አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ለኀጥአን_የመጣ #ክፍል_አስራ_ሶስት #የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ #በኢስማኤል_ቤህ #ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው መሳሪያየን አንግቼ ከኬን እና አል ሃጂ ወደ ከተማው ገባን።በከተማው ያሉ ግንብ ቤቶች ከእኛ ከተማ እና እስከ አሁን ካየሁቸው መንደሮች ካሉ ቤቶች ትልቅ ናቸው፡፡ በዙሪያ ብዙ የማላውቃቸው አይቻቸው የማላውቅ ሰዎች አየሁ፡፡ ራሳችንን ዝቅ እያደረግን…»
#እስኪምን_አለበት !?

ፈገግታሽ . . .
እንደ በጋ መብረቅ
አንዴ ብልጭ ብሎ ፣ ዓመት የሚቀድስ
ዘመን የሚያስቀድስ ፤

ሣቅሽ . . .
ደራሽ አውሎ ነፋስ ፤
ሐዘን ግብስብሱን ባ'ንደዜ የሚያድስ።

እንባሽ . . .
የጤዛ ጠብታ ፣
ካ'ስፈሪው ዝናብ ላይ እፍታን ጨልፎ
እምቡጥ ጉንጮችሽ ላይ በጨረፍታ አርፎ
( ዕፎይታ የሚሰጥ ፤ ገጸ ውበት ኾነ ! )

ዝምታሽ . . .
ልክ እንደ ደመና ፤
የፀሓዩን ንዳድ ፣ የጨረቃን ጮራ
ሰማይና አድማሱን . . .
በግርዶሽ ያስረዋል አንዳች ሳያወራ።

ታዲያ ምን አለበት . . .?!
አንድ ጊዜ ብቻ ፣
አንድ'ዜ ብቅ ብለሽ
ከጎጄዬ መጥተሽ
ከ'ልፍኜ ተገኝተሽ
ቤቴን ብታደምቂው ፤

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ሕገ_ደንብ

ከጥቁሩ ሰሌዳ . . .
ከጨቅሎች ፊትለፊት ፤
እንደ'ዚኽ ተጻፈ .
ከጨዋታ በፊት።

"በተሰጣችኹ መብት
እዉነትን መስክሩ
ሐቃችኹን አውሩ ! "
ብሎ እንዳ'ሠመረ ፤
"ሕጉ ለእኔ አይሠራም!"
ብሎ ተናገረ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#የፈጣሪ_ልሳን

እጆቼን ዘርግቼ . . .
ልጸልይ፣ ልማልድ ፣ ከደጅኽ ተገኘኹ፤
አንጋጥጬ ሽቅብ በሐሳቤ ዋኘኹ።
ተንበርክኬ ለምሕላ በግንባሬ ተደፍቼ
ቀና ማለት ተዘነጋኝ ፤ የቃል ጸሎት ረስቼ።

ያ'ንደበትኽ ልሳን ከየት ተሠወረ?
ቃል ከምላሴ ላይ እንደምን ታወረ ?
ዝም ...!
ዝም ዝም . . .!
እንደው ዝም! ዝምታዬ ቀረ ፤
ሰምተኸኛል አንተ ፤
በዝምታ ልሳን ጸሎቴም ሰመረ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_አራት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


“ኑ ወደ ማዕድ ቤት ትንሽ ምግብ ያስፈልጋችኋል።” አለ ሴራሊዮናዊው የዩኒሴፍ ሰራተኛ፡፡ ተከተልነው።

በማዕድ ቤቱ ውስጥ አግድም ወንበርአ ላይ ከሌሎች ልጆች ጋር ተቀመጥን። ሩዝ በጎድጓዳ ስሃን ቀረበልን፡፡ እሱን ያለምንም
ፋታ መብላት ጀመርን። አል ሃጂ ከየት ናችሁ ብሎ እስከሚጠይቅ ድረስ ምንም አላወራንም: አል ሃጂ ሲጠይቃቸው
ደስተኛ አልነበሩም:: ማነህ አንተ? ያንተን ጥያቄ ልንመልስ ነው የመጣነው?” ሲል አል ሃጂ ተነስቶ ገፈተረው። ልጁ ተነስቶ
ሊደባደብ ሲል አንድ ሰው ተዉ ልጆች!” አለ።

ቦምብ አውጥቼ ይሄ የመጨረሻችሁ እንዲሆን ነው የምትፈልጉት ወይስ ጥያቄውን ትመልሳላችሁ?” አልኩ፡፡

ከኬኖ ወረዳ ነው የመጣነው”
“አልማዝ ከሚገኝበት አካባቢ?” አለ አል ሃጂ።
“ከጦሩ ጋር ነው ወይስ ለአማጺዎች ነው የተዋጋችሁት?”
ምኔ አማጺ ይመስላል? ለጦሩ ወግኜ ነው የተዋጋሁት።
አማጺዎች መንደሬን አቃጥለው ወላጆቼን ገለዋል፤ አንተ ግን እነሱን ትመስላለህ።”

በአንድ ወገን ነዋ የተዋጋነው” አለ አል ሃጂ። ተቀመጥን።ቦምቡን እንደያዝኩት ነበር። ፊቴን ወደ ማዕድ ቤቱ ያመጣን
ሰውየ አዙሬ “ መቶ አለቃ ለምን ለእነዚህ ያልታጠቁ ሴታ ሴት ሰዎች አሳልፈው እንደሰጡን ታውቃለህ?” ብየ ጠየቅኩት።
በፍርሃት ርዶ፣ በላብ ተጠምቆ ሊመልስ ሲል አንዱ ልጅ “ እሱ ያልታጠቀ ነው ሌሎች ልጆችን እንጠይቃቸው”አለ። ማቡ ይባል ነበር በኋላ ጓደኛሞች ሁነናል፡፡ ተነስተን ቤት ደጃፍ ላይ ወደ ተቀመጡት ታዳጊዎች ሄድን፡፡

“ጓዶች አዛጋችሁ ለምን ለእነዚህ ሰዎች እንደሰጡዋችሁ ታውቃላችሁ?” ብሎ አል ሃጂ ጠየቀ። ዝም አሉ፡፡ “ኣትሰሙም
እንዴ?

“ማንም እንዲያስቸግረን አንፈልግም” አለ በሸካራ ድምጸ።በዛ ላይ ላልታጠቀ ተራ ሰው ጥያቄ መልስ መስጠት አንፈል
ግም።”

“ተራ ሰው ሲቪል አይደለንም! አለ ማቡ በቁጣ።” ተራ ያልታጠቀ ሰው ካለ እናንተ ናችሁ። መለዮ እንኳን ያልለበሳ
ችሁ። ምን አይነት ወታደር ነው መለዮ ማይለብሰው ባካችሁ?!”

“ለአማጺዎች ነው የተዋጋ ነው፤ ጦሩ ጠላታችን ነው።ለነጻነት ነው የተዋጋነው! ጦሩ ቤተሰቤን ገድሏል መንደሬንም
አፍርሷል፡፡የጦሩን አባላት ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እገላለሁ”ብሎ ተነሳ።

“አማጺዎች” ብሎ ማቡ ጮኸ። ሰንጢዎቻችን አውጥተን ተፋጠጥን፡፡ እንደገና ጦርነት! ፈረንጆቹ ቦታ ስለቀየርን ከጦር ቀጠና ስለተገለልን ብቻ ደህና የምንሆን መስሏቸዋል።አዕምሮችን የተበረዘ አደገኛ ነፍሰ ገዳይ መሆናችንን አላወቁም! አሁን በቀላሉ እንደማናገግም ይገባቸዋል።

ቦምብ ወረወርኩ ግን ዘገየ፡፡ ድብድቡ ቀጠለ አንዳንዶቻችን ሰንጢ ይዘን ሌሎች በባዶ እጅ መታገል ጀመርን። አንዱን እግሩን ወጋሁት ሌላው እኔን ሊወጋ ሲል አል ሃጂ ቀድሞ ከጀርባ ወጋው፡፡ የጮኸ ወይም ያለቀስ የለም ሁላችንም ለምደነዋል በዛ ላይ አደገኛ ዕፅ ወስደን ነበር፡፡ ፖሊሶቹ “አቁሙ አቁሙ” እያሉ
ወደ እኛ መጡ፡፡ከአገላገሉን በኋላ የወደቀውን ሊያነሱ ሲጎነበሱ ገፍትረን ጥለን መሳሪያቸውን ቀማን። ማቡ ተኩሶ የተወሰኑትን ገደለ ሌሎችን ደግሞ አቆሰለ፡፡ አማጺዎች ከእኛ ወገን ሁለት
ታዳጊዎችን ገደሉ፡፡ ፖሊስ ወደ ሰማይ ቢተኩስም መታገል አላቆምንም:: ስለዚህ በጉልበት ለያዩን መሳሪያ ድቅነው
አቆሙን። አምቡላንስ እየጮኸ መጥቶ የተጎዱትን ወሰደ።ስድስት ታዳጊዎች ሲሞቱ ሁለት ፖሊሶችን ጨምሮ ብዙዎች
ቆሰሉ።

በማቡ ጀብድ ተገረምን፤ማዕድ ቤት ተመልሰን ስለእሱ ነበር የምናወራው። አንዱን ልጅ አይኑን መትቶት ልጁ ቡጢ ሊመልስ ቢፈልግም ማቡን ማየት አልቻለም። ድብድብ ረብሻው ለእኛ
ጨዋታ ነበር። ከማዕድ ቤት አውጥተው ወሰዱን። የጦር መኪና እየጠበቀን ነበር፡፡ “ወደ ጦርነቱ ሊመልሱን መሆን አለበት::” አለ አል ሃጂ። ዝም ብለን ብሔራዊ መዝሙሩን መዘመር ጀመርን::ወደ ጦርነቱ አልመለሱንም ነገር ግን ቤኒን ቤት ወደ ሚባል ሌላ የማገገሚያ ማዕከል ነበር የወስዱን፡፡ ለምን ወደ እዚህ ቦታ
እንደመጣን አሁንም አላወቅኩም፡፡ G3 ሽጉጤ፣ የጦርነት ፊልም እና የምወስደው ክኒን ትዝ ይለኛል። ከሁሉም በላይ መቶ
አለቃ “ከአሁን በኋላ ያገኘነውን አማጺ እንገላለን፧ ምህረት ምርኮኛ የሚባል ነገር የለም”የሚለው ንግግር ወደ አዕምሮየ
ይመላለስ ነበር።

ባልታጠቀ በሲቪል መታዘዝ ያበሳጫል፡፡ ድምጻቸውን መስማት እንኳ አልፈልግም:: ለቁርስ እንኳ ሲጠሩን ሳጥን ያገኘሁትን ነገር በቡጢ እመታለሁ። ከመመገብ ውጭ የታዘዝነውን አንፈፅምም ነበር።
እንቢተኛ ነበርን! ቁርስ ሻይ እና ዳቦ፣ ምሳ እና እራት ደግሞ ሩዝ እና ሾርባ እንበላ ነበር። መሳሪያችን እና አደገኛ ዕፅ ከእኛ
ጋር ስላልነበር ደስተኞች አልነበርንም።

ተደጋጋሚ የጤና ምርመራ እና የምክር አገልግሎት በነርሶቹ እና ሌሎች ሰራተኞች ይደረግልን ነበር፡፡ አንወደውም ነበር፡፡ ገና
ሲጀምሩ ያገኘነውን እቃ እንወረውራለን እንደበድባቸዋለን።ከምግብ በኋላ ያለምንም ምክንያት እንደባደብ ነበር። ሰራተኞቹ ምንም ብናደርግ እነሱን እንኳ ብንደበድባቸው አያዝኑብንም።
“የእናንተ ጥፋት አይደለም እንደዚህ ልታደርጉ የቻላችሁት”ብለው ፈገግታ ያሳዩናል።በእኛ ተስፋ ላለመቁረጥ የተስማሙ ይመስላሉ።

