የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.05K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#በኢትዮጵያ_ቃለሕይወት_ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ ቤት ከአስር ቀጣናዎችና አጥቢያዎች ህብረቶች እንዲሁም ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት የተወጣጡ #86_ሰልጣኞች_የአሰልጣኞች_ስልጠና_ወሰዱ። ስልጠናው በ15 ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነዉ።
በስልጠናው መሐል የቤተክርስቲኒቱ የሙያተኞች አገልግሎት ክፍል ባለፉት ስድስት አመታት በንግድ፣በመንግስት ስራ እና በልዩ ልዩ ሞያ ላይ ለተሰማሩ ሰራተኞች አጥቢያን መሰረት ያደረገ የማደራጀትና የማሰልጠን አገልግሎት በርካታ ውጤቶች መምጣታቸውን ከየቀጣናው የመጡ ሰልጣኞች በምስክርነታቸው አረጋግጠዋል። የሙያተኞች አገልግሎት ክፍል በቀጣይ ከመዋቅሮች ጋር በመነጋገር የስልጠና ማዕከላትን በወጥነት በማቋቋም በየዙር ሰልጣኞች እየገቡ እንዲሰለጥኑና ተግባራዊ ርምጃ በመውሰድ ሁለንተናዊ ለውጡን እንዲያቀጣጥሉ ለማስቻሉ መታቀዱን ተናግረዋል።በመጨረሻም በቤተክርስቲያኒቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ የተሰጠውን የመመዘኛ ፈተና ከ80% በላይ ውጤት ላመጡ ሰልጣኞች ሠርተፊኬት ከተሰጠ በኋላ በዋና ጸሐፊው በዶ/ር ስምኦን ሙላቱ የመዝጊያ መልዕክት ሁሉም በየቦታው የተሰጠውን መክሊት በአግባቡ በመጠቀምና በማትረፍ በምድር ላይ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት በሰማይ ደግሞ እንደታማኝ ባሪያ አክሊልን ለማግኘት እንዲሮጥ በማሳሰብ ስልጠናው በጸሎት ተጠናቋል። መረጃዉን ከቤተክርስቲያኒቱ ማህበራዊ ትስስር ገፅ አገኘነዉ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/HJAM9N5lCN8
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1
#የኢትዮጵያ_የሃይማኖት_ተቋማት ጉባኤ #በኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ቤተክርስቲያን እና #በኢትዮጵያወንጌላዊት_ቤተክርስቲያን_መካነ_ኢየሱስ #ንጹሐን_አማኞች_ላይ_የተፈጸመውን_ግድያ በእጅጉ #አዉግዟል
ጉባኤዉ “በንጹሐን ላይ የሚፈጸም ግድያ፣ ኢሰብአዊ ድርጊትና አያያዝ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ ወንጀል ነው” ብሏል።

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ንፁሐን አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን የሚገልጽ ከሁለቱ አባል ቤተ እምነቶች ካወጡት መግለጫ ተገንዝበናል ያለዉ ጉባኤዉ ድርጊቱ በእጅጉ የሚያሳዝን ከመሆኑም በላይ በሃይማኖት አገልግሎት ላይ የነበሩ ንፁሐን አማኞችን መግደል ደረቅ የወንጀል ተግባር በመሆኑ በእጅጉ የሚወገዝ ድርጊት ነው ብሏል።
በተጨማሪ ባለፈው ዓመት በተለያዩ ቦታዎች ላይ የቤተ ክርስቲኒቱ አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን በመግለጫው ተገልፃል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ይህ አይነቱ የወንጀል ድርጊት በእጅጉ እያወገዘ የሚመለከተው የመንግስት አካልም የዜጎችንና የሃይማኖት ተቋማትን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ሕገ መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤው በአጽንኦት አሳስቧል።
በንጹሐን ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸሙትንም ወንጀለኞች በአፋጣኝ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግና ፍትህን አንዲያስከብር ይጠይቃል፡፡
ከዚህም ባለፈ በሀገራችን የሚታየው ማንኛውንም ዓይነት ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታረም፣ የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት ሳይሸራረፍ የመጠበቅ መንግስታዊ ሃላፊነተን ሕግንና መመሪያን መሠረት በማድረግ ሊሠራ ይገባል፡፡
ጉባኤዉ በንፁሀን ላይ ስለተፈጸመው ጥቃትና ግድያ በድጋሚ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጆች ዘመዶች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢያሱስ አባቶችና መሪዎች ልባዊ መጽናናትን ተመኝቷል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/8f0kbYG0EJM
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#በኢትዮጵያ_ አማኑኤል_ ህብረት_ የሃልዎት_ቤተክርስቲያን #ደም የመስጠት መርሃ ግብር አካሄደች።
ቅዳሜ ህዳር29/3/16 ዓ.ም የሃልዎት አማኑኤል ቤተክርስቲያን የናታኒም አገልግሎት ክፍል ከኢትዮጵያ ደም ባንክ ጋር በመተባበር ለ10ኛ ጊዜ የቤተክርስቲያኗ ምዕመን እና መሪ ነብይ ዘነበ ግርማ በተገኙበት ደም የመስጠት መርሃ ግብር ተካሄዶአል።
