አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
“አይደለም ! በጭራሽ አይደለም ! ሳይንሱ እውነታውን ጋርዶብናል፡፡ እንጀራን ማን ህሊና ውስጥ ቦታ ሰጠው ? 'የምድር ፍሬ፣ የወንዝ ውሃ ይሙላህ የተባለን ሆድ ማነው የሰው መሰረት
ያደረገው? የለም! በየጫካው በየዱሩ ርቃናቸውን የሚኖሩ ወገኖቻችን ርቃናቸው ጌጣቸው ነው፤ ቤትስ ቢሆን - የሰው ልጅ ተንኮሉን ሊከልል፣ ማካፈሉን ሊጋርድ ግድግዳ አቆመና ስስታም
እንዳይባል 'ቤት መሰረታዊ ፍላጎት ነው አለ ለግርዶሹ ስም አወጣ፡፡ ልጆች ልብ በሉ…የሰው መሰረታዊ ፍላጎት አንድ ነው፣ እሱም ፍቅር ነው:: ካለፍቅር ሰው የቁም ሙት ነው፡፡ ሰው ሰውን ሲያፈቅር፣ ሰው አምላኩን ሲያፈቅር፣ ሰው አገሩን ሲያፈቅር፣ ሰው እውነትን ሲያፈቅር፣ሰው ነፃነትን ሲያፈቅር ነው ህያው የሚሆነው:: ሰው ነገውን ሲወድ፣ ነገውን ሲያፈቅር ነው ነገ ለሚፈጠር ትውልድ ፍቅር የሚያወርሰው እስትንፋሱ የሚቀጥለው:፡ በሉ መልሱልኝ፣
“በዛብህ እንጀራ አጣ?” ይጠይቁናል፡፡
“አላጣም!” በአንድ ላይ እንመልሳለን፡፡
“ልብስ እጣ?”
“አላጣም”
“ቤትስ”
“አላጣም"
“አያችሁ! ፍቅርን ብሎ፣ ፍቅርን ተርቦ፣ ፍቅርን ተራቁቶ ሲንከራተት ኣባይ በረሃ የሽፍታ ሲሳይ ሆኖ ቀረ” እዝን ብለው በመስኮት ወደ ውጭ እየተመለከቱ ከቆዩ በኋላ፣ “ፍቅር ነው የሰው መሐሉ” ይሉና ሁላችንንም ያዩናል.

መምህር በለጠ ይሄው ሞቱ ! እጅጋየሁ እንዳለችው በሚስታቸው ብስጭት ሞተው ከሆነ የሰበኩትን ፍቅር አጥተው ሞቱ !!

ሃና የክፍላችን ጎበዝ ተማሪ ታዲያ ያሏትን ለቀም አደረገችና የአካባቢ ሳይንስ ፈትና ላይ የሰው
መሰረታዊ ፍላጎት 'ፍቅር' ነው ብላ በመመለሷ ኤክስ' ገባባት፡፡

ቲቸር በለጠ ይሄን ሰምተው ሳቅ አሉ፤ ከዛም ረጋ ብለው መከሩን፣

“ልጆች! በሉ የተባልነውን ስንላችሁ ብቻ ነው ትምህርት ተማራችሁ የሚባለው፡፡ የነፍስ ሃቅ ትምህርት መስሏችሁ ተቀብላችሁ አትሩጡ! ነፍስ ያመነው እና ወረቀት የሚያምነው የተለያየ ነው፡፡ ይሄን አትርሱ፡፡ የነፍስን እምነት የሚሸከም ትከሻ ያለው ወረቀት እምብዛም ነው፡፡ ስንቱ ነብሱ ሹክ ያለውን ለወረቀት ሹክ ብሎ እንጦሮጦስ ወርዷል !!” ብለው በዝምታ ከዳር እስከ ዳር የተኮለኮልነውን ተማሪዎች ይቃኙንና ድንገት፣

“ሃና !” ብለው ይጣራሉ፣
“አቤት ቲቸር!”
“..አስተማሪሽ ነፍስሽን ማረም አትችልም፣ ለዛ ነው ኤክስ' የገባብሽ” ካሉ በኋላ የሃናን አማርኛ ደብተር ወስደው በቀይ እስክርቢቶ ፈረሙበት፡፡ “አማርኛ ፈተና ላይ ሁለት ነጥብ ጉርሻ
ሰጥቼሻለሁ፡፡” የሃና ነፍስ ታረመ !! (ሃኒን ከብዙ ዓመት በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ በጦርነት ስለሚጎዱ ህፃናትና እናቶች የምርምር ወረቀት አቅርባ በቴሌቪዥን አየኋት፡፡
ያቀረበችውን ወረቀት አፈላልጌ አነበብኩት፡፡ እውነትም ሃኒ ነፍሷ ታርሟል፡፡)

መምህር በለጠ…ትረካቸውን ቀጥለው እንደፈዘዝን…ድንገት፣

“አንተ እሳት ትውልድ ዝሙትና ፍቅር የየቅል ነው:: ሰብለ ዝሙት ብትሻ እንደ ውሻ እግሯን
የሚከተል መኳንንት ነበረላት፡፡ ልብ በሉ ትዳር አያስጨፍርም:: 'ብቻዬን ከመውደቅ ሁለት ሆኜ ልውደቅ' የሚሉም ጅሎች ናቸው ፤ አብሮ መሆን እና አንድ መሆን የየቅል ነው፡፡ ትዳር አንድ መሆን ነው !! በጥቅም በሰከረ ትዳርና በፍቅር በሰከረች ሰብለ መሐል አንድ የሰከረ እርምጃ ሲቀር ፍቅር በመሐል ገባ፡፡

በላይ ዘለቀ ከነተከታዮቹ ቤልጅግ ይዞ የናኘበትን ጫካ ሰብለ ፍቅር ታጥቃ ብቻዋን ዘመተችበት፡፡ በላይም ለአገሩ ፍቅር፣ ሰብለም ለበዛብህ ፍቅር አያችሁ ... የአባይን በረሃ የሚያሻግር ድልድይ ምንድን ነው ፍቅር ! ያልተበረዘ ያልተከለለ ሃቅን ወደ ትውልድ ማስተላለፊያው መንገድ ምንድን ነው ? ፍቅር! ሰብለ አንበሳና ነብሩን ፊት ለፊት ተጋፈጠች ..."

“መስፍን"
"አቤት ቲቸር?"
አንተ ዱርዬ ፓስቲ ቤት ለፓስቲ ቤት ልጃገረድ ይዞ መዞር ፍቅር አይደለም. የከፍሉ ልጅ
በሳቅ ያውካካል፡፡ መስፍን ሁልጊዜም ከሴቶች ጋር ሻይ ቤት መታየቱ የታወቀ ነው፡፡

"አበባ!"

"አቤት!"

(ወደ አበባ በመጸሐፉ እየጠቆሙ) "ከማንም ጎረምሳ ጋር ሲገቡና ሲወጡ መላፋትና መጓተት
ፍቅር አይደለም፡፡ ፍቅር ራስን ያስከፍላል፡፡ ፍቅር ብታገኘውም ያስከፍልሃል፣ ብታጣውም
ያስከፍላል .. ክፍያው የየቅል ቢሆንም !!

መምህር በለጠ በአማርኛ ክፍለ ጊዜ የፍቅር ሰዋሰው የሚያስተምሩ፣ የነፍሳችን ስንኝ ከፍቅር ስንኝ ጋር ቤት እንዲመታ የገለፁን መምህር ይሄው እንደተባለው ከሆነ ፍቅር ተርበው' ሞቱ !

እሳት ትውልድ ንቃ፣ ዘመኑ የእነ ቄስ ሞገሴ ዘመን ነው:: ተመሳስሎ፣ ተለጥፎ የመኖር
ዘመንና። ሆድን አናት ላይ አስቀምጦ እዩኝ ማለት፡፡ ፊት ለፊት ለምን?” ከማለት ፊት እያዩ፣
ፊትን የመምሰል እስስትነት አዋቂ የሚያስብልበት ዘመን ነው:: እባብነት ዝና የሆነበት፡፡ እነጉዱ
ካሳን የማውገዘ ዘመን..” ይላሉ ሲናገሩ አንዳንድ ከተረከዛቸው ብጅግ ብለዉት በጥፍራቸው
እየቆሙ መፅሐፉን በአመልካች ጣታቸው እልባትነት ከፍለው ይዘው ከፍ ዝቅ እያደረጉ ስለሆነ፣
የሙዚቃ ኦርኬስትራ መሪ ይመስሉ ነበር፡፡

ሞቱ መምህሩ !

አንድ ቀን አበበ በሶ በላ ብለው ፃፉና፣ " አበበ አንተ ነህ፣ አበበ እኔ ነኝ፣ ከበበ በዛብህ ... አበበ
ሰብለ ናት፡፡ አበባ ጉዱ ካሳ፣ አበበ ቄስ ሞገሴ፣ አበበ ፊታውራሪ መሸሻ .. አበበ ወዛደሩ፣
አበበ ምሁሩ፡፡ እነጋገራቸው ስብከት ይመስል ነበር፡፡

... አበበ ሰብለ ስትሆን፣ በሶው .. የታሰርክበትን የባህል ሰንሰለት በፍቅር ቢላዋ መበጣጠስ
የጥቅም ጣኦትህን አሽቀንጥረህ የፍቅር ፅላትህን ማንገስ ነው፡፡ አበበ በዛብህ ቢሆን፡ በሶው መርገምትና ማስፈራሪያን የናቀ ፍቅር ነው፡፡ ሌሎች በራሳቸው ደስታ የጫኑብህን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስእለት ማሽቀንጠር ነው::ላልተሳልከው ስእለት ህይወትህን አለመስጠት አበበ ፊታውራሪ መሸሻ ሲሆን በሶው ቅራሪ ርዝራዥ የዘር ማንዘር ክብር ነው... በዘር መኮፈስ .. ትዕቢት፡፡ አበበ ጉዱ ካሳ ሲሆን፣ በሶው በጨለመ ዘመን በእብደት ደመና የተሸፈነ መብረቃዊ መግለጥ ነው…” እሉና ኮስተር ብለው ቃኙን፡፡

ይሄው 'ቲቸር በሰጠ፥ ሞቱ !

የቲቸር በለጠን አስክሬን ከተሸከሙት ሰዎች መካከል እንዱ እኔ ነበርኩ፡፡ ከፊቴ መስፍን አለ፤
አስክሬኑ ከበደኝ፡፡ የተሽከምኩት የመምህሬን ኮስማና አካል መሆኑን እስክጠራጠር አስክሬኑ
ከበደኝ.. !!

ከአብረቅራቂ ልብስ ተሸፍኖ በእሳት ትውልድ ታጅቦ ወደ መቃብር የሚጣደፈው አስከሬን ጋር..ሰብለ …በዛብህ ..ጉዱ ካሳ … ፊታውራሪ መሸሻ የኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ ..ታላላቆቹ የጥበብ
ሰዎች ..ፍቅር ራሱ አብረው ወደ መቃብር እየተወሰዱ መሰለኝ፡ ካለነገሩ አልከበደኝም ይሄ
አስክሬን !! እህሳ ....ማን ተረፈ፣ እና ቄስ ሞገሴ አልቃሽ ሆነው፣ ቀብር ቆፋሪ ሆነው፣ አጃቢ
ሆነው ምድርን ሞልተው

አበበ መምህር በለጠ ሲሆን፣ በሰው ነፍሱ የታረመ ትውልድ ነበር!!

ይሄን ያለ ግን አልነበረም፡፡ ሁሉም ሰው የሚያወራው ስለሚስታቸው አቃጣይነት ብቻ ነበር፤ ከሟቹ ይልቅ የሞቱ ምክንያት መግነኑ የሞተን ሰው ሥራ ህያው ከማድረግ ይልቅ የቋሚን መቆም
በምክንያት መዝለፍ ስለሚቀል ይሄንኑ ተራ መንገድ የመከተል አምልኮ መሰለኝ፡፡

አለቀ
👍341
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰባት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

...ወጥመድ ውስጥ የገባ አይጥ ማምለጫ አጥቶ ይቅበዘበዛል፡፡ ከድመት ጥፍር ውስጥ የገባ ፍጡር ግን ይበልጥ ይጨነቃል፡፡

ማዳምና ሚስተር ቴናድዬ ምን ዓይነት ሰዎች ይሆኑ?

ምድባቸው እውቀት ኖሯቸው ግን ጊዜ ከጣላቸው ሳይሆን የተናቁ
ሆነው ጊዜ ካነሳቸው ሰዎች ውስጥ ነበር፡፡ ጊዜ ያነሳቸው ሰዎች ጥፋት ቢፈጽሙ የሠርቶ አደሩ ትጋት ወይም የቡርዣው ክብር የተጐናጸፉ ባይሆነም ስህተታቸው ጊዜ ከጣላቸው ሰዎች ላይ ተደፍድፎ እነርሱ
ከጥፋቱ ነፃ ይሆናሉ፡፡

ይህም በመሆነ ባልና ሚስት መደባቸው ከተናቁ ሰዎች መካከል
ቢሆንም ጊዜ ስለሰጣቸው ብቻ እንደ ትልልቅ ሰዎች ይከበራሉ:: ሴትዮዋ ጨካኝ፣ ሰውዬው በዋል ፈሰስ ዓይነት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሁለቱም ትንሽ ቀዳዳ ካገኙ ተንኮል ከመሥራት አይቆጠቡም:: እንደ ትል ከብርሃን ወደ ጨለማ፤
እንደ አባያ በሬ ወደፊት ከመራመድ ወደኋላ ማፈግፈግ፤ እንደ እባብ ከቀና አስተሳሰብ ተንኮል ወደ መሽረብ፤ ከሰፊው ጠባብ መንገድን የሚመርጡ
ዓይነት ሰዎች ናቸው::

የሚገርመው ግን ክፋት፧ ተንኮልና ምቀኝነት ለኑሮ መሳካት ዋስትና
ሊሆን ስለማይችል እነዚህ ሰዎች በሆቴል ቤታቸው ብዙም አልተጠቀሙም።

ፋንቲንን ያመስግኑና ሳያስቡት በድንገት ሃምሣ ሰባት ፍራንክ
አግኝተዋል፡፡ ይህን ገንዘብ በማግኘታቸው ሆቴል ቤታቸው ከመታሸግ ዳነ፡፡ግን አሁንም ቢሆን በሚቀጥለው ወር ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልጋቸው ስለነበር ሴትዮዋ የኮዜትን ጋቢና ቀሚሶች ወደ ገበያ ወስዳ ስልሣ ፍራንክ
ሽጠቻቸው፡፡ ገንዘቡ ሲያልቅ ኮዜትን ለነፍሳችን ብለው ያስጠግዋት እንጂ ጥቅም እንዳገኙባት ረስተው በጣም ጨከኑባት፡፡ የራስዋ የሆኑ ልብሶች
ተሽጠው የተቦጫጨቁትን የልጆቻቸው ውራጅ ኣለበስዋት:: ለውሻ እንደሚሰጥም አጥንት ከበላተኛ የወዳደቀ ትርፍራፊ አበልዋት:: ምድብዋ በር
ላይ ተኝቶ ዓይን ዓይን ከሚያይ ውሻና ከተመጋቢ እግር ስር ድምፅ እያሰማ ከሚሄድ ድመት ጋር ሆነ፡፡ ምግብ እንደ ውሻና ድመት በገበቴ መሣይ ነገር መሬት ተጣለላት::

እናትዋ አገርዋ ከገባች በኋላ ከእዚህ ግባ የማይባል ሥራ አገኘች፡፡በየወሩ ደብዳቤ ለእነሚስተር ቴናድዬ ጻፈችላቸው:: በደብዳቤዋ ከልጅዋ
ደኅንነት በስተቀር ሌላ የምትጠይቀው ነገር አልነበራትም፡፡ ባልና ሚስት
የመልስ ደብዳቤ ሲልኩ ኮዜት ተመችቶአት እንደምትኖርና ጤናዋም ደህና መሆኑን ገልጸው ነበር የሚጽፉላት::

ኣንዳንድ ልቦች በአንድ ጎናቸው ጥላቻን ካላቀፉ ፍቅር ብቻውን
መንተራስ የማይችሉ አሉ፡፡ መዳም ቴናድዬ የራስዋን ልጆች በጣም
ትወዳለች:: የልጆችዋ ፍቅር አዲስዋን ልጅ እጅግ እንድትጠላ አደረጋት፡፡ኮዜት ያለ አግባብ ስትነቀፍ፤ ስትገረፍ፤ ስትሰደብ፧ ስትመናጨቅና ስትጠላ
እኩዮችዋ የሆነ ሌሎቹ ሁለት ልጆች ሲታቀፉ፤ እሽሩሩ ሲባሉ፤
የማይገባቸውን ምስጋና ሲያገኙ በማየትዋ ነገሩ ሊገባት አልቻለም:: የሰው ልጅ ጭካኔ፤ የዚህ ዓለም ውጣ ውረድ፤ የእግዚኣብሔር ሽረትና ምህረት
ምን እንደሆነ ለማወቅ እድሜዋ አልፈቀደላትም::

ሴትዮዋ ትጨክንባታለች:: ኢፓኒንና አዜልማም ይጨክኑባታል፡፡ምናልባት የጭካኔው መጠን ይለያይ ይሆናል እንጂ በዚያ እድሜ ልጆች
ቤተሰቦቻቸው የሚፈጽሙትን ነው የሚከተሉት፡፡

ዓመት አለፈ፤ ሌላውም ተደገመ::

የሰፈር ሰዎች ምን ብለው ያወሩ ጀመር፧ «እነመዳም ቴናድዬ ምን
ዓይነት ርህሩህና ደግ ቢሆኑ ነው እባካችሁ:: እነርሱ ለራሳቸው ምስኪኖች ሆነው መጠጊያ የሌላትንና እናትዋ የጣለቻትን ልጅ ያሳድጋሉ::»

የዜት እናት ልጅዋን የረሳች መሰላቸው::

ዓመት እስከ ዓመት ቁመትዋ እየጨመረ ሲሄድ መከራዋና
ስቃይዋም እንዲሁ ጨመረ::

ኮዜት ሕፃን ሆና ሳለ የሁለቱ ልጆች ጥፋት ማስተባበያ ነበረች::
እያደገች ስትሄድ ማለት አምስት ዓመት ሳይሞላት የቤቱ አሽከር ሆነች::

ኮዜት ትላላካለች ፤ ቤት ትጠርጋለች፤ ግቢ ታጸዳለች ፤ እቃ
ታጥባለች ፤ ከባድ ነገር ትሸከማለች:: እናትዋ በየወሩ የምትከፍለውን ገንዘብ ባጓደለች ቁጥር ልጅትዋ የምትሸከመው ሸክም እየከበደ ይሄዳል::
እናትዋ የጥቂት ወሮችን ክፍያ አልላከችም::