የራስ ምታት ማይግሬን እንደገና ተንስቶ ያሰቃየኝ ጀምሯል። አንጥረኛ በመዶሻ ራሴን የሚቀጠቅጥ ይመስለኛል።
አንዳንድ ቀን ራሴን መቆጣጠር ከብዶኝ መሬት ላይ እንከባለላሁ:: አል ሃጂ ደግሞ የቤቱን ምሰሶ በመደብደብ ሆስፒታል ገብቶ ነበር፡፡ ቆይቼ እኔም ራሴን ስቼ ሆስፒታል ገባሁ:: ሰውነቴን ሙሉ ያመኝ ነበር፤ ጉሮሮየ ደርቆ የማጥወልወል ስሜት ይሰማኝ ነበር። ነርሷ ፈገግታ እያሳየች ወደ እኔ አልጋ መጥታ መርፌ ወጋችኝ። አካሌ ተዳክሞ ተኛሁ።
በሚቀጥለው ቀን ከሆስፒታል ወጣሁ። ነርሷ ውሃ በደንብ ጠጣ አለች::

አንዳንዴ ከማጥወልወል ስሜት እና ድንገት እራስን ስቶ ከመውደቅ ባለፈ ከሁለት ወር በኋላ በአብዛኛው እየተሻለን
መጣ፡ የጦርነቱ መጥፎ ትዝታዎች ትርፍ ጊዜ ስለነበረን ወደ አዕምሮዋችን እየመጣ ያስጨንቀን ነበር። ይሄን ለማስረሳት ይመስላል ትምህርት ትጀምራላችሁ ተብለን የትምህርት
መሳሪያዎች ተሰጠን። ደብተር፣ እስክርቢቶ እና እርሳስ ከተሰጠን በኋላ ከሰኞ እስከ አርብ ከአራት ስዓት እስከ አስራ ሁለት ስዓት ትምህርቱ እንደሚሰጥ ተነገረን።ወዲያው ግን የተሰጠንን የትምህርት መሳሪያዎች አቃጠልን።
እንደገና ተሰጠን። እንደገና አቃጠልነው፡፡

አንድ ቀን ቀትር ላይ የማገገሚያው ሰራተኛች የተወሰነ የትምህርት መሳሪያዎች ደጃፍ አስቀምጠው ሂዱ። ማቡ የትምህርት መሳሪያዎችን አየና ለምን አንሸጠውም የሚል ሃሳብ
አመጣ። “ማን ይገዛናል? ሰዎች ይፈሩናል? አለ አንድ ታዳጊ ልጅ፡፡ “የሚረከበን ነጋዴ እንፈልጋለን” አለ ማቡ። በፕላስቲክ ቦርሳ ተሸክመን ቅርብ ወደ ሚገኝ ገቢያ ወስደን ለአከፋፋይ
ሸጥነው:: “ብዙ ገንዘብ ነው ያገኘነው” አለ ማቡ። ምሳ እንዳያመልጠን ወደ ማዕከሉ ቶሎ ተመልሰን። ከምሳ በኋላ ማቡ ድርሻችንን አከፋፈለ። ግማሾቹ ኮካ ኮላ፣ ከረሜላ እና ሌሎች ነገሮች ሲገዙ ማቡ፣ አል ሃጂ እና እኔ ደግሞ ለሽርሽር ወደ ፍሪ ታውን ለመሄድ አቀድን።

ጥዋት ቶሎ ቶሎ በላይ በላይ ቁርሳችንን ከበላን በኋላ አንድ በ አንድ ሾልከን ከመመገቢያ አዳራሹ ወጣን። ከውጭ ከተገናኘን በኋላ አውቶብስ መጠበቅ ጀመርን።

“ከተማውን ታውቁታላችሁ? ከዚህ በፊት ወደ ከተማው

ሂዳችሁ ታውቃላችሁ?”
አልሃጂ ጠየቀን።
አይ ሂጄ አላውቅም” አልኩ::

' ለትምህርት ወደ ፍሪ ታውን ልመጣ ነበር ግን ጦርነቱ ቀድሞ ተከሰተ። ውብ ከተማ እንደሆነ ግን ሰምቻለሁ” አለ አል
ሃጂ።

“እንግዲህ ታውቁታላችሃ! አውቶብሱ መጥቷል” አለ ማቡ። እስከ አንቃሩ የተከፈተው ሙዚቃ ከሰው ጫጫታ ጋር
ተዳምሮ አውቶብሱ ገበያ መስሏል። የሚዳንሱ ሰዎችም ነበሩ።ከጀርባ ተቀምጠን የሚያልፉትን ቤቶች አና ሱቆች አየን።

መሃል ከተማው አካባቢ ኪሲ መንገድ ወረድን። ሰዎች ለዕለት ተዕለት ኑሮቸው ከዚያ ወደዚህ ይጣደፋሉ፡፡ ትላልቅ
ሱቆች በሁለቱም የመንገድ አቅጣጫ ሲገኙ የመንገድ አዟሪዎች መንገዱን አጣበው ይሸጣሉ። የአይን አዋጅ ሆነብን በቀላሉ ተማረክን”::

“ጥሩ እንደሚሆን ነግሬችሁ ነበር” አለ ማቡ በደስታ እየዘለለ።ይሄን ረዥም ፎቅ ተመልከት” ወደ አንድ በእጄ እያመለከትኩ።
“ ያን ተመልከት በጣም ረዥም ነው” ብሎ አል ሃጂ ጮኸ።
“ሰዎች እንዴት ነዉ እዛ ላይ የሚወጡት?” ብሎ ማቡ ጠየቀ።
ቀስ ብለን ሁሉን እየቃኘን ፤የመኪናውን ብዛት እና ሁሉም አይነት ምግቦች ባላቸው የሊባኖስ ሱቆች እየተደነቅን መራመድ ጀመርን፡፡ ስንዞር ከቆየን በኋላ የሃገሪቱ ብሔራዊ ምልክት ወደ
ሆነው የጥጥ ዛፍ ደረስን። አፋችንን ከፍተን አትኩረን ተመለከትነው:: ከዚህ በፊት ከገንዘብ ጀርባ ላይ ነበር ያየነው።


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#መንገድ

የመኼድ ርዝመት በዕርምጃ ስኬት
የሕይወትም ዳና በመሥመሩ ልኬት

ከተነጻጸረ . . .!
ይመተራል ዕድሜ ፣ ይሰበዛል ታሪክ
ይፍታታል ትርጓሜ ፣ በተጓዙበት ልክ።

ዕርምጃ - ፩
ዕንቅፋት በበዛው በጠባብ ጎዳና
ዐይነ ስውር ተጓዥ በእዝነ ልቦና ፣
ያለ መሪ ጒዞ በሐሳብ በትሩ
ያለመደናቀፍ ፣ መድረስ ከመንበሩ።

ዕርምጃ – ፪
በፍሥሓ ጕዝጓዝ ፣ በተደላደለ
የሚደነቃቀፍ ፣ ማየት ያልታደለ
ትላንቱን የረሳ ፣ በነግ አልባ ጕዘት
በለኮሰው እሳት ፣ ያልወጣ ከፍዘት።

እንግዲኽ . . .
በመንገድ ርቀት በ'ርምጃችን ዕድሜ
ከምንም መጀመር . . .
ያልጀመሩት ጉዞ የለም ፍጻሜ።

ለቅጽበት አይተሺኝ
በድኔን ዳብሰሺኝ
ያንቀላፋው ልቤን
ነክተሽ ብታነቂው።

እስኪ አኹን ምን ነበር . . . ?!
በምኞት ሠቀቀን ያ'ላንቺ ከምኖር
አንድ'ዜ ዳብሰሽኝ ዘላ'ለም ብቀበር።

እስኪ ምን አለበት . . . ?!
ፍቅርሽን ሰጥተሺኝ ፣
ሞትን ብንቅበት
ትንሣኤን ባውቅበት።

እስኪ ምን አለበት . . . ?!
ዘመኑን በሙሉ ባክኖ እንደኖረ
የመናፈቅ ዕድሜው በፍቅር ተሻረ።
( . . . የሚል ገድል ታሪክ . . . )
(. . . ተጽፎ ቢተረክ . . .)
እስኪ ምን አለበት . . .?!

ድንገት ተከስተሽ ፣
ፍካት ባጣው ቤቴ ፣ ሣቅሽን ብትዘሪበት
ብለሽ ብትነግሪያቸው ሕያውነት ቅጽበት።
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_አምስት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

...ቅጠሎቹ አረንጓዴ ሲሆኑ ግንዱ ግን በጣም አርጅቷል። “ይሄን ስንነግራቸው ማንም አያምነንም” አለ አል ሃጂ።

የእራት ስዓት እየደረሰ ስለነበር ወደ ማዕከል መመለስ ነበረብን፡፡ ያን ምሽት ጓደኞቻችን ስለ ረጃጂም ህንጻዎች :
መኪናዎች እና ገበያው ነገርናቸው፡፡ ሁሉም ደስ ብሏቸው ማየት ፈለጉ። ማዕከሉም ይሄን በመረዳት በሳምንት አንድ ቀን የሽርሽር ፕሮግራም ተያዘልን፡፡

ቀስ በቀስ ወደ ትምህርት ተመለስን። ቀለል ያለ የትምህርት ስርዓት ነበር፡፡ ለሂሳብ መደመር፣ማባዛት እና ማካፈል ስንማር እንግሊዝኛ ደግሞ ምንባብ ማንበብ፣ ቃላቶችን ትርጉም ማወቅ
እና የእጅ ጽሁፍ እንማራለን። ብዙም አንከታተልም ; ትኩረታችን በትንሽ ነገር ይሰረቃል። በእርሳስ እንወጋጋላን
እንደባደባለን። “የናንተ ጥፋት አይደለም
ወደፊት ትስተካከላላችሁ' ይለናል መምህሩ።

ከምሳ በኋላ የጠረጴዛ ቴንስ ወይም እግር ኳስ እንጫወት ነበር። ለሊት ግን አስጨናቂ ነበር። በቅዥት እንባንናለን፣ በላብ እንጠመቃለን፣ ጩኸት እና ግድግዳ መደብደብ ነበር። ሰራተኞቹ
ይህን ስለሚያውቁ ጥበቃ ያደርጉልን ነበር።

የሴራሊዮን ዝናባማ ወቅት ከግንቦት እስከ ጥቅምት ሲሆን ሐምሌ፣ ነሐሴ እና መስከረም ደግሞ ከባድ ዝናብ ይኖራል።
ዝናቡ አንዳንዴ የጦርነቱን መጥፎ ትዝታዎች ይቀሰቅስብኛል።
የሰለጠንኩበት ቦታ እና የሞሪባ ሞት ትዝ ይለኛል። ሞሪባ በተኩስ እሩምታ ሲገደል መቅበር ቀርቶ ማልቀስ እንኳ አልቻልንም። አንድ ዛፍ ላይ አስጠግተነው በአፉ ደም እየደፈቀ ትተነው ሄድን።

