‹‹እውነቶትን ነው አያቴ?››
‹‹አንተ ቀላማጅ…ስዋሽ አይተሀኝ ታውቃለህ?››
‹‹አይ ለዛሬ እንኳን በራፍን ቢከፍቱልኝ ጉንጮትን አገለባብጪ ብስም እንዴት ደስተኛ እሆን ነበር መሰሎት?››
‹‹ብልጡ ይቅርብኝ ግዴለም…..ግድግዳውን ሳም››
‹አያቴ በጣም ነው ማመሰግነው….እኔ ጋር እንደነገርኮት 70 ሺ ብር አለ.. ደሞዜን ስቀበል 75 ሺ ብር አካባቢ ይሆንልኛል...እንደምንም እርሶ ጋር የተወሰነ ከተገኘ የሆነ ነገር መጀመር እንችላለን..በእውነት በጣም ነው የተደሰትኩት፡
‹‹ልጄ ››
‹አቤት አያቴ››ደንግጬያለሁ…ያን ያህል ብር ከየት አመጣለሁ ሊሉኝ ነው የመሰለኝ…ቢዝነሱ የጋራ ከሆነ እኩል እኩል ብር ማወጣት አለብን ..በዛ ላይ ምንም እንኳን የደሀ ጉልበት ሂሳብ ውስጥ አይገባም እንጂ ቢገባማ ስራውን የምሰራው እኔ ነኝ›› ስል በውስጤ አጉረመረመኩ…አያቴ ግን ተአምራዊ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
‹‹ያንተን ብር ቢዝነሱን ለማጥናት ተጠቀማት..እኔ አንድ ሚሊዬን ብር እሰጥሀለሁ››
ትን አለኝ..ምራቄ ስርኔ ውስጥ ተወተፈ‹‹ምን አሉ አያቴ?››
‹‹ሰምተሀል››
‹‹ይሄማ አይሆንም …ይህ ሁሉ ብር. በዛ ላይ እርሶ እሺ ቢሉ እንኳን ጋሼ አይፈቅድሎትም… ››ጥርጣሬዬን ነው የተናገርኩት፡፡
‹‹አንተ ቀልማዳ..መቼ ነው የምፈልግ ነገር ለማድረግ የአንተን ጋሼ ሳስፈቅድ ያየሀው…ወለድኩት እንጂ አልወለደኝም እኮ››
‹‹ቢሆንም…እንደዛ አይነት ብር ደፍሬ ልቀበል አልችለም››
‹ከችግርሀ ለመውጣት ፍላጎት ካለህ ትቀበላለህ..አየህ እያንዳንዱ ስኬታማ ሰው ቆም ብለህ ብትጠይቀው በአየር ላይ ተንሳፎ አሁን የደረሰበት ቦታ አልደረሰም..እንዲህ አሁን አንተ እንዳጋጠመህ አይት ቅጽበታዊ እድል አጋጥሞት ያንን በምስጋና ተቀብሎ በጥረት አሳድጎና አበርክቶ ነው፡፡አሁን ይሄን እድል ከገፋህ ምን አልባት የዛሬ ሃያ አመትም ተመሳሳይ እድል አታገኝም፡፡
ባለህ እውቀት፤ በቀናነት እና በፅናት ስራህን ስራ፡፡ ከዛ ውጭ ከቁጥጥርሀ ውጭ በሆነ ሁኔታ ብትከስር እኔ ግድ የለኝም..ከእኔ በላይ ከሳሪው አንተ ነህ ብታተርፍም ከእኔ በላይ ተጠቃሚው አንተ ነህ፡፡፡ምክንያቱም እደምታዬኝ በትርፉ ልጃገረድ አላገባበትም….በኪሳራውም እራሴን አላጠፋም፡፡ደግሞ ዝም ብዬ ስለምወድህ ብቻ አይደለም ይሄንን ብር የምሰጥህ በብዙ መንገድ ነገሮችህን ገምግሜና አይቼ ነው..ጓደኛ አታግተለትልም….ወደቤት መግባት ባለብህ ሰዓተ ተቆጪ አለኝ ወይም የለኝም ሳትል ታደርገዋልህ…ስራህ ሰው አየኝ አላየኝ ሳትል በታማኝነት ትሰራለህ… ስላለህ ብቻ ገንዘብህን አትረጭም…..የምትፈልጋቸውን ነገሮች ሳይሆን በጣም የሚያስልጉህን ነገሮች በመጠቀም በመጠን እና በልክ የመኖር ልዩ ችሎታ አለህ…….ይሄ ደግሞ ብትከስር እንኳን በአንተ ጥፋትና እንዝላልነት እንደማይሆን እንዳማይሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡
‹‹አያቴ ካሉ ደስ ይለኛል፡፡
‹‹እንግዲህ ተዘጋጅ…. ለጋሼህ ሰሞኑን እነግረዋለሁ..ከዚህ ወር በኃላ አስተናጋጅ ስለማትሆን በድንብ አጣጥመው››
‹‹አያቴ ››
‹‹አሁን ደግሞ ምን ቀረህ?››
‹‹ጥዋት እቤትህ ውሰደኝ ብላ ለምናኝ ነበር….አያቴን እንረብሸዋለን ብዬ እምቢ አልኳት፡፡›
‹‹አይ እንደውም ላወራት እፈልጋለሁ››
‹‹ማለት ከክፍሎት ይወጣሉ? ››
‹‹አንተ ቀልማዳ….የእኔን ወደውጭ መውጣት እንዴት እንዲህ ፈለከው..?እንድኖር አትፈልግ ማለት ነው..?ቢያንስ እስኪ ቃል የገባሁልህ ብር በእጅህ አስገባ››
‹‹አያቴ እርሶ ከሌሉ ብሩ ምን ያደርግልኛል ..ስለሚናፍቁኝ እኮ ነው ….. ደግሞ ይደብራቸው ይሆን እያልኩ እጨነቃለሁ›››
‹‹በል ወሬውን ተውና ይዘሀት ና…ግን ስለአለው ሁኔታ አስረዳት...ልክ ካንተ ጋር እንደማወራው አወራታለሁ..አጫውትታታለሁ፡፡›
‹‹እሺ አያቴ አመሰግናለሁ››
‹ደግሞ ልምድ ስለሌለህ በተዝረከረከ ቤት ዝም ብለህ ጎትተህ እንዳታመጣት፡፡ ለክብሯ በሚመጥን ዝግጅት ነው መምጣት ያላባት.፡፡.ሴት ነች..በዛ ላይ ወታደር ሴት፡፡እና ሀገርህን ወደቤትህ እንደጋበዝክ ቆጥረህ ተዘጋጅ››ብለው ጭንቅላት የሚበላ የቤት ስራ ሰጡኝ፡፡
✨ይቀጥላል✨

👍88❤13🥰6🔥5🤔4
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
እንደተለመደው እቤቴ አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተዘርሬ በመተኛት ጣፋጮና ተወዳጇ ልጄ በቴሌግራም የላከችልኝን የእናቷን ዲያሪ በከፍተኛ ተመስጦና ውስጥን በሚሸረካክት የልብ ድማት ያለፈ ታሪኬን እያነበብኩ ነው፡፡
////
ማትሪክ በተቀበልን በአንድ ወር ውስጥ ለሰርግ ሽር ጉድ ተጀመረ..፡፡ለሠርጉ 15 ቀን ሲቀረው ጨነቀኝ..፡፡በረሽ ጥፊ ጥፊ..ወይም እራስሽን አጥፊ የሚል ስሜት ይተናነቀኝ ጀመር...፡፡እስቲ በፈረሰኛው በግድ ካላገባሽ እቆራርጥሻለሁ ብሎ ያስፈራራኝ ሰው የለ... ሁሉንም ያደረኩት በራሴ ፍቃድና ምርጫ ነው። እንደውም ቤተሠቦቼ በዚህ ሀሳብ እንዲስማሙ ለማሳመን ብዙ ነገር ቀባጥሬ ነበር...እና ታዲያ ?የቁርጡ ቀን ሲመጣ ምነውሳ...?ዋናው ጉዳይ ከእዬቤ እንዴት አድርጌ የምር እለያለሁ ?የሚለው ሀሳብ ነው እረፍት የነሳኝ....፡፡ እርግጥ አውቃለሁ ወደ ጋብቻው የገባሁበት ዋና አላማ ከእዬብ ለመራቅ ከአምላክ የተላከ ልዩና ረቂቅ ዘዴ አድርጌ በደፈናው ተቀብዬው ነበር እንጂ ዝርዝር ጉዳዬች ላይ በደንብ ያሰብኩባቸው አልነበረም። ይታያችሁ ባል ካገባው እኮ አብሮ ማደር ከዛም ያለፈ ነገር ማድረግ የግድ ነው ፡፡ በህልሜም ሆነ በእውኔ ከእዬብ ገላ ውጭ የወንድ ገላ ታስቦኝ በፍፁም አያውቅም።የሚገርመው እናትና አባቴን ጨምሮ የቤቱ ሰው ሁሉ በደስታ ሰክሮ ለድግሱ መሳካት ጠብ እርግፍ ሲል እዬቤ ግን ልክ እንደእኔ በተመሳሳይ ሁኔታ ድባቴ ውስጥ ገብቶ ነበር።አሳዘነኝ።እሱም እንደ እኔ ያፈቅረኝ ይሆን እንዴ?ለመጀመሪያ ጊዜ በአእምሮዬ የተሠነቀረ አስደሳች ጥርጣሬ ነበር ፡፡
ለማንኛውም የሰርጉ ቀን ደረሰ በተክሊል ስለምንጋባ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ለሊት ስምንት ሰዓት ነው ቤተክርስቲያን የሄድነው። ግን በተክሊል እንዴት ልንጋባ ወሰንን? እርግጥ ሀሳብን ቀድሞ ያቀረበው መስፋን ነው።ግን እኔም ያለምንም ማቅማማት ነበር እሺ ያልኩት ፡፡ለዚህም ምክንያቴ በዋናነት ሁለት ነው። አንደኛው በተክሊል መጋባት ጋብቻውን ጥብቅ ስለሚያደርገው ወለም ዘለም የሚለውን ልቤን ያቃናልኛል ወይም መስመር ያስገባልኛል ብዬ ስላመንኩ ነው።ሁለተኛው ብዙ የሠንበት ት/ቤት ጓደኞቼ በተክሊል ሲያገቡ ሚዜም ሆነ አጃቢ ሆኚ አይቼ ስለነበረ እኔም አንድ ቀን እንደዚህ አገባ ይሆን የሚል የተደበቀ ምኞት በውስጤ ስለነበረ ያንን ምኞቴን ለማሳካት ያገኘሁትን እድል ለመጠቀም ነበር።
ስርዓቱም ከቅዳሴው ጥዋት ሶስት ሰዓት ተጠናቀቀ።በሰንበት ት/ቤት መዘምራን የሠርግ መዝሙር በመታጀብ ወደ የቤታችን ሄድን።እንግዲህ ምሳ ሰዓት ላይ ሙሽራው ከሚዜዎቹና አጃቢዎቹ ጋር መጥተው እስኪወስድን የተወሰነ ለማረፍና ለመዘገጃጀት የሚሆን ጊዜ ይኖረናል ብዬ ነው።እቤት ከገባን በኃላ ትንሽ ለማረፍ ሞከርኩ እንቅልፍ ሊወስደኝ ግን አልቻለም፡፡ ተነሳሁና እየተኳኳሉና እየተቆነጃጅ ካሉት ሚዜዎቼ ጋር ተቀላቀልኩ።እኔም መዘገጃጀት ስላለብኝ ያሳምሩኝ ጀመር...፡፡ሁሉም ደስተኛ ይመስላል... የተከፈተ ጥርስ..የፈገገ ፊት...በማይክራፎን የተለቀቀ መዝሙር እኔ ግን ቅር እንዳለኝ ነው ።ከቤተ ክርስቲያን መልስ ጀምሮ እዬቤን አላየሁትም።የት ገባ?ከአሁኑ በጣም ነው የናፈቀኝ።እህቴን ጠራኋትና ጠየቅኳት..እንዳላየችው ነገረችኝ።ሌላ የምትሰራውን ስራ ሁሉ ትታ እሱን ፈልጋ እንድትጠራልኝ ጠየቅኳት...ሌላ ቀን ቢሆን የራስሽ ጉዳይ ነበር የምትለኝ።በእለቱ ግን ያው የቤቱ ንግስት ነኝና ጥያቄዬን በእሺታ ተቀብላ ልትፈልገው ወጣች።
15 ከሚሆኑ ደቂቃዎች በኃላ ይመስለኛል እየተጎተተ በግድ የፈገገ ግን ደግሞ የዳመነ ፊቱን ይዞ መጣ..ሴቶች የሞሉበትን ክፍል በራፍ ላይ ቆሞ አንገቱን ወደውስጥ አስግጎ ‹‹ሪች ፈለግሺኝ" ሲል ጠየቀ….ገና ድምፁ ጆሮዬ ከመድረሱ ሰውነቴ በጠቅላላ ነዘረኝ፡፡
‹‹አዎ ግባ››
‹‹ወዴት ልግባ..?››
‹‹ጥፋሬን ቀለም እየተቀባሁ ስለሆነ እኮ ነው..ግባ የማታውቀው ሰው የለም "ብዬ አደፋፈርኩት፡፡ገባና ወደእኔ ቀረበ..እንዲቀመጥ ኩርሲ ከጎኔ አስቀመጥኩለት እያቅማማ ተቀመጠ።እዛች ክፍል ውስጥ የተጠቀጠቁት ሴቶች ጆሮና አይን በጠቅላላ እኛ ላይ እንደሰፈረ አውቃለሁ። ቢሆንም ምርጫ የለኝም።ድምፄን ቀነስ አድርጌ በሹክሹክታ መጠን
"የት ጠፍተህ ነው? ናፈቅከኝ እኮ"አልኩት
"ደክሞኝ ተኝቼ ነበር"
"የት?"ይህንን ጥያቄ የጠየቅኩት የእኔና የእሱን የጋራ ክፍል አሁን እያተረማመሰነው ስለሆነ ብዬ ነው፡፡
"እቴቴ ክፍል"
"አይንህ ግን ምንም የተኛ ሰው አይን አይመስልም"
እንደዛ ያልኩት አይኑ በርበሬ ይመስላል እንደሚባለው ቀይ ሆኖ ስለደፈራረሰ ነው።
"ተኝቼ ነበር እኮ አልኩሽ...አሁን ለምን ፈለግሺኝ?"ቆጣ አለ፡፡
"አትቆጣኛ"
"አልተቆጣሁሽም"
"አብረኸን ትሄዳለህ አይደል?"
ደንግጦ"የት?"
ለእሱ መልስ ከመመለሴ በፊት ‹‹ተነሡ ተነሱ ሰርገኛው ደረሰ ተዘጋጅ ..››የሚል የማንቂያ ድምፅ ከውጭ ተሰማ…ትርምስምስ ተፈጠረ... የእሱን አደነጋገጥ እስከዛሬም በፊቴ ላይ አለ።በርግጎ ተነስቶ ፊቴ ተገተረ...እኔም ተነስቼ ቆምኩ።ተጠመጠምኩበት..ጭምቅ አድርጎ አቀፈኝ።እንባዬን ዘረገፍኩት እሱም ተንሰቅስቆ ማልቀስ ጀመረ።ሊያላቅቁን መሀላችን ገቡ።
‹‹አረ ቆርበሽ እንዴት ታለቅሺያለሽ?››
"አገባች እንጂ አልሞተች… የምን ሟርት ነው?።››
"አረ ተው ነውር ነው።››
ሁሉም የመሰለውን ተንጣጣ...አላቀቁን ።እዬቤ ተስፈንጥሮ ክፍሉን ለቆ ተፈተለከ።ከፋኝ ።በጣም ከፋኝ።ፈፅሞ ጥሎኝ እንዲሄድ አልፈለኩም ነበር።እጥፍጥፍ አድርጌ ጡቶቼ መሀከል ከትቼ በየሄድኩበት ይዤው ብሄድ ደስተኛ ነበርኩ።..የምሳ ፕሮግራሙ ሲካሄድም ሆነ እኛ ቤት የነበረው ዝግጅት ተጠናቆ ከእኛ ቤት ወጥተን ስንሄድ አይኔ ቢንከራተትም እዬቤን ዳግመኛ ሳላየው ነበር የእናትና አባቴን ቤት ለዘላለም በሚመስል መንገድ ለቅቄ በቅርብ ከተዋወቅኩት እና በቅጡ እንኳን ያለመድኩትን ሰው ተከትዬ የሄድኩት።
ሙሽራው ሙሽሪት..እንኳን ደስ ያላችሁ
የአብርሀም የሳራ-ይሁን ጋብቻችሁ።
እንደዛ እንደዛ እያለ ሰርጉ ተጠናቀቀ ..መሸ ጫጉላ ቤት ገባን ..እግዚያብሄር ይመስገን ፡፡ በተክሊል ስለተጋባንና በእለቱም ስለቆረብኩ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድም ነበርና አንድ አልጋ ላይ ብንተኛም ሰውነታችንን እንኳን ሳናነካካ ተራርቀን ተኛን ፡፡የሁለት ቀን የተጠራቀመ እንቅልፍ ስለነበረብኝ የት እንዳደርኩ አላውቅም ነበረ ።የሚገርመው ጥዋት እንደነቃሁ በእጆቼ የሞጨሞጩ አይኖቼን እያሻሸው"እዬብ ነጋ እንዴ?"ብዬ ነበር ጠየቅኩት ።ደግነቱ ክፍል ውስጥ ማንም ስላልነበረ የሰማኝ ሰው አልነበረም። እንደምንም አልጋዬን ለቅቄ በመውረድ ልብሴን እየለበሰኩ ሳለ በሩ ተከፈተና መስፍኔ ገባ፡
"እንዴ ተነሳሽ እንዴ?"ዝም አልኩት።
"ምነው አመመሽ እንዴ?"አለኝ ወደእኔ እየተጠጋ።
ጭራሽ እየታገልኩት የነበረውን ስሜቴን ነቅንቆ አደፈራረሠው...እንባዬን ዘረገፍኩት።
"እንዴ ምነው?ምን ተፈጠረ?"
"እዬቤ"
"እዬቤ ምን ሆነ?››

