አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የጦር ሃኪሙ የሆነ ነገር ወጋኝ እና ደነዘዝኩ።
ሌሎች ጓደኞቼ እጆቼን ሲይዙ አፌ ላይ ጨርቅ ተደረገ። ቀጥሎ ሃኪሙ በመቀስ ጥይቷን አወጣት:: ከሶስት ሳምንታት በኋላ ነበር የተሻለኝ፡፡ ሃኪሙ ቁስሌን እያጠበ ደጋግሞ “እድለኛ ነህ”
ይለኝ ነበር። ጦርነትን ለማሸነፍ ወይም ከጦርነት ለመትረፍ ጥሩ ስልጠና ወይም ድፍረት ጀግንነት እንጂ እድል ቦታ ያለው
አይመስለኝም ነበር፡፡ ቆይቶ ግን ገባኝ:: ብዙ መከራዎችን በሚገርም ተዓምር ተረፍኩ። ሞት ማይደርስብኝ የማይነካኝ
ይመስለኝ ጀመር።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ስድስት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


ይሄን ነግሬያት ከሆስፒታሉ ለመውጣት ተነሳሁ። አስቴር ግን “በኮንናውት ሆስፒታል ሙሉ ምርመራ እንድታደርግ
ሁኔታዎችን አመቻቻለሁ።” ብላ ላፍታ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ ሙዚቃ ማዳመጫው ከእኔ ጋር ይቆይ ሌሎች እንዲቀኑብህ
እና እንዲሰርቁህ አያስፈልግም፡፡ በፈለከው ቀን መጥተህ ማዳመጥ ትችላለህ። ሁሌም እኔ ከዚህ ነኝ” አለች። ሙዚቃ ማዳመጫውን ወርውሬ ወጣሁ።

አንድ ቀን ከስዓት አስቴር ከስራ እረፍት ብትሆንም ከሁለት ሌላ ሰዎችጋር በነጭ ቶዮታ መጣች። አንዱ ሰው ሹፌር ሲሆን
ሌላው ግን የ ጦርነት ጋር የተገናኙ ህጻናት ወይም Children Associated with War የመስክ ሰራተኛ ነበር። ድርጅቱ ከ ዩኒሴፍ እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚሰራ የካቶሊክ ድርጅት ነበር።

“ ወደ ሆስፒታል ሂደን ከተመረመርክ በኋላ ከተማ ሽርሽር ትሄዳለህ።” አስቴር በደስታ ምን ትላለህ ብላ ጠየቀችኝ፡፡

“እሺ” ብየ ተስማማሁ። ደስ ብሎኛል።”ጓደኛየ አል ሃጂ መምጣት ይችላል?” ብየ ጠየቅኩ።

“ይችላል” ስትል እንደምጠይቃት የጠበቀች ይመስላል።ወደ ፍሪ ታውን መንቀሳቀስ ስንጀምር የመስክ ሰራተኛው
“ ስሜ ለስሊ ይባላል፤ ስላገኘሁህ ደስ ብሎኛል” ብሎ ተዋወቅን።ወደ መሐል ከተማው ስንደርስ አስቴር እጆቿን እየጠቆመች ፖስታ ቤት፣ ሱቆችን፣ የተባባሩት መንግስታት ድርጂት
ህንጻዎችን እና የጥጥ ዛፉን አሳየችኝ። በከተማው ሁሌም እደነቃለሁ። በስራ የተጠመዱ ሰዎች ሲጣደፉ ሲወጡ ሲወርዱ የነጋዴዎች የግዙኝ ጩኧት ደግሞ ልዩ ድምፅ ይሰጣል።

ዶክተሩ የቆሰለ ወይም በጥይት የተወጋ ሰውነቴን እየነካ እና እየጨበጠ “የሚሰማህ ነገር አለ” እያለ ደጋግሞ ይጠይቀኝ ነበር፡፡መናደድ ስጀምር ጨርሰሃል አለኝ፡፡ ልብሴን ለብሼ አስቴር ፣
ለስሊ እና አል ሃጂ ወደ ሚገኙበት መቆያ ክፍል ሄድኩ::ተያይዘን ወደ ገበያው ሄድን። አስቴር ለ አል ሃጂ የስፖርት
ማሊያ ስትገዛለት ለስሊ ደግሞ ለእኔ የ ቦብ ማርሌን ኤክሶዶስ (ስደት) የሚለውን አልበም ገዛልኝ፡፡ አል ሃጂ ማሊያውን
ወዲያው ለበሰው:: ማሊያው የሃገሪቱን ብሔራዊ ሰንደቃላማ ማለትም አረንጓዴ፣ ነጭ እና ሰማያዊ ቀለማቶችን ይዟል።
አስቴር ለሁላችንም ኮካ ኮላ ገዛችልን። ለስለ እኔ እና ሌሎች ልጆችን ለማገዝ እንደተመደበ እና ዋና ስራው እኛ ከማገገሚያው በኋላ ለሚኖረን ህይወት ነገሮችን ማመቻቸት ነው።

በሚቀጥለው ቀን ወደ ከተማ ተመልሰን እኔ ሆስፒታል ሄድኩ። አስቴር ራሴን እያሻሸች “ መልካም ዜና ነው። ውጤትህ
መጥቷል። ዶክተሩ ለክፉ የሚሰጥ ህመም እንደሌለብህ አረጋግጧል። ለበለጠ እርግጠኝነት የተወሰኑ መድሃኒቶችን ትወስድ እና ዳግም ምርመራ ይደረግልሃል” አለች። ምንም
አላልኩም ! እሷ ግን ካሴት እና ማዳመጫውን ሰጠችኝ። አስቴርን እየለመድኳት ስመጣ ስለ ብዙ ነገር ማውራት ጀመርን፡፡በተለይ ግን ስለ ሙዚቃ ቦብ ማርሌ እና ራን ዲ.
ኤም.ሲ፡፡ ለስሊ በሳምንት ሁለት ጊዜ ይመጣ ነበር። ስለ ራስ ተፈሪያኒዝም ማውራት ይወዳል። እኔም #የኢትዮጵያ ታሪክ ደስ ይለኛል በተለይ ንግስት ሳባ እና ንጉስ ሰለሞን የተገናኙበት ታሪክ
ይገርመኛል። የተጓዙት ረዥሙ ጉዞ ፣ የመረጡት ቦታ እና ለመድረስ ያሳዩት ፅናት ሁሌም ይገርመኛል። ከህይወቴ ጋርም ለማገናኘት እጥራለሁ፡፡ የእኔ የህይወት ሩጫ እንደ እነሱ ትርጉም ያለው እና ደስታ የሞላበት እንዲሆን እመኛለሁ።

አንድ ምሽት አስቴር ቤቷ ወሰዳ እራት ጋበዘችኝ፡፡ ከእራት በኋላ ወደ ከተማ ወጥተን መናፈስ ጀመርን። ራውዶን መንገድ ጫፍ ወዳለ የባህር ዳርቻ ሄድን። ጨረቃ በድምቀት ወጥታ ነበር እና ደርቻው ላይ ሁነን መመልከት ጀመርን፡
ልጅ እያለሁ በጨረቃ ውስጥ የተለያየ ቅርፆችን እንመለከት እንደነበር ለ
አስቴር ነገርኳት። ገረማት። ጨረቃዋን እያየን የያዘችው ቅርፅ ምን እንደሆነ መገመት ጀመርን።

ልጅ እያለሁ አያቴ አስተውሎ ለሚያይ እና ለሚያዳምጥ ሰው ሰማይ ይናገራል ትል ነበር፡፡ በሰማይ ሁሌም የጥያቄዎቻችን
መልስ እና የነገሮች ምክንያት ይገለፃል። የእያንዳንዱ ስቃይ፣ ጉዳት፣ ደስታ እና ግራ መጋባት መንስዔ ይነገራል፡፡” ያ ለሊት ሰማዩ እንዲያወራኝ ፈለኩ።

ከአምስት ወር የቤኒን ማገገሚያ ቆይታ በኋላ አንድ ቀን ዓለት ድንጋይ ላይ ተክዤ ተቀምጬ እያለሁ አስቴር አየችኝ። ምንም
ሳትናገር መጥታ ከጎኔ ተቀመጠች። በሰለለ ድምፅ “ ከዚህ በኋላ የምኖርለት ምክንያት ያለ አልመስለኝ እያለ ነው” አልኩ።” ቤተሰብ የለኝም። እኔ ብቻ ነው የቀረሁት። የልጅነት ታሪኬን እንኳ የሚናገር የለም::”

አስቴር እጆቹዋን ወደ እኔ ልካ ጎትታ አስጠጋችኝ እና አቅፋ
“እኔን እንደ ቤተሰብህ አስበኝ፤ እንደ እህት ” አለች:: ግን እህት እኮ የለኝም”
አሁን አለህ፡፡ የአዲስ ህይወት ገፀ በረከት ነው። የተለያዩ የቤተሰብ አባላትን ማፍራት ትችላለህ።” ብላ አየችኝ፡፡

“እሺ! እህቴ መሆን ትችያለሽ ለጊዜው።”

“ይሁን ስለዚህ ነገ ጊዚያዊ እህትህን ለማየት ትመጣለህ አይደል።”

“እሺ!”

በሚቀጥለው ቀን አስቴር ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ጎብኚዎች እንዳሉ ነገረችኝ። ሰራተኞቹ የተሰጥዎ ውድድር እንድናደርግ ጠየቁን፡፡ የምንችለውን ማንኛውንም አይነት ነገር እንድናቀርብ
ነበር የተፈለገው።

ሬጌ ሙዚቃህን ለምን አትዘፍንም” ብላ አስቴር ሃሳብ አቀረበች።

• የሼክስፒርን ቃለ ተውኔትን ባቀርብስ”

“እሺ ትንሽ ሙዚቃ ብትጨምር ጥሩ ይመስለኛል” አለች

እጆችዋን ትከሻየ ላይ አደርጋ። ወድጃታለሁ ግን መውደዱን አላሳያትም:: ስታቅፈኝ ቀስ ብየ ከእቅፏ እወጣለሁ፡፡ ስትሄድ ግን አያታለሁ። ከትምህርት በኋላ ሩጬ እሷን ላይ እሄዳለሁ።ጓደኞቼ ማቡ እና አል ሃጂ “ የሴት ጓደኛህ መጣች እስማኤል” እያሉ ይቀልድብኛል፡፡

ጎብኚዎቹ ከ አውሮፓ ኮሚሽን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጂቶች የተውጣጡ ናቸው። ሙሉ ልብስ ከነከራባቱ ለብሰዋል። እርስበርሳቸው
ስላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ማዕከሉን እየዞሩ ቃኙ። በኋላ ለተሰጥኦ ውድድሩ በሚገባ ወደ ተዘጋጀው ወደ ምግብ አዳራሽ ገቡ። የማዕከሉ ዳሬክተር አቶ ካማራ የመክፈቻ ንግግር ካደረጉ
በኋላ ውድድሩ ቀጠለ። ተረቶች፣ አስፈሪ ታሪኮች እና የባህል ጭፈራዎች ቀረቡ። እኔ ከጁሊየስ ቄሳር የተወሰነ ቃለ ተውኔት
ካቀረብኩ በኋላ አንድ የሂፕ ሆፕ ሙዚቃ ተጫወትኩ።ሙዚቃው ስለ አንድ ታዳጊ ወታደር ትንሳኤ ሲሆን በአስቴር
የሞራል ድጋፍ እራሴ የፃፍኩት ነው::

ከውድድሩ በኋላ በማዕከሉ ታዋቂ ሆንኩ። የማዕከሉ ዳሬክተር አቶ ካማራ ቢሯቸው ጠርተው “ አንተ እና ጓደኞችህ የእውነት ጎብኚዎችን አስደምማችኋል። አሁን ታዳጊዎች ማገግም እንደሚችሉ አውቀዋል።” አሉ። ወደፊት እንደገና የማቅረብ እድሉ እንዳለኝ ሳውቅ በጣም ደስ አለኝ፡፡ አቶ ካማራ ደግሞ ከእኔ
በላይ በከፍተኛ ስሜት ላይ ነበሩ።

