አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያመት_በአል_ማግስት_ትእይንቶች!!

- የተመጠጠ ቤት
የሞላ ሽንትቤት
ጭር ያለ ቤተሰብ
የተጠረገ ድስት -ድርቅ የመታው ሞሰብ!!
-ያደፈ ቄጤማ
በበግ በሰው እግር- የተደቀደቀ
ወዙ ባንድ ሌሊት -ተመጦ ያለቀ
መጥረጊያ ሚጠብቅ -ወድቆ ተበታትኖ
ትናንት ጌጥ የነበር- ዛሬ ጉድፍ ሆኖ!!
-የተወቀጠ ፊት -የነጋበት ድንገት
በዳንኪራ ብዛት-ወለም ያለው አንገት
የዞረበት ናላ -ጌሾ ያበከተው
እንኳንስ መገንዘብ -መጀዘብ ያቃተው
የወለቀ ወገብ -የዛለ ትከሻ
መኪና ይመስል -ብየዳ የሚሻ
-የጠጅና የጢስ- ድብልቅ እስትንፋስ
ከሆድ ሸለቆ ውስጥ -የታፈነ ነፋስ
ባንጀት የታሰረው
እንደተከበበ አመፀኛ ሽፍታ
መውጫ የቸገረው!
-የማይፈካ ሰማይ -የማይዘንብ ደመና
በላባና በፈርስ -ያደፈ ጎዳና
በበግ ራስ ምላስ -የተልከሰከሰ
የጠገበ ውሻ-
በመንፈቅ አንድ ጊዜ አጥንት የቀመሰ::
ሀንጎቨር ያዛገው-መሂና አሽከርካሪ
እግረኛ አስደንባሪ
በከፊል የነቃ -በከፊል የተኛ
ከሱ የማይሻል- የመኪና እረኛ
ካውራ ጎዳናው ዳር -ቁሞ ሚያንቀላፋ
ድብርትን ባናቱ -እንደ ቆብ የደፋ!!
The moral of the story :
የተድላ ማገዶ!!
ላጭር ጊዜ ነዶ
ላጭር ጊዜ ደምቆ
ላጭር ጊዜ ሙቆ
አመዱ ብዙ ነው: አያልቅም ተዝቆ!!

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#የመጀመሪያዋ_ግብዣ

ምድርም ሰማይም ባዶ እንደነበሩ ነው ድሮ ! …እና ባዶው ምድር ላይ …እግዚአብሔር ሳር ነሽ ቅጠል ነሽ ውሃ ነሽ ፀሃይ ነሽ እንደጉድ ፈጠረው ….
በግ ነሽ... ዶሮ ነሽ... በሬ ነሽ... ዳይኖሰር ነሽ …..ፈጠረ ፈጠረና ከዳር እስከ ዳር አየት አድርጎ ሲያበቃ ‹‹ፓ መልካም ነው ›› አለ ! ከዙፋኑ በታላቅ ግርማ ሞገስ ተነስቶ ወደፈጠረው ምድር እጁን ዘረጋ …..እናም ትኩሱን አፈር ቆንጠር አድርጎ ትንፋሹን እፍ ቢልበት ሰው ሁኖ እርፍ ! ያውም አዳምን የመሰለ ጎምላላ ትካሻ ከባድ ሰው !!
‹‹ ያውልህ በተዘጋጀ ምድር ላይ ዘና ብለህ ኑር ….›› አለው #አዳምን
ምን ዋጋ አለው አዳም ነጭናጫ ነበር ….እግዜር ብቅ ብሎ ‹‹ እንዴት ነው ኑሮ›› ሲለው
አዳም ይነጫነጫል ‹‹ ምን ኑሮ ……… ሳር ቅጠል ውሃ …ተራራ.. ሸንተረር ጫካ ዝሆን ዳይኖሰር ወፍ ወንዝ ዥረት ይሄ ሁሉ ኮተት ገና በፈጠርከኝ በሳምንቱ ደበረኝ ›› …..
‹‹ ጥሩ ! ምን ልፍጠርልህ ታዲያ ›› አለ እግዚአብሔር የሆዱን በሆዱ ይዞ ….መቸስ የሚጠቅመንን ነገር ቢያውቀውም ሰዎችን መጠየቅ ልማዱ ነው መሻታችን በፈቃዳችን ይሆን ዘንድ ይፈልጋልና
‹‹ እኔ ምን አውቄ ብትችል እንደገና ወደአፈር ብትመልሰኝ ›› ሲል አዳም ተነጫነጨ ተማረረ ….የአዳም መነጫነጭ መነሻው የእናት ፍቅር አለማውቁ የእናት ጡት ወተትም ሳይጠባ ማደጉ እደሆነ ይጠረጠራል …
እና እግዚአብሔር ሄዋንን አሰበ …አሰበ ማለት ያው ፈጠረ ነው ….ሒዋን ሁለት ተልእኮ ነበራት አንድም እናት ለሌለው የቲም ወንድ የእናት ፍቅር መስጠት …ሁለትም ሚስት ሁና አዳምን በስጋም በነፍስም ሙሉ ማድረግ ….ለዛ እኮ ነው በእያንዳንዷ ባፈቀርናት ሴት ውስጥ ትንሽ እናትነት ትንሽ እህትነት ብዙ ሚስትነት ተቀላቅሎ የሚገኘው ….ለዛ እኮ ነው የሴቶች እቅፍ የሴቶች ጠረን የሴቶች ድምፅ እና አብሮነት ከባድ ምቾት ውስጥ የሚሞጅረን !
ፍቅረኛችን ፍቅረኛ ብቻ ስትሆንኮ ትደብረናለች …እናት ብቻም ስትሆን ምቾት ነው የሚነሳን ….ቅመማ ቅመሙ እናትነት እህትነትና ሚስትነት አብሮ ሲቀመም ነው ደገፍ የምንላት ምቹ የነፍስ አጋር በነብሳችን ራስጌ ትራስ መከዳ ሁና በምቾት ቀና የምታደርገን …. ወንዶች ብዙ ጊዜ በፍቅር ትንታ የሚሞቱት ይህን ትራሳቸውን እያጡ እኮ ነው …. ይችን ያልተቀመመች ሴት እየተደገፉ ….አቤት ስትጎረባብጥ ….ከማይመች ፍቅር በኋላ ማጅራትህን ነው ስትራፖ የሚጨመድድህ …. ለምን መሰል ታዲያ ወንዶች ሴት ባዩ ቁጥር ወዳኋላ ወደጎን አንገታቸውን የሚያዞሩት …..ያሉበት ትራስ አልመች ቢላቸው ነው ወይም የተሸለ ትራስ ፍለጋ ……
(ሴቶች #የሚያሙን ሌላ ነው የአይን አመል ምናምን ነው ይላሉ ) እንግዲህ ሴትን ከአዳም ጎን አጥንት ሰራና ሲቀምማት ትንሽ እናትነት ትንሽ እህትነት በዛ ያለ ሚስትነት ለከለር ደግሞ ትንሽ ጓደኝነት ነስነስ አደረገባት ….በቃ ሴት ሆነች ኬክ የሆነች ሴት …!!
ሰነባብቶ እግዜር አዳምን ጠራና ‹‹ እህ እንዴት ነው ሂወት ? ›› ሲለው
‹‹ ኧረ ተወኝ ! አሁን ገና ገነትን ሙሉ አደረካት ›› ብሎ እግዜርን በሳቅ ሊገለው (ያው ድሮ አዳምና እግዚአብሄር እንዲህ ነበር በወዳጅነት የሚያወሩት ) እንግዲህ ሂዋን አዳም ጋር ወዲያ ወዲህ እያለች ስለወደፊቱ ብቻ እያወሩ(ያው ኑሮን ከመሃል ስለጀመሩት ትዝታ አልነበራቸውም ) በደስታ ፍንክንክ ብላ ስትኖር አንድ ቀን እንዲሁ ብቻዋን ወደጫካው ጎራ አለች …
እባብ እያፏጨ ቁሞ ነበር …ሂዋንን ሲያያት እንዲህ አላት

‹‹ ሃይ ቆንጅት እዚህ ሰፈር ነሽ እንዴ ? ››
‹‹ አዎ አንተስ ?››
‹‹ እኔም እዚሁ ነኝ …አንችን የመሰልሽ ቆንጆ ግን እንዴት እዚህ ጫካ ውስጥ ያስቀምጥሻል ….. ? እኔ እንዳንቺ አማላይና ውብ እግሮች ቢኖረኝ ኖሮ የት በደረስኩ››
ሂዋን ለመጀመሪያ ጊዜ አካባቢዋን ቃኘችው የተሸለ ሰፈር ይኖር ይሆን እንዴ ብላ ነፍሷን አባነነችው …..በዛ ላይ አዳም ራሱ ‹‹ቆንጆ›› አያውቅም ‹‹ውብ እግሮች እንዳላት›› ዛሬ ገና መስማቷ ነው …. እግሮቿን አየቻቸው ሂጅ ሂጅ አላት …. አድናቆቱ ጣማት ! በዛ ላይ አክብሮቱ ….መፅሃፉ ‹‹እባብ እግዜር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ተንኮለኛው ነበር ›› ሲል ሄዋን
‹‹ ግን ምናይነት ፀዳ ያለ ለሴት ልጅ አክብሮት ያለው ፍጥረት ነው ›› ስትል አሰበች!
‹‹ እስኪ ሳር ቅጠል እንበል የኔ ቆንጆ ›› አላት እባብ …ያኔ ሳር ቅጠል እንበል ማለት በአሁኑ ቋንቋ ‹‹ሻይ ቡና እንበል›› እንደማለት ነው…እናም ሴት ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብዣ የተጋበዘችው የዛን ጊዜ ነው ….(ከዛ ጊዜ ጀምሮ ሴቶች ሻይ ቡና እንበል በሚል ግብዣ ከሻይ ቡና አልፈው ሌላ ታሪክ ውስጥ መግባት እንደጀመሩ የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ)
እንግዲህ ሂዋን በእባብ ተጋብዛ ግብዣው መዘዝ መዘዘና አዳምንም ይዞት ዘጭ አለ
‹‹ አዱሻ የማውቃት ዛፍ አለች አሪፍ ነገር ልጋብዝህ ›› አለችው ተከትሎ ሂዶ እጣ ፋንታውን ገመጠ ! በሰውኛ ሂሳብ ስናየው በሰው ልጅ ታሪክ ወንድን ለመጀመሪያ ጊዜ የጋበዘችው ደግሞ ሄዋን ናት(ግብዣ ድሮ ቀረ… የዛሬ ሴቶች በናታቸው አልወጡም ግብዣ ላይ ሂሂሂ )
አዳም ፍሬውን ሲበላ መብላትን መሰረት ያደረጉ ሁለት ርግማኖችን ተረገመ
‹‹አዳም›› አለው እግዜር
‹‹ አቤት ›› አለ እየፈራ
‹‹ግረህ ጥረህ ብላ …(ሄዋንን ግን በምግብ ጉዳይ አረገማትም ምናልባት በግብዣ እንድትኖር ሳይሆን አይቀርም የሚሉ አሉ)
ሁለተኛው እርግማንም ያው መብላት ጋር የተያያዘ ነው ……
‹‹ አዳም ቅድም ግረህ ጥረህ ብላ ብየሃለሁ አይደል ….?.››
‹‹አዎ ›› አለ ምን ሊለኝ ነው ብሎ በጉጉት እየጠበቀ ‹‹ አሁን ደግሞ እለሃለሁ …… አፈር ብላ ›› በቃ ትሞታለህ እንደማለት !
አዳም ግሮ ጥሮ ሲበላ ሄዋንን ግሮ ጥሮ ሲጋብዝ ይሄው እስካሁንም ሴትን መጋበዝ የአዳም
‹‹ሆቢ ›› ሁኖ ቀረ አፈር እስኪበላ ይጋብዛል ….በነገራችን ላይ ፊትህ የቆመ የተራበ ሚስኪን ሽ ጊዜ እጁን እየዘረጋ ምፅዋት ሲለምንህ እንዳላየህ አልፈህ ….. አንዷን ሴት ለምነህ ‹‹አፈር ስሆን›› ብለህ የምትጋብዘው ለምን ይመስለሃል ….እንደውም ግብዣ የተጀመረው ሴት ልጅ ከተቀመመችበት ቅመሞች አንዱን እናትነትን ከጣለችው በኋላ ነው …. አንተ የጎደለ ሆድ ፒዛ በርገር ቦንቦሊኖ ትጋብዛለህ የጎደለ መንፈስ ዘላለም ያዛጋል ! ለዛ እኮ ነው እናትነት የሚባለው ቅመም በተለይ ከተሜው ሴት ላይ ድራሹ የጠፋው ….እናት ሁልጊዜም ምን አንደምታደርግልህ እንጅ ምን እንደምታደርግላት አታስብም …ብታደርግላትም ፍቅሯ አይጨምርም ባታደርግላትም ፍቅሯ አይቀንስም … ዋናው ቅመም ሲከሽፍ ከቦንቦሊኖ ጋባዥ አንተ ፒዛ ጋባዥ እሱ የፍቅር ሃዋሪያ ተደርጎ በሚስትህ አይን ሲቀማጠል ብታይ እንዳይገርምህ !
እና በ ‹‹ግረህ ጥረህ ብላ›› እና ‹‹ በአፈር ብላ›› መሃል ….ኑሮ የሚባል ሂደት ተዘረጋ …..አዳም ሆድ እንዳይብሰው የተቀማትን ዘላለም ያስታውሳት ዘንድ በቀናት መካከል …በልፋቶች መሃል አንዲት አጭር ዘላለም….. አንዲት ቅልብጭ ያለች ረፍት አስቀመጠለት
….አዳም ታዲያ ለውዱ እንዲህ ይላታል
‹‹ ውዴ ነይ ልጋብዝሽ ….የእናትነት …የእህትነት የሚስትነት ቅመሞችሽን ይዘሽልኝ ነይ …………ነይ
ነ……..ይ ውዴ በአጭር ዘላለማችን አጭር ገነትን በነፍሳችን ጊዮን ዳርቻ ላይ እንመስርት …. !!
👍2🤔2
#ቲቸር_ጥጋቡ

