ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
+#አቡነ_ኪሮስ_ጻድቅ +
የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው: ክቡር ነው::
በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን
ይበጃል::
ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው
"ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ::
"ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት
መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል:: በዚህ
ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል::
ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል:: አካላቸውንም
እንደነበረ መልሶላቸዋል::
አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው
መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ:: ሱባዔ
ገብተው: ፍጹም አልቅሰው: ከጌታም አማልደው: የዛን
ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል:: በሌላ ጊዜ
ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና
መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ::
ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው:
ሙታኑን አስነስተው: ንስሃ ሰጥተው: ገዳሙን የጻድቃን:
ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል:: ጻድቁ
#እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት
አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር:: እመ አምላክም
ተገልጣ ትባርካቸው ነበር::
ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57
ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ:: ጌታችን
#ኢየሱስ_ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና)
በየቀኑ ይጐበኛቸው: ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር::
በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን:
ጻድቃን ሰማዕታትን: ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን
አስከትሎ ወረደ::
#ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው: በበገናው
እየደረደረላቸው: ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው
ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ጌታችንም ታቅፎ: ስሞ
ይዟቸው አረገ:: ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት:: የአቡነ
ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ: ጽሕማቸውም የተንዠረገገ
ነበር:: እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል
አይመስለኝም::
በረከታቸው ይደርብን!