♥እንኳዋን ለሐዋርያው "ቅዱስ ናትናኤል" ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ♥
+✝ቅዱስ ናትናኤል ✝+
በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት
መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ
ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ
ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን
ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000
ሕጻናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል::
እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር::
ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም #ስምዖን ሲሆን
ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ደግሞ #ናትናኤል ብሎታል::
በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና
አካባቢ ስላደገ) አንዳንዴም #ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር::
ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: በገሊላ ቃና
ሰርግ የደገሰው #ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ
ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ
ምክንያትም ይሔው ነው::ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን #ከገማልያል ተምሮ : ከበለስ ቁጭ
ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ?" እያለም ይተክዝ
ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ
#በፊልዾስ አማካኝነት ጠርቶታል::
ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በሁዋላ ግን የጌታችንን
ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት
ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል
አመስግኖታል::
ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምስጢረ
መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ:
ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ
ክርስቶስ) መልሷል::
እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል::
የጌታችን ወንድም የተባለ #ቅዱስ_ያዕቆብ በአይሁድ
ከተገደለ በሁዋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም 2ኛ
ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ
ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት
አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ
ሰማዕት የሆነው በ150 ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ
ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል::

#ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ
ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ #ማርያም_እግዝእት
በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ
መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
✝ከግራ ቁመት:
✝ከገሃነመ እሳት:
✝ከሰይጣን ባርነት:
✝ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
✔ እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ ✔ እንዳለ
ሊቁ::
✝ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ
ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው
ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ
አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም
ራሷ አርአያ #ትዕምርተ_መስቀል ናት::
✝እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት
(ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
✝ #ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
✝ #ቅዱስ_ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
✝ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ.
48:14):
✝ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው #የሙሴ_በትር (ዘጸ.
14:15):
✝ # የናሱ_ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8)
ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ
መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
✝ # ቅዱስ_ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ
ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ
መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)
✝በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ
መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን
አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት::
ስለዚህም "#መስቀል_ብርሃን_ለኩሉ_ዓለም :
#መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን " ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
✝ #ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ
ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን
ይነግረናል:: #ብርሃነ_ዓለም #ቅዱስ_ዻውሎስም ስለ
መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን
ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)
✝አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል::
የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ:
የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ:
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ
በወዴት አለና::
✝ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር
አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን:
እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት:
ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ
ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን
ተሻግረዋል::
✝በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም
አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን
እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ
ምስክርን አንፈልግም::
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ
ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ #ማርያም_እግዝእት
በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ
መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
✝ከግራ ቁመት:
✝ከገሃነመ እሳት:
✝ከሰይጣን ባርነት:
✝ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
✔ እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ ✔ እንዳለ
ሊቁ::
✝ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ
ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው
ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ
አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም
ራሷ አርአያ #ትዕምርተ_መስቀል ናት::
✝እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት
(ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
✝ #ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
✝ #ቅዱስ_ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
✝ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ.