አበበ በሶ በላ ….ጫላ ጩቤ ጨበጠ …ቲቸር ጥጋቡ …… ››
የአስራ ሁለተኛ ክፍል ስፖርት አስተማሪያችን ጋሽ ጥጋቡ እንደዛን ቀን ተበሳጭቶ አይተነው አናውቅም ! ሁልጊዜ ሰኞ በመጀመሪያው?ቨ ክፍለጊዜ ‹‹ስፖርት ›› ነበር የምንማረው ! ታዲያ ወንዶቹ ሁላችንም ደስተኞች ነበርን ! ሴቶቹ ግን ክላሱን አየወዱትም ! ምክንያቱም ቅዳሜና እሁድ ፀጉራቸውን ተተኩሰው ጥፍራቸውን በጥፍር ቀለም አስውበው ‹‹ዩኒፎርማቸውን›› አጥበውና ተኩሰው ሰኞ አበባ መስለው የሚመጡት ሴቶች እዛ ሜዳ ላይ ‹‹ተኙ ተንከባለሉ ሩጡ ዝለሉ ›› ሲባሉ ውለው ፀጉራቸው ተንጨባሮና ሳርና ሌላም ሸቀጥ ተሸክሞ ላብ በላብ ሁነው ሰኟቸውን መጀመር አስከፊ አይፈልጉም ነበር !
እንደውም አንዳንዴ ስፖርት ላለመስራት ‹‹ቲቸር ማንስትሬሽን ላይ ነኝ›› ብለው የሚያስፈቅዱ ሴቶችን ‹‹አ…ይ በየሰማንቱ ነው እንዴ የእናተ ….›› ብሎ ይቆጣቸዋል ! በእርግጥ ቲቸር ጨካኝ አልነበረም ግን የሴቶች ስፖርት መጥላት ያበሳጨው ነበር! አንድ ቀን ታዲያ ‹‹ እራስን ከአደጋ መከላለከል ›› የሚል የማርሻል አርት አንድ ክፍል የሆነ ትምህርት እያስተማረን ነበር…. ትምህርቱ ስለሚያዝናና በተለይ ወንዶቹ ደስ ብሎን ነበር የምንሰራው ! ተሰልፈን ያ….ሄይ….. ሁ እንላለን ! ሴቶቹም ድምፃቸውን ቀንሰው ኤጭ ! ይላሉ !
‹‹ ለምሳሌ ጩቤ የያዘ ሰው አይኑን አፍጥጦ ሊያጠቃችሁ ፊት ለፊታችሁ ቢቆም ምን ታደርጋላችሁ ›› ብሎ ጠየቀን ቲቸር
‹‹መጀመሪያ አማትባለሁ ›› አለ ፍቅረ ማርቆስ ሁላችንም ሳቅን
‹‹ደህና ድንጋይ ፈልጌ እፈነክተዋለሁ ›› አለ ታደሰ የሚባል የክላሳችን ልጅ
‹‹ አግሬ አውጭኝ ብሎ ፈትለክ ነው ወደኋላ ›› ይላል ሌላው ! ቲቸር ግን እንዴት ጩቤውን አንደምናስጥለው በምሳሌ አንድ ልጅ ወደፊት አስወጥቶ አሳየን ! ቲቸር ‹‹ለምሳሌ የሚሆን አንድ ሰው ወደፊት ይምጣ እስኪ ›› ሲል ሁላችንም ፈርተን ዝም ነበር ያልነው ቲቸር ራሱ አንዱን ጠራው እና ተማሪውን እስክርቢቶ እንደጩቤ አስይዞ አንዴት ማስጣል እንደሚቻል አሳየን !
‹‹ በመጀመሪያ ሊያጠቃችሁ የመጣው ሰው እንኳን ጩቤ ጎራዴ ቢየዝ እንዳትፈሩ እንዳትደነግጡ ተረጋግታችሁ አያያዙን ተመልከቱ ‹ አያያዙን አይተህ ጭብጦውን ቀማው › አይደለ ተረቱ ….ከዛ እንዲህ እጁን አንጓው ላይ በፍጥነት ትይዙና ወደግራ እጁን ጠምዝዛችሁ …..ልክ እንደዚህ ያ …ሁይ ›› ብሎ ለምሳሌ የወጣውን ልጅ መሬት ላይ በጀርባው ዘረጋውና እና የያዘውን ቢክ እስክርቢቶ አስጣለው ! ቲቸር ጎበዝ ነበር ! (#በነገራችን ላይ ዱርየወች ቲቸርን ማታ ላይ በጩቤ አስፈራርተው ላፕቶፑን እንደቀሙት ቆይቶ ዩኒቨርስቲ ከገባን በኋላ ሰምተናል ‹የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም› )
ቀጥሎ ሴቶች እራሳቸውን ከጥቃት እንዴት እንደሚከላከሉ ማስተማር ጀመረ
‹‹ ሊሊ ››
‹‹የስ ቲቸር ›› አለች ሞልቃቃዋና ቆንጆዋ የክላሳችን ልጅ ›› የሊሊ ቁንጅና መቸም ተአምር ነው በቃ ተአምር !
ቲቸር ቀጠሉ ‹‹ለምሳሌ አንድ ወንድ አስገድዶ ሊደፍርሽ ቢሞክር እንበል ….››
‹‹ኦ ማይ ጋድ ›› አለች ሊሊ ቲቸር ሳይጨርሱት ቀድማ !
‹‹ ምሳሌ ነው …እንዴት እንደምትከላከይው በምሳሌ እናያለን ….›› ብሎ ሊሊን ወደፊት አስወጣትና ወደእኛ ዙሮ ‹‹ እስቲ አንድ ወንድ እንደሊሊ ደፋሪ ሁኖ ምሳሌውን የማሳይበት ሲል ›› ሁላችንም ወንዶቹ እጃችንን አውጥተን ወደፊት ተንደረደርን ! እንዴ ሊሊ ጋር ለምሳሌም ቢሆን መደፋፈር ፅድቅ ነበር ለእኛ ! ሊሊ እኮ ነች ! በተለይ እንዲህ ጥብቅብቅ ባለ ታይትና በጃፖኒ ቁማ ጡቶቿ ተቀስረው አስተማሪው ‹‹ኑ ድፈሯት ›› ሲል ማን ሞኝ አለ አርፎ የሚቆም ዘራፍ ! ምን ያደርጋል ‹‹ ተውት በቃ እራሴ አሳያችኋለሁ ›› አለና ኩም አደረገን ቲቸር !እግዜር ይይለት ! ‹‹….ምን አይነት ነገር ነው ተማሪ ተኮር ነው ትምህርቱ አልተባለም እንዴ ሁሉን ነገር አስተማሪው ብቻ ….›› ብያለሁ በሆዴ !
ቲቸር ሜዳው ላይ በጀርባው ተኛና ..‹‹ አሁን እኔ ደፋሪ ነኝ አንች ነይ እግርሽን ክፈችና ከላየ ሆዴ ላይ ውጭ ›› አላት
‹‹ እንዴ ቲቸር አልወጣም !›› አለች ሊሊ ፊቷን አጨፍግጋ !
‹‹ለምንድነው የማትወጭው››
‹‹ ከመቸ ወዲህ ነው ሴት ከላይ ሁና የምትደፈረው ›› አለች ሊሊ
‹‹ነይ ዝም ብለሽ ውጭ ››
‹‹አልወጣም ››
‹‹ ነግሪያለሁ ውጭ ››
‹‹እኔም ነገርኮዎት አልወጣም ቲቸር ደግሞ ከላይ ሁኖ መደፈር አለ እነ….ዴ …ሆሆ ››
‹‹ከላይ ሆንሽ ከታች ምን ለውጥ አለው ››
‹‹ ከላይ ከሆንኩማ ‹ኦልሬዲ› እራሴ ፈልጌ ነው ማለት ነው !! ምኑን ደፈራ ሆነ ቲቸር አልወጣብወትም ›› ብላ ቲቸር እንደተንጋለሉ ትታቸው ወደቦታዋ ተመለሰች !
ቲቸር በጣም ስለተበሳጩ ሊሊን ወላጅ አስጠሯት ! ወላጆቿ ቲቸርና ሊሊ የትምህርት ቤታችን ርእሰ መምህር ጋር ቀረቡ
ቲቸር የሊሊን ጥጋብና አስተማሪ መናቋን አስረዱ ….ሊሊ በበኩሏ ‹ሴት ከላይ ሁና ስትደፈር ታይቶም ተሰምቶም እንደማይታወቅ አስረዳች › የሊሊ ወላጆች ግራ ተጋብተው ዝም አሉ ….በመጨረሻም ርእሰ መምህሩ ውሳኔያቸውን አሳልፉ !
‹‹መምህር ጥጋቡ…. መቸም አንተ ምስጉን መምህራችን መሆንህን ማንም ያውቃል….. በሙያህም ጣልቃ መግባት የለብኝም ቢሆንም ተማሪወችን በሚወዱት መንገድ ማስተማር የተሸለ ትምህርቱን እንዲረዱት ያደርጋልና ካሁን በኋላ ከላይ ሁነህ በመድፈር አስተምራት …አንችም አርፈሽ አደፋፈሩን ተማሪ አንድ ቀን ይጠቅምሻል ››ሲሉ ሸኟቸው!😃

🔘በ አሌክስ አብርሀም🔘
👍7😁2
#በቀኝ_አሳድረኝ

ቀጭ ….ቀጭቀጭ …ሲጥ ..ሲጥጥ
እህህህ ..‹‹ቀስ በል የኔ ጌ….ታ …››
በ ሹ ክ ሹ ክ ታ
ከግድግዳየ ወዲያ …
ሁሉም ባረፈበት ማታ
ካዲስ ተጋቢዎቹ ቤት
አልፎ የሚመጣ ንዝረት
ጆሮ የሚያቆም ወላፈን
ደምፃቸውን ለቀቅ ….አፈን
‹‹ውይይይይ ….›› የሷ ድምፅ …... በሲቃ ሲተን
የዝምታ አለት …. በፍቅር ፈንጅ… አልጋቸው ላይ
ሲበታተን
ደግሞ የሱ ከንፈር ዋይታ …….እ…..ሟ
የወንድ ልቡ ብረት ወኔው …በፍቅር እቶን
ሲሟሟ
‹‹እፉፉፉፉፉ ››ድምፃቸውን እንደጅራፍ ባንድ
ፈትለው ባንድ ገምደው
ድቅድቅ የጨለማን መንጋ በሲቃ ጩኸት አሳደው
ባንድ ላይ ሲቀላቀሉ የብቻን ግንብ ወዲያ ንደው
አውሎ እፎይታ
ከቀኝ ግድግዳየ ተጎራባች…. ሁሉ ባረፈበት ማታ
ዝምምምምምምታ !
ተኙ መሰል !!
* ** *
ሌላ ድምፅ ደግሞ ከግራ
በቆመ ጆሮየ ግርጌ ያልፋል ድሩን እያደራ
‹‹ እእእእእ ›› ይችኛይቱ ጎረቤቴ
እንዲህ በሙሉ ጨረቃ የሚያስቃዣት በሽተኛ
ሙሉ ሌሊት ስትዋትት ስትሰቃይ የማተኛ
ድፍን ሌሊት ስትዛብር ስታቃስት የሚነጋ
ሲጥ ሲጥጥ ወጉ እንዳይቀር የሷም አልጋ
ቀንም በመቀነቻ ነው … ወገቧን አስራ
የምትቆመው
የበሽታ ክፉ አካናድ ስጋዋን እየጎሰመው
በሁለት ቅስቻ መሃል … ግራ ቀኙኝ እያደመጥኩ
ካንዱ <ጆሮየ አውጭኝ> እያልኩ… ሌላውን
ባሳብ እያለምኩ
በመሃል የምኖር እኔ …
እንቅልፍ ሊጥለኝ ሲዳዳ በግዜር ላይ ቅኔ
እቀኛለሁ
የወጉን ፀሎት ሰም አድርጌ ‹‹በቀኝ አሳድረኝ
››እላለሁ
**
**** ****
ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ ኳ ኳ
አዲስ ተጋቢወች ማለዳ ተነስተው…. ለቁርስ
ቲማቲም እየቀጠቀጡ
ሲጥጥጥጥጥጥጥጥጥ
ታመው ያደሩቱ ቤተስኪያን ሊስሙ …..ከቤት
እየወጡ
በቀኝም በግራ እንዲህ የሚል ልሳን
‹‹ሰላም ያሳደርከን በሰላም አውለን ››
ይች ናት አገሬ … እኩል እግዚሃርን
የሚዘይሩባት… እኩል ያላደሩ
እኩል ቀን ጀማሪ እኩል ባልሆነ ቁርስ ተስፋ
እየቋጠሩ !
ከታች እስኪሾሙ ከላይ እስኪጠሩ !!
ከቀኝም ከግራም …መሃል ለሰፈሩ
ይች ናት አገሬ እንዲህ ነው አዳሩ !

🔘አሌክስ አብርሃም🔘
👍1
#ብቸኝነት_ማለት


ውዴ... ብቸኝነት...
ከሰዎች መነጠል...ለብቻ መቀመጥ...አይደለም ትርጉሙ፣
ጓደኛ አለመኖር...ብቻ ቀን ማሳለፍ...እሱ አይደል ህመሙ፣
ብቸኝነት ማለት...
ከሰው መንጋ ውሎ... ከሰው ተቀላቅሎ... ባዶነት መሰማት፣
የናፈቁትን ድምጽ... ከሩቅ እየሰሙ...በውስጥ ማዋራት፣
.
የናፈቁትን መልክ...ለብቻ እያለሙ...በናፍቆት መብከንከን፣
ቅርብ የሌለን ጠረን...ባፍንጫ እየማጉ...በሽታ'ው መታጠን፣
.
የድሮን ትዝታ ዛሬ እያሰቡ...፣
ከሃሳብ ማህደር ደግመው 'ያነበቡ...፣
.
በናፈቁት ሰው ድምጽ...የቅርቡን ሲጠሉ፣
የሚልቅን ጠረን...ካጠገብ አስቀምጠው...በሩቅ ሰው ሩሩሩሩሩቅ ጠረን...ባ'ሳብ ሲነጠሉ፣
.
ድሮ የሳቁትን...ደግምመው እያሰቡ...ሀዘን መሃል ሆነው...ለብቻ ሲፈግጉ፣
ድሮ ያዘኑበትን...ዛሬ እያስታወሱ...ከሞቀ ሳቅ መሃል...ለብቻ መንሰቅሰቅ...ማልቀስ ሲፈልጉ፣
.
ብቸኝነት ማለት...ትዝታ ማለት ነው...ማለት ነው ትዝታ፣
ከብዙ ሰው መሃል...ብ ቻ ነ ት መሰማት...ቀን የውሸት ስቀው...ብቻ ማልቀስ ማታ፣
.
ልክ እንዳሁናችን...ካጠገቤ 'ያለህ እንደምትናፍቀኝ...፣
ፍቅራችን አርጅቶ ምልክት በቀረው በትዝታ ሽበት... ዛሬ 'ንደሚታየኝ፣
.
ብቸኝነት ማለት የትዝታ ድርሳን...ነው የናፍቆት ክርታስ ...፣
ውዴ ፍቅሬ እያሉ በቋጠሩት ትላንት ዛሬን አንጀት ማራስ...፣
.
"እይዋት ስትናፍቀኝ ካጠገቤ አያለች" የሚል ዘፈን ማቆም
በመሃሙድ ዘፈን..."ምንድነው ትዝታ"... ከትካዜ መስጠም!

🔘የአብስራ ሞላ🔘
👍6
#እንቧለሌ

ያረጀ ቂም ይዘን ፤ዘላለም ስንደግም፤
ዓለም ጥሎን ሄደ ፤እኛ ስናዘግም።
በወጣንበት በር ፣መልሰን ስንገባ፤
ስንት አደይ ረግፎ ፣ስንት ዘመን ጠባ።
ለኛ አልተሰጠም ወይ በይቅርታ መንፃት?
ስለ ፍቅር ሲባል ፣ያለፈን ቂም መርሳት።
መሪው ምረት የለሽ ፤ተመሪው ቅጥ ያጣ፤
በእንቧለሌ መንገድ ፣ማን አርነት ይውጣ ?።
እንዴው የሞኝ ዘፈን ሁል ጊዜ አበባዬ፤
ክፈል ትለኛለች ፤እኔን ያለዳዬ።
እንዴው ልክፈልስ ብል፣ በየትኛው ቁና ፣
መስፈሪያዋም ዐፈር ፣ሰፋሪው ጋር ሆና።
በመንታ ፊት ኑሮ ፣ቀን ይመላለሳል፤
እጅ እየሻከረ ፣እርፍ ይለሰልሳል።
በክንድ አዝል ሃገር ፣ሠው ከእንጨት ይረክሳል፤
እልፍ እየተለፋ ፣እፍኝ ይታፈሳል።
የትልቅ ፀብ ይሆን ፣ያማልዕክት እርግማን፣
መድረስ የተሳነን ፣እንዲህ ባገር አማን ።
ኧረ ምን መዓት ነው ? እንዴት ያል መለከፍ ?
ወንዙን ውሃ በላው ፤እኛ ስንጣለፍ ።
እንቧለሌ ስንዞር፣ ክቡን እንደምጣድ፤
ለእንጀራ እስከመቼ እሣት ላይ እንጣድ ።
ነቅቶ እየቀደመ ፣ኑሮን ካላደሰው ፣
ፀዳሉ ይረግፋል፤የቀንም እንደሰው።

🔘ኑረዲን ዒሣ🔘
#ህመሜን_ፍለጋ

ትኩሳት ነው ብለው
ሰዎች ይነግሩኛል፣
ራስ ምታት ነው ብለው
ይገምቱልኛል፣
:
ግማሹ እየመጣ
ጨጓራ ይዞሃል
ብሎ እየነገረኝ፤
ግማሹ ሰው ደግሞ
ኩላሊት አለብህ
ብሎ እየነገረኝ፤
ህመሜን ሰው ሁሉ
ስም እያወጣለት፤
ለየትኛው ህመም ክኒን ልዋጥለት፤
ለየትኛው ህመም መርፌ ልወጋለት።
:
የቱ ነው ህመሜ?
እንደምን ልወቀው?፣
ወይ ህመም አይዋጥ
ህመም በሽታዬን እንዴት ልደብቀው?፣
:
ቸገረኝ!
:
ብቻ!
የበሽታዬን ስም
ንገሩኝ ልለየው፤
ፍለጋው ነው እንጂ
ህመም ስቃዩ አይደል
ነፍሴን የሚለየው፤
:
ሞትማ ክብር ነው
ሞትማ 'ረፍት ነው
ቅር ቢሉት የማይቀር፤
ከነጥያቄዬ ወደ ሌላኛ ዓለም
መሄድ መጓዜ ግን
ሰላም እንዳይነሳኝ
ከነፍሴ ጋር ሄዶ እንዳይሰነቀር።
:
ግድ የለም ንገሩኝ
ህመሜ ምንድነው?
:
ጠሃይዋን እያየው ብርድ ብርድ የሚለኝ
በረዶ እየጣለ ሙቀት የሚገለኝ
ከቶ ምን ሆኜ ነው?
:
ወባ ነው እንዳልል
አጎበር ዘርግቼ፤
ብርድ ነው እንዳልል
ልብስ ደራርቤ
እሳትም አንድጄ ቤቴንም ዘግቼ፤
:
ለምን ይበርደኛል?
:
ለምን ይሞቀኛል?
:
እጅ እግሬ ጉልበቴስ
ምን ሆንኩኝ ብሎ ነው
'ሚቆረጣጥመኝ?
ምን ሆንኩኝ ብዬ ነው
ስኳር የሚመረኝ እሬት የሚጥመኝ?
:
ምን እንደሆንኩ እንጃ!
:
ህመሜን መለየት
ማወቁን አላውቀው፤
እንዳው ዝም ብዬ ነው
ቁስሌን እያየሁ
ትናንት ዛሬም ነገም
ሁሌም ምጠይቀው፤
:
ኬት መጣ ይህ ቁስል?
የት ነው የተጋጋጥሁ?
ወዴት ልዘል ይሆን
እግሬን ተሰብሬ
የስቃይ ምጥ ያማጥሁ
:
እንዳው ላመል እንጂ!
:
እንደታመምኩኝስ
እንዳልታመምኩኝስ
ከወዴት አውቄው፤
እንዳው ላመል እንጂ
ጠይቅ ስለተባልኩ
እንዲህ ምጠይቀው፤
:
እንደዚህ እያልኩኝ!
:
ህመሜን ሰው ሁሉ
ስም እያወጣለት፤
ለየትኛው ህመም ክኒን ልዋጥለት፤
ለየትኛው ህመም መርፌ ልወጋለት።