ሲነጋ ሰራተኛዋ ብርድ ልብሱን መልሳ እያለበሰችኝ “ያንተ ጥፋት አይደለም በፍጹም! አይዞህ ትረሳዋለህ ይሻልሃል”
ትለኛለች፡፡

አንድ ቀን ረፋድ ላይ ቴንስ ስንጫወት የግቢው ሰራተኞች በሙሉ ይመለከቱን ነበር። አንድ ሰው ከኋላ ትከሻዬ ላይ ሲነካኝ ተሰማኝ ። ነርሷ ነበረች ። ነጭ ደምብ ልብስ እና ነጭ ኮፍያ ለብሳለች። ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ፊት ለ ፊት ሳያት። ነጭ ጥርሷ ከጥቁር እና አንጸባራቂ ቆዳዋ ጋር ተጣምሮ ልዩ ውበት
ሰጥቷታል። ስትስቅ ደግሞ የበለጠ ውበቷ ይፈካል። ረዥም ናት፤ ትልልቅ አይኖች አሏት፡፡ ጠርሙስ ኮካ ኮላ ሰጥታኝ በሚያስፈልግህ ጊዜ ና እና እየኝ” ብላ ፈገግታ ሰጥታኝ ሄደች::
ከአል ሃጂ ጋር ጨዋታውን ትተን ወደ ውጭ ወጣን እና ኮካውን መጠጣት ጀመርን። “ወዳሃለች” እያለ አል ሃጂ ሊቀልድብኝ ሞከረ። ምንም አላልኩም::

እህ ትወዳታለህ እንዴ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡
“ እኔ አላውቅም:: ትልቅ ናት በዛ ላይ ነርሳችን ናት” አልኩ።
ማለት ሴቶችን ትፈራለህ?” አለ
“አንተ እንደምታስበው ወዳኝ አይመስለኝም” ብየ አል ሃጂን
ተመለከትኩት። የምለውን ነገር እያዳመጠ ይስቃል።

ኮካውን ጠጥተን እንደጨረስን አል ሃጂ ሄደ እኔ ግን ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ወሰንኩ፡፡ በሩ ስደርስ ነርሷ ስልክ እያወራች አየኋት። እንድገባ እና እንድቀመጥ በእጇ ምልክት አሳየችኝ።
ወዲያው ስልኳን አቁማ ፈገግታ እያሳየችኝ ወንበሯን ወደ እኔ
አቀረበች፡፡ ስለ ጦርነቱ ጥያቄ ልትጠይቀኝ እንደሆነ ገመትኩ።
እሷ ግን በተረጋጋ መንፈስ “ ስምህ ማነው” ብላ ጠየቀችኝ፡፡ገረመኝ! ስሜን እንደምታውቀው እርግጠኛ ነበርኩ። “ስሜን ታውቂዋለሽ” ብየ በቁጣ መለስኩ።
“ ምን አልባት ላውቀው እችላለሁ ግን ስምህን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ?” አለች አይኗን እያፈጠጠች::

እሺ እሺ እስማይል” አልኩ፡፡

“ጥሩ ስም” አለች እራሷን እየነቀነቀች፡፡ “ የእኔ ስም አስቴር ነው። ጓደኛሞች እንሁን።”

“እርግጠኛ ነሽ ከእኔ ጋር ጓደኛ መሆን ትፈልጊያለሽ” አልኳት::ለተወሰነ ጊዜ ካሰበች በኋላ “እርግጠኛ ላልሆን እችላለሁ” አለች።

ምን ማለት እንዳለብኝ ስላላወቅኩ እና ማንንም ስለማመን ለተወሰነ ጊዜ ዝም አልኩ። እንዴት መትረፍ እና እራሴን
መንከባከብ እንዳለብኝ ብቻ ነው ነበር የተማርኩት። እንደ መቶ አለቃ ጃባቲ ያሉ ያመንኳቸው የታዘዝኳቸው ሰዎች እንኳ
ሰዎችን በተለይ አዋቂዎችን እንድጠራጠር አድርገውኛል::
የሰዎችን ሃሳብ መጠራጠር ከጀመርኩ ቆይቻለሁ። ሰዎች ጓደኛ የሚሆኑት አንዱ ሌላው ላይ ጥቅም ለማግኘት ነው ብየ አስብ ነበር፡፡ ስለዚህ ለነርሷ ምንም መልስ አልሰጠኋትም።

“ያንተ ነርስ ነኝ በቃ ይሄ ነው። ከእኔ ጋር ጓደኛ መሆን ከፈለክ ልትጠይቀኝ እና ላምንህ ይገባል” አለች። ተመሳሳይ ሃሳብ
ስለነበረን ፈገግ አልኩ። ፈገግታህ ያምራል” አለች። አፍሬ ቁጥብ ሆንኩ።
“ከከተማ እንዳመጣልህ የምትፈልገው ነገር አለ?” ብላ ጠየቀችኝ፡፡ መልስ አልሰጠሁም::

“ለዛሬ ይበቃናል” አለች፡፡

ከተወሰነ ቀን በኋላ ነርሷ ስጦታ ሰጠችኝ። የተጠቀለለ ነገር ነበር ምን ይሆን እያልኩ መክፈት ጀመርኩ። ልክ እንዳየሁት በደስታ ተነስቼ አቀፍኳት። “ጓደኛ ካልሆን ለምን ይሄን ማዳመጫ እና ካሴት አመጣሽልኝ? ራፕ ሙዚቃ እንደምወድ እንዴት አወቅሽ?”

“እባክህ ተቀመጥ” አለች። የጆሮ ማዳመጫውን አደረኩ
D.M.C የዲ.ኤም.ሲ ሙዚቃ ነበር የምሰማው “It's like that and that the Way it is...” እንደዛ ነው እንደነገሩ” ራሴን ማንቀሳቀስ ጀመርኩ።አስቴር የጆሮ ማዳመጫውን ከጆሮዬ አውጥታ “አንተ ሙዚቃ ስታዳምጥ እኔ ልመረምርህ ነው”
አለች። ተስማማሁ። ምላሴን ፣ አይኔን አየች ከዛ እግሬን ስታይ ጠባሳ ነበረኝ። “ይሄ ጠባሳ እንዴት ወጣብህ?”

“በጥይት ተመትቼ ቆስየ ነው” እላለሁ በቀላሉ።

ፊቷ በሃዘን ተሞላ “ምን እንደሆንክ ምን እንደሚሰማህ ከነገርከኝ መድሃኒት ላዝልህ እችላለሁ” አለች። ሁሉንም
ነገርኳት፡፡ እንዴት በጥይት እንደተመታሁ፣
ስንት ጊዜ እንደተመታሁ እና ከዛ ምን እንዳደረኩ ነገርኳት። ልነግራት ግን
ፈልጌ አልነበረም፡፡ አስቃቂውን የጦርነቱን ክስተት ስነግራት መጠየቅ ታቆማለች ብዬ እንጂ። እሷ ግን በጥንቃቄ ታዳምጣለች። የትናንቱን ታሪኬን ማስታወስ ስጀምር አንገቴን ደፋሁ።

በበጋ ወቅት ስለነበረው ጦርነት ነገርኳት። ምግብ እና ጥይት ያጠረን አስቸጋሪ ወቅት ነበር። ሌላ መንደር ማጥቃት ነበረብን።ከትንሽ ስለላ በኋላ የሶስት ቀን ጉዞ ወደ ሚጠይቅ አንድ ሰፈር ሄድን። እቅዳችን ምግብ እና ጥይት ይዞ መምጣት ሳይሆን የምናጠቃውን ሰፈር ወደ ዋና ማዕከል መቀየር ነበር። ያለን
መሳሪያ እና ምግብ ይዘን ወጣን። ቦታው ደርሰን ለደፈጣ ውጊያ ስንዘጋጅ መንደሩ ባዶ መሆኑን ተገነዘብን። ከስዓት በኋላ
አምስት ታጣቂዎች መጥተው ባልዲ ይዘው ወደ ወንዙ ወረዱ..ገና መጠርጠር ስንጀምር ከኋላ ተኩስ ተከፈተብን። ለሊቱን ሙሉ ተታኮስን፡፡ አምስት ሰዎች ሞቱብን፣ የተረፍነውንም ተከተሉን። መቶ አለቃ ጠንክሮ ከመዋጋት ሌላ አማራጭ
እንደለለን ነገረን። ሌላ መንደር ለመሄድ በቂ ምግብ ወይም ጥይት የለንም፡፡ይሄን ጦርነት ካላሸነፍን ጫካው ውስጥ
መንከራተት ከዛም ማለቃችን ነው:: ስለዚህ ወደ ማጥቃት ገብተን መጀመሪያ ከሞቱት መሳሪያ አገኘን እና ተበተን::
በሁለተኛው ዙር እንደገና ተሰባስበን ማጥቃት ጀመርን::በመጨረሻ ከጠላቶቻችን በላይ ሐይል አግኝተን መበተን ቻልን:: የተኩስ እሩምታው በረደ፡፡ መንደሩ በእኛ ቁጥጥር ውስጥ ሆነ::
በድንገት ጥይቶችን በምሰበስብበት ወቅት የጥይት ዝናብ ወረደብን።

ሶስት ጊዜ እግሬ ላይ ተመትቼ ራሴን ስቼ ወደቅኩ። ሁለቱ ጥይቶች ገብተው ወጥተዋል አንዱ ግን እግሬ ውስጥ ቀረ::
በሚቀጥለው ቀን ስነቃ እግሮቼ ላይ ምስማር የተተከለ ይመስላል።
የጦር ሃኪሙ የሆነ ነገር ወጋኝ እና ደነዘዝኩ።
ሌሎች ጓደኞቼ እጆቼን ሲይዙ አፌ ላይ ጨርቅ ተደረገ። ቀጥሎ ሃኪሙ በመቀስ ጥይቷን አወጣት:: ከሶስት ሳምንታት በኋላ ነበር የተሻለኝ፡፡ ሃኪሙ ቁስሌን እያጠበ ደጋግሞ “እድለኛ ነህ”
ይለኝ ነበር። ጦርነትን ለማሸነፍ ወይም ከጦርነት ለመትረፍ ጥሩ ስልጠና ወይም ድፍረት ጀግንነት እንጂ እድል ቦታ ያለው
አይመስለኝም ነበር፡፡ ቆይቶ ግን ገባኝ:: ብዙ መከራዎችን በሚገርም ተዓምር ተረፍኩ። ሞት ማይደርስብኝ የማይነካኝ
ይመስለኝ ጀመር።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ስድስት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


ይሄን ነግሬያት ከሆስፒታሉ ለመውጣት ተነሳሁ። አስቴር ግን “በኮንናውት ሆስፒታል ሙሉ ምርመራ እንድታደርግ
ሁኔታዎችን አመቻቻለሁ።” ብላ ላፍታ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ ሙዚቃ ማዳመጫው ከእኔ ጋር ይቆይ ሌሎች እንዲቀኑብህ
እና እንዲሰርቁህ አያስፈልግም፡፡ በፈለከው ቀን መጥተህ ማዳመጥ ትችላለህ። ሁሌም እኔ ከዚህ ነኝ” አለች። ሙዚቃ ማዳመጫውን ወርውሬ ወጣሁ።

አንድ ቀን ከስዓት አስቴር ከስራ እረፍት ብትሆንም ከሁለት ሌላ ሰዎችጋር በነጭ ቶዮታ መጣች። አንዱ ሰው ሹፌር ሲሆን
ሌላው ግን የ ጦርነት ጋር የተገናኙ ህጻናት ወይም Children Associated with War የመስክ ሰራተኛ ነበር። ድርጅቱ ከ ዩኒሴፍ እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚሰራ የካቶሊክ ድርጅት ነበር።