እናት ከሦስት ዓመት በኋላ ወደ ሞንትፌርሜ ከተማ ብትመለስና
ልጅዋን ብታያት አታውቃትም፡፡ ያኔ ጥላት ስትሄድ ድምቡሽቡሽ ብላ
ንከሱኝ፣ ግመጡኝ ትል የነበረችው ልጅ በቁራና መንምና አጥንትዋ .
ገጥጦ ፣ ፊትዋ ገርጥቶ ሌላ ልጅ መስላለች፡፡ «እደለ ቢስ፣ ገዳፋ» እያሉ ነው ባልና ሚስት የሚጠርዋት::

እድልዋ ዝምተኛ እንድትሆን ፧ ችግርዋ ፉንጋ እንድትመስል
አድርጓአታል። ዓይኖችዋ ቢጎደጉዱም ከቦታቸው አልጠፉም፣ ሲያይዋቸው
ያስፈራሉ፡፡ ስቃይ እንዳንገበገባቸው ያስታውቃሉ፡፡ ትላልቅ ስለነበሩ ያዘሉትም የስቃይ መጠን ትልቅ ነበር::

ዓይኖችዋ እንባ አቅርረው፣ በክረምት ቡትቶ ለብሳ አፈር ላይ
ስትተኛና በበጋ ደባደቦ ለብሳ በጠራራ ፀሐይ ከቁመትዋ የሚበልጥ መጥረጊያ ይዛ ደጃፍ ስትጥርግ ማየት ልብ ላለው የሚዘገንን ትርኢት ነበር፡፡ ሆኖም
ሰዎች «እድለቢስ... ገዳፉ... እበይ» እያሉ ነበር የሚጠርዋት::
ጠዋት ጠዋት እየተባችና እየፈራች ሰውነትዋ ተንቀጥቅጦ በቅጡ
ሳይነጋ ነበር የምትነሳው:: ከሰፈር የምታመጣው ነገር ካለ የሰፈር ሰው ሳይነሳ ትሄድና እስኪነሱ ትጠብቃለች፡፡ከገበያም የምትገዛው እቃ ካላ
ገበያተኞች እቃቸውን ሳያወጡ እርስዋ ቀድማ ትገኛለች::

ደጉ ሰው

የዚያች ምስኪን ልጅ እናት ምን ሆነች? ሞንትፐርሜ ውስጥ ይኖሩ
የነበሩ ሰዎች ልጅዋን ከድታ እንደጠፋች ሲናገሩ ሰምተናል:: የት ነው ያለችው? ምን እየሠራች ነው?
ኮዜትን ከነማዳም ቴናድዩ ቤት ትታ ከሄደች በኋላ ትውልድ አገርዋ
በደህና ደርሳለች:: ከአሁን በፊት እንደተጠቀሰው IIመነ 1818 ዓ.ም. ነበር፡፡ፋንቲን ወደ ትውልድ አገርዋ የተመለሰችው አገሩን ለቅቃ በወጣች በአሥራ
ሁለተኛ ዓመትዋ ነበር፡፡ አገሩ በጣም ተለዋውጦ ነው ያገኘችው:: የእርስዋ ኑሮ እያቆለቆለ ሲሄድ የትውልድ አገርዋ ከተማ በጣም እያደገና እየተሻሻለ ሄድዋል፡፡ በመጨረሻዎቹ ሁለት ዓመታት በተለይ ትልቅ መሻሻል ተገኝቶ
አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ተቋቁመዋል፡

በዚያ አገር ፋብሪካ ውስጥ ተመርተው የሚወጡ ዕቃዎች ዋጋ እጅግ የናረ ነበር፡፡ ነገር ግን ፋንቲን ወደ አገርዋ ስትመለስ ያ ሁናቴ ተለውጦ ነው የደረሰችው:: አንድ ያልታወቀ ሰው በ1815 ዓ.ም. መጨረሻ ገደማ
መጥቶ አስደናቂ የሆነ የፈጠራ ሥራ በመሥራቱ የፋብሪካ ውጤቶች ዋጋ ዝቅ ይላል::

ሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሰውዬው ከመጠን በላይ ሀብታም
ይሆናል፡፡ ፋብሪካው ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሰዎች ደግሞ ጥሩ ደመወዝ ስለተከፈላቸው እነሱም የተሻሻለ ኑሮ መኖር ቻሉ፡፡ ሰውዬው ማን እንደሆነና
ከየት እንደመጣ ግን ማንም አያውቅም:: ወደ ከተማው ሲመጣ ምንም ገንዘብ ይዞ እንዳልመጣ ሁሉም የሚያውቀው ፥ነው:: ግን እርሱ በወጠነው
የፈጠራ አሳብ እርሱ ብቻ ሳይሆን አገሩ ሁሉ ከበረበት:: ወደዚያ ሲመጣ አለባበሱም ሆነ አነጋገሩ የጭቁን ሰው ነበር፡፡ በታኅሣሥ ወር ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ወደ ከተማው ሲገባ የለበሰው ልብስ የተቦጫጨቀ እግሩና እጁ
👍171
በሥራ ብዛት የሻከረ ሲሆን በአንድ እጁ ምርኩዝ መሳይ ነገር ይዞ፧ በሌላ እጁ በጨርቅ የተጠቀለለ ነገር አንጠልጥሎ ነበር፡፡ በእለቱ እርሱ ወደ ከተማው ሲገባ ሰፈር ውስጥ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ስለነበር ሰውዬው በቀጥታ ወደ እሳት ቃጠሎው ይሄዳል፡፡ ልክ እርሱ ሲደርስ ሁለት ትንንሽ
ልጆች በእሳቱ ተከብበው ያያል፡፡ ክልሉ ገብቶ ይዞአቸው ይወጣል፡፡ ልጆቹ የባለሥልጣን ልጆች ነበሩ፡፡ በዚያ ግርግር የከተማው ሹሞች የመታወቂያ ወረቀት ሳይጠይቁት ከሕዝብ ጋር አብሮ ይቀላቀላል፡፡ እንኳን የመታወቂያ ወረቀት ሊጠየቅ ስለፈጸመው በጎ ተግባር ሰው ሁሉ ከብቦ ያመሰግነዋል፡፡
ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ሰው «አባባ ደጉ ማንደላይን» እያለ ጠራው::

ዕድሜው በግምት ሃምሳ ይሆናል:: አሳብ ስለሚያጠቃው ዘወትር ትክዝ ከማለቱ በስተቀር ስለዚህ ሰው ከዚህ ይበልጥ በአሁኑ ሰዓት ማውራት
አይቻልም፡፡ ብቻ እርሱ በፈጠረው ጥበብ ሳቢያ በብዛት ተሠርቶ ለሚወጣው የፋብሪካ ውጤት ምስጋና ይግባውና የብዙ ሰው ሕይወት ተሻሻለ፡፡ ከተማዋ
የነጋዴዎች መናኸሪያ ሆነች:: እቃው ከአገር ውጭ ወደ እስፓኝ በብዛት ተወሰደ:: የእቃው ዓይነት እንግሊዝና ጀርመን አገር ተመርተው ከሚወጡት
ተመሳሳይነት ካላቸው እቃዎች የተሻለ ሆኖ በመገኘቱ ተወዳጅነትን አተረፈ፡፡
ስለዚህ ገበያው ደራ! የሚገኘውም ጥቅም እጅግ ብዙ ስለሆነ አባባ ማንደላደን
በሁለተኛው ዓመት ሌላ መጠነኛ ፋብሪካ ከፈተ:: ፋብሪካው ውስጥ አንደኛው ክፍል ውስጥ ሴቶች ብቻ የተሰማሩበት ነበር፡፡ ከእዚያ ከተማ ስራ ያጣ ሁሉ ከእነዚህ ሁለት ፋብሪካዎች ውስጥ በደህና ደመወዝ ሥራ በቀላሉ ማግኘት ቻለ፡፡ አባባ ማንደላይን ከመምጣቱ በፊት ብዙ ሰው ሥራ
ስላልነበረው ከተማይቱ ውስጥ ብዙም እንቅስቃሴ አልነበረም:: አሁን ግን ሁሉም በየፊናው መፍጨርጨሪያ መንገድ ስለተከፈተለት ከተማው
ተንቀሳቀሰ፡፡ የኢኮኖሚ መንቀሳቀስ የተፈለገው ነገር ሁሉ የትም አስገኘ፡፡ሥራ መፍታትና ችግር ከከተማው ተወገዱ፡፡ እያንዳንዱ ነዋሪ መጠነኛ
የሆነ ገቢ ስለኣገኘ ሁለም እንደአቅሙ፣ በደረጃው ደስ ብሎት ይኖር ጀመር፡፡

ነገር ግን አባባ ማንደላይን ለሁሉም ሥራ ቢያስገኝም ሥራ ለሰጠው ሁሉ «ታማኝና እውነተኛ ሰው መሆን አለባችሁ» እያለ ያስጠነቅቅ ነበር።

ተደጋግሞ እንደተገለጸው በዚህ አጋጣሚ የአባባ ማንደላይን ሀብት ተትረፈረፈ፡፡ የሚገርመው ግን ይህ ሰው ለሀብት ይህን ያህል ደንታ አልነበረውም፡፡ ከሀብቱ ይልቅ ስለሌሎች ሰዎች ደኅንነት እጅግ ያስባል፤ ይጨነቃል፡፡ ስለራሉ ግን ብዙም ግድ አልነበረውም፡፡ በ1920 ዓ.ም. ባንኪ ውስጥ ስድስት መቶ ሰላሣ ሺህ ፍራንክ ነበረው:: በዚያው ዓመት ደግሞ
ለከተማው እድገትና ለተቸገረ ድሃ ያወጣው ገንዘብ ወደ አንድ ሚሊዮን ፍራንክ ገደማ ነበር፡፡

ከተማው ውስጥ የነበረው ሆስፒታል የተሟላ ክፍልና አልጋ
ስላልነበረው የሕሙማን ማስተኛ አሥር ተጨማሪ አልጋዎች እንዲገዙ አደረገ፡፡ ከተማው የላይኛውና የታችኛው ተብሎ ከሁለት የተከፈለ ሲሆን
እርሱ ይኖርበት የነበረው የታችኛው ከተማ ብዙ የጎደለው ነገር ነበር::አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ነበር ያለው፡፡ እርሱም ቢሆን ሊፈርስ ምንም ያህል አልቀረው:: ስለዚህ ሁለት አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን አሠራ አንደኛው ትምህርት ቤት ለሴቶች ሌላው ለወንዶች ተመደበ፡፡ ከግሉ ወጪ
አራት አዳዲስ አስተማሪዎችን ቀጥሮ መንግሥት ከሚከፍለው የአስተማሪ ደመወዝ እጥፍ ከፈላቸው፡፡ ይህን ያየ ጎረቤቱ ስለሠራው ሥራ አድንቆ ሲናገር «ነርስና እስተማሪ እኮ ምርጥ የአገር ገንቢዎች ናቸው» አለ ይባላል።ፈረንሣይ አገር እጅግ የታወቀ ጠዋሪና ደጋፊ ለሌላቸው የሚሆን ትልቅ ቤትም እሠራ:: ፋብሪካው መሃል ከተማ ውስጥ ስለነበር በፋብሪካው ጭስ
ሰበብ የሰፈሩ ነዋሪዎች ስለተጎዱ በነፃ መድኃኒት የሚወስዱበት የመድኃኒት ቤት ከፈተላቸው::

በ1817 ዓ.ም. ይህ ሰው የሠራው በጎ ምግባር በመላ ፈረንሣይ
በመሰማቱ በዚያን ጊዜ የነበረው ንጉሥ አባባ ማንደላይንን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሊሾመው ነው ተብሎ ተወራ፡፡ ወሬው አሉባልታ ሆኖ አልቀረም፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ የአባባ ማንደላይን መሾም በጋዜጣ ታትሞ ወጣ፡፡ አባባ ማንደላይን ግን ሹመቱን የማይበቀለው መሆኑን አስታወቀ፡፡

ወደ ከተማው በገባ በአምስተኛው ዓመት ማለት በ1820 ዓ.ም. ደጉ
ሰው ለሕዝብ ጥቅም ብሎ ያሠራው ነገር እጅግ በጣም የገነነ በመሆኑ የከተማው ነዋሪ ሁሉ እርሱ የከተማው ከንቲባ እንዲሆን ጥቆማው አስተጋባ፡፡ ንጉሡ እንደገና ሾሙት፡፡ አሁንም ሹመቱን አልቀበልም አለ፡፡ ግን የከተማው
ፖሊስ አዛዥ ‹ሹመቱን እንዲቀበል በግድ መታዘዝ አለበት» ሲል አስታወቀ፡፡ የከተማው ታላላቅ መኳንንትም ከቤቱ ድረስ ተሰብስበው መጥተው ሹመቱን
መቀበል አለብህ» አሉት:: የወዝ አደሮችም እሳብ ከዚህ የተለየ አልነበረም።ሰው ሁሉ ሹመቱን እንዲቀበል ስለወተወተው በመጨረሻ እሺ ብሉ የከተማው ሹም ሆነ፡፡

ሰው ሁሉ ሹመቱን እንዲቀበል የገፋፋው አንዲት የኑሮ ደረጃዋ
ዝቅተኛ የሆነ አሮጊት ከሰፈር ሰፈር እየዞረች በቁጣ «ጥሩ ከንቲባ ማግኘት እኮ ጥሩ ነገር ነው ! ደግ ሥራ የሚሠራ ሰው አይወድላችሁም?» እያለች
ሕዝቡን በመቀስቀስዋ ነበር፡፡ ብዙ ሕዝብ ካልበዛበት ከተማ ወሬ ስለማይደበቅ ይህች ሴት የምትለው ነገር በአጭር ጊዜ ከተማው ውስጥ ተሰራጨ፡፡ ጊዜ
እያለፈ ሲሄድ ግን ቁጥሩ አነስተኛ ቢሆንም የሚቃወም አልጠፋም፡፡
መቼም የሕይወት እውነታ ነው፤ በራሳቸው ጥረትና ችሎታ ወይም
በሌሎች ደግነት ሥልጣን ላይ የወጡ ሰዎች ተቃዋሚ አያጡም:: መሴይ ማንደላይንም ቢሆን ከዚህ ሊርቅ አይችልም:: ግን ተቃውሞው ብዙ ጊዜ
አልቆየም። እንዲያውም የሚገርመው ከተሾመ በኋላ በሕዝቡ ዘንድ ያለው አድናቆትና አክብሮት እየጨመረ ሄደ፡፡ የተጣላን ያስታርቃል፤ የታመመን
ይጠይቃል፤ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውን ይቀብራል፡፡ ሰውም በራሱ ፈቃድ ዳኛ አደረገው:: የዓለም ሕግ ልቡ ላይ የተጻፈ ይመስል የሚሰጠው ፍርድ የተወላገደ፤ የሚሰጠው ምክር የተጣመመ አልነበረም:: የነገርን ፊት ለፊት እንጂ ወደኋላ አያውቅም፡፡ በዚህም የተነሣ ከስድስትና ሰባት ዓመት
በኋላ ስሙ በነበረበት ክፍለ ሀገር ብቻ ሳይሆን በመላ ፈረንሣይ እጅግ ገነነ።

ነገር ግን በአንድ ሰው ብቻ ተጠምዶ ይያዛል፡፡ ይህ ሰው አባባ
ማንደላይን የሚያደርገውን ሁሉ ይቃወማል:: ሁልጊዜም ይጠራጠረዋል፡፡ስሜቱ ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነቱ ማንደላይንን አይቀበልም::ዘወትር መሴይ ማንደላይን በመንገድ ባለፈ ቁጥር ሰው ሁሉ በፍቅር ዓይን
ሲያየው ይህ ቀጠን ብሉ ከቁመቱ ዘለግ ያለና የወታደር ልብስ
የሚለብሰው ሰው በዓይነ ቁራኛ ይከተለዋል:: ከዓይኑ እስከተሰወረ ድረስ አተኩሮ ከመመልከትና መሴይ ማንደላይንን ከማጤን አይቆጠብም:: ግምባሩንም እየቋጠረ «ይሄ ሰው ማነው?» በእርግጥ ከአሁን በፊት .
አይቼዋለሁ? የት ነው የማውቀው? ሰው ሁሉ ያደንቀዋል? ይወደዋል!
እኔ ግን እጠራጠረዋለሁ» የሚል ይመስል አጠገቡ ሰው ሳይኖር ከንፈሩን ያነቃንቃል፡፡ መሴይ ማንደላይንን ባየ ቁጥር ከሃሳብ ጋር ሙግት መግጠሙን
ያስታውቅበታል፡፡.....

💫ይቀጥላል💫
👍25
#የኔ_ዓለሞ!
አብረሽኝ እያለሽ...
አገኝሽ ነበረ ፤ እግሬ እንደቋመጠ፤
ስትለዬኝ ግና...
አካሌ በሙሉ ፣ ክንፍ አቆጠቆጠ፤
ለምን?
መብረር እንደሳተ አክናፍ
አንቺ ሆነሽብኝ ፣ የጉዚዬ አጽናፍ
ተፈጥሮን አወቀ ፤ የተሰጠን አክናፍ። -
(እንደታወረ ወፍ)
እከንፍልሻለሁ፤
እነፍስልሻለሁ፤
የቱ ጋር ቆመሻል? ልምጣልሽ እላለሁ።
ክንፍ ክንፍንፍ
ነፋስን መሰንጠቅ ፤ በመሄድ መደምደም፤
ቀሪ መንገድ ሕልሜን ፣ካንቺ ለመካደም።
አላውቀውምና፣
አይገባኝምና ፣ያንቺ መዳረሻስ፣
እኔ ልብ የለኝም
አጠገብሽ ቆሜሞ ፣ አጠገብሽ ልሆን
እነሳለሁ ጭራሽ።
(ለየልኝ ማለት ነው።)
ማለትም...
ማለት የምችለው...
የክንፋም ልብ ወዳጅ ፣ ነፋስን ማርገብገብ፤
በነፋስ መንገብገብ፤
ነፋስን መጠርጠር፤ ነፋስን መመገብ፤
ከንፋስ መጓተት ፤ ከነፋስ መሳሳብ፤
እሷ ነች አያሉ፣ ከነፋስ መሣሣም፤
እነፍስልሻለሁ!
ባየር ፣በብርሃን ፣በጨለማ መብረር፤
አንቺ ጋር እንደቆምኩ ፣ ክንፊን አጥፍ ጀመር።
ደረስኩኝ ማለት ነው!

ማለትም
የክንፋሞ ቀልብ ጦስ ፣ መርግፊያ ሞኝነት፣
መሄጃ ሰበብ ጋር ፣ በቶሎ መገኘት።
ዓለሜ...
መጓዝ ዳራ ኖሮት ፣ካስረገፈ ላባ፣
ማማር መርገም ሆኖ ፣ካስነቀለ አበባ፣
መድረስ ከመገኘት ፣ ከእቅፍሽ ቢያሞቀኝ፣
መፈለግ ደስታዬ ፣ ሳገኝሽ ራቀኝ።
መሄዴን ብውደው...
በቆይልኝ ብዬ ፣ ክንፊ መቼ ደክሞት፣
እጸልይ ጀመረ
ስቀርብሽ ሂጂልኝ ፣ ሳገኝሽ እንዳልሞት።



🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍13👏4
#ምንዱባን


#ክፍል_ስምንት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

መሴይ ማንደላይንን ባየ ቁጥር ከሃሳብ ጋር ሙግት መግጠሙን
ያስታውቅበታል፡፡.