እንጃ!
👍2
#የመልስ_ጉዞ
:
ክፍል- #አንድ

:
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
ፍእማዊ መንግስታዊ አስተዳደር ፤ፍፁማዊ ማህበረሳብ አወቀቀር፤ፍፁማዊ የተፈጥሮ ሚዛኗን የጠበቀች ሀገር..በዩቶፕያ ፅንሰ ሀሳብ የታነፀች ማለት ያቺ ነች ፡፡በነብያት አዕምሮ ውሰጥ ከዘመናት በፊት ተፀንሳ ትንቢት የተነገረላት ሰማያዊ የመኖሪያ ስፍራ በነአፍላጦስ ምናብ የተፀነሰችና በምድር ለመገንባት የተመኙላት ምድራዊ እንከን አልባ የሰለጠኑና የበቁ ማህበረሰቦች የሚኖሩባት ፤በፍፅም ፍትሀዊነት እና በጋራ ህግ የሚመራ መንግስት ያላት፤ ለገነት የቀረበ ልምላሜ ኖሯት አንድ ቀን በጋራ ስምምነት ፍፅማዊ ደስታ የምታመነጭ ተደርጋ የምትመሰረት ምድራዊ ከተማ ….
ታዲያ ይህቺ የአለማዊው እሳቤ እና የመንፈሳዊው ትንቢት ቀላቅላ የያዘች ዩቶፐያ ከወዴት ነች?የሀይማኖት ነብያት እንደሚሉት በሰማይ ከሞት ቡኃላ ባለው ህይወት የሚያገኞት ወይስ ሰው የልዕለ ሰብነትን ዙፋን ሲቆናጠጥ ፍፁም ፍትሀዊ፤ ፍፁም ዘመናዊ ብቃት ባገኘ ጊዜ በብቃትና በጥበቡ እዚሁ ምድር ላይ የሚመሰርታት….?
ወደ ዩቶፕያ መሄጂያ መንገዱ በየት ነው…ዩቶፕያስ የት ነው እውን ሊሆን የሚችለው ….?
እግዚያብሄር መላክ በምስራቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ ያበጀውንም ሰው በዛ አኖረው፡፡እግዚያሄር አምላክ ለዓይን የሚያስደስት ለመብልም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ በምድር አበቀለ፡፡ በአትክልቱ ቦታ መልካም የህይወት ዛፍ ነበር፡፡እንዲሁም መልካምና ክፍውን መለየት ሚያስችል የዕውቀት ዛፍም ነበር፡፡የአትክልት ስፋራ የሚያጠጣው ወንዝ ከዔደን ይፈስ ነበር ፡፡ከዚያም በአራት ተከፍሎ ይፈስ ነበር፡፡የመጀመሪያው በምድሩ ወርቅ የሚገኝበት በሐዊላ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈሰው የፊሶን ወንዝ ነው፡፡ኤውላጥ ምርጥ ሆነ ወርቅ መልካም መአዛ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኝበት ምደር ነው፡፡ሁለተኛው በኢትዬጳያ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስው ግዬን ወንዝ ነው፡፡ሶስተኛው ከአሶር በስተምስራቅ ሚፈሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን አራተኛው የኤፍራጠስ ወንዝ ነው፡፡ (ዘፍጥረት ም 2 ቁጥር 8-14 )
ለመሆኑ ይሄስ ስፍራ የት ነው?፡፡የአዳምና ሄዋን ቀደምት መኖሪያ ስፍራ ..?የእውቀትና የዘላለም ፍሬ የሚበቅልበት ሚስጥራዊ ስፍራ…?በአዳምና ሄዋና የተወከሉት የመጀመሪያዎቹ የሰው ልጆች በፈጣሪያቸው ላይ ከብልሁ እባብ ጋር የመከሩበት ፤የመከሩበት ብቻ ሳይሆን የዶለቱበትም ስፍራ የት ነው?፡ከዛስ እርቃናቸውን እንደሆኑ የተገለፀላቸው…?ያን ሰፊ እፍረታቸውን የጋረዱበት ቅጠልስ ከየትኛው ስፍራ ከየትኛውስ ዛፍ ላይስ የተገንጥለው ይሆን? …ከዛስ ወደየት ተባረሩ ?እንዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው፡፡የመልስ ጉዞው ወደዛ ነዋ ፡፡አያቶቾ አዳምና ሄዋን ወደተባሩበት ስፍራ ወደ ሀገረ ገነት ...
ይህቺ ሀገር ኢትዬጵያ ነች፤ ይህቺ ሀገር የአያቴ ህልም ነች…ህልሙ ግን በከፊል እንኳን እውን ሳይሆን እድሜ እየተጫጫነው ነው፡፡ቢሆንም ለዚህ አንድ ዘዴ ዘይዷል …ህልሙ ህልሜ እንዲሆን አድርጎል…እንደሱ እንድመኝ ….እንደእሱ እንዳስብ…. ግን ይሄን ህልም እውን ለማድረግ እኔ ምን ማድረግ አለብኝ…ከሚስቴ ጋ እስክገናኝ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም..
አሁን ግን ወደ እዛች ስፍራ ጉዞ ጀምረናል ፡፡እኔና ሚስቴ ፡፡ሁለታችንም የተለያየ የግል ዓላማ አለን ፡፡ግን የየግል አላማችን ከተሳካን ቡኃላም የጋራም አንድ አላማ አለን፡፡ አዎ እንብርት የሆነውን ስፍራ ካገኘን ቡኃላ ዩቶፐያችንን በስፍራው ደግመን እንገነባለን..እንዴት አድርገን.? ወደፊት አብረን የምናየው ይሆናል፡፡
አሁን ወደዋናው የታሪኩ ክፍል ጠልቄ ከመግባቴ በፊት እራሴን ላስተዋውቃችሁ …መቼስ ታሪኬን ስትሰሙ አንዳንዶቻችሁ የተዛባ አዕምሮ የፈጠራቸው የእድሜ ልክ የቀን ቅዥቶች ልትሉት እንድምትችሉ እገምታለው፡፡ይሁንና የእኔን እውነት ነግራችሆለው፡፡ ሳልኩልና ሳልቀባባ ጥሬ እወነቱን ብቻ፡፡ማመን ያለማመን የእናንተ ፋንታ ነው፡፡ግን ከእኔ ጋር ወዳጅነት መስርታችሁ የምነግራችሁን ለማድመጥ በጣም ትዕግስተኛ እና አስተዋይ መሆን አለባችሁ፡፡ምክንያቱም የሆነ ርዕስ ተከትሎ የነገሮችን ቅደም ተከለተልን ጠብቆ ታሪኩን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ያጫውተናል ብላቹ ምትጠብቁ ከሆነ ከአሁኑ እርማችሁን አውጡ ፡፡እና ንባባችሁን እዚህ ጋር አቋርጡ፡፡
የገዛ የራሴን ታሪክ ለሌላ ሰው እንዴት ማውጋት እንዳለብኝ መወሰን ስልጣን ያለኝ እኔ ብቻ ነኝ ፡፡ስለዚህ ዘባራቂነቴን ካልወደዳችሁት ምንም ልረዳችሁ አልችልም፡፡ዘባራቂነቴ የነፃነቴ መገለጫ ምልክት ነው፡፡ምናቤ በማንኛውም የስርዓትና የደንብ ሰንሰለት አለመጠፍነጉን የሚያሳይ ልቅ መጋለቢያ ሜዳ አይነት ነው፡፡ወይንም በሆነ ቦታ የታጠረ የኩሬ ውሀ ሳይሆን የአባይ አይነት ሀገር ተሸጋሪ ወንዝ ፡፡አዎ የእኔ አዕምሮ እንደዛ ነው፡፡ለነፍሴ ማደሪያ በተሰጠኝ አካል ያልተወሰነ እንዳምንበት ከቤተሰቤ በውርስ በተሰጠኝ ሀይማኖታዊ ዶግማ ያልታጠረ.. በተወለድኩበት ሀገር ድንበር ያልተከለለ….በተፈጠርኩበት ምድር የልተገደበ…እንደዛ ነው ምናቤ… እንደዛው ነው ሀሳቤ …..
እና ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው ካልከኝ በዘመን ሂደት ሰው ያው ሰው ነውና መጎዝና አዲስ ነገር ማሰስ ተፈጥሮአዊው ባህሪው እንደመሆኑ መጠን አካባቢውን እየለቀቀ ሲያፈገፍግ ሲዋለድ ሲራባ ሲያፈገፍግ በሚሊዬን ዓመት ሂደት ውስጥ መቶች ውስጥ አለመን አዳረሰና በዚህ ሂደት ውስት ከተፈጥሮ እና እርስበርሱ በሚያደርገው ትግልና ፍትጊያ አእምሮውን እያዳበረ አዕምሮ ሲዳብር ደግሞ ለአካባቢውም ሆነ ለራሱ የነበረው እይታ እየተቀየረ የማምረቻ መሰሪያዎችን እየፈለሰፈ ንግድና እየጀመረ ሲመጣ መልሶ ወደ መነሻው ማየት ጀመረ…ኢትዬጵያ የሰው ዘር ተፈጥሮ የተበተነባት ምድር መልሶም አንድ ቀን የሚሰበሰብባት፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5
#ፈጣሪ_ብሔሩ_ምንድን_ነው... ?

ህመሜን ፍለጋ
ትኩሳት ነው ብለው
ሰዎች ይነግሩኛል፣
ራስ ምታት ነው ብለው
ይገምቱልኛል፣
:
ግማሹ እየመጣ
ጨጓራ ይዞሃል
ብሎ እየነገረኝ፤
ግማሹ ሰው ደግሞ
ኩላሊት አለብህ
ብሎ እየነገረኝ፤
ህመሜን ሰው ሁሉ
ስም እያወጣለት፤
ለየትኛው ህመም ክኒን ልዋጥለት፤
ለየትኛው ህመም መርፌ ልወጋለት።
:
ብቻ ይሄው ምልክቱ፣
የያዘኝ በሽታ ፈጣሪን ደፍሬ
እንዲህ ያስብለኛል፤
ለንፁሀኑ በደል
ለንፁሀኑ ደም ወርደህ እንድትፈርድ
በምነኛ እንፁም በምነኛ እንስገድ፤
በትግርኛ እንስገድ?
በአማርኛ እንስገድ?
በኦሮምኛ እንስገድ?
የቱ ነው ሚቀርብህ
የትኛው ነው ያንተ ብሔር ያሰኘኛል፤
ስሙ ጠፋኝ እንጂ እውነት ነው አሞኛል፤
:
ግን ግን ይህ ህመም ምንድን ነው?
እንደምን ልወቀው?
ህመሜን እንዳልውጥ
ስቃዩ በዛብኝ እንዴት ልደብቀው፤
:
ቸገረኝ!
:
እስኪ ታውቁ እንደሆን
የበሽታዬን ስም
ንገሩኝ ልለየው፤
ፍለጋው ነው እንጂ
ህመም ስቃዩ አይደል
ነፍሴን የሚለየው፤
:
ብቻ ይሄው ምልክቱ
የያዘኝ በሽታ ፈጣሪን
ደፍሬ እንዲህ ያስብለኛል፤
ጥበብ ያልከኝን ቃል
በቃሌ መዝገብ ላይ እየተረጎምኩኝ
ጠብቤ ጠብቤ ጎሳህን ዘረክን ብሄርክን ጠየኩኝ
ጌታ ግን ምንድን ነህ ?
ኦሮሞ
ጉራጌ
ሱማሌ
ሀረርጌ
ትግሬ ነህ አማራ፤
ቤተስኪያን አልሄድም
መስጊድም አልሄድም ዘርክን እስካጣራ
ማለትም ያምረኛል
ስሙ ጠፋኝ እንጂ እውነት ነው አሞኛል፤
ግን ግን ይህ ህመም ምንድን ነው?
እንደምን ልወቀው?
ህመሜን እንዳልውጥ
ስቃዩ በዛብኝ እንዴት ልደብቀው፤
:
ሞትማ ክብር ነው
ሞትማ 'ረፍት ነው
ቅር ቢሉት የማይቀር፤
ከነጥያቄዬ ወደ ሌላኛው ዓለም
መሄድ መጓዜ ግን
ሰላም እንዳይነሳኝ
ከነፍሴ ጋር ሄዶ እንዳይሰነቀር።
:
ብቻ ይሄው ምልክቱ
የያዘኝ በሽታ ፈጣሪን
ደፍሬ እንዲህ ያስብለኛል፤
:
በፈጠርካት ምድር ድንበር አበጅተን
የኔ ነው የኔ ነው ተባብለን አድረናል
ሁሉ ያንተ መሆኑን ዘንግተን ከኖርን
ብዙ አመት ሆኖናል፤
:
ይሄው ስማኝማ በባቢሎን
ምክንያት ሀጥያታችን በዝቶ፤
:
ቋንቋ ልሳናችን ለይተህ ቃኝተካል
ግድ የለም አሁን ግን ቋንቋችንን ቀማን
እንዳደርስብህ ግንቡ ይሻልካል፤
:
ይሄው ስማኝማ አንተን ልናከብር
የፈጠርክልን አንደበት ተዘጋ፤
:
አንተን ዘንግተናል ውዳሲያችን ሁሉ
ዘሬ ዘሬ ሆኖል በነጋ በጠባ
:
ግን ግን ይህ ህመም ምንድን ነው?
እንደምን ልወቀው?
ህመሜን እንዳልውጥ
ስቃዩ በዛብኝ እንዴት ልደብቀው
:
:
ግድ የለም ንገሩኝ
ህመሜ ምንድነው?
:
ጠሃይዋን እያየው ብርድ ብርድ የሚለኝ
በረዶ እየጣለ ሙቀት የሚገለኝ
ከቶ ምን ሆኜ ነው?
:
ወባ ነው እንዳልል
አጎበር ዘርግቼ፤
ብርድ ነው እንዳልል
ልብስ ደራርቤ
እሳትም አንድጄ ቤቴንም ዘግቼ፤
:
ለምን ይበርደኛል?
:
ለምን ይሞቀኛል?
:
እጅ እግሬ ጉልበቴስ
ምን ሆንኩኝ ብሎ ነው
'ሚቆረጣጥመኝ?
ምን ሆንኩኝ ብዬ ነው
ስኳር የሚመረኝ እሬት የሚጥመኝ?
:
ምን እንደሆንኩ እንጃ
:
የያዘኝ በሽታ ፈጣሪን ደፍሬ
እንዲህ ያስብለኛል፤
:
በልሙጥ ሰማይ ላይ ሰንደቄን ስላየው
ኮከቡን አጥፋልኝ ብዬ እጠይቃለው
ስሙን ባላውቀውም እውነት ታምሚያለው፤
:
ካስርቱ ትዛዛት አንድ የጨመርክበት
አልያም ያጎደልከው ሆኖ እየተሰማኝ
ህግ ሻርክ ብዬ መበታተን ጠማኝ፤
እንዲህም አስባለው
ስሙን ባላውቀውም እውነት ታምሜአለሁ

ምን እንደሆንኩ እንጃ!
:
ህመሜን መለየት
ማወቁን አላውቀው፤
እንዳው ዝም ብዬ ነው
ቁስሌን እያየሁ
ትናንት ዛሬም ነገም
ሁሌም ምጠይቀው፤
:
ኬት መጣ ይህ ቁስል?
የት ነው የተጋጋጥሁ?
ወዴት ልዘል ይሆን
እግሬን ተሰብሬ
የስቃይ ምጥ ያማጥሁ
:
ምን እንደሆንኩ እንጃ!
:
እየጠዘጠዘኝ
እየቀዘቀዘኝ
እየገዘገዘኝ
:
የኔ ሰው እርቆኝ
ነው ጠላት የገነዘኝ፤
እያልኩ አስባለው
:
ከወዳጄም ጥል ነኝ
ከጠሌቴም ጥል ነኝ
ከራሴም ጋር ጥል ነኝ
:
እውነት ታምሜአለሁ
:
እንዲያው ዝም ብዬ እንጂ
:
እንደታመምኩኝስ
እንዳልታመምኩኝስ
ከወዴት አውቄው፤
እንዳው ላመል እንጂ
ጠይቅ ስለተባልኩ
እንዲህ ምጠይቀው፤
:
እንደዚህ እያልኩኝ!
:
ህመሜን ሰው ሁሉ
ስም እያወጣለት፤
ለየትኛው ህመም ክኒን ልዋጥለት፤
ለየትኛው ህመም መርፌ ልወጋለት።

