YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ጎንደር

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች መሪዎቹን አደባባይ በመውጣት አቀባበል #አደረጉላቸው፡፡

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች መሪዎቹን #እንኳን_ደህና_መጣችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ፣ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እና ፕሬዝዳንት #ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የመገጭ ሰራባ መስኖ ፕሮጀክትን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፎቶ ፦ አብመድ
@yenetube @mycase27
#መሪዎቹ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና #አቀረቡ፡፡

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት #ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ እና ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ አፈወርቂ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቀረቡ፡፡

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት #ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ባደረጉት ንግግር ጉብኝታችን የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን በልማት ለማስተሳሰር #የሚረዳ ነው።

በቀጣይ ቀጠናው አንድነቱን አጠናክሮ ለመቀጠል መሰረት #የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

የኤርትራው ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ አፈወርቂ በበኩላቸው በተደረገልን አቀባበል እጅግ ኮርተናል፤ ምስጋናም እናቀርባለን ላደረገላችሁን ሁሉ #እናመስግናለን ብለዋል፡፡

📌ሁለቱ መሪዎች ጎንደር ሲገቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የተመራ ልዑክ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡
ምንጭ ፦አብመድ
@yenetube @mycase27
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ አህመድ፣ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዝዳንት #ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በደንቢያ ወረዳ የመገጭ ሰራባ መስኖ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል፡፡

📌ከደቂቃዎች በኋላም ባሕር ዳር ይገባሉ፡፡
ምንጭ ፦ አብመድ
@yenetube @mycase27
መሪዎቹ ባሕር ዳር ገቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ አህመድ፣ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዝዳንት #ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ አሁን ባሕር ዳር ገብተዋል፡፡

📌በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል #የሀይማኖት አባቶች.#የሀገር ሽማግሌዎች እና #ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አደርገውላቸዋል፡፡
ፎቶ ፦ አብመድ
@yenetube @mycase27