የማዕከሉ ቃል አቀባይ ብትሆን ምን ይመስልሃል?” ብለው ጠየቁኝ፡፡
“ምን! ምንድን ነው ምሰራው ወይም የምናገረውስ?”አልኩ።

“ በመጀመሪያ ስለ ታዳጊ ወታደሮች ዝግጅት በሚኖርበት ጊዜ የምታነበውን ነገር እንፅፍልሃለን። ስራውን ከለመድከው በኋላ ፀ የምታቀርበውን ንግግር እራስህ ልታዘጋጅ ትችላለህ” አሉኝ::
ሳምንት ሳይቆይ በታዳጊ ወታደርነት እና እንዴት መቆም አለበት በሚሉ ሃሳቦች ላይ ንግግር አደረኩ። “ማገገም እንችላለን ብየ እራሴን ምሳሌ በማድረግ ህፃናት ከችግሩ መውጣት
👍3😁1
እንዳለባቸው እና እድሉን ካገኙ መውጣት እንደሚችሉ በአፅንዖት ተናገርኩ።

የስድስተኛ ወር የማገገሚያው ቆይታን በማገባደድ ላይ እያለሁ የልጅነት ጎደኛዬ መሐመድ ወደ ማዕከሉ መጣ።
ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት ሞግዊሞን ለቅቄ ከቶሊ እና ጅንየር ጋር ወደ ማትሩ ጆንግ የሙዚቃ ውድድር ለመሳትፍ በሄድንበት ወቅት ነበር። ያኔ ከአባቱ ጋር የሳር ቤታቸውን እያደሱ ስለነበር
መምጣት አልቻለም፡፡ ሁሌም ምን ሁኖ ይሆን ብየ አስብ ነበር::ነገር ግን እንደገና አየዋለሁ ብየ አስቤ አላውቅም::

ጠይም ቀጫጫ ልጅ እየሮጠ መጥቶ
አስታወስከኝ” ካለ በኋላ መደነስ መዝፈን ጀመረ:: መዶሻው መጣልህ” የሚለውን ሲዘፍን አብሬው መዝፈን ጀመርኩ።
አብረን ከዳነስን በኋላ ተቃቀፍን። ስለልጅነታችን መጫወት ስንጀምር “ አንዳንዴ ያ መልካም ጊዜ በሙዚቃ ውድድሮች ተሳትፈን የምንደንሰው፣ አዳዲስ የዳንስ አይነቶች የምንለማመደው እና ኳሷን ማየት እስከሚሳነን እግር ኳስ የምንጫወተው ትዝ ይለኛል..ከረጅም ጊዜ በኋላ ይመስላል።አይገርምም? "

“ይገርማል”

በሰባተኛው ወር መጀመሪያ ለስሊ አስጠርቶኝ በማዕከሉ አንድ ክፍል ተገናኘን፡፡ ሳገኘው ፊቱ የሃዘን እና ደስታ ስሜቶች በመፈራረቅ ይነበቡበታል...


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#የፈሪ_ሰው_ጸሎት

አምላክ ሆይ .
ይግባኝ ዐለኝና አቤት የምልበት
በአርባ አራት ጾሜ ሕግን 'ምሽርበት።
ለምን? የሚል ሐሳብ . . .
በመሸነፍ ብእር ልብ ወለድ ተደርሶ
ይጠይቃል ልቤ ከዙፋንኽ ደርሶ።

እዚኽ . . .
ሕግን እያወጣ ደንብ እያረቀቀ
ሕዝብ እያስከበረ እራሱ እየናቀ፣
ይበይንብኻል . . .!
አያድን ከቅጣት ሕግን ያላወቀ።
( . . . እያለ. . .)

( ፈተና ፩ )
ሠፊው የ'ኔ ዓለም . . .
ስልቻ ላይሞላ ሠርክ ፍዳ ኾነ
ሆድ የሚሉት ዋሻ ለግብሩ ታመነ ፣
ድንጋይን ከዳቦ እያፎካከረ
ኅሊናን ረስቶ ተገዛ ፣ታሰረ።

( ፈተና ፪ )
መከራዬ ኹሉ ዕንገት እያስደፋኝ
መንገዴ በሙሉ 0ጉኖ እያፋፋኝ ፣
ጠረጠርኩኝና ...
በኾነው በቀኑ መድረስኽን ረሳኹ ፤
በማወቅ ጉጉቴ . . .
ከመቅደስ ከፍታ ለመውደቅ ተነሣኹ።

( ፈተና ፫ )
ነባዊ . . .
ልባዊ . .
ሕያዊ . . .
መገመት ጀመሩ ፤ አንሰው ኮሰሱና
እሩጫው ዐየለ ፤ መስገድ እረሱና ፣
ሙዳይ መስፈራዬ አስገምቶኝ ከ'ኔ
ገዛኹ ፣ተገዛኹኝ ፤ በምድራዊው ቅኔ።

እናም . .
ልቤ ቃልን ስቶ
ለሥጋ ተገዝቶ
በዓለም ተመርቶ።
በሰው መኾን ግብር
አልችል ካለች ነፍሴ ፈተናውን ማለፍ፤
ይግባኝ ባሉት ብሂል ይቺ ጽዋ ትለፍ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ሰባት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


“ደህና ነህ?” ብየ ጠየቅኩት::

ደህና ነኝ ብሎ ራሱን እያሻሸ ይቅርታ ይሄን ነገር እንደገና ስላነሳሁት እንደሚያስከፋህ ይገባኛል ግን እውነቱን መናገር አለብኝ” አለ። ክፍሉን እየዞረ የቅርብ ቤተሰቦችህን ማግኘት አልቻልንም። ስለዚህ አሳዳጊ ቤተሰብ ልንፈልግልህ ነው።
እንደሚስማማህ ተስፋ አለኝ፡፡ ሌላ ሃሳብ አለህ?”

“አዎ!” ብየ አባቴ ከጦርነቱ በፊት በዚህ ከተማ የሚኖር አንድ አጎት እንዳለኝ ይነግረኝ እንደነበር ነገርኩት።

ስሙ ማን ነው?”

“ቶሚ ይባላል እና አባቴ አናፂ እንደሆነ ነግሮኝ ነበር” ብየ መለስኩ።

“ምንም ቃል አልገባልህም፤ ግን የቻልኩትን እሞክራለሁ።በቅርብ እንገናኛለን” ብሎ ዝም ካለ በኋላ ትከሻየን እየነካካ “ ጥሩ እየሰራህ እንደሆነ ሰምቻለሁ። በርታ”አለኝ። ለስሊ በሰጠሁት ትንሽ መረጃ አጎቴን ከትልቅ ከተማ መሐል ያገኘዋል ብየ ተስፋ
አልታጣኩበትም ነበር። ለስሊ ከሄደ በኋላ ወደ አስቴር ሄድኩ።ለአስቴር ከ ለስሊ ጋር ስለበረን ቆይታ እና አጎቴን ያገኘዋል ብየ
እንደማልጠብቅ ነገርኳት። “ አይታወቅም! ሊያገኘው ይችላል” ” አለች::

አንድ ቀን ቅዳሜ ከስዓት ይመስለኛል ከአስቴር እና መሐመድ ጋር እየተጫወትኩ እያለ ለስሊ እየሳቀ መጣ። ጉድፈቻ የሚወስደኝ ቤት አግንቶልኛል፤ ልቀላቀል ነው ብየ ገመትኩ። ከማህበረሰቡ ጋር “መቀላቀል” ይሉታል ታዳጊ ወታደር የነበሩ ልጆችን ከ ዘመዶቻቸው ወይም ከአሳዳጊዎች ጋር ሲያገናኙ።

“ምንድን ነው መልካሙ ዜና?”ለስሊ ዜናውን ለመስማት ፤ጉጉቴን ፊቴን ላይ እያነበበ ወደ በሩ ተመልሶ በሩን ከፈተው።
አንድ ረጂም ሰውየ ገባ፡፡ ከአባቴ ትንሽ ጠቆር ያለ ፈገግታው ግን ደመቅ ያለ ሰው ነበር።

“አጎትህ ነው አለ ለስሊ በኩራት።

' እንዴት ነህ ልጄ እስማየል? አለ ሰውየው:: ጎንበስ ብሎ በረጅም እጆቹ ጠበቅ አርጎ አቀፈኝ፡፡ ምን አልባት እያስመስለ ቢሆንስ ብየ አሰብኩ። ለቆኝ አለቀሰ። ሲያለቅስ እውነትም ዘመዴ
እንደሆነ አመንኩ፡፡ ምክንያቱም የእውነት ነበር ያነባው፤ በሃገራችን ባህል ወንዶች እምብዛም አያለቅሱም::

“ይህን ሁሉ ጊዜ መጥቼ ስላላየሁህ ይቅርታ አድርግልኝ:: ከዝች ቀን በፊት መጥቼ አይቼህ ቢሆን ንሮ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር። አሁን ያለፈው አልፏል። ዛሬ መጀመር እንችላለን። ስለ አጣሃቸው ቤተሰቦችህ በጣም አዝኛለሁ መፅናናተትን እመኝልሃለሁ። በርታ። ለስሊ ሁሉንም ነግሮኛል።” ለስሊን በአክብሮት አይን እየተመለከተ ቀጠለ “ ከዚህ ጨርሰህ ስትወጣ ከእኔ ጋር መጥተህ መኖር ትችላለህ። ልጄ ነህ! ብዙ የለኝም ግን የምታድርበት ቦታ፣ምግብ እና ፍቅር እስጥሃለሁ።” አለ።

ተነስቼ አጎቴን አቀፍኩት፤ እሱም አቅፎ ግንባሬን ሳመኝ፡፡ትንሽ ዝም ብለን ከቆየን በኋላ “ብዙ መቆየት አልችልም ከከተማ
ውጭ የጀመርኩት ስራ አለ። ለጊዜው ቅዳሜ እና እሁድ እየመጣሁ እጠይቅሃለሁ። አንተም ስትችል አንድ ቀን መጥተህ ቤቴን ታያልኛለህ:: ልጆቼን እና ባለቤቴን ቤተሰቦችህን ትተዋወቃለህ” አለ፡፡

“ጋሼ ከዚህ በኋላ ስለዚህ ልጅ ደህንነት እነግርዎታለን” አለ ለስሊ።

አመሰግናለሁ” አለ አጎቴ።

አጎቴ ስንሸኘው አባትህን ነው የምትመስለው ፤አስተዳደጋችንን አስታወስከኝ። እንደ አባትህ አስቸጋሪ
እንደማትሆን ግን ተስፋ አለኝ” አለ እየሳቀ። እኔም ሳቅኩ።

ስንመለስ አስቴር የቦብ ማርሌን ሙዚቃ ከፈተች እና አብረን ማዜም ጀመርን። “Three Little Birds” ሶስት ትናንሽ ወፎች “Dont Woy about a thing” ስለ ምንም ነገር አትጨነቅ
"Cause every little thing gonna be all right...."
ምክንያቱም ሁሉም መልካም ይሆናል

አጎቴን ስለማግኘቴ ለ አል ሃጂ እና ማቡ ልነግራቸው ፈለኩ ግን እነሱ ቤተሰብ ስላላገኙ ተሰማኝ።

አጎቴ ቃሉን ጠብቆ ቅዳሜ እና እሁድ እየመጣ ይጠይቀኝ ጀመር። ስጦታ ያመጣልኛል፣ ስለ አስተዳደጉ ይነግረኛል ስለ አባቴም ይጠይቀኝ ነበር። አንዴ አባቴ ስለነገረኝ አንድ የልጅነት ትውስታቸው ነገርኩት። አባቴ እና አጎቴ ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ሲወርዱ ድንገት የንብ ቀፎ ያንቀሳቅሱ እና ንቦቹ ይከተሏቸዋል። አባቴ አጭር ስለነበር አብዛኛው ንብ ከአጎቴ ራስ
ላይ ነበር፡፡ ሩጠው ወንዝ ውስጥ ቢገቡም ጠብቆ ሊለቃቸው አልቻለም:: ስለዚህ ከውሃው ወጥተው ወደ መንደር ሲሮጡ ንቦቹን ወደ ሰፈር ይዘዋቸው መጡ።

“አዎ አስታውሳለሁ፡፡ ሁሉም ሰው ንቦቹን ወደ መንደር ይዘናቸው ስለመጣን አዝኖብን ነበር። መሮጥ የማችሉትን
ሽማግሌ ሰዎች እና ትንንሽ ህፃናትን ንቡ ነድፏቸው ነበር።አባትህ እና እኔ ግን በር ዘግተን አልጋ ስር ተደብቀን በሰዉ
እንስቅ ነበር” ብሎ ሲስቅ አብሬው ሳቅኩ፡፡