“ ወደ ሆስፒታል ሂደን ከተመረመርክ በኋላ ከተማ ሽርሽር ትሄዳለህ።” አስቴር በደስታ ምን ትላለህ ብላ ጠየቀችኝ፡፡

“እሺ” ብየ ተስማማሁ። ደስ ብሎኛል።”ጓደኛየ አል ሃጂ መምጣት ይችላል?” ብየ ጠየቅኩ።

“ይችላል” ስትል እንደምጠይቃት የጠበቀች ይመስላል።ወደ ፍሪ ታውን መንቀሳቀስ ስንጀምር የመስክ ሰራተኛው
“ ስሜ ለስሊ ይባላል፤ ስላገኘሁህ ደስ ብሎኛል” ብሎ ተዋወቅን።ወደ መሐል ከተማው ስንደርስ አስቴር እጆቿን እየጠቆመች ፖስታ ቤት፣ ሱቆችን፣ የተባባሩት መንግስታት ድርጂት
ህንጻዎችን እና የጥጥ ዛፉን አሳየችኝ። በከተማው ሁሌም እደነቃለሁ። በስራ የተጠመዱ ሰዎች ሲጣደፉ ሲወጡ ሲወርዱ የነጋዴዎች የግዙኝ ጩኧት ደግሞ ልዩ ድምፅ ይሰጣል።

ዶክተሩ የቆሰለ ወይም በጥይት የተወጋ ሰውነቴን እየነካ እና እየጨበጠ “የሚሰማህ ነገር አለ” እያለ ደጋግሞ ይጠይቀኝ ነበር፡፡መናደድ ስጀምር ጨርሰሃል አለኝ፡፡ ልብሴን ለብሼ አስቴር ፣
ለስሊ እና አል ሃጂ ወደ ሚገኙበት መቆያ ክፍል ሄድኩ::ተያይዘን ወደ ገበያው ሄድን። አስቴር ለ አል ሃጂ የስፖርት
ማሊያ ስትገዛለት ለስሊ ደግሞ ለእኔ የ ቦብ ማርሌን ኤክሶዶስ (ስደት) የሚለውን አልበም ገዛልኝ፡፡ አል ሃጂ ማሊያውን
ወዲያው ለበሰው:: ማሊያው የሃገሪቱን ብሔራዊ ሰንደቃላማ ማለትም አረንጓዴ፣ ነጭ እና ሰማያዊ ቀለማቶችን ይዟል።
አስቴር ለሁላችንም ኮካ ኮላ ገዛችልን። ለስለ እኔ እና ሌሎች ልጆችን ለማገዝ እንደተመደበ እና ዋና ስራው እኛ ከማገገሚያው በኋላ ለሚኖረን ህይወት ነገሮችን ማመቻቸት ነው።

በሚቀጥለው ቀን ወደ ከተማ ተመልሰን እኔ ሆስፒታል ሄድኩ። አስቴር ራሴን እያሻሸች “ መልካም ዜና ነው። ውጤትህ
መጥቷል። ዶክተሩ ለክፉ የሚሰጥ ህመም እንደሌለብህ አረጋግጧል። ለበለጠ እርግጠኝነት የተወሰኑ መድሃኒቶችን ትወስድ እና ዳግም ምርመራ ይደረግልሃል” አለች። ምንም
አላልኩም ! እሷ ግን ካሴት እና ማዳመጫውን ሰጠችኝ። አስቴርን እየለመድኳት ስመጣ ስለ ብዙ ነገር ማውራት ጀመርን፡፡በተለይ ግን ስለ ሙዚቃ ቦብ ማርሌ እና ራን ዲ.
ኤም.ሲ፡፡ ለስሊ በሳምንት ሁለት ጊዜ ይመጣ ነበር። ስለ ራስ ተፈሪያኒዝም ማውራት ይወዳል። እኔም #የኢትዮጵያ ታሪክ ደስ ይለኛል በተለይ ንግስት ሳባ እና ንጉስ ሰለሞን የተገናኙበት ታሪክ
ይገርመኛል። የተጓዙት ረዥሙ ጉዞ ፣ የመረጡት ቦታ እና ለመድረስ ያሳዩት ፅናት ሁሌም ይገርመኛል። ከህይወቴ ጋርም ለማገናኘት እጥራለሁ፡፡ የእኔ የህይወት ሩጫ እንደ እነሱ ትርጉም ያለው እና ደስታ የሞላበት እንዲሆን እመኛለሁ።

አንድ ምሽት አስቴር ቤቷ ወሰዳ እራት ጋበዘችኝ፡፡ ከእራት በኋላ ወደ ከተማ ወጥተን መናፈስ ጀመርን። ራውዶን መንገድ ጫፍ ወዳለ የባህር ዳርቻ ሄድን። ጨረቃ በድምቀት ወጥታ ነበር እና ደርቻው ላይ ሁነን መመልከት ጀመርን፡
ልጅ እያለሁ በጨረቃ ውስጥ የተለያየ ቅርፆችን እንመለከት እንደነበር ለ
አስቴር ነገርኳት። ገረማት። ጨረቃዋን እያየን የያዘችው ቅርፅ ምን እንደሆነ መገመት ጀመርን።

ልጅ እያለሁ አያቴ አስተውሎ ለሚያይ እና ለሚያዳምጥ ሰው ሰማይ ይናገራል ትል ነበር፡፡ በሰማይ ሁሌም የጥያቄዎቻችን
መልስ እና የነገሮች ምክንያት ይገለፃል። የእያንዳንዱ ስቃይ፣ ጉዳት፣ ደስታ እና ግራ መጋባት መንስዔ ይነገራል፡፡” ያ ለሊት ሰማዩ እንዲያወራኝ ፈለኩ።

ከአምስት ወር የቤኒን ማገገሚያ ቆይታ በኋላ አንድ ቀን ዓለት ድንጋይ ላይ ተክዤ ተቀምጬ እያለሁ አስቴር አየችኝ። ምንም
ሳትናገር መጥታ ከጎኔ ተቀመጠች። በሰለለ ድምፅ “ ከዚህ በኋላ የምኖርለት ምክንያት ያለ አልመስለኝ እያለ ነው” አልኩ።” ቤተሰብ የለኝም። እኔ ብቻ ነው የቀረሁት። የልጅነት ታሪኬን እንኳ የሚናገር የለም::”

አስቴር እጆቹዋን ወደ እኔ ልካ ጎትታ አስጠጋችኝ እና አቅፋ
“እኔን እንደ ቤተሰብህ አስበኝ፤ እንደ እህት ” አለች:: ግን እህት እኮ የለኝም”
አሁን አለህ፡፡ የአዲስ ህይወት ገፀ በረከት ነው። የተለያዩ የቤተሰብ አባላትን ማፍራት ትችላለህ።” ብላ አየችኝ፡፡

“እሺ! እህቴ መሆን ትችያለሽ ለጊዜው።”

“ይሁን ስለዚህ ነገ ጊዚያዊ እህትህን ለማየት ትመጣለህ አይደል።”

“እሺ!”

በሚቀጥለው ቀን አስቴር ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ጎብኚዎች እንዳሉ ነገረችኝ። ሰራተኞቹ የተሰጥዎ ውድድር እንድናደርግ ጠየቁን፡፡ የምንችለውን ማንኛውንም አይነት ነገር እንድናቀርብ
ነበር የተፈለገው።

ሬጌ ሙዚቃህን ለምን አትዘፍንም” ብላ አስቴር ሃሳብ አቀረበች።

• የሼክስፒርን ቃለ ተውኔትን ባቀርብስ”

“እሺ ትንሽ ሙዚቃ ብትጨምር ጥሩ ይመስለኛል” አለች

እጆችዋን ትከሻየ ላይ አደርጋ። ወድጃታለሁ ግን መውደዱን አላሳያትም:: ስታቅፈኝ ቀስ ብየ ከእቅፏ እወጣለሁ፡፡ ስትሄድ ግን አያታለሁ። ከትምህርት በኋላ ሩጬ እሷን ላይ እሄዳለሁ።ጓደኞቼ ማቡ እና አል ሃጂ “ የሴት ጓደኛህ መጣች እስማኤል” እያሉ ይቀልድብኛል፡፡

ጎብኚዎቹ ከ አውሮፓ ኮሚሽን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጂቶች የተውጣጡ ናቸው። ሙሉ ልብስ ከነከራባቱ ለብሰዋል። እርስበርሳቸው
ስላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ማዕከሉን እየዞሩ ቃኙ። በኋላ ለተሰጥኦ ውድድሩ በሚገባ ወደ ተዘጋጀው ወደ ምግብ አዳራሽ ገቡ። የማዕከሉ ዳሬክተር አቶ ካማራ የመክፈቻ ንግግር ካደረጉ
በኋላ ውድድሩ ቀጠለ። ተረቶች፣ አስፈሪ ታሪኮች እና የባህል ጭፈራዎች ቀረቡ። እኔ ከጁሊየስ ቄሳር የተወሰነ ቃለ ተውኔት
ካቀረብኩ በኋላ አንድ የሂፕ ሆፕ ሙዚቃ ተጫወትኩ።ሙዚቃው ስለ አንድ ታዳጊ ወታደር ትንሳኤ ሲሆን በአስቴር
የሞራል ድጋፍ እራሴ የፃፍኩት ነው::

ከውድድሩ በኋላ በማዕከሉ ታዋቂ ሆንኩ። የማዕከሉ ዳሬክተር አቶ ካማራ ቢሯቸው ጠርተው “ አንተ እና ጓደኞችህ የእውነት ጎብኚዎችን አስደምማችኋል። አሁን ታዳጊዎች ማገግም እንደሚችሉ አውቀዋል።” አሉ። ወደፊት እንደገና የማቅረብ እድሉ እንዳለኝ ሳውቅ በጣም ደስ አለኝ፡፡ አቶ ካማራ ደግሞ ከእኔ
በላይ በከፍተኛ ስሜት ላይ ነበሩ።

የማዕከሉ ቃል አቀባይ ብትሆን ምን ይመስልሃል?” ብለው ጠየቁኝ፡፡
“ምን! ምንድን ነው ምሰራው ወይም የምናገረውስ?”አልኩ።

“ በመጀመሪያ ስለ ታዳጊ ወታደሮች ዝግጅት በሚኖርበት ጊዜ የምታነበውን ነገር እንፅፍልሃለን። ስራውን ከለመድከው በኋላ ፀ የምታቀርበውን ንግግር እራስህ ልታዘጋጅ ትችላለህ” አሉኝ::
ሳምንት ሳይቆይ በታዳጊ ወታደርነት እና እንዴት መቆም አለበት በሚሉ ሃሳቦች ላይ ንግግር አደረኩ። “ማገገም እንችላለን ብየ እራሴን ምሳሌ በማድረግ ህፃናት ከችግሩ መውጣት
👍3😁1
እንዳለባቸው እና እድሉን ካገኙ መውጣት እንደሚችሉ በአፅንዖት ተናገርኩ።

የስድስተኛ ወር የማገገሚያው ቆይታን በማገባደድ ላይ እያለሁ የልጅነት ጎደኛዬ መሐመድ ወደ ማዕከሉ መጣ።
ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት ሞግዊሞን ለቅቄ ከቶሊ እና ጅንየር ጋር ወደ ማትሩ ጆንግ የሙዚቃ ውድድር ለመሳትፍ በሄድንበት ወቅት ነበር። ያኔ ከአባቱ ጋር የሳር ቤታቸውን እያደሱ ስለነበር
መምጣት አልቻለም፡፡ ሁሌም ምን ሁኖ ይሆን ብየ አስብ ነበር::ነገር ግን እንደገና አየዋለሁ ብየ አስቤ አላውቅም::

ጠይም ቀጫጫ ልጅ እየሮጠ መጥቶ
አስታወስከኝ” ካለ በኋላ መደነስ መዝፈን ጀመረ:: መዶሻው መጣልህ” የሚለውን ሲዘፍን አብሬው መዝፈን ጀመርኩ።
አብረን ከዳነስን በኋላ ተቃቀፍን። ስለልጅነታችን መጫወት ስንጀምር “ አንዳንዴ ያ መልካም ጊዜ በሙዚቃ ውድድሮች ተሳትፈን የምንደንሰው፣ አዳዲስ የዳንስ አይነቶች የምንለማመደው እና ኳሷን ማየት እስከሚሳነን እግር ኳስ የምንጫወተው ትዝ ይለኛል..ከረጅም ጊዜ በኋላ ይመስላል።አይገርምም? "

“ይገርማል”

በሰባተኛው ወር መጀመሪያ ለስሊ አስጠርቶኝ በማዕከሉ አንድ ክፍል ተገናኘን፡፡ ሳገኘው ፊቱ የሃዘን እና ደስታ ስሜቶች በመፈራረቅ ይነበቡበታል...


