አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰው_ሆኜ_አፈቀርኩሽ

የረገጥሽው አፈር እየለመለመ
በቃል ያወራሽው
የሰማይ ዳመና ጠፍቶ እየከሰመ
ስመሽ ያፈካሽው
ስቀሽ ያፀደቅሽው
የበረሃ አበባ አብቦ እያፈራ
ሰው ነሽ ብዬ አምኜ
መልኣክ ሆነሽ ሳይሽ
እንዴት አልደነግጥ እንደምን አልፈራ?

#መልአክ_ነሽ_አንችዬ

ጣፋጭ አንደበትሽ
ለቀናት ያደረ ሙት ይቀሰቅሳል
በዓይንሽ የጠቀስሽው
ጎባጣው ተቃንቶ ዲዳው ይናገራል
'ረግጠሽ ያለፍሽውን
ለም አፈር ተቀብቶ ሽባው ይራመዳል።

#መልአክ_ነሽ_አንችዬ

ጥላቻ ሰማይ ላይ
የቆመችን ፀሐይ ፍቅር ለውሰሻት
ለታወረ አህዛብ
ፈውስ ይሁን ብለሽ ብርሃን አርገሽ ላክሻት
ይኸው ከዚያ ወዲህ
ፅልመቱ ተገፏል በባርኮትሽ ምክንያት
አቤት ስትችይበት!!

አቤት ስትችይበት

ከተከፋ ፊት ላይ
ያ'ዘን አረም ነቅሎ የተስፋ ሳቅ መዝራት
ኣልፏል ካሉት ቅድም
የለም የሚሉትን ነገን ዛሬ መስራት
በህይወት ምጣድ ላይ
አሁንን አሟሽቶ ወደ ነገ መስፋት
አቤት ስትችይበት!!
(እንግዲህ እንዲህ ነው ..
አንቺ ከመለኮት እኔ ከሰው ወገን
አንቺ ተዓምረኛ
እኔ እግርሽ ስር ሆኜ ድነት የምለምን
ለክብርሽ መግለጫ
በልቤ ግዛት ላይ ገዳሜ ያደረኩሽ
እኔ ነኝ ምስኪኑ
ዝናሽን ሰምቼ ሰው ሆኜ ያፈቀርኩሽ ..
#ሰው_ከቀየው_እንጂ

ወጥቼ ከቀሳው
ለጊዜው ታግየ
ሞትን ድል ብነሳው
መኖር አሸነፈኝ
ቤቴ ተደፍቶብኝ፣ ሁለት ወር አለፈኝ።

ተፈጥሮየ ከዳኝ፣ ፈሊጡን ቀየረ
አካሌ ሸፈተ፣ አዲስ ወግ ተማረ
ገላየ በቁሙ፣ ሳር ማብቀል ጀመረ።

እንዳልቆይ መታከት፣ እንዳልወጣ ሽብር
ሳይደከመኝ ተኝቼ
እንቅልፍ አንገቴ ላይ፣ ቀንበሩን ሳይሰብር
ካልጋ ተነስቼ
እየተደናገርሁ
እየተደናበርሁ
በምሳ ሰአቴ፣ ራት እየጋገርሁ
ኑሮ እንደ ሳር ጉንጉን፣ እያደናቀፈኝ
ሁለት ወር አለፈኝ!

ዛሬ ኮበለለ
ትላንትናን ቀድሞት፣ ባምባላይ ፈረሱ
ቀኔና ሌሊቴም፣ ሰልፍ እያፈረሱ
ይተራመሳሉ
ይርመሰመሳሉ

አርባም እድሜ ሆና
ያችን ለማሳጠር

ነፋስ በሰው ሲያድም፣ ከሞት ሲመሳጠር
ወዴትስ ይኬዳል
ሰው ከቀየው እንጂ፣ካለም ይሰደዳል?"
#ሰው_ነጻነት_ሲያጣ

ሰው ነጻነት ሲያጣ
ለመኖር ሲቸገር
በገዛ ሀገሩ ላይ
ይማጸናል ሀገር
“ፍታልኝ” አትበለኝ
ይሄን እንቆቅልህ
ከአንዷ ሀገር በስተቀር
ሌላ ምን አውቅልህ??
ተመጽዋች በመምሰል
ሞኛሞኝ.ገራገር.
“ስጠኝ እኮ አልከኝ
እንደቀላል ነገር
ኩነኔም አልገባ
ክፉም አልናገር
“እግዜሩ ይስጥልኝ!"
ከማለትም በስተቀር
ለእግዜሩም አልሰጠው
ቢጠይቀኝ ሀገር

🔘በፋሲል🔘
#ሰው_መሆን_ምንድን_ነው???

