መጠጥ አይጠጣም .... ውሀ ይዞ እነሱን መከታተል ነበር ዋና ስራው፡፡ሲጨፍሩ ያየቸዋል... ሲንገዳገዱ ይደግፋቸዋል... ፡፡ እነሱም በእሱ ተማምነን ዘና ብለን እየቀወጡ ነው ምሽቱን በፈንጠዝያ ያሳለፉት።ለነገሩ ልዩም በአብዛኛው ከእሱ ተለጥፋ ነው ያመሸችው፡፡

‹‹ሚስትህ ባሌን እኳ አንሳፋፈችው››አለችው፡፡

‹‹ምነው ቀናሽ እንዴ?››

‹‹ለምን አልቀና እኔ እንደአንተ ደመበራድ አይደለሁም››

እና ምን ይሻላል

‹‹ያው ምን ይሻላል .መጨረሻቸውን ማለት ነው››

እስከወዲያኛው ብትቀማሽስ››

ትሞክረዋ›

<<ምን ታደርጊያለሽ››
እሾክን በሾክ ነዋ…እሷ እኮ ባል አላት›› አለችው…ፉከራዋ አሳቀው፡፡

መድህኔና ጊፍቲ ስለእነሱ ሹክሹክታ ደንታም ሳይሰጣቸው በጭፈራቸው ተመስጠዋል፡፡ ሁለቱም አደገኛ ጨፋሪዎች ናቸው ...ደግሞ በሚገርም ጥምረት ተግባብተው በአየር ላይ የመብረር ያህል አቅላቸውን ስተው ተጣብቀው ሲደንሱ ላያቸወ ከአየን ያውጣችው ያስብላሉ ፡፡ አሁን እዚህ ጭፈራ ቤት ያሉ ሁሉ ልዩና ቃልን ቀዝቃዛ ፍቅረኞች ….ጊፍቲና መድህኔ ደግሞ የበለጡ የሚያምሩና የሚግባብ የጋለ ፍቅር ላይ ያሉ ጥንዶች እንደሆኑ ምሎ ሊናገር ይችላል። ‹‹ግን በትክክልም መሆን ያለበት እንደዚህ ነው።አዎ መድህኔ እኮ በጣም ቆንጆ ፤ዘናጭ፤ ሀብታምና ጥሩ ስነምግባር ያለው ሰው ነው...እና ጊፍቲ መድህኔ ፍቅረኛዋ ቢሆን በጣም ጥሩና የተመቸ ኑሮ ትኖራለች...አዎ እሱን ብታገኝ በጣም እድለኛ ነች።›ስትል አብሰለሰልች፡፡

ግን መድህኔ እንደምትይው ሁሉን የሚያሟላ ተመራጭ ወንድ ከሆነ አንቺስ ለምን እሱን ለቀሽ ቃልን ተመኘሽ?ብሎ የሚጠይቃት ሰው ካለ ምን አይነት መልስ ልትመልስ እንደምትችል አታውቅም..

.ስለቃል የሚሰማት ስሜት ጥልቅና መንፈሳዊ ነው"..ልክ የመድህኔን ኳሊቲ በቀላሉ ዘርዝራ እንደተናገረችው የቃልን እንደዛ ማድረግ አትችልም...እና ደግሞ የቃልን ጉዳይ ባይሆንባት በማንም ሌላ ወንድ መድህኔን መቀየር አትፈልግም ነበር...እና ደግሞ ማንም ሌላ ሴት መድህኔን ልትቀማት ሞክራ ቢሆን ኖሮ አንገቷን ቀንጥሳ ነበር የምትጥላት።ስለ ቃል ሚሰማት ስሜት ይሄን ያህል ውስብስብ ነው