አንድ ቀን አጎቴ ቤተሰቦቹን ሊያስተዋውቀኝ ወደ ቤቱ ወሰደኝ::
ፍንትው ያለ ፀሐያማ ቅዳሜ ነበር። ኒው ኢንግላንድ ቬል New England Vile ውስጥ ነው የሚኖረው፡ውብ ከተማ ነበር። ቤቱግን መብራት ሆነ የቦንቧ ውሃ የለም። ወደ ደጁ ስንጠጋ የአጎቴ
ባለቤት ወጣች:: ፊቷ ያበራ ነበር፡፡ አጥብቃ አቀፈችኝ፡፡ ለቀቀችኝ እና ካየችኝ በኋላ ጉንጨን ቆንጥጣ “ እንኳን ደህና መጣህ ልጅ አለች:: አጠር ያለች ጥቁር ፣ ክብ ፊት እና አይኖቿ ጎላ ጎላ ያሉ ሴትዮ ነበረች። አባቴ የራሱ ልጆች አልነበሩትም ግን የቤተሰብ ልጆችን እንደራሱ አድርጎ ያሳድግ ነበር፡፡ አራት ነበሩ፦ አሌ
ትልቁ ሲሆን፣ ማቲልዳ፣ ኮና እና ሶሞ ይከተላሉ፡፡ የሚሰሩትን ስራ አቁመው መጥተው ሰላም አሉኝ፡፡ “ሌላ ወንድም ማግኘት ደስ ይላል” አለ አሌ እያቀፈኝ፡፡ ከተዋወቅን በኋላ ከአክስቴ እና ከአጎቴ በስተቀር ሁሉም ወደ ስራቸው ሄዱ። አክስቴ የምግብ አይነት እያመጣች ትደረድራለች፦ ሩዝ፣ አሳ፣ ሾርባ፣ አትክልት
ሌሎች ምግቦች። ሆዴ እስከሚነፋ ድረስ ብዙ በላሁ። ከምግብ በኋላ አጎቴ የአናፂ መሳሪያዎችን እና መስሪያ ቦታውን
አስጎበኘኝ፡፡

“ አናፂ መሆን የምትፈልግ ከሆነ ረዳቴ ልትሆን ትችላለህ። ግን እንደ አባትህ ትምህርት ቤት መግባት የምትፈልግ
ይመስለኛል” ሲል ፈገግ አልኩ። አሌ ተመልሶ መጣና አጎቴን ከእኔ ከእሱ ጋር ኳስ እንዲጫወት ፍቃድ ጠየቀ፡፡ አጎቴም እሱ ከፈለገ እሽ አለ፡፡ እኔ እና አሌ ተያይዘን ብሮክፊልድስ Brookfields ወደ ሚባል አካባቢ ሄድን።

“ወደ እኛ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል:: የእኔን ክፍል መጋራት እንችላለን” አለኝ፡፡ በእድሜ ከእኔ ይበልጠኛል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም አጠናቋል። ደስተኛ ፣ ስርዓት ያለው እና ተናጋሪ ነው። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት አንዲት ቆንጆ ልጅ ወደ እኛ እጇን ታውለበልባለች። ማናት ብየ ከ መጠየቄ በፊት አሌ የአጎታችን ልጅ ናት ከመንገዱ ማዶ ከጉድ ፈቻ አሳዳጊዎቿ ጋር ነው የምትኖረው፡፡ አሚናታ ትባላለች ትተዋወቃላችሁ” አለኝ፡፡አሚናት የአባቴ ሁለተኛ ወንድም ልጅ ነች።
ኳስ ጨዋታውን እየተመለከትን የእኔ ልብ ግን የነበረው ይኖራል ብየ አስቤው የማላውቀው ቤተሰብ መገኘት ላይ ነበረ።
ደስተኛ ነበርኩ። ስንመለስ አጎቴ ወደ ማዕከሉ ሊመልሰኝ እየጠበቀኝ ነበር። እጄን ይዞ አውቶብስ ጣቢያው እስከምንደርስ ድረስ ምንም አላልኩም:: አውቶብስ ጣቢያው ስንደርስ ሌላ ጊዜ
በእራስህ ልትጎበኘን ከፈለክ ብሎ ገንዘብ ሰጠኝ፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ለስሊ ወደ ማህበረሰቡ እንደምቀላቀል ነግሮኝ ነበር፡፡ ከአጎቴ ጋር ነው የምኖረው ሁለቱ
ሳምንቶች ቤኒን ቤት ካሳለፍኩት
ስምንት ወራቶች በላይ ረዘሙብኝ። ፈርቻለሁ። ከቤተስብ ጋር ለመኖር ፈርቻለሁ..
ለአመታት ብቻየን እራሴን ጠብቄ ያለ ማንም ምክር ነው የኖርኩት። ምናልባት አጎቴን እንዳላስቀይመው ፈራሁ። ራስ
ምታቴን፣ የለሊት ቅዠቴን፣ ልደብቀው የማልችለው መከፋት ምን እንደማደርግ አላውቅም።

ቀኑ ሲደርስ ዕቃየን ሰብስቤ በፌስታል ቋጠርኩ። መጀመሪያ አዳሪ ትምህርት ቤት ስገባ እንደተሰማኝ ስሜት ነበር የተሰማኝ፣ ልቤ ይመታ ነበር። መሐመድ ፣አል ሃጂ እና ማቡ አብረውኝ ነበሩ። አስቴር ትንሽ ቆይታ መጣች። “መሄድ አለብኝ” ብየ እጄን ወደ መሐመድ ስዘረጋ እሱ ግን ዘሎ አቀፈኝ። ማቡም አጥብቆ
አቀፈኝ፡፡ በኋላ ማቡ ቤተሰቦቹ ስላልተቀበሉት ወደ ጦርነቱ
ተመልሷል። አል ሃጂን ትክሻውን እየነካካሁ ፈገግ ስል “ ቻው አለቃ” አለኝ። ከአንድ ጉድ ፈቻ ቤት ወደ ሌላ ይቀያይር ስለነበር ከዚህ ቀን በኋላ አላየሁትም፡፡ አስቴር አይኖቿ እንባ አቀረዉ ነበር፡፡ አጥብቃ አቀፈችኝ፡፡ ከለቀቀችኝ በኋላ ወረቀት ሰጠችኝ።“ ይሄ አድራሻዬ ነው በማንኛውም ቀን መምጣት ትችላለህ
አለች::

አስቴርን ብዙ ጊዜ ተመላልሼ አይቻታለሁ። የሄድኩበት ስዓት ጥሩ አልነበረም። አቀፈችኝ እና አይኖቼን ቀጥታ እያየች በቀጣይ ቅዳሜ ወይም እሁድ ና እና እየኝ ሰፊ ጊዜ ይኖረናል አለች፡፡ ነጭ የደንብ ልብሷን ለብሳ ወደ ሌሎች የተጎዱ ህጻናት እየሄደች ነበር።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#ፍጻሜ_ሥጋ

አንዳንድ ቀን አለ . . .!
በደማቅ ቀለማት ከልብ የሚታተም
ልክ እንደፏፏቴ ካ'ለት የሚላተም።

በዚያ ቀን ...!
ጽልመት አሸንፋ የጠራች ጨረቃ፣
ሆደ ሠፊን ሰማይ አበራችው ደምቃ፤
ገዴ ዕጣ ክፍሌ . . .
አንዲት ፍኩ ኮከብ ፣ መለዮ ሰንደቋ።

ያን ቀን ...!
የምኞቴ እውነት ፣ የጸሎቴ ብሥራት
የልመናዬ ጥግ ፣ የሥለቴ ስምረት።
ጎኔ ተኝታለች፤
በዙሪያዬ ጸንታ ዕቅፌ ገብታለች።
ለደቂቃ ቅጽበት
በዐይኔ ዕቅፋት
በአንድ ጥቅሻ ፤
በከንፈርሽ ነጻ የልቤ ጥቀርሻ።

ይህ ቀን . . .!
ዐርብ ዕለት
ምሽት ኹለት ሰዓት ፣
እንዲሁም .
ጥንድ እውነት።

ያነፋስ ውብ ዜማ ፣ የቀልቤ ውልብታ
ያ'ብሪ ትሎች ፋና . . .
ምንጩ ያልታወቀ የነፍስ ፈገግታ።

(. . . ሠንቆ ነበረ . . . )

ፍጥረታት አኩርፈው ሰማይ ከል ለብሶ ፣
ትንቢት ተፈጽሞ . .
የሾኽ አክሊል ደፍቶ ቃል ሥጋ ተላብሶ።

ከእልፍ እንስት ዐይኖች ፣ እንባ እየጎረፈ፤
ፍጹሙ ፍቅራችን ፣
በፍጻሜው ዕለት ፣
የነፍስ ሐቃችን ውል ፣ እየተጠለፈ ፤
ሰውኛ ግብራችን . . .
የተፈጥሮን ኩርፊያ በጻድቅ ደም ጻፈ።
እናም በዚኽ ዕለት
የነፍሳችን ክብር በ'ርቃን ከታሠረ ፤
ሥጋ ፍጻሜ ነው !
በ'ርቃንሽ ተዋርዶ በደምሽ ከበረ።

🔘ተስፍሁን ከበደ🔘
👍2
#የነፍስጥም_ጽዋ

በሠቀቀን መኖር . .
በፍርሀት መስጋት ነገን በመናፈቅ፣
በይኾናል ተስፋ . . .
ዛሬን ሠውተኸው ለመጪው መንፈቅፈቅ።

( ..ምን ይሉት ፈሊጥ ነው . . ?)
ለምን ነው መጠበብ . . . ?
ለምን ነው መብሰልሰል ?
አኹን ላይ ተገልጦ ዘላለምን መምሰል።
ኖረኽ ለማታውቀው ሠርክ ከምትለፋ ፣
ዝም ብለኽ ጠጣና . .!
ሞት እንደኹ ያው ሞት ነዉ ፤ ዐይነ ስቡ ይጥፋ !

በእጅኽ ጨብጥና የብርሌን ዐንገት
ተጎንጭ ፣ አጉድልለት፤ የኑሮኽን ንፍገት።
ኹሉም እውነት አለው ፤ ከስካር በኋላ
የሚገለጥበት ፣ ከተሸፈነበት መጋረጃ ጥላ።

እንግዲኽ ሞት ማለት ..
ጽዋኽ ላይ የቀረው ፣ ማክተሚያው የጥማት
ባ'ንድ ትንፋሽ ወስደኽ ፣ የምትፈጽመው ቋት።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ስምንት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

....ብዙ የጦርነት ታሪክ እያዳመጡ መኖር
ይከብዳል። እኔ የራሴ አንድ አስቸጋሪ፣ አስጨናቂ እና በየ ጊዜው የሚጎዳ ታሪክ አለኝ፡፡ ለምንድን ነው ግን እሷ ይህን የምትሰሪው? ለምንድን ነው ግን እነሱ ይሄን የሚሰሩት? በየፊናችን የሄድን ይመስለኛል። ለመጨረሻ ጊዜ ያየኋት ጊዜ ነው። እወዳታለሁ ግን አልነገርኳትም::

አጎቴ በእጆቹ አንስቶ መኪና ውስጥ አስገባኝ፡፡ “ እንደ አለቃ (ሊቀ መንበር) ነው የምቀበልህ። አለቅነትህ ዛሬ ይጀምራል” አለኝ። አራቱ የአጎቶቼ ልጆች አሌ እና ሶስቱ ሴቶች ማቲልዳ፣
ኮና እና ሶሞ ተራ በተራ እያቀፉ ሳሙኝ። ፊታቸው በፈገግታ በራ። “እርቦሃል አይደል፤ እንኳን ደህና መጣህ በማለት ቆንጆ ዶሮ ወጥ ሰርቼለሁ” አክስቴ፡፡ እውነትም ቆንጆ ነበር። ታፋጭ!
እጄን እየላስኩ ነበር፡፡ ከምግብ በኋላ ምኝታ ቤቱን አሌ አሳየኝ።መሬት ላይ ነበረ ምተኛው። ምንጣፍ፣ አንሶላ እና ብርድ ልብስ የት እንዳለ አሳየኝ፡፡ ወደ ደጃፍ ስወጣ አጎቴ ከተማውን ታውቀዋለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ “ብዙም አለመድኩትም” አልኩ።