👍76❤8🥰1😢1
"ናፈቀኝ"አሁን ሳስበው እንደዚህ ማለቴን ማመን ይከብደኛል።ሰው እንዴት እናቱ ሳትናፍቀው..አባቱ ሳይናፍቀው ..እህቶቹ ሳይናፍቁት የአክስቱ ልጅ ይናፍቀዋል..መስፍኔ ነገር የሚበላ ሰው ቢሆን ወዲያውኑ ምን ነበር ሊያስብ የሚችለው?።እሱ ግን አባበለኝ... መጥቶ እንዲያየኝ መልእክት እንደሚልክበት ቃል ገባልኝ ..በዛ ተደስቼ ለመጀመሪያ ጊዜ ጉንጩን ሳምኩት...ደስ አለው።
ቀኑን እንዲህም እንዳም እያለ አልፎ ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ ሆነ። ድንኳኑ በቅርብ ሰዎችና በመስፍኔ ቤተዘመድ እና በጋራ ጓደኞቻችን ተሞልቷል።እኛ ከሚዜዎቻችን እና ከነፍስ አባታችን ጋር መድረኩ ላይ በግዙፍ ጠረጳዛ ዙሪያ ከበን በደመቀ ጫወታ አድምቀነዎል።ይበላል ይጠጣል...ይሳቃል ። እኔ ወሰድ መለስ እያደረገኝ ነው .፡፡.ለሆነ ሀያ ሰላሳ ደቂቃዎች ጋል ባለ ስሜት በጫወታው እሳተፍና ድንገት ሁሉን ነገር ጣጥዬ በድኔን እዛው ጎልቼ ወደወላጆቼ ቤት በራለሁ...
ክፍሌ ትዝ ይለኛል ፤እዬቤ ይናፍቀኛል።በዚህ የተቀባዠረ ስሜት ላይ እያለሁ ድንገት እኛ ባለንበት በጎን በኩል ድንኳኑ ገለጥ ሲደረግ አየሁ "የትኛው እብድ ነው የተንቦረቀቀ በር ከፊት ለፊት እያለለት ባልተገባ ቦታ ለመግባት የሚታገል...? ሰርስሮ አንገቱን ብቅ ሲያደርግ ግን ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለች።እዬቤ ነው...የእኔ ማር...
"እዬቤ"
ድንኳን ውስጥ ያሉ አይኖች ሁሉ እሱ ላይ ተሰኩ ..ሙሉ በሙሉ ወደ ድንኳኑ ገባ።በአብዛኛው ስለሚያውቁት በሞቀ ሰላምታ ነው የተቀበሉት.፡ከእኔ ጎን ተቀምጣ የነበረችው ሚዜዬ መቀመጫውን ለቀቀችለት ..ከጎኔ ተቀመጠ..በአንድ ቀን በጣም ከስቶ ታየኝ..በፈገግታ ለማውራትና በሳቅ ለመድመቅ ይጥራል ..ግን ውስጡ ሀዘን እንደተጠራቀመና የተተራመሰ ስሜት ላይ እንደሆነ በቀላሉ ማወቅ ችያለሁ.. ይሄ ሁሉ የእኔ ጥፋት ነው...እዛ ሁሉ ሰው መሀል እንባዬን ለቀቅኩት፡፡ የድንኳን ሁሉ ድባብ ተቀየረ...በቀኜ ያተቀመጠው መስፍን እና በግራዬ የተቀመጠው እዬቤ ተከሻዬን እየዳበሱ ጉንጬን እያበሱ ያባብሉኝ ጀመር...(ግን ቆይ በግራዬ መቀመጥ የነበረበት ማን ነበር?።)..መጨረሻም በጓደኞቼ ውትወታና በቄሱ ግዝት እንደምንም ተረጋጋሁ።እዬቤም ብዙም ሳይቆይ እንዳመጣጡ ሹልክ ብሎ ሄደ... ስለመጣና ስላየሁት በጣም ብደሰትም ተመልሷ ሲሄድ ግን ሀሉን ነገር ጣጥለሽ ተከትለሽው ሂጂ የሚል መጥፎ ስሜት ነበር የተፈታተነኝ።እራሴን አመመኝ ...መቀመጥ ሁሉ ነው ያቃተኝ።ሁለት ሰዓት ሳይሞላ ወደመኝተ ቤቴ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ፡፡መስፍኔም ቆያይቶ ቢመጣም ሊነካካኝ ሳይሞክር ርቀቱን ጠብቆ ለሁለተኛ ቀን አደብ ገዝቶ ተኛ፡፡

👍55❤8👏2
#እህቴ_በባትሆኚ_አገባ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል። ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ... የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር እስከእርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች እንሆናለን ።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል.. ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር በቃላት ልውውጥ እና በአይን መሠራረቅ ላያልፍ ይችላል።ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቆረጥ ይችላል ወይም እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ "የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ የለንም?።ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ አልቆ ብቻ አይደለም...አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው ጉዞቸውን በተለያየ ጎዳና ይቀጥላሉ።ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።
እንዲህ ስለፍቅር የምፈላሰፈው ከጄኔራሏ ጋር ወደ ቤቷ እየሄድኩ ባለሁበት ጊዜ ነው፡፡በራሷ መኪና ሰፈር ድረስ መጥታ ነው የወሰደችኝ፡፡ …ከ20 ደቂቃ በኃላ ፍፀም ያልጠበቅኩት ሰፈር ይዛኝ ገባች…፡፡አደነጋገጤን አትጠይቁኝ፡፡ይሄነው ቤቴ ብላ የመኪናውን አፍንጫ ወደአንድ ቢላ ቤት በራፍ አዙራ በማስጠጋት የመኪናዋን ጡሩንባ አስጮኸች፡፡
እኔ በራፉ ከመከፈቱ በፊት የመኪናውን በራፍ ከፍቼ ወረድኩና ፊቴና ወደማዶ አዙሬ ፈዝዤ ቆምኩ፡፡.ይሄ እንዴት አጋጣሚ ሊሆን ይችላል..?ከጄኔራሏ ቤት ፊት ለፊት የሚታየው የድሮ ስሪት ቢላ ቤት እትብቴ የተቀበረበት ቤት ነው.. የወላጆቼ ላብ ጉልበት የፈሰበት ጥሪት ሀብታቸው ነው፡፡እዚህ ቤት ውስጥ ነው ደግሰው የተጋቡት፤እዚህ ቤት ውስጥ ነው ተፋቅረው ኖረው ልጅ የወለዱት፤ ከእዚህ ግቢ ውስጥ ነው እሬሳቸው ወጥቶ የተቀበረው….፡፡የዚህ ቤት ወራሽ አሁን እኔ ነኝ፡፡ግን በሞግዚትነት ስታስተዳድረው የነበረችው እቴቴ ማለት አክስቴ ስለነበረች አሁንም በእሷ እጅ እንዳለ ነው፡፡የእሷን አይን ለማየት ድፍረት በማጣቴ ምክንያት ይሄንን ንብረቴን መረከብ አልቻልኩም፡፡በአሁኑ የአዲስአባ ገበያ ባዶ መሬቱ ብቻ ቢያንስ 10 ሚሊዬን ብር ያወጣል.፤አቤቱ ሲጨመርበት ገምቱት..አዎ አሁን እኔ ባልጠቀምበትም ወደፊት ለልጄ ይሆናል ስል ተፅናናሁ፡፡
‹ኸረ ግባ በራፉ ተከፍቷል…ምንድነው እንዲህ ያፈዘዘህ..?››
‹‹እ እሺ ›ብዬ ከደነዘዝኩበት እንደመባነን አልኩና ወደውስጥ ገባሁ፡፡
እሷም መኪናዋን ወደግቢው ውስጥ አስገብታ አቆመችና ወረደች፡፡ለዘበኛው ሰላምታ ሰጠችውና ወደ ውስጥ ገባን ፡፡ግቢው ማህል ላይ እድሜ ጠገብ ትልቅ ቢላ ቤት ያለ ሲሆን ወደ አንድ ጥግ ደግሞ በግምት ሶስት ወይም አራት ክፍል ያለው አዲስ ህንፃ ይታያል…ወደ አዲሱ ህንፃ በረንዳ ላይ ሁለት ህፃናት ይጫወታሉ…
.‹‹ያንን አከራይቼው ነው››፡፡ብላ ወደ አሮጌው ቤት ይዛኝ ገባች፡፡
የድሮ መኳንንት መኖሪያ የመሰለ ባለብዙ ክፍል ቤት ነው፡፡ሙሉ ቤቱ የባለሞያ ጥበብ ያረፈበት ባለግርማ ሞገስ ሲሆን በጥንታዊና ዘመናዊ እቃዎች ስብጥር ተሞልቷል፡፡ለምሳሌ ከወደቀኝ ኮርነር አካባቢ ዘመናዊ የሆነ ባለነጭ ልባስ ሶፋ ሲታይ፤ ከእሱ ፊት ለፊት ፍፅም ባህላዊና ከጠፍርና ከእንጨት የተሰራ ልዩ መቀመጫዎች ይታያሉ፡፡ብቻ ቤቱ መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚዬም ነው የሚመስለው፡፡
‹‹ደህና አደራችሁ?››ብዬ ገባሁ
‹‹ቁልፍ ከፍቼ እየገባሁ እያየህ ደህና አደራችሁ ትላለህ እንዴ?፡፡››
‹‹ምን ላድርግ ይሄንን የሚያህል ግዙፍ ቤት ሰው አልባ አይሆንም ብዬ ነዋ››
‹‹በጊዜውማ ልጇች ትላለህ የልጅ ልጆች ሲተረማመሱበት ነበር.. ቁጭ በል
ቁጭ አልኩ‹አሁንስ?››
‹አሁን ግማሹ የራሱን ቤት እየመሰረተ ወጣ…ሌላው አውሮፓ..የተቀረው አሜሪካ ገብቷል…እኔና ቤቴ ግን ይሄው አለን››
‹‹ወላጆችሽስ?.››
‹›አባቴ ሞቷል ፤ እናቴ ትንሽ የጤና እክል ስላለባት አሜሪካ እህቶቼ ጋር ነው የምትኖረው….መጣሁ ዘና በል…››ብላኝ ወደኪችን መሰለኝ ገባች፡፡
‹‹ለዚህ ቤት አዲስነት አልተሰማኝም..ምንድነው ፊልም ተሰርቶበት እዛ ላይ አይቼው ይሆን እንዴ…?.››ሪሞት አነሳሁና ፊት ለፊት ያለውን ቴሊቭዝን ከፈትኩ..ጄኔራሏ ከነማዕረጎ የተነሳችው ፎቶ በትልቁ ፊተ ለፊት ግድግዳ ላይ ገጭ ብሏል፡፡ በሙሉ አይን ማየት ፈራሁና አንገቴን አቀረቀርኩ…፡፡የሙሉ ቤተሰቡ ፎቶ እዚህና እዛ በተናጠልና በጋራ የተነሱት ቤቱን ሞልቶታል፡፡ሲታዩ የደላቸው ቤተሰብ መሆናቸው ያስታውቃል፡፡ድንገት የተቀመጥኩበት ጠረጴዛ ስር የፎቶ አልበም አየሁ፡፡ መቼስ አልበም ፊት ለፊት እንግዳ ሲመጣ የሚቀመጥበት ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጠው…የመጣው ሁሉ እንዲያየው ነው ብዬ አወጣሁና ማየት ጀመርኩ…፡፡አብዛኛውን ስለማላውቃቸው ብዙም ስሜት አይሰጠኝም፡፡ ቤዛወርቅ ያለችበትን የህፃንነቷን ቲኔጀር ሆና የተነሳችው ….የሚገርመው ከልጅነቷም ስፖርተኛና ተቦቃሽ ነገር ነች..እንዴ ምንድነው..?ይሄ ፎቶ እዚህ ምን ይሰራል…..?ፎቶውን እንደያዝኩ ከመቀመጫዬ ተነሳውና ወደኪችን ተንደረደርኩ፡፡
‹‹…ቤዝ.ቤ..ዝ….››እያለከለኩ ቅድም ስትገባ ወደያኋት ክፍል ገባሁ
‹‹ምነው ምን ተፈጠረ ..?ቢላዋ በእጇ እንደያዘች ጥሪዬን ሰምታ ስትወጣ በራፍ ላይ ተገጣጠምን …..አልበሙን ወደ እሷ ዘርግቼ‹‹ይህቺ ማነች…?ይህቺኛዋስ?›
‹‹ጤና ትባላለች…በሚያሳዝን ሁኔታ አሁን በህይወት የለችም…..?ምነው ከሰው ጋር ተመሳሰለችብህ እንዴ?››
‹ጤናዬ ማለት? ጤናዬ አስረስ…የበሪሶ አያና ሚስት፡፡››
‹‹አዎ ጋሼ በሪሶ..የት ነው የምታውቃቸው….?››በገረሜታ ጠየቀችኝ፡፡
ፊቴን አዞርኩና ወደሳሎን ተመለስኩ…ሶፋው ላይ ዝርፍጥ አልኩና ጭንቅላቴን ያዝኩ፡፡
ቤዛ ሁሉ ነገር ግራ ገባትና ከኃላዬ ተከትላኝ መጣች ‹‹ቆይ ቆይ እነሱ እኮ ከሞቱ ቢያንስ 20 አመታት አልፏቸዋል….ቅድም ስንመጣ ከመኪና ወርደህ እቤታቸው ላይ ስታፈጥ ነገሩ ምድነው ብዬ ግራ ተጋበቼ ነበር››
‹‹ለመሆኑ አንቺ ታስታውሺያቸዋለሽ…?››
‹‹አዎ ሲሞቱ የደረስኩ ወጣትና 12ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ ሁሉን ነገር ነበር የማስታውሰው…ቤተሰብ ነበርን…አንድ ልጅ ነበራቸው..የሚያምር ወንድ ልጅ… ክርስትና ያነሳው አባቴ ነበር.አበልጆች ነበርን..?አይ እዬብ ይሄኔ አድጎ ትልቅ ሰው ሆኗል….ስሙ እዬብ ነበር…፡፡››
‹አዎ ስሜ እዬብ ነው፡፡››
‹‹ምን ?አንተ…!!!እኔ አላምንም..፡፡እዬቤ ነህ…፡፡ቆይ ቆይ…. ››አልበሙን ነጠቀችና ገለጥ ገለጥ አድርጋ እኔ ያለሁበትን ፎቶዎች አወጠች…፡፡ እሷ አቅፋኝ የተነሳሁት..አባቷ ታቅፈውኝ የተነሳሁት..አራት የሚሆኑ ፎቶዎችን አሳየችኝ….ከዛ በኃላ ቁርሱም ተረሳ.፡፡
✨ይቀጥላል ✨