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#የፈሪ_ሰው_ጸሎት

አምላክ ሆይ .
ይግባኝ ዐለኝና አቤት የምልበት
በአርባ አራት ጾሜ ሕግን 'ምሽርበት።
ለምን? የሚል ሐሳብ . . .
በመሸነፍ ብእር ልብ ወለድ ተደርሶ
ይጠይቃል ልቤ ከዙፋንኽ ደርሶ።

እዚኽ . . .
ሕግን እያወጣ ደንብ እያረቀቀ
ሕዝብ እያስከበረ እራሱ እየናቀ፣
ይበይንብኻል . . .!
አያድን ከቅጣት ሕግን ያላወቀ።
( . . . እያለ. . .)

( ፈተና ፩ )
ሠፊው የ'ኔ ዓለም . . .
ስልቻ ላይሞላ ሠርክ ፍዳ ኾነ
ሆድ የሚሉት ዋሻ ለግብሩ ታመነ ፣
ድንጋይን ከዳቦ እያፎካከረ
ኅሊናን ረስቶ ተገዛ ፣ታሰረ።

( ፈተና ፪ )
መከራዬ ኹሉ ዕንገት እያስደፋኝ
መንገዴ በሙሉ 0ጉኖ እያፋፋኝ ፣
ጠረጠርኩኝና ...
በኾነው በቀኑ መድረስኽን ረሳኹ ፤
በማወቅ ጉጉቴ . . .
ከመቅደስ ከፍታ ለመውደቅ ተነሣኹ።

( ፈተና ፫ )
ነባዊ . . .
ልባዊ . .
ሕያዊ . . .
መገመት ጀመሩ ፤ አንሰው ኮሰሱና
እሩጫው ዐየለ ፤ መስገድ እረሱና ፣
ሙዳይ መስፈራዬ አስገምቶኝ ከ'ኔ
ገዛኹ ፣ተገዛኹኝ ፤ በምድራዊው ቅኔ።

እናም . .
ልቤ ቃልን ስቶ
ለሥጋ ተገዝቶ
በዓለም ተመርቶ።
በሰው መኾን ግብር
አልችል ካለች ነፍሴ ፈተናውን ማለፍ፤
ይግባኝ ባሉት ብሂል ይቺ ጽዋ ትለፍ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ሰባት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


“ደህና ነህ?” ብየ ጠየቅኩት::

ደህና ነኝ ብሎ ራሱን እያሻሸ ይቅርታ ይሄን ነገር እንደገና ስላነሳሁት እንደሚያስከፋህ ይገባኛል ግን እውነቱን መናገር አለብኝ” አለ። ክፍሉን እየዞረ የቅርብ ቤተሰቦችህን ማግኘት አልቻልንም። ስለዚህ አሳዳጊ ቤተሰብ ልንፈልግልህ ነው።
እንደሚስማማህ ተስፋ አለኝ፡፡ ሌላ ሃሳብ አለህ?”

“አዎ!” ብየ አባቴ ከጦርነቱ በፊት በዚህ ከተማ የሚኖር አንድ አጎት እንዳለኝ ይነግረኝ እንደነበር ነገርኩት።

ስሙ ማን ነው?”

“ቶሚ ይባላል እና አባቴ አናፂ እንደሆነ ነግሮኝ ነበር” ብየ መለስኩ።

“ምንም ቃል አልገባልህም፤ ግን የቻልኩትን እሞክራለሁ።በቅርብ እንገናኛለን” ብሎ ዝም ካለ በኋላ ትከሻየን እየነካካ “ ጥሩ እየሰራህ እንደሆነ ሰምቻለሁ። በርታ”አለኝ። ለስሊ በሰጠሁት ትንሽ መረጃ አጎቴን ከትልቅ ከተማ መሐል ያገኘዋል ብየ ተስፋ
አልታጣኩበትም ነበር። ለስሊ ከሄደ በኋላ ወደ አስቴር ሄድኩ።ለአስቴር ከ ለስሊ ጋር ስለበረን ቆይታ እና አጎቴን ያገኘዋል ብየ
እንደማልጠብቅ ነገርኳት። “ አይታወቅም! ሊያገኘው ይችላል” ” አለች::

አንድ ቀን ቅዳሜ ከስዓት ይመስለኛል ከአስቴር እና መሐመድ ጋር እየተጫወትኩ እያለ ለስሊ እየሳቀ መጣ። ጉድፈቻ የሚወስደኝ ቤት አግንቶልኛል፤ ልቀላቀል ነው ብየ ገመትኩ። ከማህበረሰቡ ጋር “መቀላቀል” ይሉታል ታዳጊ ወታደር የነበሩ ልጆችን ከ ዘመዶቻቸው ወይም ከአሳዳጊዎች ጋር ሲያገናኙ።

“ምንድን ነው መልካሙ ዜና?”ለስሊ ዜናውን ለመስማት ፤ጉጉቴን ፊቴን ላይ እያነበበ ወደ በሩ ተመልሶ በሩን ከፈተው።
አንድ ረጂም ሰውየ ገባ፡፡ ከአባቴ ትንሽ ጠቆር ያለ ፈገግታው ግን ደመቅ ያለ ሰው ነበር።

“አጎትህ ነው አለ ለስሊ በኩራት።

' እንዴት ነህ ልጄ እስማየል? አለ ሰውየው:: ጎንበስ ብሎ በረጅም እጆቹ ጠበቅ አርጎ አቀፈኝ፡፡ ምን አልባት እያስመስለ ቢሆንስ ብየ አሰብኩ። ለቆኝ አለቀሰ። ሲያለቅስ እውነትም ዘመዴ
እንደሆነ አመንኩ፡፡ ምክንያቱም የእውነት ነበር ያነባው፤ በሃገራችን ባህል ወንዶች እምብዛም አያለቅሱም::

“ይህን ሁሉ ጊዜ መጥቼ ስላላየሁህ ይቅርታ አድርግልኝ:: ከዝች ቀን በፊት መጥቼ አይቼህ ቢሆን ንሮ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር። አሁን ያለፈው አልፏል። ዛሬ መጀመር እንችላለን። ስለ አጣሃቸው ቤተሰቦችህ በጣም አዝኛለሁ መፅናናተትን እመኝልሃለሁ። በርታ። ለስሊ ሁሉንም ነግሮኛል።” ለስሊን በአክብሮት አይን እየተመለከተ ቀጠለ “ ከዚህ ጨርሰህ ስትወጣ ከእኔ ጋር መጥተህ መኖር ትችላለህ። ልጄ ነህ! ብዙ የለኝም ግን የምታድርበት ቦታ፣ምግብ እና ፍቅር እስጥሃለሁ።” አለ።

ተነስቼ አጎቴን አቀፍኩት፤ እሱም አቅፎ ግንባሬን ሳመኝ፡፡ትንሽ ዝም ብለን ከቆየን በኋላ “ብዙ መቆየት አልችልም ከከተማ
ውጭ የጀመርኩት ስራ አለ። ለጊዜው ቅዳሜ እና እሁድ እየመጣሁ እጠይቅሃለሁ። አንተም ስትችል አንድ ቀን መጥተህ ቤቴን ታያልኛለህ:: ልጆቼን እና ባለቤቴን ቤተሰቦችህን ትተዋወቃለህ” አለ፡፡

“ጋሼ ከዚህ በኋላ ስለዚህ ልጅ ደህንነት እነግርዎታለን” አለ ለስሊ።

አመሰግናለሁ” አለ አጎቴ።

አጎቴ ስንሸኘው አባትህን ነው የምትመስለው ፤አስተዳደጋችንን አስታወስከኝ። እንደ አባትህ አስቸጋሪ
እንደማትሆን ግን ተስፋ አለኝ” አለ እየሳቀ። እኔም ሳቅኩ።

ስንመለስ አስቴር የቦብ ማርሌን ሙዚቃ ከፈተች እና አብረን ማዜም ጀመርን። “Three Little Birds” ሶስት ትናንሽ ወፎች “Dont Woy about a thing” ስለ ምንም ነገር አትጨነቅ
"Cause every little thing gonna be all right...."
ምክንያቱም ሁሉም መልካም ይሆናል

አጎቴን ስለማግኘቴ ለ አል ሃጂ እና ማቡ ልነግራቸው ፈለኩ ግን እነሱ ቤተሰብ ስላላገኙ ተሰማኝ።

አጎቴ ቃሉን ጠብቆ ቅዳሜ እና እሁድ እየመጣ ይጠይቀኝ ጀመር። ስጦታ ያመጣልኛል፣ ስለ አስተዳደጉ ይነግረኛል ስለ አባቴም ይጠይቀኝ ነበር። አንዴ አባቴ ስለነገረኝ አንድ የልጅነት ትውስታቸው ነገርኩት። አባቴ እና አጎቴ ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ሲወርዱ ድንገት የንብ ቀፎ ያንቀሳቅሱ እና ንቦቹ ይከተሏቸዋል። አባቴ አጭር ስለነበር አብዛኛው ንብ ከአጎቴ ራስ
ላይ ነበር፡፡ ሩጠው ወንዝ ውስጥ ቢገቡም ጠብቆ ሊለቃቸው አልቻለም:: ስለዚህ ከውሃው ወጥተው ወደ መንደር ሲሮጡ ንቦቹን ወደ ሰፈር ይዘዋቸው መጡ።

“አዎ አስታውሳለሁ፡፡ ሁሉም ሰው ንቦቹን ወደ መንደር ይዘናቸው ስለመጣን አዝኖብን ነበር። መሮጥ የማችሉትን
ሽማግሌ ሰዎች እና ትንንሽ ህፃናትን ንቡ ነድፏቸው ነበር።አባትህ እና እኔ ግን በር ዘግተን አልጋ ስር ተደብቀን በሰዉ
እንስቅ ነበር” ብሎ ሲስቅ አብሬው ሳቅኩ፡፡

አንድ ቀን አጎቴ ቤተሰቦቹን ሊያስተዋውቀኝ ወደ ቤቱ ወሰደኝ::
ፍንትው ያለ ፀሐያማ ቅዳሜ ነበር። ኒው ኢንግላንድ ቬል New England Vile ውስጥ ነው የሚኖረው፡ውብ ከተማ ነበር። ቤቱግን መብራት ሆነ የቦንቧ ውሃ የለም። ወደ ደጁ ስንጠጋ የአጎቴ
ባለቤት ወጣች:: ፊቷ ያበራ ነበር፡፡ አጥብቃ አቀፈችኝ፡፡ ለቀቀችኝ እና ካየችኝ በኋላ ጉንጨን ቆንጥጣ “ እንኳን ደህና መጣህ ልጅ አለች:: አጠር ያለች ጥቁር ፣ ክብ ፊት እና አይኖቿ ጎላ ጎላ ያሉ ሴትዮ ነበረች። አባቴ የራሱ ልጆች አልነበሩትም ግን የቤተሰብ ልጆችን እንደራሱ አድርጎ ያሳድግ ነበር፡፡ አራት ነበሩ፦ አሌ
ትልቁ ሲሆን፣ ማቲልዳ፣ ኮና እና ሶሞ ይከተላሉ፡፡ የሚሰሩትን ስራ አቁመው መጥተው ሰላም አሉኝ፡፡ “ሌላ ወንድም ማግኘት ደስ ይላል” አለ አሌ እያቀፈኝ፡፡ ከተዋወቅን በኋላ ከአክስቴ እና ከአጎቴ በስተቀር ሁሉም ወደ ስራቸው ሄዱ። አክስቴ የምግብ አይነት እያመጣች ትደረድራለች፦ ሩዝ፣ አሳ፣ ሾርባ፣ አትክልት
ሌሎች ምግቦች። ሆዴ እስከሚነፋ ድረስ ብዙ በላሁ። ከምግብ በኋላ አጎቴ የአናፂ መሳሪያዎችን እና መስሪያ ቦታውን
አስጎበኘኝ፡፡