ቤተክርስቲያን በየ3 ወሩ ደም የመስጠት መርሃ ግብር የምታካሄድ ሲሆን ይህም በመልካም ተግባሮች በማህበረሰቡ ውስጥ በንቃት በመሳተፍ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ የምስራችሁን ማድረስ መሆኑን ተገልጾአል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/MG9E0q4Lr58
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍4
#በአዲስ #አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት #በኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን #አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት እና ጠቅላይ ቤተክህነት የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ማክሰኞ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም “ትብብርና አብሮነትን ማጎልበት ለዘላቂ #ሰላም" በሚል #መሪ #ቃል በተካሄደው ጉብኝት #እና ምክክር ላይ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አባላት አባቶች የተሳተፉበት ሲሆን በኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤ/ክ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የጉባኤው ቦርድ ሰብሳቢ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ እና የሀገረ ስብከቱ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች መሪዎችን ተቀብለው አስተናግደዋል። በዚሁ የጉብኝት መርሐ ግብር ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዳይሬክተር እና የአ/አ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አባል የሆኑት መጋቢ አሸብር ከተማ ተገኝተዋል።
ብጹዕነታቸው የቦርድ አባላቱን በጽ/ቤታቸው በተቀበሉበት ወቅት ወደ ታሪካዊው ሀገረ ስብከት እንኳን በሰላም መጣችሁ በማለት ሀገረ ስብከቱ ከምስረታው #ጀምሮ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ አገልግሎትን እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን #ይህ ጉብኝት አብሮነታችንን የሚያጠናክር በመሆኑ ሊቀጥል ይገባል በማለት እንግዶች በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ #ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው በሃይማኖቶች መካካል መቀራረብ፣ መተዋወቅ፣ መማማር እና መደጋገፍ አብሮነትን ይበልጥ የሚያጎለብት ሁነኛ መሳሪያ ነው። ያሉ ሲሆን ጉባኤው #ይህንን ጉብኝት ያዘጋጀው በሃይማኖቶች መካካል የሚኖረው መከባበር፣ ትብብር እና አብሮነትን ማጠናከር ለሃገራችንም ሆነ ለከተማችን ዘላቂ ሰላምና ልማት ያለው ፋይዳ #ትልቅ በመሆኑ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት የሊቀ ጳጳሱ ልዩ ጸሐፊ ሊቀ ሕሩያን #ዮሐንስ ቀኖ የሃገረ ስብከቱ መዋቅር ፤ #ከዚህ ቀደም የሰራቸውን ስራዎችን እና ሚሰራቸው ስራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።
በሃይማኖቶች መካካል የሚኖረው ትብብር እና አብሮነትን ማጠናከር አላማ ያደረገው የጉብኝት መረሃ ግብር መሰረት በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ቤተመጽሐፍት ወመዘክር እንዲጎበኙ ተደርጓል።
የጉባኤያችን የቦርድ አመራር የሆኑ መሪዎች በጉብኝቱ እና ቤተክርስቲያኒቱ በመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አገልግሎት ላይ እየሰራች ያለችውን ስራዎች በመመልከታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በሃይማኖት ተቋማት መከካል የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቶቻቻንን ማጠናከር በመሆኑ በተቋማችን #ስራ አመራር ቦርድ ውሳኔ መሰረት ይህንን የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴት ይበልጥ ለማጎልበት እንዲረዳ የአባል #ቤተ እምነቶቹ ጉብኝት የመጀመሪያ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በአዲስ አበባ #ከተማ #እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የሚከወን ይሆናል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/eIQ2PeyOHN0
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#በአዲስ #አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት #በኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን #አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት እና ጠቅላይ ቤተክህነት የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሄደ።
1
#በኢትዮጵያ_ቃለ_ሕይወት_ቤተ_ክርስቲያን_ኩሪፍቱ_ማእከል_ላይ
#በቢሾፍቱ_ከተማ_አስተዳደር_እየተወሰደ_ያለውን
ኢ/ህገ_መንግስታዊ_ጥሰት_ለመቃወም_የተሰጠ
መግለጫ!
