YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
📌ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ‼️

ዜጎች በሃገራቸው ውስጥ በነፃነት የመንቀሳቀስ እንዲሁም በመረጡት ኣከባቢ የመኖር እና ሃብት የማፍራት ህገ-መንግስታዊ መብታቸው መሆኑ ከተረጋገጠ ቆይቷል፡፡ የፌደራልና የክልል መንግስትም ይህ ህገ-መንግስታዊ የዜጎች መብት ሳይሸራረፍ ተግባራዊ ለማድረግ ኣስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉና ጥሰት ሲያጋጥም ደግሞ ኣስቸዃይ መፍትሔ በመስጠት በእንደዚህ ዓይነት የጥፋት ድርጊት ለሚሳተፉ ኣካላት ህግ ፊት ማቅረብ ደግሞ ህግ-መንግስታዊ ግዴታ ኣለባቸው፡፡

ይሁን እንጂ ባለፉት ጥቂት ኣመታት በተለያዩ የኣገራችን ክፍሎች የተለያዩ ብሄረሰብ ተወላጆች ማንነታቸውን መሰረት ያደረገ በህይወት እና ንብረታቸው ላይ የሚደርስ የጥቃት ዜና መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡ በትግራይ ተወላጆችም ተመሳሳይ #በደል መፈፀሙን የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይም በኣማራ ክልል ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የትግራይ ተወላጆች ህይወትና #ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድና በተደጋጋሚ ህገ-መንግስታዊ ጥሰት እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ የየኣከባቢው ህዝብ አደጋውን ለመቀነሰ ጥረት ባያደርግ ንሮ ከዚህ የከፋ ጥፋት ሊደርስ ይችል እንደነበረ ይታመናል፡፡ የተለያዩ ኣጀንዳዎች በመቅረፅ በትግራይ ህዝብ ሰላምና ድህንነት በማወክ ዙርያ የሚደረግ ዘመቻ ኣሁንም ሳያቋርጥ እንዲቀጥል እየተደረገ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ እጅን ከማስገባት በተጨማሪ ከትግራይ ጋር የሚያስተሳስሩ መንገዶች በመዝጋት እና የትግራይን #መሬት በሃይል #ለመውረር መፈለግ የመሳሰሉ #ያረጁና_ሃሏ_ቀር ኣስተሳሰቦችና ክፉ ተግባራትም እየታዩ ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኣሁንም ትላንት #በመተማና ሌሎች አከባቢዎች ተመሳሳይ ግፍ ተፈፅሟል፡፡ ችግር በተፈጠረባቸው ኣከባቢዎች ኣንዳንድ የኣማራ ክልል #ከፍተኛ_የስራ_ሃላፊዎች ኣስቀድመው በማንቀሳቀስ የደረሰውን ግፍ እንዲፈፀም ኣመራር የሰጡ መሆኑን ታውቆ _ባስቸኳይ_ወደ_ህግ ሊቀርቡ ይገባል፡፡

ሰዎች ለማህበራዊ ልማት ሊተጉ ሲገባ ለጥፋት እንቅልፍ ኣጥተው ሌተቀን ሲሰሩ ማየት ኣሳዛኝ ሲሆን ጥፋትን በጥፋት መመለሰ ግን ቀላል መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል፡፡