48:14):
✝ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው #የሙሴ_በትር (ዘጸ.
14:15):
✝ # የናሱ_ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8)
ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ
መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
✝ # ቅዱስ_ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ
ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ
መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)
✝በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ
መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን
አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት::
ስለዚህም "#መስቀል_ብርሃን_ለኩሉ_ዓለም :
#መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን " ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
✝ #ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ
ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን
ይነግረናል:: #ብርሃነ_ዓለም #ቅዱስ_ዻውሎስም ስለ
መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን
ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)
✝አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል::
የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ:
የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ:
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ
በወዴት አለና::
✝ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር
አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን:
እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት:
ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ
ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን
ተሻግረዋል::
✝በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም
አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን
እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ
ምስክርን አንፈልግም::
💚💛 ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ 💛❤️
ሐናንያ ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ተመዝግቦ ከተቀመጠልን ከጥቂቶቹ ዋነኛው ነው:: ከነገደ እሥራኤል ተወልዶ : በሕገ ኦሪት አድጐ : ከወጣትነት ዕድሜው ትንሽ እልፍ ሲል ጌታችን ወንጌልን ማስተማር ጀምሯልና ጠራው:: እርሱም በበጐ ፈቃድ ተከትሎታልና ከ72ቱ አርድእት ደመረው::
ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ተምሮ : ከዕለተ ስቅለት በፊት ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ነበር:: ምክንያቱም ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈልን ሰብዐው አርድእት "ጌታ ሆይ! አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ማለታቸውን አስቀምጦልናል:: (ሉቃ. 10:17) ቅዱስ ሐናንያ በበዓለ ዕርገት ተባርኮ በ50ኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::
በሚያስተምር ጊዜ የሶርያዋን ደማስቆን ማዕከል አድርጐ ነበር:: በሁዋላም አበው ሐዋርያት የዚህች ከተማ የመጀመሪያው ዻዻስ አድርገው ሹመውታል:: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ክርስቲያኖችን ያሰቃይ የነበረው ሳውል (የሁዋላው ቅዱስ ዻውሎስ) ወደ ደማስቆ የተጉዋዘው ክርስቲያኖችን በተለይም ቅዱስ ሐናንያን ለማሠር ነበር::
ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ይሆን ዘንድ መብረቅ ዐይኑን አጠፋው:: ወዲያውም ጌታችን ሳውልን ወደ ሐናንያ እንዲሔድ ነገረው:: ከ3 ቀናት በሁዋላ ጌታችን ለሐናንያ ተገልጦ አነጋግሮታል::
ሳውል (ዻውሎስ) ወደ ሐናንያ የደረሰው በመሪ ነበር:: 2ቱ እንደተገናኙ ቅዱስ ሐናንያ ሳውልን አስተማረው : ፈወሰው : አጠመቀው : በጐ መንገድንም መራው:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ሐዋርያ የቅዱስ ዻውሎስ የንስሃ አባቱ ይሰኛል:: (ሐዋ. 9:1-19)
ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ሐናንያ ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን አስተማረ:: መከራንም ተቀበለ:: በመጨረሻም በዚህ ቀን ክፉዎች ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል::
💚💛ቅዱስ ቶማስ ዘሰንደላት 💛❤️
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ሰማዕታት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ወደ ሰማዕትነት ሕይወት የገባው በ11 ዓመቱ በመላእክት መሪነት ነው:: ገና ወደ ምስክርነት አደባባይ እንደ ቀረበ መኮንኑ "ክርስቶስን ካድና ልሹምህ" ቢለው ሕጻኑ ቅዱስ ቶማስ ተቆጥቶ : "አንተ ሰነፍ መኮንን" ብሎ ገስጾ : በጐችን ይመልስባት በነበረችው ጅራፍ ገርፎታል:: ይሔም በዘመኑ የመጨረሻው የድፍረት ደረጃ ነበር::
በዚህም ምክንያት በሕጻን ገላው ላይ የተቀበለው መከራ ሊናገሩት ይከብዳል::
¤ግርፋት:
¤እሳት:
¤አራዊት በእርሱ ላይ አልፈዋል::
አካሉ ተቆራርጧል:: አንድ ጊዜም "ለጣዖታችሁ እንድሰግድ አምጡት" ብሏቸው ልክ ከፊቱ ሲደርሱ ወደ ጌታ ቢጸልይ መሬት ተከፍታ ውጣቸዋለች::
እሱን ያሰቃየው የነበረውን መኮንንም ከደዌው አድኖ ከነ ሠራዊቱ አሳምኖታል:: ሕጻኑን ቅዱስ ቶማስን ግን ያላመኑ አረማውያን በዚህች ቀን አንገቱን ሰይፈውት በሰማዕትነት ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔዷል::
🌿 አምላከ ቅዱሳን ከሐዋርያው በረከት : ከሰማዕቱም ምልጃ አይለየን::🌿
💚💛ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ💛❤️
በቤተ_ክርስቲያን_ታሪክ በደራሲነታቸው: በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው::
ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር::
አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ገና በ3 ዓመቱ እናቱ አቅፋ ወደ #ቤተ_መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "#አንሰ_እፈርሕ_ሠለስተ_ግብራተ-እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ::
ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም:-
1.ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ
2.ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ
3.ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው::
ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "#እግዚአብሔር_በዚሕ_ሕጻን_አድሮ_ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል::
+ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው::
"እንግዲያውስ #ትንቢተ_ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል::
ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በሁዋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን: ዕጸበ ገዳምን: ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ: #ጾምና_ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል::
በዘመኑም:-
1.የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል
2.ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል
3.በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል
4.ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል::
በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በሁዋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች::
#አምላከ_ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን::
From:-d/n yordanos abebe
ቀን:- 27/10/2011
@senkesar @senkesar