“ አናፂ መሆን የምትፈልግ ከሆነ ረዳቴ ልትሆን ትችላለህ። ግን እንደ አባትህ ትምህርት ቤት መግባት የምትፈልግ
ይመስለኛል” ሲል ፈገግ አልኩ። አሌ ተመልሶ መጣና አጎቴን ከእኔ ከእሱ ጋር ኳስ እንዲጫወት ፍቃድ ጠየቀ፡፡ አጎቴም እሱ ከፈለገ እሽ አለ፡፡ እኔ እና አሌ ተያይዘን ብሮክፊልድስ Brookfields ወደ ሚባል አካባቢ ሄድን።

“ወደ እኛ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል:: የእኔን ክፍል መጋራት እንችላለን” አለኝ፡፡ በእድሜ ከእኔ ይበልጠኛል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም አጠናቋል። ደስተኛ ፣ ስርዓት ያለው እና ተናጋሪ ነው። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት አንዲት ቆንጆ ልጅ ወደ እኛ እጇን ታውለበልባለች። ማናት ብየ ከ መጠየቄ በፊት አሌ የአጎታችን ልጅ ናት ከመንገዱ ማዶ ከጉድ ፈቻ አሳዳጊዎቿ ጋር ነው የምትኖረው፡፡ አሚናታ ትባላለች ትተዋወቃላችሁ” አለኝ፡፡አሚናት የአባቴ ሁለተኛ ወንድም ልጅ ነች።
ኳስ ጨዋታውን እየተመለከትን የእኔ ልብ ግን የነበረው ይኖራል ብየ አስቤው የማላውቀው ቤተሰብ መገኘት ላይ ነበረ።
ደስተኛ ነበርኩ። ስንመለስ አጎቴ ወደ ማዕከሉ ሊመልሰኝ እየጠበቀኝ ነበር። እጄን ይዞ አውቶብስ ጣቢያው እስከምንደርስ ድረስ ምንም አላልኩም:: አውቶብስ ጣቢያው ስንደርስ ሌላ ጊዜ
በእራስህ ልትጎበኘን ከፈለክ ብሎ ገንዘብ ሰጠኝ፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ለስሊ ወደ ማህበረሰቡ እንደምቀላቀል ነግሮኝ ነበር፡፡ ከአጎቴ ጋር ነው የምኖረው ሁለቱ
ሳምንቶች ቤኒን ቤት ካሳለፍኩት
ስምንት ወራቶች በላይ ረዘሙብኝ። ፈርቻለሁ። ከቤተስብ ጋር ለመኖር ፈርቻለሁ..
ለአመታት ብቻየን እራሴን ጠብቄ ያለ ማንም ምክር ነው የኖርኩት። ምናልባት አጎቴን እንዳላስቀይመው ፈራሁ። ራስ
ምታቴን፣ የለሊት ቅዠቴን፣ ልደብቀው የማልችለው መከፋት ምን እንደማደርግ አላውቅም።

ቀኑ ሲደርስ ዕቃየን ሰብስቤ በፌስታል ቋጠርኩ። መጀመሪያ አዳሪ ትምህርት ቤት ስገባ እንደተሰማኝ ስሜት ነበር የተሰማኝ፣ ልቤ ይመታ ነበር። መሐመድ ፣አል ሃጂ እና ማቡ አብረውኝ ነበሩ። አስቴር ትንሽ ቆይታ መጣች። “መሄድ አለብኝ” ብየ እጄን ወደ መሐመድ ስዘረጋ እሱ ግን ዘሎ አቀፈኝ። ማቡም አጥብቆ
አቀፈኝ፡፡ በኋላ ማቡ ቤተሰቦቹ ስላልተቀበሉት ወደ ጦርነቱ
ተመልሷል። አል ሃጂን ትክሻውን እየነካካሁ ፈገግ ስል “ ቻው አለቃ” አለኝ። ከአንድ ጉድ ፈቻ ቤት ወደ ሌላ ይቀያይር ስለነበር ከዚህ ቀን በኋላ አላየሁትም፡፡ አስቴር አይኖቿ እንባ አቀረዉ ነበር፡፡ አጥብቃ አቀፈችኝ፡፡ ከለቀቀችኝ በኋላ ወረቀት ሰጠችኝ።“ ይሄ አድራሻዬ ነው በማንኛውም ቀን መምጣት ትችላለህ
አለች::

አስቴርን ብዙ ጊዜ ተመላልሼ አይቻታለሁ። የሄድኩበት ስዓት ጥሩ አልነበረም። አቀፈችኝ እና አይኖቼን ቀጥታ እያየች በቀጣይ ቅዳሜ ወይም እሁድ ና እና እየኝ ሰፊ ጊዜ ይኖረናል አለች፡፡ ነጭ የደንብ ልብሷን ለብሳ ወደ ሌሎች የተጎዱ ህጻናት እየሄደች ነበር።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#ፍጻሜ_ሥጋ

አንዳንድ ቀን አለ . . .!
በደማቅ ቀለማት ከልብ የሚታተም
ልክ እንደፏፏቴ ካ'ለት የሚላተም።

በዚያ ቀን ...!
ጽልመት አሸንፋ የጠራች ጨረቃ፣
ሆደ ሠፊን ሰማይ አበራችው ደምቃ፤
ገዴ ዕጣ ክፍሌ . . .
አንዲት ፍኩ ኮከብ ፣ መለዮ ሰንደቋ።

ያን ቀን ...!
የምኞቴ እውነት ፣ የጸሎቴ ብሥራት
የልመናዬ ጥግ ፣ የሥለቴ ስምረት።
ጎኔ ተኝታለች፤
በዙሪያዬ ጸንታ ዕቅፌ ገብታለች።
ለደቂቃ ቅጽበት
በዐይኔ ዕቅፋት
በአንድ ጥቅሻ ፤
በከንፈርሽ ነጻ የልቤ ጥቀርሻ።

ይህ ቀን . . .!
ዐርብ ዕለት
ምሽት ኹለት ሰዓት ፣
እንዲሁም .
ጥንድ እውነት።

ያነፋስ ውብ ዜማ ፣ የቀልቤ ውልብታ
ያ'ብሪ ትሎች ፋና . . .
ምንጩ ያልታወቀ የነፍስ ፈገግታ።

(. . . ሠንቆ ነበረ . . . )

ፍጥረታት አኩርፈው ሰማይ ከል ለብሶ ፣
ትንቢት ተፈጽሞ . .
የሾኽ አክሊል ደፍቶ ቃል ሥጋ ተላብሶ።

ከእልፍ እንስት ዐይኖች ፣ እንባ እየጎረፈ፤
ፍጹሙ ፍቅራችን ፣
በፍጻሜው ዕለት ፣
የነፍስ ሐቃችን ውል ፣ እየተጠለፈ ፤
ሰውኛ ግብራችን . . .
የተፈጥሮን ኩርፊያ በጻድቅ ደም ጻፈ።
እናም በዚኽ ዕለት
የነፍሳችን ክብር በ'ርቃን ከታሠረ ፤
ሥጋ ፍጻሜ ነው !
በ'ርቃንሽ ተዋርዶ በደምሽ ከበረ።

🔘ተስፍሁን ከበደ🔘
👍2
#የነፍስጥም_ጽዋ

በሠቀቀን መኖር . .
በፍርሀት መስጋት ነገን በመናፈቅ፣
በይኾናል ተስፋ . . .
ዛሬን ሠውተኸው ለመጪው መንፈቅፈቅ።

( ..ምን ይሉት ፈሊጥ ነው . . ?)
ለምን ነው መጠበብ . . . ?
ለምን ነው መብሰልሰል ?
አኹን ላይ ተገልጦ ዘላለምን መምሰል።
ኖረኽ ለማታውቀው ሠርክ ከምትለፋ ፣
ዝም ብለኽ ጠጣና . .!
ሞት እንደኹ ያው ሞት ነዉ ፤ ዐይነ ስቡ ይጥፋ !

በእጅኽ ጨብጥና የብርሌን ዐንገት
ተጎንጭ ፣ አጉድልለት፤ የኑሮኽን ንፍገት።
ኹሉም እውነት አለው ፤ ከስካር በኋላ
የሚገለጥበት ፣ ከተሸፈነበት መጋረጃ ጥላ።

እንግዲኽ ሞት ማለት ..
ጽዋኽ ላይ የቀረው ፣ ማክተሚያው የጥማት
ባ'ንድ ትንፋሽ ወስደኽ ፣ የምትፈጽመው ቋት።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ስምንት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

....ብዙ የጦርነት ታሪክ እያዳመጡ መኖር
ይከብዳል። እኔ የራሴ አንድ አስቸጋሪ፣ አስጨናቂ እና በየ ጊዜው የሚጎዳ ታሪክ አለኝ፡፡ ለምንድን ነው ግን እሷ ይህን የምትሰሪው? ለምንድን ነው ግን እነሱ ይሄን የሚሰሩት? በየፊናችን የሄድን ይመስለኛል። ለመጨረሻ ጊዜ ያየኋት ጊዜ ነው። እወዳታለሁ ግን አልነገርኳትም::

አጎቴ በእጆቹ አንስቶ መኪና ውስጥ አስገባኝ፡፡ “ እንደ አለቃ (ሊቀ መንበር) ነው የምቀበልህ። አለቅነትህ ዛሬ ይጀምራል” አለኝ። አራቱ የአጎቶቼ ልጆች አሌ እና ሶስቱ ሴቶች ማቲልዳ፣
ኮና እና ሶሞ ተራ በተራ እያቀፉ ሳሙኝ። ፊታቸው በፈገግታ በራ። “እርቦሃል አይደል፤ እንኳን ደህና መጣህ በማለት ቆንጆ ዶሮ ወጥ ሰርቼለሁ” አክስቴ፡፡ እውነትም ቆንጆ ነበር። ታፋጭ!
እጄን እየላስኩ ነበር፡፡ ከምግብ በኋላ ምኝታ ቤቱን አሌ አሳየኝ።መሬት ላይ ነበረ ምተኛው። ምንጣፍ፣ አንሶላ እና ብርድ ልብስ የት እንዳለ አሳየኝ፡፡ ወደ ደጃፍ ስወጣ አጎቴ ከተማውን ታውቀዋለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ “ብዙም አለመድኩትም” አልኩ።

“አሌ ያስጎበኝሃል። ካልሆነ ደግሞ በራስህ እየጠፋህ እየተገኘህ ልታጠናው ትችላለህ። ከተማው ለማውቅ ጥሩ ነው::”

ከአጎቴ ጋር መኖር ከጀመርኩ ከአንድ ወይም ሁለት ቀናት በኋላ አሌ ሸሚዝ፣ ቀበቶ እና ከሙሉ ልብስ ጋር የሚለበስ ጫማ ሰጠኝ:: “ ጨዋ መሆን ከፈለክ እንደ ጨዋ ልበስ” ብሎ ሳቀና ቀጠለ፡፡ “ሚስጥር ነው:: ዛሬ ማታ ጭፈራ ቤት ልወስድህ እፈልጋለሁ:: ትንሽ ዘና ትላለህ:: አጎቴ ወደ ምኝታ ከሄደ በኋላ
እንወጣለን::”

