የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.05K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ_የሃይማኖት_ተቋማት ጉባኤ #በኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ቤተክርስቲያን እና #በኢትዮጵያወንጌላዊት_ቤተክርስቲያን_መካነ_ኢየሱስ #ንጹሐን_አማኞች_ላይ_የተፈጸመውን_ግድያ በእጅጉ #አዉግዟል
ጉባኤዉ “በንጹሐን ላይ የሚፈጸም ግድያ፣ ኢሰብአዊ ድርጊትና አያያዝ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ ወንጀል ነው” ብሏል።

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ንፁሐን አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን የሚገልጽ ከሁለቱ አባል ቤተ እምነቶች ካወጡት መግለጫ ተገንዝበናል ያለዉ ጉባኤዉ ድርጊቱ በእጅጉ የሚያሳዝን ከመሆኑም በላይ በሃይማኖት አገልግሎት ላይ የነበሩ ንፁሐን አማኞችን መግደል ደረቅ የወንጀል ተግባር በመሆኑ በእጅጉ የሚወገዝ ድርጊት ነው ብሏል።
በተጨማሪ ባለፈው ዓመት በተለያዩ ቦታዎች ላይ የቤተ ክርስቲኒቱ አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን በመግለጫው ተገልፃል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ይህ አይነቱ የወንጀል ድርጊት በእጅጉ እያወገዘ የሚመለከተው የመንግስት አካልም የዜጎችንና የሃይማኖት ተቋማትን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ሕገ መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤው በአጽንኦት አሳስቧል።
በንጹሐን ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸሙትንም ወንጀለኞች በአፋጣኝ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግና ፍትህን አንዲያስከብር ይጠይቃል፡፡
ከዚህም ባለፈ በሀገራችን የሚታየው ማንኛውንም ዓይነት ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታረም፣ የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት ሳይሸራረፍ የመጠበቅ መንግስታዊ ሃላፊነተን ሕግንና መመሪያን መሠረት በማድረግ ሊሠራ ይገባል፡፡
ጉባኤዉ በንፁሀን ላይ ስለተፈጸመው ጥቃትና ግድያ በድጋሚ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጆች ዘመዶች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢያሱስ አባቶችና መሪዎች ልባዊ መጽናናትን ተመኝቷል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/8f0kbYG0EJM
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!