ሰባት ሰዓት ስላለፈ እዛው ሲጨፍሩበት ካመሹበት ሆቴል አንድ ባለ ሁለት አላጋ ክፍል ተያዘና እየተጓተቱ ሄድን ፡፡እውነት ለመናገር ብክት እስኪሉ ሰክረዋል.... መኝታ ቤት እንደገቡ ብርድ ልብስ ገልጦ ከውስጥ የገባ የለም...ልዩና መድህኔ አንድ አልጋ ላይ ቃልና ጊፍቲ አንድ ላይ ተመሳቅለው ተኙ። ልዩ ከጎኖ እጮኛዋን መድህኔ ሰውነቷ ላይ ተለጠፋ የተኛች ቢሆንም ነፍሷ ግን ቃል እቅፍ ውስጥ ነበር ተሸጉጣ ያደረችው።
///
ጥዋት አንድ ሰዓት ተኩል ሲል ከአንቅልፋቸው ተነስተው ሁሉም ለብሰው ያደሩትን የተጨማዳደ ልበሳቸውን በተቻለ መጠን አስተካከሉና ወደሬስቶራንት ጎራ ብለው ፤አፒታይታቸው በፈቀደላቸው መጠን ቁርስ በልተው በማጠናቅ ሆቴሉን ለቀው ለመውጣት ዝግጁ ሆኑ ከዛ ልዩ ጊፍቲን ቢሮዋ ድረሰ ሸኝታት ወደትምህርት ቤት እንድትሄድ በተመሳሳይ ደግሞ መድህኔ ቃልን መስሪያ ቤቱ ድረስ አድርሶት ወደስራው ሊሄድ ድልድል አወጡ፡፡ልዩ እንዲሆን የፈለገችው ተቃራኒውን ነበር...እሷ ቃልን እንድትሸኘው መድህኔ ደግሞ ይህቺን መዥገር ነገር እንዲያደርሳት… በዛውም ሁለቱ ስለማታው የሰመረ የዳንስ ጥምረታቸው እያወሩና ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ እንዲሄዱ ፈልጋ ነበር ….ግን እንዴት ብላ ተቃውሞ ታቅርብ …?ሳትወድ በግድ በድልድሉ ተስማማችና ደስተኛ እንደሆነች ለማስመሰል እየጣረች ጊፍቲን አሳፍራ ወደቢሮዋ ጉዞ ጀመረች…ለረጂም ደቂቃ ምንም አልተነጋገሩም…..ጊፍቲ ነበረች ከዝምታዋ ያነቃቻኝ፡፡
‹‹ምነው እኔን ጥለሽ ጭልጥ አልሽ .?››
ድንገት አፏ ላይ የመጣላትን መልስ መለሰችላት‹‹ስለማታው አስደሳች ምሽት እያሰብኩ ነበር› …እንደዛ ያለችው. እውነት ስላለችው ነገር እያሰበችበት ስለነበር ሳይሆን ሰለማታው ቆይታቸው ምን እንደተሰማት ለመገምገም እንዲረዳት ነው፡፡
‹‹ውይ ብታይ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል...እንዲህ አይነት ፍንጥዝጥዝ ያለ ምሽት ካሳልፍኩ ረጂም ጊዜ ሆኖኝ ነበር.በጣም አመሰግናለሁ›› አለች ጊፍቲ…
ልዩም‹‹አሀ አንዳሰብኩት በጣም ደስተኛ ነበረች ማለት ነው?››ስትል በውስጧ አሰበቸና ይበልጥ ዝርዝሩን ለመረዳት ንግግሯን ቀጠለች ‹‹ደግሞ በጣም ደናሽ ነሽ›ስትል የአድናቆት ቃል ሰነዘረች፡፡
‹‹አዎ ዳንስና ጭፈራ በጣም ወዳለሁ..ግን ባልሽን ጫፍ ላይ አልደርስም…በስመአብ አጥንት ያለው እኮ አይመስልም››