ሰውዬው ኮስተርተር የሚል ዓይነት ስለነበር እንኳን በዓይነቁራኛ
ተከትሎ ለአንድ አፍታ ቢያይም «ይሄ ሰውዬ ከኔ ነገር አለው?» የሚያሰኝ ዓይነት ፊትና አመለካከት ያለው፧ ሳይወዱ በግድ ጭንቀትን ከልብ ውስጥ በማሳደር የሕሊና መረበሽን አንጎል ውስጥ የሚፈጥር ዓይነት ሰው ነበር::
ስሙ ዣቬር ይባላል፡፡ ፖሊስ ነው:: ተራ ፖሊስ ሳይሆን የከተማው
ፖሊስ አዛዥ ነው:: መሴይ ማንደላይን ወደ ከተማው ሲመጣ ከዚያ አልነበረም::

አንዳንድ የፖሊስ መኮንኖች የተለየ መልክ አላቸው:: አንዳንዴ
ደማቸው ውስጥ ከእልቅናቸው ጋር የተቆራኘ ክፋት ለመኖሩ ገጽታቸው ላይ ይታያል፡፡ ዣቬር የዚህ ዓይነት ገጽታ ቢኖረውም በውስጡ ግን ክፋት የተቀበረበት ዓይነት ሰው ነበር ለማለት አያስደፍርም:: እስር ቤት ነው
የተወለደው:: እናቱ ደግሞ ጠንቋይ ነበሩ፡፡ አባቱ የወህኒ ቤት ሠራተኛ ስለነበሩ ሁልጊዜም ሕብረተሰቡ የእነርሱን ቤተሰብ ከማኅበራዊ ኑሮ ያገለላ
ይመስላቸው ስለነበር ዣቬር ቀቢጸ ተስፋ ያዉቃዋል፡፡ የሰውን ልጅ ከሁለት ከፍሎ ነው የማያየው:: አንደኛው ወገን ሕብረተሰብን የሚያጠቃ ሲሆን
ሌላው ወገን ከዚህ ጥቃት የሚከላከልለት ክፍል ነው:: ዣቬር በሥነ ሥርዓትና በቅንነት በጣም ያምናል:: ጎሳውን ግን ይጠላል፡፡ ፖሊስ ለመሆን ፈልጎ ነው የፖሊስ ኃይል አባል የሆነው:: በሥራው ምስጉን ፖሊስ መሆን
ስለተረጋገጠ በአርባ ዓመቱ ከፍተኛ የማዕረግ እድገት አግኝቶ የክፍል አዛዥ ሆነ፡፡ በወጣትነት ዘመኑ ደቡብ ክፍለ ሀገራት ውስጥ ከሚገኝ ወህኒ
ቤት እንዲሠራ ይመደባል፡፡
አፍንጫው እንደ ቀትር እባብ ቀጥ ያለ ሲሆን ሪዘን ከግራና ከቀኝ
በጣም ኣሳድጎት ጉንጮቹን ሸፍኖበታል:: ዣቬር ድንገት የሳቀ እንደሆነ ስስ ከንፈሮቹ ተገልጠው ጥርሶቹን ብቻ ሳይሆን የሚያሳዩት ድዶቹንም ጭምር ነው:: ግን ብዙ ጊዜ መኮሳተርን እንጂ ሳቅ አያውቅም:: ከአፍንጫው ግራና
ቀኝ የተሸበሸበ ሥጋ ኣለው:: ይህም ሲቆጣ የአደን ውሻን፣ ሲስቅ ደግሞ ነብርን ያስመስለዋል፡፡ ከዚህ በተረፈ ጭንቅላቱ፡ ትንሽ፣ አገጩ ሰፊ፧ ፀጉሩን ወደፊት እያበጠረው ግምባሩ እስከ ቅንድቡ በፀጉር የተሸፈነ፤ ጨገጎ ፊት ያለው ፤ ፊቱ፡ የሚ.ያርበደብድና የኮስታራ አለቃ ሰውነት ያለው ሰው ነው።

ይህ ሰው በሁለት ዓይነት አመለካከቶች የተወጠረ ነበር፡፡ በመሠረቱ፡ሀሳቦቹ ምንም ዓይነት ስህተት የሌለባቸው ቀላል አመለካከቶች ሲሆን ዣቬር ግን በጣም ስላጋነናቸው እንደ ከባድ ነገር ነበር የሚያያቸው::
እነርሱም ባለሥልጣንን ማክበርና ሕግ የሚፃረሩትን መጥላት ናቸው:: በእርሱ አመለካከት ሌብነት፣ ግድያና ማንኛውም ወንጀል መፈጸም ማለት
ሕግን መፃረር ማለት ነው:: በማንኛውም የሥራ መስክ የተሰማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ማለት ከአገር መሪ ጀምሮ እስከ ተራ ወታደርና ተላላኪ. ድረስ የእርሱን እምነት መቀበል እንዳለባቸው ያምናል፡፡ በእርሱ
አመለካከት ሕግ የሚጥሱትን ሁሉ ተከታትሎ ማጥፋትና ማስወገድ ተገቢ እርምጃ ነው:: ሕግ የሚጥሱትን ከመጠን በላይ ያጠላል:: ማንንም ሳይለይ
ሕግን ማስከበር ለእርሱ ትልቅ ቁም ነገር ነው::

«በአንድ በኩል» ይላል ዣቬር፤ የመንግሥት ባለሥልጣንን ማታለል አይቻልም፧ ሕግ አስከባሪ ዳኛ ደግሞ ፈጽሞ አይሳሳትም:: በሌላ በኩል ደግሞ» ይላል፤ «መዳኛ ከሌለው አዘቅት ውስጥ ከተዘፈቁ ክፉ ሰዎች በጎ
ተግባር አይጠበቅም፡፡»

«ሰው የሠራው ሕግ መጣስ የለበትም» ብለው የሚያምኑ የአንዳንድ ወግ አጥባቂዎችን እምነት ይከተላል፡፡ ከተጠራጠረ እንደ ጦር የሚወጋውን ዓይነት ሰው ላይ እንዲተክል የማገፋፋው ይህ እምነቱ ነበር፡፡ ይህም
በመሆነ «ነቅቶ መጠበቅ› በሚል ፍልስፍና ሕይወቱን ያንፃል። በዚህም የተነሳ ሕሊናው ሕግን በማስከበር፧ እምነቱ የእለት ተግባሩን በመከታተል ላይ ያተኮረ ሲሆን ቄሶች ለቅዳሴ እንደሚራሯጡ ሁሉ እሱም ለስለላ ተግባር ይሯሯጣል፡፡

ይብላኝለት እርሱ መዳፍ ውስጥ ለሚወድቅ፡፡ አባቱ፡ ከእስር ቤት
ሲያመልጥ ቢያየው ሮጦ ሄዶ ያሲዘዋል:: እናቱ አንድ ጊዜ ቲኬት
ስታጭበረብር ስላገኛት አሳልፎ ሰጥቶአታል፡፡ ዣቬር ተመሳሳይ የሆነ ሥራ በሚሠራበት ጊዜ ትክክለኛ ነገር እንደፈጸመ ሰው መንፈሱ ይረካል::ሕይወቱ በብቸኝነትና በግላዊነት የተሞላ ሲሆን ከዓለማዊ ምቾት የራቀ
ነበር፡፡ የእርሱ ደስታ ወንጀለኞችን ተከታትሎ ማደን እንጂ ዳንኪራ መርገጥ ወይም መዚቃ ማዳመጥ አልነበረም::

ዣቬር ማለት ይህ ሲሆን አሁንም ዓይኑን ከመሴይ ማንደላይን
አላነሳም፤ በጣም ይጠራጠረዋል፡ግን የተጨበጠ ማስረጃ ሊያገኝ አልቻለም::በመጨረሻ በክፉ ዓይን እንደሚያየው መሴይ ማንደላይን ደረሰበት:: ሆኖም ከምንም አልቆጠረውም:: ዣቬር ማን እንደሆነ ለማወቅ ፈልጎ ጥያቄ
አልጠየቀውም:: ለማንኛውም ብዙም አላቀረበውም፤ ብዙም አልሸሸውም፡፡በየጊዜው ሲያፈጥበት እያየ እንዳላየ ሆኖ ያልፈዋል፡፡ ሌሎችን በሚያይበትና
ማንደላይን ሁናቴ ዣቬርን በይበልጥ ግራ አጋባው፡፡ ሆኖም አንድ ቀን የዣቬር ሁኔታ መሴይ ማንደላይንን ያስቆጣዋል:: ነገሩ እንዲህ ነበር፡፡

አንድ ቀን መሴይ ማንደላይን ከአንዲት መንደር ውስጥ ከወዲያ
ወዲህ እያለ ይንሸራሸራል፡፡ ጩኸት ሰምቶ ዞር ሲል ሰዎች ተሰብስበው ያያል፡፡ ወደ ሥፍራው ቢሄድ ደብተራ ፎሽለማ የተባሉ ሽማግሌ ወድቀው እቃ የጫነ ጋሪ ተጭኖአቸዋል፡፡ ፈረሱም ወድቆ እግሩ ስለተሰበረ መነቃነቅ
እንዳቃተው ሁሉ ሽማግሌውም ጋሪው ተጭኖአቸው ሊነቃነቁ አልቻሉም። ጋሪው ላይ መጠነኛ ጭነት ስለነበረ ሽማግሌው የጣር ያህል ነበር የተጨነቁት:: ሰዎች ተሰብስበው ጭነቱን ብድግ አድርገው ሊያላቅቋቸው
ቢሞክሩም አልሆነላቸውም:: ዋጋ የሌለው ሙከራ የአንዳንዱ አያያዝ
የአላዋቂ ሲሆን የአንዳንዱም አያያዝ ለማስመሰል ያህል ብቻ ነበር፡፡ ሽማግሌው ትንፋሽ አጥሯቸው ሊሞቱ ሆነ፡፡ መፍትሔው ከሥር ገብቶ ጋሪውን ብድ ማድረግ ነበር፡፡ ከጋሪው ላይ ወጥቶ የተጫነውን ጭነት ለማራገፍ ከሞከሩ የባሰውን ሊጫንዋቸው ሆነ፡፡ ከሥሩ ገብቶ በሸክም ብድግ ለማድረግ ለራስ
የሚያስፈራ ሆነ፡፡ ስለዚህ ሁሉም ተፋጠጡ፡፡ ዣቬር አደጋው እንደደረሰ መጥቶ ስለነበር የእቃ ማንሻ መሣሪያ እንዲመጣ ሰው ልኮአል::

መሴይ ማንደላይን ከሥፍራው ደረሰ፡፡ ሕዝቡ መንገድ ለቀቀለት
«እርዱኝ እባካችሁ» ብለው ሽማግሌው ጮኹ፡፡ «የማነው ሳምራዊ ይህን ሽማግሌ የሚያድን?» ሲል መሌይ ማንደላይን ጠየቀ፡፡
መሴይ ማንደላይን ዞር ዞር እያለ ተመለከተ፡፡
«የእቃ ማንሻ መሣሪያ ያለው የለም?»
«ሰዎች ሊያመጡ ሄደዋል» አለ አንድ ሰው::
«ቶሉ ይደርሳሉ?»
«ፍሉቮ ከተባለ ሥፍራ ወደሚገኝ አንጥረኛ ነው የሄዱት፡፡ መቼስ
ቢያንስ አንድ ሩብ ሰዓት ያህል ያቆያቸዋል፡፡›
«ሩብ ሰዓት!» ሲል ጮኸ፡፡
ሌሊቱን ሲዘንብ ስላደረ ኣካባቢው ጨቅይቶ ነበር፡፡ ፈረሰ ተንሸራትቶ
የወደቀበትም ሥፍራ እንደማጥ ዓይነት ስለነበር የጋሪው እግሮች በአንድ በኩል ከጭቃው ውስጥ እየዘለቁ ወደ ውስጥ ሰመጡ:: በዚህ ዓይነት በአምስት ደቂቃ ጊዜ ውስጥ የሽማግሌው ወገብ ሊቀነጠስ ሆነ፡፡

«ሩብ ሰዓት መቆየት አንችልም» አላቸው መሴይ ማንደላይን እዚያ
የተሰበሰቡትን ሁሉ እያየ::
👍23😁3
«ሌላ ምርጫ የለም::»
«ከሩብ ሰዓት በኋላማ ዋጋ የለውም:: ጋሪው እየሰመጠ መሆኑን አይታያችሁም እንዴ!»
«ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡»
«ስሙ» አለ መሴይ ማንደላይን፤ «አሁኑኑ ከሆነ ከእቃ መጫኛው
ሥር ራስን ለማስገባት የሚያስችል ቦታ አለ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ግን ይህ አይቻልም::» ስለዚህ አሁን ጥቂት ሰዎች ተንፏቅቀው ገብተው በጀርባቸው ጋሪውን ብድግ ማድረግ አለባቸው:: ይህ ከሆነ ሰውዬው
በግማሽ ደቂቃ ውስጥ ይወጣሉ፡፡ ማነው እስቲ ጎበዝ ሰውዬውን የሚያድን? መቶ ፍራንክ ይከፈለዋል፡፡»
ሁሉም ዝም!
«ሁለት መቶ ፍራንክ» አለ መሴይ ማንደላይን፡፡
የተሰበሰበው ሰው መሬት መሬት ያይ ጀመር፡፡
«ከእዚያ ውስጥ ደፍሮ የሚገባ ሰው በጣም ጡንቸኛ መሆን አለበት፡፡
ግን እኮ ያ ሰው ከዚያ በኋላ እንዴት ይወጣል፣ እዚያው ተጨፍልቆ ይቀራል እንጂ» አለ አንድ ሰው በመካከሉ፡፡
«በሉ እባካችሁ! አራት መቶ ፍራንክ»
«አሁንም ዝም»
«ፈቃደኛነቱ እኮ አይደለም የጠፋው» አሉ አንድ ሰው::
መሴይ ማንደላይን ዞር ብሉ ሲያይ ዣቬርን አየው:: ከዚያ ለመኖሩ
አልተገነዘበም ነበር፡፡ ዣቬር ቀጠለ፡፡
«ኃይል ነው የሚያስፈልገው:: ከዚያ ውስጥ የሚገባ ሰው ደፋርና
እጅግ በጣም ጉልበተኛ መሆን ይኖርበታል:: ይህን የሚያህል የእቃ መጫኛ ጋሪ በጀርባው ተሸክሞ ለማንሳት የሚችል ምን ዓይነት ጉልበተኛ ነው?»
ከዚያ በኋላ ዣቬር መሴይ ማንደላይንን እንደልማዱ አፍጥጦ እያየው እያንዳንዱን ቃል ረገጥ አድርጎ የሚከተለውን ተናገረ::

«መሴይ ማንደላይን፣ አሁን እርስዎ የሚጠይቁትን ሥራ ለመፈጸም የሚችል አንድ ሰው ብቻ ነበር የማውቀው::
ማንደላይን ደነገጠ፡፡
ዣቬር ዓይኑን ከመሴይ ማንደላይን ሳያነሳ የአነጋገሩን ዘይቤ ለውጥ አድርጎ ቀጠለ፡፡
«ይህ ሰው ወንጀለኛ ነበር፡፡»
«እሱን ተወው እባክህ» እለ መሴይ ማንደላይን፡፡
«ቱለን ከተባለ ሥፍራ ታስሮ ነበር፡፡»
የማንደላይን ፊት አመድ መሰለ፡፡
«ወይኔ ተጨፈለቅሁ!» ሲሉ ሽማግሌው ጮኹ::
መሴይ ማንደላይን ቀና ብሎ ተመለከተ፡፡ ዣቬር አሁንም
እንዳፈጠጠበት መሆኑን ተገነዘበ፡፡ የተሰበሰበውን ሰው ቃኘ፡፡ የሃዘኔታ ፈገግታ እያሳየ:: ከዚያም ቃል ሳይተነፍስ በጉልበቱ ተንበረከከ፡፡ ወዲያው ከጋሪው እቃ መጫኛ ስር ከመቅጽበት ገባ፡፡

ሁሉም ተጨነቀ፡፡ ሰው ሁሉ ወሬ ለማየት ተርመሰመሰ፡፡ ለመቀመጥ ይችል እንደሆነ ከአንዴም ሁለቴ ሞከረ፡፡
«መሴይ ማንደላይን ከዚያ በቶሎ ብትወጣ ይሻላል» ሲል ሕዝቡ
ጮኸ፡፡ ሽማግሌውም ይህንኑ አሉ፡፡ «መሴይ ማንደላይን ከዚያ ቶሎ ብለህ ውጣ፡፡ እኔ ልሙት እንጂ አንተ ምን በወጣህ! ካልወጣህ አንተም
ትጨፈልቃለህ::»
ማንደላይን መልስ አልሰጠም፡፡ የተሰበሰበው ሕዝብ እንደገና ዝም
አለ፡፡ ጋሪው ሲነካካ ጊዜ የባሰውኑ ወደ ውስጥ ይሰምጥ ጀመር፡፡ እንዲያውም ከነአካቴው መሴይ ማንደላይን ራሱን ማላቀቅ ተሳነው::ሰው ተጨነቀ፤ ግን ጭቃው ውስጥ ሰምጦ የነበረው እግር መነቃነቅ ጀምሮ ቀስ እያለ ወደላይ መጣ፡፡ «ከግራ ቀኝ ያዘ እንጂ» ሲል ማንደላይን
ጮኸ፡፡ በአለው ኃይል ለማንሳት ሞከረ፡፡ ሁሉም ለመያዝ የሚችለውን ያህል ያዘ፡፡ የአንድ ሰው ድፍረት ሁሉንም ሰው አነቃንቆ ጉልበት ሰጣቸው::
ሃያ ሰው ያህል ጋሪውን አነሳው፡፡ ሽማግሌው ከሞት ዳነ፡፡

መሴይ ማንደላይን ተነሳ፡፡ ፊቱ፡ በአንድ ጊዜ የገረጣ መሰለ፧ በኃይል አልቦት ነበር፡፡ ልብሱ በጭቃ ከመለወሱም በላይ አንዳንድ ቦታ ላይ ተቀድዷል:: ሰው ሁሉ አለቀሰ፡፡ ሽማግሌው የማንደላይንን ጉልበት ሳመ::
«ደጉ አምላክ» ሲሉ ጠሩት፡፡ ራሱም ቢሆን በጣም ደስ አለ:: በእርካታ ዓይን ዣቬርን አየው::: ዣቬር ግን አሁንም በዓይነ ቁራኛ ይጠብቀዋል።