“አሌ ያስጎበኝሃል። ካልሆነ ደግሞ በራስህ እየጠፋህ እየተገኘህ ልታጠናው ትችላለህ። ከተማው ለማውቅ ጥሩ ነው::”

ከአጎቴ ጋር መኖር ከጀመርኩ ከአንድ ወይም ሁለት ቀናት በኋላ አሌ ሸሚዝ፣ ቀበቶ እና ከሙሉ ልብስ ጋር የሚለበስ ጫማ ሰጠኝ:: “ ጨዋ መሆን ከፈለክ እንደ ጨዋ ልበስ” ብሎ ሳቀና ቀጠለ፡፡ “ሚስጥር ነው:: ዛሬ ማታ ጭፈራ ቤት ልወስድህ እፈልጋለሁ:: ትንሽ ዘና ትላለህ:: አጎቴ ወደ ምኝታ ከሄደ በኋላ
እንወጣለን::”

ማታ ከቤት ሾልከን ወደ መጠጥ ቤት ሄድን። ከአሌ ጋር ስንሄድ ትምህርት ቤት እያለሁ የሄድኩባቸው የጭፈራ ምሽቶች
ትዝ አሉኝ፡፡ ረጂም ጊዜ ነው ግን የጭፈራ ምሽቶቹ ስያሜዎችን አይረሱኝም፡፡ Back to School” ወደ ትምህርት ቤት
እንመለስ፣ “Pens down” ብዕራችንን እንጣል፣ “Bob Marley Night የቦብ ማርሌ ምሽት እና ሌሎችም ነበሩ። አውራ ዶሮ እስከሚጮህ ድረስ እንጨፍር ነበር። ያኔ በጣም ደስተኛ ነበርኩ።

“ደርሰናል” አለ አሌ። ብዙ ወጣቶች ወደ ጭፈራ ቤቱ ለመግባት ሰልፍ ይዘው ነበር፡፡ ወንዶቹ በደንብ የተተኮስ ሱሪ
እና ሸሚዝ ለብሰዋል፡፡ ሴቶቹ ደግሞ ቆንጆ አበባ ቀሚስ ከረጂም ተረከዝ ጫማ ለብሰው ከአንዳንድ ወንዶች በላይ ረዝመው ይታዩ ነበር። ከንፈሮቻቸውን ደማቅ ቀለም ተቀብተዋል። አሌ ደስተኛ
ሁኖ ከሰልፉ ፊት ካሉት ሰዎች ጋር ያወራ ነበር። ስንገባ ሙዚቃ እስከአንቃሩ ተከፍቶ ነበር። አሌን ተከትየ ጠረጴዛ አግንተን አንድ ከፍ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥን።

“ ወደ ዳንስ መድረኩ ልሄድ ነው” ብሎ ተነሳ፡፡ ብዙም ሳይቆይ በህዝቡ መሐል ተሰወረ። ለደቂቃዎች ሳስብ ከዛ ብቻየን ስደንስ ከቆየሁ በኋላ ድንገት አንድ በጣም ጥቁር ሴት አንስታ ወደ ዳንስ
መድረኩ መራችኝ። አብረን ከምቱ ጋር መደነስ ጀመርን።በሙዚቃው መሐል አንድ ከእኔ ተለቅ ያለ ልጅ ጎትቶ ወሰዳት።

“ አማላይ ነህ አየሁህ እኮ” አለ አሌ ከአጠገቤ ቁሞ። እየሳቀ ነበር። እኔ ምንም አላረኩም:: ከእኔ ጋር መደነስ ፈልጋ ነው።አልኩ

እውነት ምንም ሳትል ሴቶች ወደ አንተ ይመጣሉ” ብሎ ቀለደ፡፡ ለሊቱን ሙሉ ደነሰን አጎቴ ከመንቃቱ በፊት ተመለስን።

ከተወሰኑ ምሽቶች በኋላ ብቻየን ወደ መጠጥ ቤቱ ሂጂ ልጂቱን አገኘኋት። ስሟ ዘይናብ እንደሆነ ነገረችኝ፡፡

“ባለፈው ስለሆነው ነገር ይቅርታ አድርግልኝ” አለች።ወንድሜ ወደ ቤት መሄድ ፈልጎ ነው እና ከእሱ ጋር መሄድ
ነበረብኝ፡፡ ካልሆነ ወላጆቼ ይጨነቃሉ።”

ልክ እንደ እኔ እሷም ብቻዋን ነበረች።

ለሶስት ሳምንታት ያህል አብረን ከቆየን በኋላ ብዙ ጥያቄ መጠየቅ ጀመረች፡፡ ከየት እንደመጣሁ? ክፍለ ሃገር ማደግ
እንዴት እንደሆነ? ክፍለ ሃገር ብዙ የፍሪ ታውን ሰው የሚጠቀምበት ቃል ሲሆን ገጠሬነትን ከኋላ ቀርነት እና ስርዓት
ማጣት ጋር አያይዞ ይገልፃል። ምንም ልነግራት አልፈለኩም ስለዚህ ተወችኝ። በቃ ከ ፍሪታውን ሴቶች ጋር የነበረኝ የፍቅር ታሪክ ይሄው ነው። ስለ እኔ ማወቅ ይፈልጋሉ እኔ ደግሞ ታሪኬን ለመንገር ዝግጁ አልነበርኩም። ምንም አይደል። ብቻየን መሆኔን ወድጀዋለሁ።

ለስሊ ሊያየኝ መጣ፡፡ እንዴት እንደሆንኩ እና ምን እየሰራሁ እንደሆነ ጠየቀኝ፡፡ ከትንሽ የራስ ምታት በስተቀር ደህና
እንደሆንኩ ነገርኩት። ማስታወሻ ደብተር ነገር አውጥቶ ፃፈ። “አንድ ስራ አለ ላንተ: በጣም አስፈላጊ ነው::”

ሁሌም የመልካም ዜና አብሳሪ ነህ” አልኩት።

“ ጠቃሚ ነው:: ሁለት ልጆችን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኒው ዮርክ አሜሪካ በመላክ የህፃናት ህይወት
በሴራሊዮን ምን እንደሚመስል ለማስረዳት ታስቧል። ስለዚህ
ቃለ መጠይቅ እየተደረገ ነው:: አቶ ካማራ አንተ ቃለ መጠይቅ እንድታደርግ ጠቁመው ነበር። ከፈለክ ይሄ አድራሻው ነው።አለና ሲፅፍበት የነበረውን ወረቀት ከማስታወሻው ገንጥሎ ሰጠኝ፡፡ “አብሬህ እንድሄድ ከፈለክ ቢሮ ና። ለቃለ መጠይቁ

የሚመጥን ልብስ ለብሰህ ና እሺ” ብሎ ሄደ::

የቃለ መጠይቁ ቀን ሲደርስ ግን እንደነገሩ የ አዘቦት ልብስ ለበስኩ። ስኒከርስ ፣ ጂንስ ሱሪ እና ረጅም እጅጌ ቲ ሸርት ለብሼ ሄድኩ። ለማንም የት እንደምሄድ አልተናገርኩም። ለአሌ
ልነግረው አሰብኩ ግን መናገር ከጀመርኩ ስለ ራሴ ከሚያውቀው አጎቴም ከነገረው በላይ ልነግረው ስለምችል ብየ ፈርቼ
ተውኩት።

ጠያቂው አትኩሮ ተመለከትኝ እና ቀስ ብሎ በእንግሊዝኛ

“ስምህ ማነው” ብሎ ጠየቀኝ።

“እስማየል” አልኩ።

ለምን አንተ ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሂዶ በዚህ ሃገር ስላሉ ህፃናት ችግሮች ለመናገር ትክክለኛው ሰው ነኝ ብለህ ታስባለህ?”

“ከክፍለ ሃገር ነው የመጣሁት:: በጦርነቱ የተጎዳ ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ የተሳተፍኩ እና በህፃናት ማገገሚ ያለፍኩ ነኝ፡፡ በቃለ
መጠየቁ ከተሳተፉት የከተማ ልጆች በላይ የተሻለ ግንዛቤ አለኝ፡፡ እኔ አልፌበታለሁ። እነሱ ግን እዛ ሄደው ምን ሊሉ ይችላሉ? ከዜና የበለጠ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም::” ፈገግ ብሎ
የሚያየኝ ጠያቂ ትንሽ አበሳጭቶኛል።

“ሌላስ ምን ትላለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡

“ምንም! ለምንድን ነው ምትስቅብኝ?” ብየ መልሼ ጠየቁኩት::

“አሁን መሄድ ትችላለህ” አለ ሰውየው አሁንም እየሳቀ።

ተነስቼ ወጣሁ። በኋላየ በሩ እንደተከፈተ ትቼው ወደ አሳንሰሩ ሄጄ ቆምኩ አልተከፈተም። ለቃለ መጠየቁ የመጡት
ልጆች ሳቁብኝ። ትንሽ ቆይቶ አንድ ሰው መጣና ግድግዳው ላይ ቁልፍ ተጭኖ ከፈተልኝ፡፡ ቁጥር ተጫነልኝ እና እጁን
በማውለብለብ ተሰናበተኝ፡፡ አሳንሰሩ መንቀሳቀስ ሲጀምር የምይዘው አጣሁ ወዲያው ግን ከወለል ደረስኩ። ከህንጻው
ወጥቼ ቅርጹን መመርመር ጀመርኩ። ለመሐመድ አግኝቼ ልነግረው ጓጓሁ።

ቀስ ብየ የሚያልፉትን መኪናዎች እያየሁ መጓዝ ጀመርኩ፡፡ብዙ መኪናዎች፣ የጦር መኪና እና የሃገሪቱን ባንዴራ እላያቸው
ላይ ያደረጉ መርሰዲስ መኪኖች ተከታትለዉ በፍጥነት አለፉ።ቤት ስደርስ በብዙ መኪኖች ታጂቦ የሚልፈው የተከበረ ሰው ማነው ብየ አሌን ጠየቁኩት። ቲጃን ከባህን ይባላል። አዲሱ ፕሬዝደንት ነው አለኝ፡፡ የሴራ ሊዮን ህዝቦች ፓርቲ የሚባለው ፓርቲው ግንቦት 1996 ምርጫ አሸንፎ ሃገሪቱን ከ ሰምንት
ወራት በፊት ጀምሮ እየመራ እንደሆነ ነገረኝ።

አንድ ጥዋት አቶ ካማራ ወደ አጎቴ ቤት መጣ። ከቀናቶች በፊት
👍2
ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደምሄድ ነግሮኝ
ነበር። ግን ኒው ዮርክ እሄዳለሁ ብየ ስላላመንኩ ከመሐመድ ዉጪ ለሌላ ሰው አልተናገርኩም::

“ሰላም አደርክ” አለ አቶ ካማራ ገና ጥዋት መሆኑን ከስዓቱ እያረጋገጠ፡፡

“ሰላም አደርክ” አልኩ መልሼ፡፡

ወደ ከተማ ለመሄድ እና ለጉዞህ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ዝግጁ ነህ?”