..እናልሽ ቆንጅቴ
የሆነ ዕለት ማታ
ገና አይኗ ያልበራ - የውሻ ቡችላ
ከእናቷ ተነጥቃ - መንገድ ዳር ተጥላ፣
ያውም በክረምቱ
ያውም በምሽቱ፣
እናቴን፣
ሙቀቴን፣
ህይወቴን እያለች
ቱቦ ስር ተኝታ - ታለቃቅሳለች፡፡
ምናልባት ሌሊቱን
ዝናብ ከዘነበ - ጎርፉ ይወስዳታል
ጎርፍ ካልወሰዳት
ራቱን ፍለጋ የወጣ ቀበሮ - ራት ያደርጋታል፡፡
ይህንን ስታይ - መኖር ይገርምሻል
ህይወት ግን ምንድን ነች?- ያፈላስፍሻል፡፡

ደግሞ በሌላ ቀን
አያቴ 'ሚሆኑ - እድሜ ጠገብ ባልቴት
በጠራራ ፀሐይ - ጥላ በሌለበት፣
ከአካላቸው ሚገዝፍ - የእንጨት ክምር አዝለው
ገዢ ይመኛሉ - ገንዘብ ተስፋ አድርገው፡፡
አንዲት ወጣት መጥታ - እየተቻኮለች
እንጨቱን ለመግዛት - ባልቴቷን ጠየቀች፤
“ስንት ነው?” ጠየቀች ወጣቷ
“ሃያ ብር” መለሱ አሮጊቷ፣
“ቀንሱልኝ ማዘር?”
“አስራ ስምንት አርጊው”
“አስራ አምስት ልውሰደው?”
“አላነሰም ልጄ?”
“ይህንም ማደርገው- ከምዞር ብዬ ነው!”
“በ...ይ እሽ ውሰጅው”::
ይታይሽ እንግዲህ
ሌሊቱን በሙሉ - የተጓዙበትን
መቼም ላይቃኑ - የጎበጡበትን፣
ከአራዊት ጋር ታግለው - ያመጡትን እንጨት
በአንድ ቢራ ዋጋ - አስራ አምስት ብር ሽጡት፡፡
አስራ አምስት ብር ብቻ!!!

አየሽ ያቺ ወጣት የ'ሷ ድካም እንጅ የባልቴቷ ኑሮ
አላስጨነቃትም
የምታወጣቸው አምስት ብሮች እንጅ - የአሮጊቷ ድካም
አላሳሰባትም፡፡
ይህንን ስታይ እንባ ያስወጣሻል
“መተዛዘን የታል?” ግራ ያጋባሻል፡፡

ትላንትና ደግሞ
በአንድ ቴሌቪዥን - ሰበር ዜና አይቼ
ሲያስታውከኝ አደርኩ - ከእንቅልፍ ተፋትቼ፤
ምን አየሁ መሰለሽ :-
አንድ የሰዎች ቡድን - ሰዎችን አግቶ
ሁሉንም በአንድ ላይ - ጠባብ ቤት ውስጥ ዘግቶ፣
እንደ በቆሎ እሸት - እያንከባለለ
ከነህይወታቸው - በእሳት አቃጠለ፡፡
በስመ አ..........ብ!!!
ይህንን ስታይ ህይወት ያስጠላሻል
የሰው ልጅ ምንድን ነው?' ያወዛግብሻል::

ታዲያ ግን አለሜ፤
ስንቱን ጉድ አይቼ፣
ስንቱን ጉድ ሰምቼ፣
በብዙ ቆስዬ፣
በብዙ ነድጄ፣
ነድጄ
ነድጄ........
አንቺን እንዳገኘሁ
ያስከፋኝን ሁሉ በአንዴ ረሳውና-
«ይህች ዓለም ጣፋጭ ነች - ቆንጆ ነች!› እላለሁ፡፡
እውነቴን ነው ምልሽ
አንቺን እንዳገኘሁ፡-
ባገባኋትና - አይኔን በአይኔ አይቼ
እስከፍፃሜየ - በኖርኩ ተደስቼ!
እያልኩ አመኛለሁ፡፡

ታዲያ ይህ ምኞቴ - ለኔም ይገርመኛል
'ሰው መሆን ምንድን ነው?” - ውስጤ ይጠይቀኛል፡፡

ምስኪኗን ቡችላ - በቆፈኑ ክረምት - ቱቦ ስር የጣሏት
ደካማዋን ባልቴት - ከእንጨት አሳንስው - ጣል ጣል ያረጓት፣
ስውን ሚያህል ፍጡር- ከነህይወታቸው - በእሳት ያጋዩዋቸው
እውነት ሰዎች ናቸው?