ጊፍቲ በአንድ ቀን ቆይታ ለመድሀኔ ያደረባት አድናቆቶ ካሰበችው በላይ የተጋነነ ሆኖ ነው ያገኘችው…እርግጥ መድሀኔ ሁሉም የሚያወራለት ጨፋሪ እንደሆነ እራሷም ልዩ ታውቃለች…ጊፍቲ በምታወራለት ልክ ግን ሌላ ሰው ሲያደንቀው ሰምታ አታውቅም..እሷ ያው እንደቃል የቀዘቀዘች ባትሆንም ለጭፈራ ያን ያህል ስለሆነች በእሷ ልክ የመድሀኔን ችሎታ ባይታያት አይፈረድባትም፡ስለዚህ ይሄ መደነቋ ሳይበርድ ልትጠቀምበት ይገባል ብላ አሰበች…በጣም ፈጣን የሆነ እቅድ በእምሮዋ ተሰነቀረ፡፡
‹‹ውይ ይቅርታ…አንድ ነገር እያሰብኩ ነበር…ከመድህኔ ጋር ሳምንት ኩሪፍቱ ለመሄድ ቀጠሮ ነበረን፤ በእኛ እስፖንሰርነት ለምን አንቺና ቃል አትቀላቀሉንም››
ከተማ ወጥቶ የመዝናናት ምንም አይነት ዕቅድ የላቸውም ….ግን እሷ ከተስማማች መድህኔን ከከተማ ወጥቶ መዝናናት እንደምትፈልግ መናገር ብቻ ነው የሚጠበቅባት….ምንም አይነት ወሳኝ የስራ ቃጠሮ ይኑረው ወይም ሌላ ፕሮግራም ሁሉንም ጣጥሎ ፍላጎቷን እንደሚያሞላላት እርግጠኛ ነች…ለዛ ነው በልቧ ሙሉነት የግብዣውን ሀሳብ ያቀረበችላት፡፡
‹‹ወይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…?ግን ቃል የሚመቸው አይመስለኝም….መስሪያ ቤቱ ለአምስት ቀን ፊልድ ክፍለሀገር ሊለከው ነው…ነገ ክፍለሀገር ይሄዳል..››አለቻት፡፡
ልዩ በጊፍቲ መልስ ደስ አለት ፡፡ደስ ያለት ለአምስት ቀን ሙሉ ቃልን ላታየው ባለመቻሏ አይደለም…ግን በጉዞችን የቃል አለመኖር ጥሩ ሆኖ ነው ያገኘችሁት… ጊፍቲን ከመድህኔ ጋር ይበልጥ እንዲቀራረብ ለማድረግ አሪፍ እድል ይሆናል ብላ ስላሰበች ነው፡፡
‹‹ታዲያ ለምን አንቺ አትቀላቀይንም ?..በሌላ ዙር ደግሞ ቃልን ጨምረን ተሟልተን እንሄዳለን››
‹‹ተይ ባክሽ..ብቻችሁን ብታሳልፉ ይሻላል?፡፡››መግደርደር መሆኑን በደንብ በሚያሳብቅ ፈራ ተባ ባለ ንግግር መለሰችላት፡
👍845🔥2😱2
‹‹ባክሽ እኛ እኮ ይሄንን አይነት ትሪፕ ሰልችቶናል…እንደውም ያንቺ መኖር የተለየ ጉዞ ያደረግልናል …ለዛውስ ሳገባ የመጀመሪያ ሚዚዬ መሆንሽ የት ይቀራል...ከባሌ ጋር በደንብ መተዋወቁ አይከፋም..››
‹‹ማልደብራችሁ ከሆነማ ደስ ይለኛል፡፡››ስትል ተስማማች፡፡
‹‹በቃ …አርብ ወደማታ እንወጣና እሁድ ማታ እንመለሳለን…››
‹‹አሪፍ ነው ››
ደስ አለት….በውስጧ እያብሰለሰለች ያለችው ሀሳብ ሰይጣንም አያስበውም….. ቢሮዋ በራፍ ጋር አወረደቻትና ጉንጯን ስሜ በደስታ እየተፍነከነከች ወደክላስ ነደቻው፡