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#ለኀጥአን_የመጣ #ክፍል_አስራ_ስምንት #የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ #በኢስማኤል_ቤህ #ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው ....ብዙ የጦርነት ታሪክ እያዳመጡ መኖር ይከብዳል። እኔ የራሴ አንድ አስቸጋሪ፣ አስጨናቂ እና በየ ጊዜው የሚጎዳ ታሪክ አለኝ፡፡ ለምንድን ነው ግን እሷ ይህን የምትሰሪው? ለምንድን ነው ግን እነሱ ይሄን የሚሰሩት? በየፊናችን የሄድን ይመስለኛል።…»
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


አክስቴን ተሰናብቼ መኪና ውስጥ ዘልዬ ገባሁ እና የይለፍ ወረቀት (ፓስፖርት) ለማግኘት በረርን፡፡ የከተማው ሰው ሁሉ
ፓስፖርት አውጥቶ ከሃገር ለመኮብለል የወሰነ ይመስላል። ብዙ ሰው ነበር። አቶ ካማራ ግን ቀጠሮ ስላስያዘ ገብተን ፎቶ፣
አስፈላጊ መረጃዎችን አስገባን እና ክፍያ ፈፅምን። ፓስፖርቱ ከአራት ቀን በኋላ እንደሚደርስ ለአቶ ካማራ ነገሩት።

“የመጀመሪያው ደረጃ ተጠናቋል፤ አሁን ቪዛ ማግኘት አለብን።” አለ አቶ ካማራ ከዛም ከፓስፖርት ቢሮ ወጣን፡፡

ማታ ቤት ስመለስ አጎቴ ቤት ነበር ሰላምታ ስሰጠው ፈገግ ብሎ
“ምን እየተካሄደ እንደሆነ ልትነግረኝ ትችላለህ” አለ። በዝርዝር ኒው ዮርክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሂጄ ስለ ጦርነቱ እና በህፃናት ላይ ስለ ሚያደርሰው ተፅዕኖ ንግግር ላደርግ
እንደሆነ ነገርኩት። አጎቴ ብዙም አላመነም። “ሰዎች ብዙ ጊዜ
እንደዚህ አይነት ተስፋ እየስጡ ሌሎችን ያታልላሉ። ልጄ ተጠንቀቅ! ተስፋህን ሙሉ በሙሉ በእሱ ላይ ብቻ እንዳትጥል!”
አለኝ::

ጥዋት ወደ ስራ ከመሄዱ በፊት “የአሜሪካው ጉዞ ዘግጅት እንዴት ነው?!”ብሎ ይቀልዳል።
አቶ ካማራ ገበያ ይዞኝ ሄደና የልብስ ሻንጣ እና የተለያዩ አይነቶች ልብሶች፦ ረጂም እጅጌ ሸሚዝ፣ ጨርቅ ሱሪ እና ባህላዊ ልብሶች ገዛልኝ፡፡ ለአጎቴ አሳየሁት ግን ትሄዳለህ ብሎ ሊያምን
አልቻለም:: “ትንሽ ቀየር ብትል፤ ቢያምርብህ ብለው ነው” ብሎ
ይቀልድብኛል።

አንዳንዴ አጎቴ እና እኔ ከስራ በኋላ ዘወር ዘወር እንላለን። እንደት እንደሆንኩ
ይጠይቀኛል። ደህና እንደሆንኩ
እነግረዋለሁ። ረጂም እጆቹን ትክሻዬ ላይ ያደርግ እና ወደ እሱ ያስጠጋኛል። አንዳንድ ነገሮችን ልነግረው ፈልጌ ቃላቶችን እንዳጣሁ የሚውቅ ይመስለኛል፡፡ እንደዛ ነው ሚሰማኝ፡፡ ከአጎቴ ልጆች ጋር ወደ ጫካ ሂደን እንጨት ስንለቅም አዕምሮዬ ባለፈው
ያየሁት እና የተሰራው በማስታወስ ይዋዥ ቃል።

ሰኞ ጥዋት ዶ/ር ታምባ የተባለ ሰው በአሜሪካን ኢምባሲ እንዳገኘው ተነግሮኛል። ወደ ኢምባሲው ሲሄድ የከተማው ቀስ በቀስ መንቃት ይሰማኝ ነበር። በከተማው ሙሉ የሚሰማው
ማህል ከተማ ያለው የመስጊድ የጸሎት ጥሪ፣ የአዟሪዎች የግዙኝ ተማፅኖ፣ የመኪና ረዳቶች ጥሪ “ሉምሌ፣ሉምሌ” ወይም ኮንጎ ሰፈር። በጣም በጥዋቱ ብደርስም ብዙ ሰዎች ኢምባሲ በር ላይ
ተሰልፈዋል። ፊታቸው የተቆጣ ሰው ይመስላል። ፍርድ ትሞታለህ ወይም ትኖራለህ የሚል ፍርድ የሚጠብቁ ነው
ሚመስሉት፡፡ ምን እንደማደርግ አላውቅም ነበር። ዝም በዬ ሰልፉን ጠብቄ ተሰለፍኩ። ከአንድ ስዓት በኋላ ዶ/ር ታምባ ከአንድ ልጅ ጋር መጣ እና እንድከተለው ጠየቀኝ። ልጁም ቀድሞ
ወታደር እራሱን አስተዋወቀ “ቤህ እባላለሁ። አብረን ስለምንሄድ ደስ ብሎኛል” ብሎ እጄን ጨበጠ። የአጎቴ መልስ ትዝ አለኝ ልጄ ተጠንቀቅ! ተስፋህን ሙሉ በሙሉ በእሱ ላይ ብቻ እንዳትጥል”

ከሚያማምሩ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጥን ቃለ መጠየቁን መጠባበቅ ጀመርን፡፡ አንድ ነጭ ሴትዮ በግልፅ መስታውት ጀርባ ቁማ በድምፅ ማጉያ “
ለምን አላማ ነበር ወደ አሜሪካ የምትጓዘው?” ብላ ጠየቀች፡፡

የእኛ ተራ ሲደርስ ከመስታውቱ ጀርባ ያለችው ሴትዮ ፓስፖርታችንን ይዛ ነበር፡፡ ወደ እኔ አላየችም ይልቅ የፓስፖርቴን ገጾች ትገልጥ ነበር። መስኮቱ ለምን እንደዚህ የሰው ንክኪ እንዳይኖር ታስቦ እንደተሰራ ገረሞኝ እመለከት ነበር።

“በድምፅ ማጉያ ተናገር” አለች እና “ለምን አላማ ነበር ወደ አሜሪካ የምትጓዘው?” ብላ ጥያቄዋን ጀመረች::
“በህፃናት ላይ ስለ ሚያደርሰው ተፅዕኖ” ብየ ገለጸኩ::
“ጉባኤው የት ነበር?”
“ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኒው ዮርክ ከተማ
“ወደ ትውልድ ሃገርህ ለመመለስህ ዋስትናህ ምንድን ነው?እያሰብኩ ነበር “ንብረት አለህ፣ መመለስህን ሊያረጋግጥ
የሚችል የባንክ ተቀማጪስ አለህ?”
ተናደድኩ። በዚህ ሃገር ስላለው የህዝብ ኑሮ የምታውቂው ነገር አለ? ብዬ ልጠይቃት አስብኩ። ቀና ብላ ብታየኝ ኖሮ ይሄን ጥያቄ አትጠይቅም ነበር። በእኔ እድሜ ያለ ማንኛውም የሃገሬው ሰው የባንክ ሂሳብ መኖር አይደለም እስከ ጪራሹ ህልሙም የለውም:: ዶ/ር ታምባ በጦርነት የተጎዱ ህጻናት ተራድኦ
ድርጅት ሊቀ መንበር እንደሆነ እና አብሮን እንደሚሄድ፣ጉባኤው ሲያልቅ ወደ ሴራሊዮን እንደሚመልሰን አስረዳት።
ሴትዮዋ የመጨረሻ ጥያቄ ጠየቀች: “ አሜሪካ የሚኖር የምታውቀው ሰው አለ?”

“ማንም የለም። ከዚህ ሃገር ወጥቼ አላውቅም እንዳውም በዚህ ከተማ እንኳ የመጀመሪያየ ነው” አልኩ። ፓስፖርቴን
ዘግታ ነጥላ አስቀመጠችው።

ውጭ ዶ/ር ታምባ ቪዛ እንዳገኘን እና ፓስፖርታችንን ነገ እንደሚወስድ ነገረን፡፡ በመጨረሻ መንገደኛ መምስል ጀመርኩ፡፡
በቀኝ እጄ ሻንጣየን ይዣለሁ ፤ ቡናማ ባህላዊ ሱሪ እና ሽሚዝ ለብሼ ነበር። ከአሌ ክፍል ስወጣ አጎቴ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ነበር።

“ወደ አየር መንገድ እየሄድኩ ነው” አልኩ ፈገግ ብዬ፡ አጎቴ እንደሚቀልድብኝ አውቅ ነበር፡፡አዎ! አሜሪካ ስትደርስ ደውልልኝ፡፡ አይ መች ስልክ አለኝ፡፡በል በአሚናታ ቤት ደውልልኝ መጥታ ታገኘኛለች” ብሎ አጎቴ
ፈገግ አለ።

“እሽ እደውላለሁ” ብየ በፈገግታ መለስኩ።

“ልጆች ኑ ወንድማችሁን ተሰናበቱት። የት እየሄደ እንደሆነ አላውቅም ግን ይቅናህ እንበለው” አለ አጎቴ። ማቲልዳ፣ ኮና እና
ሶሞ ባልዲ እንደያዙ ወደ ደጃፍ መጡ። ውሃ ሊቀዱ ሊሄዱ ነበር፡፡ አቀፉኝ እና በመንገዴ እንዲቀናኝ ተመኙ። አክስቴ ጪስ ጪስ እንደሸተተች ከኩሽና ቤት መጥታ አቀፈችኝ። “ የትም ብትሄድ ቤትህን ጠረን መሽተት አለብህ። ይሄ ላንተ የምሰጥህ ሽቶየ ነው”አለች በፈገግታ:: አጎቴ ተነስቶ አቀፈኝ እጆቹን ትክሻየ ላይ አድርጎ “መልካም ምኞቴ ካንተ ጋር ነው። በኋላ ለእራት እጠብቅሃለሁ” ብሎ ወደ ደጃፍ ወጣ፡፡

ስለ ኒው ዮርክ ያለኝ አመለካከት የሚመነጨው ከራፕ ሙዚቃዎች ነበር። ሰዎች መንገድ ላይ የሚታኮሱበት እና ምንም እንዳልተፈጠረ የሚመስሉበት፣
ማንም የማይጓዝበት ይልቅ በስፖርት መኪኖች ለጭፈራ እና ለሁከት የሚሄድበት ቦታ አድርጌ ነበር በአዕምሮዬ የሳልኩት። እንደዚህ አይነት የእብድ ቦታ መገኘት አልፈልግም። ሃገር ቤት በቅቶኛል::

ጆን ኤፍ ኬኔዲ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ስንደርስ ጨልሞ ነበር። 4፡30 ነበር። ዶር ታምባን ለምን በጠዋት እንደጨለመ
ጠየቅኩት።” (Winter ) በጋ ስለሆነ” አለኝ። “አሃ”ብየ ራሴን ነቀነቅኩ ግን በጠዋት መጨለም የሚለው ነገር ሊገባኝ
አልቻለም:: Winter ዊንተር የሚለውን ቃል በሼክስፔየር ጹሑፎች አውቀዋለሁ ግን ትርጉሙን እንደገና ማየት ያለብኝ
ይመስለኛል።

ዶ/ር ታምባ ፓስፖርታችንን ይዞ ሄደ እና ከኢምግሬሽን ሰዎች ሁሉንም ነገር አስረድቶ አለፈ። ሻንጣችንን አገኘን ወደ
ተንሸራታች በሮች አመራን። ዶ/ር ታምባ ውጭ ነበር። ባህ እና እኔ በተንሸራታች በሩ ስናልፍ በጣም ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበለን።ቆዳየ ሲኮማተር ይሰማኛል፣ ፊቴ ሊሰማኝ አልቻለም፣ እና ጆሮዬ
ተቆርጦ የወደቀ ይመስላል፣ እጣቶቼን አመመኝ ጥርሴም ተንቀጠቀጠ። ንፋሱ በሱሪየ እና ሸሚዜ አልፎ ገብቷል፤ ምንም
የለበስኩ አልመስለኝ አለ፡እየተንቀጠቀጥኩ ነበር። በህይወቴ
እንደዚህ በርዶኝ አያውቅም። ሰው እንዴት ነው ከዚህ ሃገር የሚኖረው? ብዬ አሰብኩ፡፡ ዶ/ር ታምባ ታክሲ ይዞ እኔ እና ባህን አስገባን እና ለሹፌሩ ወረቀት ላይ እያነበበ ወደ የት መሄድ እንደሚፈልግ
👍2
ነገረው።የሆነ ነጭ ነገር ከስማይ እየወደቀ መሬት ላይ ይከማች ነበር። ምንድን ነው ከሰማይ የሚወድቀው ነጭ ነገር?ብዬ እያሰብኩ እያለ ሹፌሩ “ የመጀመሪያችሁ ነው ወደዚህ ከተማው ስትመጡ? በረዶውን ወደዳችሁት” ጠየቀን።