እንጃ!
#አጭር_ልብወለድ

#የልጅነት_ዕይታ

ይህ ታሪክ የተከሰተው የሁለተኛ ክፍል ተማሪና የዘጠኝ ዓመት ልጅ እያለው ነው በወቅቱ ዱርዬው አባቴ እና ጭምቶ እናቴ በእኔ ላይ የፈጸሙትን አሻጥር ነው የምተርክላችሁ እለቱ ቅዳሜ 10 ሰዓት አካባቢ ነው አባቴ ና ዘመድ ጠይቀን እንምጣ ብሎኝ እናቴን በማስፈቀድ ይዞኝ ወጣ የምንሄደው ወንድሙ ጋር ነው እኛ ከምንኖርበት በመኪና የአንድ ሰዓት መንገድ ነው ፤ አድረን ነገ በማግስቱ እንድንመጣ ማለት ነው፡፡በጥም ነበር የፈነጠዝኩት አንደኛ ሁሌ ከአበቴ ጋር ሆኜ ወደ ሆነ ቦታ ስጓዝ በራስ መተማመኔ ይጨምራል.ሁለተኛ አጐቴ የእኔ እኩያ የሆነ ልጅ አለው ከእሱ ጋር በመጫወት የማሳልፈው ጊዜ ለእኔ ጣፋጭ ነው፡፡
ሄድን…አጐቴ ቤት ደረስን የአጐቴ ሚስት በጣም በጥሩ መስተንግዶ ነበር የተቀበለችን መክሰስ ቀረበልን.ቡና ተፈላ…12 ሰዓት አካባቢ ሲሆን አባቴ መጣው ተጫወት ብሎኝ ከቤት ሲወጣ እምቢ ብዬ ተከተልኩት.ግንባሩን ቢቆጥርብኝም…ሊያስፈራራኝ ቢሞክርም ምን እንደነካኝ አላውቅም ያለወትሮዬ እምቢኝ አልኩት..እንደ ፍላጐቱም ልታዘዝለት አልቻልኩም..በመጨረሻም ብቻ ሳይመስለው..ሁለተኛ ይዞኝ እንደማይመጣ እየዛተብኝ ይዞኝ ሄደ፡፡‹‹ የት ይዞህ ሄደ አትሉኝ…?››ሆነች ቀይ ወፈር ያለች…አዲስ የሚያምር ቀሚስ የለበሰች ሴትዬ ቤት እሱን ስታየው በደስታ ተፍነከነከች ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙና ወደ እኔ ጐንበስ ብላ አገላብጣ ሳመችኝ..ልትስመኝ ጐንበስ ባለችበት ወቅት ከሁለት የተቀሰሩ ቀይ ጡቶቾ ስንጥቅ መሀከል የሚመነጭ የሚመስል ደስ ሚል ሽታ ተበትኖ በአፍና በአፍንጫዬ ተመሰገብኝ…
‹‹የቀረህ መስሎኝ እኮ ተበሳጭቼብህ ነበር››አለችው ‹‹እመጣለው ብዬሽ ጨክኜ እንዴት እቀራለው?››አላት..ወደእኔ ገልመጥ እለ
‹‹ልጅህ ደግሞ አንተን ይመስላል ››አለችው እኔን እኔን እያች
‹‹ታዲያ እኔ ወልጄው ማንን እንዲመስልልሽ ትፈልጊያለሽ?››አላት..
ለምን እንደሆነ አላውቅም ሁሌ አባትህን ነው የምትመስለው ሲሉኝ እግዚያብሄርነው ነው ምትመስለው እንዳሉኝ ነገር ትንሾ ልቤ በድስታ ትንፈራፈራለች ሴትዬዋ እኛን አስቀምጣ ወደ ጐዲያ ገባችና ሲኒዋን ይዛ በመምጣት አቀራረበች ….ከሰል አቀጣጠለች..እጃችንን አስታጠበችን ና ሚያስጐመዥ የዶሮ ወጥ አቀረበችልን፡፡
‹‹ብሉ… ብሉ…..››ስትል
‹‹ነይ አንቺም ቁጭ በይ አላት››አባቴ ቀብረር ብሎ
‹‹ቡናውን ብቆላ አይሻልም ብለህ ነው?›› አለችው.. ግን ሁኔታዋን ሲያዬት ከእኛ ጋር ቁጭ ብላ ለመብላት የቋመጠች ትመስላለች
‹‹ተይ ባክሽ ይደርሳል››ሲላት ብዙም ሳታቅማማ ኩርሲዋን ይዛ በመምጣት በእሱ እና በእኔ መሀከል ተሰክታ ቁጭ አለች በፈገግታዋ እና ባቀረበችልን ሚያስጐመዥ ዶሮ ወጥ ያስደሰተችኝ ቢሆንም በመሀከላችን በመሰካቶ ግን ቅር አሰኝታኛለች..እንኳን ሌላ ሴት ይቅርና እናቴ እንኳን ከአባቴ ስታርቀኝ ደስ አይለኝም ነበር..እውነቱን ንገረን ካላችሁኝ ግን ብዙውን ጊዜ ቅር ይለኝ የነበረው በእኔና በእናቴ መሀከል አባቴ ሲሰነቀር ነው .አባቴ ከእናቴ ሲያርቀኝ ያበሽቀኛል…ልክ አሁን ይህቺ ሴትዬ እንዳበሸቀችኝ፡፡
አባቴ ምግቡን ደህና አድርጐ ጠቀለለና ይጐርሳል ብዬ ስጠብቅ ለእሷ አጐረሳት…. እሷም የመጀመሪያውን ጉርሻ አጐረሰችው ፈጥጬ የሁለቱን ጉርሻ ቅብብል በማየት ስቁለጨለጭ ‹‹ብላ እንጂ ምን ያደፈዝሀል?›› በሚል የቁጣ ይሁን የትዕዛዝ ባለየለት ንግግር አስበረገገኝ ታምረኛው አባቴ ፡፡
‹‹ወይ አፈር ስሆን እረሳንህ አይደል›› በብጣቂ እንጀራ ወጥ ነካ ነካ አድርጋ እኔንም አጐረሰችኝ ፡፡የአባቴ ሁኔታ ግን በጣም ገርሞኛል እናቴን ብቻ ይመስለኝ ነበር እንደዛ የሚያጐርሰው..ለካ ሌሎችንም ሴቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ያጐርሳል…ድግሞ እኮ ‹‹…እኔ ከአንቺ ውጭ እኮ ማጉረስም መጉረስም አልወድም›› እያለ ለእናቴ ጉራውን ሲነፋ ስንት ቀን ሰምቼዋለው መሰላችሁ…ይሄኔ ይቺንም እንደዛ ብሎት ይሆናል? ዳሩ ምን አገባኝ አርፌ ጣፋጩን ምግብ አልበላም…ምግቡን በልተን ካጋመስን ቡኃላ አንድ አንድ እንቁላል ፊታችን አስቀመጠች…እሱን እየፈረካከስን ስንበላ ለአባቴ ደገመችለት ለእኔም ድጋሜው ይደርሰኛል ብዬ ስቁለጨለጭ ዘለለችኝና በምትኩ ስጋ ያዘለ አጥንት ፊት ለፊታችን ደረደረች፤ እሱን መጋጥ ጀመርኩ ቀጥሎ አባቴ ‹‹በቃኝ…. በቃኝ ››ሲላት
‹‹ቆይ እንጂ መቋደሻውስ ?››አለችና የሆነ ስጋ በማውጣት በእጆ አንጠልጥላ ወደ እሱ ዘረጋችለት እሱም አንደኛውን ጫፍ ያዘ ሁለቱም ወደ ራሳቸው ሳብትና ጠመዘዙት ሁለት ቦታ ተከፈላ እሷ እጅ ላይ የቀረውን ለእሱ ስታጐርሰው የእሱን ደግሞ ለእሷ አጐረሳት…‹‹ ምን ያሽቃብጡብኛል?… የየራሳቸውን ለየራሳቸው አይጐርሱም እንዴ..?››ስል አሰብኩ በልቤ ግን ምን ያሽቃብጡብኛል ማለት ምን ማለት ነው? እኔ እናጃ ብቻ የሆነ ሰው የሆነ ቦታ ይህቺን ቃል ለእንደዚህ አይነት ድርጊት ሲጠቀምባት ሰምቼ ይሆናል..የሆነ ሆኖ ጠገብንና ምግቡ ተነሳ ብና ተፈላ ጠጣን….ኸረ ተሳስቼ ነው እነሱ ናቸው የጠጡት እኔ አልጠጣውም..ዳግሞ አንድ የዘለልኩት ነገር አለ የሆ የፈረንጅ አረቄ ነው ብላ በትንሾ ብርጭቆ ሞልታ ሰጠችው..
‹‹ ጅን ትወዳለህ አይደል?›› እያለች
‹‹አዎ ግን..!››
‹‹ግን ምን ?ባክህ አትፍራው አያሰክርህም… ለዛ ነገርም አሪፍ ነው ሲሉ ሰምቼያለው››አለችው.ለየትኛው ነገር እንደሆነ ግን ለእኔ ሊገባኝ ባይችልም
‹‹አኸ!! ለራስሽ ብለሽ ነዋ ያዘጋጀሽው?››
‹‹አነተ..አረ አበልጆቼ አክፋይ ሲመጡ አምጥተውልኝ ነው…ሆሆሆ..!!!እንዲሁ በባዶውስ መች ቻልኩህ?›››አለችውና ለምን እንደሆነ አላውቅም ደንግጣ ወደእኔ አየች እሱንም ሳየው ምቾት አይነበብበትም
‹‹.ደግሞ መች ቻልኩህ ስትል ምን ለማለት ፈልጋ ነው ?ነው ወይስ ይዋጣልን ተባብለው ይደባደቡ ይሆን?››ብዙ ጊዜ የትልልቅ ሰዎች ወሬ ለምን እንደሚወሳሰብ አይገባኝም….ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ሲሆን አፍ ለአፍ ገጥመው ትንሽ በመንሾካሾክ ልሰማው ያልቻልኩትን ነገር ከተነጋገሩ በኃላ እኔና አባቴ ተያይዘን ወደ አጐቴ ቤት ተመለስን ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ቡኃላ አባቴ ድንገት ሹልክ ብሎ ጠፋ….ከአጐቴ ልጅ ጋር እየተጫወትኩ እና እየተላፋው ልጠብቀው ብሞክርም የውሀ ሽታ ሆኖ ቀረ… እኔም ድካም አዛለኝና በእንቅልፍ ተሸነፍኩና ተኛው..ጥዋት ስነሳም አልመጣም
ግራ ገባኝ ‹‹ጥሎኝ ወደ ቤት ተመለሰ እንዴ….?››የአጐቴን ሚስት ጠየቅኮት
‹‹አይ አለ እዚሁ ነው አረፋፍዶ ይመጣል››አለቺኝ ቅሬታ በሚነበብበት ፊት…
እኔ ግን ከዚህ በላይ በትዕግስት ልጠብቀው አልፈለግኩም….አረሳሳውና ማንም ሳያየኝ ሹልክ ብዬ ወደ ትናንትናዋ ሴትዩ ቤት አመራው
ስደርስ አባቴ እንደ ትናንትናው መቀመጫ ላይ ሳይሆን ሴትዬዋ አልጋ ላይ ጉብ ብሎል..ስሩ ያለው ጠረጰዛ ላይ በጓዱጓዳ ሰሀን ትኩስ እንፋሎቱ ከላዩ ላይ መትነን ያላቆመ ገንፎ ቀርቦለታል..እሷም ከጐኑ ቁጭ ብላ እየተጐራረሱ ሳለ ነበር ድንገት ዘው ያልኩባቸው ሁለቱም ብትን ብለው ነው የደነገጡት
‹‹እንዴ ምን ሆንክ ?››አለኝ
‹‹ጠፋህብኛ››መለስኩለት
‹‹ከልጆቹ ተጣላህ እንዴ?››
‹‹አልተጣላውም ግን ጠፋህብኝ››ደግሜ ያንኑ ዓረፍተ ነገር በመናገር ወቀሳዬን አጠናከርኩ
‹‹ና ግባ ቁጭ በል ከአባትህ ጐን››አለቺኝና ሌላ ማንኪያ አምጥታ አስጨበጠቺኝ በልተን ከጨረስን ቡኃላ እሷንም ሆነ የአጐቴን ቤተሰቦች ተሰናብተኝ የመልስ ጉዞ ወደ ቤት እንደደረስን አባቴ በቁሙ እኔን እቤት አስገባኝና ወጥቶ ወደ ዙረቱ ሄደ እናቴ ልጄ እርቦታል ብላ በቆንጆ ሁኔታ ከሰራቸው ልሙጥ ሽሮ በግማሽ እንጃራ ላይ ፈሰስ አድርጋ
አቀ
👍8
ረበችልኝ..ገና ሳየው ዘጋኝ
‹‹በቃኝ››
‹‹ምነው?››
‹‹አራበኝም..ገንፎ ብዙ ቅቤ ጭቅ ያለበት ጥግብ እስክል ነው የበላውት››አልኮት እንደ ቤተክርስቲያን ከበሮ የተወጠረውን ሆዴን ገልጬ እያስቃኘዋት
‹‹ይመኙሻል እኮ ጐበዝ ነች..እኔም የእሷ ገንፎ ናፍቆኛል››አለቺኝ ይመኙሻል ማት የአጐቴ ሚስት ነች‹‹የእሷን ገንፎ እኮ አይደለም የበላውት…. እነሱ ጋር ቁርስ ገንፎ ሳይሆን በሶ ነበር››
‹‹እና ታዲያ የት በላህ?››
‹‹ከአባዬ ጋር ሌላ ቦታ ሄደን ነው የበላነው›› የዚህን ጊዜ የእናቴ ጆሮ ለወሬ ሲቀሰር ታወቀኝ፡፡እኔ ደግሞ ለማወራው ወሬ ትኩረት ሲሰጡኝ ደስታዬ ይጨምራል የማውራት ሞራሌም ከገደብ ያልፋል
‹‹ሌላ ሴትዬ ማነች?››
‹‹ከእነ አጐቴ ቤት ወደታች በሚወስደው መንገድ ሀኪም ቤቱ ጋር ልትደርሺ ስትይ የሆነ ቀርከሀ አጥር ያለው ቤት የለም?››
‹‹አዎ አለ››
‹‹ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ ኪወክስ ያለበት ቤት የለም?››
‹‹አዎ አለ››ጮክ ብላ በተሞጠጠ ትዕግስት
‹‹እዛ ቤት ፀዳለ የምትባል ሴት የለችም?››
‹‹አለች አልህ እኮ››አንቦረቀችብኝ….ግን እኮ አላላችኝም
እሷ ቤት ነው ገንፎ የበላነው እናቴ ተንጨረጨረች እናባዋ ሁሉ በዓይኖቾ ግጥም አለባት..እኔም በዛው ልክ ግራ ገባኝ… እስቲ የእኛ ገንፎ መብላት እሷን እንዴት ነው እንዲህ ሊበሳጫት የቻለው?ነው ወይስ ገንፎ ጥሩ አይደለም ሌላ ምግብ ለምን ሳታበላቸው ብላ ተናዳ ይሆን ?
‹‹ጥዋት ቁርስ ስለሆነ ነው እንጂ ማታ እኮ የሚጣፍጥ ዶሮ ወጥ… እንቁላል ስጋ ሁሉ ያለበት ነው የበላነው››
‹‹ይህቺ ናት እና ልጅት..ደግሳ ነዋ የጠበቀቻችሁ››
‹‹አዎ ደግ ሴት ነች ግን የሆነ ስጋ ላይ…››
‹‹እሺ የሆነ ስጋ ላይ ምን ሆነ?›.እናቴ ነች የወሬ ረሀቦ እያንቀጠቀጣት የጠየቀችኝ፡፡
‹‹ሁለቱ ብቻ እንደዚህ ከጫፍና ጫፍ ያዙና ጐትተው በመበጠስ ከተካፈሉ ብኃላ ለእኔ ሳይሰጡኝ ለራሷቸው ተጐራረሱ
‹‹መቋደሻም እስከመቋደስ ደርሰውልኛላ..የለውማ፡፡ እናትህን ነዋ ወስዶ ያስተዋወቀህ››
‹‹ኸረ እናቴ አይደለችም››ገና ለገና ለአንድ ቀን ዶሮ ወጥ እና ገንፎ ስላበላች እንዴት ነው አስናቴ የምትሆነው?››
‹‹ነች ባክህ››ብላኝ እቤቱን ጥላልኝ ወጣችና ወደ ጐሮ
የእናቴ የብስጭት መንስኤው ምንም ሊገባኝ አልቻለም…..ነው ወይስ ዶሮ ወጥ አምሮት ይሆን? ሴትዬዋን ለምኜት ይዤላት በመጣው ኖሮ… ብዬ ተቋጨው፡፡ ተነሳውና ወደ ጐሮ ተከተልኮት እያለቀሰች ነበር ፡፡ ሄድኩና ስሮ ቆምኩ ፈርቼያታለው..ትመታኛ ይሆን..?ብዬ ሳስብ ጭራሽ ወደ ራሷ ጐተተቺኝና ጉልበቶ ላይ አስተኝታኝ ፀጉሬን ታሻሽልኝ ጀመረ፡፡
‹‹ውሻዬ››
‹‹አቤት እማ››
‹‹ማታ ከማን ጋር ነው የተኛሀው …ፈራ ተባ እያለች በፍራቻ የጠየቀችኝ ጥያቄ እንደሆነ ያስታውቅባታል
‹‹ከነ ደጉ ጋር››መለስኩላት ደጉ ማለት እኩያዬ የሆነ የአጐቴ ልጅ ነው
‹‹አባትህስ?››
‹‹እሱ እኔ እንጃ የት እንዳደረ››
‹‹እንዴት?››
‹‹አላውቅማ… ማታ መጣው ብሎ ወጣና ቆየብኝ እኔ እንቅልፍ ወሰደኝ ፡፡ጥዋት ስነሳ እቤት የለም እና ፈለግኩትና ሳጣው እዛ ሴትዬዋ ጋር ሄድኩ.. አልጋዋ ላይ ቁጭ ብሎ ገንፎ ሲበላ ደረስኩ … ከዛ እኔም አብሬያቸው በላው››
ከዛ ኃላ እናቴ ፀጥ አለች፡፡ከተወሰነ ቆይታ ብኃላ ከተቀመጥንበት ተነሳንና ወደቤት ገባን..ትልቁን ሻንጣ አወጣችና የእሷን እና የእኔን ልብስ ብቻ እየመረጠች ትጠቀጥቅ ጀመር ….ግራ ገባኝ
‹‹እማ የት ልንሄድ ነው?››አልኮት
‹‹አያቶችህ ጋር››አለቺኝ ለስለስ ብላ..ደስ አለኝ በህይወቴ አያቶቼ ጋር እንደመሄድ የሚያስደስተኝ ነገር የለም
‹‹ግን ትምህርቴስ?››
‹‹አስፈቅድልሀለው›› ብላ አረጋጋችኝ
ሌላ የሚያሳስብ ሀሳብ ደግሞ በአዕምሮዬ መጣብኝ
‹‹አባዬስ ከእኛ ጋር ይሄዳል?››
‹‹ሁለታችን ብቻ ነን የምንሄደው››
‹‹ግን ምሳ ምናምን ማን ይሰራለታል?››
‹‹አይዞህ አታስብ አፀደ ጋር ሄዶ ይበላል››አለቺኝ
ሻንጣውን ጠቅጥቃ ዚፑን ዘጋግታ ከጨረሰች ቡኃላ ሻንጣውን ወደ በራፍ ጐትታ ለጉዞ እና ለነገር ዝግጁ ሆና አባቴን ትጠብቅ ጀመር፡፡
ቀጠዩ እና የመጨረሻው ምእራፍ ነገ ይቀጥላል
ብዙም ዛይቆይ አንድ የእናቴ ጓደኛ ወደ ቤታችን መጣች፡፡
‹‹ምን ሆነሽ ነው አይንሽ ያባበጠው?››እናቴን በማዳነቅ ጠየቀቻት
‹‹አይ ምንም አልሆንኩ…ዝም ብዬ ነው››
‹‹እንዴት ዝም ብለሽ ?አይንሽ እኮ ደም ለብሷል››
‹‹ቁጭ በይ ባክሽ›› አለቻት እናቴ ቆማ በጥያቄ ምታፋጥጣትን ጐደኛዋን…ልትቀመጥ ወደመቀመጫዋ ስትሄድ ዓይኖቾ ለጉዞ ዝግጁ የሆነው ሻንጣ ላይ አረፈ
‹‹እንዴ !!!ሻንጣ የት ለመሄድ?››
‹‹ወደቤተሰቦቼ ››
ኸሀ ገባኝ..ከባልሽ ጋር ተጣላቹ ማለት ነው?››
ዝም አለች እናቴ
‹‹ንገሪኝ እንጂ ምን ይዘጋሻል..ከእኔ ምን ምደብቂው ነገር አለሽ?››
‹‹ባክሽ ሰውዬው ፀዳለ ምትባል ሴት ወሽሞል አሉ››አለቻት…‹‹መወሸም ››ማለት ምን ማት ነው? አልገባኝም..ግን የሆነ መጥፎና የሚያናድድ ነገር እንደሆነ ገባኝ፡፡
‹‹ አትይኝም…ውይ ወንዶች!!!!›› ከእናቴ በላይ ተንዘረዘረች
‹‹ይሄውልሽ እንዲህ ተጫወተቨብኝ እልሻለው››
‹‹ለመሆኑ ካንቺ ምን አጣው ብሎ ነው?››አለቻት በከፍተኛ ማዳነቅ አፎን በእጆቾ አፍና
‹‹ያንቺስ ባል አንቺን ጥሎ ቤቱን እና ልጆቹን ጥሎ ሌላ አግብቶ የሄደው ካንቺ ምን አጥቶ ነው?››አናዳጅ ጥያቄዋን በአናዳጅ ጥያቄ መለሰችላት
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው…ወንዶች ሲባሉ ያቺንም.. ያቺንም መልከፍ የሚወዱ ውሾች አይደሉ››
‹‹እና እንደዛው ነው››
‹‹እና ምን ልታደርጊ ነው?›.
‹‹በቃ ልጄን ይዤ ወደቤተሰቦቼ እሄዳለው….ከፈለገ ያምጣትና አብሮ ይኑር››
‹‹ጐበዝ..የታባቱ!!1 ይብላኝ ለእሱ እንጂ አንቺስ ደህና ቤተሰቦች አሉሽ..በዛ ላይ ገና ነሽ የፈለግሽውን ማግባት ትችያለሽ››አትል መሰላችሁ ስሬ ያለውን የውሀ ብርጭቆ አንስጬ ግንባሮን ብተረክክላት ደስ ይለኝ ነበር…እየሰማው አባቴን ‹ምናባቱ› ብላ ፊቴ ትሰድነበዋለች በጣም አናደደችኝ፡፡
‹‹አረ የምናባቱ ማግባት..ሁለታኛ…አርፌ ልጄን አሳድጋለው..ብቻ በሰላም ይልቀቀኝ እንጂ››
‹‹እሱማ ያው ሽማጊሌ ማንጋጋቱ አይቀርም››ቀጠለች ጐደኛ ተብዬዋ
‹‹…አይ እንዴት አንጀቴ እንዳረረ አታውቂም…. እንኮን የሰው ሽማግሌ ይቅርና እግዚያብሄርን ቢልክ አልሰማው፡፡ታውቂያለሽ አይል..ይሄ እኮ የመጀመሪያው አይደለም ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ በደል በድሎኝ ለልጄ ስል ነበር በመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ይቅር ያልኩት አሁንማ እራስን ማስናቅና የእሱ መጫወቻ መሆን ነው..በሽታውን ተሸክሞብኝ መጥቶ ልጄን እንዳላሳደግ አጉል ቢያደርገኝስ?››
‹‹እና ጥዋት ልትሄጂ ነው?››
‹‹አዋ አሁንም መኪና አላገኝም እንጂ እዚህች ቤት ማደር አልፈልፈግም ነበር››
‹‹ይሁን እስቲ እኔም ሰሞኑን ስለምመጣ ጠይቅሻለው አይዞሽ በርቺ እንደእኔ ጥሎሽ ከመውጣቱ በፊት አንቺ ቀድመሽው ጥለሽው መውጣትሽ አሪፍ ነው››ብላ የውሳኔዋን ትክክለኝነት አረጋገጠችላት እና እናቴን አበረታታ እና ተሰናብታ ከቤት እንደወጣች እኔም ከኃላ ዋ ተከትዬት እቤቱን ለቅቄ ወጣው ነገ ወደ አያቶቼ መሄዴ ቁርጥ ጉዳይ ስለሆነ ጐደኞቼን ለመሰናበት…ስዞር ቆይቼ ሲጨልም ወደቤት ተመለስኩ አባቴ አልመጣም እናቴ ሰውነቴን አጥባ እራቴን አብልታኝ ‹‹ በለሊት ስለምንነሳ በጊዜ ተኛ›› ብላ አስተኛችኝ ረጅም ቀን አሰዋልፌ ስለነበር ወዲያው እንቅልፍ ወሰደኝ ስንት ሰዓት እንደሆነ አላውቅም በግምት ከለሊቱ 5 ወይም 6 ሰዓት ይሆን ይመስለኛል ሀይለኛ የበር መንጐጐት ከእንቅልፌ አባነነኝ
👍71
...እናቴ ሳያት ከመተኛቴ በፊት የተቀመጠችበት ቦታ እንደተቀመጠች ነው..እስከአሁን እንዳልተኛች በሁኔታዋ ያስታውቃል፡፡
‹‹አንቺ ሴትዬ አትሰሚም እንዴ?››የአባቴ ድምፅ ነው..ትንሽ ኮልተፍተፍ ብሎል፡፡ልከፍትለት ከአልጋዬ ስወርድ
‹‹አርፈህ ተኛ››ብላ አንቦረቀችብኝ..ከራማዬ ተገፈፈና ወደ መኝታዬ ተመለስኩ
‹‹ኸሀ… እየሰማሽ ነው ለካ..?ነው ወይስ ማልመጣ መስሎሽ ያስገባሽው ሰው አለ ?››
‹‹ሰው ሁሉ እንደአንተ ሸርሙጣ ይመስልሀል አይደለ?››ብለው እርፍ..ይ እንግዲህ ሰውን ቀና ብላ ማናገር እንኮን ከምትፈራው ከጭምቶ እናቴ የወጣ ዓረፍተ ነገር ነው
‹‹ሸርሙጣ…እኔ ሸርሙጥ?››ይሄንን በር ሳልገነጥለው ክፈቺ››አባቴ ድንፋታ መጠኑን ጨመረ
‹‹አልከፍትም..ትናንት ያሳደረችህን ጋር ሄደህ እደር››
በራፉን የተደረመሰ እስኪመስል ተነቃነቀ..እናቴ ተሸነፈችና በአቋሞ መፅናት አቅቶት የበራፉን መሸንጐሪያ ጐትታ አላቀቀችው..በር ወለል ብሎ ተበረገደ፡፡ አባቴም ተንደርድሮ ወደ ውስጥ እንደገባ መሀል ወለል ላይ የተገተረችውን እናቴን በጥፊ አላሳት..በርግጫ ደገማት..፡፡ በቅፅበት ቤቱ ቀውጢ ሆነ፤ እኔም እሪታዬን አስነካውት…የእሷን ጩኸት ማስቆም ሲያቅተው ወይም የእኔ ጩኸት ከእሷ ጩኸት በላይ ስለረበሸው ይመስለኛል ተንደርድሮ መጣና በዛ ሰፊድ እጁ አንዴ በጥፊ ሲያልሰኝ ፀጥ አልኩ ..በቃ ድዳ ሆንኩ፡፡እናቴ ግን ጭራሽ አበደች‹‹ልጄን አትንካው..እኔኑ እንደጀመርክ ጨርሰኝ….ይሄውልህ…››በዚህን ጊዜ ጐረቤቶቻችን ከየአቅጣጫው የጩኸት ድምፅ ሰምተው ይመስለኛል እየተሮሮጡ ሲመጡ ተሰማ…..ደርሰው ቤታችንን ደጃፍ አልፈው ወደ ውስጥ ገመዝለቃቸው በፊት አባቴ እየተንገዳገደ ሄዶ በራፉን ጠረቀመባቸው
እናቴ ‹‹አሳወጣኝ እዚህ ቤት አላድርም፣››ብትል ከውጭ ያሉት ሰዎች ‹‹በራፉን አንዴ ክፈትልን ››ብለው ቢማጸኑት..በራፉን ቢደበድቡ አንባገነኑ አባቴ ሊሰማቸው አልፈልግም፡፡ ቡኃላ እናቴ ተስፋ ስትቆርጥ መሰለኝ ጐረቤቶቾን‹‹ በቃ ወደ ቤታችሁ ግቡ… ብቻ ያደረገኝን ሁሉ በልቦናችሁ ይዙት ..ሞቼ ከተገኘውም እሱ እንደሆነ እወቁና ለዘመዶቼ ንገሩልኝ ሰላም ካደርኩ ነገ በህግ አንቀባርረዋለው..መንግስት ባለበት ሀገር እንዲህ አይጫወትብኝም..የሴቶች መፍት በተከበረበት ዘመን ላይ ነው ያለነው…››በማለት ከሰፊ መግለጫ ጋር እንዲሄዱ አደረገች፡፡ከዛ ቡኃላ ሲጨቃጨቁ ሲነታረኩ‹ ተኚ …አልተኛም፤ ልንካሽ …አትነካኝ› ሲባባሉ እኔ ሳዳምጥ ሳዳምጥ እነሱ ከመድከማቸው በፊት እኔ ዛልኩና እንቅልፍ ይዞኝ ጥግ አለ፡፡
…. ስባንን የጥዋት ፀሀይ በበራፋችን ስንጥቅ ወደ ቤት ገብቶ ሳሎናችንን አድምቆታል፡፡ አባቴ በጥፊ ያላሰኝ ፊቴ እየለበለበኝ ነው‹‹..እንዲህ አቃጥሎኝማ ሁለተኛ አላናግረውም ..አሁኑኑ ነው ጠዬው ወደ አያቴቶቼ ጋር እናቴን ተከትዬ የምሄደው…››በማለት ዓይኔን በመከራ ከፈትኩና ከአልጋዬ ወረድኩ..እናቴ ያሰናዳችው ሻንጣ እዛው በራፍ አካባቢ ዝግጁ እንደሆነ ነው
‹‹…እናቴ የት ሄደች..? እንዴት እስከአሁን አረፈደች…? በለሊት አልነበረ እንዴ እንሄዳለን ያለቺኝ?›› ግራ እንደተጋባው ዝም ብዬ ወደ ወላጆቼ መኝታ ቤት አመራው በራፉ አልተቀረቀረም ገርበብ እንዳለ ነው፡፡ገፋ አደረግኩና ወደ ውስጥ ገባው ጠላታችሁ ክው ይበል ክው ነው ያልኩት..ከዛን ቀን በፊት ሆነ ከዛ ቡኃላ በእንደዛ ዓይነት ሁኔታ ደንግጬ አላውቅም….ከወገብ በላይ ሁለቱም እርቃናቸውን ናቸው.. እቅፍቅፍ ብለው ከመጣበቃቸው የተነሳ ሁለት ጫንቅላት ያለው አንድ ሰው ነው የሚመስሉት፡፡የ ሁለቱም ልብስ ወለል ላይ ተዝረክርኮል፡፡በሁለቱም በጣም ተበሳጨው… በተለይ በእናቴ ፡፡አስጠሉኝ ፡፡ተመልሼ ወደ ሳሎን ገባው የእናቴን የገንዘብ ቦርሳ ጠረጵዛ ላይ አየውት… ከፈትኩት እና ከውስጡ የተወሰነ ብር ዛቅ አድርጌ ኪሴ ከተትኩ፡፡እናቴ ስትፎክርበት እና ስታስፈራራበት ያመሸችውን ትልቅ ሻንጣ ከፈትኩና ከውስጡ ራሴን ልብሶች መርጬ በትንሽ ፔስታል ጨመርኩና የሳሎኑን በር ከፍቼ ቤታቸውን ለቅቄላቸው ወጠው ፡፡ወደ መነኸሪያ..ሁለቱም ናቸው ያስጠሉኝ፡፡ እነደዛ ለእሷ ስል በጥፊ ተቃጥዬ ጭራሽ አቅፋው ትተኛለች..?ኸረ ከእነዚህ ጋር ማን ይኖራል…? አያቶቼ ይሻሉኛል፡፡