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
13🙏8👍2😢2
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_የተሰጠ_ጋዜጣዊ_መግለጫ
በመጋቢ ጌቱ ለማ የካውንስሉ ጽ/ቤት ሃላፊ
#በኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፋቱ ማዕከል ላይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እየተወሰደ ያለውን ኢ/ህገ መንግታዊ ጥሰት ለመቃወም የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፋቱ ማዕከል በህጋዊ መንገድ ለቃለ ሐይወት ቤተክርስቲያን የተሰጠ ሰነድ ያለው ይዞታ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከቤተክርስቲያኒቱ ቦታ ላይ 40 ሺህ ካሬ ሜትር የሚሆነውን በኃይል በመቀማት ለሁለት ግለሰቦች በመስጠት ኢ.ህገ መንግስታዊ በደል ፈጽሞብናል።
ይህንን ጉደይ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ቤተክርስቲያን ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርባ ፍርድ ቤቱ ቦታው የቃለ ሕይወት ይዞታ መሆኑን ውሳኔ አስተላልፎ ባለበት ሁኔታ የከተማ አስተዳደሩ የግንባታን ሂደቱን እያስተጓጎለ ስለነበር ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ለፌዴራል መንግስት አቅርበን በከፍተኛ አመራር ደረጀ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየታየ ባለበት ሁኔታ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ የቤተክርስቲያኒቱ ይዞታ ውስት ወታደሮችንና የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችን ይዞ በመግባት ችካል በማስቀመጥ የቤተክርስቲያኒቱን ይዞታ ለግለሰቡ በማስተላለፉ ህግ ወጥ ተግባር ፈጽሞብናል ።
ይህ ሁኔታ ከባድ እና በወንጌላውያን አምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ ሐይማኖታዊ ጥላቻ ባለቸው ግለስቦቸ የተቀነባበረ መንግስት የማይወክል የግለሰቦች ፍላጎት እና በልማት ሰበብ ሕዝብን ከመንግስት ጋር ለማጣላት እና ታሪካው ቅራኔ ለመፍጠር ሆን ተብሎ እየተሰራ ያለ መሆኑን እንረዳለን ።
ዛሬ ሃምሌ 4 የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች ወደ ስፍራው፡ በሄዱበት ወቅት የማዋከብ የማሸማቀቅ እና ወደ እስር መውሰድ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል።
በመሆኑም መለው የወንጌል አማኞች በዚሀ የህልውናችን ጉዳይ ህግ መንግስታዊ መብታችንን እስከሚከበር ድረስ ለሚመለከታቸው ለክልሉ እና ለፌዴራል መንግስት አካላት ጥያቄያችንን ከማቅረብ ባሻገር ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ የምንከፍል መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።
በመሆኑም የሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት፣ከፍተኛ አመራሮችና የፌዴራል መንግስት አካላት ይህ ጉዳይ የህዝብ ሰላም በማይፈልጉ አካላት በልማት ሰበብ እየተሰራ የለውን ህግ መንግስቱን የጣሰ ስራ አንድታስቆሙልን እና አስቸኳይ ምላሸ እንዲሰጡን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍112😢2