ይቀጥላል
👍63🤔2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሁለት ፡ ፡ #ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ‹‹ በቅርቡ ልታየው አይደል ››በማለት ድፍን ያለ መልስ መለስችለትና ተያይዘን ወጡ ... ‹‹እሺ ቦታ ትመርጣላችሁ ወይስ እኔ ልምረጥ?››መድህኔ ነው ወደ መኪና ከመግባታቸው በፊት የጠየቀው፡፡ "ቦታውን አንተ ምረጥ ..ግን ጭፈራ ቤት መሆን አለበት"አለችው ልዩ፡ "አሪፍ ነዋ"አለ ፊቱ በርቶ..ከዛ ወደ መኪናው መራመድ…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

በእቅዷ መሰረት ኩሪፍቱ ይገኛሉ….ትናንትና ከመሸ ነው የገቡት፡፡ከጥዋቱ ሁለተ ሰዓት አካባቢ ሆኗል..መኝታውን ለቆ ተነስቶ ክፍል ውስጥ ሲንጎራደድ ከጀመረ 30 ደቂቃ ያህል አልፎታል አንዴ መታጠቢያ ቤት ይገባል…አንዴ ወደበረንዳ ይወጣል…እኔ እየሰማው ቢሆንም አንቅልፍ ውስጥ እንዳለ ሰው አድፍጣ ዝም….መታጠቢያ ቤት ሲገባ ፈጠን ብላ ተነሳችና ከቦርሳዋ ውስጥ መከታተያ ካሜራዋን በማውጣት ወንበር ላይ የተንጠለጠለው ጃኬቱ ላይ አንዳይታይ አድርጋ ኮሌታው አካባቢ አጣበቀችውና ቶሎ ብላ ወደመኝታዋ ተመለሰች …በስተመጨረሻ ትግስት አጥቶ ,..ፈራ ተባ እያለው ወደአልጋው ቀረበና ትከሻዋን ይዞ እየነቀቃት…..

‹‹ፍቅር ተኝተሸ ቀረሸ እኮ …በጣም እርቦኛል..ተነሽ ቁርስ እንብላ››አላት
‹‹ተወኝ በናትህ እንቅልፌን አልጠገብኩም…ጊፍቲን ቀስቅሳትና አብራችሁ ብሉ››
‹‹ተይ እንጂ ፍቅር..››
‹‹እየረበሽከኝ አኮ ነው..በፈጣሪ ተወኝ››ተነጫነጨችበት፡፡
‹‹እሺ.ስትነሺ  ተቀላቀይን›› ብሎ ዘረጥ ዘረጥ እያለ ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበሩ መራመድ ጀመረ…ፍፁም ንቁ ሁና ከአንገቷ ቀና አለችና..

‹‹እንዴ?››አለችው፡፡

በሁኔታዋ ግራ በመጋባት‹‹ምነው ልጠብቅሽ ?ትመጪያለሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አይ አልመጣም ግን የውጩን ቅዝቃዜ አታየውም እንዴ…?››

‹‹እና ምን ?