እኔ ራሴስ ብሆን?
ይህን ሁሉ ህመም - እያየሁ ያስቻለኝ
በምችለው መጠን - ርዳታ ፈላጊን - መርዳት የተሳነኝ
ጭራሽ ከአንቺ ጋራ - ሁሉን ረስቼ - መቦረቅ የሚያምረኝ
እውን እኔ ሰው ነኝ ??

ልጠይቅሽ እስኪ፡-

የምስኪኗን ጩኸት፣
የባልቴቷን ብሶት፣
የንፁሃንን ሞት፣
የሰውን ልጅ እክል፣
የምድርን ምስቅልቅል፣
አንቺ ካስረሳሺኝ
ጠቀምሽኝ?
ጎዳሽኝ?
ገደልሽኝ?
አዳንሽኝ?
መልስ እፈልጋለሁ
ሰው መሆን ምንድን ነው???

🔘መሉቀን ሰለሞን🔘
#ሰው_አፈር

አዕዋፍ በሰማይ ላይ ሲበሩ
በማራኪ ዜማቸው ሲዘምሩ፤
ውብ ተፈጥሯቸው ይደንቀኛል
እኔም ወፍ በሆንኩ ያሰኘኛል፡፡

እንስሳትም በየፊናቸው
ተመሳስለው ከአካባቢያቸው ፤
በጎጡ በስርጓጉጡ
ሲሽሎከሎኩ ሲሮጡ፤
ውብ ተፈጥሯቸው ይስበኛል
ፈጣሪ ስራው ይደንቀኛል፡፡

አንዱ ከዛፍዛፍ ሲዘል - ሌላው በመሬት ሲንፏቀቅ
አንዱ በሰማይ ሲበር - ሌላው ውሐ ውስጥ ሲሞላቀቅ፤
አንዱ ጮማውን ሲቆርጥ
ሌላው ደግሞ ሳሩን ሲግጥ፤
ልዩነታቸውን መመልከት - ሲሽቀዳደሙ ማየት
አቻ የሌለው ቲያትር - ተፈጥሯዊ ድንቅ ተውኔት።

ታዲያ
ከዚህ ሁሉ ውብ ተፈጥሮ - ከዚህ ሁሉ ትዕይንት
ለተመልካች የሚደንቀው - የሚገርመው አስቂኝ ትርዒት
አፈር -አፈርን ሲንቅ
አፈር - ከአፈር ሲተናነቅ፣
አፈር - በአፈር ላይ ሲያሴር
አፈር - ለአፈር ሲቆፍር..
..እንደ አፈር ቁጭ ብሎ ማየት።

🔘?🔘
#ሰው_እና_ዘመን

የሰው ልጅ እንደ ዘመን ነው
ዕድሜውን የሚያሳልፈው፡፡

አንዴ በጋ - አንዴ ክረምት
አንዴ ብርዳም - አንዴ ሙቀት፡፡

አንዳንዴ አይኑ ይረጥባል
አንዳንዴ- ጥርሱ ያብባል፤
አንዳንዱ- ወዙ ይረግፋል
አንዳንዴ- ፊቱ ይፈካል፡፡

የትም ይሁን
ማንም ይሁን
የሰው ልጅ እንደ ዘመን ነው - ባንድ ባህሪ የማይዘልቅ
እንባና ሳቅ የሚያጅቡት - ባህሪው የሚፈራረቅ፡፡

🔘ሙሉቀን🔘
👍1
#ሰው
ምን የአለት ግግር
የፀና ቢመስል
ምን የብረት ክምር
ጠንካራ ቢመስል
መሰረቱ ያው ነው
ስስ የህዋስ ንጥር፡፡

እሱም እንባ አለው
እንደ ጅረት ሚፈስ
እሱም ሀዘን አለው
እንደ ድንጋይ ሚከብድ
እሱም ስቃይ አለው
እንደ ምንጭ የሚፈልቅ
እንደ ዝናብ ሚወርድ፡፡