👍70😱9❤7😁5
#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
፡
፡
#ክፍል_አስር
ሽማግሌዎች ከዘርሲዎች አለቃ ጎጆ ፊት ለፊት ቁርበት
ተነጥፎላቸው ሲያወሩ እንደቆዩ ኮቶ ቡና የያዘ ሾርቃ አደለቻቸው"
ካርለት ጎጆው ውስጥ ሆና በቀዳዳ ታያቸዋለች ዘግይታ የወጣችው የጨረቃ ብርሃን ምሽቱን ፍንትው አድርጋ አስውባዋለች ካርለት
በልጅነቷም ሆነ በአፍላ ወጣትነቷ ብዙ ስነ ግጥሞች ስለጨረቃ
ውበት፥ ስለጨረቃ ፍቅር: ስለጨረቃ ስደት ... ተፅፈው አንብባለች
የሰለጠነው ዓለም ግን ፀሐይን እንጂ የጨረቃን ውበት ራሱ በፈበረከው የኤሌክትሪክ ብርሃን ተነጥቋል የጨረቃ ውስጠ ሚስጥር ትዝታውም ተረስቷል ሐመር ላይ ግን ጨረቃ እንደ ጥንቱ ዘመን ሙሉ አቅም: ጥንካሬ ውበት
አላት
ሽማግሎች በጨረቃ ብርሃን ምረቃ ጀመሩ፤ ምኞታቸው
ፍላጎታቸው የጋራ ነው" ሐመሮች አምላካቸውን አያስቸግሩም አንዱ ጤንነት ሌላው ንዋይ ፍቅር . ... እየተመኘ አምላኩን የሚይዘው የሚጨብጠውን
እያሳጣ ግራ አያጋባውም
ሐመሮች ዝናብና ጤንነት
ሁሌም የሚለምኑት ሁለት ነገር ነው ውስን
ብቻ ዝናብ ካለ ሳር አለ ሣር ካለ ከብቶች አሉ ከብቶች ካሉ ይኖራሉ" ሐመር ላይ ቦርጫም ምኞት የለም
የህይወት ልዩነት እንዲኖር የሚፈልግ ወይንም የሚመኝ የለም በእኩልነት እንጂ በልጦ ለመኖር የሚያስብ የለም የቤቱ ቅርፅ አንድ መልክ የቤቱ ዕቃ አንድ አለባበሱ አንድ
ሁሉም አንድ መልክ አለው ሐመር ላይ የተለዬ ያፍራል እንጂ አይኮራም፤ በመለየቱ
ይወቀሳል እንጂ አይከበርም
ሽማግሎች ቡናቸውን እንዲህ ተመራርቀው ከጠጡ በኋላ ወደ
መደነሻው ገላጣ ሜዳ ሄዱ ከተሰባሰበው የመንደሯ ሰው አቅራቢያ ተይዞ የቆመው በሬ ጂራቱን እያጠማዘዘ: ወገቡን እየለመጠ፥አንገቱን እየቀበረ ለማምለጥ ቢሞክርም ቀንድና ቀንዱን፥ ጅራቱን
የያዙት ጎረምሶች ሊያንቀሳቅሱት አልቻሉም
ሽማግሎች ከመረቁና ደልቲን የአባቱን ደንብ በማክበሩ ፕስስ እያሉ ትንፋሻቸውን ካርከፈከፉበት በኋላ የአመጣውን የቅጣት
ከብት ጉሮሮ ከወገቡ ባወጣው ጩቤ ወጋው፤ ደሙ በሾርቃ ተጠራቅሞ
የተወጋውን ከብት ጎረምሶቹ ለቀቁትና ወድቆ ተፈራገጠ ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ ብልቱ እየወጣ ጥብሱ ተጀመረ የተዘጋጀው ከተበላ በኋላ ዳንሱ ቀጠለ ሽማግሎች ከጎረምሶችና
ልጃገረዶች ጋር ሲደንሱና ሲፎክሩ ቆይተው እኩለ ሌሊት አካባቢ
ተጠራርተው የዳንሱን ቦታ ለጎረምሶችና ልጃገረዶች ለቀው ሄዱ ልጃገረዶች በጨሌና ዛጎል የተዋበውን የፍየል ቆዳቸውን እያወናወኑ: አንባራቸውን እያፋጩ ፊታቸው ላይ የተቀቡት የአኖ ቀለም ከጨረቃዋ ብርሃን ጋር እንደ ከብቶች እያንፀባረቀ ሳቃቸው እንደ ከርሰ ምድር የእንፋሎት ውሃ ቡልቅ ፍልቅልቅ ሽቅብ ወደ ወንዶች ጆሮ እየፈሰሰ ጭፈራው ደመቀ
ጎረምሶች ረጋ ብሎ ሲፈስ የነበረውን ዳንስ ሲለውጡት
መአበሉን ሊያስነሱት ፍቅር
በጥቅማ ጥቅም የጠቦት ስብ ያልሆነበትን የፍቅር ገበያ እንዲደራ በአይነት ሰጦ ለመቀበል እንዲቻል
የቦዮን ጎዳና ሊከፍቱት
ዳንስ ሊለውጡት የወንድን ጭን ከሴት ጭን ጋር እያፏጩ የፍቅር
አረፋ ሊያስደፍቁት በማዕበሉ እየተወረወሩ
ነፍሳቸው የመጨረሻውን እርካታ ለቅፅበት ወደምታገኝበት ጫካ
ለመግባት የሚያስችላቸውን ቅላፄ ጀመሩት።
… አንች ከርታታ ከልቡ የሚያስተናግድሽ በአልኮል ፈረስ ሳይጋልብ በጥቅም
ዓይኑ ሳይታወር በምኞት ህሊናው ሳይበሰብስ
በመምሰል ቀሳፊ በሽታ ሳይጠመድ፥ በራስ መተማመኑን አኝኮ
ሳይውጥ ደስታ ሆይ! ከልቡ የሚቀበልሽ ስላለሽ ደስ ይበልሽ' እግዚኦ! በስንቱ አገር: በስንቱ ሰው ሰራሽ አበባ ለማስጌጥ በተሞከረ
ውብ ስፍራ' እየተጠራሽ ዝክር ጠይቀሽ አዝነሽ ተመለሽ! እግዚኦ!
ስንቱ በውሸት ሊያገኝሽ ተንጠራራ አንች ምስኪን ከርታታ ክብርት ደስታ ሆይ! ደስ ይበልሽ እግዚኦ! ... የሚል የመላእክት ማህሌተ
ቡራኬ በዳንሱ አካባቢ
ተሰማት ካርለት
ከርከር ከርከር ዳሌ ወዝወዝ ወገብና አንገት ሰበቅ
ሰበቅ ... እጥፍ እጥፍ፥ ዘርጋ ዘርጋ ዳሌ ወዝወዝ: ሣቅ ሣቅ ሆኖ አሀሀ-ሎሜ!
መባል ተጀመረ ተሟሟቀ የወንዶችና የልጃገረዶች
ሰውነት ልጃገረዶች የሚፈልጉትን ወንድ
እየተወረወሩ እየሄዱ ጋብዘው ወዲያ ወዲህ ሽርር ሽርር … እያሉ
ሲጠብቁ የተመረጡት ወንዶች ወገብ ለወገብ ከጓደኞቻቸው ጋር
ከተያያዙበት እየተላቀቁ እንደ ጎራዴ ምዝዝ: መሬቷን ድልቅ፥ ሸብሸብ ደሞ ዝልል
እያሉ ወደ ጋባዦቻቸው ተጠጉና ወገብ ለወገብ እየተያያዙ ገቡ ባልጩቱ
ተጠልፎ እንደ ኤሌክትሪክ ገመድ ጫፍ ተገናኘ ሞገዱ ተለቀቀ የጡት ጫፍ ሊወርድ እንደተቃረበ ጀት ጎማ ከተጣጠፈበት እየተዘረጋጋ ቆመ ተሳሳለ ቢላዋና ሞረዱ ስለቱ የፍቅር ጮማውን ቆርጦ ወደ የአፋቸው አስጠጋው አላመጡት: አደቀቁት አልመው ዋጡት ያን ምርጥ የሐመር ሰንጋ የፍቅር ጮማ ልብ ቦታውን
እየለቀቀች ዘለለች ህሊና ትዕዛዝ ሰጠ ደስታ ሆይ አንቺ ከርታታ ምስኪን ሆይ ደስ ይበልሽ! ማህሌቱ አላቆመም ካርለት
ይህን ሰማያዊና ምድራዊ የተጣጣመ ትርዒት ፈዛ ስትመለከት ለረጅም ጊዜ ቆየች ኮቶ ከኋላዋ መጥታ ባትነካትማ የምትነቃ
አትመስልም ቅዠት የሌለበት ህልም ... ፍርሃት የሌለበት ደስታ።
"ኮቶ ልትደንሽ ወደ ዳንሱ ገብተሽ ከኋላዬ የምትመጭው ከየት
ነው?" አለቻት ካርለት ዐይን ዐይኖችዋን እያየች
"ይእ! ጥጆችን ሳራክብ እሁ አለፉኝ ሲራከቡ!" ብላ
የካርለትን ትከሻ ተደገፈች "ነው!" ካርለት ገባት የቆየችበት የኮቶ ሰውነት ዛል ብሏል ሰውነቷ እንደ እንቦሳ ሰውነት ያረግዳል
የእርካታ ትንፋሽዋ በመላ ሰውነቷ ይትጎለጎላል
"ኮቶ ደልቲን ልጋብዘው?"
"ይእ! ኧረ ተይ ከእጮኛ ጋርማ አይደነስም እሱ ከፈለገ መጥቶ ሲጠራሽ ባይሆን አጠገቡ ትሄጃለሽ ከዚያ እያወጋችሁ ቀስ
በቀስ ከዳንሱ ቦታ ፈንጠር፥ ፈንጠር ... እያላችሁ በመጨረሻ ጨረቃዋን እፍ' ብላችሁ አሹፋችሁባት ትጠፋላችሁ እሷም ቀልድ
ስለምትወድ እየሳቀች ትከተላችኋለች ካለ ጨረቃ የወንድና ልጃገረድን ፍቅር ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ የሚያውቀው
የለም!"
"የመንደራችን ጎረምሶች ግን ተእንግዲህ ትቀመስ ማለታቸው አይቀርም የአባትሽ ዘመዶች (እንደናሶችም) እንደ እኛ ይገርፉሻል"በይ እቴ ወሬው ይብቃ እንጫወት" ብላ በቆሙበት መወዛወዝ
ጀመሩ"
ደልቲ ከዳንሱ ወጥቶ ካርለት አባት ብላ የመረጠችውን ዘመድ
ረምሳ ጠራውና በርኮታው ላይ ተቀመጠ" ጎረምሳው
ጥሪውን ተቀብሎ አጠገቡ ሄዶ ቁጭ አለ
"ሚሶ!" አለው ደልቲ
"ሚሶ!" አለ ጎረምሳው"
"...ይህችን ልጅ የአባት ወጓን አስተምሯት እንጂ?"
"እእ! - ካርለቴን ነው?"
"አዎ! ከብትና ፍዬል ትጠብቅ ቀፎም ትስቀል ዳንሱ ላይም ግረፏት እንጂ. አሁን ታልሰባች በኋላ እኔ ስንቱን ላርማት ነው?"
"እእ! እሽ ኧረ እኛም ስንመክርበት ነበር እንዳልኸውስ ተሌሎች እህቶቻችን ነጥለን ለምን እናያታለን! ትንሽ
እሚያሰቃጥጠው እንኳን ተገርፋ ሌሎቹ ሲገረፉ ስታይ ንዳድ
እንደያዘው ሰው እየተንቀጠቀጠች መግቢያው ነው የሚጠፋት,,
"አይቻታለሁ ባትለምደው ነው! ግዴለም አስለምዷት
ተዚያ እሷው ያምራታል እሷ እኮ ህፃን ማለት ናት ህፃንን
ብትመታው ያለቅሳል
ሴቷ ግን እድሜ ለአባቷ
ለመንደሯ ጎረምሶች እያደገች ስትሄድ እያየች ትማርና በኋላ በተግባር ደሞ ቀስ በቀስ ትለምዳለች, ትፈራለች ብላችሁ አትተዋት
የኖረችበትን መገመቱ ይከብዳል! እነሱ በድለዋታልና እኛም ግን
ደግመን ልንበድላት አይገባም የዱላን ፍቅር አሳይዋት እሷም ተተወሰነ ጊዜ በኋላ ፍርሃቱ ይወጣላታል!"
"እእ!- እሽ ዛሬስ እኛም አስበናታል ና እንጂ አንተስ
ተጫዋት?"

