አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በቀኝ_አሳድረኝ

ቀጭ ….ቀጭቀጭ …ሲጥ ..ሲጥጥ
እህህህ ..‹‹ቀስ በል የኔ ጌ….ታ …››
በ ሹ ክ ሹ ክ ታ
ከግድግዳየ ወዲያ …
ሁሉም ባረፈበት ማታ
ካዲስ ተጋቢዎቹ ቤት
አልፎ የሚመጣ ንዝረት
ጆሮ የሚያቆም ወላፈን
ደምፃቸውን ለቀቅ ….አፈን
‹‹ውይይይይ ….›› የሷ ድምፅ …... በሲቃ ሲተን
የዝምታ አለት …. በፍቅር ፈንጅ… አልጋቸው ላይ
ሲበታተን
ደግሞ የሱ ከንፈር ዋይታ …….እ…..ሟ
የወንድ ልቡ ብረት ወኔው …በፍቅር እቶን
ሲሟሟ
‹‹እፉፉፉፉፉ ››ድምፃቸውን እንደጅራፍ ባንድ
ፈትለው ባንድ ገምደው
ድቅድቅ የጨለማን መንጋ በሲቃ ጩኸት አሳደው
ባንድ ላይ ሲቀላቀሉ የብቻን ግንብ ወዲያ ንደው
አውሎ እፎይታ
ከቀኝ ግድግዳየ ተጎራባች…. ሁሉ ባረፈበት ማታ
ዝምምምምምምታ !
ተኙ መሰል !!
* ** *
ሌላ ድምፅ ደግሞ ከግራ
በቆመ ጆሮየ ግርጌ ያልፋል ድሩን እያደራ
‹‹ እእእእእ ›› ይችኛይቱ ጎረቤቴ
እንዲህ በሙሉ ጨረቃ የሚያስቃዣት በሽተኛ
ሙሉ ሌሊት ስትዋትት ስትሰቃይ የማተኛ
ድፍን ሌሊት ስትዛብር ስታቃስት የሚነጋ
ሲጥ ሲጥጥ ወጉ እንዳይቀር የሷም አልጋ
ቀንም በመቀነቻ ነው … ወገቧን አስራ
የምትቆመው
የበሽታ ክፉ አካናድ ስጋዋን እየጎሰመው
በሁለት ቅስቻ መሃል … ግራ ቀኙኝ እያደመጥኩ
ካንዱ <ጆሮየ አውጭኝ> እያልኩ… ሌላውን
ባሳብ እያለምኩ
በመሃል የምኖር እኔ …
እንቅልፍ ሊጥለኝ ሲዳዳ በግዜር ላይ ቅኔ
እቀኛለሁ
የወጉን ፀሎት ሰም አድርጌ ‹‹
በቀኝ አሳድረኝ
››እላለሁ
**
**** ****
ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ ኳ ኳ
አዲስ ተጋቢወች ማለዳ ተነስተው…. ለቁርስ
ቲማቲም እየቀጠቀጡ
ሲጥጥጥጥጥጥጥጥጥ
ታመው ያደሩቱ ቤተስኪያን ሊስሙ …..ከቤት
እየወጡ
በቀኝም በግራ እንዲህ የሚል ልሳን
‹‹ሰላም ያሳደርከን በሰላም አውለን ››
ይች ናት አገሬ … እኩል እግዚሃርን
የሚዘይሩባት… እኩል ያላደሩ
እኩል ቀን ጀማሪ እኩል ባልሆነ ቁርስ ተስፋ
እየቋጠሩ !
ከታች እስኪሾሙ ከላይ እስኪጠሩ !!
ከቀኝም ከግራም …መሃል ለሰፈሩ
ይች ናት አገሬ እንዲህ ነው አዳሩ !

🔘አሌክስ አብርሃም🔘
👍1