አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ስምንት

መማርን ጌታ ይባርከው ! መማር መቃጠል ነው ይላሉ ተምሮ ማቃጠል ለእኔ ዓለሜ ሆነች "
ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት አንደኛ ከፍል እስከመዘገብ የአባት ስም አልነበረኝም፡፡ አሸብር ብቻ
ነበርኩ፡፡ ልክ ትምህርት ቤት አቲዬ ወስዳኝ ስመዘገብ ጉጉት የመሰለው መዝጋቢ የእናቴ ድሪቶ ቀሚስ ለዓይኑ ቀፎት እያመናጨቃት አይቼዋለሁ፡፡ ተመዝግቤ ስንመለስ አቲዬ ከፊቱ ዞር ስትል፣ ፊቱን አጨፍግጎ መጥፎ ጠረን እንደሚያባርር ሰው በግራ እጁ አየሩን እያራገበ ሲያባርር አይቼዋለሁ፡፡

በእርግጥ አቲዩ እማማ የብርጓል ቤት እንኩሮ እያነኮረች ነበር፡፡ ምዝገባው ዛሬ ነው የሚያልቀው
ሲሏት ብድግ ብላ ነው የመጣችው፡፡ ቢሆንስ ልክ ቆሻሻ እንደሸተተው ሰው ሰው እንዲያየው አድርጎ እጁን ያራግባል እንዴ…፡፡ የእማማ የብርጓል ቁጥር አንድ የጠላ ደንበኛ እንዳልሆነ ሁሉ፡፡ ሊያስተምረን ክፍል ውስጥ ሲገባ እንደባቡር ሀዲድ የረዘመ የጠላ ትንፋግ ተከትሎት
እንደማይገባ ሁሉ ነብር አየው ያንን የውሻ ልጅ። አስተማሪውን እንደጠመድኩት ጡረታ
ወጣ !! ደግሞኮ አያፍርም መንገድ ላይ ላገኘው ሁሉ፣ እኔ ነኝ ያስተማርኩት“ እያለ በኩራት
ያወራል፡፡ በርሱ የትምህርት ዓይነት ብቻ ዶክተር የሆንኩ ይመስል!!

“ስም ?” አላት አቲዩን ድሮ፡፡

“የእኔን ነው ?” አለች እየፈራች፡፡

ፈሪ ነበረች እናቴ፡፡ ፈሪው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደያቅሙ ደሀ ማስፈራራትን ተክኖበታል።

“አንች ነሽ አንደኛ ክፍል የምትመዘገቢው?" አላት፡፡ አጠገባችን ያሉት ሁሉ ሳቁለት፡፡ አቲዬ ተሳቀቀች፡፡ ሰውነቷ ሽምቅቅ ሲል ቀሚሷን አንቄ ተሰምቶኛል መሸማቀቋ፡፡

የልጅሽን ሰም ንገሪኝ ሴትዮ አላት እያከላፈታት፡፡

“የእሱ አሸብር…አሸብር ነው ስሙ አለች ራሴን እያሻሸች፡፡

“የአባት ስም ?”

“እባ…ት” ብላ ዝም አለች፡፡

“የአባቱ ስም ማነው…

'ቀ' መጨረስ አልቻለችም፡፡ ቀለመወርቅ ልትል ፈልጋ እንደነበር የገባኝ ካደግኩ በኋላ ነው፡፡

የዛሬዋ ደግሞ የጉድ ናት፡፡ የልጇም አባት የሚጠፋት
እንደገና እንዲስቁለት ሰዎቹን አየ
ያልደመቀ ሳቅ ተሳቀለት፡፡

"በይ ወደዛ ሁኝ! ስታስታውሽ ትመለሻለሽ፤ ተረኛ ቀጥል!” አለ እስኪርቢቶውን እያወናጨፊ፡፡

(አልረሳትም ግማሽ ድረስ ቀለሟ ያለቀ ሰሚያዊ ቢክ እስክርቢቶ።

እናቴ ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው፣ “በአምላክ..በአምላክ ነው የአባቱ ስም፡፡” አለች፡፡

መዝጋቢው ራሱን ግራና ቀኝ በብስጭት እያወዛወዘ መዘገበኝ፡፡

የአባት ሰም በአምላክ (በአምላክ አባቴ አይደለም፡፡ እቲዬ ለአምላክ ሰጠችኝ፡፡) የሃምሳ ብሩ ሲገርመው፣ ለእግዜር ሰው አበደረችው አቲዬ፡፡ የእኔ እናት በሕይወት ባንክ ውስጥ ብድር
ለሚመልስ ብድር በመስጠት የተካነች ባለሙያ ነበረች ነገን የምታይ !! እግዜር የተበደረው
ትውልድ፣ ወለዱ የተባረከ ዘር ማንዘር ነው፡፡ “እስከ ሺ ትውልድ ዘርህን እባርካለሁ፡፡ ብሏል
ራሱ እግዜር

ትምህርት ቤት ገባሁ…!!

የክፍላችን ልጆች የኑሮ ደረጃ በዳግማዊትና በእኔ መካከል የተወሰነ ነበር፡፡ ዳግማዊት የሚታዘል ባለዚፕ ቦርሳ ያላት ቆንጆ አንደኛ የሀብታም ልጅ ስትሆን፣ እኔ ከሹራብ የተሰራች ኮሮጆ የነበረኝ አንደኛ የደህ ልጅ፡፡ ይሁን እንጂ በንፅህና አልታማም፡፡ ልብሶቼ ሁልጊዜም ንፁዎች ነበሩ
ንፁህና አሮጌ፡፡ ሰኞ ሰኞ ሰልፍ ሜዳ ላይ የእጅ ጥፍሮቻችን ሲታዩ ንፁሀ ጥፍርቼን በኩራት
ነበር የምዘረጋው:: የዳግማዊትን ያህል በፈገግታ “ጎበዝ“ ባልባልም፣ ከቆሻሻና ከስንፍና የተጣላች ቆራጥ ደሀ እናት አለችኝና ስንፍናና ቆሻሻ አጠገቤ ዝር አይሉም ! (ሰው ወዶ አይደለም ለካ ዘራፍ የሚለው፡፡)

አንድ ቀን ግን በሕይወቱ ስሳቀቅበት የኖርኩበት ነገር ተፈጠረ፡፡

እንግዲህ አስቴር ከዋናው ቤት እሮጌ ፍራሽ (የሆቴሉ አልቤርጎ ውስጥ የነበሩ፡፡) እና ሌሎችም
ከፍል ውስጥ ቤት፡፡ እናም ቤታችን ውስጥ በታጨቀው ዕቃ ምከንያት ቤቱን አንደ ልብ ማፅዳት ባለመቻሉ ቁንጫ እንደጉድ ይፈነጭ ጀመረ፡፡

ጋሽ መሀሪ ኣካባቢ ሳይንስ መምህራችን ነበር፡፡ ሲያስተምር ስወደው:: የርሱን ትምህረት አስር
ካስር ነው ሁልጊዜም የምደፍነው፡፡ እኔ ስለምወደው፣ የሚወደኝ ይመስለኝ ነበር ፡፡ አንድ ቀን ግን ዘላለማዊ ጠላቴ ያደረገውን የማይረባ ነገር አደረገ።

ስለ ጓር አትክልት ጥቅም እያስተማረ ነበር፡፡ ድንገት ዳግማዊት፣ “ ዋይ” ብላ ጮኸች::
ቦርሳዋ ላይ ሁለት እሳት የመሳሰሉ ቁንጫዎች ዘለውባት ነበር፡፡ የክፍሉ ልጅ ሁሉ በድንጋጤ
ወደ ዳግማዊት ዞረ፡፡ መምህሩ ሁኔታውን ሊያጣራ ከምኔው አጠገባችን እንደደረሰ እንጃላት::

“ምንጩን ነው?”

“ቁ..ን..ጫ አለች ለቅሶ በሚመስል ሞልቃቃ ድምፅ፡፡

እኔ ከዳግማዊት ጎን ነበር የምቀመጠው፡፡ ባልገባኝ ምክንያት ተቆጣ፡፡

"እስቲ ቦርሳህ” አለኝ፡፡ በቃ እንዲህ ነው ያለኝ፡፡ ከወንበሩ ስር ከተሰራው የደብትር ማስቀመጫ፣
የሹራብ ኮሮጆዬን አወጣሁ፡፡ በዚህች ቅፅበት የተከሰተው ነገር አስደንጋጭ ነገር ነበር፡፡ በርካታ
ቁንች ከእኔ ኮሮጆ ላይ ተፈናጠሩ፡፡

መምህር ምሀሪ ፊቱን አጨፍግጎ ኮሮጆዬን አነሳና ወደፊት ወደ ጥቁር ሰሌዳው ወረወረው::
ደብተሮቼ በአየር ላይ ወረቀታቸውን እያርገበገቡ ተበታተኑ፡፡ (እስከዛሬም ደብተሮቼ በአየር ላይ እየተንሳፈፉ ይታዩኛል አላረፉም፡፡)

“ውጣ ጆሮህን ያዝ ብሎ በኩርኩም አፈለሰኝ፡፡ ወጥቼ ጆሮዬን ያዝኩ፡፡ ከኩርኩሙ በላይ
ሀፍረቱ ጠዝጥዛኝ ነበር፡፡

የታፈነ የጓደኞቼ ሳቅ፡፡ በትምህርት አልችለኝ ሲሉ እችን እንደውድቀት፣ እችን ከእነሱ እንዳነስኩባት አጋጣሚ ሊጠቀሙባት፡፡ የእፉኝት ልጆች…ስንቱን ትምህርት ስደፍን ለጭብጨባ በመከራ የሚነሳ እጃቸው፧ ዛሬ ሳቃቸውን ሊያፍን ወደ አፋቸው ተወነጨፈ።

ቡፍ.….ቡፍ...ሂሂሂ..

መምህሩ መሀሪ (ስሙን ቄስ ይጥራውና!) ስለጓሮ አትክልት የፃፈውን አጥፍቶ ጥቁር ሰሌዳው ላይ፣

“ተስቦ" ብሎ በትልቁ ፃፈና ከስሩ በድርቡ አሰመረበት፡፡ ያውም አረንጓዴ ቀለም ባለውና እንደ
ብርቅ በምናየው ጠመኔ !!

ከዛም ስለተስቦ ሙሉ ክፍለጊዜውን ሲለፈልፍ ዋለ፡፡

“አያችሁ ልክ እናንተ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ዘመድ ለመጠየቅ በታክሲ፣ በአውቶብስ
ተሳፍራችሁ እንደምትሄዱት፣ ቁንጫዎችም በአይጦች ተሳፍረው ንፅህናው ወዳልተጠበቃ ቤት ይሄዳሉ፡፡ አሁን እሱ ደብተር መያዣ ላይ እንዳያችሁት እኔን እየጠቆመ)፣ ንፅህናው ባልተጠበቀ የልብስ ሻንጣ፣ የደብተር መያዣ፣ በሌላም ቁሳቁሶች አማካይነት እየተንጠላጠሉና እየተደበቁ
ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ፣ እንደ ዳግማዊት ዓይነት ንፁህ ልጆች በተስቦ ይያዛሉ..” በማለት
አስተማረ፡፡ ምን ያስተምራል አስተማሪ የሚባለው ነገር የጠላት ስም እንዲመስለኝ እደረገ እንጂ !
ለረዥም ጊዜ 'ተስቦ' እያሉ ጓደኞቼ ያበሽቁኝ ነበር፡፡ ከአርባው ስንፈተን ግን ስለተሳቦ ተጠይቀን
የደፈንኩት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ ሰው ስድሱን አይረሰማ !! በተለይ እኔ ስድቤን አልረሳም !! መገፋቴን አረሳም።

ስድስና መግፋት እንደ አረግራጊ ሳንቃ ሽቅ

ብ ተኩሰው በቀል የሚባል ጨረቃ ላይ የሚያሳርፉኝ
👍36🥰32😁1😢1
ሮኬቶቼ ነበሩ፡፡ እንዲያ ካልሆነ በቀል መቼ አምሮ !! የሰደበኝን ሁሉ አልለቀውም !! ለምን
ዘላለም አይኖርም፣ አልረሳም! የአዲስ አበባ ሕዝብ ሂትለሩን እቅፍ እያሳደገ መሆኑን መች
ጠርጥሮ? ለፋሽስቱ እድገት ኩርኩምና እርግማን እያዋጣ እንደሆነ መቼ ቀልቡ ነግርት? ሬዲዮና ቴሌቪዥኑ አደንቁሮት፣ ፊልምና ድራማው አሳውሮት፣ ሽቅርቅሮቹ ልቡን አጥፍተውት፣ ሕዝቡ ምን እያሳደገ እንደሆነ ያስተውልም !! እያንዳንዱ መንደር አለ የተጎፋ ሕፃን ሂትለር - የሕዝብ
ንቀትና ጥላቻ በክፋት ያፈረጠመው፡፡ በቀጥታ ሳይሆን ሳያውቁ ለልጆቻቸው በሚያለብሱት ልብስ፤ በሚያገምጡት ኬክ እንቁልልጭ እያሉ አርፎ የተኛ ረሀቡን ቀስቅሰው ያስነከሱት
የቆሰለ አቦሸማኔ አለ። ሕዝብ ጠላቱን የሚጠብቀው ድንበሩ ላይ ወታደር አሰልፎ ነው:: አገርና
ሕዝብ ንፋስ እንደገረሰሰው ዛፍ ከስራቸው ተነቅለው የሚወድቁት ግን ውስጣቸው ባሳደጉት
ጭቆና፣ ባፈረጠሙት የጥላቻ ክንድ በተደቆሱ ግለሰቦች ነው::

ሕዝቤ ያሳረፈብኝን የጥላቻ ኩርኩም ነገ በጅምላ እልቂት እከፍለዋለሁ ብቻ ልደግ ።
ማሪያምን አልለቀውም ይሄን ሕዝብ፡፡ ደግሞ ብቻዬን አይደለሁም ይሄ ሁሉ ተገፍቶ
ጎዳና የሚንከራተት ሕፃን፣ ነገ ተንደላቀው የሚማሩትን ቆንጆ የለበሱትን ልጆችህን ሕይወት
ያመሳቅለዋል፡፡ የዘራኻትን የጥላቻ ፍሬ ታፍሳታለህ፡፡ ነገ የበደልከው፤ ያከላፈትከው፤ የረገምከው
ሕፃን እጅ ላይ ትወድቃታለህ፡፡ ያኔ በቀሉን በሁለት እጅህ ትቀበላለህ፡፡ ድፍን አገር ይስማ
ተቀምጣችሁ የሰቀላችሁትን ቆማችሁ ማውረድ የሚያቅትባችሁ ቀን ይመጣል፡፡ ቱ !! አሸብር አይደለሁማ !! እንዲህ ነበር ሁሌም የምለው፡፡

እኔ ዶከተር አሸብር የሚስኪን እናቴን በደል የምከፍልበትን የመጨረሻውን ክፉ በቀል እያሰብኩ ነው ያደኩት። ኒውክሌር ቦንብ ሲኖረኝ እያልኩ፣ ወስጄ ቀለመወርቅ ግቢ እጥለውና ቁልፉን እጫነዋለሁ፡፡ የቀለመወርቅ ባርኔጣ ከነራስ ቅሉ በርሮ ኪንያ ጠረፍ ቢገኝ ግድ አለኝ? እነዛን የአሜሪካ ላሞች እንደ ኢላማ ፊት ለፊት አቁሜ በመድፍ ነገር ሆዳቸውን ብደረማምሰው፣ ወተታቸው ወደ ሰማይ ጎኖ አዲስአበባ ላይ እንደ ነጭ ዝናብ ቢዘንብ.ዠ እችን ያህል ሊሰማኝ ነው?

በአውቶሞቢል፣ በታክሲ፣ በአውቶብስ የሚጓዘውን ሕዝብ አንዳች ኃይል ኖሮኝ አፋፍሼ ቀበና
ብከተው አይወጣልኝም፡፡ የእሳት ዲንጋይ እንዲያወርድ እግዚአበሄርን ብዙ ቀን ለምኜዋለሁ፡፡ ዝም ሲል፣ “እግዚአብሄር ለአዲስ አበባ ህዝብ እዝኖ ሳይሆን ህዝቡን ተፀይፎ፣ ለእነዚህ ማን እሳት ያባክናል? ብሎ ትቷቸው ነው እያልኩ አስባለሁ፡፡

ቢሆንም አንድ ቀራፎ አስተማሪ አፉን ከፈተብኝ ብዩ አልተዘናጋሁም፡፡ ብዙ ስዎች ጎበዝ ተማሪ ነህ ሲሉኝ ይገርመኛል፡፡ እኔ ምንም የተለየ ነገር አላደርግም፡፡ አስተማሪው ሲናገር፣ የፃፍኩትም
ሳነብ፣ ከዚህ በፊት የማወቀውን ታሪክ የምሰማ ነበር የሚመስለኝ፡፡ ፈተናዎችን ሁሉ እኔ ራሴ
ያወጣኋቸው እስኪ መስለኝ ነበር መልሶቻቸውን ጠንቅቄ የማውቀው። በትምህርት ቤታችን
ማንም ጎበዝ ነኝ የሚል ተማሪ ሲያድግ ከእኔ ጋር እኩል መሆን ይመኝ ነበር ብል ማጋነን
አይሆንም፡፡ እነሱ እስከሚያድጉ ቆሜ እጠብቃቸው ይመስል !! “የዛሬ ምናምን ዓመት አሽብር
የደረሰበት እንደርሳለን” የዛሬ ምናምን ዓመት አሸብር የኒውክሌር ቦምብ ባለቤት ይሆናል ቡምምምምምምምምምምምምምም ጥርግርግ !

እነዚህ ጉረኛ ሴቶች ሁሉ ሰው ሰራሽ ፀጉራቸው እንደችቦ አናታቸው ላይ እየነደደ በቀላ
ጫማቸውን ወርውረው በባዶ እግራቸው ለመዳን ሲሮጡ ሆዴን ይዤ እስቃለሁ፡፡

ሽማግሌዎች መሸሽ አቅቷቸው ሲንቀጠቀጡ፣ እነዛ ልጆቻቸውን በትልቅነት ያልገሰፁ ሁሉ
አላዝንላቸውም፡፡ የቀለመወርቅን ቀደል ዓይተው እንዳላዩ ያለፉ ዓይኔ አፍንጫዬ ቁርጥ
ቀለመወርቅን መምሰሉን እያዩ፣ “ብየት ቤት ብሎ! ኧረ ቀለመወርቅ ቀጭን ጌታ ነው፡፡ እዚህ
ቋቁቻም ጋር ምኑም አይመሳሰል” እያሉ ያሽቃበጡ ሁሉ አባቴ ጣረሞት ነው ብዬ እልቂት
ይዤ ፊታቸው ስቆም፥ “ቁርጥ ጣረሞትን” ይሏታል አልምራቸውም ! “ታላላቆቻችሁን
አክብሩ፣ ከወንበራችሁ ተነሱላቸው ሲሉ ይገርመኛል፡፡ ብችል ታላላቆቹን ከነከዘራቸው
እያነሳሁ ሳፈርጣቸው፣ አልያም ከወንበር መነሳት ሳይሆን ወንበር አንስቼ ጎባጣ ወገባቸው
ላይ፣ ሽበታም አናታቸው ላይ ባፈጋባቸው ደስታዬ ነው፡፡ ቅሌታም፣ አስመሳይ ሁሉ፡፡ ነገር
ከዛ ከዚህ ሲያቃሉ ስላረጁ ትልቅ የሆኑ ይመስላቸዋል፡፡ ውቤ በረሀ ሴት ሲያሳድዱና አተላ
ሰጋፉ ያረጁ አስመሳዮች፤ በአባቶቻችን ስም አድዋ የዘምቱ፣ ማይጨው ላይ እልፍ የመከቱ
መስለው ደኮፈሳሉ፡አላከብራቸውም፡፡ የአንዲትን ሴት እንባ ማበስ ያቃታቸው፣ በጠራራ
ፀሐይ እውነትን የሸመጠጡ “እንምከር" ሲሉ ያቅለሸለሹኛል፡፡..