💫አለቀ💫

Like 👍እየቀነሰ ነው አትቆጥቡ😜
👍 እያረጋቹ

አስተያየታችሁን በ @atronosebot አድርሱን
👍8😁4
#የመልስ_ጉዞ_ወደመነሻ
:
#ክፍል_ሁለት
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...ኢትዬጵያን በዩቶፐያ ፅንሰ ሀሳብ ዳግም መገንባት ከአያቴ የወረስኩት ህልሜ እና ዓላማዬ እንደሆነ ነግሬያችኃለው …ግን እንዴት አድርጌ ነው የማሳካው …?እንደማሳክው የማምነው ከራሴ በላይ በሚስቴ እምነት ስላለኝ ነው፡፡ሚስቴ …የዋናው የታሪኬ ማጠንጠኛ እሷ ነች፡፡እሷ ደግሞ መንፈስ ነች፡፡ገራሚ መንፈስ፡፡አስፈሪ መንፈስ፤ታሪካዊ መንፈስ፤አፍዛዥ መንፈስ…ሁሉን አድራጊ ፈላጭ ቆራጭ መንፈስ፡፡አዎ ስለእሷ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር የደረስኩበትን እና ያወቅኩትን ብቻ ነው፡፡ያንን ስላችሁ በቃ ስለእሷ የማትነግረን ጥቂት ነዋ..?››ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡አይደለም:: እንደውም በተቀራኒው የምነግራችሁ ከእሷ ታሪክ አንጻር ጥቂቱን ግን በእኛ በሰውኛ ልኬት ከጆሮአችን የመስማት አቅም በላይ ከአይኖቻችንም የማየት ጉልበት በላይ በሆነ መጠን ነግራችሆለው፡፡
ምክንቱም ይህቺ ፍቅሬ ከሰፈር ጎረምሳነት በአንዴ ስለዓለም መፅአዊ እጣ ሚያስብና ለዛም የሚሰራ የሚተጋ ሰው አድርጋ መልሳ ዳግመኛ የፈጠረቺኝ ሴት ነች፡፡እሷ ደፋርም ገራሚም ፍጡር ነች፡፡ ሁሉ ነገር የማድረግ አቅም እንዳላት አምናለው፡እንዴት አድርጌ የምታደርገው ነገር ሁሉ የምትለውን ሁሉ አምናታለው፡፡የማምናት ጅል ሆኜ አይደልም፡፡በአፍቃሪነቴም ዓየነ-ልቦናይ ታውሮም አይመስለኝም፤የምትሰራቸውን የእጆቾን ተአምራቶች በአይኖቼ ደጋግሜ ሳላየው ላለማመን አልችልም፡፡ ግን ደግሞ ሚስጥሯን ሁሉ ትነግረኛለች ብዬ አላስብም…ከእኔ የተደበቀ የሆነ ዕቅድ ያላት መስሎ ይሰማኛል ፡፡ቢሆንም ደፍሬ ጠይቄያት አላውቅም፡፡
ግን የምታወራው ስለአፈቀርካት ሴት ነው ወይ..? ካላችሁኝ አዎ ስለእሷው ነው፤ግን እንደምታውቋት አይነት ሴት ብቻ አይደለችም… መንፈስም ጭምር ነች፡፡ምን አይነት መንፈስ..?እሱን ወደ ፊት አስረዳችሆለው….
ይህቺን ሴት ያገኘዋት በተለየ አጋጣሚ ነው፡፡በህይወቴ የመጨረሸውን ሀዘን ባዘንኩበት ቀን …የመጨረሻውን እጦት ባጣውበት ቀን…ወደ ልቤ ደም የሚወስዱና የሚመልሱ ትላልቅ የደም ስሮች የተበጠሱ የመሰለኝ ቀን፡፡አዎ የዛን ቀን ነበር ያገኘዋት …፡፡እንዴት እጦቴን በተአምሮ መለሰችልኝ…ሀዘኔን በድንቅ ስራዋ ወደምስራች ቀየረችልኝ…የተበጣጠሱትን የልብን ደም ስሮች ቀጣጥላ ለሞት ከቆረጥኩበት ስሜት አውጥታ መኖርን እንድናፍቅ አደረገቺኝ እና በዛኑ ቅፅበት ይህቺን ሴት ደነዘዝኩላት….፡፡
ወዲያው ነበር እግሯ ስር ተንበርክኬ እንዳፈቀርኳት የነገርኳት..ይቺን ሴት ፍቅሬን እንደተቀበለች ነበር ትንፋሽ ሳልሰጣት እንድታገባኝ የጠየቀኳት፡፡አግቢኝ ስላት ቤት አልነበረኝም .አግቢኝ ስላት ስራ አልነበረኝም…አረ አግቢኝ ስላት የሀይስኩል ትምህርቴን እንኳን አልጨረስኩም…አግቢኝ ስላት የማግባት ዕቅድም አልነበረኝም….አግቢኝ ስላት ዕድሜዬ እንኳን 18 ሊደፍን ገና 3 ወራቶች ይቀሩት ነበር..
ይህ ሁሉ ቢሆንም ዳሩ እንድታገባኝ ስጠይቃት
-እንዳገባህ የጠየቅከኝ ውለታ ስለዋልኩልህ ነው ወይስ ስላፈቀርከኝ›ነበር ያለቺኝ
-ሁለቱም ምክንያት ነው፡፡-መለስኩላት
-ይሁን የመጣውትም አንተን ለማግባት ስለሆነ ተቀብዬሀለው ››አለቺኝ
-አልገባኝ
-ቀስ ብሎ ይገባሀል ..ለማንኛውም ጥያቄህን ተቀብያለው ፡፡አገባሀለው፡፡
መልሶን ስሰማ ደንግጬ ነበር..እሺታዋን ስሰማ ፈዝዤ ነበር፡፡አዎ እሺታዋን አልጠበቅኩም ነበር፡፡
-ግን ቆይ የመጣውት ስትይ ከየት ነው የመጣሽው.?
ከዛኛው አለም ….ላለፈት መቶ አመት እዚህ አልነበርኩም፡፡
-ያው እየቀለደች ነው ብዬ
‹ከዛ በፊትስ?፡›ጠየቅኳት
-ከዛ በፊት አንድ አራት ጊዜ ተመላልሺያለው፡፡ፈርዶብኝ ጀግና ወዳለው፡፡በዚህ አካባቢ ማለቴ በኢትዬጵያ ጀግና መኖሩን ከሰማው በርሬ ለመምጣት ቀናትን አላባክንም›
-ይገርማል…አሁን ታዲያ ማን ተገኝቶ ነው የመጣሺው.?›
-ነገርኩህ አንተን..
-እኔን …እኔ ታዲያ እንዴት ነው ከሌላ አለም የሚመጣልኝ ጀግና የሆንኩት?››ጠየቅኳት ያው በቀልድ ቅላፄ
-አይ እስከአሁን እንኳን ጀግና አይደለህም ….ግን ጀግና የሚሆን ልብ ይዘሀል፡፡በሺ አመት አንዴ የሚገኝ ጀግና ልብ…ስለዚህ አገባሀለው፡፡ግን አንድ አላማ አለኝ ያንን እንዳሳካ ታግዘኛለህ …እርግጥ ለእኔም ብቻ ሳይሆን ለአንተም ይጠቅማል፡፡
-አረ ግድ የለም ፡፡ለአንቺ ብቻ የሚጠቅምም ቢሆን ያልሺኝን ሁሉ አደርገዋለው›አልኳት ከልቤ እንደማደርገው በውስጤ እየማልኩ
የእለቱ ንግግራችንም ሆነ ጠቅላላ ታሪኩ በዚህ አልተቆጨም ሙሉውን ወደፊት አወራችሆለው …አሁን ከዚያች የህይወት አጋጣሚ አክለፍልፋ ወስዳ እሷ እጅ ወይም ልብ ላይ እስክትጥለኝ ድረስ ያሰለፍኩትን የእኔንና የቤተሰቤን ታሪክ ልክ እንደቅምሻ በሚቀጥሉት ክፍል አወራችሁና ስጨርስ ወደመነሻዬ እመልሳችሆለው፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3
#አስራ_ሶስተኛው_ፍቅር !