ያ ግዙፍ ማንነት
ከህይወት ራሷ ይገዝፍ የሚመስለው
እሱም እንባ አለው
እሱም ሀዘን አለው
ምን ኑሮ ባፀደይ
ምን ህይወት ቢሞላ
ለሀዘን የሚሆን ክፍተት እንዳይጠፋ፡፡

🔘መንግስቱ በስር🔘
👍4😱31
#ሰው (አጭር ልቦለድ)


#በበእውቀቱ_ስዩም

ጢም ማቀምቀም በጀመርኩበት ዘመን በከተማችን አንድ ተአምረኛ ባህታዊ ብቅ አለ፤ 'ጥቁር ኢየሱስ ብለው ሊጠሩት የደፈሩ ሰዎች ሁሉ ነበሩ ፤ ባህታዊው እውር ያበራል፤ ጎባጣ ያቀናል፤ ባንድ ጊዜ የከተማው ሆስፒታሎች ሁሉ ባዶ ሆኑ፤ የሆነ ጊዜ ላይ እንዲያውም ሙት ማስነሳት ሁሉ ጀምሮ ነበር፤ የከተማችን አስተዳዳሪ ግን “ ለተነሺዎች ማቋቋሚያ የሚሆን በጀት የለንም ብሎ ከለከለው፤

ባህታዊው ባንድ ወቅት ከተማውን አቋርጦ ሲያልፍ ወልደ ሰንበት ከተባለ የከተማው ነዋሪ ጋራ ተገናኘ፤ ወልደ ሰንበት በራዛ ዘመቻ ጊዜ ፈንጅ ብልቱን ቆርጦበታል፤ በጥሮታ ከተገለለ በሁዋላ ‘መራባት የተሳናቸው ወንዶች ማህበር’ ፕሬዚዳንት ሆኖ ያገልግላል፤

ወልደሰንበት ባህታዊውን ሲያየው “ አባት ሆይ፥ አገሬን አገሬን ብየ ስዋትት ዘሬን ሳልተካ ላልፍ ነው፤ ፈውሰኝ “ ሲል እግሩ ላይ ወድቆ ተማጠነው።

ባህታዊው ወደ ሰማይ አንጋጦ ትንሽ ከጸልዩ ሲያበቃ ወልሰንበትን አስወልቆ ጉያውን ዳበስ አደረገው ፥ መቸም አታምኑኝም ፤ ግን ሀቅ ከከመመስከር አልታገድም፤ የሰውየው ጉምድ ብልት ወዲያውኑ አቆጠቆጠ። ተአምረኛውን ሰውየ ያጀቡ ወንዶች አፋቸውን በጋቢያቸውና በኮሌታቸው ጫኑ !የሴቶች እልልታማ ፤እስከመተማ ፤ ተሰማ፥

ባህታዊው ይህንን ተአምራዊ የብልት- ተከላ ፈጽሞ ትንሽ አለፍ እንዳለ ወልደ ሰንበት እያለከለከ ደረሰበትና እግሩ ስር ተደፋ፤

“ አሁን ደግሞ ምን ፈለግህ?” አለው ባህታዊ፥ በታከተ ሰው ድምጽ ፥
ወልዴ እንዲህ ሲል መለሰ፥

“አባት ሆይ ! በነካ እጅህ ትንሽ ተለቅ ልታረግልኝ ትችላለህ?”🙄
😁29👍18
#ሰው_ሁን_በይኝ

በቀደም ለት ጉንጬ መሐል
በከንፈሯ ብትዳብሰኝ፣
ሙት አካሌ ፊት እንዳለኝ አስታወሰኝ፣

ደሞ ድንገት ቀልድ ነግራኝ
ስቄ ስቄ እንዳባራሁ ፤
"ጥርስህ ሲያምር" ስላለችኝ
ዘላለሜን ማልቀስ ፈራሁ ፤

ተካተትኩኝ ከተፈጥሮ
እፍ ...አልሸብኝ ድብቅ ውበት፤
እስቲ ባክሽ አሁን ደሞ
'ሰው ሁን ብለሽ ሹሚኝና
ሰው መሆኔን ልመንበት ፤

ሰው ተብዬ ልጠራበት።

🔘አስታወሰኝ ረጋሳ🔘
👍44🥰5🔥43👏1