አላለቀም
24👍17
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ከፕሎሜ ጎዳና ላይ ያለ ቤት

ፕሎሜ ከተባለ ጎዳና ላይ ንብረትነቱ የመንግሥት ባለሥልጣን የሆነ ባለአንድ ፎቅ ቤት ነበር፡፡ ቤቱ ሁለት ክፍል ቤት ከፎቁ ላይ፣ ሁለት ክፍል
ደግሞ ከምድር ቤት ነበረው፡፡ በተጨማሪ እንደ ወጥ ቤት የሚያገለግል ተጨማሪ ክፍል ፎቁ ላይ ነበረው:: ከዋናው ጎዳና ጋር የተያያዘ ትልቅ የውጭ በር ሲኖረው በአበባ ያጌጠ ሰፊ ግቢ አለው:: ከበስተጓሮው እንደ
እቃና ማድቤቶች ሊጠቅሙ የሚችሉ ሌሎች ሦስት ክፍሎች ነበሩ:: በጓሮ በኩል ደግሞ የምሥጢር በር አለው::
ምስጢሩን ለሚያውቅ እንጂ ይህ
በር፣ በር መሆኑ በቀላሉ አይታይም:: ቤቱ ብዙ ጊዜ ሰው አይከራየውም::

በ1829 ዓ.ም አንድ በእድሜ በሰል ያለ ሰው መጥቶ ይህን ቤት
ይከራየዋል፡፡ ሰውዬው ብቻውን አልነበረም:: አንዲት ወጣት አብራው ነበረች፡፡ ይህ ሰው ዣን ቫልዣ ነው:: ወጣትዋ ልጅ ደግሞ ኮዜት ናት፡፡ ቀደም ሲል ዣን ቫልዣ ይረዳት የነበረችው አሮጊት ደግሞ አብራቸው ናት:: ስምዋ ቱሴይ ይባላል:: ዣን ቫልዣ ቤቱን የተከራየው መሴይ ፎሽለማ በሚል ስም ነው::

ዣን ቫልዣ ለረጅም ጊዜ የኖረበትን ገዳም ለቅቆ ከወጣ በኋላ ምን
ተፈጸመ ቢባል ምንም የሆነ ነገር የለም:: እንደሚታወሰው ዣን ቫልዣ ገዳሙ ውስጥ ደስ ብሎት ነበር የሚኖረው:: በየቀኑ፡ ኮዜትን ያገኛታል።በተገናኙ ቁጥር ፍቅራቸው እየጠናና የአባትነት ስሜቱ እየዳበረ ይሄዳል፡፡
ልጅትዋን ፈጣሪ የሰጠው ፀጋ እንደሆነች ከማነ ባሻገር ይህችን ልጅ ከእርሱ ማንም ሊለያት እንደማይችል ገምቷል:: እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ከእርሱ የማትለይ ፍጡር ለመሆንዋ አልተጠራጠረም:: ይህም ደስታውን እጥፍ አደረገለት፡፡ ነገር ግን ልጅትዋን የግሉ ሀብት አድርጎ በመቀበልና የደስታው ምንጭ እንድትሆን በማድረጉ በመጠኑም ቢሆን የሕሊና ወቀሣ
ነበረበት::

ይህቺ ልጅ ገና እምቡጥ ናት:: ምንም ነገር አታውቅም:: ሕይወትዋን እንደፈቀደ የሚመራው ዣን ቫልዣ ነው:: ይህንንም ያደረገው ከክፉ ነገር
ላይ እንዳትወድቅ በማሰብ ነበር፡፡ ሆኖም ይህን ዓይነቱ አስተዳደግ የዓለምን ምንነት ለማወቅ እድል አልሰጣትም:: የራስዋን እድል ራስዋ ልትወስን አልቻለችም:: እንደ እውነቱ ከሆነ ሰውዬው ይህቺን ልጅ እንደ ቦይ ውሃ የመራት ከእርሱ እንዳትሄድ እንጂ ሙሉ በመሉ ለእርስዋ ብሎ አልነበረም፡፡
ይህ ነው የሕሊና ወቀሣ ያስከተለበት::
ከመነኩሴ ትምህርት ቤት ያስገባት እርሱ ነው:: መነኩሲት እንድትሆን የወሰነው እርሱ በመሆኑ ምናልባት ስታድግ በዚህ የተነሣ ልትጠላው ትችላለትች፡ ይህንና ይህን የመሳሰለ አሳቦች ናቸው ገዳሙን ለቅቆ እንዲወጣ
ያደረጉት:: ከዚህ ለመውጣት ከውሳኔ አሳብ ከደረሰ በኋላ አልቆየም::ግቢውን ለቅቆ ለመውጣት ጥሩ አጋጣሚ እየጠበቀ ሳለ ሽማግሌው ፎሽለማ መሞታቸው በዚሁ ሳቢያ ግቢውን ለቅቆ ወጣ፡፡

ከገዳሙ ሲወጣ ለገዳሙ አለቃ የነገራቸው ወንድሙ በመሞታቸውና እንደ እርሳቸውም መሞት የተነሣ መጠነኛ ሀብት ስለወረሰ ሌላ ቦታ ሄዶ መኖር የሚችል መሆኑን ነበር፡፡ ስለዚህ ልጁን ይዞ ያለ ብዙ ድካም ከሌላ
ቦታ ለመኖር የወሰነ መሆኑን ሲነግራቸው አልተቃወሙትም:: ልጅትዋን በማስተማር ገዳሙ ላበረከተው አስተዋጽኦ ለገዳሙ አምስት ሺህ ፍራንክ በስጦታ መልክ ሰጥቶ ነው የወጣው::

ከገዳሙ ሲወጣ የማንንም እርዳታ ሳይጠይቅና ማንንም ሳያስቸግር
ያቺን ትንሽ ሳጥን እርሱ ራሱ በእጁ ይዞ ነው የወጣው:: የሳጥንዋን ቁልፍ ዘወትር ከእርሱ አይለያትም:: ስለሳጥንዋ ኮዜት ሁልጊዜም ትገረማለች፡፡አንድ ዓይነት የተለየ ጠረን አላት:: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሳጥንዋን ከራሱ አይለያትም:: ሁልጊዜም የሚያስቀምጣት ከራሱ ክፍል ውስጥ ነው:: ከቦታ ወደ ቦታ በተዘዋወሩ ቀጥር እርስዋን ብቻ ነው አንጠልጥሉ የሚሄደው::
ኮዜት «ይህቺን ሣጥን ቀናሁባት» እያለች አንዳንዴ ብቻዋን ትስቃለች::

ከጊዜ በኋላ ዣን ቫልዣ ወደ ከተማ በወጣ ቁጥር እየተጨነቀ እንጂ
መዝናናትን ከተወ ሰንበት ብሉአል:: ፕሎሜ ጎዳና ላይ ካለው ቤት ውስጥ ከገባ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ከቤት አይወጣም:: ከዚያ ቤት ውስጥ እያለ ስሙ የሚታወቀው ኧልቲስ ፎሽለማ በሚል ስያሜ ነው::

እዚያው ቤት ውስጥ እያለ ሌሉች ሁለት አነስተኛ ቤቶች ከተለያዩ
ሰፈር ተከራይቶ በስሙ ይይዛል:: አልፎ አልፎ ወደ እነዚህ ቤቶች ተራ በተራ አንድ ጊዜ ከአንደኛው በሌላ ጊዜ ደግሞ ከሁለተኛው እየሄደ ወርም ሁለት ወርም ኮዜትን ይዞ ይቀመጣል:: አሮጊትዋን ግን ይዟት አይሄድም፡፡ይህንንም ያደረገው ከፖሊሶች ለመሰወር ነበር፡፡

ከቤት ውስጥ ሲሆኑ ቤቱን የምትመራው ኮዜት ናት ገዳም ውስጥ እያለች ስለቤት አያያዝ ትምህርት ቀስማለች:: ብዙውን ጊዜ ዣን ቫልዣ በጓሮ በኩል ከነበሩት ቤቶች ውስጥ ሲቀመጥ ኮዜት ከትልቁ ቤት ውስጥ
ፎቅ ላይ ነው የምትቀመጠው:: በየቀኑ ዣን ቫልዣ የኮዜትን እጅ እየያዘ ከዚያ ከተንጣለለውና ስአበባ ከአጌጠው ግቢያቸው ውስጥ ይንሸራሽራሉ፡፡
ወደ ከተማ የሚወጠበት ቀን
ውሰን ነው:: እሑድ እሑድ ግን
ወደ ውጭ ወጣ ብለው ይንሸራሸራሉ በዚህ ጊዜ የኮዜትን ቁንጅና ተመልካች እየበዛ መጣ በርግጥ እርሷም ሁሌ የምታስበው ነው ለሽርሽር በወጡ ቁጥር ወንዶች ሰብሰብ ብለው አንዱን አፍጥጣ ስታይ አንድ ሰው ‹‹በእርግጥም ቆንጆ ነሽ የሚላት መሰላት::ትንሽ ተሽኮረመመች:: ያን እለት ማታ ጥሩ እንቅልፍ አልተኛችም፡፡ ከተኛች በኋላ «እውነትም ቆንጆ ነኝ፤ የወንዶች ልብ አሁን እኔን ይመኛል?»
ስትል ብዙ አሰበች:: ገዳም ውስጥ በነበረችበት ጊዜ የምታውቃቸውን ጓደኞችዋን በማስታወስ መልክዋን ከእነርሱ መልክ ጋር ማነፃፀር ጀመረች::
«እኔ እኮ ከእገሊት አላንስም፡፡ እገሊትም ብትሆን እስከዚህም የምትደነቅ ልጅ አይደለችም፡፡ ውይ እገሊት ግን በጣም ቆንጆ ናት:: እኔን ትበልጠኛለች ብቻ ምንዋ ነው ከእኔ የሚበልጠው?» እያለች ስለውበትዋ ታሰላስል
ጀመር::

አንድ ቀን ከግቢው ውስጥ እየተንሸራሸረች ሳለ አሮጊትዋ ቱሴይ
«ጌታዬ ይህቺ ልጅ እንዴት እየቆነጀች እንደሄደች ልብ ብለዋል?» ብላ ስትናገር ትሰማለች:: አባትዋ ምን መልስ እንደሰጠ ግን አልሰማችም::
የቱሴይ ንግግር ግን ስሜትዋን ነካው:: እየሮጠች ወደ ክፍልዋ ሄደች::
ከመስታወት ፊት ቆማ መልክዋን አየችው:: መስታወት በማየት መልክዋ ካስደነገጣት አንድ ሦስት ወር ያህል አልፎአል፡፡ የመጀመሪያው ቀን ሰው
ሳያያት ትንሽ አልቅሳለች:: የምታየው ራስዋን ሳይሆን የሌላ ሰው መስሎአት ነበር።

በጣም ቆንጆ ለመሆንዋ ለሁለተኛ ጊዜ አረጋገጠች:: መስታወቱና
ቱሴይ ያሉት ነገር ትክክል እንደሆነ አልተጠራጠረችም:: ቅርጽዋ፣ የቆዳዋ ቀለም፣ ፀጉርዋ፣ ዓይንዋ፣ ጥርስዋ፣ አፍንጫዋ ይህ ቀረሽ የምትባል ልጅ አልነበረችም:: ውበትዋ እንደጠዋት ፀሐይ ፊትዋ ላይ በራ፤ ተንጸባረቀ፣ ደመቀ፡፡ ወደ አበባው ቦታ ተመለሰች:፡ ወፎች ስለእርስዋ የሚዘምሩ መሰላት።
ራስዋንም እንደ ንግሥት ለመቁጠር ቃጣች::

ተመልሳ ስትመጣ ዣን ቫልዣ በአያት ጊዜ ልቡ ደነገጠ፡፡ የኮዚት
👍194
ውበት በየቀኑ እየፈካ መሄዱን ቀደም ብሎ የተገነዘበው ቢሆንም ያን እለት ግን በጣም አስደነገጠው:: እርሱን እንደዚያ ያስደነገጠው ውበት የወጣቶችን
ልብ በቀላሉ ሊሰርቅ እንደሚችል አመነ፡፡
«እንዴት ቆንጆ ናት» አለ ለራሱ፡፡ «መጨረሻዋ ምን ይሆን? ማን
ይሆን ከእኔ ነጥቆ የሚወስዳት?» ሲል አሰበ:: በሚቀጥለው ቀን «እውነትም ቆንጆ ነኝ» ስትል ተናገረች:: ከዚያን ቀን ጀምሮ ስለምትለብሰው ልብስ ጥንቃቄ ታደርግ ጀመር:: ከዚያ በኋላማ
ኮዜት ከሰፈሩ ቆንጆዎች እንደ አንድዋ ከመቆጠር አልፋ ጥሩ ጥሩ ልብስም የምትለብስ ዘናጭ ልጅ በመባል በሰፈሩ እየታወቀችና ዝናዋ እየገነነ ሄደ።
አንድ ቀን ዝንጥ ብላ ለብሳ ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ «አባዩ ዛሬ እንዴት ነው አለባበሴ?» ብላ ጠየቀችው::

ምኑ ይነገራል፧ በጣም አምሮብሻል» ሲል የሀዘን ስሜት እየተሰማው መለሰላት::

ይህን መልስ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ «አባዩ፣ እቤት ካንተ ጋር መቀመጡ በጣም ደስ ይለኛል» ትል የነበረችዋ ልጅ ሰበብ አስባብ እየፈጠረች «ልሂድ፣ ልሂድ » ሆነ፡፡ እውነትዋን ነው፤ ቆንጆ ሆኖ ቆንጆ ልብስ እየለበሱ ከቤት መዋል ምን ይባላል፡፡ እንዲህ አምራና ደምቃ የመስከረም አበባ በመሰለችበት
ጊዜ ነው ማሪየስ ስድስት ወር ሙሉ ከጠፋችበት በኋላ ያያት::

ልክ እንደ ማሪየስ ኮዜትም ከፍቅር ረመጥ ውስጥ ገብታ ለመቃጠል
ዝግጁ ሆነች:: ተፈጥሮ በሚደነቅ ሁኔታ እነዚህን ሁለት ወጣቶች ለማገናኘት ታጥቆ የተነሣ ይመስል ሁለቱም በየፊናቸው የሰው ያለህ የሚሉበት
ጊዜ ሲሆን ሁለቱ ቢገናኙ ማርና ወተት መሆናቸው አያጠራጥርም::
ሁለት ሰዎች በዓይን በመተያየት ብቻ ፍቅር አይዛቸውም የሚሉ
አሉ:: ግን መዘንጋት የሌለበት ፍቅር የሚጠነሰሰው በመተያየት መሆኑን ነው:: የተቀረው በኋላ ይቀጥላል፡፡ ልብን ከሁለት ከሚሰነጥቀው ከመጀመሪያው እይታም ይበልጥ የእውነተኛ ፍቅር ብልጭታ፣ ጥንስስ፣ እንቅልፍ የሚነሳና የሚያስደነግጥ የለም፡፡ ኮዜትና ማሪየስ ከአንድ የሽርሽር
ቦታ ብዙ እየተሰራረቁ መተያየታቸው የምናስታውሰው ነው::

ማሪየስ ኮዜት ከምትገኝበት ሲሄድ ምን ያህል ይፈራ፣ ይተባ፧ ምን
ያህል ይጨነቅ፤ ምን ያህል ያመነታም እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ለካስ ራቅ
ብሎ ተቀምጦ ኮዜትን በሩቁ ብቻ ሊያያት ያንገበግባት ኖሮአል:: አንድ ቀን ዣን ቫልዣን «አባባ፣ በዚህ በኩል እንሂድ እስቲ» አለችው ማሪየስ ወደ
ተቀመጠበት እያመለከተች፡፡ ይህን ያለችው ማሪየስ ወደ እርስዋ አለመምጣቱን በመገንዘብዋ ነበር፡፡ እርሱ አልመጣ ሲላት እርስዋ ወደ እርሱ ሄደች::
ያን እለት የኮዜት አስተያየት ማሪየስን አሳበደው:: የማሪየስ አመለካከት ደግሞ ኮዜትን አርበተበታት፡፡ ኮዜት እንዳፈቀረችው ማሪየስ እርግጠኛ ሆኖ ሲሄድ ኮዜትን ግን አስጨነቃት፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ አንዱ ሌላውን ያመልካል፤ልባቸው በጽኑ ይፈላለጋል::
ኮዛት በመጀመሪያ የተሰማት በጭላንጭል የሚታይ የሀዘን ስሜት ነበር፡፡ የወደፊት ሕይወትዋ በጭንቀት ተሞልቶ የጨለመ መሰላት::
የወጣት ልጃገረዶች ልብ እንደ በረዶ ነው:: ልባቸው ገራገር ስለሆነ እንደ በረዶ የነጣ ሲሆን የፍቅር ፀሐይ የወጣለት በቶሎ ይሟሟል፡፡ በሕልምዋም
ሆነ በእውንዋ የሚታያት መሽኮርመም፣ መዳራትና መላፋት ይሆናል::ስለዚህ ከማሪየስ ጋር ይህን ለመፈጸም ፈለገች ፧ ጓጓች፤ ተመኘች:: በአንድ በኩል ማሪየስን በማድነቅ በሌላ በኩል መቼ ነው የማገኘው በማለት
ተጨነቀች::

ማሪየስ ማንና ምን እንደሆነ አታውቅም:: እርሱም ቢሆን ስለእርስዋ ያለው እውቀት ከዚህ የተለየ አይደለም:: ቃል አልተለዋወጠም፤ ሰላምታ
አልተሰጣጡም፤ አልተዋወቁም:: እውቀታቸው በዓይን ብቻ ሲሆን እንደ ሰማይ ከዋክብት በአካል ተራርቀዋል፡፡

በእለት ኑሮአችን ለእያንዳንዱ ሁናቴ ስሜታችን መልእክት
ያስተላልፍልናል፡፡ በዚህ ዓይነት ተፈጥሮ ማሪየስ በቤቱ አካባቢ ለመኖሩ ዣን ቫልዣን አስጠንቅቃዋለች:: ዣን ቫልዣ ያየው ወይም የሰማው ነገር
አልነበረም፡፡ ሆኖም አንድ ነገር እየዳበረ ለመምጣቱ ታውቆታል፡፡ ያቸው ተፈጥሮ ማሪየስን ከልጅትዋ አባት ጋር ፊት ለፊት አላጋለጠችውም፡፡ ነገር
ግን ፊት ለፊት ባይገጣጠሙም ማሪየስ ኮዜትን ለመፈለጉ ገብቶታል፡፡

ኮዜትን ለመጠየቅ አልደፈረም:: አንድ ቀን ግን ስሜቱን ለመደበቅ
አልቻለም:: ማሪየስን ባየው ጊዜ «ምን ዓይነት ልጅ ነው!» ብሎ በማንቋሸሽ ይናገራል::

ይህን ያለው ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆን ኖሮ «ምነው፣ በጣም ደስ
ይላል» ትለው ነበር፡፡ አሁን ግን «ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም» እንዲሉ ይህን ብላ መናገር አልቻለችም:: ምናልባት ከኣሥር ዓመት በፊት ቢሆን ደግሞ «ልክ ነህ፣ ሁኔታው ይህን ያህል ደስ አይልም» ብላ በተናገረች፡፡
አሁን የደረሰችበት እድሜና ያደረባት የስሜት መቧጠጥ ግን ስሜትዋን ሰብሮ «የቱ፣ ያ ወጣት!» የሚል መልስ በማንቋሸሽ እንድትሰጥ ገፋፋት፡፡
ይህን መልስ የሰጠችው ልክ በሕይወትዋ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየችው አስመስላ ነው::

«እንዴት አላስብም» አለ ዣን ቫልዣ በልቡ:: በአጠገባችን ማለፉን እንኳን ልብ አላለችም፡፡ እንድታየው እኔው ራሴ ገፋፋኋት::
አይ የዋህነት! አይ ብልጠት!
ዣን ቫልዣ ልቡ ላይ አንድ ዓይነት ሕመም ተሰማው:: ኮዜት ፍቅር ሲይዛት ታየው፡፡ ይህ ደግሞ ቶሎ እንደሚሆን ተገነዘበ፡፡ ከፍቅር ማንቋሸሽ ይቀድም የለ!

ኮዜትና ማሪየስ በተያዩ ቁጥር እርሱ ያፈጣል፤ ኮዜት የፈገግታ አበባ ታስታቅፈዋለች፡፡ ዣን ቫልዣ ማሪየስን በዓይን አለንጋ ይገርፈዋል፡፡ ኮዜት እንዳታውቅበት ግን በተቻለ ሁሉ ይጠነቀቃል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ከዚያ
ከሽርሽር ቦታ ሲሆን ከዚያ በኋላ ምን እንደተከተለ ሁላችንም የምናውቀው ነው::

ከዚያ ሥፍራ ሲቀሩ ኮዜት ጥያቄ አልጠየቀችም ፧ ተከፋሁም
አላለችም፡፡ ምክንያቱን ለማወቅ ብትጓጓም ስሜትዋን አምቃ ዝም አለች::ዣን ቫልዣ በፍቅር ሳቢያ ስለሚደርስ የውስጥ ጭንቀትና መከራ ልምድ የለውም፡፡ ስቃዩ እንደሚያስደስት፧ ስቃዩ እንደሚያስለቅስ አያውቅም::
ነገሩ «ያልተነካ ግልግል ያውቃል» ነው:: ኮዜት ስትደበር፤ ኮዜት ስትዘጋ፤ ኮዜት ስትከፋ እያየ ለማየት አልቻለም:: ማዘንዋን ግን ትንሽ ጠርጥሮአል፡፡
ነገር ግን፦ «ምን ያስከፋታል» በማለት እንደማጽናናት እርሱ ራሱ ቅር ተሰኘ፡፡

አልፎ ኣልፎ «ምን ነካሽ?» እያለ ይጠይቃታል፡፡

«ምንም» ብላ ትመልስለታለች::

አብረው ሲሆኑ ዝምታ ይሰፍን ጀመር፡፡ እርስዋ እንዳዘነችው እርሱም አዝኖአል:: ይህ በሚሆንበት ጊዜ ነው በተለይ «ምን ነካሽ?» እያለ
የሚጠይቃት::
እርስዋም ‹ምንም» ብላ አትተወውም:: ኣንዳንድ ጊዜ «አንተስ ኣባዬ ፧ ምንም አልሆንክም?» በማለት ትጠይቀዋለች::
«እኔ! ምንም፣ ምንም አልሆንኩም» ሲል ይመልሳል::
እነዚህ በፍጹም ልቦና የተዋደዱ ለረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ ሁለት
ሰዎች አንዱ ለሌላው ስቃይ ምክንያት ሆነ:: ሆኖም «አንተ አስቀየምከኝ፣አንቺ አስቀየምሽኝ» አይባባሉም ፣ አልተቀያየሙም ፤ አልተኳረፉም:: በፈገግታ ይነጋገራሉ፡

💫ይቀጥላል💫
👍28
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ዘጠኝ

የአስቴር ትልቋ ልጅ ዛፒ ትባላለች፡፡ ትርጉሙ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ምናልባትም 'ሰይጣናዊ መዝገበ ቃላት የሚባል ነገር ካለ፣ ትክከለኛ ትርጕሙ እዛ ላይ ሳገኝ አይቀርም፡፡ እስከዛው
ግን በግምት “ዋጋ ቢስ' ብዬ ተርጉሜዋለሁ።

ዘር ከልጓም ይስባል እንዲሉ ቁርጥ እናቷን (ለነገሩ አባቷን የት አውቄው?)እኔ ከስምንተኛ ክፍል
ወደ ዘጠነኛ ክፍል ሳልፍ እሷ የሀያ አምሰት ወይም የሀያ ስድስት ዓመት ወጣት ነበረች፥ ተስፋ
የቆረጠች ወጣት፡፡ እናቷ አስቴርና ትንሽ እህቷ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ውጭ አገር ሲመለሱ
እሷ እዚሁ እኛ የነበርንበት ግቢ ውስጥ ከንድ ደስ የሚል የተረጋጋ ወጣት ጋር መኖር ጀመረች፣

ምናልባት እዚሁ የቀረችው ልጁን ስለወደደችው ይሆናል፡፡

መጀመሪያ መኪናውን ውጭ ጋር ያቆምና ተያይዘው ይሄዱ ነበር፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ዋጋ ቢሷ ትጠራኝና አሸብር ኛ እችን መኪና ወልውል!” ትላለች፡፡

ዛፒዩ አሁን እኮ ነው ያሳጠብኳት!” ይላታል፡፡ እርሱ የዋጋ ቢሷ መልዕክት ተንቀጥቅጦ
የሚታዘዛት ሚስኪን መኖሩን ማሳየት መሆኑን መቼ አውቆ፡፡

ቆይታ እቤት እየገባ መቆየት ጀመረ፡፡

“አሽብር ና ለስላሳ ግዛ! ና ቢራ ግዛ” ብታምኑም ባታምኑም ኮንዶም ሁሉ ታስገዛኝ ነበር፡፡
መላላኬ ሳይሆን በዛ እድሜ ፋርማሲ ሂዶ ኮንዶም መግዛት ያሳቅቀኝ ነበር፡፡ ፋርማሲስቶቹ
በትዝብት ያዩኛል፣ “የተቀደደ ሱሪውን ሳይቀይር…” በሚል ግርምት…ሱሪው የተቀደደ ሰው
እንትን አያደርግም የተባለ ይመስል፡፡