ደብተራ ፎሽለማ መላላጥ እንጂ ስብራት ስላልደረሰባቸወ ቶሎ ዳኑ፡፡
ግን ጉልበታቸሁ አልነቃነቅ ብሎ አስቸገራቸው:: መሴይ ማንደላይን ከሲሮች ጋር ተነጋግሮ ሽማግሌው ፓሪስ ከተማ አጠገብ ከሚገኝ ገዳም በአትክልተኝነት እንዲሠሩ አስቀጠራቸው::


💫ይቀጥላል💫
👍107
#ችርስ...
አንጀታችን ቢርስ!
እኔና ፈጣሪን ፣ውድድር ሲቃጣን፣
ላለመስከር ማልን፤ወይን እየጠጣን፡፡
ወይን
እያጋጨን፤
ነገር
እየፈጨን፤
ጨዋታ…ጀመርን፤
(አቦ ተባባል)
ስለ ሙሴ ታቦት፤
ስለ ዳዊት መሞት፤
ስለ እየሱስ ታምር
ስለበተነው ፣ከንቱ ሠላሳ ብር፤
ስለ ቤተሳይዳ..
እግዜር ወይን ቀዳ!
ስለቤታሳይዳ፤
ስለብሽቅ ይሁዳ፤
ስለዘማዊት ሴት፤
ስለ ፍጥሞ ደሴት፤
አወጋኝ፤
ስለ ሰው ሰውነት፤
ስለድብብቆሽ ፣ ስለጉራንጉሩ፧
ደርቶ ክርክሩ፤
ከቁዘማ ድሪያ ፣ከሐዘን ተሪክቦ፣
በወይን ተከቦ።
ደገምን፤
ደጋገምን፣
ወይን ሌላ ቀዳን፤
ጨለጥን፤
ቀለጥን፤
በወይን ሮጥን።
ሰው ግን ፤ሞቅ እያለው፣
እግዜር ባለበት ነው።
"ሙላው” እስቲ ቢልም፣
ንቅንቅ እንኳ አይልም።
የሰውን ግፍ ሁሉ እየተረኩበት፣
ካላንገዳገደው ፣ ሁሉን ቻዩን ጉልበት፣
እውነትም ጽኑ ነው ፤ብርቱ ለዘላለሞ፤
አትስከሩ ያለው ፣ ቢሰክር አይደለም፤
እያልኩ..
እየበገንኩ፤
የቀረው ወይን ፣ ልቀዳ እያነሣው፣
ከራድዮን ስለው ፣ ጠርሙሱን አነሣው፤
ነደደ፤
እጁን ጨመደደ፤
ሃ ሃ ሃ ሃ
እግዜር ተናደደ።
በነገራችን ላይ (ከራድዮን! ማለት ለኔ
የዘላለም ስለት፤
የልቤ ሐቅ፤
የነፍሴ ሳቅ፤
እምነቴ፤
ክህደቴ፤
ክስተቴ፤
ክፍተቴ፤
ስሕተቴ፤
የአንድ ወቅት ሕይወቴ፤
የሁል ቀን ሞቴ፤
ናት...
እና...
“ከሪደዮን” ብዬ ፣ ልክ እንደቀጠልኩኝ፣
ሰውነቴ ጠፋ ፣ አምላኬን አከልኩኝ።
ስላንቺ ሳነሣ፣
አብሾው ተነሣ፤
ንዴትና ዕንባ ፣ ቀልቡን ቢያወያየው፣
እግዜር አለ "ወየው!"
“እምቢየው፧"
"አልፈልግም" አለ! በእጄ እንደያዝኩት
ወይኑን ፣ ወሬውን ፣ መልሼ ጠየኩት፤
ዝሞ አለ...ዐሰበ!
ኹለቱሞ ግሪ ነው ፤ አንቺን ስላሰበ።
እወድሽ ነበረ!
ነገርኩት...ዝም አለ፤
እስምሽ ነበረ!
አሁንሞ..ዝም አለ፤
መልክሽ ከስሞ በላይ፤
ስሞሽ ከቃል ሰማይ፤
ልቤ መረገጫሽ፤
የምወደው ሣቅሽ ፣ ወደምድር መሞጫሽ፤
የከንፈሯ ወዙ ፣ ስትስመኝ እንጃልኝ
እግዜር ተናደደ ..."አዚጋ ቅዳልኝ፤”
አለልኝ
ስላንቺ ብመክረው
ስላንቺ ብነክረው፣
ስላንቺ ብነግረው፣
ቅናት አሰከረው፤
እንግዲህ እግዚሐር.. እግዚሐር ይኸነው።


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍157🔥1👏1
#ምንዱባን


#ክፍል_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ፋንቲን ወደ ትውልድ አገርዋ ስትመለስ ከተማው ይህን መስሎ ነው የቆያት፡፡ ማን እንደሆነች ግን ማንም አላስታወሳትም:: ደግነቱ የመሴይ ማንደላይን ፋብሪካ በር ለእርስዋም ተከፍቶ በፈገግታ ተቀበልዋት:: ሴቶች ከሚቀጠሩበት ክፍል ሥራ አግኝታ ሥራ ጀመረች:: ነገር ግን ሥራው
ለእርስዋ ጨርሶ እንግዳ ነበር፡፡ የማታውቀው ዓይነት ሥራ ስለነበር ግራ ተጋባች፡፡ ስለዚህ የሚከፈላት ገንዘብ ዝቅተኛ ሆነ፡: ግን ትንሽም ቢሆን ለእርስዋ በቂ ነበር፡፡ ሠርታ ለመኖር በመቻልዋ ችግርዋ ተቃለለላት፡፡

ፋንቲን ራስዋን ለማስተዳደር በመቻልዋ በጣም ደስ አላት:: ሰውን ሳያስቸግሩ ራስን ችሎ በሁለት እግር ቆሞ ማደር በጣም ደስ ይላል።የጉልበትዋን ዋጋ አገኘች፡፡ በመጀመሪያ ወር ደመወዝዋ መስታወት ገዛች፡፡
ውብ የሆነ ፀጉርዋን፣ ከወተት የነጡ ጥርሶችዋን፣ የልጅነት መልክዋን ጠዋት ማታ ለማየት በመቻልዋ ደስታዋ እጥፍ ሆነ፡፡ የሰው ልጅ ራሱን ከማየት የበለጠ የሚያስደስተው ነገር የለም:: ከልጅዋ ከኮዜት በስተቀር
ብዙ ነገሮችን ረሳች:: የጠዋት ማታ ሕልምዋ ልጅዋ ነበረች:: ወደፊት ምን ሊሆን እንደሚችል በአሳብ በታያት ጊዜ በደስታ ፈነደቀች:: አንዲት ትንሽ ክፍል ተከራይታ ደሞዟል በቅድሚያ በብድር መልክ ወስዳ ክፍሏን አስጌጠቻት።

«ባል አግብቼ ነበር» ብላ ለመናገር ስለማትችል ስለልጅዋ ሰው ፊት እንዳታነሳ ዘወትር ጥንቃቄ አደረገች::ሰዎች ይህን ካወቁ «ጋለሞታ» እያሉ
ስምዋን ሊያጠፉ እንደሚችሉ ታውቃለች::

ቀደም ሲል እንደተመለከተው ልጅዋን ለወሰዱላት ሰዎች ቃል
የገባችበትን ገንዘብ በወር በወር ሳታጓድል ትልካለች:: ስምዋን ከመፈረም በስተቀር መጻፍ ስለማትችል ለልጅዋ ደብዳቤ ስትጽፍ በሰው ነበር የምታጸፈው::

አዘውትራ ደብዳቤ ትጽፍ እንደነበር ተገንዝበናል:: በመሥሪያ ቤትዋ አካባቢ «ፋንቲን ብዙ ደብዳቤ ትጽፋለች፤ የሚጽፍላትና የምትፅፍለት ሰው አለ ማለት ነው» ተብሎ ብዙ ተወራ:: ስለዚህ ተከታታይዋ በዛ፡፡ ከዚህም
በላይ መልክዋ በተለይ ፀጉርዋና ጥርስዋ በጣም ቆንጆ ስለነበር የሚቀነባትም አልጠፉም::

በአማካይ በወር ሁለት ጊዜ ደብዳቤ እንደምትጽፍና ደብዳቤውንም ለተመሳሳይ ሰው እንደምትልክ የሥራ ባልደረቦችዋ ደረሱበት፡፡ ትክክለኛ
አድራሻውንም አወቁ፡፡ ደብዳቤ የሚጽፍላት ሽማግሌ መጠጥ ቤት ሲለፈልፍ አግኝተውት በሞቅታ ሁሉንም ነገራቸው:: ፋንቲን ልጅ እንዳላት ተሰማ::

«አንዳንድ ሴቶች አሉ፤ የትም ሲዘሉ ልጅ የሚቀፈቅፉ፤ የእዚያ
ዓይነት ሰው ናት ማለት ነው» እያሉ አሟት፡፡

ፋንቲን ፋብሪካው ውስጥ ሥራ ከጀመረች ወደ ዓመት ገደማ
ሆኖአታል፡፡ ኣንድ ቀን ጠዋት እርስዋ ትሠራበት የነበረው ክፍል ተቆጣጣሪ አምሳ ፍራንክ በከንቲባው ስም ትሰጣታለች:: «ምንድነው?» ብላ ስትጠይቃት
ከዚያን እለት ጀምሮ ከሥራ የተሰናበተች መሆኑንና ገንዘቡም ለመሣፈሪያ እንዲረዳት ብሎ ከንቲባው በሀዘኔታ የሰጣት መሆኑን ትገልጽላታለች.
ክንፉ እንደተመታ ዶሮ ክው ብላ ቀረች፡፡ ከተማውን ለቅቃ ልትሄድ
አትችልም:: የቤት ኪራይ እዳ አለባት:: አንዳንድ የቤት እቃ በዱቤ ገዝታለች፡፡ ስለዚህ እዳው መከፈል አለበት:: አምሳ ፍራንክ ደግሞ ለዚህ ሁሉ አይበቃም:: ምን እንዳለች ሳታውቅ እንደመጣላት ተናገረች::
ተቆጣጣሪዋ ወደ ቤትዋ እንድትሄድ ምልክት ሰጠቻት፡፡ አፍራና ተከዛ ከሥራዋ ቦታ ወጥታ ወደ ቤትዋ ሄደች። ጥፋትዋ ምን እንደሆነ በሁሉም ዘንድ ታወቀ፡፡ ለሌሎች ሴቶች አርአያ ልትሆን የምትችል ጋለሞታ! በዚህ
ላይ ቅናትም አለ፡፡

መልስ ለመስጠት ኃይል አጣች፡፡ ከንቲባውን እንድታነጋግር ሰዎች
መከርዋት:: ከንቲባው አምሳ ፍራንክ ሰጥቶ አባርሯታል፡፡ ያውም ደግና አዛኝ ሰው ቢሆን ነው እንጂ በገዛ ፋብሪካው ማን ያዝዘዋል:: ያለ ዳረጎት ዝም ብሎ ሊያባርራትም ይችል ነበር፡፡ «ከዚህ በኋላ ምን ማነጋገር ያስፈልጋል። በማለት ወደ ከንቲባው ሳትሄድ ቀረች::

መሴይ ማንደላይን ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቀው ነገር አልነበረም::
ብዙ ጊዜ አዋቂዎች ሥልጣንን ለሚመለከተው ማስተላለፍ እንደ ግዴታ ይቆጥሩታል:: ይህን የመሰለ የሥልጣን ውክልናን መከታ በማድረግ ነበር
ተቆጣጣሪዋ ራስዋን ከሳሽ፣ ዳኛና ፍርድ አስፈጻሚ በማድረግ በፋንቲን ላይ የፈረደችውና ከሥራ ያባረረቻት::

ፋንቲን በነበረችበት አካባቢ በግርድና ለመሥራት ሰዎች ይቀጥራት እንደሆነ ከቤት ቤት እየዞረች ጠየቀች:: ማንም ሊቀጥራት አልፈለገም፡፡

ከተማውንም ለቅቃ ለመውጣት ኣልቻለችም፡፡ የቤት እቃዋን በዱቤ የገዛችው ውራጅ እቃ ከሚሽጡ ባለሱቅ ስለነበር «እዳሽን ሳትከፍዪ ከአገር ብትጠፊ
ለፖሊስ ነግሬ ካለሽበት አሲዝሻለሁ» እያሉ ይዝቱባታል፡፡ የምትኖርበት ቤት ባለቤት ግን «ወጣት ነሽ፤ ከዚህም በላይ ቆንጆ ስለሆንሽ ያለብሽን የቤት
ኪራይ እዳ መክፈል አያቅትሽም» እያሉ ያበረታትዋታል፡፡ አምሳውን ፍራንክ ከፊሉን ቤት ላከራይዋት ስትሰጥ ከፊሉን ለውራጅ እቃ ሻጭ ከፈለች፡፡የእቃው እዳ ብዙ ስለነበር ለጊዜው በጣም የሚያስፈልጓትን እቃዎች
አስቀርታ ቀሪውን ማለት ሦስት አራተኛ የሚሆነውን ለባለቤቱ መለሰች፡፡ የሚቀርባት እዳ ወደ አንድ መቶ ፍራንክ ገደማ ነበር፡፡

ጎረቤትዋ የሆነ ወታደሮች ልብስ ያሳጥቧት ስለነበር ከዚህ የምታገኘው ገቢ ቆሞ ለመሄድ የሚያስችል ስንቅ መግዣ አደረገችው:: ለልጅዋ
የምትልከው የወር ኪራይ ግን መክፈል አቃታት::

ወደ ትውልድ አገርዋ የተመለሰችለት ያሳደረቻት አሮጊት ተቸግሮ መኖር እንዴት እንደሚቻል የሰጠቻት ትምህርት ለአሁን ኑሮዋ የጨለማ መብራት ሆናት:: ትንሽ ዋሽቶና ትንሽ ገቢ አብቃቅቶ መኖር መቻል የችግር ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን አስረድታት ነበር፡፡ የመጀመሪያው ስውር
ሲሆን ሁለተኛው እንደ ጨለማ ድብቅ ነው» ስትል መክራትም ነበር፡፡

ፋንቲን በጨለማ ያለ መብራት መኖር ለመደችው:: የምትቀምሰውን እራት ለመብላት ከጎረቤት መስኮት በሚመጣ የብርሃን ውጋገን እየተጠቀመች
ትጎርሳለች:: እራት ከሌለም ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ጥቅልል ብላ መደፋት ነው::

ትምህርት የለገሰቻት አሮጊት ሩህሩህ ሴት ነበረች:: ስምዋ ማርጋሬት ይባላል፡፡ ድሃ ብትሆንም ለተቸገረ አዛኝ ፣ ቤተክርስቲያንን መሳም
የምታዘወትር ጽኑ አማኝ፣ ምፅዋት መስጠት የሚያስደስታትና ስምዋን ከመፈረም በስተቀር ማንበብና መጻፍ የማትችል ሴት ነበረች::

የሚገርመው፤ ብዙውን ጊዜ እንዲህ ያለው ደግነት፧ እንዲህ ያለው እምነት የኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ ከሆነ ሰዎች ዘንድ አይጠፋም:: ኣንዴ ሲከፋቸው፣ አንዴም ደስ ሲላቸው ይኖራሉ:: በነገ በጣም ያምናሉ::በመጀመሪያ ፋንቲን በጣም አፍራ ለጥቂት ቀናት ከክፍልዋ ሳትወጣ ከቤትዋ
ውስጥ ቁጭ አለች:: ከቤት ከወጣች ሰዎች ኋላ ኋላዋ እየተከተሉ ጣት በመቀሰር የሚጠነቁሉባት መሰላት:: እውነትም ከቤት በወጣች ቁጥር ሰው ሁሉ ያያታል፤ ሰላምታ ግን አይሰጥዋትም:: መንገደኛ ሁሉ ደግሞ በክፉ ዓይን ሲያያት መጥፎ ስሜት አሳደረባት:: ይህም ስሜት እንደ ጥቅምት
👍18
ብርድ አካልዋን እየሰረሰረ አስጨነቃት::
ፋንቲን ባዶ እጅዋን የቀረች ድሃ በመሆንዋ ሌሉች እንዲያከብርዋት መጠበቅ የለባትም:: በመጀመሪያ ይህን እውነታ ባትገነዘብም ወደኋላ ኑሮ
ስላስተማራት ቀስ በቀስ ደረሰችበት:: ከሦስት ወር በኋላ ምንተእፍረትዋ ጨርሶ ተገፈፈ:: አደባባይ በይፋ ትወጣ ጀመር፡፡ «ለእኔ እንደሆነ ሁሉ ያው ነው» ትላለች ራስዋን በራስዋ ስታናግር፡፡ እንደ አልተሟላለት ገበሬ ብዙ ትለፋለች ፤ ግን የምታገኘው ትንሽ ነው፡፡ በጣም ስለምትለፋ ሰውነትዋ እየዛለ በቀላሉ ለበሽታ በመዳረጉ ሳል ይዞ አጣደፋት፡፡ አንዳንዴ ጎረቤትዋን ማርጋሬትን እየጠራች ‹‹እዩ እስቲ ሰውነቴ እንዴት እንደጋለ» ትላለች::

ጠዋት ጠዋት በሰባራ ማበጠሪያ ፀጉርዋን ስታበጥረው ዞማ በመሆኑ ደረጃ እያበጀ ስታየው ደስ ይላታል፡፡ ፀጉርዋን አልቆረጠችውም::

ክረምት ሊወጣ ሲል ነበር ከሥራ የተባረረችው:: አሁን የበጋ ወራት
ተገባድዶ እንደገና ክረምት ሊገባ ተቃርቦአል:: ክረምት ሲገባ ሁሉም ነገር ጭልምልም ይላል፡፡ ብርዱም አጥንት ሰርስሮ ይገባል:: የሰው ልብም እንደ ብርዱ ይቀዘቅዛል፡፡ ይህ ሁሉ ለፋንቲን ቀላል አልነበረም:: ከዚህም በተጨማሪ
ባለእዳዎችም «እዳሽን ክፍዬ እንጂ.» እያሉ ጨቀጨቅዋት::

ፋንቲን ብዙ ብትለፋም የምታገኘው ገንዘብ በጣም አነስተኛ ስለነበር የነበረባት እዳ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልሄደም:: ልጅዋን ያስጠጉላት
ሰዎች ለረጅም ጊዜ ስላልተከፈላቸው ደብዳቤ እየደጋገመ፡ ጻፉላት።
የሚደረድራቸው ክፉ ቃላት ልብን የሚያቆስለ ነበሩ:: አንድ ቀን የደረሳት ደብዳቤ ስለልጅዋ ሁኔታ የሚገልጸ ነበር፡፡ «ኮዚት ልብሶችዋ በመሉ አልቀው ራቁትዋን ነው ያለችው፤ በአስቸኳይ ቢያንስ አሥር ፍራንክ ላኪና
የሚሞቅ የክረምት ልብስ ይገዛላት፡፡»