ማታ ከቤት ሾልከን ወደ መጠጥ ቤት ሄድን። ከአሌ ጋር ስንሄድ ትምህርት ቤት እያለሁ የሄድኩባቸው የጭፈራ ምሽቶች
ትዝ አሉኝ፡፡ ረጂም ጊዜ ነው ግን የጭፈራ ምሽቶቹ ስያሜዎችን አይረሱኝም፡፡ Back to School” ወደ ትምህርት ቤት
እንመለስ፣ “Pens down” ብዕራችንን እንጣል፣ “Bob Marley Night የቦብ ማርሌ ምሽት እና ሌሎችም ነበሩ። አውራ ዶሮ እስከሚጮህ ድረስ እንጨፍር ነበር። ያኔ በጣም ደስተኛ ነበርኩ።

“ደርሰናል” አለ አሌ። ብዙ ወጣቶች ወደ ጭፈራ ቤቱ ለመግባት ሰልፍ ይዘው ነበር፡፡ ወንዶቹ በደንብ የተተኮስ ሱሪ
እና ሸሚዝ ለብሰዋል፡፡ ሴቶቹ ደግሞ ቆንጆ አበባ ቀሚስ ከረጂም ተረከዝ ጫማ ለብሰው ከአንዳንድ ወንዶች በላይ ረዝመው ይታዩ ነበር። ከንፈሮቻቸውን ደማቅ ቀለም ተቀብተዋል። አሌ ደስተኛ
ሁኖ ከሰልፉ ፊት ካሉት ሰዎች ጋር ያወራ ነበር። ስንገባ ሙዚቃ እስከአንቃሩ ተከፍቶ ነበር። አሌን ተከትየ ጠረጴዛ አግንተን አንድ ከፍ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥን።

“ ወደ ዳንስ መድረኩ ልሄድ ነው” ብሎ ተነሳ፡፡ ብዙም ሳይቆይ በህዝቡ መሐል ተሰወረ። ለደቂቃዎች ሳስብ ከዛ ብቻየን ስደንስ ከቆየሁ በኋላ ድንገት አንድ በጣም ጥቁር ሴት አንስታ ወደ ዳንስ
መድረኩ መራችኝ። አብረን ከምቱ ጋር መደነስ ጀመርን።በሙዚቃው መሐል አንድ ከእኔ ተለቅ ያለ ልጅ ጎትቶ ወሰዳት።

“ አማላይ ነህ አየሁህ እኮ” አለ አሌ ከአጠገቤ ቁሞ። እየሳቀ ነበር። እኔ ምንም አላረኩም:: ከእኔ ጋር መደነስ ፈልጋ ነው።አልኩ

እውነት ምንም ሳትል ሴቶች ወደ አንተ ይመጣሉ” ብሎ ቀለደ፡፡ ለሊቱን ሙሉ ደነሰን አጎቴ ከመንቃቱ በፊት ተመለስን።

ከተወሰኑ ምሽቶች በኋላ ብቻየን ወደ መጠጥ ቤቱ ሂጂ ልጂቱን አገኘኋት። ስሟ ዘይናብ እንደሆነ ነገረችኝ፡፡

“ባለፈው ስለሆነው ነገር ይቅርታ አድርግልኝ” አለች።ወንድሜ ወደ ቤት መሄድ ፈልጎ ነው እና ከእሱ ጋር መሄድ
ነበረብኝ፡፡ ካልሆነ ወላጆቼ ይጨነቃሉ።”

ልክ እንደ እኔ እሷም ብቻዋን ነበረች።

ለሶስት ሳምንታት ያህል አብረን ከቆየን በኋላ ብዙ ጥያቄ መጠየቅ ጀመረች፡፡ ከየት እንደመጣሁ? ክፍለ ሃገር ማደግ
እንዴት እንደሆነ? ክፍለ ሃገር ብዙ የፍሪ ታውን ሰው የሚጠቀምበት ቃል ሲሆን ገጠሬነትን ከኋላ ቀርነት እና ስርዓት
ማጣት ጋር አያይዞ ይገልፃል። ምንም ልነግራት አልፈለኩም ስለዚህ ተወችኝ። በቃ ከ ፍሪታውን ሴቶች ጋር የነበረኝ የፍቅር ታሪክ ይሄው ነው። ስለ እኔ ማወቅ ይፈልጋሉ እኔ ደግሞ ታሪኬን ለመንገር ዝግጁ አልነበርኩም። ምንም አይደል። ብቻየን መሆኔን ወድጀዋለሁ።

ለስሊ ሊያየኝ መጣ፡፡ እንዴት እንደሆንኩ እና ምን እየሰራሁ እንደሆነ ጠየቀኝ፡፡ ከትንሽ የራስ ምታት በስተቀር ደህና
እንደሆንኩ ነገርኩት። ማስታወሻ ደብተር ነገር አውጥቶ ፃፈ። “አንድ ስራ አለ ላንተ: በጣም አስፈላጊ ነው::”

ሁሌም የመልካም ዜና አብሳሪ ነህ” አልኩት።

“ ጠቃሚ ነው:: ሁለት ልጆችን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኒው ዮርክ አሜሪካ በመላክ የህፃናት ህይወት
በሴራሊዮን ምን እንደሚመስል ለማስረዳት ታስቧል። ስለዚህ
ቃለ መጠይቅ እየተደረገ ነው:: አቶ ካማራ አንተ ቃለ መጠይቅ እንድታደርግ ጠቁመው ነበር። ከፈለክ ይሄ አድራሻው ነው።አለና ሲፅፍበት የነበረውን ወረቀት ከማስታወሻው ገንጥሎ ሰጠኝ፡፡ “አብሬህ እንድሄድ ከፈለክ ቢሮ ና። ለቃለ መጠይቁ

የሚመጥን ልብስ ለብሰህ ና እሺ” ብሎ ሄደ::

የቃለ መጠይቁ ቀን ሲደርስ ግን እንደነገሩ የ አዘቦት ልብስ ለበስኩ። ስኒከርስ ፣ ጂንስ ሱሪ እና ረጅም እጅጌ ቲ ሸርት ለብሼ ሄድኩ። ለማንም የት እንደምሄድ አልተናገርኩም። ለአሌ
ልነግረው አሰብኩ ግን መናገር ከጀመርኩ ስለ ራሴ ከሚያውቀው አጎቴም ከነገረው በላይ ልነግረው ስለምችል ብየ ፈርቼ
ተውኩት።

ጠያቂው አትኩሮ ተመለከትኝ እና ቀስ ብሎ በእንግሊዝኛ

“ስምህ ማነው” ብሎ ጠየቀኝ።

“እስማየል” አልኩ።

ለምን አንተ ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሂዶ በዚህ ሃገር ስላሉ ህፃናት ችግሮች ለመናገር ትክክለኛው ሰው ነኝ ብለህ ታስባለህ?”

“ከክፍለ ሃገር ነው የመጣሁት:: በጦርነቱ የተጎዳ ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ የተሳተፍኩ እና በህፃናት ማገገሚ ያለፍኩ ነኝ፡፡ በቃለ
መጠየቁ ከተሳተፉት የከተማ ልጆች በላይ የተሻለ ግንዛቤ አለኝ፡፡ እኔ አልፌበታለሁ። እነሱ ግን እዛ ሄደው ምን ሊሉ ይችላሉ? ከዜና የበለጠ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም::” ፈገግ ብሎ
የሚያየኝ ጠያቂ ትንሽ አበሳጭቶኛል።

“ሌላስ ምን ትላለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡

“ምንም! ለምንድን ነው ምትስቅብኝ?” ብየ መልሼ ጠየቁኩት::

“አሁን መሄድ ትችላለህ” አለ ሰውየው አሁንም እየሳቀ።

ተነስቼ ወጣሁ። በኋላየ በሩ እንደተከፈተ ትቼው ወደ አሳንሰሩ ሄጄ ቆምኩ አልተከፈተም። ለቃለ መጠየቁ የመጡት
ልጆች ሳቁብኝ። ትንሽ ቆይቶ አንድ ሰው መጣና ግድግዳው ላይ ቁልፍ ተጭኖ ከፈተልኝ፡፡ ቁጥር ተጫነልኝ እና እጁን
በማውለብለብ ተሰናበተኝ፡፡ አሳንሰሩ መንቀሳቀስ ሲጀምር የምይዘው አጣሁ ወዲያው ግን ከወለል ደረስኩ። ከህንጻው
ወጥቼ ቅርጹን መመርመር ጀመርኩ። ለመሐመድ አግኝቼ ልነግረው ጓጓሁ።

ቀስ ብየ የሚያልፉትን መኪናዎች እያየሁ መጓዝ ጀመርኩ፡፡ብዙ መኪናዎች፣ የጦር መኪና እና የሃገሪቱን ባንዴራ እላያቸው
ላይ ያደረጉ መርሰዲስ መኪኖች ተከታትለዉ በፍጥነት አለፉ።ቤት ስደርስ በብዙ መኪኖች ታጂቦ የሚልፈው የተከበረ ሰው ማነው ብየ አሌን ጠየቁኩት። ቲጃን ከባህን ይባላል። አዲሱ ፕሬዝደንት ነው አለኝ፡፡ የሴራ ሊዮን ህዝቦች ፓርቲ የሚባለው ፓርቲው ግንቦት 1996 ምርጫ አሸንፎ ሃገሪቱን ከ ሰምንት
ወራት በፊት ጀምሮ እየመራ እንደሆነ ነገረኝ።

አንድ ጥዋት አቶ ካማራ ወደ አጎቴ ቤት መጣ። ከቀናቶች በፊት
👍2
ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደምሄድ ነግሮኝ
ነበር። ግን ኒው ዮርክ እሄዳለሁ ብየ ስላላመንኩ ከመሐመድ ዉጪ ለሌላ ሰው አልተናገርኩም::

“ሰላም አደርክ” አለ አቶ ካማራ ገና ጥዋት መሆኑን ከስዓቱ እያረጋገጠ፡፡

“ሰላም አደርክ” አልኩ መልሼ፡፡

ወደ ከተማ ለመሄድ እና ለጉዞህ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ዝግጁ ነህ?”