ከዛ ማደር ጀመሩ፡፡ በጨለማ በዛ በኮረኮንች መንገድ ቢራ ተሽከሜ እጀን የፌስታሉ እጄታ እየከረከረኝ የተላላኩበት ጊዜ መቼም አይረሳኝም (እስከዛሬ እቃ በፌስታል መያዝ አልወድም፡፡ አቲዩ የግቢው በር ላይ ብርድ እያቆራመታት ቆማ ትጠብቀኛለች፤
ገብቼ ቢራውን ስሰጥ ዛፒ ልክ ከፍሪጅ ያወጣችው ያህል ከእጄ ላይ ትወስድና፣ እንካ ሁለት ፓኬት ሮዝማን ግዛና ና” ትላለች፡፡
በመጨረሻ ጠቅልሎ ገባና አብረው መኖር ጀመሩ፡፡ መኪና ማጠብ ቋሚ ስራዬ ሆነ፡፡ እውነቱን
ለመናገር ጥሩ ባል ነበር፡፡ ዋሲሁን ይባላል። ቤቱ የባለትዳር ቤት እንዲመስል የተቻለውን ሁሉ
ይጥር ነበረ፡፡ ዛፒ ግን የሚቋቋማት ዓይነት 'ሚስት አልነበረችም፡፡ ጉራዋ ፀጉር ያስነጫል፣ በውበቷ ስትመካ ልክ የላትም፡፡ የእናቷ ጫማ ውስጥ ዘላ የገባች ጉረኛ ! አቤት ጉረኛ ሴት እንዴት እንደምትቀፍ፡፡ ከምትናገራቸው አስር ዓረፍተ ነገሮች፣ አስራ አንዱ ስለራሷ ውበት፣ ስለቆዳዋ ጥራት፣ ስልጣቶቿ አለንጋነት፣ ስለልብስና ሽቶዎቿ ብራንድ በቀጥታ አልያም በተዘዋዋሪ ይተርካሉ ፡፡

ዘላ የተዘፈቀችበት ትዳር ከጭፈራ ቤት መዳራት በምን እንደሚለይ ገና ያልገባት አካሏ ብቻ
ህሊናዋን ጥሎ ያደገባት ከንቱ ነበረች፡፡ ዋሲሁን ውጭ መመገብ አይወድም፡፡ የታሸጉ ምግቦችን
ገና ሲመለከታቸው ያንገሸግሸዋል፡፡ እንጀራ በሽሮ ወጥ ነፍሱ ነው:፡ ዛፒ ታዲያ ቤት ውስጥ ለባለቤቷ ምግብ አብስሎ ማቅረብን በሴት ልጅ ላይ የሚፈፀም ታላቅ በደል አድርጋ ነበር የምታየው፡፡አበሻ ወንድ ጓዳለጓዳ ካልተንደፋደፈች ሚስቱ ሚስት አትመስለውም፡፡ ሴት አደባባይ መውጣቷ ያማቸዋል” የምትለው ከእናቷ የወረሰችው ዘይቤ አላት፡፡ በጓዳም በአደባባይም ምንም የማትፈይድ የወሬ ቋት፡፡ ኩኪስ አልያም ጭማቂ ነገር ከፍሪጅ ታወጣና ሶፏዋ ላይ እግሯን አጣጥፋ ቴሌቪዥን እያየች ትበላለች፣ ትጠጣለች፡፡ ስለፋሽን ሳታቋርጥ ትቀባጥራለች፤ በዓለም ላይ ስላሉ የቅንጦት ሆቴሎችና ጌጣጌጦች ዋ.….ው” እያለች ትቋምጣለች፡፡ ቤትም የለችም፡ የምትመኘውም ቦታ የለችም፡፡ የትም የሌሎች የውሀ ላይ ኩበት ነገር!!

ዋሲሁን ያደበትን የቤተሰብ ስነስርዓት፣ የኢትዮጵያዊነ ወግ ምሳ ተዘጋጅቶ፣ ቡና ተፈልቶ፣ ቤቱ
ሞቅ ብሎ እንደሚጠብቀው በማመን እንደ ኣባወራ
ምሳ ሰዓት ላይ ሲመጣ ዛፒ ጠረጴዛው ላይ እግሯን ሰቅላ ዙሪያዋን የጥፍር ቀለም ጠርሙሶች ከበዋት ቤቱ በአልኮል ሽታ ታፍኖ ስትቆነጃጅ
ያገኛታል፡፡ ማታ ሲመጣ ዛፒ ለባብሳ ኣንዲወጡ ስትጠብቀው ይደርሳል፡፡

ሀኒ ዎከ እናድርግ ትለዋለች፣ ባል ጋር መታየት እንጂ የባልን መሻት ማየት አልፈጠረባትም፣
የሆሊዉድ ተረቶች ባዶ ጭንቅላቷን ሞልተውት ነበር፡፡ ከንዱን ይዛ መንገድ ላይ ስትውረገረግ ብጤዎቿ፣ “ዋው ምናይነት ጥምረት ነው? ማች ያደርጋሉ" እያሉ ያወሩላታል፡፡
ሚስኪን ዋሲሁን ሳይወድ በግድ እግሩ እስኪቀጥን ሲዞር አምሽቶ እኩለ ሌሊት ላይ ስልችት
ብሎት ይመለሳሉ፡፡ የተሰቀለችበት ባለ ተረከዝ ጫማ ለመራመድ ስለማይመቻት ክንዱ ላይ
ተዘፍዝፋ ትወናገራለች፡፡

“ሃኒ ዲጄው ሽቶሽ ብራንዱ ምንድን ነው?' ሲለኝ ሰምተኸዋል?”

“አልሰማሁትም ይላል ትክት ብሎት፡፡

"ሃሃሃሃሃሃሃ ጠጥተህ ነበር ብዙ.ሰካራም ሃሃሃሃሃ” ትላለች እየተለፉደደች፡፡ አብሯት አይስቅም፡፡

"በናትህ ቀሚሴ ላይ ዋይን ደፋብኝ ያ ወልካፋ አስተናጋጅ" ትላለች ረዥም የራት ቀሚሷን
እያሳየችው::

“ይታጠባል.ደግሞ አንቺ ስታልፊ እኮ ነው የገጨሽው” ይላታል ስልችት ብሎት፡፡

“እዚህ አገር ምን ላውንደሪ አለ? ሰባት መቶ ዶላር የወጣበት ቀሚስ እንደቀልድ - ምን አይነት
አገር ነው? ብላ ቀሚሷ ባአደባባይ ባለመከበሩ አስራ አምስት ቀን ታወራለች፡፡ ስለ ተራ ቀሚስ
ሳይሆን ስለ ባንዲራ መደፈር የምታወራ ነው የምትመስለው::
ጧት ተነስቶ በተሳሳት መንፈስ ወደ ስራ ሲሄድ ዛፒ አትሰማም አትላማም ተኝታለች፡፡ ምሳ
ሰዓት እንደገና ጓደኞቿ ጋር እንደሄደች ትደውልለትና፣ “ምሳህን ውጭ ብላ ሃኒ" ትለዋለች፣ በዛውም አያችሁ ባሌን ሳዘው!' እያለች በከንቱ ጓደኞቿ፡፡ ምሳ፣ ራት፣ ቁርስ በአበሻ ባህል
ከምግብ የዘለለ ፋይዳ ያለው ጉዳይ መሆኑ ለዛፒ አልታያትም ነበር፡፡

የቤተሰብ እትብት ከእናት ማዕድ ጋር እንደሚያያዝ ማን ይመከራታል? ዋሲሁን ለአንድ ዓመት አብሯት ቆየና ከፉ ደግ ሳይናገር፣ አንቺ ጋር እንግዲህ በቃኝ ብሏት ሄደ...!! መሄድ ብቻ
አይደለም፡ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ድል ባለ ሰርግ ሌላ ሴት አገባ፡፡ ዛፒ መጀመሪያ፣ “ጥርግ
ይበል! ለሞላ ወንድ!" አለች፡፡ ቆይታ፣ “ይሄ ችጋራም ፒዛ እንኳን መብላት ያለማመድኩት እኔ
ነበርኩ፡ ጥጋበኛ የደሀ ልጅ” ማለት ጀመረች፡፡ በመጨረሻ ፎቶውን እያየች ማልቀስ ሆነ ስራዋ፡፡

ዛፒ ሲበዛ ቆንጆ ናት፡፡ ልብሶቿ ጌጣጌጦቿ የብዙ ሴቶች የቁም ቅዠት፡፡ ግን ዋሲሁን ከሄደ በኋላ
ወንድ የሚባል አልቀርብ አላት፡፡ ይፈሯታል፡፡ የተጋነነ ቁንጅናዋና ውድ ጌጣጌጦቿ የማትደፈር
ግዛት ስለሚያስመስሳት የሚመኛት እንጂ ድፍሮ የሚቀርባት ጠፋ፡፡

የአበሻ ወንድ ተመካከሮ ሸሸ

ዛፒ ታዲያ የለየላት ስካራም ሆነች። ማታ ማታ ሰክራ ትመጣና፣
በምን አባታችሁ ዕድላችሁ ነው እኔን የምትስሙት!? እዛ የጉራጌ ጫማ ደንቅረው የቻይና ሱሪ ውስጥ የተቆጠሩ ኋላ ቀር ሠራተኛ ሴቶቻችሁ ጋር ኑሩ! ጎ ቱ ሄል ቆሻሾች! ቦርጫሞች! ቀ'ጂም'
አጠገብ አልፋችሁ የማታውቁ” እያለች በረንዳዋ ላይ ቆማ ድፍን የአበሻን ወንድ ትሳደባለች ።

በጣም ስከር ብላ ጨርቅ ሆና ያመጣት ባሰታከሲ ግቢ ውስጥ ደግፎ አስገብቷት ሲመለስ
ትጠራኛለች፣

“አሸብር ና ጫማዩን አውልቅ!”
👍26👏1
ጫማዋን አወልቅላታለሁ፡፡ እች የውሻ ልጅ! የእግሮቿ ጣቶች የመላዕክትን ጣቶቻ ይመስላሉ፤
አረዛዘማቸው፣ ጥራታቸው፡፡
ቀስ በል እንተ ! ሶሉን ልትገነጥሰው ነው፡፡ የእናትህን ኮንጎ ጫማ አደረከው፡፡ ይሄኮ አራት መቶ ዶላር የወጣበት ነው። በዚህ ችጋራም አገር ወረቀት ሲመነዘር ስንት ይሆናል አንደኛ እይደል ከክላስ የወጣኸው” (እደግጣለሁ፡፡ ማን ነገራት? ስለመፈጠሬም የማታስታውስ ሴት ደረጃዬን አወቀችው፡፡)

እስኪ አስበዋ፣ እኔ የቻይና ሸራ ጫማ የምደነቅር መሰለህ?” እየለፈለፈች መኝታ ክፍሏ
አስገባታለሁ፡፡ አቤት ሽቶዋ! ቆም ብላ አልጋውን በጥላቻ ታየውና፣ ወደ ሳሎን ትገፋኛለች፡፡
አንዘፋዘፍኩ ሳሎን ሶፋው ላይ አስተኛታለሁ፡፡ እየለፈለፈች እንቅልፍ ይወስዳታል፡፡

ጧት ምንም እንዳልተፈጠረ አታናግረኝም፣ መኖሬም ትዝ አይላትም፡፡

ዛፒን እጠላታለሁ፡፡ጉረኛ ናት፡፡ ሰው ትንቃለች፡፡ ግን የማይደበቀው ሀቅ ከእናቷ ትሻላለች፡፡ድንገት አቲዬን ትጠራትና፣

“ያውልሽ ይሄን ውሰጅ!” ብላ ገና ያልተከፈት ውድ ሽቶ ትሰጣታለች፡፡


አቲዬ ግን እጇን የሆነ ነገር ሲቆርጣት ብቻ ቁስሉ ላይ ስትረጨው ነው የማያት፡፡

ሊላ ቀን አቲዩን ትጠሪትና፣ እስቲ ቡና አፍይ!" ትላታለች፡፡ አቲዬ ሽር ጉድ ብላ፣ እጫጭሳ ቤቱን ነፍስ ትዘራበታለች፡፡ ዛፒ ግን ቡና አትጠጣም፡፡ አቲዬም ስለምትፈራ አትጠጣም፣ አነሳሰታ ወደ ቤት ትመለሳለች፡፡

ዛፒ እዕምሮዋ ጤነኛ አለመሆኑን መጠራጠር ጀምሬ ነበር፡፡

አንድ ቀን ሰላማዊት የምትባል የሰፈራችን ልጅ አገባችና ሰፈሩ በጭፈራ ቀውጢ ሲሆን ዛፒ
ጠራችኝ

"ማናት ያገባችው?” አለችኝ፡፡

ነገርኳት፡፡

“ቆንጆ ልጅ ናት እንዴ?”

“አንድ ቀን ጋሽ ዋሲሁን ጋር ሆናችሁ አሟት በመኪና ሆስፒታል የወሰዳችኋት ልጅ ናት እኮ::

“እና እሷ ልጅ ቆንጆ ናት እንዴ
ምን ልበል፣ ጨነቀኝ፡፡ “እኔ እንጃ!” አልኩ፡፡

ዝም ስትል፣ የጨረሰች መስሎኝ ልሄድ ስል፣

“መልኳ ከእኔ ይበልጣል ?” አለችኝ፡፡

“ኧረ…" ብዬ ሳቅኩ፡፡

“ምን ያስቅኸል? ዝም ብለህ የጠየቅኩህን አትመልስም?" አለች በቁጣ--

ፈገግታዬ ፊቴ ላይ ከስም፣ “አንች ላይ ጫፍሽ ላይ አትደርስም፣ እንች እኮ በጣም ቆንጆ ነሽ
እልኳት፡፡ ከልቤ ነበር የተናገርኩት፡፡

ትኩር ብላ አየችኝና፣ ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡ የክፍል ደረጃዬን የማታውቀው እንዳስገረመኝ
ቁንጅናዋን አይቼው የማላውቅ መስሏት ነበር መሰል፡፡
“ምን አስለፈለፈኝ” እያልኩ ወደ ቤቴ ገባሁ፡፡ ግን ያደነቅኳት ሳይሆን ልኳን የነገርኳት ያህል
ውስጤን ደስ ብሎት ነበር፡፡

እየው እንግዲህ፣ “የነገር አመጣጥ እንደ ውሀ አፈሳሰስ ነው ነው የሚለው መጣፉ፡፡ ይሄን
ነው ጠብጠብጠብ ፈስስ፣ ከለል.ጎረፍ ዥቅዥቅዠቅ፣ ከዛ ግንድ የላ ድንጋይ ይጠራርገዋል፡፡
ጠብታው መኝታ ቤቱ ነው፣ ግንዱ ሰርቪሲ.:: አስቴር አወቀ ዛቲ መኝታ ቤት ድምጽዋን ከፍ
ኢድርጋ ትዘፍናለች፡፡ ምን እያለች እኔንጃ ! ምናልባት እንዴት እንደምትጎርፍ፣ እየመከረቻት
ይሆናል፡፡ አስቴር እኮ ዘፋኝ አይደለችም መካሪ ናት፡፡ ሰንቱ መኝታ ቤት እየገባች በጆሯቸው
የሚድንም የማይሆንም ነገር ሹክ ስትል ከርማለች፡፡ አስቴር ሴረኛ ናት! የዛፒ ዓይን እንደ አንቴና መዞ ወዲያው አሳድጎኛል፣ ሳድግ የባሰ ፈሪ ሆንኩ፡፡...

አላለቀም
👍373👎1🤔1
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

መጨረሻው እንደ አጀማመሩ አልሆነም

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ኮዜት ከሀዘንዋ እያገገመች መጣች:: የጊዜው
መርዘም፣ ወጣትነትዋ፣ የአባትዋ ፍቅርና የአካባቢዋ ማማር ቀስ በቀስ ሀዘንዋን እንድትረሳ ረዱዋት:: ቀን አልፎ ቀን ሲተካ፧ ወር አልፎ ወር ሲተካ የፍቅርዋ ሙላት በየቀኑ በጠብታዎች እየጎደለ ሄደ:: ወላፈኑ በርዶ
ወደ መጥፋት ተቃረበ፡፡ ሆኖም ረመጠ ጨርሶ ስላልጠፋ ማቃጠሉ፣ ማስጨነቁና ማሰቃየቱን ትቶአታል እንጂ ጨርሶ አልተወገደም::

አንድ ቀን በድንገት ማሪየስ ታወሳት:: «ምን!» አለች:: «ደግሞ ከየት መጣ? ረስቼው አልነበረም እንዴ!» በማሪየስ በኩል ደግሞ «ምነው ከመሞቴ በፊት አንድ ጊዜ ብቻ ባየኋት!» የሚልበት ወቅት ነበር፡፡

የማን ጥፋት ነው? የማንም::

አንዳንድ ሰው ከገባበት ወጥመድ በቀላሉ መውጣት አይችልም፡፡
ማሪየስ የዚያ ዓይነት ሰው ነው:: ከደረሰበት ሀዘን እንደ ኮዜት በቀላሉ ሊላቀቅ አልቻለም:: ሀዘን ውስጥ ገብቶ እዚያው ነው ተዘፍቆ የቀረው።

አንድ አጋጣሚ ይከተላል፡፡ በትልቁ በር በኩል ከአንድ ግቢ ውስጥ
አንድ እንደ መቀመጫ የሚያገለግል ጥርብ ድንጋይ ነበር፡፡ እንደ ሴት ጎፈሬ
የተከረከመ የዛፍ አጥር በአጠገቡ ስለነበር ማንም ሰው በመንገድ ሲያልፍ ወደ ውስጥ ማየት አይችልም፡፡ ነገር ግን ከውስጥ ያለ ሰው ከፈለገ እጁን
በአጥሩ ቀዳዳ በማበጀት አሾልኮ በውጭ የሚያልፈውን ሰው ማየትና መጨበጥ ይችላል፡፡

አንድ ቀን ማታ ዣን ቫልዣ ወደ ውጭ ወጥቶ ነበር፡፡ አየሩ ጥሩ
ስለነበር መሸት ሲል ኮሴት ከዚያ ድንጋይ ላይ ተክዛ ቁጭ ብላለች፡፡ የጥንት ትዝታዋ ተቀሰቀሰባት፡፡ ጊዜው ጨለምለም ብሏል፡፡ የእናትዋ መንፈስ ከዚያ ያለ መሰላት፡፡ ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ሄደች::

ቀደም ሲል ዝናብ ዘንቦ ስለነበር ሳሩ ያቀዘቅዛል፡፡ «ይህስ ጉንፋን
ያሲዛል ፧ ብቀመጥ ይሻላል» ብላ ወደ ድንጋዩ መቀመጫ ስትመለስ
መቀመጫው ላይ አንድ ነገር አየች:: አንድ እጥፍጥፍ ብላ የተጠቀለለ ነገር ከትንሽ ጠጠር ጋር ተያይዟል:: ከመቀመጫው ተነስታ ስትሄድ ከዚያ
አልነበረም::

ኮዜት ገርሞኣት «ምንድነው እሱ?» ስትል ራስዋን ጠየቀች:: መቼም ሰው ካላስቀመጠው በራሱ ኃይል ሊመጣ እንደማይችል ተረዳች:: ፍርሃት፣ፍርሃት፣ አላት፡፡ ድንጋዩን መንካት አልደፈረችም:: ወደኋላ ሳታይ ቤትዋ ሮጠች፡፡ ቤትዋ ከገባች በኋላ በርና መስኮት ዘጋጋች፡፡ መቀርቀሪያዎቹን
ሁሉ ቀረቀረች:: ከጥቂት ጊዜ እረፍት በኋላ ‹አባባ ተመልሷል እንዴ?»
ስትል ቱሴይን ጠየቀቻት::

«ኧረ አልተመለሰም» አለቻት::

ክፍሎቹ በሙሉ ተዘግተው እንደሆነና ከቤት ውስጥ ሰው እንዳለ እንድታይ ቱሴይን አዘዘቻት:: አጎንብሳ ከአልጋዋ ስር እንዲሁም ቁም ሣጥንዋን ከፍታ ሰው እንዳለና እንደሌለ አጣራች:: ከተኛች በኋላ ያ ያየችው
ጠጠር ተራራ አክሉ በውስጡ ዋሻ እንዳለበት አለመች::

ጠዋት ፀሐይ ስትወጣና ጨለማ ለብርሃን ቦታዋን ስትለቅ ማታ
እንደዚያ ያስፈራሩን ነገሮች እንደሚያስቁን ይታወቃል:: ኮዜት ስትነቃ ማታ እንደዚያ ያስፈራት ነገር ቅዠት መስሎ ታያት:: ስለምን ነበር የምቃዠው?» ስትል ራስዋን ጠየቀች::

ልብስዋን ለብሳ ወደ አትክልቱ ቦታ ሄደች:: ስትፈራኛ ስትቸር ማታ
ተቀምጣበት ወደነበረው የድንጋይ መቀመጫ ሄደች:: የተጠቀለለው ነገር ከዚያው ቁጭ ብሉአል:: በመጀመሪያ ትንሽ ፈርታ ነበር:: በኋላ ግን ፍርሃቱ ተወገደላት:: ደግሞም በጨለማ የሸሸነወ ነገር በብርሃን እንጓጓለታለንና ምን እንደሆነ ለማየት ቸኩለች፡፡

«አይ ምን አስፈራኝ፤ ፈትቼ ልየዋ» አለች ለራስዋ:: የተጠቀለለውን
ነገር አንስታ ከፈታታችው በኋላ አብሮ ታስሮ የነበረውን ድንጋይ ጣለችው::

አድራሻ ያልተጻፈበትና በውስጠ ወረቀት ያለው እንደ ደብዳቤ ያለ ነገር መሆኑን ተገነዘበች:: ወረቀቱን ከውስጡ ሳታወጣ አገላብጣ አየችው:: አሁን መፍራትዋ ቀርቶ «ከውስጡ ምን አለ» በማለት በመጓጓት ለማወቅ ፈለገች::
ፖስታውን ከፍታ ከውስጡ የነበረውን ወረቀት አወጣች:: በጥሩ የእጅ ጽሑፍ እንደ ጥቅስ ያሉ ነገሮች ተጽፎበታል፡፡ የገጹ ብዛት ከአንድ በላይ ነው:: እያንዳንዱ ገጽ ላይ ቁጥር ተጽፎበታል:: ሆኖም እያንዳንዱ ገጽ ሞልቶ የተጻፈበት ሳይሆን መሐሉ ላይ ብቻ ነው የተጻፈው:: የመጻፊያ ቦታ እያለ ወደ ሚቀጥለው ገጽ ይዞራል::

ፊርማ ወይም ስም ካለበት በሚል በችኮላ ፈለገች፤ ግን አላገኘችም::
ለማነው የተጻፈው? ለራስዋ እንደሆነ ጠረጠረች፡፡ ምክንያቱም እርስዋ ተቀምጣበት ከነበረው ሥፍራ ነው የተገኘው፡፡ ታዲያ ማነው ጸሐፊው?
ግራ ገባት:: በመገላመጥ አካባቢዋን ቃኘች፡፡ ከርግቦች በስተቀር ምንም ነገር የለም:: ወረቀቱን ማንበብዋን ቀጠለች::
ቀጥሎ የተመለከተው ነበር በወረቀቶቹ ላይ የተጻፈው::

«ዓለም ተጨብጣ አንዲት ትንሽ ነገር ስትሆን፧ አንዲት ትንሽ ነገር
ደግሞ ተነፍታ እግዚአብሔርን ስታክል ፍቅር ትባላለች፡፡ ፍቅር ነፍስን ትመስላለች፤ አፈጣጠራቸው አንድ ነው፡፡ እንደ ነፍስ የመንፈስ ቅዱስ
ብልጭታ ኣለባት፡፡ እንደ ነፍስ ግን አትገድፍም፣ አትነጣጠልም
አትጠፋም፡፡ የእሳት ረመጥ ስትሆን በውስጣችን አለች፤ ዘላለማዊ ናት..ማለቂያና መደምደሚያ የላትም፡፡ ረመጥዋ በምንም ነገር አይጠፋም::
ከአጥንታችን ውስጥ እንኳን ገብታ ስትፋጅ ይሰማናል:: እንዲሁም ከሰማየ ሰማያት ወርዳ፧ ከአካል ውስጥ ዘልቃ ትገባለች፡፡ ሆኖም ስታንፀባርቅ አካላችን ውስጥ በጉልህ እናያታለን፡፡

«ፍቅር! አድናቆት! የሁለት የሚግባቡ አእምሮዎች ፣ የሁለት
የሚወሳሰቡ ልቦች፣ የሁለት አካልን ሰነጣጥቀው የሚገቡ ዓይኖች ያላት ብርሃን! አንቺ ደስታ ወደ እኔ ትመጪያለሽ ወይስ አትመጪም! ፍቅር
ብቸኝነትን ሲያጠቃ አብሮ የሚጓዝ፤ የሚንሸራሽር! የተባረኩ ቀኖች! የሰዎችን እድል፣ የሰዎችን እጣ ፈንታ ለመካፈል መላእክት ከሰማየ ሰማያት ወርደው
በዚህች ምድር ሲኖሩ በሕልሜ ያየኋቸው ነው የመሰለኝ፡፡ አይ ፍቅር!