👍29❤2😢2
አለሁ የት እሄዳለሁ አዳሬ ተዚሁ ነው" ብሎ ደልቲ
ከበርኮታው ላይ ተነሳ ጎረምሳው ደግሞ የባራዛ አርጩሜውን ወደ
ደበቁበት ጉቶ ሄዶ ሶስት ለበቆችን አነሳ ደልቲም ከወንዶች ግማሽ ክብ ሰልፍ ገብቶ ወገብ ለወገብ ተያያዘ
.
💫ይቀጥላል💫

👍15👏2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
ከጋሽ ሙሉ አለም ጋር ከተነጋገርን በኃላ አዎጪ ስራ ለመምረጥ ያልበረበርኩት ዌብ ሳይት ያላማከርኩት የቢዝነስ ሰው...በሰበብ አስባብ ያልጎበኘሁት የንግድ ተቋም የለም።ምንም ግን ልቤን እርግጥ አድርጎ ሞልቶ በቃ ይሄንን ነው ብዬ እንድወስን የሚያደርገኝ ስራ በቀላሉ ማግኘት አልቻልኩም። ሰው ደግሞ አላውቅም የሚለው ነገር የለውም፡፡ ትንሽ መንገድ ካሳዪት በማንኛውም ነገር ከኤክስፐርት በልጦ ይቦተረፈዋል።
"እኔነኝ ያለ አሪፍ ቡቲክ ብትከፍት በጣም ትርፋማ ነው የምትሆነው...በተለይ የሴቶች ካረከው ትርፍህ ባለሁለት ስለት ነው የሚሆነው..እነዚህ የሀብታም ቺኮችን ገንዘባቸውንም ውበታቸውንም እጥብ ነው የምታደርገው...››እንደዚህ የመከረኝ ጎረምሳ ነጋዴ እንዳይመስላቹሁ የአምስት ልጆች አባትና ባለሁለት ቀለም ፀጉር ባለቤት የሆነ አዛውንት ነው።
"ለምን ማሳጅ ቤት አትከፍትም›› ያለኝ ሰውም አለ...
"በአሁኑ ጊዜ አዎጪው ስራ ድለላ ነው፡፡ ፍቃድ አውጣና የውጭ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ብትሆን አሪፍ ትሸቅላለህ..በጎንም ቤት መደለል ፤:መኪና መደለል ፤ሴት መደለል አይነት አዋጪ ስራዎችን ትሰራለህ
የሪል እስቴትና የባንክ ቤት ኤጀንቶችም "ከሰርኩ አልከሰርኩ እያልክ ምን አጨናነቀህ፡፡ በገንዘብህ አክሲዬን ግዛበት.፡፡ አንተ ዘና ብለህ በየአመቱ በምትዝቀው የትርፍ ድርሻ ብቻ ዘና ብለህ መኖሮ ነው››ብለውኛል
"በአጠቃላይ በሰሞኑ ውጣ ውረዴ የተረዳሁት አንድ ነገር ቢኖር ከዚህ በፊት ስራ ለመጀመር ትልቁ መስፈርት መነሻ ካፒታል ማግኘት ብቻ ነበር የሚመስለኝ፤ለካ መጀመሪያ አውጥተን አውርደን ይሄንን ስራ በዚህ አይነት ሁኔታ እንሰራለን የሚል ቢያንስ መነሻ የሚሆን ሀሳብ በውስጣችን ከሌለን ገንዘቡ ቢኖር እንኳን ትልቅ እራስ ምታት ውስጥ ነው የምንወድቀው ?
ስዞር ውዬ ደክሞኝ ወደቤት ገባሁና አልጋዬ ላይ በቁሜ ወደቅኩበት ...ተንሳጠጠ፡፡
"ጎረምሳው ቀስ..."
"አያቴ...ደክሞኛል"
""የትኛውን ተራራ ወጥተህ ነው ይሄ ሁሉ ማለክለክ?"
"አረ ተራራ መውጣት ይሻላል...ሰው የሚሰራበት ገንዘብ ለማግኘት ይባክናል እኔ የምሰራው ስራ ማሰብ ና መወሰን ያቅተኝ።አረ ምን አይነት ቀሺም ነኝ?››
"እንኳንም አቃተህ"
"እንዴት አያቴ?"
"አየህ ተጨንቀህ ተጠበህ ያፈለቅከው ሀሳብ ጥልቀትም ውጤትም ይኖረዋል።"
"አይ አያቴ እስከአሁን ምንሞ የረባ ሀሳብ ላይ አልደረስኩም እኮ...የማማክረው ሰው ሁሉ ሺ ሀሳብ ነው የሚሰጠኝ...አንድ አሪፍ ነው ይሄን ስራ ጀምር ብሎኝ አሳምኖኝ ዞር ስል ሌላው ደግሞ ያንን ስራ ተሳስተህም ቢሆን እንዳትጀምረው አገርምድሩ የከሰረበት ስራ ነው ብሎ ኩም ያደርገኛል።
"እንደዛ ከሆነ ከማንም ምክር መጠየቅ አቁም.."
"ማለት?"
"ስለቢዝነስ መሠረታዊ ግንዛቤ ለማግኘት ይሄው በዚህ 15 ቀን ውስጥ የጠየቅካቸውና ያማከሩህ ሰዎች ከዩቲዩቨ እያወረድክ ያየሀቸው ቨዲዬዎች በቂ ናቸው"
"እና ምን ላድርግ?"
"እየሠማሀኝ አይደለም እንዴ ..?ምክር መጠየቅ አቁም እያልኩህ እኮ ነው"
"አያቴ ደግሞ… እርሷ እኮ ሌላ ሰው አይደሉም የቢዝነስ ፓርትነሬ ኗት"
"ቢሆንም ስራአስኪያጅና ፈላጭ ቆራጩ አንተ ነህ"
"አያቴ ደግሞ..እሺ የመጨረሻ ምክር ከእርሶ ልወሰድና ከዛ ያሉኝን አደርጋለሁ።››
"እንደዛ ከሆነ ሶስት ምክር ልስጥህ "
‹‹ደስ ይለኛል"
"1 አንተ የተሻለ ግንዛቤ ወይም እውቀት ባለህ የስራ ዘርፍ ብትሰማራ ተመራጭ ነው።ቀጥረህ የምታሠራው ስራ ቢሆን እንኳን ለመቆጣጠር የተወሰነ ግንዛቤና እውቀት ሲኖርህ ውጤታማ ይሆናል፡፡
2/የምትወደውና የምትደሰትበት...ትርጉም የሚሰጥህ ስራ ቢሆን የግድ ባይሆንም የተሻለ ነው"..ኢንጂነር ኮንትራክተር እንደሚሆነው...የህክምና ዶክተር ክሊኒክ እንደሚከፍተው ማለት ነው
3/ኪሳራ የሚባል ነገር ከአዕምሮህ አውጣ...ፍፅም ኪሳራ የሚባል ነገር በህይወት የለም ..ይህ የመጀመሪያ የቢዝነስ ስራህ ነው፤ አሁን የምትጀምረውን ስራ ለሁለት አመት ከሰራህ በኃላ ከስረህ ብትዘጋው ያጣሀው ገንዘብ ነው ግን ከፍተኛ ልምድ ታካብትበታለህ… ቀጣይ ስራ ሀ ብለህ ለመጀመር እንደአሁኑ ድንብርብርህ አይወጣም...በል አሁን ተኝተህ አስብ››
"እሺ አያቴ አመሰግናለሁ "
ይሄንን ከተነጋገርን ከአራት ቀን በኋላ የሚገርም አጋጣሚ ተከሰተ፡፡ አንድ አለማያ አብረን የተማርን የቢሾፍቱ ልጅ ነበር..ከዛ እንደወጣ ወላጆቹ የችግኝ ስራ ይሰሩ ስለነበር እሱም ተቀላቀላቸውና መስራት ጀመረ..ሞያው ስለሆነ በሁለት አመት የሚገርም ለውጥ አመጣ ፡በሶስተኛው አመት 2 ሺ ካሬ መሬት ተከራይቶ ...የተለያዩ የአበባ አይነቶች ፤ለግቢ ውበት ማስጌጫ ተክሎች፤ ለምግብ የሚሆኑ አትክልቶች መንጎ፤ፓፓያ ፤አቡካዶ በስፋት አምርቶ ማቅረብ ጀመረ…
የዘንድሮውን ምርትም ለገበያ ለማቅረብ ሁለት ወር ሲቀረው የውጭ እድል አገኘና ጠቅላላ ልማቱን ባለበት ለመሸጥ ገዢ በማፈላለግ ላይ እንደሆነ ሰማሁና ደወለኩለት ..፡፡እርግጥ ከአንድ ሰው ጋር ተነጋግሬና ተስማምቼ ነበር፤ ቢሆንም.እኔ ስራውን ለሚያውቅና ለማውቀው ሰው መሸጤ ነው በጣም የሚያስደስተኝ…የአትክልት የማልማት ስራ ልጅ ከማሳደግ ጋር የሚያመሳስል ነገር አለው…ዝም ብሎ ብር የማግኛ ስራ ብቻ አይደለም…የተቀዳደደ እና የተቦተራረፈውን የተፈጥሮ ልብስ በጥንቃቄ የመስፋትና የማደስ ፤ እፍረቷንም የመሸፈን ስራ ነው፡፡ ..ግን ትንሽ ተወደደብኝ ካላልክ.. እርግጥ ከሁለት ወር በኃላ ብሸጥ አገኘዎለሁ ካልኩት ብር ከግማሽ በላይ ቀንሼ ነው የምሸጠው አለኝ
"መጀመሪያ ልየው አልኩት፡፡በፈለከው ሰአት ቢሾፍቱ ናና ደውልልኝ አለኝ..ጊዜ ሳልፈጅ እየበረርኩ ሄድኩና አየሁት ..ከገመትኩት በላይ በጣም ማራኪና አስደማሚ ሆኖ አገኘሁት ...እሱም በቦታው ላይ ስራ ከሁለት አመት በፊት ሰራ ሲጀምር እንደዚህ አይስፋ እንጂ የተወሰነውን ባለበት ከሰው ገዝቶ እንዳስፍፍው አስረዳኝ ..በተቻለኝ መጠን ፎቶም ቪዲዬም አነሳሁ።አንዳንድ ብቻውን በመኪና ተጭኖ ሄዶ ሲተከል መለስተኛ ዛፍ የሚሆንና ከ10 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ በርከት ያሉ ዛፎች ያሉበት ነው። ዎጋውን የአምስት ወር ከተከፈለበት የመሬት ኪራይ ጋር 350 ሺ ብር አለኝ። ከሸሪኬ ጋር ተማክሬ በአንድ ቀን ውስጥ አሳውቅሀለሁ ብየው ወደአዲሳባዬ ተመለስኩ።
እቤት እንደደረስኩ .."አያቴ"
"አቤት መጣህ..የት ጠፍተህ ነበር?"
"የሆነ ቦታ ሄጄ ነበር፡፡ ቀላል እቃዎችን በምንቀባበልበት ስንጥቅ እጄን አሸልኬ""እንኩ ይቀበሉኝ"
"ምንድነው...?ሞባይልህን ምን ላድርገው?።››
"አሁን ትክክለኛ የምንሰራውን ስራ ያገኘው ይመስለኛል...እስኪ ቪዲዬውንም ፎቶዎችንም ይዩት"
"ከተቀበሉኝ በኃላ..ለ15 ደቂቃ ንግግር አልነበረም... ዝም ማለታቸው ያልጣማቸው ነገር ስለአለ ነው ብዬ ደነገጥኩ .. ፈራሁም።ምክንያቱም ስራውን በጣም ከልቤ ነው የፈለኩት.ደግሞም በሙሉ የራስ መተማመንና በዕውቀት የምሰራው ስራ ነው….ይሄ ግን ለእሷቸው ካልተገለፀላቸው የእኔ መሻት ብቻ ዋጋ የለውም፡
"ለዚህ እኮ ነው የምወድህ?"
"ምን አሉኝ አያቴ?"
"ውብ የሆነ ስራ መርጠሀል"
"ወደዱት..ልጁ ጓደኛዬ ነው ማለት አለማያ አብረን ነው የተማርነው ..አሜሪካ የመሄድ እድል ስላገኘ ባለበት ሊሸጠው ነው የፈለገው። ሌላ ሰው ሊገዛው ጠይቆታል እሱ ግን ሰውዬው የሰጠኝን ምትከፍለኝ ከሆነ ላንተነው መሸጥ የምፈልገው ብሎኛል››