ደብዳቤውን አንብባ እንደጨረሰች ጭምድድ አድርጋ ከመዳፍዋ ውስጥ አስገብታ ቀኑን ሙሉ ያዘችው:: ወደ ማታ ፀጉር ቤት ሄዳ በምናምን ተጠቅልሎ የነበረውን ፀጉርዋን ለቀቀችው:: ተንዠርግጎ ከኋላዋ ተንጠለጠለ::

«እንዴ! እንዴት ያለ ፀጉር ነው ያለሽ?» ሲል ፀጉር ሠሪው ጠየቃት::
«ቆርጠህ ብትወስደው ስንት ትከፍለኛለህ?» አለችው::
«አሥር ፍራንክ፡፡»
«« ቁረጠው::»
በገንዘቡ ወፈር ያለ ቀሚስ ገዝታ ለልጅዋ ላከችላት፡፡ ባልና ሚስት
በጣም ተናደዱ::
ገንክህቡን ነበር የፈለጉት:: ቀሚሱን ለራሳቸው ልጅ
ለኢፖኒን ሰጥዋት:: ምስኪንዋ ኮዜት የክረምቱን ብርድ የተቦጫጨቀ ጨርቅ
ብቻ ለብሳ አሳለፈች::

እናት ግን «ልጄ ትንሽ ይሞቃታል፤ ፀጉሬን ሸጬ አለበስኳት» ስትል
አሰበች፡፡ የተቆረጠው ፀጉርዋን እንዳይታይ በጨርቅ ሸፈነችው:: ሆኖም አላስጠላባትም፡፡ ነገር ግን ልብዋ ውስጥ መጥፎ ስሜት ማሳደሩ አልቀረም፡፡

ሰው ሁሉ ስላስጠላት ሁሉንም እንደጠላት ማየት ጀመረች:: ለመሴያ ማንደላይን ብቻ የተለየ ስሜት ነበራት:: ነገር ግን እርሱም ሲሆን ከሥራ ያባረራትና ኑርዋን ያበላሽባት ስለሆነ ለእርሱም የነበራት አክብሮት ከጊዜ
በኋላ እየቀዘቀዘ ሄደ፡፡ ሠራተኛ ሲወጣ በአጋጣሚ በፋብሪካው አካባቢ ያለፈች እንደሆነ ያበደ ለመምሰል ትስቃለች፤ ትዘፍናለች:: ፋብሪካው ውስጥ የምትሰራ አንዲት ሴት ፋንቲን ስትስቅና ስትዘፍን አይታት የዚህች
ልጅ መጨረሻ አያምርም» ስትል ተነበየች::

ፋንቲን በልጅነትዋ እንደ ወርበላ ወደድኩሽ ብሎ ሲቀርባት ልብዋ
ውስጥ ፍቅር ባይኖርም ለጊዜ ማሳለፊያ ብላ አብራው ዘለለች:: ይህ ሰው የማይረባ ዱርዬ ስለነበር በየቀኑ ማታ ማታ ይደበድባታል፣ ይረግጣታል።
በመጨረሻ ልጅ አስታቅፎአት ከአገር ጠፋ፡፡ ጥሉአት በመጥፋቱ በጣም ጠላችው:: ልጅዋን ግን እንደአምላክ ታመልካታለች::

ችግር እየጠናባትና ብቸኝነት በይበልጥ እየተሰማት በሄደ ቁጥር የልጅዋ ፍቅር ግለት እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ሰው ሁሉ ሲሽሽት በዓለም ላይ የቀረቻት የእኔ ናት የምትላት ኮዜት ብቻ መሆንዋ ሊታወሳት ሀብታም
ስሆን፣ ሲያልፍልኝ የእኔ ኮዜት ከኔ ጋር ትቀመጣለች፤ አብረን እንኖራለን» ትላለች:: ይህ ሲሆን በአሳብ ሲታያት ፈገግ ትላለች:: ሆኖም በሽታዋ ጠንቶባታል:: ማታ ማታ በጣም እያላበ ያስላታል፡፡

አንድ ቀን እነሚስተርና ሚስስ ቴናድዬ የጻፉላት ደብዳቤ ደረሳት:: «ሰፈራችን ተስቦ ገብቷል ፤ ኮዜትም ታምማለች:: የመድኃኒት ዋጋ ደግሞ ንሮአል፤ እየገደለን ነው:: ከአሁን በኋላ መግዣ የለንም:: በአንድ ሳምንት
ጊዜ ውስጥ አርባ ፍራንክ ካላክሺልን ልጅትዋ መሞትዋ ነው» የሚል መልእክት ነበር ደብዳቤው ያዘለው::

ከት ብላ ሳቀች:: ወደ ጎረቤትዋ ሄዳ የቁጭት ንግግር ተናገረች::
«ይገርማል!» ጥሩ ሰዎች ናቸው፧ አይደሉም! አርባ ፍራንክ! ያስቡት
እስቲ! የቱጃር አጠያየቅ አይደል? ገንዘብ ከየት የሚመጣ ይመስላቸዋል? ደደብ! የቀን ጅቦች አይደሉም!»

ወደ መስኮት ተጠግታ ደብዳቤውን እንደገና አነበበችው:: በደረጃው ወደ ምድር ቤት ወረደች:: ከቤት ወጥታ መንገዱን ተያያዘችው:: ሮጠች፧
ዘለለች፤ ከትከት እያለች ሳቀች:: እንደ እብደት አደረጋት::
ከአደባባይ ስትደርስ ብዙ ሰው ተሰብስቦ አየች፡፡ ሰው የተሰበሰበው ከአንድ ጋሪ ዙሪያ ሲሆን ቀይ ልብስ የለበሰ ሰው ጋሪው ላይ ወጥቱ ይለፈልፋል፡፡ የጥርስ ሐኪም ነበር፡፡ የሐኪሙ ሥራ ከአገር አገር እየዞረ ጥርስ ማከም ስለነበር አሁንም ጥርሱን ያመመው ሰው ካለ እያጠያየቀ
ነበር፡፡

ፋንቲን ከሕዝቡ ጋር ተቀላቀለች:: ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ሳቅዋን
ለቀቀችው፡፡ የጥርሱ ሐኪም ጥርስ እያወጣ ሳለ ሳቁን ሰምቶ ቀና ሲል ፋንቲንን አያት:: ሐኪሙ በቶሎ ተጣራ፡፡ «አንቺ ከዚያ የምትስቂው እንዴት ያሉ ጥርሶች ናቸው ያሉሽ? ከወተት የነጡ ናቸው፡፡ እነዚያን የሚያማምሩ ሁለት የፊት ጥርሶችሽን ብትሰጪኝ አርባ ፍራንክ እከፍልሻለሁ» አላት፡፡

«ምንድነው የሚሉት? የፊት ጥርሶችሽ ምንድን ናቸው ነው ያሉት?» ስትል ፋንቲን ጠየቀች::

«የፊት ጥርሶችሽ» አለ ሐኪመ•፧ «የላይኞቹ ማለቴ ነው!
ብትሽጪልኝ?»
«የሚገርም እኮ ነው» ስትል ፋንቲን ተናገረች፡፡
ጥርሳቸው የወለቀ አሮጊት «አይገርምም፣ ለጥርስ ነው አርባ ፍራክ እከፍላለሁ ያለው» አሉ በመገረም፡፡ «ልጅትዋ እድለኛ ናት::»
የሐኪሙን ንግግር ላለመስማት ፋንቲን እየሮጠች ሄደች፡፡ ሐኪሙ
ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ። «ብዙ ገንዘብ ነው የሰጠሁሽ፧ ይጠቅምሻል::
አሳብሽን ከለወጥሽ ወደ ማታ ቲላክ ሆቴል ብቅ በይ ፧ ከእዚያ ታገኝኛለሽ:
ፋንቲን ወደቤትዋ ተመለሰች፡፡ እየሮጠች ነበርና የሄደችው እየቃሰተች የተባለችውን ለወዳጅዋ ለማርጋሬት ነገረቻቸው፡፡

«ምን ልስጥሽ ነው ያለው?» ሲሉ አሮጊትዋ ጠየቁ፡፡
«አርባ ፍራንክ፡፡»
«አርባ ፍራንክ ነው ያልሽው?»
«አዎን አርባ፡፡»
ፋንቲን ይህንነ እያሰላሰለች ወደ ሥራዋ ሄደች፡፡ ከሩብ ሰዓት በኋላ
ሥራዋን ኣቁማ ደብዳቤውን እንደገና ለማንበብ ወደ መስኮቱ ጠጋ አለች፡፡
ደብዳቤውን አንብባ እንደጨረሰች ወደ ወዳጅዋ ዞር ብላ «ስለተስቦ
በሽታ የሚያውቁት ነገር አለ?» ስትል ጠየቀች፡፡
«ያው በሽታ ነዋ ልጄ» ሲሉ መለሱላት::
👍164👎1
«ልጆችን ይተናኮላል?»
«በተለይ ልጆችን ይጎዳል፡፡»
«ይገድላል?»
«ብዙ ጊዜ አሉ» ወ/ሮ ማርጋሬት::
ፋንቲን ደብዳቤውን እንደገና ለማንበብ ወደ መስኮት ጠጋ አለች፡፡
ማታ በጊዜ ከቤትዋ ወጥታ ሐኪሙ ወደ ነገራት ሆቴል አመራች፡፡
በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ገና ጎሕ ሳይቀድ ወ/ሮ ማርጋሬት ወደ
ፋንቲን ክፍል ሄዱ፡፡ ብዙ ጊዜ አብረው ነበር የሚያመሹት፡፡ በዋዜማው ስላልተገናኙ፣ ሥራም አብረው ስለሆነ የሚሄዱት አሮጊትዋ ከፋንቲን ቤት መጡ፡፡ ፋንቲን ከደረቅ የእንጨት ወንበር ላይ ተቀምጣለች:: ፊትዋ
ገርጥቷል፤ ዓይንዋ እንባ አቅርራል፡፡ ሌሊቱን በሙሉ አልተኛችም:: ሻሽዋ
ጉልበትዋ ላይ ወድቋል፡፡
ወ/ሮ ማርጋሬት ደነገጡ፡፡ «ምነው? ምን ሆንሽ? ሌሊቱን ቁጭ ብለሽ
አደርሽ እንዴ?» ካሉ በኋላ ፋንቲንን አጤንዋት:: ፋንቲን ፊትዋን ቀና
አደረገችው፡፡ በአንድ ቀን ከእድሜዋ አሥር ዓመት የጨመረች መሰለች::
«ምንም አልሆንኩም» አለች ፋንቲን፡፡ «እንዲያውም ደስ ነው ያለኝ፣
ልጄ ላትሞት ነው፤ መንፈሴ ሁሉ የረካ ነው የመሰለኝ::»
ይህን እንደተናገረች ከጥርስዋ ሽያጭ እጅዋ የገባውን አርባ ፍራንክ ለአሮጊትዋ አሳየቻቸው::
«የሥላሴ ያለህ!» አሉ ወ/ሮ ማርጋሬት:: «ይኽ ሁሉ ገንዘብ ከየት ተገኘ? ከሰማይ ነው የወረደው ወይስ ከምድር ፈለቀ?»
«ከየትም ይሁን ብቻ፧ አግኝቻለሁ» አለች ፋንቲን የኩራት ስሜት
አድሮባት ፈገግ እያለች:: ሆኖም ፈገግታዋ ዓይንን የሚያሸሽ እንጂ የሚስብ አልነበረም:: ከንፈርዋ በደረቀ ደም ተበክሎአል:: ወላቃዋም በግልጽ ይታያል፡፡
ሁለቱ የላይኞቹ የፊት ጥርሶችዋ ተነቅለዋል:: ጥርሱ የውበት ቀዳዳ
በቅጡ አልተደፈነም::
አርባውን ፍራንክ፡ ለልጅዋ ኣሳዳጊዎች ላከች:: ሚስተርና ሚስስ ቴናድዬ ገንዘብ ለማግኘት የፈጠሩት ዘዴ ነበር እንጂ ኮዜት አልታመመችም::

ፋንቲን ፊትዋን ታይበት የነበረውን መስታወት በመስኮት ወደ ውጭ
ወረወረች::

ባለ እዳዎችዋ በጣም እየጨከኑባት ሄዱ፡፡ ያገለገለ እቃ የሚሸጡ ሰውዬ ባገኝዋት ቁጥር «አንቺ እድለቢስ፣ ገንዘቤን አትሰጪኝም?» እያሉ
ሰደብዋት::

ምን አድርጊ ነው የሚልዋት? ፋንቲን እንኳን እዳ ልትከፍል ለሆድዋ ስላልሆነላት ከሰውነት ወጥታለች:: ልጅዋን የሚያሳድጉላት ባልና ሚስት
ሌላ ደብዳቤ ጻፉ::

«ኮዜት ከበሽታዋ ድና በማገገም ላይ ነች:: ነገር ግን እስከ ዛሬ
የተጠራቀመውን መቶ ፍራንክ አሁኑኑ ካልላክሽ ከቤት አስወጥተን መንገድ ነው የምንጥላት» የሚል ነበር፡፡
«መቶ ፍራንክ! አሁን ደግሞ የት ይሆን ይህን ያህል ገንዘብ የማገኘው? ይሁና!» አለች:: «የቀረውን ጥርሴን እሸጣለኋ!»
እድለቢስዋ ፋንቲን የሰው መዘባበቻ ሆነች::..

💫ይቀጥላል💫
13👍8😢2
አትሮኖስ pinned «#ምንዱባን ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ ....ፋንቲን ወደ ትውልድ አገርዋ ስትመለስ ከተማው ይህን መስሎ ነው የቆያት፡፡ ማን እንደሆነች ግን ማንም አላስታወሳትም:: ደግነቱ የመሴይ ማንደላይን ፋብሪካ በር ለእርስዋም ተከፍቶ በፈገግታ ተቀበልዋት:: ሴቶች ከሚቀጠሩበት ክፍል ሥራ አግኝታ ሥራ ጀመረች:: ነገር ግን ሥራው ለእርስዋ ጨርሶ እንግዳ ነበር፡፡ የማታውቀው ዓይነት ሥራ…»
#ጎሽ
ነይ ግቢ ዓለሜ ፣ አነሣሽው ቤቱን
መጋረጃው ይውረድ ፣ ይግለጥ እመቤቱን።
ይውጣ መቀመጫው፣ ለቸገረው ይሰጥ፣
በጥፍራችን ቆመን ፣ መቼ ልንቀመጥ?
አንቺ ነሽ መንበሬ ፧ እኔ ነኝ ወንበርሽ፤
የሰው ሕጉን ሁሉ ፣ በኔው ሕግ ሽረሽ፣
ኑሪብኝ፤
ስፊብኝ፤
ነይብኝ ክረሚ ፤ ሁሉን አውጣጪ፤
እቃ የሞላውት ፣ አንቺ እስክትመጪ፤
ሰወ የራቀው ቤት፣ ጉዳጉድ ደርድሮ
"ሞላልኝ ይልሻል”፤ ባሕር ሙሉ ኑሮ፡፡
ሞልቶልኝ አይደለሞ ፤ ዕቃ ምሰበስብ፤
ክፍተት ባየሁ ቁጥር ፣ አንቺን እንዳላስብ...
ነበረ።
ተመስገን
ነበረ አልኩ እኔሞ ፣ እንደሰው ዘየረኝ፤
ነበር እንዲኾን ነው ፣ ደብር የማያዞረኝ፡፡
ሳፋውንም ጣይው ፣ ምንሞ አላጥብበት
መቆሸሽ የለውሞ ፤ ነፍስ የሰፈረበት፤
መስታወቱን ጣይው
ሞንሞ አላይበት ፣ ልይስ ብልሽ ምኔን?
ሥትሥቂ አውቃለሁ ፣ ቆንጆ ሰው መሆኔን።
የሀገሩን ዛፍ ልጥረብ ፤ በሱ ላልጠለል፤
አንቺን ስፈልግ ነው ፣ወትሮም የምቃጠል፤
ሁሉንም አውጭልኝ
ሁሉንም አንሺልኝ
ከወላዲት አምላክ
ከሥዕሏ በቀር ፣ ከሐዘኔ እናት
ስትሄጂ ስትርቂኝ
ቤቴን ሙይው ብዬ ፣ ደሞ እንደለማመናት።

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍14
#ምንዱባን


#ክፍል_አሰር


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


የፋንቲን ታሪክ ምን ዓይነት ታሪክ ነው? ያሽከር ታሪክ! አሽከርን
የሚገዛው ሕብረተሰቡ ነው?
ከማን?
ከችግር? ከመከራ? ከስቃይ? ከረሃብ? ከብቸኝነት? የሚቀፍ ግዢ ነፍስ በዳቦ ሲለወጥ! ችግር ግለሰቦች ያልፈቀዱትንና ያልፈለጉትን እንዲሠሩ
ሲያስገድዳቸው! ሕብረተሰቡ ደግሞ በግዳጅ የሚያደርጉትን በደስታ ሲቀበል አይገርምም!

