#የማያልፍ_የትአለ
ስምን ያተረፈ ያበቀለ ዝና
ሳይለፋ ያገኘ ማንም የለምና
ክብርና ዝናን አንቱታንጰተላብሶ
ተወልዶ ያየሁት የለምና ነግሶ
የድርሻዬን መጠን የልፋት ድካሜን
መች እቀመጣለሁ ሳላሳካው ህልሜን
ችግር ፈተናውን እየተወጣሁት
በብርቱ ጥረቴ ሁሉን ካሳለፍኩት
ደግሞ የነገውን ከፊቴ ያለውን
ካይኔ ተሰውሮ ባላውቀው መጪውን
ከሕይወት ጥለት ላይ እስኪቋጭ አለሜ
ሩጫዬ አይቆምም እውን ሳይሆን ህልሜ።
🔘ሰላም ዘውዴ🔘
ስምን ያተረፈ ያበቀለ ዝና
ሳይለፋ ያገኘ ማንም የለምና
ክብርና ዝናን አንቱታንጰተላብሶ
ተወልዶ ያየሁት የለምና ነግሶ
የድርሻዬን መጠን የልፋት ድካሜን
መች እቀመጣለሁ ሳላሳካው ህልሜን
ችግር ፈተናውን እየተወጣሁት
በብርቱ ጥረቴ ሁሉን ካሳለፍኩት
ደግሞ የነገውን ከፊቴ ያለውን
ካይኔ ተሰውሮ ባላውቀው መጪውን
ከሕይወት ጥለት ላይ እስኪቋጭ አለሜ
ሩጫዬ አይቆምም እውን ሳይሆን ህልሜ።
🔘ሰላም ዘውዴ🔘