👍73❤5👏1
"እና አንተ ምን አልክ?"
"እኔማ ከአያቴ ጋር ተማክሬ መልሱን እስከነገ እነግርሀለሁ ነው ያልኩት"
‹ስንት ነው የጠየቀህ?"
"ሁለት ሺ ካሬ ሜትር ነው፡፤ የመሬቱ የአምስት ወር ኪራይ ተከፍሎበታል ፡፡350 ሺ ብር ይላል"
"እና ነገ ድረስ ምን አስጠበቀህ ..ዛሬውኑ ንገረው"
"ምን ልበለው...?››
‹‹ነገ ብሩን ይዤልህ እመጣለሁ ..ውልና አስፈላጊ መረጃዎችን አዘጋጅተህ ጠብቀኝ በለው"
"እና ልንገዛው መሆኑ ነው"
‹‹"ይልቅ እዚህም ከዛ እያመጣህ የምታከፋፍልበት መቶ ወይም ሁለት መቶ ካሬ የምትሰፍ ቦታ ፈልግ...ከዛ እየመጣ እዚህ ቢሸጥ አሪፍ ይሆናል"
ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ዘለልኩ፤ ጨፈርኩ ‹...አያቴ በጣም ነው የምወዶት ...››
"ቤቱን አፈረስከው ..በል እንካ ስልክህን ..››
እየጨፈርኩ ወደስንጥቁ ሄድኩና ተቀበልኩ..ከስልኩ ጋር ወረቀት አለ‹‹
ምንድነው?›› ከፈትኩት ቼክ ነው"1 እና ስድስት ዜሮ ይታየኛል"
"ምንድነው አያቴ?"
"በል ሂድና ወደ ደብተርህ አዘዋውር፡፡ ከዛ እንደአስፈላጊነቱ እያወጣህ ለአስፈላጊው ነገር አውል...በቃ አሁን ስራ ተጀመረ እኮ›
አለቀስኩ ..ልክ ወላጆቼ ዛሬ እንደሞቱብኝና መርዶ እንደተረዳ ሰው ወለል ላይ ተዘርፍጬ አለቀስኩ... ሲደክመኝ ፊቴን ታጠብኩና ቼኬን ይዤ ወጣሁ... መንገድ ላይ ሆኜ ለልጁ ደወልኩለት....እንደተስማማሁና ነገ ስለምመጣ ተዘጋጅህ ጠብቀኝ አልኩት...፡፡ደስ አለው። እንዲህ በቀላሉ ስምምነት ላይ የምንደርስ እንዳልመሰለው ከሁኔታው ያስታውቅበታል..፡፡ባክህ ትንሽ ቀንስልኝ...እቺን ያህል ብር ጎደለችኝ እያልኩ የማስቸግረው መስሎት ነበር..ያው የባንክ ውጣ ውረድ አልፌ ብሩን ወደ ባንክ ደብተሬ አስገባሁ..ምንም የሚያስፈነጥዝ ነገር እየተሠማኝ አይደለም...ሸክሜ ነው የጨመረው..ትከሻዬ ነው በኃላፊነት የጎበጠው..
ቤዛ ወርቅ ጋር ደወልኩላት
"የት ነሽ?"
"ዝም ብዬ ልደታ አካባቢ ካፌ ቁጭ ብያለሁ"
"መኪና ከያዝሽ ስቴዲዬም ትመጫለሽ?"
"እችላለሁ ፡፡ ምነው ናፈቅኩህ እንዴ?"
"አዎ..ግን በጣም የተቀዣበረ ስሜት ላይ ነው ያለሁት ..ብዠ ብሎብኛል ፡፡ብቻዬን ስንገላወድ የሰው የመኪና ጎማ እንዳላበላሽ ስለፈራሁ ነው የደወልኩልሽ።
"ምነው አሞሀል እንዴ?"ደነገጠች
‹አይ ደህና ነኝ ግን ሰው ያስፈልገኛል"
"መጣሁ መጣሁ ባለህበት ሆነህ ጠብቀኝ"አለችና ስልኩን ዘጋችው፡፡
..ሰባት ወይሞ ስምንት ደቂቃ ነው ያስጠበቀችኝ፡፡ ስሬ መኪናዋን አቆመችና የገቢናውን በራፍ ከፈተችልኝ ...ገባሁ"ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳምን .
‹‹..አንተ ሠውነትህ ሁሉ ይግላል...አሞሀል ሀኪም ቤት ልውሰድህ...››
"አይ ህመም አይደለም"
"እና ምንድነው?"
"ድንጋጤ መሠለኝ"
"አልገባኝም"
የባንክ ደብተሬን ከኪሴ አወጣሁና ሰጠኋት፡፡

👍57🥰8❤7
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ልጄ ስልክ ደውላልኝ እያወራኋት ነው፡፡
‹‹አባዬ እንዴት ነህ?››
"አለው የእኔ ማር ትምህርት እንዴት ነው?።››
"ትምርት ጨርሰናል አላልኩህም..እሁድ የወላጆች በአል ነው..ካርድ ይሰጠናል።››
‹‹በእውነት ደስ ሲል.."
"አዎ !!ቲቸር ደግሞ ተሸላሚ ስለሆንሽ ወላጆችሽ እንዳይቀሩ አለችኝ...ለእቴቴ ስነግራት ‹ጎበዝ ልክ እንደአባትሽ ብሩህ ጭንቅላት ነው ያለሽ› አለችኝና አለቀሰች።"
እንባዬን መቆጣጠር ተሳነኝ...ያለፍቃዴ እየተንጠባጠበ ነው።
"አባዬ ምነው ዝም አልከኝ ?"
"ልጄ ደስ ብለኸኝ እኮ ነው ... እና ማነው አብሮሽ የሚሄደው...?››
"እቴቴና አክስቴ ትልቆ አብረንሽ እንሄዳለን ብለውኛል...ደግሞ እቴቴ ቆንጆ ቀሚስና ጫማ ገዝታልኛለች ..."
"አሪፍ ነው ...እናትሽ ጀግና ልጅ እንዳላት ሰምታለች?"
"አዎ ….በቀደም በእስካይ ፒ ስናወራ ነገርኳትና ..ከሀይስኩል በኃላ እዚህ አሜሪካ ነው ምትማሪው አለችኝ"
"እና ምን አልሻት ..?.ደስ አለሽ?"
"አይ አላለኝም..እኔ አባቴን ፈልጌ ሳላገኘው አንቺ ጋር መምጣት አልፈልግም .. ከፈለግሽ አንቺ ነይ አልኳት..."
ደንግጬ"እና ምን አለችሽ?"
"ከየት አባሽ ነው ፈልገሽ የምታገኚው...?በህይወት መኖሩን እራሱ እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚችል ሰው የለም ።"አለችኝ
እኔ ደግሞ‹‹ እኔ ልጅ ስለሆንኩ ይታወቀኛል በቅርቤ አለ...በጣም እንደሚወደኝም አውቃለሁ›› ስላት ተበሳጨችና ዘጋችብኝ።››
"አትቀየሚያት …እኔ ዝም ብያት ስለጠፋሁ እስከአሁን እንደተናደደችብኝ ነው።››
"አይ አውቃለሁ.. ከዛ እኮ ቆይታ ደውላ ይቅርታ ጠይቃኛለች ..ወደፊት እመጣና አብረን እንፈልገዋለን አለችኝ"
"የእውነትሽን ነው ..አራሷ እንደዛ አለቺሽ?"
"አዎ …ቃል ገብታልኛለች...ሁኔታዎችን አመቻችቼ ረጅም ፍቃድ ወስጄ እመጣና እንፈልገዋለን …በህይወት ካለ እናገኘዋለን..››አለችኝ፡፡
‹‹አና አንቺ ምን አልሻት?››
"እማዬ አንቺ ብቻ ነይ እንጂ ፈልገን አናገኘዎለን...በልቤ ይታወቀኛል።"አልኳት፡፡
‹‹ልጄ በጣም ነው የምኮራብሽ...እና ለሚመጣው አመት እንደአሁኑ ተሸላሚ ከሆንሽ እንደምንም ብዬ ከጎንሽ እገኛለሁ!››
"አባዬ ›
ወዬ ልጄ..?
‹‹ቻው እማዬ የላከችልኝን ፎቶዋን በቴሌግራም ልኬልሀለሁ.. ከናፈቀችህ ብዬ ነው"
‹‹እሺ የእኔ ልጅ አመሠግናለሁ..ሰሞኑን ደውይልኝ።››
"እም ጶ… የእኔ ውድ አባት እወድሀለሁ።"ስልኩ ተዘጋ፡፡ የእኔም አንደበት ተዘጋ..
."የፈጣሪ ያለህ!!እኔ ምን አይነት እድለኛ ሰው ነኝ...፡፡ምን አይነት እንደስሟ ተአምር የሆነች ልጅ ነው የሠጠኝ?።እሷ በመወለዷ ምክንያት ህይወቴ ተሠነካከለ ብዬ ለረጅም ጊዜ በማሰብ ሳማርር ቆይቼ ነበር ..፡፡ግን አሁን ለዚህች በረከት ለሆነች ልጅ ከዚህ በላይ መከራና ስቃይ ቢቀበሉላት የማታስቆጭ ልጅ ሆና በማግኘቴ ደስተኛ ሰው ሆኜያለሁ።
✨ይቀጥላል..✨

👍81❤17🥰11👏2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
ስበሳጭ ጀርባዬን ይበላኛል...የበላኝን ቦታ ለማከክ እጄን በወገቤ አዙሬ አሽከረክራለሁ፤ ግን ደግሞ አልደርስበትም.. በትከሻዬ በኩል አጠማዝዤ ሞክራለሁ፤ ትርፉ ድካም ነው። ከእከኬ ስቃይ እራሴን ለማስታገስ እገዛ መፈለጌ ያበሳጨኛል ደካማነቴንና ማድረግ የማልችላቸው ነገሮች ብዛት ያስጨንቀኛል...ጀርባዬን በላኝ እከኩልኝ ብዬ የሰው እገዛ ላለመጠየቅ ልብሴን አወልቅና ከሻካራ ግድግዳ ጋር እራሴን አፋትጋለሁ... ቢያቆስለኝም ያስተነፋሰኛል። ቢያንስ ገበናዬ ጠብቄያለሁ፡፡
አለመቻሌንም በሚስጥር በውስጤ አፍኜ ይዘዋለሁ፡፡አዎ አንዳንዴ ህይወት በዛ መጠን ትጨክንብኛለች በዛ መጠንም ታሰቃየኛለች፡፡
ዛሬ እርግጥ አልተበሳጨሁም ፤ግን ደግሞ በጣም ተጨንቄያለሁ፡፡ ጊዜው ጨለምለም ብሎል...አንድ ሰአት ከሩብ አካባቢ ነው›፡፡ ጀማሪ ማፊያ ይመስል ተጀባብኜ ወደሰፈር ተጠጋሁ...፡፡
እየተንቀጠቀጥኩ ነው ፡፡መቼስ ብርድ ብቻ አይመስለኝም እንደዚህ ውስጤ ገብቶ እያንቀጠቀጠኝ ያለው ።ኳስ እንጫወትበት የነበረው ሜዳ ባለአራት ፎቅ ህንፃ ተገማሽሮ ቆሞበታል። መቼስ ደፍረው ጠጠርና አሸዋ አምጥተው የሠፈሩ ሰው እያየ ሲሚንቶ አውርደው ፤ቀስበቀስ የገነቡት ሳይሆን ድንገት ከእለታት በአንድ ቀን ሁሉም የሰፈር ጎረምሳ ሆነ አሮጊት መተኛታቸውን አረጋግጠው ከሆነ ቦታ ጭነው መተው የተከተሉት ነው የሚመስለው። ወደቤታችን አየተቃረብኩ ስመጣ እግሬ እየተሳሰረ አስቸገረኝ፤ መራመድ ሁሉ አቃተኝ።
የውጩ ፍሬንች ዶር በአዲስ ከመቀየሩ ውጭ ቤታችን ከውጭ ያለው እይታ በፊት እንዳነበረ ነው።አለፍ ብዬ ሄድኩና ኮርነር ጋር ስደርስ ጨለማን ተገን አድርጌ ቆምኩ፡፡ ፊቴን ወደ በራፋችን አነጣጠርኩ
፡፡ ...ምንድነው የምጠብቀው..?.ማን እንዲወጣ ወይ ማን እንዲገባ ነው ? ልጄን አሁን የማየት እድል አለኝ ይሆን?በዚህ ጨለማ ምን ልትሰራ ትወጣለች...?ምን አልባት አክስቴ...አዎ ምንአልባት እሷን ነው ላይ የምችለው...፡፡ባላናግራትም ላያት ምኞቴ ነው፡፡ ሶስት ሰአት ድረስ እዛው በቆምኩበት ደንዝዤለሁ… የጨው ሀውልት እንደሆነችው ልክ እንደ ሎጥ ሚስት እኔም የበረዶ ሀውልት ከመሆኔ በፊት ወደ ሆቴሌ ልመለስ ወስኜ እግሬን ሳንቀሳቅስ ስልኬ ተንጫረረ ።በደነዘዘ እጄ አወጣሁና አየሁት ..የደዋዪን ማንነት ሳይ ከሰውነቴ ላይ በረዶ የሠራው ቅዝቃዜ በቅፅበት የረገፈ ይመስል ሙቀት ተሠማኝ ።ልጄ ነች።እንዴ አይታኝ ይሆን እንዴ? ዙሪያ ገባዬን ተገላምጬ ተመለከትኩ።ምንም የለም፡፡ስልኩን አነሳሁት
"ሄሎ የእኔ ልዕልት"
"አባዬ እንዴት ነህ..?ምን እየሠራህ ነው?"
"ስለአንቺ እያሰብኩ"
"ታድዬ" ታድዬ አባባሏ ልቤን ስንጥቅ አድርጎ ቃላቱ በስንጥቁ እየተንጠባጠበ ወደውስጤ ሲዘልቅ ተሠማኝ።
"ምን እየሠራሽ ነው...?ነገ ዝግጅት ስላለብሽ በጊዜ አትተኚም እንዴ?
"እነቴቴ እንደዛ ብለው አጠፋፍተው በጊዜ ተኙ።እኔ ግን ክፍሌ ከገባሁ ብኃላ ከመተኛቴ በፊት መስኮቴን ከፍቼ ጨረቃን ሳያት አንተ ትዝ አልከኝ...እና ደወልኩልህ"
ቀና ብዬ ምትላትን ጨረቃ አያየኋት… ግማሽ ቅርፅ፤ግማሽ ውበት፡፡
"ልጄ እውነትሽን ነው ..ታምራለች"
"ማን ነች የምታምረው አባዬ"
"ያልሻት ጨረቃ ነቻ..አይኖቼን አንጋጥጬ እያየኋት ነው… ግማሽ ብትሆንም ልክ እንደአንቺ ታምራለች"
"አባዬ ዛሬ ከጎኔ ሆነህ እቅፍ አድርጌህ ብተኛ ደስ ይለኝ ነበር"
"እንግዲያው መስኮቱን ክፍት አድርጊና ለጥ በይ ..እኔ በርሬ እመጣና በመስኮት ክፍልሽ ገብቼ እቅፍ አደርግሻለሁ..ግን ከተኛሽ በኃላ ነው የምመጣው"
"አባዬ ደስ የሚል ጫወታ ነው ...በቃ ሳልዘጋው ነው የምተኛው..ነገ ከዝግጅቱ በኃላ ደውልልሀለሁ.ወድሀለሁ።››
"እኔም ወድሻለሁ "ስልኩ ተዘጋ..
የእኔም ወደሆቴሌ የመመለስ አፒታይቴም አብሮ ተዘጋ፤
"ምን ላድርግ?"ከሀያ ደቂቃ በላይ ባለሁበት ቦታ ተገትሬ ማሰብ እንኳን አቅቶኝ ደንዝዤ ቆየሁ።ወደጓሮ ሄድኩ ..፡፡.ካልተቀየረች አንድ ወደጊቢ ዘሎ መግቢያ ምቹ ቦታ ነበረች..አዎ አገኘኋት።ዙሪያ ገባውን ዞር ዞር ብዬ ሰው አለመኖሩ አረጋገጥኩና እንደምንም ተንጠላጥዬ ዘልዬ ግቢውስጥ ገባሁ። ድሮ የሀይእስኩል ተማሪ እያለሁ በተለያየ ምክንያት ውጭ ሳመሽና በራፍ ሲዘጋብኝ በዚህ ዘዴ ነበር ወደ ውስጥ የምገባው..፡፡ይሄው የዛን ጊዜው ልምድ ለዛሬ ረዳኝ።
የውጭ መብራት ስለጠፍ ግቢው በፀጥታና በጭለማ ተውጧል።ኮቴዬን ሳላሰማ ቀስ ብዬ ወደልጄ ክፍል ማለት ወደእኔ የድሮ ክፍል አመራሁ...፡፡ወይ የእኔ ማር እንዳልኳት መስኮቱን ከፍታ ነው የተኛችው። እንደምንም ተንጠላጠልኩና መስኮቱ ላይ ወጣሁ ..ደግነቱ መስኮቱ አጠር ስለሚል በተለይ ከእኔ ቁመት አንፃር አልተቸገርኩም፡፡ በቀላሉ ወደላይ ወጣሁና እግሬን አሽከርክሬ ወደውስጥ ገባሁ፡፡ ልጄን እንዳላስደነግጣት ተጠንቅቄ ወደማብሪያ ማጥፊያው አመራሁ..፡፡አብዛኛውን ዕድሜዬን የኖርኩበት ቤት መሆኑ ነገሮች የት የት እንደሆኑ በቀላሉ ለመለየት ረድቶኛል ። መብራቱን አበራሁ።ልጄ እንዴት አድጋለች..ደግሞ አተኛኞ ልክ እንደናቷ ዝርግትግት ብላ ነው።በቅርቤ ያገኘኋት ኩርሲ መቀመጫ ወደአልጋዎ አስጠጋሁና ቁጭ አልኩ ...፡፡ጭንቅላቴን ሸፍኜበት የነበረውን ኮፍያ ከላዬ ላይ ገፍፌ ጣልኩት።አይኔ ላይ ሰክቼ የነበረውን መነፅር አወለቅኩና በአቅራቢዬ ያለ ትንሽ ጠረጰዛ ላይ አስቀመጥኩ። ሙሉ ትኩረቴን ወደልጄ ሰበሰብኩ።እጆቼን በእርጋታ ወደጭንቅላቷ ሰደድኩ .."ቀስ ብዬ ስዳብሳት አይኖቾን ገለጠች...፡፡ደነገጥኩና እጄን ሰበሰብኩ...እሪ ብላ የምትጮህ መሠሎኝ ፈራሁ። ምን ላድርግ...?ፈጠን ብዬ ዘልዬ እንደአመጣጤ ልውጣ እንዴ?ብዙ ነገር አስቤ አንድንም ሳላደርግ
"አባዬ....ህልም አይደለም አይደል..?"አለችኝ፡፡
"አይደለም የእኔ ማር ...››በተኛችበት ጉንጮቾን ሞጨሞጭኳት...እሷም እጇቾን በአንገቴ ዙሪያ ጠመጠመችና ግንባሬን፤ጉንጬን ፤አገጬን ምንም የቀራት ቦታ የለም...ሙሉ በሙሉ ንቁ ሆና አልጋዎ መካከል ቁጭ አለች።
"አባዬ እኔ እኮ እመጣለሁ ስትለኝ በህልሜ መስሎኝ ነው ቶሎ የተኛሁት።
"በጣም ስለናፈቅሺኝና ..ነገ የደረጃ ተማሪ ሆነሽ ልትሸለሚ ስለሆነ እኔ አባትሽ በጣም ኩራት ስለተሰማኝ እንዴ ተደብቄም ቢሆን በዚህ ቀን ልጄን ካላየኋት እኔ ምን አይነት አባት ነኝ ?ብዬ ነው በዚህ ለሊት ሹልክ ብዬ ክፍልሽ የተገኘሁት።
"አባቴ ውድድድ ነው የማደርግህ...አሁን አቅፍቅፍ ብለን እንተኛ"
"ግን አቴቴ ለሊት ልታይሽ ብትመጣስ?"
"አትመጣም ..ደግሞ እኮ ከውስጥ ተቀርቅሯል ..ብትመጣም ገና ስታንኳኳ ቶሎ ብለህ በመስኮት ትሄዳለህ"
"ምን አይነት ብልጥ ልጅ ነው ያለኝ"አልኩና ከላይ የለበስኩትን ጃኬት በማውለቅ ጠረጳዛ ላይ አኑሬ አልጋ ላይ ወጣሁ..ይሄ አልጋ የእኔና የእናትሽ እንደነበር ታውቂያለሽ?"
"አዎ …ለዛ እኮነው ክፍሌንም አልጋዬንም የምወደው"