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#ለኀጥአን_የመጣ #ክፍል_አስራ_ስምንት #የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ #በኢስማኤል_ቤህ #ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው ....ብዙ የጦርነት ታሪክ እያዳመጡ መኖር ይከብዳል። እኔ የራሴ አንድ አስቸጋሪ፣ አስጨናቂ እና በየ ጊዜው የሚጎዳ ታሪክ አለኝ፡፡ ለምንድን ነው ግን እሷ ይህን የምትሰሪው? ለምንድን ነው ግን እነሱ ይሄን የሚሰሩት? በየፊናችን የሄድን ይመስለኛል።…»
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


አክስቴን ተሰናብቼ መኪና ውስጥ ዘልዬ ገባሁ እና የይለፍ ወረቀት (ፓስፖርት) ለማግኘት በረርን፡፡ የከተማው ሰው ሁሉ
ፓስፖርት አውጥቶ ከሃገር ለመኮብለል የወሰነ ይመስላል። ብዙ ሰው ነበር። አቶ ካማራ ግን ቀጠሮ ስላስያዘ ገብተን ፎቶ፣
አስፈላጊ መረጃዎችን አስገባን እና ክፍያ ፈፅምን። ፓስፖርቱ ከአራት ቀን በኋላ እንደሚደርስ ለአቶ ካማራ ነገሩት።

“የመጀመሪያው ደረጃ ተጠናቋል፤ አሁን ቪዛ ማግኘት አለብን።” አለ አቶ ካማራ ከዛም ከፓስፖርት ቢሮ ወጣን፡፡

ማታ ቤት ስመለስ አጎቴ ቤት ነበር ሰላምታ ስሰጠው ፈገግ ብሎ
“ምን እየተካሄደ እንደሆነ ልትነግረኝ ትችላለህ” አለ። በዝርዝር ኒው ዮርክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሂጄ ስለ ጦርነቱ እና በህፃናት ላይ ስለ ሚያደርሰው ተፅዕኖ ንግግር ላደርግ
እንደሆነ ነገርኩት። አጎቴ ብዙም አላመነም። “ሰዎች ብዙ ጊዜ
እንደዚህ አይነት ተስፋ እየስጡ ሌሎችን ያታልላሉ። ልጄ ተጠንቀቅ! ተስፋህን ሙሉ በሙሉ በእሱ ላይ ብቻ እንዳትጥል!”
አለኝ::

ጥዋት ወደ ስራ ከመሄዱ በፊት “የአሜሪካው ጉዞ ዘግጅት እንዴት ነው?!”ብሎ ይቀልዳል።
አቶ ካማራ ገበያ ይዞኝ ሄደና የልብስ ሻንጣ እና የተለያዩ አይነቶች ልብሶች፦ ረጂም እጅጌ ሸሚዝ፣ ጨርቅ ሱሪ እና ባህላዊ ልብሶች ገዛልኝ፡፡ ለአጎቴ አሳየሁት ግን ትሄዳለህ ብሎ ሊያምን
አልቻለም:: “ትንሽ ቀየር ብትል፤ ቢያምርብህ ብለው ነው” ብሎ
ይቀልድብኛል።

አንዳንዴ አጎቴ እና እኔ ከስራ በኋላ ዘወር ዘወር እንላለን። እንደት እንደሆንኩ
ይጠይቀኛል። ደህና እንደሆንኩ
እነግረዋለሁ። ረጂም እጆቹን ትክሻዬ ላይ ያደርግ እና ወደ እሱ ያስጠጋኛል። አንዳንድ ነገሮችን ልነግረው ፈልጌ ቃላቶችን እንዳጣሁ የሚውቅ ይመስለኛል፡፡ እንደዛ ነው ሚሰማኝ፡፡ ከአጎቴ ልጆች ጋር ወደ ጫካ ሂደን እንጨት ስንለቅም አዕምሮዬ ባለፈው
ያየሁት እና የተሰራው በማስታወስ ይዋዥ ቃል።

ሰኞ ጥዋት ዶ/ር ታምባ የተባለ ሰው በአሜሪካን ኢምባሲ እንዳገኘው ተነግሮኛል። ወደ ኢምባሲው ሲሄድ የከተማው ቀስ በቀስ መንቃት ይሰማኝ ነበር። በከተማው ሙሉ የሚሰማው
ማህል ከተማ ያለው የመስጊድ የጸሎት ጥሪ፣ የአዟሪዎች የግዙኝ ተማፅኖ፣ የመኪና ረዳቶች ጥሪ “ሉምሌ፣ሉምሌ” ወይም ኮንጎ ሰፈር። በጣም በጥዋቱ ብደርስም ብዙ ሰዎች ኢምባሲ በር ላይ
ተሰልፈዋል። ፊታቸው የተቆጣ ሰው ይመስላል። ፍርድ ትሞታለህ ወይም ትኖራለህ የሚል ፍርድ የሚጠብቁ ነው
ሚመስሉት፡፡ ምን እንደማደርግ አላውቅም ነበር። ዝም በዬ ሰልፉን ጠብቄ ተሰለፍኩ። ከአንድ ስዓት በኋላ ዶ/ር ታምባ ከአንድ ልጅ ጋር መጣ እና እንድከተለው ጠየቀኝ። ልጁም ቀድሞ
ወታደር እራሱን አስተዋወቀ “ቤህ እባላለሁ። አብረን ስለምንሄድ ደስ ብሎኛል” ብሎ እጄን ጨበጠ። የአጎቴ መልስ ትዝ አለኝ ልጄ ተጠንቀቅ! ተስፋህን ሙሉ በሙሉ በእሱ ላይ ብቻ እንዳትጥል”

ከሚያማምሩ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጥን ቃለ መጠየቁን መጠባበቅ ጀመርን፡፡ አንድ ነጭ ሴትዮ በግልፅ መስታውት ጀርባ ቁማ በድምፅ ማጉያ “
ለምን አላማ ነበር ወደ አሜሪካ የምትጓዘው?” ብላ ጠየቀች፡፡

የእኛ ተራ ሲደርስ ከመስታውቱ ጀርባ ያለችው ሴትዮ ፓስፖርታችንን ይዛ ነበር፡፡ ወደ እኔ አላየችም ይልቅ የፓስፖርቴን ገጾች ትገልጥ ነበር። መስኮቱ ለምን እንደዚህ የሰው ንክኪ እንዳይኖር ታስቦ እንደተሰራ ገረሞኝ እመለከት ነበር።

“በድምፅ ማጉያ ተናገር” አለች እና “ለምን አላማ ነበር ወደ አሜሪካ የምትጓዘው?” ብላ ጥያቄዋን ጀመረች::
“በህፃናት ላይ ስለ ሚያደርሰው ተፅዕኖ” ብየ ገለጸኩ::
“ጉባኤው የት ነበር?”
“ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኒው ዮርክ ከተማ
“ወደ ትውልድ ሃገርህ ለመመለስህ ዋስትናህ ምንድን ነው?እያሰብኩ ነበር “ንብረት አለህ፣ መመለስህን ሊያረጋግጥ
የሚችል የባንክ ተቀማጪስ አለህ?”
ተናደድኩ። በዚህ ሃገር ስላለው የህዝብ ኑሮ የምታውቂው ነገር አለ? ብዬ ልጠይቃት አስብኩ። ቀና ብላ ብታየኝ ኖሮ ይሄን ጥያቄ አትጠይቅም ነበር። በእኔ እድሜ ያለ ማንኛውም የሃገሬው ሰው የባንክ ሂሳብ መኖር አይደለም እስከ ጪራሹ ህልሙም የለውም:: ዶ/ር ታምባ በጦርነት የተጎዱ ህጻናት ተራድኦ
ድርጅት ሊቀ መንበር እንደሆነ እና አብሮን እንደሚሄድ፣ጉባኤው ሲያልቅ ወደ ሴራሊዮን እንደሚመልሰን አስረዳት።
ሴትዮዋ የመጨረሻ ጥያቄ ጠየቀች: “ አሜሪካ የሚኖር የምታውቀው ሰው አለ?”

“ማንም የለም። ከዚህ ሃገር ወጥቼ አላውቅም እንዳውም በዚህ ከተማ እንኳ የመጀመሪያየ ነው” አልኩ። ፓስፖርቴን
ዘግታ ነጥላ አስቀመጠችው።

ውጭ ዶ/ር ታምባ ቪዛ እንዳገኘን እና ፓስፖርታችንን ነገ እንደሚወስድ ነገረን፡፡ በመጨረሻ መንገደኛ መምስል ጀመርኩ፡፡
በቀኝ እጄ ሻንጣየን ይዣለሁ ፤ ቡናማ ባህላዊ ሱሪ እና ሽሚዝ ለብሼ ነበር። ከአሌ ክፍል ስወጣ አጎቴ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ነበር።

“ወደ አየር መንገድ እየሄድኩ ነው” አልኩ ፈገግ ብዬ፡ አጎቴ እንደሚቀልድብኝ አውቅ ነበር፡፡አዎ! አሜሪካ ስትደርስ ደውልልኝ፡፡ አይ መች ስልክ አለኝ፡፡በል በአሚናታ ቤት ደውልልኝ መጥታ ታገኘኛለች” ብሎ አጎቴ
ፈገግ አለ።

“እሽ እደውላለሁ” ብየ በፈገግታ መለስኩ።

“ልጆች ኑ ወንድማችሁን ተሰናበቱት። የት እየሄደ እንደሆነ አላውቅም ግን ይቅናህ እንበለው” አለ አጎቴ። ማቲልዳ፣ ኮና እና
ሶሞ ባልዲ እንደያዙ ወደ ደጃፍ መጡ። ውሃ ሊቀዱ ሊሄዱ ነበር፡፡ አቀፉኝ እና በመንገዴ እንዲቀናኝ ተመኙ። አክስቴ ጪስ ጪስ እንደሸተተች ከኩሽና ቤት መጥታ አቀፈችኝ። “ የትም ብትሄድ ቤትህን ጠረን መሽተት አለብህ። ይሄ ላንተ የምሰጥህ ሽቶየ ነው”አለች በፈገግታ:: አጎቴ ተነስቶ አቀፈኝ እጆቹን ትክሻየ ላይ አድርጎ “መልካም ምኞቴ ካንተ ጋር ነው። በኋላ ለእራት እጠብቅሃለሁ” ብሎ ወደ ደጃፍ ወጣ፡፡

ስለ ኒው ዮርክ ያለኝ አመለካከት የሚመነጨው ከራፕ ሙዚቃዎች ነበር። ሰዎች መንገድ ላይ የሚታኮሱበት እና ምንም እንዳልተፈጠረ የሚመስሉበት፣
ማንም የማይጓዝበት ይልቅ በስፖርት መኪኖች ለጭፈራ እና ለሁከት የሚሄድበት ቦታ አድርጌ ነበር በአዕምሮዬ የሳልኩት። እንደዚህ አይነት የእብድ ቦታ መገኘት አልፈልግም። ሃገር ቤት በቅቶኛል::

ጆን ኤፍ ኬኔዲ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ስንደርስ ጨልሞ ነበር። 4፡30 ነበር። ዶር ታምባን ለምን በጠዋት እንደጨለመ
ጠየቅኩት።” (Winter ) በጋ ስለሆነ” አለኝ። “አሃ”ብየ ራሴን ነቀነቅኩ ግን በጠዋት መጨለም የሚለው ነገር ሊገባኝ
አልቻለም:: Winter ዊንተር የሚለውን ቃል በሼክስፔየር ጹሑፎች አውቀዋለሁ ግን ትርጉሙን እንደገና ማየት ያለብኝ
ይመስለኛል።

ዶ/ር ታምባ ፓስፖርታችንን ይዞ ሄደ እና ከኢምግሬሽን ሰዎች ሁሉንም ነገር አስረድቶ አለፈ። ሻንጣችንን አገኘን ወደ
ተንሸራታች በሮች አመራን። ዶ/ር ታምባ ውጭ ነበር። ባህ እና እኔ በተንሸራታች በሩ ስናልፍ በጣም ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበለን።ቆዳየ ሲኮማተር ይሰማኛል፣ ፊቴ ሊሰማኝ አልቻለም፣ እና ጆሮዬ
ተቆርጦ የወደቀ ይመስላል፣ እጣቶቼን አመመኝ ጥርሴም ተንቀጠቀጠ። ንፋሱ በሱሪየ እና ሸሚዜ አልፎ ገብቷል፤ ምንም
የለበስኩ አልመስለኝ አለ፡እየተንቀጠቀጥኩ ነበር። በህይወቴ
እንደዚህ በርዶኝ አያውቅም። ሰው እንዴት ነው ከዚህ ሃገር የሚኖረው? ብዬ አሰብኩ፡፡ ዶ/ር ታምባ ታክሲ ይዞ እኔ እና ባህን አስገባን እና ለሹፌሩ ወረቀት ላይ እያነበበ ወደ የት መሄድ እንደሚፈልግ
👍2