«ዘላለማዊ ከማድረግ በስተቀር ማንም ከሁለት ከሚዋደዱ ፍጡሮች ደስታ ላይ የሚጨምረው ነገር የለም፡፡ በእርግጥ የፍቅር ዘላለማዊነት
ከፍቅር ዘመን በኋላ የሚታከል ነው:: ግን የፍቅርን መጠን፣ የፍቅርን ግለት ለማሳደግ ከፍቅረኞቹ ከራሳቸው በስተቀር ማንም ሊያስቀረው አይቻለውም፡፡ ፍቅር የሰዎች ፍጹምነት ይታይበታል፡፡

«ከዋክብትን የምናይበት ምክንያት ሁለት ነው:: ይኸውም
ስለሚያብረቀርቁ ወይም ምንነታቸውን ስለማናውቅ! ከጎናችን ግን ከከዋክብት
ይበልጥ ምሥጢሩ ያልታወቀ የላመ፣ የለሰለሰና የሚያንፀባርቅ ፍጡር አለ... ሴት::

«ድንጋይ ከሆንክ ትልቅ ድንጋይ ሁን፤ የዛፍና የቅጠላቅጠል ዘር
ከሆንክ ስሜት፤ ሰው ከሆንክ ደግሞ ፍቅር ይኑርህ::

«ወደ ሽርሽሩ ቦታ ትመጣለች? የለም ጌታዬ! በየሳምንቱ እሑድ ወደ ቤተክርስቲያን ትመጣ የለ? የለም መምጣቱን ትታለች:: አሁን ከዚሁ ቤት ውስጥ ነው የምትኖረው? የለም ለቅቃለች፡፡ አሁን ከየት ሰፈር ገባች?
አድራሻዋ አይታወቅም፡፡ ስትሄድ አልተናገረችም? አልነገረችንም:: ምን ዓይነት የተዳፈነ ጨለማ ነው እባካችሁ የአንድን ነፍስ አድራሻ አለማወቅ!

በፍቅር ምክንያት የምትጨነቅ፣ የምትሰቃይ ነፍስ! አሁንም ውደድ፤ በይበልጥ አፍቅር፡፡ በፍቅር መሞት ማለት በፍቅር መኖር ማለት ነውና፡፡
👍17😱1
«መወደድ እንዴት ያለ ትልቅ ፀጋ ነው:: ስለዚህ መውደድ፣ ማፍቀር
በበለጠ ፀጋን መጎናጸፍ ሲሆን በፍቅር ስሜት ልብ ይደነድናል፣ ጀግና ይሆናል ፤ ይጠራል፡፡ ማረፊያው የከበረ፣ መቆሚያው ከፍ ያለ ይሆናል፡አንጎል በፍቅር ከተሞላ ተልካሻ አሳብ ከጭንቅላት ውስጥ መግባቱን ያቆማል፡፡ አንዱ ለሌላው ያለው ፍቅር ሲያከትም የፀሐይ ብርሃን አብራ በማክተም ምድር ትጨልማለች::

ኮዜት ደብዳቤውን በተመስጦ አንብባ ስትጨርስ ስሜትዋ ረካ፡፡
ጽሑፉ ጉልህ ሆኖ ነው ያገኘችው:: እያንዳንዱ መስመር ዓይንዋን በአዲስ ብርሃን የሞላው:: እያንዳንዱ ቃል ልብዋን አፈነደቀው:: ገዳም ውስጥ
የተማረችው ትምህርት ዘወትር ይመክራት የነበረው ስለነፍስዋ ነበር እንጂ በወንድና በሴት መካከል ስላለው ፍቅር አልነበረም:: ይህ ጽሑፍ ግን
በተጣጣመና በጣፈጠ ቋንቋ ስለፍቅር ዘላለማዊነት ፣ ሀዘንና ደስታ፣ መጨረሻና መጀመሪያ ገለጸላት:: አንድ ሰው የፀሐይ ጨረርን በእጁ ጨብጦ በድንገት የወረወረባት መሰላት:: በእነዚያ ጥቂት መስመሮች ውስጥ
የጋለ ስሜትን፣ ግልጽ በሆነ ተፈጥሮ የተቀደሰ በጎ ምግባርን፤ ስፍር ቁጥር የሌለው ሀዘንና ደስታን፤ የተጨቆነ ልብን፣ የመንፈስ እርካታን አየች::

ታዲያ ይህን ጽሑፍ ማን ሊጽፈው ይችላል? ማነው ወደ እርስዋ
በአጥር ኣሾልኮ የሰደደው? ጥያቄዎቹን ለመመለስ ለአንድ አፍታ እንኳን አላመነታችም:: ከአንድ ሰው ብቻ ነው ሊመጣ የሚችለው ስትል ደመደመች::

‹‹እሱ ራሰ ነው!»

የሽርሽሩ ቦታ ትዝ አላት፡: ላይ ላዩን በጣም ደስ ሲላት ውስጥ
ውስጡን ግን የፍቅር ጥማት አንገበገባት፡፡ ይህን የመሰለ ደብዳቤ የጻፈላት ሰው ያን እለት ማታ ከአጠገብዋ ነበር ማለት ነው:: እጁን በአጥር አስገብቶ
ነው ደብዳቤውን የወረወረላት፡፡ «ከዓይን የራቀ ከልብ ራቀ» እንዲሉ ካአጠገበዋ ባለመኖሩ ልትረሳው ስትል እንደገና አገኛት:: አድራሻዋን እንዴት አገኘው?

በእርግጥ ረስታው ነበር እንዴ? የለም፣ በጭራሽ! የዚህ ዓይነት አሳብ ጭንቅላትዎ ውስጥ በመግባቱ እብድ አደረጋት፡፡ ሁልጊዜም እንዳፈቀረችውና
እንዳደነቀችው ነበር እንጂ አልረሳችውም፡፡ እሳቱ ተዳፍኖ ነበር እንጂ አልጠፋም፡፡ የፍቅር አመድ ስለበዛ ፍሙ ተቀበረ እንጂ አለመጥፋቱን ታውቃለች:: አሁን አመዱ ሲነሣ ጊዜ የፍሙ ወላፈን ሁለንተናዋን አቃጠለው፤ ለበለበው:: ደብዳቤው እንደ ብልጭታ ተፈናጥሮ ከልጁ ነፍስ
ወደ እርስዋ ነፍስ ተሻገረ፡፡ ብልጭታው አካልዋ ውስጥ ሲፋፋ ተሰማት:: የጽሑፉ እያንዳንዱ ቃል የፍቅር እሳት ብልጭታም መሰላት፡፡ «አዎን፣ አሁን አስታወስኩ፤ አሁን ገና ገባኝ» አለች፡፡ «ይኼ ሁሉ ስሜት ያኔ
ዓይኖቹ ውስጥ ያየሁት አይደለም!»

ወደ ቤትዋ ተመለሰች:: የክፍልዋን በር ዘግታ እንደገና ደግማ ደጋግማ አነበበችው ፤ በቃልዋ አጠናችው:: በደምብ ከያዘችው በኋላ ወረቀቱን ሳመችው:: እንደ ሕፃን ልጅ ከጡትዋ መካከል አስገብታ ታቀፈችው:: አሁን
አለቀ፡፡ ኮዜት ማለቂያና መጨረሻ ከሌለው የፍቅር ማጥ ውስጥ ተዘፈቀች፡፡በሩ ወለል ብሎ እንደገና ተከፈተ::

ያን እለት ቀኑን ሙሉ ደብሮአት ዋለ:: ማሰብ እንኳን አልቻለችም።
አሳብዋ ሁሉ እንደ ጢስ ተነነ እንደ ጉም ፎለለ፡፡ የምትይዘውንና
የምትጨብጠውን ስላጣች ያን እለት ነገሩ ሁሉ እንዲያው ጭንቅ፣ እንዲያው ጥብብ፣ ያዝ ለቀቅ ሆነ፡፡ ልብዋ እየመታና ሰውነትዋ እየተንቀጠቀጠ አንድ
ነገር ተስፋ አደረገች:: ምን? ለማወቅ አይቻልም፤ ምክንያቱም የተጨበጠ ነገር አይደለምና፡፡ ለራስዋ ቃል ለመግባት አልደፈረችም፡፡ ሆኖም ምንም
ነገር ብትጠየቅ እምቢ ለማለት አልደፈረችም:: ነገር ሁሉ አዛንተዘ ሆነ፡፡ ታዲያ ፍቅር አዛንተዘ አይደለም እንዴ? እኔ አንጃ ፍርዱን ለአንባብያን፡፡

ፊትዋ መከፋቱን፤ ስርዋ መሸማቀቁን፤ ጉሮሮዋ መጠማቱን ከሁሉም በላይ አንጀትዋ መንሰፍሰፉ መሸሸግ አልቻለችም።
አዲስ ዓለም ውስጥ
መግባትዋን እየታወቃት እውነት ነው እንዴ ስትል ራስዋን ጠየቀች፡፡
በዚህ ጊዜ ከጡቶችዋ መሀል በመወሸቅ የታቀፈችው ደብዳቤ ትዝ አላት። ጫን በማለት ከልብዋ ጋር አጣበቀችው:: የወረቀቱ ጫፍ ገላዋን ሲቧጭረው
ተሰማት፡፡ በዚያን ሰዓት ዣን ቫልዣ ቢያያት እንዴት በደነገጠ፡፡ ከዚያ በፊት ያላየው የደስታ ወላፈን ከዓይኖችዋ እንደዚያ ሲፍለቀለቅ ቢያይ በእርግጥ ይደነግጣል:: ልብዋ ምን ያህል እንደተጨነቀ ግን ልብዋ ውስጥ ግን ልቧው ውስጥ ገብቶ ማየት አይችልም::

«ወይ ጉድ!» አለች፣ «በእርግጥ እርሱ ነው! እርሱ ለእኔ የላከው
ነው? መላእክት ከሰማየ ሰማያት ወርደው አማልደውኛላ! እነርሱ ጣልቃ ገብተው መልሰው አመጡልኛ! እንዴት ያለ እድል ነው» ስትል አሰበች፡፡

ማታ መሸት ሲል ዣን ቫልዣ እንደ ልማዱ ወጣ አለ:: ኮዚት ጥሩውን ቀሚስ መርጣ ለበሰች:: ፀጉርዋን ወርቅ አድርጋ አበጠረችው፡
የለበሰችው ቀሚስ ከወደ ደረትዋ መቀስ የጎዳው ነበር:: ከወደ አንገትዋ መቀሱ አላርፍ ብሎ ስለሸረከተወ፡ ወደ ጡትዋ በጣም ዝቅ ብሏል፡፡ ዓይን በቀላሉ ያርፍበታል ነገር ካልፈለጉ በስተቀር፣ አደባባይ የሚወጣበት ዓይነት ልብስ አደለም አለ አይደል፣ አንዳንድ ወጣት ልጃገረዶች «ኧረ ትንሽ ያስፈራል» የሚሉት አይነት ቀሚሱ ግን የሚያሳፍር ሳይሆን ልብን
ስቅል፣ የሚያሳምር፣ ፉንጋ ቢሆኑ እንኳን ቆንጆ የሚያደርግ ዓይነት ነበር በጣም አቆነጃት ለምንድነው እንዲህ እንደማለዳ ፀሐይ ያጌጥሽው?» ብላ ብትጠየቅ መልስ የላትም፡፡ ያጌጠችውና ምርጥ ልብስ የለበሰችውም
ይታወቃት ነው::

ወደ ውጭ ለመውጣት ፈልጋ ነው? አይደለም:: ከቤት የሚመጣ ሰው አለ? የለም::
ወደ ግቢው የአትክልት ቦታ ሄደች:: ቱሌይ ማድቤት ውስጥ ሥራ ላይ ነች:: በመስኮት ወደ ውጭ ማየት ትችላለች:: ከግቢው ውስጥ መንሸራሸር ጀመረች:: የዛፎችን ቅርንጫፍ ትነካካለች፡፡ አንዱን ለቅቃ ሌላውን ትይዛለች:: በቁመትዋ ልክ የተንዠረገጉ ዛፎች በብዛት ነበሩ:: በትናንትናው ምሽት ተቀምጣበት ከነበረው መቀመጫ ደረሰች፡፡ ከደብዳቤው ጋር
የተወረወረው ድንጋይ እዚያው እንዳለ ነው::

ቁጭ አለች:: ልክ ፍቅረኛዋን የምትደባብስ ይመስል በለስላሳ እጆችዋ ድንጋዩን በማሻሸት አመሰገነችው:: «ምነው ተጫጫነኝ፣ ማን አለ ከአጠገቤ»
እንደሚባለው ሁሉ ምንም እንኳን በዓይንዋ ባታየውም ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ ከበዳት:: ይህ እንዴት ሆነ ቢባል በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡
ፊትዋን አዙራ ከተመለከተች በኋላ ብድግ አለች::

💫ይቀጥላል💫
👍35
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስር

....ጥቁር አምበሳ፣ ኮከብ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲስ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ የአስረኛ
ክፍል ተማሪዎች ሁሉ፣ “አንደኛ ጎበዝ አንተ ነህ” አሉና የምስክር ወረቀት ሸለሙኝ፡፡ እኔ ግን ጥቁር አምባሳ፣ ኮከበ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲስ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ቆንጆ የሆነችው ዮርዳኖስ የት ተቀምጣ ይሆን እያልኩ በዓይኔ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀል እየፈለግኳት ነበር፡፡

ዮርዳኖስ ማለት ማንም አይደለችም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሬት ተነስታ ጉንጬን የሳመችኝ ልጅ ናት፡፡ ጉንጬን ሳይሆን በቀኝ በኩል ከከንፈሬ ጥግ ሁለት….አረ አንድ ተኩል ሴንቲ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሳመችኝ (ለሞላ ጉንጭ፡፡)

ዮርዳኖስ ቀይ ልጅ ናት፡፡ ለነገሩ ቀይ ሳትሆን ጠየም ያለች ግን ቀይ ዳማ እንደሚሉት ሳትሆን
አትቀርም፡፡ አቦ የራሷ ጉዳይ ገደል ትግባ ብትፈልግ ኤጭጭጭ!! ይሄው ስንት ጊዜ ሌትም ቀንም
ዮርዳኖስ ቀይ ናት ቀይ ዳማ እያልኩ ስዛብር ማደር ከጀመርኩ፡፡ እንኳን ሴት ልጅ፣ ቆንጆ ወጣት ሴት ልጅ፣ ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ ሰው ሲስመኝ የመጀመሪያዬ ስለነበር ዮርዳኖስ ጉንጬን
ሳይሆን ልቤ ላይ እንደሳመችኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ማስረጃ ብባል፣ ከዛን ጊዜ ጀምሮ አተነፋፈሴ ልክ አይደለም፤ ሳያት የሆነ ነገር ያፍነኛል፡፡ ሳላያት እንደ ነብር አዳኝ ትንፋሼን ውጬ በጉጉት በዓይኔ እፈልጋታለሁ፡፡ ሳላያት ታፍኜ ሳያትም ታፍኜ ልሞት ሆነ፡፡

"አንቺ ዮርዳኖስ የምትባይ፤ ምን ቆርጦሽ ነው ኧረ ከከንፈሬ አንድ ተኩል ሴንቲሜትር ርቀት
ላይ በሚሞቅና በሚለሰልስ እርጥብ ከንፈርሽ የሳምሽኝ?” ብላት ደስታዬ፡፡ ግን ታፍኛለሁ!!

አርብ ቀን ከትምህርት ቤት ወጥቼ ወደ ቤቴ እሄዳለሁ፡፡ ምንም እያሰብኩ አልነበረም፡፡ ዝም
ብዬ እየተራመድኩና በግዴለሽነት ሁሉንም ከፊቴ ያለውን ነገር እየተመለከትኩ እራመዳለሁ፡፡

“አሸብር፣” አለችኝ ከኋላዬ፡፡

ስሜ ሲጠራ የምደነግጠውን ያህል የሰይጣን ስም ቢጠራ እንኳን አልደነግጥም፡፡ ሰዎች ስሜን ሲጠሩኝ ከዝምታዬ ባሕር በምላሳቸው መንጠቆ ጠልፈው ያወጡኝ ይመስለኛል፡፡

ጭራሽ ጠሪዎ ዮርዳኖስ ስትሆን ደግሞ፣ በመንጠቆው ላይ መረብ ተተበተብኩ !! ከእኔ ጋር
ብዙ ሰዎች ወደኋላ አብረው ዞሩ፡፡ ሰዉ ሁሉ ሳይጠራ ሲዞር፣ ጠሪዋን ተመልከቶ ደሰ ካሰችው
ስሙን አሸብር ሊያስብል ያሰበ ይመስል እኔ ለተጠራሁት መዓት ሰው ዞረ፡፡

ዮርዳኖስን ዞሬ አየኋት፡፡ ጉርድ ቀሚሷ በደንብ አላራምዳት ስላለ በእጇ ሰብሰብ አድርጋ ወደ
እኔ ትጣደፋለች፡፡ እግሯ ቀይ ነው፡፡ ባቷ ፍርጥም ያለ ከእድሜዋ በላይ ትልቅ የሚያስመስላት
ነው፡፡ ባቷ ብቻውን አስራሁለተኛ ክፍል ይመስለኛል። ጡቶቿ ደግም እዛና እዚህ ይላጋሉ:: ስትጣደፍ፣ በሁለት እጆቿ ክንዶች ገፋ አድርጋ ታረጋጋቸዋለች፡፡ ፀጉርዋ አጭር ነው፡፡ ግንባሯ ትንሽ ወጣ ያለ፡ ቀረበችኝ ፈገግ አለች፡፡ ዓይኖቿ እንዴት ያምራሉ፡፡

ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍ አሁን ስትጠራኝ መኪና እየነዳሁ ቢሆን ኖሮ ከዓይኖቿ ለማምለጥ ስል
ፊት ለፊት የሚያላዝነው ቦት መኪና ጋር እላተም ነበር፡፡ የያዘው ነዳጅ ይዘረገፍና ከዮርዳኖስ
ፈገግታ እሳት ለኩሶ ጭሱ ፀሐይን ጥቁር ጉልቻ እስከትመስል የሚያጥን፡፡ ሰማይ የሚነካ እሳት
ይነሳ ነበር፡፡ በቁሜ ቅዥት ስጀምር ታወቀኝ፡፡

“እንዴት ነው የምትርጠው ወተት ጥደሄል ቤትህ ?” ቀለደች።

አልሳቅኩላትም፡፡ ስላልሳቅኵላት ግን ራሷ ከመሳቅ አልታቀበችም፡፡ እየሳቀች ወሬዋን ቀጠለች፡፡

"ቤትህ በዚህ በኩል ነው እንዴ ?”