👍56❤4
"ደረቴ ላይ ልጥፍ አለች..እናቷም እንዲህ መለጠፍ ትወድ ነበር"
////
ለካ እንቅልፍም እንደሁኔታው የተለያየ አይነት ጣዓም አለው እንዴ? ምን አይነት የጅል ጥያቄ ነው የምጠይቀው? በደንብ ይኖረዋል እንጂ!ለብቻ የገዛ ጉልበትን አቅፈው ሲተኙ ...ልባችንን ካጠፍችብን ውብ ልጅ ጋር ተቃቀቅፈን ስንተኛ...ከወንድ ጓደኛችን ጋር ስንተኛ...ከአባታችን ገዳይ ጋር ህይወት በእስር ቤት ውስጥ በአጋጣሚ አገናኝታን በጠባብ ክፍል አካል ለአካል እየተሻሸን ስንተኛ… ሁሉም እንቅልፍ የተለያየ አይነት ጣአምና አለው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ልክ እንደአሁኑ እኔ እንዳጋጠመኝ ከአብራካችሁ ተከፍላ ከወጣች የማንነታችሁ ክፍይ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ጉያችሁ ስር ሸጉጣችሁ ትንፋሿ ጆሮ ግንዳችሁን እያሞቀው መተኛት ስሜቱ ያለፅድቅ ስራ በእግዚያብሄር ምህረት የተነሳ ብቻ ገነት የመግባትን አይነት ነው።
ለብ ያለ በመንቃቃትና በመተኛት መሀል ያለ፤ ያለክንፍ የመንሳፈፍ ስሜት ያለው እንቅልፍ ላይ እያለው የበራፍ መንኳኳት ድምፅ ሰማሁ..፡፡.መጀመሪያ በህልሜ መስሎኝ ነበር ...ፈጥኜ ከእንቅልፌ ባንኜ ሳዳምጥ የእውነት ነው ..በር እየተንኳኳ ነው።

🥰30👍22❤11😁2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
"አባዬ ምንድነው?
"በሹክሹክታ ጠየቀችኝ
"እኔ እንጃ ..የውጭ በራፍ እየተንኳኳ ነው" ብዬ የተኛሁበትን አልጋ ለቅቄ ወረድኩ፡
‹‹ምነው ልትሄድ ነው እንዴ?"
"አይ ልነሳና ሁኔታውን እንይ"
"ምንድነው?
ማነው?"የእቴቴ ድምፅ ይሰማል
"ቀስ በይ.. ጫማ አላደረግሺም"እህቴ ነች
በዚህ ጊዜ ልጄ"አባዬ" አለችኝ በሹክሹክታ
"ወዬ ማሬ "በተመሳሳይ ቶን
"የውጩን በራፍ ሊከፍቱ ሲወጡ መስኮቱን ክፍት ሆኖ ያዩታል...ለምን ተከፈተ ብለው ወደእዚህ እንዳይመጡ ፈራሁ"
በበሳል አዕምሮዋ ተደምሜ ወደራሴ ሳብኩና ግንባሯን በመሳም ፈጠን ብዬ ወደ
መስኮቱ በመሄድ ዘጋሁት.፡፡አውልቄ ጠረጰዛ ላይ አስቀምጬ የነበረውን ጃኬቴን ለበስኩ ፡፡ጫማዬን አጠለቅኩ..፡፡መነፅሬን ግንባሬ ላይ ሰካሁና ዝግጅ ሆኜ ወንበሩ ላይ በተጠንቀቅ ቁጭ አልኩ።
እቴቴና እህቴ በራፍ ከፍተው ሲወጡ ሰማን ...ልጄ ከመኝታዋ ወረደችና ወደእኔ መጣች፡፡ ስሬ ቆመች ፡፡በቀልጣፍ የአስተሳስብ ብቃቷ ታላቄ ብትሆንም ያው በእድሜ ልጄ ነችና አነሳሁና ታፍዬ ላይ አስቀምጬ ወደ ውስጤ ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት ፡አንገቴ ስር ሽጉጥ አለች
..."ማን ነው?"
"እኔ ነኝ ክፈቱ"የሚል የደበዘዘ አይነት የቃላት ልውውጥ ይሰማል"አሁን በዚህ ድንገተኛ ግርግር ምክንያት ሲኦል ከመግባት በላይ በምፈራት በአክስቴ ፊት እቆም ይሆን..?.አረ ፈጣሪ ምንም ሀጢያተኛና ዳተኛ ሰው ብሆንም ይሄን ያህልማ ጨክነህ አሳልፈህ አትሰጠኝም" ስል ፀለይኩ...ፀሎቴን ተከትሎ ‹‹ጉድ ጉድ …››እያለች አክስቴ ወደቤት ስትመለስ ሰማሁ
..‹‹.በቃ መርዶ ነው›››ስል አሰብኩ ..የታላቅ እህቴ ልጅ ምን ሆነው ይሆን?"ከአሁን አሁን ቤቱ በለቅሶ ይደበላለቃል ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ...አሁን ደግሞ ከእኔ መጋለጥ በላይ ለቀናት ስታስበውና ስትዘጋጅበት የከረመችው የልጄ ፕሮግራም መሰነካከሉን ሳስብ ልቤ ላይ ህመም ፈጠረብኝ።
"አባዬ ምንድነው? ጨነቀኝ?"
"አይዞሽ ልጄ.. አይዞሽ"እኔ እራሴም ውስጤ በፍራቻ እየራደ ቢሆንም እሷን ግን ላበረታት ሞከርኩ፡፡
"በጊዜ አንድ ወይም ሁለት ሰዓት እኮ ነበር የምንገባው.. ሸኖን እንዳለፍን መኪናዋ ተበላሸችብን....መከራ አይተን ከሸኖ መካኒክ መቶ ነው ያስነሳት....››
በስመአብ እየቃዠሁ ነው እንዴ? ይሄንን ድምፅ አውቀዋለሁ፡፡
"እንደምትመጪ እኮ አልነገርሺንም...አዲስ አበባ ከገባሽ በኃላ እንኳን አትደውይም እንዴ..?›.
"በእኔ ቤትማ ሰርፐራይዝ ላደርጋችሁ ነበር....ግባ ….አዎ ሻንጣው እዛው ጋ ይሁን..ሌላው መኪናው ላይ ይደር …ነገ ይወርዳል..ተቀመጥ ..አዎ ሶፋው ላይ ተቀመጥ››
"አባዬ. …እማዬ መጣች መሰለኝ"ልጄ ነች ጥርጣሬዋን በጆሮዬ ሹክ ያለችኝ
"አዎ መሰለኝ"
እቅፍ አድርጋ ሳም አደረገችኝ ...እሷ ደስ ስላላት ደስ አለኝ...አረ በራሴም ደስ ብሎኛል ልቤ በውስጤ ስትንፈራፈር ሁሉ ይታወቀኛል።
አሁንም ጆሮዬ እዛኛው ክፍል ነው፡፡..."እማዬ ዛሬ እንኳን አታናግረኝም?"
"ተያት ... ደንግጣ ነው…እንኳን እሷ እኔ እራሱ በድንጋጤ ደርቄልሻለሁ"
"ታዲያ አሁን የት ሄደች ...?"
"ክፍሏ ገብታለች መሠለኝ"
"እሺ ልጄስ....?"
‹‹ተኝታለቻ..."
"ንፍቅ ብላኛለች ..በናትሽ ልቀስቅሳት"
"አይ ..ነገ ዝግጅቷ ላይ ከምትንገላጀጅ ይቅርብሽ..እንደውም በጥዋት ስትነሳ ሰርፐራይዝ ታደርጊያታለሽ"
"ጥሩ ነው… እንደውም እንደዛ ይሻላል።"
ተንፈስ አልኩ...ወደእኛ አይመጡም ማለት ነው፡
"እማ አሁን እናትሽን ልታገኚያት ትፈልጊያለሽ?››ፈራ ተባ እያልኩ ታፋዬ ላይ የተቀመጠችውን ልጄን ጠየቅኳት፡፡
"አይ አሁን ምፈልገው ከአንተ ጋር ተመልሶ መተኛት ነው..ከእሷ ጋር ነገ እተኛለሁ"
እቅፍ አደረኩና ወደአልጋው ይዤት ሄድኩ፤ ጫማዬን አወለቅኩና እቅፍ እንዳደረኳት ተኛሁ...ጆሮዬ ግን እዛው ሳሎን ነው ያለው፡፡
"የሚበላ ነገር ትፈልጋላችሁ ላሙቅ"እህቴ ነች እንግዶቹን የጠየቀችው
"አረ መንገድ ላይ ጂውስና ብስኩት ተጠቅመናል...አሁን መተኛት ነው የምንፈልገው...ለሀሰኖ የእንግዳ ክፍሉን ታሳይዋለሽ ..?እኔ ያው ካንቺ ጋር ነው ምተኛው?
"ምን ጥያቄ አለው...ወንድም ተነስ መኝታህን ላሳይህ››
‹እሺ›
የእግር ኮቴ .ከዛ ረዘም ያለ ዝምታ..ቀጥሎ ማንኳኳት ተሰማኝ
‹‹እቴቴ..እማ.እማዬ››
‹‹አረ አናግሪኝ..ውቅያኖስ አቆርጩ የመጣሁት እኮ አንድም አንቺ ስለናፈቅሺኝ ነው..በአመታት ርዝመት እንኳን ይቅር አትይኝም››
‹‹እማ እንዳልተኛሽ አውቃለሁ›
‹‹እንዴ ምን እየሰራሽ ነው.››እህቴ ነች እንግዳውን አስተኝታ ስትመጣ ያየችው ነገር በመቃወም የተናገረችው፡
‹‹ብታናግረኘ እኮ ብዬ ነው››
‹‹ታገሺ….ነው ወይስ ዛሬውኑ ተመልሰሽ ሀጄ ነሽ››
‹‹ከገዛ እናት ጋር መዘጋጋት እንዴት እንደሚጨንቅ እኮ ስለማታውቂ ነው..›
‹በይ በይ አሁን ወደመኝታችን እንሂድ››
ፀጥታ ሰፈነ…
…….በነጋታው
ከትምህርት ቤቱ ቅፅር ግቢ የፊት ለፊት በራፍ ራቅ ብዬ በአንደኛው መንገድ ቆሜያለሁ።በተቻለኝ መጠን አለባበሴ በቀላሉ ማንነቴን ለመለየት የማያስችል እንዲሆን የተቻለኝን ጥንቃቄ አድርጌያለሁ።በአንድ እጄ ከጄኔራሏ የተዋስኩትን ካሜራ ይዣለሁ ሌላ እጄ ዝም ብሎ ከወዲህ ወዲያ እየተወናጨፈ ግራ መጋባቴን ለተመልካቹ እያሳበቀብኝ ነው። ተማሪዎች ለብቻቸውም ከወላጆቻቸው ጋርም በመሆን ወደውስጥ መግባት ከጀመሩ ደቂቃዎች አልፈዋል። እዛው ከቆምኩበት ሳልንቀሳቀስ ከፊት ለፊቴ ካለው መንገድ ሙሉ ቤተሠቤ ሲመጡ ተመለከትኩ።ፈጠን ብዬ ከመሀል መንገድ በመውጣት ደር ላይ የሚገኝ የት/ቤቱ ቢልቦርድን ተከልዬ እይታዬን ወደእነሱ አስተካከልኩ።
ቀድሞ በእይታዬ የገባችው ደርባባዎ እመቤት አክስቴ ነች።ቅሬታ ያረበበት የደግነት ተምሳሌት መሆኑ የሚያስታውቅ የእናት ፊት ...ሮጠህ ሄደህ እግሯ ስር እዛ አቧራው ላይ በመንከባለል ይቅርታ ጠይቃት የሚል ስሜት ከጀርባዬ ወደ ፊት ሲገፈትረኝ ይታወቀኛል።እራሴን በመቆጣጠር ችሎታዬ ላይ ጥርጣሬ ስለገባኝ የተከለልኩበትን የቢልባርድ ብረት ጨምድጄ ያዝኩ።ከመዋረዴ በፊት ትኩረቴን እንደምንም ከእቴቴ አንስቼ ወደ ልጄ አሸጋገርኩት።ልጄ ትንሽ ልዕልት መስላለች..ቦፍ ብሎ ሜዳውን የሞላ ነጭ ቀሚስ ከነጭ ጫማ ጋር ለብሳለች...ያ ክብ ፊቷ የደስታ ብርሀን እየረጨ ነው።በአጠቃላይ ድምቀትና ውበት የተዋሀደባት ሙሉ ጨረቃ መስላለች።አዎ ከአመታት የናፍቆት መቃተት በኃላ በአንድ ቀን እናትንና አባትን ማግኘት ከዚህ በላይም ቢያስፈነድቅ የሚገርም አይሆንም።የእኔ ልጅ የእኔ መላአክ እንኳንም ፈካሽልኝ።
ቀጥሎ እናትዬውን ነው ያየሁት፤ሩቾ ፍፅም ተቀይራ ሌላ ሰው መስላላለች ።በሳቋ ነው የለየኋት።ሙሉ ቆዳዋን አስገፍፋ በሌላ እንደተካች አይነት ነው የተሠማኝ።ደግሞ እንዲህ እረጅም ነበረች እንዴ?እርግጠኛ ነኝ ይሄንን እጄን እንደጥንቱ ፊቷ ላይ አሳርፌ ፊቷን ብዳብስ ይሸረካክታታል...ጉንጮቻ እኮ ተንጠልጥለዋል"ተአምርን በቀኝ እጆ ሌላ አነስ ያለ ወንድ ልጅ በግራ እጇ ይዛ ጠብ እርግፍ ትላለ…ወንድ ልጅ የማነው ልጅ?"
"ውይ ለካ ሁለት ልጆቾ ነው ያሏት….አሁን እቺ ምኗ ነው የሁለት ልጅ እናት የሚመስለው፤ . .ይልቅስ እኔ ነኝ በመጎሳቆሌ የተነሳ ግርጅፍጅፍ ብዬ የአራት ልጆች አባት የምመስለው።