አዎ አዲሶች ናቸው ለከተማው” አለ ዶ/ር ታምባ መረጃዎቻችንን እያገላበጠ። (Snow)ስኖ ”በረዶ” የሚል ቃል
ሰምቼ አላውቅም። ሴራ ሊዮን ብዙ የሚወራበት ነገር አይደለም።
Christmas የገና ፊልሞች ግን ተመልክቻለው ነጩ ነገር ከብዙ
ፊልሞች ላይ አይቸዋለሁ። እዚህ ሃገር ሁሌም ገና ነው እንዴ ብየ አሰብኩ።

ወደ ከተማው ስንገባ ረጃጅም ፎቆች በብርሃን ይንቦገቦጋሉ።ከሩቅ ሲታዩ እሳት የተለኮሱ ነው የሚመስሉት። በብዙ ቀለማት አሸብርቀዋል። የትኛውን እንደምመለከት እንኳ ግራ ገባኝ። ፍሪ
ታውን ረጃጂም ፎቆች ያየሁ መስሎኝ ነበር ግን እነዚህ ከረጂም በላይ ናቸው ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች። ብዙ መኪኖች ትዕግስት አጥተው ጡሩንባቸውን ይነፋሉ። በእግረኛ መንገድ በእግራቸው
የሚጓዙ ብዙ ሰዎች ሳይ ማመን አልቻልኩም።አይኔ ነው ብዬ።
እንደሰማሁት አደገኛ አይደለም። መብራቶቹ ከፍሪ ታውን የበለጠ ብርሃን ይሰጣሉ። የኤሌትሪክ ገመድ ማስተላለፊያ ምሰሶ ግን አይታይም::

ቫንዴርቢሊት ዋይ ኤም ሲ ኤ ሆቴል ደርሰን ሻንጣችንን እንደያዝን ወደ እንግዳ መቀበያ ገባን። ዶ/ር ታምባን ተከትለን
ከእንግዳ ተቀባይዋ የክፍላችንን ቁልፍ ተቀበልን። ለመጀመሪያ ጊዜ የራሴ ክፍል ኖረኝ። በተጨማሪ ቴሌቪዥን ለሊቱን ሙሉ ተመለከትኩት። ክፍሉ በጣም ሞቃት ስለ ነበር ልብሴን አውልቄ
ከቴሌቭዥኑ ፊት ለፊት ቁሜ በጣም አላበኝ። ከሁለት ቀን በኋላ ግን ክፍሉ ውስጥ ማሞቂያ ራዲያተር እንደነበር እና
እስከመጨረሻው ተለኩሶ እንደነበር አወቅኩ። ምን እንደሆነ?እንዴት ሙቀቱን መቀነስ ወይም ማጥፋት እንደሚቻል አላውቅም ነበር። ምን አይነት ገራሚ ሃገር ነው ውጩ በጣም ቀዝቃዛ ውስጥ ደግሞ በጣም ሞቃት እያልኩ ሳስብ ነበር።


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#ዐዲስ_ገጽ

ያላለምኩት
ያልጠየኩት ኾነ !
ልቤ ጥበብ ገባው . . .፤
ምስጢርን ዐወቀ
ዐውቆ ተራቀቀ
ተራቆም ራቀ።
ነጎደ በፍጥነት . . .።

ሐሳቡን አፍታታ ፤ ሐሳቡን አናኘው
ጥያቄው ምሶ ፣ ምላሹን አገኘ።
በሐሳብ ተሞልቶ
በሐሳብ ተመርቶ
መጠየቅ ጀመረ ፤
ያልተፈቀደውን
የተደበቀውን
እየመረመረ።

በከፍታ ጕዞ . . .
ሽቅብ ተምዘግዝጎ ከኅዋው ላይ ዋለ
ከእርሱ ተገናኘ ከዚያም ይኼን አለ።
ጠቢቡ ሠለሞን . . .
“ከፀሓይዋ በታች ዐዲስ ነገር የለም ! “
ብሎ በመናገር . . .
የተሰጠው ኹሉ በከንቱ ከኾነ ፣
ከታችኛው ሳይኾን . . .
ከከፍታው ላይ ነው ፤ ሕልሙ የመከነ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ሀያ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

...በቀጣዩ ቀን ጠዋት አንድ ደረጃ ወርዶ ወደ ሚገኘው ካፍቴሪያ ሄድኩ። ከሃያ ሶስት ሃገራት የተወጣጡ ሃምሳ ሰባት ህጻናት ቁርስ ሊበሉ እና የተባበሩት መንግስታት የመጀመሪያ አለም
አቀፍ የህጻናት ፓርላማን ለማስጀመር እየተጠባበቁ ነበር::ከሊባኖስ፣ ካምቦዲያ፣ ኮሶቮ፣ ብራዚል፣ ኖርዌይ፣ የመን፣ሞዛምቢክ፣ ፍልስጤም (ፓላስታይን)፣ ጓቲማላ፣ አሜሪካ (ኒው
ዮርክ)፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ፔሩ፣ ሰሜን አየር ላንድ፣ ህንድ፣ ፓፕዋ ኒው ጊኒ፣ ማላዊ እና ሌሎች ሃገራት የተውጣጡ ህጻናት ነበሩ።ባህ እና ዶ/ር ታምባን እየፈለኩ እያለ አንዲት ነጭ ሴት ወደ
እኔ መጣችና እራሷን አስተዋወቀችኝ፡፡

“ክርስቲን እባላለሁ ከኖርዌይ ነው የመጣሁት” ብላ እጇን ለሰላምታ ዘረጋች::

“እስማይል ከ ሴራሊዮን” ብየ እጇን ጨበጥኳት። ወረቀት አወጣች እና ስሜን ደረቴ ላይ ለጥፋ የቁርሱን ሰልፍ
እንድቀላቀል ካደረገች በኋላ ፈገግ እያለች ወደ ሌሎች ህጻናት ሄደች፡፡ በሰልፉ የተከተልኳቸው ሁለት ታዳጊዎች ሰምቸው
በማላውቅ ባዕድ ቋንቋ ያወሩ ነበር። እነሱ የሚፈልጉትን ያውቁ ነበር፡፡ እኔ ግን ምን እንደምፈልግ ወይም የምግቦቹ ስሞች ምን እንደሚባል እውቀቱ አልነበረኝም፡፡ በቆይታየ ሙሉ ግራ ተጋብቼ ነበር። “እንደነሱ” እያልኩ አዛለሁ ወይም ሌሎች ሳህን ላይ ያየሁትን አነሳ ነበር።

ከቁርስ በኋላ ሁለት ህንጻዎች አልፈን ወደ መሰብሰቢያው ህንጻ ሄድን። አሁንም በረዶ ይዘንብ ነበር፡፡ አፍንጫዬ፣ ጆሮዬ
እና ፊቴ ከአሁን ካሁን ወደቀ ብዬ በምሰጋበት፤ በዚህ ቀፋፊ ብርድ
ባለበት ሃገር እማ መኖር የለብኝም አልኩ ለራሴ።

በመጀመሪያው ቀን ስለ እየራሳችን አወራን አንዱ ስለ አንዱ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ነበር ወደ ጉባኤው የመጡት።
ሌሎቹ ደግሞ ወደ ጎረቤት ሃገር መቶ ኪሎ ሜትሮችን ካቁረጡ በኋላ ነበር በረራ ማድረግ የቻሉት። በደቂቃዎች ውስጥ ክፍሉ አስቸጋሪ የልጅነት ጊዜ ያሳለፍን ታዳጊዎች ተሰበሰብንበት
መሆኑን ተረዳን፡፡ ከትውውቅ በኋላ አስተባባሪዎች ስለ ራሳቸው ነገሩን፡፡

አብዛኞቹ አስተባባሪዎች በተለያዩ ተራድኦ ድርጅቶች የሰሩ ናቸው፡፡ አንድ አጠር ያለች ፣ ረጅም ጥቁር ፀጉር እና ጎላ ጎላ
ያለ አይን ያላት ሴት ግን “ እኔ ተረት ነጋሪ ነኝ” አለችን። ስሟ ሎራ ሲም ነበር ሁኔታዋ ገርሞኝ በትኩረት አዳምጣት ነበር።
እጆቿን እየተጠቀመች እያንዳንዱን ቃል ረግጣ በአፅንኦት ትናገር ነበር፡፡ ንግግሯን ከመጨረሷ በፊት የእሷን ስልጠና
ለመውሰድ ወሰንኩ፡፡ ታሪካችንን እንዴት በሚመስጥ እና ተፅዕኖ በሚፈጥር መልኩ መናገር እንዴት እንደምንችል
አስተምራችኋለሁ አለች፡፡ ኒው ዮርክ ከተማ ተወልዳ ያደገች አንዲት ነጭ ሴት እንዴት ተረት አዋቂ እንደሆነች ገርሞኛል።

ያን ቀን ሎራ አይኗ ባህ እና እኔ ላይ አርፎ ነበር። የሳሳ ቲሸርት እና ሱሪ ለብሰን ማሞቂያው አካባቢ ኩርምት ብለን
ተቀምጠን ነበር፡፡ ብርድ አጥንታችን ሰርስሮ ሳይገባ አልቀረም፡፡አሁንም አሁንም ያንቀጠቀጠን ነበር። በምሳ እረፍት ስዓት ሎራ ወደ እኛ መጥታ
ብርድ የሚከላከል ጀኬት አላችሁ?” ብላ
ጠየቀችን።ራሳችንን እየወዘወዝን እንደሌለን ነገርናት። ምሽት
ላይ ጃኬት፣ ኮፍያ እና ጓንት ይዛልን መጣች፡፡ ደስ አለኝ። አሁን ከተማውን ዘወር ዘወር ብዬ መመልከት እችላለሁ። ከአመታት በኋላ ሎራ ጃኬቷን ልትሰጠኝ ብትል ግን አልተቀበልኩም::
የሴት ጃኬት ስለነበር! ያኔ ግን የወንድ ይሁን የሴት ጉዳይህ አልነበረም እያለች ትቀልድብኛለች።

ባህ እና እኔ ከስራ ጋር እየተቀራረብን መጣን። እንዳንዴ በጣም ልጅ ሁኜ የሰማኋቸውን ተረቶች ትነግረናለች::
ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ባሻገር ያለች አንዲት ነጭ ሴት እንዴት የሃገሬን ብሎም የጎሳየን ወግ እና ታሪክ እንዳወቀች እንቆቅልሽ ይሆንብኝ ነበር። ከአመታት በኋላ ደግሞ እናቴ ሆነች። እጣ ፈንታ ወይስ አጋጣሚ? አንድ ተረት አዋቂ እና የወግ ባህል ካለው ማህበረሰብ የወጣ ልጅ ተረት አዋቂ የሆነች እናት በኒው
ዮርክ ሲያገኝ::

ኒው ዮርክ በገባሁ በሁለተኛው ቀን ወደ አጎቴ ደወልኩ።አሚናታ ነበር ያነሳችው። “እስማኤል ነኝ። አጎቴን ማግኘት
እችላለሁ?ብየ ጠየቅኩ።
“ላምጣቸው ከሁለት ደቂቃ በኋላ ደውል” ብላ ዘጋችው።ደውልኩ። አጎቴ ሲያነሳው “ ኒው ዮርክ ከተማ ነው ያለሁት”
አልኩት።
“እንግዲህ አምንሃለሁ።ሰሞኑን እኮ አላየሁህም።” ብሎ ፈገግ አለ፡፡ መስኮት ከፍቼ የኒው ዮርክ ን ጫጫታ አሰማሁት።
አይ ፍሪ ታውን አይመስልም፡፡ እና እንዴት ነው?” በጣም ይበርዳል” ስለው መሳቅ ጀመረ።

ምናልባት የምዕራቡ አለም አቀባበል ይሆናል። ስትመለስ ሁሉንም ነገር ትነግረኛለህ። ወደ ውጭ መውጣት ከሌለብህ አትውጣ::