ተኝተን እንዋል?››

ምን ለማለት እንደፈለገች አልተገለፀለትም፡፡

‹‹አላልኩም..በኃላ ኩሪፍቱ ወስደሽ ብርድ አስመታሺኝ እያልክ ስትወቅሰኝ እንዳትከርም….ጃኬትህን ለብሰህ ውጣ››

‹‹አረ ተይ… እንዲህ ተመችቶኛል››

‹‹አይሆን …ነገርኩህ እኮ….››

‹‹አንቺ ደግሞ በሚሆነውማ በማይሆነውም  መጨነቅ ታበዢዋለሽ…እኔ እኮ እስፖርተኛ ነኝ የምን በርድ ነው››እያለ በማጉረምረም ወደኃላ ተመልሶ ጃኬቱን ከተንጠለጠለበት ወንበር በማንሳት እየለበሰ ወጥቶ ሄደ…ፈገግ አለች…‹‹አይ ወንዶች ነገረ ሰራቸው  እኮ የህፃን ነው..በቀላሉ የሚታለሉ ገራገር ፍጥሮች… ሲመጣባቸውም እንደዛው ደንባራ አውሬዎች ናቸው…›አለችና …ከተኛችበት ተስፈንጥራ በመነሳት ክፍሉን ከውስጥ ቆለፈችው…ከዛ ላፕቶፖን አወጣችና ከፈተችው.. በገዛ እጮኛዋ  ደረት ላይ የሰካችውን ካሜራ ጋር የሚየገናኝውን አፕ ቁልፍ አበራችው…በዛን ሰከንድ አዲስአባ ቤቱ አልጋ ላይ ተኝቶ የሚገኘው  የቃል ስልክ ድምፅ አሰማ …ፈጥኖ ተነሳና ልክ ልዩ እንዳደረገችው ላፕቶፑን አነሳና አበራ…ከፈተውና ልዩ የምታየውን ማየት ጀመረ….
አዎ መድህኒ እየሄደ ነው..ጊፍቲ የተኛችበት መኝታ ክፍል በረንዳ ላይ እየወጣ ነው..አንኳኳ፡፡በራፍ ተከፈተና ጊፍቲ ከውስጥ ወጣች…ለባብሳና ሜካፖን ተቀባብታ ዝንጥ ብላለች…
‹‹እንዲህ ነው ንቁ ሴት..››አለ መድህኔ
እንደመሽኮርም አለችና‹ያው ለስራ ለሊት አይደለ ተነስቼ ምዘጋጀው ልምድ ሆኖብኝ ነው››

‹‹አይ በጣም ጥሩ ነው…በይ ወደ ቁርስ እንሂድ››

‹‹ልዩስ?››

‹‹እሷ እንቅልፍ ይበልጥብኛል ብላ እምቢ አለች›

በራፉን እየቆለፈች‹‹ምነው ማታ አምሽታችሁ ነበር እንዴ?››አለችው

‹‹ማለት? ጎድተሀታል ወይ እያልሺኝ ነው?›ሲል ጥያቄዋን በሌላ ጥያቄ መለሰላት፡፡

ፊቷ ቀላ..‹እረ እኔ…ማለቴ..›ተንተባተበች፡፡

‹‹ግድ የለም ስቀልድ ነው ..እውነታው ግን ልዩ እንዲህ ነች…አንዳንዴ ቅምጥል የሀብታም ልጅ  መሆን አጎጉል ያደርግሻል…›ወደቁርስ እየሄዱ ነው ልዩን የሚያሟት፡፡

ጥያቄ አስመስላ በውስጡ ግን አድናቆት እና ልብ ሚያሞቅ ቃል ጨምራበት፡፡‹‹አንተም እኮ የሀብታም ልጅ መሰልከኝ…ግን ይሄው   በጥዋት ንቁ ሆነህ ተነስተሀል›› አለችው….

‹‹አይ…የእኔ ስሙ ብቻ ነው…አባቴ እንዲህ የዋዛ ሰው መስሎሻል…እቤት ውስጥ ከ12 ሰዓት በኃላ የአንድ አመት ህፃን እራሱ አይተኛም…እያንዳንዱ የቤቱ ልጅ የየራሱ የስራ ድርሻ አለው….አልጋችንን እናነጥፋለን….አትክልት ዉሀ እናጠጣለን…ግቢ እንጠርጋለን…ከዛ በኃላ ነው ልብሳችንን ቀይረን ቁርሳችንን በልተን ወደ ትምህርት ቤት የምንሄደው….ከዛም ስንመለሰ ተመሳሳይ የተግተለተለ ስራ ይጠብቀናል…. የሚገርመው ደግሞ ይሄን ሁሉ ስራ የምንሰራው እኮ መአት ሰራተኞችና የደረሱ የዘመድ ልጆች ጭምር እቤት ውስጥ እያሉ ነው››

