#የነፍስጥም_ጽዋ
በሠቀቀን መኖር . .
በፍርሀት መስጋት ነገን በመናፈቅ፣
በይኾናል ተስፋ . . .
ዛሬን ሠውተኸው ለመጪው መንፈቅፈቅ።
( ..ምን ይሉት ፈሊጥ ነው . . ?)
ለምን ነው መጠበብ . . . ?
ለምን ነው መብሰልሰል ?
አኹን ላይ ተገልጦ ዘላለምን መምሰል።
ኖረኽ ለማታውቀው ሠርክ ከምትለፋ ፣
ዝም ብለኽ ጠጣና . .!
ሞት እንደኹ ያው ሞት ነዉ ፤ ዐይነ ስቡ ይጥፋ !
በእጅኽ ጨብጥና የብርሌን ዐንገት
ተጎንጭ ፣ አጉድልለት፤ የኑሮኽን ንፍገት።
ኹሉም እውነት አለው ፤ ከስካር በኋላ
የሚገለጥበት ፣ ከተሸፈነበት መጋረጃ ጥላ።
እንግዲኽ ሞት ማለት ..
ጽዋኽ ላይ የቀረው ፣ ማክተሚያው የጥማት
ባ'ንድ ትንፋሽ ወስደኽ ፣ የምትፈጽመው ቋት።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
በሠቀቀን መኖር . .
በፍርሀት መስጋት ነገን በመናፈቅ፣
በይኾናል ተስፋ . . .
ዛሬን ሠውተኸው ለመጪው መንፈቅፈቅ።
( ..ምን ይሉት ፈሊጥ ነው . . ?)
ለምን ነው መጠበብ . . . ?
ለምን ነው መብሰልሰል ?
አኹን ላይ ተገልጦ ዘላለምን መምሰል።
ኖረኽ ለማታውቀው ሠርክ ከምትለፋ ፣
ዝም ብለኽ ጠጣና . .!
ሞት እንደኹ ያው ሞት ነዉ ፤ ዐይነ ስቡ ይጥፋ !
በእጅኽ ጨብጥና የብርሌን ዐንገት
ተጎንጭ ፣ አጉድልለት፤ የኑሮኽን ንፍገት።
ኹሉም እውነት አለው ፤ ከስካር በኋላ
የሚገለጥበት ፣ ከተሸፈነበት መጋረጃ ጥላ።
እንግዲኽ ሞት ማለት ..
ጽዋኽ ላይ የቀረው ፣ ማክተሚያው የጥማት
ባ'ንድ ትንፋሽ ወስደኽ ፣ የምትፈጽመው ቋት።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