ባርነት ቀርቷል ይባላል፡፡ ውሸት ነው፧ አልቀረም:: አሁንም አለ።
ግን በአሁኑ ጊዜ ጎልቶ የሚታየው በሴቶች ላይ ነው:: ስሙን ቀይረው
ዝሙት አዳሪ ይሉታል፡፡

እስካሁን ባየነው ድራማ ፋንቲን ቀደም ሲል የነበራትን ሁሉ አሟጥጣ ጨርሳ የቀራት ነገር የለም :: ክብርም፧ ስምም፧ እናትነትም፤ ውበትም ምኑ ቅጡ ሁሉም ሄዶአል:: ቢነኳት አካልዋ እንደ በረዶ ቀዝቅዟል። ስሜትዋም ሞቷል፡፡ የፈለገችውን ነው የምታደርገው:: እያወቀች
አታውቅም ፡ እየሰማች አትሰማም፡፡ የተከፋን ፊት አንግታ፤ ሆድ የባሰውን ልብ ተሸክማ እያየ የማያይ ዓይን ሰክታ እየሰማ የማይሰማ ጆሮ አንጠልጥላ እንደፈቀደችው ትኖራለች:: ሕብረተሰቡም ሆነ ሕይወት ከፋንቲን ጋር የነበረውን ግንኙነት አቋረጠ፡፡ እሷም ለምንም ነገር ደንታ አጣች፡፡ሊደርስባት የሚችል መጥፎ ነገር ሁሉ ደርሶባታል፡፡ እርሷም የቻለችውን ያህል ተሸክማዋለች፡፡ ሁሉንም አየችው:: የነበራትን ሁሉ አጣች:: ለሁሉም
አለቀሰች፤ አነባች፡፡ ታዲያ አሁን ምን ይሁን? ሁሉንም እርግፍ አድርጋ ተወችው:: ምቾትና ድሎት ችግርን ስለማያውቁት እንደማይጨነቁለት
ሁሉ እንዲሁም ሕፃን ሞት እንቅልፍ መስሎት ዝም እንደሚል ሁሉ እርስዋም ምንም ነገር እንዳልሆነ ቆጥራ ችግር አልተው ቢላት እርስዋ ተወችው:: የምትፈራው ወይም የምትሸሸው ነገር የለም:: ደመና
ቢያጠልልባት፣ ውቅያኖስ ቢደፋባት ምን ደንታ አላት! የኑሮዋ ስፍንጎና ሞልቶ ፈስሷል፡፡

የፋንቲን እምነት ይህ ነበር፡፡ ግን ተሳስታለች:: ማነው እስቲ
መጨረሻውን የሚያውቅ? ዛሬ እንዴት እንደሚያልፍ፤ ነገ ደግሞ እንዴት ሆኖ እንደሚመጣ ማን ያውቀዋል? ሁሉንም የሚያውቅ ፈጣሪ አምላክ ብቻ ነው::

ትንንሽ ከተማዎች ውስጥ አሉ አይደል ኣንዳንድ ልባቸው ያበጠ
ጎረምሶች! በትንሽ ገቢ እንደ ሀብታም የሚንቀባረሩ! ጉራቸው አያድርስ፤ ሳይኖራቸው ሀብታም፧ ሳይማሩ ተመራማሪ፧ ያልሆኑትን ለመሆን ሞካሪ፤ ቡና ቤት ሲገቡ የሚጀነኑ፤ ሲጃራ ማጨስ፤ ሸሚዝ መጠቅለል፤ የጫማ ተረከዝ ማስረዘም፧ ሳይነኩ መነጫነጭ፤ «እስቲ ቅጂ እባክሽ» ማለት፧ ሻይ
ቤት የሚያዘወትሩ፤ አላፊ አግዳሚውን የሚለክፉ፧ ይህን የመሰሉ ሰዎች የትም አሉ:: በተለይ ትንንሽ ከተማ ውስጥ እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ
እየደደቡ የሚሄዱና በአንጎላቸው ሳይሆን በቂጣቸው የሚያስቡ ሞልተዋል፡፡

በ1823 ዓ.ም. ይህን የመሰለ ጠባይ የነበረው አውደልዳይ፤ ጎፈሬ ብርቁና ዘመናዊ መስሎ በሰው ስቃይ የሚደሰት ጎረምሳ ነበር:: ይህ ጎረምሳ ሰው ከተሰበሰበበት ቡና ቤት ላይ ታች የምትለውን፧ ኑሮ ያንገላታትን፤
የማይሆን ልብስ የለበሰችውና ክበር ገላዋን ለጎረምሳ አሳልፋ የምትሸጠዋን ሴት ደጋግሞ የሚለክፍ ወጣት ነበር፡፡ አንድ ቀን ፋንቲንን እንደልማዱ ለከፋት:: እንዳልሰማ ዝም አለችው:: ሲጃራ ማጨስ ፋሽን ነውና ተመልሳ
በአጠገበ ስታልፍ የሲጃራ ጭስ አቦነነባት:: በአጠገቡ በአለፈች ቁጥር «ፉንጋ፧ ኡኡቴ፣ የምን መኮሳተር ነው? ጥርስ አልጠፋብሽም? እና ሌላም
ሌላም እያለ ሰደባት:: ይህ ሰው ፋንቲንን ሲያናግራት ቀና ብላ እንኳን አላየችውም:: ልክ ቅጣት እንደተወሰነበት ወታደር ከወዲያ ወዲህ ገልመጥ ሳትል ወደፊት ትሄድና ትመለሳለች:: አሁንም እንደገና ወደፊት ትሄድና
ተመልሳ ትመጣለች:: ሰውዬው ብዙ ጊዜ ከለከፋት በኋላ በመጨረሻ ዝም ስትለው በጣም ተናድዶ ኖሮ ቀስ ብሎ ተከትሎአት ይሄድና ልክ ለመመለስ ፊትዋን ስታዞር መንገድ ግራና ቀኝ ተቆልለ ከነበረው በረዶ ያነሳና
በጀርባዋ በኩል ይመታታል፡፡ ይህን ጊዜ ልክ እንደነብር ዘልላ አንገቱ ላይ በመጠምጠም በጥፍርዋ ፊቱን ደም በደም አደረገችው:: ሰምቶት የማያውቅ
የስድብ ናዳ አወረደችበት፡፡

ጩኸትዋ በአካባቢው ከነበረው ሻይ ቤት ተሰምቶ ሰዎች ምንድነው ብለው ወጡ፡፡ ቀስ በቀስ ብዙ ሰው ተሰበሰ ሰውዬው አልሞት ባይ ተጋዳይ ከሚቧጥጠው ጥፍር ይከላከላል፡፡ የተሰበሰበው ሕዝብ «ብራቮ እያለ ይስቃል፤ ያጨበጭባል፡፡ ፋንቲን መቧጠጥ ብቻ ሳይሆን በጥፊ በርግጫ
ትማታለች፡፡
ድንገት አንድ እረጅም ሰው እየሮጠ መጥቶ ሴትዮዋን በጭቃ
የቦካውን ወገብዋን ይዞ «በይ ተከተዪኝ አላት::

እንገትዋን ቀና አደረገች፡፡ የጋለው ሰውነትዋ በረደ ፣ በቁጣ የነደደው
ድምፅዋ ቀዝቀዝ አለ፡፡ በፍርሃት ተንቀጠቀጠች፡፡ የፖሊሱ አዛዥ ዣቬር እንደሆነ አውቀች::

በግርግር አውደልዳዩ ሹልክ ብሎ ከዚያ ጠፋ::

ከዚያ ከብበው የቆሙትን ሁሉ ዣቬር በተናቸው:: ከዚያም ሴትዮዋን እየጐተተ ወደ ቢሮው ወሰዳት፡፡ ቢሮው ከዚያ ሩቅ አልነበረም:: ሴትዮዋ ብዙም ሳታመነታ ተከተለችው:: ቃል አልተነፈሰችም፡፡ ተሰብስቦ የነበረው ሕዝብ ሴትዮዋን ለእብደት በሚዳርግ ፌዝና ሰቆቃ አሽሟጠጣት::

ከፖሊስ ጣቢያ እንደደረሱ ዣቬር በር ከፍቶ ፋንቲንን ይዞ ገባ፡፡ በሩን
መልሶ ዘጋው:: ፋንቲን እንደ ፈራ ውሻ ቃል ሳታሰማ ጥግ ይዛ ከወለሉ ላይ ቁጭ አለች፡፡ ዘበኛው መብራት አበራ፡፡ ዣቬር ከኪሱ ወረቀት አውጥቶ መጻፍ ጀመረ::

የፖሊሱ አዛዥ ኮስተርተር ያለ ሰው በመሆኑ ፊቱ ላይ የመቅበጥበጥ
ምልክት አይታይበትም፡፡ ሕግን የማስከበር ጥማቱ የሚያረካባት ቅጽበት በመሆኑ ሥልጣኑን ለማሳየት ተነሳሳ፡፡ የተቀመጠበት ወንበር ትክክለኛ ፍርድ የሚሰጥበት ሥፍራ እንደሆነ ከልቡ ያምናል፡፡ ከሳሽም፧ ፍርድ
ሰጪም ራሱ ነው፡፡ የሴትዮዋን አድራጎት በይበልጥ በአጤነ ቁጥር ወንጀለኝነቷን ከመጠራጠር ይገታል፡፡ ወንጀል ስትፈጽም በዓይኑ አይቷል፡፡ አንዲት
ሴት አዳሪ አንዱን የከተማ ነዋሪ ከሰው ፊት ደብድባለች፡፡ ለዚህ ጥፋት ዣቬር ራሱ የዓይን ምስክር ነው፡፡ ፀጥ ብሎ ሁኔታውን መዘገበ፡፡

የጊዜውን ራፖር መዝግቦ ሲጨርስ ፊርማውን አኖረበት፡፡ ወረቀቱ አጣጥፎ ለዘበኛው ሰጠው::
«ሦስት ሰዎች ይዘህ ይህችን ሴት እስር ቤት ውሰድዋት፡፡»
ወደ ፋንቲን ዞር ብሎ «የስድስት ወር እስራት ተፈርዶብሻል» አላት፡፡
እድለ ቢስዋ ሴትዮ ሰውነትዋ ተንቀጠቀጠ፡፡
«ስድስት ወር! ወህኒ ቤት ውስጥ ስድስት ወር ሙሉ!» ብላ በኃይል
ተነፈሰች፡፡ «ልጄስ!» ስድስት ወር ሙሉ ምን ልትሆን ወይኔ ልጄ! እስከዛሬ ለእነቴናድዬ ያልከፈልኩት ከመቶ ፍራንክ በላይ እዳ አለብኝ፡፡ ጌታዬ ይህን
ያውቃሉ?» ስትል ዣቬርን ጠየቀችው::

መሬት ላይ ተንከባለለች:: ሦስቱ ሰዎች ከአፈሩ ላይ እንደወደቀች
ጎትተው አስወጥዋት::
«መሴይ ዣቬር ማሩኝ፡ ይቅር በሉኝ» ስትል ጮኸች:: «ምንም
ዓይነት በደል እንዳልፈጸምኩም! እምልልዎታለሁ:: ከመጀመሪያው ጀምሮ ከሥፍራው ቢኖሩ ኖሮ እውነቱን ያዩ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ስም እምላለሁ!
👍161🔥1
ሰውዬውን አልበደልኩትም:: ያ የማላውቀው ሰውዬ በረዶ አፍሶ ነው የመታኝ፡፡ ዝም ብሎ የሚሄድ መንገደኛን በበረዶ የመምታት መብት አለው? እስቲ ይፍረዱኝ! ያ ነው አውሬ ያደረገኝ፡፡ እንደሚያዩኝ ጤነኛ አይደለሁም፡፡ ሰውዬው አንቺ ወላቃ! አንቺ ዱርዬ' እያለ ሰድቦኛል፡፡ ጥርስ እንደሌለኝ አውቃለሁ! ቢሆንም ያስከፋኛል፡፡ ይህ ሆኖብኝ ነው እንጂ
ሆን ብዬ ያደረግሁት አይደለም:: እርሱ ዝም ብሎ ነካካኝ እንጂ እኔ
አልደረስኩበትም፡: ዝም ስለው በረዶ አንስቶ መታኝ፡፡ ጌታዬ መቶ ፍራንክ ያልተከፈለ እዳ አለብኝ፡፡ እዳዬን ካልከፈልኩ ልጄን ከቤታቸው አስወጥተው
ሜዳ ነው የሚጥሉብኝ፡፡ ጌታዬ ስለልጄ ብለው ይራሩልኝ፡፡ እኔ ዘንድ እንዳላመጣት አቅም የለኝም:: እዩ ጌታዬ ከቤታቸው አስወጥተው መንገድ
ከጣልዋት ራስዋን ለመጠበቅ የማትችል ሕፃን ናት፡፡ ጊዜው ደግሞ ክረምት ነው፡፡ ለጨቅላዋ ልጄ ይዘኑላት ጌታዬ! በእድሜ ከዚህ ትንሽ ከፍ ያለች ብትሆን እንኳን እንደምንም ብላ ከወዲያ ወዲህ ተሯሩጣ መኖር ትችል
ነበር፡፡ በዚህ እድሜዋ ግን አትችልም:: ይራሩልኝ፤ ይዘነልኝ ጌታዬ፡፡»
በዚህ ዓይነት ብዙ ለፈለፈች፡፡ ደግማና ደጋግማ መሬት ሳመች::
እጆችዋን ወደ ሰማይ ዘረጋች:: ጉንጮችዋ በእንባ እስኪርሱ ድረስ አለቀሰች ! ተንሰቀሰቀች:: አምርራ እየጮኸች ስታለቅስ ሳልዋ ተነስቶ ደረቅ ሳል ሳለች፡፡ መሪር ጭንቀትዋ ፊትዋ ላይ ጎልቶ ሲታይም የልጅነት ውበትዋን
ጨርሶ ሊያከስመው አልቻለም:: ከዚያ የነበሩ ሰዎች አትኩረው ሲመለከትዋት ቆንጆ ሴት ለመሆንዋ አልተጠራጠሩም፡፡ ብድግ ብላ የአዛዡን ኮት ጫፍ
ሳመች፡፡ ሁናቴዋ እንደ ድንጋይ የጠጠረ ፤ እንደ በረዶ የቀዘቀዘ ልብን በቀላሉ የሚያሟሟ ነበር፡፡ ሆኖም እንደ እንጨት የደረቀ ልብን ሊፈታ አልቻለም፡፡ ዣቬር ኣልተበገረም::

«በይ ተነሽ» አለ ዣቬር፡፡ «አትለፍልፊብኝ ፤ ይበቃል! ምን
ትነፈርቅብኛለች! መንገድሽን ቀጥይ፡፡ ስድስት ወር ተፈርዶብሻል፡፡ ክርስቶስ
እንኳን ይህን ውሳኔ ሊሽር አይችልም::»
በመጨረሻ የተናገረው ቃል እጅግ አስደነገጣት፡፡ «ክርስቶስ እንኳን
ይህን ውሳኔ ሊሽር አይችልም:: መሬት ላይ እንደ ሕፃን ልጅ ተንፈራፈረች። አሁንም «ማሩኝ» ስትል ጮኸች::

ዣቬር ፊቱን አዞረ:: ፖሊሶቹ ሁለት እጆችዋን ያዙ፡፡

ሴትዮዋ እንደዚያ ስትለፈልፍ ጥቂት ሰዎች ተሰባስበው ነበር፡፡ ከዚያ የማይሠራ አንድ ሌላ ሰው ደግሞ ደብለቅ ብሎ ቆሞአል፡፡ በግርግር ማንም ሳያየው የውጪውን በር ከፍቶ ገብቶ ፊቱን ወደ ግድግዳ አዙሮ ስለቆመ
ፋንቲን የተማጠነችውን ሁሉ ሰምቷል፡፡

ፖሊሶቹ እጆችዋን ይዘው ጎትተው ሲያወጥዋት ይህ ሰው ዘወር
ብሎ «አንድ ጊዜ እስቲ» ሲል አዘዘ፡፡ ፖሊሶቹ እጆችዋን ለቀቁ::
ዣቬር ወጣ ብሎ ሲመለከት ከንቲባው መሴይ ማንደላይን እንደሆነ አየ፡፡ ጎንበስ ብሎ እጅ ነሳው:: ሆኖም ፊቱ ላይ የመቆጣትና የመቀየም
ምልክት ይታይበት ነበር፡፡

«ይቅርታ፣ ክቡር ከንቲባ!»

ክቡር ከንቲባ የሚለውን ቃል ስትሰማ የፋንቲን ፊት ተለዋወጡ፡፡
ከመቅጽበት ብድግ ብላ ቆመች:: ሳይታሰብ በድንገት ማንም ሊያቆማት በማይችል ፍጥነት ተወርውራ ከንቲባው እግር ስር ወደቀች:: ወዲያው አንገትዋን ቀና አደርጋና ዓይንዋን አፍጥጣ ከንቲባውን እያየች የከተማው
ከንቲባ ማለት እርስዎ ነዎት» ካለች በኋላ የፌዝ ሳቅ ሳቀች፡፡ ከዚያም
ከከንቲባው ፊት ላይ ምራቅዋን ተፋች:: ከንቲባው መሀረቡን አውጥቶ ፊቱን ከጠራረገ በኋላ የሚከተለውን ተናገረ፡፡
«መሴይ ዣቬር ይህችን ሴት ልቀቅዋትና ትሂድ»
ዣቬር ከመደነቅ ብዛት የሚለውን አጣ፡፡ በጣም ገርሞት አፉን
እንደከፈተ ቀረ፡፡
ከንቲባው የተናገራቸው ቃላት በዚያው መጠን ፋንቲንንም አፈዘዛት ራሱን ያዞረው ሰው እንዳይወድቅ አንድ ነገር ለመያዝ እንደሚጣደፍ ሁሉ እርስዋም እጅዋን ዘርግታ ቶሎ ብላ የደረሰችበትን ቋሚ ያዘች፡፡ ከዚያም አካባቢዋን ከቃኘች በኋላ እርስ በራስዋ እንደምትነጋገር ድምፆዋን ዝቅ አድርጋ ተናገረች::

«ልቀቅዋት! በነፃ ሊለቁኝ! ወህኒ ቤት ኣልወርድም! ስድስት ወር
አልታሰርም ማለት ነው! ማነው ይህን ያለው? ማንም ይህን ሊል አይችልዎ፧ ተሳስቼኣለሁ:: ይህ ሰው ያ እኩይ ከንቲባ ሊሆን አይችልም:: ወይ መሴይ
ዣቬር ! እርስዎ ኖት፧ ሲያፌዝ ነው ልቀቅዋትና ትሂድ ያሉት አይደለም? ቤታቸወን ያከራዩኝን ሰው ሄደው ይጠይቁ:: የቤት ኪራይ በጊዜው
እንደምከፍልና ታማኝ ሰው እንደሆንኩ ራስዎ ሄደው ያረጋግጡ፡፡ እባክዎን
ይቅርታ ያድርጉልኝ፤ ይራሩልኝ::»
ወደ ፖሊሶቹ ዞር ብላ ደግሞ «ይህን ሰው ተመልከቱት ፤ እንደት
እንደተፋሁበት አያችሁ አይደል? የኛ ከንቲባ፤ ሊያስፈራሩኝ አይደለም ከዚህ
የመጡት? እኔ ግን እርስዎን አልፈራም:: እኔ የምፈራው መሴይ ዣቬርን ብቻ ነው:: ደጉን መሴይ ዣቬርን ብቻ ነው የምፈራው::»
ይህን እንደተናገረች ወደ ከተማው ፖሊስ እዛዥ ፊትዋን አዞረች::
«አይ ጌታዬ! እውነተኛ ዳኛ መሆን አለብዎት፡፡ መሴይ ዣቬር
ትክክለኛ ዳኛ እንደሆኑ አውቃለሁ:: ሴት ልጅን በጠጠረ በረዶ ወርውር መምታት ልክ አይደለም ፤ ያውም ሳትደርስበት:: ድብደባውን የተመለከቱት
መኮንኖች በትርኢቱ ተደስተው ሳቁ፡፡ እኛ ምስኪኖች የእነሱ መደሰቻና መሳለቂያ ነን፡፡ እርስዎ የደረሱት ከዚያ በኋላ ነው:: እርግጥ ነው እርስዎ
ሕግ የማስከበርና ሥርዓት የማስጠበቅ ኃላፊነት አለብዎት:: ለዚህ ነው እኔን የያዙኝ:: ግን ነገሩ ትክክል አለመሆኑን ሲረዱ ልቃቅዋትና ትሂድ" አሉ፡፡ ትክክለኛ ዳኛ እንደመሆንዎ አሁንም በድጋሚ ሂጂ ይበሉኝ፡፡ ይህንንም
የሚሉት ለሕፃንዋ ልጄ ሲሉ እንደሆነ አውቃለህ::: ስድስት ወር ከታሰርኩ ልጄን ለመርዳትና ለማሳደግ አልችልም:: ሁለተኛ ሌላ ጥፋት አላጠፋም:: እንደፈለጉ ይሳለቁብኝ፤ ይዝለፉኝ፤ መልስ አልሰጣቸውም:: መሴያ ዣቬር
ሁለተኛ ጥፋት አጥፍቼ ከፊትዎ ብቆም እንደፈለጉ ያድርጉኝ እኔም ዝም እላለሁ:: ዛሬ እኮ ሰውዬው በጣም ስላናደደኝ ነው ዘልዬ ጉብ ያልኩበት:: ደግሞም ነግሬዎታለሁ ፤ አሞኛል:: ሳል ይዞ ያጣድፈኛል:፡ እንደዚህ ተይዤ ሳለ በበረዶ ሊመታኝ ስሜቴ ጋለ፤ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ ; ራሴን መቆጣጠር
ተሳነኝ:: ሐኪም ደግሞ ብትጠነቀቁ ይሻላል ሲል ነግሮኛል፡፡ ቆዩ እስቲ ጌታዬ እንዲያውም አይፍሩ እንጂ ሰውነቴን ይንኩትና ትኩሳቴን ይመልከቱ ፤ ይኸውሎት፡: »