‹‹እና አሁን አንደዛ በመሆኑ እያማረርክ እንዳይሆን?››

‹‹አይ ሙሉ በሙሉ እያማራርኩ አይደለም...የእሱ አስተዳደግ አሁን ስራ ወዳድና ውጤታማ እንድሆነ አደርጎኛል….ግን ደግሞ ልጅነቴን ልክ እንደልጅ ሆኜ አጣጥሜ ተጫውቼ ስላላደኩ አሁንም የሆነ ከፍት ይሰማኛል…መኪና እየነዳሁ በሆነ መንደር ውስጥ በማልፍበት ወቅት  ልጆች መንገድ ዳር ተሰብስበው ብይ ሲጫወቱ ካየሁ ወርደህ አብርህችው ተጫወት የሚል ስሜት ይቀስፈኛል..ሌላው ይቀር ጭቃ እያቦኩ ግድብ የሚገድቡ ህፃናት ሳይ ውሰጤ ይቀናል እና አሁንም ያላደገ ህፃን በውስጤ ያለ ይመስለኛል፡፡››

‹‹እና አንተ ከልዩ ምትወልዳቸውን ልጆች እንዴት ለማሳደግ አሰብክ?››ብላ ጠየቀችው፡
በዚህ ጥያቄ ልዩን በጣም ነው ያስገረማት‹‹እኔ እንኳን አስቤ የማላውቀውን  ገራሚ ጥያቄ ነው›በማት መልሱን ልትሰማ ቋመጠች…ይህ መገረም አዲስአባ ያለው ቃልም ተጋብቶበታል፡፡
ጊፍቲና መድሀኔ ይሄን በሚያወሩበት ጊዜ ፊት ለፊት ተቀምጠው የሚፈለጉትን ቁርስ ከተደረደረው ቢፌ ላይ ወስደው ቁርስ እየተመገብ ነው፡፡

‹‹ልጅቷ ግን ፀሀፊ ሳትሆን ጋዤጠኛ ነው የምትመስለው፡፡ምን ብሎ ይመስልስላት ይሆን›አለች ልዩ…መድህኔ  የጎረሰውን አላምጦ ማውራት እስኪጀምር በጉጉት ትጠብቅ ነበር..
‹‹እንደእኔም ወግ አጥባቂ አስተዳደግ ሳይሆን እንደልዩም መረን የለቀቀ ስንፍና የተጫጫነው ሳይሆን በመካከል ባላ ዘመናዊ አስተዳደግ  እንዲያድጉልኝ ነው ምፈልገው››ሲል መለሰላት፡፡
ከትከት ብላ ሳቀች‹‹መረን የለቀቀ›› ስላለኝ የተደሰተች ይመስላል፡፡

‹‹ግን ስንት ልጅ ምትውልደ ይምስልሀል?›

‹‹እኔማ ስድስት ልጆች ብንወልድ ደስ ይለኛል…ግን ከማን?››
በዚህ መልሱ ፊት ለፊት ተቀምጣ ምታዳምጠው ጊፍቲ ብቻም ሳትሆን ከጀርባ ሆነው በሚስጠጥር የሚከታተሎቸው ልዩና ቃልም ጭምር ናቸው የደነገጡት