እንዴት ዋላችሁ ህዝቤ? ሁሉ ፒስ ነው ወይ? በቃ ምንም እንደሌለብህ ሐገርህን ለአክቲቪስት ጥለህ ለጥ ትልልኛለህ ኣ? ለነገሩ ለምን ይዋሻል እኔም በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ሆኜ ነው ያደርኩት! ህልሜን ሁሉ በሪሞት እየቀያየርኩ ሳይ ነበር። “ደሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ” .... አሉ አበው (መቼስ የኛ ሐገር አበውና የኛ ሐገር አክቲቪስት ማይለው የለም) የምር ግን እኛ ድሆች በህልማችን ቅቤ ባንጠጣ ኖሮኮ ...... ያው አልጠጣንም ነዋ ምናባታችን እናመጣለን!😄
እና በተረፈ ሁሉ አማን ነው ወይ? እኔ ለአስራሶስተኛ ግዜ ፍቅር ይዞኝ መከራዬን ሳይ ነው የከረምኩት። ያው እንደህንድ አክተር ፍቅር ሚያጠቃኝ ነገር አለ ኣ?? .... ልቤ ተላላ ነገር ነው። ከአንድ ሴት ጋር ተግባብቼ ትንሽ ከተጨዋወትኩ ጠላታችሁ ቅይር ይበል ቅይር እላለሁ። ፈገግታዋ ልቤን ትርክክ ያደርገዋል። ሰባት ግዜ የሰማሁትን ቀልድ ስትነግረኝ እየተንፈራፈርኩ እስቃለሁ። አረ ስተኛ ራሱ በህልሜ አያታለሁ። ይኸው እኛ መስሪያቤት የምትሰራው ትርሲትም ሰው ነው ብላ ብትቀርበኝ አፍቅሪያት አረፍኩት! ባፈቀርኳት ማግስትም የናቲ ማንን «የመጀመሪያዬ ነው ሰው ስወድ አምርሬ» የሚለውን ዘፈን ጋበዝኳት! (በርግጥ «አስራሶስተኛዬ ነው ሰው ስወድ አምርሬ» አይባል ነገር ችግር ሆኖብኝ እንጂ የመጀመሪያዬንኳ አልነበረም!)
ከትርሲት ጋር ብዙ ግዜ አብረን ብንሰራም በፍቅር አይን አይቻት አላውቅም ነበር። ባለፈው የአንድ የስራ ባልደረባችን እናት ድንገት አረፉና ማታ ከመስሪያ ቤታችን ሰዎች ጋር ለቅሶ ቤት ሄድን።
ድንኳኗ በሰው ተሞልታለች። ወጣቶቹ በካርታ ቁማር እየተጫወቱ ድንኳኑን ካሲኖ አስመስለውታል። በሩ አካባቢ ቁጭ አልን። ያው እኔ አርፌ አልቀመጥም አይደል አይኔን ማንከራተት ጀመርኩ። እናንተ!! ሰዉ ይሄን ንፍሮ ይዝቀው የለ እንዴ? ጥግ አካባቢ ያለው ሰውዬማ ንፍሮውን ከሰሃኑ እየዘገነ በሁለቱም የጃኬቱ ኪስ ውስጥ ጠቅጥቆ ብድግ ሲል ቦንብ የታጠቀ ነበር የመሰለኝ።
ትንሽ እንደቆየን አንዱ ሰካራም ገድገድ እያለ ከውጪ ገብቶ ወደኛ ጠጋ አለና
«ጋሽ ለገሰ ሞቱንዴ?» አለን
«አይ የጋሽ ለገሰ ለቅሶ አይደለም» አልነው።
«አሃ አሃ! ለካ እሳቸው አምና ሞተዋል። ፊት ለፊት ያለው ግቢ የሚኖሩት መምህር ጥበቡ ነዋ የሞቱት» ሲል
«አረ ኔ አለሁ ምን ያሟርትብኛል ይሄ» አሉ ከኋላችን የተቀመጡ ሰውዬ።
በወሬው የተሰላቸው ሰካራም «በቃ ማንም ይሁን ማን የሆነ ሰው ሞቷል። ዋናው ጥያቄ እራት ሰአት አልፏል ወይ? የሚለው ነው» ሲለን ሳቃችንን እንደምንም ተቆጣጥረን ጠጋ ብለን አጠገባችን አስቀመጥነው።
ትንሽ ቆይቶ ራት ቀረበ። ፒፕሉ የተቆረጠውን እንጀራ እንደቆሎ ዘገነው። ሰውዬውም እንጀራውን እንደአንሶላ ደራርቦ ሰሃኑ ላይ ካነጠፈ በኋላ ወጥ አስደርጎ ከራሱ ጋር እየተሻማ ሁለት ሶስቴ ጎረሰና ረሃቡ መለስ ሲልለት ወደኔ ዞሮ
«ምን ሆነው ሞቱ ግን?» አለኝ
«መኪና ገጭቷቸው መሰለኝ» አልኩት። ከልቡ አልሰማኝም እንጀራውን እየጠቀለለ
«እና ተረፉ?» አለኝ
«እንዴት ተረፉ?» አልኩት ግራ ገብቶኝ
«ውይ የኔ ነገር ሞተዋል ለካ ... ባክህ ስሞትልህ አንዴ ላጉርስህ» አለኝ እንጀራውን ወደአፌ እያስጠጋ
«አይ በልቻለሁ ይቅርብኝ» ስለው «ይሁና» ብሎ ምግቡን ጨርሶ ከበላ በኋላ ከመቀመጫው ተነሳና ባርኔጣውን ከፍ አርጎ
«ያመት አመት ሰው ይበለን። መጥተን አንጣችሁ» ብሎ ወጣ።
በሰውዬው ሁኔታ እየሳቅን ሳለ ነው ትርሲት ከተፍ ያለችው! እግዚኦ ውበት! እግዞኦ ቁንጅና! ሰው ለቅሶ ቤት ለመምጣት እንዲህ ይሽቀረቀራል በናታችሁ? መስሪያ ቤት የማውቃት ትርሲት አትመስልም። ያቺን ትርሲት እዛው መስሪያቤት አወላልቃ ጥላ አዲስ ታጥቦ የተተኮሰ ቆዳ ለብሳ የመጣች ነው ምትመስለው። መስሪያ ቤት ጠቅልላ የምትቋጥረው ፀጉሯ ራሱ ተለቆ ትከሻዋ ላይ እየተዘናፈለ ልዩ ውበት ሰጥቷታል (ያው የራሷ መሆንና አለመሆኑ በሂደት ይጣራል) አንገቷን እንዳቀረቀረች ወደድንኳኑ ገብታ ተቀመጠች።
«እቺን ልጅ እስካሁን እንዴት አላፈቀርኳትም» አልኩ በልቤ። አንዳንዴኮ አይጋርድባችሁ ወንድሞቼ!
ከለቅሶ ቤቱ ስትወጣ ተከትያት ወጥቼ ሸኘኋት። በቃ ከዛን ቀን ወዲህ ተቀራረብን። በየቀኑ መገናኘት ጀመርን። ሻይ ቡናም ተባባልን። አረ እራትም በልተናል። በርግጥ እራት በላን ከምል ማጅራት ተመታሁ ብል ይቀለኛል።
ማውቀው ቤት አለ ብላኝ የከተማዋ ቱጃሮች ሚዝናኑበት ባር እየጎተተች ይዛኝ ሄደች።
የባሩ ዋቴ የጀመረው ገና ስንገባ ነው። ጋርዱ ጠብ እርግፍ ብሎ እጅ ነስቶ በር ከፍቶ በትህትና ሲያስገባኝ ነው መፍራት የጀመርኩት። ልክ ገብተን እንደተቀመጥን አስተናጋጇ ወርቃማ ፍሬም የሚመስል ሜኑ አመጣች። ትርሲት ልክ ማትሪክ እንደሚፈተን ሰው ሜኑውን በጥሞና ስታነብ ቆይታ የሆነ ምግብ አዘዘች። እኔም አይኖቿን እያየሁ ፈዝዤ እሷ ያዘዘችውን አምጪልኝ አልኩ። ከአፍታ ቆይታ በኋላ በሁለት ሰሃን ባቄላ ቲማቲም ምናምን ቀረበልን። ስታርተር መስሎኝ ዋናውን ምግብ ስጠብቅ ቀረ። ቢቸግረኝ ባቄላዬን በላሁና ሚጠጣ ለማዘዝ ቀና ስል አስተናጋጇ አጠገቤ ደርሳ «ምን ይጨመር የኔ ጌታ» አለችኝ። አስተናጋጇ ቤቱን ለማየትም እድል አትሰጥም። ቀና ባልኩ ቁጥር ተፈናጥራ እየመጣች «ምን ይጨመር» ስትለኝ ነው ያመሸችው። ዋይን በግላስ አዘዝኩ። ትርሲትም ነጭ ዋይን አለች። ብቻ ላሳጥረውና ቢሉ መጥቶ የወር ደሞዜን ዱቅ አርጌ ያን ምሽት እንዳኮረፍኩ ብዙም ሳናወራ ተለያየን።
ትርሲት ሁሉ ነገሯ ጥሩ ነው። እሷን ማፍቀሬም የሚካድ አይደለም። ግን ችግር አለ! በጣም ጨምላቃ ነች! ፍላጎቷ ከኔ አቅም በላይ ነው። ፋይፍ ስታር ሆቴል ካልሄደች እህል አይወርድላትም። አራት ዲጂት ያለው ቢል ካልመጣ የተዝናናች አይመስላትም። ሳስበው የቀድሞ ቦይፍሬንዷ ከሜቴክ ጋር ግንኙነት ሳይኖረው አይቀርም። መርከብ የበላ እንጂ እንደኔ አይነት ሚጢጢ ደሞዝ ሚበላ ሰው አይችላትም። በቃ ሁሉ ነገሯ ወጪ አለው። አንዳንዴማ የነዳጅ ጉድጓድ ያለኝ ሁሉ ሳይመስላት አይቀርም።
ፍቅርኮ ደስ የሚለው እንደአማርኛ ፊልም ቆሎ እየቆረጠሙ በሻይ እያወራረዱ፣ በቆሎ እየጋጡ ወክ ሲያደርጉ ምናምን ነው። እቺኮ ከእንትን ባር ወደእንትና ላውንጅ ነው። ከእንትና ላውንጅ ወደእንትና ስፓ ነው። ሁሉ ነገሯ ኤክስፔንሲቭ!
ቁጭ ብዬ የወደፊት ሂወቴን ከሷ ጋር ማሰብ ጀመርኩ። ምርጫዬ ሁለት ነው። ወይ ባንክ መዝረፍ ወይ ፍቅር ምናምን ሚባለውን ነገር እርግፍ አርጎ መተው! ድህነቴን እንደዘንድሮ ጠልቼው አላውቅም። ሟቹ ጠቅላያችን “ትልቁ ጠላታችን ድህነት ነው” ያሉት ራሱ እንደኔ አይነቷ ገጥማቸው ሳይሆን አይቀርም! .... ትርሲትን መተው ከባድ ነው። ባንክ መዝረፉም ቀላል አይደለም። ይሄኔኮ «ምን ጣጣ አለው ሰው አስራስምንት ባንክ ይዘርፍ የለንዴ» ትዪ ይሆናል አዳሜ። (ወዳጄ አንድ ቡድንኮ ከሶስት ግዜ በላይ ባንክ ከዘረፈ ከስተመር ነው እንጂ ዘራፊ አይባልም። እንደውም ባንኩ ቆጥሮ አስፈርሞ “አትጥፋ በሰላም ግባ” ምናምን ብሎ ነው ሚሸኘው)
በቃ ተሸበለልኩ! ነፋስ ሆንኩ! በኪሎሜትር እራቅኋት!
«አቅምን አውቆ መኖር ጥሩ ነው» ብሎ የዘፈነው ሰዉዬ ማን ነበር? ....ብቻ ማንም ይሁን ማን አፈላልጋችሁ የክብር ዶክትሬት ስጡልኝ!😂

🔘ዘውዳለም ታደሠ🔘
👍5😁1
#የመልስ_ጉዞ_ወደመነሻ
:
#ክፍል_ሶስት
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
....እናቴ ማለት….፨
ለእናቴ ያለኝ እይታ አምልኮ ደረጃ የደረሰ ዓይነት ነወ ፡፡ይሄን ቃል ስናገር በአላዋቂነት ስሜት ልቤን በትዕቢት አጨልሜ አይደለም፤በፍጽም ወይን
ም በእግዜያብሄር የፈጣሪነት ስልጣን ላይ እምነቴ የላላም ስለሆነም አይደለም፡፡አዎ ብቻ እንደዛ ማለት ስላለብኝ ነው፡፡እውነትም ስለሆነ ነው፡፡
የምፈራው እሷን ብቻ ነው፡፡የምሰማውም እንደዛው ፡፡እናቴን በአምስቱም የስሜት ህዋሳቶች ስጠቀም የመጨረሻውን ስሜት የማጣጥምባት ቅዱስ ጨረቃዬ ነች፡፡አፍንጫዬን ተጠቅሜ የመጨረሻው መሳጭ ሽታ ወደውስጤ የምምገው የእናቴን ጠረን ነው፡፡:በምላሴ ቀምሼ የምደነዝዛበት የመጫረሻው ጣፍጭ ጣዕም የእናቴ እጅ የነካው ምግብ ነው፡፡አይኖቼ ሲከፈቱ ሊመለከቷቸው የሚጓጉት የመጨረሻው መሳጭ ውበት የእናቴ ማንነት ነው፡፡በእጆቼ ሲዳሰሱ ስሜት የሚሰጡኝ ልቤን የሚያደነዝዘው የመጨረሻው ለስላሳ ልብ ነዛሪ ገላ የእናቴ ሰውነት ነው፡፡የመጨረሻው የሰማይ መላዕክት የሚደመሙበት አይነት ከያሬድ ዝማሬ የላቀው ጥኡመ ዜማ ከእናቴ አንደበት የሚወጣው ድምጽ ነው፡፡
እርግጥ ይሄ ስለእናቴ ያለኝ ስሜት የእኔ የተዛባ አመለካከት ሊሆነው ይችላል፤ቢሆንም ግድ የለኝም ፡፡እንደውም ይሄንን ስሜት ከውስጤ የሚያጠፋብኝን ጤንነት አልፈልገውም፡፡ለእኔ ዓለም ጠቅላላ ማለት እሷ ነች፡፡እሷ ብቻ ነች፡፡እሷ ብቻ ነች የምታወደኝ፡፡እሷ ብቻ ነች የምትኮራብኝ፡፡እሷ ብቻ ነች ውስጤን አንብባ ነገዬን በድፍረት የምትነግረኝ፡፡እሷ ብቻ ነች ያላትን በጠቅላላ ያለመሰሰት ልትሰጠኝ የማታንገራግር፡፡አሁን እርግጥ ከእናቴ በተጨማሪ ይህች አለም ሌላ እውነት እንዳለት ተረድቼያለው፡፡ሚስቴ …..
እናቴ ወላጄ ነች፡፡ከማይታወቀው አለም ለእናቶች ከእግዚያብሄር በተሰጠ የተፈጥሮዊ ፀጋ በመጠቀም ከሚስጥራዊው ዓለም መዛ አምጥታኝ በቅዱስ ማህፀኖ ዘጠኝ ወር ተንከባክባ ከረቂቅ ህዋስነት ወደ ሰዋዊ ፍጡርነት በመቀየር በሚዳሰሰው ዓለም ላይ እንድኖር ያደረገቺኝ እናቴ፡፡
አንድ ሴት ወደ ማህፀኗ ከገብት 5 ሚሊዬን በላይ የዘር ፍሬዎች መካከል አንዶ እድለኛ በሰበረችው እንቁላል ልጅ ይወለዳል፡፡እንዴት እኔ እንደዛ እድለኛ ሆንኩ..….?እንዴት ከአምሰት ሚሊዬን አንዶ እኔን የያዘች ሴል ተሳካላት…….?እዚህ ላይ የእናቴ አስተዋፅኦ ይኖርበት ይሆን ወይስ የፈጣሪ ፍቃድ….?፡፡የፈጣሪስ ከሆነ ምንድ ነው ምክንያቱ….? ምንድነውስ መስፈርቱ …….?፡፡
ለማንኛውም ይሄን ለጊዜው ልተወው…እናቴ ወደዚህ ምድር አመጣችኝ..ማለት ወለደቺኝ፡፡ይሄ ማኛውም እናት በእውቀትም ሆነ በደመነፍስ የምታደርገው ነገር ነው፡፡የእናቴ ብቃት፤የእናቴ ልዩ መሆን፤የእናቴ ፈጣሪነት ከዛ ቡኃላ የሚገለጽ ነው፡፡መጀመሪያ ወለደቺኝ ከዛ ቀጥላ ፈጠረቺኝ፡፡ቅደም ተከተሉ አዛባውባችሁ አይደል….?፡፡መፈጠር የነገር ሁሉ መጀመሪያ እንደሆነ ስቼው አይደለም፡፡ እናቴ ስትወልደኝ እንደማንኛውም ሰው ሰው ነበርኩ፡፡ግን ዝም ብሎ ስው፡፡እየዳህኩ ሰሄድ ምኔም ምኔም የማይጥም ሰው ነበርኩ፡፡
እራሴን ላስተዋውቃችሁ አይደል፡፡እራስን ማስተዋወቅ እንዴት ነበር.. ….?አዎ ሰዎች እራሳቸውን ማስተዋወቅ የሚጀምሩት ስማቸውን ከመናገር አይደል ….?፡፡ሰው እራስ ወዳድ የመሆኑን አንዱ ማስረጃ ይሄ ነው፡፡ በየምክንያቱ ስሙን መጥራት ስለሚወድ እራሱን ለሌላ እንግዳ ስው የማስተዋወቅ ስርአት ላይ ስምን ቅድሚያ መናገር የሚል ሀረግ አሰፈረ……፡፡
ማህሌት ትባላለች፡፡ማህሌት ገዳ፡፡የእናቴን ሙሉ ስም እየነገርኮችሁ ነው፡፡የእኔ ስም ደግሞ ፀጋ ፡፡ፀጋ ማህሌት ገዳ፡፡ሙሉ ስሜ እስከአያቴ ሲጠራ ነው፡፡የሴት ልጅ ነኝ፤ ለዛ ነው በእናቴ የምጠራው፡፡አባቴን አላውቀውም..እንዳለኝ እንኳን እርግጠኛ አይደለውም፡፡እንዲኖረኝም ፈልጌም ጠብቄም አላውቅም ፡፡የተወለድኩት በ1994 ዓ.ምህረት ነው፡፡ስንት ዓመቴ እንደሆነ ቆጥራችሁ ድረሱበት፡፡እጆቼን ከመሬት አላቅቄ በአየር ላይ በማወናጨፍ ፤በሁለት እግሮቼ ቆሜ ሰው እንደሚያደርገው መራመድ የቻልኩት አራት አመት ካለፈኝ ቡኃላ ነው፡፡ከዛ በፊት ልክ እንደዝንጀሮ ወይም ጦጣ ወይንም ደግሞ እንደተሳቢ እንስሳት ባለአራት እግር ተሳቢ ወይም ተንፎቃቂ ነበርኩ፡፡
እናቴ በዛን ወቅት በተለይ ሁለት ዓመት ካለፈኝ ቡኃላ መራመድ ባለመቻሌ በጣም ተጨንቃ የተለያዩ ቦታ በመውሰድ ዘመናዊውንም ሆነ ባህላዊውን ህክምና እንዳገኝ እና እንደሌሎች እኩዬቼ መራመድና መናገር እንድችል ሞክራ ነበር ፡፡ግን አንዳቸውም ምንም ሊፈይዱልኝ አልቻሉም ነበር፡፡በመጨረሻ እናቴ ተጨንቃ እኔን ማስጨነቁን ለማቆም ከወሰነችና እሰከማንነቴ ልትቀበለኝ ከቆረጠች ቡኃላ ነበር ድንገት ተስፈንጥሬ በመቆም መሄድ የቻልኩት፡፡እንዴት መራመድ ቻልኩ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እያረጋቹ አደለም ያነበበ የተመቸው 👍
እያረጋቹ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3
#የሰፋ_ሀገር_ይዘን_ጠቦ_መሞት_ይብቃን