“እዎ"

“እኔ ግን አይቼሀ አላውቅም"

ዝም አልኩ፡፡ ካላየችኝ ምን ይሁን፣ ወሬዋን ቀጠለች፡፡
አዎ

አዎ

አዎ

“አዎ ብቻ ነው እንዴ የምታውቀው ?
“አይ” እላታለሁ፡፡ አነጋገሬ ሴት የመፍራት ሳይሆን ሰው የመሰልቸት ነበር፡፡ እንዳንዴ የሰዎች ንግግር ይረዝምብኛል፡፡
"ሰላም ሲሉኝ ይረዝምብኛል፡፡ ሰላም፤ እጃቸውን አንስተው፣ ግንባራቸውን ነቅንቀው፣ ፈገግ
ብለው፡፡ አንዳንዴም እጃቸውን ለሰላምታ ዘርግተው፣ ይሄን ሁሉ አድርገው፣ “ሰላም” ብቻ "

ዝም አለች፡፡ አብረን ሄድን ሄድንና የሆነ መገንጠያ ላይ ስንደርስ ክንዴን ይዛ አቆመችኝና ተንጠራርታ ሳመችኝ፡፡ ምንም አላማ የሌለው፣ ምክንያት የሌለው ወይም “ደፋር ነኝ አየህ" የሚል ምናልባትም፣ “ዘመናዊ ነኝ መንገድ ላይ የወንድ ጉንጭ መሳም አልፈራም” አሳሳሟ
የሆነ ድምፅ አለው፣ የሚያፏጭ ዓይነት ድምፅ፡፡ የመምጠጥ አይነት ድምፅ፡፡ የበዛ ግለኝነቴን
ምጥጥ አድርጋ የሐሳብ ሀይቄን አደረቀችው፡፡ የሰው አለማያ ሆንኩ !! ባደረቀችው የብቸኝነት
ኩሬ ራሷን ሞላችው፡፡እዚህ ዮርዳኖስ የምትባል ውሃ የሞላችው ባህር ውስጥ ልቤ አምልጦኝ ገባ፡፡ ይሄው አስባታላሁ፣ የተረገመች ዮርዳኖስ ! እየጠበቀችኝ ይሁን እየተገጣጠምን ብቻ ከዛን ጊዜ በኋላ በየቀኑ እንገኛኝ ጀመረ፡፡ ሲቆይ ግን ጉዳዩ የነፍስ ቀጠሮ ሆነ፡፡ ጠበቅኩሽ ላለማለት በቀስታ እየተራመድኩ እጓዛለሁ፣ ከየትኛውም ርቀት ላይ አውቃታለሁ፡፡

ፊት ለፊት ሳላያት መንፈሷ እዛ አካባቢ ካረበበ ትካሻዬ ሹክ ይለኛል፡፡ ትከብደኛለች፣ “ሃይ አሹ” የሚል ድምጽ እጠብቃለሁ፡፡ ሀይ አሹ ትለኛለች ውስጣችን ያውቃል እንደምንጠባበቅ፡፡ ከዛም ታወራኛለች።

"ዛሬ ይበርዳል!”

"አዎ"

"ሆም ወርክ ሰራህ ?”

"አዎ"
.
.
.
“አዎ ብቻ ነው የምታውቀው፡፡”

"አይይ"። አሁን ግን ምን ማውራት እንዳለብኝ እያሰብኩ ነው ችግሩ፣ አስቤ ሳልጨርስ እንደርሳለን፡፡

ስንመለስም እንገናኛለን፡፡ ስንመለስ መለያያችን ላይ ትስመኛለች፣ “ቻው” ከሚል ስርቅርቅ ያለ መለያየቱ ያስከፋው ድምፅ ጋር ከንፈሯ ጆሮዬ ላይ ያፏጫል፡፡

አንዴ መሀል ጉንጩ ላይ፣ አንዴ ዝቅ አንዴ ከፍ እያለች ትስመኛለች፡፡ በየቀኑ ትስመኛለች፡፡ ዝም ብዬ አሳማለሁ፡፡ ከንፈሯ ክብ ነው፤ በሃሳቤ ስትስመኝ ከብ ቅርፅ ጉንጩ ላይ የታተመ ይመስለኛል፥
የሳምንቱ ክቦች ተቆላልፈው፤ ቅዳሜ የኦሎምቲካ አርማ ጉንጩ ላይ ታትሞ በጉልህ ይታየኛል፡፡
እንዱ ከብ እንደ ደቡብ ኦሞ ሴቶች፣ ከንፈሬን ተልትሎ ከንፈሬ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት በህልሜ!

አንድ ቀን ግጥም ጻፍኩ፡፡ በህይወት ዘመኔ የጻፍኩት ብቸኛ ግጥም ነበር፡፡ ወደፊትም ግጥም
አልጽፍም " ግጥም ያስጠላኛል፡፡ ሰው ዝም ማለት እያለለት፣ ለማውራት ቃል መጠምዘዝ
መድከም ምን ያደርግለታል? ቢፅፍ ላይጠቀም፣ ባይፅፍ ላይጎዳ ባይ ነኝ፡፡ ደግሞ አዲስ
ግጥም ሰምቼ አላውቅም፡፡ ግጥሞች ሁሉ አንድ ናቸው፤ ደራሲያቸው ይለያይ እንጂ ባይ ነኝ::

እኔን የገረመኝ (ርእሱ)

እኔን የገረመኝ፣
እኔ የጠላሁትን፣
እኔነት ሳትጠላ፤
ልጅቱ ስትስመኝ !!

በቃ !! ይሄው ነው ግጥሙ።

ግጥም ማለት ቤት የሚመታ፣ ቀለሙ፣ ስንኙ የሚሉ ሰዎችን ተዋቸውና ግጥም ማለት እስክርቢቶ ሳትጨብጥ ወረቀት ፊትህ ሳይነጠፍ አንደ አፍ ወለምታ ከከንፈርህም፣ ከነፍስሀም፣ ከአዕምሮህም
የሚያመልጥ እውነት ነው፡፡ ለምሳሌ በዚች ዓለም ላይ ከሰማኋቸው ግጥሞች አሳዛኙ የአቲዬ ግጥም ነው፡፡ ርእሱ፣ “እሺ፤ ግጥሙም፣ “እሺ” አበቃ፡፡

ማንም ለጀመረው የትዕዛዝ ስንኝ፣ አቲዩ 'እሺ' የሚል ግጣም እየሰራችለት፣ የማንም ቤት
እንዲቆም አድርጋለች። የእኔ እናት ገጣሚ ናት፡፡

“ቤት ጥረጊ!”
“እሺ!"
“ልብስ እጠቢ”
“እሺ”
“ሂጂና ሳሙና ግዢ!
"እሺ"
“እንጀራ ጋግሪ”
"እሺ
“ደመወዝሽን ሌላ ቀን ውሰጂ!”
"እሺ"
ግጥም ይሄ ነው !! ከትዕዛዘ እኩል ይሁንታው ዜማ ሲፈጥር፡፡ እናም ያሉትን ሲሆኑ፡፡
👍39
ቤት መምታት ይሄ ነው፡፡ መጥፎ ቃል የደሀ ስጋ ለብሶ አዛዥ ቤት ሲያድር፣ በዓመቱ አይኑ
በምኞት የሚባብር 'ገጣሚ' “ውዴ ዘላለም ልፈጥፈጥልሽ፣ ልቆራመትልሽ” ሲል አይገባኝም፡፡
ግጥም ከቃል ሲሰረሰር ሳይሆን፣ ከነፍስ ሲምዘዝ ከሕይወት ሲቀመም ነው ቤት የሚመታው፡፡
ቢሆንም ግጥም ገጠምኩ፡፡ አላሰብኩም፣ አልደለዝኩም፣ አልቆረብኩም፡፡ አንድ ደብተሬ ጀርባ ላይ በቀጥታ ጻፍኩት፡፡ ያውም ኬሚስትሪ የሚባል ትምህርት እየተማርን ልክ ስልክ ቁጥር እንደሚጽፍ ሰው ሳላስብ ግጥም ጻፍኩ፡፡ ከብዙ ዓመት በኋላ ይሄን ግጥም ያሳየሁት ገጣሚ፣
“ጭብጡ የላላ ወደታች የተጻፈ ስድ ፅሁፍ ነው የሚመስለው” አለኝ፡፡ ጉዳዬ አልነበረም፡፡ ድሮስ
መቼ ግጥም መጻፈ ገረመኝ፡፡ በልጅቱ ጉንጬን፣ ያውም አንድ ተኩል ሳንቲሜትር ለከንፈሬ
የቀረበ ቦታ ላይ መሳሜ እንጂ !!

ዮርዳኖስ አንድ ቀን ጠራችኝ፣ “አሹ” ብላ !!

"አሹ” ማለት ለካ አሸብር ማለት አይደለም፤ በጭራሽ አሹ ማለት ከአሸብር ጋር የሚገናኘው
ሁለቱም አጠራር ስለሚያስደነግጡኝ ብቻ ነው እንጂ አሸብር "አሹ” አይደለም፡፡ ከየት አመጣቸው ግን እች ዮርዳኖስ !! ደግሞ “አሹ" ከአሸብር ይረዝማል፡፡ አሹ፣ ሙሉ ቀን ጆሮ ላይ ያቃጭላል
አይገርምም ?

ከተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ወጥቼ የተሸለምኩ ቀን ሌሊት ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡ ምን እንዳነቃኝ
እኔንጃ፡፡ ፀጥታው የነቃ ያስተኛል እንኳን የተኛ ሊቀሰቅሰ፡፡ ግን ነቃሁ፡፡ ነቃሁና ልክ ዓይኔን
ስከፍት፣ ዮርዳኖስ ያንኳኳችወን በር የከፈትኩ ይመስል ምስሏ ፊት ለፊቴ ተደቀነ፡፡ ልትስመኝ
ስታሞጠሙጥ፣ ስትስቅና “አሹ" ስትለኝ፣ “ፍቅር ይዞኛል” የሚል የማልፈልገው ዓረፍተ ነገር
ከምኔ እንዳመለጠ ሳላውቅ ፈነዳ ቡምምምምምምምምምምምምምም ፍቅር እርፍ !

ልክ እንደ ግጥሙ ያልፈለኩት እንባ ጉንጬ ላይ ተንኳለላ፡፡ በምድር ላይ አለኝ ከምለው አንድ
የሆነ እምነት የተካድኩ መሰለኝ፡፡ ለነብስ ጉዳይ የተበደርኩት ብር ከኪሴ የጠፉ ያህል ተሰማኝ፡፡
እንባዬን ጠረግኩና መብራቱን አበራሁት። ፊት ለፊት ያለው ግድግዳ ላይ በፌስታል የተሰቀለ የአቲዬ ልቃቂት፡፡ ራቅ ብሎ ትንሽ መጋረጃ እንደ ዕቃ ቤት የምንጠቀምባትን ቦታ የከለለች፣ ከመጋረጃዋ ፊት ልፊት አቲዬ ፍራሽ ላይ አሮጌ ብርድ ልብስ ለብላ ኩርምት ብላ ተኝታለች፡፡ ቤታችን አስጠላኝ፡፡ራሴ አስጠላኝ፡፡ አስረኛ ከፍል አስጠላኝ፡፡ ከአሁን በኋላ ስንት ዓመት ተምሬ ነው ስራ የምይዘው?

አቲዬ ድንገት ባነነችና፣ “አሸብር ምነው አመመህ እንዴ?” አለችኝ፣ ከወገቧ ቀና ብላ፡፡ ዝም
ብዬ አየኋት፡፡ አቲዩ እያረጀች ነው፡፡ ደረቷ ክስት ብሏል፡፡ ፊቷ ላይ ማዲያት ነገር አለ፡፡ ግንባሯ ላይ ብዙ መስመሮች ተጋድመዋል፡፡ አንገቷ ስር ያለው ቆዳዋ ተሸብሽቧል፡፡ እስከዛሬ
አላየኋትም ወይስ “እውር ያደርጋል" የሚሉት ፍቅር የእኔን ዓይን ገለጠው ገመናዬን አሳይቶ፣
ልክህን እወቅ! ሲለኝ፡፡ አቲዬን ስራ እስከምይዝ በምን ላፅናናት?

“አቲ ደስ ብሎኝ ነው አልኳት ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ።

"እሰይ፣ አረ ደስ ይበልልኝ" ከለች ከእኔ የበለጠ ፈገገ ብላ፡፡ ምኑንም ሳትሰማ፣ ምን ተገኘ? እንኳን አላለችኝም፡፡ በቃ ደስ ካለኝ ደስ ይላታል፡፡

“ከአዲስ አበባ ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ወጥቼ ሰልፍ ሜዳ ተማሪዎች ፊት ተሸለምኩ” አልኳት፡ አዲስ አበባ ያልኩት ሆን ብዬ ነበረ፡፡ 'የገፋሽ ሕዝብ ሰነፍ ነው፣ ያንከራተተሽ ሕዝብ ልጆች
በአንቺ በተንከራታቿ፡ በአንቺ ልጅ አፈር ድሜ ግጧል፡፡ ተበልጠዋል፡፡ በእጅ አዙር በልጠሻቸዋል ለማለት፣ ሌላም ለማለት

አቲዬ ፊቷ በፍርሀት ተወረረ፣ “ልጄን የሰው ዓይን ውስጥ ሊያስገቡብኝ” አለች።

“አቲዩ ደግሞ፣ ሁልጊዜ እንታያይ የለ" አልኳት፡፡ ዓይን ውስጥ ግን ጎብቻለሁ ልክ ነው፡፡
ዮርዳኖስ የምትባል ቡዳ በልታኛለች በከንፈሯ !!

"በል ጧት ሂድና ማለፍህን ንገራት!" አለችኝ በኣገጪ ወደ ዛፒ ቤት እየጠቆመች፡፡ አቲዬ
ከሚገርመኝ ባህሪዋ ማንንም በስም አትጠራም፡፡ ተመልከቱ ምን ያህል እንደተበደለች እች
ሴት፡፡ የሰውን ስም መጥራት በራሱ መናቅ እንዳይመስልባት ትፈራለች ትፈራለች ! እናም
ለዛፒ ምን ብዬ እንደምነግራት አሰብኩ፡፡

'ዛፒ አንደኛ ወጣሁ ዛፒ አለፍኩ..ዛፒ ሰካራም..ዛፒ ጠብራራ ዮርዳኖስን አፈቀርኳት…
ኡፍፍፍፍፍፍ ላብድ መሰለኝ፡፡ መብራቱን አጠፋሁት፡፡ ጨለማው ውስጥ ዮርዳኖስ ገጭ አለች እች ግንባራም ! እግሯ ቀይ ነው፡፡ ጡቶቿ ትልልቅ ናቸው:: ስትራመድ ይነቃነቃሉ። ግን ጡት ሴቶችን ይከብዳቸዋል…አይከብዳቸውም? ታዲያ 'ዮርዲ ለምንድን ነው ስትራመድ ጎበጥ የምትለው፡፡

ዮርዲ” ነው ያልኩት ? ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ከአቲዬ ቀጥሎ በዚች ምድር ያቆላመጥኩት ስም እነሆ..

አላለቀም
👍225
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ልክ ፍቅረኛዋን የምትደባብስ ይመስል በለስላሳ እጆችዋ ድንጋዩን በማሻሸት አመሰገነችው:: «ምነው ተጫጫነኝ፣ ማን አለ ከአጠገቤ»
እንደሚባለው ሁሉ ምንም እንኳን በዓይንዋ ባታየውም ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ ከበዳት:: ይህ እንዴት ሆነ ቢባል በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡
ፊትዋን አዙራ ከተመለከተች በኋላ ብድግ አለች:: እሱው ነበር:: ቆብ
ወይም ኮፍያ አላጠለቀም:: ሰውነቱ ገርጥቶአል፡፡ ትንሽ ከሳ ያለ ሰውነት ያለው ሲሆን የለበሰው ልብስ ጠቆር ያለ ነው፡፡ ፊቱ ጎልቶ ይታይ እንጂ አፍንጫው ሰልከክ ያለ ለመሆኑ ይታያል::

ኮዜት ብትደነግጥም የጩኸት ድምፅ ለማሰማት አልደፈረችም::
አንድ ነገር ወደፊት የሳባት ስለመሰላት ወደኋላ ሸሸት አለች:: ልጁ ከነበረበት አልተነቃነቀም:: ዐይኑን ለማየት ባትችልም በሀዘን መሞላቱን ገመተች::

ኮዜት ወደኋላ ስትሸሽ ከግንድ ጋር ስለተላተመች ያንኑ ግንድ ተደግፋ
ቀረች:: ዛፉን ተደግፋ ባትቆም ኖሮ እጅ እግርዋ ስለዛለባት ትወድቅ ነበር፡፡ዛፉን ተደግፋ እንደቆመች ድምፁን ሰማች:: ያን ድምፅ ከዚያ በፊት ሰምታው አታውቅም:: በጣም ዝግ ብሎ ነበር የሚናገረው::

«ይቅርታሽን፣ እዚህ ነው ያለሁት፡፡ ልቤ ሊፈነዳ ነው:: መኖር እየተሳነኝ ነው ከዚህ የመጣሁት፡፡ ከመቀመጫው ላይ የወረወርኩትን ፅሑፍ አንብበሽዋል? ለመሆኑ ማን እንደሆንኩ አውቀሽኛል? አትፍሪኝ::ጊዜው በጣም
ቆይቷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተያየንበት ቀን ታስታውሺዋለሽ?
ዘወትር ትሄጅበት የነበረው የሽርሽር ቦታ! በአጠገቤ ያለፍሽበት ቀንስ ቀኖቹ ሰኔ 16 እና ሐምሌ 2 ነበሩ፡፡ አሁንማ ዓመት ሊሞላው ምን ቀረው።
ዓይንሽን እንኳን ሳላይ ብዙ ጊዜ አለፈ፡፡ ማታ ማታ ከዚህ እመጣለሁ አትፍሪ፣ ግድ የለሽም፣ ከዚህ ማንም የለም:: ከዚህ የምመጣው የመኝታ ክፍልሽን መስኮት በሩቁ ለማየት ነው:: ከዚህ አካባቢ በምመጣበት ጊዜ
ደግሞ ድንገት በአካባቢው ካለሽ እንዳትደነግጪ እያልኩ ስራመድ
በዝግታ ነበር፡፡ አንድ ቀን ስትዘምሪ ሰምቼሽ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ከክፍልኝ ውስጥ ሆነሽ ስትዘምሪ መስማቴ ያስከፋሻል? ጉዳት ያለው አይመስለኝም። አየሽ፣ አንቺ እኮ ለእኔ መልአኬ ነሽ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እስቲ ከዚህ እንድቀመጥ
ፍቀጂልኝ፡፡ በቅርቡ እንደምሞት አውቃለሁ፡፡ ይህን ብታውቂ! እኔ እኮ እንደ አምላክ ነው የማመልክሽ! ይቅርታ አድርጊልኝ፤ ንግግር አላውቅም
ከአንቺ ጋር ማውራቴን ረስቼአለሁ፡፡ ምናልባት ሳላውቀው አናድጄሽ ወይ አበሳጭቼሽ ይሆናል፡፡ አዘንሽብኝ?

«ወይ እማዬ!» አለች፡፡ ልክ እንደሚሞት ሰው ተዝለፈለፈች፡፡

ከነበረበት ወደ እርስዋ ሮጠ፡፡ ከወደቀችበት እቅፍ አድርጎ አነሳት!
ምን እንደሚያደርግ ሳይታወቀው በጣም በመጭመቅ አቀፋት:: እየተንገዳገደ ወደ ላይ ብድግ አደረጋት፡፡ አካሉ በጭስ የተሞላ ይመስል ሰውነቱ ውስሳ
እየተነነ የሚሄድ ነገር እንዳለ ተሰማው:: መንፈሳዊ ተግባርም የሚያከናው መሰለው፡፡ ምንም እንኳን ከልቡ አስጠግቶ ቢያቅፋትም የፍቶተ ስሜት ጨርሶ አልተሰማውም፤ እውነተኛ ፍቅር የፍቶተ ሥጋ መርካት አይደለምና፡ ልጁ ከእውነተኛ ፍቅር ወጥመድ ውስጥ ለመግባቱ ምልክት
ነበር፡፡

እጁን ይዛ ወደ ልብዋ አስጠጋችው:: ወረቀት ከጡቶችዋ መኖሩን ተገነዘበ፡፡ ዝግ ባለ ድምፅ ተናገረ::

«እንግዲያውማ ትወጂኛለሽ ማለት ነዋ!»
ጆሮን በኃይል ካላቀኑ በማይሰማ በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ መልስ
ሰጠችው::

«እስቲ ዝም በል፤ እሱንማ የምታውቀው ነው::»

በሀፍረት የቀላው ፊትዋን ላለማሳየት ኩራት በተሰማውና በፍቅር በሰከረው ወጣት ብብት ስር ራስዋን ደበቀች::

ከድንጋዩ መቀመጫ ላይ ቁጭ ሲል እርሱዋም ከአጠገቡ
አለች:: ዝምታ ሰፈነ፡፡ ከዋክብት ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል:: እንዴት ነው ከንፈሮቻቸው የተገናኙት? እንዴት ነው አእዋፍ በዚህ ሰዓት ማዜም
የጀመሩት? እንዴትስ አበቦች ሊፈኩ ቻሉ?
አለቀ! በቃ ! ሥሮቻቸው የተነቀሉ እስኪመስላቸው ተሳሳሙ::

የሁለቱም ሰውነት ነፋስ እንዳወዛወዘው ቅጠል ተንቀጠቀጠ፡፡ በጨለማ
የሁለቱም ዓይኖች ቦግ ስላሉ ተፋጠጡ፡፡ ብርዱ አልተሰማቸውም፤ ድንጋዩ
አልቆረቆራቸውም፤ መሬቱና ሳሩ አልቀዘቀዛቸውም:: አሁንም በመፋጠጥ እየተያዩ ነው፡፡ ልባቸው በአሳብ ተሞልቷል፡፡ ሳይታወቃቸው እጅ ለእጅ
ተጨባብጠዋል፡፡

ለማንኛውም እንዴት አድርጎ ከአጥር ግቢው ውስጥ እንደገባ
አልጠየቀችውም፤ ለመጠየቅም አልፈለገችም፡፡ የእርሱ ከዚያ መገኘት እንግዳ ነገር
አልሆነባትም::

አልፎ አልፎ የማሪየስ ጉልበት የኮዜትን ጉልበት ሲነካ ሁለቱም
በደስታ ይፈካሉ፡፡ ቆይታ ኮዜት አንዳንድ ቃል ትወረውራለች፡፡ ስትናገር ነፍስዋ ከከንፈርዋ ጫፍ ላይ እንደሆነች ከከንፈርዋ ጋር አብሮ ተንቀጠቀጠ ለማለት ይቻላል፡፡

ቀስ በቀስ ዝምታው ተወግዶ ማውራት ጀመሩ፡፡ እንደገና የፍቅር
ስበታቸው ሞልቶ ስለፈሰሰ ዝም ተባባሉ፡፡ ምድርም ዝም አለች፡፡ ነፋስ እንኳን «ዝም በል» ብለው ያዘዙት ይመስል ፀጥ አለ፡፡ እንደገና ጨዋታ ጀመሩት፡፡ እነዚህ ሁለት እንደ ጥቅምት ውሃ የጠሩ ፍጡሮች ስለነበሩ ስላለፈው ምኞታቸው፣ ወፈፍ አድርጎአቸው ስለፈጸሙት ተግባር፣ ስለደስታ
ዘመናቸውን ፣ ስለተከፉበት ጊዜ እንዲሁም አንዱ ሌላውን ምን ያህል ይመኝ እንደነበር አንድም ነገር ሳይደባበቁ ተጫወቱ፡፡ አንዱ ስለሌላው ስለነበረው
ምኞትና አድናቆትም ተነጋገሩ፡: ሳይተያዩ ሲቀሩ ሁለቱም ምን ያህል ተስፋ ቆረጠው እንደነበር ተገላለጹ፡፡ ከሁለቱም ልብ ውስጥ የነበረው ሁሉ እንደ ውሃ ፈሰሰ፣ ተንቆረቆረ:: ስለዚህ ከአንድ ሰዓት በኋላ ወጣቱ የወጣትዋ፣
ወጣትዋ የወጣቱ ሕይወት ማለት እርሱ እርስዋን፣ እርስዋ እርሱን ሆኑ፡፡አንዱ ሌላው ልብ ወስጥ ዘልቆ ገባ፡፡ አንዱ የሌላው ጌታ ሆነ፡፡ አንዱ በሌላው ረካ፤ ፈካ፤ ተደሰተ፡፡

ልባቸው ውስጥ የነበረው ነገር ተሟጥጦ ሲያልቅ ጭንቅላትዋን
ከትከሻው ላይ አሳርፋ ጥያቄ ጠየቀችው::

«ስምህ ማነው?»

