#የኔ_ዓለሞ!
አብረሽኝ እያለሽ...
አገኝሽ ነበረ ፤ እግሬ እንደቋመጠ፤
ስትለዬኝ ግና...
አካሌ በሙሉ ፣ ክንፍ አቆጠቆጠ፤
ለምን?
መብረር እንደሳተ አክናፍ
አንቺ ሆነሽብኝ ፣ የጉዚዬ አጽናፍ
ተፈጥሮን አወቀ ፤ የተሰጠን አክናፍ። -
(እንደታወረ ወፍ)
እከንፍልሻለሁ፤
እነፍስልሻለሁ፤
የቱ ጋር ቆመሻል? ልምጣልሽ እላለሁ።
ክንፍ ክንፍንፍ
ነፋስን መሰንጠቅ ፤ በመሄድ መደምደም፤
ቀሪ መንገድ ሕልሜን ፣ካንቺ ለመካደም።
አላውቀውምና፣
አይገባኝምና ፣ያንቺ መዳረሻስ፣
እኔ ልብ የለኝም
አጠገብሽ ቆሜሞ ፣ አጠገብሽ ልሆን
እነሳለሁ ጭራሽ።
(ለየልኝ ማለት ነው።)
ማለትም...
ማለት የምችለው...
የክንፋም ልብ ወዳጅ ፣ ነፋስን ማርገብገብ፤
በነፋስ መንገብገብ፤
ነፋስን መጠርጠር፤ ነፋስን መመገብ፤
ከንፋስ መጓተት ፤ ከነፋስ መሳሳብ፤
እሷ ነች አያሉ፣ ከነፋስ መሣሣም፤
እነፍስልሻለሁ!
ባየር ፣በብርሃን ፣በጨለማ መብረር፤
አንቺ ጋር እንደቆምኩ ፣ ክንፊን አጥፍ ጀመር።
ደረስኩኝ ማለት ነው!
ማለትም
የክንፋሞ ቀልብ ጦስ ፣ መርግፊያ ሞኝነት፣
መሄጃ ሰበብ ጋር ፣ በቶሎ መገኘት።
ዓለሜ...
መጓዝ ዳራ ኖሮት ፣ካስረገፈ ላባ፣
ማማር መርገም ሆኖ ፣ካስነቀለ አበባ፣
መድረስ ከመገኘት ፣ ከእቅፍሽ ቢያሞቀኝ፣
መፈለግ ደስታዬ ፣ ሳገኝሽ ራቀኝ።
መሄዴን ብውደው...
በቆይልኝ ብዬ ፣ ክንፊ መቼ ደክሞት፣
እጸልይ ጀመረ
ስቀርብሽ ሂጂልኝ ፣ ሳገኝሽ እንዳልሞት።
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
አብረሽኝ እያለሽ...
አገኝሽ ነበረ ፤ እግሬ እንደቋመጠ፤
ስትለዬኝ ግና...
አካሌ በሙሉ ፣ ክንፍ አቆጠቆጠ፤
ለምን?
መብረር እንደሳተ አክናፍ
አንቺ ሆነሽብኝ ፣ የጉዚዬ አጽናፍ
ተፈጥሮን አወቀ ፤ የተሰጠን አክናፍ። -
(እንደታወረ ወፍ)
እከንፍልሻለሁ፤
እነፍስልሻለሁ፤
የቱ ጋር ቆመሻል? ልምጣልሽ እላለሁ።
ክንፍ ክንፍንፍ
ነፋስን መሰንጠቅ ፤ በመሄድ መደምደም፤
ቀሪ መንገድ ሕልሜን ፣ካንቺ ለመካደም።
አላውቀውምና፣
አይገባኝምና ፣ያንቺ መዳረሻስ፣
እኔ ልብ የለኝም
አጠገብሽ ቆሜሞ ፣ አጠገብሽ ልሆን
እነሳለሁ ጭራሽ።
(ለየልኝ ማለት ነው።)
ማለትም...
ማለት የምችለው...
የክንፋም ልብ ወዳጅ ፣ ነፋስን ማርገብገብ፤
በነፋስ መንገብገብ፤
ነፋስን መጠርጠር፤ ነፋስን መመገብ፤
ከንፋስ መጓተት ፤ ከነፋስ መሳሳብ፤
እሷ ነች አያሉ፣ ከነፋስ መሣሣም፤
እነፍስልሻለሁ!
ባየር ፣በብርሃን ፣በጨለማ መብረር፤
አንቺ ጋር እንደቆምኩ ፣ ክንፊን አጥፍ ጀመር።
ደረስኩኝ ማለት ነው!
ማለትም
የክንፋሞ ቀልብ ጦስ ፣ መርግፊያ ሞኝነት፣
መሄጃ ሰበብ ጋር ፣ በቶሎ መገኘት።
ዓለሜ...
መጓዝ ዳራ ኖሮት ፣ካስረገፈ ላባ፣
ማማር መርገም ሆኖ ፣ካስነቀለ አበባ፣
መድረስ ከመገኘት ፣ ከእቅፍሽ ቢያሞቀኝ፣
መፈለግ ደስታዬ ፣ ሳገኝሽ ራቀኝ።
መሄዴን ብውደው...
በቆይልኝ ብዬ ፣ ክንፊ መቼ ደክሞት፣
እጸልይ ጀመረ
ስቀርብሽ ሂጂልኝ ፣ ሳገኝሽ እንዳልሞት።
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍13👏4