እሱ ሲያወራ በቤቱ ግቢ የሚያልፈውን ኮረኮች መንገድ አስታወስኩ። የአክስቴ ሾርባ ውል አለብኝ፡፡

ጠዋት ጠዋት በረዶ የተከመረበትን መንገድ አቋርጬ ሂጄ ጉባኤውን እታደም ነበር። ችግራችንን ያሳለፍነውን ሰቆቃ
ስለ ልጆች በተለይዩ ሃገራት ያሉ ህጻናት
ስለሚገጥሟቸው ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው እንወያይ ነበር። ከረጅም ውይይት በኋላ ግን ፊታችን ወደፊት
የሚመጣውን ደስታ በማሰብ እና በተስፋ ይበራል፡፡ ለችግሮች መፍትሄ ስናቀርብ እና ዓለም እንዲያውቀው ስናደርግ ደግሞ ጉዳታችንን ያከምን ወደ በጎ የቀየርን ይመስላል።

በሁለተኛው ቀን ማታ የማሊው ማዱካ እና እኔ በምዕራብ በኩል በአርባ ሰባት ማዞሪያ ስንራመድ ሳናስበው ወደ ታይምስ አደባባይ እየተጠጋን ነበር። ህንጻዎችን እና የሚጣደፈውን ሰው
በማየት ተጠምደን እያለ ብዙ ብርሃን አየን፡፡ በትላልቅ እስክሪኖች የተለያዩ ማስታወቂያዎች ይቀርቡ ነበር። በምስል የተደገፈ ሙዚቃ እና ብዙ ቁጥሮችም ይዞሩ ነበር። ሁሉም በጨረፍታ
ታይቶ በፍጥነት ይቀየራል። በምናየው ነገር ተገርመን ለደቂቃዎች ገረን ቆምን :: ብርዱ እንኳን አልተሰማንም። ልብስ
ቤቶች እና ሌሎች ሱቆችን በመስኮት አፍጠን ስናይ የሚያብረቀርቁ
ህንጻዎች እና የመኪኖች ድምፅ ደግሞ ህልም እስኪመስለን ቀልባችንን ገዛ፡ ወደ ሆቴል ስንመለስ ለሌሎች ልጆች ያየነውን
ነገርናቸው:: ከዛን ቀን በኋላ ሁላችም ምሽት ምሽት ታይምስ አደባባይ እንድንሄድ ተደረገ።
ማዱካ እና እኔ ከቡድን ጉብኝት በፊት አንዳንድ ቦታዎችን ጎብኝተናል በሮክፌለር ፕላዛ የተዋበ ግዙፍ የገና ዛፍ፣የመላዕክት ቅርጻ ቅርጸ እና ብዙ ሰዎች የበረዶ ሸርተቴ ሲጫወቱ ተመልክተናል። በበረዶ ሸርተቴ ሰዎች በተደጋጋሚ እምቧለሌ ሲዞሩ ማዱካ እና እኔ ግን ሰዎች ምን እንዳስደስታቸ አልገባነም፡፡ የአለም ንግድ ማዕከልንም አይተናል፡፡ አንድ ቀን
በባቡር ስንሄድ ማዱካን “እንዴት ነው ሁሉም ሰው ዝምተኛ የሆነው” ብዬ ጠየቁኩት፡፡ ባቡሩን ዞሮ ቃኘና “ እንደ እኛ ሃገር የህዝብ ማመላለሻ አይደለም” አለ። እያንዳንዱን ነገር በአዕምሮዬ ለመያዝ እና በኋላ ለአጎቴ፣ ለአጎቴ ልጆች እና ለመሐመድ ለመንገር እታገል ነበር፡፡ ያምኑኛል ብየ አልጠበቅኩም::

በጉባኤው መጨረሻ ቀን እያንዳንዱ ህጻን ስለመጣበት ሃገር እና ስላሳለፈው ሁኔታ ንግግር እንዲያደርግ ተደረገ።
ዲፐሎማቶች እና የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ነበሩ። ሙሉ ልብሳቸውን ለብሰው በስርዓት ተቀምጠው በጥሞና ያዳምጡን
ነበር፡፡ ከፍሪ ታውን ይዠው የመጣሁት የተጻፈ ንግግር ቢኖርም ከልቤ ለመናገር ወሰንኩ። ስላሳለፍኩት ጊዜ እና ስላለኝ ተስፋ በአጭሩ ተናገርኩ:: ተስፋዬ ጦርነት እንደሚያበቃ ሲሆን ይሄ
👍1
የሚሆነው ደግሞ አዋቂዎች ህጻናትን ለውትድርና መመልመል ሲያቆሙ መሆኑን አስረግጬ ተናገርኩ:: እንደዚህ ነበር የጀመርኩት
ከ ሴራሊዮን ነው የመጣሁት፡፡ ህፃናትን እየጎዳ ያለው ጦርነቱ ሲሆን ጦርነቱ ከቤታችን ወጥተን እንድንሰደድ፣
ቤተሰቦቻቸውን እንድናጣ እና በጫካ ውስጥ እንድንከራተት አድርጎናል፡፡ በዚህ ምክንያት ያለ እድሜያችን በጦርነቱ እንደ
ወታደር እንድንሳተፍ፣ መሳሪያ እንድንሸከም እና ሌሎች አስቸጋሪ ስራዎች እንድንሰራ ተገደናል:: ይሄ ሁሉ የሆነው ደግሞ ስለተራብን ፣ ቤተሰቦቻችን ስላጣን እና የምንጠጋበት ስላጣን ነበር ። ጦሩን የተቀላቀልኩት ቤተሰቦቼን ስላጣሁ እና ስለተራብኩም ጭምር ነው፡፡ የቤተሰቦቼን ደም መመለስ መበቀል
እፈልግ ነበር። በህይወት ለመቀጠል ምግብም ያስፈልገኛል። ይህን ለማድረግ ብቸኛ መንገዱ ጦሩን መቀላቀል ነበር። ወታደር መሆን ቀላል አልነበረም ግን መሆን ነበረብን። አሁን አገግሜ ወጥቻለሁ። አትፍሩኝ፡፡ አሁን ወታደር አይደለሁም። ህጻን ነኝ፡፡ሁላችንም ወንድማማቾች እህትማማቾች ነን፡፡ ካሳለፍኩት ህይወት የተረዳሁት በቀል መልካም አለመሆኑን ነው።ጦሩን
የተቀላቀልኩት የቤተሰቦቼን ደም ለመበቀል እና በህይወት ለመቀጠል ነበር። ግን ቆይቼ የተረዳሁት እኔ ከተበቀልኩ ድርጊቱ ይቀጥላል። እኔ እገድላለሁ፤ የገደልኩት ሰው ዘመዶች ደግሞ ወደ በቀል ይገባሉ። በቀል በቀልን ይወልዳል። በቀል በቀል በቀል
ማቆሚያ የለውም...”

ከንግግሩ በኋላ በጋራ ያዘጋጀነውን መዝሙር ዘመርን።ሌሎች ዘፈኖችንም ዘፈን; አለቀስን፣ ሳቅን ተወዛወዝንም። ልዩ
ቀን ነበር። መለያየታችን ግን ከፋን ምክንያቱም የምንመለስባቸው ቦታዎች ሰላማዊ እንዳልሆኑ አናውቃለን።እጅ ለእጅ ተያይዘን እየዘለልን ጨፈርን።ሎራ ንግግሬ እንደማረካት ነገረችኝ።

ያን ምሽት ለእራት ወደ አንድ የህንድ ምግብ ቤት ሄድን።ሩዝ ስለነበር በጣም ደስተኛ ነበርኩ። ብዙ በላን፣ አወራን፣
አድራሻ ተቀያየርን በኋላ ወደ ሎራ ቤት ሄድን፡፡ የስራ ቤት ወደፊት የምኖርበት ቤት ይሆናል ብየ አልጠበቅኩም ነበር።
ግድግዳው ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ የባህል ልብሶች
ተንጠልጥለዋል። የታሪክ እና ልብ ወለድ መጻህፍትን የያዘ ትልቅ መደርደሪያ ላይ የእንስሳት ቅርጻ ቅርፅ ሲሰቀል የሸክላ
ጌጣ ደግሞ ጠረጴዛ ተቀምጦ ይታያል። ቤቱ ሰፊ ሲሆን ሃምሳ
ስባት ታዳጊዎችን ያለ ምንም መጣበብ ነበር የያዘን።ምቹ፣
ማራኪና በሚያስደንቁ ታሪኮች የተሞላ ቤት! ሳሎኑ ተቀምጠን
ተረቶች ካወራን በኋላ ለሊቱን በመደነስ አጋመስነው።
የመጨረሻውን ቀን በኒው ዮርክ ለማሳለፍ ትክክለኛው ቦታ
ነበር።
በሚቀጥለው ምሽት ሎራ እና ሻንታህ አንድ ላይ በመሆን
ባህን፣ ዶ/ር ታምባን እና እኔን አየር መንገድ ድረስ ሸኙን::
መጀመሪያ መኪና ውስጥ ዝም ብለን ነበር። ቀስ በቀስ ግን እኔ
እና ባህ ማልቀስ ጀመርን። ተርሚሉ ደርሰን እየተቃቀፍን
ስንሰነባበት ደግሞ እለቅሷችን ጨመረ። ሎራ እና ሻንታ
አድራሻቸውን እና ስልክ ቁጥራቸውን ፅፈው ሰጡን፡ ህዳር 15፡
1996 ኒው ዮርክን ተሰናብተን ወጣን። በረራ ላይ በሃሳብ ጭልጥ
ብየ ነበር። ቆይታየ እንደ ህልም ይመስለኝ ጀመር። ከህልሙ ግን መንቃት አልፈልግም ነበር። ከፍቶኛል! ከኒው ዮርክ መውጣቴ ከፍቶኛል ግን ከሴራ ሊዮን ውጭ ሰው ማፍራቱ አንድ ነገር ነው። መመለስ ማለት ወደ ሞት መገስገስ ነው። ብሞትም የመኖሬ ትዝታ በሌላ አለም ህይው ሁኖ እንደ ሚኖር ግን አውቃለሁ።


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#ለኀጥአን_የመጣ #ክፍል_ሀያ #የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ #በኢስማኤል_ቤህ #ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው ...በቀጣዩ ቀን ጠዋት አንድ ደረጃ ወርዶ ወደ ሚገኘው ካፍቴሪያ ሄድኩ። ከሃያ ሶስት ሃገራት የተወጣጡ ሃምሳ ሰባት ህጻናት ቁርስ ሊበሉ እና የተባበሩት መንግስታት የመጀመሪያ አለም አቀፍ የህጻናት ፓርላማን ለማስጀመር እየተጠባበቁ ነበር::ከሊባኖስ፣ ካምቦዲያ፣…»
#አገሬ 💚💛❤️

አገሬ ውበት ነው፣
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣
ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣
ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣
ክረምቱም አይበርድም፣
አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው፣
እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነፃነት፣
በሃገር መመካት፣
በተወላጅነት፣
በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነፃነት።
አገሬ ሃብት ነው፤
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ፣
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፣
ጠጁ ነው ወለላ፣
ከኮኛክ ያስንቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣእም አለው እንጀራው ያጠግባል፣
ከቢራ ከሻምፓኝ ውሃው ይጣፍጣል፣
በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣
ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ፣
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር፣
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ፤
ገነት ነው አገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ ?
ምነው ለምን እንዴት ?
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ፣
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ፣
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት፣
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ፣
አሻፈረኝ እምቢ፣
መቅደስ ነው አገሬ፣
አድባር ነው አገሬ፣
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት፣
ካያት ከቅደም አያት የተረካከቡት፣
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
አገሬ ዓርማ ነው፣ የነጻነት ዋንጫ፣
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።
እሾህ ነው አገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው ፣ መቅደስ የሃይማኖት፣
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው አገሬ፣
ውበት ነው አገሬ፣
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣
እዚያ ነው አፈሩ፣ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ፣
ካሳደገኝ ጓሮ።

🔘ሰዓሊ እና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ🔘
👍1
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ሀያ_አንድ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

