አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ችርስ...
አንጀታችን ቢርስ!
እኔና ፈጣሪን ፣ውድድር ሲቃጣን፣
ላለመስከር ማልን፤ወይን እየጠጣን፡፡
ወይን
እያጋጨን፤
ነገር
እየፈጨን፤
ጨዋታ…ጀመርን፤
(አቦ ተባባል)
ስለ ሙሴ ታቦት፤
ስለ ዳዊት መሞት፤
ስለ እየሱስ ታምር
ስለበተነው ፣ከንቱ ሠላሳ ብር፤
ስለ ቤተሳይዳ..
እግዜር ወይን ቀዳ!
ስለቤታሳይዳ፤
ስለብሽቅ ይሁዳ፤
ስለዘማዊት ሴት፤
ስለ ፍጥሞ ደሴት፤
አወጋኝ፤
ስለ ሰው ሰውነት፤
ስለድብብቆሽ ፣ ስለጉራንጉሩ፧
ደርቶ ክርክሩ፤
ከቁዘማ ድሪያ ፣ከሐዘን ተሪክቦ፣
በወይን ተከቦ።
ደገምን፤
ደጋገምን፣
ወይን ሌላ ቀዳን፤
ጨለጥን፤
ቀለጥን፤
በወይን ሮጥን።
ሰው ግን ፤ሞቅ እያለው፣
እግዜር ባለበት ነው።
"ሙላው” እስቲ ቢልም፣
ንቅንቅ እንኳ አይልም።
የሰውን ግፍ ሁሉ እየተረኩበት፣
ካላንገዳገደው ፣ ሁሉን ቻዩን ጉልበት፣
እውነትም ጽኑ ነው ፤ብርቱ ለዘላለሞ፤
አትስከሩ ያለው ፣ ቢሰክር አይደለም፤
እያልኩ..
እየበገንኩ፤
የቀረው ወይን ፣ ልቀዳ እያነሣው፣
ከራድዮን ስለው ፣ ጠርሙሱን አነሣው፤
ነደደ፤
እጁን ጨመደደ፤
ሃ ሃ ሃ ሃ
እግዜር ተናደደ።
በነገራችን ላይ (ከራድዮን! ማለት ለኔ
የዘላለም ስለት፤
የልቤ ሐቅ፤
የነፍሴ ሳቅ፤
እምነቴ፤
ክህደቴ፤
ክስተቴ፤
ክፍተቴ፤
ስሕተቴ፤
የአንድ ወቅት ሕይወቴ፤
የሁል ቀን ሞቴ፤
ናት...
እና...
“ከሪደዮን” ብዬ ፣ ልክ እንደቀጠልኩኝ፣
ሰውነቴ ጠፋ ፣ አምላኬን አከልኩኝ።
ስላንቺ ሳነሣ፣
አብሾው ተነሣ፤
ንዴትና ዕንባ ፣ ቀልቡን ቢያወያየው፣
እግዜር አለ "ወየው!"
“እምቢየው፧"
"አልፈልግም" አለ! በእጄ እንደያዝኩት
ወይኑን ፣ ወሬውን ፣ መልሼ ጠየኩት፤
ዝሞ አለ...ዐሰበ!
ኹለቱሞ ግሪ ነው ፤ አንቺን ስላሰበ።
እወድሽ ነበረ!
ነገርኩት...ዝም አለ፤
እስምሽ ነበረ!
አሁንሞ..ዝም አለ፤
መልክሽ ከስሞ በላይ፤
ስሞሽ ከቃል ሰማይ፤
ልቤ መረገጫሽ፤
የምወደው ሣቅሽ ፣ ወደምድር መሞጫሽ፤
የከንፈሯ ወዙ ፣ ስትስመኝ እንጃልኝ
እግዜር ተናደደ ..."አዚጋ ቅዳልኝ፤”
አለልኝ
ስላንቺ ብመክረው
ስላንቺ ብነክረው፣
ስላንቺ ብነግረው፣
ቅናት አሰከረው፤
እንግዲህ እግዚሐር.. እግዚሐር ይኸነው።


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍157🔥1👏1