የትግራይ ህዝብና መንግስት ደግሞ ለጥፋት ሳይሆን ለጋራ ልማትና ሰላም የቆመ በመሆኑ የሁለቱን #ህዝብ ወንድማማችነት የሚያጠናክሩ እንጂ የሚያፈርሱ ስራዎች የማንሰራ መሆኑን አሁንም በድጋሜ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ #ይህ_ማለት_ግን በህዝባችን ላይ የሚፈፀሙ የጥፋት ተግባሮች ኣይተን እንዳላየን እንሆናለን ማለት ኣይደለም፡፡ በህዝባችን ንብረትና ህይወት ላይ ጉዳት ያደረሱ በሙሉ እንደ ክልል መንግስት በህግ እንዲጠየቁ ጥረት የምናደርግ ይሆናል፡፡ የኣማራ ክልል እና የፌደራል መንግስትም ህገ-መንግስቱን ያለ ማቋረጥ በተደጋጋሚ በሚጥሱ ኣካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል፡፡ ለዘመናት ኣብረው የነበሩና በብዙ መንገድ የተሳሰሩትን ህዝቦች ኣንድነታቸውና ወዳጅነታቸው ኣጠናክረው እንዲቀጥሉ ከማስቀጠል ይልቅ #ማንነት ላይ መሰረት ያደረገ ጥቃት ሲፈፀም ማየት የሚያሳዝን እና የሚሳፍር ድርጊት ነው፡፡ የኣማራ ክልል ህዝብና መንግስት እንዲሁም የፈደራል መንግስት ይህ ማንነት መሰረት ኣድርጎ እየተፈፀመ ያለውን በደል ኣጥብቆ በማወገዝ ኣስቸኳይ ምላሽ በመስጠት የዜጎችን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የወደመ #ንብረታቸው እንዲተካና በተለያዩ ግዚያት በህዝብ ላይ ግፍ የሚያደርሱትን ወንጀለኞች በሙሉ እንዲሁም መንግስት በቅርብ በምህረት ለቋቸው ሲያበቃ በወንጀል ተግባር ላይ የተሰማርቱን ጨምሮ ወደ ህግ እንዲቀርቡ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በማንነታቸው ምክንያት ጥቃት እና ግፍ ለተፈፀመባቸው ሁሉ የተሰማውን ሓዘን በመግለፅ የዚህ ኣስነዋሪ ተግባር ሰለባ ለሆኑ ቤተሰብና ኣካላት በትግራይ ህዝብ እና መንግስት ስም #መፅናናትን ይመኛል፡፡

የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

መቐለ

ጥቅምት 27/2011 ዓ.ም
@YeneTube @Fikerassefa
ኦዲፒ‼️

በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የተሰጠ #መግለጫ

የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ #አይደናቀፉም!
በአገራችን ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የፖለቲካ ምህዳሩ #ሰፍቶ ማንኛዉም አካል በነጻነት የመደራጀት፣ የፈለገዉን የፖለቲካ አጀንዳ በሰላማዊ መንገድ እንዲያራምድ፣ የሀገራችን ህዝቦች ለዘመናት የታገሉለትና ዉድ መስዋዕትነት የከፈሉበት እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እዉን እንዲሆን በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ረገድ #ተስፋ_ሰጪ ተጨባጭ ዉጤቶችም በመመዝገብ ላይ ናቸዉ፡፡

ሆኖም አንዳንድ የፖለቲካ ሃይሎች ዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት የተፈጠረዉን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመዉ በሰለጠነና በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ #አጀንዳቸዉን_ከማራመድ ይልቅ የብሄር ጽንፈኛ አስተሳሰብን አንግበዉ በመነሳት፣ ህጋዊና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴን ከህገ ወጥና #የግጭት መንገድ ጋር እያጣቀሱ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታይቷል፡፡

እነዚህ ጽንፈኛ የፖለቲካ ሃይሎች የከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ለዘመናት በአብሮነት እና #በፍቅር የኖረን ህዝብ ሊያቃቅሩ ብሎም ሊያጋጩ የሚችሉ አጀንዳዎቸን በመቅረጽ ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጨትና ንፁሃን ዜጎችን በእሳት በመማገድ ሀገራችን ከማትወጣበት የግጭት አዙሪት ዉስጥ በመክተት የለዉጥ እንቅስቃሴዉን ማደናቀፍ ዋነኛ አላማቸዉ አድርገዉ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሰሞኑንም በአማራ ክልል #የኦሮሞ_ብሄረሰብ አስተዳደርና በክልሉ በሰሜን #ሸዋ_ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በነዚህ ሃይሎች ቀስቃሽነት ግጭቶች መከሰታቸዉና በሰዉ ህይወት፣በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡

ኦዲፒ በግጭቱ ለጠፋዉ የሰዉ ህይወት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ዉድመት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ በግጭቱ ዉድ ህይወታቸዉን ያጡ ወገኖች ፈጣሪ ነብሳቸዉን በገነት እንዲያኖር እየተመኘ ለተጎጂ ቤተሰቦችም #መፅናናትን ይመኛል፡፡ የጥፋት ድርጊቱንም አጥብቆ #ያወግዛል፡፡

በህዝብ ደም የሚነግዱ የፖለቲካ ቁማርተኞች የተፈፀመዉ ጥፋት በየትኛዉም መልኩ ተቀባይነት የሌለዉና ማንኛዉንም ህዝብ የማይወክል መሆኑን አዲፒ ይገነዘባል፡፡ የግጭቱን ጠንሳሾች እና ተሳታፊዎች ለህግ ለማቅረብ በህግ አስከባሪ አካላት የሚደረገዉን የህግ የበላይነት የማስከበር እንቅስቃሴ እንዲሳካ ፓርቲያችን ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደርጋል።

ፓርያችን ኦዲፒ የተፈጠረዉን ችግር ለማረጋጋት እና ተመሳሳይ ችግር ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከል ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) እና ከአማራ ክልላዊ መንግስት ጋር በመቀናጀት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በእኩይ የጥፋት ድርጊት የሰከሩ ሀይሎች ሰሞኑን የለኮሱት የጥፋት እሳት የህዝብ ለህዝብ ግጭት በማስመሰልና ችግሩ በኦሮሚያ ክልል እንዲስፋፋ በማድረግ ለዘመናት በወንድማማችነትና በመተሳሰብ በሰላም አብረዉ እየኖሩ ያሉ የኦሮሞና የአማራ ወንድማማች ህዝቦችን በግጭት እሳት በመማገድ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ታዉቋል፡፡

በሰላም አብሮ የሚኖሩትን ወንድማማች ህዝቦች ለማጋጨት የሚደረግ ማንኛዉም ሙከራና ድርጊት ህዝቦች ለዘመናት ባካበቱት የአብሮነት ዕሴት እና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሴራዉን ለማክሸፍ ኦዲፒ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጠንክሮ ይሰራል፡፡

በዚህ አጋጣሚም የኦሮሞ ህዝብ በተለመደዉ የአቃፊነት ባህሉ ወንድም ከሆነዉ የአማራ ህዝብ እና ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያለዉን አብሮነት በማጠናከር፣ በክልሉ በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚደረጉ የጥፋት ሀይሎቸን ሴራ ለማጋለጥ እና ለማክሸፍ እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ኦሮሚያ የሁሉም ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቤት እንደሆነች ኦዲፒ በጽኑ ያምናል፡፡ በክልላችን የሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች አሁን የደረሰንበት የለዉጥ ምዕራፍ ላይ እንድንደርስ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር አንድ ሆነዉ ከመሪዉ ፓርቲ ኦዲፒ ጎን ተሰልፈዉ ታግለዋል፡፡ ዉድ መስዋዕትነትም ከፍለዋል፡፡ ፓርቲያችን ኦዲፒ ለዚህም ታላቅ አክብሮት እንዳለዉ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

በክልላችን ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሰላም፣ በእኩልነት፣ በወንድማማችነት እና በነጻነት እንዲኖሩ ችግሮች ሲከሰቱም ከአሁን ቀደም እየፈታናቸዉ በመጣንበት መንገድ እየተወያየን መፍትሄ እየሰጠን ለመሄድ ዝግጁ መሆናችንና ለጽንፈኛ እና ለከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎች የሚከፈት በር እንደማይኖር፤ ለዚህም ፓርቲያችን መላዉን የክልሉን ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ ከማንኛዉም ጊዜ በበለጠ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

ፓርቲያችን ኦዲፒ የህዝቦች ወንድማማችነት፣ የኢትዮጵያን አንድነት እና የለዉጡን እንቅስቃሴ ለመገዳደር የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ እና የከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎችን ከመላዉ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከለዉጥ ኃይሎች ጋር በመተባበር በጽናት የሚታገላቸዉ መሆኑን ደግመን እናረጋግጣለን!

የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ
ሚያዚያ 01፣ 2011
@YeneTube @FikerAssefa