‹‹እንዴት ከማ…?ከሚስትህ ነዋ..›ጊፍቲ በገረሜታ ተሞልታ ጠየቀችው፡

‹‹ከሚስትህ ማለት ከልዩ?››
‹‹እንዴ ግራ አጋባሀኝ እኮ…ሌላ ሚስት አለህ እንዴ?››
እሱማ የለኝም...ልዩን ሳስባት ግን አንድ ልጅ እንኳን በስርአቱ አምጣ መውለድ የምትችል አይመስለኝም…ምግቧን እንኳን በእጆቾ ጠቅልላ መብላት የሚከብዳት እና በአጉራሽ የምትመገብ ቅንጡ .ልጅ ነች፡፡ታዲያ ልጅን  የሚያህል ነገር አርግዛ…. ለዛውም ዘጠኝ ወር….ለዛውም  ደጋግማ… ምን አልባት የመጀመሪያውን እንደወረት ልታደርገው ትችላለች.. ከዛ በኋላ ላሉት ግን እርግጠኛ ነኝ መሀፀን ተከራይልኝ ነው የምትለው››
ጊፍቲ ከት ብላ ሳቀች…‹‹ጓደኛዬንማ እንዲህ አትላትም…ይሄን ያህል ምነው?››መቆርቆሮ ሳይሆን የሆነ የሽሙጥና እሷ የተሻለች እንደሆነች በሚያረጋግጥ ስሜት ነው፡፡
እሱ ግን ቀጠለበት‹ባክሽ በጥልቀት ስለማታውቂያት ነው….የእሷ ጉዳይ ከምልሽም በላይ ነው….እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ያማውቃት….ቤተሰብ ነን….አሁንም የማስተዳድረው ካማፓኒ የሁለታችን ቤተሰቦች በጋራ የመሰረቱት ነው››
👍7012😁4👏3
አሁን ቁርሳቸውን አጠናቀው ወደኃይቁ በመሄድ ለእይታ ምቹ የሆነ ቦታ መርጠው በመቀመጥ ነወ እያወሩ ያሉት…መግባባታቸው ልዩ ከጠበቀችው በላይ በጣም የፈጠነ ሆነባትና በውስጧ በጣም ታዘበቻቸው….እርግጥ እሷም የፈለገችው እንዲህ እንዲሆን ነው….ግን ምንድነው በጣም ፈጠነ….ደግሞም የእሱ ሀሚት ልክ እንደሴት ነው የሆነባት…ከመናደዷ የተነሳ ‹‹ይሄንንስ በነጻም ብትወስጂልኝም ያዋጣኛል..››አለች…ማንም ይሰማኛል ብላ ስላልገመተች ድምፅ አውጥታ ነበር የተናገረችው….ቃል በኪሎ ሜትሮች ርቀት መኝታ ቤቱ ሆኖ እሷንም ጭረር እየተከታተላት መሆኑን ብታውቅ..እራሷንም ልትስት ትችላለች…ቃል አሁን የልዩ እቅድ ሙሉ በሙሉ ፍንትው ብሎ ሰለተገለፀለት ከዚህ በላይ ለመከታተል አልፈለገም….ላፕቶፑን አጠፋና  ከአልጋው በመውረድ ወደመታጠቢያ ክፍል ገባ….
ልዩ  በራሷ ንግግር ብቻዋን ፈገግ አለች….እነሱ ወሬቸውን ቀጥለዋለል
‹‹ጋብቻው የፍቅር ብቻ ሳይሆን የቢዝንስ ጭምር ነዋ››
‹‹እንደዛ በይው››
‹‹ታፈቅራታለህ ግን?››
‹‹ምነው እሷ አላፈቅረውም አለቺሽ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም…››
‹‹ማፍቀርስ አፈቅራታለሁ…ከልጅነቴ ጀምሮ ሚስትህ አሷ ነች ስባል ነው ያደኩት…ለእኔ እሷን ማግባት የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታ ሆኖ ነው ነው የሚሰማኝ…አረ እንደውም እንደነገርኩሽ ልጅ ሆኜ ነው አግብቼ የጨረስኳት… የአሁኑ ሰርግ ምናምን እንዲሁ ለፎርማሊቲ ነው፡፡››
‹‹የሚገርም ነው፡››
‹‹አዎ ይገርማል …እኔን ይሄን ያህል አስለፈለፍሺኝ እስኪ አሁን ደግሞ ወደአንቺ እንመለስ››
‹‹ወደእኔ ምን?››አለች ምቾት እንዳልተሰማት በሚያሳብቅ የፊት መጨማደድ
‹‹ፍቅር እና ትዳር ነዋ›፡፡
‹‹ፍቅር በሽበሽ ነው…ትዳሩ ግን ገና ነው››