አይችለው የለ እንጂ የልባም ትከሻ፣
ከውርደቱ ደጃፍ ነውሩን ማምለጥ ሲሻ፣
ገርፎ ማሳመን ነው የፈሪ ሰው በትር የሽንታም ሰው ጋሻ።
እንመን ግድ የለም…
ፍትህ አይታለምም ሀቁን እየሸሹ፣
የጠፋው እንዲገኝ እስኪ መጀመርያ ይፈተሽ ፈታሹ።
አቀርቅራ ታዝግም ትጎናበስ እንጂ መሄድ እስኪያድላት፣
ሰብረህ ስታበቃ ምርኩዝ እንኪ ብለህ ደርሰህ አትደልላት።
በኔ ብቻ በሽታ ጥበት እየቀጣን፣
በእናታችን እርስት በአባታችን መሬት መደገፊያ እያጣን፣
ቁልቁል እያሰቡ ምንድነው ከፍታ፣
መብት እየነጠቁ ምንድነው ግዴታ?
እስከ መቼ ተረት ግዴለም ይነጋል፣
መንገድ እየቀሙ ምርኩዝ ምን ያደርጋል?
አንተ እንደው ልማድህ አለስልሶ መግደል አሳስቆ
መግፋት፣
ካብኩ እያሉ ማቅለል ሳምኩ እያሉ መትፋት፣
የበደል ላይ ጀግና እሬሳ ላይ መዛት፣
መዋረድን ሽሽት የአሽቃባጭ አፍ መግዛት።
እየሸሹ ትግል እየሮጡ ዛቻ፣
በጉንዳን ልቦና የነብር ዘመቻ።
የበላ እያሰረ የቀማ ቢገፈው፣
የሳተ እያረመ ያጠፋ ቢገርፈው፣
ጀግና ልማዱ ነው ባርያ ሆኖ ታሽቶ ንጉስ ሆኖ መግዛት፣
እያነሰ ገዝፎ እየሞተ መብዛት።
ያ ሽንታም ላመሉ በሬሳ ይፎክራል፣
ከፈሪ ገዳይ ድል የጀግና ሞት ያምራል።
ይልቅ……
በእኔ ልቅደም ትርክት የዘር ደዌ አያጥቃን፣
ከጎጥ ቀንበር ፍቱን ጠቦ መሞት በቃን።
የጸደይ ወይን ሆኖ የሀቅ እንባ ቢጥም፣
በድሎ መጀገን ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣
የትግላችን ልኩ ያሳር ደም ቢያስምጥም፣
በሰፋ ሀገር ጠበን ኢትዮጵያን አንሰጥም!!!

🔘ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ🔘
#የመልስ_ጉዞ_ወደመነሻ
:
#ክፍል_አራት
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
አራት አመት ካለፈኝ ቡኃላ አንድ ቀን አናቴ ከጓደኛዋ ጋር የገዛ ቤታችን ውስጥ ታወራለች
‹‹እንደው ስንቱ እያፈቀረሽ እኮ ሁኔታሽን እያየ ነው የሚሸሸሽ››ድንገት ነው ጓደኛዋ አስተያየት የሰነዘረችው
-ሁኔታዬ ምን ሆነ ?
-ያው የልጅሽ ሁኔታ ነዋ
-የልጄ ሁኔታ ምን ሆነ..?በቃ በማንም ሰው ላይ እንደሚያጋጥም የጤና መጓደል አራት አመት ቢሆነውም መናገርና መራመድ አልቻለም..እና ምን ይጠበስ …….?በንዴት እና በሚርገበገብ ድምፅ
-ቀስ በይ ምን ያስቆጣሻል…ለማለት የፈለኩት ሙሉ ህይወትሽን ለእሱ መስዋዕት አድርገሽ ሰጥተሸል ነው፡፡ልጅሽ ቢሆንም አንቺም ሰው ነሽና ለራስሽ ማሰብ መጀመር አለብሽ ልልሽ ፈልጌ ነው….ቀንም ሌትም ከእሱ ጋር ተቆራምደሽ መዋልና ማደሩን አቁሚና ለሰራተኛ ሰጥተሸው እንደድሮሽ ወጣ ወጣ በይ….ወደቢሮ ስራሽም ተመለሺ እያልኩሽ ነው፡፡
-እኔ ወንድ ያስፈልገኛል ብዬ ለማንም ተናግሬ አላውቅም፡፡ወንድ ለማግኘት ከእኔ በስተቀር ሌላ ሰው ሊረዳው የማይችለውን ልጄን ለሰራተኛ ጥዬ ተቆነጃጅቼ ለመውጣት ፍላጎቱ የለኝም፡፡ለምበላውና ለምጠጣው የሚሆን ብር አለኝ፡፡ስለዚህ አትልፊ ከአሁን ቡኃላ ባለው ህይወቴ ዋና አላማዬም ሆነ ቋሚ ስራዬ ልጄ ነው፡፡…እናቴ ፍርጥም ያለ መልስ ትመልስላታለች፡፡
-አይ ተስፋ ለሌለው ነገር እራስሽን መስዋዕት እንድታደርጊ ስለማልፈልግ ነው እንደዚህ የምልሽ..ደግሞ ለአባትሽም ብታስቢላቸው መልካም ነው::
እዚህ ላይ እናቴ ብትበሳጭም የጓደኛው ምክር ግን እንዲሁ ችላ ተብሎ የሚጣል አልነበረም፡፡በተለይ ለአባትሽ ብታስቢላቸው መልካም ነው ያለችው ዝም ብላ ከመሬት ተነሳታ አይደለም፡፡የእናቴ አባት ማለት አያቴ በእናቴ ላይ የነበረው ተስፋ እንዲህ ቀላልና ተራ የሚባ አይነት አልነበረም፡፡እሷ ላይ ብዙ ተስፋ ነበረው፡፡እናቷ በልጅነቷ ስለሞተች ከ10 አመቷ ጀምሮ ብቻውን ነው ያሳደጋት ፡፡ከዛን ጀምሮ ሚስት ላግባ አላለም….ከዛን ጀምሮ ለራሴ ምቾት ላስብ አላለም፡፡ጭንቀቱ እሷብቻ ነበረች፡፡ኢትዬጵዬ ይላታል፡፡አያቴ ሀገሩን ይወደል ፡፡ከሀገሩም እኩል ልጁን ይወዳል፡፡
አያቴ ኮረኔል ነው ፡፡በሀይለስላሴ የመጨረሻዎቹ ዘመን የውትድርናውን አለም ተቀላቅሎ በደርግ ሙሉ ከምስራቅ እስከሰሜን በተለያ አውደውጊያዎችና አገልግሎት ሰጥቶ ኢህአዲግ ሲገባ ጎደኞቹ ሲበተኑ አብሮ የተበተነ ግን ደግሞ እንደእድል ሆኖ ደህና ቤተሰብ ስለነበረው ወደትውልድ ከተማው ሲመለስ በመንደላቅ የሚያኖረው ንብረት ከቤተሰቦቹ በውርስ የጠበቀው ሰው ነው፡፡ እና አያቴ እሱ የጀመረውን ሀገርን ለእድሜ ልክ ማገልገል ልጁም በተለየ መንገድ ቢሆንም እንድትቀጥል ይፈልግ ነበር፡፡‹ጓደኞቼ ለዚህች ሀገር ህይወታቸውን ሰጥተዋል እኔ ደግሞ በአጋጣሚ በህይወት ቆይቼ ልጅ ወልጄ እንድስም ከተፈቀደልኝ ይህቺን ልጅ ለሀገር አገልጋይ እንድትሆን በስርዓት አሳድጌ ፤ በአግባቡ አስተምሬ እንሆ ኢትዬጵያዬ ልጄን እንደልጅሽ ተረከቢኝ ፡የደቀቀ ጎንሽን አሽታ ትጠግንልሽ ዘንድ፤የጎበጠ ወገብሽን ደግፋ ታቃናልሽ ዘንድ..እግርሽን ጣቶች መካከል የተጠቀጠቁትንና ያቆሰሉሽን እሾኮች ቀስ ብላ ህመምሽ እያማት በወረንጦ ለቅማ ታክምሽ ዘንድ ….የአይኖችሽን ዳር አይናሮች አፀዳድታ መታወርሽን በፈዋሽ ጠብታ እንድታድንሽ ዘንድ ….አዎ ህመምሽ ሚያማት፤ ጭንቀትሽ የሚጨንቃት ልጅ አድርጌ አሳድግን አስረክብሻለው፡፡ ብሎ ለዘመናት እየፎከረ አሳደጋት ፡፡ እንዳለው አድርጎ አስተማራት፡፡ዩኒቨርሲቲ ገባች በማእረግ ጨረሰጭ ፡በጥሩ ደሞዝ ጥሩ መስሪያ ቤት ተቀጠረች፡፡አያቴ ተኩራራ ..በራሱም በልጁም ስኬት ታበየ፡፡ድንገት ግን እናቴ ከጋብቻ ውጭ እኔን ፀነሰች፡፡አያቴ ደነገጠ፡፡ተወለድኩና ታየው፡፡ይበልጥ አንገቱን ደፋ፡፡በእኔ ሁኔታ ..ያንን ተከትሎ የእናቴ ስራዋን መልቀቅ ፤እቤት ኩርምት ብሎ መቀመጥ እና መላ ህይወቷን ለእኔ ለበሽተኛ ልጇ መስዋዕት ማድረግ አያቴን ከእርጅናውም ገፍቶ የሞት አፋፍ ላይ አደረሰው …አዎ ይሄ ደግሞ የእናቴን ጓደኛ ቢያሳስባት ያስመሰግናት ይሆናል እንጂ በክፋት አያስቀወቅሳትም…እናቴን ግን ከፋት
ለዚህም ነው -አይ ተስፋ ለሌለው ነገር እራስሽን መስዋዕት እንድታደርጊ ስለማልፈልግ ነው እንደዚህ የምልሽ..ደግሞ ለአባትሽም ብታስቢላቸው መልካም ነው::…ያለቻት
.እንዴት ተስፋ የሌለው ነገር ….?......እናቴ በገረሜታም በንዴትም ጓደኛዋ ላይ ተንዘረዘረች ፡፡
-ለምን ሁሉንም ነገር ዘርግፌ እንድናገር ታስገድጂኛለሽ..….?አሁን አራት አመት አልፎታል.. መናገሩ ይቅር ቢያንስ በእግሮቹ ቆሞ መረመድ ካልቻለ ምን ተስፋ ይኖረዋል፡፡ይሄ ከአዕምሮው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው ነው የሚመስለኝ››
-የልጅሽ አዕምሮውም አይሰራም እያልሽኝ ነው….?
-እንግዲህ እንደፈለገሽ ተርጉመሽ ተረጂው…ግን ለሚወዱሽ ሰዎች ስትይ ያልኩሽን ብታደርጊ እመርጣለው፡፡
-በቃ ውጪልኝ..ታያላችሁ ደግሞ ስንት ዓመትም ይፍጅ ስንት ዓመት ልጄ ቆሞ ይሄዳል፡፡ አንደበቱንም ከፍቶ ይናገራል….?አምላኬ በልጄ ላይ ታአምሩን እንደሚገልጽ አምናለው….የዘላለም አምላክ ፈጣሪ …ሁሉን አድራጊና ሁሉን መታሪ ኤልሻዳይ ለጊዜው ዝም ቢለኝም እስከመጨረሻው እንደማይረሳኝ እርግጠኛ ነኝ…የቅድስና እሳት የሚተፉ የማዳን እጆቹን የልጄ ሰውነት ላይ አንድ ቀን ያኖራል፣..አዎ ቀኑ ሲደርስ እንደዛ ያደርጋል››እናቴ በተለመደ መልኩ በፈጣሪዋ ላይ ያላትን እምነት በንዴት እየተንቀጠቀጠች ለጓደኛዋ አነበነበችላት
-አይ…ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም ሲባል እኮ እንዲህ አይደለም….እንዲሁ የእናት አንጀት ሆኖብሽ ነው..››አላገጠችባት….እኔ ከዛ በላይ ታግሼ እናቴ እቅፍ ውስጥ ተዘፍዝፌ መቀመጥ አልቻልኩም..ወይንም አላውቅም እናቴ የምትተማመንበት ኃያሉ አምላክ እንደጠየቀችው ሚስጥራዊ እሷት የሚተፉትን የድህነት እጆቹን ሰውነቴ ላይ ጭኖብኝም ሊሆን ይችላል፡፡ብቻ የእናቴ ንግግር ተከትሎ በጉንጮቾ እየፈሰሰ ግንባሬ ላይ የሚንጠባጠበው እንባ ወደመሬት ከመውረድ ይልቅ ግንባሬ ላይ እያረፈ ወደ ህብረሰረሰሬ በመስረግ ውስጤን ሲያቃጥለኝ እና በዛው ቅጽበት የሆነ ነዛሪና የሚያንቀጠቅጥ አይነት ኃይል በሰውነቴ ሲራወጥ ታወቀኝ ..ከእናቴ እቅፍ ላይ ተወራጨው እና ተንሸራትቼ በአግሮቼ መሬት ረገጥኩ፡፡
እሷን ይዤ መሬት ረግጪ መቆም ሁሌ የማደርገው ስለሆነ ሁለቱም ትኩረት እልሰጡኝም…ግን ታአምራዊ በሆነ ፍጥነት የእናቴን ድጋፍ ለቅቄ የሩጫ ያህል እየተንደረደርኩ የሴትዬዋን የሚወናጨፍ እጅ ተንጠራርቼ ያዝኩና ወደውጭ እጎትታት ጀመር …..እናቴ እልልታዋን እያሰማች በጉልበቷ ተደፍታ መሬቱን ስትስም ጓደኛዋ ፃረሞት ፊት ለፊቱ እንደተጋረጠበት ሰው እጆን መንጭቃ ከእጆቼ በማስለቀቅ በሩጫ ከቤታችን አምልጣ በመውጣት ከውጭ የአጥር በራፍ ጋር ተላትማ ተዘረረች….