👍60❤2🤔2
ከሙግቴ ሳልወጣ ሁሉም ተከታትለው ወደግቢ ገብ ።የተወሰነ የጊዜ ክፍተት ሰጠሁና ከኃላቸው ተከትዬ ገባሁ...የዝግጅቱን ቦታ ባላውቀውም ሌሎችን ተከትዬ በመሄድ አገኘሁት ..ከተወሰነ የአይን መንከራተት በኃላ ቤተሰቦቼ የተቀመጡበትን ቦታ ማግኘት ቻልኩ ...በጥንቃቄ ዳር ዳሩን ይዤ በእነሱ ትክክል በተወሰነ ርቀት ከኃላቸው ልታይ አልችልም ብዬ ባሰብኩበት ቦታ ተቀመጥኩ።ሁኔታው ሁሉ አስጨናቂና ትንፍሽ አስቆራጭ ነበር።
✨ይቀጥላል✨
✨ይቀጥላል✨
👍48❤9🥰7👎2
# ሚስቴና አባቷ!!
/በጥላሁን ተስፋዬ/
ክፍል -አንድ
በሰርጌ ሰሞን ነው። የሚሽቴ አባት ደግሰው በጠሩን ድግስ ላይ ተታደሙት መሀል ታመታት በፊት የኔን ሚሽት ታላቅ እህት ታገባው ጥጋቡ መሸሻ ጋር ቁጭ ብለን ትንጨዋወት ተፊት ለፉታችን ተባልንጀራዎቻቸው ጋር በሚያስፈራ ግርማ ሞገስ ተቀምጠው ወደሚያወጉት አቶ ዘርጋው በአይኑ እያመላከተይ።
"ዘርጋውን እንዴት አገኘኸው ? "አለይ።
አቶ ዘርጋው የሚሽቴ አባት ቲሆኑ በጥቅሉ ስድስት ሴት ልጆይ አሏቸው። ተስድስቱ ሁለቱ ገና ያላገቡ ቲሆን የኔዋን ጨምሮ አራቱ አግብተዋልይ ። አንዷ መፋታቷን ሰምቻለሁ።
"እንዴት አገኘሀቸው ስትል አልገባኝም!" አልሁት። በሰርጌ ማግስት ስለአማቼ ምን ሊያወራይ ነው ብዬ እያሰብሁ።
"ያው አማችህም አይደሉ ቅርርባችሁ እንዴት ነው ባህሪያቸውስ?" ማለቴ ነው አለይ።
ያው እስታሁን ባየሁት በቀያቸው በጣሙን የሚፈሩ እና የተከበሩ ትልቅ ሰው መሆናቸውን ተግንዝቢያለሁ ።
ታታሪ የስራ ሰው እንደነበሩም ያላቸው ሀብትና ንብረት ምስክር ነው ።
ተዛ ውጪ ለልጆቻቸው ታላቸው ፍቅር እና ስስት የተነሳ ልጆቻቸው ተአይናቸው እንዲርቁ የማይፈልጉ አባት መሆናቸውን አውቄያለሁ። ትለው•••
"በምን አወቅህ "አለይ።
" ምኑን?" ትለው••• "አሁን መጨረሻ ላይ ያልከውን" አለይ።
"ያው እንግዲህ እኔና ተዋቡ በትዳር ስንጠቃለል ይዣት ወደትውልድ መንደሬ ልገባ ተሰናድቼ ታበቃ•••"
ተጋብቻው በፊት እኔና ተዋቡን ጠሩንና ••• " ልጄ ከኔ ብዙ እንድትርቅ አልፈልግም የሚስፈልጋችሁን በሙሉ እኔ አሟላለሁ ትለዚህ እላይ መንደር ተስንት አመት በፊት ዝም ብዬ ገዝቼ ያስቀመጥሁት ሁለት ክፍል ቤት ያለው ትልቅ ግቢ አለ።
አጠገቡም የሚታለቡ ከብቶይ ያሉበት ሌላ ግቢ አለ ሁለቱንም ልሰጣችሁ ወስኛለሁ እዛው ትናራላችሁ!" አሉን"" ብለው•••
በረጅሙ ተነፈሰና •••
"ልክ ብለሀል ደግስ ደግ ናቸው
ደግነታቸው እንዳለ ሆኖ ሀይለኝነታቸው ግን አያድርስ ነው!
ለኔ እና ለምሽቴም ብዙ ነገር አርገውልናል ቆይቼ ታያቸው ግን ያረጉልን ነገር ቀርቶብን በኔና በሚሽቴ መሀል የማይገቡ አማች ቢሆኑ ይሻለይ ነበር!"አለይ።
"መሀል መግባት ማለት? " አልሁት ግር ብሎይ።
መሀል መግባት ቢሉህ መሀል መግባት መሰለህ ! አንዷ ልጃቸው ተባሏ ጋር ለመለያየት የበቃችው በሳቸው ጣልቃ መግባት ከባሏ ጋር ነገር ተካሮ እኮ ነው እይ ጠባቸው ለመለያየት የሚያበቃ ሆኖ መሰለህ?
በኔና በሚሽቴ መሀል እዚህ ግባ የማይባል ፀብ ተፈጥሮ ጆሮቸው ከደረሰ አበቃ ከታረቅን ቡሀላም ቢሆን መጥተው እንደአዲስ ነገር ይቀሰቅሳሉ።
መጥተው በገዛ ትዳራችን እኔ ፈላጭ ቆራጭ ታልሆንኩ እያሉ ስንት ግዜ እንዳማረሩይ የማውቀው እኔ ነኝ።
*በኔና በሷ መሀል ኮሽ ታለ ቴት መጡ ታይባል ከች ነው። አይጀመር እንጂ ጠብ ተተነሳ አባቷ አጠገባችን ባይኖሩም ተሁለት ሰው ጋር እንደምጣላ ነው እሚሰማይ
አሁንማ ድንገት ከሚሽቴ ትንጣላ ተሷ እና ተኔ ፀብ በላይ ያባቷ ነገር ነው የሚያሳስበኝ! "
"ኧረ ተው ጥጋቡ እሄን ያህል?" አልሁት ገርሞይ ። በልቤ እንደስምህ ሚሽትህን የምትደበድብ ጥጋበኛ ሆነህ እንዳይሆን ብቻ እያልሁ።
ዝርዝሩ ብዙ ነው እኔ አሁን የቤቴን ገበና ላወራልህ ፈልጌ ሳይሆን በኔም በሌሎቹም ላይ ከደረሰው አንፃር ፀብ ሲፈጠር ያላግባብ መግባት ከሚገባቸው በላይ ጣልቃ ገብተው እኔ ያልኩት ካልሆነ የማለት ባህሪ እንዳላቸው እንድታውቀው ያህል ነው።
ከሚስትህ ጋር ሰላም ከሆንክ አይደርሱብህም አትስጋ!" ሲለይ•••
ኧረ እኔ ምን አሰጋይ ! ቀድሞውንስ ተዋደን ተፋቅረን ተተጋባን ኋላ ምን ያጣላናል ብለህ ነው ?" ብለው•••
እኔም ፀብ በመሀላችሁ እንዲኖር አልመኝም ግን አለ አይደል እግር ተግርም ይጋጫል ይባል የለ በኑሮ መሀል የከፋ አይሁን እይ ጠብ አይጠፋም እንደውም የማይፋቀሩ ናቸው የማይጋጩት "
ብሎይ እርፍ ።
አላመንሁትም ። የማይፋቀሩ ናቸው የማይጣሉ ምን ማለት ነው? ምን ይላል እሄ!!?
ፊደል ቆጥሩያለሁ ብሎ ነው የማይሆን ነገር የሚቀባጥርብይ። እያልሁ ውስጥ ውስጡን ታልጎመጉም።
"ደሞ አንቱ መባል አይወዱም አንቱ አትበላቸው እሺ መልካም የጫጉላ ግዜ ይሁንላችሁ ብሎይ ወጣ።
የጫጉላ ግዜውም አለፈ ። ተትጋባን
በአመት ታአምስት ወራችን ወንድ ልዥ ወለድን ።
እስክንወልድ ድረስ በኑሮ መሀል አለመግባባት ቢኖርም ሀይለ ቃል እንኳ ብዙ ሳንጠቀም ለዘብ ያለ ጠብ እንጣላለን ። አልፎ አልፎም እንኳረፋለን። ኩርፊያችን ግን ተሁለት ቀን ዘሎ አያውቅም።
ተኳርፈን በተታረቅን ቁጥር አልጋው አፍ አውጥቶ እርይ እስቲል በፍቅር ትንጨፍርበት እናድራለን ።
አንዳንዴ እንደውም ተዋቡ ሚሽቴ ነገር ትትፈልገኝ ኋላ ስንታረቅ ልቧችን እስቲወልቅ የምንሰራው ፍቅር ናፍቋት ይሆን? እላለሁ።
ተወለደይ ቡሀላ ጠባዩዋ ተቀየረ ደርሳ በረባው ባልረባው ቡፍ ትላለይ።
እሱም ቢሆን የከፋ ጠብ ውስጥ ታይከተን ነብር ትትሆን ታጠገቧ ራቅ እያልሁ አሳልፈው እና አምሽቼ ትገባ በርዳ ትጠብቀኛለይ። ጠጅ እንደምወድ ታውቃለይ ። አታብዛ እይ አትጠጣ ብላይ አታውቅም ።
ነገር መመላለስ ታልሆነ በቀር እጄን አንስቼባት አላውቅም። አሁን በቀደም ልጃችን ሁለት አመት እንደሞልላው በማግስቱ እንደሁልግዜው አምሽቼ ወደ ቤት ትገባ
"እይይይይ ••ዛሬማ ጠጥተህ ታይሆን የጠጅ በርሜሉ ውስጥ ተነልብስህ ተጠምቀህ ነው መሰል የመጣህው ገና እበሩ ደጃፍ ላይ ትትደርስ ነው የሸተተይ!!" አለይ ።ለነገር እየተንዘረዘረይ።
"ተይ እንጂ ተዋቡ አሁን ትናንት ተጠጣሁት የዛሬው በምን ተለየ ትናንትም አምስት ብርሌ ዛሬም አምስት ብርሌ ነው እንግዲህ የጠጣሁት " ብላት•••
" የዛሬውማ ይለያል እግዚኦ ኧረ እንደው አንተስ ምን ይሻልሀል ብርሌ አልቆ በርሜሉ ውስጡ ገብተህ ነው እንዴ ትትጋት ያመሸኸው?"
ተይህ በፊት ጠጥቼ ትገባ አጉርሳ አልብሳ እንዳላስተኛችይ ዛሬ ሆን ብላ ስትለክፈይ
ተጠጣሁት በላይ የሷ ነገር ስካሬን ሁለት እጅ አደረገው መሰል•••
"አይ እንግድህ ያንቺ አፍንጫ ጢስ ቲደፍነው ስራውን እየረሳ ፣ ባዶ ሲሆን ከሩቅ እያሸተተ ይሆናል እይ እኔስ ትናንትም ዛሬም የጠጣሁት ለውጥም የለው ነገር አትፈልጊይ ይልቅ!"
"የማንን አፍንጫ ነው ጢስ እሚደፍነው አንተው የኔን ? እያለይ ያን እንደነገሩ ሸብ አርጋ የለቀቀችው ጠጉሯ ወርዶ የተጋደመበትን ቀጭን ወገቧን በሁለት እጆቻ ይዛ፣ እየተውረገረገይ ተኮሳትራ እንኳን እየሳቀይ የሚያስመስላትን ጠይም ክብ ፊቷን ለመጨፍገግ ፍዳዋን እያየይ ተፊቴ ቆመይ።
ብድግ እልሁና ተጠግቻት ቆምሁ። እስተደረቴ መጥታ የተቋረጠችውን የኔን ተዋቡ በንዴት ትትቁነጠነጥ ቁልቁል እያየኋት ምን ልትሆኚ ነው ዘለሽ የመጣሽው ?
ወደሽ ነው!! ጢስ እንኳን ያንቺን ጎራዳ አፍንጫ ስንት ነገር ይደፍን የለ እንዴ ! ስላት በገነይ•••
"አብዬ ዘርጋው ድረስ! የማን አፍንጫ ነው ጎራዳ አንተው! የኔ የተዋቡ! አለይ።
ሽቅብ ተንጠራርታ አንገቴን ልታንቅ እየከጀለይ።
"አይኔን አታስቀው ጥርሴስ ልማዱ ነው " አለይ እምዋ !""
ምን ልትሆኚ አማረሽ አንቺ ? ብዬ እጃን ያዝ አደረግሁና•••
"ተዋቡ ብለው ስም ያወጡልሽ እንደሆን ታድያ ቆንጆ የሆንሽ መሰለሽ እንዴ ስም አፍንጫ አያሳድግ እንግዲህ ምን ትሆኚ ካካካካካ"
መጣህብይ እንጂ አልመጣሁብህ ዛድያ ቆንጆ ታልሆንኩ ማን አግባኝ አለህ?!" ስትለይ•••
"ቆንጆ ሴት ብቻ ነይ እምታገባ ያለሽ ማነው አንቺው?