አንዳንዴ ማታ ማታ ለቤተሰቦቼ መሐመድን ጨምሮ (አሁን ከእኛ ጋር ነው የሚኖረው) ስለ ጉዞዬ እነግራቸው ነበር።
ሁሉንም ነገር አስረዳቸው ነበር፡፡ አየር ማረፊያውን፣ አውሮፐላኖቹን በአውሮፐላን መስኮት አሻግሮ ደመናን ማየት የሚሰጠውን ስሜት ሳይቀር እነግራቸው ነበር፡፡ ስነግራቸው የናፍቆት ስሜት ይሰማኝ ነበር። በአምስተርዳም አየር ማረፊያ እግረኛ መንገድ ስንቀሳቀስ ብዙ ነጮች ቦርሳቸውን እየጣሉ እና በተለያየ አቅጣጫ ሲሯሯጡ ትዝ ይለኛል።
ስለተዋወቅኳቸው ሰዎች፣ ስለ ኒው ዮርክ ረጃጂም ፎቆች፣ ስለ ስስ በረዶቿ እና ሰዎች መንገድ ላይ እንዴት እንደሚሰዳደቡ ሳይቀር ነገርኳቸው።

“የሚገርም ጉዞ ነው” ይላል አጎቴ፡አንዳንዴ በእውኑ አለም የሌለ አዕምሮዬ ውስጥ ለእኔ ብቻ የተከሰተ ይመስለኝ ነበር።

መሐመድ እና እኔ በኤድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደገና ትምህርት ጀመርን። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሁኜ ጠዋት ትምህርት ቤት ስሄድ ትዝ ይለኛል። የወደቁ የማንጎ ቅጠሎችን የሚጠርጉ መጥረጊያዎች ድምፅ እና የደነበሩ ወፎች ጫጫታ ታጅበን ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ ትዝ ይለኛል።ትምህርት ቤቱ በጨቃ ጡብ እና ቆርቆሮ የተሰራ ትንሽ ህንፃ ሲኖረው ህንፃው በር አልነበረውም:: ከጥበቱ የተነሳ ሁሉንም ተማሪ መያዝ አይችልም ነበር። ብዙ ክፍለ ጊዜ ውጭ በማንጎ
ዛፍ ስር ጥላ ነበር የምንማረው:: መሐመድ በ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የነበረውን የትምህርት መሳሪያ እጥረት በደንብ ያስታውሳል። ብዙ ጊዜ ደግሞ መምህራን በእርሻ ያግዝ እንደነበር ይነግረኛል። ዘር በመዝራት፣ በመኮትኮት እና
በማጨድ ያግዝ ነበር። አብዛኞቹ መምህራን ኑሮቸውን በእርሻ ይደጉሙ ነበር። ብዙ ባወራሁት ቁጥር ብዙ ነገር እንደዘነጋሁ ማወቅ ጀምሬለሁ፡፡ ተማሪነትን ክፍል ውስጥ መቀመጥ፣
ማስታወሻ መያዝ፣ የቤት ስራ፣ ጓደኛ መያዝ እና ብሽሽቁን ሁሉ ረስቼዋለሁ ። አሁን ግን እንደገና ወደዛ ለመመለስ ጓጉቻለሁ:: በፍሪ ታውን የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ግን ሁሉም ተማሪዎች ከእኔ እና መሐመድ እርቀው ነበር የተቀመጡት::በአንዴ የምንገድላቸው ነበር የመሰላቸው። እንዴት እንደሰሙ
ባላውቅም ታዳጊ ወታደሮች እንደነበርን አውቀዋል፡፡በጦርነቱ ልጅነታችንን ብቻ አይደለም ያጣነው ስማችንም ከዚህ ስቃይ እና መከፋትን ካተረፍንበት መጥፎ ገጠመኝ ጋር እንዲጠራ ሁኖ ጠልሽቷል።

ቀስ ብለን ነበር ቤት ምንመለሰው። ቀስ ብሎ መራመድ ለማሰብ፤ ህይወት ወደየት አቅጣጫ እየተጓዘ እንደሆነ
ለመገምገም እድል ስለሚሰጥ ደስ ይለኝ ነበር። ህይወቴ ካለፈው እንደማይብስ እርግጠኛ ነበርኩ። እሱም የመፅናኛ እና ፈገግታየ ምንጭ ነበር። ቤተሰብ የአንድ ቤተሰብ አባልነትን ገና እየተለማመድኩ ነው፡፡ ለሰዎችም መሐመድ ጓደኛየ እንደሆነ መናገር ስለ ጀመርኩ ብዙ ማብራራት አይጠበቅብኝም።
ያለፈውን ታሪኬን መርሳት እንደማልችል አውቃለሁ። ነገር ግን ስላለፈው ማውራት ማቆም እና ዛሬን በአዲስ ህይወት መኖር
እፈልጋለሁ።

እንደተለመደው በጠዋት ነበር የተነሳሁት። ተነስቼ በቤታችን ጀርባ የሚገኝ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጨ
የከተማውን መንቃት እጠብቃለሁ። ግንቦት 25, 1997 የተኩስ እሩምታ ሰማሁ።ከተማዋ ከተለመደው ድምፅ ወጥታ በተኩስ እሩምታ ደነቆረች። የተኩስ እሩምታ በሃገሪቱ የህዝብ መወሰኛ ሁሉንም ከእንቅልፍ ቀስቀስ። እኔም ደጃፍ ላይ ወደ ነበረው አጎቴ
ምክር ቤት አካባቢ ነበር የሚሰማው።የተኩስ እሩምታው
ምን እየተካሄደ እንደለ አላወቅንም። ወታደሮች ግን በፓዲባ መንገድ ሲሯሯጡ የጦር መኪኖች ሲንቀሳቀሱ አይተናል። የተኩስ እሩምታው እየጨመረ ሌሎች የከተማውን ክፍሎች እያካለለ ነበር የቀጠለው:: የከተማው አዋቂ ስዎች ደንግጠው በፍርሃት እየረዱ በራቸው
ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል። መሐመድ እና እኔ ተያየን። ወደሱ ተጠጋሁ።

ረፋድ ሲሆን ማዕከላዊ እስር ቤት ተከፍቶ እስረኞች ተለቀቁ። ከእስር ከመውጣታቸው በተጨማሪ አዲሱ መንግስት ለእስረኞች መሳሪያ አደለ። አንዳንዶቹ በቀጥታ ወደ ፈረዱባቸው ዳኞች እና ጠበቆች በመሄድ እነሱን እና ቤተሰቦቻቸውን ገደሉ ቤታቸውንም
አቃጠሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ወታደሮች ቀድሞው የጀመሩትን ዘረፋ ተቀላቀሉ:: የሚቃጠሉ ቤቶች ጪስ አየሩን ሞልቶ ከተማዋን በጭጋግ ሸፈናት::

አንድ ሰው በሬዲዩ ወጥቶ ራሱን አዲሱ የሴራ ሊዮን ፕሬዝደንት እንደሆነ አወጀ:: ስሙ ጆኒ ፖል ኮሮማ ሲሆን የአብዮታዊ ጦር ኃይሎች ምክር ቤት መሪ እንደነበር ተናገረ። ምክር ቤቱ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠውን ፕሬዝደንት
ቲጃን ከባህን ከስልጣን ለማስወገድ በጦር መኮንኖች የተመሰረተ ነበር።
የኮሮማ መፈንቅለ መንግስቱን ለማካሄድ እንዳቀረበው ምክንያት መጥፎ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር እንደሆነ እና ሁሉም ሰው ወደ ስራ እንዲወጣ ምክር ሰጠ።

ከንግግሩ ጀርባ ግን የተኩስ እሩምታ እና የተቆጡ ወታደሮች ሲሳደቡ ሲጨፍሩ ይሰማል።

ምሽት ላይ በሌላ አዋጅ አማጺዎች እና ጦሩ የሲቪሉን መንግስት “ለሃገር ጥቅም” ሲባል ለመገልበጥ እንደተቀናጁ
በሬድዮ ተነገረ። አማጺዎች እና ጦር ግንባር የነበሩ ወታደሮችከተማውን ማጥለቅለቅ ጀመሩ፡፡ ሃገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስርዓት አልበኝነት ገባች። እየሆነ ያለው ሁሉ አላማረኝም:: ጠላሁት ወደ ቀድሞ ህይወቴ መመለስ አልችልም:: አሁን ግን በህይወት የማመልጥ አልመስልህ አለኝ፡፡

አማጺዎች እና ወታደሮቹ የባንክ ካዝናን መስበር፣ ፈንጅ ማፈንዳት፣ ሰዎችን አስቁሞ መበርበር መዝረፍ ጀመሩ::
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና የዮኒቨርሲቲ ግቢዎችን ተቆጣጠሩ። ደጅ ተቀምጦ ከመመልከት በስተቀር ምንም
የሚሰራ ነገር የለም:: አጎቴ የጀመረውን ቤት ለመጨረስ ወሰነ።በጠዋት ጀምረን እስከ ረፋድ ድረስ መስራት ጀመርን። የተኩስ እሩምታው ከቀን ቀን እየባሰ ከቤት መውጣት አስፈሪ እየሆነ መጣ፡፡ በጀምላ ብዙ ሰዎች ተገደሉ። ስለዚህ ብዙም ሳንቆይ ስራውን አቆምነው።

የታጠቁት ኃይሎች በከተማው ሱቆች እና ገበያ የሚገኘውን ምግብ በጉልበት ነጥቀው ወሰዱ። ከውጭ የሚመጣው ምግብ እና ከክፍለ ሃገር ወደ ከተማ የሚገባው ምግብ ቆሟል። ሎራ
ገንዘብ ትልክልኝ ስለነበር የቆጠብኩት ትንሽ ገንዘብ ነበረኝ ። ወደ ከተማው ወጥቼ ሩዝ፣ ደሮ፣ አሳ እና ሌሎች የታሸጉ ምግቦችን ለመግዛት ወሰንኩ፡፡ ወደ ገበያ መሄድ ግን አደጋ ነበረው። የበፊት
የጦር ሜዳ ጓደኞቼን ቢገኙኝ እና ከጦርነቱ እራሴን ማግለሌን

ቢያውቁ ይገሉኛል። ቤት መቀመጥ ደግሞ አልችልም ምግ መፈለግ ይኖርብኛል።

አንድ ድብቅ ገበያ እንዳለ እና የተለያዩ የማይገኙ የምግብ አይነቶች ለተራው ህዝብ እንደሚሸጥ ሰማን፡፡ ዋጋው ገበያ
ከመደበኛ ዋጋ ሁለት እጥፍ ቢሆንም ከአደጋ ያተርፋል።በጠዋት ማንም አንዳያየን አንገታችንን ደፍተን ወደ ገበያው
አመራን። ሩዝ፣ የወይራ ዘይት፣ ጨው፣ አሳ ገዝተን ልንወጣ ስንል መኪና እና ወታደሮች ዘለው ወረዱ። ወደ ህዝቡ
በመጠጋት የማስጠንቀቂያ ተኩስ ወደ ሰማይ ተኮሱ። በድምጸ ማጉያ አዛዡ የምግብ ዘምቢላችንን መሬት ላይ እንድናስቀምጥ እና እጃችንን ራሳችን ላይ እንድናስቀምጥ ትዕዛዝ ሰጠ።በድንጋጤ ለመሮጥ የሞከረች አንዲት ሴት ግንባሯ በጥይትተመታ:: ሁሉም ሰው ተረበሸ። እኛም ምግባችንን ይዘን ሮጥን።

ወደ ዋናው መንገድ ስንደርስ “ግድያ ይቁም” የሚል መፈክር ያነገቡ ሰልፈኞች አየን፡፡ ነጭ ቲሸርት እና ራሳቸው ላይ ነጭ
ጨርቅ አስረዋል። እንዳለየ ትተናቸው ልንሄድ ስንሞክር ወታደሮች ወደ እኛ መጡ። ስለዚህ ያለን ምንም አማራጭ
ከሰልፈኞቹ ጋር ተቀላቀልን።ታጠቂዎቹ አስለቃሽ ጭስ መልቀቅ ጀመሩ፡፡ሰዎች አፍንጫቸው መድማት ጀመረ:: ሁሉም በአገኘው መንገድ መሮጥ ጀመረ።
እግሬ አውጭኝ! አፍንጫየን በእጄ እንደሸፈንኩ በሌላ እጄ ዘምቢሌን አጥብቄ ይዤ ከመሐመድ ጋር ሮጥኩ። እንባየ ጉንጩ ላይ ፈስስ ፤ አይኔም ከበደኝ፡፡

መውጫ በመፈለግ ከህዝብ ጋር መሮጣችንን ቀጠልን። ከህዝቡ ተነጥለን ትንሽ ነፋስ አገኘን። ብዙም ሳይቆይ ሌሎች

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