በድንገት የቀሚስዋ መዛነፍ ተገንዝባ ሳብ ሳብ አድርጋ አስተካከለችው:: ሲጎትትዋት ለካ ቀሚስዋ ተዛንፎ መሸፈን የነበረበት ገላዋን ገሃድ
አውጥተውታል፡፡ ብድግ ብላ ተነስታ ፖሊሶቹን እጅ በመንሳት ወደ በር አመራች።

«ወንድሞቼ፤ የፖሊሱ ኣዛዥ ትሂድ ብለዋልና መሄዴ ነው» አለች
መሴይ ዣቬር እስከዚያች ደቂቃ ድረስ ቃል ሳይተነፍስ ወደ መሬት አቀርቅሮ ቀርቶ ነበር ለተመለከተው ቦታው ተስተካክሉለት እንዲተከል ተራውን የሚጠብቅ ሀውልት እንጂ ሰው አይመስልም:: ጨርሶ ነቅነቅ አላለም

ሴትዮዋ ራመድ ስትል አንድ ነገር ረግጣ ኖሮ አንኮሻኮሽች፡፡ ዣዤር
ይህን ጊዜ ከተዋጠበት የስሜት ባህር ነቅቶ አንገቱን ቀና አደረገ፡፡ የተሰጠው ሥልጣን ምን እንደሆነ ታሰበው:: መቼስ የበታች ሹማምንት ሥልጣ ሲሰጣቸው እንደ አውሬ ይባላሉ፡፡ ትምህርት ወይም የኑሮ ልምድ
እንዳልሞረደውና በአእምሮ እንዳልበሰለ ሰው ይጨክናሉ::

«የሃምሳ አለቃ» ሲል ጮኸ፡፡ «ይህች አገር በጥባጭና ዱርዬ ሴት መውጣትዋ እንደሆነ አይታይህም? ማነው ትሂድ ብሎ ያዘዘህ?»

«እኔ» አለ ከንቲባው::
👍9
ዣቬር የተናገረውን ስትሰማ ሲሰርቅ የተደረሰበት ሌባ የሰረቀውን ቀስ ብሎ እንደሚጥል ሁሉ ፋንቲን የያዘችውን ቀስ ብላ ለቀቀች:: የመሴይ
ማንደላይንን ድምፅ ስትሰማ ደንግጣ ሌላ ቃል ሳትናገር ፊትዋን አንድ ጊዜ ወደ ከንቲባው፣ መልሳ ወደ ፖሊስ አዛዥ እያዞረች ሁለቱን ሰዎች ማስተያየት ጀመረች:: «የትኛው ነው አሁን የተናገረው» ስትል ራስዋን ጠየቀች:: እንኳን መናገር በኃይል መተንፈስ እንኳን አልደፈረችም፡፡
«እኔ» ብሎ መሴይ ማንደላይን ሲናገር የፖሊሱ አዛዥ ዣቬር ፊቱን
ወደ ከንቲባው አዞረ፡፡ ፊቱ በንዴት ጠቆረ፧ ደሙ በብስጭት ፈላ፤ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፣፣ ድምፁን አክርሮ «ክቡር ከንቲባ፤ ይህ ሊሆን አይችልም አለ፡፡

«ለምን?» ሲል መሴይ ማንደላይን ጠየቀ፡፡

«ይህች ባለጌ ሴት አንድን የከተማ ነዋሪ ተሳድባለች፤ አስቀይማለች
«ዣቬር» ሲል መሴይ ማንደላይን ረጋ ባለ መንፈስና በዝቅተኛ
ድምዕ መለሰ፡፡ «ስማኝ፤ አንተ እውነተኛ ሰው ስለሆንክ ጉዳዩን ባስረዳህ ቅር አይለኝም፡፡ እውነቱን ልንገርህ:: እንደአጋጣሚ በዚያ ሳልፍ አንተ ይህችን ሴት ይዘህ ስትመጣ አይቻለሁ:: ብዙ ሰው ስለተሰበሰበ አላየኸኝም።
አንተ ከሄድክ በኋላ ስለግርግሩ ሰዎችን ጠየቅሁ:: ሁሉንም ተረድቼአለሁ።ጥፋተኛው አንተ የምትለው የከተማው ነዋሪ ነው:: እርሱን ነበር ፖሊሶች መያዝ የነበረባቸው::»

ዣቬር መልስ ሰጠ፡፡

«ይህች ባለጌ ሴት ከንቲባውን ተሳድባለች፤ አስቀይማለች፡፡»
«ይህ እኔን ነው እንጂ አንተን አይመለከትም» አለ መሴ ማንደላይን፡፡
«ስድቡ የተሰነዘረው በእኔ ላይ ስለሆነ ስለስደቡ እኔው ራሴ የፈለግሁትን እርምጃ እወስዳለሁ::»
«ይቅርታ ያድርጉልኝ ጌታዬ፡፡ ስድቡ የተሰነዘረው በእርስዎ ላይ
ሳይሆን በመንበርዎ ላይ ነው:: ይህ ደግሞ መዳኘት አለበት፡፡
«ዣቬር» አለ ከንቲባው፤ «ትልቁ ዳኛ ሕሊና ነው:: ይህች ሴት
የተናገረችውን ሰምቻለሁ፡፡ የምሠራውን የማላውቅ አይመሰልህ!»
«ክቡር ከንቲባ፣ በእኔ በኩል ደግሞ አሁን የማየውንና የምሰማውን ኣላውቅም» አለ የፖሊሱ አዛዥ::
«እንግዲያውስ ትእዛዜን ተቀበል::»
«ግዳጄን ነው የምታዘዘው:: ግዳጄ ደግሞ ይህቺ ሴት ስድስት ወር እስር ቤት መቆየት እንዳለባት ይጠይቃል::
መሴይ ማንደላይን በእርጋታ የሚቀጥለውን ተናገረ፡፡
«ስማ፤ አንድ ቀን እንኳን አትታሰርም::»
«ክቡር ከንቲባ፣ ቢፈቀድ…»
«ሌላ ቃል አትናገር፡፡»
‹‹ሆኖም...»
«አቁም ብያለሁ» አለ መሴይ ማንደላይን፡፡ ዣቬር ቅስሙ ተሰበረ::
እንደ መስኮብ ወታደር ደረቱን ገልብጦ ጥቂት ከቆመ በኋላ ለከንቲባው እጅ ነስቶ ከቢሮው ወጥቶ ሄደ::
ፋንቲን ወደ በር ሄዳ አየችው:: ነገሩ ሁሉ ተመሰቃቀለባት:: የሁለቱን
ሰዎች ንግግር በኃፍረት ሰማች፡፡ መሴይ ማንደላይን የተናገረው እያንዳንዱ ቃል ልብዋ ውስጥ የተቀሰረውን ጥላቻ እያሟሟ ልብዋን አስከዳት::

የምትሰማውን ማመን አቃታት:: በጥላቻው ምትክ ልብዋ በቃላት ሊገለጽ በማይችል ደስታና ፍቅር ተሞላ፡፡

ዣቬር እንደ ሄደ መሴይ ማንደላይን ፊቱን ወደ ሴትዮዋ አዞሮ በዝግታ አናገራት::

«ያልሽውን ሰምቻለሁ:: አንቺ ስላልሻቸው አንዳንድ ነገሮች የማውቀው ነገር የለም:: ነገር ግን የተናገርሽውን አምናለሁ:: ከፋብሪካዬ ሥራ ለቅቀሽ
መውጣትሽንም እንኳን አላውቅም ነበር፡፡ ለምን መጥተሽ አላነጋገርሽኝም አሁን ግን ያለብሽን እዳ እኔ እከፍልልሻለሁ:: ልጅሽንም አስመጣልሻለሁ
ከፈለግሽ ደግሞ እንቺ ወደ እርስዋ ትሄጃለሽ፡: ብትፈልጊ ፓሪስ ወይ ልቦናሽ ከፈቀደው ቦታ መኖር ትችያለሽ:: አንቺንም ሆነ ልጅሽን እኔ እረዳችኋለሁ:: ሥራ መሥራት ካስጠላሽ ከዛሬ ጀምሮ ምንም ሥራ ባትሰሪ ትችያለሽ: ለመኖር የሚያስፈልጋችሁን ገንዘብ እኔ እሰጣችኋለሁ፡፡ "ግን ታማኝነትሽን እንዳታጠፊ:: ከዚህ ሁለ ይበልጥ ጆሮሽን አቅንተሽ እንድትሰሚኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር ካአሁን ቀደም በእግዚአብሔር ፊት
ንጽህናሽን ጠብቀሽ እንደኖርሽ ስለማልጠራዉር አሁንም ቢሆን ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ክፋትና ምቀኝነት የተለየው ኑሮሽን እንድትቀጥይ አደራ ነው የምልሽ፡፡ ምስኪኒትዋ፣ አይዞሽ፤ በርቺ:: ››

ምስኪንዋ ፋንቲን ለመሸከም ከምትችለው በላይ ሆነባት፡፡ ከልጅዋ። ከኮዜት ጋር አብሮ ለመኖር! ከዚያ አስነዋሪ ኑሮ መላቀቅ! የገንዘብ ችግር
ሳይኖር በደስታና በታማኝነት ከኮዚት ጋር መኖር! ይህ ሁሉ ያልታሰበ ኑሮ ሲታያት እንዴት ትመነው? «ወይኔ ወይኔ» ብሎ ከመጮህ በስተቀር ሌላ ነገር ለማለት አልቻለችም:: ሰውነትዋ ያንን ችሮታ፣ ያንን ደግነት
ለመሸከም አቅም አነሰው:: ሰውነትዋ ተዝለፈለፈ:: ከመሴይ ማንደላይ እግር ስር ወደቀች፡፡ ጎንበስ ብሉ ሊያነሳት ሲል እጁን አፈፍ አድርጋ ሳመችው::
ከዚያም ሕሊናዋን ሳተች::..

💫ይቀጥላል💫
9👍9
አትሮኖስ pinned «#ምንዱባን ፡ ፡ #ክፍል_አሰር ፡ ፡ #ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ የፋንቲን ታሪክ ምን ዓይነት ታሪክ ነው? ያሽከር ታሪክ! አሽከርን የሚገዛው ሕብረተሰቡ ነው? ከማን? ከችግር? ከመከራ? ከስቃይ? ከረሃብ? ከብቸኝነት? የሚቀፍ ግዢ ነፍስ በዳቦ ሲለወጥ! ችግር ግለሰቦች ያልፈቀዱትንና ያልፈለጉትን እንዲሠሩ ሲያስገድዳቸው! ሕብረተሰቡ ደግሞ በግዳጅ የሚያደርጉትን በደስታ ሲቀበል አይገርምም! ባርነት ቀርቷል…»
#የነፍስ_ክረምት!

ከርስ የጎደለ እንደው ይሞሉታል በህል፤
የበረደም ዕለት..ኮት ያኮቱበታል የቁሩን ልክ ያህል።

ጤዛውን በጫማ ፤
ውርጩን በስብ ሸማ፤
ሌቱን በትኩስ ራት ፤
ደመናውን በሣት፤
አጉል የሰፈረን ወዲያልኝ ይሉታል፤
አልባሌን አየር ፤ ጢስ ይከልሉታል፡፡

ሙቀት ስጡኝ ለሚል..
ለበረደው ገላ ፤ መጋጋል ላነሰው፤
መድኃኒቱን አውቋል ፥ የተቃቀፈ ሰው ።

ግና!
ነፍስ የበረደ ዕለት፥ ምን ቤት ይጠልላል??
ለቀዘቀዘስ ልብ ፥ ማን ኮት ልሁን ይላል??

🔘ፓፒረስ🔘
9👍7
#ምንዱባን


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ዣቬር

መሴይ ማንደላይን ከቤቱ ውስጥ የሕክምና እርዳታ የሚሰጥ ክፍል ስለነበረው ፋንቲንን ወደዚያ አስወሰዳት:: የሕክምና እርዳታ የሚሰጡ ሴሮች አልጋ ላይ አስተኝዋት:: በኃይል አተኩሳለች:: ሕሊናዋን ሳታውቅ እንዲሁ እየቃዠች ጥቂት እንደቆየች እንቅልፍ ይዞአት ጭልጥ አለ፡፡

በሚቀጥለው ቀን ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ከእንቅልፍዋ ነቃች
ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ አየች:: መሴይ ማንደላይን ጣራ ጣራውን እያየ ቆሞአል፡፡ ፊቱ በሀዘኔታ ተሞልቷል:: ከንቲባው ጣራውን ሳይሆን ግድግዳ
ላይ ከፍ ብሎ የተሰቀለወን መስቀል ነበር የሚያየው፡፡
ይህ ሰው መልአክ እንጂ ሰው አይመስላትም:: ሰውነቱ በብርሃን
የታነጸ መሰላት፡፡ መሴይ ማንደላይን እየጸለየ ስለነበር ጸሎቱን ላለማቋረጥ ሳትናገር ለረጅም ጊዜ አፍጥጣ አየችው:: በመጨረሻ ግን እየፈራች ቀስ
ብላ ተናገረች::

«ምን እየሠሩ ነው?»

መሴይ ማንደላይን ከዚህ ሥፍራ የፋንቲንን መንቃት እየተጠባበቀ
ለአንድ ሰዓት ያህል ቆሞአል፡፡ እጅዋን ይዞ የልብዋን አመታት ቆጠረ::
«አሁን ምን ይሰማሻል? ደህና ነሽ!»
«በጣም ደህና ነኝ:: እየበረታሁ ነኝ፤ እንቅልፍ ወሰደኝ» አለች ፋንቲን፡፡
«እንግዲያውስ ወደ ጥያቄሽ ልመለስና ምን ትሠራለህ ስላልሽው ስላንቺው ፈጣሪን በመማጠን ጸሎት እያደረስኩ ነበር፡፡»
ያን እለት ማታ ስለፋንቲን የሕይወት ታሪክ ሲጠይቅ አምሽቶ
በሚቀጥለው ቀን ያንኑ ቀጠለ፡፡ ምንም ነገር ሳይቀረው ስለፋንቲን ኑሮ ሁሉንም አወቀ፡፡
«ከመጠን በላይ ስቃይ ተቀብለሻል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ሀዘን አይግባሽ፡፡በዚህ ዓይነት ነው ሥጋ ለባሾች ወደ መስዋዕትነት የሚለወጡት:: ከዚህ
የተለየ መንገድ እንዳለው አላውቅም:: ይህ አንቺ ያለፍሽበት ምድራዊ ገሀነም ወደ መንግሥት ሰማይ የሚወስድ የመጀመሪያ እርምጃ ነው:: ከዚያ መጀመር ግዴታችን ነው::»
ይህን ካለ በኋላ መሴይ ማንደላይን በኃይል ተነፈሰ:: ፋንቲን ጥቂት ፈገግ ስትል ወላቃ ጥርስዋ ታየ::
መሴይ ማደላይን ወደ እነቴናድዬ ደብዳቤ ጻፈ፡፡ በደብዳቤው ፋንቲን
ያለባት እዳ አንድ መቶ ሃያ ፍራንክ እንደሆነ ገልጾ የላከላቸው ግን ሦስት መቶ ፍራንክ መሆኑን ይጠቅሳል፡፡ ብልጫ ገንዘብ የላከላቸው የፋንቲንን
ልጅ ይዘው ወዲያውኑ እንዲያመጡ ነበር:: የልጅትዋ እናት እንደታመመችና
ልጅዋን ለማየት እንደጓጓች ገልጾ ነበር ልጅትዋን ይዘው እንዲመጡ
የጠየቃቸው::
እነቴናድዬ ደብዳቤውና ገንዘቡ እንደደረሳቸው በጣም ተደነቁ::
«ሰይጣን» አለ ሚ/ር ቴናድዬ ለሚስቱ:: «ልጅትዋን አንሰጥም::
ምናልባት አንድ ቂል በውበትዋ ተማርኮ ይሆናል ይህን የመሰለ ደብዳቤ የሚጸፈው::»
ሰውየው ልጅትዋን በመላክ ፈንታ ሂሳቡን በጥንቃቄ አስልቶ ፋንቲን ያለባት እዳ አምስት መቶ ፍራንክ እንደሆነ ገልጾ የመልስ ደብዳቤ
ለመሴይ ማንደላይን ጻፈለት:: ተጨማሪው ሁለት መቶ ፍራንክ ልጅት በታመመች ጊዜ ለመድኃኒት የወጣ መሆኑን አስረድቶ ነበር የጻፈው።

መሴይ ማንደላይን ደብዳቤው እንደ ደረሰው ሦስት መቶ ፍራ
ላከላቸው:: ከገንዘበ ጋር ደግሞ በተቻለ ፍጥነት ኮዜትን ይዘው እንዲመ መልዕክት አከለበት፡፡
«በምንም መንገድ ልጅትዋን አንለቅም» አለ ማ/ር ቴናድዬ::
ፋንቲን በሽታዋ ጠናባት እንጂ ስላልተሻላት አልጋ ላይ ቆየች
መሴይ ማንደላይን በቀን ሁለት ጊዜ ይጠይቃታል፡፡ በጠይቃት
ቁጥር «ኮዜትን ቶሎ በዓይኔ የማያት ይመስሎታል?» ስትል ትጠይቀዋለች።
እርሱም ሲመልስ “ምናልባት ነገ! በማንኛውም ሰዓት ልትደርስ
ትችላለች» ይላታል፡፡
በዚህ ጊዜ የእናተዬዋ የገረጣ ፊት ወገግ ይላል::
«አዬ! እንዴት ደስ ባለኝ!» በማለት ትቆጫለች::
ሕመምዋ እያደር ጠናባት:: አንድ ቀን ሐኪሙ የሳምባዋን አተነፋፈስ
በማዳመጫ መሣሪያ ካዳመጠ በኋላ ራሱን ነቀነቀ::
«እየተሻላት ነው?» ሲል መሴይ ማንደላይን ጠየቀው::
«ዓይንዋን ለማየት የጓጓችላት ልጅ አላት አይደል!» አለ ዶክተሩ
«አዎን፡፡»
«እንግዲያውስ ቶሎ ብታስመጠላት ይሻላል፡፡»
መሴይ ማንደላይን በድንጋጤ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡
«ሐኪሙ ምን አለ?›› አለች ፋንቲን፡፡
መሳይ ማንደላይን ፊቱን ፈገግ ለማድረግ ሞከረ::
«ልጅሽን በቶሎ እንድናስመጣልሽና ይህም በሽታሽን ሊያቃል እንደሚችል ነው የነገረን» ካላት በኋላ ወደ ቢሮው ሄደ፡፡
መሴይ ማንደላይን ከቢሮው ውስጥ ቁጭ ብለ ሥራውን እየሰራ
ሳለ የፖሊስ አዛዥ ዣቬር ሊያነጋግረው እንደሚፈልግ ተገለጸለት።