👍44🔥2
ነገሩ ያኔ ታይሽ ጠባዬ መልካም መስለሽይ ነበር ተጠባዩ ወይ ተመልኩ ታንዱም ያላደላት ሚሽት ማግባቴ የታወቀይ አሁን ነው •••
"መልከ ጥፉ በስም ይደገፍ "ነው ነገሩ ስም ብቻ ምን ይፈይዳል ስም ተማሪ ቤት ለመመዝገብ እይ ለመልክ አይሆን !"ብላት በንዴት እየተንተከተከይ•••
"እዛ ጠጅ ቤት ሰልካካዋን መልከመልካሟን ፍለጋ ነዋ ነጋ ጠባ የምትመላለስልይ ዛድያ ለምን እዛው አለደርህም ነበር ?" ስትለይ።
እጇን ለቀቅሁና " ተፈቀድሽ እማ ሄጄ አድራለኋ ምን ሽግር አለ ብዬ ራመድ ስል•••" እንደነብር ዘላ ተፊቴ በመምጣት ጥፍራን አንጨፍርራ ተከመረችብኝ።
ስትባጭረይ ! እኔም ብልጭ አለብይ።
ተዛ ቡሀላማ ዳር ቆሞ ፀቡ እስቲጀመር በጉጉት ምራቁን እየዋጠ ቲጠባበቅ የነበረው ሰይጣን በመሀል ፊሽካ እየነፋ የረፍት ሰአት ያውጅልናል መሰል እያረፍን ትንቧቀስ ቆይተን ቲደክመን ተኛን!
በጥዋት ተኔ ቀድማ ተነስታ ወጣይ ፣ ልጃችን እቤት ውስጥ ተኝቶ ስለነበር ከግቢያችን ጎን ወዳሉት ከብቶይ ሄዳ ሁለቱ ሰራተኛይ ወተቱን በጥዋት አልበው ለደንበኛቻችን መውሰዳቸውን አይታ ልመጣ ይሆናል ብዬ አሰብሁ።
ትንሽ እንደተኛሁ ተነስቼ ስወጣ እሷ ስትገባ ደጃፉ ላይ ተገናኘን ።
ይቅር በይኝ ተወቡ ብዬ ላናግራት ትሞክር ነብር አራስ ሆነችብይ። በቃ አምርራለይ አልሁና
ብድግ ብዬ ሁለቱ ጎረቤቶቻችን ጋር በመሄድ ሚሽቴን ማታ አድርጌው የማላውቀውን እጄን አንስቸባት አስቀይሚያታለሁና አማልዱይ ብዬ ለመንኋቸው ።
ግቢ ውስጥ ቆሜ ትጠብቃቸው ለሁለት ሰው ነግሬ ቴት እንደተጠራሩ እንጃ አምስት ሆነው ቲመጡ እንዳየሁ ደነገጥሁ።
ያልጠራኋችሁ ተመለሱ ልላቸው ምን ቀረይ።
አሁን ወሬ ማራባት ምን ይሉታል እኔ የነገርኋቸው ሁለቱ ብቻ ቢመጡ ምናለ
የድር ስብሰባ አለ የተባሉ ይመስል ተጠታርተው ይምጡ•••ጉድ እኮ ነው እናንተ" እያልሁ ትነጫነጭ ቆየሁና ገብተው እንደተቀመጡ ተከትያቸው ገባሁ።
ወድያው እሷ ተነስታ እንዲህ ብሎኝ እንዲህ አርጎኝ ፣ እንዲህ ደፍቶ፣ እንዲህ አንስቶ እያለይ የሞከርሁትም፣ የፎከርሁትንም የሰራሁትንም፣ ያልሰራሁትንም ሀጥያቴን ትታነበንብ••
ላስተባብል መሀል ትገባ •••
"ቆይ ዝም በል አንተ ትጨርስ !"
እያሉ እንዴት እንዴት ሆነው በአትኩሮት እንደሚከታተሏት ታይ ትክን እልሁ።
እሄን ግዜ አንድ ሰው ደግደጉን ወሬ እንዲህ እንደምሽቴ አንድ ሰአት ሙሉ ቆሞ ቢያወራ እንቅልፋቸው በመጣ ነበር።
የኔን ጉድ ለመስማት አይናቸው ፈጦ ጆሮቸው ተቀስሮ ታየው እኛ ተጣልተን ባንደርስላቸው በፀብ -ወሬ ጥም ሊሞቱ ተቃርበው ነበር እንዴ ?
በይህ አመት ይህን የመሰለ ጮማ ወሬ የሰሙም አይመስለይ ።
ተበዳዩን አጥናንተው፣ በዳዩን ገስፀው ወደ ሽምግልናቸው መቋጫ እኔን ተሷ በእርቅ ሊያቆራኙ አፍታ እንደቀራቸው •••
አሞራ ይንገረው ጅግራ ታይታወቅ ፣ የኔና የሚሽቴን መጣላት አጠገባችን ታሉት ጎሮቤቶቻችን ቀድሞ የሰማ የሚመስለው የሚሽቴ አባት ቴት መጣ ታይባል በሽምግልናው መሀል
በረጅም ቁመቱ ላይ ተመጥኖ በልኩ በተሰጠው ግዙፍ ሰውነቱ ጓንዴውን እጀርባው ላይ እንዳጋደመ ድንገት ዘው ብሎ ቲገባ •••
በድንጋጤ እጥዬ ዱብ አለይ !!••••
•••••••ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️

👍34
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
መቼስ የሀገራችን የሚካሄድ ትንሽም ሆነ ትላልቅ ዝግጅቶች ተሳስተው እንኳን ከመዝረክረክ አያመልጡም።እና ይጀመራል ከተባለበት ሰዓት 40 ደቂቃ አርፈደው ጀመሩ...ዝግጅቱ ከተጀመረ ከአንድ ሰአት በኃላ የሽልማቱ ፕሮግራም ተጀመረ ። እንደአጋጣሚ ሽልማቱ ከታችኛው ክፍል ነው የተጀመረው...
‹‹ አማካይ ውጤት 97.5 በማምጣት ከሁለተኛ-ለ ክፍል እንዲሁም ከአጠቃላዩ ሶስቱም የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት ልዩ ተሸላሚያችን ተአምር እዬብ ..››አካባቢው በጭብጨባ ተነጋ.. ቤተሰቦቼ ሁሉም ከተቀመጡበት ተነስተው አካባቢውን ቀወጡት..፡፡በስሜት ካሜራዬን ደቅኜ ወደፊት ተጠጋሁ .በተቻለኝ መጠን ልጄን በካሜራዬ ለማደን ሙከራዬን ቀጠልኩ...፡፡የእኔ ልዕልት እየተንሳፈፈች ወደመድረክ
እየቀረበች ነው...፡፡
እናትዬውና አክስቶቾ ሰፌድ የሚያካክል አይፓዳቸውን ቀስረው ከኃላ ተከተሏት...፡፡መድረክ ላይ ወጥታ ከክብር እንግዳው ሽልማቷን ስትቀበል ስመለከት እንባዬን ከመርገፍ ላግደው አልቻልኩም...የራስ ልጅ እንዲህ በክብር አደባባይ ላይ ብዙዎችን በአድናቆት ሲያስጨበጭብ ማየት ለአንድ ወላጅ ምን አይነት ልብን በደስታ የሚያጥለቀልቅ መባረክ እንደሆነ እድሉ የገጠመው ወላጅ ብቻ ነው የሚያውቀው።
እኔም በጊዜው እዚህ መድረክ ላይ እስኪሰለቸኝ ድረስ በተደጋጋሚ በመውጣት ተሸልሜበታለሁ...በዛን ወቅት ግን እቤተሠቧቼ አሁን እኔ የተሠማኝን አይነት ልዩ ስሜት እንደሚሰማቸው ገምቼ አላውቅም ነበር...፡፡ልጄ ሽልማቷን በአየር ላይ እያወዛወዘች ህዝብን አስጨበጨበች።ከዛ በእኔ አቅጣጫ ስትደርስ ሽልማቱን ባለበት አቆመችና ትኩር ብላ ወደእኔ ተመለከተች፤ እኔም በደስታ እጄን እስኪያመኝ በአየር ላይ አወናጨፍኩት..ከዛ ለሌላ ተሸላሚ መድረኩን ለቃ ስትወርድ እኔም ፈጠን ብዬ በፊት ወደነበኩበት ቦታ ተመለስኩ…፡፡
ዘመዶቾ ከበዋት ያውካካሉ እያንዳንዱ በየተራ አብረዋት ፎቶ ይነሳሉ…፡፡ቀናሁ… በጣም ቀናሁ…..እኔም ከመሀከላቸው መገኘት ነበረብኝ፡፡.ቁጭ አልኩና በሀሳብ ሰመጥኩ፡፡.አይኖቼ እንባ አግተዋል….፡፡ትንሽ ፊት ሚያሳየኝ ወይ ሚነካካኝ ነገር ባገኝ እዘረግፈዋለሁ….፡፡
አንድ ነገር ተከሻዬን ከኃላዬ ነካኝ…..ከሀሳብ ባነንኩና ዞር ስል ልጄ ነች…፡፡
‹‹አባዬ ተከተለኝ›› ብላ ብን ብላ ወደኃላ ሄደችና ከእኔ ጀርባ ባለ የመማሪያ ክፍል ግድግዳ ኮርነር ተጠመዘዘች፡፡ፊቴን ወደ ፊትለፊት ላኩ ፡፡ወደዘመዶቼ፡፡ በራሳቸው ነገር ተጠምደው ያውካካሉ.፡፡ፈጠን አልኩና ተንቀሳቀስኩ፡፡ ልጄ ወደሄደችበት በፍጥት ሄድኩ ፡፡እንደተጠመዝኩ አገኘኋት፡፡ እጄን ያዘችና በፈጣን እርምጃ ወደፊት መጓዝ ጀመረች.፡፡ዝምብዬ ተጎተትኩላት…፡፡ምን ልታደርግ እንደሆነ አልገባኝም…፡፡ክፍሉን አለፈችና ሌላ ጠባብ መንገድ ውስጥ ይዛኝ ገባች፡፡ጥቂት ተራመድንና በፅድና በአትክልት የደመቀ የት/ቤቱ መናፈሻ ውስጥ ገባን፡፡ ምትፈልግበት ቦታ ከደረሰች በኃላ አዲስ እንዳገኘችኝ ነገር ተጠመጠመችብኝ፡፡
‹‹እንዳያዩን ብዬ እኮ ነው እዚህ ይዤህ የመጣሁት››
‹‹አይፈልጉሽም?››
‹‹ቶሎ እመለሳለሁ… ሽንት ቤት ብያቸው ነው የመጣሁት››
‹‹የእኔ ብልጥ በጣም ነው የኮራሁብሽ….፡፡.በጣም ነው ያስደሰሽኝ ….፡፡እንቺ ይህቺ ያዘጋጀውልሽ ትንሽ ስጦታ ነች›አልኩና በሚያብረቀርቅ የስጦታ ወረቀት አምሮ የተጠቀለ እና በፔስታል ያለ ስጦታዬን ሰጣኋት..
‹‹አባዬ ምንድነው? ልክፈተው?››
‹አይ እቤት ብቻሽን ስትሆኚ ተከፍቺዋለሽ›
‹‹እሺ አበባዬ አመሰግናለሁ…በጣም አስደስተህኛል›ብላ ወደታች አስጎንብሳ ጉንጬን ሳመቺኝና
‹አባዬ ፎቶ እንነሳና ልሂዳ..›
‹‹እሺ …እሺ›› አልኩና የያዝኩትን ካሜራ በራሱ እንዲያነሳ አጀስት በማድረግ አንድ አምስት የሚሆኑ ፎቶዎች ተነሳን፡፡
‹‹አሁን ልሂድ አባዬ››
‹የእኔ ማር ሂጀ …አሁን እኔም ወደአዲስአባ ልመለስ…ማታ ብቻሽን ስትሆኚ ደውይልኝ››
‹‹እሺ አባዬ…ሌላ ጊዜም መጥተህ ታየኛለህ አይደል.?››
‹‹የእኔ ማር ከአሁን ወዲህ አንቺን ሳላይ ብዙ ጊዜ መቆየት ስለማልችል .አዎ መጥቼ አይሻለሁ›
አገላብጬ ሳምኳት.እሷም ሳመችኝና እንዳመጣጧ እየተሹለከለክች ብን ብላ ሄደች.፡፡እኔ እዛ መናፈሻ ውስጥ ለታሪክ ድምቀት የታነፀ በድን ሀውልት መስዬ ለረጅም ደቂቃዎች ቆምኩ፡፡ አሁን እንደቅድሙ የተንጠለጠለውን እንባዬን ገድቤ ማቆየት አልቻልኩም….ዝርግፍ ብሎ ሲንጠባጠብ እኔም ልክ እንደሌላ ሰው በትዝብት እያየሁት ነው፡፡ከዛ በኃላማ ወደዝግጅቱም አልተመለስኩም፡፡ ምን ላደርግ…?ሹልክ ብዬ ግቢውን ለቅቄ ወጣሁና ወደመናኸሪያ ነው ያመራሁት.፡፡ከዛ ቀጥታ ወደ አዲስአባዬ ፡፡

👍99❤8🥰6😁5🔥2👏2👎1