«ስሜ ማሪየስ ይባላል» አለ::

«የአንቺስ?»

«ኮዜት እባላለሁ፡፡››
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ማምለጥ

ምንም እንኳን ቴናድዬ የታሠረው ከተለየ ክፍል ውስጥ ቢሆንም
እርሱና ሌሎች ሦስት ሽፍቶች የማምለጥ አድማ ይመታሉ፡፡ ሁለቱ ሽፍቶች ከምድር ቤት ውስጥ ሲሆኑ ቴናድዬ ብቻውን ፎቅ ላይ ነበር፡፡ ከአደሙ
መካከል አንደኛው አደገኛነቱ ታውቆ እንዲሁ ለብቻው ነበር የታስረው::

በምን ተአምር ጠርሙስ ቪኖ እንዴት ሊያስገባ እንደቻለ ባይታወቅም መጠጡ ቴናድዬ ክፍል ውስጥ ተገኝቷል ይህ መጠጥ በውስጡ ሱስ
የሚያሲዝ እንደ ሐሺሽ ያለ ቅመም እንደነበረበት ይነገራል

መቼስ በእያንዳንዱ እስር ቤት ውስጥ እስረኞች እንዲያመልጡ
የሚተባበሩና እምነታቸውንና መሐላቸውን ለገንዘብ የሚሰጡ ጉበኞች ወይም ሌቦች ወይም ቀጣፊዎች አይታጡም: እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ከደመወዛቸው
በላይ ገቢ አላቸው::

ሁለቱ ሽፍቶች አንድ ቀን ጠዋት ማምለጣቸውና ከመንገድ
የሚጠብቋቸው ለመሆኑ የሚያወቁ ሌሎች ሁለት ሽፍቶች ከውስጥ ይቀራሉ እነርሱም ለማምለጥ ዘዴ ይፈጥራሉ በአጋጣሚ በእለቱ በረዶ የተቀላቀለበት ከባድ ዝናብ ይጥል ስለነበር በዚህ አጋጣሚ በመጠቀምና ጨለማን ተገን
በማድረግ እነዚያ ሁለት ሽፍቶች በፈጠሩት ዘዴ ተጠቅመው ለማምለጥ ችለዋል::
👍21👏21😁1
ከእስር ቤቱ እንዳመለጡ ቀደም ሲል አምልጠው የነበሩትን ሁለት
ጓደኞቻቸውን አገኙ ሰዎቹ ከተለያዩ አካባቢዎች ቢታሰሩም እንዴት
አድርገው አቅድ እንዳወጡና እንደተመካከሩ አይታወቅም፡ ለምሳሌ ባመለጡበት ሌሊት ቴናድዬ ሳይተኛ ድምፅ እስኪሰማና ምልክት እስኪሰጥ
እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ድረስ አፍጥጦ ጠብቋል እንደ ነፍሰ ገዳይ ተቆጥሮ እጅግ በጣም ይጠበቅ የነበረው ይኸው ሰው ማምለጡ ግራ የሚያጋባ ነው፡ ከነበረበት ክፍል ጠመንጃ የያዘ ዘብ ይቆም ነበር በከባድ የብረት ሰንሰለት ታስሮአል በየእለቱ በአሥር ሰዓት ፈታሽ እየገባ
ያየዋል: እግር ብረቱን ይመረምራል ይኸው መርማሪ ማታ ማታ እየመጣ በዓይነ ቁራኛ ይጠብቀዋል ለእስረኛው የተፈቀደለት ነገር ቢኖር የሚሰጠው ደረቅ ዳቦ አይጥ እንዳይበላበት ሰክቶ ከግድግዳ ላይ እንዲያንጠለጥልበ አንድ ሾል ያለ ብረት ነበር አንድ ቀን ከጠባቂዎቹ አንዱ የቴናድዬ
አደገኛነት በመገንዘብ ከብረት ይልቅ የሾለ እንጨት እንዲሰጠው
አሳስቦ ነበር።

ከሌሊቱ በስምንት ሰዓት የጠባቂ ለውጥ ተደረገ: መርማሪው
ክፍሎቹን ጎበኘ፡፡ አዲስ ነገር አላየም አስር ሰዓት ላይ የጠባቂ ለውጥ ለማድረግ ሲመጡ ቀደም ሲል የተቀየረወ ጠባቂ ቴናድዬ ተኝቶበት ከነበረው ክፍል ውስጥ ለጥ ብሎ ተገኘ: ወደ ውስጥ ቢገባ ቴናድዬ አልነበረም:: እግሩ የታሰረበት ወደ 25 ኪሎ የሚመዝን የእግር ብረት
ወለሉ ላይ ወድቋል እርሱ የነበረበት ክፍል ጣራ ቆርቆሮ ተነቅሏል፡፡ከክፍሉ ውስጥ የተከፈተ ግማሽ ጠርሙስ ቪኖ ተቀምጧል:፡ ጠባቂው
እንቅልፍ የወሰደው ያንን ስለጠጣ እንደሆነ በኋላ ተደርሶበታል፡ የጠባቂው ጠመንጃ ከእጁ ላይ የለም።

ቴናድዬ የታሰረበት ክፍል ሦስተኛ ፎቅ ላይ ስለነበር ከዚያ እወርዳለሁ ብሎ ሲታገል አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል ብለው ጠባቂዎቹ ጠረጠሩ ወደ
ጣራ ወጥተው ሲመለከቱ አንድ የተንጠለጠለ ገመድ አዩ ሆኖም ገመዱ አጭር ስለነበር ከመሬት የሚያደርሰው አልነበረም:: ነገር ግን ጣራ ለጣራ ጥቂት ከተራመዱ በኋላ ከእስር ቤቱ አጥር ውጭ አንድ የፈራረሰ ረጅም
አጥር ያለው ቤት አዩ ምናልባት ከጣራ ወደዚያ አጥር ዘልሎ ለመውጣት ይቻላል የሚል አሳብ ተቀረጸባቸው:: ግን ያም ቢሆን አደገኛ ነበር ቴናድዬ ከብዙ ትግልና ጥረት በኋላ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን በዚህ
ቤት በኩል ነበር ከመንገድ አጠገብ የደረሰው፡ ከዚህ ይበልጥ ዝርዝር ውስጥ ባንገባ ይሻላል እንጂ የደረሰበት ውጣ ውረድ ቀላል አልነበረም: ግን
ዝርዝሩን እንግለጽ ቢባልም ትክክለኛውን ለማወቅ አይቻልም:: ሆነም ቀረም ከነበረበት ለመድረስ ሰውነቱ በላብና በዝናብ መራሱ፣ ሰውነቱ መጋጋጡና መድማቱ፤ ልብሱ መቀዳደዱና መቦጫጨቁ የማይካድ ሐቅ ነው፡፡

የያዘው ገመድ አጭር ነው፡፡ ለመዝለልም ፈራ፡፡ ከዘለለ ሞት
የሚጠብቀው መሰለው፡፡ ንጋት ስለተቃረበ ቶሎ ከዚያ ካልወጣ እንደሚያዝ ያውቃል፡፡ እንዲሁ ሲያመነታ አሥር ሰዓት ሆነ
ጠባቂዎቹ የቴናድዬ መጥፋት በደረሱበት ጊዜ ብዙ ድምፅ አሰሙ ቴናድዬ በፍርሃት ተዋጠ፣ ሰውነቱ ተርበተበተ፡፡ ከወደኋላ በር እየተከፈተ ሲዘጋና የእጅ መብራት ብርሃን ላይ ታች ሲል ከሩቁ አየ መብራቱ ጠባቂዎቹ ካደረጉት ቆብ ላይ አርፎ ንቅናቄያቸውን አመላከተው እርሱን
ፍለጋ እንደሆነ ታወቀው:
አሁንም ቴናድዬ ያለው ከሦስተኛ ፎቅ ጣራ ላይ ነው ቢዘል ሞት
እንደሚጠብቀው፣ ቢቆይ እንደሚያዝ በሚገባ ያውቃል ታዲያ እንዴት ይሁን?
አሁንም ጊዜው እንደጨለመ ነው ሆኖም ሰዎች ከየጎራው ሲወጡ
ለመለየት ይቻላል አራት ሰዎች ከተለያየ አቅጣጫ መጥተው በሩቁ በመንገዱ ሲያልፉ ተመለከተ ግን እነማን እንደሆኑ ለመለየት አልተቻለውም:፡ ሰዎቹ ተሰባስበው እርሱ ወደነበረበት አመሩ፡፡ እየቀረቡ ስለሄዱ ጨዋታቸውን አዳመጠ፡፡ ድምፃቸውንና የሚጠቀሙባቸውን ቃላት በሰማ ጊዜ ጓደኞቹ እንደሆኑ አወቀ: የሚነጋገሩት በዱር አዳሪ ቋንቋ ነው ልቡ በተስፋ ተሞላ ሰዎቹ ንግግራቸውን ቀጠሉ
«እንሂድ፣ ከዚህ ምን እናደርጋለን» አለ አንዱ
«ዝናቡ ሳይቆም ከዚህ እንጥፋ: ይኸው እንደምታዩት ፖሊሶቹ
እየተንቀሳቀሱ ነው፡»

«ምን ማለታችሁ ነው፣ ከዚህ ደርሰው እንዲይዙን ነው እንዴ
የምንጠብቀው» አለ ሌላው::

«ምን ያስቸኩላችኋል፣ ጊዜው እንደሆነ ገና ነው: ትንሽ እንቆይ::
የእኛ እርዳታ አለመፈለጉን እንዴት እናውቃለን?» አለ ሦስተኛው:

አራቱም ሰዎች ሽፍቶች ጓደኞቹ እንደሆኑ ቴናድዬ አረጋገጠ:
ለመጣራት አልደፈረም:: ቢጣራ ድምፁ ይሰማል በእጁ የያዘውን የገመድ ቁራጭ ጠቅልሎ ወደ መንገዱ ወረወረው ገመዱ ከሰዎቹ እግር ስር
ወደቀ

‹‹የምን ገመድ ነው?» ሲል ባቤ የተባለ ሽፍታ

«ይሄማ እኔ እስር ቤት ሆኜ የገመድከት ነው» ሲል ብሩዦ የተባለው መለሰ::

‹‹የሆቴሉ ጌታ ከዚህ አካባቢ ነው ያለው ማለት ነው» አለ ሞንትፐርናሴ የተባለው ሽፍታ፡፡

ዓይኖቻቸውን ቀና አደረጉ፡፡ ቴናድዬ ተነቃነቀ

«በሉ ፍጠኑ» አለ ሞንትTርናሴ:: «ብሩዦ ገመድ ይዘሃል?»
«አዎን ይዤአለሁ:
«ሁለቱን ጫፎች ደህና አድርገህ ቋጥራቸወ:: ገመዱን
እንወረውርለታለን ከግምቡ ጫፍ ጋር አያይዞ መውረድ ይችላል፡»

«እንዴት አድርጎ?»

«እባክህ አንተ ብቻ የገመዱን ሁለት ጫፎች ደህና አድርገ
ቋጥራቸው»

«አልችልም»

«አንደኛችን እርሱ ካለበት እንውጣ» አለ ሞንትፐርናሴ፡፡

«ሦስት ፎቅ ነው የምንወጣው!» አለ ብሩዦ

ከእስር ቤቱ አጠገብ ከሚገኘው ፍርስራሽ ቤት የወደቀና ወደ እስር
ቤቱ ግድግዳ የተጋደመ አሮጌ የጭስ መውጫ ቱቦ ነበር፡፡ የጭስ መውጫው ቱቦ በጣም ረጅም ስለነበር ከሦስተኛው ፎቅ ወለል ለመድረስ ምንም ያህል
አይቀረውም፡፡ ይህ ከሲሚንቶ የተሠራው ቱቦ ቅጥልጥል የበዛበት ሲሆን አልፎ አልፎ ተሰነጣጥቋል ደግሞም የውስጡ ስፋት ጠባብ ነው፡

«በዚያች ቱቦ አማካይነት ልንወጣ እንችላለን» አለ ሞንትፐርናሴ፡

«በዚያች ቱቦ!» በማለት ባቤ አሽሟጠጠው፡፡ ‹‹በውስጡ ሰው ሊያልፍ! ጭራሽ አይደረግም: እንኳን ትልቅ ሰው ሕፃንም አያልፍ፡»

«ትንሽ ልጅ ብቻ ነው ከዚያ ቱቦ ውስጥ ሊያልፍ የሚችለው» አለ
ብሩዦ ::

«ታዲያ ልጅ ከየት ይገኛል?» ሲል ግዩለሜ ጠየቀ፡

«ቆዩ» አለ ሞንትፐርናሴ፣ ዘዴ አላጣም፡፡››

የዚያን የፈራረሰ ቤት የውጭ በር ቀስ ብሎ ከፍቶ ወደ ውጭ ወጣ:
ሰው አለመኖሩን ግራና ቀኝ ተመልክቶ በሩን መልሶ ዘጋው ከዚያም በሩጫ ፈረጠጠ፡፡

ሰባት ወይም ስምንት ደቂቃ አለፈ፡፡ ለቴናድዬ እንደ ስምንት ሺህ ዓመት ረዘመበት ባቤ፣ ብሩዦና ግዩለሜ ጥርሳቸውን ነክሰው ተገትረው ቀሩ በመጨረሻ በሩ እንደገና ተከፈተ ሞንትፐርናሴ ትንፋሽ አጥሮት ከጋቭሮች ጋር ብቅ አለ፡ አሁንም በኃይል ይዘንብ ስለነበር ማንም ደፍሮ
መንገድ ላይ አልወጣም፡፡
ትንሹ ጋቭሮች ከቱቦው ሥር ሆኖ ወደ ላይ ተመለከተ ሲያይ ውሃ
ጭንቅላቱ ላይ ተንጠባጠበ፡፡
«እንዴት ነው አንተ ልጅ! የአባትህ ልጅ ነህ ወይስ የእናትህ» ሲል
ግዩለሜ ልጁን ጠየቀው

«እንዴ እኔ ያለውማ የአባቱ ልጅ ነው፤ እንደእናንተ ያለው ነው
እንጂ የእናቱ ልጅ» ሲል ልጁ ትከሻውን እየነቀነቀ ተናገረ
እንዴት ያለ የሾለ ምላስ ነው ያለው?» አለ ባቤ እየተገረመ
ፓሪሱ ወጣት ከገለባ የተሠራ ይመስላችኋል» በማለት በአገሩ የአራዳ ቋንቋ ባቤ ተናገረ::

«ምንድነው የምትፈልጉት?» ሲል ልጁ ጠየቀ፡፡

«በቱቦው አድርገህ ከሦስተኛ ፎቅ ጣራ ላይ እንድትወጣ ነው
የምንፈልገው» ሲል ሞንትፐርናሴ መለሰለት::

«ይህቺን ገመድ ይዘህ ነው የምትወጣው» አለ ባቤ::
👍22
ልጁ ገመዱን አገላብጦ አየው፡፡ የጭስ መውጫ ቱቦውንና ግድግዳውን አጤነ፡፡ ከዚያም «ለምንድነው የምወጣው?» ሲል ጠየቀ::

«ከሦስተኛው ፎቅ ጣራ ላይ አንድ ሰው አለ፡፡ የምትወጣው የእርሱን
ሕይወት ለማዳን ነው» ሲል ሞንትፐርናሴ መለሰለት::

«ትወጣለህ?» ሲል ብሩገር በጉጉት ጠየቀው::

«ይቻላል» አለ ልጁ የተጠየቀውን ጥያቄ በማቃለል፡፡

ግዩለሜ ልጁን ተሸክሞ ከፈራረሰው ቤት ጣራ ላይ ወረወረው::

የበሰበሰው ጣራ ተንቋቋ፡፡፡ ብሩና ሁለቱን ጫፍ ከቋጠረ በኋላ ይዞት
የነበረውንም ገመድ ወረወረለት:: ልጁ ወደ ጭስ መውጫው አመራ፡፡ ልጁ እየተንፏቀቀ መውጣት እንደ ጀመረ ቴናድዬ አየው፡፡ ቴናድዩ ዝናብ እየዘነበበት ሳለ ውስጥ ውስጡን ከፍርሃት ብዛት እንዳላበው ታውቆታል።

ልጁ ገና ሲያየው ማን እንደሆነ አወቀው፡፡

«ቆዩ እስቲ! ይሄማ አባቴ ነው» ሲል ተናገረ፡፡ «ብቻ ይህም ቢሆን
ከመውጣት አያግደኝም» ብሎ ገመዱን በጥርሱ እንደያዘ ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ልጁ እንዴት እንደወጣ በቃላት ለመግለጽ ያዳግታል፡፡ ዱር አዳሪ
ልጆች የሚሠሩት ሥራ ተአምር ነው ብሎ ከማለፍ በስተቀር ሌላ ለመናገር አይቻልም፡፡ ልጁ ቴናድዬ ከነበረበት ደርሶ ገመዱን በማጠላለፍ ረድቶት
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከዚያ አምልጠው ወረዱ፡፡ ልክ እነርሱ ከዚያ ወርደው መንገድ ሲጀምሩ ጎሕ እንደ መቅደድ አለ፡፡ ልጁ ምናልባት አባቱ ወደ እርሱ
ፍጡር መጥቶ ያነጋግረው እንደሆነ ጠበቀ፡፡ የጠበቀውን አላገኘም:: መንገድ ዳር
ከነበረው ድንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡ ከዚያም የተቀደደ ጫማውን ካጠለቀ በኋላ «አልቋል አይደል? ከአሁን በኋላ አትፈልገኝም? ችግራችሁ ተወግዶላችኋል፤ እንግዲህ እኔ ልሂድ?» ሲል ጠየቀ::

ይህን እንደተናገረ መንገዱን ቀጠለ፡፡ አምስቱ ሰዎች ግን ተራ በተራ ከፈራረሰው ቤት ወጥተው ሄዱ፡፡ ልጁ ራቅ ብለው እንደሄደ ባቤ ወደ ቴናድዬ ዞር ብሉ «ልጁን አየኸው?» ሲል ጠየቀው::

‹‹የምን ልጅ?››

«ገመዱን ከነበርክበት ያመጣልህ ልጅ ነዋ!»

«ልብም ብዬ አላየሁት::»

«ብቻ... እኔ እንጃ፣ ልጅህ ነው መሰለኝ::»

«ወይድ እባክህ» አለ ቴናድዬ ፣

«ይመስልሃል?»....

💫ይቀጥላል💫
👍28😁2
አትሮኖስ pinned «#ምንዱባን ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ ፡ ፡ #ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ ....ልክ ፍቅረኛዋን የምትደባብስ ይመስል በለስላሳ እጆችዋ ድንጋዩን በማሻሸት አመሰገነችው:: «ምነው ተጫጫነኝ፣ ማን አለ ከአጠገቤ» እንደሚባለው ሁሉ ምንም እንኳን በዓይንዋ ባታየውም ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ ከበዳት:: ይህ እንዴት ሆነ ቢባል በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡ ፊትዋን አዙራ ከተመለከተች በኋላ ብድግ አለች:: እሱው…»
#ሰው (አጭር ልቦለድ)


#በበእውቀቱ_ስዩም

ጢም ማቀምቀም በጀመርኩበት ዘመን በከተማችን አንድ ተአምረኛ ባህታዊ ብቅ አለ፤ 'ጥቁር ኢየሱስ ብለው ሊጠሩት የደፈሩ ሰዎች ሁሉ ነበሩ ፤ ባህታዊው እውር ያበራል፤ ጎባጣ ያቀናል፤ ባንድ ጊዜ የከተማው ሆስፒታሎች ሁሉ ባዶ ሆኑ፤ የሆነ ጊዜ ላይ እንዲያውም ሙት ማስነሳት ሁሉ ጀምሮ ነበር፤ የከተማችን አስተዳዳሪ ግን “ ለተነሺዎች ማቋቋሚያ የሚሆን በጀት የለንም ብሎ ከለከለው፤

ባህታዊው ባንድ ወቅት ከተማውን አቋርጦ ሲያልፍ ወልደ ሰንበት ከተባለ የከተማው ነዋሪ ጋራ ተገናኘ፤ ወልደ ሰንበት በራዛ ዘመቻ ጊዜ ፈንጅ ብልቱን ቆርጦበታል፤ በጥሮታ ከተገለለ በሁዋላ ‘መራባት የተሳናቸው ወንዶች ማህበር’ ፕሬዚዳንት ሆኖ ያገልግላል፤

ወልደሰንበት ባህታዊውን ሲያየው “ አባት ሆይ፥ አገሬን አገሬን ብየ ስዋትት ዘሬን ሳልተካ ላልፍ ነው፤ ፈውሰኝ “ ሲል እግሩ ላይ ወድቆ ተማጠነው።

ባህታዊው ወደ ሰማይ አንጋጦ ትንሽ ከጸልዩ ሲያበቃ ወልሰንበትን አስወልቆ ጉያውን ዳበስ አደረገው ፥ መቸም አታምኑኝም ፤ ግን ሀቅ ከከመመስከር አልታገድም፤ የሰውየው ጉምድ ብልት ወዲያውኑ አቆጠቆጠ። ተአምረኛውን ሰውየ ያጀቡ ወንዶች አፋቸውን በጋቢያቸውና በኮሌታቸው ጫኑ !የሴቶች እልልታማ ፤እስከመተማ ፤ ተሰማ፥

ባህታዊው ይህንን ተአምራዊ የብልት- ተከላ ፈጽሞ ትንሽ አለፍ እንዳለ ወልደ ሰንበት እያለከለከ ደረሰበትና እግሩ ስር ተደፋ፤

“ አሁን ደግሞ ምን ፈለግህ?” አለው ባህታዊ፥ በታከተ ሰው ድምጽ ፥
ወልዴ እንዲህ ሲል መለሰ፥

“አባት ሆይ ! በነካ እጅህ ትንሽ ተለቅ ልታረግልኝ ትችላለህ?”🙄
😁29👍18
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_አንድ

...ዮርዲ” ነው ያልኩት ? ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ከአቲዬ ቀጥሎ በዚች ምድር ያቆላመጥኩት ስም እነሆ..