‹‹ፍቅር ግን በሽበሽ ነው ስትይ አይኖችሽ ላይ የተበተነው ብርሀን    ሀይቁ ላይ አርፎ ድፍርሱን ሲያጠራው ተመለከትኩ››   
ልዩ‹‹እንዴ ይሄ ሰው ግን በትክክል የእኔ እጮኛ ነው..እንዴህ አይነት ስነፅሁፋዊ ቃላትን ከመቼ ዋዲህ ነው መጠቀም የጀመረው…?ነው ወይንስ እንደአሁኑ  ከቀልቤ ሆኜ ሳላማላዳምጠው ይሆን አዲስ የሆነብኝ ?››ስትል አብሰለሰለች፡፡
‹‹አረባክህ...በጣም ታጋንናለህ...የእውነቱን ለመናገር ግን ቃልዬ አፍቃሪ ሰው አይደለም.. እራሱ ፍቅር ነው ማለት ይቻላል።በጣም ልዩ ሰው ነው"
እዚህ ላይ ጊፍቲ ከተናገረችው ጋር ልዩም ምንም ተቃውሞ የላትም..‹‹ቃልዬ አፍቃሪ ሰው ይሆን እራሱ ፍቅር ነው…..ፐ ምርጥ አገላለፅ…›ስትል አደነቀቸላት፡፡‹‹ለዚህ እኮ ነው እኔም መድሀኒን የመሰለ ምርጥ ለባልነት የተፈጠረ ሀብታም ሰው ሰጥቼት በምትኩ ፍቅር የሆነውን ቃልዬን እንድትተይልኝ በመጣር ላይ ያለሁት…››.

እሱ ንግግሩን ቀጠለ"ታድለሻል...ግን አንቺም እኮ በጣም ልዩ ሰው ነሽ..ከተዋወቅኩሽ ገና ሳምንት ያልሞላው ቢሆንም   ግን የተለየሽ መሆንሽን መመስከር እችላለሁ… በዛ ላይ ማንንም የሚያስደነብር ውበት አለሽ"
"እንዲህ ስትል ሚስትህ እንዳትሰማህ...ማንኛዋም ሴት የእሷ የሆነ ወንድ እህቱንም ቢሆን አጋኖ ሲያሞግስ አትወድም"
"ግን እኮ አጋንኜ አይደለም ..ከምሬ ነው ..ታናሽ ወንድም ቢኖረኝ ነጥቄ ለእሱ ነበር የምደርሽ"
"እንዴ ሰውዬ በቀላሉ ይነጠቃል ብሎ ማን ነው የነገረህ?"አለቺው… .ይበልጥ እንዲያወራ በሚገፋፋ የድምፅ ቅላፄ…
"በከባድም ቢሆን ዋናው መነጠቁ ነው"
‹‹በል አሁን ተነስ  እንመለስ… ይሄኔ እኮ ልዩ ፈልጋን አጥታን ይሆናል?"
‹‹ማ ልዪ ..ስለማታውቂያት ነው …እንኳን ሶደሬ ሲዊዘርላድ ወስጄት ካልመሰላት  ተኝታ የምትውል ገራሚ ሰው ነች።››
"አይ ቢሆንም እንሂድ ..ሌላ ነገር ልታስብ ትችላለች?"አለችው፡፡
"ሌላ ነገር ምን አለ ?››ከኃላዋ እየተከተለ ጠየቃት፡፡
"አንተ ደግሞ ጥያቄ ታበዛለህ?"
"ካንቺ ግን አልበልጥም።››ወደመኝታ ቤቱ  እየተቃረብ ስለሆነ ከዚህ በላይ በማየቷ ልትቀጥል አልቻለችም ሄርፎኖን ነቃቅላ ላፕቶፖን አጠፋፍችና በመዝጋት ወደ በራፍ በመሄድ የቆለፈችውን በራፍ ከፍታ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች

ይቀጥላል
👍7411🤔4🔥1