💫ይቀጥላል💫

ከወደዱት ከተመቾ Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሱ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3
#የመልስ_ጉዞ_ወደ_መነሻ
:
#ክፍል_አምስት
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

:
...አሁን እያወራዋችሁ ያለውት ተጨባጭ ስለሆነው እውነታ ነው፡፡ተጨባጭ እውነታ ማለት ምን ማለት ነው ካላችሁኝ በአምስቱ የስሜት ህዋሳቶች ተጠቅመን አዕምሮችን እንዲያስበው ወይም ልባችን እንዲሰማው ማድረግ የምንችለው ነገር ነው፡፡እርግጥ የሰው ልጅ አምስት የስሜት ህዋሳት ብቻ አይደለም ያሉት፡፡ብዙዎቻን የማንረዳውና ስድስተኛው የሆነውን የስሜት ህዋሳት ከተጨባጭ ዓለም ባሻገር ያለውን እወነታ የምን
…..አሁን ስለሌላው ችግሬ ልንገራችሁ..መናገር የቻልኩት ደግሞ በአስር አመቴ ነው፡፡ተገረማችሁ፡፡እውነቴን ነው ልክ እስከአራት አመት ስንፎቀቅ ኖሬ ድንገት ታምራዊ በሆነ መንገድ ብደግ ብዬ መሮጥ ጀመርኩ ፤በአስር አመቴም ድንገት በአንዴ ነው በሁለት ቋንቋ መናገር የቻልኩት፡፡አዎ ገብቶኛል አላመናችሁኝም አይደል፡፡እውነቱ ያነው፡፡
…የእግሬ ጉዳይ ተአምራዊ በሆነ አጋጣሚ እና ሁኔታ እልባት ካገኘ ብኃላ አንደበቴ ግን ባለበት ነበር የቀጠለው…፡፡ .አንዳንድ ትርጉም አልባ የሆኑ ድምፆችን ለምሳሌ ታታታ..ዳዳዳ የመሳሰሉትት ከአንደበቴ ለዛውም በጣም በምበሳጭበት ወቅት ይሰማ ይሆናል እንጂ የሚሰማኝ ስሜት የሚሰጥ ነገር ከእኔ አንደበት ማድመጥ ማይታሰብ ሆኖ ቀጠለ…..
በዚህ ሁኔታዬ የሰፈር ሰዎችም ሆኑ ዘመድ አዝማዶች የሆን በስህተት እንደተፈጠረ ሰው መሳይ ሸክም እንደሆነ ሰው ነበረ የሚያዩኝ፡፡ብዙዎቹ አዕምሮዬም ማሰብ የሚችል ሁሉ አይመስላቸወም ነበር፡፡‹‹ምን አለ ወዲያ ወስዶ በገላገላት ››ብሎ ለፈጣሪው መልሶ እንዲወስደኝ ስለት የሚሳሉ የእናቴ ወዳጆች ቀላል ቁጥር የላቸውም፡፡
ግን እነሱ ያልገባቸው የአዕምሮዬን የማሰብ ብቃት ስል መሆኑን ነው፡፡ከእግሮቼ እና ከአንደበቴ በልተጣጣመ መልኩ እንደውም ፍጽም ተቃራኒ በሆነ መንገድ አዕምሮዬ ክፉና ደጉን መለየት እና የሰላ እሳቤ ማሰብ የጀመረው ገና በጮርቃነቴ ነው ፡፡ይሄንን ግን ከእናቴ በስተቀር ማንም አይረዳልኝም ነበር፡፡እርግጥ አሁንም ድረስ ብዙዎቹ አያውቁም… ቢያውቁም ማመን አይፈልጉምን ፡፡
ከህፃንነቴ ጀምሮ እኔ የምጫወተው ዕቃ ዕቃ በመደርደር፤ወይም ከልጆች ጋር ሌባና ፖሊስ በመሯሯጥ ፤ወይንም ደግሞ ቡድን ለይቷ በሰፊ የሳር ሜዳ ላይ ከውሪ ህፃናት ጋር ተበትኖ በመሯሯጥ ኳስ በመጠለዝ አይደለም… ረጅም የተባለውን የልጅነት ጊዜዬን የቲቪ ስክሪን ላይ አፍጥጬ የተለያዩ አለማቀፍ የቲቪ ቻናሎችን በመከታተል ነው.....፡አረብኛ ቻናሎችን እንግሊዘኛ ቻናሎችን አማራኛ ቻናሎችን ወዘተ…
ከዛ የተረፈኝን ቀሪ ሙሉ ጊዜ ደግሞ በተመስጦ በማሰብ ነው የማሳልፈው፡፡ስለሆነ ነገር በጥልቀት እና በፍዘት ለሳዕታት በመተከዝ ማሰብ....ለዛውም ከተቀመጥኩበት ሳልንፎቀቅ እና አይኖቼን ከተከልኩበት ሳላንቀሳቅስ ..፡፡
የአማልክት ዝርያ ከሌለበት በስተቀር እስቲ አንድ የአምስት እና የስድስት አመት ልጅ በዚህ መልክ ሊያስባቸው የሚችላቸው ነገሮች ከየት ያመጣል…?፡፡ስለሆነ ነገር ለማሰብ እኮ ስለነገሩ ወይ በትምህርት ያገኙት ዕውቀት ካልሆነም በኑሮ ልምድ ያካበቱት የልምድ ክምችት ሊኖር የግድ ነው፡፡ከዛ ያንን መነሻ በማድረግ ስለነገሩ ይበልጥ ለመረዳት ወይንም ካወቅነው ጀርባ ያለን ድብቅ ወይም ሽሽግ ያልታወቀ እውቀትን ለመግለጽ ማሰብ ያለ ነው፡፡በዛ ላይ ለማሰብ እራሱ በመጠኑም ቢሆን የበሰለ አዕምሮ፤የዳበረ ስሜት ፤የበለፀገ እይታ ከሁሉም በላይ የፈካ ንቃተ-ህሊና አስፈላጊ ነው፡፡ሁሉም የሰው ልጅ ከማሰብ ችሎታ ጋር እንደሚፈጠር ባምንም ማሰብ እንደሚችሉ አውቀው በጊዜው ማሰብ የሚጀምሩ ሰዎች ግን ጥቂቶች እንደሆኑ አምናለው፡፡ ብዙዎቹ የማሰብን ፀጋ በተግባር ማጣጣም የሚጀምሩት በእርጅና ዕድሜ ውስጥ ከገቡ ቡኃላ ነው፡፡ወደኃላ በትዝታ እየተሳቡ እና በፀፀት እየተንገላቱ ፡፡ከዛም በባሰ ሁኔታ ከሚስጥራዊው አለም ይዞት የመጣውን ንጽህ አዕምሮ ሳይነካካው ይዞት የሚሞትም የሰው ልጅ ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡በደመነፍስ ብቻ በመኖር፡፡
እኔ ታዲያ በተጋነነ ሁኔታ በጮርቃነት ዕድሜዬ እንዲያ ዓይነት ብስለት ከየት አመጣውት…? ይሄንን እናቴ ነች ምታውቀው፡፡ሌላውማ በዛ ሁኔተ ሲታዘበኝ እያሰብኩ እንደሆነ ሳይሆን የሚረዱት በአዕምሮ ዝግመት በሽታ ተጠቅቼ እየነሆለልኩ እንደሆነ ነው፡፡ለነገሩ ማን ነበር ‹በጂኒዬስነትና በእብደት መካከል ያለችው መስመር በጣም ቀጭን ነች ያለው ››….በዚህ እሳቤ እንደእብድ እኔን ማሰባቸው ብዙም አልተሳሳቱም፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3👏1
#የመልስ_ጉዞ_ወደ_መነሻ
:
#ክፍል_ስድስት
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
..… እንደነርኮችሁ የመራመዴ ጉዳይ ተአምራዊ በሆነ መንገድ እልባት ካገኘ ቡኃላ እናቴ ለአንደበቴ መከፈት መጓጓት ጀመረች፡፡ያው እናት አይደለች ፡፡በተለይ ስድስት አመት ከሞላኝ ቡኃላ እኩዬቼ ሁሉ ወደትምህርት ቤት ሲጓዙ እኔ አንደበቴ መላቀቅ ባለመቻሉ ምክንያት እቤት በመቅረቴ ውስጧ ተጎዳና እንደአዲስ እኔን ለማዳን የምታደርገውን እንቅስቃሴ ጀመረች ፡፡በዚህ እንቅስቃሴዎ ወቅት ስታልፍም ሆነ ስታገድም የሚያገኞት ሰዎች ሁሉ የሆነ ነገር ሳይሏት ዝም ብለው አያልፎትም፡፡
መቼስ ሀበሻ ባህል ውስጥ አንዱ አስቸጋሪው ነገር የሆነ ሰው ችግር ላይ በወደቀ ቁጥር ምክር ሰጪ ሰው መብዛቱ የታወቀ ነው፡፡ለምን ጠበል አትወስጂውም……?አዋቂ ቤት ይሻልሻል……?እዚህ ከተማ ላይ አዲስ ሀኪም መጥቷል አሉ….…? ውጌሻ ጋር አይሻልሽም….የማይባል ነገር የለም፡፡ታዲያ ይሄ ችግር ውስጥ ላለችና ግራ ለገባት እናቴ በወቅቱ ምን ያህል ግራ አጋቢና አስጨናቂ እንደሚሆንባት መገመት አይከብድም፡፡
እናቴ አንደወትሮዋ እኔን ለማዳን ስትንከራተት ውላ ስትመለስ አባቷ ይናገራታል፡፡
-ልጄ በቃ ለአምላክ ተይው…እሱ እንዳደረገ ያድርገው
-እንዴት እንዳደረገ ያድርገው ስትል…?...ትጠይቃለች
-በቃ አንዳንዴ ከአምላክ ጋር እልክ መጋባት አያስፈልግም…አሱን አድናለው ብለሽ ከእዚህ እዛ ስትካለቢ አንቺም ከሰውነት ጓዳና ወጣሽ…እራስሺን እስኪ እይ… የአርባ አመት አሮጊት መስለሻል እኮ…ገና በሀያ ሶስት አመትሽ ፊትሽን ማድያት እየበላው ነው፡፡በዚህ ከቀጠልሽ የከፋ በሽታ ላይ መውደቅሽ አይቀርም፡፡
-እና ምን አድርጊ ነው የምትለኝ፡፡…?
በቃ እሱን አድናለው ብለሽ ከወዲህ ወዲያ መንከራተቱን አቁሚ.. እግዜያብሄር እግሩን ተርትሮልሻል …በቃ በዛ ተመስገን ብለሽ ሌላውን ተይው…ይሄው ለዓመታት ተንከረተሽ፡፡ ..ህክምናውንም ጠበሉንም ሞክረሻል፡፡ይሄ ነው ችግሩ ብሎ ሊነግርሽ የቻለ የህክምና ጠቢብ የለም፡፡ይሄ ማለት ደግሞ የልጅሽ ችግር ሚስጥር በአምላክ እጅ ብቻ እንደሆነ ነው የሚገባኝ፡፡ በእሱ እጅ ከሆነ ደግሞ ታአምሩን የሚያደርግበት የራሱ ቀንና ጊዜ አለው፡፡እሱን በትዕግስት መጠበቅ ነው፡፡ስለሆነም መንከራተቱን አቁሚ፡፡እዚሁ እንከባከበዋለን፡፡ምንም ነገር እንዳይጎልበት ማድረግ እንችላለን፡፡የሚጠብቁት ተጨማሪ ሰራተኞችም ልንቀጥርለት እንችላለን፡፡አንቺ ግን ከዚህ በላይ እራስሽን አትጣይ፡፡ ……
-አባዬ እናቱ እኮ ነኝ፡፡እንዴት ይሄ የእግዜር ስራና ፍቃድ ነው ብዬ እጆቼን አጣጥፌ ተስፋ ቆርጬ ልቀመጥ እችላለው…?፡፡አንተ እኔ እንደዛ ብሆንብህ የሆነችውን ትሁን ብለህ ተስፋ ቆርጠህብኝ ትተወኝ ነበር…?፡፡…….የትዝብት ጥያቄ ጠየቀቺው፡፡
-አይ…ስለልጅ ልጄ እኮ ነው እያወራን ያለነው… ለአንቺ ብቻ ሳይሆን ለእኔም ልጄ ነው፡፡ጨካኘ ሆኜ አይደለም፡፡ግን እሱን ለማደን በሚል ያልተረጋገጠ ተስፋ አንቺን እንዳላጣ ስለፈራው ነው፡፡ሰለጨነቀኝ ነው፡፡
-በቃ አባዬ በቃ …. መቼም በልጄ ተስፋ አልቆርጥም፡፡መቼም እግዜር እንዳደረገ ያድርገው ብዬ ልቤን አረጋግቼ እድሜ ልኩን ከሰው ተገልሎ በተዘጋ ቤት ውስጥ እንዲኖር በመፍረድ እኔ ለመሽቀርቀርና እራሴን ለማሽሞንሞን አልሞክርም…..መቼም፡፡……ብላ ከአባቷ በንዴት እና በለቅሶ ተለይታ እኔን ወደመኝታ ቤት ይዛ ገብታ ግንባሬ ላይ ተደፍታ በእንባ እየታጠበች ከፈጣሪዋ ጋር ለሳዕታት በምሬት ካወራች..(እናንተ ከፀለየች )ብላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ አቅፋኝ ትተኛለች፡፡
ማለዳ ሊነጋጋ ሲል ጥርት ያለ ህልም ታያለች፡፡ተመሳሳይ አይነት ህልም እኔም አይቻለው፡፡ልዩነቱ እሷ ያየችውን ህልም ለአባቷ መናገር ስትችል..እኔ ደግሞ ምናገርበት አንደበት ስላልነበረኝ ለእሷ እንኳን መናገር አልቻኩም፡፡
-ህልሙ እንዲህ ነው
ጠይም የተለጠለጠ ኑግ የሚመስል የሰውነት ቀለም ያላቸወ ፊታቸው በአደገ እና በተንዠረገገ ነጭ ፀጉር የተሸፈነ ሽማግሌ መኝታ ክፍላችን ሰተት ብለው ይገባሉ፡፡እናቴ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣ እኔን ጉልበቷ ላይ ታቅፋ በተመስጦ ላይ ሳለች ሰውዬው ወደእኛ ቀርበው ወለሉ ላይ በርከክ ይሉና ጭንቅላቴን እየዳበሱ
‹‹ ..ልጅሽ ታላቅ ሰው ይሆናል፡፡አንድ ቀን ዓለም ስለእሱ በመደመም ያወራል፡፡ምድራዊውን አለም ከመንፈሳዊው አለም ጋር ድልድይ ሆኖ ያስተሳስራል…ስለዚህ አንቺ መጨነቅሽን አቁሚ .. እሱ በፈለገ ቀን እራሱን ማዳን ይችላል፡፡ ከራሱም ተርፎ ሌላውን ያድናል፡፡ግን ሲፈልግ…ቀኑ ሲደርስ ብቻ ነው እንደዛ የሚያደርገው፡፡
-አባት ስለእኔ ልጅ ነው የሚያወሩት..?በጥርጣሬ እና ያሉትን ባለማመን ትጠይቃለች፡፡
-አዎ ልጄ ..እኔ የአማላክ መልዕክተኛ ነኝ፡፡ አምላክ እንደገለፀልኝ ከሆነ የልጅሽ እውቀት ጥልቅና ከዛኛው አለም ይዞት የመጣው ነው፡፡
-ከዛኛው አለም ሲሉ…?፡፡
ዳግመኛ ስለመወለድ የምታውቂው ነገር አለ ልጄ.?.
-እኔ እንጃ ብቻ ከዚህ በፊት የሰማው መሰለኝ፡፡አዎ ክርስቲያን አይደለው..ሰው ከውሀና ከመንፈስ ዳግመኘ ካልተወለደ በስተቀር ወደመንግስቱ መግባት እንደማይችል አምላክ ተናግሯል፡፡
-ትክክል እኔ ግን እያልኩ ያለውት ልጅሽች ወደ እዚህች ምድር ሲመጣ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ከሁለት ሺ አመታት በፊት ነፍሱ እዚህች ምድር ላይ ነበረች…የበለፀገ ህይወት እና በእውቀት የተሞላ ስብዕና ነበረው..እና ያንን እውቀት ነፍሱ ይዛው የመጣች ይመስለኛል፡፡
-እና እኔ ምን ላድርግ …?
-ምንም ፤እራሱ ፈልጎ የሆነ ነገር ማድረግ እስኪችል ድረስ አትጫኚው..አንቺም አትባክኚ፡፡ ብቻ በእሱ ላይ ሁሌም እምነት ይኑርሽ..ወስጡ የተቀበረውን እውነትና እውቀት ብቻ እንዲገለፅለት ሁሌ ከጎኑ ሁኚ…ከጎኑ መሆንሽ ብቻ ለእሱ በቂው ነው..ሌላውን በጊዜው እራሱ ያደርገዋል፡፡
-ሽበታሙ መልዕክት አድራሽ ሽማግሊ ከክፍላችን ሳይወጣ ነበር የሰራተኛችን የመኝታ ቤታችንን በራፍ መቆርቆር ሁለታችንንም ከእንቅልፋችን የቀሰቀሰን
-እናቴ ህልሙን ልትረሳ ሰውዬውንም ልትዘነጋ አልቻለችም፡፡ሰራ አልቻለችም..ሰውዬውን ልትዘናጋ.
ዘወትር እንደምታደርገው ማታ አካባቢ ቤተክርስቲያን ሄድን፡፡የተለመደውን የማታ ትምህርት ተከታትላ..ያው እንደወትሮዋ ከአምላኮ ጋር አንሾካሽካ ፤ስትጨርስ ስለህልሞም እያሰበች የመልስ ጉዞ ለማድረግ የቤተክርሲቲያን አጥር ግቢ ወጥተን ብዙም ሳንርቅ እኛ ሁለታችንም በህልማችን ያየናቸው ሽማጊሌ በትክክል እሳቸው ድንገት ከፊታችን ተደንቅረው መንገዳችንን ገቱት.እኔ ብዙም ባይደንቀኝም እናቴ ግን በድንዛዜ ሀውልት መስላ ነበር ባለችበት የቆመችው
-ሰውዬው ለእናቴ ድንጋጤ ብዙም ትኩረት ሳይሰጡ ጎንበስ ብለው እጃቸውን ጭንቅላቴ ላይ አሳርፈው በመዳበስ እይታቸውን ወደእናቴ አድርገው ‹‹ጌታ ችግርሽን ይፍታልሽ…እግዜያብሄር ለቅሶሽን ሰምቶል ››በማለት የብስራት ቃላቸውን አሰሟት
-ተአምር ነው፡፡እርሷ መላአክ ኖት…?
-አይ አይደለውም ሰው ነኝ፡፡ተራ ሰው ለሶስት ቀን በተከታታይ በህልሜ ሳያችሁ ነበር፡፡ህልሜን አምኜ እዚህ ስመጣ ደግሞ በአካል አገኘዋችሁ፡፡››
-እኔም አይቼዎታለው››
-በይ እንግዲህ የምኞትሽ ይሙላልሽ ?
-በህልሞት ምንም እንዲነግሩኝ አልተነገሮትም.››
-አይ ሁሉንም ለእሷ ነግሬያታለው..አንተ ብቻ አግኛትና ልጇን ደባብስላት ነው የተባልኩት፡፡……..ብለው አልፈውን መንገዳቸውን ሲቀጥሉ…እናቴ ከድንዛዜዋ ባና -እሺ እግዜር ይከተሎት..አለቻቸው
-አንቺንም ልጄ....ከእነልጅሽ እግዜያብሄር ይጠብቅሽ ፡፡ብለው ከእይታችን ተሰወሩብን
ከዛ ቡኃላ እናቴ ፍፁም ተረጋጋች
👍4