ጠዋት ዩኒፎርሚን ለብሼ ደብተሮቼን አዘጋጀሁና እየቀፈፈኝ ወደ ትልቁ ቤት ሄጀ አንኳኳሁ፡፡

“ማነው?” አለችኝ ዛፒ፡፡ ደነገጠኩ፡

እኔ ነኝ አልኩ እየፈራሁ፡፡

«ግባ ክፍት ነው»፡፡ ገፋ ሳደርገው የሚያብረቀርቀው የጣውላ ሰር ድምፅ ሳያሰማ ተከፈተ ክፍቱን ነው ያደረው ማለት ነው::
ዝርከርክ ያለው ሳሎን ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ ዛፒ ሶፋው ላይ
የአልጋ ልብስ ጣል አድርጋ ተኝታለች፡፡ ፊቷ የተቀመጠው ጠረጴዛ ላይ የሻይ ብርጭቆ፣ የውሃ ጠርሙስ፡ ሩቡ ብቻ የተበላ ሰላጣ፣ ምንም ያልተነካ ዳቦ ዝርክርክ ብሏል፡፡ ብዙ ምግብ
ማቅረብና ምንም አለመብላት ልማዷ ነው ይገርመኛል፡፡

“ምንድነው በጠዋቱ“ አለች እየተነጫነጨች፡፡ ድምጿ የወንድ ይመስላል ጎርንኗል፡፡

"እ..ትምህርት ቤት ከሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደኛ ወጣሁና ልንገርሽ ብዬ ነው"
ድምጼ ተንቀጠቀጠብኝ፡፡

ቀጥ ብላ ግራ በገባው ፊት እየችኝ፡፡ የሌሊት ልብሷን ትከሻዋና ትከሻዎ አካባቢ ይዛ አስተካከለች!
አቤት ደረቷ ቅላቱ ይንቦገቦጋል፡፡ ከኋላው ቢጫ መብራት የበራበት መስተዋት ይመስላል፡፡

"እኔ ምናገባኝ ታዲያ?!" የምትል መስሎኝ ነበር፡፡ ድንገት የሆነ ነገር ትዝ እንዳለው ሰው ፈገግ ብላ፤

"እና ሳመኛ! እንደዚህ ነው እንዴ የምስራች የሚነገረው? መርዶ አስመሰልከው እኮ!” አለችኝና
ሁለት እጆቿን እንደ ክንፍ ዘረጋቻቸው፤ ያውም በፈገግታ፡፡ ሁለት ጡቶቿ አፈጠጡብኝ፡፡

ግራ ገብቶኝ እንደቆምኩ፣ ና እንጂ ሳመኝ!” ብላ ጮኸትብኝ፡፡

በደመነፍስ እየተደነቃቀፍኩ ሄጄሄጄ ሄጄ ሄጄሄጀ.ሄጀ እጆቿ ሲጠመጠሙብኝ ሁሉ እርምጃዬን
ያቆምኩ አልመሰለኝም፡፡ ጥብቅ አድርጋ እቅፉኝ፣ “ጎበዝ የኔ ወንድም እኮራብሀለሁ!” አለችኝ፤
በለው ! ከሽ አለ የሻዩ ብርጭቆ ከጠረጴዛው ላይ ወድቆ፡፡ “ይሰበር ተወው!” አለቸኝና ጉንጬን
ስማ ለቀቀችኝ፡፡ ይሄ ቤት ለካ የወይዘሮ እጥፍወርቅ ቤት ነው !!

ከዛፒ ጋር እንደወጣሁ በደስታ ሰከሬ መንገዱን ሁሉ፣ ሰውን ሁሉ አየሁት፡፡ መቼ ነው ይሄ ትልቅ
የመኪና ኪራይ ማስታወቂያ ነዳጅ ማደያው ፊትለፊት የተሰቀለው ? መቼ ነው ይሄንኛው ሕንፃ
ተሰርቶ ያለቀው? ወቸ ጉድ አዲስአበባ እንዴት ተለውጣላች? ከሆነ አገር የመጣሁ መሰለኝ፡፡
ደግም ደስ የሚል ነገር ይሸተኛል፡፡ አፍንጫዬም ዛሬ ገና የተከፈተ ይመስል።

ዮርዳኖስ ጋር ስንገናኝ፣ “ምነው?” አለችኝ፡፡

"እ" አልኳት፡፡

"አይ ቆመህ ሳገኝህ ነዋ” አለችኝ፡፡ ለካስ ዮርዳኖስን ቆሜ አልነበረም የምጠብቃት። ያልጠበቅኳት
መስዬ ነበር መጠበቅ የነበረብኝ፡፡ ሳመችኝ ጉንጬን፡፡ ዛፒና ዮርዳኖስ እኔ በምባል ኳስ
በከንፈራቸው እየተቀባበሉ ቮሊ ቦል የሚጫወቱ መሰለኝ፡፡ "ተስመህ ትወጣለህ፣ ሰመው
ይቀባሉሀል የሚል ትንቢት ከሰማይ የታወጀም መሰለኝ፡፡ ድፍን አዲስ አበባ እንደ ዳቦ፡ እንደ
ዘይት፣ እንደታክሲ እኔን ለመሳም የተሰለፈ መስሎ ተሰማኝ፡፡(ቀስ ትደርሳላችሁ አትጋፉ ሂሂሂሂ)

ዮርዳኖስ ፈገግ ብላ አፍንጫዋን በመቀሰር ጠጋ አለችኝና፣ ደሞ አሪፍ ሽቶ ፣ እፉፉፉፉፉፉ
ያደረጉብ ማነው?" አለችኝ:: አፈርኩ፡፡ ለካ የዛፒ ሽቶ ነው ሲከተለኝ የነበረው፡፡ የዛቲ ሽፋ
የዋዛ አልነበረም፡፡ ከዚች ቀን ጀምሮ እድሜ ልኬን ሲከተለኝ ነው የኖረው፡፡ ሲያሳድደኝ ሳይሆን
ሲከታለኝ፡፡ የሆነ ዙሪያዬን ከብቦ እንደ እናት አቅፎኝ፡፡

ሰው ወደ ውስጥ የሚስበው አየር እክስጅን፥ ወደ ውጭ የማያስወጣው ካርቦንዳይ ኦክሳይድ እያሉ ያስተማሩን ቅኔ ነበር ሳይንሳዊ ቅኔ !! አሁን አሸብር ወደ ውስጥ የሚስበው ፍቅር፣ መፈቀር፣ መከበር፣ መፈለግን ነው፡፡ ወደ ውጭ የሚተነፍሰው እርካታ፡፡ የአየር ብክለት ማለት ሌላ ትርጉም የለውም እኮ የተገፉ፣ የተገለሉ፣ የተናቁ፣ ሕዝቦች ጥላቻን ወደ ውስጣቸው ሰበው መልሰው ጥላቻን ወደ መላው ዓለም መተንፈሳቸው ነው:: መፍትሄው የፍቅር ችግኝ በልባቸው
መትከል ነው:: እነሆ ዮርዳኖስ የተከለችውን ዝግባ ዛፒ የምትባል ዝናብ ስታረሰርሰው ዘርፈፍ
ብሎ በቀለ፡፡ ሕያውነት ከስሩ አረፍ የሚልበት ጥላ ሆነ፡፡

እኔማ ዛፒ ጥቁር ደመና አዝላ እያጉረመረመች ሰማይ ላይ ተንጠልጥላ ሳያት፣ መሽቆጥቆጥና ጥላቻዬን እንደ ዥንጥላ ስዘረጋ ነበር የኖርኩት፡፡ ክፉትም ጉልበት የሚኖረው እንደክፋት ልንቀበለው በተዘጋጀነው መጠን ነው::

“አንተ ሴት ነህ እንዴ?” ብላ ዛፒ ሳቀችብኝ፡፡ አፈርኩ፡፡ አንደኛ መውጣቴን ምክንያት በማድረግ
ዛፒ ልብስ ልትገዛልኝ ወሰደችኝና ምረጥ! ስትላኝ መጀመሪያ እጄ አንድ ቀሚስ ላይ አረፈ፡፡
ለእቲዬ ልኳ የሚሆን ቀሚስ ነበረ፡፡ ለዛ ነበር የሳቃችው::ልብስና ጫማ ገዛችልኝ፡፡ የሱሪዬን ቁጥር ስጠየቅ አላውቅም ነበር፡፡ ሱሪ ገዝቼ አላውቅማ፤ የጫማ
ቁጥርም አላውቅም፡፡ የሀብታም ልጆች ልብስና ጫማቸው ከሱቅ የተገባ ሳይሆን አብሯቸው
የሚወለድ ይመስለኝ ነበረ፡፡
ሃሃሃ… ግን ይሄው ሁሉ ነገር ሱቅ ውስጥ አለ ሸቀጥ ነው፡፡ ያው እዛጋ ቶማስ የሚባለው
ሁልጊዜ በሴት የሚከስሰው የክፍላችን ልጅ ጫማ ይሄው የራሄል ቦርሳ ኧረ ጉድ የቲቸር
ተስፋ የጥቁር ባለ ብዙ ኪስ ጃኬትም ያውና፡፡ ትንሽ ብቆይ እነዛ ውድ ነን የሚሉ ልጆች
እዚህ ተደርድረው ሲሸጡ አገኛቸው ይሆናል፡፡
ሲገርም ሁለት ሱሪ፣ አንድ ጫማ፣ ሁሉት ሸሚዝና አንድ ሹራብ ነፍስ ካወቅኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ልብስ ከሱቅ ገዛሁ፡፡ ለካሁት፡፡ መስተዋቱ ፊት ስቆም ደነገጥኩ፡፡ ልብስ ማለት ተራ ድሪቶ ነው ምናምን የሚሱ ሰዎች እንዴት ጅሎች ናቸው እባካችሁ! ራሴን በመስተዋት ሳየው ታላቅ ፍንዳታ እዕምሮዬ ውስጥ ተፈጠረ፡፡

እወራረዳለሁ ጥቁር አምበሳ፣ ኮከበ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲሰ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ቆንጆና ወንዳወንድ አቋም ያለኝ ልጅ እኔ ነኝ !! እፎይ! ከቤተክርስቲያን ሃጢያቱን ተናዞ እንደወጣ ሰው ሸክሜ ቀለለኝ አደግኩ ደግሞ !! የክፍሌን ልጆች በየቤታቸው እየሄድኩ እጄን ኪስና ኪሴ እስገብቼ “ሃይ!” ማለት አማረኝ፡፡

ዛፒ የለበስኩት አዲስ ሹራቡ ላይ የነበረውን ወረቀት ከኋላ ክሩን በጥርሷ በጥሳ አላቀቀችልኝና፣
አንተ ልጅ ቆንጆ እኮ ነህ አለችኝ፡፡ በሙቅ ውሃ በተሞላ ገንዳ ውስጥ የመግባት ያህል ቓሏ ይሞቅ ነበር፡፡ ቆንጆ መሆን ማለት የአፍንጫ መሰልከከ፣ የዓይን መንከባለል፤ የጥርስ መደርደርና
ንጣት ማለት አልነበረም፡፡ ለኔ ቆንጆ ማለት በሰው ዓይን መሙላት ማለት ሆነልኝ፡፡

ዝም ብላችሁ የሕይወት መንገዳችሁኝ ዙሩና ተመልከቱ! አለቀ ያላችሁበት ቦታ ላይ የነበረውን የሚመጣውን የሚያያይዝ ድልድይ ይኖራል፡፡ ይሄን ድልድይ የሚያምኑ ፈጣሪ ነው ይሉታል የማያምኑ 'የስነሕይወት መርህ ነው' ይሉታል፡፡ ለእምነቱም ለሳይንሱም ግድ የማይሰጣቸው እድል ይሉታል፡፡ እኔ ግን ይሄ አንዴ በዛ አንዴ በዚህ የሕይወቴን ተራዳ አየደገፈ የሚያቆመው
ከአቲዬ ድፍን ሃምሳ ብር የተበደረው እግዚያብሔር ነው እላለሁ፡፡
👍3316
እንዲያ ነው የመቀጠላችን ስንከሳር ባማረ የሕይወት አትሮኖስ ላይ ተቀምጦ የሚገለጠው:: ዛፒ ልብስ ከገዛችልኝ ከሳምንት በኋላ ትምህርት ቤት ቁጭ ብዬ መቁረጫ የሌለው ሃሳብ ውስጥ
ተዘፈቅኩ። እንደ ቀልድ ነበር ሀሳቡን የጀመርኩት፡፡ ልብሴ የብዙዎች ፊት እንዲበራ አድርጓል፤ መንገድ ላይ ሴቶች ያዩኛል፡፡ እንዳንዴ ማፍጠጣቸው ሲበዛ፣ እነዚህ ሴቶች ግን ያልለበሰ
ሰው፣ ያላብረቀረቅ ነገር አብስትራክት ይሆንባቸዋል - ቶሎ አይታያቸውም” እያልኩ አስባለሁ፡፡

ዮርዳኖስ ክንዴን ጨምድዳ መሄድ ከጀመረች ቆየች፡፡ ጓደኞቿ “ኤክስሬይ ነገር ነሽ ይሄ ልጅ
ለካ ገና በፊት ውበቱ ታይቶሻል፡፡” እንዳሏት ነገረችኝ፡፡ እግረ መንገዷን፡ “ዛሬ ስለለበስክ ሳይሆን በፊት ከነድሪቶህ ሰው ሳያይህ በፊት ነው የቀረብኩህ መልዕክት ማስተላለፏም እንደሆነ አንጃ !!

እውነቱን ለመናገር ሰው ራሱን ወዳድ ነው:: በዚህ ሁሉ ሃሳቤ ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳን ስለ አቲዬ አላሰብኩም፡፡ እኔነት ሲያደከመው የኖረ ሰው ሸክሙን ጣጥሎ ብቻውን የሚቆምበት ቀን አለ አይደል ጥፉታችንን ብቻችንን የምንጋፈጥበት!ራሳአችንን የምንወቅስበት፣ ደስታና ስኬታችንን በራሳችን ልፋት ያመጣነው ነው የምንልበት በቃ ራሳችንን ብቻ የምንሆንበት፣ የዛን ቀን እንደዛ ሆኜ ነበር፡፡

ታዲያ ውጤት ነበረው፡፡ በውስጤ የተትረማመሱ ሀሳቦች በስርዓት ተሰደሩ፡፡ “ሞተዋል" ያልኳቸው ጉዳዮች አፈራቸውን እያራገፉ በህሊናዬ አደባባይ በትንሳኤ ቆሙ፡፡ ፍቅር የሴት ይሁን የእናት አገር ይሁን የፈጣሪ ያልለየት ባለ ብዙ ዘርፍ ፍቅር ባዶውን የኖረ የልቤ መስቀል ላይ እንደገና የተሰቀለ መሰለኝ፡፡ እንደ ባንዲራ በሕይወት መዝሙር ታጅቦ ወደነፍሴ ከፍታ ቀስ እያለ የሚሳብ ፍቅር፡፡

እንደ ሰው ስንቆጠርና ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፡ መንደርተኛ፣ አገሬው ቦታ ሲሰጠን ወይም
የሰጠን ሲመስለን ከማሕበረሰብ ያፈነገጠ ውስጣዊም ውጪያዊም ስብዕናችንን ሰልፉን እንዲያሳምር ውስጣችን ራሱን ይመከራል፡፡ እንደዛ ነው የሆንኩት፡፡ እና ደግሞ ፈሪም ሆንኩኝ የሆነ ነገር መፍራት ጀመርኩ ፡፡

እንደ ሰው ከመቆጠር ስናልፍና እንፋሽ አከንፋሻችን ሲበዛ የሰልፉ መሪ የሆንን እየመሰለን እንደገና ያገኘንበት እንረግጣለን፡፡ መልካም መካሪ ካገኘን ወደ ሰልፉችን የመመለሳችን ነግር ያውም በጭብጨባ ታጅቦ ይደገማል፡፡ ካልሆነ ግን ማንነት፣ ስም፣ አላማ፣ ስብዕና “እብድ የበላው በሶ ሆኖ ይቀራል፡፡ የታዋቂ እውቅና መንኮታኮቱ፥ የእግር ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ በልክ እንዳልተሰፋ ቃሚስ መንዘላዘሉ፣ የትውልድ ሽሽት ከመጥበሻው ወደ እሳቱ የመሆኑም ነገር ሁሉ
የማንነትን ሰልፍ መሳት ነው፡፡
አጉል ወደድኩ ብሎ ሰልፍ ስትጥስ የሚያጨበጭብልህ፣ ጠላሁ ብሎ ጎትቶ ከሰልፍህ የሚያስወጣህ በሞላባት ምድር ጥላቻና ፍቅር እኩል የጥፋት መንገድ መሆናቸው የሚገባህ እንዲህ ራስህ ጋር ሃቅ ሃቁን ስትነጋር ነው፡፡

እናም ባነንኩ !! እኔ ማነኝ? እኔ አሸብር ነኝ፡፡ እናቴ አፀደ ትባላለች፡፡ በዚህች ምድር ላይ
የስጋ ዘመድ የምንለው የለንም፡፡ እናቴ በየሰዉ ቤት እንጀራ ትጋግራለች፣ ልብስ ታጥባለች፣
እንደ ሰው ተከብራ አታውቅም፡፡ ተስፋ የምታደርገው እኔን ብቻ ነው፡፡ ብቸኛ አላማዬ አገር፣
ሕዝብ፣ ወገን አይደለም እናቴ ናት !!

ማንም ስፖለቲካ አመለካከት ቢራኮት፣ ማንም ማንንም ቢከተል ስሜት አይሰጠኝም፡፡ የትኛውም
እምነት 'ወዮልህ! ቢል፡ በዚያ በዚህ ሲፈልግ በአምላኩ፡ ሲያሻው በፖለቲካው ተከልሎ ቢቧደን
(እችን ታህል አይገርመኝም፡፡ እናቴን ነፃ ለማውጣት የሕይወት ጦርነት ውስጥ ያለሁ ታጋይ
ነኝ፣ ሆቺ ሚኒ ነኝ ግዙፉን አምባገነን ሕዝብ ከትንሽ የእናትነት ግዛቴ የማባርር ቼጉቬራ ነኝ፤ በስግብግብና ራስ ወዳዶች ክንድ ስር በፅናት አልፌ የሚስኪን እናቴን ከፍታ የሚያረጋግጥ
አብዮት ምድርን የምንጥ እንጄላ ዴቪስ ነኝ፤ ፋራንት ፋኖን ነኝ፡፡

የእናቴ ጠላት ድህነት አይደለም 'ስለነፃነት የሚቀባጥረው ሕዝብ” እንጂ። የሕዝብ ልጅ የሚባል
ቀልድ አይገባኝም፡፡ የእናቴ ብቻ ልጅ ነኝ፡፡ ፅንፈኛ ነኝ፡ ዘረኛ ነኝ፣ አከራይ ነኝ - ከእናቴ ጋር
በጭፍን የተሰለፍኩ ሌላው የተረገመ ነው ብዬ የማምን ዘረኛ ነኝ፡፡ 'ከእናቴ ወዲያ ታጋሽ፣ ጨዋ፣
ለሰው ልጆች ኣሳቢ፣ አዋቂ ጀግና ዘር የለም የምል ! አክራሪ ነኝ፥ ከእኔ እናት ሊላ ሌላ እናት
እናት የማይመስለኝ፡፡ እናም ጠላቴ ሕዝብ ነው:: ሕዝብን መበቀል ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም
ጠላትህ የትም የሚገኝ እንደ ትቢያ እያፈስከ የትም የምትበትነው ገለባ ነው፡፡....