«ይግባ! » አለ፡፡

ዣቬር ገባ፡፡
ለከንቲባው የአክብሮት ሰላምታ ሰጠ፡፡ ፊቱን ወደ መስኮት አዙሮ
ስለነበር ዣቬር ሲገባ የከንቲባውን ጀርባ ነው ያየው፡፡ መሴይ ማንደላይን ቀና ብሎ ሳያየው ወረቀት ማገላበጡን ቀጠለ፡፡

ዣቬር የክፍሉን ፀጥታ ሳያደፈርስ ቀስ ብሉ ወደፊት ተራመደ፡፡ ፊቱ
ላይ የቆራጥነት ብቻ ሳይሆን የድፍረትም ዓይን በግልጽ ይታያል፡፡ በመጨረሻ ከንቲባው ብዕሩን አስቀምጦ ቀና አለ፡፡
«ታዲያስ፣ ምንድነው ዣቬር? ምን አጋጠመህ?»
ዣቬር አሳቡን ለማሰባሰብ ብሎ ለአጭር ጊዜ ዝም አለ፡፡ ከዚያም
ድምፁን አለስልሶ ሀዘን በተሞላበት አንደበት «ክቡር ከንቲባ፤ አንድ ወንጀል ተሠርታል» አለ፡፡

«የምን ወንጀል?»
«አንድ ግለሰብ አንድን የመንግሥት ባለሥልጣን በስህተት ስለወነጀለ ራሱን ለማጋለጥ ይፈልጋል፡፡ እኔ ደግሞ አሁን የመጣሁት ሥራዬ
እንደመሆኑ መጠን ይህን ለማሳወቅ ነው::»
«ራሱን ለማጋለጥ የሚፈልገው ሰው ማነው?» ሲል መሴይ ማንደላይን ጠየቀው፡፡
«እኔ» አለ ዣቬር፡፡
«አንተ?»
«አዎን፤ እኔ!»
«ማንን በድለህ ነው ራስህን የምታጋልጠው?»
«ክቡርነትዎን፡፡»
መሴይ ማንደላይን ወንበሩን አስተካክሎ ተቀመጠ:: ዣቬር ሳይፈራ አሁንም በትህትና ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«ክቡር ከንቲባ ፧ እኔ አሁን እርስዎን የምጠይቀው ላደረስሁት በደል
ከስራ እንዲያሰናብቱኝና ክስ እንዲመሠርቱብኝ ነው:: »
መሴይ ማንደላይን በጣም ተደንቆ ለመናገር እፉን ከፈተ:: ዣቬር
ቀድሞ ተናገረ፡፡
ስራህን ብቻ ልቀቅ ይሉኝ ይሆናል:: ግን ይህ ብቻ አይበቃም:: በገዛ
ፈቃድማ ሥራ ተመልቀቅ መቻል ክበር ነው:: ጥፋት ስላጠፋሁና በደል ስለሠራሁ ለፍርድ ቀርቤ መቀጣት አለብኝ:: ከስራም መባረር ይኖርብኛል
«እንዴ! በምን ምክንያት?»
«ክቡር ከንቲባ ጉዳዩን ሲያውቁት ይህን ጥያቄ አይጠይቁኝም::
ነገሩ ሁሉ ይገባዎታል፡፡
ዣቬር በኃይል ተነፈሰ፡፡ ሀዘን እየተሰማውና እያፈረ ንግግሩን ቀጠለ
«ክቡር ከንቲባ ከስድስት ሳምንት በፊት ያቺን ሴት በነፃ ከለቀቅዋት
በኋላ በጣም ተናድጄ ከስሽዎት ነበር፡፡»
«እኔን ነው የከሰስከው?»
«አዎን፤ ፓሪስ ድረስ ሄጄ ለፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክሴን አቀረብኩ
ብዙ ጊዜ የማይስቀው መሴይ ማንደላይን ከት ብሎ ሳቀ::
«የፖሊስን ሥልጣን ተጋፋ ብለህ ነው የከሰስከኝ?»
«የለም፧ የጥንት ወንጀለኛ ናቸው ብዬ ነው የከሰስክዎት፡፡»
ከንቲባው ደንገጥ አለ። እንዳቀረቀረ የቀረው ዣቬር ንግግሩን ቀጠሉ
«አልተጠራጠርኩም ነበር፡፡ ለብዙ ጊዜ ጥርጣሬ ነበረኝ፡፡ መልካችሁ
👍18👎1🔥1
ቁመናችሁ፤ ጉልበታችሁ እና ሌላም ሌላም ነገራችሁ ሁሉ ፍጹም አንድ ስለሆነብኝ ዣን ቫልዣ ነዎት ብዬ ደመደምኩ፡፡»
«ማን አልክ? እንዴት ብለህ ነው ስሙን የጠራኸው?»
«ዣን ቫልዣ ፧ ከሃያ ዓመት በፊት የወህኒ ቤት ሹም በነበርኩበት
ጊዜ አንድ እስረኛ ነበር፡፡ ይህ ወንጀለኛ ከእስር ቤት ካመለጠ በኋላ የአንድ የተከበሩ ጳጳስ ንብረት ዘርፎአል፡፡ በዚህም አላበቃም፤ በመሣሪያ ኃይል
በማስፈራራት የሌላም ሰው ንብረት ሠርቋል:: ይህን ወንጀለኛ ለመያዝ ብዙ ፍለጋ ቢካሄድም ስምንት ዓመት መሉ የት እንዳለ ሳይታወቅ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ፡፡ ምን አለፋዎት ብቻ ያ ሰው እርስዎ እንደሆኑ ስላመንኩ
ለጠቅላይ ፖሊስ አዛዥ ጠቆምኩዎት::»
ዣቬር ንግግሩን ሲያበዛ ወረቀት ማገላበጥ የጀመረው መሳይ
ማንደላይን ረጋ ባለ አነጋገር «እና ምን ተባልክ?» ሲል ዤቬርን ጠየቀው።
«አበድክ እንዴ!» አሉኝ፡፡
«ከዚያስ!»
«ከዚያማ እነርሱ ልክ መሆናቸውን አወቅሁ::
«ጥሩ ገምተሃል፡፡»
«እነርሱ ልክ መሆን አለባቸው:: ምክንያቱም እውነተኛው ዣን
ቫልዣ ተገኝቷል፡፡»
መሴይ ማንደላይን የያዘው ወረቀት ከእጁ አምልጦት ወደቀ፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዣቬርን አተኩሮ ተመለከተው:: ለስለስ ባለ አንደበት «ተገኘ!»
አለው፡፡
ዣቬር ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«ክቡር ከንቲባ፣ ታሪኩ እንዲህ ነው:: ገጠር ውስጥ ሻምፕማትዩ
የሚባሉ አንድ የዋህና ደግ ካህን ነበሩ፡፡ እኚህ ካህን በጣም ድሃ ናቸው፡፡ የሚረዳቸው ሰው የላቸውም፡፡ እንደ እርሳቸው ያለ ምስኪን የእለት ተእለት
ኑሮ ምን እንደሚመስል ብዘም አይታወቅም፡፡ በመጨረሻ እኚህ
የቤተክርስቲያን ሰው ፍሬ ሰርቀው ይያዛሉ፡፡ ፍሬ መስረቃቸው ይህን
ያህልም የሚያስወነጅል አልነበረም፡፡ ፍሬ የያዙ ብዛት ያላቸው የፍራፍሬ ዛፎች ተቆርጠው ቅርንጫፎቻቸው በየመንገዱ ይበተናል፡፡ ይህም እንደ ከባድ ጥፋት ተቆጠረ፡፡ ካህኑ የተያዙት ተቀንጥሶው ከወደቁት ቅርንጫፎች
አንደኛው ከነፍራው በእጃቸው ስለተገኘ ነው:: በዚህ የተነሣ ነው ሌባ ተብለው የታሠሩት:: ይህ ጉዳይ ጥቂት ቀን የሚያሳስር እንጂ ብዙ የሚያስፈርድ አልነበረም፡፡ ግን እዚህ ላይ ነው የተፈጥሮ ኃይል ሥራውን
የሠራው:: አባታችን ሻምፕማትዩ የታሠሩበት እስር ቤት ስለጠበበ ወደ ሌላ እስር ቤት ይዛወራሉ፡፡ ከአዲሱ እስር ቤት ውስጥ ለብዙ ጊዜ የታሠረ ብራሼት የሚባል ሌላ እስረኛ ጥሩ ጠባይ በማሳየቱ የእስረኞች ተቆጣጣሪ ሆኖ ይሾማል፡፡ ይህ ሰው ካህኑን ገና ሲያያቸው 'ወንጀለኛውን አገኘሁት ፤ወንጀለኛውን አገኘሁት እያለ ይጮሃል፡፡»

«ጌታው ወደዚህ ይመልከቱ! ዣን ቫልዣ አይደሉም?» ሲል
ጠየቃቸው::
«ዣን ቫልዣ! ማነው እሱ?» በማለት በመደነቅ ሰውዬውን ላማታለል ይሞክራሉ::
«እንዳላወቀ መሆን አይሞክሩ» ይላል ብሪቬት:: ዣን ቫልዣ ማለት
እርስዎ ነዎት፡፡ ከዛሬ ሃያ ዓመት በፊት ቱሉን ከሚገኝ እስር ቤት እስረኛ ነበሩ። ከእዚያ አብረን ነበርን::»
«አባታችን ሻምፕማትዩ ጨርሰው ካዱ:: ስለጉዳዩ ብዙ ምርመራና
ክትትል ተደረገ፡፡ ሰተደረገው ክትትል የዣን ቫልዣ ቤተሰቦች ከሰላሣ ዓመት በፊት የት እንደነበሩ ተደረሰበት:: ሆኖም ቤተሰቦቹ ያን ጊዜ ከነበሩበት
አልተገኙም:: የት እንደሄዱ ደግሞ ማንም ሊጠቁም አልቻለም:: ጊዘው በጣም ስለቆየ ዣን ቫልዣንም ለይቶ የሚያውቅ ሰው ጠፋ፡፡ ሆኖም ፍለጋው ቀጠለ፡፡ ከብሪቬት ሌላ ዣን ቫልዣን የሚያውቁ ሌሎች ሁለት
እስረኞች አሉ፡፡ ሁለቱም የእድሜ ልክ እሥራት የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ናቸው:: ስማቸውም ኮሸልና ቬኔልድዩ ይባላሉ፡፡ እስረኞቹ ካሉበት እንዲመጡ ተደርጎ አዩዋቸው:: ገና ሲያዩዋቸው ምንም አልተጠራጠሩም:: እነርሱም ሆነ ብሪቬት ሰውዬው ዣን ቫልዣ እንደሆኑ አረጋገጡ፡፡ እንደ
ዣን ቫልዣ እድሜያቸው 54 ሲሆን ቁመታቸውና መልካቸውም ካዣን
ቫልዣ ጋር አንድ ሆኖ ተገኘ፡፡ ይህ እውነት ከተደበቀበት የወጣው ልክ እኔ እርስዎ ዣን ቫልዣ እንደሆኑ ክስ በመሠረትኩበት ጊዜ ሲሆን ኣብደሃል ወይ! ዣን ቫልዣ እኮ አራስ ከተባለ እስር ቤት ተገኝቶ አሁን ለፍርድ ሊቀርብ ነው' ሲሉ አባረሩኝ፡፡ ምን ያህል እንደደነገጥኩና እንዳፈርኩ ሊገምቱ ይችላሉ፡፡ ይህን ዜና እንደሰማሁ ሰውዬውን አምጡና አሳዩኝ ስል ጠየቅሁ::
አምጥተው አሳዩኝ፡፡»
«ከዚያስ!» በማለት መሴይ ማንደላይን ጣልቃ ገባ፡፡
ዣቬር ሳይወላወል ሀዘን እየተሰማው ምላሹን ሰጠ፡፡
«ክቡር ከንቲባ፣ እውነት ነው:: እውነት ነው:: ስለፈጸምኩት ስህተት አዝናለሁ:: ሻምፕማትዩ ነኝ ያሉት ሰው በእርግጥ ን ዣል ቫልዣ ሆነው ነው ያገኘኋቸው::»
«እርግጠኛ ነህ?»
ዣቬር የፌዝ ሳቅ ሳቀ፡፡

«እርግጠኛ ነህ!» አለ ሰውዬው:: «የምትሉት ነገር አይገባኝም:: እኔ
ሻምፕማትዩ እንጂ ዣን ቫልዣ ኣይደለሁም አለ»::
«በጣም ጮሌ ሰው ነው:: ግን አራት ሰው ስለመሰከረበት ዋሽቶ
ሊያመልጥ አይችልም፡፡ ተገቢውን ቅጣት ይቀበላል፡፡ እኔም የምስክርነት ቃሌን ከሕግ ፊት እንድሰጥ ስለተጠራሁ ወደዚያ እሄዳለሁ፡፡»
መሴይ ማንደላይን ወደ መሬት አቀረቀረ:: ፀጥ ብሎ ጠረጴዛው ላይ ከነበሩ ወረቀቶች ላይ አፈጠጠ፡፡ ሥራ እንደበዛበት ሰው አንዴ ይጽፋል፧ ወረቀቶችን ያገላብጣል፡፡ ወደ ቬር ዞር አለ፡፡
«ይበቃናላ ዣቬር! የነገርከኝ ታሪክ ብዙም አላስደሰተኝም:: አስቸኳይ
የሆኑ ነገሮች ስላሉብኝ ከዚህ ይበልጥ ጊዜ ሳናጠፋ! ለመሆኑ ወደ አራስ እስር ቤት መቼ ነው የምትሄደው?»
«ቶሎ ሳልሄድ አልቀርም::»
«ከስንት ቀን በኋላ?»
«ሰውዬው ነገ ለፍርድ ይቀርባል፡፡ ስለዚህ ዛሬ ማታ መንገድ
እጀምራለሁ ብያለሁ፡፡»
«ቶሎ የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥ ይመስልሃል?»
«ሌላ ቀጠሮ የሚሰጥ አይመስለኝም:: ግን እኔ የፍርድ ውሳኔ እስኪሰጥ አልጠብቅም፡፡ የምስክርነት ቃሌን ሰጥቼ እንደጨረስኩ እመለሳለሁ፡፡»

መሴይ ማንደላይን «መልካም» ካለ በኋላ ዣቬር እጅ በመንሳት
አሰናበተው::

ዣቬር ግን ከቢሮው አልወጣም::

«ክቡርነትዎን በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ» አለ ዣቬር፡፡

«ከዚህ በላይ ምን ያስፈልጋል? እኔ እንደሆነ ትቼዋለሁ» አለ መሴይ ማንደላይን፡፡

«ክቡር ከንቲባ፣ የጠየቅክዎትን እንዲያስቡበት፡፡»

«ምንድነው እሱ?»

«ከሥራ እንዲያሰናብቱኝ ነዋ!»
«ዣቬር፣ መከበር ያለብህ ሰው መሆንህን አምናለሁ:: ስህተትህን
ከሚገባው በላይ ኣጉላኸው:: የተበደልኩት እኔ ስለሆንኩ ይህን ያህል ከቁም ነገር አላስገባሁትም:: ከሥራ መባረርን በተመለከተ ከሥራ መባረርህ ቀርቶ እድገት የሚገባህ ስለሆነ በሥራህ ላይ እንድትቆይ ነው የምፈልገው::»

ዣቬር መሴይ ማንደላይንን በጥሞና እየተመለከተ፡-

«ክቡር ከንቲባ፣ ይህ ሊሆን አይችልም:: በሌላው ሰው ላይ የማደርገው ነገር በእኔም ላይ መፈጸም አለበት:: 'ማንኛውንም የኅብረተሰብ አባልን የበደለ ግለሰብ ያለ ርህራሄ ከአለበት ፈልፍዬ በማውጣት ለፍርድ አቀርባለሁ እያልኩ ለራሴ ዘወትር ቃል ገብቻለሁ:: አሁን እኔ ራሴ ሌላውን ሰው በድያለሁና መታለፍ የለብኝም:: ስለዚህ ሥራዬን መልቀቅ ይኖርብኛል።እጆች ስላሉኝ የትም ሠርቼ አድራለሁ:: ግብርና ብገባም ይሆናል። ለሌሎች ሰዎች ደግሞ ምሳሌ መሆን አለብኝ:: ስለዚህ አሁንም ከሥራ እንዲያባርሩኝ በድጋሚ እጠይቃለሁ::
👍13🥰2
«እናያለና» ካለ በኋላ መሴይ ማንደላይን ሊጨብጠው እጁን ዘረጋለት::
ዣቬር ከቢሮ ለመውጣት ወደኋላ እያፈገፈገ፡ይቅርታ ክቡር ከንቲባ፤ እጅዎን መጨበጥ የለብኝም:: እንድ ከንቲባ አንድን ተራ ሰው መጨበጥ የለበትም:: ተራ ሰው ፤ አዎን ተራ ሰው፤ ሥልጣኔን መከታ በማድረግ የሠራሁት ሥራ አንድ ተራ ሰላይ ከሚፈጽመው
ተግባር የተለየ አይደለም» ካለ በኋላ ለጥ ብሉ እጅ ነስቶ ከቢሮው
ለመውጣት ወደ በሩ ኣመራ:: በሩን ከፍቶ ሲወጣም አንገቱን እንደሰበረ ነበር፡፡

«ክቡር ከንቲባ፣ የሥራ ስንብት እስከተሰጠኝ ድረስ ሥራዬን
እቀጥላለሁ፡፡»

በሩን ይዞ ይህን ከተናገረ በኋላ ወጥቶ ሄደ፡፡ መሴይ ማንደሳይን
በጣም ተክዞ ቁጭ አለ፡፡ የዣቬርን ውትወታ በመገረም ነበር ያደመጠው....

💫ይቀጥላል💫
👍87👏1