አላለቀም
22👍19
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


መማረክና መረሳሳት

ብረት በማግኔት እንደሚሳብ ፍቅረኛም ባፈቀረው ጠዋት ማታ
ይሳባል፤ ይጉተታል፡፡ ሮሚዮ በዡልየት ፍቅር ተጎትቶ በአትክልት ቦታ እንደ ተንሸራሸረ ሁሉ ማሪየስም ከኮዜት የአትክልት ሥፍራ ለመንሸራሸር ተመላለሰ፡፡ ሆኖም ማሪየስ የሮሚዮን ያህል አልተቸገረም:: ሮሚዮ ከዡልዬት
ግቢ ለመግባት ረጅም ግምብ መዝለል ነበረበት:: ማሪየስ ግን ይህ አላስፈለገውም:: የሽቦ አጥርን በቀላሉ ፈልቅቆ ነበር የሚገባው:: ቀጭን
ስለነበር ሰፊ ክፍት ቦታ አላስፈለገውም::

አካባቢውም ጭር ያለ ስለነበር ሰው ሳያየው በቀላሉ ሊገባ ቻለ፡፡
የሚመጣው ደግሞ ማታ ማታ ነው:: በዚያች በተባረከች ምሽት ከንፈር ለከንፈር ከተገናኙ ወዲህ በእየለቱ ነው የሚመጣው::

በ1832 ዓ.ም የግንቦት ወርን በሙሉ አንድ ቀን እንኳን ሳይጓደል
ማታ ማታ ተመላልሶ ከፍቅረኛው ጋር ተገናኘ:: እነዚህ ሁለት የዋህ
ፍጡሮች እንዳይገናኙ ጨለማ፣ ብርድ፣ ነፋስ አላገዳቸውም::

በየዕለቱ ሲገናኙ ምን ይሠራሉ? ምንም:: አንዱ ሌላውን በማድነቅ
ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ:: የሚረግጡትን መሬት እንደ ተቀደሰ ቦታ ነው የሚቆጥሩት:: ብዙ ጊዜ የሚያወሩት ስለፍቅር ነው:: ማሪየስ የሙት ልጅ
መሆኑን! ስሙ ማሪየስ ፓንትመርሲ እንደሚባልና የሕግ ባለሙያ እንደሆነ ገልጾላታል፡፡ ኑሮውን የሚያሸንፈው ለአሳታሚ ድርጅቶች አንዳንድ ጽሑፍ
እየጻፈ እንደሆነና አባቱ በአገሩ የታወቀ ጀግና እንደነበር ነገራት፡ እንዲሁም ከዲታው አያቱ ጋር መጣላቱንና የአባቱን ሹመት በመውረስ ባሮን እንደሆነም
ገልጾለታል። ባለማዕረግ ስለሆነ ኮዜት ላይ የተለየ ስሜት አላሳደረባትም::ለእርስዋ ምንም ይሁን ምን ማሪየስ ማሪየስ ነው:: በእርስዋም በኩል ገዳም ውስጥ ማደግዋን፣ እናትና አባትዋ መሞታቸውን፣ የእንጀራ አባትዋ ስም። መሴይ ፎሽለማ መሆኑን፣ ይህም ሰው ድሃን የሚወድ እጅግ ደግና ራሱም ምስኪን እንደሆነና እርስዋን ለማስደሰት ሲል ራሱን ረስቶ ያላደረገው ነገር
እንደሌላ ነገረችው፡፡ የእንጀራ አባትዋ ለእርስዋ ሲል ምቾቱን ሁሉ መሰዋቱንም አስረዳችው::

የሚገርመው ማሪየስ ኮዜትን ስላገኘና በምትነግረው ነገር ሁሉ
ስለረካ ሌላው ቀርቶ አንድ ቀን ሌሊት በቀዳዳ ከነቴናድዬ ቤት ውስጥ ያየውን እንኳን ረስቶ አባትዋ ላይ ደርሶ ስለነበረው ትርኢት አልነገራትም::
ሚስተርና ሚስስ ቴናድዬ በአባትዋ ላይ ስላደረሱት በደልና አባትዋ እንዴት አድርጎ ከዚያ ወጥመድ እንዳመለጠ ለጊዜው አልታወሰውም:: ሌላው ቀርቶ ማታ ያደረገውን ጠዋት፣ ጠዋት የሠራውን ማታ ይረሳል፡፡ አንድ
ሰው ቀን ላይ ተገናኝቶ «ቁርስህን ምንድነው የበላኸው?» ብሎ ቢጠይቀው አያስታውስም፡፡ ጆሮውና ሕሊናው በኮዜት ትዝታ ስለተደፈነ የማስታወስ
ችሎታውን ቀንሶበታል፡፡ ከዚህም በላይ ከኮዜት ተለይቶ የሚያሳልፈው ጊዜ ዝም ብሎ የሚያልፍ እንጂ ኑሮን እየኖረ የሚያልፍ ስላልመሰለው በሌላ
ጊዜ የሚፈጽመው ተግባር ሁሉ እርባነቢስ በመሆነ ይረሳዋል:: ለማሪየስ ኑሮ ወይም ሕይወት ማለት ከኮዜት ጋር የሚያሳልፈው ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ ይህም የእውነተኛ ፍቅር ባሕርይ ነው::

ኮዜት በጣም የተዋበች ልጅ ስትሆን ማሪየስ ነፍስዋንም ጭምር ለማየት ነው የሚፈልገው:: የአንድን ነገር ሁለንተና በጉልህ ለማየት
የሚቻለው ዓይን ሲጨፈን ስለሆነ ማሪየስ ዓይኑን ብዙ ጊዜ ይጨፍናል፡፡ ማሪየስና ኮዜት መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን አንስተውና ተነጋግረውበት
አያውቁም፡፡ ማንኛውም ነገር እንደአመጣጡ ነው የሚቀበሉት፡-
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዣን ቫልዣ ምንም አልጠረጠረም፡ኮዜት ዘወትር ደስ ብሉአት ስላየ
ከዚያ ወዲያ የሚፈልገው ነገር አልነበረምና ደስ እያለው ይኖራል፡፡ ኮዜትም ማሪየስን በማግኘትዋ መንፈስዋ ስለረካ ዘወትር የደስታ ምልክት ግንባርዋ ላይ ይነበባል:: በሁለት ፍቅረኞች መካከል መግባባት ካለ አብረው መኖር
ይችላሉ:: በመካከላቸው ሰላም እስካለ ድሬስ የተለየ ጠባይ ስለማይታይባቸው ሦስተኛ ሰው አዲስ ነገር ሊያይባቸው አይችልም:: ጥቂት ጥንቃቄ በማድረግ ከፍቅረኛቸው ጋር መኖር ይችላሉ::

አባትዋ የፈለገውን ለማድረግ ሲፈልግ ተቃውሞ አላሳየችውም፡፡ ዞርዞር ብዬ ልምጣ? እሺ አባዬ:: ዛሬ ከቤት ልዋል መሰለኝ? እንደፈለግህ፡፡
አብረን እናምሽ፡፡ ደስታውን አልችለውም::አባትዋ ዘወትር አራት ሰዓት አካባቢ ይተኛል፡፡

ማሪየስ እንደሆነ ከኮዚት ጋር ለመጫወት የሚመጣው ከአራት ሰዓት በኋላ ነው:: ቀን ቀን
ተገናኝተው አያውቁም፡፡ ዣን ቫልዣ እንደሆነ የማሪየስ በሕይወት መኖር እንኳን ረስቷል፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ግን «ምነው ኮዜት፤ ከኋላሽ ኖራ ነክቶሻል ፤ ከየት መጣ?» ብሎ ይጠይቃታል፡፡ ያን እለት ማታ ከማሪየስ
ጋር ግድግዳ ተደግፋ ቆማ ኖሮ ልብስዋን ኖራ ነክቶባታል፡፡
አሮጊትዋ ቱሴይ በጊዜ ስለምትተኛ እርስዋም እንደ ዣን ቫልዣ ምንም ነገር አልጠረጠረችም:: ማሪየስ ደፍሮ ከቤትዋ ውስጥ ገብቶ
አያውቅም፡፡ አትክልቱ ውስጥ እንኳን ቢሆን አሳቻ ቦታ ይቀመጣሉ እንጂ ራሳቸውን አያጋልጡም:: ከአንድ ቦታ ከተቀመጡ አይነሱም:: ሁለቱም
አብረው በመሆናቸው ብቻ ረክተው ወሬም ባያወሩ ደንታ የላቸውም::ሌላው ቀርቶ በመንገድ የሚያልፍ እንኳን እንዳያያቸው ይጠነቀቃሉ፡፡
አብረው ተቀምጠው ሳለ ዓይን ለዓይን መተያየት፤ በየደቂቃው እጅ ለእጅ ተያይዞ ሃያ ጊዜ መጨማመቅ ደስታ ይሰጣቸዋል፡፡ በዚያች ሰዓት መብረቅ
ካጠገባቸወ: ቢወርድ እንኳን አይሰሙትም:: ይህን ያህል ነበር
ተመስጦአቸው::
ሆኖም ሁለቱ ፍቅረኞች በዚህ ሁኔታ እንዳሉ አንዳንድ ችግሮች
ደግሞ ፈር ቀድደው እየገቡ ነበር፡፡ አንድ ቀን ማታ እንደ ለመደው ማሪየስ ወደ ቀጠሮው ቦታ ለመሄድ አቀርቅሮ ይጓዛል:: ከአንድ ኩርባ መንገድ ላይ
ደርሶ ሊጠመዘዝ ሲል ድምፅ ይሰማል::

‹‹ሚስተር ማሪየስ እንደምን አመሸህ!››

ቀና ብሎ ሲያይ ኢፓኒን ናት:: ደንገጥ አለ፡፡ የኮዜት ቤት ካሳየችው እለት ወዲህ ትዝ ብላው ወይም ተያይተው አያውቁም:: አሁን ላገኘው ደስታ ምክንያት ብትሆንም ጨርሶ ረስቷታል:: መርሳት ብቻ ሳይሆን እንደገና መገናኘታቸው አናደደው::

የተደላደለ ፍቅር አንድን ሰው ፍጹም ያደርገዋል ብንል ተሳስተናል:: በስሜት መዋጥ ዝንጉ እንደሚያደርግም መርሳት የለብንም:: በስሜት የተዋጠ ሰው ክፋትንና ደግነትን መለየት ይሳነዋል፡፡ ውለታን፣ የሥራ
ኃላፊነትንና፡ መቃወስ ያለባቸውን ጉዳዮች ሁሉ ሊያስረሳው ይችላል::

ምን! አንቺ ነሽ እንዴ ኢፓኒን?» ሲል ለሰጠችው ሰላምታ በጥያቄ
መልክ መለሰላት::

«ምነው፣ በጣም ተኮሳትረህ ነው የምታነጋግረኝ? የአጠፋሁት ነገር
አለ?»

«የለም» ሲል መለሰላት::

በእርግጥም የያዘባት ቂም አልነበረም:: ደግሞም የሚቀየምበትም ምክንያት አልነበረውም፡፡ ኮዜትን በሚያነጋግርበት አንደበት ኢፓኒንን በጥሞና ማነጋገሩ ስለከበደው ብቻ ነው እንደዚያ የሆነው:: እርሱ ዝም ሲላት
እርስዋ ጮክ ብላ ተናገረች::

«ንገረኝ እስቲ አሁን» ብላ የሚናገረው ነገር እንደጠፋው ሰው ዝም አለች:: ፈገግታ ለማሳየት ሞከረች፡፡ ግን አቃታት፤ እንደገና ለመናገር ሞከረች::

«እና….» ብላ ንግግርዋን እንደገና አቋርጣ አቀርቅራ ቀረች::

«ደህና አምሽ ማሪየስ» ብላ መንገድዋን ቀጠለች::
👍21
የሚቀጥለው ቀን ሰኔ 3 ቀን 1832 ዓ.ም ነበር፡፡ ይህ ቀን በፈረንሣይ ታሪክ ውስጥ የተለየ ትውስታ ያለው ቀን ሲሆን በእለቱ ማሪየስ እንደለመደው በተመሳሳይ ጎዳና አድርጎ ወደ ቀጠሮው ቦታ ይሄዳል:: ከዚያች በአለፈው
ቀን ከተገናኙበት ሥፍራ ኢፓኒን አጋጠመችው:: በተከታታይ ለሁለት ቀን ስላገኛት ትንሽ የበዛ መሰለው:: በሩቅ ሲያያት መንገዱን ቀይሮ ወደ ማዶ
ተሻገረና አሳብሮ ሄደ፡፡ ከዚያ በፊት አድርጋው ባታውቅም ኢፓኒን
ተከተለችው:: እስከዚያን እለት ድረስ በዚያ ሲያልፍ በዓይንዋ ካየችው ትረካ ነበር፡፡ በአለፈው ቀን ብቻ ነበር ለማነጋገር የደፈረችው::

እንደምትከተለው ማሪየስ አላወቀም:: በቀዳዳ ሾልኮ የት እንደሚገባ አየችው:: የአትክልቱን ቦታ ተመለከተች፡: አንጀት በሚበላ ድምፅ ዝግ ብላ
«ለምን!» ስትል ተናገረች:: «ወደ ቤት መግባቱ ነው::»

የሚሾልክበትን ቀዳዳ ጠጋ ብላ አየችው:: ማሪየስ የአጥሩን አንድ
ቋሚ ነቀል አድርጎ እንደሚገባ ተረዳች:: መግቢያውን ጠብቂ የተባለች ይመስል ከአጠገቡ ቁጭ አለች:: ቀዳዳው ከሚቀጥለው ቤት አጥር አጠገብ
ሲሆን ከሁለቱ ቤቶች አጥር መገናኛ ላይ እንደ ኩርባ ያለ ሰወር ያለ ሥፍራ ነበር፡፡ ኢፖኒን የተቀመጠችው ከዚያ ሰዋራ ቦታ ላይ ስለነበር ምሥጢር
ላላወቀ አትታይም::

ከአንድ ሰዓት በላይ ከዚያ ቁጭ አለች:: የአሳብ ተገዥ ሆና ቃል
ሳትተነፍስና ከወዲህ ወዲያ ሳትነቃነቅ ሀውልት መስላ ነበር የተቀመጠችው፡፡ከምሽቱ አራት ሰዓት አልፎአል፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በዚያ ብዙም
ሰው በማይተላለፍበት መንገድ ለማለፍ ሲመጡ ከሩቁ ይታያሉ፡፡ ሰዎቹ እየቀረቡ ሲሄዱ አንደኛው ሰውዬ ሲናገር ይሰማል፡፡

«እኔ እኮ በጣም የሚገርመኝ ሳያስታጉል በየቀኑ ማታ ማታ መምጣቱ ነው።

ዓይኑን አጥብቦ ወደ ውስጥ ለማየት ሞከረ:: ምንም ነገር ለማየት አልቻለም::
ኢፓኒንም የተቀመጠችበት ሥፍራ ጨለማ ስለነበር እርስዋንም አላያትም አካባቢው ጥቂት ያስፈራ ስለነበር እርምጃውን ጨምሮ ፈጠን በማለት ተራመደ:: በዚህ ጊዜ ማሪየስ ከኮዜት ጋር ነበር፡፡

ሰማዩ እንደዚያን እለት ጠርቶና ከዋክብት በዝተውበት አያውቅም፡፡ የዛፎቹ መዓዛና የነፋስ ሽውሽታም የተለየ ነበር፡፡ አእዋፍ ድምፃቸውን አጥፍተው ለጥ ብለዋል፡፡ አየሩ እጅግም አይሞቅም ወይም አይቀዘቅዝም፧
ለጤና ተስማሚ ነው:: የአየሩ ሁናቴ ሊሆን ይችላል፤ ያን እለት ምሽት ከሌላው ቀን ይበልጥ ማሪየስ ደስ ብሎታል፡፡ ኮዜት ግን ተክዛ ነው ያገኛት:: ከልቅሶ ብዛት ዓይኖችዋ ቀልተዋል:: በዚያ የሕልም ዓለም የመጀመሪያው
ጭጋግ መሆኑ ነው:: የማሪየስ የመጀመሪያዎቹ ቃላት «ምን ነካሽ?» የሚሉ ነበሩ::

«ተመልከት› ካለች በኋላ ከዚያም ከምናውቀው የድንጋይ መቀመጫ
ላይ ሄዳ ቁጭ አለች:: ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ከአጠገብዋ ሲቀመጥ እርስዋ ቀጠለች::

«ዛሬ ጠዋት አባዬ ዝግጅት እንዳደርግ ነገረኝ፡፡ ምናልባት ለሥራ ጉዳይ ወደ ውጭ አገር ሳንሄድ አንቀርም፡፡»

ማሪየስ ነፍስ እንደተለየው ሥጋ ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር
ድርቅ ብሎ ቀረ ፤ በድን ሆነ፡፡ ከሕይወት መጨረሻ ስንደርስ መሞት ማለት መሄድ ሲሆን ከሕይወት መጀመሪያ ላይ ስንሆን ግን መሄድ ማለት መሞት ነው

ማሪየስ ለስድስት ሳምንታት ከኮዜት ጋር አብሮ በቆየበት ጊዜ ቀስ እያለ ደረጃ በደረጃ በየቀኑ የኮዜትን ልብ እየበላና አንጀትዋን እየሰረቀ ነበር፡፡ በፍጹም ልቦናዋ፤ በፍጹም አካልዋ ነበር የተገዛችለት:: ሥጋዋም ሆነ ነፍስዋ ከማሪየስ መዳፍ ስር ወድቋል፡፡ ለእርሱም ቢሆን ኮዜትን ማግኘት፣ ኮዜትን መጨበጥ ማለት እንደ እስትንፋስ መዋሀድ ማለት ነበር::ከዚህ ውህደት፣ ከዚህ አንድ የመሆን እምነት፣ ከዚህ ይነጣጠላሉ ተብሎ
ካልታሰበ የተጣመሩ ነፍሳት መካከል ወደ ውጭ አገር ሳንሄድ አንቀርም የሚል የመለያየት መልእክት መስማት ማለት የአንድን ሰው ልብ በቢላዋ
ከሁለት መክፈል ማለት ሆነ፡፡ ይህም ለማሪየስ «ኮዜት የአንተ አይደለችም» የሚል መልእክት መሰለው::

ቀደም ሲል እንዳልነው ማሪየስ ለስድስት ሳምንታት በሕይወት ኖረ፡፡
«መሄድ» የሚባለው ነገር ያንን ሕይወት ነው ያሳጣው:: የሚለውና የሚናገረው ነገር ጠፋው:: እንዲያው ዝም ሆነ፡፡ ቆየች ፣ ቆየችና እርስዋ በተራዋ «ምን ነካህ?» ስትል ጠየቀችው:: አጠገቡ ሆና ለመስማት
በሚያዳግታት ድምፅ «ያልሽው ነገር አልገባኝም» ሲላት እርስዋ ቀጠለች::

«እቃዬን እንዳዘጋጅ ዛሬ ጠዋት አባዬ ነገረኝ፡፡ የእርሱንም ልብስ
ሻንጣ ውስጥ በመልክ በመልኩ እንድከት አዝዞኛል፡፡ በውዴታ ሳይሆን በግዴታ ወደ ውጭ አገር መሄድ እንዳለበት ገልጾልኛል፡፡ ለእርሱ አንዲት አነስተኛ ሻንጣ፤ ለእኔ ግን ትልቅ ሻንጣ ሊገዛ ነው፧ ገዝቶም ይሆናል::ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ልንሄድ ስለምንችል ሁሉንም እንዳዘጋጅ ነው
የነገረኝ፡፡ የምንሄደውም ወደ እንግሊዝ አገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ስለዚህ መለያየታችን ነው ማለት ነው:: »

‹‹ግን እኮ..» ብሎ ቀረ፡፡

ጥቂት ቆየና «መቼ መንገድ የምትጀምሩ ይመስልሻል?» ሲል ጠየቃት

«ቀኑን እንኳን ወስኖ አልነገረኝም::

ማሪየስ ከተቀመጠበት ተነሣ፡፡

«ኮዜት መልስ እንደመስጠት የማሪየስን እጅ ይዛ ጨመቀችው፡፡»

«ይህ ከሆነ እንግዲህ» አለ ማሪየስ፣ «እኔም ወደ አንድ ኣገር መሄድ ይኖርብኛል፡፡»

ምን ማለት እንደፈለገ ስለገባት ስሜትዋ ተለዋወጠ፡፡ የፊትዋ
መለዋወጥ በጨለማ እንኳን ታየ::

«ምን ማለትህ ነው?» ስትል ጠየቀችው::

ማሪየስ ትኩር ብሎ አያት:: ከዚያም ዓይኑን ቀስ እያለ ሽቅብ እየወረወረ

«ምንም» ሲል መለሰላት::

«ከሄድክ ሂድ! የት እንደምትሄድ ግን እኔ ነኝ የምነግርህ፡፡ እኔ
ከምሄድበት መጥተህ እዚያው እንገናኝ፡፡»

ማሪየስ ከእንቅልፉ በደምብ ነቃ፡፡ እውነታውን በደምብ ለማየት
ቻለ፡፡ ወደ ኮዜት ፊቱን አዙር ጮክ እያለ ተናገረ::

«ከአንቺ ጋር ነው የምሄደው? አብደሻል ልበል? ከአንቺ ጋር ለመሄድ እኮ ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እኔ ደግሞ ገንዘብ የለኝም::» ያውም እንግሊዝ አገር ለመሄድ! እህ! ሌላው ቀርቶ ፓስፖርት ሲወጣ የሚከፈል ገንዘብ እንኳን የለኝም።

አጠገቡ ከነበረው የዛፍ ግንድ ጋር ሳያውቀው ተጋጭቶ ኖሮ ግንዱን
ተደግፎ ቆመ:: በሁለት እጆቹ ጭንቅላቱን ይዞና ግንባሩን ከዛፉ ግንድ ላይ አሳርፎ ነው የቆመው:: የዛፉ ሸካራ ቅርፊትም ሆነ የሞቀው ሰውነቱ ትኩሳት አልተሰማውም፡፡ ተስፋ እንደቆረጠ ሰው እንደ ሐውልት ሳይነቃነቅ
እረጅም ጊዜ ተገትሮ ቀረ፡፡ በመጨረሻ ፊቱን አዞረ፡፡ ከአጠገቡ የሚንቀሳቀስ
ድምፅ ሰማ፡፡ ኮዜት እያነባችው ነበር፡፡ ማሪየስ በአሳብ ተውጦ ዛፉን ተደግፎ ሳለ ኮዜት ለረጅም ጊዜ አልቅሳለች፡፡

ማሪየስ ወደ ኮዜት ሄዶ ከጫማዋ ስር ተንበረከከ፡፡ ቀሚስዋን ገልጦ
አንድ እግርዋን ብድግ አድርጎ ሳመው::

«ስሚኝ» አለ፤ «ነገ ማታ አትጠብቂኝ፡፡»

«ምክንያቱን ንገረኝ!»

«ትደርሽበታለሽ፡፡»

«ቀኑን ሙሉ ሳላይህ ውዬ ላድር! እንዴት ተብሎ! ሊሆን አይችልም፡፡»

«የእድሜ ልክ ጊዜ ለማግኘት ሲባል አንድ ወይም ሁለት ቀን
መስዋዕት ማድረግ ጥሩ አማራጭ ነው::»

«ምኞትህ ከሆነ ይሁን፡፡»

«ኮዜት፣ ምኞቴ ብቻ ሳይሆን የምፈልገው ነው::»

በሁለት እጆችዋ ጉንጮቹን ያዘች፡፡ በቁመት ከእርሱ ጋር ለመስተካከል ከእግርዋ ጣቶች ጫፍ ላይ ቆመች፡፡ የጭንቅላቱን የውስጥ ኣካል ለማየት ትችል ይመስል ዓይን ዓይኑን አፍጥጣ አየችው:: ማሪየስ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
👍152
«አድራሻዬን ማወቅ አለብሽ መሰለኝ፡፡ ምን እንደሚሆን ለማወቅ አንችልም:: ኩርፌይራክ ከሚባል ጓደኛዬ ጋር ነው የምኖረው:: መኖሪያችን
ከደ.ላ. ቫራ ጉዳና የቤት ቁጥር 16 ውስጥ ነው::

እጁን ኪሱ ውስጥ ከትቶ ሰንጢ አወጣ፡፡ በሰንጢው አድራሻውን
ካኣጥሩ ግድግዳ ላይ ጻፈ:: ነገራት ዓይን ዓይኑን ማየትዋን ቀጠለች::

ተነገ ወዲያ ባጊዜ ትመጣ የለ? እጠብቅሃለሁ:: ልክ ከምሽቱ አራት
ሰዓት ሲሆን ብትመጣ ይሻላል፡፡ ሰማኸኝ ፍቅሬ ቀኖቹ እንዲህ መርዘማቸው ያሳዝናል፡፡ ገባህ፣ እኔ ግን ከሦስት ሰዓት ጀምሮ ከአትክልቱ ቦታ ሆኜ
እጠብቅሃለሁ::

ቃል ሳይለዋወጡ በተመሳሳይ አሳብ በመዋጥና ከኮረንቲ ይበልጥ የስበት ኃይል ባለው የፍቅረኞች ግንኙነት በመሳብ አንዱ በሌላው ላይ በመወርወር ተቃቀፉ:: በፍቅር የሰከሩ ሁለት ሰዎች በሀዘን ጊዜ እንኳን
ምን እንደሚያደርጉ ሳይታወቃቸው ከንፈር ለከንፈር ይገናኛሉ፡፡ ዓይናቸው እምባ አቅርሮ አንዱ ሌላው ላይ ማፍጠጥ ሆነ፡፡ ማሪየስና ኮዜትም የፈጸሙት
ተግባር ይኸው ነበር፡፡


💫ይቀጥላል💫
👍24